bridgethoughts | Unsorted

Telegram-канал bridgethoughts - Dildiy - (ድልድይ)

-

“Let's build bridges, not walls.” Martin Luther King, Jr. — Visit my blog: https://dildiy.net/ — ድልድይ - ግላዊ እይታና ጥልቅ የመሻገሪያ እሳቤዎች የሚጋሩበት ከንባብ፣ ከኑረት እና ከምናብ የሚቀዱ ንሸጣዎች መድረክ ነው። - ሃሳቦቹ ከየትኛውም የአስተሳሰብ ጎራ (ism) አይወግኑም!! — Concern & Concept — D.S.

Subscribe to a channel

Dildiy - (ድልድይ)

.
.
.

የኔነሽ፣ 
የኔነሽ፣
የኔነሽ ይሏታል
እርሷም ደስ ይላታል


የሁሉ መሆን ግን ምን ያደርግላታል?

.
.
.

የሁሉ የሆነ - እንዳይሆን ለማንም 
ሁሉ ዘንድ የሞቀ - እንዳይገኝ የትም፤


ጸሐይ ነግራናለች - በዘለለት ልሳን
ሰርክ አዲስ እንግዳ - እኛ እንጂ ያልነቃን፤


በጠዋት ፈገግታ

በእኩለ ቀን ዋዕይ

ከባን ብትውልም፣

ጽልመት ሲገማሸር አታስተማምንም።

___

@bridgethoughts

Читать полностью…

Dildiy - (ድልድይ)

ሰላም ወዳጆች፤

ድልድይ - ቀለም ላይ አምደኛ ሆና ተከስታለች፤ ይህንን የጥበብ ብፌ ስጋብዛችሁ ደስ እያለኝ ነው...

___

ግቡ፣ Join አድርጉ፣ አዲሱን ቅጽ አንብቡ!!

___

ቀለም መጽሔት🗞️

ቅፅ 1  እትም 5


እያነበባቹህ ለወዳጅዎ ያጋሩ
ለሀሳብ አስተያየት

@KelemMagazine

Telegram 👇❤️
@kelemofficial

Читать полностью…

Dildiy - (ድልድይ)

🔔 Before the Drums Beat Again 🔔


Once upon a time, there was no Ethiopia and Eritrea.


There were only brothers — children of the same highlands,
breathing the same wind that rises from the Red Sea
and settles on the mountains.


The rivers did not know borders.
The mothers spoke the same lullabies.
The sky covered us all — without a passport.


But then came the shadow of lines drawn on the earth —
names that separated hearts, flags that replaced embraces.


And in the name of these lines,
thousands of young men and women offered their blood to the soil.
Still, the soil cried — not for victory,
but for the innocence lost.


Years later, the world rejoiced when the two brothers met again —
smiles, handshakes, hope.

The world said, “At last, the Horn of Africa breathes again.”
You both promised peace,
and the earth, weary from the echo of guns, finally rested.


Our Prime Minister received the world’s peace prize —
but more importantly,
our people received the peace itself.


Seven years passed.


Yet now, we hear the sound of old drums beating again.


Excellencies,

Before those drums awaken the ghosts of yesterday, please —
sit and talk.


Sit not as leaders of separate lands,
but as brothers who share one ancient wound.
History has already buried too many sons.
Must we dig new graves for the same reason?


A sea is not worth a single mother’s tear.
A port is not worth the trembling of a child
who hears warplanes in the sky.


The world does not need another headline of sorrow from the Horn;
it needs the light of wisdom from its cradle.


Yes — Ethiopia needs a gate to the sea.
And yes — Eritrea needs her sovereignty respected.
But more than that, both need each other.


The sea and the highlands are not enemies;
they complete each other —
like breath and heartbeat.


If you two meet,
not to debate, but to listen —
the Red Sea will calm its waves.
Trade will flow, families will unite,
and the wounds of decades will begin to heal.


But if the guns speak again,
no one will win —
except those who sell the bullets.


Please, for the sake of history yet to be written,
for the mothers who have already buried too much,
for the youth who dream of life, not war —
Sit and talk.


Let wisdom be your weapon.
Let love be your strategy.
Let peace be your legacy.


The Horn does not need heroes of war anymore.
It needs fathers of peace.


🕊️ May reason rise above rage,
and may love remember what history forgets.

____

@bridgethoughts

Читать полностью…

Dildiy - (ድልድይ)

.
.
.

ሰዎች በአንድም በሌላም መንገድ ሊጎዱህ ይችላሉ፤ የዝቅተኝነት ስሜት እንደሚያንገላታው ሰው ግን የሚያሳምምህ አይኖርም።
___

@bridgethoughts

Читать полностью…

Dildiy - (ድልድይ)

ትዝ አለኝ የጥንቱ...


[ያው እንደነገርኳችሁ የተወለድኩት በቅዳሴና አዛን መሐል ነው... የከተማው ትልቅ ደብርና ታሪካዊው ፈትኸል መስጅድ ጎረቤቶቼ ናቸው... በደብሩ ወገን ያለው ግድም - ገዳም ሰፈር፣ ከመስጅዱ ዙሪያ ያለው መንደር ደግሞ ነፃ ሰፈር ይባሉ ነበር... እርግጥ ዛሬ የሁለቱም ሰፈር ስሞች ለጥሪ ሲውሉ አይሰማም... በኔ ዘመንተኞች ዘንድ ካልሆነ በቀር... ]


ላወራችሁ የፈለግሁት ስለዚህ አይደለም... ከልጅነቴ ትዝታዎች በአንዱ ፈገግ ላስብላችሁ እንጂ...

___


ከዓመታት በፊት የሆነ ነው...


ቀኑ አርብ... የከተማዋ የገበያ ቀን ነው...


እንደተለመደው የደብሩ የማምሻ ጉባኤ እስኪጀመር ድረስ በግዙፍ ስፒከር መዝሙር ተከፍቶ ጥሪው ከየጓዳችን እየደረሰ ነው...


ይህን የማድረግ ተራ የደረሰው አንድ ጓደኛዬ የመዝሙሩን ካሴት ቴፑ ላይ ጥዶ የመቅደሱን በር ቆልፎ ወደ ከተማ ወጥቷል... [ቴፑ ለወቅቱ ዘመናዊ ቴፕ ነው - በራሱ ስለሚገለብጥ በእርሱ ቤት 'እደርሳለሁ' ብሎ ነው የራቀው...]


[ለዛሬ ልጆች ለማስረዳት - ካሴት ሁለት Side ያለው፣ በአንዱ ጎን 30 ደቂቃ፣ ሲገለበጥም ያንኑ ያህል ዜማ ተሸክሞ የሚዞር፣ ብዙ ጊዜ እስከ አስር የሚደርሱ ስራዎች የሚሸከፉበት የክር ጥቅል ነው... 😂😂😂]


ጓደኛዬ ከደብሩ ብዙ ርቋል...


የካሴትን ችግር ታውቃላችሁ መቼም... 


ወይ የቴፑ "አልማዝ" ያልቅና ድምጹ ይነፋነፋል... 


[አድገን እንደገባን 'አልማዝ' የሚባል ነገር የለም... Read head ነው የሚባለው... መቅጃው Record head፣ መደምሰሻው Erase head እንደሚባለው ማለት ነው...]


ወይ ደግሞ ቴፑ ክሩን ይጎለጉለውና የዜማውን ስልት ወደ ብዙ ድመቶች ጠብና አምባጓሮ ያሳድገዋል...


እርግጥ ያንለት ሁለቱም አልሆነም...


መዝሙሮቹ በየተራ ሲፈሱ ቆዩና ድንገት ምዕመናን ከየቤታቸው ብቻ የሚሰሟት የአንዲት ገናና ከያኒ ድምጽ በስፒከሩ ውስጥ ተንቆረቆረ... አስቱካ ነበረች...


"... ጠይም ዘለግ ያለ - የኮራው ደረቱ..."


ሰው ሁሉ በጥፊ የተመታ ያህል ጆሮው ጭው አለ... በተለይ የገዳም ሰፈር ልጆች ድንጋጤ ቅጥ አልነበረውም... ቤተክርስቲያኗ በጠላት ቁጥጥር ስር የዋለች ያህል ተሰማን... ጎዳናውን በአንድ ጊዜ ሞላነው... [በዚያው ቀን 'መዝሙሩ የማን ነበር?' ብንባል ማስታወስ የሚከብደን ሰዎች በአስቱካ ስርቅርቅ ድምጽ ጆሮአችን የነቃበት ሚስጢር ዛሬ ድረስ እንቆቅልሽ ይሆንብኛል...]


አስቱካ ቀጥላለች... 


'እንዴ፣ አይዘጉትም እንዴ?' ሰው ሁሉ ወደ ቤተክርስቲያን አሻግሮ እያየ ይንቆራጠጣል... አንዳንዱም መላምት ይሰጣል... ያን ሰሞን 'ተሐድሶዎች ከቤ/ን ተባረሩ' የሚለው ዜና አልበረደ ኖሮ 'እነርሱ ናቸው፣ ሊያዋርዱን፣ በጠላት ሊያስቁብን...' ብቻ ብዙ ብዙ ተባለ... [በወቅቱ ሞባይል የለ ምናምን... ለማን ተደውሎ ይነገራል?] ብቻ ድንጋጤዎች አንዳንድ ጫጫታዎችን ዝም ስላሰኙ ሙዚቃው በብዙ ሰዎች የመሰማት ዕድል አገኘ...


አስቱካ ናኘች...


በዚህ መሐል ጓደኛዬ ከሄደበት ተመለሰ... እያለከለከ፣ ላቡን እያዘራ፣ ምላሱ ጉሮሮው ላይ እንዳትወተፍበት እየተጨነቀ ወደ ቤተ/ን ገሰገሰ... 


አስቱካ ወደሌላኛው ሙዚቃ ተሻግራለች... [አጠቃላይ ክስተቱ 7 ደቂቃ ቢሆነው ነው... ሆኖም የ 7 ቀን ያህል ረጅም ነበር...]


ጓደኛዬ ደርሶ ዘጋው... እፎይ... [አስቱ በቁጥጥር ስር ዋለች]


[ወዳጄ እንደነገረኝ ቤተክርስቲያን ውስጥ የነበሩ ሰዎች ቴፑን ለመዝጋት ያላደረጉት አልነበረም... ግን በየት በኩል ይግቡ... 'ባልቦላ' እንዳያጠፉ ለቆጣሪው ጥንቃቄ ሲባል የተሰራው የጣውላ ቀፎ ተቆልፎ በየት ያግኙት?...]

___


ያን ዕለት ጓደኛዬ ብዙ ወቀሳና ትችት ወረደበት... [ቀድሞ ሌላ ሐይማኖት ይከተል ስለነበር 'ድሮስ' ምናምን ያሉትም አልጠፉም...]


የካሴቱ ቅድመ-ታሪክ ሲመረመር - የአስቴር አወቀ ሙዚቃዎች ስብስብ ሸክፎ ኖሯል ለካ... ሆኖም ተደምስሶ መዝሙር ሲቀዳበት ነባሩ ሙዚቃ የነበረው ርዝመት የክሩን ሰፊ ክፍል ይሸፍን ኖሮ ሳይደመሰስ የተረፈው ሙዚቃ ነው አየሩ ላይ የናኘው... [ካሴቱ ከ 20 ደቂቃ በላይ በመዝሙር ቢሸፈንም ቀሪ ቦታውን የያዘው ሙዚቃ አልጠፋም ነበር እንደማለት - መዝሙር ሲቀዳበት ከ Erase head የተረፈ...] 


ያንለት ከወትሮው ቁጥሩ እጅግ የበዛ ሰው ቤተክርስቲያኒቱን አጥለቀለቃት... የብዙዎች የመገኘት ምክንያት ታዲያ የጉዳዩን ሰበብ መስማት ነበር... [ያን ሰሞን የከተማዋ የቡና ተርቲበኞች አቦል ቶናና በረካ የሚወራረደው በወዳጄ "ሥጋ" ነበር...]

____

አንዳንዴ... [የሰው ልጅ]


ተኩላ ማንነቱን ለመሸፈን በለበሰው የበግ ለምድ የከረመ ዓመሉን መደበቅ ሲያቅተው፣ አልያም ቂመኛ ልቡን ለመከለል ከፊቱ የሞላው አስመሳይ ፈገግታ ጨካኝ ማንነቱን መከለስ ሲሳነው ሳይ ይህን ገጠመኝ አስታውሳለሁ...

___

@bridgethoughts

Читать полностью…

Dildiy - (ድልድይ)

The Flame Without Separation
___

He did not preach;
he breathed love—
softly,
like dawn touching every face
without asking who they are.


When the land cracked
under the weight of names and tribes,
he stood in the middle—
not to divide,
but to remind us
that the middle is where Love hides.


His hands held silence
that could calm storms,
his eyes—
mirrors where strangers
remembered themselves again.


He called no one sinner,
no one pure.
He called all hearts
to return to the circle
where light knows no border.


Now he is gone,
yet not gone—
for love never dies,
it only changes form.


The flame he carried
has scattered among us—
each spark
a whisper saying,
“Be the love that remains.”

____

He reminded us that love is larger than any name, faith, or border.

Even after he’s gone, his light lives in every act of kindness we choose.

___

@bridgethoughts

Читать полностью…

Dildiy - (ድልድይ)

.
.
.

አስተውለህ ታውቃለህ?...


ለብዙ ችግሮቻችን የምናደርጋቸው ጥንቃቄዎች ዕድሜ ሰከንዶችን አይሻገርም፤ 


ሆኖም


በትዕግስት ማጣትና ቸልተኝነት ሰበብ የሚወለድ መዘናጋት ግን በዓመታት የማይሽር መዘዝ ያመጣል...


[Keep this in mind...]


✨✨✨


መኪና መንገድ ለማቋረጥ ጥቂት ሰከንዶች መታገስ ይበቃል - በምንግዴ ዘው ካሉበት ግን ከአካል ጉድለት እስከ ሥጋ ሕልፈት የሚደርስ ዋጋ ያስከፍላል... 


[አረንጓዴው መብራት በቀይ እስኪተካ ስለቆምክ ዓለም አታልፍም... እዚያስ ሄደህ ልትቀመጥ አይደል?...]


✨✨✨


የሲሊንደሩ ጋዝ ማፈትለኩን ለማረጋገጥ ለሰከንዶች ማሽተት ይበቃል - ይህን ሳያደርጉ ክብሪቱን መጫር ግን ለአካል ጉድለትም ለንብረት ውድመትም ሰበብ ይሆናል...


[ምግቡ እስኪበስል መቆየትህ ይቀራል?...]


✨✨✨


የቁጣን ስሜት ለመቆጣጠር ሰከንዶችን መታገስ በቂ ነው - ቸኩሎ እርምጃ መውሰድ ግን ዓመታት ለሚሻገር ጸጸት ሰበብ ነው... ለመገንባት ረጅም ጊዜ የወሰደን ወዳጅነት ለማፍረስ ምክንያት ነው... ዘብጥያ ወርውሮ ተስፋን ለማጨለም በቂ ነው...


[በምላስ ተናግሮ ከማስቀየም በትንፋሽ ተቆጣጥሮ ማለፍ አለ... ተኩሶ ከመግደል ይቅር ብሎ መዝለል አለ... ቸኩሎ ከመታሰር ታግሶ መከበር አለ...]


✨✨✨


እንዲህ እያልክ ብዙ ነገር ማሰብ ትችላለህ...


___

“One moment of patience may ward off great disaster; one moment of impatience may ruin a whole life.” — Chinese Proverb


ብቻ...


ጥቂት ጊዜ - የብዙ ጊዜ ደስታ መነሻም፣ የዕድሜ ልክ ህመም መቀስቀሻም ሊሆን ይችላል...


ችግሩ ግን... 


ወከባ ላይ ነን... ብዙዎቻችን ከምህዋራችን ውጭ በመጦዝ ነው ቀኖቻችን የሚያልፉት... ስክነት ይጎድለናል... በቂ አሁን የለንም... እንደምናስበው ከራሳችን ጋርም አይደለንም... የኑሮ አውታር በየአቅጣጫው ሰቅዞናል...


መላውሳ ምን ይሆን?... Stillness!!


[ትርጉም...]


በተረት -

✍️ 'የረጋ ወተት - ቅቤ ይወጣዋል'

በዜማ ስልት -

✍️ 'ያዋከቡት ነገር - ምዕራፍ እያገኝም'

በምሳሌ ውበት -

✍️ 'የቸኮለች - አፍሳ ለቀመች' 

___

"Patience is not resistance to time,
it is the silence of trust —
the knowing that what belongs to you
can never be lost in hurry.
When you stand still in awareness,
time itself becomes patient with you."

___

@bridgethoughts

Читать полностью…

Dildiy - (ድልድይ)

.
.
.

ከእያንዳንዱ ዕውቀት፣ ከእያንዳንዱ ተገንዝቦት፣ ከእያንዳንዱ መረዳት ጀርባ ግዙፍ ድፍረትና አይለኬ መስዋዕትነት አለ...


ዛሬ ላይ ባሕር ውስጥ ስላለው ዓለም ያለን ዕውቀት በብላሽ አልደረሰንም... አደገኛ በሆኑ የውሃ ሰርጦች፣ አሳነባሪና ሻርክ በሚራኮትባቸው ጥልቆች፣ ማዕበልና ወጀብ በሚንጣቸው ዳርቻዎች ላይ ለመገኘት የደፈሩ ጥቂት ሰዎች በከፈሉት ዋጋ እንጂ...


ስለ ጠፈር የምናውቀው ሁሉ በምቾት ውስጥ አልተገበየም... የምድርን ድሎት የናቁ፣ ጽልመትና ፀጥታን የደፈቁ፣ ማንም ካልደረሰበት ሕዋ በድፍረት የመጠቁ ሰዎች የማይተመን ዋጋ ከፍለው እንጂ...
 

በባዮሎጂ መነጽር የስነ-ሕይወትን ዕውቀት፣ በኬሚስትሪ ጉልበት የነገረ-ውህደትን ውጤት፣ በፊዚክስ ምጡቅ ዓይን አይዳሰሴውን ጥልቀት፣ በምህንድስና መሰረት ውስብስቡን ግንኙነት ተረድተናል... ለዚህ ሲባል ግን - ጥቂቶች ቀንና ሌት መድከም ነበረባቸው፣ ትጉሃን በእሳት ላንቃ መለብለብ ነበረባቸው፣ ለዕውቀት ጥራት መውደቅ ነበረባቸው፣ አሰልቺ ሰዓታትን በዝግ ውስጥ ማሳለፍ ነበረባቸው...


በታሪክ፣ በፍልስፍና፣ በሕግና ፖለቲካ እንረቅ ዘንድ ጥቂቶች ብጥስጣሹን ገጣጥመዋል፣ ቆራጦች የሻገቱ መዛግብትን አገላብጠዋል፣ ጽኑዎች በኑረት ትግል ውስጥ ቀልጠዋል... ስለ እልፎች ደስታ ተነጥለዋል፣ ስለ ሚሊዮኖች ምቾት ተሰደዋል፣ ስለ ቢሊዮኖች አብርሆት ሁሉን በድፍረት ጠይቀዋል...


የተዝናኖት ምንጫችን ስነጽሑፍ፣ የነፍስያ ቋንቋችን ሙዚቃ፣ የምናብ ሜዳችን ስነ-ጥበብ በገባን ልክ የታወቀው እረፍት አልባ ነፍስ ባላቸው የጥቂቶች ጥረት ነው... እነርሱ ውብ ድምፃቸውን፣ የንስር ዓይናቸውን፣ ብሩካን እጆቻቸውን ስለሰጡን በዘመናት ውስጥ ስለሚሻገር ውበት አወቅን...


ብዙ መውደቅ መነሳት - መድኃኒትን፣ ብዙ ሕመምና መገፋት - ስነልቡናን፣ በጽናት የመቆም ትጋት - ማሕበራዊ ሳይንስን እንድናውቅ አድርጎናል...  


ብዙ እንቅልፍ አልባ ለሊት፣ እልፍ ተስፋ አስቆራጭ ሙከራ፣ ገደብ የለሽ ደምና ላብ - ቴክኖሎጂን ለግሶናል... ሰውን የማፍቀር ሃሌታ፣ ህብርም የመፍጠር ከፍታ ኢንተርኔትን ሰጥቶናል...






ተ....

___

እንደ እውነቱ ከሆነ እኛ በግዙፋን ትከሻ ላይ ቆመን የሩቅ ጉዞን የምናልም፣ ሆኖም ለትከሻው ድካም ለአፍታ ዋጋ መስጠት የማናስብ ቸልተኞች ነን...


We take everything for granted...

___

አስገራሚው ታዲያ...

አንድ ሰው 'ጎበዝ' የሚባለው የዕውቀት ምንጭ በመሆኑ ሳይሆን ዕውቀትን በማነብነብ ኃይሉ ነው... ዕውቀት በማከሉ ሳይሆን ዕውቀት በመገልገሉ ስልት ነው...


አስታውስ...


የትምህርት ስርዓታችን የሚያነግሰው አስታውሰው የመለሱትን እንጂ አሰላስለው የጎለመሱትን አይደለም...


በዚህ ምክንያት ዕውቀት ባልተገባ ተገንዝቦት አዋቂና ቃራሚ የሚምታታበት እሳቤ ሆኗል...


ምናልባትም...


አዋቂው 'አዋቂ ነኝ' ሳይል፣ ቃራሚው 'ከእኔ በላይ ላሳር' የሚያበዛበት መድረክ እየሆነ ይመስላል...


ልክ እንደ ምሳሌው...


'በአትክልት እርሻ ውስጥ ፍሬ የያዙ ተክሎች አንገታቸውን ይደፋሉ፤ ፍሬውን የሚበሉት ወፎች ግን ከፍ ባለ ድምጽ ይንጫጫሉ...'

___

ክብር... ዓለምን በየቅጽበቱ ለሚያድሷት ጠቢባን!!

___

@bridgethoughts

Читать полностью…

Dildiy - (ድልድይ)

አንቺ የሌለሽበት...

[የድልድይ የሙዚቃ ግብዣ]

___
@bridgethoughts

Читать полностью…

Dildiy - (ድልድይ)

.
.
.

በዓለም ታሪክ አንድም ሃገር ጦርነትን አሸንፎ አያውቅም!... አንድም ሃገር!!...


የመስተጋብራችን ታሪክ በተሸከፈባቸው ባለፉት ብዙ ሺህ ዓመታት በምድራችን ላይ ብዙ የጦር አውድማዎች ተፈጥረዋል... የሰው ልጅ ሳይሰለች ጦር ተሳብቋል፣ ሳያሰልስ ተሞሻልቋል፣ ያለፋታ በባሩድ ጢስ ታጥኗል፣ በጥይት ጫፍ ህልም ቀጥፏል...


[ጦርነትን ግን አሸንፎ አያውቅም...]


ከባሕላዊ እስከ ዘመናዊ፣ ከእግረኛ እስከ አየር በራሪ፣ ከሃገር ድንበር እስከ ባሕር ተሻጋሪ፣ ከፊት ውጊያ እስከ ስውር ግፊያ - ተራቀቅሁ ባለባቸው መሳሪያዎች ሁሉ - የሰው ልጅ እስኪበቃው በራሱ ላይ ዘምቷል...


[ግን ጦርነትን አሸንፎ አያውቅም...]


የዓለሚቱ ጭካኔ ቅጥ አጥቷል... ጭቆናና የበላይነት የምድርን መልክ አጥፍቶታል... መግፋት፣ መንቀል፣ መግደል ተራ ጉዳዮች እየሆኑ ነው... በእያንዳንዱ ሰከንድና ደቂቃ ነፍሶች ይረግፋሉ... በእያንዳንዱ የዓለም ዳርቻ ሰቆቃ ይንበለበላል...


“In modern war, you will die like a dog for no good reason.” – Ernest Hemingway


አንዱ ሌላኛውን በብርቱ ያስጨንቃል... በመሪ እብሪት ታዝሎ እንባ ደም ያፈሳል... ግጭት ከመቀስቀስ እስከ መንግስት ማፍረስ፣ በቦንብ ከማውደም እስከ መሪ መሾም፣ ዜጋን ከገዛ ሃገሩ ከማባረር ሌላ ሃገር እስከ ማስፈር - የማንሰማው ጉድ የለም... ገራሚው ግን ይህን ሁሉ ሃይ የሚል አለመኖሩ ነው... ዜጎችን ከእብሪተኞች ጡጫና ከእብዶች እርግጫ የሚከልል የዓለም ስርዓት የለም... የሃገራትም ሆነ የዜጎቻቸው ዕጣ ፈንታ የሚወሰነው በመሳሪያ አምራቾች ምርጫ ነው...


ጥቂት የገንዘብ ብቻ ሃብት ያላቸው ሰዎች ኪስ እንዲሞላ በየቀኑ የጥይት ናዳ፣ የከተሞች ጎድጓዳ፣ የንጹሃን ዕዳ የማይተዋቸው ሃገራት ይኖሩናል... ከስልጣናቸው መክረም ውጭ አንዳች የሚሻገር ህልም በሌላቸው አምባገነን መሪዎች ቅዠት - እንቦቃቅላ ሕፃናት በጥይት ይረግፋሉ፣ ተስፋ ያላቸው ወጣቶች ይማገዳሉ፣ አዛውንቶች በየጎጆው ይደፋሉ...


[ያም ሆኖ ዛሬም ድረስ ጦርነትን አሸንፎ የሚያውቅ የለም...]


አፍሪካ በራሷ ልጆች አንገት ላይ ካራ ትሰካለች... በድሃ አደግ ሕዝቦቿ ላይ የደም አበላ ታወርዳለች... ከሰሜን ከፍታ እስከ ደቡብ ዝቅታ፣ ከምስራቅ ጫፍ እስከ ምዕራብ አጽናፍ - ሰላም ጸንቶ አያውቅም... ፍቅር አይሰነብትም...


የተፈጥሮ ሃብቷን ለመቀራመት ባላቸው ጉጉት ታውረው ልጆቿን በእልፍ ጎራ ከፍለው ያተጋትጓታል... ለዚህኛውም ለዚያኛውም ልጇ መሳሪያ ያቀርቡላታል... ለዚህኛውም ለዚያኛውም አካሏ አማካሪ ይሆኗታል... እርሷ እንቅልፍ ላይ ናት... ሴራ አታስተውልም፣ ስራይ አትገነዘብም... ዜጓቿ ሰርቶ መኖር፣ ገብቶ መውጣት፣ ተምሮ መለወጥ ሲያምራቸው ይቀራል እንጂ ጥቂቶች ኪሳቸው እስከሞላ፣ ሆዳቸው እስከቀላ ድረስ ግድ አይሰጣትም...


[ዛሬም ድረስ አፍሪካ የውስጧን ጦርነት አሸንፋ አታውቅም...]


በየመዳረሻው የሰው ልጅ በረሃብ ያሸልባል፣ በጠኔ ይረግፋል፣ በጥም ይጠወልጋል... 


ግጭት የማያውቀው፣ የጦርነት አለንጋ የማይገርፈው፣ የጥይት አረር የማያስደነብረው አንድም የዓለም ጥግ የለም... ጦርነትና ግጭት የሰው ልጅ ቋሚ ልማድ ሆኗል...


ዜጎች በገዛ ቤታቸው በሰላም አይተኙም... በገዛ ምድራቸው ተረጋግተው አይኖሩም... በዕጣ ፈንታቸው ላይ አይወስኑም... የኔ የሚሉት አንድም ዋስትና የላቸውም... ነቃይና ተካያቸው ጉልበተኛው ነው... 


“If we have no peace, it is because we have forgotten that we belong to each other.” – Mother Teresa


ሃገር በሌላ ሃገር ላይ እጅ ታነሳለች፣ መንግስት በዜጎቹ ላይ በእብሪት ይኮፈሳል፣ ክፉው ከወገኑ መከራ 'ሲሳይ' ያፍሳል...


በጣም የሚያስደነግጠኝ ብዙ ደካሞች በጥቂት ጉልቤዎች ስር መጨፍለቃችን አይደለም... ጭፍለቃውን justify የሚያደርግ አመለካከት ማዳበራችን እንጂ...


አዎን ጦርነትን የተለማመደ ትውልድ እየፈጠርን ነው... ከሌሎች እንባ የሚመነጭን ጥቅም፣ ከደማቸው የተላቆጠን ሃብት -  'አርበኝነት'፣ 'ብሔራዊ ጥቅም'፣ 'የሃገር ፍቅር' ፍቅር እያለ የሚያንቆለጳጵስ ድንዛዜ ውስጥ እየገባን ነው... ጦርነትን ምክንያታዊ ለማድረግ የምንሄድበት ርቀት ደግሞ ከጦርነቱ በላይ ያስፈራል...


“There is no flag large enough to cover the shame of killing innocent people.” – Howard Zinn


በዚህ የዓለም ስሪት ውስጥ ነገ የሚባለው ተስፋ ሁሌም የማይዳሰስ ነው... ሟችና በማንኛዋም ሰከንድ ውስጥ ተሰናባች መሆንህ የተፈጥሮ ድንጋጌ ቢሆንም ነቃይህ ከተፈጥሮ ቅኝት ውጭ የሚጓዘው እብሪተኛ መሆኑን ማሰብ ያደክማል...

___

የድልድይ አቋም...

.
.
.

ሃገር - ተፈጥሮ ከለገሳት፣ ድካሟም ከቸራት ሁሉ እንዳትበላ የሚያደርጋትን ማንኛውንም ኃይል መቃወም ጤነኛ ተግባር ነው... እያንዳንዱን ችግር ጦር መዞ፣ ሳንጃ ደቅኖ መጋተር ግን ብልህነት አይሆንም...
 

ዛሬ በጦር አስገብረህ የምታገኘው ነገር ለነገው ትውልድ የሌላ ዙር ጦርነት ሰበብ እስከሆነ ድረስ ጦርነቱን አላሸነፍከውም... የዛሬ ኃይልህ ለነገ ሰላም ዋስትና ካልሰጠ ያንተን ስግብግብነት እንጂ ለልጅህ ያለህን አሳቢነት አያመለክትም...


“Wars are poor chisels for carving out peaceful tomorrows.” – Martin Luther King Jr.


'ለልጄ የበቀል አዙሪት አላስቀምጥም' ያሉ ዛሬን ያስገብራሉ፣ ነገንም ያሸንፋሉ... 


ያልተሄደበትን መንገድ ደፍረው መሻታቸውን የሚፈጽሙ ሃገርን ይወዳሉ፣ ለትውልድ ይጨነቃሉ... 


'ልጆቼ ላይ ዕዳ ጭኜ አልሄድም' ያሉ በአስተዋይ ውሳኔያቸው ብርታት በትውልዶች ይዘከራሉ...


አዎን...


ጦርነትን ያሸነፉት ጦርነትን ያስቀሩት ናቸው...

___

@bridgethoughts

Читать полностью…

Dildiy - (ድልድይ)

✨አልከራማ - ባለቤት አልባው ጎጆ ✨

.
.
.

በቤንሻንጉል ኮረብቶች፣ በበርታዎች መንደር ውስጥ - የየትኛውንም ትውልድ አንደበት ትንግርት የሚያስብል ተግባር ይከወናል... በጸጥታ፣ በስውር፣ በድብቅ... 


ነገሩ ምን መሰላችሁ?... 


በርታዎች በነፋሻማዎቹ መመላለሻዎች ዳርቻ፣ ከተጓዥ መተላለፊያ መንገዶች ግራና ቀኝ ትናንሽ ቤቶችን ይገነባሉ... ለመኖሪያ አይደለም፣ ለንግድም አይደለም፣ ለመንገደኛ እንጂ...


ተሾመ ገ/ሥላሴ 'የባሕር ጠብታ' በተሰኘ የግጥም መድብሉ መግቢያ ላይ [በርታዎች በዚያች ቤት ውስጥ] "... ምግብ፣ ውሃ፣ የመስገጃ ምንጣፍ፣ ቡናና ከሰል ያስቀምጣሉ... ቤቱ የማንም አይደለም... የእንግዳ ቤት ነው... የራበው መንገደኛ [ምግብ] በልቶ፣ [ውሃ ጠጥቶ]፣ አርፎ ይወጣበታል... ማንንም ማመስገን አይጠበቅበትም..." በማለት በሁለት መስመር ብርታት የባሕሩን ግማድ ያሳየናል...


የቤቱ ስም 'አልከራማ' ይባላል... እናንተ 'የአብርሐም ቤት' ልትሉት ትችላላችሁ... የልግስና ታዛ፣ የደግነት አምድ ቢባልም ትርጉሙ ያው ነው... ትልቁ ቁምነገር ግን በቤቱ ውስጥ የምናገኘው ምግብና መጠጥ አይደለም - ከዚያ ጀርባ ያለው የመንፈስ ንጽሕና እንጂ... ባለቤት አልባ ቤት፣ ቀኙ 'ሚሰጠውን ግራው የማያይበት ልባም፣ ምስጋና ሽቶ ከታዛው ያልተቀመጠ ለጋሽ፣ በጸጥታ - በዝምታ - በአርምሞ የሚቸር ስጦታ... በክብረት - በከፍታ - በምልዓት የሚመለስ ውለታ...


[አዎን - ዛሬም ድረስ መንገድ መንገደኝነቱን አልተወም... ተጓዥም ደረስኩ ብሎ መጓጓዝ አልቀረም...]


አልከራማ ከቤትነት የምትሻገር ከፍታ ናት... የጥልቅ ፍልስፍና ሰንዱቅ፣ የልግስና ምጡቅ፣ የሰብዓዊነት ረቂቅ ናት... አማናዊው ስጦታ በእውቅና የማይመተር፣ በውለታ የማይታሰር፣ መቀበል ሳይጠብቁ መቸር መሆኑንም ታስተምረናለች... 


🔥 መስጠት ግን ሰጪ ሆኖ አለመገኘት - መሄድ... 
🔥 መድከም ግን ድካምን አለማወጅ - ራስ መካድ...
🔥 ማስቀመጥ ግን ጠባቂ አለመፈለግ - ማመን...


[ይገርማል!!...]


እንኳን ማዕድ አኑረህበት የእከሌ የማትለው ባዶ ቤት በግላጭ መገኘቱ፣ ማሕበረሰቡ ይሆነኝ ብሎ አልከራማን መገንባቱ - ብቻውን ድንቅ ነገር ነው... 


አዋጅ ሳይነገር ምንም በማይደረግባት ሃገር ውስጥ ድምጹን ሳያሰማ ሹልክ ብሎ ገብቶ - ለሆድ የበሰለውን፣ ለጥም የሚያረካውን የሚያስቀምጥ ንጹህ ልብ መገኘቱም አስገራሚ ነገር ነው... 


[እስኪ አስበው...]


🌼 ከተሜ እኮ ለለቅሶ ቤት እንኳ እራት የሚወስደው የዕድር ሰብሳቢዋ ስታዘው ነው... እነርሱን ማን አስገደዳቸው?... 


🌼 እዚህ ሃገር በራስ ድልም ሆነ በሌላው ድካም ስሜ ካልገነነ ባይ ብዙ ነው... መደበቅን ለእነርሱ ማን ነገራቸው?... 


🌼 በተስኪያን ተገኝቶ 'ምጽዋቴ በድምጽ ማጉያ አልተነገረም' ብሎ የሚከፋው፣ በደመወዝ እየሰራ ውለታ የዋለ የሚመስለው፣ ያበደረህን መልሰህ እንኳ አኮቴት የሚጠብቀው፣ ወዘተ - እጅግ ብዙ ነው... ውለታ ሳይጠብቁ ቅንነት መዋልን ማን አስተማራቸው?...


[ልብ አድርግ...]


የለመነንን አይተን ያለንን መስጠትና ለማያውቁት ሰው በማይታወቁበት ሁኔታ ደግ መሆን የተለያዩ ነገሮች ናቸው... በሌህበት ድርጊትህ ብቻ ሲገኝ 'ጠላቴ' የምትለውን ሰው ሳይቀር ሊጠቅም ይችላል... ቤትህ መጥቶ የለመነህ ግን በአኳኋኑ ብቻ እጅህን ሊያሰበሰብ ይችላል...


[አልከራማ... የደግነት ማማ!!]


ይህ ዓይነቱ ልምምድ በሱፊዎች መንደር የተለመደ ነው... እነርሱ ጋ መንገደኞች ስውር አገልጋይ አላቸው... በበረሃ እዚህና እዚያ በተሰሩ ታዛዎች፣ በከተሞች ውብ ተደርገው በተሰሩ ማረፊያዎች ይስተናገዳሉ... ማዕድና ቀዝቃዛ ውሃም ያገኛሉ... [አይከፍሉም - ሻጭ ከባንኮኒው የለም... ስም አይጠየቁም - ተቆጣጣሪው ከበር አልቆመም...] ለእነርሱ የማያውቁትን እንግዳ ማስተናገድ መለኮትን በሰው አምሳል ማገልገል ነው...


አዎን - ታላቁ ስጦታ ምላሽ የማይጠብቁበት ነው... ይህ ችሮታ ተናጥሎን አያውቅም - ተጓዥ እና ለጋሽ፣ መንገድና ታዛ፣ [ማዕድ ያኖሩ ልቦች፣ የተቀበሉም እጆች] - በአንድ ነጠላ ክር ይዳወራሉ... በፍቅር!!...


[ፍቅርን ከመስጠት በላይ ዕዳ አይኑርባችሁ!!...]


___

ወጋችንን ከሱፊዎች መንደር በተዋስናት ውብ መስመር እንቋጭ:


“The water does not drink itself, the tree does not eat its own fruit, the sun does not shine for itself. To live is to give.”

___

@bridgethoughts

Читать полностью…

Dildiy - (ድልድይ)

.
.
.

እነርሱ - በቅኝ ግዛት ቀንበር ስር ቆይተው የባርነት አባዜ ባይተዋቸው ወራሪዎቻቸው የፀነሱት 'ስምምነት' ጸንቶ ይግዛን ይሉናል...


እኛ - በአባቶቻችን የደም ዋጋ በነፃ ሃገር ተወልደን ጌትነት ስለተቀዳጀን በራሳችን ጉዳይ ላይ ለመወሰን እኛ እንበቃለን እንላለን...


The difference is visible!!


ኢትዮጵያ... 


[አባይ ወንዟና የታሪክ ጓዟ ጎስቋላ ያደረጓት ሃገር ነች...]


ዛሬ በአባይ ወንዟ ላይ ሰልጥናለች - ነገ በታሪክ ሰበብ የተጣባትን ቀውስ ትፈታለች...

.
.
.


አዎን...


📯 የሚጀምር ትውልድ አባል መሆን ደስ ይላል!

📯 ሂደት የሚመራ ትውልድ አካል መሆን ደስ ይላል!

📯 የሚጨርስ ትውልድ አባል መሆን ደስ ይላል!

___

@bridgethoughts

Читать полностью…

Dildiy - (ድልድይ)

ባስነጠሰ ቁጥር ፈሱ የሚያመልጠው ሰውና የወር ደሞዝተኛ ኑሮ አንድ ናቸው... 

Just saying...

___

@bridgethoughts

Читать полностью…

Dildiy - (ድልድይ)

.
.
.

ዘወትር እሁድ ምሽት ከሩቅ የሚሰማኝ አንድ ሙዚቃ አለ... የሚስረቀረቅ፣ የሚስለመለም፣ የሚያባባ ዓይነት... 


ግጥም የለውም... ዘፋኝ የለውም... የመሳሪያ ብቻ ሙዚቃ ነው... የጊታር፣ የክራር፣ የዋሽንት፣ የሳክስ፣ የቫዮሊን... [ቆይ ተውት - የመሳሪያውን ስም አላወቅሁትም...] 


ስሰማው እንባዬ ይመጣል... ባር ባር ይለኛል... ጭብጥ እላለሁ... ድምጹ የሩቅ ነው... አንዳንዴ ወደ ደጅ ወጥቼ የድምጹን አቅጣጫ አስሳለሁ... ግራና ቀኝ ከጎረቤት - አይደለም... ሽቅብ ሰማይ ቁልቁል መሬት - አይደለም... ምንጩ የት ነው?...


ዛሬም እንዲሁ ሆነ... 


አልጋዬ ላይ ጋደም ብዬ እየሰማሁት ቁልቁል እንባዬ ወረደ... እንደተለመደው ወጥቼ ከበሬ ቆምኩ... ጆሮዬን አዟዙሬ ቀሰርኩ... ምንጩን አላወቅሁትም... ከግቢ ወጥቼ ዞርዞር አልኩ... ስልኬን አውጥቼ Shazam ላደርግ ሞከርኩ... ሞባይሌ ድምጹ አልተሰማትም... [ሙዚቃውን ላገኝ አልቻልኩም] አለችኝ...


ወደ ቤቴ ገባሁ... 


የዚህ ሙዚቃ ምንጭ የት ነው?... ማድመጤን ቀጠልኩ... ዜማው አልተለወጠም... ውበቱ ግን አይሰለችም... ጣዕሙ ሁሌም አዲስ ነው...


ግራ ሲገባኝ ጆሮዬን ደፈንኩ... ግጥም አድርጌ በትራስ አፈንኩት... የሙዚቃው ጥራት ጨመረ... ጆሮዬን ከግንዱ ጋር ጨቆንኩ... ድምጹ ጭራሽ እየጎላ መጣ... 


በዚህ መሃል አንድ ድምጽ በሙዚቃው ስልት ውስጥ ሆኖ በለሆሳስ አናገረኝ...


ድምጹን አውቀዋለሁ... ያንተ ያለህ!... የራሴ ድምጽ ነው...


አንድ ቃል ብቻ ነው ደጋግሞ የሚነገረኝ...


'ትተኸኛል'... 

'ትተኸኛል'...

'ትተኸኛል'...


እንደ ሰማሁት ሲያውቅ እየሳሳ ሄደ... እየራቀ... እየራቀ...

____

✨ ለራሳችሁ ጊዜ ከሰጣችሁ ስንት ጊዜ ሆነ?... ከራሳችሁ ጋር ቁጭ ካላችሁ ስንት ጊዜ አለፈ?... በወግ ካወጋችሁ፣ ከተደማመጣችሁ፣ ሰከን ብላችሁ ከመከራችሁ - ምን ያህል ዓመት ሆነ?... ✨

____

“Nowhere you can go is more peaceful—more free of interruptions—than your own soul.” ~ Marcus Aurelius

___

@bridgethoughts

Читать полностью…

Dildiy - (ድልድይ)

.
.
.

የዛሬ ስንት ዓመት በእናትና አባቴ ጠያቂነት ምድሪቱ ከነገረ ስሪቷ የቆነጠረችውን ሥጋ በኪራይ አስረክባኝ በዚህች ውብ ዓለም ውስጥ ተከሰትኩ...


[የኑረት ስሌትህ እየገፋ ሲመጣ አባቶችህ ያስረከቡህን ስንቅ ቅርጥፍ አድርገህ ብትበላም ለልጅህ የምታቆየው ውርስ እጅህ ላይ አለመቅረቱ ስለሚያሳፍርህ ዕድሜህን አትናገርም...]


በኖርኩባቸው ዓመታት ሳቅና ለቅሶዬ ተላቁጧል... ደስታና ሃዘኔ ተጋምዷል... አክብሮት ንቀቴ ተሳስሯል... ፍቅር ጥላቻዬ ተቀይጧል... ማግኘት ማጣቴም ተዛንቋል...


እጅግ የረዘሙ ለሊቶች በጎጆ ጓዳዬ አቀርዝዘው ያውቃሉ... እጅግ አስደሳች ወቅቶችም በኑሮ ደጄ ተመላልሰው አልፈዋል... እጅግ የከፉ ሰዎች ሆዴን አሻክረው ያውቃሉ... እጅግ ልዩ ሰዎች ልቤን በሃሴት ሞልተዋል...


[የብዙ ሰዎች መዋጮ ነኝ...] 


ቆጥሬ የማልጨርሳቸው ሰዎች ቃላት የማይገዳደሩትን ውለታ እየዋሉልኝ ነው እዚህ የደረስኩት... ማወቅ ሳይገዳቸው እጅ የዘረጉልኝ፣ ስስት ሳይፈትናቸው በር የከፈቱልኝ፣ ምላሽ ሳይጠብቁ እልፍ የለገሱኝ - ብዙ ናቸው... ['የኔ የምለው አንዳች የለኝም' የምለው ለዚህ ነው]...


[መልካምነቴን እንጃ - እንጂ እኔም ብሆን ለሃዘናቸው ሰበብ፣ ለእንባቸው ምክንያት የሆንኳቸው አይጠፉም...]


ከደረሰብኝ ያልተናገርኩት ይንዛዛል... [ካልተናገርኩት የዘነጋሁት ይበዛል፣ ከተረፈው ውስጥ 'ይቅር' ያሟሟው ይገዝፋል]...


ያም ሆኖ...


እንቆቆ የጋቱኝ ማርነቴን አላጠፉትም... አይዞህ ያላሉኝ ብርታቴን አልነኩትም...


የገፉኝ ከገደል ወለል አልጣሉኝም፣ ወለል የጣሉኝ መውጫዬን መዝጋት አልቻሉም፣ ለመዝጋት ቋጥኝ ያኖሩ መብረሪያ ክንፌን አላዩም...


ሳይረዱኝ ለቀሩ ሰዎች ራሴን ላብራራ መድከሜ ያናድደኛል... ሳልረዳቸው ቀርቼ ያዘኑብኝን ሳስብ ይጸጽተኛል... [መተው ባይኖር - ከስረን ነበር]


የለመንኳቸው ሰዎች የተለማመጥኳቸው እንደመስላቸው ሲገባኝ ብስጭቴ ብቅ ትላለች... [ለመኖር ብዬ ግን አልተናነስም - ለመኗኗር ካልሆነ በቀር]... 


ግማሽ መንገድ ሊመጡ ሲገባቸው አልፌ የጠበኩዋቸው ሰዎች ግዴታዬ እንደሆነ ማሰባቸው ከገባኝ ድጋሚ አላገኛቸውም... በፍቅር ካደረጉት ግን እንደ ውለታ አልቆጥረውም...


ዝምታዬን ከሞኝነት፣ አንገት መድፋቴን ከሃፍረት ሲቆጥሩ በልቤ የናቅሁዋቸው አይጠፉም... ብልጣብልጥ መስዬ ከመንገዳቸው ግን አልወደቅሁም...


የአንዳንድ ሰዎች ክፋት አይሎ 'እንኳን አውላላ ላይ ጣሉኝ' አስብሎኝ ያውቃል... ምክንያቱም አማራጭ እንድፈልግ፣ አዲስ ሰው እንዳውቅ አድርጎኛልና...


___


የሆነስ ሆነና...


[ከመኖር ምን ተማርኩ?...]


☘ መተው! [እርግፍ አድርጎ መተው!]

☘ የኖረ ሁሉ ይሞታል! [ከውቅያኖሱ ላይ ወደላይ የወጣች የውሃ ጠብታ መልሳ ወደ ውቅያኖሱ ትቀላቀላለች]

☘ ይህም ያልፋል! [መፈራረቅ የገጽታ ደንቡ ነው]


___


እንኳንም ተወለድኩ... 


[ዛሬ የወጣችውን ፀሐይ ማን በእኔ አንፃር ያያት ነበር?...]

____

@bridgethoughts

Читать полностью…

Dildiy - (ድልድይ)

.
.
.

"ምንአገባኝ?" ብሎ መተው እኮ ይቻላል... 

"ማንን ነው የሚያገባው ታዲያ?" ቢሉን መልስ የለንም እንጂ...

__

የገጠመን ፈተና ይህ ነው... ብዙ ሰዎች ብዙ ነገር አያገባቸውም... 

ለዚህ ነው - ሃገር የጥቂት ትጉሃን መዋጮ ውጤት ነች ለማለት የምደፍረው... ብዙሃኑ ነገር ዓለሙን እኒሁ ጥቂቶች ላይ ጥሎ 'ጥቅሙን' ብቻ የሚያሳድድ ነው...

__

በተገኘህበት ቦታ - 'መገኘትህን' የሚናገር አንዳች ቁምነገር ካልተውክ መኖርህ ከቁጥርነት አልዘለለም ነበር ማለት ነው...

__

@bridgethoughts

Читать полностью…

Dildiy - (ድልድይ)

.
.
.

ሁሉንም አታወራም አይደል?... ሁሉን ከሁሉ ጋር አትካፈልም... 


አንዳንዴ... 


በግል ጉባኤህ፣ በልብ ሽሽግህ፣ በነፍስያህ ለዛ፣ ካዘመመ ጎጆህ ታዛ - ብቻህን ቆዝመህ የምታንሾካሹከው ጉዳይ ይኖርሃል...


ደግሞስ ሰው ሁሉ በየቤቱ በራሱ ድካም እየደቀቀ፣ በግሉ ሃሳብ እያለቀ፣ በዕጣፈንታው ህመም ታስሮ፣ በራስ ፈተና ተቸንክሮ - ጉስቁልቁል እያለ ምን ብለህ የኔን ብቻ ስማ ትለዋለህ?...


ከመከራህ መከራዬ ይልቃል ነው?... 

ከስቀትህ ሰቀቀኔ ይብሳል ነው?...


[በደንብ ካሰብከው - የሌሎችን ሕማም ለመታመም አይደለም - የራሱን ቁስል ከፍቶ ለማየትም ልቢቱ የሳሳችበት በየቤቱ ብዙ ነው...]

.
.
.


ይልቅ ምን አለ መሰለህ?...


ሰሚህ በችግርህ ውስጥ ጉድለቱን እያየ ከሰማህ - አደመጠህ አይባልም - ተነፈስክበት እንጂ...


ሰሚህ ስለሰማህ ድብርት ከተጫነው - አደመጠህ አይባልም - ጫንክበት እንጂ...


'ይህችማ ምን አላት? እኔ የደረሰብኝን ብታውቅ...' ብሎ ከመለሰልህ - አደመጠህ አይባልም - ቁስልህን ካደብህ እንጂ...


እና እንዳልኩህ ነው...


አንዳንድ ጊዜ... ለብቻህ የምትሸከመው መስቀል ይኖርሃል!!...

____

@bridgethoughts

Читать полностью…

Dildiy - (ድልድይ)

.
.
.

የዓለማችን 'ግዙፍ ሚዲያዎች' - የቀን ውሎ 90% ያህሉ - በጦርነት፣ በሽብር፣ በግጭትና በጉስቁልና ዜናዎች ብቻ ይሸፈናል ቢባል ድምዳሜው ግነት ተጭኖታል አያስብልም...


በጎ ነገር ባለበት በጭራሽ ዝር አይሉም - ቢሉም እንኳ ደጉን ለመዘገብ ሊሆን አይችልም... ይልቁን በሰርግህ ዕለት ተገኝተው ያንተ ደስታ ለሌሎች የሃዘን ምክንያት ሊሆን የሚችልበትን መንገድ በዘገባቸው በማንሳት ሊያስገርሙህ ይችላሉ...


ይህ በተዘዋዋሪ የሚፈጥረው ጫናና ውጥረት ቀላል አይደለም... 


ዓለሚቱ አንዳችም በጎ ነገር የሌላት መስላ ስትቀርብ ዕለታዊ መስተጋብራችን ድንዛዜ ይዋረሰዋል... ተስፋ መቁረጥና ሕይወትን አጨልሞ የማየት አባዜ ይጫነዋል...


ምዕራባውያን ሚዲያዎች ከበጎ ነገር ይልቅ 'ክፉው' ላይ ብቻ የሚረባረቡበት ምክንያት ምንም ይሁን የሚቃኙበት Editorial policy ግን አስገራሚም አሳዛኝም ነው...


ይህን እውነት ይዘን በልካቸው ስናወራ እንዲህ እንላቸዋለን...


CNN - Continuous Negative News

BBC - Brutal Biased Channel

AFP - All Fear Press

NYT - Not Your Truth

____

@bridgethoughts

Читать полностью…

Dildiy - (ድልድይ)

.
.
.

彡 Title - Three Seconds before Goodbye

彡 Artist - Sia, ft. Damian Marley

___

@bridgethoughts

Читать полностью…

Dildiy - (ድልድይ)

“My brain is only a receiver; in the Universe there is a core from which we obtain knowledge, strength, and inspiration. I have not penetrated into the secrets of this core, but I know that it exists.” ~ Nikola Tesla

___

@bridgethoughts

Читать полностью…

Dildiy - (ድልድይ)

.
.
.

ሰውነቴ ውድቅ ሲል፣ የጊዜ ቀስት ወደፊት ማለቱን ትቶ አንገቱን ሲያዘልስ ይሰማኛል... አልጋ ላይ ነኝ - የሞት አልጋዬ ላይ... አዎን - በየደቂቃው እየሞትኩ ነው... በውስጤ ሕላዌን የሚያጸና አንዳች እንጥፍጣፊ አቅም አልቀረልኝም...


🛌 እየሞትኩ ነው... 


[ከነፍሴ ማዕዘን ግን አንዳች ድምጽ ያቃጭላል...]


የስኬት ሃሳቤ ሞቷል... የማግኘት ምኞቴ ተሰናብቷል... ጆሮዬም የዓለምን ጫጫታ ሰልችቷል... የነፍሴ ቃጭል ብቻ ነው እዝነ ልቡናዬን ለመድረስ የሚቃትተው ... ስላልጨረስኩት ፍቅር፣ ስላላጣጣምኩት ነፃነት፣ ስላልተናገርኩት እውነት የሚያንሾካሹከው... 


🛌 እየሞትኩ ነው... ጅስሞቼን የሞት ሻህላ እየበረበረብኝ ነው...


ወደፊት እየሞትኩ ወደኋላ የሚጎትተኝን ሹክሹክታ እሰማለሁ... ወደፊት እየጠፋሁ ወደኋላ የሚስበኝን ድምጽ አሻትታለሁ... አዎን - ድምጹ ጸጸት የሚያኝከው የራሴው ድምጽ ነው...


'ተወኝ ልሙትበት' አልኩት... ሊሰማኝ አልፈቀደም... ብሶቱን እስከ ጥግ ተብሰከሰከ... ዝም ብዬ መስማቱን መረጥኩ...

____


🗣️ [የምሩን አልኖርኩም... ዕድሜ ከመርኩ እንጂ...] አለኝ...


አሁን ሲገባኝ በሕይወት የመዝለቅ ጽናት እንጂ በጥልቀት የመኖር ድፍረት አልነበረኝም... ትንፋሼን ይዤ ሳሳድድ የኖርኩት ምቾቴን ብቻ ነበር... የምር መኖርን አልነበረም... ዛሬ ሲገባኝ ድሎት እርባን አልነበረውም... የምሯን ሕይወት መኖር እንጂ... ምልዓቷን መዋብ እንጂ... በዚህ ረገድ ደፋር አልነበርኩም...


🗣️ [ብዙ ፍቅር አልሰጠሁም...]


ቋንቋ ፍቅርን ለመግለጽ ካልዋለ ድኩም መሳሪያ እንደሆነ አሁን ገብቶኛል... ፍቅርን ያልገለጹበት ቋንቋ ዘላለማዊነት እንደሌለው ዛሬ ታውቆኛል... ትርጉም ያለው ድምጸት - ፍቅርን የነገሩበት ነው... እኔ ግን ዝም የማለትን ምቾት ሳሳድድ ነበር... ዝምታዬ በነፍሴ ላይ ቅጥርን ከመገንባት ውጪ ምንም አላተረፈልኝም... ብዙ ጊዜዬ በቁጣ ነው የባከነው... ሆኖም ቁጣ ለአጭር ጉዞ የማይመከር ከባድ ጭነት ነበር... ጥጌ ላይ ደርሼ ሳስበው ቀለል ብዬ ተጉዤ በነበር ብዬ እመኛለሁ...


🗣️ [ሕልሜን በጸጥታ አፍኜ ገድዬዋለሁ...]


ሕልሜ ከአይለኬው የሚፈለቀቅ ንዑድ ነበር... እርሱን ቸል ማለቴ ራስን አንቆ ከመግደል የተለየ አልነበረም... አዎን - ዛሬ የሚያሳምመኝ ትናንት ያላሳካሁት አይደለም - ጭራሽ ያልሞከርኩት እንጂ... ትልቁም ሃዘን ሞት አይደለም - ኖሮ አለመታየት እንጂ... ራሴን በሚገባ አልከፈትኩም ነበር... የምሩ ፊቴን አልገለጽኩትም ነበር... ይልቁን ለመመሳሰል ስል ራሴን በዓይነርግብ ውስጥ ሸሽጌያለሁ... ለአብሮ መኖር ሸንጎ ስል ልኬ ያልሆነን ጥብቆ ለብሻለሁ... መመሳሰል በሕላዌ ስትር ውስጥ እንደ ድቡሽት ነው... ከንቱ መደለያ!...


🗣️ [በኑሮ ሩጫ ውስጥ የተላለፉኝ ቅጽበቶች ብዙ ናቸው...]


ነፍሴ ነጋ ጠባ 'ምን ያህል አገኘህ?' ትለኝ ነበር... ከውሎህ ምን ቃረምክ? ከድካምህ ምን ሰበሰብክ? ከመስተጋብርህ ምን አተረፍክ? - ትለኝ ነበር... መልሱ ግልጽ ነው - ያስተዋልኩትን ብቻ... 


የስንቱ ሕፃን ፈገግታ ከትኩረቴ አምልጧል?... የስንት ማለዳዎች የፀሐይ ሙቀት ከተገንዝቦቴ ተፋቷል?... ደግሞስ - በልብ ምቴ መሃል ያለን ጸጥታ ልቤ ስንቴ ልብ ብሏል?... እልፍ፣ ብዙ፣ ወፈ ሰማይ... [ነፍሴ ዘመኗን ሙሉ የምትጠብቀው ገነት ግን እርሱን ነበር...]


🗣️ [መንፈሴ ከሚራብበት ነበር የቆየሁት...]


ፍርሃት የፈጠረው እርጋታ ሞልቶኝ ነበር... ምቾትን ከይምሰል ሰላም ጋር እያምታታሁ ነው የኖርኩት... እውነተኛ ሰላም ታማኝ ልቦችን ብቻ እንዲጎበኝ አልገባኝ ኖሯል... እውነትን ከደህንነት ለሚያስበልጡ ብቻ እንዲገለጥ አላስተዋልኩ ኖሯል... ሃቂቃ -  ብቻ ለመቆም የሚወስኑ የሚለብሷት ሞገስ መሆኗን ዘንግቼ ኖሯል...

___

ብዙ እንባ

ብዙ ቁጭት

ብዙ ህመም...








ሞት የማይሽር - ማረር!!... 

🛌 እየሞትኩ ነው...

___

'የፈሰሰ ውሃ አይታፈስም'...

እነሆ...

በጣት የሚቆጠሩ የትንፋሽ ውጣ ውረድ ቀርቶኛል... አልጋ ላይ እንደተንጋለልኩ ነው... የሞቴ አልጋ ላይ...


'ጥንቱን ነበር እንጂ - አልሞ መደቆስ
አሁን ምን ያደርጋል - ድስት ጥዶ ማልቀስ'

___

“And in the end, it’s not the years in your life that count. It’s the life in your years.” ~ Abraham Lincoln

___

@bridgethoughts

Читать полностью…

Dildiy - (ድልድይ)

.
.
.

[History doesn’t wait for applause or agreement; it moves on with those who dare to be true.]

___

ታሪክ - ለባለታሪኮቹ እውነት እንጂ ለአንባቢዎቹ አስተያየት ቁብ አይሰጥም... ብትክደውም ሆነ ብትቀበለው እውነታውን ከመቀየር አንፃር  ሽራፊ አስተዋጽዎ እንደሌለህ ያውቃል...



🔥 ስሙን ብታጎድፍ - ግብሩን እንደማትደርስ ያውቃል... 


🔥 መልኩን ብታጠይም - ፍጥረቱን እንዳትደግም ያውቃል... 


🔥 በአፍህ ብትክደው - ከሕሊናህ እንደማትፍቀው ያውቃል... 


🔥 ማደሪያውን ብታጠፋ - አዳሪውን እንደማትገፋ ያውቃል...


___


ወዳጄ... የሆነን መካድ መሆኑን አይፍቅም!... ላለመስማት መሻት መዘከሩን አያስቀርም!... ምልክቱን ማጥፋት መንፈሱን አይከድንም...


“Truth is like the sun. You can shut it out for a time, but it ain’t goin’ away.” — Elvis Presley


መፍትሔው...


👉 ከነበር ስህተት ለነግ ብልሃት መቅዳት

👉 በእልፊት ከመቆጨት የተሻለ መስራት

👉 ለመልካም ጅማሬ የምስጋና ፍሬ - መዝራት ነው...

___

ዳይ...


ድርሻህን ኑር!!

___

@bridgethoughts

Читать полностью…

Dildiy - (ድልድይ)

.
.
.

አንብቤው እንዳልገባኝ መስመር - ፊትሽን ደጋግሜ እንዳየው የሚጎትተኝ መግነጢስ ምን ይሆን?...



የእናቱን ጡት 'ጠገብኩ' ብሎ እንደማይተው ሕፃን... ቆሎ 'በቃኝ' ብሎ እጁን ወደ ሌማት መዘርጋት እንደማይሰለች ሰው... 



በስንኞች መሃል ሲመላለስ በድግግሞሹ ልክ አዲስ የምስጢር ቋት እንደሚከፍት ጠቢብ... ከተራ መስመሮች መሃል የጠለቀ ሃሳብ፣ የረቀቀ ውበት፣ ያረመመ ቅኔ እንደሚፈለቅቅ ትጉህ አንባቢ - ፎቶሽ ሰርክ አዲስ የሚሆንብኝስ ለምንድነው?... 



ዕጹብ ነው... ድንቅ ነው...



በዝምታ፣ በጸጥታ፣ በእርጋታ ውስጥ ሆኖ ቅኔውን ያራቅቃል... በኃይል፣ በግርማ፣ በመርዕድ ዘዬ ሰምና ወርቁን ያፈልቃል...
 


[ደጋግሜ ባየሁት ቁጥር...]



አዲስ ውበት፣ አዲስ ጸዳል፣ አዲስ ሞገስ፣ አዲስ ስለት እያቀበለ ልቤን ይቦረቡራታል...



ቁራኛዬ...



ምን ይሉት መግነጢስ ነው ከፎቶሽ ስር እያጣደፈ፣ እያክለፈለፈ፣ እየሳበ የሚወስደኝ?...



Desktop እና Laptop ላይ Screensaver... ስልኬ ላይ Lock screen እና Home screen Wallpaper... Wallet ላይ፣ Album ውስጥ፣ ጠረጴዛዬ ላይ... [አልበዛም?...]



አንቺዬ... የእስከዛሬው ኩራቴ 'ከቡና ውጪ ሱስ አያውቀኝም' ነበር... ውሸቴን ይቅር በይው - ከፎቶሽ ጋር ሱስ ይዞኛል...



የምር ግን...



በአካል ጥላሽ ብርታት ልቤ ቀልቡን ካጣ - ከፊትሽ ስቆም አጥንቶቼ ላለመቅለጣቸው ዋስትናዬ ምንድነው?...

___

@bridgethoughts

Читать полностью…

Dildiy - (ድልድይ)

.
.
.

የማግኘትን ጥቅም ከማግኛው መንገድ ስህተት ጋር አላምታታም...

___

@bridgethoughts

Читать полностью…

Dildiy - (ድልድይ)

ሰላም ወዳጆች
--
ከዚህ ቀደም መንደራችን ውስጥ የሚገኙ ሦስት ምርጥ Digital magazines አስተዋውቄያችሁ እንደነበር አትዘነጉም… ዛሬ ውብ የስነጽሑፍ ስራዎች የሚስተናገዱበት ሌላ መጽሔት ላስተዋውቃችሁ ነው…

ቀለም ይባላል…

በስነጽሑፍ፣ በፍልስፍና፣ በግለ-ታሪክና በወጎች ያጌጠ መጽሔት ነው…

እስኪ ጎራ ብላችሁ፣ አዲሱን ቅጽ 1 እትም 3 መጽሔትና ሌሎች ቁምነገሮችን ከቀደሙ ህትመቶቻቸው ጋር ተቋደሱ…

/channel/kelemofficial

Читать полностью…

Dildiy - (ድልድይ)

✨Dildiy's New Year Reflection✨


As the old year dissolves into silence, may we step into the new one not as travelers bound by calendars, but as seekers of the infinite—sparks in the great mystery of existence.


This year, let us see beyond the veils of yesterday and tomorrow, awakening to the sacred rhythm of Now.


May our laughter become cosmic music, our tears cleanse illusions, and our love expand like starlight across the sky of being.


Together, let us walk as companions of the unseen, remembering that every breath is a doorway, every meeting a mirror, and every step a return home—to the timeless truth within.


For us, a New Year is not the measure of time, but the unfolding of consciousness.

___

@bridgethoughts

Читать полностью…

Dildiy - (ድልድይ)

የቁጣ ግራ ቀኝ...

.
.
.

[፩]

___

ሰዎች በቁጡነት ይወቅሱሃል እንጂ ያስቆጣህን ሰው ነውር፣ አልያም ለኮስ ያደረገህን ውስጠ ነገር ልብ ብለው አይመረምሩም... በሌላ አገላለጽ ያስቆጡሃል እንጂ ያስቆጣህን ጸባይ ጥመት በአንተ ቦታ ቆመው አይመዝኑም...
 

በምን ተቆጣህ?... No one cares [እርሱ ያንተ ጉዳይ ብቻ ነው]... ሌላው ይህን ለመጠየቅ ጊዜ አያጠፋም... ለራሱ ሲሆን ትንሽ ነገር የሚበቃው ሁሉ አንተ ላይ ሲደርስ አንዳች አይሰማውም...


ብዙ ሰዎች በእነርሱ ሰበብ ባይሆንም እንኳ ተናደህ ሲያገኙህ ሊረዱህ ከመሞከር ይልቅ ምቾታቸውን እንደነሳህ ሊያስቡ ይችላሉ... ወይ ደግሞ እነርሱ ቢሆኑ ፈጽሞ የማያደርጉትን ነገር በምክር መልክ ሊለግሱህ ይሞክራሉ...


ንዴት፣ ብስጭት፣ ቁጣ ወዘተ - ጥሩ ነገር እንዳልሆኑ እኮ ታውቃለህ... ስሜትን መግዛት መሰረታዊ የኑሮ መርህ እንደሆነም አይጠፋህም... ግን ደግሞ ስሜት አለህ... ሰውም ነህ... ነገሮች ከገደባቸው ሲሻገሩ ምላሽ መስጠት መጀመርህ ተጠባቂ ነው... 


[ብስለት ማለት ለነገሮች ስሜት ማጣት ማለት አይደለም - ሚዛን መጠበቅ እንጂ...ብልህነት ይህን ስሜት መቆጣጠር እንጂ ዜሮ ማድረግ አይደለም... ምላሹን መመጠን እንጂ እንዳልተሰማው መሆን አይደለም... 'ምንም አይሰማኝም' ምናምን የሚል ደረቅ ስታገኝ ታዝበህ እለፈው...]


አንዳንዱ ገፍቶ፣ ገፋፍቶ፣ ገፍትሮ ከብስጭት ጫፍ ያደርስህና React ማድረግ ስትጀምር በተራው መናደድ ይጀምራል... እንዴ 'ቅቤ እየቀባህ' ነበር እንዴ የመሰለው?...


ለመከፋትህ፣ ለብስጭትህ፣ ለንዴትህ ነዳጅ ሲጨምር መቆየቱን ሳይሆን በነዳጁ ብዛት መቀጣጠል መጀመርህን ነው ሰው የሚያስተውለው... ነገሩ የሆነበትን ምክንያት ሳይሆን የሆነውን ክስተት ብቻ ነው የሚመለከተው... ይህ ዓይነት ሰው ለፍርድ ቅርብ ነው... የደረሰበት ላይ ሆኖ ውሳኔ ይሰጣል... ከመነሻው ደርሶ አይመረምርም... ከመድረሻው ዘልቆም አያመሳክርም... ጭራሽ ሰው መሆንህን ይረሳዋል... ስሜትም ያለህ አይመስለው...


በእርሱ ቤት ሲቀዳልህ የቆየው ነዳጅ ተራ ውሃ ነበር... 'ደግሞ ይሄ ምን ያናድዳል?' ይልሃል... [አይገርምም?... እዚህ ጥግ ድረስ ለሌሎች ስሜት እናጣለን]... 'አካበድከው' ይልሃል... 'Emotional intelligence ላይ መስራት አለብህ' ምናምን የሚልም አይጠፋም... በሌላ ቀን ያንተን ቁራጭ በማትደርስ እንከን ሲብከነከን ብታገኘው ታዲያ አይግረምህ... 


[እኛ ከሌሎች ስንክሳር በላይ የራሳችን ስንጥር ዘልቆ የሚሰማን ግለኞች ነን]


መረሳት የሌለበት...


ሁላችንም ቅኝታችን ለየቅል ነው... ተመሳሳይ ነገሮች እኩል ስሜት አይሰጡንም... አንድ ዓይነት ነገሮች እኩል አይነዝሩንም... ለብግነትህ ምክንያት የሆነ ነገር ለእኔ ቁብ ላይሰጠኝ ይችላል... እኔን ያስደነገጠ ጉዳይ አንዳች ስሜት አይፈጥርብህ ይሆናል... [በዚህ ረገድ ልዩ ልዩ ነን]

___

[፪]
___

ቁጣህን በማሰሮ ውስጥ እንደሚንተከተክ ወተት ብታፍነው ጊዜው እየገፋ ሲመጣ መገንፈሉ አይቀርም... ስለዚህም መተንፈስ አለበት... የታፈነ፣ የታመቀ፣ የተወጠረ ነገር በራሱም ሆነ በሌላው ላይ ጉዳት ከማምጣት አይመለስም...


"ድስት ቢገነፍል የሚያቆሽሸው ራሱን ነው" ቢባልም ፍንጥርጣሪው ልብስ አያበላሽም ማለት አይቻልም...


እርግጥ ነው - ቁጣ የማይፈለግ ስሜት ነው... ከዚያ በላይ ግን ቁጣን አምቆ መቆየት እጅግ አደገኛ ነገር ነው... Buddha እንዳለው: 


“Holding on to anger is like grasping a hot coal with the intent of throwing it at someone else; you are the one who gets burned.”


ለዚህም ሲባል ቁጣን በልኩ ማስተናገድ፣ ከልብ ማዳመጥ፣ ምንጩን መመርመር፣ ቆስቋሽ ሰበቡን መለየት፣ ከምንም በላይ ደግሞ [በራስ ላይ መንቃት] እጅግ ጠቃሚ ይሆናል...


በመሰረቱ ስሜቶቻችን ጠላቶቻችን አይደሉም - ምልክቶች እንጂ... አንዳንዴ ቁጣ የጥልቁ እኛነታችን ባሕሪያዊ ጥላ ሊሆን ይችላል... በስውሩ የአዕምሮአችን ክፍል ውስጥ ያለውን ጠቋሚ መስታወት... በዚህ አውድ መምህር ሲሆን በቅጡ ለማያነበው ደግሞ የአዕምሮ ገዢ ሆኖ እውነታን ይከልላል - ያስክዳልም...


እናም ስሜቶቻችንን በማፈን ጠቢብ አንሆንም... በአንክሮ በማዳመጥ እንማርባቸዋለን እንጂ...

_

እናም እንዲህ እንላለን...


ለሌሎች ብሽቀት ምክንያት አለመሆን ደግ ነገር ነው... ሲናደዱ ለመረዳት መሞከር ደግሞ ሩሕሩሕነት ነው... ስሜት አለማመቅ ጠቃሚ ነገር ነው... በስሜት መስታወት ውስጥ ውስጠትን ማየት ደግሞ ዘላቂ መላ...

___

እነሆ ነገራችንን በሚዛን የሚጠቀልልልን የጠቢብ ቃል...

___

“Anybody can become angry — that is easy. But to be angry with the right person, to the right degree, at the right time, for the right purpose, and in the right way—that is not within everybody's power and is not easy.” – Aristotle

___

@bridgethoughts

Читать полностью…

Dildiy - (ድልድይ)

🌿

🌿

🌿

ፍቅሬን እንዴት ማሳየት እንዳለብኝ ተለማምጄ ሳልጨርስ ሄደች...


በልቤ ውስጥ ያለው ነበልባል በቃል ተሰርቶ ወደጆሮዋ ሊፈስ ይቃትት ነበር... የመውደዴ ብርታት በቃል አክናፍ በርሮ እዝነ ልቡናዋን ሊያንኳኳ ይጓጓ ነበር... ጎርፍ የመውረጃ ፈለጉን እንደሚያስስ... ሕፃን የእናቱን ጡት ፍለጋ በጨለማ እንደሚዳብስ...


በውስጤ የታመቁት ቃላት ከውክብክቡ ዓለም አይደሉምና በተራ ድምጽ አይወከሉም - በጸጥታ ይነግሳሉ እንጂ... መሻቴ ከአፍዓ ገጽዋ አልተቀዱምና ለሙገሳ የተሰሩ ፊደላት አልሰጠሁዋትም - በጥልቅ ዝምታዬ ውስጥ የሚጓደዱትን እንጂ... 


[በቅጽበታት መሃል እንደሚገኝ ትንፋሽ... ነፍሶች እንደሚያወጉበት ድምጽ የሌለው ፈሳሽ...]


አዎን - እኔ ይህን ጸጥታ ወደ ቋንቋ መለወጥ ገና አልተማርኩም ነበር... እርሷም እንዲህ ዓይነት ቋንቋ ሰምታ አታውቅም ነበር...


ሄደች... 


እውነቱን ከመግለጼ በፊት ተጨለጠች... 


[ፍቅር] 


የምሰጣት - የኔ 'ምለው፣ የምትነፍገኝ - የእርሷ የሆነው እንዳልሆነ ሳልነግራት በነነች...


የዘላለማዊው ኃይል መስታወት፣ በሁለንታ ላይ የሚፈስ የኃይል ዥረት መሆኑን ሳላስታውሳት ዱካዋን አጠፋች... ዳናዋን ሰወረች...


ሄደች... የአካል ኑረቷን ከለለች...


[አዎን ሄዳለች - ግን ደግሞ አልሄደችም...] 


መቅረቷ በሌላ ቅርጽ መኖር ሆኖ ቀጥሏል... አካሏን እንጂ በኔ ዓለም ውስጥ ያነቃችውን ፍቅር በቀላሉ ማጥፋት ስላልተቻላት በመንፈስ ነብራለች... 

 🌿

ፍቅሯ ወደ ኁልቆ አልባው ዓለም ሲያሻግረኝ ከፈራሽ ገላዋ ብፋታም በእርስዋ ሰበብ የተሰጠኝ ማሕተም የሃገሩን ኬላ ሁሉ የሚያሻግር አርነት ሰጥቶኛል... 


[በእውኑ የተወኝ ምኗ ነው?...]

___

@bridgethoughts

Читать полностью…

Dildiy - (ድልድይ)

ያገኙሽ ሁሉ በአንቺ ምክንያት የውበት መለኪያ ሚዛናቸው ተደነቃቀፈ... ትናንት 'የውበት ጥግ' ካሏት ጋር ሲያነፃጽሩሽ አልደራረስ አልሽና - አልቀው ሰቀሉሽ... 


በእውነት ከዚህ ከፍታ ላይ ሌላ ሴት አይደለም አንቺ ራስሽም መድረስሽን እጠራጠራለሁ...


ውበትሽ ምን እንደሆን ታውቂያለሽ?...


መረዳትሽ!!

___

@bridgethoughts

Читать полностью…

Dildiy - (ድልድይ)

.
.
.

[ግራ እየገባኝ ስሄድ አንድ ነገር እየተማርኩ እንደሆነ አውቃለሁ... ምናልባትም ለመንገዴ አንድ ተጨማሪ የብርሃን አምድ እየተተከለች ይሆናል...]

.
.
.

አንዳንዴ ተራ ብዬ ባቃለልኩት ነገር ውስጥ ተቆጥሮ የማያልቅ መደነቅ ይወርሰኛል... ሌላ ጊዜ ደግሞ ድንቅ ያልኩትን ሳሳድድ ከእጄ ያለውን ውበት አጣና ሃዘን ይከበኛል...


[ወደላይ ብቻ የሚያዩ ከእግሮቻቸው ስር ያለውን የምድር ሃብት አይረዱም... አዘቅዝቀው የሚመለከቱም ከበላያቸው ያለውን ንጽህና አይገነዘቡም...]

___

አንዳንዴ ብዙ አለኝ ያልኩትን ጊዜ በአልባሌ ነገር ሞልቼ አባክነዋለሁ... አጠረኝ ያልኩትን ደግሞ ከበድ ባሉ ስራዎች አጭቄ ሳልጠቀም ፈጀዋለሁ...


በሁለቱ መካከል የሚተርፈኝ አንዳች የለም - ከጭንቀትና እረፍት አልባነት ውጭ...


[ነገ ይሆንልኛል እያሉ የሚጠብቁ ዛሬን አያጣጥሙም... ዛሬ ካልሞላልኝ ብለው ሙጥኝ የሚሉም ከነግ ተስፋ አይገናኙም...]

___


አንዳንድ ቀን በፍቅር እንደተጥለቀለቅሁ ይሰማኛል - ሆኖም ወዲያው በእውር ድንብር አስረክቤው ዝምታ ይውጠኛል... ሌላ ጊዜ ደግሞ ፍቅር አጣሁ ብዬ ፍለጋ እወጣለሁ - ይሁንና ቅንስናሽ ማንነቴን በየቦታው ተቀምጦ ሳገኘው እደነግጣለሁ...


በዚህ ሰበብ የሃሳብ ድካም ያናውዘኛል... ውርሱ ሃዘን የሆነ ዘር በውስጤ ያጎነቁላል...


[መፈቀርን ብቻ የሚሻ መስጠትን ሳይማር ያልፋል... ፍቅር ሲሰጥ ብቻ የኖረም የመቀበል ቆምታን ይተላለፋል...]

___


የሕይወት መትረፍረፍ በተሰማኝ ማግስት ራሴን የሚጠፋ ጥላ ሲያሳድድ አገኘዋለሁ... ኑረት በጉድለት ስሜት ስትከበኝ ደግሞ ጫፍ በሌለው ምኞት ሸክሟን አበዛዋለሁ...

በዚህ ሰበብ ባዶነት ይወርሰኛል... ተስፋቢስነት ይጫነኛል...


[መድረሻውን ብቻ የሚያይ ጉዞውን ይረሳል... መንገዱን ብቻ ሙጥኝ ያለ አድማሱን ይዘነጋል...]

___


ነፃ የሆንኩ ይመስለኛል - ግና ራሴን የማገኘው በምርጫዎች ሰንሰለት ታብቶ ነው... ነፃ እንዳልሆንኩ አስባለሁ - ግና ውስጤ የማየው የግዞት ጫና የማይታከካቸውን ዕልፍ ቦታዎች ነው...


በዚህ ሰበብ ቀልቤን ቅዥት ሞልቶት ያታልለኝና የምር ትግል ውስጥ እገባለሁ...


[ነፃነትን የሚፈሩ የራሳቸው አዕምሮ እስረኛ ከመሆን አይድኑም... ነፃነትን ያለአግባብ የሚጠቀሙ የምኞቶቻቸው ባሪያ ከመሆን አይቀሩም...]

___

እንደነገርኳችሁ ነው...


ግራ እየገባኝ ስሄድ አንድ ነገር እየተማርኩ እንደሆነ አውቃለሁ... 

___

@bridgethoughts

Читать полностью…
Subscribe to a channel