bridgethoughts | Unsorted

Telegram-канал bridgethoughts - Dildiy - (ድልድይ)

-

“Let's build bridges, not walls.” Martin Luther King, Jr. — Visit my blog: https://dildiy.net/ — ድልድይ - ግላዊ እይታና ጥልቅ የመሻገሪያ እሳቤዎች የሚጋሩበት ከንባብ፣ ከኑረት እና ከምናብ የሚቀዱ ንሸጣዎች መድረክ ነው። - ሃሳቦቹ ከየትኛውም የአስተሳሰብ ጎራ (ism) አይወግኑም!! — Concern & Concept — D.S.

Subscribe to a channel

Dildiy - (ድልድይ)

የመጀመሪያው ጠዋት...


የካንቲኗ ንጽሕና እንከንየለሽ ነው... ሞገስ አለው... የዕቃው አቀማመጥ፣ የጠረጴዛና ወንበሩ አደራደር፣ የክፍሉ ጠቅላላ ድባብ፣ መዓዛው የመብላት አምሮትን ይቀሰቅሳል... የእናት ቤት ያስረሳል... [እዚህ ሌላ እናት አለች...]


በኮይሻ ካንቲን ውስጥ መመገብ የራበውን ሆድ ከምግብ ጋር ከማገናኘትም በላይ ረቂቅ ነው... መንፈስህ ይረካል... ዓይንህ ውበት ይሞላል... ምላስህ የጣዕም ጥጉን ይደርሳል... 


በማይቋረጥ ትህትና፣ በማይበላለጥ አክብሮት፣ በማይሰክን ብርታት፣ ሰርክ አዲስ በሆነ ትጋት መስተንግዶ ይጠብቅሃል... 


ሌላ ቀን ከሰዓት...


ሰው እንዴት ሁሌና ለሁሉም ሰው መልካም ይሆናል?... ሰው እንዴት በማይናጠብ ትህትና ከሄደ ከመጣው ጋር ይዋባል?... ምን ዓይነት ልብ ነው ይሄ?... ምን ዓይነት ርቀት ነው የምር?...


ሁሉን ወዶ፣ በሁሉ ተወዶ መገኘት ልምድ ይወልደዋልን?... በየሰው ልብ ውስጥ ያለ ልዩነት ቦታ ማግኘት ሰውነት ይቀርጸዋልን?... አይመስለኝም - ይሄ አንዳች ዓይነት መንፈሳዊ ተውህቦ ያለው ተፈጥሮአዊ ልገሳ ነው... 


ኮካ ይህ ብርቅ ጸጋ በተግባሯ ላይ ብቻ ሳይሆን በሁለንተናዋ ላይ ፈስሶላታል... እያየችህ ባልሆነ ጊዜ እንኳ የእናትነት መንፈሷ ይረብብሃል... ካንቲኑ በሰው ተሞልቶ ባለበት ሁኔታ እንኳ ሁሉም ሰው እንደ ሃጃው የሚገነዘበው ስሜት ከየእንቅቡ ይደርሳል...


ብዙዎቻችን በዚህ የስሜት ከፍታ የምናውቀው እናታችንን ብቻ ነው... ኮካን ያዩ ሰዎች ደግሞ ለሁሉም እናት መሆን የተቻላት ስለመሆኗ በግልጽ ይመሰክራሉ...


የሆነ ቀን ምሽት...


ያ ቀኑን ሙሉ በነዲድ ፀሐይ ሲጣፋ፣ ከብረት ጋራ ሲላፋ፣ ከኮንክሪት ጋር ሲጋፋ፣ በዳገት ቁልቁለቱ ሲገፋ የሚውልን ባለሙያ አስቡት...


የዛለ ጡንቻውን፣ የደከመ ገላውን፣ የተበተነ ሃሳቡን በአዕምሮአችሁ ሳሉት... ምን አበርትቶት ነው ታዲያ ወደ ስራ የሚመለሰው?... ምን ፈውስ ሰጥቶት ነው መሳሪያውን ዳግም የሚያነሳው?... 


የብርታቱ አንዱ ምንጭ የኮካ ማዕድ ነው... ሰዓት ደርሶ ወንበር ሲስብ፣ ትንፋሽ ወስዶ ኮካን ሲያስብ - ልቡ የማይረሰርስ፣ በሚቀርብለት ማዕድ የማይፈወስ የለም...


እርሷ ንድፍ ከሚያወጡ መሃንዲሶች፣ ከሚገነቡ እጆች እኩል ለቦታው ቁልፍ ነች... በዚያች የ NASA ጽዳት ሰራተኛ ንግግር ውስጥ ካየናት ደግሞ 'የኃይል ማመንጫ ግድብ እየገነባች ነው'... ግድቡ ሜጋዋቶችን ያመነጫል - እርሷ ሰብዓዊነትን ትረጫለች... 


ከመጀመሪያው ቀኔ ጀምሮ እንዳስተውላት የሚያደርግ ሞገሷን ለመገንዘብ አልሰነፍኩም... ለነገሩ እንዴትስ ይቻለኛል?... የኮካ ጸባይ እኮ የማይደብቁት ፀሐይ ነው... ለሁሉ ይታያል...


በፊት ገጿ ላይ በሚበራ የፈገግታ ፀዳል እንዳዩዋት ያውቋታል... በእጇ ሙያ በምግቧ ጣዕም፣ በሙያ ያደንቋታል... ብሉ ጠጡ ስትል በድምጽ፣ እንደ እናት ይለይዋታል...

____


የመጨረሻው ቀን...


ተግባራችን ተፈጽሞ መለየታችን ግድ ሆነ... ቁርሳችንን በልተን ስንወጣ ልንሄድ መሆኑን ሰማች... ከኩሽናዋ ስትሮጥ ወጥታ በቆዘመ ልብ አናገረችን...


'ልትሄዱ ነው እንዴ?'

'አዎን' መከፋቷ ተጋብቶብን

'ስንቅ ሳልቋጥርላችሁ?' ከፋት

___

አንድ ቀን፣ ይመስለኛል ቁርስ እየበላን ነው፤ እንክብካቤዋ ከልክ በላይ ሲሆንብኝ፣

'እናት እኮ ነሽ' አልኳት

'ነኝ እኮ ታዲያ - ልጆች አሉኝ' አለችኝ... ለእኛ እናት መሆኗን መቀበል ከብዷት

'ልክ ነሽ፣ እዚህም ግን ልጆች ወልደሻል' አልኳት - የመልካም መንፈሷ ተቋዳሽ መሆናችንን ላስታውሳት...

___


ለመንገድ ብላ የቀረቀበችልንን ሁሉ መኪናችን ላይ ጫንን... ተሰናብተናት ጉዞ ጀመርን...


ብዙ፣ ብዙ፣ ብዙ ራቅን...


ዓይኖቿ ዓይኔ ላይ ተመላለሱብኝ፣ እናትነቷ፣ ሩህሩህነቷ፣ የፊቷ ገጽታ፣ ዓይኔ የሚያየውም - ልቤ የሚረዳውም ሁሉነቷ፣ እንደ ጽላሎት እንደተከተለኝ ገባኝ... 


ሰው ጠግቦ የበላ የማይመስላት - እናት!... 
ሁሉን የምትስብ - መፍቀሬ ሰብ... 
ሁሉ የሚወዳት -  ሒሩት!...

____

አንዳንዴ እጃችን ላይ ኖሮ በቅጡ ያልተገነዘብነውን ጣዕም፣ ውጣ ውረዳችንን ሳይሻ በቀላሉ የተከሰተልንን ጥቅም for granted እንወስዳለን... እንደነገሩ እንተዋለን... 'ምን አዲስ ነገር አለው?' ብለን እናሳንሳለን... እንዲህ እያልን በጎ ልቦችን እንሰብራለን... ውብ ጅምሮችን እንገድላለን...

____

አንድ ነገር ልለምናችሁ...


ቅን ልቡ ለሚነካችሁ - ለእርሱ፣ ቅን ልቧ ለሚያርሳችሁ - ለእርሷ ይህንን የደግ ሰው ሃቲት ላኩለት/ላት... አንዲት ነፍስ ተውባ ልባችንን ደስ ስታሰኘን ካላመሰገንን ሌሎች ደጎች አይፈጠሩም፣ ውቦቹም በውብነታቸው አይጸኑም... አጋጣሚ ፈልገን 'አበጀህ ጎሽ' ካላልን፣ ምክንያት ሽተን ካላደነቅን የየልቦቻችን በረሃማነት የሰደድ ምንጭ ሆኖ ያጠፋናል...

____

ይህ ማስታወሻ - በየነፍሳችን ደጀ ሰላም ድንገት ተከስተው የደስታችንን ማድጋ ለሞሉ፣ በመኖር አንድ ቀን ለአፍታ ሳቃችን ሰበብ ለሆኑ ሰዎች መዘከሪያ እንዲሆን ተጫረ...

____


@bridgethoughts

Читать полностью…

Dildiy - (ድልድይ)

🗣️
.
.
.

ያላዩህ ያዩህ'ለት

.
.
.


“If a man is called to be a street sweeper, he should sweep streets as Michelangelo painted, or Beethoven composed music, or Shakespeare wrote poetry.
He should sweep streets so well that all the hosts of heaven and earth will pause and say, 'here lived a great street sweeper who did his job well'.” ~ Martin Luther King Jr.

____

"አንድ ሰው መንገድ ጠራጊ ነው ከተባለ... ሚካኤልአንጀሎ ረቂቅ ስዕሉን ሸራ ላይ በሚያትምበት ውበት፣ ቤትሆቨን ሙዚቃውን በሚያስማማበት ጥልቀት፣ ሼክስፒር ቅኔውን በሚያራቅቅበት ልኬት መንገዱን መጥረግ አለበት... ይህን ካደረገ የሰማይ አጋፋሪዎችም ሆኑ የምድር ተመላላሾች በዚያ ቆመው 'እዚህ ጋ ኃላፊነቱን በቅጡ የሚወጣ ጎበዝ መንገድ ጠራጊ አለ' ይላሉ"

____

የአበርክቶህን ውበት የምትስልበት የአንተ ሸራ ምንድነው?... ተመልካቹን የሚያስደስት ያንተስ ውበት ወዴት ነው?... ልብህ ትረካበት ዘንድ የአንተ ግብር ምንድነው?...

____

✍️ ድብቁን ውበት ይገልጽ ዘንድ ግልጹን መጥረጊያ ለማንሳት አታመንታ... በሌለህበት ስላንተ ይመሰክር ዘንድ አጠራረግህን ከልብ አድርግ... 

____


@bridgethoughts

Читать полностью…

Dildiy - (ድልድይ)

⭐️

የሚያየኝ እንደሌለ ባወቅሁ ጊዜ ዓይኖቼን በዕንባ ሞላሁ... የሚሰማኝ እንደሌለ ሲገባኝ በእሪታ ዙሪያዬን አናጋሁ... የሚጠይቀኝ እንደሌለ ስገነዘብ ከአውላላ ተንጋለልኩ... 


እፎይ... 


አንዳች ዕዳ ከውስጤ ሲመነጨቅ ተሰማኝ...


ቆይታዬ በረዘመ ቁጥር ተመስጦዬ እየጠጠረ ሄደ... ያለሁበትን ስዘነጋ የጨረቃ ወግ ከበደ... 


ይገርማል...


ዘግይተው ካለሁበት የደረሱ ሁሉ እብድ ነው ብለው ይሸሹኝ ነበር...


በምሽቱ ፍካት፣ በጨረቃ ውበትና በከዋክብት ንፃት የተመሰጡ ዓይኖቼን ሊያስተውል የፈቀደ አልነበረም - ከእርሷ በቀር...


ፍቃዴን ሳትጠይቅ፣ ለልብሷ ሳትጠነቀቅ፣ ስለ ትውውቃችን ሳትጨነቅ መጥታ ጎኔ ተንጋለለች...


እኔኑ መሰለች!!...


የሙዚቃው ምት አልተረበሸም... የምሽቱ ወግ አልተናጠበም... ይልቁን ታደመችበት... ሳትደናገር አዜመችው... ከደረሰችበት ቀጠለችው... አብራኝ ዘመረች... 


[ዜማውን እንዴት አወቀች?... ስንኙን እንዴት አለችው?... እስከዚያች ቀን ድረስ የኔ ብቻ አልነበረምን?...]


ጨረቃ ደስ አላት... ከዋክብትም አረገዱ...


ሆኖም...


የእንግዳዬ ብርሃን ያፈካው ዙሪያዬን ሲመለከቱ በዚያ መቆየት እንደሌለባቸው ገብቷቸው ነበር...


ይሄኔ... ልቤ ወደ ጆሮዬ አስግጋ እንዲህ አንሾካሸከች...


"ልቧን ወድጄዋለሁ፤ ምታችን ሲጣጣም ተሰምቶኛል..."


ልቤን አመንኳት... ዓይኖቼ ወደ ውስጤ ማየት መጀመራቸውን አስተውዬ ነበርና...

____


@bridgethoughts

Читать полностью…

Dildiy - (ድልድይ)

.
.
.

እናም...


እንዲሁ እየተፎጋገርን ሌላ መስከረም ይጠባል... እንዲሁ እያስመሰልን ሌላ ክረምት ይመጣል... ማልገጥ ትትርና እንደሆነልን መሰንበቻው ይቆጥራል...


ልቦቻችን እየተዋወቁ በአንደበት ልክ እንካካዳለን... ተግባራችን ጮሆ እየተናገረ በቃል ድርድር ትጉህ እንመስላለን...


ከእያንዳንዱ እንቅስቃሴ ትርፍ እንዲቆየን፣ በእያንዳንዱ ተሳትፎ ጥቅም እንዲጎበኘን የተሰባሰብን ከንቱዎች ሆነን ሳለ ከእኛ በላይ አሳቢ የሌለ ያህል መድረክ እንሞላለን...


ባቡራችን ወዴት እንደሚሄድ ግድ ስለማይሰጠን እንደ ተሳፋሪ አንጠይቅም... የየግል መነሻ እንጂ የጋራ መዳረሻ እንደሌለን እያወቅን ለተሳፋሪ ወንበር አንለቅም...


አንዳንዶቻችን ባቡሩ በልኩ እንዳይሄድ የምንጎትት ፉርጎ ነን... ሹፌሩ ልፍጠን ሲል 'እንዴት ተደርጎ!' እንላለን... 


አንዳንዶቻችን በ locomotive ድክመት ፍጥነታችን የተገታ ምስኪናን ነን... አካሄዳችን ልክ አይደለም ስንል 'ዝም በሉ!' እንባላለን... 


ከነዚህ የባስነው ደግሞ ለውጥ የማይሸተው Locomotive እና የማይሞቅ የማይበርደው Cargo ሆነን ሳለ እየሄድን ነው እያልን እንደነፋለን... 


አይጓዙም እንዳንባል ስንንከላወስ እንታያለን፤ 'የት ደረሳችሁ?' ስንባል መልስ አጥተን እናፈጣለን...


ዥንጉርጉር ነን...


አንዳንዴ የተለያየ የሃሳብ ግዛት ውስጥ ካሉ ሰዎች ጋር የጋራ ሕልም ለማዋለድ የሚደክም ምስኪን መስሎ ይሰማኝና በኔዬ ተስፋ እቆርጣለሁ...


አንዳንዴ ከራሳቸው የሚበልጥ፣ ከዘመን ልኬታቸው የሚጠልቅ ሃገራዊ ሕልም ለማዋለድ የደከሙትን አስብና እበረታለሁ...


አንዳንዴ ደግሞ ካሳካሁት ይልቅ የማስበው መግዘፍ ያደክመኛል... ከሰራሁት ይልቅ ልሰራ የተገባው መብለጥ ያሳፍረኛል... መፍጠን በምችልበት ጊዜ መጎተቴ መሄድ በማልችልበት ወቅት ለተሰማኝ ድባቴ ምክንያት መሆኑን ማወቅ ያጸጽተኛል...


ከዚህ ሁሉ በላይ ግን...

.
.
.


ያለቦታዬ ቦታ ይዤ 'ተቀምጫለሁ' ማለቴ ያሳምመኛል...

____


[ካልተቋጨ የግል ማስታወሻ የተቆነጠረ...]

____

@bridgethoughts

Читать полностью…

Dildiy - (ድልድይ)

.
.
.

በቋንቋ በኩል ስናጮልቅ...
.
.
.

እንደ እንግሊዝኛ ግን አምባገነን ቋንቋ አለ?... የምሬን እኮ ነው...  ያልሆነውን ሁሉ አሁነን እንድንጠራው፣ የሌለውን አለህ እንድንለው የሚያስገድድ፣ የመጨረሻ አምባገነን ቋንቋ ነው...


ምሳሌ ልስጥህ፤


Book - ይሄ አሁን ምኑ ነው 'ቡክ' የሚመስለው?... ቋንቋው እኮ 'ቡ' የሚባል ፊደል የለውም... 'ክ' የሚል ፊደልም ወልዶ አያቅም... ጭራሽ እኮ አራት ፊደል ነው የያዘው... እንዴት ብሎ ነው በሁለት ድምጽ ብቻ የሚወከለው?... B ሁለት O ጠቅልሎ 'ቡ' እንዲባል፣ K ያለ ስሙ ስም ፈጥሮ 'ክ' እንዲሰኝ የፈቀደው ማን ነው?...


ሌላም ነገር አለ... 'BU' ለምሳሌ 'ቡ' ነኝ ሲል ብዙ ጊዜ ሰምተሃል... Bullet ሲደመጽ 'ቡሌት' የሚሆነው ለዚያ ነው... የሚገርመው ግን እኒሁ ፊደላት ዞር ብለው 'በ' ካልተባልን ሲሉም ገጥሞሃል... Butterfly እንዲሉ...


ነገሬ በቅጡ እንዲመጣልህ እነዚህን አራት ፊደላት ተመልከት - 'Ough'...


Enough - “ኢናፍ”፣ Though - “ዶ”፣ Tough - “ታፍ” እንዲሁም Through - “ትሩ” ተብሎ ይነበባል... አራቱም ቃላት አንድ ዓይነት የመጨረሻ ፊደል ቢኖራቸውም የሚነበቡት ግን በአራት የተለያየ ድምጽ ነው... ይህ የሚሆነው በምን ሂሳብ ነው ታዲያ - በአምባገነንነት ካልሆነ...


Read - ድሮ ድሮ “ሪድ” ብለን ነበር የምንለው... ዛሬ ደግሞ “ሬድ” ሆኗል... Red ምን ተብሎ ይሆን?... ፊደሉ አንድ ነው፣ ድምጹ ግን ተቀይሯል...


Lead - “ሊድ” ሲባል ብረት (ንጥረ ነገር ነው)... ራሱ Lead “ሌድ” ሲባል ደግሞ መመራት ይሆናል... ተመሳሳይ ፊደል፣ የተለያየ ትርጉም... Colonel በትክክሉ ሲነበብ “ኮሎኔል”
ነው፤ ልክ የሚያስብለው ግን “ከርነል”
ሲባል ነው... Queue አምስት ፊደል ያለው ቃል ነው... ሲደመጽ ግን አንድ ብቻ ይሆናል - “ኩ”... ሌሎቹ ፊደላት ምን ያደርጋሉ ታዲያ?...


አዎን... 


This is not about English. This is about how agreement quietly replaces truth.


የማወራህ ስለ ፊደል አምባገነንነት አይደለም፣ ስለ ጅምላ ስምምነት እንጂ... ስለ ፊደል ድምጾች አይደለም፣ እውነትን እየደፈጠጠብን ስላለው መንጋነት እንጂ...

___


'ብዙሃን ልክ ናቸው' የሚል ስሁት መረዳት ፈጥረናል... 'ተለምዷል' የሚልን ስንፍና መሞገት ትተናል... እየሆነ ያለን ነገር በልኩ ለመመዘን ባለመፍቀድ ተረታ ተረቱን በ'ልክነት' ካባ አጎናጽፈናል... አንጠይቅም፣ አንፈትንም፣ አናናጽርም፣ ለአፍታ እንኳ ከተሰመረው ፈቅ አንልም...


ምሳሌዎቹን ካስተዋልካቸው እንግሊዝኛ ቋንቋ በራሱ እውነት አይፈጥርም... የቋንቋ ተጠቃሚዎቹ የኛ ስምምነት ነው እውነት የሚመስል ነገር የሚፈጥረው... በሌላ አገላለጽ አንድ ነገር ትክክል ስለሆነ አይደለም እንደ ትክክል የምንቀበለው፤ ስለተስማማንበት እንጂ...


ጭፍን ስምምነት ደግሞ በእውነት ላይ የሚጫን ጭቆና ነው... አስገድዶ ሃቂቃን ካድ የሚል አምባገነን ብቻ ነው... ሰዎች በአንድ ነገር ሲስማሙ
ያልሆነ ይሆናል...
የሌለ ይኖራል...
የተሳሳተው ትክክል ይባላል...


ስምምነት በፈጠረው ጫና ውስጥ ስትወድቅ ታዲያ ነገሩ ልክ አለመሆኑን ከመቀበል ይልቅ ልክነቱን ለማስረገጥ ብዙ ርቀት ትጓዛለህ... አገባብ፣ አናባቢ፣ ተናባቢ፣ ድምጸት ወዘተ የሚሉ ቅቦችን ትጠቀማለህ...

___


እንግዲህ በቋንቋው መስኮት ውስጥ ዓለሚቱን ተመልከታት... ያነበርነውን ስርዓት ገምግም... መስተጋብራችንን ሁሉ ፈትሽ... እውነት ብዙኅን ስለሚቀበሉት ቅጥፈት ሲባል በየመዳረሻው ትደፈጠጣለች... 'እነከሌ' ስላሉት ብቻ እውነትነቷን ታጣለች...


በዙሪያህ ያለው ሲስተም function የሚያደርገው በእውነት ነዳጅ አይደለም፣ በስምምነት ግዳጅ እንጂ... ብዙ ሰው የሚከተለው የፈተነውን አስተሳሰብ አይደለም፣ በደመነፍስ ያጸደቀውን እንጂ... በገባው ልክ እንዳይኖር ይሉኝታ የደፈቀውም ቀላል አይሆንም...


ስምምነት ጅምላዊነት ይጫነዋል... ከእውነት ፍለጋ ይልቅ ለስሜት ምላሽ ሰጪ ሆኖ መቅረብ ይቀናዋል... ስምምነቱ ስላለ ብቻ ልክነት፣ ብዙዎች ስለተቀበሉት ብቻ እውነትነት አለው ማለት ግን ያስቸግራል...


በሕግ ስርዓት ውስጥ ትናንት 'ልክ' የነበሩ ነገሮች ዛሬ 'ወንጀል' ሲሆኑ አይተሃል... የነገሩ ተፈጥሮ ስለተቀየረ ግን አይደለም - ሕግ አውጪዎች እንዲያ ስለተስማሙ እንጂ... (ፊደሎቹ ሳይቀየሩ ድምፃቸው እንደተቀየረው ማለት ነው)


በማህበረሰብ ውስጥ እያሉ እንደሌሉ የምንቆጥራቸው ብዙ ሰዎች አሉ... ከመኖራቸው እንገለገላለን - ግን አንሰማቸውም፤ ከድካማቸው እናተርፋለን - ፍላጎታቸውን ግን ከግምት ውስጥ አንከትም... የወል ስምምነቱ ያገለለውን ሁሉ በጸጥታ እናልፋለን... (ፊደሎቹ እያሉ Silent ተብለው እንደሚዘለሉት ማለት ነው)


ጊዜ

የእጃችን ላይ 'ሰዓት' የቀን ጅማሬና ፍፃሜን ይወስናል... የስራና የእረፍት 'ጊዜ' ገደብ ያበጃል... ግና የኛ አካል (body) ስለ ሰዓት አያውቅም... ጭራሽ ዩኒቨርሱ ላይ ጊዜ ኖሮ አያውቅም... ማሕበረሰቡ ጊዜን የሚለካው በስምምነት እንጂ በተሞክሮ አይደለም...


ድንበር

በካርታ ላይ የተጫሩ መስመሮች ሀገር ይሰራሉ... የአንድ እርምጃ ወደፊት ወይም ወደኋላ መሆን ሕጋዊነትና ሕገወጥነትን ይበይናል... ምድሪቱ ላይ እነዚያ መስመሮች የሉም... ስምምነት ግን አንብሯቸዋል...


ባለቤትነት

'ይህ መሬት የኔ ነው' ወይም 'ያ ወንዝ የነእከሌ ነው' ሲባል እናውቃለን፤ ብለንማል... የለየለት ደግሞ 'የወንዜ ልጅ' ብሎም ያዜማል... በተፈጥሮ ውስጥ ግን ስም ተለጥፎለት የተገኘ አንዳችም ነገር የለም... እንኳን 'የኛ' የምንለው ሊኖረን እኛም የኛ ሆነን አናውቅ... በመንጋ ስምምነት ግን ባለቤት ፈጥረናል...


ገንዘብ

አንዲት ቁራጭ ወረቀት በሕልውና ላይ ትወስናለች፣ መስተጋብር ትበይናለች፣ መደብ ትለያለች... እውነት ለመናገር ስምምነታችን ከፈጠረላት አቅም ነጥለን ካየናት ለመፃፊያ እንኳ የማንመርጣት ዥጉርጉር ወረቀት ናት... ዓለሚቱ ግን ጽድቅና ኩነኔዋን፣ ክፋትና ደግነቷን፣ ክብርና ውርደቷን ከዚሁ ወረቀት ትሰራለች...


ማዕረግ

ሰዎች ስለራሳቸው ከመናገራቸው በፊት title ስለነርሱ ይናገራል... የሆኑትን ከልሎ ያልሆኑትን ይሰብካል... ቃሉ ታዛዥ ይፈጥራል፣ ቃሉ አዛዥ ያደርጋል... ስለ ማዕረግ ስምምነት አዋቂና ታዋቂ ይምታታል... ማዕረግ የሌለው ጠቢብ በጊዜያዊ ስም ይዋጣል...


ትምህርት

የምስክር ወረቀት የብቃት ማረጋገጫ ይሆናል... የክላስ ውጤት የመረዳትን መጠን ይለካል... መማር ነጥብ ያስቆጥራል... ጥበብ ግን grade የላትም... ማሕበረሰብ በጠቢብ ልኬት ላይ ስምምነት የለውም...

ሌላም ብዙ ነገር...
___

መቋጫው ግን ምን መሰለህ?... 

የያዙትን መፈተን፣ የደረሱበትን መጠየቅ፣ የተስማሙበትን መፈተሽ ብልህነት ነው... ከዚህ ሁሉ በላይ ግን ስለ ብዙሃን እምነት እውነትን እንዳልጨቆኗት ማረጋገጥ የአስተውሎት ከፍታ ነው...


ጸሐፊው እንዳለው...

“Whenever you find yourself on the side of the majority, it is time to pause and reflect.” ~ Mark Twain

___

@bridgethoughts

Читать полностью…

Dildiy - (ድልድይ)

.
.
.

ለመያዝ የዘረጋ ካልቆመ፣ ለመጨበጥ የሰነዘረም ካልፈጠነ - በያዥና ተያዥ መሐል ፍላጎት ተፈትኗል...
.
.
.

ያልነበረ አይኖርም!!...

____

@bridgethoughts

Читать полностью…

Dildiy - (ድልድይ)

ሰላም ወዳጆች...

___

መጽሔታችን ቀለም በሰዓቷ ከች ብላለች... ቅጽ ፩ ቁጥር ፮ እትምን በዚህ ሊንክ ታገኛላችሁ... 

👇

@kelemofficial


ለምታውቋቸው ጋብዟት፤ ለጥበብ አፍቃሪያን ጠቁሟት...


ቻናሉን ተቀላቀሉ!!


ይህን ስለምታደርጉ እናመሰግናለን 🙏

Читать полностью…

Dildiy - (ድልድይ)

.
.
.

'ለፈረሰ ቤት ብርሃን ምኑ ነው?' አትበይኝ፤ ከብርሃኑ የሚያተርፍ እስካለ ድረስ...

___

@bridgethoughts

Читать полностью…

Dildiy - (ድልድይ)

ዶ/ር ጴሌ ዳሮታ ...
---
(ፍልስፍናን ከነነፃነቷ የኖራት፣ በልዩ ትወና የሰበካት አይረሴ ምሁር!)
-
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፍልስፍና ትምህርት ክፍል ረዳት ፕሮፌሰር የነበረውን የጴሌ ዳሮታን (ዶ/ር) ህልፈት የሰማ ከቀድሞ ተማሪዎቹ አንዱ የሆነው ‹‹አሳፍ ኃይሉ›› በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ስለ ጴሌ (ዶ/ር) ካሰፈረው ረዘም ያለ የታሪክ ማስታወሻ በጥቂቱ ቀንጨብ አድርጌ ወደ እኔው ጥቂት ትዝታ ለማለፍ ወደድኹ፤

የዕውቁን የፍልስፍና መምህራችንን የዶ/ር ጴሌ ዳሮታን ህልፈት ሰማሁ። ከልብ አዝኜያለሁ።

በእርግጥ ፔሌ ቀጥታ የእኔ አስተማሪ ሆኖ ባያውቅም፣ ዝናውን በመስማት ጉዱን ለማየት ከጓደኞቼ ጋር ከአንድም ሁለት ቀን በእርሱ ሌክቸር ክፍለጊዜ ገብቼ ሎጂክን እንደ መደሰቻ ሽቶ ተርከፍክፌ ነው የወጣሁት ብል ማጋነን አይደለም!

ጴሌ በጣም ቀልደኛ ሰው ነበረ። ስሙን በእንግሊዝኛ "Pelle" ብሎ ይፅፍና፣ ዕድሜ ለእንግሊዝኛ "ጴ" የሚል ፊደል ስለሌለው ስሜን ከጴሌ ወደ ፔሌ ቀየረልኝ — በማለት ያሳቀንን አልረሳውም!!
--
የፍልስፍና መምህሩን ጴሌ ዳሮታ (ዶ/ር) በጨረፍታ በእኔው ትውስታ!!

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ፍልስፍናን ነፍስ ከዘሩበት ምሁራን መካከል በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀስ ነው፤ በ1990ዎቹ አዲስ አበባ ተማሪ በነበርንበት ጊዜ የፍልስፍና ትምህርት ክፍል መከፈቱ ስለነበር ከሌላ የትምህርት ክፍል/ዲፓርትመንት እያስፈቀድን ጴሌ የሚያስተምርበት ክፍል እንማር ነበር፡፡

አንድ ወቅት ላይ ስለ እውነታ /what is Reality? / በሚል አርእስት የግሪክ ፈላስፋዎችና ጥልቅ አሳቢዎች /Philosophers and Great Thinkers የተናገሩት/የጻፉትን ሐሳብ እያስተማረን ሳለ፤ አብዛኛውን ጊዜ እንደሚያደርገው በሌክቸሩ መካከል አንድ ጥያቄ ለእኛ ለተማሪዎች እንዲህ ሲል አነሳ፤

‹‹እውነት ለእናንተ ምንድን ነው? ማነው?››

ተማሪዎች እርስ በርስ እየተያየን ዝምታን አሰፈንን… ‹‹በሉ እንጂ አይዞአችሁ ባትመልሱት አያሰቅላችሁም እኮ!›› ሲል ለማደፋፋር ሞከረ፡፡ ከጥቂት አፍታ በኋላ ከፊት ተቀምጦ የነበረ ተማሪ ፍርሃትና ሥጋት በቀላቀለ ድምፀት፤

‹‹ለእኔ እውነት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው!›› ሲል መለሰ፡፡

ጴሌ፡- መላጣውን አሸት አሸት እያደረገ ‹‹አረ ባክህ… ተው እንጂ… ይሄኔ በእርሱ ዘመን ኖረህ ቢሆን ኖሮ ሲወገርና ሲሰቀል አንዱ ድንጋይ አቀባይ አንተ ትሆን ነበር?!›› ሲለው ክፍሉ በሣቅ አውካካ…

ከዚህ በፍርድ ወንበር ፊት ከተቀመጠው ከጲላጦስ፤ ‹‹እውነት ምንድ ነው?›› ጥያቄ ጋር በተያያዘ ጴሌ አንድ በገሃዱ ዓለም የሆነ ይሁን ወይም ራሱ የፈጠረው ይሁን ለጊዜው ትዝ ባይለኝም አንድ ታሪክ እንዲህ ሲል አወጋን፤

በናዚ ዘመን አይሁዶች በያሉበት እየታደኑ በመርዝ ጋዝ ሲያልቁ በነበረበት ክፉ ጊዜ አንዲት አይሁዳዊት እናት እና ልጇ ተደብቀው ይኖሩ ነበር፡፡ ይህቺ አይሁዳዊት እናት ለብቸኛው ልጇ እንዲህ እያለች ትነግረው/ታስተምረው ነበር፤

‹‹ልጄ እውነትን ውደድ፤ ሁሌም እውነት ተናገር!››

ታዲያ አንድ ወቅት ላይ የናዚ አሳሽ ወታደሮች በጥቆማ ወደ ቤታቸው ይመጣሉ፤ ወታደሮቹ በሩን ሲያንኳኩ ልጅ በሩን ይከፍታል፤ ልጁን በጥያቄ ያፋጥጡታል፤ ‹‹እዚህ ቤት ውስጥ አንተ ብቻ ነህ የምትኖረው?››

ልጅ ይመልሳል… ‹‹አይ እናቴም አለች ግን እናቴ በታችኛው ምሥጢራዊ ክፍል ውስጥ ነው ያለችው፤›› በማለት የናዚ ወታደሮችን እናቱ ወዳለችበት ይመራቸዋል፡፡

ወታደሮቹ እናቱን እና ልጁን ይዘዋቸው ሄዱ፤ የእናቲቱና የልጁ ዕጣ ፈንታ እንደ ወገኖቻቸው ሁሉ በመርዝ ጋዝ ጭስ ተቃጥሎ፣ ታፍኖና ተልብልቦ መሞት ሆነ…

ጴሌ፡- ታሪኩን ተርኮ ከጨረሰልን በኋላ የተለመደውን ጥያቄውን አስከተለ፤

‹‹ለመሆኑ ለዚህ የግፍ ሞት ተጠያቂው ማነው… እናት፣ ልጅ ወይስ የናዚ ወታደሮች?! ከመመለሳችሁ በፊት ጥቂት አስቡ ዝም ብላችሁ እንዳመጣላችሁ እንዳትመልሱ… ጎበዝ ‹‹F›› ለማግኘትም እኮ ትንሽ ማሰብ፤ ማሰላሰል ይጠይቃል…›› ዳግመኛ ክፍሉ በሳቅ ማዕበል ተናወጠ…

ጴሌ እንዲህ ዓይነት የፍልስፍና መምህር ነበር… ነፍሱ በጥበብ ፍቅር የነደደች…!!

ጴሌ ዳሮታ (ዶ/ር) ነፍስህ በሰላም ትረፍ!!
---
ጸሐፊ - ተረፈ ወርቁ (ወዳጄ ምስጋናዬ ይድረስህ) 🙏

—-
@bridgethoughts

Читать полностью…

Dildiy - (ድልድይ)

.
.
.

የኔነሽ፣ 
የኔነሽ፣
የኔነሽ ይሏታል
እርሷም ደስ ይላታል


የሁሉ መሆን ግን ምን ያደርግላታል?

.
.
.

የሁሉ የሆነ - እንዳይሆን ለማንም 
ሁሉ ዘንድ የሞቀ - እንዳይገኝ የትም፤


ጸሐይ ነግራናለች - በዘለለት ልሳን
ሰርክ አዲስ እንግዳ - እኛ እንጂ ያልነቃን፤


በጠዋት ፈገግታ

በእኩለ ቀን ዋዕይ

ከባን ብትውልም፣

ጽልመት ሲገማሸር አታስተማምንም።

___

@bridgethoughts

Читать полностью…

Dildiy - (ድልድይ)

ሰላም ወዳጆች፤

ድልድይ - ቀለም ላይ አምደኛ ሆና ተከስታለች፤ ይህንን የጥበብ ብፌ ስጋብዛችሁ ደስ እያለኝ ነው...

___

ግቡ፣ Join አድርጉ፣ አዲሱን ቅጽ አንብቡ!!

___

ቀለም መጽሔት🗞️

ቅፅ 1  እትም 5


እያነበባቹህ ለወዳጅዎ ያጋሩ
ለሀሳብ አስተያየት

@KelemMagazine

Telegram 👇❤️
@kelemofficial

Читать полностью…

Dildiy - (ድልድይ)

🔔 Before the Drums Beat Again 🔔


Once upon a time, there was no Ethiopia and Eritrea.


There were only brothers — children of the same highlands,
breathing the same wind that rises from the Red Sea
and settles on the mountains.


The rivers did not know borders.
The mothers spoke the same lullabies.
The sky covered us all — without a passport.


But then came the shadow of lines drawn on the earth —
names that separated hearts, flags that replaced embraces.


And in the name of these lines,
thousands of young men and women offered their blood to the soil.
Still, the soil cried — not for victory,
but for the innocence lost.


Years later, the world rejoiced when the two brothers met again —
smiles, handshakes, hope.

The world said, “At last, the Horn of Africa breathes again.”
You both promised peace,
and the earth, weary from the echo of guns, finally rested.


Our Prime Minister received the world’s peace prize —
but more importantly,
our people received the peace itself.


Seven years passed.


Yet now, we hear the sound of old drums beating again.


Excellencies,

Before those drums awaken the ghosts of yesterday, please —
sit and talk.


Sit not as leaders of separate lands,
but as brothers who share one ancient wound.
History has already buried too many sons.
Must we dig new graves for the same reason?


A sea is not worth a single mother’s tear.
A port is not worth the trembling of a child
who hears warplanes in the sky.


The world does not need another headline of sorrow from the Horn;
it needs the light of wisdom from its cradle.


Yes — Ethiopia needs a gate to the sea.
And yes — Eritrea needs her sovereignty respected.
But more than that, both need each other.


The sea and the highlands are not enemies;
they complete each other —
like breath and heartbeat.


If you two meet,
not to debate, but to listen —
the Red Sea will calm its waves.
Trade will flow, families will unite,
and the wounds of decades will begin to heal.


But if the guns speak again,
no one will win —
except those who sell the bullets.


Please, for the sake of history yet to be written,
for the mothers who have already buried too much,
for the youth who dream of life, not war —
Sit and talk.


Let wisdom be your weapon.
Let love be your strategy.
Let peace be your legacy.


The Horn does not need heroes of war anymore.
It needs fathers of peace.


🕊️ May reason rise above rage,
and may love remember what history forgets.

____

@bridgethoughts

Читать полностью…

Dildiy - (ድልድይ)

.
.
.

ሰዎች በአንድም በሌላም መንገድ ሊጎዱህ ይችላሉ፤ የዝቅተኝነት ስሜት እንደሚያንገላታው ሰው ግን የሚያሳምምህ አይኖርም።
___

@bridgethoughts

Читать полностью…

Dildiy - (ድልድይ)

ትዝ አለኝ የጥንቱ...


[ያው እንደነገርኳችሁ የተወለድኩት በቅዳሴና አዛን መሐል ነው... የከተማው ትልቅ ደብርና ታሪካዊው ፈትኸል መስጅድ ጎረቤቶቼ ናቸው... በደብሩ ወገን ያለው ግድም - ገዳም ሰፈር፣ ከመስጅዱ ዙሪያ ያለው መንደር ደግሞ ነፃ ሰፈር ይባሉ ነበር... እርግጥ ዛሬ የሁለቱም ሰፈር ስሞች ለጥሪ ሲውሉ አይሰማም... በኔ ዘመንተኞች ዘንድ ካልሆነ በቀር... ]


ላወራችሁ የፈለግሁት ስለዚህ አይደለም... ከልጅነቴ ትዝታዎች በአንዱ ፈገግ ላስብላችሁ እንጂ...

___


ከዓመታት በፊት የሆነ ነው...


ቀኑ አርብ... የከተማዋ የገበያ ቀን ነው...


እንደተለመደው የደብሩ የማምሻ ጉባኤ እስኪጀመር ድረስ በግዙፍ ስፒከር መዝሙር ተከፍቶ ጥሪው ከየጓዳችን እየደረሰ ነው...


ይህን የማድረግ ተራ የደረሰው አንድ ጓደኛዬ የመዝሙሩን ካሴት ቴፑ ላይ ጥዶ የመቅደሱን በር ቆልፎ ወደ ከተማ ወጥቷል... [ቴፑ ለወቅቱ ዘመናዊ ቴፕ ነው - በራሱ ስለሚገለብጥ በእርሱ ቤት 'እደርሳለሁ' ብሎ ነው የራቀው...]


[ለዛሬ ልጆች ለማስረዳት - ካሴት ሁለት Side ያለው፣ በአንዱ ጎን 30 ደቂቃ፣ ሲገለበጥም ያንኑ ያህል ዜማ ተሸክሞ የሚዞር፣ ብዙ ጊዜ እስከ አስር የሚደርሱ ስራዎች የሚሸከፉበት የክር ጥቅል ነው... 😂😂😂]


ጓደኛዬ ከደብሩ ብዙ ርቋል...


የካሴትን ችግር ታውቃላችሁ መቼም... 


ወይ የቴፑ "አልማዝ" ያልቅና ድምጹ ይነፋነፋል... 


[አድገን እንደገባን 'አልማዝ' የሚባል ነገር የለም... Read head ነው የሚባለው... መቅጃው Record head፣ መደምሰሻው Erase head እንደሚባለው ማለት ነው...]


ወይ ደግሞ ቴፑ ክሩን ይጎለጉለውና የዜማውን ስልት ወደ ብዙ ድመቶች ጠብና አምባጓሮ ያሳድገዋል...


እርግጥ ያንለት ሁለቱም አልሆነም...


መዝሙሮቹ በየተራ ሲፈሱ ቆዩና ድንገት ምዕመናን ከየቤታቸው ብቻ የሚሰሟት የአንዲት ገናና ከያኒ ድምጽ በስፒከሩ ውስጥ ተንቆረቆረ... አስቱካ ነበረች...


"... ጠይም ዘለግ ያለ - የኮራው ደረቱ..."


ሰው ሁሉ በጥፊ የተመታ ያህል ጆሮው ጭው አለ... በተለይ የገዳም ሰፈር ልጆች ድንጋጤ ቅጥ አልነበረውም... ቤተክርስቲያኗ በጠላት ቁጥጥር ስር የዋለች ያህል ተሰማን... ጎዳናውን በአንድ ጊዜ ሞላነው... [በዚያው ቀን 'መዝሙሩ የማን ነበር?' ብንባል ማስታወስ የሚከብደን ሰዎች በአስቱካ ስርቅርቅ ድምጽ ጆሮአችን የነቃበት ሚስጢር ዛሬ ድረስ እንቆቅልሽ ይሆንብኛል...]


አስቱካ ቀጥላለች... 


'እንዴ፣ አይዘጉትም እንዴ?' ሰው ሁሉ ወደ ቤተክርስቲያን አሻግሮ እያየ ይንቆራጠጣል... አንዳንዱም መላምት ይሰጣል... ያን ሰሞን 'ተሐድሶዎች ከቤ/ን ተባረሩ' የሚለው ዜና አልበረደ ኖሮ 'እነርሱ ናቸው፣ ሊያዋርዱን፣ በጠላት ሊያስቁብን...' ብቻ ብዙ ብዙ ተባለ... [በወቅቱ ሞባይል የለ ምናምን... ለማን ተደውሎ ይነገራል?] ብቻ ድንጋጤዎች አንዳንድ ጫጫታዎችን ዝም ስላሰኙ ሙዚቃው በብዙ ሰዎች የመሰማት ዕድል አገኘ...


አስቱካ ናኘች...


በዚህ መሐል ጓደኛዬ ከሄደበት ተመለሰ... እያለከለከ፣ ላቡን እያዘራ፣ ምላሱ ጉሮሮው ላይ እንዳትወተፍበት እየተጨነቀ ወደ ቤተ/ን ገሰገሰ... 


አስቱካ ወደሌላኛው ሙዚቃ ተሻግራለች... [አጠቃላይ ክስተቱ 7 ደቂቃ ቢሆነው ነው... ሆኖም የ 7 ቀን ያህል ረጅም ነበር...]


ጓደኛዬ ደርሶ ዘጋው... እፎይ... [አስቱ በቁጥጥር ስር ዋለች]


[ወዳጄ እንደነገረኝ ቤተክርስቲያን ውስጥ የነበሩ ሰዎች ቴፑን ለመዝጋት ያላደረጉት አልነበረም... ግን በየት በኩል ይግቡ... 'ባልቦላ' እንዳያጠፉ ለቆጣሪው ጥንቃቄ ሲባል የተሰራው የጣውላ ቀፎ ተቆልፎ በየት ያግኙት?...]

___


ያን ዕለት ጓደኛዬ ብዙ ወቀሳና ትችት ወረደበት... [ቀድሞ ሌላ ሐይማኖት ይከተል ስለነበር 'ድሮስ' ምናምን ያሉትም አልጠፉም...]


የካሴቱ ቅድመ-ታሪክ ሲመረመር - የአስቴር አወቀ ሙዚቃዎች ስብስብ ሸክፎ ኖሯል ለካ... ሆኖም ተደምስሶ መዝሙር ሲቀዳበት ነባሩ ሙዚቃ የነበረው ርዝመት የክሩን ሰፊ ክፍል ይሸፍን ኖሮ ሳይደመሰስ የተረፈው ሙዚቃ ነው አየሩ ላይ የናኘው... [ካሴቱ ከ 20 ደቂቃ በላይ በመዝሙር ቢሸፈንም ቀሪ ቦታውን የያዘው ሙዚቃ አልጠፋም ነበር እንደማለት - መዝሙር ሲቀዳበት ከ Erase head የተረፈ...] 


ያንለት ከወትሮው ቁጥሩ እጅግ የበዛ ሰው ቤተክርስቲያኒቱን አጥለቀለቃት... የብዙዎች የመገኘት ምክንያት ታዲያ የጉዳዩን ሰበብ መስማት ነበር... [ያን ሰሞን የከተማዋ የቡና ተርቲበኞች አቦል ቶናና በረካ የሚወራረደው በወዳጄ "ሥጋ" ነበር...]

____

አንዳንዴ... [የሰው ልጅ]


ተኩላ ማንነቱን ለመሸፈን በለበሰው የበግ ለምድ የከረመ ዓመሉን መደበቅ ሲያቅተው፣ አልያም ቂመኛ ልቡን ለመከለል ከፊቱ የሞላው አስመሳይ ፈገግታ ጨካኝ ማንነቱን መከለስ ሲሳነው ሳይ ይህን ገጠመኝ አስታውሳለሁ...

___

@bridgethoughts

Читать полностью…

Dildiy - (ድልድይ)

The Flame Without Separation
___

He did not preach;
he breathed love—
softly,
like dawn touching every face
without asking who they are.


When the land cracked
under the weight of names and tribes,
he stood in the middle—
not to divide,
but to remind us
that the middle is where Love hides.


His hands held silence
that could calm storms,
his eyes—
mirrors where strangers
remembered themselves again.


He called no one sinner,
no one pure.
He called all hearts
to return to the circle
where light knows no border.


Now he is gone,
yet not gone—
for love never dies,
it only changes form.


The flame he carried
has scattered among us—
each spark
a whisper saying,
“Be the love that remains.”

____

He reminded us that love is larger than any name, faith, or border.

Even after he’s gone, his light lives in every act of kindness we choose.

___

@bridgethoughts

Читать полностью…

Dildiy - (ድልድይ)

የካንቲኗ ውበት - የሁሉ እናት

_

[የንጹህ ልብ ማስታወሻ]

[Tip የማይወዱ ሰዎች ይህን ጽሑፍ እንዲያነቡ አይመከርም]

____

መኪናው ወደፊት እየተወነጨፈ ልቤን ወደኋላ የሚስበው ነገር ምን ይሆን?... በመድረስ ጉጉቴና በተጓዥ ልቤ መሃል ተሰንቅሮ የሚቆረቁረኝስ ምንድነው?... 


የእኛ ነገር - መገናኘት ደግሞ መለያየት፣ መተዋወቅ ደግሞ እልም ብሎ መራቅ፣ መግባባት ደግሞ እስኪረሳሱ መጥፋት... 


በሕይወት አንድ ቀን ጉዳይ ሰበብ ሆኖ ሰዎች ወደ ልባችን ጓዳ ይገባሉ... በሌላ አንድ ቀን መራቅ ምክንያት ሆኖ ከልቡናችን ሸራ ይደበዝዛሉ...


እያንዳንዱን የሕይወት አፍታ ከናቅን፣ እያንዳንዲቷን በጎነት ቸል ካልን ሕላዌ ጣዕም አልባ ትሆናለች... ካስተዋልን ግና ከዕለት መገረም የሚሻገር የትዝታ ስንቅ እንፈጥራለን... ለሌሎች የሚነገር አብነት እናቆያለን...

____


በኮይሻ የኮንስትራክሽን ሁዳድ... 


ማሽኖች ሰርክ በሚያጓሩበት፣ ጸሐይ በወበቅ በምታነድበት፣ በተራሮች መሃል፣ በጥቅጥቅ ጫካ ውስጥ - አንድ ልዩ ኃይል አየሁ...


ይህ ኃይል ከተርባይኖች የሚመነጭ አይደለም... ይህ ኃይል በኬብል ውስጥ የሚፈስ አይደለም... ይህ ኃይል - በጸጥታ፣ በእርጋታ፣ በትጋት ከአንዲት ሽርጥ ለባሽ ሴት እጅ ላይ የሚፈስ ኃይል ነው... 


እርሷ ሼፍ ናት... ግና ቃሉ ለእርሷ ሲሆን በቂ አይደለም... ኮካ ይሏታል ባልደረቦችዋ... ሁነኛ ስምዋ ፋንታነሽ ነው... የኮይሻ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት የሰራተኞች ካፌ ሼፍ ናት... በአጭር ቆይታዬ ከአካል ግዝፈት ማዶ ያስተዋልኩዋት እናት!!...

___


እስኪ ልጠይቃችሁ...


የቅን ሰውን ልብ ለማየት ምን ያህል ጊዜ ይወስዳል?... የዋህ ልብን ለመረዳት ስንት ዓመት ይበቃል?... ርህራሔን፣ ፍቅርን፣ ትህትናን ለመገንዘብ ስንት ወር ያስጠብቃል?... ስንት ሳምንት? ስንት ቀን? ስንት ደቂቃ?...


አንዳንዴ - ቅጽበት የብዙ አስርት ዓመታትን እውነት ይገልፃል... ሌላ ጊዜ - ቀጭን አፍታ በከረመ ዕውቀት የማይገባ ሃቂቃን ያሰርፃል... ድንገት ልቦች ይገቡሃል፣ ድንገት ስሜት ይሸትሃል፣ ድንገት መንፈስ ይጋባሃል...
 

በዚያ ጨረፍታ እናትነት፣ በዚያች ቅጽበት ርህራሔ፣ በዚያች አፍታ የስብዕና ጥልቀት ይታይሃል...

___


ኮይሻ የቆየሁት ጥቂት ቀን ነው ብያችሁ ነበር - አዎን አራት ቀን ብቻ... እርሷ ውስጥ ያየሁት ቀለም ግን ዕድሜ ልኬን የማውቃት ያህል እንዲሰማኝ አድርጓል...


ካፌ ተቀምጠህ ቤትህ እንዳለህ ተሰምቶሃል?... ምግብ ጣት አስቆርጥሞ የእናት እጅ አስታውሶሃል?... የመስተንግዶ ልዩነት ክብር እንዲሰማህ አድርጓል?... እንግዲያው አንዳች ልዩ ነገር በዚያ ነበር ማለት ነው... ምናልባት አንዲት ምርጥ ነፍስ እዚያ ነበረች ማለት ነው...


[በነገራችን ላይ...]


Tip የሚለው የእንግሊዝኛ ቃል የተፈጠረው በኢትዮጵያ ቡና ምክንያት ነው ይባላል... አንድ አውሮፓዊ በሃገሩ ከሚገኝ ካፌ ውስጥ ቡና አዝዞ ሲጠጣ፣ የጣዕሙ ለዛ የተለየ ስሜት ይፈጥርበታል፤ ከዚያ በፊት ተመሳሳይ ቡና ጠጥቶ አያውቅም ነበርና ስሜቱን የሚገልጽበት መንገድ ማሰቡ አልቀረም...


እናም የቡናውን ክፍያ ሲፈጽም ከዋጋው በላይ የሆነ ሂሳብ አስቀመጠ... ወዲያው አስተናጋጇ መጥታ፣

'ጌታዬ፣ መክፈል ያለብዎ ይህን ያህል ብቻ ነው' ትለዋለች

'አውቃለሁ - ትርፉ Tip ነው' አላት፤

'አልገባኝም'

'ሁሌም ተመሳሳይ አገልግሎት እንድታቀርቡ ማበረታቻ ነው - [To Insure Promptness]' አላት... ከዚህ ጊዜ በኋላ Tip መስጠት ባሕል ሆነ... ቃሉም በአጽሮት መንገድ የቋንቋችን አካል መሆን ጀመረ...

እንግዲህ ይህ ጽሑፍ ባልተጠበቀ ሁኔታ ለተገኘ የላቀ መስተንግዶ የቀረበ የምስጋና Tip ነው...

____

(ይቀጥላል...)

Читать полностью…

Dildiy - (ድልድይ)

🗣️
.
.
.

... ከዚያ እስከዚህ ድረስ እቡይ ዘመን ተደንብቶብናል። አስማታዊ ዓለም ውስጥ፣ ተሳትፏችን እንደባህር ትል፣ ፈልቶ በቀዘቀዘ የድንጋይ ኩርፍርፍ ውስጥ፣ ፈሪ ልቡና እያስታመምን ሌላ ዘመን መጠበቅ ሆነ፡፡ ባለብዙ ደጃፍ ጉሮኖ በመፍጠር እራስን መታደጊያ የአይጥ ደመነፍስ እንኳ የለንም…



... መነሻ ትናንታችንና መድረሻ ነገአችን እንደ እትብታችን የተቀበረበት ጠፍቶን ዛሬአችን ላይ መተራመስ የማይለወጥ ዕጣፈንታችን ሆኗል፡፡



... የተበጠሰ ጣት እንደ እንሽላሊት መሸሸጊያ ሲያስስ የመመልከት ያህል ህልውና ተአምር ናት፡፡ እንደገና ሌላ ጣት... ከጣት ላይ ሌላ ጣት፣…ጣት፣ ጣት፣ ጣት… ከምንጩ የተጨለፈ ሌላ ምንጭ… ነባሩን ምንጭ ያድበሰበሰ ሐሰተኛ ምንጭ በተተኪው ሌላ ምንጭ ይረሳሳል።

.
.
.

____

ዓለማየሁ ገላጋይ

"ሐሰተኛው በእምነት ስም"

____

@bridgethoughts

Читать полностью…

Dildiy - (ድልድይ)

.
.
.

⚡️ የለቅሶ ቤት ምስር የሚጣፍጥህ ቤትህ እስኪሰራ ድረስ ነው።⚡️

___

@bridgethoughts

Читать полностью…

Dildiy - (ድልድይ)

.
.
.

ነገሩ...


በጭቃ የተሞላውን 100 ሜትር መንገድ በጥንቃቄ ስትጓዝ ቆይታ ዘጠና ስምንተኛው ላይ ስትደርስ ያዳለጣትን ሴት ታሪክ ይመስላል... 


ይህች ሴት ተነስቶ ለመሄድ አልሰነፈችም... ውጥኗን ለመጨረስም አልደከመችም...


ተመልካቹ ግን ክረምት በመጣ ቁጥር የሚያስታውሳት ጠንክራ ባለፈችው አስቸጋሪ የመንገዱ ክፍል ሳይሆን አዳልጧት ሸርተት ባለችበት የጉዞዋ መቋጫ ነው...


ይገርማል...


ወሬውን ከሚያወሩት ሰዎች ውስጥ ብዙዎቹ መውደቅን ፈርተው መንገድ መቀየራቸውን አብረው አያነሱም...


___

@bridgethoughts

Читать полностью…

Dildiy - (ድልድይ)

እየራራን
(በእውቀቱ ስዩም)

ዛሬ በስሱ እንድሰብካችሁ ፍቀዱልኝ!

ከአውሮፓ ከተሞች በአንዱ እግር ከጣለህ የሆነ ነገር ታያለህ፤ መንገድ ላይ ስትሄድ የደላቸው የጠገቡ ርግቦች ያጋጥሙሀል’፤ አጠገባቸው መድረስህን አውቀው መንገድ አይለቁልህም፤ ከመጤፍ ሳይቆጥሩህ፥ ለቀማቸውን ወይም ጨዋታቸውን ይቀጥላሉ፤ እንዳትረግጣቸው ርምጃህን ቆጥበህ ለመራመድ ትገደዳለህ፤

‘ቅዲስቲቱ ምድር’ ላይ ነህ፤ አንዲት ወፍ ከከረጢት ያመለጠ እህል እየለቀመች ነው፤ ድንገት ባቅራቢያው ዳናህን ከሰማች ብድግ ብላ ወደ እንጦጦ ብሄራዊ ፓርክ ታፈገፍጋለች፤ በወፎች ዓይን ስንታይ ጭራቆች ነን፤ ግን ያለ ምክንያት ነው?...

አንድ ባለቤት አልባ ውሻ ባጠገቡ ካለፍህ ሽምቅቅ ብሎ ገለል ይላል፤ ይመግቡኛል ብሎ ሳይሆን ይደበድቡኛል ብሎ እንደሚያስብ ግልጥ ነው ፤ በከተማችን የዕለት ዱላውን ሳይቀበል የሚውል ውሻ የለም፤ ድሮ ሰዎች የጎዳና ውሻ የሚደበድቡት “ሊጣችንን ደፋብን፣ ከቅርጫው መደብ ላይ አንድ ጎድን መነተፈብን” በሚል ሰበብ ነበር፤ አሁን አሁን ያለ ሰበብ ውሻና ድመት የሚነርት ነዋሪ ጥቂት አይደለም፤ ለመዝናናት ወይም የቆረፈደ ክንዱን ለማፍታት ውሻ የሚደበድብ አለ፤ ረሀቡን በአንቅልፍ ለማሳለፍ የተኛውን ውሻ ከመንገድ አፈንግጦ በወጣ ኮብል ድንጋይ የሚወግር አይጠፋም፤

በቀደም አንዱ ከሱቅ በር ላይ ተጎልቶ የሚቅም ጎረምሳ ባንድ ምስኪን ውሻ ላይ ድንጋይ ወረወረበት፤ ውሻው ከድንጋዩ ለማምለጥ ደመነፍሱን አስፋልት ለማቋረጥ ሲሞክር ከላይ የመጣ ታክሲ በጎማው እግሩን ዳጠው! ውሻው እያነከሰ ያለቀሰው ለቅሶ!...

ካዲስአባ እምብርት እየራቅን ስንሄድ እቃ የሚያጉዋጉዙ ጋሪዎችን እናገኛለን፤ አንድ የጠወለገ ፈረስ ትልልቅ ጎማ ያለው ጋሪ ለመጎተት የሞት የሽረቱን ሲፍጨረጨር ታያለሽ፤ በጋሪው መዓት የስሚንቶ ከረጢት ተከምሯል፤ ከስሚንቶው በተረፈው ቦታ ቡልኬት ተገጥግጦበታል፤ በዚያ ላይ ጋሪ ነጂው እንደ ፈርኦን ተኮፍሶ ፈረሱን በጅራፍ ይጠብሰዋል፤

በእንስሳት መገልገል አንድ ነገር ነው፤ በአንስሳት አለምክንያት መጨከን ሌላ ነገር ነው፤ የከተማው አስተዳደር የጋማ ፈረሶችን ያላግባብ የሚጨኑ፥ በግልጋሎታቸው ሳይሆን በስቃያቸው የሚደሰቱ ሰዎችን መቅጣት አለበት፤

ለመኖር እንስሳትን መግደል አለብን፤ ይህ የህይወት አንድ አሳዛኝ ግን አይቀሬ ገጽታ ነው፤ ከዚያ ባሻገር ለእንስሳት ርህራሄ የማሳየት ዝንባሌም አናጣም፤ የኢትዮጵያ ባህል ባንድ ገጹ ለእንስሳት መራራትን ያስተምራል፤ ድንግል ማርያም የተጠማ ውሻ እንዳጠጣች ሲነገረን አድገናል፤ ያገራችን የባላባት ወግ ስለ ዝሆን ገዳዮች ጀብድ ባድናቆት የሚተርከውን ያህል ስለ “ቆቅ ማሪ አቦየ”ም ይተርካል፤

እኒህ አቦየ የዳግማይ ምኒልክ አያት የንጉስ ሳህለስላሴ አማች ነበሩ፤ ባንድ ወቅት አንድ ባላገር ቆቅ አጥምዶ እጅመንሻ አመጣላቸው፤ ለባላገሩ የሚገባውን ከሰጡት በሁዋላ ወደ መኝታ ቤታቸው መስኮት ተራመዱ፤ ማጀት ውስጥ ገረዶቻቸው ቢላዋ እየሳሉ ነው፤ አቦየ ቆቂቱን መስኮት ላይ አስቀመጡና “ደህና ሰንብቺ” አሉዋት፤ ወደ መጣችበት በረረች፤

ያገሩ ሰው ከዚያን ጊዜ ጀምሮ አቦየን “ ቆቅ ማሪ አቦየ” ብሎ ባድናቆት ይጠራቸው ጀመር!

አለምክንያት በእንስሳት ላይ የመጨከንን ልማድ አስወግደን የመንፈስ ስልጣኔ ያለን ህዝቦች መሆናችንን እናሳይ!

--
@bridgethoughts

Читать полностью…

Dildiy - (ድልድይ)

.
.
.

Responsibility [Response + Ability]
.
.
.

ሰው ፈሪ ሲሆን መሆን የሌለበት ብዙ ነገር ሊኖር ይችላል፤ የስራ ኃላፊ አለመሆንን የሚስተካከል አስተዋይነት ግን አይኖርም...


ፈሪ ሆነህ ውሳኔ በሚፈልግ ወንበር ላይ መቀመጥ ኃላፊነት ለወሰድክበት ጉዳይ የቁም ሞት ግድ ማጣት ብቻ ሳይሆን ለከት አልባ ራስ ወዳድነትም ነው...


ስሙን ሽተህ፣ ኃላፊነቱን ግን ሸሽተህ እንዴት ይቻላል?... ክንውኑን ፈልገህ፣ መከወኑን ግን ገፍተህ እንዴት ይሆናል?...


የምልህ... 


እስከመቼ ነው ከውሳኔ ጋር ሌባና ፖሊስ የምትጫወተው?...


ወይ ውረድ! ወይ ፍረድ...


በየቀኑ ዕዳህን ለሌሎች እየገፋህ መሹለክለክ አትችልም... አንተ የሸሸኸውን ኃላፊነት ሌሎች እንዲወጡት በማድረግ ተራ ብልጣብልጥነት መዝለቅም ብልህ እያስብልም...


ምንድነው እንዲህ መንቀጥቀጥ?... ምንድነው እንዲህ መራድ?... እንዴ... ትንሽ እንኳ ደፈር በል እንጂ ጎበዝ... Risk ውሰድ... 


"The biggest risk is not taking any risk... In a world that is changing really quickly, the only strategy that is guaranteed to fail is not taking risks." ~ M. Zuckerberg

.
.
.

አንዳንድ ሲስተም ግን ይገርመኛል... ያንተ ዓይነቱን ለመሸከም ምንም አያቅማማም... ውሳኔህን የሚፈልጉ ሁሉንም ጉዳዮች ተጠያቂነት በመፍራት ስም እያሸሸህ ተድበስብሰህ ብትኖርም ምንም እርምጃ አይወስድብህም... 


*ምን ጀምረህ - ምን ፈጸምክ?...* 
*አንተ ነክተኸው ምን ከዳር ደረሰ?...* 
*ባንተ ነገር ማወሳሰብ ስንቱ ነገር ተፋረሰ?...* 
*ባንተ ጠርጣሪ ልብ ስንት ዕቅድ ፈረሰ?...*


[ማንም አይጠይቅህም... ያ - ነው ችግሩ...]


ይህ ግን ከሕሊና ወቀሳ አያስጥልህም... የጊዜ ጉዳይ ነው... ቢያንስ በሽኮኮ አያያዝህ እየሞቱ ያሉ ነገሮች በአደባባይ ያሰጡሃል... 'ስንት ነገር እጅህ ላይ ሞተ?' ይሉሃል...


ደግሞ አለመወሰንም የሚያስጠይቅ ሆኖ ይመጣል እኮ... ቀሽም ሲስተም ስለተሸከመህ ሲስተሙን የሚገፋ ዘመን አይመጣም ብለህ አታስብ...


አነሰም በዛ በዙሪያህ ውሳኔ የሚሰጡ ሰዎች አሉ... ምንም ሲሆኑ አላየንም... በጤነኛ አዕምሮ ካሰብከው አንተ ስታደርገው የሚያስጠይቅ ሌሎች ሲከውኑት የሚያስፈነድቅ የሚባል ነገር የለም... 


[አንዳንድ ሁኔታህ ሲታይ ግን፣ የሆነ ጥግ ተቀምጦ እስክትፎርሽ የሚጠብቅህ ሰው ያለ ነው የሚመስለው...]


የአንድ ነገር የልክነትና ስህተት ዳሩ የሚመዘነው በተሰጠህ ኃላፊነት ወሰን እንጂ በማን መሆንህ ሚዛን አይደለም...


ሆን ብለህ ካጠፋህ ትጠየቃለህ፣ ካለማህም እሰየው... Period!!


ወትሮስ Position የ Responsibility እና Accountability ድምር ካልሆነ ምን ሊሆን ነው?...

___


እባክህ...


ወይ ከፍርሃት ቆፈንህ ተላቀቅ - ወይ ወንበሩን ልቀቅ!!...

___


“The coward asks the question, Is it safe? The leader asks the question, Is it right?” ~ James Freeman Clarke

___

@bridgethoughts

Читать полностью…

Dildiy - (ድልድይ)

The Fallen Lineman

.
.
.

ለእርሱ...

ስሙን ከማወቃችን በፊት፣ ያኔ ድሮ - ራሱን ለመስመር ለሰጠው... ከተሞች ባንቀላፉበት ቀዝቃዛ ለሊት በምድሪቱ ለተመላለሰው... በሚንቀለቀል ነበልባል ሙቀት ከምሰሶ ጋር ለታከከው... ብናኝ ካፈነው ንፋስ ጋር ታግሎ ታወር ለደመረው... ፒንሳ፣ ሽቦ፣ ቀበቶና ስታፌ ታጥቆ ብርሃን ለሚያዋልደው...


ለእርሱ...


በጊዜ ቤት መግባት ለማይሆንለት... ልጆቹን በንቃት ማግኘት ለሚናፍቀው... እንቅልፍ ሲጥላቸው ተኝተው፣ ሲበረቱ ከበር ጠብቀው - አቧራ የጠገበ ጫማውን፣ በላብ የተላቆጠ ልብሱን፣ ድካም ያዛለው ገላውን እያዩ ለሚያዝኑለት...


[ግን ደግሞ ለማያዝኑበት...] 


ብርሃን ለናፈቀ ሕዝብ የሚደርስ አባት እንዳላቸው ስለሚያውቁ ለሚኮሩበት... ለእርሱ!!

__

[ከተማው ሲፈካ ሰዎች ይደሰታሉ... ጨለማው ሲገፈፍ እልፎች ይረካሉ...]

የመጨረሻዋን ምሰሶ በዝናብ እየተደበደበ የወጣትን ሰው ግን አያውቁትም... 

የመጨረሻዋን ገመድ በሃሩር እየደበነ የሳባትን ሰው ግን አያውቁትም... 

ለዚያች ከተማ ድምቀት አካሉን የገበረውን ሰው ግን አያውቁትም... 

ለዚያች አምፑል ብርሃን ሕልውናውን ያጣውን ሰው ግን አያውቁትም...

[ቢያውቁትም አበጀህ አይሉትም... ይልቁን ለስድብ፣ ለውርደት፣ ለነቀፋ የሚቀላቸው ሰው ነው...]

__

ሕዝቤ መብራት ሲጠፋ ጠብቆ 'ዓይናችሁ ይጥፋ!' ለማለት ብርቱ ነው...

ግና...

ለጥቂት የሳቱት የታወር ብረት፣ ዝናብ አርሶት ያዳለጠ መሬት፣ የተወረወረ የሽቦ ብጥሳት፣ የተለኮሰ የመስመር እሳት - የስንቱን ሕይወት ቀጥፎ ብርሃኑ እንደተገኘ አያውቅም...


ወፍ ሳይጮህ፣ ፀሐይ ሳትወጣ ከቤቱ የወጣ - ግና በበሮቹ መሃል መመለስ ያልቻለ ባሏን አስባ ሚስት እንዴት እንደምታነባ አያውቅም... 


የአባት ኮቴ፣ የጎብኚ ድምጽ፣ የዘመድ ሰላምታ ሲርቅ - ልጆች እንዴት እንደሚሆኑ አይገምትም...


[ሕዝብ አንድ ነገር ብቻ ያውቃል... ከሆዳቸው በላይ ሕልም የሌላቸውን ከንቱዎች፣ ከድሆች አፍ መንጠቅ የማይቆረቁራቸውን ነጣቂዎች፣ ለማገልገል የተሰጣቸውን ዕድል የሚገለገሉበት ነውረኞች...]

_

ይህን የወደቀ ሰውን ጓዳ ግን አያውቁም...

__

[እርግጥ ነው -ይህ ሰው በስጋ አልፏል...] 

እያንዳንዲቷ ደማቅ አምፑል ግን ደማቅ ትግሉን ትናገራለች...


[እርግጥ ነው - አንደበቱ በሞት ክንድ ተሸብቧል...] 

እያንዳንዷ መስመር ግን የሕይወት መስዋዕትነቱን ትመሰክራለች... 


[እርግጥ ነው -ስምና ታሪኩ ተዘንግቷል...] 

በእያንዳንዱ ታወር የምትፈሰው ኢነርጂ ግን ቦይ የቀደደላትን እጅ ታስታውሳለች... 

__

እርሱ የመስመር ሰራተኛ ብቻ አልነበረም... 

የማይታይ የሃገር ዋልታ፣ የሰርክ ድምቀቷ ባለውለታ እንጂ...

እርሱ ቴክኒሺያን ብቻ አልነበረም...

የምድሪቱን ጭለማ በብርሃን ስለት የሚገልጥ መምህር፣ አጥንትና ወዙን ለሃገሩ የሰጠ ወታደርም እንጂ... 

__

ዛሬ ይህን ብርቱ ሰው አሰብኩ!!... 


[በእርሱም ውስጥ...] 


እያንዳንዱን ምሰሶ ያለፍርሃት የሚወጣ፣ እያንዳንዱን ታወር በልበ ሙሉነት የሚረግጥ፣ ከእያንዳንዱ ሽቦ ብርሃን የሚያፈስ ቋሚውን የመስመር ሰው አወደስኩ...


___


ክብር ለወደቀው የመስመር ሰው!!...


የወጣባቸው ምሰሶዎች ዛሬም እንደቆሙ ነው... 

የጠገናቸው መስመሮች የብርሃን ጅረት እያፈሰሱ ነው...

በእጁ የዳሰሳቸው አምፑሎች መደብርና መንደሩን እያደመቁ ነው... 

እርሱ በአካል ባይኖርም የስራው ፍሬ በዙሪያችን እንደከበበን ይኖራል...

_

ይህ ሰው ዝነኛ አልነበረም - አይታወስም... 

ሀብታም አልነበረም - በስሙ ሐውልት የለም...

ሆኖም...

[ሃገሩ በግብሩ ቀና እንድትል የሚያደርግ ያልተዘመረለት ጀግና ነው...]

___

ይህ ድምጽ ለእርሱ ለወደቀው ለመስመር ሰው የቀረበ አኮቴት ነው...

___

[ጓዴ ነፍስህ በሰላም ትረፍ]

___

@bridgethoughts

Читать полностью…

Dildiy - (ድልድይ)

.
.
.

ሳንወሻሽ 😄

አንዳንድ ጉዳዮች ላይ ምን ያህል 'ሰነፍ' ናችሁ?...

___

@bridgethoughts

Читать полностью…

Dildiy - (ድልድይ)

.
.
.

"Let him who is without sin among you be the first to throw a stone at her." ~ Jesus

__

ፍርድ እውቀት አይጠይቅም... ማንም ሰው ላይ መፍረድ ቀላል ነው... የሞራል ጥያቄ ግን አለው... 'አንተ ማን ሆነህ ነው ሌላው ላይ ጣት የምትቀስረው?' የሚያስብል...


የ blame shift ጨዋታ በጣም ያስተዛዝባል... 'ከደሙ ንጹህ ነኝ' ክህደት በጣም ያሳቅቃል... 'የወደቀ እንጨት' ላይ ምሳር መጠቅጠቅ የባለ እጁን ቁሸት አይከልልም... 'እነ እከሌ' የማለት ድፍረት የእኔታን በደል አይፍቅም...


ሁላችንም ቤት ጉዶች አሉ... ወይ እስኪመቸን የምንጠብቅ 'አድፋጮች'፣ አልያም ነጥቀን የምንሰጋ 'ድንጉጦች' ነን... ይህን መካድ አይቻልም...


አዎን...


እስክንያዝ እንጂ ሁላችንም የሰረቅነው አለን... ስላልተመቸን እንጂ ልንዘርፍ የምናደባለት አለን... ይህ የሚዋሽ አይደለም...


በነገራችን ላይ ሌሎች ላይ የምንቀስራት ጣት ስሟ 'ሌባ ጣት' ይባላል...

___

ሃበሻ ጥሩ ብሂል አለችው... 


"ስራው ያውጣው" የምትል... 


በምሳሌዋ ውስጥ... በግል - ከፍርድ የመቆጠብ ትህትና፣ ለሌሎች - ከተግባር የሚወለድ አርነት፣ ለሁሉም - በጥፋት ልክ የመዳኘት ፍትሕ ተዛንቆ ይታያል...


አዎን... ሁሉም ስራው ያውጣው!!

__

እጆቹን በማንፃት ላይ የተጠመደ ድንጋይ ይወረውር ዘንድ አይቻለውም...

___

@bridgethoughts

Читать полностью…

Dildiy - (ድልድይ)

.
.
.

"ምንአገባኝ?" ብሎ መተው እኮ ይቻላል... 

"ማንን ነው የሚያገባው ታዲያ?" ቢሉን መልስ የለንም እንጂ...

__

የገጠመን ፈተና ይህ ነው... ብዙ ሰዎች ብዙ ነገር አያገባቸውም... 

ለዚህ ነው - ሃገር የጥቂት ትጉሃን መዋጮ ውጤት ነች ለማለት የምደፍረው... ብዙሃኑ ነገር ዓለሙን እኒሁ ጥቂቶች ላይ ጥሎ 'ጥቅሙን' ብቻ የሚያሳድድ ነው...

__

በተገኘህበት ቦታ - 'መገኘትህን' የሚናገር አንዳች ቁምነገር ካልተውክ መኖርህ ከቁጥርነት አልዘለለም ነበር ማለት ነው...

__

@bridgethoughts

Читать полностью…

Dildiy - (ድልድይ)

.
.
.

ሁሉንም አታወራም አይደል?... ሁሉን ከሁሉ ጋር አትካፈልም... 


አንዳንዴ... 


በግል ጉባኤህ፣ በልብ ሽሽግህ፣ በነፍስያህ ለዛ፣ ካዘመመ ጎጆህ ታዛ - ብቻህን ቆዝመህ የምታንሾካሹከው ጉዳይ ይኖርሃል...


ደግሞስ ሰው ሁሉ በየቤቱ በራሱ ድካም እየደቀቀ፣ በግሉ ሃሳብ እያለቀ፣ በዕጣፈንታው ህመም ታስሮ፣ በራስ ፈተና ተቸንክሮ - ጉስቁልቁል እያለ ምን ብለህ የኔን ብቻ ስማ ትለዋለህ?...


ከመከራህ መከራዬ ይልቃል ነው?... 

ከስቀትህ ሰቀቀኔ ይብሳል ነው?...


[በደንብ ካሰብከው - የሌሎችን ሕማም ለመታመም አይደለም - የራሱን ቁስል ከፍቶ ለማየትም ልቢቱ የሳሳችበት በየቤቱ ብዙ ነው...]

.
.
.


ይልቅ ምን አለ መሰለህ?...


ሰሚህ በችግርህ ውስጥ ጉድለቱን እያየ ከሰማህ - አደመጠህ አይባልም - ተነፈስክበት እንጂ...


ሰሚህ ስለሰማህ ድብርት ከተጫነው - አደመጠህ አይባልም - ጫንክበት እንጂ...


'ይህችማ ምን አላት? እኔ የደረሰብኝን ብታውቅ...' ብሎ ከመለሰልህ - አደመጠህ አይባልም - ቁስልህን ካደብህ እንጂ...


እና እንዳልኩህ ነው...


አንዳንድ ጊዜ... ለብቻህ የምትሸከመው መስቀል ይኖርሃል!!...

____

@bridgethoughts

Читать полностью…

Dildiy - (ድልድይ)

.
.
.

የዓለማችን 'ግዙፍ ሚዲያዎች' - የቀን ውሎ 90% ያህሉ - በጦርነት፣ በሽብር፣ በግጭትና በጉስቁልና ዜናዎች ብቻ ይሸፈናል ቢባል ድምዳሜው ግነት ተጭኖታል አያስብልም...


በጎ ነገር ባለበት በጭራሽ ዝር አይሉም - ቢሉም እንኳ ደጉን ለመዘገብ ሊሆን አይችልም... ይልቁን በሰርግህ ዕለት ተገኝተው ያንተ ደስታ ለሌሎች የሃዘን ምክንያት ሊሆን የሚችልበትን መንገድ በዘገባቸው በማንሳት ሊያስገርሙህ ይችላሉ...


ይህ በተዘዋዋሪ የሚፈጥረው ጫናና ውጥረት ቀላል አይደለም... 


ዓለሚቱ አንዳችም በጎ ነገር የሌላት መስላ ስትቀርብ ዕለታዊ መስተጋብራችን ድንዛዜ ይዋረሰዋል... ተስፋ መቁረጥና ሕይወትን አጨልሞ የማየት አባዜ ይጫነዋል...


ምዕራባውያን ሚዲያዎች ከበጎ ነገር ይልቅ 'ክፉው' ላይ ብቻ የሚረባረቡበት ምክንያት ምንም ይሁን የሚቃኙበት Editorial policy ግን አስገራሚም አሳዛኝም ነው...


ይህን እውነት ይዘን በልካቸው ስናወራ እንዲህ እንላቸዋለን...


CNN - Continuous Negative News

BBC - Brutal Biased Channel

AFP - All Fear Press

NYT - Not Your Truth

____

@bridgethoughts

Читать полностью…

Dildiy - (ድልድይ)

.
.
.

彡 Title - Three Seconds before Goodbye

彡 Artist - Sia, ft. Damian Marley

___

@bridgethoughts

Читать полностью…

Dildiy - (ድልድይ)

“My brain is only a receiver; in the Universe there is a core from which we obtain knowledge, strength, and inspiration. I have not penetrated into the secrets of this core, but I know that it exists.” ~ Nikola Tesla

___

@bridgethoughts

Читать полностью…

Dildiy - (ድልድይ)

.
.
.

ሰውነቴ ውድቅ ሲል፣ የጊዜ ቀስት ወደፊት ማለቱን ትቶ አንገቱን ሲያዘልስ ይሰማኛል... አልጋ ላይ ነኝ - የሞት አልጋዬ ላይ... አዎን - በየደቂቃው እየሞትኩ ነው... በውስጤ ሕላዌን የሚያጸና አንዳች እንጥፍጣፊ አቅም አልቀረልኝም...


🛌 እየሞትኩ ነው... 


[ከነፍሴ ማዕዘን ግን አንዳች ድምጽ ያቃጭላል...]


የስኬት ሃሳቤ ሞቷል... የማግኘት ምኞቴ ተሰናብቷል... ጆሮዬም የዓለምን ጫጫታ ሰልችቷል... የነፍሴ ቃጭል ብቻ ነው እዝነ ልቡናዬን ለመድረስ የሚቃትተው ... ስላልጨረስኩት ፍቅር፣ ስላላጣጣምኩት ነፃነት፣ ስላልተናገርኩት እውነት የሚያንሾካሹከው... 


🛌 እየሞትኩ ነው... ጅስሞቼን የሞት ሻህላ እየበረበረብኝ ነው...


ወደፊት እየሞትኩ ወደኋላ የሚጎትተኝን ሹክሹክታ እሰማለሁ... ወደፊት እየጠፋሁ ወደኋላ የሚስበኝን ድምጽ አሻትታለሁ... አዎን - ድምጹ ጸጸት የሚያኝከው የራሴው ድምጽ ነው...


'ተወኝ ልሙትበት' አልኩት... ሊሰማኝ አልፈቀደም... ብሶቱን እስከ ጥግ ተብሰከሰከ... ዝም ብዬ መስማቱን መረጥኩ...

____


🗣️ [የምሩን አልኖርኩም... ዕድሜ ከመርኩ እንጂ...] አለኝ...


አሁን ሲገባኝ በሕይወት የመዝለቅ ጽናት እንጂ በጥልቀት የመኖር ድፍረት አልነበረኝም... ትንፋሼን ይዤ ሳሳድድ የኖርኩት ምቾቴን ብቻ ነበር... የምር መኖርን አልነበረም... ዛሬ ሲገባኝ ድሎት እርባን አልነበረውም... የምሯን ሕይወት መኖር እንጂ... ምልዓቷን መዋብ እንጂ... በዚህ ረገድ ደፋር አልነበርኩም...


🗣️ [ብዙ ፍቅር አልሰጠሁም...]


ቋንቋ ፍቅርን ለመግለጽ ካልዋለ ድኩም መሳሪያ እንደሆነ አሁን ገብቶኛል... ፍቅርን ያልገለጹበት ቋንቋ ዘላለማዊነት እንደሌለው ዛሬ ታውቆኛል... ትርጉም ያለው ድምጸት - ፍቅርን የነገሩበት ነው... እኔ ግን ዝም የማለትን ምቾት ሳሳድድ ነበር... ዝምታዬ በነፍሴ ላይ ቅጥርን ከመገንባት ውጪ ምንም አላተረፈልኝም... ብዙ ጊዜዬ በቁጣ ነው የባከነው... ሆኖም ቁጣ ለአጭር ጉዞ የማይመከር ከባድ ጭነት ነበር... ጥጌ ላይ ደርሼ ሳስበው ቀለል ብዬ ተጉዤ በነበር ብዬ እመኛለሁ...


🗣️ [ሕልሜን በጸጥታ አፍኜ ገድዬዋለሁ...]


ሕልሜ ከአይለኬው የሚፈለቀቅ ንዑድ ነበር... እርሱን ቸል ማለቴ ራስን አንቆ ከመግደል የተለየ አልነበረም... አዎን - ዛሬ የሚያሳምመኝ ትናንት ያላሳካሁት አይደለም - ጭራሽ ያልሞከርኩት እንጂ... ትልቁም ሃዘን ሞት አይደለም - ኖሮ አለመታየት እንጂ... ራሴን በሚገባ አልከፈትኩም ነበር... የምሩ ፊቴን አልገለጽኩትም ነበር... ይልቁን ለመመሳሰል ስል ራሴን በዓይነርግብ ውስጥ ሸሽጌያለሁ... ለአብሮ መኖር ሸንጎ ስል ልኬ ያልሆነን ጥብቆ ለብሻለሁ... መመሳሰል በሕላዌ ስትር ውስጥ እንደ ድቡሽት ነው... ከንቱ መደለያ!...


🗣️ [በኑሮ ሩጫ ውስጥ የተላለፉኝ ቅጽበቶች ብዙ ናቸው...]


ነፍሴ ነጋ ጠባ 'ምን ያህል አገኘህ?' ትለኝ ነበር... ከውሎህ ምን ቃረምክ? ከድካምህ ምን ሰበሰብክ? ከመስተጋብርህ ምን አተረፍክ? - ትለኝ ነበር... መልሱ ግልጽ ነው - ያስተዋልኩትን ብቻ... 


የስንቱ ሕፃን ፈገግታ ከትኩረቴ አምልጧል?... የስንት ማለዳዎች የፀሐይ ሙቀት ከተገንዝቦቴ ተፋቷል?... ደግሞስ - በልብ ምቴ መሃል ያለን ጸጥታ ልቤ ስንቴ ልብ ብሏል?... እልፍ፣ ብዙ፣ ወፈ ሰማይ... [ነፍሴ ዘመኗን ሙሉ የምትጠብቀው ገነት ግን እርሱን ነበር...]


🗣️ [መንፈሴ ከሚራብበት ነበር የቆየሁት...]


ፍርሃት የፈጠረው እርጋታ ሞልቶኝ ነበር... ምቾትን ከይምሰል ሰላም ጋር እያምታታሁ ነው የኖርኩት... እውነተኛ ሰላም ታማኝ ልቦችን ብቻ እንዲጎበኝ አልገባኝ ኖሯል... እውነትን ከደህንነት ለሚያስበልጡ ብቻ እንዲገለጥ አላስተዋልኩ ኖሯል... ሃቂቃ -  ብቻ ለመቆም የሚወስኑ የሚለብሷት ሞገስ መሆኗን ዘንግቼ ኖሯል...

___

ብዙ እንባ

ብዙ ቁጭት

ብዙ ህመም...








ሞት የማይሽር - ማረር!!... 

🛌 እየሞትኩ ነው...

___

'የፈሰሰ ውሃ አይታፈስም'...

እነሆ...

በጣት የሚቆጠሩ የትንፋሽ ውጣ ውረድ ቀርቶኛል... አልጋ ላይ እንደተንጋለልኩ ነው... የሞቴ አልጋ ላይ...


'ጥንቱን ነበር እንጂ - አልሞ መደቆስ
አሁን ምን ያደርጋል - ድስት ጥዶ ማልቀስ'

___

“And in the end, it’s not the years in your life that count. It’s the life in your years.” ~ Abraham Lincoln

___

@bridgethoughts

Читать полностью…
Subscribe to a channel