dbu_entertain | Unsorted

Telegram-канал dbu_entertain - DBU Daily Entertainment

-

በደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ የተዘጋጀ አዲስ የመዝናኛ ቻናል። YOUTUBE https://youtube.com/channel/UCAS829K6929J4CVsxrwsyzA 👉 All in one! Contact @at_theTime

Subscribe to a channel

DBU Daily Entertainment

ለሁሉም አንደኛ አመት ሁለተኛ ሴሚስተር ተማሪዎች

@DBU11
@dbu_entertain

Читать полностью…

DBU Daily Entertainment

DBU DAILY NEWS

በደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ከተማሪዎች ለተማሪዎች የተቋቋመ ቻናል ሲሆን ነው።

ምንጮቹን ከተለያዩ የዩኒቨርሲቲው የሃላፊነት ባለድርሻዎች በሃላፊነት ይቀበል እንጂ በነገሮች ላይ ገለልተኛ የሆነ ነፃ ቻናል ነው።

ከ4 ዓመታት በላይ አገልግሎትን እየሰጠ የመረጃን እጥረት እንዲሁም የተማሪዎችና የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብን ከመጉላላት ለመታደግ የተቻለውን ሲያደርግ ቆይቷል።

በተጠቃሚነት ከማስታወቂያ ከሚያገኘው ገቢ ባለፈ ይህን አገልግሎት በመስጠቱ ልዩ ጥቅምም አያገኝም።

ቻናሉ ትምህርታዊ መረጃ ልውውጥ በተጨማሪ ለመዝናኛ አገልግሎት እና ለቴክኖሎጂ መረጃ @dbu_entertain

ለተማሪዎች የሃሳብ መስጫ @dbu111

እንዲሁም አሁን ደግሞ ለonline market እንዲሆን @dbudailymarket ግሩፖችን አቅርቧል።

የተለያዩ ሰዎችን አድንቆት፣ልዩ ባህሪ፣ወቀሳ፣ስድብና ማበረታቻዎችን ችሎ ለዚህን ያህል አመታት ቢቆይም ሊያጋጩ ወይም የግለሰብ privacyን ሊነኩ የሚችሉ አካላትን የሚያስወግድ banBot @dbudailybanbot ተዘጋጅቶለታል።

ይህን ቻናል ከፍተው ለተማሪዎች ላቀረቡት የሃገሬ ቲቪ ጋዜጠኛ ወንድምአገኝ እና የፋና ቲቪ ጋዜጠኛ እና አትሌት የአብቃል ዛሬም ምስጋናችን ከፍ ያለ ነው።

Читать полностью…

DBU Daily Entertainment

https://vm.tiktok.com/ZM259WBCF/

Читать полностью…

DBU Daily Entertainment

🌕ጨረቃዬ

✍ናትናኤል ብርሃኑ

@DBU11
@DBU_ENTERTAIN

Читать полностью…

DBU Daily Entertainment

《 The world is nothing but your owun magnified mind..enjoy your life today don't worry about unborn tomorrow and the dead yesterday ...when a moment you accept your self you are beautiful really ...don't race your self with anyone comparison is jealous but respect all of as...just life is survey by your own mind the time now.》

((ትዙ የ osho))

@gemini_girl1

Читать полностью…

DBU Daily Entertainment

ቀጣይ አመት ላይ ፕሪንትና ኮፒ ለማድረግ አቅማቸው ለማይፈቅ ተማሪዎች እንዲሆን የተጠቀማችሁትን ሞጁል እና ሃንድአውት ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ለበጎ አድራጎት አውሉት።

@DBU11
@DBU_ENTERTAIN

Читать полностью…

DBU Daily Entertainment

ትዝታዬ ይሁን(ኦሿዊት)
★ግጥም ተመስጦን እስከ ሰባቱ ሰማያት የሚያመጥቅ የጥበብ ሰረገላ ነው♥፡፡
✔ስነ ጥበብ
✔ብቸኝነት ሌላ ሰውን የምናጣበት ሁኔታ ሲሆን፡
♥ለብቻ መሆን ግን ራሳችንን የምናገኝበት ሁኔታ ነው፡፡
✍በትዝታ ለገሠ
✔ፍልስፍና
★ለ አስተያየት እና cross
@gemini_girl19
★ቻናሉን ለመቀላቀል
/channel/gemini_girl1

Читать полностью…

DBU Daily Entertainment

ሆሄ ተስፋ የኪነጥበብ ቡድን

እንኳን ወደ ዩኒቨርስቲያችን በሰላም መጣችሁ እያለ የ2015 የመጀመሪያ የሆነውን ምሽት
ለጥበብ አፍቃርያኑ ዛሬ ዕለተ ማክሰኞ ከ 10፡30 ጀምሮ በ "PR አዳራሽ" ጥበብ ደግሶ ይጠብቃችኋል።
በጥበብ ምሽቱ ላይ
-ግጥሞች
-ወጎች
-ሙዚቃዊ ግጥሞች
-ድምፅ
-የመፅሃፍ ጥቆማ
-ተውኔት
እንዲሁም የተለያዩ አዝናኝና አስተማሪ ዝግጅቶች ስላሉ በሰዓቱ ተገኝታችሁ ጥብብን እንድታደንቁ ተጋብዛችኋል።
ዛሬ 10፡30 አይቀርም!

ሆሄ ተስፋ የኪነጥበብ ቡድን
ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ

@dbu11
@dbudailynews

Читать полностью…

DBU Daily Entertainment

* ጥንቃቄ

የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና መቃረብን ተከትሎ የተለያዩ ሀሰተኛ መረጃዎች በስፋት እየተሰራጩ በመሆኑ ተማሪዎች እንዲሁም የተማሪ ወላጆች ጥንቃቄ ልታደርጉ ይገባል።

" የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ተሸጋገረ " እየተባለ በአንዳንድ የማህበራዊ ገፆች ላይ የሚሰራጨው መረጃ ምንጩ የማይታወቅ በትምህርት ሚኒስቴር ሆነ በሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ያልተገለፀ ነው።

ተማሪዎች ከፈተና ጋር በተያያዘ ማንኛውም አዲስ መረጃ ሲኖር በትምህርት ሚኒስቴር / በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፆች እንዲሁም በህዝብ መገናኛ ብዙሃን የሚገለፅ መሆኑን በማወቅ በሀሰተኛ መረጃ ሳትረበሹ ተረጋግታችሁ ዝግጅታችሁን ልታደርጉ ይገባል።

የተማሪ ወላጆችም ትክክለኛና የተረጋገጡ መረጃዎች በትክክለኛ የመስሪያ ቤቶቹ አድራሻ እንዲሁም በህዝብ መገናኛ ብዙሃን የሚነገሩት መሆናቸውን በማስገንዘብ ልጆቻችሁ እንዳይረበሹ ልታድርጉ ይገባል።

ተማሪዎች እንዲረበሹና ዝግጅታቸው እንዲደናቀፍባቸው የሚያደርጉ ሀሰተኛ የፈጠራ ወሬዎችን የምታሰራጩ አካላት ድርጊታችሁ ፍፁም ተገቢ ያልሆነ ትውልድ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ ያለው መሆኑን በማወቅ ከድርጊታችሁ ልትታቀቡ ይገባል ፤ ተማሪዎችም ምንጩ የማይታወቅ እና የተለያዩ አካላት ተከታይ ለማፍራት እንዲሁም ሆን ብለው ተማሪ እንዲረበሽ ለማድረግ ሲሉ በማህበራዊ ሚዲያ የሚያሰራጩትን መረጃ ወደ ጓደኞቻችሁ ባለመላክ ሀሰተኛ መረጃዎችን ተከላከሉ።
@dbu11

Читать полностью…

DBU Daily Entertainment

2014 በብዙው የስኬት ዓመታችን ነበር። አንድ እርምጃ ከፍ ያልንበት አንድ እንደሆንን ያየንበት ብሩህ ዓመት። በአንፃሩ ብዙ ደስ የማይሉ ድምፆችን ሰምተናል። ከሆነብን በላይ ግን የሆነልንን ብናስብ እሱ ይበልጣል።

አዲሱም ዓመት ከመቼውም በላቀ እርምጃችን የሚጠነክርበት መልካሙን ሁሉ ምንሰማበት የሰላምና የፍቅር ዓመት እንዲሆን ምኞታችን ነው።
መልካም አዲስ ዓመት!
ሆሄ ተስፋ የኪነጥበብ ቡድን

Читать полностью…

DBU Daily Entertainment

ምስጋና እና የመረጃ ማማቃኛ
ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ
___

ሰሞኑን አሜሪካ ወደሚገኘው IOWA ዩኒቨርስቲ ከማምራቴ ጋር ተያይዞ እዚሁ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ሃሳቦች ሲንሸራሸሩ ሶስት ነገሮችን አስተዋልኩ።

የመጀመርያው በደግ ዐይናቸው የሚያዩኝና ስኬቴን የሚናፍቁ ሰዎች መብዛታቸው! የምሥራቹን ለማብሰር መጣደፋቸው! (ክብረት ይስጥልኝ ከማለት ውጪ ምን እላቸው ኖሯል?)

ሁለተኛው ማቃኛ የሚፈልጉ መረጃዎች በፍጥነት መራባታቸው። አንዳንድ ቦታ እንደተባለው ቆይታዬ ለአመታት አይደለም ለጥቂት ወራት እንጂ። IOWA ዩኒቨርስቲ ብቻ ለአስር ሳምንታት ስንቆይ ሶስት አራት ሳምንቱን ደግሞ ይህን በመሰለ በሌሎች ፕሮግራሞች እንጠመዳለን። እርግጥ ለዚህ ፕሮግራም ተመራጭ ሆኖ መገኘት ይህን ለመሰለ ሌላ ዕድል በር የሚያስከፍት መሆኑን የቀደመ ተመክሯቸውን አንስተው ነግረውናል።

ሶስተኛው ደግሞ " አንተ ከሄድክ ዘወትር ቅዳሜ ከአስር እሰከ አስራሁለት ሰአት ከተለያዩ ደራስያን ጋር የምናደርገው (ዛጎል የመጻሕፍት ባንክና ዋልያ መጻሕፍት አንድ ላይ የሚያሰናዱት) ቆይታስ? ዛጎል የመጻሕፍት ባንክ መጻሕፍት እየሰበሰበ መልሶ በገጠር ከተማው የሚያሰራጨው ነገርስ? በእጥልጥል ሊቀር?" የሚሉ ጥያቄዎች እየተነሱልኝ ነው። ከደራስያን ጋር የሚደረገው ውይይት እኔን ተክቶ ሌላ ሰው እንዲያወያየው ተወጥኖ የነበረ ቢሆንም ይህም በልዩ ልዩ ምክንያቶች ሳይሆንልን ቢቀርም: ፕሮግራሙ ግን በተለመደው ሰአት በልዩ ልዩ ኪናዊ ስራዎች ዝግጅቱን ያቆዩታል። ውይይቶች ዲስኩሮችና የመጻሕፍት ምርቃቶች ይካሄዱበታል። የመጻሕፍት ባንካችን አገልግሎትም አይቋረጥም። (እስካሁን ከሰላሳ አራት ሺህ በላይ መጻሕፍት በገጠር ከተማው እንዲዳረስ ምክንያት በመሆናችን እና ከዋልያ መጻሕፍት ጋር ሆነንም
ከሰባ በላይ የሆኑ መጻሕፍት ላይ ትኩረት ማድረጋችን ደስታ ቢሰማንም ካደረግነው ይልቅ ልናደርግ ያሰብነው እንደሚልቅ ደግሞ ደጋግመን ልንነግራችሁ እንወዳለን)

በመጨረሻም አሸናፊ ስለሆንኩበት ፕሮግራም በአጭሩ! (ወደፊት ዘለግ አድርገን እስክናወጋ)

IOWA ዩኒቨርስቲ በየአመቱ ከየአለማቱ ደራስያንን መርጦ ፕሮግራም የማሰናዳት ልማድ አለው። ጉምቱ ጉምቱ የብዕር ሰዎችም የኖቤል ሽልማት ወሳጆችም የዕድሉ ተቋዳሽ ሆነዋል። እንዲህ ያለው አጋጣሚ ኢትዮጵያ ሊያልፋት አይገባም በማለት ሲብሰከሰክ የምናውቀው ጌዲዮን ማሞ እንዳጫወተኝ ኤምባሲው በየአመቱ ያለመታከት አወዳድሩልኝ ብሎ ምርጦቹን ቢልክም እንደዘንድሮ ግን በለስ ቀንቶት አያውቅም።

የሆነው ሆኖ ዘንድሮ ውድድሩ የተከናወነው በሚከተለው መንገድ ነው። መጀመርያ እያንዳንዱ አገር ለዚህ ዕድል ብቁ ናቸው የሚላቸውን ደራስያን ስም ዝርዝር ላከ። ለምሳሌ ኢትዮጵያ የሚገኘው ኤምባሲ ሶስት ደራስያንን መርጦ ስለሚጽፉበት ርዕሰጉዳይ ገልጾ "አርአያ ናቸው: ኢትዮጵያን ይወክሉልኛል: ቢያሸንፉ እነሱም እናንተም ደስታና ኩራት ውስጥ ትገባላችሁ!" ብሎ ዝርዝር መረጃ ላከላቸው። እነሱ ደግሞ ስለደራስያኑ የተባለውን በራሳቸው መንገድ አጠኑ። ከዚያም ከሶስቱ አንዱን ብቻ ለይተው ዕጩ አደረጉ። እንደገና እሱንና የሌሎች አገራት ዕጩዎቹን ደግሞ አወዳደሩ። መቶ አስራአምስት ገደማ(?) ደረሱ። የሚፈልጉትና እርስ በርስ ልምድ እንዲለዋወጡ የሚፈልጓቸው የደራስያን ቁጥር ደግሞ ከሰላሳ እስከ ሰላሳአምስት ባለው ቁጥር ቢወሰኑ እንጂ እንዲበዙባቸው አይፈልጉም።
ስለዚህ የአሸናፊዎች አሸናፊን ለይቶ ለማውጣት ቃለመጠይቅ አደረጓቸው። መረጃዎቻቸውን አሰባሰቡ። ስለሚያተኩሩባቸው ርዕሰ ጉዳዮች መረመሩ።

በመጨረሻም አሸናፊ ሆኖ ሲገኝ ለኤምባሲውም ለደራሲውም የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ።

እንኳን ደስ አለን

Читать полностью…

DBU Daily Entertainment

ዛሬ ሐምሌ 22 የአቡነ ጴጥሮስ የሰማዕትነት መታሰቢያ ቀን ነው።

ቅምሻ ታሪክ ነጋሪ
3.4 mb
ድምጽና ቅንብር ናትናኤል ብርሃኑ

@dbu11
@dbu_entertain

Читать полностью…

DBU Daily Entertainment

ለተመራቂ ተማሪዎች

ብዙ ተማሪዎች መፅሔትና ባይንደር ለማሰራት ቢያስቡም ፈቃደኛ ያልሆኑ ተማሪዎች ባይንደር ብቻውን እንዲሰራ በጠየቁት መሰረት "የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት" ስም
1000025325347 ብር 250 በማስገባት ደረሰኝ እስከ ቅዳሜ ድረስ ለጂሲ ኮሚቴ እንድታደርሱ የተማሪዎች ህብረት ፅ/ቤት ገልፁአል።

@DBU11
@DBU_ENTERTAIN

Читать полностью…

DBU Daily Entertainment

ዛፍ ጥላ ነው ልጄ ...ዛፍ ዙፋን ነው ልጄ...
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
ዘመንህ ዘመኔ
አፍ ብቻ ቢሆንም
ብታምንም ባታምንም
አንድ ታሪክ ላውራህ ፣ ጆሮ ስጠኝ ልጄ
እንዲህ እንደዛሬው ፣ ኦና ሳይሆን ደጄ
እኔው የተከልኩት
በለጋነት እድሜው የተንከባከብኩት
አድጎ ልክ እንደ አድባር ፣ ሲታይ የነበረ
ቅርንጫፉ ሰፍቶ ፣ ግንዱ የወፈረ
እዚህ እበሬ ላይ ፣ አንድ ዛፍ ነበረ።
።።።
እናምልህ ልጄ
እንዲህ እንደዛሬው ፣ ቆሌያችን ሳይርቀን
ወበቅ ሳይወብቀን ፣ ድርቅ ሳያደርቀን
ንፁ አየር ፍለጋ ፣
ዛፍ ያለበት ሳንሔድ ፣ ቤታችንን ለቀን
እዚህ እበሬ ላይ
አንድ ችግኝ ነበር ፣ አድጎ የሆነ አድባር
ይህንን ዛፍ አይተው
እዚ ነው መሸፈት
ይል ነበረ ቋምጦ ፣ ምድረ ነፃ ግንባር።
።።
እንዲህ እንደዛሬ
የወፎች ዝማሬ
በሰው ልጆች ጩኸት ፣ ሳይጠፋ ተውጦ
ሁሉም ላዚም ሳይል ፣ ማይኩን ጨብጦ
ምስኪን ጆሯችንን ፣
የነጠላ ዜማ ፣ዋይታ ሳይጠልዘው
እኔና እናትህ
ከዛፍ የተቀዳ
የወፍ ዜማ ነበር ፣ ምንገባበዘው።
።።
እንዲህ እንደዛሬው
ዩንበርስቲ በዝቶ
ትምህርት ተስፋፍቶ
ምሁር ነኝ ባይ ሁላ ፣ እውቀት የቸገረው
ከመሆኑ በፊት
እዚህ ዛፍ ስር ነበር ፣ ፊደል ሚቆጠረው።

።።
እናምልህ ልጄ

እንዲህ እንደዛሬው ፣ ፅድቃችን ሳይርቀን
ወበቅ ሳይወብቀን ፣ ድርቅ ሳያደርቀን
ንፁ አየር ፍለጋ
ዛፍ ያለበት ሳንሔድ ፣ ቤታችንን ለቀን
አንድ ዛፍ ነበረ
ቅርንጫፉ ሰፍቶ ፣ ግንዱ የወፈረ
ቅጠሉ የበዛ ፣ ጥላ የሚሰጠኝ
እንጃ ብቻ አንድ ቀን ፣ ምን እንዳቀበጠኝ
ዛፉ የሚጥለው
ጭራሮና ፍሬ ፣ ጣሪያዬ ላይ ወድቆ ፣እያስደነገጠኝ
አላስተኛ ብሎ ፣ ስለበጠበጠኝ
ቅርንጫፉን ልቆርጥ ፣
ግንዱን መውጣት ጀመርኩ ፣ አንድ ቀን በምሬት
ቅርንጫፍ ላይ ሳልደር
ድንገት ዛፉ አዳልጦኝ ፣ ወደኩ ወደመሬት።
።።።
መቼም ሰው ነኝና
ስድስቴ ወድቄ
ሰባቴ መነሳት ፣ እንደ ትል አልታደልኩ
ዛፉ አንዴ ጣለኝ ፣ ሰባቴ ተሰበርኩ
ተሰብሬ አልቀረሁ
መታከሚያ ባጣ
ዛፉን አስቆርጬ ፣ ሽጬው በሱ ታከምኩ።
።።።
እናምልህ ልጄ
ዛፉን የገዛኝ ሰው ፣ ጣውላ ቤት ነበረው
ካላጣው ቁሳቁስ ፣ ሞያ ሳይቸግረው
ባለ ጊዜ ሁሉ
እንዲቀመጥበት ፣ በ"ተራበ"ተራ
እኔ በሸጥኩት ዛፍ ፣ ግዙፍ ዙፋን ሰራ።
የሰራውን ዙፋን
ቤተ መንግስት ወስዶ ፣ በስልጣን ለወጠው
ፀሐይ መንግስት ሁሉ
እዛ ዙፋን ላይ ነው ፣
ህዝቡን ለማቃጠል ፣ ታግሎ ሚቀመጠው።
።።።
እናምልህ ልጄ
ችግኝ ተክዬ ፣ ግዙፍ ዛፍ አሳደኩ
ከዛፍ ላይ ወድቄ ፣ ዛፌን ሽጬ ታከምኩ
እኔ ግን ጥላ አጣሁ ፣ ኦና ሆነ ደጄ
ለመዳን ዛፍ ስሸጥ ፣ ህመም ገዛው በጄ
ከግዜር ፀሐይና
ከፀሐይ መንግስታት ፣ ልጠለል የት ሔጄ?
ከሁለቱም ፀሐይ
ለመዳን ዛፍ ትከል ፣ ዛፍ ጥላ ነው ልጄ።
ዛፍ ትንፋሽ ነው ልጄ
ዛፍ ዜማ ነው ልጄ
ዛፍ ህይወት ነው ልጄ
ዛፍ ዙፋን ነው ልጄ
።።።።

Читать полностью…

DBU Daily Entertainment

😂😂ይህን መውጫ ከፃፈው በላይ እሺ ብሎ የፈረመው ሰው ያስቀኛል።
ሱሪ
ሹራብ
ብርድልብስ
ጫማ
አንሶላ
ልብስ😂
ቀበቶ😂
ካልሲ😂
ቦርሳ😂
በሶ😂
ስኳር😂
😂ወዘተ😂

እና ውድ ተማሪያችን ልምድህን ስላካፈልከን እናመሰግናለ። ለካ "ወዘተ"😁ም ይወጣል።

@DBU_ENTERTAIN
@DBU11

Читать полностью…

DBU Daily Entertainment

---ይገበያዩ----

ሻጭና ገዢ በአንድ እንዲሆኑ ወደድን...
ወደ DBU DAILY ONLINE MARKET በመቀላቀል ማንኛውም አይነት ግብይቶችን እርስ በእርስ እንድትገበያዩ ግብዣችን ነው።

መሸጥ፣መግዛት፣ማስተዋወቅ
በቀጣይ በሚዘጋጀው የቦት ሲስተም ደግሞ ግንኙነቶችን ቀለል ለማድረግ እንሞክራለን

ለመቀላቀል ይህን ይጫኑ

@dbudailymarket

Читать полностью…

DBU Daily Entertainment

የሳይበር ወንጀለኞች Google አካውንትን ያለምንም የይለፍ ቃል መቆጣጠር የሚያስችላቸውን አዲስ መንገድ ማግኘታቸው ተገለፀ።

የሳይበር ደህንነት ኩባንያ CloudSEK እንዳለው ያልተፈቀደ የሰዎችን የግል መረጃ ለማግኘት የሶስተኛ ወገን ኩኪዎችን የሚጠቀም አዲስ የማልዌር አይነት በጠለፋ ቡድኖች ተሞክሮ ወደ ተግባር መግባታቸውን ገልጿል።

ኤክስፕሎይቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘው በጥቅምት 2023 ሲሆን ጠላፊው ስለ ጉዳዩ በቴሌግራም ቻናል ላይ በለጠፈ ጊዜ ነው።

Google ኩባንያ በበኩሉ በአሁኑ ጊዜ Chrome browser ላይ የሶስተኛ ወገን ኩኪዎችን ለማጥፋት በሂደት ላይ ነኝ ብሏል።
"ከእንደዚህ አይነት ቴክኒኮችን ለመለየትና የማልዌር ሰለባ የሆኑትን ተጠቃሚዎችን ለመጠበቅ በመደበኛነት የማሻሻያ ስራዎችን እንሰራለን። ብዙ እርምጃዎችንም ወስዷል። ተጠቃሚዎች ማንኛውንም ማልዌር ከኮምፒውተራቸው ላይ ለማስወገድ በንቃት መከታተልና እርምጃዎችን በቀጣይነት መውሰድ አለባቸው።
Chrome ላይ phishing እና የmalware downloadን ለመከላከል Safe Browsing በማብራት መጠቀም እንዳለባቸው እንመክራለን።" ሲል ገልጿል።


Safe Browsing እንዴት ማብራት እንችላለን
ይቀጥላል...

@DBU_ENTERTAIN
@DBU11

Читать полностью…

DBU Daily Entertainment

https://vm.tiktok.com/ZM2ARH5wt/

Читать полностью…

DBU Daily Entertainment

https://youtu.be/jZvnQioU6r0

Читать полностью…

DBU Daily Entertainment

《 The world is nothing but your owun magnified mind..enjoy your life today don't worry about unborn tomorrow and the dead yesterday ...when a moment you accept your self you are beautiful really ...don't race your self with anyone comparison is jealous but respect all of as...just life is survey by your own mind the time now.》

((ትዙ የ osho))

@gemini_girl1

Читать полностью…

DBU Daily Entertainment

Watch "የሰላሜ ሰው ያልኩት። ከእጄ የበላው ነው" on YouTube
https://youtube.com/shorts/CqULxvB-fcI?feature=share

Читать полностью…

DBU Daily Entertainment

አስቸኳይ ማስታወቂያ

ለሁሉም የትምህርት ክፍል የክፍል ተወካዮች(
#Representatives) በሙሉ
ዛሬ ማለትም ማክሰኞ በ13/3/15 ዓ.ም ለአስቸኳይ ውይይት ስለምንፈልጋችሁ
#ምሽት_1:30 ላይ በተማሪዎች ካፌ ውስጥ እንድትገኙ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡

#ማሳሰቢያ በዚህ ውይይት ላይ አለመገኘት በፍፁም አይቻልም፡፡

"የተማሪዎች ህብረት"

Читать полностью…

DBU Daily Entertainment

ልዩ ተሰጥዖ ላላቸው የግቢያችን ተማሪዎች DBU DAILY NEWS ሁሌም አብሯቸው ነው አሁን ደግሞ @DBU_ENTERTAIN የመዝናኛና የመማማሪያ ቻናልን በመቀላቀል አጋር ሊሆኑም ይችላሉ።

ይህ የቢኒያም ጸጋዬ ገጽ 👇👇👇
የተመረጡ የተለያዩ አስተማሪ የሆኑ ግጥሞች በድምፅ በፁሑፍ እንዲሁም በ pdf ወደናንተ በጉርፖችን ይቀርባል።ለማንኛውም ጥያቄና አስተያዬት @Yop21
/channel/YOPPPP

👆👆👆👆👆👆
Join
Join
Join



@YOPPPP
@YOPPPP
@YOPPPP

Читать полностью…

DBU Daily Entertainment

የ12ኛ ክፍል ፈተናን በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ መስጠቱ ፋይዳው ምንድነው ?

በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በዩኒቨርሲቲዎች መሰጠቱ በርካታ ጠቀሜታዎች እንደሚኖሩት  የፈተናዎች አገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ከበደ ገልፀዋል፡፡

ዶ/ር እሸቱ ከበደ ፦

- የፈተና ስርቆትና ኩረጃ  ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር በማድረግ ተማሪዎች የራሳቸውን ብቻ እንዲሰሩ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።

- ፈተናውን በማጓጓዝ ወቅት የሚያጋጥሙ ችግሮችንም ለመፍታት ትልቅ እገዛ ይኖረዋል።

- የፈተናውን ሂደት ለማበላሸት ጥረት ከሚያደርጉ ሰዎች ለመጠበቅ ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል።

- ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ መፈተናቸው ቀድመው ዩኒቨርሲቲዎቹን በአካል እንዲያውቋቸው ያደርጋል ብለዋል።

ለፈተናው ተማሪዎች ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉና ወላጆችም አስፈላጊውን ድጋፍ ለልጆቻቸው እንዲያደርጉ ዋና ዳይሬክተሩ ጠይቀዋል።

የ2014ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሁለት ዙር በዩኒቨርሲቲዎች ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ እንዳለ ይታወቃል፡፡

(ትምህርት ሚኒስቴር)

@DBU11
@DBU_ENTERTAIN

Читать полностью…

DBU Daily Entertainment

ይህ መጀመሪያ እንጂ መጨረሻ አይደለም።
(የአንዱ ፍፃሜ ለሌላው መጀመሪያ ነው)

ከሁኔታዎች ሁሉ በላይ ፍቅርን ተማምረናል። ጥበብ አሰባሰበን፣ጥበብ አኖረን።

#ከሁሉ በላይ የውስጥን መኖር ይልቃልና።በውስጣችን ድብቅ እውነት ግልፁን እውቀት ተለዋውጠናል።

በጓደኝነትም፣በወዳጅነትም አብራችሁን ለቆያችሁ ሁሉ ቀጣይ ህይወታችሁ የሰመረ እንዲሆን ምኞታችን ነው።
ሆሄ ተስፋ የኪነጥበብ ቡድን

መልካም የስራ ዘመን

@DBU11
@DBU_ENTERTAIN

Читать полностью…

DBU Daily Entertainment

መልካም የትምህርት ዘመን ይሁንልህ።

ደራሲና ኃያሲ እንዳለ ጌታ ከበደ ለከፍተኛ ትምህርት ወደ አሜሪካ ጉዞ ጀመረ ፦

ተወዳጁ ደራሲ ይህን የትምህርት እድል ያገኘው ከ 115 የዓለም ሀገራት ጸሐፍቶች ጋር ተወዳድሮ ሲሆን ፤ ከሀገራችንም ለእጩነት ከቀረቡት 3 ተፎካካሪዎቹ በብቸኝነት አሸንፎ ነው።

አፍሪካን በመወከል ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ግብፅ፣ ዚምባብዌ፣ ጋናና ቤኒን የተሳተፉ ሲሆን አንድ አንድ አሸናፊዎቻቸውን በመላክ አህጉራችን በአምስት ደራሲያን እንድትወከል አድርገዋል።

ዛሬ ማምሻውን ጉዞ የጀመረው እንዳለጌታ ቆይታውን የሚያደርገው የሥነ-ጽሑፍ ከተማ ተብላ በዩኔስኮ በተመዘገበችዋ Iowa ግዛት ሲሆን ፤ ለዓመታት እንደሚቆይና ሙሉ ወጪውንም ዩኒቨርስቲው እንደሚሸፍንለት ሰምተናል።

ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ በታሪክ እንደዚህ አይነት እድል አግኝታ የምታውቀው በ 1947 ዓ.ም. ሲሆን ፤ የወቅቱ ተመራጭ ደራሲዋ ደግሞ ዳኛቸው ወርቁ ነበር።

ምንጭ-ኢትዮፒካሊንክ
@DBU_ENTERTAIN

Читать полностью…

DBU Daily Entertainment

የፃድቅ ሞቱ ህይወትን ትዘራለች
የገፊ ሰው ህይወቱ ግን ሞትን ታበቅላለች

ሐምሌ 22 በዚህች ዕለት ሰማዕተ ጽድቅ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ሃገራቸውና ሃይማኖታቸው በአደራነት የሰጧቸውን ኃላፊነት ለመወጣት ሕዝበ በእውነትና በእምነት በማስተዳደር ላይ እንዳሉ በ1928 ዓ.ም በአረመኔው የኢጣልያ ፋሺስት በግፍ የተገደሉበትና ሰማዕትነት የተቀበሉበት ዕለት ነው።

@DBU11
@DBU_ENTERTAIN

Читать полностью…

DBU Daily Entertainment

ወሎ እና ጨዋታዎቿ
(ትንሽ ዘና ትሉ ዘንድ🤣)

የወሎ ሰው ጨዋታ አዋቂና ወግ አሳማሪ እንደሆነ ብዙ ጊዜ ሰምተናል፡፡ ለምስክር እንዲሆን ከሱፊስቶች ጋር የሚመሳሰል ጨዋታቸውን ከብዙ በጥቂቱ እነሆ፡፡ [በዚህ አጋጣሚ ይህንን ጨዋታ የነገሩኝ ወዳጆቼን አመሰግናለሁ]

የቡና ቁርስ

ወሎ ውስጥ ነን፡፡ አንድ እንግዳ ቡና እንዲጠጣ ከጎረቤቶቹ ጥሪ ይደርሰዋል፡፡ ቤታቸው ሄዶ ቁጭ እንዳለ ቡና ከመቅረቡ በፊት ምግብ እንዲቀምስ የእጅ ውኃ አመጡለት፡፡ እንግዳው በቅርብ ስለበላ ቡና ብቻ መጠጣት እንደሚፈልግ ይነግራቸዋል፡፡ ሰዎቹም ፤ እንግዳው ሊያፍር ይችላል በሚል እጁን እንዲታጠብ ገፋፉት፡፡ በቀላሉ እንደማይለቁት ሲያውቅ መብላቱን በመሀላ አስረግጦ ተናገረ፡፡ ይሄን ጊዜ ሴትዮዋ ሳቅ አሉና፤

"ተው?! ወጡን ቀምሶ ነበር ወላሂ ማለት" አሉ፡፡ እነሆ ጨዋታ . . .

[አቦል]

ደሴ ውስጥ የነበረ ምግብ ቤት አሉ፡፡ ሙስሊሙም ክርስቲያኑም በጋራ ይጠቀሙበታል፡፡ ከፈለጋችሁ ስሙን "ቄስ መሐመድ" ልትሉት ትችላላችሁ፡፡ የክርስቲያን እና የእስላም ምግቤት ይላል፡፡ አንድ ከመሀል አገር የሄደ ሰው በከተማው ሲዘዋወር ምግቤቱን ያየዋል፡፡ ከድሮ ጀምሮ ስለ ወሎ ሙስሊምና ክርስቲያን ተስማምቶ መኖር ይሰማ ነበር፡፡ እንዴት እንደሚኖሩ ለማየት ፍላጎት ስላደረበት ጎራ አለ፡፡

ፈራ ተባ እያለ ወደ ምግብ ቤቱ ገቤቶ የቤቱን አንድ ምግብ እንድያመጡለት አዞ ቁጭ አለ፡፡ ብዙ ሳይቆይ የታዘዘው ምግብ ቀረበ፡፡ ማዕዱን ሲያይ ከመደነቁ የተነሳ ከጉርሻው በፊት ሳቁ ቀደመ፡፡ የቀረበለት ሽሮ ነበር! የምግብ ቤቱ ስም ኀብረታቸውን ለማጠናከር ያደረጉት መላ እንጂ ሌላ እንዳልሆነ ገባው፡፡

[ቶና]

አንድ በመንደሩ የታወቀ ጀግና አንድ ቀን ምንሽሩን ታጥቆ ከቤት ወጣ፡፡ ሰው ሁሉ አገር አማን ብሎ በተቀመጠበት ወደ ሰማይ ካልተኮስኩ ብሎ ይገላገል ጀመር፡፡ አንድ ወዳጁ ደርሶ ምን ለማድረግ እንዳሰበ ይጠይቀዋል፡፡

"አላህን ልገለው ነው!" አለ ፈርጠም ብሎ፡፡ ሰውዬውም ቀበል አድርጎ፤

"ካገኘኸው ገላገልከን፡፡ ከሳትከው ግን አስጨረስከን" አለው፡፡



[በረካ]

ይህቺ ደግሞ ባቲ ውስጥ ያለች አነስተኛ ምግብ ቤት ነች፡፡ [ አሉ ናት ] የምግብ ዝርዝር መጻፊያ "ሜኑ" የላትም፡፡ በቤቱ የሚዘጋጀው ሁለት ዓይነት ምግብ ብቻ ስለሆነ የምግቡ ዓይነት እና ዋጋ ግድግዳው ላይ ነው የተጻፈው፡፡

1. ቀይ ወጥ

2 .ስፔሻል ቀይ ወጥ

አንድ እንግዳ ወደ ምግብ ቤቷ ገብቶ አስተናጋጁን ጠራና ምሣ ምን እንደደረሰ ይጠይቀዋል፡፡ አስተናጋጁም ወደ ግድግዳው እየጠቆመ፡፡ "ቀይ ወጥ፣ ስፔሻል ቀይ ወጥ" ይለዋል፡፡ እንግዳው ትንሽ ካሰላሰለ በኋላ ስፔሻሉ ቀርቶ ቀይ ወጥ ብቻ እንዲመጣለት አዘዘ፡፡

ምግቡ ቀርቦ መብላት ሲጀምር በቤት ውስጥ ያሉ ድመቶች፤ ሠላሳ ይሆናሉ፡፡ በሙሉ ወደ እሱ መጡ፡፡ አንዳንዶቹ የሚበላውን ለከፉበት፡፡ ከቁጥጥሩ ውጭ ሲሆን የሚበላውን ትቶ በዛውም ስፔሻል ቀይ ወጡን ለማየት ሌላ ምግብ አዘዘ፡፡

ትንሽ ቆይቶ አስተናጋጁ ያንኑ ቀይ ወጥ ከዱላ ጋር ይዞለት መጣ፡፡

[ምርቃት]

አንድ ደረሳ [ዲያቆን እንደማለት ነው] ብዙ ዓመት አብራው የኖረች ሚስቱ ትሞትበታለች፡፡ ጓደኞቹ የሐዘኑን ክብደት አይተው ሌላ እንዲያገባ አግባቡት፡፡ እርሱ ግን እንደ ሚስቴ የሚሆን አላገኝም በሚል እምቢ አለ፡፡

ከሁለት ዓመት ውትወታ በኋላ አንድ ጓደኛው አንዲት ልጅ ፈልጎ ይድረዋል፡፡ ዐዲስ ሕይወትም ይጀምራል፡፡ ለሱ ሁሉም ነገር እንግዳ ስለሆነበት በጣም ተገረመ፡፡ በተለይ አልጋ ላይ ያለው ቆይታ ከጠበቀው በላይ አስደሳች ሆኖ አገኘው፡፡

አንድ ቀን ይሄ ወዳጁ ትዳር እንዴት ነው ለማለት እሱ ዘንድ ይሄድና፤

"እህ ልጅት እንዴት ናት አንተው?" ብሎ ይጠይቀዋል፡፡

"አጃኢብ ነው ወላሂ፡፡ መቼም አላህ አያልቅበትም፤ ምነው ይቺንም በገደላት"

ቸር ሰንብቱ!

Читать полностью…

DBU Daily Entertainment

ወይኔ ደብረብርሃን😂እንዲህም ይቀለድብናል😁

@DBU11
@DBU_ENTERTAIN

Читать полностью…

DBU Daily Entertainment

በአንድ ወቅት ጋሽ ስብሃት ገ/እግዚአብሔር ቃለ መጠየቅ እየተደረገላቸው

በጣም የሚመችህ የወቅቱ ሙዚቀኛ?

"ነይልኝ እያለ የሚዘፍነው"

የማይመችህስ?

"ነይለት እያለ የሚሽቃብጠው"😂 ሙዚቃውን የሚያውቀው ይገባዋል

ከ90ቹ ገፅ

@DBU11
@DBU_ENTERTAIN

Читать полностью…
Subscribe to a channel