🔆እየጠየቁ መኖር መልስን፣ መልስን ፈልጎ ማግኘት ዕውቀትን፣ እውቀት ነፃነትን፣ ነፃነት ሙሉ ስብዕናን፣ ሙሉ ስብዕና ሠላምና እርካታን፣ እርካታ ደግሞ ደስተኛ ሆኖ መኖርን ያስገኛል፡፡ አብረን እንደግ !! @EthioHumanity @Ethiohumanity ✍የተሰማቹን አጋሩን! ቤቱ ሁሌም ክፍት ነው፣ሃሳባቹን ፃፍፍ አርጉልን @EthioHumanitybot
📍ፔሩሉስ የተባለ ቀራጺ ባለእጅ ነበር። ካላጣው መሣሪያ ሰዎችን የሚጠብስና የሚያቁላላ የመዳብ ኮርማ ተጨንቆና ተጠቦ አበጀ። አገኘሁ ብሎ ፋላሪስ ለተባለ ጨካኝ ግሪካዊ ገዥ "እንሆ በረከት" በማለት ሰጠው። ፋላሪስ ይህን የመዳብ ኮርማ ሲያይ ተገረመ፤ ለአማልክቱ እጅ መንሻ፥ መባ አደረገው። ይህ የመዳብ ኮርማ በሆዱ በኩል ይከፈታል። ሰው በውስጡ ይጠበስበታል። በስተ ጉሮሮው በኩል ደግሞ ሰውዬው እየጮኸ ሲሰቃይ ይህን ድምፅ ወደ ኮርማ ድምፅ የሚቀይር ሽቦ ተበጅቶለታል።
💡ታዲያ ፔሩሉስ ሆዬ የኮርማውን ሆድቃ እየከፈተ "ፋላሪስ ሆይ፥ ያሻህን ሰው በኮርማው ውስጥ ጠርቅምበትና በሥሩ እሳት ልቀቅበት፥ ሰውዬው የሰቆቃ ድምፅ ሲያሰማ አንተ "እምቧ" የሚል የኮርማ ድምፅ ትሰማለህ” አለው። ፋላሪስም ይህን ካደመጠ በኋላ "ቀራፂ እንኪያስ ፔሩሉስ ሆይ፥ ና፥ አንተ መጀመሪያ ግባና አሠራሩን አሳየና" በማለት ግልፅ እንዲያደርግለት ፔሩሉስን በማታለል ወደ መዳቡ ኮርማ ይገባ ዘንድ ግድ አለው። ፔሩሉስ "እኔ ምንተዳዬ፥ ለሚቃጠለው ይብላኝለት" እያለ ጕረሮውን እየጠራረገ ገባ።
♦️ፋላሪስ የፔሩሉስ መሣሪያ አሽሙር ሳይመስለውም አልቀረም። ጨካኝ ሕፃናትን እንኳን ሳይቀር የሚበላ ርህራሄ የሌለው ገዢ ነበርና። ፔሩሉስም እንደ ገባ ይሄው ጨካኝ ገዥ በሥሩ የሚንቀለቀል እሳት ለቀቀበት። በመዳቡ ኮርማ ሆድ ውስጥ ያለው ፔሩሉስ ሆዱ ተላወሰ። ላንቃው እስኪበጠስ የምሩን ጮኸ።
ፋላሪስ "የታባቱንስ ይህ ከብት፤ ጨካኝ ነህ ማለቱም አይደል" እያለ ከዚያ የመዳብ ኮርማ ሩሑ ሳይወጣ አስወጣው። ያስወጣውም አዲሱ መዳብ ከጅምሩ እንዳይጨቀይበት ብሎ ነው። ከዚያም ከገደል አፋፍ አውጥቶ ወረወረው። የፔሩሉስ ዕጣ ፈንታ ይህ ሆነ።
💡በዚህ መሣሪያ የብዙዎች ሕይወት ተቀጠፈ። ጭስስ ብሎ የታቃጠለ ዐጥንታቸውም እንደ አልቦና አንባር ያገለግል ጀመር። የሚገርመኝ ይህ አይደለም። በፋላሪስ ላይ ቴሌማኹስ የተባለ ሌላ ጨቋኝ ገዢ ተነሣበት። እርሱንም ይዞ ከመዳቡ ኮርማ ከተተው፤ አቃጠለውም።
🔑እናም አማካሪ ሆይ፥ ስትመክር ጠንቀቅ ብለህ ምከር። ገዢ ሆይ፥ በጭካኔ መንገድ መሄዱ ይቅርብህ።
✍ናምሩድ
ማለፊያ የሆነች ቅዳሜን ተመኘን❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
✍ @EthioHumanityBot
https://youtu.be/C6qboCAhUEY?si=i8VvdJ8aiDpEeK0P
Читать полностью…ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም በጤና አደረሳችሁ!
የመስቀል ደመራ በህብረት ቁሞ ደመቅ ያለ ብርሃን ይሰጣል። የበዓሉ ውበት እና ድምቀት ህብር አንድነት ነው። በዓሉን በመረዳዳት፣ በመጠያየቅ፣ በመከባበር እና በፍቅር በማክበር አብሮነታችንን እናጠንክር።
መልካም በዓል❤️
@Ethiohumanity
@Ethiohumanity
🌗ንብ እና እርግብ ተገናኝተው እየተጫወቱ ነው። እርግብም በማፅናናት መንፈስ ሆና <<እኔ የምልሽ ወይዘሪት ንብ እንዲህ ታትረሽ እየሰራሽና ማር እያመረትሽ የሰው ልጅ ግን ያንችን ማር እየሰረቀ እየበላና እየሸጠ ሲኖር ባንቺ ልፋት ሲከብር አያሳዝንሽም>> ? እርግብ ጠየቀቻት።
ንብ እንዲ ስትል መለሰች "በፍፁም አይሰማኝም፤ ምክንያቱም የሰው ልጅ ማሬን እንጂ ማር የማዘጋጀት ጥበቤን ሊሰርቀኝ አይችልም፡፡"
💡ሰዎች ብልጠታቸውን ተጠቅመው ገንዘባችንን፣ ያለንን ንብረት ሊወስዱብን ይችላሉ፤ ነገር ግን ያን ሁሉ እንድናፈራ ያስቻለንን እውቀትና ጥበብ መስረቅ አይችሉም፡፡ ስለዚህ በተወሰደብህ ነገር ላይ አትብሰልሰል። ባለህ እውቀት ላይ ትኩረትህን አድርግ።
ሕይወትህን መስዋዕት ያደረግህለት ሥራህ በተናደ ጊዜ ይህንን ፈተና ተቀብለህ ተስፋ ሳትቆርጥ የጠፋውን ሁሉ መልሰህ ለማቋቋም በደከመ መሣሪያህም ቢሆን ለመሥራት ሳታመነታ ተነሣ። የአሰራሩ ጥበብ እና ልምድ ያለው አንተ ጋር ነውና።
📍ከውድቀትህ በኋላ እንደገና መጀመርን አትፍራ፡፡ እንደገና ስትጀምር እኮ የምትጀምረው ከዜሮ ሳይሆን ከስህተትህ ትምህርትና ልምድ ካገኘህበት ደረጃ በመነሳት ነው። ከትናንትናው ዛሬ አድገሀል ፣ ተለውጠሀል፣ በስለሀል ፣ ጥበብ አግኝተሀል ፣ በርትተሀል፣ ነገሩ ገብቶሀል ማለት ነው ፡፡
🔑እናም ወዳጄ ማሰብ ላይ በርታ፤ መስራት ላይ ጠንክር፣ አምላክህን ይዘህ ፈተናህን ተጋፈጥ፣ በፀሎትህ ፅና፣ ምስጋናህን ደጋግመህ አቅርብ፣ ካንተ በላይ የሚሰራብህ፣ ተአምር የሚያደርግብህ ፈጣሪህ አብሮህ እንደሆነ አስብ። ብቻህን የሆንክ ቢመስልህ እርሱ ከጎንህ አለ፤ የተገፋህ ቢመስልህ በእርሱ እቅፍ ውስጥ ነህ፤ የወደክ ቢመስልህ እርሱ ያነሳሃል፤ በሚገባህ ስፍራም በክብር ያቆምሃል።
ውብ አሁን❤️
@Ethiohumanity
@Ethiohumanity
✍ @EthiohumanityBot
🌼እንኳን ለአዲሱ አመት በሰላም አደረሳችሁ
🌼አዲስ ሀሳብ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣
ከትላንት ስህተቶች የምንማርበት፣
አዲስ አላማ ቀርፀን የምናሳካበት፣
ጥላቻና ልዩነትን አስወግደን በአንድነትና በፍቅር ወደ ተሻለ እድገት የምንሸጋገርበት የተባረከ ዘመን ይሁንልን !
🌻ለመላው ኢትዮጵያውያን እንኳን ለ 2017 ዓ.ም አዲስ ዓመት በሠላም አደረሳችሁ፤
❤️በዓሉ የሠላም፣ የጤና፣ የደስታ እና የፍቅር አመት እንዲሆን እንመኛለን።
መልካም አዲስ ዓመት ለሁላችን
💛 ስብዕናችን 💛
@EthioHumanity
@EthioHumanity
💎በተሰጠን እድሜ በሀቅ መንገድ መሮጥ ነዉ
አንድ ቀን ስለ ዉልደትና ሞት ፍልስፍና ሲወራ በዋለበት የአንድ ወዳጃችን ጠባብ ክፍል ዉስጥ ከድር ሰተቴ የተወራውን ሁሉ ሲታዘብ ቆይና እንዲህ ብሎን ጥሎን ወጥቶ ሄደ ።
"ቢተኮስ ቢፎከር እኛ ምን አስፈራን
ሰተት ብለን ገብተን...
ሰተት ብለን ወጣን"
ሰተት ብለን በዉልደት በር እንደገባን ፣ በሞት በር ደግሞ ሰተት ብለን ዉልቅ እንላለን ። ብልጭ ብላ ድርግም እንደምትል ብርሃን ነን።... መነሻዋም ሆነ መድረሻዋ በግልጽ የማይታወቅ ብርሃን ።
📍ይህን ጥያቄ መመለስ ሳይሆን፣ ሰዉ የመሆን ቁም ነገሩ በተሰጠን እድሜ በሀቅ መንገድ መሮጥ ነዉ። በመጠላለፍ ብልጣ ብልጥነት ሳይሆን በመደጋገፍ ሰዋዊነት። የክፋት ጠቢባን ለራሳቸው በሚመች መልኩ ያበጁልንን ቦይ ትተን የነብሳችንን እንከተል። ፈጣሪ የሰው ልጅን በእድሜው ብራና ላይ የየራሱን መልካም ታሪክ ይከትብ ዘንድ በስጋና ነፍስ ፈጥሮታል፣ የልባችሁን ሀቅ በመከተል ለሚደርስባችሁ የትኛውም ግፍ ፈጣሪ ከእናንተ ጎን ለመቆሙ አትጠራጠሩ።
📓መንገደኛዉ ባለቅኔ
ከድር ሰተቴ
ውብ ምሽት❤️
@Ethiohumanity
@Ethiohumanity
✍ @EthiohumanityBot
🔊በዶ/ር ምህረት ደበበ
ምርጫችሁ ስለሆንን
ስናመሰግን ከልብ ነው !!!
ውብ ሰንበት❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
✍ @EthioHumanitybot
የበሰበሰው ጥርስ
(ካህሊል ጂብራን)
🔷በአፌ ውስጥ በስብሶ የሚያስቸግረኝ አንድ ጥርስ አለኝ በቀን ሰላማዊ ሆኖ ይውላል። ምሽቱ ሲገፋ፣ የጥርስ ሃኪሞቹ እንቅልፍ ሲጥላቸው እና መድሃኒት ቤቶቹ ሲዘጉ ግን ይጠዘጥዘኝ ይጀምራል።
አንድ እለት ትዕግስቴ ተሟጠጠና ወደ አንድ የጥርስ ሃኪም ሄጄ ያንን ስቃይ ያበዛብኝንና የምሽቴን ፀጥታ ወደ ማቃሰት እና ማጓራት በመለወጥ እንቅልፍ የነሳኝን ጥርስ እንዲነቅልልኝ ነገርኩት።
🔶 የጥርስ ሃኪሙ ራሱን ከግራ ቀኝ እየወዘወዘ "ጥርሱን ማዳን ስንችል መንቀሉ ቂልነት ነው" አለኝ። ከዚያም ጎንና ጎኖቹን በስቶ ቀዳዳዎቹን በማፅዳት ወደ ቀድሞ ሁኔታው ሊመልሰው እና ከብስባሴው ሐራ ሊያወጣው ያለውን መንገድ ሁሉ ተጠቀመ። መብሳቱን ከጨረሰ በኋላ በንፁህ ወርቅ ሞላውና "የበሰበሰው ጥርስህ አሁን ከጤነኞቹ የበለጠ ጠንካራና ብርቱ ነው" አለኝ በኩራት። አመንኩት። ከፈልኩትና ስፍራውን ለቅቄ ሄድኩ።
🔷ነገር ግን ገና ሳምንቱ ሳይገባደድ የተቀሰፈው ጥርስ ወደ ህመሙ ተመለሰና የነፍሴን ጥዑም ዜማ ወደ ለቅሶና ስቃይ ለወጠብኝ። እናም ወደ ሌላ የጥርስ ሃኪም አመራሁና "ምንም ጥያቄ ሳይጠይቀኝ ይህንን ጥርስ አውጥተህ ጣልልኝ። የደረሰበትና ያልደረሰበት ግልግልን እኩል አያውቃትም!" አልኩት።
ትዕዛዜን በማክበር ጥርሴን ነቀለልኝ። ከዚያም ጥርሴን እያየ "ይህ ጥርስ እንዲነቀል በማድረግህ መልካም አድርገሃል" አለ።
🔴 በአፍ ማህበረሰብ ውስጥ እስከ መንጋጋ አጥንት ድረስ የበሰበሱ ብዙ ጥርሶች አሉ። ይሁንና ማህበረሰቡ እነዚህን የተበላሹ ጥርሶች ለማስነቀልና ከስቃዩ ለመገላገል ምንም ጥረት አያደርግም። ራሱንም በወርቅ ፍቅፋቂ ይሞላል። አብዛኞቹ የበሰበሱትን የማህበረሰብ ጥርሶች በሚያብለጨልጭ ወርቅ እንደሚያክሙ የጥርስ ሃኪሞች ናቸው ።
እንደዚህ ተጠጋግነው በመደለል የሚኖሩ ብዙዎች ናቸው ስቃይ ህመምና ሞት ዕጣ-ፈንታቸው ናቸው።
🔶ሃገር አፍ ውስጥ ብዙ የበሰበሱ፣ ያመረቀዙ ጥርሶች አሉ። ሃኪሞቹ ከመንቀል ይልቅ በወርቅ ፍቅፋቂ አክመዋቸዋል። ህመሙ ግን እንዳለ ነው።
የበሰበሰ ጥርስ ያለው ሃገር የታመመ ጨጓራ እንደሚኖረው እርግጥ ነው። በዚህ ያለመፈጨት ችግር ውስጥ የሚገኙ ብዙ ሃገራት አሉ።
🔷ሃገር ዳቦውን በበሰበሰ ጥርሱ እንደሚያኝክ እና እያንዳንዱም ጉርሻ ከተመረዘ ምራቅ ጋር በመዋሃድ በሽታውን በሃገሩ ጨጓራ ውስጥ እንደሚያሰራጭ ስትነግሯቸው "አዎ ግን የተሻሉ የጥርስ ሙሌቶች እና ማደንዘዣዎች እየፈለግን ነው" ይሏችኋል።
ውብ አዳር❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
✍ @EthioHumanitybot
📍አብዛኛዎቻችን የነፍስ ደስታን ተነጥቀናል። ቀና ብለን አንሄድም። ምሬት መለያችን ሆኗል። ከአፋችን በረከት የለም፣ ምስጋና የለም። ወዳጄ ሆይ በመኖር ሂደት በሚገጥሙህ ፈተናዎች ሁሉ አታማር። የዛሬን ቀን ማግኘትህ ብቻ ትልቅ ስጦታ ነውና በጥልቅ ደስ ይበልህ፤ የፈጠረህን በእጅጉ አመስግን።
💡ፀሐይ ስለ መጥለቋ ከተማረርክ ፣ ከዋክብትም ይሰወሩብሃል” ይባላል። ቢወጡም አታያቸውም ማለት ነው። ምሬት ዓይንን ያጨልማልና። "ከምንማረርባቸው ነገሮች ይልቅ ልናመሰግንባቸው የሚገባን ብዙ ነገሮች አሉ። ስለተመረጥን በፈጣሪም ስለተወደድን ዛሬ ተሰቶናል፣ስለተደረገልን ነገር ሁሉ እናመስግን፤አሁን እየተደረገልን ስላለውም ነገር ሁሉ እናመስግን፤ ወደፊትም ስለሚደረግልን ነገር ሁሉ እናመስግን ምስጋና ህይወታችን ውስጥ ያለውን መልካም ነገር ያበዛልናልና።
📍እኛ ካሰብነው ይልቅ ያሰበልን ፈጣሪ ይበልጣል። ዋና ነገሬ ያለው እኔና ፈጣሪ ጋር ነው በማለት በእረፍት እንኑር፣ ሰማያዊ ጥበብ በጆሮ አይሰማም። እምነት በዓይን አይታይም። ለሆነልህ፣ ላለሆነልህ፣ ላለህ፣ ለሌለህ ዘወትር አመስግን ሁሌም ቢሆን ፈጣሪ ሁሉን በግዜው ውብ አድርጎ መስራት፣ ማከናወን ያውቅበታልና።
💡ፈጣሪህን አመስግን፣ ወላጆችህን አመስግን፣ ቤተሰብህን ባለቤትህን ልጆችህን አመስግን፣ እህቶችና ወንድሞችህን አመስግን፣ ጓደኞችህን፣ ጎረቤቶችህን፣ አለቆችህን፣ አመስግን። ሁሉም ላንተ ምንም ባይሰጡህ እንኳን አብረውህ እንዲሆኑ ስለተሰጠህ እድል አመስግን። ዛሬ በሕይወት ስላለህና ይህንንም መልዕክት በማንበብህ ዕድለኛ ነህ። ደስ ይበልህ!!
ውብ አሁን !!❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
✍ @EthioHumanityBot
🔴እስቲ ዛሬ ስለ ሱፊዮች እናውጋ ቅዳሜ የምትደምቀው በእሱ አስተምህሮቶች ነው።😉
.
. ተከተሉኝማ
.
🔷የሰረቀን ሁሉ እጅ በመቁረጥ፥ አይን ያጠፋን አይኑን በማጥፋት ልናተርፍ የምንችለው ብዙ እጀ-ቆማጣ እና ብዙ ዓይነ-ስውሮችን ነው!"- ይላሉ ሱፊዮቹ
ስለዚህም ይላሉ...
🔺"ማንም ይቅርታና ምህረትን ያላወቀ ሁሉ ፍቅርን አያውቅም፤ ፍቅርን ያላወቀ ደግሞ በፈጣሪው አልታቀፈም! ሕግጋቶቹ በሙሉ በፍቅር እንጂ በሌላ አልታቀፉምና!
🔹 ስለዚህም እኛ ተግባራትን በሙሉ የምንከውነው [ከገሀነም/ጀሃነም] ርቀን ወደ [ጀነት/ገነት] ለመግባት ሳይሆን ለሱ ካለን ፍቅር ነው! መፈ'ቀር ስለሚ'ገ'ባው ነው! የገነት ጉጉትም ሆነ የገሃነም ፍርሃት ከኛ ይራቅ!' እንደዛ ካልሆነ ግንኙነቱ የጥቅም ብቻ ይሆናል!" ይላሉ።
ይቀጥላሉም....
🔺አንዳንድ ሰዎች ጥቅሙን ብቻ ለማግኘት አስበው ፈጣሪን ያመልካሉ - ይህ የነጋዴዎች አምልኮ ነው! አንዳንዶች ደግሞ ቅጣቱን በመፍራት {ከጀሃነም/ገሀነም} ርቆ {ገነት/ ጀነት} ለመግባት ሲሉ እርሱን ያመልኩታል - ይህ የፍርሀት አምልኮ ነው!
🔹አንዳንዶቹ ግን እርሱን የሚያመሰግኑት መመስገን ስለሚገባው አልፎም የእርሱን ፍቅር እና ይቅር ባይነት በመረዳት ከልብ አመስጋኝነታቸውን ለመግለፅ ባህሪውን በተግባር ይኖሩታል - ይህ የነፃዎች አምልኮ ነው!
After all, if our actions are driven only by reward or punishment – if our seeking is for eternal life or otherwise – then we are motivated by greed and selfishness, not by faith or love.
— James Islington
ምስጋናን ጠብቀህ መልካም ሥራን የምትሠራ ከሆነ ወይም ቅጣትን ፈርተህ የምትሰጥ ከሆነ፣ ይህ ፍቅር ሳይሆን ራስ ወዳድነት ነው፡፡
📍ሰው በፍቅር ለመታቀፉስ ማሳያው ምንድን ነው?-
ሱፊዮችን እንጠይቃለን!
እነርሱም ይመልሳሉ!..
🔺ፍቅር ያለበት ሰው ዋና ባህሪው ይቅር ማለትን [ምህረት ማድረግን]ማወቁ ነው!
...ለሰው ይቅርታን ሳያደርግ ከሰማይ ይቅርታን እንደሚጠብቅ ሰው ከንቱ የለም!። ፍቅር-የፈጣሪ ዋና ባህሪና ስሙም ነው፥ እርሱም አፍቃሪዎችን እንጂ አስመሳዮችን አይወድም፥ ፍቅር የሌለው አምልኮም ጩኸት ብቻ ነው! ልብህ ከፈጣሪ ካልተገናኘ የቱንም ያህል ቃላት በፊቱ ብትደረድር ከንቱ ድካም ነው ። እንዲህ አይነቱ ሰውም ከቤቱ ውስጥ ቆሞ በሩን የሚያንኳኳ ሰውን ይመስላል ይላሉ...
📍እስቲ ይቅርታን በደንብ ግለፁልን?- ያለመታከት ሱፊዎችን እንጠይቃለን
🔹"ይቅርታ[ምህረት ማድረግ] ማለት ልክ እንደ [ፅጌረዳ] አበባው እየቀጠፍከውም እንደሚሰጥህ ጥሩ ሽታ ማለት ነው!" እኛ ሰዎች ግን ለምናደርገው ነገር ሁሉ ምላሽ ስለምንሻ ነገሮች እንዳሰብናቸው ካልሆኑ ደስታችንን ያጎድሉብናል። ሰዎች ይቅር ሳይሉን ይቅር ማለቱን አንችልበትም ፤ ብንችልበት እንኳን ገር ደካማ የሆንን ይመስለናል። ለምናደርገው ነገር ሁሉ ምላሽ እንሻለን ፤ ለፍቅራችን፤ ለይቅርታችን ፤ ለክብራችን ምላሽ ካልተሰጠን ደስተኞች አይደለንም።
የሌላውን ምላሽ ሳንጠብቅ ትክክለኛውን ነገር ማድረግ ከቻልን ከራሳችን ላይ ትልቅ ቀንበር አነሳን ማለት ነው። ፈጣሪን እናስብ ያለ-ምላሽ ይቅር እንደሚባል ፤ ያለ-ምላሽ ቸር መሆን እንደሚቻል ማስረጃ ነው።
♦️በመጨረሻም ሱፊዎች እንዲህ ይሉናል
ዘር ሲበቅል ድምፅ የለውም ግን ዛፍ ሆኖ ሲወድቅ ትልቅ ድምፅ ያሰማል ብዙ ግዜ ውድቀትም ይህው ነው ጩህት አይጠፋውም ፍጥረት ግን ምን ግዜም በዝምታ ውስጥ ነው። ይህ የዝምታ ሀይልና በዝምታ ማደግ ይባላል እናም ዝምታን የሚያሸንፍ ጬኸት ፍቅርን የሚያንበረክክ ብልጣ ብልጥነት የለም ።
ፍቅር ውብ ዝምታ ነው ፣ ፍቅርና ዝምታ መለኮታዊ ኃይሎች ናቸው። ፈጣሪን የምንፈራውም ከተከታዮቹ ብዙ ጩኸት ይልቅ በጥልቅ ዝምታው ግርማ-ሞገሱ ውስጥ ለኛ በሚሰጠው የማያቋርጥ ፍቅር ሳይሆን አይቀርም።
ፏፏቴ የሆነች ቅዳሜን ተመኘን😊
የምንፓስተውን እያነበባቹ ሪአክት ማታረጉ ሰዎች ግን፦ ወይ አስሉ ወይ አስነጥሱ ብቻ የሆነ ነገር አድርጉ... ደህንነታቹ ሀሳብ ስለሆነብን...😉
@Ethiohumanity
@Ethiohumanity
✍ @EthiohumanityBot
📍የተስፋ አለመቁረጥ ምሳሌ
የጀመርኩትን አላቋርጥም ያለችው አትሌት መነጋገሪያ ሆናለች።
ሀገሯ ቡታንን በመወከል የሮጠችው ኪንዛንግ ላሃሞ የተባለች አትሌት በሴቶች የማራቶን ውድድር የወርቅ ሜዳሊያ ካገኘችው አትሌት ሲፋን ሀሰን ከ1 ከሰዓት ከ30 ደቂቃ በኃላ በመግባት ውድድሯን አጠናቃለች።
አትሌቷ ውድድሯን ስትጨርስ በቦታው የነበረው ታዳሚ እጅግ በጋለ ሞራል ተቀብሏታል።
የመጨረሻ ደረጃ ይዛ ያጠናቀቀችው አትሌቷ በፍጹም የጀመርኩትን ውድድር አላቋርጥም ብላ የውድድሩ የወርቅ አሸናፊ ከታወቀ ከ1 ሰዓት ከ30 ደቂቃ በኃላ ገብታለች።
80ኛ ደረጃ የወጣችው አትሌቷ ውድድሯን ለመጨረስ 3 ሰዓት ከ52 ደቂቃ / 4 ሰዓት ደገማ ወስዶበታል።
በዚህ ሁሉ ፥ የቴሌቪዥን ስርጭት ያልተቋረጠ ሲሆን እያንዳንዷ እንቅስቃሴዋን ሲያሳይ ነበር ፤ በስፍራው የነበረው ተመልካችም የትም ሳይሄድ በክብርና በትልቅ ሞራል ተቀብሏታል።
የቡታኗ አትሌት የጀመረችውን ውድድር እስከመጨረሻ ድረስ ያለ ማቋረጥ ተፋልማ በመጨረሷ በበርካቶች " የተስፋ አለመቁረጥ ምሳሌ " ተደርጋ ተወስዳለች።
ሁላችንም በምንም አይነት ሁኔታ ቢሆን የጀመርነውን መጨረስ፣ ለቆምንለት ዓላማ እስከመጨረሻው መሄድ እንዳለብን ያስተማረ ነው።
" እኔ አልችልም " ብለህ ተስፋ ቆርጠህ ከመቆም መራመድን ምረጥ ፣ ከውስጥ የመነጨ ጠንካራ መንፈስ ሲኖረን ምንም ያህል ችግር ምንም ያህል ስቃይ ከላያችን ቢረበረቡ ምንም ሳያሳስበን ምንም ተስፋ ሳያስቆርጠን ወደፊት ግስጋሴያችንን እንቀጥላለን። ሩጫችንንም መሰናክሉን እያለፍን እንሮጣለን። ከግባችንም እንደርሳለን። በተንቀሳቀስን ቁጥር ግባችን ጋር መድረሳችን የማይቀር ነው።
ውብ ሰንበት❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
@EthioHumanityBot
📍በሱፊዎች ዘንድ የሚነገር አንድ ታሪክ አለ..
♦️በስቃይ የተሞላ ህይወትን የሚመራ አንድ ሰው ነበር... ሰውዬው ወደ አምላኩ በሚጸልይበት ጊዜ ሁሉ "ሁሉም ሰው ደስተኛ ሆኖ እየኖረ ለምንድነው እኔ ብቻ የምሰቃየው?" እያለ ይጠይቅ ነበር፡፡
አንድ ቀን ጥልቅ በሆነ የተስፋ መቁረጥ ስሜት ውስጥ ሆኖ ለአምላኩ እንዲህ ሲል ጠየቀ... "አምላኬ የማንኛውንም ሰው ስቃይ ብትስጠኝ ልቀበል ዝግጁ ነኝ... እባክህ የእኔን ግን ውሰድልኝ... ከዚህ በላይ ልሸከመው አልችልም" ብሎ ተማረረ፡፡
ጸሎቱን ጨርሶ እንደተኛ ታዲያ ውብ የሆነ ህልም አየ... በህልሙ ውስጥ አምላክ ሰማይ ላይ ተከስቶ እንዲህ ሲል ይደመጣል... "ስቃያችሁን ሁሉ ወደ ቤተ መቅደሱ አምጡ..."
እያንዳንዱ ሰው የየራሱ ስቃይ ያታከተው ስለነበር "የማንኛውንም ሰው ስቃይ ለመቀበል ዝግጁ ነኝ፤ የእኔን ግን ውሰድልኝ፤ ከዚህ በላይ መሸከም አልችልም" ብሎ ይጸልይ ነበር...
🔺በዚህም ምክንያት ሁሉም ሰው ስቃዩን በቦርሳ አጭቆ ወደ ቤተ መቅደሱ አመራ... ባለታሪኩን ጨምሮ ሁሉም ሰው ጸሎቱ በአምላኩ ዘንድ ተቀባይነት ስላገኘለት በስፍራው ላይ ከፍተኛ የደስታ ስሜት ነግሶ ነበር...
💡ከቤተ መቅደስ ሲደርሱ አምላክ እንዲህ ሲል እወጀ... "ቦርሳችሁን ከግድግዳው ስር አስቀምጡት"... ሁሉም ሰው ቦርሳውን አስቀምጦ ጨረሰ... አምላክም እንዲህ ሲል በድጋሚ አወጀ... "አሁን መምረጥ ትችላላችሁ፤ ማንኛውም ሰው የፈለገውን ቦርሳ መውሰድ ይችላል"...
🔺በዚህ ጊዜ ቀን ከሌሊት 'የማንኛውንም ሰው ስቃይ ለመቀበል ዝግጁ ነኝ' እያለ ሲጸልይ የነበረው ሰውዬ ሌላ ሰው የእርሱን ቦርሳ እንዳያነሳበት እየተጣደፈ ወደ ራሱ ቦርሳ ሄደ... ሁሉም ሰው እንደ ሰውዬው ሁሉ የየራሱን ስቃይ ያጨቀበትን ቦርሳ ፍለጋ ተራወጠ... በሚያስገርም ሁኔታ እያንዳንዱ ሰው የየራሱን ስቃይ በድጋሚ ለመሸከም ዝግጁ ነበር...
ምንድን ነበር የተከሰተው?...
💡በህይወታቸው ለመጀመሪያ ጊዜ አንዳቸው የሌላኛቸውን ችግር ስቃይና መከራ ተመለከቱ... እንዲያውም ከራሳቸው የሚበላልጡ፣ የሌሎች ሰዎች ስቃይ የታጨቀባቸው ትላልቅ ቦርሳዎች እንዳሉም ተገነዘቡ... በዚህ ላይ ሁሉም ሰው ከራሱ ስቃይና መከራ ጋር ተላምዷል... የራሱን ስቃይ ማባበልና መቻል አይቸግረውም... የሌላውን ሰው የመከራ ቦርሳ ቢወስድ ግን ከቦርሳው ውስጥ ያለው አዲስ አይነት መከራ ምን አይነት እንደሆነ አያውቅም... ምናልባት የባሰም ሊሆን ይችላል...
አላሚው ሰው ከእንቅልፉ ሲነቃ በድጋሚ ጸለየ... "አምላኬ ስላሳየኸኝ ህልም አመሰግንሃለሁ...ከዚህ በኋላ እንዲህ አይነቱን ጥያቄ ደግሜ አልጠይቅህም... የሰጠኸኝን ነገር ሁሉ የሰጠኸኝ በምክንያት ነው" ሲል ተናገረ...
📍የቅናት ስሜት ካለባችሁ በማያቋርጥ ስቃይ ውስጥ ትወድቃላችሁ፤ የምትቀኑ ከሆነ ሀሰተኛ ትሆናላችሁ፤ ማስመሰልም ትጀምራላችሁ፤ ያልሆናችሁትን መስላችሁ ለመታየትም ትሞክራላችሁ... የሆነ ሰው ጋር ኖሮ እናንተ ጋ የጎደለ ነገር ያለ ሲመስላችሁና ነገርዬውን ማግኘት የማትችሉ ከሆነ ከሰው ላለማነስ ብላችሁ የረከሱ ነገሮችን ማበጀት ትጀምራላችሁ...
💡ለቀናተኛ ሰው ህይወት ሲኦል ትሆንበታለች... ስለሆነም ቅናታችሁ ይጠፋ ዘንድ ራሳችሁን ከሌላው ጋር ማነጻጸር አቁሙ... ይህን ስታደርጉ ያልሆናችሁትን መስላችሁ ለመታየት የምታደርጉትን ጥረትና ሌላውን ለመምሰል የምታደርጉትን ሙከራ ታቆማላችሁ...
🔑ይህ ሁሉ ሂደት የሰመረ የሚሆነው ግን ውስጣዊውን ሀብታችሁን ማሳደግ ስትችሉ ነው... ለማደግ ጣሩ... ይበልጥ እውነተኛ ግለሰብ ለመሆን ሞክሩ... እራሳችሁን አፍቅሩ... ለራሳችሁ ክብር ስጡ... ይህ ሲሆን የገነት በሮች ክፍት ይሆኑላችኋል... በእርግጥ ወደ በሮቹ ተመልክታችሁ ስለማታውቁ ነው እንጂ እስካሁንም በሮቹ ክፍት ነበሩ...
✍ ደምስ ሰይፉ
ውብ ቅዳሜ❤️
@EthioHumanity
@BridgeThoughts
✍ @EthioHumanityBot
💎እንደ ወርቅ እንደ አልማዝ ሁኑ
ወርቅና አልማዝ ውድ ናቸው። የትም አይገኙም። ብዙ ተቆፍሮ፣ ተለፍቶ ነው የሚገኙት። የትም በቀላሉ የምትገኙ አትሁኑ። የራሳችሁን ዋጋ እንደ ወርቅ፣ እንደ አልማዝ ውድ የምታደርጉት ራሳችሁ ናችሁ። ለጠራችሁ ሁሉ አቤት፣ እንሂድ እንጂ ላላችሁ ሁሉ ወዴት አትበሉ።
💡Rarity [አለመገኘቱ] ብቻ ግን በቂ አይደለም። ወርቅና አልማዝ ጌጥ ናቸው። ያምራሉ። ወርቅ የቀይ ቢጫ ውብ መልክ አለው። አልማዝ በባህሪው colorless ከለር አልባ ነው። አልማዝ ብዙ አይነት ቀለም ይዞ የምናገኘው በውስጡ ካሉት impurities የተነሳ ነው። ግን መሰረታዊ ውበቱን አይቀንሱትም። የሰው ልጅ ውበት ንጽህና ነው። ንጹህ አካል፣ ንጹህ መንፈስ፣ ንጹህ አስተሳሰብ!!
📍አንድ ነገር በቀላሉ የማይገኝ ብቻ መሆኑ ተፈላጊ አያደርገውም። ዋናው ጉዳይ ባህሪያቶቹ ናቸው። የወርቅ በጣም ተፈላጊ ባህሪ ወርቅ አይዝግም። እንደ Iron ብረት ከሆንን ወደ ውስጣችን ሰርጎ የገባው ውሃ ሁሉ ያዝገናል። መንፈሳችንን ይረብሸዋል። ወርቅ ሁኑ። ወርቅ ሚሊየን አመት ውሃ ውስጥ ቢቀመጥ አይዝግም። በዚያ ላይ malleable ተዛዥ ተጣጣፊ ነው። እንደ ወርቅ ሊቀጥን የሚችል ሌላ ኬሚካል ኢለመንት የለም።
💡አልማዝ ደግሞ በጣም ጠንካራ ነው። ማንኛውንም ነገር በብቃት መቁረጥ ይችላል። በነገራችን ላይ አልማዝና ከሰል አንድ ናቸው ደግሞም አይደሉም። አንድነታቸው ሁለቱም የተሰሩት ካርበን ከሚባል ኢለመንት መሆኑ ሲሆን ልዩነታቸው እነዚህ የካርበን አተሞች በአልማዝና ከሰል ውስጥ ያላቸው ኬሚካል ስትራክቸር ነው። ከሰልን ወደ አልማዝ መለወጥ በብዙ ፓስካል ፕሬዠር [Pascal Pressure] ወይም ብዙ ግፊትና እና ብዙ ኬልቪን [Kelvin] ሙቀት ያስፈልጋዋል።
📍ውስጣችን ያለው ማንነት ካርበን ነው። ከሰል ወይም አልማዝ ማድረግ የኛ ፋንታ ነው። የህይወት ፈተና የከሰል ማንነታችንን ወደ አልማዝ የሚቀይር እርሾ ግፊት ነው። እነዚህ የወርቅና የአልማዝ ኬሚካላዊ ባህሪያት ብዙ ኢንደስትሪያል ጠቀሜታ አላቸው። ወደዚያ በዝርዝር አንገባም። አሁን የምንወስደው ከወርቅና ከአልማዝ ለህይወት የሚጠቅመንን ብቻ!
✍ ቴውድሮስ ሸዋንግዛው
ውብ ሰንበት❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
@EthioHumanitybot
💚ንቁ የሃሳብ ሰው ስንሆን የምንሰራው ዓለምን ነው። ለዚህ ደሞ የስብዕና ግንባታ ወሳኝ ነው ብሎ ያምናል ቻናላችን. . ታድያ ሁሉን አልፈን በአብሮነት ከእናንተ ጋር ተያይዘን አሁን ላይ ደርሰናል።
💛ከጎናችን በመሆን አጋርነታቹን እደምሰሶ ላፀናቹልን ቤተሰቦቻችን ልባዊ ምስጋናችን በያላችሁበት ይድረሳችሁ !!
❤️ዛሬም እደትናንቱ ታስፈልጉናላቹ ፣ ወድ ሀሳብ አስተያየታችሁ ለኛ ትልቅ ግብአቶቻችን ናቸው። ሁላቹሁም ሀሳብ አስተያየት እንድታደርሱን በአክብሮት እንጠይቃለን።
የሚሰማችሁን እዚች ላይ ፃፍፍ አርጉልን
👉 @EthiohumanityBot
👉 @EthiohumanityBot
✍ሁሉም የለንምና በእናንተ ሀሳብ
የጎደለውን እንሞላለን!!
ከልብ እናመሰግናለን ❤️
@EthioHumanityBot @EthioHumanityBot
💡በየትኘውም የህይወት መንገድህ መልካም ስብዕናን አየዘራህ ስትጓዝ ባታይውም ለሌሎች ፍካት ሆኖ ይቆያል ።ደግነትህ ለብዙዎች የዕድሜ ማራዘሚያ ሰበብ ስለሆነ እንዳይከስም ጠብቀው። ለጋስ በመሆንህ በምላሹ ከሌሎች ምንም ነገር አትጠብቅ። የጊዜ ጉዳይ ቢሆን እንጂ መልካም ነገር ሁሌም ከፈጣሪህ በጎ ምላሽ አለው።
📍ህሊናህ ይረካ ዘንድ ከመቀበል ይልቅ ሰጪ ሁን። በምግባርህ ፈጣሪህን ለማስደሰት ሁሌም ጥረት አድርግ። እርሱ ከወደደህ ደስታ በእጅህ ትገባለች። በመልካም ስነ ምግባር ሽቶ የተርከፈከፈ ስብዕና ከመሬት በታች አፈር ለብሶ እንኳ መዓዛው ያውዳል።
💡አስተሳስብህ ካለባበስህ የበለጠ ሲያምር መልካምነትህ ከምትቀባው ሽቶ የበለጠ ሲያውድ ስነምግባርህ ከመልክህ የበለጠ ሲያምር የዝነጣ ጣሪያ ላይ ደርሰሀል ማለት ነው። ላመነን ሰው መታመን ከህሊና ወቀሳ መዳን ነው። ማንን እንደምታገኝ አታውቅምና ለሁሉም ሰው ቅን ሁን፡፡ በህይወታችን የምናሰፍራቸው ነጥቦች ሁሉ በኋላ ላይ ተያይዘው መስመር መስራታቸው አይቀርም።
ውብ አዳር❤️
@Ethiohumanity
@EthioHumanity
@EthiohumanityBot
✨ደስታ ቢራቢሮ ሲሆን፤ ለመያዝ ብንሞክር የማይጨበጥ....ነገር ግን ፀጥ ብለን ስንቀመጥ ከአጠገባችን ብልጭ የሚል ነው።
🦋ለደስተኝነት አንድ መንገድ ነው ያለው። እሱም ከምኞታችን አቅም በላይ በሆኑ ነገሮች ላይ መጨነቅን ማቆም ነው። እጅህ ላይ ያለው ካላስደሰተህ እርግጠኛ ሁን ሊመጣ ያለውም አያረካህም። በበርሃ አበባ ሳትፈነድቅ በገነት ውበት አትመሰጥም። የፍላጎት ስሌትህን ወደ ጎን አርገውና፣ ስለ ንጋት ፀሀይዋ መሞቅ ፣ ስለ ቀኑ ብራነት፣ በነፃ ስለምትተነፍሰው ውድ አየር፣ ደክሞህ እንኳ ሰለማይደክማት ልብህ፣ በዙሪያህ ስላሉት ወገኖች፣ ይህንን ማንበብ እንኳ ስላስቻለህ አይንህ ስታስብ ...
.
.
.
በደንብ ስታጤን ... በእርግጥ ከሌለህ ይልቅ ያለህ ብዙ እንደሆነ ትረዳለህ ፡፡ ያኔ እድለኝነት ይሰማሀል፡፡ ያኔ እንዳልጎደልክ ይገባሀል .... ያኔ አመሰጋኝ ትሆናለህ....
💎 የራስህ አመለካከት ሲጠራ ደስታህና መልክህ እንደፀሓይ ያበራል። በቁስ ያልተደገፈ ደስታ ውስጥህን ይሞላዋል፡፡ ነገ ራሱ የብዙ ዛሬዎች ድምር ነውና ለደስታህ ቀጠሮ አትያዝለት ...
የደስታህ ጊዜ አሁን ነው።
https://youtu.be/C6qboCAhUEY?si=i8VvdJ8aiDpEeK0P
ውብ አሁን❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
@EthioHumanityBot
🛑‘የእኔ’ እንደምትለዋ ቃል ጣፋጭ ቃል የለችንም ፣ በየትኛውም ዕለታዊ የንግግር ብፌያችን ላይ የማትቀር ጨው ናት… ሁሉም ውስጥ አለች… ‘የኔ’ የባለቤትነት ማስረገጫም ናት ፣ ቤቱ የእኔ ነው፣ ዛፉ የእኔ ነው፣ ስራው የእኔ ነው፣ ብሩ የእኔ ነው፣ ሰፈሩ የእኔ ነው ፣ ሃገሩ የእኔ ነው፣ እውቀቱ የኔ ነው ፣ ሃሳቡ የኔ ነው…. ሺህ ምንተ ሺህውን ሁላ ጠቅልላ የእኔ /የእኛ የምታሰኝ አግላይ ነፍስያ አለች።
የኔታችን ከፋ ስትል ደግሞ ህይወት ያለውን ሰው እንደ ንብረት አድርጎ እስከማሰብ ይዘልቃል፣ የኔ ነው እሱ/እሷ እያልን እንደፈለግን የምንዘውረው የባለቤትነት ስሜት አለ።
🔷የኔ ስለምትሉት ነገር በደንብ አስቡ እስኪ ፣ በስማችሁ የተመዘገበ ሃብት፣ እናንተን የሚያስጠራ ንብረት፣ የእርሱ/ሷ የሚባል አንድ ቁስ፣ እናም ያ ነገር የእናንተ የሆነበትን በቂ ምክንያት አስቡ እስኪ፣ ያላችሁበት የስልጣን ወንበር፣ በኑረት ውስጥ የቋጠራችሁት ጥሪት ፣ በላቤ በወዜ ያገኘሁት የምትሉት ወረት ፣ ድንገት ከእጃችሁ የገባ በረከት… ብቻ አንድ የኔነት.........
♦️እውነት ለመናገር ምንም የላችሁም ፣ ኑረት የመዋጮ ውጤት ነው… እያንዳንዱ ስምረት ብዙ አለሁ ባይነትን ከጎኑ ይዟል። የሰው ልጅ ከእናቱ እቅፍ እስከ ቃሬዛ ሽክፍ ድረስ በመዋጮ ነው የሚጓዘው። ለብቻው መጥቶ፣ ለብቻው ኖሮ፣ ለብቻው የተሻገረ አንድ ስንኳ የለም፣ አለኝ የምትለውን ነገር ከመነሻው ጠገግ እስከ መድረሻው ጥግ ብታጠናው የኔ ያስባለህን አመክንዮ ባዶነት ትረዳለህ ፣ ከእኛ የሆነ አንዳች የለም ፣ በዙሪያችን ካለው ምልዓት ነው እንዳፈተተን የሸከፍነው፣ የእኛ ስለሆነ የተጨመረ ነገር አይደለም፣ ከነበረው ላይ ነው የተቀዳው።
🔷ታዲያ እኛ ዘንድ ስለምን ተጠጋ?… መንገድ ነን እኛ፣ ለሌሎች መድረሻ ቦይ ፣ እኛ ዘንድ ያለው ሌሎች ዘንድ እስኪደርስ ነው። አንባሪዎች ነን ፣ ባላደራ እንደማለት ነው። ከፍም ዝቅም ብሎ እኛን የተጠጋው ለጎደለው በእኛ በኩል እንዲደርስ ነው። እናም… ሃብታም አይደለም ያለው – ብዙ ሰጪ እንጂ፣ ድሃ አይደለም ያለው ጥቂት ሰጪ እንጂ፣ ምንም ሁን ግን የምትሰጠው አለህ ፣ ማንም ሁን የምትቀበለው አለህ፣ አንተ ለኑረት መጻተኛ ነህ ፣ አለቀ።
🔑ያፈራኸው ሃብት፣ ያካበትከው እውቀት፣ የኖርክበት ቀዬ፣ ያለፍክበት መንገድ፣ የታወቅህበት ፈለግ፣ ያቀረብከው ማዕድ፣ የተጠለልከው ታዛ፣ የተሰጠህ ማዕረግ፣ የጨበጥከው ሥልጣን ፣ የሁሉም እጅ አለበት።
💡ዲዮጋን ፈላስፋ ነው..."ምናምኒት የሌለው" ፈላስፋ፣ በዘመኑ የነበሩ ኃያላን መሪዎች ሳይቀሩ ለአማካሪነት የሚፈልጉት፣ የሚያውቁት በተገኘበት ቃሉን ለመስማት የሚሻሙበት፣ ዝናውን ከሩቅ የሰሙ ሀገር አቋርጠው ወንዝ ተሻግረው ሊያደምጡ የሚሹት ድንቅ የዘመኑ ፈላስፋ። ግን ደግሞ ምንም "የሌለው" ዓይነት… 'ንብረት' ከተባሉ ንብረቶቹ ውሻ፣ አንድ ከቀፎ የተሰራ ማደሪያና ውሃ መጠጫ ቅል ናቸው። ቅሉንም አንድ ቀን ወንዝ ሲሻገር፣ አንድ ሌላ ሰው በርከክ ብሎ በእጆቹ ውሃ እየጠለቀ ሲጠጣ ስላየው "ለካስ ቅልም ትርፍ ኖሯል?" ብሎ ጥሎታል...
📍ታላቁ እስክንድር አለምን በሙሉ እየተቆጣጠረ፡ ቆሮንጦስ ሲደርስ፡ እሱን ለማየትና ለማመስገን ሁሉም ሰው ተሰበሰበ፤ ዲዎጋን ግን አልመጣም። ታላቁ እስክንድር ለማየት የፈለገው ግን ዲዎጋንን ነበር። ንጉሱ ከኋላው በጣም ብዙ ሰው አስከትሎ እየሄደ ሳለ አቀበቱ ላይ ተንጋሎ ፀሐይ ሲሞቅ ዲዎጋንን አገኘው።
እስክንድርም ሰላምታ ካቀረበለት በኋላ እንዲህ አለው፦ ”ዲዎጋን!ስላንተ ጥበብ ብዙ ሰምቻለሁ። የማደርግልህ ነገር ይኖራል?“
”አዎ“ አለ ዲዎጋን ” ጸሀይዋን ስለጋረድከኝ ወደ ጎን ዞር በልልኝ“ አለው። ለሰማይና ለምድሩ የከበደውን ታላቁን ንጉስ በንቀት ስለተናገረ ብለው የእስክንድር ወታደሮች ሊቆራርጡት ሰይፋቸውን ሲመዙ እስክንድር ግን "ተውት አትንኩት እኔ እስክንድርን ባልሆን ኖሮ ዲዎጋንን መሆን እመርጥ ነበር" አላቸው።
🔷ሕይወት ከቁሳዊው ዓለም ጀርባ ካረገዘችው ትክክለኛው እኔነት ውስጥ ካልሆነ በቀር ከውልደት እስከ ሥጋ ሞት በተዘረጋው አፍታ ውስጥ የምታጋብሰው ንብረት አልያም ስልጣን ያንተ አይደለም። ያንተ የሆነው የማይጠፋው ነው። ከኑረት ፈለግ ላይ የሥጋ ሞት ሲነጥልህ አብሮ የማይነጠለው፣ የመንፈስ ከፍታህ፣ የነፍስ ልዕልናህ ነው፣ ይህ ሃብት ሌባ ሲዘርፈው አልታየም፣ ብልና ዝገት ሲበላው አልታየም፣ እሳትና ጎርፍ ሲያወድመው አልታየም፣ የመድኅን ዋስትናም አይፈልግም፣ እውነተኛ ሃብትህ እርሱ ብቻ ነው፣ ሌላው ሁሉ ትርፍ ነው።
♦️ምንም ነገር ይኑርህ ምንም ነው… ልክ እንደ ቅዠት፣ አሁን ላይ ቁም ፣ ምንድነው ያለህ? እጅህ ላይ ያለው ከትናንት ያደረና በየትኛውም ቅጽበት ሊጠፋ የሚችል ነው።በነግ ተስፋህ ላይ የተንጠለጠለው ስለመምጣቱ የማታውቀው ምኞት ነው… አሁን ምንድነው ያለህ?… ምንም… አንተ ብቻ ነህ ያለኸው፣ ከእጅህ ያለውን ግን የኔ ነው እንዳልከው አጥተኸዋል፣ ቋሚ አይደለምና።
መልሰህ የምትሰጠውን ከእጅህ ታቆያለህና አንተ ባለጸጋ ነህ!!
✍ደምስ ሰይፉ
ፏ ያለች ቅዳሜን ተመኘን!! 😉
@BridgeThoughts
@EthioHumanity
✍ @EthioHumanityBot
📍ተፈጥሮ በአጠቃላይ እጅግ በጣም የተወሳሰበ ሂደት ነው ፣ እናም በውስጡ ጥሩም ይሁን መጥፎ ነገር እንደያዘ ለመናገር ከባድ ነው። ምክንያቱም የመጥፎ ነገር ውጤት ምን እንደሚሆን በጭራሽ አይታውቅም ፣ ወይም ደግሞ መልካም ዕድል ምን ይዞ እንደሚመጣ በጭራሽ አይታውቅም።
🔆በአንድ ወቅት አንድ የቻይና ገበሬ ፈረሱ ሸሽቶ ተሰወረበት ፡፡ የዚያን ዕለት ምሽት ሁሉም ጎረቤቶቹ ተሰብስበው ሊያፅናኑት መጡ ፡፡ እነሱም “ፈረስህ በመጥፋቱ በጣም አዝነናል ፡፡ ይህ በጣም መጥፎ ነገር ነው አሉት ፡፡
”ገበሬውም“ ምናልባት ”አላቸው ፡፡
በሚቀጥለው ቀን ፈረሱ ሰባት የዱር ፈረሶችን ይዞ ወደ ቤቱ ተመለሰ
ምሽት ላይ ሁሉም ጎረቤቶቹ ወደ ቤቱ በመምጣት“ ዕድለኛ ነህ በጣም ፡፡ እንዴት ያለ ታላቅ ክስተት!! አሁን እኮ ስምንት ፈረሶች አሉህ! ” አሉት።
ገበሬው እንደገና“ ምናልባት ”አላቸው ፡፡
በሚቀጥለው ቀን ልጁ ከፈረሶቹ አንዱን ለመጋለብ ሲሞክር ወድቆ እግሩን ተሰበረ ፡፡ ጎረቤቶቹም “ ይሄ ደግሞ በጣም መጥፎ አጋጣሚ ነው” አሉት።
ገበሬውም በድጋሚ “ምናልባት” ብሎ መለሰላቸው ፡፡
🔆በሚቀጥለው ቀን የግዳጅ መኮንኖች ሰዎችን ወደ ጦርርነት ለማሰማራት በመጡበት ጊዜ የገበሬው ልጅ የተሰበረ እግር ስለነበረውው ልጁን አይመጥንም ብለው ጥለውት ሄዱ ፡፡ እንደገና ጎረቤቶቹ ሁሉ መጡ እና “ይሄ እንዴት ደስ ይላል ልጅህ እኮ ጦርነት ከመግባት ተረፈ!” አሉት ፡፡
አሱ ግን እንደገና “ምናልባት” አላቸው፡፡
🔑ገበሬው ስለ ትርፍ ወይም ኪሳራ ፣ ጥቅምና ጉዳት ከመሳሰሉ ነገሮች ከማሰብ በጥብቅ ተቆጥቧል፣ ምክንያቱም የህይወት ክስተቶች በጭራሽ ይዘው የሚመጡትን ነገር ማናችንም አናውቅም። ብዙዏቻችን በህይወት ባህር ውስጥ የምንሰምጠው፤ እንደገበሬው ከኑሮ ጋር በቀላሉ መንሳፈፍን ስላለመድን ነው። በህይወታችን ወስጥ በእኛ ቁጥጥር ስር የሆኑ ነገሮች አሉ፤ ሌሎች ከእኛ ቁጥጥር ውጪ የሆኑ ደግሞ እጅግ ብዙ ነገሮች ይኖራሉ።
💡በኑሮ ባህር ውስጥ መስመጥ የሚከሰተው ታዲያ፤ ከእኛ ቁጥጥር ወጪ የሆኑ ነገሮች ላይ ግትርነታችንን ለማሳየት ስንሞክር ነው። መለወጥ የማንችለውን ነገር በጉልበት ለመለወጥ ስንሞክር፤ የመዋኘት ጥበቡ ጠፍቶናል ማለት ነው። ህይወት ወደድንም ጠላንም ባልታሰቡ ፈተናዎች እና ስጦታዎች የተሞላች ነች። እንደ ገበሬው ረጋ ብለን ካልተንሳፈፍን በፍጹም ከለውጥ ጋር ተግባብተን ለመኖር አይቻለንም።
📍እናም ወዳጄ ዓለም እና የሰው ልጅ ተፈጥሮ በብዙ ስንክሳር የተሞሉ ናቸው። ባሳለፍከው ህይወት ብዙ ክስተቶች ታይተዋል። የሚያሳዝንም የሚያስደስቱም ሁኔታዎች የህይወት ገጾች ናቸው። ሁሉ ይመጣል፣ ሁሉም ይሄዳል። ያለፈውና የሚሄደውን በሰላም ሸኘው። አሁን ካለው ጋር በሰላም ተከባብረህና ተሳስበህ ኑር። ዘልዓለማዊ ክስተት የለም፣ ለውጥ እንጂ ። ከሁኔታዎች በላይ መሆንን እወቅበት። መረጋጋት መልካም ነው።
ውብ ምሽት❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
✍ @EthioHumanitybot
💡የሆነ መንደር ውስጥ አንድ ጅል ይኖራል። የመጨረሻ ጅል ከመሆኑ የተነሳ አምሳ ሳንቲም እና አስር ሳንቲም መለየት አይችልም። እና የመንደሩ ነዋሪዎች ይመጡና "አንተ ጅል ና እስቲ ከዚህ ምረጥና ውስድ" ብለው አምሳ ሳንቲም እና አስር ሳንቲም ሲያስቀምጡለት አስሯን ያነሳል። "ይሄ (አምሳውን) ይሻልሃል" ሲሉት "እምቢ ብሎ ያለቅሳል።
🔆 "አይ ይሄ ጅል … ኑ ጉድ እዩ፤ ኑ ጉድ እዩ" ይሉና አስር ሳንቲም እና አምሳ ሳንቲም ድጋሚ ያስቀምጡለታል። አሁንም አስሯን ያነሳል። ኧረ ይሄ ይሻልሃል ሲሉት "እምቢ፣ እምቢ" ብሎ ያለቅሳል።
በኋላ በዚህ ጅል ዘመዶቹ እያፈሩ ሄዱ። አንዱ ዘመዱ መጣና "አንተ ጅል … ሁሌ ባንተ እንዳፈርን እንቅር? ኧረ ተው ግድ የለህም፣ ተው ግድ የለህም። አምሳ ሳንቲም እና አስር ሳንቲም መለየት አቅቶህ አምሳ ሳንቲም ሲሰጡህ በአስር ሳንቲም ታለቅሳለህ? ኧንደው ምናለ አምሳውን ብታነሳ?" ብሎ ሲመክረው። "ጅልስ አንተነህ ነህ! አምሳውን ያነሳው ቀን አያስመርጡኝም።
🔆ማነው ጅል? እነሱ ወይስ ጅል ብለው የሚያስቡት ብልጥ? አያችሁ እሱ ብልጥ ጅል ነው፤ እስከ ኖረ ድረስ አስር፣ አስር ሳንቲሟን እየመረጠ የተጃጃለ መስሎ ያጃጅላቸዋል፤ ምክንያቱም አምሳዋ አንዴ ነች፤ አስሯ እስካለ ትቀጥላለች።
💡እንደነሱ ከሆነ አምሳ ሳንቲሟን የብልጠቱ፣ አስር ሳንቲሟን ደግሞ የጅልነቱ መገለጫ አድርገዋታል። ለሱ ግን አስር ሳንቲሟ የብልጠቱ መሰወሪያ፣ መደበቂያ ነች። አምሳዋን የመረጠ ቀን ጅልነቱ ያበቃል፤ ማንም አያስመርጠውማ። ምክንያቱም አውቋል፤ ነቅቷል ይሉታላ።
✍ዓለማየሁ ገላጋይ
ከሞኝ ብልጦች ብልጥ ሞኞች የሚያዋጣውን ያውቃሉ!
ሸጋ ቅዳሚትን ተመኘን😁
@Ethiohumanity
@Ethiohumanity
✍ @EthiohumanityBot
🌍ምክር ለወዳጅ
📍ወዳጄ ሆይ
ወንዝ መርጦ አያጠጣም። አጎንብሶ ሊጠጣ ለወደደ ሁሉ ሳይሰስት ያጠጣል። ደግነትህ እንደ ወንዝ ይሁን! ሳትመርጥ፣ ለለመነህ ሁሉ እጅህን ዘርጋ። ሁልጊዜ እንደ ወንዝ የሚፈስ መልካምነት፣ በጎነት ይኑርህ። መርዳት ዕድል ነውና ተጠቀምበት ፡፡... ሌላው የወንዝ ውበቱ ዝቅ ብሎ በዝምታ መፍሰሱ ነው። ዝቅ ብሎ ሌሎችን ከፍ እንደማድረግ ምን ውብ ነገር አለ? ይህንን አደረግኩኝ፤ እንዲህ ደግ ሰራው እያሉ መጮህ የደግነትን ክብር ይነካል፤ እንደ ወንዝ በዝምታ፤ ለሌሎች መልካም መሆን ነው እውነተኛው ደግነት ነው። ወደኛ የመጣች ደግነት ወደሌሎቹ ካልሔደች ደስታ አይኖረንም የተቀበልነውን ደግነት እኛም ለሌሎች እናሳይ፡፡ ጥሩ ሥራን ለሕሊና ምግብነቱ እንጂ ለሰማይ ሽልማቱ ብቻ አትሥራው ። የመልካም ነገር ዋጋ ከፋይ ፈጣሪ መኖሩንም እመን ።
📍ወዳጄ ሆይ !
ባለሀብት ብዙ ያለው ሳይሆን ካለው ብዙ የሚሰጥ ነው።ከሚደልሉ አንደበቶች የሚመፀውቱ እጆች እጅግ ይልቃሉ ። ልግስና ማለት የኪሳችንን ቦርሳ መክፈት መቻላችን ብቻ ሳይሆን ልባችን መክፈት መቻላችን ነው። አንተም ለመልካም ስራ እጅህን ለግስ "ልግስና የነፍስ ምግብ ነውና'' ደስታ ለሚሰጥ አብዝቶ ይመለስለታል። ሌሎችን መረዳት የመጀመርያው ንቃት እና ዕውቀት ነው፣ መንፈስህንም ወደ ላይ ክፍ ከፍ ያደርገዋል። ታላቅ የሆነ ጥበብ እና ማስተዋልንም ይዞልህ ይመጣል ። ደስተኛ የመሆን ቀላሉ መንገድም መልካም ነገር ማድረግ ነው። ውብ ነገርን ተመርኩዘው የሰሩት ስራ ሁሌም ውብ ነውና።
📍ወዳጄ ሆይ !
አቅመ ደካማን ሰው ጥሪቱን ብትገፈው የምታጌጠው በተቀደደው ልብሱ ነው ፣ ድሀን ዘርፈው ባለጠጎች የሆኑም ሲያፍሩ የሚኖሩ ናቸው ። አንተም የግፍን እንጀራ እንዳትበላ ተጠንቀቅ!! ጭካኔ የሕሊና ሰላምህን ያቀነጭራል። ፈጣሪ መስረቅን በትእዛዙ ቢከለክልህም ፣ የዘረፍከውን እንዳትበላ ግን በፍርዱ ያግድሃል።ፈጣሪ ባህሪና ተግባራችንን ያያል። ከሰው የወሰድነውን ከሰውየው ብንደብቅ ከአምላክ አንደብቅም። የምናተርፈው ነገር ቢኖር የሆነ ጊዜ ላይ የሚመጣ መጥፎ ስቃይን ነው። ያውም ለልጅ የሚተርፍ የበደል ክፍያን ነው፣.........የቆምን መስሎን የዘነጋን ሰው የዘራውን ያጭዳልና እናስተውል።
📍ወዳጄ ሆይ !
ከጓደኛህ መልካም የሆነውን ነገሩን አውጣለት ፣ አበረታታው ፣ እንደማይጠቅም አትንገረው ፣
ለሀዘኑ ሳይሆን ለደስታው ምክንያት ሁን ፣ ለስኬቱ እንጅ ለውድቀቱ መንስኤ
አትሁን ።መልካም ዘር ዘርተህ መልካም ምርት እፈስ፣ፍቅር የዘራ ፍቅር ያገኝል። ጥላቻ የዘራም ጥላቻ ያመርታል። ቅሬታ የተከለ ቅሬታ ይለቅማል። መልካም ዘር የዘራ መልካም ፍሬ ያጭዳል።አለም የአስተሳሰብህ ግልባጭ ናት፣ መስታወትህም ናት።
📍ወዳጄ ሆይ !
ከሚንጫጫ ብዙ ፣ ዝም ያለውን አንድ ሰው ፍራ ። ከሚጮኸው ውሻ ፣ የማትጮኸው ግመል ብዙ በረሃ ታቋርጣለች ። ያነበበ ቢተኛ እንኳ ነቅቶ የተኛ ነው ። ሳታነብ ሰው ሁሉ ከሚወድህ አንብበህ ብቸኛ ብትሆን ይሻላል ። ዓለም በጫጫታና በመዋከብ ውስጥ ብቻ ትልቁ ደስታ ያለ ይመስላታል፣ ዝም ያለች ጥበብ ግን አጥብቆ ለሚሻት እጅጉን ቅርብ ናት። ብልህና ትጉ የሆነ ማንኛውም ግለሰብ በየትኛውም የህይወት ዘርፍ ላይ ላሉበት ክፍተቶች በዙሪያው ከሚያስተውላቸው የቀን በቀን ክስተቶች እርማርትን ነቅሶ ይወስዳል፣ በሌሎች ላይ የሚመለከተውን ደካማና እኩይ አካሄድንም በራሱ ላይ እንዳይታይ በመጠንቀቅ እራሱን ወደተሻለ አቋም ያሸጋግራል!
📍ወዳጄ ሆይ !
ዓለም ዋዣቂ ናት ። ከፍና ዝቅ ስትል አትደናገጥ ፤ ፀሐይ ዝናብን ተከትላ ትፈነጥቃለች ። ከመከፋትም በኋላ ትልቅ መፅናናት ይሆናል ። ከሌሊት በኋላም ሌሊት አይመጣም ። ከሀዘን በኋላ ደስታ ይሆናልና በርታ! መነቀፍን አትፍራ ፤ ነቀፋህን ግን አጥራው ፤ ስለ ሀሰት ሳይሆን ስለ እውነት ተገፋ ፤ ሁሌም ከሰዎች ውስጥ መልካም ገጻቸውን ፈልገህ አንጥረህ ተመልከት፣ ጥሩነታቸውን በማድነቅ ገንባ፣ ከአፍህ መልካም ቃል ይውጣ፤ መልካም ዘር ዝራ። ልብ በል! ክፋት፣ ጥላቻ፣ ቂም፣ ቅሬታ አይጠቅሙህም። ይልቅስ ይጎዱሃል፣ በሽታ ያመጡብሃል፣ ወደታች ይስቡሃል።
🔑እናም ወዳጄ
ዛሬ የመዝራት ዘመንህ ነገ መከርህ ነውና በእምነት እውነትን ዝራ ፤ በምታውቀው ቦታ ላይ አገልጋይ በማታውቀው መልካም ተግባር ላይ ደጀን ሁን ፤ በቦታህ መምህር ያለቦታህ ተማሪ ሁን ፤ ክብሩ እንዳይቀንስብህ ከዕቃ ትምክህት ፣ ከዕውቀት ሙግት ራቅ ።ሰዎች የዘሩትን ሲያጭዱ ስታይ አንተም ዛሬ እየዘራህ ነገ ደግሞ የምታጭድ መሆኑን አስብ። አለም ሁሉ ሲዋዥቅ፣ ሳትዋዥቅ የምትኖር እውነት ብቻ ናት ።
መጪው ዘመን ሰላማዊ እንዲሆን
ፈጣሪ ይዘዝልን❤️
ውብ አዲስ ዘመን😊
@Ethiohumanity
@Ethiohumanity
✍ @EthiohumanityBot
🌗በምድር ላይ ዘላለም እንዲኖር የተፈረደበት አንድ ሰው ነበር፡፡ ይህን ፍርጃ ሲሰማ ሳቀ... ዘላለም መኖርስ እንዴት ቅጣት ይሆናል? አራት መቶ አመታት አለፉ ... አንድ ማለዳ ላይ ከአልጋው ሳይወርድ ማስብ ጀመረ... ዘመናትን በምድር ላይ ያሳለፈ... የአለማችን ምርጥ ሰዓሊ፣ ምርጥ ሙዚቀኛ ሆኗል፡፡ ብዙ ጀግኖች በጦር ሜዳ ገድሏል... የሚወዳቸው የቅርብ ወዳጆቹም እድሜያቸውን ጨርሰው ሄደዋል። ሁሉንም ምግብ ቀምሷል፤ ያልረገጠው የምድር ክፍል የለም። አሁን ላይ ግን ለምን ከአልጋው መውረድ እንዳለበት ግልጽ አልሆነለትም። ሁሉም ነገር ሰልችቶታል። ለእርሱ ምድር እስር ቤቱ ሆናለች፡፡ በስተመጨረሻም ቀናቶቹ ሁሉ ትርጉም አልባ ሆኑበት፡፡
📍የ”አምላክ” ትልቁ ጥበቡ ሞትን መፍጠሩ ይመስለኛል፡፡ እያንዳንዱ ሃይማኖት እግሩን ያቆመው በሞት ላይ ነው፡፡ ሞት ባይኖር የሰው ልጅ፣ በአምላክ አያምንም ነበር። ሃይማኖቶች እግር ይከዳቸዋል፡፡ …ዘር ካልሞተ/ካልበሰበሰ ፍሬ አይሆንም፡፡ በዚህች ሰከንድ በሰውነታችን ውስጥ ህዋሳት እየሞቱ እራሳቸውን ባያድሱ ህልው መሆን አንችልም፡፡ ሞት እንደብዙዎቻችን እምነት፣ የህይወት ማብቂያ አይደለም፡፡ ወደ ቀጣይ ምዕራፍ መሸጋገርያ ድልድይ እንጂ ፣ የብዙዎቹ ሐይማኖቶች መሠረቱ ይሄ ነው ። እኛ ዘመናችንን ሙሉ ከሞት ለማምለጥ ብንመኝም፣ ሞት እርግማን ሳይሆን በረከት ነው ። ያለ ሞት “መኖር” ትርጉም ያጣል፡፡
💡ዘላለም የሚኖረው ሰው እያንዳንዱ ቅፅበቶቹ ጣዕም አልባ ይሆናሉ። በዘላለማዊነት ውስጥ የሰውነት ባህሪ ይታጣል።የምንኖረው በአንፃራዊ አለም ውስጥ ነው። ሞትና ሕይወትም ሁለቱም የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ስለሆኑ ነው፡፡ ሞት ያለሕይወት፤ ህይወትም ያለሞት አልተፈጠረምና፡፡ ህይወትን ተቀብለህ ሞትን መተው አትችልም፡፡ ብዙዎች ከማያመልጡት ወጥመድ መሸሽ ይፈልጋሉ፡፡ ሞት የህይወትህ አካል ነው፡፡ ለሕያዋን ሁሉ የተሰጠ ስጦታ ነው፡፡ አስር ዓመትም፣ መቶ ዓመትም፣ ሺ ዓመትም በሕይወት ብትኖር ከሞት ጋር ክርክር የለህም፣ የትም ብትሄድ አታመልጠውም፡፡ ይልቁንስ ህይወትንም ሞትንም ጠልቀህ ከተገነዘብክ አኗኗርህንና አኳኋንህን፤ መካከሉን በማስተዋል ሕይወትህን እንድታስተካክል ይረዳሃል፡፡
🔑ሞት እና ጊዜ የተባሉ መልህቆች በሕይወታችን ውስጥ ያስፈልጉናል። ህይወት በትክክለኛው መንገድ ከተኖረ ሞት አይፈራም። ህይወትን ከኖራችሁ ሞትን በፀጋ ትቀበላላችሁ ምክንያቱም እንደ እረፍት፣ እንደ እንቅልፍ ትመለከቱታላችሁ። ከህይወት ጫፍ መድረስ ከቻላችሁ ሞት ውብ እረፍት ፣ ብረከት ይሆናል። በተቃራኒው ካልኖራችሁ ግን በርግጠኝነት ሞት ጊዜያችሁን ፣ የህይወት እድሎቻችሁን ይነጥቃችኋል። ካልኖራችሁ ነገ የሚባል ነገር የለም ፍርሃት ይነግሳል። ፍርሃቱ የሚመጣው በሞት ሳቢያ ሳይሆን በደንብ ህይወትን ካለመኖር ነው።"
ውብ አሁን❤️
@Ethiohumanity
@Ethiohumanity
✍ @EthiohumanityBot
💡አንዳንዴ በመታነጽ ላይ ሳለህ የቦዘንክ ቢመስላቸው አትደነቅ። ስኬት ቀድሞ በመራ አይደለም። ከእውቀት ሥራን ባስቀደመም አይደለም። ሥራ በዕውቀት ካልሆነ ልፋት ነው።
አንተ ብቻ ለዕውቀት ትጋ ፣ ጊዜው ደርሶ ሥራ ስትሠራ ደግሞ "ነገ ትቼው ለምሞተው ወይም ብሠራ የሚጠቀመው ሌላ ነው" በሚል ተስፋ ቢስ ሆነህ ሳይሆን ዘላለም እንደምትኖር ያክል በመትጋት ነው ። ትጋት ጥሩ ነው ። ችኮላህ ግን ውጤት አያመጣም ፣በችኮላ መሥራትና በፍጥነት መሥራት የተለያዩ ናቸው ።
📍አየህ አንተ ስትታነጽ፣ ስትተጋ ማንም ልብ አይልህም። ያንተ ራስን ማነጽ አርቀው ለማያስቡት ቦዘኔነት ነው። ሲያዩህ መሬት አትቆፍርም፣ እንጨት አትልግም፣ ምስማር አትመታም፣ ልብስ አትሰፋም፣ ዳቦ አትጋግርም፣ መርፌ አትወጋም። ለእነርሱ አንተ እየቦዘንክ ነው።
💎መጨረሻ ተሳክቶልህ፣ በኑሮ ከፍ ብለህ ሲያዩህ ግን "እድለኛ ነህ" ይሉሃል። እውነት ነው እድል ማለት ስትተጋ ሳትታይ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ መቻል ነው። ስንዴዋ አፈር ውስጥ ገብታ ስትበሰብስ ውጤቱን ለሚያውቀው ለገበሬው እንጂ ለሌላው ብክነት ነው። ሌሎች ውጤቱን የሚያዩት ስንዴዋ ስታፈራ ነው። ዘሩን የሚያናንቁ በፍሬው ቢደነቁ አትገረም።
አንተ ግን ለሌሎች ታይታ ሳይሆን በገባህ መንገድ አቅጣጫህን መርጠህ ትጋ! አንድ ቀን ውጤቱን ሲያዩ "እድለኛ ነህ" ይሉሃል።
💡እናም ወዳጄ
ምስጋና የደስታ ውጤትና ምንጭ ናትና። ባለህ ተደሰት! የምትፈልገውን ለማግኘት በትዕግስት ትጋ! አትዋከብ! አትቸኩል።
ምስጋናህ ግን በኑሮህ ላይ ባለህ ደስታ ይገለጽ። ኑሮህ፣ ህይወትህ፣ ስብከትህ ደስታህን ይመስክር።
ውብ ምሽት❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
@EthioHumanitybot
🌍እኔ” ሲደመር “እኔ”
💡ሁሉም ነገር ከራስ ይጀምራል። አንተ እና እኔ “ከእኔነታችን” ጀርባ “እኛነታችን” እንዳለ እንዘነጋዋለን። እያንዳንዳችን ከሃገር ደመራ ውስጥ የተሰገሰግን ችቦዎች ነን። አንዱ ሲጎድል ደመራው ቀጥ ብሎ ለመቆም ይቸግረዋል። ሃገርም እንደዛ ናት ብዬ አምናለው። “ሃገር” የሚለው ትልቅ ማንነት የሚፈጠረው “እኔ” በሚባሉ ጥቃቅን ማንነቶች ነው። እኛ ማንነታችንን መቅረፅ ሲሳነን ከእኛ አልፈን ቤተሰብን፤ ከቤተሰብ አልፈን፤ ማህበረሰብን፤ ከማህበረሰብ አልፈን ሃገርን እንጎዳለን።
🌍ሃገር የሚፈጠረው ከምንድን ነው? ከግለሰብ አይደለምን? ታዲያ ስለምን የግለሰብ አስተዋጽዎ እንደ ኢምንት ይቆጠራል? “እኔ ብቻ እንዲህ ባደርግ፤ ምን ዋጋ አለው?” የሚለው አስተሳሰብ የሚመጣው፤ “እኛን” ከ “እኔ” ስንነጥለው ነው። ተቀበልነውም አልተቀበልነውም ሁላችንም ሃገር ነን። የአንዳችን ቀጥ ብሎ አለመቆም የሃገርን ደመራ ያንገዳግደዋል።ሰዎች እራሳቸውን መለወጥ ሲችሉ፤ ያለምንም ድካም ቤተሰብ ይለወጣል፤ ማህበረሰብ ይለወጣል፤ ሃገር ትለወጣለች። ሃገር የብዙ “እኔዎች” ድምር ናት። ታዲያ ለምን ለውጣችን ከእኛ አይጀምርም?
📍በተተራመሰው አሰራር ውስጥ የእኔ አስተካክሎ መስራት ምን ለውጥ ያመጣል? የምንለው ብዙዎቻችን ነን። ግን አስቡት ሁላችንም እንደዛ ባንል እና ብንለወጥ፤ ትርምስምሱ አይሰተካከልም ትላላችሁ? እኔ በግሌ የሁሉም ነገር መሰረት ከገዛ እራሳችን ይጀምራል ብዬ አምናለው። ሃላፊነት የጎደለው ትውልድ፤ ታሪክ ለመስራት እንዴት ይችላል?
🌍ሁላችንም መልካም ቤተሰብ፤ መልካም ማህበረሰብ፤ ድንቅ ሃገር፤ እንዲኖረን እንመኛለን ብዬ አምናለው። ነገር ግን ሃገር የ”እኔ” ድምር መሆኑን ዘነጋንና፤ እራሳችንን ከለውጥ ሰልፈኛነት አወጣን። አስቡት፤ ሁሉም ሃላፊነቱን ወስዶ፤ እራሱን መለወጥ ቢችል፤ ስለ ትልቁ ለውጥ እንጨነቅ ነበር?
📍ሃገርን እንደ አንድ ንፁህ ባህር አስቧት፤ ሁሉም ያሻውን ቆሻሻ የሚደፋባት፤ ግን ያን ባህር ለማፅዳት ቢታሰብ መፍትሄው ምንድን ነው? ሁሉም የራሱን ሃላፊነት መውሰድ !!! “እኔ ቆሻሻ መድፋት ብተው፤ ሌላው ይደፋ የለ?” የሚል አስተሳሰብ ባይኖር፤ ሁሉም ባይሆን አብዛኛዎቹ ቆሻሻ መድፋታቸውን ያቆማሉ። መቼም ከብዙ ቆሻሻ ትንሽ ቆሻሻ ይሻላል።
እናም ሌላው ስለሚያደርገው ነገር ባንጨነቅ እና የራሳችንን ሃላፊነት ወስደን የገዛ እራሳችንን ብንለውጥ፤ ቢያንስ ካለብን ቆሻሻ፤ በእጅጉ የቀነሰ ቆሻሻ ነው የሚኖረን።
💎የኔ መልዕክት፤ እራስን ስለመለወጥ ነው፤ የእያንዳንዳችን መልካም ማሰብ፤ በጎ ማድረግ፤ ቀና መመልከት፤ ስራ መውደድ፤ ለውጡ ለገዛ እራሳችን ብቻ አይደለም። የሁሉም ነገር መሰረት “እኔ” ነው። “እኔ” ሲደመር ብዙ “እኔዎች” ናቸው ማህበረሰብን፤ ብሎም ሃገርን የሚፈጥሩት። ሰው ከሆንክ መኖርህን የምትለካው ለሌላው በምትሰጠው ስጦታ ነው ሌላው ደግሞ የሰው ልጅ ሁላና መላው ተፈጥሮ ነው - ስጦታህ ደግሞ ምንም ሳይሆን ፍቅር ብቻ ነው . ሁሉ በየራሱ ዱር ውስጥ እየኖረ ሀገሬ የስህተት ማዘያ አንቀልባ ስትሆን ሳያት አዝናለሁ። እኔ እንደወጣት ትልቅ ምኞት አለኝ። መልካም እራዕይ ያለው ትውልድ ለመፍጠር፤ ሁላችንም የገዛ እራሳችንን መፈተሽ አለብን።
🌍 “እኔ መልካም ባደርግ፤ ሌላው አያደርግም” ብለን የተሻለ ነገር ለማድረግ አንቆጠብ፤ እንደዛ ማለት ካቆምን ብዙ “እኔዎች” ይለወጣሉ፤ ብዙ “እኔዎች” ሲለወጡ፤ ማህበረሰብ ብሎም ሃገር ትለወጣለች። በመጨረሻ ሁላችንም ለማንኘውም ነገር ሃላፊነታችንን እንድንወጣ እለምናለው።
"ከህይወት ጽዋ እስካሁን እሬት ስንጠጣ ቆይተናል፤ አቅጣጫችንን መለወጥ ያለብን አሁን ነው፤ በራሳችን ላይ ከመዝመት የበለጠ ንቅናቄ (Revolution) የለም።"
- በዓሉ ግርማ
✍ ሚስጥረ አደራው
ውብ ምሽት❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
✍ @EthioHumanitybot
ህፃን ሄቨን ላይ የተደረገውን ድርጊት ለመናገር ሁሉ ያሸማቅቃል
ምን አይነት የጭካኔ ዘመን ውስጥ እንደደረስን የሚያሳይ ቆ ሻሻ የሆነ ግፍ😢ለቤተሰቦቿ ጥንካሬውን ያድላቸው ።
ይህው እናትም የልጄን ፍትህ አሰጡኝ እያለች የኢትዮጵያ ህዝብ እየለመነች ትገኛለች።
ለዚች እናትስ ምን ቃላት ያፅናናት ይሆን ?😪
ለህፃን ሄቨን ፍትህ ይገኝ ዘንድ ጫና ለመፍጠር እየተሰበሰበ ያለውን petition እንቀላቀል፣ ሼርም እናድርግ።
https://chng.it/rrSzFxp7PW
ድምፅ ሁኑ 🙏
ብላቴናዋ ሚጣ
@Ethiohumanity
💡 ትላንት አልፏል ስለዚህ ሞቷል። ነገ ደሞ ሚስጥር ነው ካልደረስንበት አናውቀውም።እንዲሁም ነገ ስጦታ ነው ካልተሰጠን አንደርስበትም። ዛሬ ግን በእጃችን ላይ ነው። ስለዚህ ስለ ትላንት በማሰብ ስለነገም በመጨነቅ ዛሬን አናበላሽዉ። ትልቅ ጥበብ ዛሬን መኖር ነው ከዛሬም ደሞ አሁን።
እናም ወዳጄ ያለን ዛሬ ላይ እናተኩር
💡 ሕይወት ትላንት ወይም ነገ አይደለችም። ሕይወት አሁን ናት። አሁንነት ሲያልፍ ትላንት ይሆናል የወደፊት አሁንነት ደግሞ ነገ ይሆናል። ሕይወት ተኖረ የሚባለው በአሁንነት ውስጥ ጤናማ በሆነ መልኩ ስንኖርበት ብቻ ነው። በአሁንነት ውስጥ ያልተኖረ ሕይወት የመከነ ሕይወት ነው።ዳሩ ግን ብዙዎቻችን በአሁንነት ውስጥ እየኖርን አለመሆኑ ነው። አእምሯችን በባለፈውና በወደፊቱ ጊዜ የተሞላ ነው። ከዚህም የተነሳ አዘውትሮ ያስባል ይጨነቃል።
ዛሬ የትናንት ተማሪ ነው፡፡ ዛሬ ነገን ውብ ቀን ለማድረግ የሚሰራ በእጃችን ያለ መክሊታችን ነው፡፡ የትናንትን ኋላቀርነት የሚደግም የዛሬ ቀን ለዛሬም አይሆንም፣ ለነገም አይተርፍም፡፡ ያለፈውን ደካማ ነገር መሻር ሲገባ የምንደግም ከሆነ ወደፊት መራመድ አንችልም፡፡ ትናንትን ወደነገ የሚያሻግረው ዛሬ ነው፡፡
⌛️ በትላንትናና በነገው አፍራሽ ስሜቶች ከመሞላትና ከመረበሽ በዛሬው ማንነት ውስጥ በትክክል መኖር ምርጫችን እናድርግ። ነገን የኖረ ማንም የለም። ነገን ስትደርስበት ህይወት እራሷ ትገለፅልሀለች። ሁሉም ነገር ጊዜ ተቀምሮለታል እኛ እድለኞች ነን ዛሬን ማየት ችለናልና።
ያበራ ማንነት ለሁላችን
ውብ አሁን❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
✍@EthioHumanitybot
💎ወዳጄ ሆይ የሚገርም ነገር ልንገርህ ድልድይም ግርግዳም ከድንጋይ ነው የሚሠራው። ግን ተግባራቸው ለየቅል ነው ድልድይ አንዱን ከሌላው ሲያገናኝ ግርግዳ ግን አንዱን ከሌላው ይለያል። ፍላጎትህ ሃሳብህ ተሰጥዎህ አልሳካ ቢልህ በፍላጎትህና ባንተ መካከል ያለውን ዶፍ የሚያሳልፍህን ድልድይ ገንባ እንጂ ፍላጎትህን ግርግዳ ሠርተህ አትከልክለው አስተውል ያሰብከው ካልተሳካ የተስፋ መቁረጥ ግርግዳ ሳይሆን የጽናት ድልድይ ስራ።
💡ጽናት- ድልድይ ነው፣ ተስፋ መቁረጥ - ግርግዳ ነው። ሁለቱም በቃላት ይገነባሉ። እናም ወዳጄ መማር ባለብህ ጊዜ ተማር፣ መሥራት ባለብህ ጊዜ ሥራ፣ መዝፈን ባለብህ ጊዜ ዝፈን፣ መዘመር ባለብህ ጊዜ ዘምር፣ መጻፍ ባለብህ ጊዜ ጻፍ። ያሰብከውን ነገር ለማድረግ ምቹ ጊዜ አትጠብቅ፣ ምቹው ጊዜ ሃሳቡ ወደ ጭንቅላትህ የመጣበት ጊዜ ነው።
💎ልብህ ያሰበውን ጥሩ ነገር ከመፈጸም አትቦዝን። ሃሳቡ በውስጥህ አርጅቶ እስኪሞት አትጠብቅ። ሰው በልቡ አላማውን ከጸነሰ በኋላ ወደ ቀኝ ወደ ኋላ ሳይወላውል፤ ወደ ግቡ የሚያደርሰውን ቀጥተኛ መንገድ ሊያሰምር ይገባዋል። የማስፈጸም ፍላጎት፤ የሚበቅለው “ይቻላል” ከሚል ስሜት ነው። ከአላማ ጋር የተሳሰረ አስተሳሰብ እጅግ ግዙፍ ሃይል ነው። አሁን ካለበት ሁኔታ ለተሻለ ኑሮ እና አስተሳሰብ እራሱን ያዘጋጀ ሰው፤ አይምሮውን በብልሃት የሚያሰራ ለስኬት የተዘጋጀ ነው።
💡ትላንት ነገ ያልነው ዛሬ፣ ቅድም ቡሃላ ያልነው አሁን ደረሰ፣ግን ማድረግ የፈለግነውን አላደረግን ይሆናል፣ሆኖም በዚህ ተስፋ አንቆርጥም፤ደግመን ምኞታችንን ለማግኘት ተስፋችንን ለመጨበጥ እናቅዳለን።የምንመኘውን ያን ምኞት፣ መሆን ያለብንን እስክንሆን አንቆምም፣ ተስፋም አንቆርጥም፡፡
ውብ አሁን❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
✍@EthioHumanityBot
✨የጥበብ ምሽት
ማህበረሰብ አንቂው እና ወግ አዋቂው።
🔊አቶ በሀይሉ ገብረመድህን
ውብ ምሽት♥️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
@EthioHumanityBot
🛑እያንዳንዳችን ፍቅርን የምንገልጽበት የራሳችን የሆነ መንገድ አለን። እናትና አባት ለልጆቻቸው፤ ወንድም ለእህቱ፤ እህት ለወንድሟ፤ ጓደኛ ለጓደኛ፤ ሚስት ለባሏ፤ ባል ለሚስቱ፤ ፍቅራቸውን በተለያየ መጠንና መንገድ ይገልጹታል። በፍቅር ስም ብዙ ስህተቶች ሲፈጸሙ ይስተዋላል። ፍቅር ስህተት ሆኖ ሳይሆን የሚገለጽበት መንገድ ልክ ስላልሆነ ብቻ። ምክንያቱም ፍቅር ምን ጊዜም በየትኛውም ጊዜ እና ቦታ ስህተት ሆኖ አያውቅም።
🔷ፍቅር ጉዳት የሚሆነው፤ ስህተት የሚመስለው የሰዎችን ልብ የሚሰብረው፤ ፍቅር ስህተት ሆኖ ሳይሆን ያስተላላፊው ስህተት ሲኖር ነው። ፍቅር ሳይበረዝ እና ሳይከለስ ለመተላለፍ ነጻነትን ይፈልጋል። ነጻነትን የተነፈገ ፍቅር ለተቀባዩ እዳ ይሆናል። ወላጆች ለልጆቻቸው ያላቸውን ፍቅር ለመግለጽ አለቅጥ ሲቆጣጠሩ በልጅ እና በወላጅ መካከል ያለው የግልጽነት ድልድይ ይሰበራል። ወላጅ ፍቅሩን “እኔ
አውቅልሃለው” በሚል አገላለጽ ሲገልጽ ልጆች በወላጅ ተጽዕኖ ነጻነታቸውን መስዋት ያደርጋሉ።
♦️ ይህ ማለት ወላጆች ልጆቻቸውን መቆጣጠር የለባቸውም ሳይሆን ፤ እስከምን ደረስ መሆነ እንዳለበት ልብ ሊባል ይገባል። ወላጆቻቸውን ፍራቻ ልጆች ብዙ ስህተቶችን ይፈጽማሉ ። ውድቀታቸውን እና የህይወት ፈተናዎቻቸውን ለወላጆቻው መግለጽ የሚከብዳቸው፤ ወላጆች ፍቅራቸውን የገለጹበት መንገድ ልክ ባለመሆኑ ነው። በተለይ በኛ ማህበረሰብ ግልጽነት የሚጎድለን ፤ ወላጆቻችን ፍቅር አንሷቸው ሳይሆን አገላለጻቸው ወደ ፍርሃት ስለሚወስደን ነው።
🔷በየትኛውም ቦታ እና ግንኙነት ፍቅር ህይወት ሊዘራ የሚችለው ነጻነት ስኖረው
ብቻ ነውና ፣ የምንወደውን ጽጌሬዳ ቆርጠን ቤት አናስቀምጠው ምክንያቱም ይሞታልና። ይልቁንም እውነተኛ ፍቅር ካለን ባለበት እንዲያብብ እንፈቅድለታለን። የምወዳቸውን ሰዎችም ማስተናገድ ያለብን እንዲህ ነው፤ እውነት የምንወዳቸው ከሆነ ነጻነታቸውን እንስጣቸው። በፍቅር ስም እነሱ የመረጡትን ሳይሆን እኛ የመረጥልናቸውን እንዲኖሩ አናስገድዳቸው።
📍በዚህም ምድር ላይ ለሰው ከነጻነት የበለጠ ስጦታ የለም። በነጻነት ውስጥ እምነት አለ በራሷ እንደትበር የተለቀቀች ወፍ ሌሎች በሷ እንደሚያምኑ ይሰማታል። በነጻነት ውስጥ ግልጽነት አለ፤ የሚሸፈን የሚከደን ምንም ነገር ስለሌለ። ፍቅር ደግሞ ያለእመነት እና ግልጽነት ዋጋ አይኖረውም። ለዚህ ነው ፍቅር እና ነጻነት ተለያይተው መሄድ የማይችሉት።
የምንወዳቸውን ሰዎች እናስብ ፍቅራችንን እንዴት እየገለጽንላቸው ነው? ነጻነታቸውን በሚጋፋ መልኩ ከሆነ እስቲ ትንሽ ቆም ብለን እናስብበት⁉️
ውብ አሁን❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
✍ @EthioHumanityBot
♦️ምክር ለወዳጅ
📍ወዳጄ ሆይ !
አዲስ ግኝት የመሰለህ እውቀት ከራስህ የመነጨ ሳይሆን ፈጣሪ ከሰጠህ አእምሮና አብርሆት የተገኘ ነው ። እውቀትን የጣለ እምነት ፣ እምነትን የጣለ እውቀት አይኑርህ ። እውቀት የሌለው እምነት ራስን ማደንቆር ነው ። የሚታወቅ ነገር ሳለ ፣ ማወቂያ መሣሪያው አእምሮ ከተሰጠህ የማወቅ ግዳጅ አለብህ ። ሰውን ሰው የሚያደርገው በእውቀት የተፈጠረና በእውቀት የሚያድግ መሆኑ ነው ። እምነት የሌለው እውቀት ግን ማለስለሻ እንደሌለው ተሽከርካሪ እርስ በርሱ የሚፋጭ ፣ ድምፁ የሚረብሽ ፣ ዕድሜው የሚያጥር ነው ።
📍ወዳጄ ሆይ !
እኔ እንጂ እነርሱ ምን አለባቸው ? አትበል ። ብዙ ባለበት ዓለም ምንም የሌለበት ፍጡር የለም ። ሕፃናትም በረሀብ ፣ ልጆችም በበሽታ ይሰቃያሉ ። እንስሳትም በሰው የመጣውን ሐሣር ይካፈላሉ ። አንተ ስላለህ ሁሉ ያለው አይምሰልህ ። አንተ ስላጣህም ሁሉ ያጣ ሁኖ አይሰማህ ፣ ብርታት ሌላውን ከማበርታት ይገኛል ። ሌላውን ስታበረታ አንተም በርትተህ ትገኛለህ ።
📍ወዳጄ ሆይ
ሰዎችን የምታሸንፋቸው በፍቅር ፣ የሚያሸንፉህ በክብር ነው ። እውነተኛ ፍቅር መስጠት ካልቻልህ በሽንገላ ራስህን ማድከም ፣ ትዝብት ላይ መውደቅ አያስፈልግህም። የጎላ ታይታ መውደድ ወደ ብዙ መሰወር ይለወጣል ። “እዩኝ ፣ እዩኝ ያለ ገላ ፣ ደብቁኝ ደብቁኝ ይላል” እንዲሉ ፣ ጓዳህን ለሁሉ አታሳይ፣ ምሥጢርህን በአደባባይ አትግለጥ። ክብር በትግል አይገኝም ፣ መፈራትም እውነተኛ ክብርን አያመጣም።
📍ወዳጄ ሆይ
ከፍታህን ከፍ ባለ ቃል ሳይሆን ከፍ ባለ ኑሮ ግለጠው። ሕያው መንፈስ አለህና በቁሳቁስ አትመካ፣ የሰው ንብረት አትቀማ! ሰውን ወልዶና ተዋልዶ ኑሮውን ከመሰረተበት መሬት አትንቀል፤ አታፈናቅል። እንጀራው ለሁሉ እንዲበቃ አድርገህ አስፋው! ለዚህ ፍቅር ያስፈልግሃል ፣ ይህ የሚቻለው ፍቅር ሲኖር ብቻ ነውና፣ ልብህ ለሰው ልጅ ሁሉ በፍቅር እንዲሞላ ይሁን።
📍ወዳጄ ሆይ
የሆነው መሆን ስላለበት ነው ። ፍርሃት የታዘዘን ነገር ከመምጣት አያድነውም ። በፈቃድህ ወደ እዚህች ዓለም ምንም ነገር አላመጣህምና ፣ እንዴት ይህ ይደርስብኛል? አትበል። የቀለጠ ወርቅ ጌጣጌጥ እንደሚይሆን የተጠረበ ድንጋይ ሐውልት እንደሚይሆን ሁሉ ፣ እንተም በብዙ ችግሮች ውጣ ውረዶች ባለፍክ ቁጥር አንተነትህ እያደገ መሆኑን አትርሳ !
🔺ታዲያ ወዳጄ፦
ቅን ልብ የጨለማ ዘመን መብራት ነውና ቅንነት ይኑርህ ። ማስተዋል የሌለበትን ዓይናማነትን አትውደደው ። ሰውን በፍቅር እንጂ በኃይል አትሳበው ፣ የሚያደምጡህን አድምጣቸው ። ራስህ የሠራኸውን ራስህ እንዳታፈርሰው ሥራህን በችኩልነት አትፈጽም ፣ ትዕግሥት የጎደለው ቤት በተገነባ ቁጥር መፍረሱ ይፈጥናል ። የረዳሃቸው ሌሎችን ሲረዱ ለማየት ናፍቆት ይደርብህ፣ የሰው ሰውነቱ መታያው ልቡናው ዉስጥ በሰነቀው ቅንነት ነውና፣ በሽተኛን ከሚፈውስ ባለ ስጦታ ፣ የተከዘን ልብ የሚያጽናና ወዳጅ ይበልጣል።
ውብ አሁን❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
✍ @EthioHumanityBot
📍ደፋር መሆን ይኖርብናል ያልተሄደበትን መንገድ ለመሄድ መድፈር
ትእቢትን እልህን ጥላቻን ይሉኝታን ለመተው መድፈር
ራስን ለማዳመጥ መድፈር
💡አዎ ብዙ በደል ፈፅመሀል ተፈፅሞብሀል። ብዙ ሰው ጠልተሀል፣ ተጣልተሀል ፣ ተጠልትሀል ፣ ልብህ ተሰብሯል፣ ልቦችን ሰብርሀል ፣ግን ደግሞ ከዚህ ሁሉ ጋር ታርቀህና ራስህን አስታርቀህ ዳግም ለመውደድ ፣ ዳግም ለማዘን ፣ዳግም ለመርዳት፣ ዳግም እርዳታ ለመጠየቅና በቅንነትና በፍቅር ለመኖር ድፈር።
📍መጀመርያ ግን ከራስህ ጋር ለመታረቅ ድፈር። ራስህን ከነሙሉ ስህተቶቹ፣ ግድፈቶቹ ፣እንከኖቹ፣ውሸቶቹ፣ ቅጥፈቶቹ፣ አስመሳይነቶቹ ሁሉ ለመቀበል ለማዳመጥና ለመውደድ ድፈር
የፍቅር የይቅርታ ዘመን ነው ሲባል ወደሰማይ አታንጋጥ፣ ወደጎረቤቶችህና ጠላቶቸ ብለህ ወደፈረጅካቸው ሁሉ አታፍጥጥ
መጀመርያ ከራስህ ጋር ለመታረቅ ወደውስጥህ ተመልከት፣ ወደራስህ ተመለስ ፣ ውስጥህን ፣ልብህን ፣ ህሊናህን አፅዳ፣ሰው የሚሰጥህ ክብር አንተ ለራስህ በምትሰጠው ሚዛንና መጠን ነውና ለራስህ ትልቅ ዋጋና ብዙ ክብር ይኑርህ
💡ራስን መመልከት ራስን ወደ መሆን የሚያደርስ ወሳኝ መንገድ ነው። ራስህን ስትመለከት የወንድምህን ጉድፍ ሳይሆን የአንተን ተራራ ታስተውላለህ፥ በዚህ ውስጥ ደግሞ ተራራህን እየነቀልክ ራስን ወደ መሆን ታድጋለህ። ራስህን ስትሆን ብዙ ነገሮችን ታሸንፋለህ፥ መሰናክሎችን በቀላሉ አልፈህ፥ የነከሰህን የመከራ ጥርስ ውሃ የማድረግን ጥበብ ትጎናጸፋለህ።
🔑ብቻ ምን አደከመህ ራስህን ስትሆን ብዙ የደረብካቸው አላስፈላጊ ኮተቶችን ከራስህ ላይ አውርደህ፥ ንጹህ አንተነትህን ብቻ ያነገበ ማንነት ስትገነባ ያን ጊዜ ሰው መሆን ትጀምራለህ።እናም ራስህን ለመውደድ ድፈር።
ውብ አሁን❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
✍@EthioHumanitybot