lovefkr | Unsorted

Telegram-канал lovefkr - Love - ፍቅር

7362

ስለተቃራኒ ጾታ ግንኙነት አብረን እንድንማማር መድረኩን ከፍተናል። በሚመቸን እንሳተፍ። @kkzinu1 @TgKassa @Nahooom @Yona4501 @Fkr_Orthodox https://t.me/lovefkr https://t.me/lovefkrlove youtube.com/lovefkrlove https://LoveFkrLove.com www.facebook.com/lovefkrlove

Subscribe to a channel

Love - ፍቅር

❤️ለፍቅር ግንኙነት መስፈርቶችሽ/ህ የማትደራደረው/ሪው የቱ ነው? 2&3ን ኮመንት አድርጉልን።
anonymous poll

በአስተሳሰብ የምንግባባ – 3
👍👍👍👍👍👍👍 60%

የሚወደኝ – 2
👍👍👍👍👍 40%

በቂ ስራ ያለው
▫️ 0%

የምወደው
▫️ 0%

ውበት / ቁንጅና
▫️ 0%

ጥሩ የሰውነት አቋም/ቅርፅ
▫️ 0%

እምነት አጥባቂ
▫️ 0%

በቤተሰቤ ተወዳጅ
▫️ 0%

ከትዳር በፊት የማልተኛው/ት
▫️ 0%

👥 5 people voted so far.

Читать полностью…

Love - ፍቅር

በሳምንት የስንት ብር ካርድ 📱 ትሞላላችሁ? @LoveFkrLove
anonymous poll

>100 – 8
👍👍👍👍👍👍👍 80%

>50 – 1
👍 10%

>200 – 1
👍 10%

>500
▫️ 0%

>1000
▫️ 0%

👥 10 people voted so far.

Читать полностью…

Love - ፍቅር

❤️በፍቅርና ማህበራዊ ግንኙነት ዙርያ ምሽት ውይይት ለማድረግ አስበናል። ለአብዛኛው የሚመቸውን ሰዓት እንድናውቅ ምርጫችሁን አሳውቁን።⏰
public poll

ከምሽቱ 2-3 🕑 – 11
👍👍👍👍👍👍👍 73%
@Wendu35, @my12key, @fewazbaba, ዝናሽ, @Wedi12, @seste12, Tilahun, @Kuzienc, Tg, Demisse Denbo, Ğíźëŵ

ከምሽቱ 1-2 🕐 – 2
👍 13%
@LoveEthiopia, Tamirat

ከምሽቱ 3-4 🕒 – 2
👍 13%
@Like_tec, Sintayehu

👥 15 people voted so far.

Читать полностью…

Love - ፍቅር

ፀጋ አግኝታ ከሰማያት
ብሩክ ነች እውነት ለሚያያት
https://www.youtube.com/watch?v=ZuWoAQ3ZaLE

Читать полностью…

Love - ፍቅር

አዳምና ሄዋን በገነት ሆነው አትብሉ የተባሉትን በሉ። ህግንም ተላለፉ። ይኸው ዛሬም ምንም ሳናጣ የተከለከልነውን በማድረግ ሃጢያት እንሰራለን፤ እንበድላለን፤ እናስቀይማለን። ሃጢያት የሰው ልጅ ባህሪ ነው።

ነገር ግን እግዚአብሔርም የሰውን ልጅ ስለወደደ በይቅርታ ከሃጢያታችን የምነነፃበት ሁለተኛ እድል ሰጠን።

ይቅርታ ሁለት አይነት ትርጉም አለው። አንድ የእግዚአብሔርን ህግ በሃጢያት ስንስት፡ ተፀፅተን ይቅርታ የምንጠይቅበት፣ በዚህም ካለፈ እድፋችን የምንነፃበት ነው።

ሁለተኛው እኛ የበደሉንን ይቅርታ የምናደርግበት ነው።

ሁለተኛው ለመጀመሪያው ቅድመ ሁኔታ እንደሆን አስበንበታል።
ለሌሎች ይቅርታ ስናደርግ የእግዚአብሔርን ይቅርታ አድራጊነት የምንመሰክርበት ነው።
ይቅርታ እንዲደረግልን፡ ይቅር ማለት አለብን!

ተቀይማችሁ፡ በቂም የምትኖሩ፡ ሽንፈት፡ የሚመስላችሁ ካላችሁ ፡ ከፈጣሪ ህግ ይሉኝታ የባሰባችሁ የሚባክን ግዜ የለምና ዛሬውኑ ከልብ ይቅር በሉ።

ይቅርታ ያደረጋችሁበት፡ ወይም ይቅርታ ለማድረግ የከበዳችሁ አጋጣሚ አለ? እስቲ አካፍሉን።
@LoveFkrLove

Читать полностью…

Love - ፍቅር

🥰 #ብቁ_ናችሁ!

☝️ከሕይወት ትልልቅ የፍርሃት ምንጮች አንዱ “ብቁ ያለመሆን” ፍርሃት ነው፡፡ በሰዎች ለመወደድ፣ ለመፈቀር፣ ተቀባይነት ለማግኘት፣ ለማወቅ፣ ለመሰልጠን፣ እድገት ለማግኘት . . .ብቁ እንዳልሆንን የማሰብ ፍርሃት!

✨እውነት እውነቱን እንነጋገር፡፡ አንድ ሰው እናንተን ለመቀበልና ለመውደድ የማይችል ወይም የማይፈልግ ከሆነ፣ ይህ ማለት እናንተ የዚያ ሰው አይደላችሁም ማለት ነው - አለቀ! ይህ ማለት ግን የዓለም መጨረሻ ነው ማለት አይደለም፡፡ ይህ ሰው እናንተን የመቀበልና የመውደድ ብቃቱ ወይም ፍላጎቱ የለውም ማለት ነው እንጂ እናንተ ተቀባይነት የማግኘትና የመወደድ ብቃቱና ማንነቱ የላችሁም ማለት አይደለም፡፡

🌞እናንተን የመውደድም ሆነ የመቀበል ብቃቱና ፍላጎቱ ያለው ብዙ ሰው በዙሪያችሁ እንዳለ አስታውሱ፡፡ እነሱን ለማየትና ለመገናኘት ግን “ካልተቀበለኝና ከልወደደኝ” ብላችሁ ችክ ካላችሁት ሰው ላይ አይናችሁን ማንሳት፣ ስሜታችሁንም ማላቀቅ የግድ ነው፡፡ ይህንን ማድረግ ለጊዜው ከባድ ነው፣ ነገር ግን በሚልየን የሚቆጠሩ ሰዎች ችለውታልና እናንተም ትችላላችሁ!

✨አንድ ነገር አልሆን ሲላችሁ ሁል ጊዜ እናንተ ለዚያ ነገር ብቁ ስላልሆናችሁ እንደሆነ የማሰብን የእሳቤ ንድፍ መቀየር አለባችሁ፡፡ በዚያ ምትክ ያ ሰውም ሆነ ሁኔታ ለእናንተ የማይመጥን ስለሆነ እንደቀረላችሁ ማሰብም አስፈላጊ የሚሆንበት ጊዜም እንዳለ አትዘንጉ፡፡

🔆በአጭሩ፣ ለመወደድ ብቁ ናችሁ! ለማደግ ብቁ ናችሁ! ለማወቅ ብቁ ናችሁ! በዚህ ዓለም ፈጣሪ ለሰው ልጆች ደስታና ስኬት ለፈጠረው መልካም ነገር ሁሉ ብቁ ናችሁ! ሕይወት ትክክለኛውን ሰውና ስፍራ ገልጣ እስከምታቀርብላችሁ ድረስ ግን ራሳችሁን በመቀበል የድርሻችሁን መወጣት የግድ ነው፡፡

✍ዶ/ር እዮብ ማሞ

ውብ ምሽት🙏🙏

@lovefkrlove
@Lovefkr

Читать полностью…

Love - ፍቅር

📊 👨‍🦰 ባለትዳር ወንድ "እስቲ ላስብበት" ካለ ምን ማለቱ ነው?

ላስብበት (35%)

አልፈልግም (22%)

ሚስቴን ላስፈቅድ (28%)

የተለየ አስተያየት አለኝ (15%)

212 👥

Читать полностью…

Love - ፍቅር

  🔶የደስታ ሁሉ ምንጭ አእምሮ ነው ፣ የመከራ የሥቃይ ምንጭም ራሱ አእምሮ ነው ፡የአዕምሮአችንን ተፈጥሮ በጥልቅ ተረድተን ከተጠቀምበት እውነተኛ ደስታ እና የነፃነት ውጤት ማግኘት እንችላለን ፡፡

💚 ወዳጄ ሆይ አንድን ነገር ለመረዳት ስትፈልግ ያንን ነገር መውደድ ይኖርብሀል ፣ስትወደው ሕይወት ቀላል ይሆናል። ከዚያ ስሜት በሚነካ ሁኔታ ነገሮችን ማስተዋል እና መረዳት ትጀምራለህ።ሁሉንም ለመረዳት ግን መጀመርያ በልብህ ውስጥ ፍቅር ሊኖርህ ይገባል ፡፡

♦️ማንነትህን ጠንቅቀህ ስትረዳ ዋጋህን ታውቀዋለህ ።የምትኖርበትን እና የምትኖርለትን ትለያለህ ።ወደ አዚች ምድር የመጣኧው ለምክንያት ነው ። አንተ የዚህች አለም ገፅ ውብ እና ሙሉ ይሆን ዘንድ እንደ አንዱ ጡብ ነህ ።ዋጋህን ባለመኖርህ አትተምን በመኖርህ እንጂ።የአንተ መኖር ለሌሎቹ ጡቦች ድጋፍ እንዲሁም ለግንባታው ውበት አስፈላጊ ነው።

💛 ይህን ባስተዋልክ ጊዜ ራስህን ነፃ ታወጣለህ ፣ፍቅር ሲኖርህ ደግሞ የማንም ትዕዛዝ ሳያስፈልግህ የሰዎችን ሥቃይ የሚያስታግስ መንገድ ትፈጥራለህ።

#ውብ_ምሽት

@Lovefkrlove
@Lovefkr

Читать полностью…

Love - ፍቅር

☝️ከማንም አልበልጥም፣
#ከማንም_አላንስም!

🙋‍♀በተፈጥሮ “ #ሰው ’ ነት” - ከማንም አልበልጥም ከማንም አላንስም! በዘርና በቋንቋ - ከማንም አልበልጥም፣ ከማንም አላንስም! በመልክና በቁመና ከማንም አልበልጥም፣ ከማንም አላንስም! በቆዳ ቀለም - ከማንም አልበልጥም፣ ከማንም አላንስም!

💥በእነዚህ ከላይ በተጠቀሱት የፈጣሪ ስጦታዎች አማካኝነት በማንም ላይ የበላይነት፣ ከማንም ስርም የበታችነት ከተሰማኝ በራሴ ላይ ያለኝ አመለካከት ላይ መስራት እንደሚገባኝ ጠቋሚ ነው፡፡

〽️ከሌላው ሰው የመብለጥና የማነስ ሁኔታ ሊከሰት ከቻለ፣ ሊሆን የሚችለው በሶስት ነገሮች ምክንያት ነው፡-

☝️. ባሳደኩትና በየእለቱ በማሳየው መልካም ወይም መጥፎ ባህሪይ አማካኝነት የበላይ ወይም የበታች ልሆን እችላለሁ፡፡

✌️የእኔን፣ የቤተሰቤንና የሕብረተሰቤን ሕይወት ወደተሻለ ደረጃ ለማድረስ በማከናውናቸው ወይም ችላ በምላቸው ተግባሮቼ አማካኝነት የበላይ ወይም የበታች ልሆን እችላለሁ፡፡

🤟ባዳበርኩት ወይም ችላ ባልኩት የሕይወት ዲሲፕሊን አማካኝነት የበላይ ወይም የበታች ልሆን እችላለሁ፡፡

🌕ከራሳችን አልፈን ለሌሎች የሚተርፍ ሕይወት ውስጥ ለመግባት ካስፈለገ ትርጉም የለሹንና የውሸቱን የበላይነትና የበታችነት ስሜት ተወት በማድረግ በእርግጥም ተሽለን እንድንገኝ በሚያደርግን ልማድና ልምምድ ላይ እናተኩር፡፡

✍ዶ/ር እዮብ ማሞ

#ውብ_ምሽት ❤️

@Lovefkrlove
@Lovefkr

Читать полностью…

Love - ፍቅር

✨" Go find Yourself first
So you can also find Me. "


🤷‍♀አንድ ሰው ሌላውን "አላውቀውም " ማለት ሲጀምር ፤ ያኔ ከራሱ ጋር እንደማይተዋወቅ ፤ እሱም ለራሱ ባዳ እንደሆነ መገንዘብ ይኖርበታል ። ለምን ቢባል ሁሉም ሰው እንደሰው የሚጋራቸው የወል የጋራ ስሜቶች አሉት ።

👫በሁለት ግለሰቦች መካከል ከሚኖሩት ልዩነቶች ይልቅ ተመሳሳይነታቸው ትልቁን ድርሻ ይይዛል ። " እኔ ከሌላው የተለየሁ ነኝ " ብለን ማሰብ ስንጀምር በእርግጥ አላዋቂነታችን በውስጣችን የነገሰበት ሰአት ላይ ደርሰናል ማለት ነው ።

💎ስው ማለት ፥ በየጊዜው የሚያድግ ፣ የሚለወጥ ፣ የሚደሰት ፣ የሚያዝን ፣ የሚስቅ ፣ የሚያለቅስ ፣ የሚተክዝ ፣ የሚጨክን ፣ የሚራራ ፣ የሚረሳ ፣ የሚያስታውስ ፣ በተስፋ እና በትዝታ መሐል የሚኖር ፤ .... የሚበርደው ፣ የሚሞቀው ፤ የሚይርበው ፣ የሚጠግብ ፣ ከወደቀ በኋላ የሚነሳ ፤...ወዘተ

🔴.. በመሳሰሉት የተለያዩ ስጋዊ-ወይም መንፈሳዊ ስሜት ጋር የሚኖር ነው ። . እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ስሜቶች ፤የትኛውም የአለም ክፍል የሚገኝ "ሰው " ሆኖ የተፈጠረ ሁሉም የሚጋራው ነው ። ታድያ ለምንድነው አንዱ ሌላውን " አላውቀውም " በማለት የሚክደው? - አንዳችን ጋር ያለ ስሜት ሌላውም ጋር ይኖራል ።

🔵... ሰው በመሆናችን በጋራ የምንጋራቸው እንጂ ፤ አንድም ከዚህ ቀደም ያልተከሰተ በሰው ልጅ ታሪክ ያለነበር ምንም አዲስ ነገር የለም ። ... ..የከፋው ሰው ስመለከት እኔ በህይወቴ የተከፋሁበት ዘመን ለምን ትዝ አይለኝም ?
ገንዘብ ወይም ስራ አጥቶ የተቸገረ ሰው ስመለከት ፤ ለምን ይሆን ያ የሱ ስሜት እኔን የማይሰማኝ ? ምናልባት የምበላው ሳይኖረኝ የተቸገርኩበት አጋጣሚ ምነው ትውስታው ደብዛው ይህን ያህል የሚርቀኝ ! ትውስ የማይለኝ ? በሁላችንም ደርሶ የሚያውቅ ፤ አልያም አንድ ቀን ሊደርስ የሚችል እንጁ ከቶ አዲስ የሆነ ነገር የለም ።
-
🔴ህይወት በአጋጣሚዎች የተሞላች ናት ። የምንደሰትበት ቅፅበት ሲያልፍ ትካዜ ቦታውን ይረከባል። አብረን የኖር ንበት ዘመን ሲያበቃ መለያየት በተራው ይመጣል ። የተለያየም አንድ ቀን ዞሮ መገናኘት ይኖርናል። የጉብዝና ወራት ሲያልቅ እርጅና በቦታው ይተካል ። ከፀሃይ በታች ምንም አዲስ ነገር የለም ። ሁሉም የነበረና ወደፊትም የሚቀጥል ይሆናል። ትውልድ በትውልድ ይተካል ። የህይወት ኡደት በተመሳሳይ ድግግሞሽ ይዘልቃል ።
-
🔴እኔን ለማወቅ ከፈለግክ አንተነትህን ማወቅ ይገባል ። አንተ ማለት እኔ ፤ እኔ ማለት አንተ ከአንድ ምንጭ የተቀዳን ፤ በትውልድ በየዘመናችን የምንፈስ ወንዝ ነን ጅረት ፤ ...ከመሬት ከአፈር የተፈጠርን ስጋ ለባሽ ፤ ተመሳሳይ ስሜት ያለን። ፤ በስተመጨረሻ ተመልሰን ወደ መጣንባት መሬት የምንገባ ።

✍Rumi

#ውብ_ምሽት

@lovefkrlove
@Lovefkr

Читать полностью…

Love - ፍቅር

✨ Happiness is not absence of sufferings but acceptance of sufferings ,Stop worrying about things which are beyond your control.

👉አንዳንዶቻችን ያሰብነውን ስራ እስክንይዝ፤ የምንፈልገውን ገንዘብ እስክናገኝ፤ የምንወደውን
ሰው በእጃችን እስንካስገባ፤ የምንፈልግበት የህይወት ደረጃ ላይ እስክንደርስ፤ እያልን ደስታችን ቤታችን እንዳይገባ እንከለክለዋለን። ሞኝነታችን እንግዲህ እዚህ ላይ ነው፤ ምን አልባት ያሰብነውን ብናገኝ እንኳን ላንደሰት እንችላለን፤ ምክንያቱም ደስታ ከውጫዊ ነገሮች ጋር አብሮ የሚቋጠር ቁስ ባለመሆኑ። ደስታ ሁሌም ከበራችን ቆሟል በቀጠሮ አላስገባ ብለነው ነው እንጂ።

👉ወደ ደስታ የሚውስድ ምንም አይነት መንገድ የለም፤ ይልቁንም ደስታ ወደ ምንፈልገው ቦታ የሚያደርሰን ብቸኛው መንገድ ነው እንጂ። ባለህ ነገር ደስተኛ ለመሆን ሞክር፤ ያኔ ፈጣሪ ይጎደለውን በተዓምሩ ይሞላዋል።

🤞ዛሬ በመኖርህ አመስግን አሁንህንም እንዲሁ አጣጥም።

🙏 #መልካም_አዳር 🙏

✍Humanity

@Lovefkrlove

Читать полностью…

Love - ፍቅር

“ #በህይወት ውስጥ የምንሰራው ትልቁ ስህተት ምንድነው?” ተብሎ ሲጠየቅ

⏰:- “ትልቁ ስህተት ጊዜ አለኝ ብሎ ማሰባችን..”

🖍አየህ ጊዜ ነፃ ነው ግን በዋጋ ሊተመን የማይችል። የጊዜ ባለቤት መሆን አንችልም ግን ልንጠቀምበት እንችላለን::

ልናቆመው አንችልም ነገር ግን ልንደሰትበት ወይም ልንሰራበት እንችላለን::

እናም አንዴ ካጣነው መልሰን ማግኘት አንችልም::

#መልካም_አዲስ_አመት

#ፍቅር_አሁን !! 💚💛❤️

@Lovefkrlove
@lovefkr

Читать полностью…

Love - ፍቅር

🌙የጨረቃዋን ውበት የሚሻ ጨለማውን አይሸሽም
🌹ጽጌረዳዋን ብሎ የሄደ እሾሁን ፈርቶ አይመለስም
😘ፍቅርን ከልቡ የሚፈልግ ሰው ከራሱ አይደበቅም ........................እራሱን ፈጽሞ አይሸሽም

🌘ውብ ነገሮችን ለማግኘት ሰው ፍርሃቱን አልፎ መሄድ አለበት፤ በምንፈግልጋቸው ነገሮችና በእኛ መካከል የቆመው ትልቁ ግድግዳ ካለማውቅ የሚመነጨው ፍርሃት ነው::
ጨለማውን የደፈረ ጨረቃን፤ እሾሁን ያልፈራ ጽጌረዳዋን፤ እራሱን ያወቀ ፍቅርን ማግኘታቸው አይቀርም::

🌙The best definition I heard for "Fearlessness" was that Fearlessness is not the absence of fear but the ability to step into your fear. It's the courage to acknowledge your fear, but not letting it stop you from anything you want. Don't make your fear your Enemy. If you make your fear your enemy it will kill you but, if you make it your friend you will always win.

🌔When you make the darkness your friend you get to enjoy the beauty on the Moon. When you become your own friend, Love will find you everywhere.
✍ በሚስጥረ አደራው

🙏#ውብ_ምሽት🙏

@Lovefkrlove
@Lovefkr

Читать полностью…

Love - ፍቅር

የማይሆን ሰው ለምን እናገባለን?
የማይመቸንን ፍቅረኛስ ለምን እንይዛለን?

Читать полностью…

Love - ፍቅር

በጠዋት ተነስቶ ማህበራዊ ሚዲያ ማየት ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል? እንወያይ💬
የሚስማማ 👍
ያልተስማማ 👎

Читать полностью…

Love - ፍቅር

❤️ህይወት ወጣ ገባ ናት። ብቻችንን ብንወለድም ስንኖር የሰው ልጅ ያስፈልገናል። ከሰው ጋር ስንኖር #በጓደኝነት#በተቃራኒ ፆታ ፍቅርም ይሁን #ትዳር #መተማማን ወሳኝ ነው። የሰው ልጅን ቶሎ የሚያምን ልብ አለህ? አለሽ? ለምን? እንወያይ💬 @LoveFkrLove
anonymous poll

ሰውን ቶሎ አምናለሁ – 11
👍👍👍👍👍👍👍 73%

ቶሎ የሚያምን ልብ የለኝም – 2
👍 13%

የወንዶች ልብ አይታመንም – 1
👍 7%

ሴቶችን አላምናቸውም – 1
👍 7%

የተለየ አስተያየት
▫️ 0%

👥 15 people voted so far.

Читать полностью…

Love - ፍቅር

👉ስለማህበራዊ ሚዲያ ስታስቡ በጣም የሚመቻችሁ ምኑ ነው?

👉👉 ማህበራዊ ሚዲያ በሀገርም በቤተሰብም ላይ ያሳጣን ነገር አለ?

እንወያይ። @LoveFkrLove 💬 🎤

Читать полностью…

Love - ፍቅር

#ለፍቅር_ግንኙነት ጠቃሚ ምክር።
1- የፍቅር ግንኙነት ለመጀመር በቂ ምክንያት ይኑርህ!
ወጣቶች በተለያየ ምክንያት የፍቅር ግንኙነት ይጀምራሉ:
👉በይሉኝታ
👉በጥቅም
👉በጓደኛ ተፅዕኖ
👉ልጅ ለመውለድ
👉በሃይማኖት ስም
👉በቤተሰብ ግፊት
👉ብቸኛ ላለመሆን
👉ማህበረሰብ ጫና
👉በማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ

ውድ የፍቅር ቤተሰቦች ፍቅር የምንጀምረው በፍቅር ምክንያት ካልሆነ የጋራ አላማ ከሌለን በስሜታዊነትና በሌሎች ጫና ፍቅርና ትዳር ውስጥ ከገባን ለመውጣት ወይንም ተደስቶ ለመኖር ብዙ እንቸገራለን። መፍትሂውስ ምንድነው?

ከላይ በተጠቀሱት ወይም በማይሆን ምክንያት የፍቅር ግንኙነት ከጀመራችሁ ብዙም ሳትርቁ ፊትለፊት ተነጋገሩበት። አንዱ ወገን ብቻ አስቦና ተብሰልስሎ የትም አይደረስም።

ነገር ግን ህይወት ጀምራችሁ ልጆች ተወልደው እየኖራችሁ ግዜ ካለፈ በኋላ ይህን ከተረዳችሁ ያለን አማራጭ ችግሩን ተረድቶ ተቻችሎ ለመኖር የበለጠ ጥረት ማድረግ ነው።
....ይቀጥላል።

Читать полностью…

Love - ፍቅር

ፍቅራችን ድንበር ሳይኖረው
      ዘር ቀለም ፍፁም ሳይለየው
      በኖረው አብሮነታችን
      እናብር ላንዷ ጎጆአችን
https://youtu.be/dRc4m0QOYAg

Читать полностью…

Love - ፍቅር

🙋‍♀ትናንት ስታዜመው የነበረ፣ ለዛሬ ያላደረ አስተሳሰብ አለህ?…

አይግረምህ!!.. ይልቅ ዛሬ የምታወግዘው ሃሳብ የነገ ተረኛ ቅኝትህ ሆኖ ሊከሰት እንደሚችል አስብ… በመኖር ውስጥ ወጥ የሚባል ቅኝት፣ የማይለወጥ የሚባል የማሰብ ፍኖት የለም… ‘ልክ’ ይመስለኝ ነበር ያልከውን መረጃ ‘ልክ እንዳልሆንክ’ ባሳየህ የዛሬ ክስተት ለመለወጥ ስትንደረደርም ሆነ ሽንጥህን ገትረህ የተሟገትክለት ሃሳብ ነገ ደርሶ ብን ሲልብህ ስታይ ውል አልባነት አይሰማህ

☮በሕላዌ ሕዋ ውስጥ ወዲህ ቢሉት ወዲያ የማይለወጥ አንድ ነገር እውነት ብቻ ነው… እውነት እውነትነቷ ነው ውበቷ - እውነት እውነት ትባል ዘንድ የድጋፍ ሰልፍ አትፈልግም… በራሷ የምትቆም ጽኑ ናት… የተከታዮቿ ማነስና መብዛት የእውነትነቷን ሞገስ አይነቀንቀውም… “The truth is like a lion; you don’t have to defend it. Let it loose; it will defend itself.” እንዲሉ... እስስት ሆኖ የሚዘልቀው ምን ይሆን ታዲያ?… መረዳትህ ነው… ግንዛቤህ… የእይታ አንፃርህ /Level of understanding/…

❤️የብዙ ውይይቶች ውጤት ጽንፍ ለጽንፍ በሚተያዩ ሃሳቦች መደምደም የየትኛውንም ወገን ትክክለኛነት አይናገርም… የማንኛውንም ስህትነትም አይገልጽም… የየወገኑን አንፃር እንጂ… ስለዚህ እንደኔ ካላሰብክ ብሎ ሙግት መግጠምም ሆነ የሌላውን ሌላነት የመግለጽ ነፃነት መጋፋት በደል ነው… የእውነት ተክለ ቁመና በአንፃራዊነት ባይዳኝም ታዳሚዎቿ ግን በየልካችን የምንሰፋው ‘እውነት’ ያለን መሆኑ እርግጥ ነው…

☯ፈጣሪ ሕይወትን ሳንሰለች እንዋብባት ዘንድ የተለያየ መነጽር እያቀበለን የእውነት ፀሐይ ከደመና ጥጥ ውስጥ ተፈልቅቃ ስትወጣ ያለውን ሂደት ጊዜ በሚሉት ሃዲድ ላይ ሆነን እንመለከታለን… ግና የገባን እንጂ ደርሶ የጨበጥነው እውነት የለንም!!!

🤍እና ምን ለማለት ነው… ‘ፍጹም እውነትን ይዘናል’ ከሚሉኝ ይልቅ ‘እውነትን እየፈለግን ነው’ በሚሉኝ ሰዎች ዙሪያ መገኘት ያስደስተኛል…

✍ ደምስ ሰይፉ

#ውብ_ምሽት
@Lovefkrlove
@lovefkr

Читать полностью…

Love - ፍቅር

☝️ከምንም በላይ አንዳችንን ከሌላኛችን የሚለየን ነገር ቢኖር ለራሳችን ያለን አመለካከት ወይም ምስል በእንግሊዘኛው ደግሞ "Self Image" ነው። ሁላችንም በዚህ አለም ላይ ስንኖር የኑሮዋችን መጠንና ልኩ የሚወሰነው ለራሳችን ባለን አመለካከት ወይም በአይምሮዋችን ውስጥ ስለራሳችን በምንቀርጸው ምስል ነው። ባህሪያቶቻችን፤ ውሳኔዎቻችን፤ አጋጣሚዎቻችንና በህይወታችን የምንስባቸው ሰዎች በሙሉ ለራሳችን ባለን አመለካከት ተጽዕኖ ስር ይወድቃሉ።

✌️ለራስ የሚሰጥ አመለካከት (self Image) በህይወታችን እጅግ ወሳኝ ነገር ነው። አንድ ሰው ስኬታማና ደስተኛ ሊሆን የሚችለው ለራሱ የተስተካከለና አወንታዊ አመለካከት ሲኖረው ብቻ ነው። ችግሩ ይህንን እውነታ ማንም ሰው ከልጅነታችን ጀምሮ ስለማያስተምረን አብዛኛዎቻችን ለራሳችን የተሳሳተ አመለካከት በመያዝ እናድጋለን። አቅምና ችሎታችንን የሚገድቡ እምነቶች "Self Limiting beliefs" ሳናውቀው በአይምሮዋችን ውስጥ ስር ይሰዳሉ። እኒህ አመለካከቶቻችን ናቸው የምንፈልገውን ኑሮ እንዳንኖር እንቅፋት የሚሆኑብን።

🤞ህይወታችንን ሊቀይሩ የሚችሉ እውነታዎች በሙሉ ቀላልና ያልተወሳሰቡ ሀሳቦች ናቸው። ምናልባት ለዛም ይሆናል በቁም ነገር ወስደን የማንተገብራቸው። እኛ ሰዎች በተፈጥሮዋችን የተወሳሰበና ከባድ ነገር ይበልጥ ተዓማኒነት ያለው ይመስለናል። ለችግሮቻችን መፍትሄ ስንፈልግ እንኳን ቀለል ያለ ሃሳብ አንቀበልም። እቃ ስንገዛ የተወደደው እቃ ሁሌም ከረከሰው የተሻለ ይመስለናል፤ በወረፋ ካልተሰለፍን በቀር የምናገኘው አገልግሎት ጥራት ያለው አይመስለንም።

🤟ተሻምተን ካላገኘናቸው በቀር ነጻ ለምናገኛቸው ነገሮች ዋጋ አንሰጥም። እራሳችንን ለመለወጥ ስናስብም እንደዛው፤ በቀላሉ አስተሳሰባችንን በመቀየር ህይወታችንን መቀየር እንደምንችል አምነን መቀበሉ ይከብደናል። ሰው አስተሳሰቡን በመቀየር ኑሮውን መቀየር እንደሚችል ለብዙ መቶ አመታት ሲንገር የነበረ ቢሆንም፤ እኛ ግን ይህን ለመረዳት አልፎም በቀላሉ ስራ ላይ ለማዋል አልቻልንም።

✊እያንዳንድችን ስለራሳችን በአይምሮዋችን የምንቀርጸው ምስል አለ። ይህ ምስል መልካም ምስል ካልሆነ በኑሮዋችን ላይ የሚጸባረቁት እውነታዎችም ከዚህ ምስል የተለዩ አይሆኑም። በተቃራኒው ስለራሳችን ያለን አመለካከት ወይም በውስጣችን የምንስለው ምስል መልካም፤ጠንካራና አወንታዊ ከሆነ፤ በኑሮዋችን ላይ የሚንጸባረቁት እውነታዎች በሙሉ የአወንታዊው አመለካከታችን ነጸብራቆች ይሆናሉ።

🙏ይህ ለራሳችን የምንሰጠው አመለካከትና ግምት ነው፤ በራሳችን ላይ የሚኖረንን እምነት የሚወስነው። በራስ መተማመናችን የሚበቅለው ለራሳችንን ባለን አመለካከት አፈር ላይ ነው።በትምህርትም ሆነ በስራ፤
በፍቅርም ሆነ በግል ህይወታችን ውስጥ የምናገኛቸው ውጤቶች ለራሳችን ካለን አመለካከት የሚመነጩ ናቸው።

ውብ አሁን🤍🖤
@lovefkrlove
@Lovefkr

Читать полностью…

Love - ፍቅር

  🥰የደስታ ሁሉ ምንጭ አእምሮ ነው ፣ የመከራ የሥቃይ ምንጭም ራሱ አእምሮ ነው ፡የአዕምሮአችንን ተፈጥሮ በጥልቅ ተረድተን ከተጠቀምበት እውነተኛ ደስታ እና የነፃነት ውጤት ማግኘት እንችላለን ፡፡

💚 ወዳጄ ሆይ አንድን ነገር ለመረዳት ስትፈልግ ያንን ነገር መውደድ ይኖርብሀል ፣ስትወደው ሕይወት ቀላል ይሆናል። ከዚያ ስሜት በሚነካ ሁኔታ ነገሮችን ማስተዋል እና መረዳት ትጀምራለህ።ሁሉንም ለመረዳት ግን መጀመርያ በልብህ ውስጥ ፍቅር ሊኖርህ ይገባል ፡፡

♦️ማንነትህን ጠንቅቀህ ስትረዳ ዋጋህን ታውቀዋለህ ።የምትኖርበትን እና የምትኖርለትን ትለያለህ ።ወደ አዚች ምድር የመጣኧው ለምክንያት ነው ። አንተ የዚህች አለም ገፅ ውብ እና ሙሉ ይሆን ዘንድ እንደ አንዱ ጡብ ነህ ።ዋጋህን ባለመኖርህ አትተምን በመኖርህ እንጂ።የአንተ መኖር ለሌሎቹ ጡቦች ድጋፍ እንዲሁም ለግንባታው ውበት አስፈላጊ ነው።

💛 ይህን ባስተዋልክ ጊዜ ራስህን ነፃ ታወጣለህ ፣ፍቅር ሲኖርህ ደግሞ የማንም ትዕዛዝ ሳያስፈልግህ የሰዎችን ሥቃይ የሚያስታግስ መንገድ ትፈጥራለህ።

ውብ ምሽት ፍቅሮችዬ❤️

@Lovefkrlove
@lovefkr

Читать полностью…

Love - ፍቅር

🥰🥰 #እስቲ_አፍቅሩ !

😘በምድር ላይ ያልባከነ ምርጥ ጊዜ ማለት በፍቅር ያሳለፋችኋቸው ደይቃዎች ናቸው … እስቲ አፍቅሩ …መልካችሁ ምንም ይሁን አፍቅሩ …እድሚያችሁ ምንም ይሁን አፍቅሩ … ኑሮ ቢከብዳችሁ ራሱ ኑሮ ከከበደው ጋር ተፋቀሩ …ፍቅር ተያይዞ ማደግ ብቻ አይደለም ተያይዞ መውደቅም ነው ! በጥላቻና በድርቅና ከመቆም ለፍቅር መውደቅ ተለማመዱ !

💜``አገር፣ህዝብ ፣ፖለቲካ በሚል ግዙፍ ነገር ውስጥ እየዳከራችሁ የጤፍ ቅንጣት አክላችሁ አትሙቱ … ፍቅር የሚባል እጅግ ረቂቅ አየር ወደውስጥ ሳቡና አገር አክሉ ! የማታፈቅሩበት አገር ምን ያደርግላችኋል? ገብስ ልታመርቱበት ነው? …የማታፈቀሩበት ህዝብ ምን ያደርግላችኋል ቀብራችሁን እንዲያደምቅ ነው …?የማታፈቅሩበት ፖለቲካ ምን ያደርግላችኋል? ፓርላማ ልተሰየሙበት ነው? …የማታፈቅሩበት ህገ መንግስት ምን ያደርግላችኋል ሲጀመር ይልተጣመራችሁትን መገንጠል እንዲፈቅድላችሁ ነው? …

❤️ተያዩ ተነጋገሩ ትዝብት ጥርጣሬ ፍርሃትን ወደዛ ጣሉና በፈገግታ በተሞላ ፊታችሁ የወደዳችኋትን ወደእናተ ሳቡ የወደድሽውን ወደራስሽ ጋብዥ ! ተቃቀፉ …አብራችሁ ቡና ጠጡ … ተደዋወሉ ‹ቴክስት› ተላላኩ ! በሚወዷችሁ ሰዎች እቅፍ ውስጥ ስጋችሁ ይድላው !ነፍሳችሁም ደስ ይበለው !ተሳሳሙ …ለመጨረሻ ጊዜ በፍቅር ከተሳማችሁ ስንት ቀን ስንት ወር ስንት ዓመት ሆናችሁ … ኪሳራ !

❤️ ህግ ስርዓትና አሉባልታ አትፍሩ …ደግሞ አትንቀዠቀዡ! ብቻ ማፍቀርም መፈቀርም ፈልጉ ..ራሳችሁን ብቻ ቀለል አድርጉት አየሩ ራሱ ወደየት እንደሚወስዳችሁ ያውቃል !…ለምርጫችሁ ብዙ መስፈርት አታስቀምጡለት ….ፈልጉ ተፈላለጉ ያለምንም ወሰን በነፍስም በስጋም ወደፍቅር ድንበር ቅረቡ ….ፀብ አትፍሩ መለያየት አያስጨንቃችሁ …ዘላለማዊ ጥላቻም ሆነ ጊዚያዊ ፍቅር ብሎ ነገር የለም ! አልፎ ሂያጅ ፍቅር የሚባል ነገር የለም ፍቅር ወደየትም አያልፍም …ፍቅር ራሱ መንገዱ ነው ! ተራመዱበት ፍጠኑበት …ብቻ አትቁሙ ! መንገድ ላይ በቆማችሁ ቁጥር ለሌላው እንቅፋት ትሆናላችሁ !

🤔ማህበረሰቡ የሰከነ... ረጋ ያለ... ቁም ነገር …ሁነኛ ሰው… የማይሆን ሰው…የሚሆን ሰው… እያለ ከጫነባችሁ የጉልት ሂሳብ ውጡና እብደታችሁ በሰፈረላችሁ ልክ ከዚህ ነዝናዛ አዕምሮ ተላቃችሁ በልባችሁ ደስታ ኑሩ ! ካለፈ ታሪካችሁ ውጡ …ካለፈ ህመማችሁ አገግሙ … በዘፈን ስም ሙሾ ከሚያስወርዱ ሙዚቃዎች ራቁ ….እንዴ…! …እንዳሰባችሁና እንደተመኛችሁ እስከመቸ ትኖራላችሁ ?! ባለፈ ጥላቻችሁ ከሬዲዮና ከምናምን በተለቃቀመ የመካካድና ተጎዳሁ ተሰበርኩ ታሪክ (ያውም እንደዛም ብለው ማፍቀር ላያቆሙ) በፍርሃት ተሸማቃችሀ ትኖራላችሁ እንዴ ?!

❤️አንዳንዴማ ልብሳችሁን ጣሉ …እራቁታችሁን መኖር ተለማመዱ …እራቁታችሁን ከሆናችሁ ልብስ አይኖራችሁም… ልብስ ከሌላችሁ ኪስ አይኖራችሁም ….ኪስ ከሌላችሁ በኪስ ከሚያዙ ነገሮች ሁሉ ነፃ ናችሁ … ምንም ነገር ልትይዙ የምትችሉት ብቸኛ ነገር ልባችሁ ብቻ ይሆናል … እንደልባችሁ ኑሩ ! የነፍሶቻችሁ ባሉን ላይ የተቋጠሩ ክሮችን ከራሳችሁ የፍርሃት እጅም ይሁን ከሌሎች ሰዎች የቁጥጥር እጅ ላይ አላቁና ወደሰፊው ህዋ ልቀቋቸው በአየሩ ላይ ይንሳፈፉ !

✍ #አሌክስ_አብርሃም

💚💛❤️ ውብ ቀን
@lovefkrlove
@lovefkr

Читать полностью…

Love - ፍቅር

#ለራሳችሁ_ዋጋ_ስጡ!

💥አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች እኛን በምን መልኩ እንደሚያስተናግዱን (Treat እንደሚያደርጉን) የምናስተምራቸውና የምንፈቅድላቸው እኛው ራሳችን ነን፡፡

🌆ራሳችንን ከናቅን ሰዎች እኛን ይንቁናል፣ ራሳችንን ስናከብር ደግሞ ያከብሩናል፡፡ ራሳችንን ርካሽ አድርገን ካሰብንና ልክ የትም መሄጃ እንደሌለው አይነት ሰው ሆነን ራሳችንን ካቀረብን ሰዎች እንደ ተራና የትም መሄጃ እንደሌለው ሰው ያስተናግዱናል፣ ለራሳችን ዋጋ ከሰጠን ደግሞ ዋጋ ይሰጡናል፡፡

🎈ሰዎች በምን መልኩ እየቀረቧችሁና እያስተናገዷችሁ እንዳሉ ተመልከቱትና ምናልባት በዚያ መልክ እንዲቀርቧችሁና እንዲያስተናግዷችሁ የፈቀዳችሁት እናንተው የመሆናችሁን ጉዳይም በዚያው ለመቃኘት ሞክሩ፡፡

🌙እናንተ ሳትፈቅዱላቸው ሰዎች ሊንቋችሁና በወረደ መልኩ ሊያስተናግዷችሁ አይችሉም፡፡ ከእናንተ ፈቃድ ውጪ በዚያ መልክ እንዳይቀርቧችሁ ማድረግ ባትችሉም ሁኔታው ልክ በማስያዝ ድርጊታቸው የመጀመሪያና የመጨረሻ እንዲሆን የማድረግ መብቱም ሆነ አቅሙ አላችም፡፡

ፈጣሪ ከሰጣችሁ “ሰውነት” በታች አትኑሩ!

✍ዶ/ር እዮብ ማሞ

#ውብ_አዳር_ይሁንልን
@lovefkrlove
@Lovefkr

Читать полностью…

Love - ፍቅር

✌️ #እርግጠኝነት!!!

💎በህይወታችሁ ውስጥ የሆነ ቀን፣ የሆነ ጊዜ፣ የሆነ ቦታ "... #እርግጠኛ ነኝ!" የሚል ሰው አጋጥሟችሁ ያውቃል? አዎን! ብዙዎቻችን አጋጥሞናል።

"ከእውቀት ጋር ጥርጣሬ ይጨምራል" ይባላል።

With knowledge doubt increases.

🕰ነገር ግን የምታውቀው ትንሽ ሲሆንና የህይወት ልምድህ ካልዳበረ በሁሉ ነገር "እርግጠኛ ነኝ" ትላለህ። በተለይ አንተ የምታውቀው ትንሽ ሆኖም በሌሎች ካልታወቀማ አይፈረድብህም! የህይወት ልምድህ ትንሽ ነውና ልኩ መንገድ፣ ልኩ ነገር እሱ ብቻ ይመስልሃል። ምን ይደረግ፣ ሌላ አላየህማ! አልበራልህማ!

💡1+1 = 10 የሚለውን ስህተት ነው ብለህ እርግጠኛ ሆነህ የምትደመድመው ስለ Binary Addition እስክትማር ነው። እውቀትና መረዳትህ ሲጨምር 1+1= 2 ወይም 1+1=10 ወይም 1+1 > 2 ወይም... ብለህ የምትቀበልባቸው ሁኔታዎች እንደሚኖሩ ይገባሃል። ካልሆነስ?

💎ካልሆነማ አንዱን የገባህን መንገድ ይዘህ ሙጭጭ ትላለህ። ያ ግን ልክ አይደለም። ሁሉንም መርምር፣ መልካሙን ግን ያዝ። ሳትፈትሽ ሙጭጭ አትበል።

Understanding opens the door of many possibilities.

💡እርግጠኝነት የእድገት፣ የመሻሻል፣ የአዲስ ነገር ጠላት ነው። "ነገ የሚሆነው ዛሬ ከሆነው አይለይም" ብሎ በእርግጠኝነት መናገርን የመሰለ የመሻሻል ጠላት የለም። ያላየኸውን የቅድመ-አያትህን ድምጽና እርምጃ እንዲህ ይመስል ነበር ብሎ በእርግጠኝነት መናገርን የመሰለ ውሸት የለም። የማላውቃቸውን የቅማያቶችን ብሔር በእርግጠኝነት መተንተንን የመሰለ በሽታ የለም።

💡ከሁሉ በላይ ግን የሰው ዘር አመጣጥ እንዲህ ነበር ብሎ በእርግጠኝነት መደምደምን የመሰለ ቅጥፈትና ቅዠት የለም!

💎ግዴለም! እርግጠኝነቱን እንተወው፣ ለጥርጣሬ ትንሽ ቦታ እንተው። ሁሉም ነገር ቋሚና የማይቀየር ሳይሆን ተለዋዋጭ እንደሆነ እንገምት።
jHH
❤️አሁን ያን ሁሉ የተደከመባት ሀገር እንዲህ ትሆናለች ብሎ ማን አሰበ? ያ ቤተሰብ እንዲህ እንደሚሆን ማን ገመተ? ይሄ ኢኮኖሚ እንዲህ እንደሚንፈራፈር ማን ጠረጠረ? ያ ዳይናስቲ እንዲህ እንደሚበተን ማን አሰበ? ግን ሁሉም ያልታሰበውና ያልተገመተው ሆነ።

አየህ የማይቀየረው እና ቋሚው ለውጥ ብቻ ነው።

ሌላውስ?
ሌላውማ እንደማይቀየር እርግጠኛ አይደለሁም።

"ማንም የቆመ ቢመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ" ተብሏልና!

✍Getu k. Toughe

# ውብ_አርብ❤️

@Lovefkrlove
@Lovefkr

Читать полностью…

Love - ፍቅር

#ወቅት_ያቀበለኝ_ስሜት......

👆ህይወት እንዲሁናት መሰለኝ.. ..።

👉ከእለታት አንድ ቀን ድንገት ከእንቅልፍህ ስትነቃ .....ሁሉም ነገር የሌለህ መስሎህ በሚሰማህ ጊዜ ሁሉን ነገርህን የምትሆንልህን እናትህን አጥተህ እራስህን ታገኘዋለህ.....ትኖራለህ።

👉ደሞ ሌላ ግዜ ድንገት ሁልግዜ የምትኮራበትን የምትመጻደቅበትን አባትህን ሞቶ እራስህን ታገኘዋለህ.....ትኖራለህ።

👉ደሞ እንደገና በመኖርህ ውስጥ ድንገት ስትነቃ ፍልቅልቅ ጨቅላ ልጆችህን አጥተህ እራስህን ታገኘዋለህ......አሁንም እየኖርክ ነው። ኑሮ እየቀጠለ ነው።

🤞አሁንም በምንቃትህ ውስጥ ደሞ ድንገት በህይወት መንሸራተት ወንድሞችህ ርቀውህ አጥተሃቸው እራስህን ታገኘዋለህ ........መኖር ቀጥሏል።

🤞......ደሞ ድንገት ስትነቃ እንዲሁ የወደድከውን ያፈቀርከውን አጥተህ እንደተለመደው እራስህን ታገኘዋለህ ......ህይወት እንደቀጠለች ነው። የማጣቱ ምክንያቱ....ተፅእኖው.....አይነቱ ይለያያል።

..... #ግን ግን ሁሉም ማጣትን መለየትን ያሸክሙሃል። ሌላ ግዜ ደሞ ድንገት ሸክምን ችሎ ለመኖር በልምምድ ውስጥ ሆነህ እራስህን ታገኘዋለህ .... ከተስፋ መቁረጥ ጋር ትንቅንቅ ገጥመህ። አንዳንዴ ለመኖር የምትፈተነውን
ያክል መኖር ለማቆምም ከባድ ፈተና መሆኑን ትረዳለህ። .
.
.
#ድንገት ደሞ ሌላ ግዜ ስትነቃ የትዕግስትህ መጠን አድጎ ....ቻይነትህ ጎልብቶ ....... ማስተዋልህ በዝቶ በህይወትህ ያገኘሃቸው ... የተደረጉልህ ......ያሉህ ነገሮች በህይወትህ ካጣሃቸው ....ካልተደረጉልህ .... ከሌሉህ ነገሮች እጅግ በጣም የበዙ መሆናቸውን ተገንዝበህ ፈጣሪን ስታመሰግን እራስህን ታገኘዋለህ ። .......
.
.
በጊዜው ድንገት በመንቃታቹ ውስጥ
በየትኛው ስሜት ውስጥ ሁናቹ እራሳቹን አገኛችሁት???

@Lovefkrlove
@Lovefkr
✍balmbaras

Читать полностью…

Love - ፍቅር

#ወዳጄ_ሆይ፡-

. . . መልካም ቀን ከጣፋጭ ቁርስ ትልቃለች
የሚያስደስትህን ስታደርግ . . .ሰዎች ባንተ ሲደሰቱ ስተይ . . .ስራህ ትርጉም ሲኖረው . . .ከሰዎች ጋር በፍቅር ስትመራ
ቀንህ ውብ እና ያማረ ይሆናል።
#ወዳጄ_ሆይ፡-

" የፍቅር መንገድ ዳር ዳሩ አበባ ሰላም እና ደስታ ከመሀል አስገባ"‼️ በፍቅር አለም ሚሰለች ነገር የለም . . .
ትናንትና. . .
ዛሬ . . .
ነገም . . .
ሁሉም ቀን አዲስ ብርሀንን ይዞ ይመጣል በሁሉም ብርሀን ውስጥ ፍቅር ካለ ሁሉም ቀናቶች የሰላም እና የደስታ ይሆናሉ፡፡
💚ወዳጄ ሆይ፡-

በህይወትህ ውስጥ መቼም ልታጣቸው ማይገቡ 3 ነገሮች . . .‼️
1. ፍቅር
2. ፍቅር
3. ፍቅር
. . . ፍቅር ካለ ሰላም አለ. . .ሰላም ካለ ጤና አለ. . . ጤና ካለ ደስታ አለ . . . እነዚህን ነገሮች ስታገኝ ህይወትህ ሙሉ ይሆናል። ግን ምንጩና መነሻው ፍቅር ነው።
💛ወዳጄ ሆይ፡-

ሁሉንም ነገር ተናግረህ ፣. . . ሁሉንም ነገር አዳምጠህ ፣. . . ሁሉንም ነገር አይተህ ፣. . . .ሁሉንም ነገር ጠይቀህ አትዘልቅም ፣ . . . ሁሉም ነገር የየራሱ የሆነ ሚስጥር አለው . . . የነገሮች ገፅታ ከቆምክበት ቦታ አንፃር ልዩነት ይፈጥራልና

❤️ወዳጄ ሆይ፡-

"ከክፋት ስትርቅ ሰላም ትሆናለህ። ለሰዎች መልካም ስታስብ ውስጥህ የተረጋጋ ይሆናል። በሰዎች ደስታ ስትደሰት ጤናማ አስተሳሰብን እየገነባህ ትመጣለህ። የዛኔ ውስጥህ ከጭንቀት እና ከፀፀት የፀዳ ይሆናል።"

🙏#መልካም_ምሽት🙏

@Lovefkrlove
@lovefkr

Читать полностью…

Love - ፍቅር

5 አይነት ግራ የሚያጋቡ አፍቃሪዎች

Читать полностью…

Love - ፍቅር

💬በህይወታችሁ ተስፋ ቆርጣችሁ ታውቃላችሁ?
💬አስቸጋሪ ነገር ሲገጥማችሁ ምን ታደርጋላችሁ? ፃፉልን።
🎙በድምፅ የምትልኩት በሰላም ካሳደረን በነገው ፖስት ይካተታል።

Читать полностью…

Love - ፍቅር

☝️በፍቅር ግንኙነት የወላጅ ድርሻ ምን ሊሆን ይገባል? እንወያይ 💬

Читать полностью…
Subscribe to a channel