thiqaheth | Unsorted

Telegram-канал thiqaheth - THIQAH

15262

ይህ ቲቃ (ታማኝ) ኢትዮጵያ የኢትዮጵያን ጨምሮ ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ መረጃዎች የሚቀርቡበት ገጽ ነው።

Subscribe to a channel

THIQAH

ተመድ በሊባኖስ በየቀኑ 19,000 ህፃናት እንደሚፈናቀሉ ገለጸ።

እስራኤል ከሄዝቦላህ ጋር የጀመረችው ጦርነት ለንፁሃን መፈናቀል ምክንያት መሆኑን በሊባኖስ የተመድ ህፃናት ቢሮ (UNICEF) ሀላፊ ማርኮሉጂ ኮርሲ ተናግረዋል።

ኮርሲ በስዊዘርላንድ ጄኔቫ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ባለፉት ሶስት ሳምንት ውስጥ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሊባኖስ ዜጎች ለመሰደድ ተገደዋል ብለዋል።

ከእነዚህም ውስጠሰ ከ370,000 በላይ የሚሆኑት ህፃናት መሆናቸውን ገልጸዋል።

በተጨማሪም 19,000 ወንዶች እና ሴቶች በየቀኑ እንደሚፈናቀሉ ኮርሲ በመግለጫቸው አብራርተዋል።   #trtworld

@EyobTikuye @ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

UAE የሆርሙዝ ሰርጥን ለማስከፈት በሚደረገው ወታደራዊ ዘመቻ እንደምትሳተፍ አስታወቀች።

የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በጦርነቱ ምክንያት የተዘጋውን ይህን ሰርጥ በሀይል ለማስከፈት አሜሪካ ያቀረበችውን ጥሪ ተቀላቅላለች።

ኢራን በአሜሪካ እና እስራኤል አማካኝነት ጥቃት በተፈፀመባት ወቅት ነበር የሆርሙዝ ሰርጥን ሙሉ በሙሉ የዘጋችው።

በዚህ ሰርጥ መዘጋት ምክንያት የነዳጅ ዋጋ ከፍተኛ ጭማሪ በማሳየቱና ስርጭቱ በማቆሙ የዓለም የሀይል ፍላጎት ላይ ተፅዕኖ ፈጥሯል።

በዚህ የነዳጅ ቀውስ ጫና የበዛባቸው ዶናልድ ትራምፕ የሀይል አማራጭን በመጠቀም ሆርሙዝን ለማስከፈት አለማቀፍ የትብብር ጥሪ ቢያቀርቡም በቂ ምላሽ አላገኙም። #apa

@EyobTikuye @ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

ሩሲያ ኢራንን በይፋ "ልታስታጥቅ" ነው ተባለ።

ሞስኮ ጦርነቱ ከተቀሰቀሰ በኋላ የድሮን እና የህክምና ድጋፍ መላኳ ተገልጿል።

ሩሲያ የአሜሪካ እና እስራኤል ጥምር ጥቃት ኢራን ላይ ከተጀመረ በኋላ ቀጥተኛ ተሳትፎ ባታደርግም አሁን ግን ከኢራን ባለስልጣናት ጋር መግባባት ላይ ተደርሷል ተብሏል።

ሩሲያ ስለ ጦር መሳሪያ እገዛ የሰጠችው ማብራሪያ ባይኖርም በአዘርባጃን በኩል ሰብዓዊ ድጋፍ ማድረጓን አረጋግጣለች።

አሜሪካ በጉዳዩ ላይ የሰጠችው መግለጫ ባይኖርም የምዕራባውያን ኢንተሊጀንስ መረጃዎች ግን ሩሲያ የኢራን ፖለቲካ ለማረጋጋት እጇን ማስገባቷ የማይቀር መሆኑን ገልጸዋል። #kyivpost

@EyobTikuye  @ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

የኢራን ጦርነትን ተከትሎ የምግብ ደህንነት ስጋት መጨመሩ ተገልጿል።

ሱዳን፣ ሶማሊያ፣ ታንዛኒያ እና ሞዛምቢክ በጦርነቱ የተጎዱ ቀዳሚ የአፍሪካ ሀገራት ሆነዋል ተብሏል።

ምክንያቱ ደግሞ ሀገራቱ ማዳበሪያ የሚያስገቡት በሆርሙዝ ሰርጥ በኩል  እንደሆነ ተገልጿል።

በተጨማሪም በዚሁ ጦርነት ሰበብ የተፈጥሮ ጋዝ ለማስገባት አለመቻላቸው ሌላኛው የሀገራቱ ችግር ሆኗል ነው የተባለው። #africanews

@EyobTikuye @ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

የሄዝቦላህ መሪ ናዒም ቃሲም "ከእስራኤል ጋር የሚደረግ ድርድር እጅ መስጠት ነው" ሲሉ ተቃወሙ።

በሊባኖስ የሚንቀሳቀሰው እና በኢራን የሚደገፈው ይህ ቡድን ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ ከእስራኤል ጋር ጦርነት ውስጥ ይገኛል።

እስራኤል በደቡባዊ ሊባኖስ የሚገኙ ነዋሪዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ባወጣችው ማሳሰቢያ መሰረት በሺዎች የሚቆጠሩ ተፈናቅለዋል።

የእስራኤል ጦር በበኩሉ፣ በደቡብ ሊባኖስ ተቆጥጠርኩ ባላቸው አካባቢዎች ላይ የደህንነት ዞን በመመስረት መስፈሩን አስታውቋል። #thekoreaherald

@EyobTikuye @ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

ፕሬዝዳንት ትራምፕ የኢራንን ጦርነት ለማስቆም ባለ 15 ነጥብ የስምምነት ዕቅድ አቀረቡ።

አሜሪካ እና እስራኤል ኢራን ላይ የጀመሩትን ጦርነት ለማስቆም ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የዲፕሎማሲ ጥረት ማድረግ መጀመራቸው ተገልጿል።

ትራምፕ ይህን የሰላም ዕቅድ ያቀረቡት በፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ሸባዝ ሸሪፍ አማካኝነት ነው ተብሏል።

ፓኪስታን አሜሪካ እና ኢራንን ለማሸማገል ዝግጁ መሆኗን በትናንትናው እለት አስታውቃለች።

ይሁን እንጅ ኢራን ባለ 15 ነጥቡን የሰላም እቅድ በተመለከተ እስካሁን የሰጠችው ማብራሪያ የለም። #ENA

@EyobTikuye  @ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

#ቪዲዮ፥ ኢራን የተከለከለ ቦምብ መጠቀም ጀመረች።

የኢራን ጦር በእስራኤል ላይ በዓለምአቀፍ ደረጃ ጥቅም ላይ እንዳይውል የተከለከለውን የክላስተር ቦምብ "መጠቀሙ" ተገልጿል።

ቦምቡ ከፍተኛ ሰብዓዊ ጉዳት እንደሚያደርስ በመረጋገጡ ነው እግድ የተጣለበት። #aljazeera

@EyobTikuye @ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

አሜሪካ ወደ መካከለኛው ምስራቅ ተጨማሪ ወታደሮችን ልትልክ መሆኑ ተሰማ።

ፕኤዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጦርነቱ ሊቆም እንደሚችል የሚያመላክቱ ንግግሮችን እያሰሙ ባለበት ወቅት፣ ፔንታጎን ወታደሮችን ለማሰማራት መወሰኑ ተገልጿል።

82ኛው የአሜሪካ አየር ሀይል ዲቪዥን አባላት ትዕዛዝ ተላልፎላቸዋል ተብሏል።

ለኢራኑ ጦርነት እንደ አዲስ የሚላኩት ወታደሮች ብዛት በትክክል ባይገለፅም፣ በሺዎች የሚቆጠሩ መሆናቸው ተመላክቷል።

ይህ እርምጃ አሜሪካ እና ኢራን ከኢራን ጋር የገቡበትን ጦርነት ሊያባብሰው ይችላል የሚል ስጋት አጭሯል።  #asiaone #reuters

@EyobTikuye @ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

#Ethiopia

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ30 ዓመት የሚከፈል የ184 ሚሊዮን ዶላር ብድር አጸደቀ።

ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው 12ኛው መደበኛ ስብሰባ፣ ከዓለም ባንክ ጋር የተደረገውን የ184 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የብድር ስምምነት በሙሉ ድምፅ አጽድቋል።

ብድሩ በተለይ ለከተማ ልማታዊ ሴፍትኔት እና ለሥራ ፈጠራ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የሚውል፤ ከወለድ ነፃ እና የስድስት ዓመት የችሮታ ጊዜን ጨምሮ በ30 ዓመታት ውስጥ የሚከፈል ነው ተብሏል።

የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ፣ ብድሩ ለሀገሪቱ ወጣቶች ሰፊ የሥራ ዕድል ለመፍጠር እና የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉን ለማጎልበት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብለዋል።

የምክር ቤት አባላት ብድሩ ለታለመለት ዓላማ መዋሉን ለማረጋገጥ "ጥብቅ" የክትትልና ቁጥጥር ሥራ ሊሰራ እንደሚገባ አሳስበዋል። #Capital

@EyobTikuye  @ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

በአሜሪካ የቫልናሮ ነዳጅ ማጣሪያ ላይ ፍንዳታ ተከሰተ።

በቴክሳስ ግዛት በሚገኘው በዚህ አደጋ ከፋብሪካው ከባድ ጭስ ሲወጣ ታይቷል።

የአደጋው ምክንያት እና የደረሰው የጉዳት መጠን አልተገለጸም ተብሏል።

ቫልናሮ የነዳጅ ማጣሪያ በቀን 435,000 በርሚል ነዳጅ የማጣራት አቅም አለው ተብሏል።

በስሩ 800 ሰራተኞች እንደሚገኙ ተገልጿል። #sana

@EyobTikuye @ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

"እሱ ነው ጦርነቱን እንጀምረው ያለኝ" - ትራምፕ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኢራንን ጦርነት የጀመሩት በሌሎች ሰዎች ተገፋፍተው መሆኑን ተናገሩ።

ለጦርነቱ የአሜሪካ መከላከያ ቢሮ ሀላፊ ፔት ሄግስቴ ተጠያቂ አድርገዋል። "ፔት ጦርነቱን በመደገፍ ያናገረኝ የመጀመሪያው ሰው ነው" ሲሉ ተናግረዋል።

ፕሬዚደንቱ "እሱ ነው ጦርነቱን እንጀምረው ያለኝ" ሲሉ ሄግስቴን ወንጅለዋል።

"ኢራን በአሜሪካና አጋሮቿ ላይ የተደቀነውን ስጋት ለማስወገድ አንድ እድል አላት" ያሉት ትራምፕ፣ "ያን ያደርጉታል ብየ አስባለሁ" በማለት ገልጸዋል።

ፕሬዝዳንቱ ኢራን አላት ያሉትን እድል ከመግለጽ ተቆጥበዋል። #newsam #rawstory

@EyobTikuye  @ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

የአሜሪካ ኢሚግሬሽን ፖሊሶች (ICE) በድጋሚ በአየር መንገዶች መሰማራት ጀመሩ።

ፖሊሶቹ የተሰማሩት የትራንስፖርት ደህንነት አስተዳደር (TSA) ድጋፍ ለማድረግ ነው ተብሏል።

በ13 አየር መንገዶች ውስጥ እንዲሰፍሩ ይደረጋል ሲል የአሜሪካ የሀገር ውስጥ ዲፓርትመንት (DHS) አስታውቋል።

አይሲኢ ስምሪት የጀመሩት በትራምፕ አስተዳደር እና የዲሞክራት አባል በሆኑ የኮንግረስ አባላት መካከል የበጀት ስምምነት ባለመደረሱ መሆኑን ተገልጿል።

የኢሚግሬሽን ፖሊሶች ከዚህ በፊት ሰነድ አልባ ስደተኞችን ለመያዝ በተደረገው ዘመቻ የሰብዓዊ መብት ጥሰት በመፈጸም ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሟቸዋል።   #anadoluagency

@EyobTikuye @ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

"ትራምፕ አደጋውን ፈርቷል" - ኢራን

ኢራን ዶናልድ ትራምፕን አስተያየት በመተቼት ውድቅ አድርጋለች።

ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከኢራን ባለስልጣናት ጋር "ውጤታማ ውይይት አድርገናል" በማለት ለአምስት ቀናት የሚዘልቅ የተኩስ አቁም ማወጃቸውን ገልጸዋል።

ይሁን እንጂ ስማቸው ያልተገለጸ አንድ ከፍተኛ የቴህራን ባለስልጣን፣ "ከትራምፕ ጋር የተደረገ ቀጥተኛም ይሁን ተዘዋዋሪ ውይይት የለም" በማለት የትራምፕን ሀሳብ ውድቅ አድርገውታል።

"በዓለም ገበያ ላይ የተከሰተው ውድቀት በአሜሪካ እና በአውሮፓ ላይ ፍርሃት ፈጥሯል" ሲሉም ተናግረዋል።

"ከጦርነቱ ጀምሮ ከአሸማጋዮች ለቴህራን ብዙ መልዕክቶች ይላኩ ነበር፤ ነገር ግን መልሳችን እራሳችንን እንከላከላለን የሚል ነበር" ነው ያሉት።

አክለው "ትራምፕ አደጋውን ፈርቷል" በማለት አዲሱን አስተያየት ተችተዋል።

እኚሁ ባለስልጣን "ትራምፕ የኢራንን የሀይል መሰረተ ልማት አወድማለሁ ካሉ በኋላ የሚደርስባቸውን የአጸፋ እርምጃ በመፍራት ከድርጊታቸው ተቆጥበዋል" ሲሉ ተናግረዋል። #apa

@EyobTikuye  @ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

ሁለቱም አብራሪዎች ህይወታቸው ሲያል፣ 41 ሰዎች ተጎዱ።

የኤይር ካናዳ እና የዩናይትድ ኤይላይንስ ፕሌን በኒዮርክ እርስበርስ ተጋጭተዋል።

በላጓርዲያ አውሮፕላን ማረፊያ በተከሰተው አደጋ 41 ሰዎች ተጎድተው ሆስፒታል መግባታቸውን የአየር መንገዱ አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ካትሪን ጋርሺያ ተናግረዋል።

አደጋው የተከሰተው አራት የበረራ ባለሙያዎችን እና 78 ሰዎችን የጫነው ኤይር ካናዳ በፍጥነት በመንቀሳቀስ ላይ እያለ መሆኑን ጠቁመዋል።

የአሜሪካ ፌደራል አቪየሺን (USFA) በጉዳዩ ዙሪያ ምርመራ መጀመሩን ገልፀዋል።  #theweek

@EyobTikuye @ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

#Ethiopia

"Ok" በረኪና ጥቅም ላይ እንዳይውል ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አሳሰበ።

"ኦኬ በረኪና "አስገዳጅ የኢትዮጵያ ደረጃ መስፈርትን የማያሟላና የጥራት ችግር" ያለበት መሆኑ ስለተረጋገጠ ህብረተሰቡ እንዳይጠቀም ሲል አሳስቧል።

በተደረገው የእይታ ፍትሻ በምርቱ ላይ የአምራች ስም፣ አድራሻና ብሄራዊ የደረጃ ምልክት የሌለው መሆኑን፣ አስገዳጅ የኢትዮጵያ ደረጃ መስፈርትን የማያሟላና የጥራት ችግር ያለበት መሆኑን ገልጿል።

በተደረገው የላቦራቶሪ የጥራት ፍተሸ ውጤት መሰረት "በStability እና Sodium hydroxide conent" አስገዳጅ የኢትዮጵያ ደረጃ "CES 234:2023" የደነገገውን የጥራት መስፈርት አላሟላም ብሏል።

በመሆኑም ህብረተሰቡ እንዳይጠቀም፣ ነጋዴ በገበያ ቦታ፣ በንግድ ሱቆች እና ሱፐር ማርኬቶች ውስጥ ምርቱን እንዳይሸጥ አሳስቦ፣ ሲሸጥ በተገኘ አካል እርምጃ እወስዳለሁ ብሏል።

@EyobTikuye @ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

"ሀሰተኛ ሚዲያዎችና ሌሎች ከሚያሰራጩት ዘገባ በቀር ድርድሩ ጥሩ ደረጃ ላይ ነው" - ትራምፕ

"ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄን አማራጭ ያደረጉት" ትራምፕ የተኩስ አቁሙን ወደ 10 ቀናት ከፍ አደረጉ ተባለ።

ትራምፕ በኢራን ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ለአምስት ቀናት እንዲቆሙ ያስተላለፉትን ትዕዛዝ ተጨማሪ አምስት ቀናት ጨምረውበታል ተብሏል።

ምንም እንኳን የኢራን ባለስልጣናት የተጀመረ ውይይት እንደሌለ ቢገልፁም፣ ትራምፕ ግን "ንግግሮች በጥሩ ሁኔታ ላይ ናቸው" ብለዋል።

ፕሬዚዳንቱ "የኢራን ባለስልጣናት ጦርነቱ ለሰባት ቀን እንዲቆም ጠይቀው ነበር" ሲሉ ተናግረዋል።

የኢራን ባለስልጣናት ድርድሩን በተመለከተ ስለሚሰጡት አስተያየት የተጠየቁት ትራምፕ "ሀሰተኛ ሚዲያዎችና ሌሎች ከሚያሰራጩት ዘገባ በቀር ድርድሩ ጥሩ ደረጃ ላይ ነው" በማለት አስተባብለዋል። #trtworld

@EyobTikuye  @ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

"ኢራን ቀጣዩ ጠቅላይ መሪ አድርጋ ልትሾመኝ ነበር፣ ግን እኔ ውድቅ አደረኩት" - ትራምፕ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አያቶላህ አሊ ኮሚኒን እንዲተኩ ጥያቄ ቀርቦላቸው እንደነበር አነጋገሪ ንግግር አድርገዋል።

"ቦታውን የተወሰኑ ወገኖች የሚፈልጉት ቢሆንም እኔ ግን አልፈልግም" ሲሉ ተደምጠዋል።

ትራምፕ በዋሽንግተን በተካሄደው የብሄራዊ የሪፐብሊካን የኮንግረስ ኮሜቴ (NRCC) ገቢ ማሰባሰቢያ መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር አሜሪካ እና እስራኤል የቀድሞውን የኢራን መሪ ኮሚኒን ለመግደል ያደረጉትን ዘመቻ "ስኬታማ" ብለዋል።

"የኢራን መሪ ከመሆን በላይ ያነሰ የመሪነት ስራ የለም" ሲሉ ተችተው፣ "ኢራን ቀጣዩ ጠቅላይ መሪ አድርጋ ልትሾመኝ ነበር፣ ግን እኔ ውድቅ አደረኩት" ነው ያሉት።

"የተወሰኑ ነገሮችን ሰምተናል፣ አንተን የኢራን መሪ ልናደርግህ እንፈልጋለን የሚል ጥያቄ ቢያቀርቡልኝም፣ አመሰግናለሁ ብዬ ትቸዋለሁ፣ አልፈልግም" ብለዋል ትራምፕ።

ከ1989 እስከ 2026 የኢራን መንፈሳዊ መሪ የነበሩት አያቶላሕ አሊ ኮሚኒ በእስራኤል እና አሜሪካ የመጀመሪያው ቀን ጥቃት መገደላቸው ይታወሳል።

ይህን ተከትሎ የኮሚኒ ሁለተኛ ልጅ የሆኑት ሞጅታባ ኮሚኒ በአባታቸው ቦታ ተተክተው የኢራን ጠቅላይ መሪ ሆነው ተሹመዋል።

ዶናልድ ትራምፕ የቬንዙዌላ ፕሬዚዳንት ኒኮላስ ማዱሮ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ ራሳቸውን ጊዚያዊ የቬንዙዌላ መሪ አድርገው መሾማቸው አይዘነጋም።  #thenewarab

@EyobTikuye  @ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

"ስምምነት እንድናደርግ እየለመኑን ነው" - ትራምፕ

ዶናልድ ትራምፕ የኢራን ተደራዳሪዎችን "እንግዳ" ሲሉ ገለጿቸው። የኢራን ተደራዳሪዎችን "ስምምነት እንድናደርግ እየለመኑን ነው" ብለዋል።

"ከመርፈዱ በፊት በስርዓቱ መነጋገር አለባቸው" ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

ትራምፕ ባለ 15 ነጥብ የሰላም እቅድ ያቀረቡ ሲሆን፣ ኢራን በበኩሏ፣ በእቅዶቹ ላይ አልተስማማችም ተብሏል። #anadoluagency

@EyobTikuye  @ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

"አሜሪካ ዶንባስን እንደሚመለስ ቃል ገብታልናለች" - ዘለንስኪ

የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮለድሚር ዘለንስኪ በሩሲያ ከተያዙት ግዛቶች የተወሰኑት እንደሚለቀቁ ገልጸዋል።

ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ "አሜሪኪ ለሰላም ስምምነቱ የደህንነት ዋስትና አቅርባልናለች" ብለዋል።

"የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት በትክክል በፕሬዚዳንት ትራምፕ ላይ ጫና ፈጥሯል" ሲሉ ተናግረዋል።

ፕሬዝዳንቱ "አሜሪካ ዶንባስን እንደሚመለስ ቃል ገብታልናለች" ብለዋል።

"እኔ የአሜሪካ ልዑካን እንዲያውቁልን የምፈልገው የምስራቁ የሀገራችን ክፍል የደህንነታችን ቁልፍ ጉዳይ መሆኑን ነው" በማለት ገልፀዋል።  #asiaone

@EyobTikuye @ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

ተመድ ኢራን በገልፍ ሀገራት ለፈጸመችው ጥቃት ካሳ እንድትከፍል ጠየቀ።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኢራን "በንጹሐን" ላይ እና "በነዳጅ ማመንጫ ጣቢያዎች" ላይ የምትፈጽመው ጥቃት ቀጠናዊ አለመረጋጋት ያስከትላል ሲል አስጠንቅቋል።

በተመድ የሚገኙት የኢራን አምባሳደር በበኩላቸው፣ በመካከለኛው ምሥራቅ ለተከሰተው ጦርነት አሜሪካ እና እስራኤልን ተጠያቂ አድርገዋል።

ከኢራን ተደጋጋሚ ጥቃት የደረሰባቸው ሀገራት በበኩላቸው፣ ጥቃቱ እንዲቆምላቸው ጥሪ አቅርበዋል። #thenewarab

@EyobTikuye @ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

ሞጅታባ ኮሚኒ ጦርነቱን ለማቆም ተስማሙ።

አዲሱ የኢራን ጠቅላይ መሪ ሞጅታባ ኮሚኒ የኢራን ጥቅሞች የሚከበሩ ከሆነ ለስምምነት ዝግጁ መሆናቸው ተገልጿል።

የኢራን ባለስልጣናት ንግግር እንዲጀምሩ "አረንጓዴ መብራት ሰጥተዋል" ሲሉ የእስራኤል ከፍተኛ ባለስልጣናት ተናግረዋል።

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ እና የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ በጉዳዩ ዙሪያ ቀጥተኛ ውይይት ማድረጋቸው ተገልጿል። #albawaba

@EyobTikuye @ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

ሩሲያ በዩክሬን ላይ ከባድ የአየር ላይ ጥቃት አደረሰች።

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 1,000 የሚጠጉ ድሮኖችን አስወንጭፋለች ተብሏል።

ይህም በአንድ ቀን ውስጥ የተፈጸመ ከባድ ጥቃት ሆኖ ተመዝግቧል። በዚህ ጥቃት ቢያንስ ስምንት ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ ተገልጿል።

ከዚህ በተጨማሪም በላቪቭ ከተማ የሚገኝ በዩኒስኮ የተመዘገበ ቅርስ ወድሟል ተብሏል። #france24

@EyobTikuye @ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

ፓኪስታን አሜሪካን እና ኢራንን ለማደራደር ዝግጁ መሆኗን አስታወቀች።

ኢስላማባድ ድርድሩን በቀጣይ ሳምንት ለማስጀመር ማሰቧ ተገልጿል።

ይሁን እንጂ ከሁለቱም ወገኖች ይሁንታንም ሆነ ነቀፌታን የተመለከተ የተሰጠ ምላሽ የለም።

ፓኪስታን ባሳለፍው አመት ግንቦት ለ12  ቀናት የቆውን የአሜሪካ፣ እስራኤል እና  ኢራን ጦርነት በሰላም ስምምነት አስቁሚያለሁ ላሉት ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሰላም ኖቤል እንዲሸለሙ እጩ አድርጋ መርጣለች።

በአንፃሩ ህንድ እና አፍጋኒስታንን ተጠያቂ በምታደርግበት የሽብር ጥቃት ተጋላጭ በመሆን በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎቿ ተገድለዋል። #timeslive

@EyobTikuye @ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

ፊሊፒንስ ያላት ነዳጅ ለ45 ቀናት ብቻ የሚሆን መሆኑ ተገለጸ።

የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት የአደጋ ጊዜ አዋጅ አውጀዋል።

ፕሬዚዳንት ፈርዲንድ ማርቆስ በመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ሳቢያ ሀገራቸው በሀይል አቅርቦት ችግር ውስጥ እንደገባች ተናግረዋል።

ፕሬዚዳንት ማርቆስ በሀገራቸው የነዳጅ አቅርቦት ላይ "የማይቀር አደጋ ገጥሞናል። በነዳጅ፣ ምግብ እና ህክምና ላይ ክትትል የሚያደርግ ኮሜቴ ተቋቁሟል" ብለዋል።

ፕሬዚዳንቱ "የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መንግስት የተጠናከረ እርምጃ ለመውሰድና የሀገር ኢኮኖሚን ለማረጋጋት ያግዛል" በማለት ገልጸዋል።

የፊሊፒንስ ኢነርጂ ቢሮ ሀላፊ ሻሮን ጋሪ አሁን ያላት የነዳጅ ብዛት ለ45 ቀናት ብቻ እንደሚያገለግል ተናግረዋል። #cna

@EyobTikuye @ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

#Update

በኮሎምቢያ በአውሮፕላን አደጋ የሟቾች ቁጥር 66 ደረሰ።

በአደጋው የተጎዱት 57 ወታደሮች ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል። የጠፉት አምስት ሰዎችን የማፈላለግ ስራው መቀጠሉን የኮሎምቢያ መከላከያ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ ገልጸዋል።

የሀገሪቱ ሄርኩሌስ ሲ-130 ወታደራዊ አውሮፕላን ከ120 በላይ የአየር ሀይል አባላት ጭኖ በረራ ከጀመረ ከደቂቃዎች በኋላ ተከስክሷል።

መንስዔው እስካሁን በትክክል ባይገለጽም አደጋው የተከሰተው አውሮፕላኑ ቦርድ ላይ የተፈጠረ ፍናዳታ ባስከተለው የእሳት ቃጠሎ መሆኑ ተነግሯል። #independent

@EyobTikuye @ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

#Colombia #Planecrash

በኮሎምቢያ በደረሰ የአውሮፕላን አደጋ ከ70 በላይ ሰዎች ሲጎዱ፣ 48 ያሉበት ሁኔታ አልታወቀም።

በደቡባዊ ኮሎምቢያ በወታደራዊ አውሮፕላኑ አደጋው የደሰረው 125 ሰዎችን አሳፍሮ የበረራ እንቅስቃሴ በጀመረ በደቂቃዎች ልዩነት ተከስክሶ ነው።

በዚህም ​የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ጉስታቮ ፔትሮ ባወጡት መግለጫ፣ ይህ ዘገባ እስከተዘጋጀበት ጊዜ ድረስ፣ 48 ተሳፋሪዎች ያሉበት ሁኔታ አልታወቀም፤ አንድ ሰው ሞቷል፣ 77 የሚሆኑት ደግሞ ተጎድተዋል።

ከ125 ተሳፋሪዎች መካከል 114ቱ ወታደሮች ሲሆኑ፣ 11ዱ ደግሞ የበረራ አካላት ናቸው። #Bbc

@EyobTikuye @ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

#US #VISA

ከመጋቢት 24/2018 ዓ/ም ጀምሮ ኢትዮጵያ የቪዛ ዋስትና የሙከራ መርሃ ግብር ውስጥ እንደምትካተት ኤምባሲው ገለጸ።

በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ አዲስ ማሳሰቢያ አውጥቷል።

ኤምባሲው ከመጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ/ም (ኤፕሪል 2/2026) ጀምሮ ኢትዮጵያ የቪዛ ዋስትና (Visa Bond) የሙከራ መርሃ ግብር ውስጥ እንደምትካተት አስታውቋል።

በዚሁ መሰረት ወደ አሜሪካ ለመጓዝ ለንግድ ወይም ለቱሪስት (B1/B2) ቪዛ ብቁ ሆነው የተገኙ አመልካቾች ቪዛው ከመሰጠቱ በፊት እስከ 15,000 የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ ዋስትና እንዲያስይዙ ይጠየቃሉ።

ተጓዦች የቪዛውን ደንቦች በሙሉ አክብረው ከተገኙና የተፈቀደላቸው የቆይታ ጊዜ ሳያበቃ ከአሜሪካ ከተመለሱ ያስያዙት የዋስትና ገንዘብ እንደሚመለስላቸው አመላክቷል።

ይህ መስፈርት ከመጋቢት 24 ቀን በፊት የተሰጠ ሕጋዊ የንግድ ወይም የቱሪስት (B1/B2) ቪዛ ያላቸውን ሰዎች አይመለከትም ብሏል።  #usembassyaddisababa

@EyobTikuye @ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

"አሜሪካ በኢራን ላይ የምትፈጽመውን ጥቃት ለአምስት ቀናት ታቆማለች" ፕሬዚዳንት ትራምፕ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኢራን ጦርነት "ሊቀር" እንደሚችል ጠቁመዋል።

ከኢራን ባለስልጣናት ጋር መነጋገራቸውን የገለጹት ፕሬዚደንቱ ለኢራን የሰጡት የ48 ሰዓት የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ 24 ከሞላው በኋላ አቋማቸውን ቀይረዋል።

ትራምፕ በኢራን የሀይል መሰረተ ልማት ላይ ሊፈፅሙት ያሰቡትን ጥቃት እንዲቀር ወስነዋል ተብሏል።

በግል የትሩዝ ሶሻል ገፃቸው ላይ "የጦር ዲፓርትመንቱ ወታደራዊ ጥቃቶችን እንዲያቆም ትዕዛዝ አስተላልፊያለሁ" ብለዋል።

"አሜሪካ በኢራን ላይ የምትፈጽመውን ጥቃት ለአምስት ቀናት ታቆማለች" በማለት አስፍረዋል።

ትራምፕ "ከኢራን ባለስልጣናት ጋር ቀጣይነት ያለው ስብሰባ እያደረግን ነው" በማለት ገልጸዋል።  

አዲሱ የፕሬዝዳንቱ ውሳኔ የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ሊያቆም እንደሚችል ተስፋ የሰጠ ሆኗል። #thenewarab

@EyobTikuye @ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

የ75 ሀገራት ዜጎች በአዘርባጃን በኩል ከኢራን እንዲወጡ ተደረገ።

በዚህም 2,921 ሰዎች በአሁኑ ወቅት አዘርባጃን መግባታቸው ተገልጿል።

ከእነዚህም መካከል ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው 722 የቻይና ዜጎች ሲሆኑ፣ 58 ኢራናውያን፣ 11 የአሜሪካ ዜጎች ይገኙበታል። ከኢራን የወጡት ኢራናውያኑ ሁለት ዜጎነት ያላቸው ናቸው። #apa

@EyobTikuye @ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

ሄዝቦላህ በእስራኤል ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ 61 ጥቃቶችን ፈጸመ።

ይህም በአንድ ቀን የተፈጸመ ከፍተኛ ጥቃት ሆኖ ተመዝግቧል።

በኢራን የሚደገፈው የሊባኖስ ታጣቂ ቡድን በዚህ ጥቃቱ የእስራኤልን ወታደራዊ ስፍራዎች ኢላማ ማድረጉ ተገልጿል።

የእስራኤል ጦር አባላትን፣ ወታደራዊ ቁሳቁሶችን፣ መሰረተ ልማቶችን እና የድንበር ስፍራዎችን አጥቅቷል ተብሏል።

ቡድኑ አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ የሚያደርሱትን ጥቃት ካላቆሙ እርምጃ መውሰዱን እንደሚቀጥል አስጠንቅቋል።  #parstoday

@EyobTikuye @ThiqahEth

Читать полностью…
Subscribe to a channel