abduftsemier | Unsorted

Telegram-канал abduftsemier - Abdu & Hasu

6302

Abdulhak & Hasenet <የኢቅራእ ቢስሚ ረቢከ /አንብብ በጌታህ ስም/ ትውልዶች እንጂ ፣ የኢቅራእ /የአንብብ / ትውልዶች አይደለንም።> የምንኖረውም: የምንሰራውም : የምናነበውም ለአላህ ነው። አላህ ያወቅነውን የምናሳውቅ ፣ ባወቅነው ደግሞ የምንጠቀም ያድርገን። አሚን!! For any comment ⇄ @ABDU_EMRE

Subscribe to a channel

Abdu & Hasu

መውሊድ #ይፈቀዳል ወይስ #አይፈቀድም የሚለውን በማስረጃ በማስደገፍ ከሁለቱም ወገን ኡስታዞችን በመያዝ ትልቅ የውይይት ቻናል ከፍተናል እናንተም ተቀላቅለው ክርክሩን በቀጥታ ይመልከቱ ♻️


🚫ማስታወቂያው ከ30 ደቂቃ በኋላ ስለሚጠፋ ቶሎ Join በሉ🚫

Читать полностью…

Abdu & Hasu

✅የተለያዩ #ኪታቦችን ደርስ በቤትዎ ሆነው በAudio የሚያደርስ ምርጥ ቻናል ይዤላችሁ መጥቻለሁ❤️

🔰ወላሂ የውሸት ማስታወቂያ አይደለም🔰

🚫ከ3⃣0⃣ ደቂቃ በኋላ ይጠፋል❗️

Читать полностью…

Abdu & Hasu

አግብታችኋል❓❓❓


For wave፦@Al_Meliku

Читать полностью…

Abdu & Hasu

💔ከተከፋችሁ ፣ ህይወት ካስጠላችሁ ኢሆ ቻናል ለናንተ ነው የተከፈተው💔
😔 ተቀላቀሉን 😔

Читать полностью…

Abdu & Hasu

እኔ ምልሽ እህቴ ወክቱ #ክረምት ነው ለምን በቤትሽ ቁጭ ብለሽ ቁርአንን በ3ወር ብቻ ሙሉ 30 ጁዝ ቁርን በጭንቅላትሽ "መሃፈዝ" ትፈልጊያለሽ? ሌላው ምርጥ አስገራሚ ደሰስስስ የሚሉ አጫጭር ምክሮች ደእዋዎችን ታሪኮች ኢስላሚክ ቻናል ተፈልገለሽ...?እንግድያውንስ እድለኛ ነሽ አሁኑኑ join በይ

JOIN የምትለዋን ብቻ ይጫኚ!! ወደ ኸይር መንገድ እንጣራ!!

Читать полностью…

Abdu & Hasu

አይ ማማር
አይ ውበት
አይ ግዜ
አይ ዘመን....
ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን

''They bared their brains to heaven..'' ይላል allen የታላላቆቹን ሞት ማለፍ ከሰማ በኋላ!

የታላላቆቹ ማለፍ ምድር ላይ ለቀሩ ዋይታ
ለሰማይ ደግሞ ደስ የሚል ፈገግታ እንደሚሆን ጥርጥር የለውም።
ሚቀበሏቸውን ፣ ሚገናኟቸውን ማሰብ አካሄዳቸውን መከተል ያስመኛል።
እጆቻቸውን ይዞ ወደ ሚሄዱበት አብሮ መጎዝ...
ወደዛ ደስ ወደሚሉት ሰዎች...

የታላላቆቹ ማለፍ ታላቅ ሀዘን ብቻ ሳይሆን የሚጥልብን እነሱን የመከተል ፣ እነሱን የመፈለግ መሪር ናፍቆት ያሸክመናል።
ደጋጎቹ ሁሉ ጥለውን አንዲት ትንሽ ቦታ ይበሰባሉ።
እዚህ የኖሩትን ተሰብስበው ይደግሙታል።
ዘላለም የሚያምር ነገር መስራት አይደክማቸው እነሱ እንደሆነ...

እንደ ሰይዲ ሚቅባስ ያሉ ሰዎች በሰማይ እና በምድር መሀከል ያለውን ወግ የሚያገናኙ ድልድዮች ነበሩ።
ከእንግዲህ ስለ ትናንትና ማን ይነግረናል?
ስለ ደጋጎቹ ሰዎች ማን ያጫውተናል?

በህይወት ያሉት በአለፉት ይቀናሉ! ማለት ይሄ ነው።

😭 ላንቱ ሳይሆን ለራሴ ነው የማለቅሰው፤ ላንቱ እረፍት ለኔ ምሬት፤ ከእንግዲህ ሀበሻ ላይ የሚሆነው ነገር ያስጭንቀኛል... አላህዬ ተካልን😭

    የታላቆች ልጅ ታላቅ ስብዕና፤
ሰይዲ ሚቅባስ የመድሁ መውላና፤
ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ሀገሩን ያቀና፤
በቀጣይ ሀገር ያስደሳችሁ አላሁ ረበና።

@abduftsemier
@abduftsemier

Читать полностью…

Abdu & Hasu

ቁርአንን የተመለከተ አጭር መረጃ
'''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''
=> ቁርአን የወረደው ለ23አመታት ነዉ።
=> ቁርአን በመካ ዉስጥ ለ13 አመታትወርዷል።
=> ለቁርአን መዲና ዉስጥ ለ10 ለአመታትወርዷል።
=> የቁርአን ክፍሎች(ጅዞች) 30 ናቸው።
=> የቁርአን ሂዝብ 60 ናቸው።
=> የቁርአን ምዕራፎች (ሱራዋች) 114ናቸው።
=> የቁርአን"ሩቡዕ" 240 ናቸው።
=> የቁርአን ስሞች ብዛት 77439 ናቸው።
=> የቁርአን አንቀፅ ብዛት 6236 ናቸው።
=> የቁርአን ፊደላት ብዛት 321250 ናቸው።
=> ከቁርአን ውስት ታላቁ ምዕራፍ (ሱራ)ሱረቱል አል-ፋቲሀ።
=> ከቁርአን ዉስጥ ትልቁ አንቀፅ (አያህ)አያተል አል-ኩርሲ።
=> ቁርአን ውስጥ ረጅሙ ምዕራፍ (ሱራ)ሱረቱል አል-በቀራ ።
=> ረጅሙ የቁርአን አንቀፅ "አያተል ደይን"ሱረቱል አል በቀራ አንቀፅ 282 ነው።
=> ቁርአን ውስጥ ረጅሙ ቃል"ፈአስቀይናሙሁ"የሚለው ነው።
=> ቁርአን አጭሩ ቃል "ጣሃ"የሚለው ነው።
=> የቁረአን ሲሶ የሆነውቃል ሱረቱል አል-ኢህላስ(ቁል ሁ ወላሁ አሃድ)ነው።
=> የቁርአን ቀልብ ነው ተብሎ የተነገረለት ሰራ(ሱረቱል ያሲን)ነው።
=> የቁራን ሙሽራ ነው ተብሎ የተነገረለት ሱራ(ሱረቱል -አል -አረህማን)ነው።

*አልሀምዱሊላህ *ስርዝ ድልዝ የሌለበትን ቁርአንን ለለገሰን አላህሱ•ወልናመሰግን ይገባል።

አላህ ሱ• ወ ቁርአንን እሱ እንዳወረደው እሱ እንደሚጠብቀው ተናግሯል።

ሰደቀላሁል ዐዚም
@abduftsemier
@abduftsemier

Читать полностью…

Abdu & Hasu

#የነቢዩ_ﷺ_ብርሃን

አሏህ (ሱ.ወ) የነብዩን (ሰ.ዐ.ወ) የፈጠረው ከፍጥረት ሳይሆን ከስሙ “አን-ኑር” ነው። “አን-ኑር” ከሚለው ቃል የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እና የፍጥረት ምስጢር ነው። ለነብዩ (ሶ.ዐ.ወ) እንደ ቃል ወይም ምንነት ታየ፣ ከዚያም ሌሎች ውብ ስሞችና ባህሪያት ሁሉ መጀመሪያና ፍጻሜ ሳይኖራቸው ተራ በተራ ተገለጡ። አላህ (ሱ.ወ) በሰጣቸው ብርሃን ነብዩ (ሶ.ዐ.ወ) የነዚህን ሁሉ ውብ ስሞችና ባህሪያት ሚስጢር ለማየት ችለዋል እና ኡማቸውን አልብሰውላቸዋል። የአውሊያን እና የሊቃውንቱን ብርሀን እንደ አቅማቸው ሰጣቸው። ሰዎች እነዚህን ምስጢሮች እንዲያዩ እንዲመሩ እና እንዲረዳቸው የአላህ ወሊዮች ተሰጥቷቸዋል፣ መደበኛ ሰው ደግሞ አቅሙ ስለሚቀንስ ትንሽ ተሰጥቷል።
በቂያማ ቀን የአላህን (ሱ.ወ) ውብ ስሞች እንደ ብርሃን የለበሱት! የነብዩ (ሶ.ዐ.ወ) ወዳጆችና ተከታዮች በመባል ይታወቃሉ አላህም (ሱ.ወ) ሲያያቸው ያውቃቸዋል።

@abduftsemier
@abduftsemier

Читать полностью…

Abdu & Hasu

#የአይኔ_ማረፊያዬ_ጁነይድ

ከኢማም ጁነይድ ደቀ መዛሙርት አንዱ በሼይኹ አልተደሰተም ነበር፤ ከመድረሻው ላይ መድረሱን በማሰብ ጥሎቸው ሄደ ይባላል። አንድ ቀን ሸይኹን ለመፈተን ተመለሰ። ኢማም ጁነይድ ረዲየላሁ ዐንሁ በልቦናው ያለውን ያውቁ ነበር። ኢማም ጁነይድ ረዲየላሁ ዐንሁ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፡- “መደበኛ ወይስ መንፈሳዊ መልስ ትፈልጋለህ?” እሱም “ሁለቱንም እፈልጋለሁ” አለ።
ኢማሙ ጁነይድ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ብለዋል፡- “የትኛውም ደረጃ ላይ ብትደርስ ኖሮ ልትፈትነኝ ባልመጣህ ነበር። መደበኛው መልስ ይህ ነው። መንፈሳዊው መልስ፦ ከዊላያ ( ቅዱሳን) ጓራ አባርሬሀለሁ የሚል ነበር። ይህን እንደተናገሩ ደረሳው ፊቱ ወደ ጥቁር ተለወጠና፡- “ጌታ ሆይ! ይቅርታ፣ የነበረኝን የኢማን (የእምነት) ጣፋጭነት አጣሁ። በደግነት ይቅር በሉኝ" ሲል ለመነ፤ ኢማሙ ጁነይድ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ብለዋል፡- “የአላህ አውሊያዎች የአላህ ፀጋዎች ጠባቂ መሆናቸውንና የነሱን ብስጭት መሸከም እንደማትችል ረስተሃል። በዚህም መሰረት በሙሪዱ ላይ ተነፈሱበት እና የጠፋውን ሁሉ ወዲያውኑ መልሶ አገኘ፤ ለሞኝነቱ በእጅጉ ተጸጸተ።

@abduftsemier
@abduftsemier

Читать полностью…

Abdu & Hasu

#እድለኛው_ዑማ

ነብዩ ሰዐወ ሚእራጅ በወጡ ጊዜ ብርሀናቸው እንደ ከዋክብት የሆኑ ሰዎችን ተመለከቱ። ለጅብሪል (አ.ሰ) እነዚህ ሰዎች እነማን ናቸው? ብለው ጠየቁት። "እነዚህማ ከዑመትህ የሆኑ ሐበሾች ናቸው።" ብሎ መለሰላቸው። "አላህ ሆይ እርዳቸው" ብለው ዱኣ አደረጉ። ሁሉም ምንጫቸው ከታላቁ ሰው ሰይዲና ወመውላና ሸኽ ዳኒ ነው።
ከዚህ በተጨማሪ የሸኽ ሙሀመድ አሚን ልጅ ሰይድ መህዲ አንደነገሩኝ። "ነብዩ ሰዐወ ከሰማይ ጉዳያቸውን ጨርሰው ሲመለሱ ሶስት የኑር ብርሀኖች (አንደኛው እንደ ግመል የሆነ፣ 2ኛው እንደ ላም፣ 3ኛው እንደ በግ የሆነ) አብሯቸው ወረደ። እንደ ግመል የሆነው ትልቁ በሂጃዝ (ሳኡዲ አረቢያ) ላይ ሲያርፍ፤ ላም የመሰለው ሞቃዲሾ (ሶማሊያ) ላይ አረፈ፤ እንደ በግ ያለው በሐበሻ መሀከል የጁ በተባለ ቦታ አርፏል። ለዚህም ነው ሐበሻ የተለያዩ የአስገራሚዎች አስገራሚ የሆኑ ጉዳዮች የተከሰቱባት ሀገር የሆነችው።

የወለኔ ሼኽ ጥሮነ መፀሀፍ (ገፅ: 25-26)

*አላሁመ ሷሊ አላ ሰይዲና ሙሀመድ ኢማሙል አንቢያእ፤ ወአላ አሊ ሰይዲና ሙሀመድ ኢማሙል አውሊያእ።

@abduftsemier
@abduftsemier

Читать полностью…

Abdu & Hasu

"በጣም አስቸጋሪ ጊዜ ነው። ሙስሊሞች የእስልምና ፍቅርን በቤታቸው፣ በአካባቢያቸው እና ከጎረቤቶቻቸው ጋር መኖር እንዳለባቸው ማወቅ አለባቸው። ያለበለዚያ አደጋ ውስጥ እንገባለን። አላህ እስልምናን ጠበቀው ማንም ሊጨምርበትም ሆነ ሊቀንስበት አይችልም። ሙስሊሞች አደጋ ላይ ሊወድቁ ይችላሉ፣ እና ስለዚህ ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው። እኛ እዚህ የመጣነው በኢስላማዊ መንግስት ለመኖር አይደለም። በሰላም ለመኖር፣ ለመስራት፣ ልጆቻችንን ኢስላማዊ መንገድ ለማሳደግ እና አዲስ ትውልድ ለማፍራት ነው የመጣነው። ከዚያ በላይ ከፈለግን ችግር ውስጥ እንገባለን።

"በዱንያ ስትኖር በመልካም ሁኔታ ተናኖር።" ነብዩ ሰዐወ

@abduftsemier
@abduftsemier

Читать полностью…

Abdu & Hasu

😳ቴሌግራም ልክ እንደ ቲክቶክ ብዙዎችን ባለሀብት እያደረገ ነው። 🤩

5,000 Star = 10 (80$+)TON 🔥🔥🔥

ቴሌግራም የቲክቶክን ፈለግ በመከተል አዲስ Telegram Stars የተሰኘ Gift Coin አምጥቷል።

ከስር የተቀመጠውን ሊንክ ተጭናቹ ስታርት ስትሉት የሚሰሩ task አሉ ስራውን ስትሰሩት ከ 5,000+ star በቀላሉ ታገኛላቹ። 

1 invite ስታደርጉ 75 Star ማግኘት ትችላላችሁ

አሁኑኑ ከስር ያለውን ሊንክ በመንካት Start በማለት ስራውን ይጀምሩት👇👇👇

/channel/major/start?startapp=1122916146

Читать полностью…

Abdu & Hasu

#በሙሀረምና_በአሹራ_ምን?

1. "ከኢብኑ አባስ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደተላለፈው ነብዩ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- “የዙልሂጃህን የመጨረሻ ቀን እና የሙሀረምን የመጀመሪያ ቀን የፆመ ሰው የሃምሳ ዓመታት ወንጀሉ ይማራል።

2. ከአነስ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደተላለፈው ነብዩ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- “የሙሀረምን የመጀመሪያ ጁምዓ የፆመ አላህ የቀደመ ወንጀሎቹን ይማርለታል፣ የሙሀረምን ሶስት ቀን የፆም ሰው አላህ እያንዳንዱ የመልካም ስራ ምንዳውን በዘጠኝ መቶ ያባዛለታል።

3. ከአኢሻህ ኡሙል ሙእሚኒን (ረዐ) እንደተላለፈው ነብዩ (ሶ.ዐ.ወ)። “እስከ ዐሹራ ድረስ የመጀመሪያዎቹን አስር የሙሀረም ቀናት የጾመ ሰው ጀነት አል-ፍርዶስ ይወርሳል።"

4. የዐሹራ ጾም ሱና ነው ሙአከዳህ በጣም ተፈላጊ ነው። ነብዩ (ሶ.ዐ.ወ) የመዲና አይሁዶች በእለቱ ሲጾሙ ባዩ ጊዜ ምን እንደሆነ ጠየቆቸው። ሙሳ በኒ ኢስራኢል ከፈርዖን እጅ የመራቸው ቀን እንደሆነ ነገሮቸው። ነብዩ (ሶ.ዐ.ወ) “ከእናንተ አይሁዶች የበለጠ በሙሳ ላይ መብት አለኝ” አሉ። ያን ቀንም ጾሞ እንዲፆምም አዘዙ። ይህ ከዓኢሻ (ረዐ) የረዘመ ዘገባ አካል ነበር።

5. ነብዩ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- “የዐሹራን (10ኛውን ሙሀረም) የፆመ ሰው አላህ አንድ ሺህ ወንጀል ይሰርዝለታል አንድ ሺህ ምንዳ ይፅፍለታል፣ የሺህ ሸሂድንም ምንዳ ይሰጠውል፣ በጀነትም ውስጥ ሰባ ቤተ መንግሥቶችን ይገነባለታል፣ አካሉንም ከጀሀነም እሳት እርም ያደርገዋል።

6. በሌላ ሀዲስ ነብዩ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹አሹራን የፆመ ሰው የሺህ መላኢኮች ምንዳ ይሰጠዋል ። በዐሹራ ቀንም ‹ቁል ሁዋ አሏሁ አሀድ›ን ሺ ጊዜ ያነበበ ሰው አላህ በእዝነት አይኖች ያየውና ከሲዲቂን (ከእውነተኞቹ) አድርጎ ይፅፈዋል።

7. በሌላ ሀዲስ ነብዩ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- “ከአሹራ በፊት ያለውን ወይም ከዚያ በኋላ ያለውን ቀን በመፆም ከአይሁዶች ተለዩ።"

8. በዐሹራ ቀን አራት ሱና ረከአት የሰገደ ሰው ከፋቲሐ በኋላ በእያንዳንዱ ረከዓ ‹ቁል ሁዋ አሏሁ አሀድ› አስራ አንድ ጊዜ ያነበበ አላህ የሃምሳ አመት ወንጀሉን ይማርለታል። በዐሹራ ቀን የሱና ሻወር ያወሰደ ሰው በዚያ አመት ከሞት ህመም በስተቀር አይታመምም እና ኩህልን በአሹራ ቀን አይኑን የተቀባ ሰው በዚያ አመት ህመም አይሰማውም።

9. የአሹራ ዱዓ፡-
“ሀስቡን አላሁ ወኒመል ወኪል፣ ኒእመል መውላ ወኒእማን ነሲር” [70 x]፣

“ሀስቡን አሏህ መለአል ሚዛን ወሙንታሀል ኢልም፣ ወመብለገል ሪዳ፣ ወዚነተል አርሽ፣ ላ መልጃአ ወላ መንጃ ሚነሏህ ኢላ ኢለይህ። ሱብሀን አሏህ 'አደደ- ሸፍኢ ወል አርሺ፣ ወአደደ ከሊማቲ ረቢና- ታማቲ ኩሊሀ። አስዓሉከ ሰላመ ቢራህማቲከ ያ አርሃመ ራሂሚን፣ ወላ ሀውላ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላሂል አሊይል አዚም ወሁወ ሀስቢየላህ ወኒእምል ወኪል፣ ኒዕማል መውላ ወኒእማን ነሲር። ወሰለሏሁ ዐላ ሰይዲና ሙሐመዲን ወአላ አሊሂ ወሷቢሂ አጅመዒን። [7x]

@abduftsemier
@abduftsemier

Читать полностью…

Abdu & Hasu

📍ከፍቶሀል ሀቢቢ?🥺💔🙇‍♂

         አንቺስ ከፍቶሻል ኡህቲ?🙇‍♀🥺💔

👌 ቀናቹን ፍክት የሚያረጉ 😍😍😍

💖ስሜታቹን የሚቀይሩ ምርጥ ቻናሎችን ተቀላቀሉ ስሜታቹ ይቀየራል ❣️❣️❣️❣️

🔰 ሊያመልጥ የማይገባ ቻናሎች ናቸዉ❗️

Читать полностью…

Abdu & Hasu

📌📌📌📌📌📌📌
Telegram Premium የምትፈልጉ በቅናሽ


🚩6 months ዋጋ =2500
⭐️12 months ዋጋ =3500
Bezih anagrugn 🌐 @fuye00

ዋጋ ሳንጨምር እድሉን ተጠቀሙበት📌👍

Читать полностью…

Abdu & Hasu

ÄŠĒŁÄMÛ ÅĹËŸĶŰM WĖŘÊHMÊŤŮĻŁÁHÏ WĖBĒŘÊĶĀŤÛH


እነሆ ኢስላማዊ አስተማሪ እንዲሁም አስፈላጊ የሆኑ ቻናሎችን ይዘን ብቅ ብለናል።
ቁርኣንን በተለያዩ ቃሪእ
አንዳንድ የ ጋዛን መረጃ
ለሽልማት እንዲሁም ለ እውቀት የተዘጋጁ ጥያቄ ና መልሶች
ኢስላማዊ ቀልዶች
ኢስላማዊ ትምህርቶችን በ አማርኛ እንዲሁም በ AFAAN OROMOO
የመሳሰሉትን ሁሉንም ያጠቃለሉ ቻናሎችን ይዘናል።
ከእርሶ ሚጠበቀው JOIN አርጎ መከታተል ብቻ።


Free wave 🌊
👇👇👇👇👇
@F618994

Читать полностью…

Abdu & Hasu

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

እስቲ አሪፍ አሪፍ የ ሱና ቻናሎችን ልጋብዛቹ
ቁርአንን የፈለጉትን ሱራ በፈለጉት ቃሪእ
ኢስላማዊ ምክሮች የመሳሰሉት
ሁሉም እኛ ጋር አለና ጉብተው ይጠቀሙ

Wave ለመመዝገብ
👇👇👇👇

@F618994

Читать полностью…

Abdu & Hasu

አሰላሙዓለይኩም እህቴ ቁርዓን ለመቅራት ፈልገሽ አጋጣሚዎች አልተመቻቹልሽም❓እንግዲያውስ ባለሽበት ሆነሽ የምትቀሪበትን መንገድ ተመቻችቷል

Читать полностью…

Abdu & Hasu

አብዛኞቻችሁ የማታውቁት ነገር ስለ '' Instagram '' 😱

Instagram ይሄን ያህል አስፈሪ ነው?😱
የምትሉበትን ሁለት ታሪኮች ይዤላችሁ ቀርቤያለሁ ክፍል 1
ክፍል 2 የሚለውን ነክታቹ አንብቡ
ወላሂ ትገረማላቹ 😳🤯

ውሸት አይደለም ሙስሊም አይዋሽም ገብታቹህ አንብቡ!

Читать полностью…

Abdu & Hasu

ሴት ከሆንሽ እባክሽን ተጠንቀቂ!

ወንድ ከሆንክ ለምታውቃቸው የ ሴት ወዳጆችክ ሼር አድርግ እና የበኩልህን
ተወጣ...
:
ወላሂ ውሸት አይደለም ገብተው ይመልከቱ።



😱 Open||ክፈት

Читать полностью…

Abdu & Hasu

#ዘይኒ_ኩሊ_ዘይን
ክፍል አንድ

✍️አብዱ ኤምሬ
 
*የረቢዕ_መዳረሻ
በነብዩ ሙሀመድ (ሰዐወ) ህይወት ውስጥ የቀን ውሎ እናየለን
"በታሪክ ውስጥ በሃይማኖታዊም ሆነ በዓለማዊ ደረጃዎች ከፍተኛ ስኬት ያለው ብቸኛው ሰው ነበሩ."
ሚካኤል ሃርት ነቢዩ ሙሐመድን (ሰ.ዐ.ወ) “History 100: A Ranking of the Most Influential Persons” በሚለው መጽሐፉ ውስጥ ቁጥር 1 ላይ አስቀምጦቸዋል።


የኔ ነቢይ ልጅ፣ ባል፣ አባት፣ ጓደኛ፣ሰባኪ፣ ተመሪ፣ የሀገር መሪ፣ የጦር አዛዥ ነበሩ በህይወታቸው ውስጥ ባሳለፉት እያንዳንዱ ሚና ውስጥ ምርጥ ነበሩ። እነዚህን በርካታ ሚናዎች በሚያስደንቅ ሁኔታ እንዴት እንደሚመሩ ጠይቀህ ታውቃለህ? ምናልባት የእለት ተእለት ተግባራቸው ላይ ማስተንተን ብርሃን እንዲፈነጥቅ እና ለእያንዳንዳችን መነሳሳት ሆኖ ያገለግላል! የሚገርመው ነገር የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ህይወት ጥብቅ ልማድ አልነበረም። ይልቁንም ዓላማ ያለው እና የተባረከ ሥራ ነበር እናም የተደረገው ነገር በጥሩ ሁኔታ መከናወኑን ማረጋገጫ ነው። በግልጽ ለማየት እንደሚቻለው የነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የእለት ተእለት ተግባር በጣም አስፈላጊው ባህሪ በአምስቱ የግዴታ የሰላት ሰአቶች ዙሪያ ያጠነጠነ ነበር። የእሳቸው ቀናት እያንዳንዱ ክፍል ከፈጣሪ ጋር በሚያደርጉት መለኮታዊ ስብሰባዎች ላይ በሚያምር ሁኔታ የተቆራኘ ነበር። የበለጠ ለማወቅ እንሞክር!

#ፈጅር/ጠዋት
ነቢዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) በፈጅር አዛን (የሶላት ጥሪ) ከእንቅልፋቸው ተነሱ (በተለምዶ) የሌሊት ረዣዥም የተሀጁድ ሶላታቸውን ከሰገዱ በኋላ። ለጀመአዊ ፈርዶች ወደ መስጂድ ከመሄዳቸው በፊት የሱና ሶላትን በቤት ውስጥ ይሰግዱ ነበር።

ከፈጅር በኋላ ሰሃቦች እና እሳቸው አላህን (ሱ.ወ) ጀንበር እስክትወጣ ድረስ ያስታውሳሉ። አንዳንድ ጊዜ ወደ ነብዩ (ሶ.ዐ.ወ) አጠገብ ይሰበሰቡ እና ከሳቸው ጋር ሞቅ ያለ፣ ውይይት ያደርጋሉ። በዚህ ወቅት ነብዩ (ሶ.ዐ.ወ) ምክራቸውን ወይም ልምዳቸውን ያካፍላሉ ወይም አንዳንድ ጊዜ ሶሓቦች ከእስልምና በፊት ስላዩት ህልም ወይም ሕይወታቸው ይነጋገራሉ። በአጠቃላይ ከሶላት በኋላ ከባልደረቦቻቸው ጋር የሚያሳለፉት ጊዜ ከእነሱ ጋር ለመነጋገር፣ ለማስተማር፣ ለመምከር፣ ለማስታወስ፣ ቅሬታቸውን ለመስማት እና በመካከላቸው ለማስታረቅ ይጠቀሙበት ነበር። ከዚህ በኋላ ለቁርስ ወደ ቤት ይመለሳሉ፤ ቁርስ ብዙውን ጊዜ ቀለል ያለ የተምር ወይም የወተት ምግብ ነበር እናም ይህ ከሌለ ይጾሙ ነበር።

የቀረውን የጠዋት ጊዜ በመስጂድ ውስጥ የእለቱን ዋና ዋና ተግባራትን ይፈፅሙ ነበር። እስልምናን ማስተማርን ይጨምራል። አንድ ልብ ሊባል የሚገባው ነገር ነብዩ (ሶ.ዐ.ወ) ለባልደረቦቻቸው ብዙ ጊዜ ረጅም ትምህርቶችን አይሰጡም ነበር። ይልቁንም የአድማጮቹን እውቀት እና ኢማን የሚያሳደጉ ውይይቶችን የሚያደርጉ ጥያቄዎች ያሏቸው አጫጭር ትምህርቶች ነበሩ። በኋላም ሴት ልጃቸውን ፋጢማ፣ ባልደረቦቻቸውን፣ የተቸገረን ወይም የታመመን ሰው ለመጠየቅ ይወጣሉ። በአንድ ሰው ከተጋበዙ ግብዣውን ተቀብለው ደስ እንዲላቸው እና ልዩ ስሜት እንዲሰማቸው ያደርጋሉ። ወይም በገበያ ውስጥ እየተዘዋወሩ በደስታ ለሰዎች ሰላምታ በመስጠት በዕለት ተዕለት ንግድ ላይ ፍትህ እንዲሰፍን ያደርጋሉ።

ይህ ከተደረገ በኋላ ለዱሃ ሶላት እና ለተወሰነ ጊዜ ከሚስቶቻቸው ጋር ወደ ቤት ይመለሳሉ። በዱሃ እና በዙህር አዛን መካከል ያለው አብዛኛውን ጊዜ ሚስቶቻቸው እሳቸውን ለማየት እና እርስ በርስ የመጋባት ግዴታቸውን የሚወጡበት አጋጣሚ ነበር። ይህን ተከትሎም ለጥቂት ጊዜ ትንሽ ቀትር ወስደው ከዙህር አዛን ይነቃሉ።
ይቀጥላል...

@abduftsemier
@abduftsemier
 

Читать полностью…

Abdu & Hasu

"አስታራቂው_አህመድ!"

ቢስሚላሂ ብዬ መድሁን ልጀምረው፤
ስለ ዘይኔ ላውራ ስለዛ ደግ ሰው፤
ታማሚ ናፋቂ በየሀገሩ ሞልቷል፤
በመናም ለማየት አንቱን ይናፍቃል፤
መዲና መርገጥን ሁሉም ተመኝቷል፤
አንቱ ያ ሙስጠፋ አሽረፉል ሹረፋ፤
ዝናዎት የጎላ ውዴታው የሰፋ፤
እኛም ለመጠጋት እርሷ ጋር ለመድረስ፤
በሳዳቶቹ በኩል ጉዞ ስንገሰግስ፤
ከአብሬት ጀምረን ሼኽ መህሙድ ድረስ፤
በነዚህ ሰዎች ነው የልባችን ሚደርስ።

መጀን በሰይዲ በገውስ አብዱልቃድር፤
ትንሹም ትልቁ ለሱ ገብቶ ሚያድር፤
መጀን በሀሰነል በስሪ መገን በቢያዚድ፤
አሳምረው ሰፉት የሱፊዩን መንገድ፤
መጀን በጋዛሊ መገን በሩሚው ጀላሉዲን፤
የእውቀት አብነት ያበጁ ኪታቡን፤
መጀን በረመዳን ቡጢ መገን በጁነይድ፤
የጠላትን መሰረት ገንድሶ የሚንድ፤
መጀን በሼህ ካባኒ መገን በሼህ ናዚም፤
ፈጥነው ያደርሳሉ ሀድራውን ለሚያልም፤
መጀን በቡራኢ መገን በሼህ መህሙድ፤
ሁልጊዜ እንኑር በሙሀባው ስንነድ፤
መጀን በኔው በአለቃዬ ዩኑስ ኤምሬ፤
የግጥሙ ሰዳሪ የቅኔ መምህሬ፤
ላንቱ ገብቻለው ባንቱ ነው ማማሬ።

መጀን በአልፈቂህ መገን በአባድር፤
የተቅዋቸው ፅናት ፆም የማያሳድር፤
መጀን በራያ ሙፍቲ መገን በጀማ ንጉስ፤
ሲጠሯቸው ጊዜ በቶሎ የሚደርስ፤
መጀን በወረዋዩ መገን በቃጥባሪዩ፤
ህይወታቸውን ሙሉ በዲኑ የሰዩ፤
መጀን በአህመድ በደዊ መገን በዳኖቹ፤
ሀድራቸው የሚያጠገብ ለሁሉ የሚመቹ፤
መጀን በሼህ አሊ መገን በጫሌ፤
ለአቅል የከበዳ ስራቸው አያሌ፤
መጀን በሼህ ኢልያስ መገን በኑርሁሴን፤
ስማቸው ሲነሳ ሸረኛ የሚያበን፤
መጀን በገዳባኖ መገን በአልከሶ፤
ሀይባቸው ያማረ ከላማቸው ለስልሶ፤
መጀን በዘመናችን ኡስታዝ ፈድሉ፤
የመውሊድ አጋፋሪ እውቀት የሚያበሉ፤
መጀን በአብሬቶች መገን በሚቅባስ፤
ከሙስጠፋ ዘንዳ በቶሎ የሚያደርስ።

መጀን በፋጢማ መገን በእናቴ አሚና፤
በጀነት አለቆች ሀሳባችን ይቅና፤
መጀን በአኢሻ መገን በረሱል ሚስቶች፤
ከፊልስጤም ምድር ይሰማ የምስራች፤
መጀን በአሲያ መገን በመርየም፤
ለጀነቱ ሰርግ ሁሉ ሰው ይታደም፤
መጀን በኔ ራቢዓ መገን በሰይዳ ነፊሳ፤
የአላህ ሙቀረብ ዱኣቸው በላዕ ሚያነሳ፤
መገን በአውገረድ ሀዋ መገን በዙለይካ፤
ልባችን በፍቅር ያብብና ይፍካ፤
መጀን በሴቶች ሁላ መገን በእንስቶች፤
ዱኣችን ይሰማ ያድርገን ማንሰለች።

መጀን በአባቶች መገን በእናቶች፤
አድርገን ጌታዬ ለሰይዲ ምንመች፤
መጀን በአውሊያው አለምን በሞሉት፤
ወራሾች ተደርገው ከላይ በተሰጡት።

በነዚህ ሁሉ ወዳጆቻችሁ ብለናል፤
ዛሬ ከሀድራችሁ መታደም ሽተናል፤
ከሰይዲ ሚቅባስ በኩል ለምነናል፤
በሼህ መህሙድም ደብዳቤ ልከናል፤
በሙፍቲ ዑመር ቶሎ አስከትለናል፤
ሰይዲ ለወዳጅ አያውቁምና እንቢ፤
እኛንም አዝልቁን ከመዲናው ግቢ፤
ከረውዷው እንፍሰስ ሁኑልን ዋቢ፤
ወዳጅ አድርጋችሁ ምረጡን እድሉን፤
ከሀድራችሁ ስብሰባ እኛንም ሰብስቡን፤
በባለከራማው ጠላት በሚያርዱት፤
በሙፍቲ ዑመር በኩል ቪዛ ይስጡት፤
እኛም እንደነሱ በከንቱ አንሙት፤
በዘንድሮው አመት ታሪክ ይመዝገብ፤
ሀጅ የምናደርግበት ይሁንልን ያረብ፤
ሌላ ወሬ የለን ስላንቱ ነውንጅ፤
እንዲው እንደናፈቀን ሳናይ እንዳናረጅ፤
በመካ መዲና አስጉዘን መውላና፤
ሁሉ ባንተ ነው የጠመመው ሚቃና።

አሚን!!!!

@abduftsemier
@abduftsemier

Читать полностью…

Abdu & Hasu

#ተገላቢጦሽ

ኢብራሂም አድሀም ወደ በስራ በሄዱ ጊዜ ሰዎች መስጂድ ተሰብስበው ተቀበሏቸው ሰዎቹም ኢብራሂምን ጥያቄ ጠየቁ "ዱኣ ብናደርግም ዱኣችን ምላሽ አያገኘም ምክንያቱ ምን እንደሆነ ንገሩን" አሏቸው። ኢብራሂም አድሀም አስር ምክንያቶችን ዘረዘሩ።

1፦ አላህን እወዳለሁ ትላላችሁ ነገር ግን ትዕዛዙን አትታዘዙም።
2፦ ቁርአን ታነባላችሁ ነገር ግን አትኖሩትም።
3፦ ነብያችንን እንወዳለን ትላላችሁ ግን መመሪያ አድርጋችሁ አትከተሎቸውም።
4፦ ሸይጣን ጠላታችን ነው ትላላችሁ እናንተ ግን የእርሱ ወዳጆች ናችሁ።
5፦ ጀነትን ትመኛላችሁ ግን ለእሷ ብቁ ለመሆን አትጥሩም።
6፦ ጀሀነምን እንፈራለን ትላላችሁ ግን እዚያ የሚያደርስ ስራ ትሰራላችሁ።
7፦ ሞት እውነት ነው ትላላችሁ ግን ለእሱ አትዘጋጁም።
8፦ በሁሉም ሰው ላይ ስህተት ታያላችሁ የራሳችሁን ግን አታዩም።
9፦ አብዝታችሁ ትበላላችሁ ነገር ግን ለእዚያም አላህን አታመሰግኑም።
10፦ በየቀኑ ሬሳ ትቀብራላችሁ ነገር ግን አትማሩበትም።
ሰሉ ዐለል ሀቢብ💚💚
اللهم صل على سيدنا محمد!
ውብ የዱኣ ለይል
@abduftsemier
@abduftsemier

Читать полностью…

Abdu & Hasu

#ሰይድ_ጁነይድ

ኢማም ጁነይድ አል ባግዳዲ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ አሉ፡- “አንድ ጊዜ ኢብሊስን (ሰይጣንን) ለማየት ፈለግኩ። ከመስጂድ በር ላይ ቆሜ ሳለ አንድ በጣም የሚያስጠላ መልክ ያላቸው ሽማግሌ ወደ ፊት ሲመጡ አየሁ። ወደ እኔ ሲቀርቡ ‘አንቱ ማን ኖት? አጸያፊ ቁመናችሁን መቋቋም አልችልም አልኳቸው።' ልታየው የፈለከው እኔ ነኝ አለ። 'እና ጎስቋላ ፍጡር ሆነህ ሳለ ለምንድነው በአደም ፊት ለመስገድ እምቢ ያልከው?' እሱም፦ ጁነይድ ሆይ ከአላህ ውጭ መስገድ የነበረብኝ ይመስልሃል? ይህን ሰምቼ ግራ ተጋባሁ፤ ነገር ግን ብዙም ሳይቆይ አንድ ድምፅ ተሰማ፡- እውነተኛ የአላህ ባሪያ ብትሆን ኖሮ በፍጹም እርሱን ባልታቃወምክ ነበር፡ አለ። ከዚያም ‹ጁነይድ ሆይ በአላህ ይሁንብኝ! አቃጥለህኛል' አለ ከዚያም ጠፋ።'
ይቀጥላል...

*ይህ የሚያሳየው አሏህ ተአላ ወዳጆቹን ከሰይጣን ጥፋት እንደሚጠብቃቸው ነው። ወዳጆቹን ስትወድ፣ ስትከተል ደግሞ አንተንም ይጠብቅሀል።

@abduftsemier
@abduftsemier

Читать полностью…

Abdu & Hasu

#መጀን_በሀሰነት!
#የሰለዋት_ስጦታ

በኸሚሱ ለይል ሳነሳው ስምሽን:
መደድ ተሞሽሬ እጠራለሁ ጌታሽን:
የምስጋና መልክት እሰድራለሁኝ:
ለፍቅርሽ ግጥም እገጥማለሁኝ:
ስለ ናፍቆቴ ነሺዳ አዜማለሁኝ:
ስለ ውልደትሽ መንዙማ እመድሀለሁኝ:
ይህን ሁሉ አድርጌ አንድም አልጠገብኩኝ።

ውልደትሽ ነው በኸሚስ ለይሉ:
9 ወር እስኪሆንሽ ሰለዋት እያበሉ:
ስትውጪ ጊዜ ሁሉ ተቀበሉሽ ሰለዋት እያሉ:
ታድያ ምን ይሁኑ አንቺን የታደሉ:
ልጅ ስታዩ ጊዜ ዚክር አብዙ አሉ:
አንቺን ሳይሽ ጊዜ ሰለዋት ይታየኛል:
አንቺን ሳስብ ጊዜ ነብዬ ትዝ ይሉኛል:
የወዳጄ መቅረቢያ አንቺን አድርጌለሁ:
በዛሬዋ ለሊት የነብዬን ሀድራ ከጅያለሁ:
ንፁህ ልቦናሽን አይተው ይራሩልኝ:
ምንም ባይኖረኝ አንቺን አይተው ይቅረቡኝ።

አንቺ የኔ አለም የደስታ ኩሬ ነሽ:
ከዚህ በላይ ለኔ ምን አለ ብለሽ:
ምኞቴ አንቺን ማየት በራቢያ ተምረሽ:
ከነ ሲቲ ነፊሳ ጋር ተሰድረሽ:
ከአውገረድ ሀዋ ሚስጥርን ተችረሽ:
በመርየም ፋጢማ ሀድራ ተኩለሽ:
በዲኑም በዱንያ ልይሽ ተመንድገሽ።

ውብ ለይል በሰለዋት እንጣፍጥ!
አላሁመ ሷሊ አላ ሰይዲና ሙሀመድ።
እንኳን ተወለድሽልኝ ውብ 4አመታት!

@abduftsemier
@abduftsemier

Читать полностью…

Abdu & Hasu

#ሁሉ_ለእርሱ_ነው!

አላህ ኑህን (ዐለይሂ-ሰላም) መርከቧን እንዲሠራ ባዘዘው ጊዜ ከ124,000 ሳንቃዎች(እንጨቶች) ሠራት። በኢብኑ አባስ ሱረቱል አእራፍ ላይ በተናገረው ተፍሲር ላይ በእስልምና ውስጥ አላህ 124,000 ነብያትን እንደላከ እና ከነሱም 313 መልእክተኞች እንደነበሩ እናውቃለን። ሰይዲና ኑህ (ዐለይሂ-ሰላም) እያንዳንዱን ሳንቃ በየቦታው ማስቀመጥ ሲጀምሩ የነብያት ስም በላያቸው ላይ ይሰፍር ነበር። የሰይዲና ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ስም በ124,000ኛው እንጨት ላይ ታየ። ከዚያም ኑህ (ዐ.ሰ) የመጨረሻው ነብይ ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) መሆናቸውን አወቁ። ከዚያም መርከቧን ለማጠናቀቅ አራት ተጨማሪ እንጨቶች አስፈለጉ እነዚህን እንዳስቀመጡ የአራቱ ኸሊፋዎች ስም በእነዚያ ጣውላዎች ላይ ታየ። አላህም ለኑህ (ዐ.ሰ) እንዲህ አላቸው፡- ‹‹ለውዴ መሐመድ ክብር ስል መርከቧን እያዳንኩ ነው።" ነብዩን (ሰ.ዐ.ወ) እና ባልደረቦቻቸውን የሚወድ አላህ ይወደዋል።
<አጢኡላህ ወአጢዑ ረሱል፣ ወኡሊል አምሪ ሚንኩም> የሚለውን አንቀፅ ላስታውስህ እወዳለሁ።- አላህን ተገዙ፣ ነብዩንና ከናንተ ውስጥ መሪዎቻችሁን ታዘዙ።[4:159]
ነብዩ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፦ "በመጨረሻው ዘመን በኡማዬ ላይ የጨለማ ቁርጥራጮች ይመጣሉ። በዚያን ጊዜ የሚቀመጠው ከሚሄደው ይበልጣል፣ የሚሄደውም ከሚጋልበው ይሻላል…”
*ችግር ካጋጠመህ ቤትህ ተቀመጥ። ጊዜህን ቤት ውስጥ ማሳለፍ ተለማመድ በአላስፈላጊ ነገሮች ውስጥ ራስህን አታሳትፍ።

@abduftsemier
@abduftsemier

Читать полностью…

Abdu & Hasu

#የአሹራ_ክስተቶች

"አሹራ ማለት አላህ ሁሉንም አንቢያዎች በማህበረሰባቸው ከሚደርስባቸው በደል ያዳነበት እለት ነው። ትርጉሙ 'አሻ ኑራ - 'የበራ ቀን' ማለት ነው።
በዚህች ቀን አላህ ብዙ ነብያትን አከበረ። 1) አደምን (ዐ.ሰ) ለሰው ልጆች አባት እንዲሆን መረጠው። 2) ኢድሪስን (ዐ.ሰ) ወደ ሰማይ ከፍ አደረጋቸው። 3) ሰይዲና ኑህን (ዐለይሂ-ሰላም) በእለቱ በመርከባቸው ውስጥ ካሉ ሰዎች ጋር አዳነ። 4) ሰይዲና ኢብራሂም (ዐ.ሰ) ከእሳት የወጡበት። 5)ሰይዲና ዩኑስ (ዐ.ሰ) ከአሳ ነባሪው የወጡበት 6) ሰይዲና ዳውድ (ዐ.ሰ) ይቅር የተባሉበት ቀን። 7) የሱለይማን (ዐለይሂ-ሰላም) መንግሥት መለሰለት። 9) ሰይዲና ዩሱፍ (ዐ.ሰ) ከጉድጓድ የወጡበት 10) ሙሳ (ዐ.ሰ) ከፊርኦን ጭቆና የዳኑበት 11) አዩብን (ዐለይሂ-ሰላም) በዚያ ቀን ከህመማቸው ገላገላቸው። 12) ሰይድና ዒሳን (ዐለይሂ-ሰላም) በዚያ ቀን ወደ ሰማይ አነሳቸው። 13) የመልእክተኞች መደምደሚያ የሆኑት ሰይዲና ሙሐመድን (ሰ.ዐ.ወ) እና ሰይዳታ ኸዲጃን (ረ.ዐ) እንዲጋቡ አደረገ በዚህም ቀን ወደ መዲና እንዲሰደዱ አደረገ። 14) ሁለቱ የጀነት ወጣቶች የውዱ (ሰ.ዐ.ወ) የልጅ ልጆች መሰዋእት የሆኑበት። በዚህ ቀን ሰማያትንና ምድርን ፈጠረ፤ ብዕርንም በዚህች ቀን ፈጠረ።"

@abduftsemier
@abduftsemier

Читать полностью…

Abdu & Hasu

#አስረኛው_ቀን

"አሹራ የሚለው ቃል መነሻ በሴማዊ ቋንቋዎች አስረኛ ማለት ነው ; ስለዚህም ስሙ በጥሬው ሲተረጎም "አሥረኛው ቀን" ማለት ነው።

ሙሀረም በእስልምና ወር አስረኛው የአሹራ ቀን መፆም በእስልምና መጀመሪያ ዘመን በነብዩ መሐመድ ሰዐወ የተጀመረው በሙሳ የቀይ ባህርን መክፈል የሚዘክር ነው። አጀማመሩ በኢብኑ አባስ በኩል በአል-ቡኻሪ በተመዘገበው ሷሂህ ሐዲስ ላይ ተዘግቧል ፡-

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ወደ መዲና በመጡ ጊዜ (አይሁዶች) የዐሹራን ቀን (ማለትም የሙሀረም 10ኛ) ቀን ሲጾሙ አገኞቸው። ምክንያቱም ጠየቁ ‹ይህ ታላቅ ቀን ነው አላህ ሙሳን ያዳነበት የፈርዖንንም ቤተሰቦች ያሰጠመበት ታላቅ ቀን ነው፡ ሙሳም በዚህች ቀን የጾመው አላህን ለማመስገን ነው› ሲሉ መለሱ። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከናንተ ይልቅ ለሙሳ ቅርብ ነኝ አሉ። ስለዚህም ጾሙን (በዚያን ቀን) ጾመው ሙስሊሞች እንዲጾሙበት አዘዞቸው።

ፆሙ በቀድሞ ጊዜ የእስልምና እና የአይሁድ የቀን አቆጣጠር በተመሳሰሉበት ወቅት ነበር። ነገር ግን በኋላ ነብዩ መሐመድ ሰዐወ ኢስላማዊውን የቀን አቆጣጠር እንዲያስተካክሉ በነሲሀ አንቀፅ ተገለጸ እና በዚህ ረመዳን ዘጠነኛው ወር የፆም ወር ሆነ እና አሹራን የመፆም ግዴታው ቀርቷል ። ከዮም ኪፑር ከአይሁድ ፆም የተለየ ቀን ሆነ።
በእናታችን አኢሻ ረዐ በኩል በተዘገበው ሷሂህ ሐዲስ ፡-
"ከእስልምና በፊት በነበረው የድንቁርና ዘመን ቁረይሾች የዐሹራን ቀን ይጾሙ ነበር፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ራሳቸውም ይጾሙት ነበር። ነገር ግን ወደ መዲና በመጡ ጊዜ ያን ቀን ጾመው ሙስሊሞች እንዲጾሙት አዘዛቸው። የረመዷን (የግዴታ ፆም ቅደም ተከተል) በወረደ ጊዜ ረመዷንን መፆም ግዴታ ሆነ፣ ዐሹራንም መፆም ግዴታነት ተተወ መፆም የሚፈልግ ሰው ፆሟል፣ መፆም ያልፈለገ ሰው መብቱ ነው።"

አሁንም ቢሆን አሹራ (10ኛ ቀን)ና (9ኛ ቀን) መፆም እንደ ተፈላጊ ( ሙስተሃብ ) ይታሰባል። በቲርሚዚ ውስጥ አላህ የዓሹራን ጾም ለሚጾሙ ሰዎች የቀደመውን አመት ኃጢአቶች ይቅር ማለቱን የሚያመለክት ሐዲስ ተዘግቧል።"

*ነገን ፆመን ከነገወዲያ ብናስከትል የተሻለ ነው፣ ያልቻለ ማክሰኞን ቢፆም።

@abduftsemier
@abduftsemier

Читать полностью…

Abdu & Hasu

😍😍ገብተህ ማትወጣበት ቻናል ላሳይህ ናና ከስር ያለውን ንካው🙋‍♂/ንኪው🙋‍♀🤩🤩🤩

Читать полностью…

Abdu & Hasu

🔰Current price 🔥🔥🔥

Finally verified

አሁንስ ምን አሰባችሁ


የኖት Coin መስራች @takoy_sasha በዚ game ላይ ይሳተፋል


🤩DOGS - BINANCE ለይ list ሊደረግ ነዉ🤩

🚀በቴሌግራም መስራች Du Rove የሚደገፍ project

🔰Tap Tap ማረግ አያስፈልግም😍

🔰የቴሌግራም አካውንታቹ የተከፈተበትን ቼክ አርጎ coin ይሰጣቹሃል

🔰 Telegram username ስለሚያስፈልግ አስቀምጡ

👀ያልጀመራችሁ ካላችሁ አሁኑኑ ጀምሩ 👇


/channel/dogshouse_bot/join?startapp=FxIvABfRTPCPexm8aAaeJg

ለጥያቄ

@halal_crypto1

Читать полностью…
Subscribe to a channel