ይሄ የመጨረሻው ከኔ ላንቺ የተፃፈ ደብዳቤ ነው ሲጀምርም ሲጨርስም እንታረቅ ይላል። ሌላ ስፅፍልሽ እነግርሻው ግን ይሄንም መች እንደማነብልሽ አላቅም።
✍ እና🎙 #አቤኔዘር
✏️ @ABEN_E 💌
እብደት ሲጀማምር.....🏃♂🏃♂🚶♂🚶♂
ብናጎነብስም ከወደቁት ቀና ስላልን ብቻ አልሞቱም ተብለን አለን። ሞተናል?...... አልሞትንም እየተነፈስን ነው። ምንኖረውም እየኖሩ ነው ሳይሆን አልሞቱም እንዲባል ከሆነ ቆየ......ለነገሩ ባዮቹስ ምን ያድርጉ ከሞቱት በላይ ከሚኖሩት በታች የሆነን ሰው አልሞተም ከማለት ውጪ ሌላ ምን ይበሉት? ምንም!
🤒 ✍#አቤኔዘር (29/09/13) 🤕
@ITSmeABENI_23
እግዜር ይመስገን*******🙏
መሽቶ ነበር እግዜር ይመስገን እኛም አረቄ ቤት ነበርን.....እየጠጣን የሞቀ ጨዋታ ላይም ነበርን.....ስለ ሚጠሉን ሳይሆን ስለምንወዳቸው እያወራን.....እግዜር ይመስገን ሰዉ ሲተኛ እኛ አረቄ ቤት ነበርን......በተፈጠረንበት ሳይሆን በፈጠርነው አለም ውስጥ ሆነን ሁሉም የሆነውን ሲሆን እግዜር ይመስገን የዛች ቀን ምሽት እኛ አረቄ ቤት ነበርን።
✍ #አቤኔዘር
ከ ሰው ጋር ተላምዶ መለያየት ይከብዳል አይደል? መልስሽ አዎ እንደሆነ አውቃለው። አብረን ለሰከርንባቸው እና ላበድንባቸው 23 ቀናት በእኔ ና በ ሰካራም ጓደኞቼ ስም አመሰግናለው። ደግሞ እንደምትናፍቂኝ አትርሺ! ብቻሽን እየሰከርሽ ወይም ደግሞ እያበድሽ አስታውሺኝ……እሺ!
😘😞😞😞😞😞😞😞😞😞😘
ከኔ ላንቺ አሁን ሄደሽ ነገ ለምትመጪው
🚶🚶🚶🚶🏃🏃🏃🏃🏃🏃
ተጓዥ ነን እና ተጠርተንም ሳንጠራ እየሄድን ነው። እስካሁን በመጣንበት መንገድ ብዙ ነገሮችን አልፈናል...በሁላችንም መንገድ ላይ የማይቀሩ ነገሮች አሉ....ማግኘት እና ማጣት። ግን ደግሞ ስናገኝም ስናጣም ከጎናችን የነበሩ፣ ያገኘነወን ፍለጋ ያልመጡ፣ ያጣነውን ተከትለው ያልሄዱ ልዩ ሰዎች ህይወታችን ውስጥ አሉ። ጌታ እነኚን ሰዎች ይጠብቅ🙏 ለዛሬ ለዝችም ቦታ የደረስነው በ እኛ መሻት ብቻ ሳይሆን ከጎናችን ባሉ ጥሩ ሰዎች ምክንያት እና በ እግዜር ምህረት የተነሳ ነው። ምስጋና ለ እርሱ ከዛም ለነሱ.....።
✍ አቤኔዘር 🤒
☘ @ABEN_E 💐 🌘 30/07/2013 (ሀሙስ)🌑
አንድ ሰው አለ... በጠዋት ሲነሳ ቀድሞ ሊያይሽ የሚፈልግ🌞፣ ቁርስ ሰርቶ የሚቀሰቅስሽ🍝፣ አይኖቹ ውስጥ ላንቺ ያለውን ፍቅር እና ስስት የምታነቢበት👀፣ መኖሩ በመኖርሽ የተመሰረተ፣ መውደዱ መውደድ ብቻ ያልሆነ💛፣ ከማፍቀር በላይ የሚያፈቅርሽ♥️፣ ሲለይሽ የሚያመው😔፣ ቻው ሲልሽ የሚከፋው😞፣ አለም ላይ ካንቺ ሌላ ሴት የሌለ እስኪመስልሽ ድረስ የሚንከባከብሽ👧፣ እንዲህም አለ እንዴ🤔ብሎ የሚያሳስብሽ፤ መፈቀር የሚያንሰው አንድ ሰው አለ🥰።
ታዲያ የምታፈቅሪውን ስትከተይ ይሄን አፍቃሪሽን እንዳታጪ! በተዓምር ይሄን ፍቅር ለሌላ አሳልፈሽ አትስጪው። አላፈቅረውም ብለሽ ብታስቢ እንኳን ራስሽን አሳምኚው፤ ዛሬ ባይሆንም አንድ ቀን በፍቅሩ መሸነፍሽ የማይቀር ስለሆነ...
💖የምትወጂውን ሳይሆን የሚወድሽን ምረጪ💖
✍ #ተስኒም
💌📨የአቤኔዘር ደብዳቤዎች◎◎◎💌
💞 @ABEN_E 💞
ትዝታ ከዛ ሰፈር....
ግን አንዳንድ ጊዜ ህይወት እንደዚ ናት መለያየት ሲኖር ፍቅር በ ትዝታ ይተካል። አንዳንድ ትዝታ ይጎዳልና እኔም አንቺን ከሚያስታውሱኝ ነገሮች መራቅን እመርጣለው። ከዛ ሰፈርም መሄድ ይቅርብኝ እንኳን ይሄ አንቺም ቀርተሻል።
✍እና🎙 #አቤኔዘር🤒
👫 @ABEN_E 🚶♂
መቼ፣ እንዴት፣ ለምን.......እኔንጃ
አልዋሽሽም ማፍቀሬን አልጠላም። አንቺን ማፍቀሬን ግን በጣም ጠላዋለው። ሰው አይደለው ማፍቀር እንጂ ማፈቅረውን መምረጥ አልችልም። ነግሬሽ የለ መምረጥ ብችል ኖሮ ደስ እያለኝ አላፈቅርሽም ነበር።
🎙እና✍ #አቤኔዘር
Join👉 @ABEN_E 💌
የማሂ ክፍል አንድ ታሪክ በዚህ አብቅትዎል ። በክፍል ሁለት በተከታታይ ክፍሎች እስከምንገናኝ ድረስ መልካም ጊዜ ይሁንላችሁ
@ABEN_E
ካነበብኩት
… የቀጠለ
የምጠላት እናቴ እና የምትወደኝ ልጅዋ
… እኔ አንድ ልጅዋ እንዲህ ከህይወት እስር ቤት ማምለጥ ወይም ከጨለማው ጋር ተስማምቼ መኖር እንዳልችል ያደረገኝ ማን ነው? እስዋ አይደለችም ? በግዴታም ቢሆን መኖርን እንድመርጥ ያደረገችኝስ እስዋ አይደለችም ?
… አንደ ሙሴ << አይን ያወጣ አይኑ ይውጣ>> ማለት ቢከብደኝም እንደ ክርስቶስ <<ግራህን ለመታህ ቀኝህን ስጠው >> ማለትም አልችልም ። አይንም እያወጡ ጉንጭም እየሰጡ መኖር ወይም አንዱን መምረጥ አለመቻል ስቃይ አይደለም? ለዚህም ምክንያትዋ እርስዋ ብቻ ናት !
ከእናቴ የከፉ በደሎች አንዱ ፍቅርዋ ነው ። ፍቅር አሰጣጥዋ በዚህ አለም ከተሸከምኳቸው መስቀሎች ሁሉ እጅግ የከበደኝ ነው ። ግን ደግሞ እንዲህም ሆና : ውስጤ ቢጠላትም ምስኪንነትዋን አልዘነጋውም ። እንደ ክርስቶስ ፍቅር እዳ የሆነባት ሴት አታሳዝንም ? እንደ ክርስቶስ ናት እርስዋ ። መነሳቱ ለምህረትም ቢሆን እርሱ ለፍቅር አይደል የሞተ ? ይህችም ሴት እንዲሁ ናት ። በየእለቱ ለፍቅሬ እንደሞተች ነው ። ስለ አንዱ ልጅዋ ስለኔ ፍቅር ስትል መሞት ህይወት ሆኑዋታል ።
እስዋ እየኖረች ነው ሚመስላት … ግን ሞታለች … ጉልበትዋ በፍቅር ዝሎል … መልኳ ጠውልጎል … ደምዋ ተመጥዋል … ትንፋሽዋ ስልዋል …
… ይቀጥላል
ምንጭ ~ ፍልስምና መፅሀፍ 📘📙
📖 @ABEN_E✏️
ፀፀት ታቅፌ ብቻዬን 🤦♂ በናፍቆት ልቤ ሲጉላላ
በረዶ ቤቴን አየሁት ጎዳው ካሁኑ ሲላላ
ልቤን እንቢ አለው ብዙ ነው ለውጤ ንፁህ ሰው ገባ እያለኝ ውስጤ .… 🚶🚶
አውቃለው በኔ ልብሽ 💔💔💔 ቢደማም
ይቅር🙏🙏 ለ እግዚያብሄር ማለት አይከፋም
💗💗💗💗💞
ያልተነበበው ደብዳቤ......
እሺ አንተ ማን ነክ ማነው ብዬ እራሴን ላሳምነው የጥፋተኝነት ጥግ በምህረት የምትሸፋን.....ኧረ እንደው ስላንተ ከማን ክፉ ልስማ ምክንያት እንኩዋን አግኝቼ ብጠላክ........... ከሸማኔ ውርዋር የፈጠነው የልቤ ትርታ ❤ .......እራሴ ላይ ካሉት ፀጉሮች ይልቅ የሚበዛው የፍቅርህ ልክ እያወኩት እንዳላወኩ ለማስመሠል እንጂ መቼ አጥቼው ስሜትህን ........ግን እንዳስታምማቸው ግድ የሚሉኝ ንዴትና😠 አልሸነፍ ባይነቴ እራስ ወዳድ አድርገውኛል ለዛ ነው የምጠላክ ለዛ ነው የምርቅህ ለአይንም የጠላሁክ ሀጥያቴን አስታምሜ ነፃና ፍፁም ለመሆን የምጥረው ......አዎ.......በቃ እንደውም ልንገርህ አንተ ማለት ክፉ ለሠው የማታስብ እራስ ወዳድና ትዕቢተኛ ፍቅር የማይገባህ ደረቅ ነክ .........አዎ........በቃ....እኔንም አቶደኝም ምክንያቱም እራስ ወዳድ ነካ በቃ እሠይ እንኩዋን ሠደብኩህ ........😔😔😔እንደዚህ እያልኩ እራሴን ካልደለልኩ በፀፀት ብዛት እራሴን ረሳለው ስለዚህ በቃ አንተ ክፉ ነክ እላለው ደሞም ነፃ ወጣለው🙇..............ግን አልችልም መልካምነትን መሸሸግ አልችልም .........😔❤
✍ ተፃፈ #በሚሊያርድ
✏️@ABEN_E📝📝
አውቃለው እንዲ የሆንሽው ፈልገሽ አይደለም......አንድ ቀን መቀየርሽ አይቀርም ግን እንዳታረፍጂ ፣ ከረፈደ እንዳትቀየሪ እፈራለው።
✍#አቤኔዘር 🕓
✍✍✍የግጥም ቤት✍✍✍
ለአስተያየት.ለጥያቄ እና ግጥሞትን ማጋራት ከፈለጉ @meqdicatho
ቻናላችን ይኸው ሊንኩ@gttem
/channel/gttem
🌿 ዒድ ሙባረክ 💝 Eid Mubarak 🌿
እንኳን ለ1442ኛው ለዒድ አል-ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ 💐💐
🥀መልካም በአል🥀
🍃Happy Eid AL Fitr 🍃
🍂 @Red_ii 🍂
🍂 @ABEN_E 🍂
የፈሲካ ዋዜማ…
የዛሬው ምሽት እንደሌሎቹ ምሽቶች አይደለም። ይሄኛው ይለያል። እንደወትሮ የጎዳና መብራቶች አልጠፉም…ዛሬ በርተዋል። ዝናቡም መዝነብ ጀምሯል። አረቄዬን ይዤ እየሮጥኩ ወደ ቤቴ ገባው። ለምን እንደሆነ እኔንጃ ግን ውጪ የነበረውን ድባብ ወድጄዋለው… መስኮቴንም ከፍቼ ወደ ውጪ ማየት ጀመርኩ።…
ዛሬ ዝናቡን የፈራ የለም፤ ሁሉም ሰው አልተጠለለም። ብዙዎቹ እየረጠቡ ፣ እየተንቦራጨቁ እየሄዱ ነው። አንዳንዶች ግን ዣንጥላ ይዘዋል። መብረቁም ድምፁን እያሰማ ብልጭ ድርግም ይላል።
ዛሬ የፋሲካ ዋዜማ ነውና… እናቶች የገዙትን ዶሮ ይዘው በየሱቁ ተጠልለዋል። ያልተጠለሉም በዝናብ ውስጥ ወደቤታቸው እየሄዱ ነው። ልጆች በደስታ ዝናብ ውስጥ ይሯሯጣሉ። አባቶችም የገዙትን በግ ይዘው እየጎተቱ ቤታቸው ለመድረስ በችኮላ እየተራመዱ ነው…
እኔ መስኮቴ ጋ ቆሜ አረቄዬን እየጠጣው ነው። እየመሸ ሲመጣ እንቅስቃሴውም መቀነስ ጀመረ። አሁን ሁሉም ቤት ሞቅ ሞቅ ብሏል እናቶች የገዙትን ዶሮ እየሰሩ ነው። እኔ ቤት ግን እንደዚ አይነት ነገር የለም… ምክንያቱም ያው!! ዱርዬ፣ ሰካራም እና እብድ ስለሆንኩ ሚስት የለኝማ……
አረቄዬን ከነጠርሙሱ እንደያዝኩ ከመስኮቴ ፊት ለፊት ካለው ወንበር ላይ ሄጄ ቁጭ አልኩ…ሸለብም አረገኝ። ከሰዓታት በኋላ ስነቃ ለካ ወንበር ላይ ነው ያደርኩት፤ አይኖቼንም ጠራርጌ ተነሳው… ፀሀዩአም ድምቅ ብላለች… መንገዱም ነጫጭ ልብስ በለበሱ ሰዎች ተሞልቷል።… አራጆችም፤ አራጅ አራጅ አራጅ እያሉ ይጣራሉ…
መስኮቴንም ዘጋው…ቤቴንም አፀዳው። ጀምሬ ያልጨረስኳቸውን ደብዳቤዎቼንም ለይቼ አስቀመጥኩ… የገነፈሉ እስኪብርቶዎቼንም አውጥቼ ጣልኩ። ከቁምሳጥኔም ውስጥ ንፁህ እና ነጭ የባህል ልብስ አውጥቼ፤ ለብሼ ፋሲካን ለማክበር ከቤቴ ወጣው።
ጌታ ምትወዱትን ህይወት ይስጣችሁ!!! መልካም የፋሲካ በዓል።
✨✍በ አቤኔዘር✨
10/08/2012
⛈ቅዳሜ⛅️
🌹◉◉◉የአቤኔዘር ደብዳቤዎች◎◎🌹
✥-- @ABEN_E --✥
የኔን አለም የሚወዱት እኔን የሚመስሉ ብቻ ናቸው። ልክ ነህ የሚሉኝም እኔ ን የሚመስሉ ብቻ ናቸው። ልክ ነኝ ሰክሬም፣ አልሰከርክም ብትሰክርም አልተንገዳገድክም፤ ብትወድቅም ስለሰከርክ ሳይሆን መሬት ስለጣለችህ ነው፤....... ብታብድም ጤነኛ ስለሆንክ ነው የሚሉኝ እኔን የሚመስሉ ስሜቴ የገባቸው ብቻ ናቸው።
✍#እኔ_ነኝ_አቤኔዘር 🤒
ይሄ የመጨረሻው ከኔ ላንቺ የተፃፈ ደብዳቤ ነው ሲጀምርም ሲጨርስም እንታረቅ ይላል። ሌላ ስፅፍልሽ እነግርሻው ግን ይሄንም መች እንደማነብልሽ አላቅም።
✍ እና🎙 #አቤኔዘር
✏️ @ABEN_E 💌
፨አንድ ቀን ላንቺ መጻፍ የጀመርኩትን ደብዳቤ✉️ ስጨርስ ቢቀናኝ ማታ ከጎኔ ሆነሽ👫 በጨረቃ ብርሀን🌙 ላነብልሽ ፈልጋለው። እሱም ካልሆነ ሌላ ሚሆነው ይሆናል፨
🤒🌺🌺🌺🌕🌺🌺🌺🤒
✍#እኔ_ነኝ_አቤኔዘር✍
የት ነበርሽ?.........
የት ነበርሽ? ያኔ ስፈልግሽ፤ ትተሽኝ መሄድሽን መቀበል አቅቶኝ የሄድሽበትን ሳላውቅ ፈልጌ ሳስፈልግሽ፤ እሱም አልሆን ሲለኝ መምጣትሽን ሳላውቅ ካገኘውሽ ቦታ ቆሜ ስጠብቅሽ፤ ያለሽ አስመስዬ ብቻዬን ሳወራ እብድ ስባልልሽ፤ ከምጣትሽ በፊት ይሄን ሁላ ስሆን የት ነበርሽ?
✍ #አቤኔዘር🤒
❓ #4/04/2013 ❓
መቼ፣ እንዴት፣ ለምን.......እኔንጃ
ምን ብዬ ልጀምርልሽ? መቼ እንዳፈቀርኩሽ ወይስ እንዴት እንዳፈቀርኩሽ? የሁለሀቱንም መልስ እኔ አላውቅም። ብዙ ጊዜ መልስ ልሰጣቸው አስቤ መስጠት አልቻልኩም። በርግጥ ለነዚህ ጥያቄዎቼ ብቻ አይደለም መልስ ያጣውት ለምን እንዳፈቀርኩሽም አላውቅም......እኔንጃ.......
እና ምን ብዬ ልጀምርልሽ? የማውቀውን አንድ እውነት ነግሬሽ ልጀምርልሽ። "አፈቅርሻለው" ይሄ አንቺን አይገባሽም ግን ደግሞ በዚህቀን፣ እንደዚህ፣ በዚህ ምክንያት ነው ያፈቀርኩሽ ብዬ ውሸት ከምነግርሽ አንቺ የማይገባሽን እኔ የሚገባኝን እውነት ብነግርሽ ይሻለኛል። በይገባሽም ልድገምልሽ "አፈቅርሻለው"
አልዋሽሽም ማፍቀሬን አልጠላም። አንቺን ማፍቀሬን ግን በጣም ጠላዋለው። ሰው አይደለው ማፍቀር እንጂ ማፈቅረውን መምረጥ አልችልም። ነግሬሽ የለ መምረጥ ብችል ኖሮ ደስ እያለኝ አላፈቅርሽም ነበር። ይሄን ያለምክንያት ይሄን እንዳላልኩ አንቺም ታውቂያለሽ።
ዝምታ መልስ ነው ይባላል ግን መልስነቱ ለየቱ ነው? ለእሺ ወይስ እምቢ? እውነት ንገሪኝ እስቲ ያንቺ ዝምታ ለየቱ ነው? ከሁለት ለአንዱ ወይስ ያልኩሽ ስላልገባሽ ነው። ከሁለት ለአንዱ ከሆነ ማለት ትችይ ነበር እሺ ወይም እምቢ። ያልኩሽ ስላልገባሽ ከሆነ እና እውነት ለዝምታሽ ምክንያትሽ እሱ ከሆነ አፈቅርሻለው ከማለቴ ውጪ እንደማፈቅርሽ እስኪገባሽ እነግርሽ ነበር።
አልገባሽም እንጂ ማፍቀሬን ሳልነግርሽ ከዝምታሽ በፊት፣ በወሬያችን መሀል ስላንቺ ላንቺ ነግሬሽ ነበር። አንቺም አላወቅሽም ሌላ ሴት አፍቅሬ የማወራሽ መስሎሽ ከጎኔ ቁጭ ብለሽ ስላንቺ ትሰሚኝ ነበር።
ብቻ መቼ፣ እንዴት እና ለምን እንዳፈቀርኩሽ ሳላውቅ ከንፌልሽ ነበር። አንቺንም እስኪበቃኝ ወቀስኩሽ የእብድ ወቀሳ እንዲ ነው ከበዛብሽ ደግሞ ቻይው አልቀንስልሽም ባረሳሽም ከውስጤ ምትወጪበትን ቀን እናፍቀዋለው፣ እስከዛው ግን እየጠላውሽ "አፈቅርሻለው"!
✍በ #አቤኔዘር 🤒
💔26/04/2013 (ሰኞ)💔
@ITSmeABENI_23
JOIN👉 @ABEN_E
ካልኖሩት ደጃፍ
………………………
ክፍል ሶስት
አዘጋጅ ሚሊያርድ @thelifeilive
… ያየውትን ማመን ከበደኝ የሁለት ወር ናፍቆቴ ገንፍሎ የደስታ አይሉት የንዴት የእንባ ዘለላዎች ከጉንጬ ላይ ሲወርዱ ታወቀኝ። ፊቴን ዞር አድርጌ እንባዬን ጠራረኩኝ ።በዛው ቅፅበት ሄጄ ብጠመጠምበት እና ከስሩ ብሸጎጥ ብዬ ተመኘው ግን ደሞ በገነባውት የህልሜ ድር ስጠለፍ በውሸት ጠፈፍ ላይ እንዳልወድቅ ፈራው እና ከፍላጎትነት ሳይዘል ቀጨውት። እናም በዚህ በተመሰቃቀለ ስሜት ውስጥ እንዳለው ልጁ ተራው ደርሶ ውጤቱን ሊያይ ገባ ።እኔ ግን እዛው ስሜት ውስጥ ሆኜ ልቤ ለ2 ተከፈለ ። አንደኛው ልቤ ስለ ናፍቆቴ ሲሰብከኝ ሊቆጣጠረኝ ያለው የህሊናዬ ሚዛን ደሞ ስለ ውጤቴ አጥብቆ ይወቃኝ ነበር። ታዲያ ከራሴ ጋር ባልተግባባውበት ሁኔታ ሁለቱን ዲምኘሎቹን አጉልቶ ልክ እንደከዋክብት የሚያብረቀርቁት በጥበብ የተደረደሩ ጥርሶቹን እያሳየ ከ net cafe ወጣ ።ወዲያው ጓደኞቹ "እና "ብለው ተንሰፍስፈው ሲጠይቁት አይኔን ከአይኑ ላይ በስርቆሽ ምልከታ ወጋ ነቀል እያደረኩ ጆሮዬን ቀስሬ ማዳመጤን ቀጠልኩ ከዛ ምንም የስሜት ለውጥን ባላስተናገደ ፊቱ በፈገግታ ከሽኖ"ያው እንደጠበኩት 4.00 ነዋ አለ" ከማለፉ የበለጠ ውጤቱ አስፈነጠዘኝ😇 ብቻ በዛን ሰአት ምሆነው ነበር የጠፋኝ። በዚህ ስሜት ውስጥ ስዋዥቅ ሳምሪ "እኛስ ገብተን አናይም እንዴ? "ብላ በአንዴ ከደስታ አለሜ መንጭቃ የፍርሀት ዶፍ ውስጥ ከተተችኝ። እውነት ነው የእኔስ ውጤት ? አልፌ ይሆን ?ወይስ?ብቻ ምንም ይሁን ምን ማለፍ አለብኝ አለበዚያ ግን ልጁን………………
መሆን የለበትም አልፋለው እያልኩ ሞራሌን መደገፍ ተስፋዬን ማቀፌን ቀጠልኩ ። ከዛ እንደምንም ትንፋሼን ሰብስቤ ወደ ውስጥ ገባው። ID ዬንም ሰጥቼ ውጤቴን መጠባበቅ ጀመርኩ ።ከሁለት የስቃይ ደቂቃዎች ቦሀላም ውጤቴን አየሁት 😳ወይኔ……………
ክፍል አራት ይቀጥላል
ለአብሮነታቹ እናመሰግናለን🙏🏼
@Lbe_Lbe
ካነበብኩት
የምጠላት እናቴ እና የምትወደኝ ልጅዋ
ብዙዎቹ እናቶች መወደድ ይገባቸው ይሆናል ። እኔም ማገናዘብ በማልችላችልባቸው የልጅነቴ ወራት እንደ እናቴ የምወደው ሰው አልነበረኝም ። እየደግሁ ስመጣ ግን መጠየቅ ጀመርኩ ። በእርግጥ እስዋን እናት ስለሆነች ብቻ መውደድ አለብኝ? መቼም ለሰው ልጅ እንደ መጠየቅ ጠላት የለውም ። በፍለጋው ሂደት ውስጥ እናቴ የምትወደድ ሳትሆን የምትጠላ : የምትሞገስ ሳትሆን የምትወገዝ ሆና አገኘዃት ። እናም እናቴን ጠላዋት ። በሆድዋም በጀርባዋም ተሸክማ ላኖረችው እና አምጣ ለወለደችው ልጅዋ ምህረት እና ርህራሄ የሌላት ሴት እንዴት ልትወደድ ትችላለች? እንዴትስ መጠላት የለባትም ? ደግነቱ እንደ እስዋ አይነት ሴቶች ቁጥራቸው ትንሽ መሆኑ ።
ስለ አለምና የሰው ልጆች ያለኝ አስተያየት የተዛባ እንዲሆን … በትርምሱ መሀል ግራ የተጋባሁ ሆኜ እንድጎዝ … የሌለን ፍቅር እና ፍፅምና በመፈለግ እንድባዝን ያደረገችኝ እስዋ ሆና ነፍሴን ባሰቃየቻት ልወዳት እንዴት እችላለው ?
… ይቀጥላል
ምንጭ ~ ፍልስምና መፅሀፍ 📘📙
✏️@ABEN_E📚
ያልተነበበው ደብዳቤ........... በቃ........🙋
የተዘመረለት እና የተባለለት ብዙዎች አብዝተው የተጠበቡበትን እውነት አይቼ ከማያልቀው የፍቅር ማዕድህ በሃሴት የተቋደስኩበትን ወንጭፍ ሠባሪ ሆንኩኝ .......በቃ ጠገብኩኝ አዋ በቃ አብዝተህ ስትወደኝ አብዝቼ ጠላሁክ ስሸሸው የኖርኩትን ፍቅር አንተ ጋር ሳየው በቃ ተፀየፍኩህ ምክንያቱም ፍቅር ጥፋት ትልቅ ዋጋ የሚያስወጣ ኪሳራ እንደዛር አናት ላይ የሚሠፍር ህመም ጭምር የቅዠት ልጅ የሞት ወንድም ሆኖ ሳለ ቁጥብነት በተሞላው ትግስትህ እስትንፋሴ ሆኖ መተንፈስን በከለከለኝ እውነተኛው ፍቅርህ ያልተገራችውን እኔን አርመህ ሳይ አመመኝ 😔ሀጥያቴ የዳገትን ያህል ተከመረብኝ ፊደላትን ቀምሬ ቃላቴን አሳምሬ ስደልል ና ሳታልልህ መኖሬን ሳስብ , በዝምታህ እልፍ መልሶችን ስሰማ እና ስለፍቅር የማስበው እንደረከሰ ሲሰማኝ በቃ ቀፈፍከኝ።
ምክንያቱም የወደቀን ማንሳት በእጅህ ያምርልሀል የተጠላን መውደድ አንተስ ታድለሀል
አንተ መልአክ ሆነህ ሳይህ የሳጥናኤልነን የሆንኩ ያህል ሲሰማኝ እያፈቀርኩህ ጠላሁህ 💔💔እብዱን ፍቅር አፍቅሬ በሞኙ ጠላሁህ አጥፍቼና ተሳቅቄ ስመጣ በጠንካራ እጆችህ የሙጥኝ አቅፈህ የምታበረታኝን ጥፋቴን ፍቅር ባዘለ አንደበትህ የምታስረሳኝን ነገር ሳስበው አመመኝ ከሀያሉ ፍቅርህ ይልቅ የአፍህን ወለምታ ፈልጌ ያለ ርህራሄ እልኬን እንዳስታመምኩት, እንደጨከንኩብህ ሳስታውስ እራሴን ጠላሁት እያፈቀርኩህ አስጠላኸኝ ካንተ ጋር መሆን ሀጥያቴን ማብዛት መስሎ ታየኝ ለዛ ነው ሁሉን ጥዬ የጠፋሁት ካንተ የአሸዋ ብታኝ ከምታክል ጥፋት ይልቅ የኔ ተራራ የሠራ ሀጥያት ታወሰኝ በቃ ጠላሁካ በቃ አስጠላሃኝ ሳጠፋ የምታመሠግን , ስሸሽህ የምትቀርብ , ስጠላክ የምትወድ እሺ አንተ ማን ነክ....🙇
✍ #ሚሊያርድ
✨ @ABEN_E ✨
እመን እንጂ አትፍራ አይደል ቃሉም የሚለው እኔም አምናለው … አንድ ቀን ጥሩ ህይወት ይኖረናል … ላንቺ እኔ ለኔ አንቺ ኖረን ደስተኞች እንሆናለን ። … እስከዛ ግን እናቴ ጌታ ክፉውን አርቆ ሠላምሽን እና ጤናሽን አብዝቶ ያኑርሽ
ጌታ ሆይ🙏 ትወደኝ የለ አበርታኝ!
✍ እና🎙አቤኔዘር @ABEN_E