😭😭መራር ቁጭት😂😂
በራሴ አለም ኖሬ እንዳሻኝ ፈንጭቼ
ትዛዝና ህጉን ፈልጌ ዘንግቼ
በመኖር ውስጥ መሞት እንዳለ እረስቼ
አለሁኝ እላለሁ ከሞትኩ ሰንብቼ
እነሱም ይላሉ ልክ እንደኔው አለች
ትላንት እዚ ቦታ ዛሬ እዚ ታይታለች
መኖር ቢመስላቸው ባካል መታየቴ
መብላት መጠጣቴ መሳቅ መጫወቴ
ሲጠሩኝ ሰምቼ መልስንም መስጠቴ
መባልን ሽቼ እንጂ መች ሆነና ኖሬ
ለህድ ውስጥ እስክገባ እስኪያመች ለወሬ
አለችም ይበሉ በቁም ሞቼ ዛሬ
የህይወት ጥፍጥና ጥሙን ቆርጦ በኔ
ትርጉም አልሰጥ ብሎ የእድሜ እርዝማኔ
ስሜት አልባ ሆኖ ከእርካታ ተገሎ
ፀፀት እና ቁጭት በውስጡ አይሎ
ትላንቱንም ነገን ዛሬውን በክሎ
እንዴት አለ ይባላል ሰው እራሱን ገሎ
@abipoem
........✍Hiku neberku/neqe
Date 10/07/2014
አፍታ☄
🌿#ኪርክጋርድ
ክፍል- 1
:አንድ የቻናላችን ቤተሰብ ምን ይለኛል *
(ዛሬ ጠዋት -
ወደ ቢሮ እየሮጥኩ ሳለ የሆነ ሀሳብ መጥቶ ጭንቅላቴን አፈነኝና ... መሀል መንገድ ላይ ቆምኩ።
(እየኖርክ ነው!እየኖርክ ነው!እየኖርክ ነው)ጠንከር ባለ ድምፅ ለራሴ ነገርኩት።
(እየኖርኩ ነው?) ግራ በተጋባ ለስላሳ ድምፅ እንደጠየቀ አዋሳኝ ለጥቆ
እድሜዬን አሰልቺው ስራዬን እና በስንፍና የተሞላው የድግግሞሽ ህይወቴን አሰብኩና
እርግጠኛ በሆነ ድምፅ ....... (እየሞትኩ ነው!) .......ብዬ ጮኬ መንገዴን ቀጠልኩ ይለናል።
_
፡
ስለምወደው ፈላስፋ ኪርክጋር'ድ ላወራ ነው.... ከምን ልጀምር? በ21 አመቱ በዲያሪው ላይ ካሰፈረው ቁራጭ ሃሳብ
፡
1/ "ምን ያህል ማወቅ አለብኝ የሚለው አያሳስበኝም። ምክንያቱም ዋናው ነገር ፈጣሪዬ ለምን ወደዚህ ምድር እንዳመጣኝ ተረድቶ በጋለ ስሜት እና በፀና እምነት የምኖርለትና የምሞትለትን አንድ የራሴን እውነት ማግኘትና እሱን እስከመጨረሻ መከተል ነው። ይህን እውነት ደግሞ መፅሀፍት አይነግሩኝም ፤ ጨረቃና ከዋክብትም አያወሩም ። እኔው ራሴ ከውስጤ መፈለግ ይኖርብኛል።
፡
2/ "ሲጋራዬን እያጨስኩ ጭልጥ ወደአለ ሀሳብ ውስጥ ገባሁ። እድሜህ እየሄደ ነው አልኩት ራሴን። ማንንም ሳትሆን ምንም ሳታሳካ ወደርጅና እና ሞት እየገሰገስክ ነው። ....... እስኪ ዙሪያህን ተመልከት የዘመንህ አሳቢያን በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ህይወትን ምቹና ቀላል እያረጉ ስማቸውን ተክለው እያለፉ ነው። የተቀሩት የዘመንህ ጠቢባንም መንፈሳዊ ህይወትን በጣም ቀላል ግን ደግሞ እጅግ ጠቃሚ አድርገውታል።
አንተስ ምን እያደረክ ነው?
እዚህ ጋ ሲጋራዬ አለቀና ከሀሳቤ አባነነኝ ................ ሌላ ለኩሼ ወደ ሀሳቤ ተመለስኩ።
አዎ የዘመናችን አደጋ አንድ ብቻ ነው አሁን ባይታየንም ቅሉ። ሁሉም ነገር ይቀል ይቀል ይቀልና ህይወት ትርጉም ያጣል። ይኸው እኔም የህይወት ጥሪዬን በድንገት አገኘሁት ለሰው ልጆች ካለኝ ጥልቅ ፍቅር የተነሳ ህይወታቸውን ለማክበድ ቀን ከሌት እለፋለሁ።"
፡
-
፡
እነ ኪርክጋርድ ህይወቴን ባያከብዱት ኖሮ እኔም እንደአብዛኛው ሰው የምውልበት ውዬ ፣ በሰላም ተኝቼ አድር ነበር። ግን አልችልም። በተለይ አሁን ሁሉም ነገር 100 እጥፍ በቀለለበት እና 100 እጥፍ ትርጉም ባጣበት በዚህ ዘመን ( ስኬት ማለት ብዙ ብር መሰብሰብ ፣ ደስታ ደግሞ ጃምቦ ከፍ ሲል ውስኪ መጠጣት ………… ፍቅር ከቆንጆ ሴት ጋር መውጣት ፣ እምነት በሣምንት አንዴ ቸርች መገኘት!! )
ዝምብሎ እድሜዬ እየጨመረ እንጂ እየኖርኩ እንደሆነ አይሰማኝም።
፡
ወደድንም ጠላንም ግን እየኖርን ነው። ምን ያህል እንደሆነ ለማናውቀው አጭር ግዜም እዚህ እንቆያለን። ከዛ ሁሉም ያበቃል። ያ ከመሆኑ በፊት ለደቂቃዎች ቆም ብለን ስለህይወት እናስብ። እንዲህ ብለንም እንጠይቅ…….. እንዴት ብኖር ነው ሞት ሊወስድኝ ሲመጣ 'ኖሬያለሁ' ለማለት የማላፍረው? ህይወቴ ካንዲት የምድር ትል ህይወት የሚሻለው? what is the best way to live?
:
በኤግዚስቲንሺያሊዝም ፍልስፍና ውስጥ ግን ለዚህ ጥያቄ መልስ አታገኝም።
" የኔ መንገድ ይህ ነው። ያንተስ መንገድ የታል? 'ብቸኛው' 'እውነተኛው' የሚባል መንገድ?።" ይልሃል ኒቸ…….
ኪርክጋርድ ደግሞ 3 የህይወት ሞዴሎችን አቅርቦ ያስመርጥኃል ። አለመምረጥ አይቻልም(to live is to choose) ………..
ዋናው ነገር ግን ማሰብ እና መጠየቅ መጀመራችን ነው። ……………..
..... ይቀጥላል...
@abipoem
@abipoem
❤️🔥💞ተሸነፍኩልህ ♥️❣
በጠራችው ሰማይ ደምቃ በፈካችው
ከእንከን ከጉድለት ፍፁም በፀዳችው
በአምላክ ጥበባት ባሸበረቀችው
ህሊናን አድሳ ሀሴት በዘራችው
በጨረቃ ልማል ጭልመት ባልጋረዳት
በጉሙ ግነት ውበቷ ባልከዳት
ወይስ በፀሀይዋ ቀትር ላይ ባለችው
ምድርን አቀጣጥላ አንገት ባስደፋችው
እሺ .....................
በንፋሱ ልማል ለእይታ ባልበቃው
እራሱን ሰትሮ አለም በሚያናጋው
ከአይን ተጋርዶ በተግባሩ ገኖ......
.................... ምድርን ባካለለው
🤦♀ እሺ በምን ልማል🤦♀
መሸነፌ ገብቶ ጎልቶ እንዲታይህ
በፍቅርህ መውደቄ በውል እንዲገባህ
ፍቅር አሰጣጡን ባልችል አቀባበል
የሴትነት ክብሬ እኔነቴን ቢዘኝ
ሽንፈቴን ከመግለፅ ከቶም አይገድበኝ
በቃ ልማልልህ አንዱን ምረጥልኝ
ከሰማይ ከምድር ዋስህን ጥራልኝ
ሰማይን መርጠሀል ይሆናል ወይ ብዬ
መሀላ ጀምሬ በውበቱ ተታልዬ
ለካ ከሱ በላይ አንድዬ ያየኛል
በምድር እንዳልምል ይመለከተኛል
በአላህ ምያለሁ በብቸኛው ጌታ
የፍቅር ሀብታሙ በሆነው መከታ
እኔስ ምያለሁኝ ልብህ ከተረታ
ከፍቅርም በላይ በፍቅር አፍቅሬህ
ከመውደድም በላይ ከልቤ አኑሬህ
በናፍቆትህ በትር ውስጤ ሚታመሰው
ከመውደድም በላይ ስለ ምወድህ ነው
ለሂኩ ጥበቡ ነው የተሰጣት በረከት
ልቤ እንዲፀና በሳቅህ እንድደሰት
.....እኔስ ተሸነፍኩኝ.........
መኖር ለሚያስመኘው ለውቡ ፈገግታህ
ቀንን ለሚያፈካ ለደማቁ ሳቅህ
ከወንድነት እርቆ ላለው አንተነትህ💘💝
✍Hiku neberku/neqe
date 25/06/2014
የቀበሮ ፀሎት
▬▬▬▬◍◍◍◍▬▬▬▬
እባክህ አምላኬ- ብትሬን ቀባና
እኔም ልወዝወዘው-የሙሴን ጎዳና
ያላንዳች ፍርሃት-ያለምንም ችግር
ባህሩን ከፍዬ- ህዝቤን እንዳሻግር፡፡
*
አቤት የኔ ጌታ ይህም አያረካም
በቃልህ ታምኜ -ከሆንኩልህ መልካም
ለእኔም ፍቀድልኝ-ያብራምን ምልክት
ከምድር አሸዋ-ዘሬ እንዲበረክት፡፡
*
አቤቱ ምን ልሁን-ይህም አልጠቀመኝ
እስቲ እንደ ዮናስ-ህዝብ ፊት አቁመኝ
*
ትንቢቴን ሰምቶልኝ-ሀገር ይተራመስ
ሰው እህል ይጡም-ከብቱም ሳር አይቅመስ፡፡
ይህም አያረካም-ይልቅ እንደዳዊት
አንተን በሚፈራ-ብዙ ሺህ ሠራዊት
ዙፋኔ ተከቦ-በደስታ እንዳመልክህ
የዚህን ሰው ኮከብ -አውጣልኝ እባክህ
*
አደራህን ታዲያ- ጭንቅ አትወድም ነፍሴ
ልመናዬን ሰምተህ-ካደረግከኝ ሙሴ
መከራውን ማረኝ-ያርባ ዓመት ስደቱን
በሲና በረሃ-መራብ መጠማቱን፡፡
*
ነቢዩ ዮናስን -አርገህም ስትፈጥረኝ
የባህሩን ፍዳ- ያሳውን ሆድ ማረኝ፡፡
*
አብረሃምን ሆኜም-በደስታ ሳመልክህ
ልጅህን እረደው-አትበለኝ እባክህ፡፡
***
የዲዊትም ኮከብ-በኔ ላይ ሲወጣ
እባክህ አምላኬ -ጎልያድ አይምጣ፡፡
✍ታገል ሰይፉ
#share #Join
📚@gbw_dan
📚📚@gbw_dan
📚📚📚@gbw_dan
➕ ቀ ላ🀄️ ል➘➘➘
@gbw_dan
🇨🇬🇨🇬🇨🇬🇨🇬🇨🇬🇨🇬🇨🇬🇨🇬🇨🇬
Photo Collage Editor https://play.google.com/store/apps/details?id=com.photo.collageimagemaker
Читать полностью…🏃🏃♀ይሩጥ ልከተለው🚶♀🚶♀
ከደጃፌ ፀንቶ ቆሞ ባይጠብቀኝ
ከመዳፌ ነጥቆ ዛሬን ቢያሻግረኝ
ትላንቴ ላይ ቆሜ ነገን እየኖርኩኝ
በሂወት ኡደት ውስጥ ዛሬን ተነጠኩኝ
ማለዳ ነቅቼ
ዛሬዬን ዘንግቼ
ትላንቴን አንኳኩቼ
ፎርፌ ተበላሁኝ በሂወት ጨዋታ ጊዜዬን አሲዤ
ፈትልኮ እንደ ወጣ እንደ ብልጭታ መብረቅ
ብልጭ ድርግም ሲል እድሜን ሲያስጨንቅ
ላይደርሱበት ጊዜ እሩጦ ሲያመልጥ
ፈልገው ላይዙት እንዲሁ ሲፈረጥጥ
እሱስ አመሉ ነው ግድ የለም ይሩጥ
እኔም ልከተለው በጊዜ ውስጥ ልስመጥ
@abipoem
@abipoem
✍Hiku neberku/ nege
...........Date 24/03/2014
ከግጥም አታልፊም
።🌓
🌓1
መጣሽም :አልመጣሽ
ኮራሽም: አልኮራሽ
ደመቅሽም ፡አልደመቅሽ
አወቅሽም ፡አላወቅሽ
ብትሽኮረመሚ፡ ብትኮሳተሪ
ዝም ፡ጭጭ ፡ብትይ ፡ደሞም፡ ብታወሪ
ብትገላመጪ ፡ብትንቀባረሪ
መፅሐፍ ፡ብትደግሚ፡ ቁርአን ፡ብትቀሪ
መሐይም፡ ብቶኚ፡ አልያ ፡ብትማሪ
ያሻሽን፡ ቢያረግሽ፡ ያሻሽን ፡ብቶኚ
,ልብሽ ፡ቢርገበገብ፡ አልቅሰሽ፡ ብታዝኚ
ብትንከራተቺም እኔን አታገኚ!
ምናልባት!
አንጀቴ፡ እንኳን ፡ሳስቶ፡ ልቤ ፡ቢወድሽም
አድናቆት፡ ካለው፡ ቃል፡ ከግጥም፡ አታልፊም
poet :🔆 ዳዊት ጥዑማይ
@jawithpoetdeva
jawithpoetdeva
Join ✌👆👆
እኔ_ነኝ #ፈጣሪሽ
ግጥም የስሜት ነው
ግጥም የመንፈስ
የሚያደርግ አዲስ
ገጣሚ ራስ ወዳድ - እራሱን አፍቃሪ
በቃላቶች ድርድር - መልኩን አሳማሪ
ስኬትን ከማሪ
ውድቀትን ቀማሪ
የውስጡን አዳማጭ የልቡን መርማሪ
እኔ ግን ሸግዬ
አንቺን ለማስደሰት ደፋ ቀና ብዬ
ስዱን የምዘራ ተራ_ደራሲ ነኝ
ልክ እንደ ገጣሚሽ
ቃላትን መጥኜ ቅኔ የማልቀኝ
እኔ ማለት ላንቺ .....
የማንንም ታሪክ ሲፅፍ እየዋለ
አንቺን ቆንጂዬዋን
የውበት ሚዛኗን
የፍቅር አርማዋን
በስባሪ ሆሄ መግለፅ ያልታደለ
አንድ ብሽቅ ደራሲ!
ግን
ባትታይሽ እንጂ እውነት ተገላልጣ
ይቻት ተወልዳለች ከልቤ ተምጣ
ያ ታላቅ ገጣሚሽ
ዛሬ..
በስንኞች ብዛት ቢያስውብ ቢያሳምርሽ
ነገም እንደዛሬው ከቶ እንዳይመስልሽ
አይግረምሽና
የአሁን ስሜቱ ድንገት ካንቺ ጋራ ደርሶ ቢቆራኝም
ይበናል በቅፅበት
ይሄዳል በርቀት
የገጣሚ ልቡ ከቶ አይገኝም
እየሰማሽኝ ነው?
የፊደላት ጌታ የዜማ ባለቤት
ይዞሽ የሚሰወር ሰማየ -ሰማያት
እንደዛ ነው አይደል እሱ ማለት ላንቺ?
ከቶ አትሳሳቺ
አትሰሚኝም እንዴ!
ግጥም የስሜት ነው
ግጥም የመንፈስ
የሚያደርግ አዲስ
ገጣሚ ራስ ወዳድ -እራሱን አፍቃሪ
በቃላቶች ድርድር መልኩን አሳማሪ
ስኬትን ከማሪ
ውድቀትን ቀማሪ
የውስጡን አዳማጭ የልቡን መርማሪ
አንተስ አትበይኝ
ባያውቀው ነው እንጂ ገጣሚ ወዳጅሽ
እኔ ነኝ ፈጣሪሽ እኔ ነኝ አርቃቂሽ
ልቡ ደስ እንዲለው
ስንኞቹ መሀል ሁሌ የማኖርሽ።
✍ ......🤓
@abipoem
@abipoem
🤦♀🤦♀ያማል🤦♀🤦♀
መኖሩን ሰውቶ እራሱን ለሰጠ
እድሜው ገብሮ በጭንቅ ላጌጠ ባለመድረስ ብሂል መድረስ የተገታ
አለ በየቤቱ ለፍቶ የተረታ
ሊነጋ ሲል ይጀግናል አሉ ድቅድቁ ጨለማ
ጥቁረቱን አይሎ ህልምን ሚያስቀማ
ፅልመትን አውርሶ ስብእናን የሚንድ
በፍርሀት ማእበል የሚያርበደብድ
የነበልባል ፍጅት በቁም የሚያስቃኝ
ሞትን ብቻ ሳይሆን ሲኦል የሚያስመኝ
ሲኦል ከላይ ወርዶ አለ በጓዳው ስር
በሁላችን ጎጆ ባለንበት ሀገር
ላንዳንዱ ታውሮ ባይታይ ችግሩ
በችግር ወላፈን በትር ለታሰሩ
በሽርፍራፊ ደቂቃ በመጨረሻ ቅፅፈት
ከባድ ህመም የለም ወቶ እንደመቅረት
......✍Hiku neberku/nege
Date 25/01/2014
ከሴትም ሴት!
ምድር አላየችም እሷን የመሰለ;
ዛሬም ወደፊትም የሚያክላት የለ::
ሊያል'ቃት መረጣት:የፈጠራት ጌታ;
ለጋ ወጣት ሳለች:የማታውቅ ተነክታ;
ክቡር አረገዘች:ከነ ክብሯ ታጭታ::
መርየም ለማን ትንገር:ማን ሊረዳት አምኖ;ዐ.ሰ
ወንድ አላውቅም ብትል:ልጅ ከሆዷ ሆኖ::
ከበረሀው ገባች:ምንም ከሌለበት;
ብትጮህ ብትጣራ: ሰው ከማይሰማበት...
ብቻዋን አማጠች:ብቻዋን አርግዛ;
እናት ልትሆን በቃች:አንድ አምላኳን ይዛ!
ምግብ በሌለበት:ፅንታ በእርሱ ተስፋ;
አምላኳን ስትጠብቅ:ህፃኑን ታቅፋ;
ከዛፍ ስር ነበረች:ግንዱን ተደግፋ;
አላት ፈጣሪዋ "ዛፉን አርጊው ገፋ"...
ነቅነቅ አረገችው ሀይሏን አንጠፍጥፋ;
በርግጥ አልነበረም:በእሷ አቅም ሚገፋ::
ለሷ ግን ተገፍቶ:ተምሩ ረገፈ ;
ለስለስ ያለም ሆኖ:በዙርያዋ አረፈ;
ምግብም ሀይልም ሆናት ረሀብ ያሳለፈ::
እሷ ከሴትም ሴት:ልጇ ከሰውም ሰው!
ዒሳ ህዝብ እንዲድን:አምላክ ያነገ'ሰው! ዐ.ሰ
ያለ ወንድ ፍሬ:ተዕምር የፅነሰው::
መልክተኛ ሆነ:በእጁ መድህን ይዞ;
ለዕይን ብርሀንን:ለሞት ነፍስን አዞ;
ተዕምርን አሳየ:በተዕምር ተረግዞ::
እውነትን አንግሶ:ክህደትን አዋርዶ;
መንገዱን አቀና:በአምላኩ ተወዶ;
በሁን አምላክ ጥበብ:ኩን እንዳለው ፈቅዶ;
ነበረ መቻሉ:ከአምላክ ለሱ ወርዶ::
ግን ደረሰ ጊዜው:ፍተናው በርትቶ;
ለሞት ሚታጭበት:ሞት መርታቱ ቀርቶ!
ዒሳ ተፈተነ:በካዱት ተረቶ; ዐ.ሰ
በገሀድ ሊሰቀል:ሆነ ፍርዱ ፅንቶ::
ዒሳ ፅሎት ያዘ:ወደ አንድ አምላኩ; ዐ.ሰ
ቀን ከሌት ተማፅኖ:ወደ ፍትህ ልኩ;
እንዲያርግም ሆነ:ምድር ቀርቶ መልኩ;
ይሰማል አምላኩ!
✍️M.R
ጳግሜ .5 .2013
ይህ አመት አለፈ ይህ አመት ነጎደ
ግፍ እንደተሰራ ሰው እንደ ታረደ
ነገ ሌላ አመት ነው በድሎት ላለሰው
ችግር ላልቀመሰ አፈር ላለበሰው
✍️seada
💙 ዱኒያ የተውሶ ሸቀጥ ናት።
በሷ ውስጥ ያለው ሁሉ እንግዳ
ነው። የተዋሱትን ነገር መመለሱ
ግድ ነው። እንግዳም ወደ ሀገሩ
መመለሱ አይቀሬ ነው።
《ኢብኑ መስዑድ》
ሸጋ ጁምዓ💚💛❤️
@abipoem
@abipoem
Watch "ህዝቡን በሳቅ ጦሽ ያደረገው ግሩም ወግ | "የፀበኛን ቤት እራት ገላጋይ ይበላዋል" በመምህርት እፀገነት ከበደ" on YouTube
https://youtu.be/SGRMDH_zfZc
"የሐበሻ ቀጠሮ"
ትንንሽ ምሁራን፣
ከቀጠርነው ሰዓት፣
ቀድመው እየወጡ፣
እኛን አዘግይተው፣
ማልደው እየመጡ፣
የሐበሻ ቀጠሮ፣
የሚል ስም አወጡ፡፡
@abipoem
@abipoem
🤷♀🙅♀መስራት🤷♀🙅♀
ትጋትና ስኬት የህይወት ኡደቶች
ከህልም አቀበት ላይ ደርሶ አስፈንጣሪዎች
የጨለመን ትላንት በነገው ብርሀን..
................. ዛሬን ማስዋቢያዎች
ቀናቶች ሲሮጡ ዘመናት ሲከንፉ
መቆሚያችን ደርሶ ስንደርስ ከአፍፉ
ማነው መከታችን ከጎን የሚገባው
ስራችን ነው እንጂ አለኝታ የሚሆነው
አንገትን ከመድፍት የሚከላከለን
የሰው እጅ እያዩ ህሊናን ከማቁሸሽ
መተረቻ ሆኖ እራስን ከመሸሽ
እረፍት አይደለም ወይ?............
በልክ የተሰፍ የራስ ስራን ማግኘት
ስራውን ሳይንቁ.................
ስራው ውስጥ ሆነው በስርአት መስራት
.........✍Hiku neberku/neqe
Date 8/07/2014
ቅኔ ቢጤ
*******
ሲያሳሳቸው ጊዜ ነገውን ሊሰቅሉት
ሮብ ርቧቸው አስቀድመው በሉት
ስቀለው ስቀለው ስቀለው ይላሉ
ጠርጴዛ ከበው ከጁ እንዳልበሉ
አጠገበው ህብስት አሰከረው ወይኑ?
በ3ተኛው ጩኸት ተገለጠን አይኑ
የፋሲካ ቂጣ ስንዴው ምን ምን አለክ?
ሰው ሰው ይላልን ወይስ አምላክ አምላክ?
ከየት በላህ ስጋ ደምስ ከምኑላይ
ከ'ኔ ትለፍ ብሎ በጽኑ ሲጸልይ
ጽዋ ነበረ ወይ የተራራው ድንጋይ
የወዝ ደም የሞላው የጠጣችሁት ማይ
የፋሲካው ወይን ምን ምን አለክ ደሙ?
የልጅ የልጅ ነውን? ያባት ያባት ጣ'ሙ
ስትቀባበሉት ስትቆርሱ ያየች ለታ
ልጄን ልጄን ነውን? አባቴን አባቴን
የናቲቱ ዋይታ?
ሃሙስ ጾሜን ልዋል አልፈልግም ንፍሮ
አርብ ስጋ አለልኝ ህዝብ ያልበላው አፍሮ
እጅ እጅ ይላል ምነ እማ ያነፈርሽው
የአይሁድን ሞያ መቼ በቀመስሽው
ምንአስቦ ይሆን በ ባዶ እሚለፋ
ቅጭጭት ከግራቸው ባጠባ ላይጠፋ።
አለም ለረገጣት እድፍ ነው ምንጣፏ
ላዘላት ነው እንጂ የሚበራ ጧፏ።
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
መልካም ምሴተ ሃሙስ ይሁንልን
******
✍tomi
(Toma's tigistu)✍
@abipoem
@abipoem
❣❣ፈገግታዬ❤️❤️አ=
አይቻለው ውበት አንደበት ተዘግቶ
ማንነት ሲናገር
ፈ=ፈርጥ ሆኖ የኖረ የምድር ላይ ብርሀን
ቅ=ቅንነት ተሞልቶ እምነት እሚያሰፍን
ር= ርቀት ሳይገድበው በሰሞች ልብ ላይ
ሀሴትን እሚያድስ
ሀ=ሀያል ማንነትህ ማንነትን ሰርቆ
ልብን የሚያፈርስ
ለ=ላይወጣ ተከትቦ ከልቤ ሰሌዳ
ው=ውስጣዊ ደስታዬ ለፈገግታህ ተማርኮ
ሆኖ ባለ እዳ
ላይደበዝዝ ደምቆ ከደም ተቀላቅሎ
ደስታዬ ከሳቅህ ከፈገግታህ ውሎ
ሽንፈቴን አረዳኝ...........
ከሳቅህ ከመራቅ ሞት እነደ ሚቀለኝ
............ደስታ እንደሚርቀኝ
Hubiye❤️🔥 አንተን ምገልፅበት
ቃላት ስላጠረኝ
ከዝምታዬ በፊት ይሄንን ልንገርህ
የመኖሬ ምክንያት ፈገግታዬ ነህ💋
Hiku neberku/ neqe
le (hubi)
Date12/06/2014
እናቱ ሸርሙጣ ልጅ ደግሞ ዲቃላ
እያለ ሲለፍፍ ሰፈርተኛው ሁላ
ላባት ስም ታጣለት
ሁለት ነፍስ ጥሎ ለሄደው ካውላላ
👉Abi
@abipoem
@abipoem
.. እኛ :እየኖርን: ነው!
ይብላኝ:ንዋይ:ገንዘብ:ብሩር እና:ሜቲ
ንብረቶች:ሳይጎሉት:ለስጋ:መዋቲ
ከእለት:ጉርስ:አልፎ:ለምቾት:የበቃ
ተትረፍርፎ:በዝቶ:የምግቡ:ገበታ
ጥበብ :ላልቸረችው:"የመንፈስ:ርካታ!!
,,..
ይብላኝ:ለአንባቢ:ለባለማዕረግ
እውቀቱ:ሲመስለው:ሁሉን:ነገር:ማድረግ
ብዕር;ለማይጨብጥ:ባለቀለሙን:ዘንግ!
ክህሎትን:ለነሳው:የተፈጥሮ:ጋዳ
ይብላኝለት:እንጂ :ለተመስጦ:ባዳ!
ደራሲ:መች:ከፍቶት:!
ክስተት:የምንቃርም:የምንፅፍ:ገድል
'ህይወት:እኛ:ጋር:ናት':ጠብታ:ሳትጎድል!!
poet:ዳዊት:ጥዑማይ
26:3:14 ዓ,ም!!
hawassa ፍቅር ሐይቅ!
😭ወዳጅ ባጣ😓🥵
አልነቃም ማልጄ ፀሀይ ሲሞቅ ከደጄ
ወዳጅ ባጣ የሚያነቃ
ጨልሞብኝ ፀሀይ ጠልቃ
እነሳለሁ በጨረቃ
@
@abipoem
ገጣሚ Hasinat
Wife is busy packing her clothes.
Man: And where are you going?
Wife: I'm moving to my mother.
Husband also starts packing.
Wife: And where do you think your going?
Husband: I'm also moving to my mother.
Wife: And what about the kids?
Husband: Well if you are moving to your mother and I'm moving to my mother then I guess they must also move to their mother....
ነይ አንቺም
አንቺ...
ከውበት መዛኞች ውለሽ በማደርሽ
የጥፍሮችሽ ነገር
የቻቢስቲክ ነገር
የአካልሽ ነገር ...ነው የሚያሳስብሽ
እኔ ግን
ህሊና ካላቸው እውቀት ከተሞሉ
በመልካም ቃላቶች ውስጥን ከሚያክሙ
ከነሱ ጋር ውዬ...
የአንቺን አኗኗር ውሉን ዘነጋሁት
እዚህ...
ማማርን ማበብን በአይኔ ስላየሁት።
ነይ አንቺም በሞቴ....
✍ ብእር አናቂዋ
@abipioem
@abipoem
🤷♀🤷♀ግራ ተጋባሁኝ🤦♀🤦♀
መደሰት ፈልጌ መሳቅን ናፍቄ
ሀዘኔን ሸሽቼ አንባዬን አምቄ
በፈገግታ ውበት እንድታይ ደምቄ
በእንባ ጥላሸት ላይበልዝ ጉንጮቼ
በጅግ ላይማቅቁ በድኑ አካሎቼ
መስዋት ከፈልኩኝ ግራ ተጋብቼ
ደስታዬ እጄ ላይ መሆኑን ዘንግቼ
.......ብዙ ተንከራተትኩ .........
ሰዎች ልብ ላይ አላግባብ ገብቼ
የቀረብኩት ሁሉ .............
...ደስታን የሚሰጥ ፍሬ እየመሰለኝ
ሁሉን ቀጠፍኳቸው
ውስጣቸው ግን ባዶ ቀፎ ናቸው
እራስ ወዳድ ሆኜ ምርትን ቀማሁዋቸው
አላግባብ ቀንጥሼ ነገን ወረስኳቸው
እኔም ላልደሰት እነሱም ላይስቁ
ከትላንታቸው ላይ ነገን ሰረኳቸው
ዛሬን እንዳይስቁ እንቅፋት ሆንኩዋቸው
ግራ ተጋባሁኝ ላስቅ ወይስ ልሳቅ
ሳቄ እስኪመጣ ብቻዬን ልደበቅ
ሳቃቸውን ሳልነጥቅ ከልቤ እንድስቅ
@abipoem
.....✍Hiku neberku/nege
Date 25/01/2014
🙀🧝♀እንዲ ያረገኛል🧝♀
የምድር አንባሳደር ሆኜ ሳለ መሪ
እኔ ብኩኒቷ ምድርን ተሽከርካሪ
ፍሬ አልባ የሆነ የእንክርዳድ ብቃይ
በብርሀን ምድር በውብ ደማቅ ፀሀይ
በወፎች ዝማሬ በአበቦች መአዛ
ልቤ ማይበገር ሆነና ደንዛዛ
በብርሀን ምድር ጨለማ እያዋዛ
ከተፈጥሮ ደስታ ከልቤ መንጭቆ
ውል አልባ አረገኝ በኔ ላይ ስሜቴ እጅጉን ተጣብቆ
አድማስ ወገግ ሳይል በኔ ጨልሞብኝ
መንጋቱን ስጠብቅ ለሊቱ ታጥፎብኝ
በድቅድቁ ለሊት ጭልመት በጋረደው
በሮችን ከርችሞ አይንን በከደነው
ልሳኖች ተዘግተው ተግባሮች ተገተው
ከፊሉ ........................
ከሞቀ አልጋው ስር በሰፊው ተንጋሎ
ቀሪዉ ደሞ ሌላው ............
በሰሌን ምንጣፍ ላይ እንዲያው ተዘርሮ
አለፍ ሲል ደሞ ................
ከሰው በረንዳ ስር በጎን ተወርውሮ
በእንቅልፍ ድልድይነት ከአለም ተሻግሮ
ከዚ ምድር ሂወት ለሰአታት አርፎ
ደርሶ ይመለሳል ነብሱን አሳርፎ
.............እኔ🤦♀.................
ለሊቱ ታጥፎ እጅግ ረዝሞብኝ
ትንሹ ሞት እንኩዋን እንቅልፍ እንቢ ብሎኝ
ይኸው ቁጭ ብያለሁ ህልሜ እየናፈቀኝ
ኖሬ ያልሆንኩትን ሞቼ እስከማገኝ
......Hiku neberku/ nege
Date pagume2/13/2013
🙎♂🚶አንድ ሰውዬ በጫካ ውስጥ እየተጓዘ ሳለ 🐅ነብር ከፊት ለፊቱ
ይመጣል...ሰውዬው ማምለጥ እንደማይችል ይገባውና
ተንበረከከ አይኑን
ጨፍኖ ከጉድ እንዲያወጣው አምላኩን በጸሎት መማጸን🙇
ይጀምራል……:.🙄
ከጥቂት ደቂቃዎችን በኃላ አይኑን ሲገልጥ ነብሩም🐅 ፊትለፊቱ
ተንበርክኮ
ይጸልያል ሰውዬው በጣም ደስ😊 ብሎት ከነብር መንጋጋ ስላተረፈው
ፈጣሪውን ካመሰገነ በኃላ በደስታ ፈገግ😊 ብሎ……"ነብርዬ አንተም
አማኝ
ነህ እንዴ?" ብሎ ይጠይቀዋል……:.
:
:
🐆ነብሩም……:በደንብ እንጂ! ምንጊዜም ምግብ ከመብላቴ በፊት
እጸልያለሁ ❗️😂😰😭ተበላህ ሰውየው
⁉️Share to your friends @feta_tube
...
ከመኖሬ ዛፍ ስር የሰው ጥላ አያለሁ
ማንም ስለሌለ የኔ ነው እላለሁ...
ውሸት....
ከንጋቴ ረፋድ ከቁጭት ስጋደም
ጥላዬን መራገም፡፡
እውነት...
ጥላ....
ጥላህ ይርገፍ
ዘላለም ህልምን ለመሬት አቀርቅር
አትደግ....ባጭር ቅር፡፡
እረግምሀለሁኝ...
ጥላዬን በፀሀይ ያቀለምከው ኬላ
አብቅል አሜኬላ፡፡
እረግምሀለሁኝ....
የተውኩዋትን እሷ መቆሜን አሳብቦ
ጥላ 'ሚያስታውሰኝ መከዳቴን ከብቦ
ጥላ ጥላህ ይርገፍ
አካሌን ስትስል ህልምክ ይጨናገፍ፡፡
እረግመሀለሁኝ....
እጄም ቅርፅ ሰራ ፀሀይን ተውሶ
እግሬም ቅርፅ ሰራ ፀሀይን ተውሶ
ልቤ ግና ሞቷል ከጥላው ስር ምሶ፡፡
እረግምሀለሁኝ ....
ፀሀይን ሰደባለሁ
መሬትን ሰድባለሁ
አካሌን ረግማለው
አካሏን........?እላለሁ::
ካንተ መኖር ቀድሞ
በዚህ ትንሽ መሬት
Yየርሷን ጥላ ነበር የማውቀው ተጋድሞ፡፡
ጥላዬ ጥላዋን
ሲዘምር በቀትር ሲዘክር በመንፈስ
ቀን እገባ ጀመር በተዘጋ መቅደስ
በክርችሙ ታዛ
አንዳንዱ መውደድህ ከዕድልህ ሲያድፍ
ስትሞት የሚሞት ነው ትዝታ 'ሚያስታቅፍ፡፡
ካልሞትኩኝ የማይሞት
ትናንቴ ይቆጣል ...መውደዴ ይቀጣል
ታዲያንስ ወዳጄ
የአካሌን ክፋይ ጥላዬን የት ልጣል?
፡
፡
፡
ነይልኝ ጠላቴ
በጥላዬ ስለት ነፍሴ አይታረድ
ነይልኝ ወዳጄ
የምንረሳውን ትዝታን እንውለድ፡፡
✍ ኤልያስ ሽታሁን
@abipoem
@abipoem
........"ፍቅር ማለት ........
የተራ ሆሄያት ባዶ ጥርቃሚ ፤
የሶስት ፊደል ጥምረት የቃል ልቅምቃሚ ፤
የደቂቃ ስሜት.......
ወይ ጊዜያዊ ጥቅም አይደለም ምስጢሩ
፡
......ፍቅር ማለት ...
በአንዲት ውብ ማሳ ውስጥ..
ከአረም ከቁጥቋጦ ፈፅሞ በራቀች ፤
ከአንድ ገበሬ እጅ..
በፅናት ተዘርታ በዕምነት የበቀለች ፤
ፍቅር ቡቃያ ነች ፤
የአለምን ሃይሎች አጣምሮ ያደላት ፤
የተንኮል ገሞራ .....
የሃሜት አውሎ ንፋስ ገፍትሮ ማይጥላት ፤
ገንዘብ ጎርፍ ሆኖ.....
ስሯን ቢያጥለቀልቅ ፈፅሞ ማይነቅላት ፤
ፍቅር ቡቃያ ናት..........."
"ገበሬው አምላክ ነው ማሳዋ ልባችን ፤
ዘሩ የፍቅር ቃል ቡቃያው ልጃችን ፤"
እንዲያውም እንዲያውም....
ከተራ ቃላት ጋር ምን አፈታተነን ፤
ፍቅር ማለት ውዴ!!!! በቃ እኔና አንተ ነን ።
✍ ህሊና ደሳለኝ
@abipoem
@abipoem
አላዋቂ አማንያን (የሁልጊዜው እውነታ)
ሳያዩ በጭፍን
ረቂቁን መታመን
በምላስ ሳይቀምሱ
ቀርበው ሳይዳስሱ
በእዝነ ስጋዌ ድምፀቱን ሳይሰሙ
ሰማያዊን ጥሪ በምናብ ሚያልሙ
በአፍንጫቸው ህዋስ ጠረኑን ሳይምጉ
በየዋህ ልቡና
..ድንቅ ና ተዓምር የሚጠባበቁ😁
በእግረ ህሊናቸው
..ወደ ላይ ተጉዘው የታቹን የረሱ
በመፍቅሬ ርዕስ
የተፈጥሮን ስርዐት በእምነት የጣሱ
በሲዖል ፍራቻ በጎን የሚሰሩ
ከቅጣት ለመሸሽ በምግባር ሚኖሩ
ብዙሃኑ ናቸው
..በአላዋቂነት ጦስ ጥፋት የሚዘሩ
አንዳንዴ ሳስበው ፣
..አምላክ ባይኖሩ እንኳን
አንድ መፍጠር ያሻል በምናብ አራቀን
ለምን?
በአላዋቂነት ላይ፣
በአምላክ አለማመን ከተጨመረበት
ይዞ ይመጣልና እጅግ ታላቅ ጥፋት
፡
ሞራላዊነትን በሲዖል ፍራቻ ለገነባ ትውልድ
እምነት ያገራዋል፣
በስሜት ወላፈን እንዳሻው እንዳይነጉድ !!
✍ Abi
@abipoem
@abipoem