#ግጥም
ወፉም ነጋ ሲል እየሰማሽው
ጅቡም መሸ ሲል እየሰማሽው
በምን ምስክር ቀኑን ጀመርሽው!!!
✍ እያዪ ፈንገስ
@abipoem
@abipoem
ወሰደው ከፊትዋ
ልጅነት ሆነና ዕረፍት የሌለበት
አንገት ያለሃሳብ የሚመዘዝበት
ልብ ከግንባር ላይ የሚነበብበት
ለጋነት ባጠራው ይሉኝታ ቢስ ፊትዋ
በስልት ያልተገራው ግልጽ አስተያየትዋ
መልሶ ቢያሳየው የራሱን አንካሳ
የባህሉን ጅራፍ የወጉን ጠባሳ
“ምነው ዓይን በላች ይሉኝታ አጣችሳ”“
እያለ ጮኸና ልቧን አስበርግጐ
ወሰደው ከፊትዋ ልጅነትዋን ጠርጐ
በሞረድ ምላሱ ፈግፍጐ ፈግፍጐ . . .
✍ ታገል ሰይፉ
@abipoem
@abipoem
በዝናብ ቅጠሪኝ
:
አማልዱኝ ባልልም አስታራቂ
ልኬ
ባልማፀንሽም ፊትሽ
ተንበርክኬ
እንባዬ እንዳይታይ ካንቺ
ተደብቄ
አነባለሁ ዛሬም ዝናቡን ጠብቄ
:
ልቤ በስቃይ ጣር ብሶቱን
ሲያሰማ
ሀዘኔ ተሰምቶሽ ልብሽ
እንዳይደማ
ቀኑ ጨላልሞልኝ ክረምቱ
እስኪገባ
መጥተሽ አትጠይቂኝ
ሆድሽም አይባባ
:
ዝናብ የኔን ብሶት ሃዘኔን
ባያጥበው
ሳለቅስ እንዳታዪ እንባዬን
ይጋርደው
በጉንጨ 'ሚፈሰው ዝናብ
እንዲመስልሽ
ሁሌ ክረምት ይሁን ጉዳቴ
አይታይሽ
:
ውዴ፥
ጥፋቴ ሲገባኝ ዛሬ ተመልሼ
ነይልኝ አልልም እፊትሽ
አልቅሼ
አዲሱ ኑሮሽን ልረብሽ በ'ንባዬ
በበጋ አልጣራም "ናፍቀሽኛል"
ብዬ
:
ሳለቅስ እንዳታዪኝ
ሁሌ በያመቱ በክረምት ነዪልኝ
የናፈ'ኩሽ እንደሁ
ጉርምርምታው ሲብስ በዝናብ
ጠይቂኝ
አንቺን ያገኘሁ 'ለት
ከንፈሬ ተላ'ቆ ስስቅ
እንድታዪኝ
ቀን የጨለመ 'ለት
ዶፍ እየወረደ ዝናብ ውስጥ
ጠብቂኝ።
@abipoem
@abipoem
በፈቃዴ እየሮጥኩ
ስባክን ብኖርም ከእቅፍህ ሾልኬ
እንደቸርነትህ
የጠበከኝጌታ ተመስገን አምላኬ🙏
መልካ❣ም አዳር
@abipoem
@abipoem
#የሰው ልጅ ሳይኮሎጂ
💠 ከመተኛትህ በፊት ለመጨረሻ ጊዜ አእምሮህ ውስጥ ያሰብከው ሰው ለደስታህ አለበለዚያ ለሀዘንህ ዋናው ምክንያት ነው።
💠 በሰው ቸል የመባል ህመም ሰውነት ላይ እንደደረሰ አደጋ አይነት ከባድ ነው።
💠 ከዚህ በፊት ስለሆነው ነገር ለማስታወስ ስትሞክር ለመጨረሻ ጊዜ መቼ እንዳስታወስከው ለማወቅ እንጂ የፈፀምከውን ድርጊት አይደለም።
💠 የሆነ ሰው መጥቶ "አንዴ የምጠይቅህ ጥያቄ አለኝ " ካለህ በቅርቡ የፈፀምካቸውን መጥፎ ነገሮች አእምሮህ ማሰብ ይጀምራል።
💠 በደስታ ካለቀስክ የመጀመሪያው የእንባህ ዱብዳ የሚወጣው ከቀኝ አይንህ ሲሆን በመጥፎ ስሜት ካለቀስክ ደግሞ የግራው አይንህ እንባ ቀድሞ ይፈሳል።
💠 በቀላሉ ነገሮችን ለማስታወስ አይንን መጨፈን ጠቃሚ ነው።
💠 ስትሞት በህይወት ዘመንህ ስለ ነበሩህ እቅዶችና ስለሰራሃቸው ነገሮች ለ 7 ደቂቃ ያህል በትዝታ ትጓዛለህ።
Join us share
👇👇👇👇👇
@simon_bzuayehu
@simon_bzuayehu
አፍታ☄
ቿቿቿቿ ቿቿቿቿ👏
የሆነ ጊዜ ካልዲስ ቡና እየጠጣሁ ….አንዱ ሰውየ አስተናጋጇን ለመጥራት ጭብጨባውን አቀለጠው ቿ ቿ ቿ ቿ ቿ ቿ (እልልታ አልተጨመረበትም እንጅ ሰርግ ቤት ነው ያስመሰለው) እና አስተናጋጇ ተሯሩጣ
‹‹አቤት ምን ልታዘዝ?›› ስትለው
‹‹ሻይ!!›› እሽ! ብላ ….ዘወር ስትል እንደገና ቿቿቿቿ ቿቿቿቿ
ደንግጣ ፊቷን እንዳጨፈገገች ‹‹አቤት …?››
‹‹በሎሚ አድርጊው!! ››
እና ብስጭት ብላ ባጠገቤ እያለፈች ምን ስትል ሰማኋት …?
‹‹ይሄ ሁሉ ጭብጨባ ለሻይ…?!››
ምን ለማለት ነው …? በሌላው ዓለም በቃ መደበኛ የሆነው ጉዳይ አገራችን ላይ የሆነ ጭብጨባ የበዛበት ዜና የሚሆነው ነገር ይገርመኛል! ባለስልጣኑ ….ቿቿቿቿ ካድሬው ቿቿቿቿቿቿ…ሚዲያው ቿቿቿቿ ቿቿቿቿ ከአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነው ምናምን ቿቿቿቿቿቿቿቿ ...ሚስኪኑ ህዝብ ምን መጣልኝ ብሎ ሰፍ ሲል ….
‹‹በእንግጭላ ወረዳ አስራዘጠኝ ኪሎ ሜትር የጠጠር መንገድ ሊሰራ የመሰረት ድንጋይ ተጣለ›› ለዚህ ነው እንዴ ብሎ ህዝቡ ዞር ሲል እንደገና ቿቿቿቿ ቿቿቿቿ
‹‹እ ምን ቀራችሁ ?››
‹‹ከአለም ባንክ በተገኘ ዘጠኝ ሚሊየን ዶላር ብድር ነው የሚገነባው ››
✍ አሌክስ አብርሃም
@abipoem
@abipoem
አፍታ☄
ጥቂት ስለ አልኬሚ
-------------------------
አልኬሚ (ቅመማ) ጥንታዊ መነሻ ያለው የቅመማና የፍልስፍና ልማድ ነው። መንፈሳዊ ጉዳይ ማዕከሉ ነው። ሰዎች አልኬሚን እንደየፍላጎቶቻቸው ሲከውኑት ቢቆዩም፣ ዋነኛ ግባቸው ግን ከመንፈሳዊው ዓለም ጋር የሚኖራቸውን መስተጋብር የተሻለ ማድረግ ነው። ልዩ ልዩ ተፈጥሯዊ ቁሶችን ከመንፈሳዊ አካላት ጋር በማዛመድ ማንነታቸውን ሲፈልጉ ከርመዋል።
የከበሩ ድንጋዮችን ፈልጎ ማግኘት፣ በሰው አእምሮ ብቻ የሚቻል እንደሆነ ያምናሉ አልኬሚስቶች!... ከመናፍስት ጋር መገናኘትን ግብ ያደረጉ፣ የመንፈሳዊ ክዋኔ ልማዶች አሏቸው፤ ድግምቶችንና አስማቶችን ይከታተላሉ፤ ይከውናሉ፤...!
የቀማሚዎቹ ዓላማ እንደየሀገሩ ቢለያይም፣ በአብዛኛው ፍላጎታቸው ተመሳሳይ ነው። በአፈታሪክ የሚነገረውን የፈላስፋውን ጠጠርና የሕይወትን ዛፍ ማግኘት ዐቢይ ዓላማቸው ነበር። የምሥራቃውያኑ የቀማምያን ባህል፣ በተወሰነ ደረጃ ለወጥ ያለ ዓላማ ይከተላል።
ቀማሚዎቹ የ"ዕድሜ ማርዘሚያ"ን ምስጢራዊ ንጥረ ነገር ለማግኘት ይሰሩ ነበር (ቻይናዎች ይህን ንጥረ ነገር ሲፈልጉ ነው ባሩድን ያገኙት...! ለማርዘሚያ ያሉት ማሳጠሪያ ሆኗል) የተለያዩ መደበኛ ብረቶችን (Base metal) ቀላቅሎ በመቀመም፣ ወርቅ ለማግኘት ይጥራሉ።
የ"ፈላስፋው ጠጠር" የሚባለውም በቅመማው የሚገኘው ወርቅ ነው። ታሪኩ ከመካከለኛው ምሥራቅ ይመዘዛል። ለቅመማው የሚጠቅሙ ልዩ ልዩ ድግምቶችን የያዘው መጽሐፍ፣ ከእስልምናው ዓለም ወደ ላቲኑ ዓለም የገባው በመካከለኛው ዘመን እንደሆነ ይታመናል።
ይህ የድግምት፣ የአስማቶችና የጥንታዊ ጥበቦች ክምችት ያለበት መጽሐፍ ኋላ ላይ ከ"ክርስትና አስተምህሮ ጋር ይጋጫል" የሚል ተቃውሞ ተነስቶበት ሊከለከል ችሏል። ይሁንና አንዳንዴ በድብቅ ሌላ ጊዜ በይፋ እየተሠራበት እስከ 17ኛው ክፍለ ዘመን ደርሷል። በምሥጢራዊ አስተምህሮዎች እንደተሞላ የሚነገረው ይህ የአልኬሚ እንቅስቃሴ፣ የዘመናዊው ዓለም ሳይንስ ወላጅ ተደርጎ ይወሰዳል።
....
@abipoem
@abipoem
አፍታ ☄
የህይወት ሰበዝ
ሰዎች እንደተቀየርክባቸዉ ያወራሉ፤ በእነርሱ ምክንያት እንደተቀየርክ ግን አይገባቸዉም፤
:
ስለዚህ ሲወዱህ የሚወድ ሲጠሉህ የማይጨነቅ ብርቱና ቅን ልብ ይኑርህ...?
:
በኑሮህ ሁሉ የምታዉቀዉን ሁሉ መናገር ላይጠበቅብህ ይችላል፤ የምትናገረዉን ሁሉ ግን ማወቅ አለብህና...! ግለ ኑሮህን በአስተዉሎት ኑር...?
:
በዚህ ምድር ሰዉ መሆን ነዉ እንጂ፤ ሰዉ መምሰል ቀላል ነዉ፤ እንዲሉ በፍጹም ራስ ተማመን፣ ሁሌም ራስህንም ሁን፤ በዙሪያህ ላሉ ጩኸቶች ሁሉ ጆሮህን አትስጥ...?
:
"ሀይቅ ዳር ተሰብስበዉ እንቁራሪቶች አብዝተዉ ስለጮሁ ሀይቁ የእንቁራሪቶች ነዉ ማለት አይደለም:: ለክብራቸዉ ሲሉ ዝም ያሉ ብዙ ዓሳዎች በሀይቁ ዉስጥ አሉና...!"
✔️ ጸጋዬ ገ/መድህን
መልካ❣ም አዳር !
@abipoem
@abipoem
ስደት
እንደ ታህሣሥ ንፋስ ለመንፈስ ቆርጬ ፣
የሀገሬን ዕንቁ ወርቅ ንቄ ረግጬ ፣
ለመሄድ ተነሣው ሻንጣዬን አንግቼ፣
የስደትን ጣዕም ሳላውቀው ለይቼ፣
የሩቁን አልሜ በምናብ ቃኝቼ ፣
እትብቴ ከተቀበረበት ከሀገሬ ተነስቼ ፣
የት ልድረስ ባላውቅም በመላ ገምቼ፣
አምላኬን ተማፀንሁ እንዳልቀረ ከደጄ፣
በባይተዋር ምድር ሳልኖር ተሰድጄ ፣
እንዲያው ቢሆን እንጂ፣
በሀገሬ ምሰራው ጠፍቶብኝ አጥቼ፣
በጭራሽ አይደለም ሀገሬን ጠልቼ።
፩፱፱፮EF,eye
@abipoem
@abipoem
----ሙግት----
ጊዜ በሰዉ ህይዎት ፣ ዘበት አይታክተዉ
እኔም ምላሽ ባጣ ፣ መጠየቄን አልተው
ኩታ ገጠም ናቸው ፣ አልፋና ኦሜጋ
እንዴት ቀን ይመሻል ፣ በቅጡ ሳይነጋ
ማን ዘረፈዉ ጠጉሬን?
ማን አሰረዉ እግሬን?
ጉልበቴን ማን በላዉ? አቅሜን ማን ወረሰዉ?
ተወልዶ ሳይጨርስ
እንዴት ያረጃል ሰዉ?
✍ በእውቀቱ ስዩም
@abipoem
@abipoem
Watch "ህዝቡን በሳቅ ጦሽ ያደረገ ግሩም ወግ "ከሸንበቆ ስብዕና ይሰውረን" በመምህርት እፀገነት ከበደ" on YouTube
https://youtu.be/Bo92qKsJuRo
@abipoem
@abipoem
ጌታህን ከማውሳት ከሚያርቅህ #ምቾት ወደ ጌታህ የሚቃርብህ
#ችግር ይሻላል !!!
(((ሸጋ ጁምዓ )))💚💛❤️
@abipoem
@abipoem
የጉለሌው ሰካራም
በተመስገን ገብሬ
ክፍል ፩
በጉለሌ የነበረው የታወቀ ዶሮ ነጋዴ ማነው ብለው ከገፈርሳ እስከ ደጃዝማች ይገዙ ሰፈር ለጠየቁ ሰዎች፤ ተበጀ ሰካራሙ
ተበጀ ዶሮ ነጋዴው፤ ተበጀ ነው ብለው ይነግሯቸዋል፡፡
የሕይወቱ ታሪክ ፍፁም ገድል ነው፡፡ ጢም ያለው ሽማግሌ ሰው ነው፡፡ ራሱን ጠጉር ውሃ ወይም መቀስ ነክቶት
አያውቅም፡፡ ማለዳ አይናገርም፡፡ በጠርሙስ የከመረውን ከጠጣ በኋላ ሲራገም ወይም ሲሳደብ ሲፈክር ወይም ሲያቅራራ
ድምጡ ከፈረንጅ ውሻ ድምጥ ይወፍራል፡፡ ቢያውቀውም ባያውቀውም ላገኝው ሁሉ ማታ ሰላምታ ይሰጣል፡፡
ቢያውቀውም ባያውቀውም ካገኝው ሁል ጋር ማታ ይስቃል፡፡ ቢውቀውም ባያውቀውም የሰላምታው አይነት እንደ ወታደር
ወይም እንደ ሲቪል ቢሆን ለእርሱ እንደተመቸው ነው፡፡ ከሰላምታው ጋር ድምጥ ትሰማለችሁ፡፡ ከአፉ ከሚወጣው
ከሚወጣው ግን አንድ ቃል መለየት አትችሉም፡፡
ቡን በተፈላ ጊዜ በጉለሌ በየምድጃው ሥር የሰካራም ተረት በየተጫወተ ሰው ሁሉ የተናገረ በተበጀ ላይ ነው፡፡ መልኩን
አይተውት ያላወቁት ባልቴቶች እንኳ ከፍንጃል ቡን ፉት እያሉየሌላውን ሰካራም ተረትበተበጀ ላይ ያላክኩት ነበር፡፡ይህ
እውነት ነበር፡፡ በጠባዩ ከተባለለት የባሰ ሰካራም ይሁን ወይም የጉለሌ ባህር ዛፍውስጥ ወጥቶ እንደ አዲስ እንግዳ ሰው
ሆኖ ለአዲስ አበባ ታይቷል፡፡
ከዱሮ የእንጨት ጉሙሩክ አጠገብ ወደ ምሥራቅ ሲል ሲል ካለው ወንዝ ማዶ ድልድዩን ወደ ምሥራው ተሻግሮ
መጀመሪያ የሚገኝው አነስተኛ ሳር ክዳን ቤት የተበጀ ቤት ማለት ያ ነው፡፡ በዚያ በቤቱ በዚያ በጉለሌ በሠፈሩ ኖረ፡፡
እንጨቱን ተሸክሞ አፈሩን ቆፍሮ ቤቱን የሰራው እርሱ ነው፡፡ ዋጋ ከፍሎ አስከድኖታል፡፡
ተበጀን ኩራት ተሰማው፡፡ ቆይቶ ደግሞ አይኖቹ እንባ አዘሉ፡፡ በጉንጩም የእንባ ዘለላ ወረደው፡፡ በግራ እጁ መዳፍ
ከጉንጩ የተንከባለለውን እንባ ጨፈለቀው፡፡ ዓይኖቹ እንባ ያፈሰሱ ለራሱ ጎጆ ስላለው ነው፡፡ ሊነገር በማይችል ደስታ ልቡ
ተለውስዋል፡፡
ዝናም ያባረራቸው ም ከቤቱ ጥግ ሊያጠለሉ ይችላሉ፡፡ ቤት የእግዚአብሄር ነውና ውዥብ እንዳያገኛቸው ከቤት ውስጥ
ዝናቡ እስኪያባራ ይቆያሉ፡፡ ተበጀን ‹‹ ቤትህን ይባርክ ››ሊሉት ነው፡፡
ይቀጥላል
@abipoem
@abipoem
አፍታ☄
የግዕዝ ፊደላት ይህን ያህል ትርጉም አላቸው
ሰአሊ= ለማኝ
ሠዓሊ=ሥዕል ሣይ
ሠረቀ = ወጣ
ሰረቀ = ገንዘብ ሰረቀ
ፈፀመ = ነጨ
ፈጸመ = ጨረሰ
ማኅሌት = ማመስገን
ማሕሌት = ማሰብ
ሰርግ = የጋብቻ ድግስ
ሠርግ = መስኖ
@abipoem
@abipoem
#ግጥም
እውነት እና ክብር
ቀልድና ቁም ነገር
ቦታቸው ቢዛባ
ፍቅርና ገንዘብ
ባደረጉት ትግል
እምነት ገደል ገባ ።
✍ ሳሙኤል አዳነ
@abipoem
@abipoem
"አይደለም ምኞቴ"
አይደለም ምኞቴ....
ለምለም አንገትሽ ላይ፣ ክንዶቼን መጠምጠም
ዳሌሽ ላይ መንሳፈፍ፣ ጭንሽ ማሃል መስጠም
እይደለም ምኞቴ
ከንፈርሽን ማለብ፣ ቀሚስሽን መግለብ
ከገላሽ ቆርሼ፣ ገላየን መቀለብ
ደረትሽን ማለም፣ ጡትሽን መሳለም
በቁንጅናሽ ጅረት፣ ገነቴን ማለምለም
አላማየ አይደለም።
ምኞቴን ልንገርሽ?
ካለሺበት ቦታ፣ ቀልቤን ማሰማራት
ወትሮ ካንቺ ጋራ፣ ቡና መጠራራት
ሰላም መገባበዝ፣ ትዝታ መጋራት
የጨለመ ፊቴን፣ ባይንሽ ጮራ ማድመቅ
በቃላትሽ መስከን፣ በሳቅሽ መጠመቅ
በጎ መንፈስሽን፣ ካይንሽ ላይ መሻማት
ርጋታሽን ማጥመድ፣ ዝምታሽን መስማት።
🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
#በዕውቀቱ ሥዩም
🧍♀🏃♀ወጣትነት🧍🏃♂
ተስፋና ፍቅር እምነትና ክደት
እሩጫና ድካም ስኬትና ውድቀት
ህልምን አሳድጎ ወደፊት መጎምዠት
ዛሬን እየረሱ ነገን ማሳደድ
በመኖር ላይ ሆኖ አለመኖር መርሳት
ወጣትነት መስሎን የሂወት ኢንሹራንስ
ሞትን ዘነጋናት ሆንንና ወጣት
ሰውነት ወንድነት ሴትነት
ያልፍና እንደዘበት ይመጣል አሬሳነት
ወንድነት ከሆነ የስሜት መወጫ
ማሰብን ተስኖ በጭፍን ማምለጫ
በጭልመት ተዘፍቆ ህሊናን ማንደጃ
ከሆነ ወንድሜ ፈራሁልህ እንጃ
ከሆነ ሴትነት ሴትነትን ብቻ
ስሜትን መወጫ የሁሉ ማጮቻ
የባህር ዛፍ ሆኖ የማእበል ሲሳይ
ከነብሳት እረክሳ በሰው ሚዛን ሚታይ
ብርሀንን ገፍትሮ ፅልመትን የሚያሳይ
ከሆነ ሴትነት ቢቀር ምን አለበት
ስም ሲያጎድፉ በቅፅፈት መቀጣት
አለና እህቴ ባክሽ አስቢበት
በቃ ሰውነትም ይሁን
ወንድነት ሴትነት
ጊዜን መሻገሪያ ድልድይ እንስራበት
ድማሚት እሚንድ ሀይል እናበጅለት
አለት የሚያቀልጥ ሙቀት እንሁንበት
ሰውነት ወንድነት ሴትነት
ብቻ አይምሰላቹ አለና ሬሳነት
እሱም የኛ አካል ነውና የሰውነት!!
@abiPoem
@abiPoem
....✍Hiku neberku/nege
Date 17/05/2013
...ባትመጭም ቅጠሪኝ💖
ከግራም ከቀኝም ባይኔ እያማተርኩኝ
ከቀጠርሽኝ ቦታ ዛሬም ቁሜአለሁኝ
'
እኔ ብቻ እኮ ነኝ ፍቅርሽን ናፋቂ
አንቺ መቅጠር እንጅ መምጣትን አታውቂ
'
,,,,,,ስለዚህ ፍቅርዬ
ራሴን ሸንግዬ ልቤን አታልዬ
ስጠብቅሽ ልኑር ትመጫለሽ ብዬ
'
ባትመጭም ቅጠሪኝ መንፈሴ ይፅናና
አንቺን ያገኜሁሽ
..የበፊቷን ፍቅሬን ስጠብቅ ነውና።
✍ ....
@abipoem
@abipoem
ስለ አውነት
ምድር ሳታሸልብ ጽልመት ሳይጋረድ
ፀሀይ እንደ ፈካች ወደ ጀንበር ሳትነጉድ
በደራው ገበያ በእልፍ ሰው መሀል
ሰው የተራበ ልብ ፋኖስ ይዞ ይዞራል
የሚያየው በሙሉ በግብሩ ተደንቆ
ፋኖስ የማብራቱን ፣
ም/ያት ለማወቅ ሲጠይቅ አጥብቆ
የጥያቄው ምላሽ ሰው ጠፍቶኝ ነው ሆነ
<ከአጀብ ተነጥሎ ለእውነት የታመነ !! >
:
እንዲህ አይደለም ወይ የዚህ አለም አውነታ
አውኑን የጋረደው
ተዋናዩ ብዙ ሚፈጥረው በዥታ
ሰው መሆን ያልቻለ
ሰው ሚመስል ህልው የአስመሳይ ጋጋታ
✍ Abi
@abipoem
@abipoem
#ናፍቆት
"የሃምሌ ዶፍ መጣ
ብርድ ተከናንቦ
ውርጭ አዝሎ ባንቀልባ፣
ሙቀቴ አንች ነበርሽ
ዘንድሮስ ምን ልሁን-የት አባቴ ልግባ?"
ብሎ ሰው ቢቀኝም፣
እንደዚህ ማርገድ ግን
እኔስ አያምረኝም።
እኔማ...
በጠራራ ፀሃይ-ገላ በሚያቃጥል፣
የለበሱትን ጨርቅ-የትሙን በሚያስጥል፣
እጠብቅሻለሁ-ካቦርቴን ደርቤ፣
በሳሳ አካላቴ-ናፍቆት ተኮንቤ።
እጠብቅሻለሁ...
ቁሩ ቢወበራም
መስኮቴን ከፍቼ ሳንቃየን ሳልዘጋ፣
አንቺ የሌለሽበት
መች ይበርዳል ክረምት
መች ይሞቃል በጋ?
✍ በዘነበ ወላ
@abipoem
@abipoem
Bonus 👍
ብቸኝነት በቀን 15 ሲጋራ ከማጨስ እኩል እእምሮ ላይ ጉዳት ያደርሳል።
በተቻለን መጠን ከስልክ ጋ ምናሳልፈውን ቆይታ ከወንድምና እህቶቻችን ጋር እናድርገው
ሰናይ ማለዳ☘
@abipoem
@abipoem
#ግጥም
የምታምኚው መልክሽ ተከታይ አብዝቶ
እኔ አለው ቢልሽም
ምሽቱ ሲቃረብ ቀን የፈካ ፀሐይ ማታ
አይኖርልሽም!
✍ ካሊድ አቅሉ
@abipoem
@abipoem
❤️Ur name💔
-----------------------
I wrote your name on the sky,
But the wind blew it away.
I wrote your name on the sand,
But the waves washed it away.
I wrote your name on my heart,
And forever it will stay.
@abipoem
@abipoem
በምን ሞተ?
ከደረቀው ቀለም ከቀደሩ ላያልፍ
የሠው ዘር በሙሉ
ጭንቁ ላይቀርለት ተመዛ ስቶጣ
..ነፍስያው ካካሉ
ምን ሊያስቀር ምክኒያት
መሞቻ መንገዱ
በምን ሞተ ?ሲሉ መልስ
.. እንዲሆን እንጂ ለወዳጅ ዘመዱ
✍ Seada
@abipoem
@abipoem
አፍታ ☄
ለጁምዓችን💚💛❤️
"ሐና!"
"አቤት ቲቸር!" ድንገት በመጠራቷ ደንግጣ ታፈጣለች። የክፍላችን ጎበዝ ተማሪ ናት ሐና…
"የሰው ልጅ መሠረታዊ ፍላጎት ምንድ ነው?" ይጠይቋታል።
"ምግብ…ልብስ…መጠለያ" መለሰችው እንላለን እኛ በሽክሹክታ። ገና ትላንት ነው አከባቢ ሳይንስ መምህራችን ያስተማረችን።
"አይደለም! በጭራሽ አይደለም! ሳይንሱ እውነታውን ጋርዶብናል። እንጀራ ማን ሕሊና ውስጥ ቦታ ሰጠው? 'የምድር ፍሬ፣ የወንዝ ውሃ ይሙላህ' የተባለን ሆድ ማነው የሰው መሠረት ያደረገው? የለም! በየጫካው በየዱሩ የሚኖሩ ወገኖቻችን ርቃናቸው ጌጣቸው ነው፤ ቤትስ ቢሆን - የሰው ልጅ ተንኮሉን ሊከልል፣ ለግርዶሹ ስም አወጣ። ልጆች ልብ በሉ…የሰው መሠረታዊ ፍላጎት አንድ ነው፣ እሱም ፍቅር ነው። ካለፍቅር ሰው የቁም ሙት ነው። ሰው ሰውን ሲያፈቅር፣ ሰው አምላኩን ሲያፈቅር፣ ሰው አገሩን ሲያፈቅር፣ ሰው እውነትን ሲያፈቅር፣ ሰው ነፃነትን ሲያፈቅር ነው ሕያው የሚሆነው። ሰው ነገውን ሲወድ፣ ነገውን ሲያፈቅር ነው ነገ ለሚፈጠር ትውልድ ፍቅር የሚያወርሰው…እስትንፋሱ የሚቀጥለው።"
"ዶክተር አሸብር፣ የታረሙ ነፍሶች"
✍ በአሌክስ አብርሃም
@abipoem
@abipoem