abipoem | Unsorted

Telegram-канал abipoem - "ኢ ቶ❤️ዮጵ" ግጥም(በAbi)

303

ለወዳጅ ለጓደኛ ግጥም እንዲፃፍላቹ ምትፈልጉ አናግሩን እንዲሁም ...ግጥም ያላቹ ደሞ ላክ ላክ አርጉልን..... @abironaldo #ምርጥ 👇 -ግጥም ❤️ -አጫጭር ታሪኮች👏 -ምርጥ አባባሎች👌 -ሰነ ክዋክብት✨ ..... #ለመንገድ ...#አፍታ ....#ለፈገግታ ከተሰኙ ልዩ መስገንዘበያዎች ጋር !! @abipoem

Subscribe to a channel

"ኢ ቶ❤️ዮጵ" ግጥም(በAbi)

አካል ሲደነድን
አእምሮ ተራቁቶ
ስውነት ተረሳ
ሰው መምረጥ በርክቶ
✍ ሰዓዳ

Читать полностью…

"ኢ ቶ❤️ዮጵ" ግጥም(በAbi)

የድሮ ማስታወቂያ 😁
@DBU11
@DBU11

Читать полностью…

"ኢ ቶ❤️ዮጵ" ግጥም(በAbi)

የተስፋዬ ዛፉ

የተስፋዬ ዛፉ
ሊከረከም ቅርንጫፉ፣
ሥሩ ሲነቃቀል
ሲበጠስ ሲፈነገል፤
ጭላንጭል ስትዳፈን
ብርሀን ዐይኑ ሲከደን፣
አንጥፌ ደርቤ ማቄን
ዘንግቻት እንቁጣጣሽን
ፀደይ አበባ ዐደዬን፣
በድቅድቅ ተቀመጥሁኝ
ላለማሰብ እያሰብሁኝ፣
የልቤን ልበ ባሻነት ገሰጽኩኝ
ተስፋ መቁረጥን ተስፋ አረኩኝ፡፡

✍ ደበበ ሰይፉ



@abipoem
@abipoem

Читать полностью…

"ኢ ቶ❤️ዮጵ" ግጥም(በAbi)

ዝምምምም

ሞፈር ከበሩ ላይ እንደተቆረጠ፣
እንደ አንድ ገልቱ፤
አይሞቀው፣
አይበርደው፣
አይከርር ጅማቱ፤
አይነዝር ቅኝቱ፡፡
ሲያስሩት - ይንፏቀቃል፣
ሲፈቱት - አይሄድም፤
ዝምምም!
አይተላም፣
አይነቅዝም፤
ዝምምም!
.
ሲቆጣ፣
ሲንጣጣ፣
ከሙቀጫ አፍ ውስጥ፣
እንደ ዶሉት ተልባ፤
ህብረቱ - ገለባ፤
የፍርሀት ሰለባ፤
በረት ሙሉ ስቃይ፣ ጮጮ ሙሉ እንባ፡፡
ዝምምምምም . . .

✍ በድሉ ዋቅጅራ


@abipoem
@abipoem

Читать полностью…

"ኢ ቶ❤️ዮጵ" ግጥም(በAbi)

ድህረ❤️ ሰንበት ❤️

የጊዜን እግረ ሙቅ ጥለሽ እንዳታልፊ
አስሮ እንዳያስቀርሽ የታዛቢው ጥፊ
የሰዉን ተይና ህሊናሽን ስሚ
ወገኛው ለራሱ፣
ትራትሽ ጎምርቶ ሀገር ብታለሚ
በነጋው ሳላንቺ
አንዳች እኩይ ነገር
ሚያወራው አለና ብዙ አትደመሚ
:
አየሽ ፣
ሁሉም ለንፁሃን ንፁህ ሆኖ ቢታይ
መች ይለይ ነ...በረ እ

ዩ ከ ...ሰናይ!
✍ Abi


@abipoem
@abipoem

Читать полностью…

"ኢ ቶ❤️ዮጵ" ግጥም(በAbi)

#ቴዎድሮስ_ካሳ

የለም ፥
አማሁሽ ለነፍሴ ህዋይ
ዘራሁሽ በፀፀት ሰማይ
ቃኘኹሽ በክፏ ሀሳቤ
ጣር ኾነ ፥ ሳቅሽ ለልቤ
የፀደይ ፊት የሚመስለዉ ፣ ብርሀን ገላሽ ጨለመኝ
ከነፍስሽ ስር የሚፈስሰዉ ፥ ቃል ልቦናሽ አሳመመኝ
አየ የእኔ'ና ያንቺ ነገር ተቋጨ ፥
..ፍቅ❣ር አበቃ መሰለኝ !


@abipoem
@abipoem

Читать полностью…

"ኢ ቶ❤️ዮጵ" ግጥም(በAbi)

እቴ..!

ይስጥሽ ከቁመቴ ከላዬ ቀንሶ
ያስረዝምሽ አንቺን እኔን አሳንሶ
ከሰጎን እረዝመሽ ስትቆሚ ከጎኔ
ቁመቴን መጽውቼሽ ጫጩት ላክል እኔ፤
ይስጥሽ ከጸጉሮቼ ከአናቴ ላይ ዘግኖ
ይገጠብ ራሴ ያንቺ ተጎንጉኖ
አወይ ጸጉሯ ብለው ኮረዶች ሲያወሩ
ድጥ ራስ ነህ ብሎ ይዝለፈኝ ሰፈሩ፤
... እቴ
ይስጥሽ ከወዜ ላይ ጨልፎ ከፊቴ
ይቅዳልሽ ከደሜ ጠልቆ ከጅማቴ
ከአይን ያውጣሽ እያለ ሲመርቅ አድናቂ
እስቲ እግዜር ይማርህ ይበለኝ ጠያቂ።

እቴ
እጄን ብትፈልጊ
እግሬን ብትፈልጊ
አንገቴን ደረቴን
ተሰጥኦ ሀሳቤን
ያደምቀኛል ብለሽ ያሰብሺውን ሁላ
እግዜር ከኔ ወስዶ ከሰጠሽ በኋላ
ያስቀርልኝ አይኔን
ያስቀርልኝ አይኔን
አንቺን ማየት ብቻ ያኖረኛል እኔን

✍ በእውቀቱ ስዩም

@abipoem
@abipoem

Читать полностью…

"ኢ ቶ❤️ዮጵ" ግጥም(በAbi)

"ስይጣን ይሻል ነበር"
(ባልና ሚስት)

ሚስት:-
እንዲህ ከምጠበስ
በነጋ በጠባ
ሰይጣን ይሻል ነበር
አንተን ከማገባ

ባል:-
ከቤተሰብሽ ጋር
ከስጋ ዘመድሽ
አይፈቅድም ጋብቻ
ኃይማኖት ባህልሽ😂🤣


@abipoem
@abipoem

Читать полностью…

"ኢ ቶ❤️ዮጵ" ግጥም(በAbi)

አፍታ ☄

ለጅምዓችን💚💛❤️

🔭የሶቅራጥስ 3ቱ 📚📚የጥያቄ መርሆች⁉️

አንድ ሠው ወደ ሶቅራጠስ ሄዶ እንዲህ አለው...🗣

👉‹‹ሶቅራጥስ ወዳጄ፣ እገሌ ስለተባለው ወዳጅህ የሠማሁት ደስ አይልም›› አለው፡፡ ሶቅራጥስ ግን ዝም አለ፡፡

ሰውየውም እንደገና፡- ‹‹ይገርማል ከእርሱ አይጠበቅም፤ በጣም ገርሞኛል›› አለ፡፡

👉ሶቅራጥስም ይህ ሰው እንደማይለቀው ስለተረዳ አንድ መደራደሪያ ሀሳብ አቀረበለት፡፡ ‹‹ስለ ወዳጄ ልትነግረኝ የፈለግከውን ልሠማው የምችለው ሶስት ጥያቄዎች አሉኝ፤ እነርሱን ስትመልስልኝ ብቻ ነው›› አለው፡፡ ሠውየውም ተስማማ፡፡

🎤የመጀመሪያው ጥያቄዬ የእውነት ጥያቄ ነው፡፡ ስለወዳጄ የሠማኸው መቶ በመቶ እውነት ነው ወይ?›› አለው፡፡ ሠውየውም፡- ‹‹መቶ በመቶ እንኳን እርግጠኛ መሆን አልችልም›› አለው፡፡ 👉ሶቅራጥስም፡- ‹‹ልትነግረኝ የፈለግከው እርግጠኛ ያልሆነ ነገር ነው ማለት ነው፡፡

🎤 ሁለተኛው ጥያቄዬ የመልካምነት ነው፡፡ የምትነግረኝ መልካም ነገር ነው ወይ?›› አለው፡፡
ሠውየውም፡- ‹‹እርሱማ መልካም አይደለም›› አለው፡፡
👉ሶቅራጥስም፡- ‹‹እውነትነቱ ያልተረጋገጠና መልካም ያልሆነ ነገር ልትነግረኝ ፈልገሃል ማለት ነው፡፡

🎤ሶስተኛውና የመጨረሻው ጥያቄዬን ልጠይቅህ?›› አለው፡፡
ሠውየውም፡- ‹‹እሺ›› አለ፡፡
👉ሶቅራጥስም፡- ‹‹የምትነግረኝ ነገር ለእኔ የሚጠቅመኝ ነገር አለው ወይ?›› አለው፡፡
ሠውየውም፡- ‹‹የለም›› ብሎ መለሠ፡፡

👉ሶቅራጥስም በመጨረሻ፡- ‹‹እውነትነቱ ያልተረጋገጠ፤ መልካም ያልሆነ፤ ለእኔ የማይጠቅም ነገር አልሠማም›› አለው


@abipoem
@abipoem

Читать полностью…

"ኢ ቶ❤️ዮጵ" ግጥም(በAbi)

ከሰው ሲመራርጥ ሪሳላ.. ነብያት
ከቀናቶች ደግሞ ጁምዓዬን❣ አላቃት
አቦ ! አቦ! አቦ!
ደሰ! ይላል ድ.....ባቡ
በአላህ ራህመት
ከእንቅልፍ ተቀስቅሰው
ሲወጡ ሲገቡ
በየውመል ጁምዓ
በሱና ሲዋቡ ‼️

ሀብታም ማለት ባለው የሚብቃቃ!!!
ደሀ ማለት ባለዉ ነገር የማይረካ!!!

(((ሸጋ ጁምዓ )))💚💛❤️


@abipoem
@abipoem

Читать полностью…

"ኢ ቶ❤️ዮጵ" ግጥም(በAbi)

አስትሮሎጂ 🌟

#ጥር
በጥር ወር የተወለዱ ሰዎች መንፈሰ ጠንካራ፣ የማይበገር አመለካከት ያላቸው እና ሰዎች እንዲህ አድርጉ ብለው እንዲመክሯቸው የማይፈልጉ ናቸው።
በዚህ ወር የተወለዱ ሰዎች ጎበዝ ነገር ግን ሌሎችን የማይሰሙ አለቃ ይወጣቸዋልም ተብሏል።
እነዚህ ሰዎች በተፈጥሮ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን የማስተማር ብቃት ያላቸው ሲሆን፥ ጠንካራ የስራ ስነ ምግባርን የተላበሱ ናቸው።
የመሰላቸውን ለመናገር ወደኋላ የማይሉ መሆናቸውም ነው የሚነገረው።
#የካቲት
የልደት በአላቸውን በየካቲት ወር የሚያከብሩ ሰዎች ደግሞ በውይይት የሚያምኑ፣ አመለካከቱ የወረደ ነው ብለው ከሚገምቱት ሰው ጋር ደግሞ መነጋገር የማይሹ ናቸው ተብሏል።
የፈጣሪ አዕምሮ ባለቤቶች፣ በአዳዲስ እና ልዩ የስራ ዘርፎች መሰማራት የሚወዱ፣ ጉብኝት የሚያዘወትሩ፣ ታማኝ እና ሀቀኛ መሆናቸውም ይነገራል።
#መጋቢት
በመጋቢት ወር የተወለዱ ሰዎች አዲስ ሀሳብ ለማፍለቅ የተፈጠሩ፣ አይን አፋር እና ጭምት እንደሆኑ ነው መረጃው የሚያመለክተው።
የኪነ ጥበብ ስራዎች ራሳቸውን ለመግለጽ የሚጠቀሙባቸው ሲሆን፥ ለመመሰጥ ጸጥታን እንደሚመርጡም ይነገራል።
እነዚህ ሰዎች ለሰዎች ሩህሩህ፣ ቅን እና መልካም አሳቢ ቢሆኑም የራሳቸውን ሚስጢር እና ግላዊ ነገር ለመደበቅ የሚሞክሩም ናቸው።
በራሳቸው አለም የሚኖሩ፣ ሰላማዊ አውድ የሚፈልጉ እና ብዙ ጊዜ ጫጫታ እና ጭንቅንቅ በሚበዛበት ስፍራ የማይገኙ ናቸውም ተብሏል።
#ሚያዚያ
ትዕዛዝን በአግባቡ የማይቀበሉ፣ ነገሮችን በራሳቸው መንገድ የሚመለከቱ እና ሌሎችንም በዚሁ አስተሳሰባቸው ወደራሳቸው ለማምጣት የሚጥሩ ፤ በሚያዚያ ወር ይህቺን አለም የተቀላቀሉ ሰዎች መገለጫ ነው ይላል የናቹራል ሂሊንግ ሜጋዚን ድረ ገፅ ዘገባ።
በአቅራቢያቸው ከሚገኝ ማንኛውም አካል ትኩረት እና ፍቅር ይሻሉ፤ በጀብዱ የተሞላ ህይዎት ይፈልጋሉ፤ አንዳንድ ጊዜም ጠንከር ባለ ንግግራቸው ይታወቃሉ።
በህዝብ ፊት የሚያደርጉት ነገር ግድ የማይሰጣቸውና ቢጸጸቱ እንኳን ከድርጊታቸው በኋላ መሆኑም ይነገራል።
#ግንቦት
ለሁኔታዎች የሚቀያየሩ (የገበታ ውሃ)፣ የዛሬ እና ነገ ፍላጎታቸው የተለያየ፣ ብቸኝነት የሚከብዳቸው እና ጠንካራ የማህበራዊ ህይወት ያላቸው ናቸው።
በዚህ ወር የተወለዱ ሰዎች ስሜታቸውን በደንብ የመግለጽ ብቃት ያላቸው ሲሆን፥ በተለያዩ የእድሜ ክልል ከሚገኙ ሰዎች ጋርም ማውራት ይወዳሉ።
በቀላሉ ለድብርት የሚጋለጡ በመሆኑም የተለያዩ የመዝናኛ አማራጮችን ይመለከታሉ ተብሏል።
#ሰኔ
በሰኔ ወር ከምቹው የእናታቸው ማህጸን ወደዚህች አለም የተቀላቀሉት ደግሞ ሰዎች የሚወዱት አይን አፋርነት እና ጭምትነትን የተላበሱ ናቸው ይላል ዘገባው።
በቀላሉ ስሜታቸው የሚቀያየር እና ለሌሎች ሰዎች ደህንነት አብዝተው የሚጨነቁ መሆናቸውንም መረጃው ያመለክታል።
አርቆ የመመልከት እና ሀሳባቸውን ወደ እውን የመቀየር ልዩ ችሎታ እንዳላቸውም ይነገራል።
#ሀምሌ
በሀምሌ ወር የተወለዱ ሰዎች በሰኔ ከተወለዱት ጋር ተመሳሳይ ባህሪ እንዳላቸው ነው የሚነገረው።
ይሁን እንጂ ወሬ የሚያበዙ፣ ከላይ ከላይ በራስ መተማመን ያላቸው እና ለጋስ መስለው ለመታየት የሚሞክሩ ነገር ግን በውስጣቸው ተንኮል እና ሚስጢር የሚይዙ፤ ህመማቸውን ለሌሎች ሰዎች ከመናገር የሚታቀቡ ናቸው።
በመዝናኛ ስፍራ የማይጠፉ፣ በሀይል የተሞሉ እና ጨዋታ አዋቂዎች በመሆናቸውም ሰዎች በአቅራቢያቸው አይጠፉም።
#ነሀሴ
በነሃሴ ወር የተወለዱ ሰዎችም፦
- ጥልቅ ሀሳብ እና ትንተና በሚፈልጉ ስራዎች ስኬታማ ናቸው።
- ህይወት በደረጃ እና በምክንያት የምትራመድ ነች ብለው ያስባሉ።
- ስሜታቸውን ለመግለፅ አይደፍሩም።
- ተፈጥሮ ለመሪነት ያጨቻቸው ናቸው።
- ልበ ሙሉ እና ሃሳባቸውን በድፍረት ለመናገር ወደኋላ የማይሉ ናቸው።
#መስከረም
በመስከረም የተወለዱ ሰዎች፦
- ሰዎች መልካም ነገር እንዲያደርጉላቸው አብዝተው ይመኛሉ።
- ለኩርፊያም ቅርብ ናቸው።
- ስራቸው ፍፁም ትክክለኛ እንዲሆን ያስባሉ።
- አዳዲስ ሀሳብ አፍላቂ፣ የተረጋጋ ስብእና የተላበሱ እና ሰዎችን ለመርዳት የሚታትሩ ናቸው።
#ጥቅምት
- ክርክር አይመቻቸውም፤ በሀሳብ የሚጋፈጣቸው ሲመጣም ከዚህ መውጫ አማራጭ መንገድ ይፈልጋሉ።
- ስኬታማ የማህበራዊ ህይወት መመስረት የሚችሉ ሲሆን፥ ጓደኞቻቸውን እጅግ በጣም ይወዳሉ።
- ለህይወት ያላቸው አመለካከት አዎንታዊ ነው።
- ማራኪ እና ወሬ የሚያበዙ ናቸው።
#ህዳር
- በጣም ሚስጢራዊ ናቸው፤ ስሜታቸውን በመደበቅ ተክነዋል።
- አይፈሩም፤ ለውጤቱ ሳይጨነቁ ወዳገኙት ሁኔታ ዘው ብለው የመግባት ልማድ አላቸው።
- በህይወታቸው የሚፈልጉትን ከማግኘት የሚያግዳቸውን ነገር ያስወግዳሉ።
- ከሰዎች ምክር መቀበል አይፈልጉም።
#ታህሳስ
- በስራ መወጠር ይፈልጋሉ፤ አንድ ቦታ ላይ ለረጅም ስአት መቀመጥ አይወዱም።
- በአጭር ጊዜ የመግባባት ብቃት አላቸው።
- ታታሪ እና የተረጋጋ ስብእና ባለቤቶች ናቸው።
- በሀይል የተሞሉ እና ሰዎችን በማዝናናት ብቃታቸውም የተመሰከረላቸው ናቸው።



@abipoem
@abipoem

Читать полностью…

"ኢ ቶ❤️ዮጵ" ግጥም(በAbi)

ለፈገግታ😂😁

ሰውየው ፖሊስ ጣብያ ደውሎ "ሚስቴ ጠፍታለች" ብሎ ያመለክታል።

ፖሊስ፦ "ከጠፋች ምን ያህል ጊዜ ሆናት?"

ባል ፦" አንድ ወር ሆኗታል"

ፖሊስ ፦ "ለምን እስከዛሬ አላመለከትክም ?"

ባል ፦ እስከ ትናንትና ድረስ መጥፋቷ ህልም ነበር የመሰለኝ። ከዛ ምንም የታጠበ ልብስ እንደሌለኝ ሳይ መጥፋቷን አመንኩ። 😡😂

#ጭብጥ፦ አንዳንድ ሰዎች እንዲህ ናቸው ። በህይወታቸው ውስጥ ምንም ቦታ የለክም፤ ነገር ግን ካንተ የሚፈልጉትን ነገር ሲኖር መቃብር ድረስ ወርደውም ቢሆን ይፈልጉሀል።

"የሰው ልጅ ያልተነበበ መፅሐፍ ነው " ወዳጄ ሁሌም ሰዎችን መርምራቸው ፤ የዛኔ እውነተኛ ወዳጅህን እና ጠላትህን ነጋሪ ሳያስፈልግህ አንተው ትረዳዋለህ።


@abipoem
@abipoem

Читать полностью…

"ኢ ቶ❤️ዮጵ" ግጥም(በAbi)

Bonus🤗

የሚፈልጉትን መፅሃፍ በነፃ አውርደው ለማንበብ የሚጠቅሙ ምርጥ 5 ዌብሳይቶች

:


1. Project Gutenberg -
www.gutenberg.org
2. Book Boon -
www.bookboon.com
3. Many Books -
www.manybooks.net
4. Free Ebooks -
www.free-ebooks.net
5. Open Library -
www.openlibrary.org



@abipoem
@abipoem

Читать полностью…

"ኢ ቶ❤️ዮጵ" ግጥም(በAbi)

አንድ ናት
ሌላን ተላምጄ እርቄ
አንኳን ብሔድ
ኑሮን ለማቃናት
ባለም ላይ ብስደድ
ከሷ ቢያርቀኝም
የሒወት መዐበል
ዳግመኛ ሳላያት
ከአዱኛ ብነጠል
ውላችን ግን ታስሯል
ትናንት በእትብቴ
በአለም ላይ ያለችኝ
አንድ ናት እናቴ
✍Ⓢeada

@abipoem
@abipoem

Читать полностью…

"ኢ ቶ❤️ዮጵ" ግጥም(በAbi)

የጭቃ እሾህ

የሰው ልጅ ሕይወቱ፣
የጭቃ 'ሾህ ሆኗል፤
ሲያዩት መንገድ መስሎ፣
ሲረግጡት ይዋጋል፤
ግድ-የለሽ ተጓዥ ሆይ፣
መሄጃህን ምረጥ፣
መቆሚያ ያሳጣል
እንዳገኙ መርገጥ ።

✍ መላኩ አላምረው


@abipoem
@abipoem

Читать полностью…

"ኢ ቶ❤️ዮጵ" ግጥም(በAbi)

አፍታ☄

ቶማስ አልቫ ኤድሰን

ኤድሰን አንድ ቀን ከትምህርት ቤቱ ወደ ቤት የተመለሰው
መምህሩ የሰጠውን ወረቀት ይዞ ነበር፡፡
እናም ኤድሰን ለእናቱ እንዲህ አላት “መምህሬ ይሄን
ወረቀት ለእናትህ ብቻ ስጣት ብሎ ሰጠኝ” በማለት
ወረቀቱን አቀበላት፡፡ እናት እንባ
በአይኖቿ ሞልቶ በወረቀቱ ላይ የሰፈረውን ሀሳብ ለልጇ
አነበበችለት፡፡

ያነበበችለት ሀሳብም ይህ ነበር “ልጅሽ በአስተሳሰቡ
ምጡቅ (ጀኒየስ) ነው፡፡ ይሄ ትምህርት ቤት ለእሱ
አይመጥነውም። ለእሱ ብቁ የሆኑ
መምህራኖችም ትምህርት ቤቱ የሌለው በመሆኑ እባክሽ
አንቸው አስተምሪው ይላል” በማለት እንባዋን
እየጠራረገች ወረቀቱን አጣጥፋ
መሳቢያ ውስጥ ከተተችው፡፡

እናቱ ካረፈች ከብዙ ዓመታት በኋላ ኤድሰን በክፈለ ዘመኑ
ካሉ የፈጠራ ውጤት ባለቤቶች አንዱና ቀዳሚው ከሆነ
በኋላ አንድ ቀን እናቱ እቃዎቿን የምታስቀምጥበትን
መሳቢያ ማገላበጥ ጀመረ፡፡
ባጋጣሚ የተጣጠፈች ወረቀት ከመሳቢያው ጠርዝ አካባቢ
ተሰክታ ይመለከትና አንስቶ ከፈታት፡፡ ወረቁ ልጅ እያለ
ከመምህሩ ለእናቱ ብቻ
እንዲሰጥ ታዞ የተሰጠው ወረቀት እንደነበር አውቋል፡፡

ከፍቶ ሲያነበውም ወረቀቱ ላይ የሰፈረው ሀሳብ እንዲህ
ይላል “ልጅሽ የአእምሮ ችግር ያለበትና ዘገምተኛ ነው፡፡
ከዚህ በኋላም ወደ ትምህርት
ቤቱ እንዲመጣ አንፈቅድለትም” ይላል፡፡
ኤድሰን ለሰዓታት ካለቀሰ በኋላ ድያሪውን ከፍቶ እዲህ ሲል
ጻፈ “ቶማስ አልቫ ኤድሰን አእምሮው ዘገምተኛ የተባለ
ልጅ ነበር፡፡ ነገር ግን

በጀግናዋና በልዩዋ እናቴ የምእተ ዓመቱ ጂኔስ ሁኛለሁ፡፡
”እናትን መግለጽ እጅግ አዳጋች ነው፡፡ በፊደል ለመግለጽ
የሚያዳግት ተፈጥሯዊ ጸጋ እናትነት ይመስለኛል፡፡ እጅ
አትስጡ፤ በፍጹም ተስፋ
አትቁረጡ በራሳችሁ ተማመኑ፣
ማንኛውንም ትግል ሁለት

ጊዜ ነው የምናሸንፈው ቀዳሚውም በአእምሮ ውስጥ
የሚያልቀው ነው ይለናል
ቶማስ ኤድሰን፡፡
እኔ በሙከራየ አልወደኩም፤ የማይሰሩ አስር ሽህ
መንገዶችን ለይቻለሁ።
ማንኛው ሰው በአንተ ድክመት ሊያወራ ይችላል ነገርግን
በፍጹም ተስፋ አትቁረጥ ስለ ራስህ ከአንተ በላይ
የሚያውቅ ሰው የለም።


@abipoem
@abipoem

Читать полностью…

"ኢ ቶ❤️ዮጵ" ግጥም(በAbi)

ተያይዞ ቢቆም ሁሉም ለአመሉ
አጥር እንዳይመስልሽ የከበበሽ ሁሉ



@abipoem
@abipoem

Читать полностью…

"ኢ ቶ❤️ዮጵ" ግጥም(በAbi)

የጉለሌው ሰካራም
የመጨረሻ ክፍል

ወደ ቤቱ የተመለሰ መስሎት ሄደ። ማወቅ አልቻለምና ወዴት እንደሄደ ግን አላወቀም። አንድ መንገድ ሲያቋርጥ ተሰናከለና ወደቀ። ከወደቀበትም ምድር ላይ በዳሰሰ ጊዜ ለእጁ የገጠመው የባቡር ሐዲድ ነው። ቤቱ ያለ በጉለሌ ነው። የሰከረበት ደግሞ የበቀለች መጠጥ ቤት ነው። መጠጥ ቤቱም ከዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን አጠገብ ነው።

ምን ያህል ቢሰክር ነው የጉለሌ መንገድ ጠፍቶት እስከ ባቡር ሐዲድ ድረስ ተሳስቶ የሄደ? ራሱን ይዞ ለመጮህም ራሱ ወዴት እንዳለ ማወቅ አቃተው። እንደ ቤቱ መንገድ ጠፋበት።

ጥቂት መስማት ከቻለ በኋላ ጩኸት በስተኋላው ይነፋ የነበረ የእሳት አደጋ ወይስ ባቡር ኑሯል? እያፎደፎደ ሲሄድ ከወደ ኋላው በኩል ምን እንደገፋው አላወቀም፤ ከኋላው በኩል ትልቅ ኀይል መታው። ከፊቱ በኩል የቀበሮ ጉድጓድ ተቀበለው። እግሩ እንደ ብርጭቆ ነከተ። ከወደቀበትም ሌሊቱን ሁሉ ደም ከእግሩ ዘነበ። ትንኝም እንደ ንብ በላዩ ሰፍሮ ደሙን መጠጠው።
ቀና ብሎ በአጠገቡ የወደቀውን የአህያ ሬሳ አሞራዎች ሲግጡት አየ። የቀረው ልቡ በድንጋፄ ተመታ። የእርሱ እድል ከአህያው ሬሳ ዕድል ቀጥሎ ሆነ። በስካሩ ምክንያት እስከ ዘላለም ድረስ ከአህያ ሬሳ እንደማይሻል ተረዳው። ነገር ግን የአሁኑ መረዳት ለምን ይበጀዋል? ማወቅ የሚያስፈልግበት ጊዜ አልፏል።
በሕይወቱ ሳለ እንደወደቀ ያህያ ሬሳ መነሳት አልቻለምና በተራው አሞራዎቹ ዓይኑን ሊመነቁሩት ነው። ሥጋውን በልተው ከጨረሱት በኋላ አጥንቱን ሊግጡት ነው። ሌሊት ደግሞ ቀበሮዎች ሊረፈረፉበት ነው። ይህን እንዲያመልጥ ለመሸሽ ከወደቀበት ሊነሳ እያቃተተ ሞከረ። ባልተቻለው ጊዜ ግን ተጋደመ።

በደሙ ላይ እንደተጋደመ አራት ቀኖች አለፉ። እግሩ እንደ ቀርበታ ተነፋ። እንደ ቅጠልያ ያለ እዥ ወረደው። ከወደቀበት ያነሳው የመንግሥት አምቡላንስ ባገኘው ጊዜ ፈጽሞ በስብሶ ነበር።

ዶክቶር ክሪመር ባዩት ጊዜ ከሰማይ በታች ሊደረግለት የሚችል ሕክምና ምንድር ነው? ደሙ አልቋል። በሽተኞችን ለመርዳት በጎ ፈቃድ ካላቸው ሰዎች የተለገሰውን ደም ለሚሰክር ጥጋበኛ አልሰጥም። እርሱን መንካትም መርዙ ያስፈራል። ከዚህ በፊት ይህ እንዳይደርስበት እንዳይሰክር ብዙ አስጠንቅቀነው ነበር አሉ።
ከንፈሩ ተንቀሳቀሰ። ላብ በፊቱ እንደ ውሀ ፈሰሰ። ለመናገር ጣረ። በመጨረሻ ግን መናገርም ሳይሆንለት ቀረ።
ሐኪሞችም የገማውን ልብሱን ገፈፉት። እንደ ቅባትም ያለ መድኀኒት ቀቡት። ከግማሽ ሊትር የበለጠ ደም ሰጡት። በመጠጥ ከተጐዳው ከልቡ ድካም የተነሳ ኤተር ለመቀበል አለመቻሉን ከተረዱ ዘንድ የሚያፈዝ መድኀኒት ጀርባውን ወግተው ሰጡት።
አንዱ ሐኪም ከጉልበቱ ይቆረጥ አለ።
ሌላው ግን ሁለተኛ እንዳይሰክር ከቂጡ አስጠግቼ እቆርጠዋለሁ አለና ከቂጡ አስጠግቶ ቆረጠው። የተቆረጠውን እግሩን ከፊቱ መዝናችሁ አስታቅፉት ብሎ አስታማሚዎችን አዘዘ።
እግሩን ከፊቱ መዘኑትና አሥር ኪሎ የሆነው እግርህ ይኸውልህ ታቀፈው ብለው አስታቀፉት።
በዚህ ጊዜ በአጥንት የተጣሉት ውሾች በላዩ ላይ ተረፋረፉበትና በድንጋፄ ከእንቅልፉ ነቃ።
ይህ ሁሉ የደረሰበት በህልሙ እንደነበር ማወቅ አቃተው።
ከአልጋው ላይ ወረደና ገረዱን ወይዘሮ ጥሩነሽን ከመኝታቸው ቀስቅሶ እየጮኸና እየተንዘረዘረ፣
“ስንት እግር ነው ያለኝ?” ብሎ ጠየቃቸው።
ወይዘሮ ጥሩነሽም፣
“ዱሮ ስንት እግር ነበረዎ ጌታ?” ብለው ጠየቁት።
እየጮኸ ሦስት ጊዜ፣
“ሁለት ሁለት ሁለት ነበረኝ” አላቸው።
ሦስት ጊዜ ሁለት ስድስት ማለት ነው።
“ልጆቼን ያሳደገች ላም ካራት እግር የበለጠ አልነበራትም። ሰለዚህ የእርስዎም እግሮች አራት ናቸው” አሉት።
“የምሬን ነው የምጠይቅዎ!” አለና ጮሆ ተንዘረዘረ።
“በእርግጥ ሁለት እግሮች አሉዎት ጌታ” አሉት።
ተበጀ እግሩን አጐንብሶ ለመሳም ሞከረና ራቀው። ወደ ሰማይ እያየ፣
“መጠጥ ማለት ለእኔ ሞት ማለት ነው” አለ።

ጊዜውም ሌሊት ነበር።

“እንደዚህ የማሉበት ሌሊት ያልፋል” ብለው ወይዘሮ ጥሩነሽ መለሱለት።
ተመስገን ገብሬ
1940 ዓ.ም
(በደራሲው ቤተሰብ መልካም ፈቃድ ለአንድምታ የቀረበ)

〰〰〰ተፈፀመ〰〰〰



@abipoem
@abipoem

Читать полностью…

"ኢ ቶ❤️ዮጵ" ግጥም(በAbi)

የጉለሌው ሰካራም
(በተመስገን ገብሬ)
ክፍል....፮

የጠጣም እነደሆነ ከሁለት መቶ ዓመት በፊት ይደረግ በነበረው የአረመኔ ቅጣት እጁና እግሩ ከመቆረጥ ይደርሳል ብሎ አላሰበም። አናጢ የጠረበው እንጨት ከቅልጥሙ ይቀጠላል ብሎ ክፉ ህልም አላለመም። አንድ ሰካራም አንካሳ በአንድ ዓመት ስንት የእንጨት እግር ይጨርሳል ብሎ ስለ ዋጋው አልተጨነቀም። ደህና ምቾት ያለው አንካሳ ለመሆንም ገንዘብ ያስፈልጋል።

አንካሳው ሰው ሰካራም እንደሆን በእንጨት እግሩ በሰላም ጊዜ ይሄድበታል። በሁከት ጊዜ ደግሞ ይማታበታል። ሲማታበት ይሰበራል ሲሰበርም ሌላ የእንጨት እግር መግዛት ያስፈልገዋል። ስለዚህ የእንጨት እግር የሚሰሩ አናጢዎች ለደንበኞቻቸው ትርፍ መጠባበቂያ እግር በሜንጦ ሰቅለው ያስቀምጡላቸዋል ይባላል። ተበጀን እንደዚህ ያለ ሕይወት አያጋጥመውም።

በበቀለች ዓምባዬ መጠጥ ቤት ደረጃውን ተራምዶ ተበጀ በገባ ጊዜ የጥንት ወዳጆቹ ሰካራሞች በእቅፉ ላይ ተነባበሩ። እንደተወደደ መሪ በጫንቃቸው ላይ ተሸክመው እየተቀባበሉት በእልልታ ጮሁ። ከመጠጥ ቤት ጠፍቶ የነበረው ተመልሷልና በሰካራሞች ሁሉ ዘንድ ደስታ ሆነ።
እንኳን በደህና ገባህ! የመጠጥ ጠርሙሶቹን እንደ ዘንባባ ይዘው ተቀበሉት። ቁማርተኛው ያረጀ ግሪክ እየሳለ ተናገረ። ሁሉም በደስታ ይጮሁ ስለነበረ አንድም የሰማው የለም። ረስቶት የነበረው መጠጥ ጣዕሙን ገና ሳያውቀው ገና ከጫንቃቸው ሳይወርድ በጩኸቱም በመጠጡም ተበጀ ሰከረ።
ከጫንቃቸው ወደ ቁልቁል ጣሉት።
የሕፃንነትህ ዘመን አልፏልና ራስህን ችለህ መሄድ ይገባሃል አሉት። ሰማህ? አቅም አንሶህ መሄድ አቅቶሃል እንደ ካንጋሮ እየዘለልህ መሄድ ትችል እንደሆነ ምርኩዜ ይኸውልህ ብሎ አንካሳው በየነ አቀበለው። ምርኩዙን ለመያዝና ለመጨበጥ እጁን ሲዘረጋ በግምባሩ ከበሬት ላይ ተደፋ። እንደወደቀም ሳለ፣ እስኪነቃ ድረስ በመካከሉ ስንት ሰዓት አልፎ እንደነበረ ለማስተዋል አልቻለም።

የመጠጥ ቤቱ እመቤት ጊዜ አልፏልና ከውጭ ጣሉትና ቤቱን ዝጉት ብላ አዘዘች ።
ይቀጥላል
.
.
.


@abipoem
@abipoem

Читать полностью…

"ኢ ቶ❤️ዮጵ" ግጥም(በAbi)

#አደን
( ደበበ ሰይፉ )
:
አሳዳጄን አመለጥኳት
አመለጠችኝ ያሣደድኳት።
ኗሪ ሆንኩኝ እንደፍየል
በነብርና በቅጠል መሀል።

አቤት አለች ያልጠራኀት
የጠራኀት ድምፅም የላት።
ራቂኝ 'ምላት ጎኔ ወድቃ
ቅረቢኝ ምላት ከኔ ርቃ።

አንዴ ስታደን አንዴም ሳድን
እረፍት አጥቼ ስባክን
የዕድሜዬን ጀምበር ብታዘባት
ልትጠልቅ ምንም አልቀራት።

✍ደበበ ሰይፉ፣ ለራስ የተፃፈ ደብዳቤ



@abipoem
@abipoem

Читать полностью…

"ኢ ቶ❤️ዮጵ" ግጥም(በAbi)

እምብዛም ዝምታ ለበግም አልበጃት
ሃምሳ ሆነ ቆማ፣ አንድ ነብር ፈጃት።


@abipoem
@abipoem

Читать полностью…

"ኢ ቶ❤️ዮጵ" ግጥም(በAbi)

#ጥቁር_ብርሃን

ከራስ እውነት አንፃር
የሌሎችን እውነት ፥ ገድለው ለተነሱ
ፀሐይ ስትከስም..
አይናቸው ለሚያዝ ፥ ፅልመት ነው ለነሱ።
ፀሐዩዋን
ፋኖሷን
ጧፍና ሻማዋን
ያንፖል ብርሐኗን ፥ ለምትለኩስ ሐገር
ስለማይቻላት
አንዱን ሳታከስም ፥ ጨለማን ማባረር
ብርሃን አይመሥላትም ፥ ያልነደደ ነገር።
ጨለማው አይነድም!
ከራስ እውነት አንፃር ፥ ሌላን ካልገዘቱ
“ጨለማ ነው” ያሉት….
ጥቁር ብርሐን ነው ፥ ለሚመለከቱ።
አንዱ ምሽት ያለው ፥ ላንዱ ነው ንጋቱ!
ሁሉ በቦታው ላይ
እውነትነት አለው !
በሌላ አንፃር ሲታይ ፥ ውሸት የሚመስል
ፀሐዩዋ ስትነድ
ላንዱ ጨለማ ነው ፥ የሚታየው ምስል
ላንዱ የሚታየው
ጥቁር ብርሐን ነው ፥ ጨለማ ሲከስል፡፡

✍ በላይ በቀለ ወያ


@abipoem
@abipoem

Читать полностью…

"ኢ ቶ❤️ዮጵ" ግጥም(በAbi)

የጉለሌው ሰካራም
ክፍል .... ፭

ይህ ሁሉ ውርደት እና ርክሰት ነው እንጂ ክብር ከቶ አይደለም። እንግዲያውስ ክቡር ድሀ ነው። ገንዘብ ስለሌለው ራሱን መግዛት ይችላል። ባለጠጋ ደግሞ መናኛ ተራ ነው። ገንዘብ ስላለው ራሱን መግዛት አይችልም። ይህን ሁሉ አሰበ። ስለኖረ ባይማር እንኳ ብዙ ከማወቅ ደርሷል።

“ባለጠጋ ሆነ ወይም ድሀ፣ ሰው ከራሱ የበለጠ መሆን ይገባዋል” አለ።

ቤቱን ከሰራ ከአምስት ወራቶች በኋላ ጀምሮ ተበጀ መጠጥ ከቶ አልጠጣም። ስለቤቱ ክብር መጠጥ እርም ነው ማለት ጀምሯል። ያለፈውንም ዘመን መራርነት እያሰበ ተንገፍግፏል። አንድ ብሎ ለመጀመር ከወደቀበት ትቢያ አንስቶ ዕድሉን ሲያራግፍ እንደ ራእይ ያያል።
ያበላሸው እድሉ አሳዘነው፣

“በዚህ እድሜየ ሁሉ ሚስትም አላገባሁም ልጅም የለኝም” አለና አዘነ።

ውሾቹ እየተባሉ ሲጫወቱ ተመለከተና፣

"አመሌ ውሻ ነበርና ከውሾች ጋር ኖርሁ” ብሎ ራሱን ረገመ።

በውሾቹ ፈንታ አሁን በዚህ እድሜው ልጆቹ ዙሪያውን እየተጫወቱ ሲፈነጩ ባየ ነበር እንዲሁ አሰበ።

ቀልድና ወዘበሬታ ስለሚያውቅ እንደዚህ እያለ ይቀልድ ነበረ፣

“ጐጃም የአበባውንና የግራር ማሩን ይጭናል። የተጉለትና የአምቦ ወረዳ ጌሾውን ያቀርባል። የሆላንድ የቢራ ፋብሪካ ቢራውን ያወጣል። የኢጣሊያ ፋብሪካ ነቢት ያፈላል። መደቅሳና ዘቶስ በግሪክ አገር ይጣራል። በስኮትላንድ ዊስኪ ይጠመቃል። ይህ ሁሉ የሚደረገው በአራዳ የሚቀመጡትን እንዳይጠማቸው ነው። በዚህም ምክንያት በዋሻዋ እንደምትጮህ ጉጉት ሰካራሞች በከተማይቱ ይጮሃሉ።

“በደብረ ሊባኖስ ግን ድምጡን ዘለግ አድርጎ የሚናገር ወፍ እንኳ የለም። ውሀ እንኳ የሚጠጣ በመቅኑን ነው። በአራዳ ይሁን ወይም በገዳም ምንም ገንዘብና ቤስቲን ለሌለው ውሀ ደግሞ እጅግ አድርጎ ይጣፍጣል።”
ይህን የመሰለ ቀልድ ይቀልድ ነበረ።
ሰካራሙ ተበጀ ግን ገንዘብ እያለው ውሀ ጣፍጦታል። ልዩ በሆነው በዚያ ማታ ወደ አልጋው ወጥቶ በተኛ ጊዜ መጠጥን እርም ካደረገው አንድ አመት ከዘጠኝ ወር ከዘጠኝ ቀን እንደሆነው ጊዜውን ቆጥሮ አወቀው። ጊዜውንስ ማወቅ ለምን አስፈለገው? “እንደ ጥንብ መጣያ ትንፋሼ ተበላሼ፤ አፌም እንደ እሬት መረረኝ። ሹልክ ብዬ ዛሬ ብቻ፣ ጥቂት ብቻ፣ አንድ ጊዜ ብቻ፣ እኔ ብቻ፣ ብጠጣ ምን ይጐዳል” ብሎ ተመኝቶ ስለነበረ ነው።

ነገር ግን ወደ አልጋው ወጥቶ ተጋደመ። ከተጋደመም በኋላ ተነሥቶ ወደ መጠጥ ቤት ለመሄድ ከባድ ከነበረው እንቅልፉ ለመላቀቅ ታገለ። በመጨረሻ ወደ መጠጥ ቤት በሄደ ጊዜ በውኑ ወይንም በህልሙ እንደነበረ ራሱም ተበጀ አላወቀውም።
ይቀጥላል........



@abipoem
@abipoem

Читать полностью…

"ኢ ቶ❤️ዮጵ" ግጥም(በAbi)

( ኤፍሬም ስዩም )


.
.
.
አቤቱ...

የብቸኝነት ጣዕም አሳየን
ምክንያቱም
መንጋ ሆነን የምንኖር አዲስ ሀሳብ የራበን ነን።

አቤቱ...

ዓይናችንን መልስልን
ምክንያቱም
በአበቦች ልብ ላይ እሾህ በትነናል
የበተነው እሾህ እኛኑ ወግቶናል
ግና ክፋታችን የወጋንን እሾህ ከእግራችን ሳንነቅል
እርሱን ወግቶታል ወይ ብለን ጠይቀናል
በዚህም አፍረናል
ስለ ፍቅር ፅፈን ፍቅርን እረግጠናል
ላሳብ ለቃላችን ባዳዎች ሆነናል
አቤቱ ይቅር በል፡፡

✍ኤፍሬም ስዩም... ኑ ግርግዳ እናፍርስ


@abipoem
@abipoem

Читать полностью…

"ኢ ቶ❤️ዮጵ" ግጥም(በAbi)

የጉለሌው ሰካራም
ክፍል .... 4
ጎረቤትህን እንደነፍስህ ውደድ ቢባልም ሰዎችን እነ እቲላን ነበር እንጂ የእቲላን አሳማዎች አልነበረም፡፡ እቲላ ጎረቤቱ አሳማ አርቢ ነው፡፡ የውሃው ሙላት ነጥቆ ወስዶ የነበረው የእቲላን አሳማ ሳለ ያላዩትን ቢያወሩ ግድ የሌላቸው ሰዎች የሾገሌን ገረድ ውሃ ወሰዳት ብለው አውርተው የተበጀ ነፍስ በአንድ አሳማ ነፍስ ሊያስለውጡት ነበር፡፡
መልካሙ የሰማዕትነት ሥራው ሁሉ ደግሞ እንዲሁ ርካሽ ሆኖ የሚቆጠር የሆነበትh ዘወትር የሚሰክር ሆኖ ስለታወቀ ነው፡፡ በሞራልም (ግብረ ገብነት) መሠረት አደረግሁት የሚለውን ሁሉ ሳያውቀው እንደሚያደርገው ይቆጥሩበታል፡፡ ‹‹ በጎ ሥራህን ሁሉ በትኩስ መቃብር ውስጥ አፈር አልብሰው አንተ ሰው ሁን ሚስት አግባ ልጆች ይኑሩህ›› ይሉትና ይዘልፉት ነበር፡፡
ድኃ ቢሆን ወይም ባለጠጋ ሰካራም ቢሆን ወይም ትኅርምተኛ ሁሉም የጉለሌ ልጆች ነን አባታችንም ጉለሌ ነው ብሎ ራሱን ሚያኮራ እርሱ ተበጀ ብቻ ነው፡፡
ከሚያሰክር ሁሉ ትኅርምተኛ ለመሆን ብዙ ጊዜ አስቦ ነበር፡፡ ሰክሮ ያደረበት ሌሊት አልፎ ብርሃን በሆን ጊዜ ከእንግዲህ ወዲህ ‹‹መጠጥ አልቀምስም›› እያለ በየቀኑ በብርሃን ተበጀ ምሏል፡፡ በነጋዉ የበለጠ ጠጥቶ የባሰ ሰክሯል፡፡ ለመስከር ይጠጣል፡፡ ደስ ያለው እንዲመስለው ይጠጣል፡፡ ብስጭቱን የሚረሳ መስሎት ይጠጣል ይህ ነው ተበጀ፡፡
‹‹ ይህን መስከርህን ካልተውህ ላንተ አበ ነፍስ አልሆንህም›› ብለው የመጀመሪያ ንስሐ አባቱ ብዙ ከመከሩት በኋላ መንፈሳዊ ልጅነቱን ከርግመት ጋራ አስወግደውታል፡፡
ገረዶቹም ለርሱ ተቀጥሮ መሥራትን ከውርደት ቆጥረውት እየነቀፉት ሄደዋል፡፡ ‹‹ መጠጥ ካልተውህ አናገባህም›› ብለው በየጊዜው ለጋብቻ የጠየቃቸው የነበሩ በቁመናው አሰናብተውታል፡፡ በሰንበቴ በማኅበርም ማኀበርተኛ ለመሆን የጠየቃቸው ነፍሱን ሳይቀር ንቀውታል፡፡
ይህ ሁሉ በእርሱ ዘንድ ከኢምንት አይቆጠርም፡፡ ያሉትን ቢሉ እርሱ ምን ቸገረው ገንዘብ እኮ አለው፣ ገንዘቡም ጥሬ ብር ነው፡፡ ባለጠጋ ነው፡፡ መስከርም የባለጠጎች ነው፡፡ ትኅምርተኛ መሆንም የድሆች ነው፡፡ እንደ ልዩ አመፅ አድርገው ለምን በእርሱ ይቆጥሩበታል? እንዲህ በተከራከረ ነበር፡፡
ነገር ግን ልዩነት አለው፡፡ እርሱ ብዙ ጊዜ ሰክሮ አውቶሞቢል በላዩ ላይ ሒዶበታል፡፡ ሰክሮ በበነጋታው ከእንቅልፉ ሲነቃ ብዙ ጊዜ ከእስር ቤት ውስጥ አድሮ ራሱን አግኝቶታል፡፡ በጉለሌ መንገድ ዳር ባሉት በብዙ የውሀ ጉድጓዶች ሰክሮ ገብቶባቸው እየተጮኸ ጉለሌ አውጥቶታል፡፡ ሰክሮ የጎርፍ ውሀ ከወሰደው በኋላ ብዙ ጊዜ እሳት አደጋ ደርሶለታል፡፡ ሰክሮ ከቤቱ መድረስ እያቃተው ከወደቀበት ባቡር መንገድ ሳይነሳ ብዙ ጊዜ ጎርፍ በላዩ ላይ ሲሄድበት አድርዋል፡፡
ይቀጥላል
.
.
.
.


@abipoem
@abipoem

Читать полностью…

"ኢ ቶ❤️ዮጵ" ግጥም(በAbi)

ህል - ፈተ ኣለም

ደረሰ ይሉናል አለም ማለፊያዋ ፣

የሰው ነገር ዋ ፣
ጊዜው መቼ ገና ፣
መች ደረሰና።
ሰው ነው በገዛ እጁ የራሱ መፍረሻ
ሌላ .....ነገር ሲሻ
አይበቃኝም ብሎ፣ ሲሰስት ሲሻማ
የሌሎቹን ኣለም፣ ሲናጠቅ ሲቃማ
ይፈጥራል ጦርነት......
ይጠዛጠዛሉ ኣለማት ካለማት።

ከመሬት ጨረቃ ከጨረቃ መሬት
.......ያቶሚኩ ርችት
ይለካል - ይመጣል
የከዋክብት መስመር ጉዟቸው ይናጋል።

እየተፋለሰ ኣንዱ ኮከብ ካንዱ
ኣለማት ሲፈርሱ፣ ኣለማት ሲናዱ
ህልፈት የሚመጣው
ወዮ! ያን ጊዜ ነው።

✍ገብረክርስቶስ ደስታ



@abipoem
@abipoem

Читать полностью…

"ኢ ቶ❤️ዮጵ" ግጥም(በAbi)

ስማን የበግ ጌታ ስማን የበሬ አምላክ
ከተኩላ ጠብቆ
አርዶ ማይበላንን እረኛችንን ላክ!!!

✍ በላይ በቀለ ወያ


@abipoem
@abipoem

Читать полностью…

"ኢ ቶ❤️ዮጵ" ግጥም(በAbi)

የጉለሌው ሰካራም
ክፍል ... ፫

የጠርሙሱ መጠጥ ሁሉ እስኪያልቅ ድረስ ከዚያው ከዛፉ ሥር ተቀምጦ ያን ጠንካራ ትምባሆውን ከአፉ አለየውም፡፡ በሳቅ ጊዜ ብቻ መልሶ ዝም እስኪል ድረስ መጠጡ ወይም ትምባሆው ከአፉ ያቋርጣል፡፡ የመጠጥና የትምባሆ ጊዜው ተበጀ ይህ ነው፡፡ማለዳ በቀዝቃዛ ውሃ ታጠበ፡፡ ቋንጣም እንቁላልም ጠበሰና በዳቦ በላ፡፡ የጦም ቀን ነበር ‹‹ ለአባ ተክለ አረጋይ አልናገርምና ነፍሴ ሆይ ግድ የለም አለ››፡፡ የነፍስ አባቱን ማለቱ ነው፡፡ ምናልባት በዓመት እንኳ አንድ ጊዜ ጠየቋቸው ወይም ጠይቀውት አያውቁም፤ እርሱንም አያደርሰውም፤ እርሳቸውም ከበዓታቸው አይወጡም፤ አንዳንድ ጊዜ የዛሬውን እሑድ ዕረፍት አደርገዋለሁ ያለ እንደሆነ እግሩን ደኅና አድርጎ የሚታጠብበት ቀን ማለት ነው፡፡
ደክሞት ነበርና ደኅና እንቅልፍ ተኝቶ ነበር፡፡ ዝናሙን ነጎድጓዱን ጎርፉን ውሃ ምላቱን አልሰማም፡፡ አንዳች ነገር ሰማ፡፡ ዘፈን እና እልልታ የሰማ መሰለው፡፡ ትናንት ከጠጣው መጠጥ ኃይል መሰለውና ይህስ ዕብደት ነው እንጂ ስካር አይደለም አለና ተመልሶ ተኛ፡፡
እንደገና አዳመጠ፡፡ የእርዳታ ጥሬ ጩኸት ሰማ፡፡ ከ አልጋው ዘልሎ ከወረደ በኋላ ቤቱን ለመዝጋት ጊዜ አላገኝም፡፡ በትልቁ ወንዝ ዙሪያ ቁመው ይጮሁ የነበሩ ሰዎች የውሃው ምላት የሾገሌን ገረድ እንደጠለፋት ነገሩት፡፡ ጎርፍ የወሰደው ሾገሌን ራሱን ቢሆን ወይም የሾገሌን ገረድ ለተበጀ ማዕረግ ምኑም አይደለም፡፡
‹‹ ገረዲቱን እናንተ በመጨረሻ ያያችኋት ወዴት ነው? ›› ብሎ ጠየቀና እየጠለቀ በዋና ይፈልግ ጀመር፡፡ ስለ ሾገሌ ገረድ በትኩስ ውሃ ሙላት ለመግባት አንሠዋም ያለው ጉለሌ በዳር ተሰልፎ ቁሞ ተበጀን ይመለከት ነበር፡፡
ብዙ ጠልቆ ከቆየ በኋላ ብቅአለና
‹‹ አገኝኋት መሰለኝ ›› ብሎ በዳር ላሉት ጮሆ ተናገረ፡፡ ለሰው ሁሉ ደስታ ሰጠው፡፡ ከሁሉም ይልቅ እርሱን ደስ አለው፡፡ የጠለቀውና የዋኘው ረጅም ጊዜ ስለሆነ ደክሞት ነበር፡፡ ነገር ግን ሊያወጣት ይገባዋል፡፡ ጠለቀና አገኛት፡፡ በአሸካከሙ ላይ ጥበብ ያስፈልጋል፡፡ አለዚያስ የውሃው ሙላት እንደገና ይነጥቀዋል፡፡ እንደተሸከማት ውስጥ ለውስጥ ዋኘና ከዳር ብቅ አለ፡፡
ከሸክሙ ክብደት ኃይል የተነሣ ወዲያው ወደቀ፡፡ እርዳታ ተነባበሩለትና ጎትተው እርሱንም እርሷንም አወጧቸው፡፡
ተበጀ ተንዘራግቶ በብረቱ ውጋት እያቃተተ የጉለሌ ሰው በሳቅ ሲፈነዳ ሰማ- ከራሱ በኩል ቀና አለና ‹‹ ሴትዮዋ ድናለች? ›› ብሎ በርኅራሄ ድምፅ ጠየቃቸው፡፡
አንዱ ቀረበና ‹‹ አሳማ ነው ያወጣኸው ›› አለው፡፡
የሚያቃትተው ተበጀ ከወደራሱ ቀና አለና ‹‹አሳማ?›› ብሎ ጠየቀው፡፡ ‹‹ ለመሆኑ ከእናንተ ውሃ የወሰደባችሁ ሰው ነበር ወይስ አሳማ ኑርዋል? ›› ብሎ ተበጀ ጠየቀና ያቃትት ጀመር፡፡
ይቀጥላል .....

@abipoem
@abipoem

Читать полностью…

"ኢ ቶ❤️ዮጵ" ግጥም(በAbi)

የነብርን ጅራት ...
┈┈•✦•┈┈
ወድጄሽ ... ወድጄሽ
ወድጄሽ ... ወድጄሽ
እንደገና ጀመርኩ
ሀ ብዬ መውደዴን
ተረት የሚቀይር
ተመልከቺው ጉዴን
"ሲኖሩ ሲኖሩ ሞቱ" ሲል ተረቱ
ኑሬ ኑሬ ኑሬ - እንዳዲስ ተወለድኩ - እኔ ያንቺ ገልቱ።
እንኳንም ተወለድኩ
እንኳን ሳትኩኝ አቅሌን
እንኳን አፀናሁት ... ላንቺ ያልኩት ቃሌን
እንደ ነብር ጅራት ስምሽን አንቄ
እንደ ርሃብ ስንቅ ፍቅርሽን ደብቄ
ያ'ሽሙር የተረቱን ስንክሳር ሳልፈራ
እንቅ ፍቅርሽን - እንደ ነብር ጭራ
ሙጭጭ ካንቺ ጋራ!!
ጥብቅ!!
"ጅልና ወረቀት
የያዘውን አይለቅ"
ብለው ቢሞግቱሽ
አትከራከሪ ሐሰትም የለበት
ወረቀት ልቤ ላይ
ጅል ፍቅርሽ ነውና የተከተበበት!!
እንቅ እኔ ጅሉ ...
እንቅ እኔ ሌጣው እኔ ወረቀቱ፣
ያዝ ለቀቅ የለም ለፍቅር ሲሞቱ
እ ን ቅ!


@abipoem
@abipoem

Читать полностью…

"ኢ ቶ❤️ዮጵ" ግጥም(በAbi)

የጉለሌው ሰካራም
ክፍል ... ፪

እንግዲህ መንገደኛው ሁሉ ‹‹ ይህ የማን ቤት ነው ? ብሎ ሲጠይቅ የተበጀ ሊባል ነው ›› አለ፡፡
ቀጥሎ ደግሞ ‹‹ ተበጀ የትኛው ነው ሲባል ዶሮ ነጋዴው ሊባል ነው ›› አለ፡፡
‹‹ ዶሮ ነጋዴው የትኛው ነው ›› ሲባል ያ የጉለሌው ሰካራም ሊባል ነው፡፡ አወይ፤ እኔ ተበጀ፤ ተበላሽቻለሁ አለና ደነገጠ፡፡ ከዚህ በኋላ ስለቤቱ ክብር እንኳ መጠጥ መተው ይገባኛል አለ ፡፡
መጠጥ ለመተው ያሰበበት የመጀመሪያ ጊዜው ይህ ነው፡፡ ሰካራምነት ጉዳት መሆኑ ተሰምቶት እንደሆን ይናገር ስለ ቤት ክብር ማለቱ ግን ወደ ዳር ይቆይ፡፡ ስለ ቤት ክብር ምን ያውቃል? ዶሮ ነጋዴው ተበጀ ሰካራሙ ተበጀ አይደለምን ?
ሰካራሙ ተበጀ የሰራውን የገዛ ቤቱን ከፍቶ ገበና ኩራዙን አስቀምጦ ክብሪቱን ለመጫር ሲያወጣ በሐሳብ ተሰቅዞ እንደዚህ አሰበ፡፡ መምረጥ አለብኝ፡፡ ከዚህ ቤት ያለው መጠጥ ሁሉ አንድ ሳይቀር እየወጣ ይፍሰስ፤ ከዚህ በኋላ ክብሪቱም ኩራዙም በቤት ይደር፤ በአዲሱም ቤት ብርሃን ይዙርበት፡፡ አለዚያም በአዲሱ ቤት መጠጥ ይዙርበት፤ ኩራዙም ክብሪቱ ከቤት ይውጣና ይፍሰስ፡፡ ሊደረግ የሚገባ ከሁለቱ አንዱ ነው እንጂ፤ በሰካራሙ ተበጀ ቤት መጠጥና እሳት በአንድነት ይህች ውሸት አለና ሳቀ፡፡
ከሁለቱ አንዱ ለማድረግ ሳይቆርጥ መብራቱን አቃጠለና ተቀመጠ፡፡ እንደገና ደግሞ እንደዚህ አሰበ፡፡ አያድርገውና ዛሬ ሰክሬ ይህ ቤት ቢቃጠልብኝ አመዱን አይቶ በሰካራሙ ተበጀ ላይ ለመሳቅ ድፍን ጉለሌ ነገ ከዚህ ነው የሚቆም ! ጉለሌ ምን ባለኝ? ወሬ ከማቡካት በቀር ጉለሌ ምን ሥራ አለው; ለአዲስ አበባም የስድስት ወር መሳቂያ በሆንኩ ነበር፡፡ መንገድ አላፊዎችም ነገ በዚህ ሲያልፉ አመዱን አይተው ይህ የተቃጠለው ቤት የማን ነበር ሲሉ የተበጀ ሊባል ነው፡፡ በሰካራሙ ተበጀ ቤት መጠጥና እሳት ባንድነት ይህች ውሸት !
ወደ ውጭ እንደ እርም ወርውሮት የነበረውን የመጠጥ ጠርሙስ ሁሉ በጨለማው ዳብሶ አንድ በአንድ ለቃቀማቸው፡፡ አንዱን ግን ቀና አደረገና ከአፍንጫው አስጠግቶ አሸተተው፡፡ በጠርሙሱ ቅርፅ የመጠጡን አይነት አወቀው፡፡ ዊስኪ ነበርና ስለዚህ ነው ሰው እንዳይሰማ ቀስ ብሎ የሳቀ፡፡ የጠርሙሱን ግማሽ ከጠጣ በኋላ ግን በአፉ ቡሽ ቢወትፍበት ለሳቁ መጠን የለውም፡፡
‹‹ ጉለሌ ተኝቷልና ከዚሁ ከባሕር ዛፍ ሥር ቁጭ ብየ ብጠጣ የሚታዘበኝ የለም›› አለና አሰበ፡፡ እውነቱን ነው፡፡ ጉለሌስ ተኝቶ ነበር ነገር ግን አሁን እርሱ ጠጥቶ የሰከረ እንደሆነ ጉለሌን ሊቀሰቅሰው ነው እርሱ ከጠጣ በጉለሌ ማን ይተኛል?
ጠርሙሱን ከከፈተው በኋላ ብርጭቆ ያስፈልገው እንደነበር ትዝ አለው፡፡ ሶስት የሚሆን ደኅና ጉንጭ ጠርሙሱን ከአፉ አስጠግቶ ጨለጠ፡፡ ከዚያ በኋላ የሚጠጣበት ብርጭቆ ሊያመጣ አሰበ ከዚያ በኋላ ደግሞ በሶስት ጉንጭ ምን ያህል ጠርሙሱን ቀና አድርጎ በጨረቃዋ ተመለከተ፡፡ ‹‹ግማሹን ያህል ሰርጉጀዋለሁ›› አለና በሳቅ ፈነዳ፡፡ ‹‹ ለዚህችስ ብርጭቆ ማምጣት አያሻም›› እያለ ጠርሙሱን አምቦጫቦጨው፡፡ በቀኝ ክንዱ መሬቱን ተረክዞ የቀረውን ጅው አድርጎ ወደ ውስጥ ወረወረው፡፡ ባዶውን ጠርሙስ ደግሞ በጁ እየጠነቆለ ‹‹አንተን ደግሞ ለአንድ ዶሮ ለውጩ ሞያ እይዛለሁ የዊስኪ ቅርፍቱም ዋጋ አለው አይጣልም›› አለ፡፡
‹‹እንዲሁ ሲጠጣ ሌሊቱን አጋመሰው፡፡ ቀጥሎ ከእግሩ በታች የወደቀውን ጠርሙስ እየቆጠረ ይህን ሁሉ እንደጠጣሁት አላምንምና በጉለሌ አፈርሳታ ይደረግልኝ እነናቄ እነተሰማ አጎቴም ይጠጣሉ›› አለ፡፡

ይቀጥላል
.
.
.

@abipoem
@abipoem

Читать полностью…
Subscribe to a channel