ከጠዋት ጣይና - ከጨረቃ ብርሃን ?
ከፊያሜታና - ከሸገሯ ሮማን ?
እንዲህ ያለው ምርጫ
ደስታ ነው እርግማን ?
በረሃብ አይደለም
በሲኦል አይደለም
ፈጣሪ 'ሚቀጣህ
ምርጫ እየሰጠ ነው ደስታ የሚያሳጣህ ።
Hd
@
❤️💋በፍቅር ልሸኝህ🤦♀🤦♀
ጊዜ እንደማይቆመው ሰአትን ጠብቆ
ማለዳ ለቀትር ቦታውን አስታጥቆ
ደቂቃዎች ሰአት ቀናትና ወራት
ለአመት ሲያዘግሙ በራሪ ሰከንዶች
መርቄ ልሸኝህ ነበርን ተክቼ
ትላንቴን ዛሬዬን አሁኔን እረስቼ
ለካ ነበርን ማለት እንደዚ ይከብዳል
ያ ሁሉ ትዝታ እንዳልነበር ያልፋል
በሂወት መወሰን መደሰትም ያልቃል
ሳቅም ተቀይሮ እንባ እንኩዋን ይደርቃል
ለካ ነበርን ማለት እጅጉንም ያማል
ምክንያት አልባ ሲሆን ውስጥንም ያደማል
ቢለያይ ስሜቱ የሁለት አንዳችን
ህመሙ ቢያጋድል አንዱ ላይ ቢገንም
ሚዛኑ ቢዛነፍ ለብይን ባይሆንም
ከሳሽም ተከሳሽ ሆኜ ቀርቤአለሁ
ደስ ያለህን ፍረድ ደስ ያለህን በይን
ይግባኝ አልጠይቅም ያሻህንም ተግብር
ባይሆን .......................
ፍቅርህን በቃላት በተግባር ስትገልፀው
መውደድንም ችለህ በእምነት ስትኖረው
ይህን ሁሉ አይቶ ለሽሽት መቅረቤ
ይቅርታ ለራሴ
መውደድን መቀበል ለተሳናት ልቤ
ላልታደለች ነብሴ
አሺ በቃ hubi መርቄ ልሸኝህ
ፍቅር እሚያፈቅረው ልዩ ማንነትህ
ከደስታ አጣምሮ ሳቅህን ያብዛልህ💔
@hikpoem
@hikpoem
@jemthelast
@abipoem
✍Hiku neberku/neqe
ተፃፈLe amar
Date30/10/2014
ያ አላህ‼
========
(እስኪ ሁላችሁም ሼር አድርጉት! አንድ ወንድም አሳዛኝ መልዕክት ነው የላከልኝ!)
||
✍ ይህ በፎቶው ላይ የምትመለከቱት ህጻን ሐምዛ ደመቀ ይባላል። እድሜው 13 ዓመት ነው።
ዘዉዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል እናቱን ሲያስታምም ቆይቶ ከሁለት ቀን በፊት ሐሙስ ዕለት ግንቦት 04, 2014 E.C. ጠፍቷል:: ዛሬ ግንቦት 06, 2014 E.C. እናቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች። ነገ ግንቦት 07, 2014 E.C. የእናቱ ስርዓተ ቀብር ይፈጸማል። እርሱ ግን የለም። መቼም እርሱ አስተማሚ የሆነው ሌላ ቅርብ ቤተሰብ ወይም የደረሰ ልጅ ቢጠፋ ነው!
አዲስ ሰለምቴዎች ናቸው። ከመስለሙ በፊት ስሙ ዮሐንስ ነበር።
እባካችሁ በፍጥነት በማፋለግ እርዱን ብሎኛል። ምናልባትም እናቱ ነገ ቀብር ከመግባቷ በፊት ቢደርስ መልካም ነው። ያማል በጣም! አላህ ይዘንላት። ማረፊያዋን ጀነተ-ል-ፊርደውስ ያድርግላት። ለልጇም ሶብርንና ጽናትን አላህ ይስጠው።
የፈላጊ ስልክ: 0911251194
እባካችሁ ሁላችሁም በየግሩፑ፣ በየገጹ በሁሉም ማኅበራዊ ሚዲያ ሼር አድርጉላቸው!
🔗SHARE 🔗SHARE
╔════════════╗
☪ JOIN: @islam_in_school ☪
☪ JOIN: @islam_in_school ☪ ╚════════════╝
አስታውስ🤔🤔
ከማድረግህ በፊት ሁልጊዜ አስታውሰው
በቀንም በለሊት ለአፍታም አትርሳው
የስሜት ማእበል ናላህን ቢያዞረው
ያ አለባበሷ ቀልብህን ቢያስጥል
ተስረቅራቂ ድምፁዋ ጆሮህ ላይ ቢያቃጭል
የሽቶው መአዛ ልብህን ቢያውደው
ሎሚ ተረከዙዋ አይንህን ቢወስደው
አማይሆን ስሜት ውስጥ ዘው ብለህ አትግባ
ይልቅ ነቃ ብለህ .............
ከ 2 ሀሳብ ጋር እራስህን አግባባ
የአላህን ትዛዝ በደንብ አስተንትነህ
አይንህንም ስበር ከፊትና ሊያድንህ
በዘላቂው አለም ዘውታሪ ሊያደርግህ
ይህን ሀሳብህን በሀላል አድርገው
ትዛዙን አክብረህ በኢህላስ ፈፅመው
........ከዛ ሁለተኛ የምታስታውሰው
የእናትህን ሳቅ ደጋግመህ አስበው
ሳቋን አስረስተህ ሲቃዋን አታብዛው
ባንተ ያላት እምነት ጨርሰህ አታጥፋው
እናማ ወንድሜ ምክሬን ተቀብለህ
ለኔ ብለህ ሳይሆን ለራስህ አስበህ
የውድ እህትህን ሂወት አታበላሽ
በራስህ ህሊና እራስህን ከሳሸ
ከመሆንህ በፊት የችግሮች ቀማሽ
ለራስህ ጊዜ ስጥ ውሳኔህን አኑር
ካለህበት ነቅተህ ሂወትህን አሳምር
@hikpoem
@jemthelast
@abipoem
✍Hiku neberku/neqe
.......Date 2/12/2011
ከሀይማኖት በፊት (ሰውነት)
✍ ካሊድ አቅሉ
~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~
ገሎ የፀደቀ የለም ባንተ መፅሀፍ የለም
በእኔም እምነት
ምነው መገፋፋት የጋራ ሀገርን የኔ ብቻ
ማለት
ተው መኖር ያግዝፈን ወጊ አገኘው ብሎ
ይቁም ጦር መሰበቅ
ክንዴ ያስፈልግሀል አብረው ሲቆሙ ነው
የሚጎላው መድመቅ ።
.
.
.
እርስቴ ነው አትበል !
ቅዬ ነው አትበል !
ከኔ እምነት ውጪ አይንካው አፈሩን
ብለክ አትገዘት
ሆኖም እኮ ያውቃል እውነትን የሚያስንቅ
የተከበረ ሀሰት ።
ከሀይማኖት በፊት . . . .
ከአውራጃ ቀድም
አምላክ ሰውነትን ጥንት ሲያበጃጀው
ህግጋት አስቀምጥዋል መስመር
የሳተውን በእሳቱ ሊፈጀው !
ሌላ እምነት ይጥፋ የኔ ብቻ ይኑር
አያዋጣም ከቶ
ምኑን ታውቀዋለህ የአብራክክ ክፍያ
ሊኖር እንደሚችል ሌላ እምነት አግብቶ
መደምደም ገዳይ ነው።
እምነት ያዝን ብሎ ከኪዳኑ መራቅ
ተጫዋች ከሌለ ቀልድም መርዶ ይሆናል
ወዝ አልባ ነው መሳቅ
የእሱን እሩቅነት ጠንቅቆ ያወቀ ዳናውን
ሚከተል
ማንሳትን ይሰብካል እንኳን በ ሰበብ
ተራማጅን ሊጥል
አንሺነት እንማር ከኔ በፊት ቀድሞ እኛነት
በቀየው ከዙፋን ይቀመጥ
መለካካት ይቁም ጠባሳ ነው ትርፉ አጉል
መረጋገጥ ።
~ ~ ~ ~ ~ ~ ~~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~
@KALIDakelu
ለአፍታ☄
ከል❤️ብ ካልሆነ አትጠቀመው/ሚው🙅♂
ብዙ ጊዜ ሰዎች የሚወዱትን ለማስደሰት ብለው ይዋሻሉ🤷♂ ለምሳሌ ፍቅረኛዬ ሳልናፍቃት በጣም ነው የናፈከኝ ትለኛለች የሚገርመው ግን ከንግግሯ ይልቅ
ተግባሯ " አልናፈከኝም እንዳይከፋህ ብዬ ነው" ብላ አፍ አውጥታ ትነግረኛለች አውቄባታለሁ ከልቧ ሲሆንና ለአፍ ብቻ እንደናፈኳት ስትነግረኝ😞
ናፍቆት ምንድነው? አንድን ሰው መናፈቅ ማለት በሰው ዙሪያ ተከበሽ አጠገብሽ ያሉትን አስረስቶሽ ያ ሰው በአይምሮሽ ሲመላለስ .በልብሽ መላ ማንነትሽ ያን ሰው አምጪው አምጪው ሲልሽ እንጂ ስራ ሳይኖርሽ እና ሰው ስታጪ ትዝ የሚልሽ አይደለም🤦♂
አንድ ሰው ሲናፍቅሽ ስራዬን ንደኞቼን ማለቱን ትቶ በአገኘው አጋጣሚ አንቺን ለማግኘት ለማውራት የማይቆፍረው የማይወጣው ተራራ አይኖርም እወድሻለሁ፣ናፍቀሽኛል እነዚህ ሁለቱ ነገሮች ከልብ ካልሆኑ ያሳምማሉ💔
ከልብ ካልሆነ አትጠቀመው/ሚው🙅♂
💞ግጥምጥሞሽ💞
@abipoem
@abipoem
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
ክፉም ንጉስ መጣ
ደግም ንጉስ መጣ
ብቻ ግን ያልፋሉ ፣ ሁሉም እንደመልኩ
ይብላኝ ከህዝብ ጋር
ለሚጣሉ ህዝቦች ፣ መሪ እያመለኩ !!!
@abipoem
@abipoem
🙀🙀ሰሜት ሲበረታ🥱🥱
ከጭልመቱ ሂወት ጭጋግ ከወረሰው
በጭቅቅት ጉድፍ ህሊናው ከራሰው
በፅልመት ተውጦ በወንጀል ካደፈው
ድንበርን ተላልፎ እይታን ተዳፍሮ
ከሰዎች ሀያ አድርጎ ከእይታ ተሰውሮ
በስሜት ተመርቶ በእሳት ተጫውቶ
ወላፈን ሳይፈራ ሰውነቱን ስቶ
እዝነትህን ሸሽቶ ቅጣትህን ንቆ
ክልከላን ገፍትሮ ከራሱ መንጭቆ
የራሱ ፈጣሪ እራሱ አስመስሎ
በስሜቱ እና በሴጣን ተታሎ
ህያው ሙታን ሆነ ነብሱ ተበክሎ
በራሱ አለም ላይ ስሜቱ አይሎ
መቀጫውን ሲኦል አድርጎ ተሳለ
ከጀሀነም ውጪ ቦታ ስለሌለ
በመረጠው ቦታ ከሲኦል ተጣለ
@abipoem
@hikpoem
.........Hiku neberku/newe
Date 28/07/2014
💫አብዛኞቹ ሰዎች እነዛ በልብህ ላይ ትልቅ ቦታ የምትሰጣቸው በህይወትህ ውስጥ ትልቁን ፀፀት እንድትፀፀት ያደርጉሀል💫
@abipoem
@abipoem
ለጁምኣችን!🤗
ሩሚ ህፃን እያሉ ነብዩ ሙሀመድ ሰ.ዐ.ወ ከቤት ወጥተው እንደጠፉ ይነግረናል ፤በምናቡ!
' ያኔ አንደበታቸው እንዲተባ ፣ መልካምነትን ከገጠሩ ይማሩ ዘንድ ለ ሀበሻዋ ሀሊማ በአደራነት ተሰጥተዋል :: አንድ ቀን ጠፉ ፤ ሀሊማም ተጨንቃ ፍለጋ ትወጣላች ...
ያ ሙሀመድ
ያ ሙሀመድ
በጥሪዋ መሀል ነው..ያንን የሚያሰገመግም ድምፅ የሰማችው
እንዲህ ነበር ሚለው
Do not grieve he will not be lost to thee; Nay, the whole world will be lost in him.
አትዘኚ ! አትጨነቂ ! አለም በርሱ ውስጥ ቢጠፋ እንጂ ፤ እርሱ ካንቺ ርቆ ሊጠፋ አይችልም "
~
ሸጋ ጁምኣ!!💚💛❤️
@abipoem
@abipoem
ሀ. ሁ. ሂ. ሃ. ሄ. ህ. ሆ
ለ. ሉ. ሊ. ላ. ሌ. ል. ሎ
አፌ ምጣድሽ ላይ ተንከባልሎ
ፊደል ፍቅርሽን ቢቀምሰው
ምላሴን ጥላሸት ወረሰው !!
,,,
@abipoem
@abipoem
የስም ቀለም ጠፍቶ የዘመን ገፅ አድፏል
ከስንት እልፍ ተራማጅ ቆሞ ቀሩ ያልፋል
ትነፍሳለች ፀሀይ ይሞቃል ደመና
እየኖርኩ ያለሁት ካቻምናን እን አምና
እናምልሽ ደ'ሞ
ለስንት ተሰባሪ
ወድቆ ነው ሚነሳው
የሚሉት እንቅፋት ምክር ይደመጣል
የት ያየነው ሁሉም የት ቦታውን ሳይለይ ለመውደቅ ይመጣል
እኔ በዚህ መሀል
ከመቆም አልታረቅኩ
ካለማሰብ ፍቺ
ይኸውልሽ ዛሬም
እንዳዲስ ኖራለው
ዛሬም ለይ ስለንቺ
እና ግን እወቂ
የጠራሽ ለት እንደው
የፍቅር ወዘና
የትዝታ ስበት
አለሁኝ በናፍቆት
በስጋ ጥለሽኝ
በነፍስ ካለሽበት
ትመጪአለሽ አይደል?
ልጅ አማን
@Zefrata
💞💞💞ተፈቃሪዬ❤️❤️❤️
እንደ ለሊት ሰላም ውስጥ እንደ ሚያድሰው
የጀምበር ወገግታ ቀን እንደ ሚያፈካው
የጠዋቷ ፀሀይ በጅግ ተናፋቂ
ልክ እንደ ህፃን ሁልጊዜ አኩራፊ
የቀትሩ ሀሩር ሁሌም ጉልበተኛ
በፍቅር ምተሀት የታየ አስማተኛ
መበገርን ማያውቅ ሽንፈት ያልዳበሰው
ሁሉን ተቆጣጥሮ እጅን በሚያሰጠው
በተሰጠው ልኬት በስልጣኑ ቀመር
የቀትሩ ሀሩር ከቶም አይበገር
ፀሀይን ስጠራ ፀሀዬን አስታወሰኝ
በኔ ላይ ጀግኖ እኔነቴን ቀማኝ
ህልሜንም ሰውሮ እሱን አሳለመኝ
ኮልታፋ አንደበቱን ሳቢ ፈገግታውን
ማራኪ ሳቁን ውብ ማንነቱን
ደስ ከሚል እብደት የተገኘ ልቡን
ለፀሀዬ ጥላ ከለላ ብፈልግ
ለካ የኔ ፀሀይ በጥላ አይከለል
ልደብቅህ በቃ አሙ የኔ ልኡል
ልከልልህ ብዬ ሆንኩልህ ጨረቃ
ማንም ላይጋራኝ ላቶነኝ ፈረቃ
የተፀነሰ ፍቅር መወለድ የራበው
የታፈነ ናፍቆት ፍንዳታ የቀረበው
እልፍ አእላፍ ናፍቆተረ በልቤ ተከትቦ
ሊገለኝ ነው መሰል .................
አማሬን አምጪ ብሎ አንገብግቦ
አንድ ፀሀይ ብትኖር ለአንድ ጨረቃ
ምድር ብትከለል በብርሀን ታጭቃ
ኮከቦች ቢኖሩ እይታ ሚያዛቡ
ከፀሀይ አርቀው ጨረቃን ሚስቡ
እይታዬን ጋረድኩ ከፀሀይ እራኩኝ
ባንተ ውብ ነብስ ስር እራሴን ሰወርኩኝ
መዳጁ ልቤንም አንተን ያስወደደው
መውደዴን ወደድኩት ...........
በፍቅርህ ተማርኮ ምርኮኛህ የሆነው
ዛሬ በእቅፍህ በጅህ እንዳለሁኝ
ቃልንም ግባልኝ ፍቅርህን አሳየኝ
ሀላልህ አድርገህ በጉድለትህ ሙላኝ
ደስታችን ይሟላ እንሁን አንድ አካል
ሸይጣን ከኛ ይራቅ በኒካህ እንከለል
ከቤተሰብ ዘመድ በዱአ አስወጣኝ
እኔነቴን ወስደህ አንተነትን ስጠኝ
✍ hiku
neberku/ neq
ተፃፈ .......
le amar
date 17/10/2014
@hikpoem
@jemthelast
@hikpoem
@abipoem
❤️❤️ልብህን አደራ🙏🙏
ደስ የሚል ማንነት አስደሳች ልቦና
የራስ ልዩ ጥበብ ገራሚ ስብእና
ፍቅርን የሚያኖር በ እፁብ ሰረገላ
በ አማን በደስታ ሰርክ የማይላላ
በብዛታ ማይሰለች በማነስ ማይደበዝዝ
ቅንጣት ፍቅር ቀምሶ ልብን የሚመርዝ
እኔነትን ለቆ አንተነትን መያዝ
በእንጭጩ ልቤ በአፍታ ልጅነት
ተፈቅሮ አፍቅሮ ባላየው ጊዜያት
ድንገት ብትከሰት ልቤን ብትረታ
ወደቁ ተሸነፍኩኝ መኖሬም ተረታ
ስቀርብህ ስትርቅ ስርቅ ስትቀርበኝ
ደስታህን ለማየት ደስታዬን ሲያሸሸኝ
ልብህ ወድጄ ፍቅርህን አምኜ
ከፍቅርም በላይ ማፍቀሬን አፍኜ
ከመውደድም በላይ ውዴታዬኝ ችዬ
ደስታን ልሰጥህ ደስታዬን ገድዬ
መኖርን መረጥኩኝ ባንተ ተከልዬ
ዛሬ ሀዘን ደርሶ በኔ ሳይሳለቅ
ፍቅርህ ልቤ ገብቶ በደማቁ ሳይደምቅ
አውቃለሁ አምናለሁ .............
መውደድ ማይሰለች ንፁ ልቦናህን
መስዋት ከፋዩ አፍቃሪ ልብህን
ዛሬን እየኖሩ ነገን የሚያስናፍቅ ሳቢ ፈገግታህን
ጆሮ ላይ ሚያቃጭል ውብ አንደበትህን
እውነትን የሚኖር ልዩ ማንነትን
ዛሬ ልብህ ዞሮ ብትሆን ደንዳና
ፍቅርህ ከጉም ተኖ ስሜትህ ቢፀና
ከቶም አልከስህም ጎድተኸኛል ብዬ
ደሞም አልጠላህም በፈጣሪ ምዬ
ባይሆን ልብህ አደራ!!.........
ጠብቃት በብዙ አኑራት በደና
ክፍት ቦታ መተው ፈተና ነውና
አጥብቀህ ጠብቃት ልብህን አደራ
በችግር በደስታ በሀዘን መከራ
ህልምህ እውን ሆኖ ደስታህ ተንሰራፍቶ
ሳቅህን ያሳየኝ ፈጣሪ አሳክቶ
የኛ እህል ውሀ አልሰመረም እና
አትርሳኝ አልልም መቼም ሰውነህና
ግን እንደ ትላንቱ አስታውሰኝ አልልም
ጥላቻንም ፍቅር መሸከም አልችልም
በዝምታ ልርሳህ እራሴን እስካገኝ
የመውደዴን ብስራት ፅድቁን እስከማገኝ።።
@abipoem
@abipoem
@hikpoem
@hikpoem
✍Hiku neberku/neqe
Date 11/09/2014
🌜🌜እንዘጋጅበት🌛🌛
ሁሉም ሲጠብቃት ወረፋውን ይዞ
ትንሹም ትልቁም በጭንቀት ተክዞ
በእኩል ሰአት በእኩል ደቂቃ
በአለም ላይ ያሉ ፍጥረታት በሙሉ
በ አንድ ትእዛዝ መጥፋት እየቻሉ
ጊዜ መጠበቁ ለምን ነው አትሉ
መጠየቁ ቀርቶ አታስተነትኑ
እኛ እኮ ነን ታዲያ የሰሚ ደንቆሮ
ሰምቶ ማይተገብር የደነዘ አይምሮ
እኛ እኮ ነን ታዲያ የሚያወራ ዲዳ
በውሸት በለፅገን እውነት የሆነብን እዳ
እኛ እኮ ነን ታዲያ የሚያዩ እውሮች
ሀቅ ተገልፆልን ባጢልን መራጮች
እኛ ማለት እኮ ተጓዦች ነበርን
ስንቅ ለመሰብሰብ ወደዚ የተላክን
ትእዛዙ ተረሳ ልባችን ቸፈተ
በዱንያ ፍቅር ሀራም ተሸመተ
ታዲያ አሁንም ...................
ሁሉም ይጠብቃል ወረፋውን ይዞ
አንዳንዱ አስታውሶ ሌላው ደሞ ፈዞ
ፈጣሪ ትግስቱ ጥበቡ ስፋቱ
ማጥፋት እየቻለ ሁሉን በቅፅፈታት
እድል ይሰጠናል ልንለወጥበት
ታዲያ ነቃ ብለን እንዘጋጅለት
ወረፋ እስኪደርስ ስንቅ እናበጅለት
@hikpoem
@abipoem
@jemthelast
✍Hiku neberku/neqe
.......Date 8/11/2012
🔥🔥 ሞት እኮ ክብር ነው🔥🔥
ጭፍን አስተሳሰብ የጠበበ አይምሮ
ጭልመት የጋረደው ደንቁሮ ታውሮ
ሰውነትን ሳይኖር ሰውነት የከዳው
ጀናዛ ላይ ቆሞ ስቆ ሚጨፍረው
ምን አይነት እብደት ነው
እኮ ምን አይነት ዝቅጠት
በሙስሊሙ ደም ላይ ስልጣንን ማቆየት
ባይሆን አትነካኩን
ሞት እኮ ክብር ነው ያውም ሸሂድነት
በረመዳን ወር ከአላህ መገናኘት
ፍላጎታችንም ምርጫችን እሱ ነው
መኖር ምንፈልገው ለሸሂድነት ነው
አኛ እኮ ሙስሊም ነን ሰለም የለበስን
አይደለም ለሰው ልጅ
ለእንስሳ ለእፅዋት እጅግ የምናዝን
በእምነት በሀገር ቀልድንም የማናውቅ
የምድር አሳማሪ አንባሳደሮች ነን
አጉል ባለማወቅ በጭፍን ብትጓዝ
በጅምላ ጨፍጭፈህ ሰይፍህንም ብመዝ
እንኩዋን ዛሬ ቆመን ትላንትም ያልወደቅን
የጥንት አባቶችህ አፄዎች ሲያጠምቁን
ከአገር አባረው ኦና ሲያደርጉን
ያኔም ያልተበገርን እኛ ውስሊሞች ነን
ታሪክ ልድገም ብለህ ዛሬ ብትወራጭ
መስኪድ በማቃጠል በደም ላይ ብትራጭ
ሴቶችን በመድፈር በሲቃ እንባ ብትስቅ
በምስኪን አዛውንቶች እንዳሻህ ብትሳለቅ
ከሳሪው አንተ ነህ ሞት እኮ ክብር ነው
በስለት ማይገኝ ሸሂድነት እድል ነው
ነገር ተገላብጦ ቢሆንም አዙሪት
ዱንያ ላንተ ጀነት ለኔ ግን ሲኦል ናት
ስልጣንና ሀብትን ከምቶደው በላይ
ልጅና ዘርህን ከምታፈቅረውም በላይ
እኛም ሞታችንን እናፍቀዋለን
ዲናችንን ተነክቶ ሂወት ነው ሚያስጠላን
ግን
ዝም ብለን አንሞትም
የአላህ ቤቶች ፈርሰው አንላቀቃትም
ቁርሀኖች ተቃጥለው ዝምታን አናውቅም
በኡለሞቻችን አንደራደርም
በቃ አትነካኩን
ብዙ ጊዜ ብንችል ፍራቻ ቢመስልም
ክብራችን ሲነካ ወደ አላህ ብንሸሽም
ከፀብ ለመራቅ እጅግ ብንሞክርም
አልተው እያላቹ .................
........በቆሰለ ቦታ እንጨት ሰደዳቹ
ሳንፈልግ ጠርታቹ ሞክሩን አላቹ
ዝምታው ሲሰበር ከጩኸት ይገዝፍል
ሂወት ጣሙ ጠፍቶ ሞትን ያስናፍቃል
ለጀነት ቤታችን ሞታችን ናፈቀን
የዱንያን ሂወት ጀነታችሁን ጥለን
እናተ ለሂወት እኛ ለሞታችን
ዘብን እንቆማለን ዲናችንን ይዘን
በአላህ ታግዘን በአንድነት ደምቀን!!!!
@hikpoem
@hikpoem
@abipoem
@jemthelast
✍Hiku neberku/neqe
......Date 20/08/2014
remedan 27/1443
ይሄው እስቃለሁ!
(አሌክስ አብርሃም)
ስትታበይ ነበር
አይጨክንም ብለሽ …
ልቡ አይችልም በኔ
ረሳሁሽና ፍክት አለ ቀኔ !
ይሄው እስቃለሁ…
ከመርፌ እስከአልጋ
አውጥቸ በተንኩት
ሳንዱቅ ሙሉ ፎቶ ሰብስቤ አነደድኩት
ጠረንሽ ከሰመ፤
ትዝታሽ ወደመ!
ይሄው እስቃለሁ…
እፎይ ቤቴ ፀዳ ካዚማም ትዝታ ካናዋዥ ናፍቆትሽ
ግና በሄድኩበት ፊቴ ሚጋረጠው
ምን ነክቶት ነው ሳቅሽ ?
የህይዎት ሸምቀቆ
የብቸኝነት እጅ
አንቆ ሲያስጨንቀኝ
ዓይኔ እንባ ሞልቶ እንኳ
ሳቅሽ ነው ሚያስቀኝ !
@abipoem
@abipoem
💫💫የአራህማን ጥሪ💨🌫
ነብሴ ተበክላ በወንጀል ታጭቃ
ጌታዋን ዘንግታ ከሀራም ተዘፍቃ
ከሰላት ተገታ ከቁርሀን ተራርቃ
ካንተ የምድር ቤት ............
........... ከመስኪድ እርቃ
ከነብዩ ሱና ከትዛዛቸውም ....
............እጅግ አፈንግጣ
ከሙታንም በታች ሆነች አጎብጣ
አይኔ ሀራም አይቶ ልቤ ከሻፈተ
ልቤ ሀራም አልሞ ደፍሮ ከዘመተ
እጄም ተከትሎ ጥፋት ላይ ተጣለ
እግሬም ተንደርድሮ ከወንጀል አከለ
ምላስ ከከንፈሬ በወንጀል ታጭቆ
................. በእሳት እየማለ
ከከባኢር ወንጀል እሱም ላይ ተጣለ
ያንተን ጥሪ ሰምቶ ጆሮዬ ያልነቃ
በውዱ ሰአትህ በአዛኑ ደቂቃ
አንተ ስትጠራኝ እኔ ስፈረጥጥ
ለአንተ በተባለች በውዷ ሰአትህ
.........በወንጀል ውስጥ ስሰምጥ
የ 1ድ ቀን ሳይሆን መለያዬ ሲሆን
በአዛኑ ሰአት በወንጀል መኳተን
እጅግ አዝነህልኝ ሰአቷን ብወፈቅ
ልቤ እጅግ ደንድኖ ከአለትም ቢደርቅ
........አንተ ግን አዛኝ ነህ......
በአዛኑ ጥሪ ልቤ ባይደነግጥ
ልዩ እድል ሰጠኸኝ መንፈስ የሚያቀልጥ
እዝነት እና እራህመትህ ምድርን በሞላው
በወደድከው ወር አንተ በመረጥከው
ቁርሀን ወደ ምድር በክብር በላከው
ለረመዳን ጋብዘህ ስሜቴን አወድከው
የውዴታህ መጠን ከወንጀሌ ከዝፎ
የእዝነትህ ልኬት ከምድር ተላልፎ
ይቅርን ልትለኝ በጅግ ልታቀርበኝ
ካደፈ ሂወቴ ጭልመት ልታርቀኝ
እድሌን አስፍተህ ረመዳንን ወፈከኝ
ምን ያህል ብቶደኝ ከቶ ብታዝንልኝ
1ዴ ሳልገዛህ ፍቅርህ የማይርቀኝ
ኢላሂ ............
በረመዳኑ ወር ምድር ባበራችው
ደሞ በለሊቱ .............
የበፊቱን ፀሀይ በሚያስንቅ ውበቱ
መአዛው በሚያውድ በመስኪዱ ድባብ
ክብርህን በሚያጎሉ በጀመአው ሸባብ
የ 1ቀን ለሊት 70ሺ ባረከው
አንተን እንድገዛ እድልን የላከው
ምን ያህል ብታዝን እጅግ ብትወደኝ ነው
ከስንት ባሮችህ እኔን የመረጥከው
አምና የነበሩ ዘንድሮ ጎለዋል
ትላንት የታዩ ዛሬ ላይ ጠፍተዋል
እረመዳንን የናፈቁ ናፍቀውት ቀርተዋል
ሊደርሱበት ሽተው ሳይደርሱ ሄደዋል
ታዲያ ያ ኢላሂ እኔን የመረጥከው
ወንጀል እጅግ በዝቶ ስላካለለኝ ነው
በተውበት እንድድን ስለመረጥከኝ ነው
የአዛኑን ጥሪ እንድመልሰው ነው
ጥሪህን ሰምቼ እንድታዘዝህ ነው
አልሀምዱሊላሂ ላንተው ለመረጥከኝ
ሙስሊምም አድርገህ ረመዳን ለቸርከኝ
ከወንጀል ለመዳን ተውበት ለወፈከኝ
@hikpoem
@hikpoem
@abipoem
@jemthelast
✍Hiku neberku/neqe
.......Date 12/08/2014
remedan 19/1443
ሲፈቀር የሚባል...
.
"ፈገግ ስትዪ...
ጥርስሽ ምስራቅ ሆነኝ ፣ የፀሐይ መውጫ በር
ከሳቅሽ ሰማይ ላይ ...
ንጋቴን አያለሁ ፣ ተሰቅላ እንደጀንበር።
አንቺ ስትስቂ...
የጨረቃ ገላ ፣ እስኪያልቅ ይሸረፋል
"ሙሉ"
"ግማሽ"
"ሩብ"
እያለ ይጠፋል
ኮከብ እንደ ቅጠል ፣ እግሬ ስር ይረግፋል።"
ብዬሽም አልነበር?
..................................
"ስታኮርፊ ደሞ
ነፍስሽ ምእራብ ነች ፣ መውጫ ለጨለማ
ከኩርፊያሽ ሰማይ ላይ...
ምሽቴን አያለሁ ፣ ንጋቴን ስቀማ።
አንቺ ስታኮርፊ...
ሳቅሽ ሚያደርቃቸው ፣
"ኮከብ ነን" ባይ ሁላ ፣ ይድናል ከመርገፍ
ጨረቃም ሙሉ ነች...
ዳግም ስትስቂ አይታ ፣ ገላዋ እስኪሸረፍ
እስከዚያው ድረስ ግን....
ምን ጨለማ ቢገዝፍ፣
ትንሽ ብርሀንን ፣ አይችልም ማሸነፍ!!"
ብዬሽም አልነበር?
...................................
"ስትስሚኝ ደግሞ...
መለኮት ከንፈርሽ ፣ ከንፈሬን ሲያጠምቀው
ምኔ እንደተነካ ፣ሳይገባኝ ሳላውቀው
ከገነት ደጃፍ ነው ፣ ደርሼ ምወድቀው።
ሲኦል ከቆመ ነፍስ ፣ ገነት የወደቀ አይደል የሚፀድቀው!!?"
ብዬሽም አልነበር?
ግን በቃ አትመኚኝ!!
ይሄን ሁሉ ያልሁሽ...
ስለጠፋብኝ ነው ፣ ልልሽ ያልሁት ነገር!!!
.....................................
አሁን ግን የምልሽ...
"ልቤና አንደበቴ ፣ አይተዋወቅም
አፍቃሪና እውነት....
ሩቅ ለ ሩቅ ናቸው!
ሰማይ ከምድር ላይ ፣ ያን ያህል አይርቅም
ሳፈቅርሽ እንዲህ ነኝ...
የምልሽ ሲጠፋኝ ፣ ያልሁትን አላውቅም!!!
ግን አፈቅርሻለሁ።"
እያልሁሽ አልነበር?
የማይባል የለም! ፣ ይባላል ሲፈቀር!!!!
👉 በላይ በቀለ ወያ
@abipoem
@abipoem
❤️💋ሀላሌ💔❣
ሳየው ደስ የሚለኝ ሀሴት የሚሰማኝ
ወንዳወንድነቱ ሁሌ ሚማርከኝ
በልኬ የተሰፋ ልክክ ያለብኝ
ከሁሉ አዳም ዘሮች ጎልቶ የሚታየኝ
ሳላውቀው በሩቁ ሁሌ ሚናፍቀኝ
በረጅሙ አለም የሚያንከራትተኝ
ባገኘው ብዬ ነው
ጊዜው ካደረሰኝ
መንገዴን ጠቁሙኝ ሀላሌን እንዳገኝ
ከሀራም እርቄ እንቁ ሆኜ ልታይ
በዱንያም ባሄራ ሙሽራ ሊያደርገኝ
ጀነተል ፍርዶስ ላይ አድርጎ ሊሾመኝ
ሀቆን ተወታለች ብሎ ሊያሞግሰኝ
እሻለሁኝ እና ሀላሌን ጠቁሙኝ
ሀቁን ተወጥቼ ሽልማትን ላግኝ
@abipoem
......✍Hiku neberku/nege
Date 9/03/2013
አባባ ፍቅር
ልቤ ላይ ጨክኜ፣
ላውጣበት ወይ እስር፣
ወይስ ልቆንጥጠው፣
ገብቼ ጭኑ ስር፣
ዝም ብሎ ያፈቅራል፣
በቀን ዘጠኝ አስር።
@abipoem
@abipoem
🌹
ረ መ ዷ ን
🌹
ርህራሄ ሰጋ ለብሶ
ሰላም ፍቅር ሐሴት ነግሶ
ቂም ጥላቻ ተደምስሶ
ይቅርታ ና ምህረት ፈሶ
ሁለንተናን አሚን ሚያድስ
ነፍስ ጅስምን ሚያረሰርስ
ጀዲድ ጀዲድ
..ባላህ መንገድ
ዱዓ ሰምሮ ሞልቶ ሙራድ
የሀላል ፍም አቀጣጥሎ
የልብ አረም ነቅሎ ጥሎ
ሚያኖር ሩህን አደላድሎ
🌹
ረ መ ዷ ን
🌹
አቤት ደራ የራህመት ወር
የሙዕሚኑን ህመም ሊያሽር
የዛለን ነፍስያ አንቅቶ
ያለፈ ታሪክ ሊቀይር
መጣ ለጉድ ተነፋፍቆ
ተውበት ሰላምን ሰንቆ
ቂም ጥላቻን አሚን ሊያርቅ
ሊደመስስ ገፍላ .. ፊራቅ
ኢብሊስ ታስሮ
ቂም ተቀብሮ
በጨረቃ ድል ተበስሮ
ሚሞትበት መይት ኑሮ
🌹
ረ መ ዷ ን
🌹
ፈተቢኡን ሲል ከላሙ
ሱናውን ሀይ ሆኖ ትልሙ
ዓቢድነት ነው መንገዱ
መቃረቢያ ከወዱዱ
ዘካ ተቅዋ ተውበት ሶላት
የሚታዩበት በፍካት
ጥልቅ ወዴታ እስከ ጀነት
የሷሊሆች ሙነል ሀያት
የሙእሚኖች ሲፋ ድምቀት
...
ያደፈን ቀልብያ አጥርቶ
በኢማን ከፍታ ሞልቶ
ያ'ኼራን ቤት ሊያደላድል
አሰረን በአንድነት ሚክሎል 😍
🌹
ረ መ ዷ ን
🌹
✍ Abi
ይቅር......ታ
"""""""""""""
በትንሽ ጭንቅላት
በእንጭጭ ልቦና ፥የተጣሉ ለታ፤
ዳግም ለመመለስ
ከሰማይ ከፍ ያለ፥ዳገት ነው ይቅርታ!
አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)
@abipoem
@abipoem
አፍታ☄
'ሀይማኖት እንጂ እምነት ከቤተሰብ አይወረስም!
🌿ኪርክጋርድ
ክፍል 2
በህይወት መስከር ነው ፤ በፍቅር መመርቀን
የፊት የፊቱን ኑር ምንድን ነው ሰቀቀን
ህያው ፍጥረት ሁሉ
ያከትርማል አንድ ቀን....
፡
ለኪርክጋርድ የፍልስፍና ቀዳሚ ግብ በሃሳብ ሲራቀቁና መልስ አልባ የሚመስሉ ጥያቄዎችን ደጋግመው ሲጠይቁ መዋል ሳይሆን ተፈላሳፊው በምድር ላይ ውብ እና ትርጉም ያለው ህይወት እንዲኖር ማስቻል ነው።
:
ታዲያ እንዴት እንኑር? ለሚለው ጥያቄ አንድ የተረጋገጠ መልስ ባይኖርም ቀጥሎ በምንመለከታቸው ሶስት ዋና ዋና ላይፍ ስታይሎች ውስጥ በጋለ ስሜት በማለፍ ከኛ ተፈጥሮ ጋር አብሮ የሚሄደውን አኗኗር መምረጥ እና 'ሙሉ ሰው መሆን' ይቻላል ……. ይለናል ኪርክጋርድ።
፡
አዕምሮህ "አይ ክርስትና እውነት ነው ሌሎቹ ሀይማኖቶች እና ሳይንስ ግን ተሳስተዋል" ካለህ …….. Guess what ምክንያቱ በክርስቲያናዊ ማህበረሰብ ውስጥ ማደግህ ነው። the point is ካልገገምን በስተቀር የትኛውንም ህይወት ይህ እውነተኛ እና ብቸኛው መንገድ ነው ለማለት ምንም ማረጋገጫ የለንም።
:
1- The aesthetic (ደስታ - ሀዘን)
፡
በዚህ 'የህይወት ሞድ' ውስጥ ያለ ሰው ዋነኛ ትኩረቱ ደስታና ውበትን 'አሁን' ላይ በጋለ ስሜት ማጣጣም ነው። after all ከትንሽ ግዜ በኋላ እንደሌላው እንስሳ ሁሉ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ግዜ ከምድር ገፅ ላይ እንጠፋለን ። ታዲያ ለዚህ እንደ ጠዋት ጤዛ ወድያው ታይቶ ለሚጠፋ አጭር ህይወት መፍትሄው ቶሎ ቶሎ ማፍቀር እና መደሰት ነው።
፡
በህይወት መስከር ነው ፤ በፍቅር መመርቀን
የፊት የፊቱን ኑር ምንድን ነው ሰቀቀን
ህያው ፍጥረት ሁሉ
ያከትርማል አንድ ቀን! ………..(ኦማር ካያም ትርጉም በውቄ)
፡
ቋሚ ስራ ፤ ትዳር እና ለሌሎች ስሜት መጨነቅ እና የመሳሰሉት ነገሮች ከዚህ የህይወት ፍልስፍና ጋር አብረው አይሄዱም።
በሞዛርት ሙዚቃ ውስጥ የሚገኘውን ዶን ጆንን እንደ አሪፍ ምሳሌ መውሰድ እንችላለን። በአውሮፓ ከተሞች እየዞረ በሺ ከሚቆጠሩ ውብ ሴቶች ጋር የሚተኛ ገፀ-ባህሪ ነው። ዕቅዱን ለማስፈፀም የተለያዩ ማንነቶችን
(ማስኮችን) ይጠቀማል። ያታልላል፣ ይዋሻል አስፈላጊ ሆኖ ካገኘው ሰዎችን ይገድላል ፤ ልክ አይደለም ማለት አንችልም ምክንያቱም ቅድም እንዳልኩት በዚህ ህይወት ውስጥ ብቸኛው የጨዋታው ህግ ለራስ ስሜት እና እርካታ ቅድሚያ ሰጥቶ ህይወትን በተለያየ መንገድ ለማጣጣም መሞከር ነው።
፡
እየቆየ ሲሄድ ግን የኤስቴቱ አኗኗር ድብርት እና መሰላቸትን ይዞበት ይመጣል ይለናል ። ዶን ጆንም በሙዚቃው መጨረሻ አካባቢ በድብርት ሲሰቃይ እንመለከታለን። ሰው አካል ብቻ ሳይሆን አእምሮም ነውና እንደእንስሳ ያገኘውን ከመብላት ከመጠጣት እና ከመዋሰብ ባሻገር የሚኖርለት አንዳች ትርጉም እና አላማ በህይወቱ ውስጥ ያስፈልገዋል። በዚህ ግዜ ታዲያ ከሌላ ምርጫ ጋር ይፋጠጣል። በተለያዩ ቅፅበታዊ ደስታዎች ራሱን እየሸወደ መቀጠል ወይም ወደሁለተኛው የህይወት ስቴጅ መሸጋገር።
፡
2- the ethical (ጥሩ -መጥፎ)
፡
ማህበረሰቡ የሚሰጠውን ህግ እና ሞራል እንደ መንጋው በጭፍን ሳይሆን በምክንያታዊነት መርምሮ ይቀበላል። ጥሩ ቤተሰብ ፣ የተሻለ ዜጋ ለመሆን ይጥራል። ባለችው አጭር የምድር ቆይታ አንድ የህይወት ፓዝ መርጦ በዲሲፕሊን በመጓዝ ታላቅ ማንነት ገንብቶና ትርጉም ያለው ህይወት ኖሮ ለማለፍ ይሞክራል።
፡
3- the religious (ፅድቅ -ኩነኔ)
፡
ሰው ግን ከአካል እና አዕምሮ በላይ የሆነ ዘላለማዊ ህይወትን የሚናፍቅ ነፍስ ባለቤት ነውና (ለኪርክጋርድ) ሙሉ ሰው መሆን የፈለገ ምንም objective ማስረጃ ባይኖርም "በማይታየው" ማመን ይኖርበታል።(leap of faith)
፡
እዚህ ጋር እምነት ስንል ዝምብሎ ቤተ ክርስትያን እና መስጊድ መገኘት እና የዚህ/የዚያ እምነት ተከታይ ነኝ ማለት አይደለም። 'ሀይማኖት እንጂ እምነት ከቤተሰብ አይወረስም' የሚለው ኪርክጋርድ ይህንኑ ለማሳየት ውብ ከሆኑት የመፅሀፍ ቅዱስ ታሪኮች ውስጥ አንዱ የሆነውን የአብርሃምን ታሪክ ያስታውሰናል።
፡
አብርሀም በስተርጅና የወለደውን እና ከምንም በላይ አጥብቆ የሚወደውን ልጁን እንዲሰዋ ታዘዘ….. አላንገራገረም ለሣራ እንኳን ምንም ሳይናገር ቢለዋውን እና ልጁን ይዞ ወደ ተራራው ወጣ።
፡
*እዚህ ጋር አማኞች ራሳችሁን በአብርሀም ቦታ አድርጋችሁ አስቡ። ምን አልባት የሰማው ድምፅ የሰይጣን ቢሆንስ ኖሮ ( in fact ልጅህን ግደል የሚል አምላክ አለ? ) ፣ ነገሮች በተለየ መንገድ ሄደው ይስሃቅን ሰውቶት ከተራራው ቢወርድስ……….. ለሣራ ምን ብሎ ነው የሚያስረዳት? ደጉ አብርሀም ነፍሰ ገዳይ ሆነ ማለት ነው?
፡
አብርሀም የእምነት አባት ነው። ………. እኛስ ግን እምነት አለን?
፡
የኪርክጋርድ ሀሳብ አንዳንዴ የፈጣሪ ትዕዛዝ ከኢቲክስ እና እውቀታችን ጋር ሊጋጭ ይችላል። በዚህ ግዜ ታዲያ ኢቲክሳችንን ወደ ጎን ብለን ለፈጣሪ ትዕዛዝ ቅድሚያ መስጠት ይኖርብናል። ይህም የእምነታችን ማሳያ ይሆናል ነው።
፡
ይበልጥ ፈላስፋውን ለመረዳት ሁለት ታላላቅ መፅሀፎቹን 'Either…..or' እና 'Fear and trembling' እንድታነቡ ጋበዝኳችሁ።
@abipoem
@abipoem
💞💞ስጦታዬ💝💝
የውበት መለኪያ መስፈሪያው ምንድነው
ውበትስ በራሱ እራሱ ከየት ነው
ሁለት አይነት ክፍል ማነውስ የሰጠው
ውስጣዊ ውጫዊ ብሎ የለያየው
አላዩ ይሆናል እኔ ያየሁትን
ውበትን በራሱ የሚያስንቅ ውበትን
ፍክት ፅድት ያለ ንፁህ ማንነትን
..............ሊገለፅ የማይችል
ከቃላቶች ልቆ ከፊደላት መጥቆ
ከአንደበት ማይወጣ ውስጥ ላይ ተጣብቆ
ልብን የሚሰርቅ በፍቅር መንጭቆ
ባልችልም ለመግለፅ ያንተን ውብ ማንነት
ትንቅንቅ ብጀምር ከቃላት ጋር ሙግት
ፊደላት በሙሉ አፍረው ተሰደዱ
ላንተነትህ ውበት ቀድመው አሸረገዱ
ላዳም ዘሮች ሁሉ ምሳሌ ሊያደርግህ
ለምድር የቸረህ አንተ ስጦታ ነህ
@abipoem
✍..Hiku neberku/ neqe
Date 11/07/2014