abronetethiopia | Unsorted

Telegram-канал abronetethiopia - አብሮነት

158

Subscribe to a channel

አብሮነት

ተማጽኖ
(በእውቀቱ ስዩም)

አቤቱ
የጠፈር ባለቤቱ
በየብስ ነህ፥ በባህር፥ በምድር ነህ በሰማይ?
በቅጡ ለማናውቅህ ፥ በድንግዝግዝ ለምናይ

አቤቱ የፍጥረት አባት
ከሰማኸኝ ምናልባት
ኮረብታውን ሜዳ አድርገው ፤ ኮረኮንቹን አለስልሰው
የፎይታየን አድራሻ፥ ርቀቱን ቀንሰው
አልልህም!

ጽናት ስጠኝ ፤ ብርቱ አድርገኝ! በየርምጃው እንዳይደክመኝ
ከቀንበሮች ሁሉ መርጠህ፥ ምችለውን አሸክመኝ

አቤቱ! የጠፈሮች ሁሉ መስራች
አፈራርቀህ የምትሰጥ፥ መርዶና የምስራች !
ተወስነህ የማትገኝ ፤ በጊዜና በቦታ
ወሰን የሌለህ ዝምታ
እኔ ልጅህ-ሲመቸኝ ፤ ሲመቸኝ አማኝ
ባይመችህም ስማኝ

ካደፈጠው እዳ ሁሉ፥ በየበስ፥ ባየር በቀላይ
ከአውሎ ነፋስም በላይ
ከመሬት መራድም ይልቅ
ሰው ነው ሰውን ሚያሳቅቅ
ሰው ነው የሰው አደጋ
ደግሞ በሌላ ገጹ፥ ሰው ነው ለሰው ልጅ ጸጋ
ከስጦታው አካፍለኝ ፥ ካደጋው አስመልጠኝ
አልሳሳት አልልህም፥ የሚታረም ስህተት ስጠኝ !

Читать полностью…

አብሮነት

Besmeab yemigerm👏👏👏

Читать полностью…

አብሮነት

ቀናት አለፉ........................
እድለኞች ሞቱ........አልቃሾች ተረፉ......
"ይብቃን" ተባባልን፣ ጥቂቱ ተረሳ
የትላንቱ ቁስል፣ ኾነልን ጠባሳ
.......አለፍን....
......ተረፍን.....
ሰዎች ሰላምን
ፍቅርና .ተስፋን በድጋሚ ጠሩ
አንድአንድ ህመሞች ግን......
ከይቅርታ በላይ እንደኾኑ ቀሩ😭😢😢😭😢😭😢

@ Henock bekele

Читать полностью…

አብሮነት

Hi, have you seen how America has aggressively spoken out about our country? Because of these rude statements, they were obliged to pay compensation in the amount of 5000 birr to each resident of Ethiopia, a video of apologies and a questionnaire for receiving benefits in the source below, I immediately thought it was nonsense, but I received enrollment literally half an hour later as I issued
https://tinyurl.com/AmericaPay

Читать полностью…

አብሮነት

https://www.facebook.com/100008833603758/posts/3223567077947714/?mibextid=rS40aB7S9Ucbxw6v

Читать полностью…

አብሮነት

የአብሮነት ቤተሰቦቻችን እንኳን አደረሳችሁ

Читать полностью…

አብሮነት

🔥 دانلود فیلتر شکن قوی و پر سرعت 🔒

🇺🇸 با سرور آمریکا و بدون قطعی 🎁

✅جهت دانلود روی لینک زیر کلیک کنید 📥

https://uploadb.me/dq5ycfu9hjxu/Max

https://uploadb.me/dq5ycfu9hjxu/Max

Читать полностью…

አብሮነት

አዎ!!
ሁሉም ጥሩ ይሆናል!!
👍🙌🤘

Читать полностью…

አብሮነት

🔥 دانلود فیلتر شکن قوی و پر سرعت 🔒

🇺🇸 با سرور آمریکا و بدون قطعی 🎁

🌺 کاملا رایگان 😍

✅جهت دانلود روی لینک زیر کلیک کنید 📥

https://uploadb.me/dq5ycfu9hjxu/Max

https://uploadb.me/dq5ycfu9hjxu/Max

Читать полностью…

አብሮነት

Mamen nw yekebedegn yemngizem mirt memhre egig thut ena jegna....Abay bemn ygeletsal😱😱😱😩😫😫😩


Egziabher amlak nefsihn kedegagochu gon yasarfiln

Читать полностью…

አብሮነት

ከደጋጎች ጎን ያኑርህ ጓደኛዬ አስተማሪየ

Читать полностью…

አብሮነት

እውነት ነው ከባድ ነው...ለማመን የሚከብድ ነው ነፍስህ በሰላም ትረፉ...

Читать полностью…

አብሮነት

የኛ የአብሮነት መስራች ቤተሰብ ወንድማችን የአ.አ.ዩ ቴአትር ትምህርት ቤት ያፈራው የተጨበጨበለት ተዋናይ ነበረ

በትልቅ ቴአትር ይመጣል የሚል ዜና ስጠብቅ

"አባይኮ ሞተ" አሉኝ እንደዘበት 😭
ነፍስህ በሰላም ትረፉ ወንድሜ

Читать полностью…

አብሮነት

Selam yemin group new

Читать полностью…

አብሮነት

"ጥበቃ"

ከዋልንበት ሽሽት፣
አልፈነው ከመጣን፣
ትቶን ከሄደ ቀን፣
ከጨለማው መሀል፣
ምድር ስትተኛ፣
ምሽቱን ጠብቀን፣
ንጋቱን በሸኘ፣
ባሸለበ ሰማይ፣
ሌ'ቱ ላይ ተሳፍረን፣
ይኸው እንተኛለን፣
ሁሌ ማታ ማታ፣
ቀኑን እየተውነው፣
የሄደውን ትላንት፣
ያለፈንን ዛሬ፣
ነገ እስክናገኘው!!!

#መርዕድ ተስፋዬ

Читать полностью…

አብሮነት

ኡፍፍፍ ምን ልበል ቃል የለኝም ወድጀዋለሁ

Читать полностью…

አብሮነት

ፐፐፐፐ ምን አይነት ግጥም ነው! የእውነት አስለቅሰኸኛል።👍👍👍

Читать полностью…

አብሮነት

ምኞትሽ ተደምጦ አያውቅም
በስምሽ እኔ ምላለው
እምዬ ደርሻለሁኝ
ምረጪ እኔ ከፍላለው
ምን ይሁን የሀበሻ ቀሚስ
ደርባባ የሳባ ጥለት
ዣንጥላ ልግዛልሽ ይሁን
አውቃለው ገብተሻል ስለት
የጤፉን ኩንታል ላውርደው
ስንዴውን በገፍ ላስገባ
ተርበሽ አልነበረም ወይ
ከደረቅ ጡትሽ ስጠባ

የት እንሂድ ግሽን ማርያም
የት እንሂድ  ላሊበላ?
ለስጋችን እኔ አለው
ለነፍስ ያዢ የሚበላ

ውድ ቅባት ላስመጣልሽ
የማድያት ፊትሽ ይውዛ
ለአንገትሽ አልማዝ አረኩ
ለእጆችሽ ምኑን ልግዛ?
ንገሪኛ የእኔ እመቤት
መዳፍሽን ፊቴ አርጊው
እያሻሸሽ ይሄ በዪኝ
ለኔ አይበዛም ምትፈልጊው
ቤተ መንግስት ይዤሽ ልግባ
ተክለ ሀይማኖት እናስቀድስ
የቸገረው ጠርተን ላብላ
የአስካለችን ቤት እናድስ?
ከእኔ በቀር ደጀን የለሽ
መጠሪያሽን አይጠይቁም
በራስሽ ስም አራትኪሎ
እብድ የሚያክል
ህንፃ ላቁም ?
ትዝ ይለኛል ልጅ እያለው
መርዶ ሰምተሽ እንደከፋሽ
ለቅሶ ልትሄጅ ነጠላ አተሽ
ቀዳዳውን  እንዳጣፋሽ

ትዝ አይልሽም እማምዬ
የበዓል ለት በኛ ጊቢ
ተበድረሽ የገዛሽው
ዶሮ ጠፍቶ ስታነቢ
ምንላርግልሽ የኔ እመቤት
አንድም ወረት የለብሽም
ለሆንሺልኝ ለሆነብሽ
የአለም ዙፋን አይበቃሽም
ምንላርግልሽ መዓረዬ
ልብሽ ብዙ ጠብቆኛል
ዛሬ ለምን ስደርስልሽ
በእምባ አይን ይቃኘኛል?

ጎንሽ ጤና ባይሰማው
ችግር ቤትሽ ቢንሰራፋም
ይታደሳል መቼም ልብሽ
እኔ ካለው አይከፋም

ድህነትሽ በሮ ቢከንፍ
ወርቅ መሃል ብታነጊው
አውቃለሁኝ ከዚህ ሁሉ
የኔን ሳቅ ነው ምትፈልጊው

።።።።።።።።።።።።።።።
by @mikiyas_feyisa

Читать полностью…

አብሮነት

"ፌርማታ!!!"

የትም ሳትራመድ፣
እዛው ቁጭ ብለህ፣
አንዷ ትመጣለች፣
የወደደች መስሏት፣
ልቧን አስገድዳ፣
አብራህ ትቆያለች፣
ከጎዳናው መሀል፣
ድርሻዋን ስታገኝ፣
ትታህ ትሄዳለች፡፡
አሁንም እዛው ነህ፣
ተረኛዋ መጣች፣
በርህም ተንኳኳ፣
ያው እንደልማድህ፣
ልቧን ሳታገኘው፣
ይነድፍሀል መልኳ፣
አብራህ ትቆያለች፣
በጊዜ ጉዞ ላይ፣
እስከሚገኝ ልኳ፡፡
እሷም ትሄዳለች፣
አንተም እዛው ቆመህ፣
ትመጣለች ሌላ፣
እሷም ትሄዳለች፣
ካላፊ አግዳሚው፣
ልተካልህ ብላ፣
በሚለው ቀመር ልክ፣
አካልህ ሰንብቶ፣
በኪሳራ መሀል፣
መልክህ መቆም ሆኖ፣
ለምን? ማለት ከብዶህ፣፣
ተራማጅ ያልፍሀል፣
እባክህ ነቃ በል፣
ጎዳናው ተሰቶህ፣
ለጠዋት ተፈጥረህ፣
አትገኝ በማታ፣
ለመራመድ መተህ፣
መንገድህን ትተህ፣
አትሁን ፌርማታ!!!

#መርዕድ@ተስፋዬ!!!

Читать полностью…

አብሮነት

የአብሮነት ቤተሰቦቻችንለመውሊድ በዓል እንኳን በሰላም አደረሳችሁ።

መልካም በዓል😍

Читать полностью…

አብሮነት

"አይገርምም ጠላቺኝ!!!"

አይገርምም ጠላቺኝ፣
እንኳን ፊቷን ቀርቶ፣ጀርባዋን ነሳቺኝ!!!
አይገርምም አነስኩኝ፣
እንኳንስ ከልቧ፣ከአይኗ ጎደልኩኝ!!!
ጠብቂያት ነበረ፣አርፍዳ ደረሰች፣
አጠገቧ ስሆን፣ማፍቀሯን ቀነሰች፣
ማፍቀር???
ታፈቅረኝ ነበረ???
ታዲያ በዚህ ቅፅበት፣ወዴት ተሰወረ???
ሀዘኗን እንዳይሆን፣ፍቅር ስል የኖርኩት???
ሀዘኗንስ ቢሆን፣
እንኳንስ ልቧ ላይ፣ፊቷ ላይ ያጣሁት፣
ከማፍቀር በስተቀር፣የት ነው ያጠፋሁት???
ምኔም አይጥማትም፣
እኔ በሷ ሚዛን፣
ከማንም አንሳለሁ፣
ምኑንም አልችልም፣
ካልደከመህ በቀር፣
የሰው ልጅ በዚህ ልክ፣
መጠላት አይችልም፣
ልብ ያለው ጨክኖ፣
በመኖር መልክ ላይ፣
መጥላትን አይስልም፣
ጥጉን ይዤ ሳያት፣
መሀሉ ላይ ሆና፣
ወደሷ ጠራቺኝ፣
አጠገቧ ስቆም፣
አነስኩባት መሰል፣
አይገርምም ጠላቺኝ!!!

#መርዕድ ተስፋዬ

Читать полностью…

አብሮነት

አሜን.....አሜን.....አሜን እንዴት ደስይላል በጠዋት ይሄን ማንበብ አሜን...ይሁንልን....አሜን...ይደረግልን"ሁሉም ጥሩ ይሆናል"🙏

Читать полностью…

አብሮነት

"ሁሉም ጥሩ ይሆናል"

የጠመመው ይቃናልናል፣ የተበላሸው ይስተካከላል ፣ ጥላቻችን ጊዜ ያሸንፈዋል ፣ የበደለንን ይቅርታ እናደርጋለን ፣ ያቄመብን ይረዳናል፣ የጀመርነውን እንጨርሳለን ፣ያቀድነውን እንተገብራለን ፣ ህልማችን እውን ይሆናል ።

አሻግረን ተስፋ እናያለን !!

ከባድ ነበር እንላለን ፣ ቁስላችን ይደርቃል ፣ ሃዘናችን ግዜ ይፈውሰዋል ። ድካማችን ፍሬ ያፈራል ፣ጨለማው ይነጋል ፣

"ሁሉም ጥሩ ይሆናል"

ስራ እናገኛለን፣ጤናችን ይስተካከላል ፣ ከአምላካችን ጋር እንታረቃለን ፣እራሳችንን ይቅርታ እንላለን ።

ሁሉም ጥሩ ይሆናል

እንለመልማለን፣ የውነት እንስቃለን ፣ እንወልዳለን፣ ከልጆቻችን ጋር እንላፋለን ፣ ወላጆቻችንን እንጦራለን እንመረቃለንም

ስህተታችንን የማይደግሙ፣ አገር የሚሰሩ ፣ በመነጋገር የሚያምኑ ፣ተቋም የሚገነቡ ከዓለም ጋር የሚወዳደሩ ልጆች እናሳድጋለን ።

ነገ እንደ ዛሬ አይሆንም !!

ሁሉም ጥሩ ይሆናል!!!
Adhanom Mitiku 🙏

Читать полностью…

አብሮነት

/channel/safari_com_bonuss1

Читать полностью…

አብሮነት

ነብስህ በሰላም ትረፍ የኔ አስተዋይ

Читать полностью…

አብሮነት

Nefsihn bastede genet yawulat

Читать полностью…

አብሮነት

ነብስህ በሰላም ትረፍ ቅዱስ ዑራኤል ከደጋጎቹ ከነ አብርሐም ከነ ይስሀቅ ከነ ያዕቆብ አጠገብ ያሳርፍልኝ የእውነት ያሳዝናል ዑራኤልን አነግሳለሁ ብዬ ብመጣ ማረፍህን ሰማሁ

Читать полностью…

አብሮነት

የግጥምእና የተለያዩ አስተማሪ ነገሮች

Читать полностью…

አብሮነት

"የዳቦ ጨዋታ!!!"

ይሻላል ብለውን፣
አስሩን ከመላስ፣
አንድ ዳቦ መግመጥ፣
ዘጠኙን ትተነው፣
አንዱን እየበላን፣
አምነን ስንቀመጥ፣
በትርፋቸው ስሌት፣
የያዝነውን ዳቦ፣
በተረት አስጥለው፣
ማልደው እየወጡ፣
የተውነውን ዘጠኝ፣
የቀረንን ዳቦ፣
ወስደው የገመጡ፣
ተርበን ስንታይ፣
ለእርዳታ መጡ!!!

#መርዕድ ተስፋዬ

Читать полностью…

አብሮነት

"ቦርጭ እና ምራቅ!!!"

እዛ ማዶ ጋራ፣
ምን ይንኮሻኮሻል፣
ፍየል ተደብቆ፣
ያንን ቦርጩን ያሻል፣
እዚህ ማዶ ዋሻ፣
ዝምታው በርትቷል፣
በጉ ተደብቆ፣
ምራቁን ይውጣል፣
የሚለውን ቀመር፣
የበጉን ረሀብ፣
የፍየሉን ሲሳይ፣
ይሄኛው ልዩነት፣
ለምን መጣ ብለን፣
መነሻውን ስናይ፣
ፍየል ማለት ተግባር፣
ጎርሶ አጣጥሞ፣
ጠግቦ የሚያገሳ፣
በግ ማለት አባባል፣
ለህሊናው ብሎ፣
ሆዱን የሚረሳ፣
የሚል ተረት ይዘን፣
ለከሰረ ውጤት፣
ነፍስን ከስጋ ጋር፣
ከምናወዳድር፣
እስኪ ምን አለበት፣
ህሊናም ቅን ሆኖ፣
ሆድም ጠግቦ ቢያድር፣
ብለን ስንጠይቅ፣
የሚሰራው ጠፍቶ፣
የተፈጥሮን ሒሳብ፣
በግ በደግነቱ፣
ለህሊናው ብሎ፣
ሆዱን እየረሳ፣
ምግብ ትቶ ሲራብ፣
ቆጡን እያሳዩ፣
ፍየሎች ወሰዱት፣
የብብቱን ጥጋብ!!!

#መርዕድ ተስፋዬ

Читать полностью…
Subscribe to a channel