"ልትመክረኝ ጠራችኝ"
በፍቅር ተጣምረን
አመታትን አልፈን
በፍቅር ከፍታ
እንዲሁም ዝቅታ
አንዴም ስንኳረፍ
ቅያሜንም ስናልፍ
አምርረንን ተጣልተን
ፍቅራችን አስታርቆን
አንተ አንቺ እኔ ልብስ
ፍቅራችን ነው ሚብስ
ለሷም ለኔ ሶስተኛ ሰው
መዋደድ ነው አስታራቂው
ይሄን እያወቀች
መለየት አሰኝች
ልትመክረኝ ጠራችኝ
ፍቅራችን ይቅርብኝ
እዚህ ጋራ ይብቃን
ይገታ ፍቅራችን
አያዛልቀንም አብረን መሆናችን
ለምን ይባክናል በከንቱ ግዜያችን
እኔ ይበቃኛል
ፍቅርህ ወቶልኛል
ልንገርህ እንደሀቅ
ተጣልቶ መታረቅ
በቃ ያሰለቻል
መለየት ይቀላል
ስትል እያነባች
ምርጫውን መረጠች
እናም እንዲህ አለችኝ
እኔም እንድረሳክ አንተም እንድትረሳኝ
ውጣ ከህይወቴ አትምጣ ወደኔ
ፍቅራችንን እርሳው እንድረሳው እኔ
ካሁን በሆላ ያንተ ምትባል የለችም
አንተም የራስክ ነክ የራሴው ነኝ እኔም
ፍቅራችንን ታሪክ ነው ነገነት የሌለው
ነበር በሚሉት ውስጥ በትላንት የቀረው
እባክህን እርሳኝ እኔም እንድረሳክ
አያስታውሰኝ ይብቃው ላንተው ይሁን ፍቅርክ
ብላ መክራኝ ሄደች
"እድቅትዮኔ" ብያት ህይወቴ ጨለመች
በላይ ኃ/ሚካኤል
30/03/2015
እኔ ያንቺ ሰይጣን
ጠገብኩኝ አይደለ፥ ይኸው ያዘኝ ቁንጣን
እኔ ያንቺ ክፉ
ጠግቤ አልቀረሁም ፥ ሄድኩ ወደ መርገፉ
የክብሬን ካባ፥ መሬት ላይ አንጥፌው
የልክነትን ልክ ባንች ልክ ጠልፌው
የማይታለፍን እንድ ጉድ አልፌው
ብቻየን ሳወራ፥ ልቤን ያላወቀ እያለኝ ወፈፌው
እኔ ያንቺ ሰይጣን
ጠገብኩኝ በአሽሙር ይኸው ያዘኝ ቁንጣን
እኔ ያንቺ ሰይጣን እኔ ያንቺ ክፉ
ከ...ት ብለው ያዘኑ ትላልቅ ትንሾች
ያው እያየኋቸው ባጠገቤ አለፉ
እኔ ያንቺ ክፉ እኔ ያንቺ ክፉ
(እሰይ ደስ ይበልሽ)
ጠግቤ አልቀረሁም ሄድኩ ወደ መርገፉ።
(ይህ ሁሉ ቢሆንም ብዬሻለሁ አፉ)
hi, come to this group, they wrote something about you there https://efiop-tg.live/group
Читать полностью…ቂም ልይዝ ስል
ልቤን አመመኝ:-
ይቅር ስል
ይቅርታ ጣለኝ።
ሕይወት ሆይ ምድር ሆይ
ዓለም ሆይ ልብ በይ
ከሁለት ጽንፎች ሌላ
ሌላ ጽንፍ አለ ወይ?
በስለት እንዳገኙት ፥
የሚያሳሳ በኩር ህፃን፥ በእቅፋቸው ሲያባብሏት፥
"ፍቅር በሽታ ቢሆን ፥ ስንቱን ገድለሽው ነበር" እያሏት፣
በፀሐይ ሲመስሏት፥
በደመና ሲከልሏት፥
ሲደልሏት...
አውቃው መልኳን፥
ስታው ልኳን፥
ከእኩዮቿ ስታደባ ፥ ከምቀኞች ስትካጠር፥
ልብን ያህል ቅዱስ ንጉስ ፥ ለመሻር ስትመሳጠር፥
አላየችም ሥራዋን፤
አልቆጠረችም እድሜዋን፤
ያልቆረጠ የእንቅልፍ ጥም፥
ዓይኗን ከድና ስታጣጥም፥
ሶታ* ሁሉ ልጅነቷን፥
ከገላዋ ዘግኖ ሊሄድ ፥ ከአልጋዋ ዳር ሲሰለፍ፤
የጊዜ ጎርፍ ከጓሮዋ፥
ተስፋ እድሏን አግበስብሶ፥
ሽምጥ ጋልቦ ሲክለፈለፍ፤
ብቻ ድንገት ስትነቃ፥
ዓይኗን ገልጣ ለደቂቃ፥
ይህቺ መልከመልካም ሴት፤
መስታወት ውስጥ ባየቻት ሰው፤
አካሄዷን አኗኗሯን ፥ ስትቃኘው ስትከልሰው፤
የዓይኖቿ ቆብ ተንጠልጥለው፥
ፀጉሯ መሐል ጥቂት ሽበት
ስትጎበኝ ስትለቅም፤
ለካስ 'ቆንጆ' ፣ 'ውቢቷ' እንጂ...
ማንም ስሟን ጠርቶ አያውቅም።
ያኔ ነው የደነገጠች፤
ያኔ ነው እጅ የሰጠች፤
ይህች..
አንዲት ውብ ሴት፥
የሃምሳ ዓመት ቆንጆ ወጣት፤
ከልጅነት ቀልድ መሐል፥
እድሜ እንደሳቅ ያመለጣት፤
________
* ሶታ:- ወጣት(ጎረምሳ)
ፉንግግ ያለ ፉንጋ ነበር። የጥርሶቹ ትልቀት፣ የአፍንጫው አቀማመጥ፣ የፀጉሩ ግንባሩ ድረስ አመጣጥ፣ አጉጩን ሳይቀር አለማስተዋል አይቻልም ... ተፈጥሮ እንዴት እንደጨከነችበት ሳየው ይገርመኛል ተቀራረብን... ከፉንጋነቱ ጎን ለጎን ጥሩ ያስባል አዛኝ ልብ አለው።
እይታው ጥሩ ነው ፣ ጭንቅላቱ ላይ ቀድሞ የተንሻፈፈ ነገር አይታየውም ፣ ፉንጋነቱ አይታወቀውም ፣ መልኩ ላይ እየቀለደ ፉንጋነቱን ኖርማል ለማድረግ አይሞክርም፣ የፊቱን አቀማመጥ እረስቶታል ....
ብዙ መደዋወል ያዝን .....ይሰማኛል፣ ይጠይቃል አሰማሙ እና አጠያየቁ እሱ ኑሮ ያለው አይመስልም ፤ ገጠመኝ የሚያገኘው አይመስለኝም።
በመስማት ብቻ ለካ መጉላት ይቻላል !!
ከአልአዛር ጋር ተዋደድን ። አልአዛር ፉንጋነቱ ተረሳኝ ...አይደለም ውበቱ ታየኝ ። አልአዛር ቆንጆ ነው። አንድ ቀን ከፍቶኝ ቤቱ ሄድኩ አልጋው ላይ ተኛን አስተቃቀፉ አለሁልሽ አለው ።
እንደ እህቱ እንደታናሹ አቀፈኝ ። ቀዝቀዝ ያለ ውሃ በማስታጠቢያ አምጥቶ ቀለል አድርጎ፣ ለግልግል እንዳላመች አድርጎ እግሬን አጠበኝ። እንደቀዝቃዛ ውሃ መንፈስ የሚያረጋጋ ነገር የለም እያለ በውሃ ዙርያ ትንታኔ አቀረበ ።
ንግስት የመሆን ስሜት ይሰማኛል ከሱ ጋ ስሆን Safe Zone
ነው ።
አልአዛር ቆንጆ እንደሆነ የማውቀው እኔ ብቻ ነኝ መሰለኝ ። እናቱ ሳይቀር መልኩ ላይ እንደሚቀልዱ በጨዋታ መሃል አንድ ሁለቴ ነግሮኛል ።
መቼ ነው ፎንጋነቱ የተነነብኝ ?
መቼ ነው ከበጣም ቆንጆ ልጅ በላይ የደመቀብኝ??
መቼ ነው የቆነጀብኝ ??
አላውቅም ግን አላዛር ቆንጆ ነው !!
አልአዛር ጋር ሳንገናኝ ወይ ሳንደዋወል አንውልም ። ገጠር ሄጄ ስመለስ ከድፍን ከተማው አልአዛር ብቻ ነው የሚናፍቀኝ ። ከአልአዛር ጋር ብሄድ ምን ምክንያት አለ ተመለሺ ተመለሺ የሚለኝ ??
አልአዛር ጋ አብሬው ተኝቼ ለሊት ላይ የተገለጠ ገላዬን ያለብሰኛል። ለጥቃቅኑ ስሜቴ ቦታ ይሰጣል ።
አብረን እቤቱ ስናድር
በጠዋት ተነስቶ የሆነ ነገር ገዝቶ ስነሳ የምንሰራው ወይ የምንበላው ያመጣል ...ለምዶኝ ችላ አላለኝም።
ምቾት ተሰማኝ ፤ ማንም አይቀማኝም ብዬ መሰለኝ ፣
ጨዋ ነው ብዬ መሰለኝ፣ የሚሰማኝ፣ የሚያግዘኝ ስላገኘሁ ነው መሰለኝ እለት እለት ፍቅሬ ጠነከረ ።
ድንገት የሆነ ቀን "እንለያይ" አለኝ ....ሳኩኝ። በርግጥ አንድ ሁለት ሳምንት ሙሉ ደብዝዞ ነበር ፣ እየራቀኝም ነበር። እኔ ከራሱ ጋር የተጣላ ነበር የመሰለኝ ።
ላለማስጨነቅ ነበር ምን ሆንክ ላለማለት የሞከርኩት
እሱ ፀቡ ከኔ ጋ ነበር መሰለኝ ...
ቀለል አድርጎ ነበር እንለያይ ያለኝ ።እኔ እና እሱ መሃል ጭቅጭቅ፣ መዋደድ ፣ መሳቅ እንጂ የመለያየት ፅንሰ ሃሳብ እንዳለ አላውቅም ነበር ።
"እንለያይ" አለኝ ..... "እየቀለድክ ነው አልአዛር ?"
"እውነቴን ነው ሶሲ "
የሆነ መፍራት ነገር ወረረኝ ። "ባይሆን አሪፍ ጓደኛ እንሆናለን እንደ ድሮ አለ ።"
የማደርገው ስላጣሁ ዝም አልኩ: እምባዬ ግን ፈሰሰ።
" ምን አደረኩ?
፣ ምን አደረገች ብለው ነግረውህ ነው? ፣
ምን ያልኩት ነገር ልብህ ውስጥ ሃዘን ፈጥሮ ነው? "
"ተይ አታወሳስቢው ሶሲ ተይ you are one of the strongest people I know ጓደኝነታችን አይቆምም እኔ ሪሌሽንሺፕ ይሰለቸኛል።"
እንዴ?! እንዴ ?! አላዛር አልመስል አለኝ
ጥሩ ልብ መኖሩ ፣ አዛኝነቱ ፣ አይነግቡ አለመሆኑ
መውደዴ .....የቱም እንዳይተወኝ ዋስትና አልሆነኝም ። ያስደነገጠኝ ፊቱ ላይ ያስነበበኝ የበቅቶኛል ሁኔታው ነው ።
ደነገጥኩ !!
ኖ
ፈራው.
ኖ
አዘንኩ መጠን አልባ ሃዘን ልቤ ውስጥ ተንከላወሰ።
መለመን ፈልጌ ነበር ፣ የሆነውን ማወቅ ፈልጌ ነበር ፣ተረጋግቼ ላናግረው ፈልጌ ነበር፣ ሲያቅተኝ ከተቀመጥንበት ጠረጴዛ ላይ አጎንብሼ አለቀስኩ ሰዎች ትኩረታቸው ወደ እኛ ሲሆን መሰለኝ ፦
"ኧረ አንቺ ልጅ This is totally attention-grabbering
አረጋጊው !
ሁኔታው ንግግሩ ከእንለያዩ የበለጠ ጎዳኝ ።ቀጥ ብዬ እያለቀስኩ ከፊቱ ከካፌው ከኑሮው ሄድኩኝ
አልተከተለኝም .....
በነጋታው ይመስለኛል ከእንቅልፌ ስነቃ ተስፋ ሙቁረጥ መላ አካላቴ ላይ ተጥለቅልቋል ። መነሳት አልቻልኩም ሁኔታው፣ አወራሩ፣ አኳኋኑ ፣ ልቤ ላይ መከዳት ተንጋለለብኝ ።
የአልፈልግሽም ውሳኔው ፣ ለሱ የነበረኝ ቦታ ፣ ክህደቱ በደም ዝውውሬ ተሰራጭተው ስነቃ አላላውስ ብሎኝ ነበር ።
ለሦስት ወር ከሃያ ቀን በራችን ጋ ካለው ሱቅ በቀር የትም አልሄድኩም።
ስልኬን ዘጋሁት ፣ ተብሰለሰልኩ፣ ተምሰለሰልኩ ፣
ሙዚቃ አልሰማሁም፣ ፊልም አላየሁም፣ ከወዳጆቼ ጋር አልተገናኘሁም ፣
ስለገንዘብ አላሰብኩም ፣ ሁሉን እርግፍ አድርጌ ተውኩት ። ከአልጋዬ አልተላቀኩም ፣ ከተከረቸምኩበት ስወጣ ከብዙ ግዜ በኃላ መስታወት አየሁ ሽበት ጣል ጣል ብሎብኝ ነበር ፣ ገርጥቼ ነበር፣ ብዙ ግዜ ጨለማ ክፍል ውስጥ የነበርኩ እመስል ነበር ።
የሆነ ቀን፤ ከሆነ ግዜ በኋላ ለፆታዊ ግንኙነት ያለኝ ቦታ ቀዝቅዟል። በወሬ መሃል ሳይታወቀኝ ከልቤ ግድ ነው እንዴ መጥበስ ? ግድ ነው እንዴ ፆታዊ ግንኙነት ፣ማግባት ግድ ነው ? የሰው ልጅን የተባለ ፍጡርን አምኖ ነገን በጋራ አብሮ ማለም መራመድ ይቻላል? ?
ምንስ ፉንጋ ቢሆን
ምንስ አዛኝ ቢሆን
ምንስ አሳቢ ቢሆን
ምንስ ቆንጆ ቢሆን
የሆነ ቀን ቢከዳንስ ዋስትናችን ምንድን ነው ?? እያልኩ ለነገ ዋስትና የሚሰጠኝ ፍለጋ ስሞግት ድምፄን ሰማሁት
ከጉዳቴ ያገገምኩ መስሎኝ ነበር ! ቁስሌ አልደረቀም ማለት ነው ? መዳን ስንት እድሜዬን ይበላ ይሆን ??
© Adhanom Mitiku
📍ምን ይዤ ልሔድ ልድከም?
ታላቁ እስክንድር እንዲህ አደረገ አሉ። ወደ ሞት አፋፍ መቃረቡን ሲያውቅ፤ ወዳጆቹን ሰብስቦ እንዲህ አላቸው "ስትቀብሩኝ፤ እጄን ወደ ላይ አርጋችሁ ቅበሩኝ" አለ። ሰዎቹም ግራ ገብቷቸው ለምን እንደሆነ ጠየቁት፤ እሱም መልሶ እንዲህ አላቸው፤ "እጄን ወደላይ አድርጋችሁ ቅበሩኝ ያልኩት፤ ስሞት ከምድር ምንም ነገር ይዤ እንዳልሄድኩኝ ሰዎች እንዲያዩ ነው " አለ ይህንን ያለው እንግዲህ በጊዜው አለምን ያስገበረው ታላቁ እስክንድር ነው። በክንዱ ስንቱን ያስገበረው ታላቅ፤ "ምንም ይዤ አልሄድም" ሲል ተናገረ። አንዳንዴ የምንኖረው እስከመቼ ነው ብለን እራሳችንን ከምር ብንጠይቅ መልሱ ያስደነግጠናል።
💡 ምክንያቱም የምንጨነቀው ከምንኖረው በላይ ነው። ፈገግታን፤ ሳቅን፤ ደስታን ሳያውቁ የሚሞቱ ሰዎች ሞልተዋል። ኖረው ሳይሆን፤ ሞተው ወደ መቃብር የሚወርዱ ምስኪኖች ብዙ ናቸው። አብዛኛዏቻችን በቁማችን ሞተናል፤ ምክንያቱም መኖር ከመንቀሳቀስ እና ከመተንፈስ የጠለቀ ስሜት አለውና። መኖር ማለት እራስን ከአሁኗ ደቂቃ ጋር አጣምሮ፤ መንፈስን፤ አይምሮን ከተፈጥሮ ጋር አዋህዶ፤ ለሁሉም ነገር ጊዜ አለው የሚለውን የጠቢቡን መርህ ተከትሎ ህይወትን መምራት ማለት ነው (በጥቂቱ)።
ይህ ትርጉም ለእያንዳንዳችን በልካችን መበጀት ይችላል። አንዳንዴ እራሴን እጠይቃለው፤ የምንጨነቅለት ነገር ሁሉ ከዚህ አለም ስንሄድ ይዘነው የምንሄደው ካልሆነ፤ ምንድን ነው ነጥቡ? የብዙዏቻችን ኑሮ ይዘነው ለማንሄድ ወይም ስማችንን ከመቃብር በላይ ለማያስጠራ፤ ተራ ነገር ተሰውቷል። የቱ መቅደም እንዳለበት አናውቅም፤ እኛ ወይስ ጭንቀታችን? ቤተሰባችን ወይስ ስራችን? ሰብዓዊነት ወይስ ቁሳዊነት?
♦️ተጨንቀን የምናጠራቅመው ገንዘብ፤ በጥላቻ የገነባነው ክብር፤ በደም ያገኘነው ስልጣን፤ በስርቆት ያካበትነው ሃብት፤ በውሸት የፈጠርነው ማንነት፤ ሁሉም ስንሞት አብረውን አይሄዱም። ያንን ማስተዋል እንዴት አቃተን? በቃ ሃቁ ይህ ነው፤ ምንም ነገር ከኛ ጋር ወደ መቃብር አብሮ አይወርድም።
💡ይህንን ሳስብ ግርምት ያዘኝ፤ እንዴት እናሳዝናለን ? ምን አልባት ስዎች ሲቀበሩ እጃቸውን ወደላይ አድርገው ቢሆን ኖሮ፤ በጥቂቱም ቢሆን ህይወታችንን እንዴት መኖር እንዳለብን ትምህርት ይሆነን ነበር። በህይውትህ የሚያስጨንቅህ ነገር ሲገጥምህ፤ እስከምን ድረስ እራስህን አሳልፈህ መስጠት እንዳለብህ ለማውቅ ሞክር፤ ምናልባት ከህይወትህ ጋር ሲነጻጸር ኢምንት ሊሆን ይችላልና።
✍ አቤል ብርሀኑ
ሰው ዓለም ሰዋሰው
አልሸሽ፣ ከእምነት እዳ
ለአንቺ ልብ፣ እንግዳ
እኔ አለሁ፣ ፍቅር አዳም
አንቺ አለሽ፣ ሰው ዓለም
አንቺ አለሽ ሰዋሰው፣
ኖረን እንለፈው ፣ሞተን ከምንቀምሰው
አወይ የሞት ቀንጃ ፣የመሳሳብ ጸሩ
እንዴት ከቅጽር አምባሽ፣ ድፍድፍ ሃኬት ይስሩ?
ዙሪ ከድጥ መንገድ፣ ከኩርንችት ገላ
መውደዴን ተከተይ፣ እንዋል ከእረፍት ባላ
ሰው ዓለም ሰዋሰው፣
ከምኔው ተንፍሶ፣ ከምኔው ወረሰው?
ከምኔው ደልድሎ፣ ከምኔው አረሰው?
ሰው ዓለም ሰዋሰው፣
የልብሽን ሙዳይ፣ በሃዘን አመሰው።
ሰው ዓለም
ከጉበኔ ቆሜ፣ በአመሻሽ ብዥታ
በዓይኔ ስንቀዋለል፣ አንድ የጊዜ አውታታ
አለፍሽ አንቺም ለካ፣ መቃኔን ተራምደሽ
ከተምሽ ወደ ነገ፣ ዛሬን ደጄ እረግጠሽ
ምን ይሉታል ታዲያ፣ ምንድን የምን መላ?
መሸሽ ከአንቺ ሲሆን፣ ማሰብ ከአንቺ ሌላ
ምን መላ ምን ባላ፣ የምን አንዳች ስቁረት?
ከመውደድ ተሰዶ፣ መውደድ ሊስቡበት
አቤት ዓለም ዘበት፣
ውጪ ከሃዘን ውርስ፣ ዝመች ከእምባ ጣቢያ
ያለፈው ጉዞ ነው ፣
የነገ ዓለም ምንጣፍ፣ የመክሰም ቡቃያ
ቢያድልሽ ዝንጋኤ፣ ቢቸርሽ ሚስጥሩ
ሞት የሚጠብቀው፣ ሞት ነበር መኸሩ
ትንሳኤ የሚያሻ ፣ህይወት ነበር ግብሩ
መውደድን የሚያልም፣ ፍቅር ነበር ዝክሩ።
ሰው ዓለም ሰዋሰው
ትንሳኤን ለምኖ፣ ሞትን ግን ከሰሰው
ፍቅርን ጠይቆ፣ ተንኮልን ለበሰው
ሰው ዓለም
አንቺስ የጊዜ እጣ፣ የመውደድ ነጭ ምንጣፍ
በሃዘን ተገምደሽ ፣
ጉበኔን ገርምመሽ ፣ተራምደሽው ማለፍ
ምን ይሉት ፈሊጥ ነው፣ የምን ክብር ካባ?
አሳድዶ መሸሹ፣ ሰው አፍሮ ሊገባ
ሰው ደፍሮ፣ ሰው አፍሮ
አላፊን ቆስቁሶ፣ ከአላፊ ጋር መክሮ
ሰው ነፍሮ፣ ሰው አፍሮ
ላይቦጭቀው ሞቱን፣ ላይጎምድ የፍቅር ስር
አንቺን ከእኔ ነጥሎ፣ ሊከተብሽ ከእሱ እግር
ይስባል በክንዱ፣ ይግጣል በጥፍሩ
የአንቺም አምኖ መትመም፣ ምን ይሆን ምስጢሩ?
ሰው ዓለም ተመለሽ፣ አልፏል የስጋ አባት
በመጓዙ አይደለ፣ ያንቺስ እንዲህ መምጣት
የለም ልብ መሳይ፣ አይፈጠር አቻ
አይደጎስ ድርሳን፣ ገድል ለአንቺ ብቻ
ነይ እኔን ተመልከች፣ እይኝ ከጉበኔ፣ ቆሜ ከመቃኑ
ስሚኝ ሹክሹክታዬን ፣ ለቃል ነው ዘመኑ
እይኝ እንደ ጊዜ፣ መስይኝ እንደ ሞት
ለብቻ ብንኖርም፣ ነገአችን ያው መሬት
ዘርጊልኝ ቀይ ግምጃ፣
መውደዴን ነው እንጂ፣ መኖሪንስ እንጃ
መከተሌን እንጂ ፣መድረሴንስ እንጃ
እናልሽ ሰዋሰው፣
መኖርን ሞግተን፣ ሞትንም ላንከስሰው
ሰው መሆንን ኖረን፣ ፍቅር እንቅመሰው
በእምነት አንዳች ገድል፣ ፍጡርን ላንወርሰው
እናማ ሰዋሰው፣
ነይ ገድልሽን ጻፊ፣ እኔ ልደጉሰው
የሰው ልጅ ሰዋሰው!
By wubarege admit
ከአንዲት ቆንጆ ልጅ ጋ ነበርኩ። መኪና ውስጥ ነበርን ፒዛ እየጋበዝኳት አስተናጋጁ ሲያልፍ በእጄ ቢል እንዲያመጣልኝ ነገርኩት
ቢል ይዞ መጣ
እያየኝ ከፊት ከኃላ ኪሴ አውጣጥቼ ሂሳብ ከፈልኩ ...
ሄደ
መልስ መጠበቅ ጀመርኩ አልመጣም ጠበኩት አልመጣም ተበሳጭቼ ክላክስ አስጮህኩ
(ሱሰኛ ይመስላል ፣ የቀረውን ገንዘብ ለማስቀረት አስቦ ነው ፣ ጉርሻ በፍቃደኝነት የሚሰጥ እንጂ በብልጠት የሚዘገን አይደለም ፣ ሲቆይብን ሰልችቶን እንድንሄድ ነው )
ያስጮኩትን ክላክስ ሰምቶ መጣ
"መልስ ስጠን እንጂ ጌታው "አልኩት
"የሰጠኸኝ አራት መቶ ነው ሂሳቡ ደሞ አራት መቶ ሰላሳ አምስት ብር ነው "አለኝ ( ስበረብር ስላየኝ የለው ይሆናል በማለት ተሳቆ ነው እንዳልገረጣ ይጎላል ያላለው )
ከሌለህ ብዬ ነው አይነት ፊት አሳየኝ ። አንዳንድ አድራጎት የሚያገዝፈው አደራረጉ ነው ።
ይቅርታ ቢሉን በደንብ ስላላስተዋልኩት ነበር።
በጣም አመሰግናለሁ አልኩት
እንደገና ኪሴን በርብሬ ድፍን ሁለት መቶ ብር ሰጠሁት እንዲመጣልኝ እንዳልቸኮልኩ እንዲሄድልኝ ቸኮልኩ
መልስ ሊያመጣልኝ ሄደ
ሳይነግሩን ለዋሉልን እየነገርን መዋል ነውር ነው አይደል ?
ሳይመጣብኝ ሄድኩኝ ።
© Adhanom Mitiku
አርቲስት ጌትነት እንየው
አምነው የወደዱ፣
ወደው የተካዱ፣
ተክደው የራዱ፣
ፍርሃት አንሸራቶ ቁልቁል የጣላቸው፣
የብቸኛ ልቦች የትነው መውደቂያቸው?
የትነው መድረካቸው?
ማነው አጃቢያቸው?
እንዴት ነው ምታቸው?
የተካዱ ልቦች አጋር የራቃቸው፣
የሚያቀነቅኑት ምንድን ነው ዜማቸው?
የተመረኮዙት እምነት ታጥፎባቸው፣
ድንገት የወደቁ ፍቅር ያዳጣቸው፣
ሚስጥር የሚያጋሩት ሰው የበረዳቸው፣
ብቸኝነት ሰርጎ ብቻ ያስቀራቸው፣
ዝምተኛ ልቦች ምን ይሆን ቋንቋቸው?
ከየት ነው ጥሪያቸው?
በየት ነው ጉዟቸው?
የት ነው መድረሻቸው?
እንደ ሰብአሰገል ጠቅሶ የሚመራቸው፣
የቃተቱ ልቦች የታል ኮከባቸው?
መቼም ከአምላክ ትንፋሽ ከውሃ ከአፈሩ፣
ከእምንት እና እውነት ከፍቅር ሲሰሩ፣
ዝምተኛ ልቦች ጥንቱን ሲፈጥሩ፣
ተገፍትረው ወድቀው፣
ደቀው እንዳይቀሩ፣
በተስፋ ጸንተው ነው ዘላለም ሊኖሩ።
እንዴት ናችሁ አብሮነቾች እ/ር መፅናናትን ያድለን በጣም አዝኛለው ግን ምንም ማድረግ አይቻልም ፈጣሪ የፈጠረውን ፍጥረት በፈለገው ጊዜ መውሰድ ይችላል ነብሳቸውን ይማርልን ሊሊ ነኝ ከአራት ኪሎ ለጋስነት ሰትወለድ ገና አብሮ የሚፈጠር ነገር ነው ከላይ ካልተሰጠህ ከባድ ነው በኔ በገኩል ግን ሲተርፍህ ሳይሆን ካለው ነገር ላይ የሚሰጥ ነው ለገሰ አሉ እንደዚህ አይነት ሰዎች ለምሳሌ እንደ አስፋው መሸሻ ያሉ አብሮነቶች እወዳችዋለው ፕሮግራማችሁ በጣም አሪፍ ነው በርቱ
Читать полностью…እኔ ያንቺ ሰይጣን
ጠገብኩኝ አይደለ፥ ይኸው ያዘኝ ቁንጣን
እኔ ያንቺ ክፉ
ጠግቤ አልቀረሁም ፥ ሄድኩ ወደ መርገፉ
የክብሬን ካባ፥ መሬት ላይ አንጥፌው
የልክነትን ልክ ባንች ልክ ጠልፌው
የማይታለፍን እንድ ጉድ አልፌው
ብቻየን ሳወራ፥ ልቤን ያላወቀ እያለኝ ወፈፌው
እኔ ያንቺ ሰይጣን
ጠገብኩኝ በአሽሙር ይኸው ያዘኝ ቁንጣን
እኔ ያንቺ ሰይጣን እኔ ያንቺ ክፉ
ከ...ት ብለው ያዘኑ ትላልቅ ትንሾች
ያው እያየኋቸው ባጠገቤ አለፉ
እኔ ያንቺ ክፉ እኔ ያንቺ ክፉ
(እሰይ ደስ ይበልሽ)
ጠግቤ አልቀረሁም ሄድኩ ወደ መርገፉ።
(ይህ ሁሉ ቢሆንም ብዬሻለሁ አፉ)
የተወለድኩ እለት ዓለም ተፈጠረ
የቀብሬለት ደግሞ በቃው ተቀበረ
እኔ ካለሁ አለ ከጠፋሁ ይጠፋል
በእይታዬ መጠን ይጠባል ይሰፋል
ታዲያ ጭንቀት ጥበት መውደቅ መነሳቴ
ምን ሊፈይድ ይሆን መሞትን መርሳቴ።
አስቸኳይ ማስጠንቀቂያ 😲😲
በስመ አብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
የፊታችን መጋቢት 29 የሚካሄደው የህዝብ ቆጠራ ምክንያት በማድገግ የተለያዩ ሀይማኖቶች የኦርቶዶርስን እምነት ሊያጠፉ ይፈልጋሉ !!!
እናም ቆጠራ በሚካሄድበት ጊዜ
😟😟 አስተውሉ 😟😟
በክርስቲያን እምነት ውስጥ ከ 35,000 በላይ የሚሆኑ እምነቶች አሉ እናም ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ በማለት እምነታችን እንዳይጠፋ እንጠብቅ፣ ማለትም ለምዝገባ ሲመጡ እኛ ኦርቶዶክሶች ነን ብላቹ አስመዝግቡ እንጂ ክርስትያን ነን አትበሉ።
አስቡት እስቲ አሁን የመንግስት ሰራተኖች እረፍታቸው በሰንበት (እሁድ) ነው እረፍታቸው ግን የሀይማኖታችን ቁጥር ካነሰ ይቀየራል ለምሳሌ ሙስሊሞች አርብ ጁማቸው ነው የእነሱ ቁጥር ከበለጠ የመንግስት ሰራተኖች እረፍታቸው የሚሆነው አርብ ቀን ነው ።
እናስብ ሀይማኖታችን እንዳይጠፋ!
ጥር 11 የሚከበረው የኢየሱስ ክርስቶስ በዓል ሊቀር ይችላል እባካችሁ ሀይማኖታችንን እንጠብቅ
ቢያንስ አንድ ኦርቶዶክስ ለጓደኞቹ 10 ሰው ቢልክ ሀይማኖቱን ይጠብቃል
ድንግል ማርያም እናቴ አንቺ ጠብቂን በእግዚአብሔር ስም እለምናቹአለሁ ሁላችሁም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች ናችሁ ቢያንስ ቢያንስ ለ10 ሰዎች ከተቻለ ከዚያም በላይ ለምትችሉት ሁሉ ይህን መልዕክት በመላክ ኦርቶዶክሳዊ ግዴታችንን እንወጣ ።የሁላችንም ግዴታ ነው በዚ ምክንያት እኛን ለመበታተን ጠላት አድብቶ ይሰራል እኛ ዛሬም ነገም እስክንሞት ድረስ ኦርቶዶክሶች ነን ስለዚህ ሼር ለሁሉም ይድረስ !!።
"አመድ አፋሽ ሆንኩላችሁ"
//አቤል ብርሀኑ(የወይኗ ልጅ)//
አንድ ሰው በበረሃ እየተጓዘ እያለ የያዘው ውሃ አልቆበት በውሃ ጥም ይያዛል፡፡ ቀስ በቀስ ውሃ ጥሙ ሰውዬውን እያደከመው ይመጣል በስተመጨረሻ ከአንድ የውሃ ጉርጓድ ጋር ይደርሳል ጉርጓዱ በጣም ጥልቅ ነበረ ውሃ ይኑረው አይኑረው አይታይም፡፡ ከዚያም ከጉርጓዱ ጎን አንድ አሮጌ የውሃ መሳቢያ ሞተር አለ ሞተሩ ላይ እንዲህ የሚል ፅሁፍ ሰፍሯል፡፡ ‹‹ይህ የውሃ መሳቢያ ሞተር የሚሰራው በውሃ ነው›› ይላል፡፡ ከሞተሩ ጎን አንድ ጆግ ሙሉ ውሃ ተቀምጧል ጆጉ ላይ እንዲሁ አንድ ፅሁፍ ሰፍሯል ‹‹ወዳጄ ሆይ ይህንን ጆግ ውሃ ሞተሩ ውስጥ ጨምረው ሞተሩ ብዙ ውሃ ያወጣልሃል ታዲያ አደራ አንተም እንዳንተ ላለ ሌላ መንገደኛ ይጠቅማልና ውሃው ከጉርጓዱ ሲወጣልህ ጆጉን ሞልተህ ማስቀመጥን አትርሳ›› ይላል፡፡ በጆግ ያለውን ውሃ ሞተሩ ውስጥ ይጨምረው ወይስ ይጠጣው? እዚጋር ሰውዬው በሁለት ሃሳብ ተወጠረ ‹‹አንደኛ ይህ ሞተር አርጅቷል ጨምሬው ባይሰራ ይህንንም ውሃ አጣሁ ማለት ነው ሞትኩ ማለት ነው ስለዚህ ልጠጣውና ህይወቴን ላድን ፡ ደሞ ማሳሰቢያውስ ውሃው ያለሞተር አይሰራም እንደኔ ውሃ የተጠማ ሰው ቢመጣ ይህንን ማንቀሳቀሻ ከጠጣሁት ይሞታሉ›› ብሎ ለራሱም ለሌሎቹም አሰበና በሃሳብ ተወጠረ በስተመጨረሻ በብዙ ጭንቀት ተወጥሮ ትልቅ ውሳኔ ወሰነ እንዲህ አለ ‹‹ውሃውን ወደሞተሩ ብጨምረው ይሻላል ከሰራ ጥሩ ካልሰራ ግን እሞታለሁ እንጂ በፍፁም ይህንን ጆግ ውሃ ጠጥቼ ሄጄ ዛላለሜን ስለዚህ ጉርጓድና ይህንን ውሃ አተው ስለሚሞቱ ሰዎች እያብኩ መኖር አልፈልግም›› አለ፡፡
ከዚያም የጆጉን ውሃ ወደ አሮጌው ሞተር ውስጥ ጨመረውና የሞተሩን ማስነሻ ተጫነው፡፡ ሞተሩም ድምፅ እያሰማ ውሃ የማውጣት ስራውን ጀመረ፡፡ ሰውዬው ተደነቀ የሚፈልገውን ያህል ጠጣ አካባቢው በሙሉ በውሃ እራሰ ከጠበቀው በላይ አካባቢው ሁሉ ውሃ በውሃ ሆነ ከዚያም በተባለው መሰረት እሱም ጆጉን በውሃ ከሞላው ቦሃላ ጆጉ ላይ ፅሁፍ ጨመረበት ‹‹እመኑኝ በትክክል ይሰራል›› አለ፡፡
እና ምን ለማለት ፈልጌ ነው ለራስ ማሰብ በህይወት መኖር ነው ለሌላው ማሰብ ግን ሰው መሆን ነው፡፡ ያለህን በሙሉ ሳትሰስት ከሰጠህ በእጥፍ ድርቡ ፈጣሪ ይሰጥሃል፡፡ ሰውዬው ጆግ ውሃ ሰቶ አካባቢን የሚያርስ ውሃ እንደተቸረው አንተም የምትሰጣት ጠብታ ከልብህ ከሆነ በእጥፉ ይሰጥሃል፡፡ በምትሰፍረው መስፈሪያ ይሰፈርልሃል በሰጠኸው ልክ ይሰጥሃል ስለዚህ ‹‹አመድ አፋሽ ሆንኩ›› ከማለትህ በፊት አመድ ሰተህ ከሆነስ፡፡ መስጠትን ብቻ ሳይሆን አሰጣጥህ ወሳኝነት አለው፡፡ አንዳንዴ ከመንጠቅ የማይተናነስ መስጠትም አለ፡፡
★የቅኔ ቋጠሮ★
መገፋት ደግ ነው...
ምናልባት አንድ ቀን ደጋጉን ይሰጣል፣
መገፋት መልካም ነው...
ምናልባት አንድ ቀን መልካሙን ይሰጣል፣
መገፋት እንባ ነው...
ደም እያስለቀሰ የደምን ዋጋ መልሶ ይከፍላል፣
ከሽንፈት አንስቶ ሹመት ይደርባል፣
ፍቅር አሳጥቶ ፍቅር ይለግሳል፣
የገፊውን ግፊት መልሶ በግፊት ለገፊው ያሳያል፣
ሲቃን አደባብሶ በሳቅ ይቀይራል።
መገፋት ጥሩ ነው፣
መግፋት ደግሞ ጡር ነው
ደጋጉን ቀምቶ...
በመልካም መስታወት ክፉውን ያሳያል፣
ደም እያስለቀሰ...
የደምን ዋጋ እያደማ ያነቅዛል፣
እያኖረ መስሎ...
በቁም ሞት መቃብር በፀፀት ያነዳል፣
ከሹመት አንስቶ በሽረት ያወርዳል፣
ፍቅር አሳጥቶ...
በጥላቻ ደዌ ሲያማቅቅ ይዘልቃል፣
የተገፊን ግፊት...
በተገፊ ደስታ እያሳየ ያርዳል፣
ሳቅን እየቀማ...
በሲቃ ሰንሰለት እያሰረ ይፈታል።
****
መፍታቱ ወዲህ ነው፣
ተገፊ ሁል ጊዜም የይቅርታ ሹም ነው፣
ፈቅር እየሰጠ...
የተቀማን ሁሉ አስመላሽ ሎሌ ነው፣
በእርሱ መልካምነት...
የሲቃን ሰንሰለት የሚፈታ ቸር ነው፣
መገፋት ጥሩ ነው፣
መግፋት ደግሞ ጡር ነው፣
በሰምና ወርቅ ውስጥ የአንዱን በአንዱ የሚያሳይ የቅኔ ዝርፍ ነው።
፠፠፠፠
©ሠለሞን ምህረት ✍
ጥቅምት ፳፮፣ ፪፼፰ ዓ.ም
ገጣሚ ሚካኤል ምናሴ🙏
ትዝታ ማለት ለእኔ...
አይደለም፥
የሄደን ጊዜ ደጅ ሆኖ - እንደላኩት ልጅ መጠበቅ፤
የሸኙትን ሰው አልመው - እምባ ለብሶ መናፈቅ፤
አይደለም።
ትዝታ ማለት ከንፈሬ ፥ በጉንጭሽ የተባረከው፤
ትዝታ ማለት ጆሮዬ ፥ በድምፅሽ የሚሰበከው፤
ታዝታ ማለት ዐይኔ ነው ፤ በዐይንሽ ማይ የሚጠበለው፤
ትዝታ ማለት ጀርባዬ ፥ ስታቅፊኝ ክንፍ ያበቀለው፤
የትም ጊዜ ላይ ብሆን፥
ከቅብዝብዝ እድሜዬ ውስጥ - ጥሞናና መስከኔ፤
ከሚያጠፋኝ ዓለም መሐል - መግዘፍና መግነኔ፤
ትላንት ይሁን ዛሬም ነገ - አንቺ ያለሽበት ቀኔ፤
ትዝታ ማለት በቃ...
ስትኖሪ የማብበው ሰው - ስትኖሪ የማምረው እኔ!