abudawd | Unsorted

Telegram-канал abudawd - ABU DAWD OSMAN

-

Subscribe to a channel

ABU DAWD OSMAN

ለረመዳን እንዘጋጅ!

አላህ በሰላም ያድርሰን!

Читать полностью…

ABU DAWD OSMAN

ታላቅ የዳዕዋ ፕሮግራም በሀዋሳ ከተማ
.
ታለቅ የደዕዋ ፕሮግራም በሀዋሳ ከተማ አረብ ሰፈር ረህማ መስጂድ ላይ መጭው እሁድ ሳምንት መጋቢት 12 ላይ "ልብን ሕያው ማድረግ" በሚል ርዕስ በኡስታዝ አቡ ሀይደር ትምህርቱ ይሰጣል።
.
በእለቱ ይህንን እድል የአካባቢውና በዙሪያው ያለ ማህበረሰብ ሁሉም እንዲጠቀሙበት ተጋብዟል።
.
SHARE በማድረግ መረጃውን አዳርሱ..!

Читать полностью…

ABU DAWD OSMAN

ሼር‼ ሼር ‼ሼር‼

የነገው ቤታችንን ዛሬ እንከባከበው !
እሁድ ኮልፌ የሙስሊሞች መካነ መቃብር እንገናኝ !

ማሳሰብያ
======
ለፅዳት ስትመጡ በተለይ የመስጂድ ጀመአዎች የተለያየ የማህበራት አባላት ዛፍ ለመቁረጥ የሚያስችል የተለያየ አይነት መቁረጫዎችን ይዛቹ መምጣት አትርሱ

እ ና ፀ ዳ ለ ን‼

Читать полностью…

ABU DAWD OSMAN

የአይኔ ማረፊያ የሆነችው ወላጅ እናቴን ትንሽ አሞብኛል :: አላህ አፊያ እንዲያደርጋት በመልካም ዱዓችሁ አግዙኝ!

Читать полностью…

ABU DAWD OSMAN

መፍትሔው አንድ እና አንድ ብቻ ነው!

በ9ኙ ተቋማዊ ለውጥ የጋራ ኮሚቴ ተጠንተው በሸራተኑ ጉባኤ የፀደቁትን የመጅሊስ መዋቅር እና የኡለሞች የመግባቢያ ሰነድ የሁሉም ክልሎች እና የመጅሊሱ የጠቅላላ ጉባኤ አአባላትን በመጥራት በጠቅላላ ጉባኤው እንዲፀድቁ ማድረግ እና የመጅሊስ አመራሮች ምርጫ እንዲካሄድ ማድረግ ብቸኛው መፍትሄ ነው::

መጅሊስ የሁሉም ሙስሊሞች ተቋም እንጂ የስራ አጦች እንጀራ ማብሰያ ቦታ አይደለም!

በጊዜያዊነት የተሰጣችሁን አማና አጠናቃችሁ ህዝብ ለሚመርጣቸው መሪዎች ቦታውን ማስረከብ ግድ ይላል!
ኡለሞች በኡለማ ምክር ቤት ቦታችሁን ይዛችሁ ሃይማኖታዊ ጉዳዬችን በመምራት ህዝባችሁን አገልግሉ::

በምርጫ የምትመረጡ ምሁራን ደግሞ የአስተዳደር እውቀት በሚጠይቀው የአስተዳደር ክፍሉን በስርዓቱ በመምራት ህዝበ ሙስሊሙ ለማገልገል እንጂ በህዝበ ሙስሊሙ ላይ ለመገልገል አታስቡ::

ሰላም ሚኒስተር ጊዜያዊ መጅሊሱ የተሰጠውን የቤት ስራ እንዳይሰራ እና የተሰጣቸው ጊዜያዊ ስልጣን ያባታቸው ርስት ይመስል የጊዜ ገደብ የለብንም በማለት ሙስሊሙን ለግጭት ሲያነሳሱ የነበሩ ጥቂት ግለሰቦችን ስርዓት አሲዞ መጅሊሱ ያለማንም ጣልቃ ገብነት በጠቅላላ ጉባኤው ችግሮቹን እንዲፈታ ማድረግ መንግስታዊ ሃላፊነቱ ነው!

በሰላም ሚኒስተር በኩል አቅጣጫ ማስቀመጡ ሳይሆን የተቀመጡ አቅጣጫዎችን በቁርጠኝነት እንዲተገበሩ በማድረግ እና በመከታተል ለህዝበ ሙስሊሙ እፎይታ ማስገኘት ያስፈልጋል::
ህዝበ ሙስሊሙ የወሬ ተስፋ ሳይሆን የተግባር ምላሽ ብቻ ነው የሚሻው!

ጠቅላላ ጉባኤው ተጠርቶ ችግሮቻችንን ያለማንም ጣልቃ ገብነት መፍታት እና ሰነዶችን አፅድቆ ወደ ተግባር መግባት ሁሉም ሙስሊም የሚጠብቀው ብቸኛ መፍትሄ ነው!

Читать полностью…

ABU DAWD OSMAN

በየትኛውም አለም ለምትገኙ የተላለፈ የበጎ ተግባር ጥሪ።

እጅ ለእጅ ተያይዘን ሁላችን ለወገኖቻችን ለመድረስ እንረባረብ። የአዲስአበባ እስልምና ጉዳይ ከዚህ ቀደም እንደሚያደርገው በጎ ፍቃደኞችን አስተባብሮ ከዛውያ ቲቪ ፣ ከነጃሺ በጎ አድራጎት፣ ከታአውን እድር፣ ከአፋቅ የልማትና መረዳጃ እድር ጋር በመተባበር በፍልውሃ ተውፊቅ መስጅድ በትግራይ ክልል ለሚገኙ ወገኖቻችን እንዲሁም መተከል ላይ ለሚገኙ ተፈናቃዮች የተለያዩ ቁሳቁሶችን ለመሰብሰብ ቅድመ ዝግጅቶችን አጠናቋል። የመጀመሪያ ዙር ለመላክም የትራንስፖርት ችግር ስላለብን በዚህ አጋጣሚ ልትተባበሩን የምትችሉ ሁሉ ጥሪ እናቀርባለን።

የእለት ደራሽ ምግብና የቁሳቁስ ድጋፍ ለማድረግ ከዛሬ ጀምሮ እንቅስቃሴ ጀምረናል።

*የማይበልሹ የምግብ ልገሳ አይነቶች
*ፉርኖ ዱቄት
*ሩዝ
*ፓስታ
* መኮረኒ
* ዘይት
* የበቆሎ እህል
* ምስር
* የህፃናት የታሸጉ ብትን ወተቶች
* የሕፃናት አልሚ ምግቦች

#የንጽህና መጠበቂያ አይነቶች

√ ሳሙና ፈሳሽና ደረቅ
√ ኦሞ
√በረኪና
√ ሳኒታይዘር
√ የሴቶች ንጽሕና መጠበቂያ (ሞዴስ)
√ የህፃናት ዳይፐር

#አልባሳት

*ብርድ ልብስ
* አንሶላ
√*ንጽሕናቸውን የጠበቁ የአዋቂዎችና ህፃናት አልባሳት

እንዲሁም አስፈላጊ የሆኑ የህክምና መርጃ ቁሳቁሶችና መድኃኒቶች ወደ ፍልውሃ ተውፊቅ መስጅድ እንድታቀርቡልን እየጠየቅን በቅርቡ ሌሎች ተባባሪ መስጅዶችና መሰብሰቢያ ጣቢያዎችን ይፋ የምናደርግ ይሆናል።

ለበለጠ መረጃ
091፞1728626 አዱኛው ሙጨ
0911282918 ኤልያስ ከድር
0911229537 ዲኑ አሊ
0911282940 ሙባረክ አደም

Читать полностью…

ABU DAWD OSMAN

የአፋር እና የሐረሪ ክልል መጅሊሶች ጠንካራ ማሳሰቢያ

የሃረሪ እና የአፋር ክልል መጅሊሶች የፌደራሉ መጅሊስ ውስጥ ያሉ ግለሰቦች ተቋሙን ለማፍረስ እየሄዱበትን ያለውን የጥፋት አካሄድ በመቃወም በቅርብ ቀናት ውስጥ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ተጠርቶ ችግሮች እልባት እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል::

የክልል መጅሊሶችንም ሆነ በፌደራል መጅሊስ ውስጥ ያሉ ኡለሞችን እና ምሁራንን በመናቅ በአንድ ግለሰብ የማንአለብኝነት አካሄድ የሙስሊሙ ተቋም መበጥበጥ ስለሌለበት የክልል መጅሊሶች የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ እና ማሳሰቢያ በመስጠት ላይ ናቸው::

አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ የማይጠራ ከሆነ የክልል መጅሊሶች በቃሲም ታጁዲን ለሚመራው ተቋም እውቅና ለጊዜው መስጠት እንደሚያቆሙ አሳስበዋል::

በዚህ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ላይ የአፋር እና የሐረሪ ክልል መጅሊሶች ቀዳሚነትን ሲይዙ የሌሎችም ክልሎች ይህን ተከትለው አቋማቸውን ያሳውቃሉ ተብሎ ይጠበቃል::

ግለሰብ ለሚበጠብጠው ተቋም መፍትሄው ሁሉም የክልል መጅሊሲች የሚሳተፉበት ጠቅላላ ጉባኤ ተጠርቶ በጉባኤው ችግሮቹ ተለይተው እሾኩን እና ሰንኮፉን ነቅሎ በመጣል ጊዜያዊ መጅሊሱ ለ6ወራት የተሰጠውን ስራ ቶሎ አጠናቆ ህዝባዊ የመጅሊስ አመራሮች ምርጫ በማካሄድ ህዝበ ሙስሊሙ የሚመርጣቸው መሪዎች ቦታውን እንዲረከቡ ማድረግ ብቸኛው መፍትሄ ነው!

Читать полностью…

ABU DAWD OSMAN

"ራትህን ከእናትህ ጋር በልተህ በዚህ እሷን ማስደሰትህ ፡ ይህ እኔ ዘንድ ከአንድ የሱና ሀጅ ይበልጣል።" ሀሰኑል በስሪ
ምንጭ፦ቢሩል ዋሊደይን(4)
አላህ ለእናታችን የደስታ ሰበብ የምንሆን ያድርገን!

Читать полностью…

ABU DAWD OSMAN

ሙስሊሙን በታትኖ ተቋም አልባ የማድረግ ጥረት መቼም አይሳካም!

አቡ ዳውድ ኡስማን

የህዝበ ሙስሊሙ የረጅም አመታት ጥያቄ የነበረው ጠንካራ በህዝብ የተመረጡ መሪዎች የሚመሩት ተቋም እንዲኖረው ሲያቀርበው እና ሲታገልልት የቆየው ጥያቄ መፍትሄ ያገኛል በሚል በሚያዚያ 23 በተደረሰው ስምምነት ለስድስት ወራት በጊዜያዊነት ተቋሙን የሚመሩ የኡለሞች እና የምሁራን ቦርድ መቋቋሙ ይታወሳል፡፡

እነዚህ ሁለት ቦርዶች እኩል ስልጣን የተሰጣቸው ሲሆን በመካከላቸው የሚና ልዩነት ብቻ ነበር የነበረው፡፡

የአስተዳደሩን እና የመዋቅር ጉዳዩን የምሁራን ቦርዱ እንዲመራው ሲደረግ ሃይማኖታዊ ጉዳዩን ደግሞ የኡለሞች ቦርድ ሃላፊነቱን ወስዶ እንዲንቀሳቀስ ሃላፊነት ተሰጥቷቸው ነበር፡፡

ሁለቱም ጊዜያዊ ቦርዶች በስድስት ወራት ውስጥ አዲሱን የመጅሊስ መዋቅር እና ህገ ደንብ አጸድቆ ወደ ስራ እንዲገባ፣የሙስሊሙ አንድነትን በተመለከተ የቀረበው የመግባቢያ ሰንድ ፀድቆ ወደ ተግባር እንዲለወጥ እንዲሁም የመጅሊሱ አመራሮች በሃገር አቀፍ ደረጃ በሚካሄድ ምርጫ እንዲመረጡ የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ ሃላፊነት ተሰጥቷቸው ነበር፡፡

ለስድስት ወራት በጊዜያዊነት የተረከቡትን ስልጣን ግን ህዝበ ሙስሊሙን በሚጠቅም እና የተሰጣቸውን ሃላፊነት ለመወጣት በሚችሉበት ሁኔታ ከመስራት ይልቅ መጅሊሱ አንድ ተቋም ሳይሆን ለሁለት የተከፈለ መሆን አለበት፣ አንድነት የሚባል ነገር የለም በሚል ከሚያዚያ 23 የሸራተኑ ጉባኤ በፊት ጀምሮ አንድነቱን አንፈልገውም መንግስት ከፈለገ ሁለት መጅሊስ ያድርግልን እስከማለት የደረሱ ጥቂት ግለሰቦች አሁንም መጅሊሱን እያመሱት ይገኛሉ፡፡(ይህን ጥያቄ ለሰላም ሚኒስተር ሳይቀር ቀርቦ የነበረ ቢሆንም የሙስሊሙን አንድነት የማይፈልግ ካለ መጅሊሱን ለቆ መውጣት ይችላል በሚል ጠንካራ አቋም የያዘ ምላሽ ተሰጥቷቸው ነበር)፡፡

መጅሊሱ በአዋጅ እንዲፀድቅ ጫፍ በደረሰበት ወቅት ሳይቀር መጅሊሱ የሁሉም ሙስሊሞች የጋራ ተቋም ሳይሆን የግላቸው ቡድን ተቋም ብቻ እንዲሆንላቸው ከፍተኛ ትግል ቢያደርጉም ሴራቸው ከሽፎ አመድ ማፈሳቸው ይታወሳል፡፡

ይህ እቅዳቸው ቢከሽፍም አሁንም ድረስ መጅሊሱ እንዲፈርስ እና ተቋሙ የሁሉም ሙስሊሞች የጋራ ተቋም ሳይሆን የቡድናቸው ተቋም ብቻ ካልሆነ እንቅልፍ አንተኛም በሚል አንድም ሙስሊሙን የሚጠቅም ስራ ሳይሰሩ በመበጥበት ድፍን ሁለት አመታትን ለመሙላት ወራት ብቻ ይቀራቸዋል፡፡

የኡለሞች ቦርድ ሃይማኖታዊ ጉዳዮችን እንዲመራ ሃላፊነት የተሰጠው ቢሆንም ሙሉ ለሙሉ የተሰጠውን ሃላፊነት በመተው በኡለሞች ቦርድ ውስጥ ያሉት የተወሰኑት ግለሰኖች ሙሉ ጊዜያቸውን የምሁራን ቦርዱ ምንም አይነት ስራ እንዳይሰሩ ደብዳቤ እየጻፉ ማገድ፣የክልል መጅሊሶች ውስጥ ጣልቃ በመግባት ለመከፋፈል እና ለመበታተን መሞከር፣ያለ ኡለሞች የጋራ ስምምነት ደስ ያላቸውን ደብዳቤ በግላቸው እየፃፉ የመጀሊሱን ማህተም በማድረግ መበጥበት የዘወትር ስራቸው አድርገዋል፡፡

ህዝባዊ ምርጫ ተካሂዶ የመጅሊሱን ቦታ በህዝበ ሙስሊሙ የተመረጡ አመራሮች ቦታውን እስኪረከቡ በጊዜያዊነት ሃላፊነት የተሰጣቸው ሰዎች ላለፉት ሁለት አመታት የመጅሊሱ ጠቅላላ ጉባኤ እንዳይካሄድ ከፍተኛ እንቅፋት ሲፈጥሩ የነበረ ሲሆን በሁሉም የክልል መጅሊሶች ጠቅላላ ጉባኤ እንዲጠራ በተደጋጋሚ ጥያቄ ቢቀርብላቸውም እስካሁኗ ደቂቃ ድረስ አሻፈረኝ እንዳሉ ይገኛሉ፡፡

የምሁራን ቦርዱ ህዝብ የሰጠውን አማና ለመወጣት እንቅስቃሴ ሲጀምር የምሁራን ቦርድ የሚባል አያስፈልግም በሚል በሸራተኑ ጉባኤ ለሁለቱም ቦርዶች የተሰጣቸው እኩል ስልጣን መሆኑን በመዘንጋት ግለሰቦቹ የምሁራን ቦርዱን አግደናል የሚል አስቂኝ ፉከራ ውስጥ ገብተዋል፡፡

የምሁራን ቦርዱም ሆነ የኡለሞች ቦርድ አንዱ አንዱን የማገድም ሆነ የማባረር ስልጣን የሌለው ሲሆን ሁለቱም ለስድስት ወራት ተቆጥሮ የተሰጣቸውን ስራ አጠናቀው በስድስት ወራት ውስጥ ምርጫ እንዲያካሂዱ ነበር ሃላፊነት የተሰጣቸው፡፡

በፌደራሉ መጅሊስ ውስጥ የኡለማ ምክር ቤቱ የጋራ ስምምነት በሌለበት ሁኔታ መጅሊሱ የአንድ ቡድን ብቻ መሆን አለበት በሚል ከበፊት ጀምሮ ሲበጠብጡ የነበሩት ግለሰቦች አሁንም የኡለማ ምክር. ሬ
ቤቱን ሌሎች አባላትን በመናቅ የግላቸውን ፍላጎት ለማሳካት እየተፍጨረጨሩ ይገኛሉ፡፡

የሙስሊሙ ተቋም ወኪሎች ሳይሆኑ የሌሎች ተላላኪ መሆናቸው በግልፅ እስኪታይ ድረስ ለሙስሊሙ መብት እና ጥቅም ከመቆም ይልቅ ሙስሊሙን ዘወትር በማዋረድ እና አንገቱን እንዲደፋ በማድረግ የሙስሊሙን አንድነት ለመበታተን ቀን ከሌት እየለፉ ይገኛሉ፡፡

መጅሊሱ አስተዳደራዊ ተቋም መሆኑን በመዘንጋት የሙስሊሙን መብት እና ጥቅም የሚያስጠብቅ፣ ሙስሊሙን በሁለንተናዊ ዘርፍ ከፍ የሚያደርግ፣ሙስሊሙ ከሃይማኖቱ አልፎ ለሃገሩም ጠቃሚ ዜጋ እንዲሆን ከማስቻል ይልቅ ዘወትር ሙስሊሙ አንድ እርምጃ እንዳይራመድ እንቅፋት እየሆኑ ይገኛሉ፡፡

ሃገራችን አሁን ባለችበት የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ አጋጣሚውን በመጠበቅ እነዚህ ጥቂት ግለሰቦች ሙስሊሙን ተቋም አልባ ለማድረግ እና የሙስሊሙን አንድነት እና ሰላም ለማናጋት ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ፡፡

የምሁራን ቦርዱ በህዝብ የተሰጠውን ጊዜያዊ ስልጣን በህዝብ በሚመረጡ አመራሮች እስኪተኩ ድረስ የትኛውም አካል የማገድም፣ ስራውን እንዳይሰራ የማስቆምም ህጋዊም ሆነ ህዝባዊ ስልጣን ያለው የመጅሊሱ አካል የለም፡፡

የምሁራን ቦርዱ ኡለሞቹን የማገድ ስልጣን እንደሌለው ሁሉ የኡለሞቹም ቦርድ ከተሰጠው ስልጣን ውስጥ በመውታት አቻ የሆነውን ቦርድ የማገድ ስልጣን የለውም፡፡

በሙስሊሙ ተቋም ላይ ስራ መስራት ካልቻሉ ተቋሙን ለሚረከቡ በህዝብ ለሚመረጡ መሪዎች አስረክቦ መውጣት እንጂ የአባታቸው ርስት ይመስል ስራም አይሰራም፣ እየበጠበጥኩኝ መጅሊሱን አፈራርሳል ብሎ መዳከር ፈፅሞ ተቀባይነት የለውም፡፡

ጊዜያዊ ስልጣናቸው እንዲያበቃ ከተፈለገ የሁሉም እኩል ያበቃል እንጂ አንዱ የአንዱን ስልጣን እና ሃላፊነት የመግፈፍ አንዳችም ስልጣን የለውም፡፡

መስራት ካልቻላችሁ አስቸኳይ ጉባኤ ጠርታችሁ ጠቅላላ ጉባኤ የሚወስነውን መተግበር እንጂ ጠቅላላ ጉባኤም አይጠራም፣ስራም አልሰራም፣ ለመስራት የሚንቀሳቀሰውንም እንቅፋት እየሆነኩኝ እቀጥላለው ማለት አይቻልም፡፡

۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩
በቴሌ ግራም መረጃዎች እንዲደርሳችሁ ካስፈለገ የሚከተለውን ሊንክ በመጫን ይቀላቀሉን
t.me/ABUDAWD

መረጃዎችን እና መልዕክቶችን በቀላሉ ወደኔ ለመላክ ካስፈለጋችሁ በዚህ የቴሌግራም አድራሻዬ በቀጥታ ልታደርሱኝ ትችላላችሁ.

/channel/abudawdosmann

በፌስቡክ ለመከታተል ገፁን ላይክ ያድርጉ
Click and Like ➤➤ @ https://www.facebook.com

Читать полностью…

ABU DAWD OSMAN

የሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጫና እየደረሰባቸው መሆኑን ገለፁ

አቡ ዳውድ ኡስማን

በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ የዋናው ገቢ ሙስሊም ተማሪዎች የኢሻ ሰላት መስጂድ ሄደው ለመስገድ መቸገራቸውን እየገለፁ ነው!

ሰገደው ሲመለሱ መግባት አትችሉም በሚል የዩኒቨርሲቲው ጥበቃ እየከለከላቸው ይገኛል! ከዚህ ቀደም ለረጅም ጊዜ ተማሪዎቹ ሰላታቸውን ሰግደው ሲመለሱ የቆዩ ሲሆን አዲስ መመሪያ ወጥቷል በሚል ሰገደው የሚመለሱ ተማሪዎችን መግባት አትችሉም በሚል እየመለሱ መሆኑ ታውቋል::

ባሳለፍነው ሳምንት ሙስሊም ተማሪዎቹ የኢሻ ሰላት ሰግደው ሲመለሱ አዲስ ህግ ስለወጣ መግባት አትችሉም በሚል በር ላይ እስከ ምሽት አራት ሰአት ካስጠበቋቸው ቡኃላ የዩኒቨርሲቲያቸውን ID card አምጡ በማለት ጠባቂ ፖሊሶቹ ድብደባ እንደፈፀሙባቸው ተማሪዎቹ ገልፀዋል::

ኢሻ ሰላት ሰገደው በመምጣታቸው ለድብደባ የተጋለጡት ተማሪዎች በመስጂድ ውስጥ ለማደር የተገደዱ ሲሆን እስካሁን ድረስ በአቅራቢያቸው ባለው መስጂድ የኢሻ ሰላት ወጥተው ለመስገድ አለመቻላቸውን ገልፀዋል::

በዩኒቨርሲቲ ውስጥ የጀምዓ ሰላት መስገድ መከልክሉን ተከትሎ ሙስሊም ተማሪዎች በአቅራቢያቸው በሚገኙ መስጂዶች የጀምዓ ሰላታቸውን እየሰገዱ የሚገኙ ሲሆን የሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ግን አዱስ መመሪያ በማውጣት ሙስሊም ተማሪዎች የኢሻ ሰላትም ከዩኒቨርሲቲው ውጪ በመስጂድ እንዳይሰግዱ እክል እየፈጠረባገው ይገኛል::

ድብደባ የተፈፀመባቸው ተማሪዎች የሚመለከተው አካል የዩኒቨርሲቲውን ህግ እና ደንብ አክብረን እየተማርን የቆየን ተማሪዎች መሆናችን ታውቆ ከዚህ ቀደም የነበረውን አሰራር በመሰረዝ ሃይማኖታዊ ግዴታችንን እንዳንፈፅም እየተደረግን በመሆኑ ዩኒቨርሲቲው ማስተካከያ ያደርግ ዘንድ የበኩላቸውን ሃላፊነት እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል::

Читать полностью…

ABU DAWD OSMAN

በዳይ እና ተበዳይ እስካሉ ድረስ ጀዛም አይቀሬ ነው!!

አቡ ዳውድ ኡስማን

በህይወትህ ውስጥ ምን ጊዜም ተበዳይ እንጂ በዳይ አትሁን፡፡ተገፊ እንጂ ገፊ አትሁን፡፡

ብትበደል ብትገፋ፣ቢያስሩህ፣ቢገርፉህ፣ ቢያሳድዱህ፣ ሃቅህን ቢከለክሉህ እና ቢያንገላቱህ፣ ክቡር የሆነ የሰው ልጅ መሆንህን ዘንግተው ቢያንቋሽሹህ፣ አላህ በሰጠህ ተፈጥሮ ቢያነውሩህ እና ቢሳለቁብህ፣ ስታምናቸው ቢከዱህ፣ስትወዳቸው እና ስታፈቅራው በምላሹ ቢጠሉህ፣እጅግ ባከበርካቸው እና መልካም በሆንክላቸው ልክ አንተን ቢያዋርዱህ እና መጥፎ ቢሆኑብህ፣ በአላህ ስም እየማሉ፣የአላህ ቃል የሆነውን ቁርዓን እየመቱ ቃልኪዳን ገብተናል እያሉህ አምነሃቸው በማግስቱ ቃላቸውን ቅርጥፍ አድርገው እየበሉ ቢክዱህ፣በውጫዊ ገፅታቸው እና አለባበሳቸው አላህን ፈሪ ናቸው ብለህ ሙሉ እምነትህን ሰጥተኃቸው እነሱ ግን የአላህን ድንበሮች እንዳሻቸው እየጣሱ በህይወትህ ላይ ቁማር ቢጫወቱብህ፣ ጊዜህን ገንዘብህን፣ጉልበትህን፣እድሜህን ቢያባክኑብህ፣........

ሲያጠፉብህ በፍቅር እና በትህትና ለማረም እና ለማስተካከል በመሞከርህ በምላሹ ባረምካቸው ስህተት አስታከው ጉድጓድ ቢምሱብህ ፣ባዘንክላቸው ቁጥር እንደ ደካማ ቆጥረውህ የጭካኔን ጥግ ቢያሳዩህ፣በውዴታ ህይወትህን አሳልፈህ ስትሰጣቸው በህይወትህ ጀርባ ቁማር ቢጫወቱብህ፣ ለነሱ ደስታ እና ምቾት ሁሌም ስትጨነቅ በተገላቢጦሹ እነሱ ደስታህን ቢነፍጉህ እና ሰላምህን ቢያሳጡህ፣ህመማቸው ህመመህ ሆኖ ስትጨነቅላቸው ባንተ ህመም ባንተ ቁስል እንጨት ቢሰዱብህ፣ ፣አማናቸውን ጠብቀህ አማናህን ባይጠብቁ፣ ክብራቸውን ጠብቀህ ክብርህን ባይጠብቁልህ .........

እምነኝ አላህ ዘንድ ፍትህ አለና በፍፁም አትዘን፡፡ ተበዳይ ሆነህ የሚፈሰው እንባህ ጎርፍ ሆኖ አንድ ቀን በዳዬችህን ባላሰቡት መንገድ መውሰዱ አይቀርም፡፡ አንተ ሃዘንህን ለአላህ ብቻ አሰማ
قَالَ إِنَّمَا أَشْكُو بَثِّي وَحُزْنِي إِلَى اللَّـهِ

«ጭንቀቴንና ሐዘኔንና የማሰማው ወደ አላህ ብቻ ነው፡፡(12፡86)

በዳይ እስካለ ድረስ ተበዳይ ይኖራል፡፡ በሁለቱ መካከል ደግሞ ፍትሃዊው ጌታ አላህ አለ፡፡ ለእያንዳንዱ ግፍ ተገቢ የሆነ ጀዛ በአላህ ዘንድ አለ፡፡ ዛሬ ላይ በመበደልህ ብዙ ነገር ብታጣም ነገ ላይ ግን አላህ የተሻለ ነገር እንደሚለግሰህ አትጠራጠር፡፡

በዳዬች የልባቸውን ፈፅመውብህ በደስታ ስካር ሲፈነጥዙ፣ ባንተ ባፈሰስከው እንባ እነሱ እየዋኙ ቢደሰቱ፣ ያንተን ህይወት ያጨለሙ መስሏቸው እና የራሳቸው ህይወት የበራላቸው ቢመስላቸውም የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ ሁሉም በሰፈረው መሰፈሩ አይቀርም፡፡

وَنَضَعُ الْمَوَازِينَ الْقِسْطَ لِيَوْمِ الْقِيَامَةِ فَلَا تُظْلَمُ نَفْسٌ شَيْئًا ۖ وَإِن كَانَ مِثْقَالَ حَبَّةٍ مِّنْ خَرْدَلٍ أَتَيْنَا بِهَا ۗ وَكَفَىٰ بِنَا حَاسِبِينَ

በትንሣኤም ቀን ትክክለኛ ሚዛኖችን እናቆማለን፡፡ ማንኛይቱም ነፍስ ምንንም አትበደልም፡፡ (ሥራው) የሰናፍጭ ቅንጣት ያክል ቢኾንም እርሷን እናመጣታለን፡፡ ተቆጣጣሪዎችም በኛ በቃ፡(21፡47)

ሁሌም ተስፋህን በአላህ ላይ አድርግ፡፡ መጥፎ ላደረገብህ መጥፎን አትመኝ፡፡መጥፎንም አታድርግ፡፡ በደልህን ለአላህ ነግረህ ጉዞህን ቀጥል፡፡ አላህ ሆይ ባጣሁት ነገር መልካም ነገርን ተካልኝ ብለህ ዱዓ አድርግ፡፡ መበደልህን የሚያስረሳህ ሌላ ህይወት ይገጥምህ ይሆናል፡፡

አንተ በደልህን ብትረሳውም ፣ያፈሰስካት እንባ ብትደርቅም፣ በፍፁም የበደለህ አካል ጀዛውን ሳያገኝ የሚቀር አይመሰልህ፡፡ አመታትን ይፈጅ ይሆናል፡፡ በርቼ አይቀሬ ነው፡፡ አልያ በዚህ በዱኒያ አለም ጀዛውን ባያገኝ እንኳን በቀጣዩ አለም ሁሉም የእጁን ማግኘቱ አይቀርም፡፡ ጊዜው ቢርቅም አላህ በደልህን ዘንጊ አይምሰልህ

አላሁ አዘወጀል ይህን ብሎናል፡-

وَلَا تَحْسَبَنَّ اللَّـهَ غَافِلًا عَمَّا يَعْمَلُ الظَّالِمُونَ ۚ إِنَّمَا يُؤَخِّرُهُمْ لِيَوْمٍ تَشْخَصُ فِيهِ الْأَبْصَارُ ﴿٤٢﴾

አላህንም በደለኞች ከሚሠሩት ግፍ ዘንጊ አድርገህ አታስብ፡፡ የሚያቆያቸው ዓይኖች በእርሱ እስከሚፈጡበት ቀን ድረስ ብቻ ነው፡፡(14፡42)

አደራ መበደልህ ለበቀል እና ለበደል አያነሳሳህ ካንተ የበቀል እርምጃ ይልቅ የአላህ ፍትሃዊ ፍርድ ላንተ በላጭ ካሳ ነው፡፡

አላህ ይህን ብሎናል፡-
أَلَيْسَ اللَّـهُ بِأَحْكَمِ الْحَاكِمِينَ ﴿٨

አላህ ከፈራጆች ሁሉ ይበልጥ ፈራጅ አይደለምን? (ነው)፡፡(95፡8)

نَّ اللَّـهَ يَأْمُرُ بِالْعَدْلِ وَالْإِحْسَانِ وَإِيتَاءِ ذِي الْقُرْبَىٰ وَيَنْهَىٰ عَنِ الْفَحْشَاءِ وَالْمُنكَرِ وَالْبَغْيِ ۚ يَعِظُكُمْ لَعَلَّكُمْ تَذَكَّرُونَ ﴿

አላህ በማስተካከል፣ በማሳመርም፣ ለዝምድና ባለቤት በመስጠትም ያዛል፡፡ ከአስከፊም (ከማመንዘር)፣ ከሚጠላም ነገር ሁሉ፣ ከመበደልም ይከለክላል፡፡ ትገነዘቡ ዘንድ ይገስጻችኋል፡፡(16፡90)

አላህ ሰዎችን ከመበደል ይጠብቀን!!
አሚን !!

Читать полностью…

ABU DAWD OSMAN

"ትልቅ አስተዋፅኦ አበርክተህልናል" በሚል በምስሉ ላይ የሚታዩት የቀድሞ ህገ ወጡ መጅሊስ አመራሮች ሽልማት የተበረከተለት የህወሃት መስራች እና መሪ የነበረው አቦይ ስብሃት ከተደበቀበት መያዙ ይፋ ሆኗል::
ጊዜ ደጉ!
በሙስሊሙ ላይ ያደረሱትን ግፍ መቼም አንረሳውም!

ትላንትም ሆነ ዛሬ እንዲሁም ነገም ሙስሊሙን ሲያጠቁ እና ለማጥቃት ለሚሞክሩ በዳዮች ሁሉ አላህ ያዋርዳቸው!

Читать полностью…

ABU DAWD OSMAN

የቁርዓን ተፍሲር ፕሮግራም በግራር ሃምዛ መስጂድ

የኪታብ ቂርኣት ፕሮግራም!
እንዳያመልጦ!

📖 ቁርኣን ተፍሲር

በኡስታዝ ሱልጣን ኸድር
ዘውትር ቅዳሜ

ከመግሪብ እስከ ዒሻእ

አድራሻ ፦ ግራር አከባቢ በሚገኘው ሀምዛ መስጂድ
Te»http://t.me/sultan_54

Читать полностью…

ABU DAWD OSMAN

"በኢስላም እይታ ከአንድ የሃይማኖቱ ተቋም አንድ አማኙ መብለጡ እርግጥ ነው። ነገር ግን ሃይማኖቱና የሃይማኖቱ ክብር ደግሞ ከአማኞቹ በላይ መሆኑ ሊረሳ አይገባም። ለሃይማኖታቸው ክብርና ነፃነት ሲታገሉ ህይወታቸውን የሚሰዉት ሃይማኖቱ ከአማኞቹ ስለሚበልጥ ነው፡፡ የአማኙ ሕይወት ከሃይማኖቱ የሚበልጥ ቢሆን ኖሮ ሸሂድ ወይም ሰማዕት የሚባል ባልኖረ ነበር። ከዚያ በተጨማሪ የኢስላማዊ የድንጋጌዎችን ዓላማ(መቃሲድ አ-ሸሪዓ) ላይ የዚህና የቀጣይ ዓለም ስኬት መሠረት የሆነውና የሰው ልጆች የተፈጠሩለት ዋናው ዓላማ ዲን በመሆኑ ዲንን መጠበቅ ነፍስን ከመጠበቅ እንደሚቀድም ማስታወሱም አይከፋም፡፡ "

© Ahmedin Jebel official - አህመዲን ጀበል

Читать полностью…

ABU DAWD OSMAN

የአልነጃሺ መስጂድ ጥቃት

አቡ ዳውድ ኡስማን

በትግራይ ክልል የሚገኘው ታሪካዊው የአል ነጃሺ መስጂድ በጦርነቱ ሳብያ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል::

እስካሁን በትግራይ ክልል በትልልቅ ተቋማት ላይ የደረሰውን ውድመት የመንግስት ሚዲያዎች በስፋት ሲዘግቡ የቆየ ቢሆንም ይህን በአለም ቅርስነት የተመዘገበ መስጂድ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበትም እስካሁን በመንግስት ሚዲያዎች አለመዘገቡ ግራ አጋቢ ሆኗል::

የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችን በእምነት ተቋማት ሲከማቹ እንደነበር እና ለቤተ እምነቶቹ ክብር ሲባል በጥንቃቄ እርምጃ ሳይወሰድ በዘዴ ቦታዎቹን ለመቆጣጠር ጥረት መደረጉ ሲገለፅ የቆየ ቢሆንም በአል ነጃሺ መስጂድ የሆነው ግን ከዚህ የተለየ ሆኖ መስጂዱ ከፍተኛ ውድመት ደርሶበታል::

ይህን ጥቃት በመስጂዱ ላይ የፈፀሙት አካላቶች የመንግስት ወታደሮች ይሁኑ የህወሃት ታጣቂዎች እስካሁን ገለልተኛ ከሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎች የተረጋገጠ ማስረጃ ባይሰማም የተለያዩ ወገኖች በሚፈልጉት መልኩ እየዘገቡት ይገኛሉ::

በምንም መመዘኛ ለሌሎች ቤተ እምነቶች ልዩ ጥንቃቄ ሲደረግ ቆይቶ በዚህ ታሪካዊ መስጂድ ላይ ግን የዚህ መሰሉ ውድመት እንዲደርስ መደረጉ ጥያቄ የሚያጭር ነው::

መንግስት አለም አቀፍ እውቅና ያለውን ታሪካዊ መስጂድ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት እስካሁን ምንም አለማለቱ የሁላችንም ጥያቄ እንደመሆኑ ይህን ጥፋት የፈፀሙ አካላትን መንግስት በይፋ ሊያሳውቅ ይገባል!

የአልነጃሺ መስጂድ ውድመት በማንም ይሁን በማን ይፈፀም ታሪክን መቀየር የሚችል አይደለም:: ትላንት በቱርክ መንግስት እርዳታ ታድሶ ለአገልግሎት እንደበቃ ሁሉ አሁንም በገንዘባችን ዳግም ታድሶ ለአገልግሎት ይበቃል::
መስጂዱን ብቻ ኢላማ ያደረገው ጥቃት ግን ውስጣችንን አብግኖታል::
አስቸኳይ ማብራሪያ ሊሰጥበት ይገባል

የአል ነጃሺን ታሪክ መስጂዱ ላይ ጉዳት በማድረስ የሚጠፋ አይደለም!

ንጉስ አስሃማ እስልምናን የተቀበለ የመጀመሪያው የአክሱም ንጉስ ነበር!

Читать полностью…

ABU DAWD OSMAN

ዝናብን ለሚለግሰን ለአለማቱ ጌታ ምስጋና ይገባው

ጌታችን አላህ በቅዱስ ቃሉ ይህን ይለናል

أَفَرَأَيْتُمُ الْمَاءَ الَّذِي تَشْرَبُونَ
ያንንም የምትጠጡትን ውሃ አያችሁን?
أَأَنتُمْ أَنزَلْتُمُوهُ مِنَ الْمُزْنِ أَمْ نَحْنُ الْمُنزِلُونَ
እናንተ ከደመናው አወረዳችሁትን? ወይስ እኛ አውራጆቹ ነን?

لَوْ نَشَاءُ جَعَلْنَاهُ أُجَاجًا فَلَوْلَا تَشْكُرُونَ

ብንሻ ኖሮ መርጋጋ ባደረግነው ነበር፡፡ አታመሰግኑምን? (ሱረቱል ዋቂያዕ68-70)

Читать полностью…

ABU DAWD OSMAN

አራጁ አፄ ዩሐንስ ላረዳቸው ሙስሊሞች ምላሽ ያገኝበት የጋላባት ጦርነት ከተካሄደ 13 2 አመታት ሞላው

አቡ ዳውድ ኡስማን

ከ20ሺህ በላይ ኢትዬጲያውያን ሙስሊሞችን እምነታችሁን ካልቀየራችሁ በሚል በቦሩ ሜዳ አንገታቸውን እየቀላ የጨፈጨፋቸው አፄ ዩሐንስ ለሰራው ግፍ የእጁን ያገኘበት ጦርነት ከተካሄደ 132 አመታት አስቆጠረ::

የመተማ (ጋላባት) ጦርነት የተካሄደው ከዛሬ 132 ዓመታት በፊት መጋቢት 1 ቀን 1881ዐ•ል ነበር፡፡

ጦርነቱ ከደርቡሾች (መሐዲስቶች) ጋር የተካሄደ ሲሆን በጦርነቱም አፄ ዩሃንስ ክፉኛ ቆስሎ በነጋታው ህይወቱ አልፏል::

ሙስሊሞችን ሲጨፈጭፍ እና አንገታቸውን ሲቆርጥ የነበረው ይህ መሪ መሞቱ ብቻ በቂ አይደለም በሚል ለመሪያቸው ለማሳየት ደርቡሾች መጋቢት 3/1881 አንገቱን ቆርጠው ወስደውታል::

በግፍ ያፈሰሰው የሙስሊሞች ደም ሳይደርቅ የሱም ደም ፈሰሰ!

ዛሬም የንፁሃን ነፍስ በግፍ በየቦታው እየፈሰሰ ነው:: ጨፍጫፊዎች ይዋል ይደር እንጂ አንድ ቀን እንደ አፄ ዩሃንስ የእጃቸውን ማግኘታቸው አይቀርም!

የሱን ራዕይ ዛሬም ድረስ ተከትለው የሙስሊሙን ደም የሚያፈሱ እና ለማፍሰስ የሚቋምጡ እንዲሁም ማንኛውንም ንፁሃን በግፍ የሚጨፈጭፉ እና የሚያስጨፈጭፉ ሁሉ የሱን መጨረሻ ታሪክ መዝግቦት አልፏል እና እናንተም ተማሩበት ልንላቸው ይገባል::

ታሪክን የምንማረው እና የምናነበው የትላንቱን ጥፋት ተምረንበት እንዳንደግመው ለመማማር እንጂ በድሮ በሬ ዛሬ ላይ ለማረስ እና የድሮ ጥፋትን ዛሬ ላይ ለመበቀያነት ለማነሳሳት አይደለም!

ጨፍጫዎች ሆይ ከአፄ ዩሃንስ መጨረሻ ተማሩ!

Читать полностью…

ABU DAWD OSMAN

የጥር 22 የሞጣ መዋጮ የት ደረሰ?
ሃሩን ሚዲያ ልዩ ዶክመንተሪ ይጠብቁን
..
ለሞጣ ተጎጂዎች የተደረገውን ታሪካዊው መዋጮ አስመልክቶ "መዋጮው የት ደረሰ?" በሚል ሀሩን ሚዲያ ቦታው ድረስ በመጓዝ ባለድርሻ አካላትን አነጋግሮ ልዩ ታሪካዊ ዶክመንትሪ አዘጋጅቷል።
..
የጥር 22 መዋጮ የት ደረሰ? ነገ ጁሙዓ ምሽት በሀሩን ሚዲያ የሶሻል ሚዲያ አድራሻና በኢስላማዊ ሳተላይት ቴሌቭዥን ጣቦያዎች BST ፥ ኑረልሁዳ ሌሎችም ይጠብቁን..
ማስታወቂያውን ይመልከቱ
..
©️ ሀሩን ሚዲያ

Читать полностью…

ABU DAWD OSMAN

"እናት አንድ ሆና ለሰው አስቸገረች፤
ምነው እንደ ዘመድ ሶስት አራት በሆነች!"
በህመም ላይ ያሉ እናቶቻችንን አላህ አፊያ ያድርግልን! የሞቱብንንም ማረፊያቸውን በጀነት ያድርግልን!

Читать полностью…

ABU DAWD OSMAN

ከሰላም ሚኒስተር ጋር የተካሄደው ስብሰባ መልካም እንደነበር ተሰምቷል::
በአስር ቀናት ውስጥ መልካም ነገር የምንሰማበት እንደሚሆን በአላህ ላይ ተስፋ ተደርጓል! ጉዳዩን እየተከታተልን
በዱዓ እንበርታ

Читать полностью…

ABU DAWD OSMAN

በኡለሞች ስም የሚነግደው ግለሰብ

ቃሲም ታጁዲን ይህን ደብዳቤ በመፃፍ የኡለማ ምክር ቤቱ ያወጣው መግለጫ በማለት በፎርጂድ ባሰራው ማህተም ደብዳቤውን ለማሰራጨት ሞክሯል::

ይህን እራሱ የፃፈውን መግለጫ የኡለማ ምክር ቤቱ በሚዲያ እንዲሰራጭ ወስኗል በማለት ለማሰራጨት የሞከረ ሲሆን የኡለማ ምክር ቤት ቀርቶ የኡለማ ምክር ቤቱ ስራ አስፈፃሚ አባላት እንኳን ይህን መግለጫ የማያውቁት እና በመግለጫው ዙሪያም ምንም አይነት ውይይት አለማድረጋቸውን ገልፀዋል::

የመጅሊሱ ምክትል ፕሬዝደንትን ጨምሮ ሼይኽ መሐመድ ሐሚዲን፣ሼይኽ ሰኢድ አህመድ ሙስጠፋ እና ሌሎችም የስራ አስፈፃሚ አባላት የሚያውቁት ነገር እንደሌለ አሳውቀዋል::

ከ26ቱ ኡለሞች 3 ሰዎች ብቻ ያሻቸውን እያደረጉ ሲሆን ቀሪዎቹ ኡለሞች ከመጅሊሱ ተገፍተው በስማቸው እየተነገደባቸው ይገኛል::

ከመጅሊሱ የኡለማ ምክር ቤት የተገፉት ኡለሞች ዝምታቸውን በመስበር ለህዝባቸው እውነታውን የሚያሳውቁበት እና እየበጠበጠ የሚገኘውን ግለሰብ የሚያጋልጡበት ወቅት አሁን ነው::

Читать полностью…

ABU DAWD OSMAN

ከሃገር ውጭ ላላችሁ ሙስሊሞች‼
=======================
«ለሌሎችም ሼር በማድረግ ወደ መልካም ሥራ ያመላክቱ!»
||
✍ ነሲሓ ቲቪንና ሌሎች በርካታ ዳዕዋዎችን ለማገዝ ታልሞ በሂደት ላይ የሚገኘውን የዳሩ-ት-ተውሒድ የወቅፍ ፕሮጀክት ዕውን ለማድረግ በርካቶች የቻሉትን በመስጠት አሻራቸውን እያሳረፉ ነው።

እናንተም በዚህ ታሪካዊ የወቅፍ ፕሮጀክት ላይ አሻራችሁን ታሳርፉ ዘንድ በቀላሉ ለመደገፍ እንዲመቻችሁ ይህ የ"ጎ ፈንድ ሚ (Go Fund Me) እድል ተመቻችቶላችኋል።

https://gf.me/u/yqswrt

... وَمَا تُنفِقُواْ مِنۡ خَيۡرٖ فَلِأَنفُسِكُمۡۚ وَمَا تُنفِقُونَ إِلَّا ٱبۡتِغَآءَ وَجۡهِ ٱللَّهِۚ وَمَا تُنفِقُواْ مِنۡ خَيۡرٖ يُوَفَّ إِلَيۡكُمۡ وَأَنتُمۡ لَا تُظۡلَمُونَ

«...ከገንዘብም የምትለግሱት (ምንዳው) ለነፍሶቻችሁ ነው፡፡ የአላህንም ፊት (ውዴታውን) ለመፈለግ እንጂ አትለግሱም፡፡ ከገንዘብም የምትለግሱት ሁሉ (ምንዳው) ወደናንተ ይሞላል፡፡ እናንተም አትበደሉም»

Surah Al-Baqarah, Ayah 272
___________
👇👇

ዳሩ-ት-ተውሒድ የወቅፍ ፕሮጀክት
የወቅፉ ገቢ ለምን ይውላል?
√ ነሲሓ ቲቪ
√ ነሲሓ መስጂድና መድረሳ
√ ዳሩል ሐዲሥ ኢስላማዊ ኮሌጅ
√ የቁርኣን ሒፍዝ ሐለቃት
√ ዒልም ተኮር ኮርሶች
√ ቃፊላ የዳዕዋ ጉዞዎች
እና ሌሎችም አንፀባራቂ የዳዕዋ ስራዎች!

ኒያዎን ለወቅፍ አካውንት ገቢ ለማድረግ
ንግድ ባንክ 1000337985328

T.me/darutewhidweqf

Читать полностью…

ABU DAWD OSMAN

መሳለሚያ ከቤታቸው ወደ መርካቶ ሸማ ተራ ሄደው ወደ ቤት አልተመለሱም። እና ያገኛቸው ካለ በዚህ ስልክ [ሞባይል] በመደወል ብታሳውቁ ይላል ልጃቸው አንዋር ደሊል [0911574406]

Читать полностью…

ABU DAWD OSMAN

በፌደራል መጅሊስ ውስጥ ምን እየተካሄደ ነው የሚገኘው? ብዙ የተደከመበትን ተቋም የማፍረስ እና የመበትን ተግባር ፈፅሞ ተቀባይነት የለውም!ዝርዝሩን እመለስበታለው

Читать полностью…

ABU DAWD OSMAN

በጦርነቱ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት የትግራይ ህዝብ የሁላችንንም እርዳታ ይሻሉ

ከ4.5 ሚልዮን በላይ ቁጥር ያለው የትግራይ ህዝብ በጦርነቱ ክፉኛ በመጎዳቱ ኣስቸኳይ እርዳታ ያስፈልገዋል።
ኢትዮጵያውያን እንደ ክልል መስተዳድሮች፣ እንደ ከተማ ኑዋሪዎች፣ እንደ ህዝብና ዜጋ እንደ ዲያስፖራ፣ እንደ ሰው በጦርነቱ ክፉኛ ለተጎዳው የትግራይ ህዝብ እርዳታ ማድረስ ይጠበቅበታል።

በመላ ኢትዮጵያና ዓለም የምትገኙ ተጋሩ ኢትዮጵያውያን ቤተሰቦቻቹ፣ ጎረቤቶቻቹና ህዝባቹ በመርዳት ግዴታቹ ተወጡ።

ሁሉም ኢትዬጵያዊ ጠላቱን በማሶገድ ሂደት ላይ ድጋፍ እንዳደረገው ሁሉ በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰበት የትግራይ ህዝብም ድጋፍ ለማድረግ በሰፊው መንቀሳቀስ ግድ ይላል

* ምግብ፣ መድሓኒት፣ ሸቀጣሸቀጥ በኣስቸኳይ ያስፈልገዋል።

#የትግራይን_ህዝብ_እንርዳ !

Читать полностью…

ABU DAWD OSMAN

ተቦዝ በርቼ ሰላም! ይላል ስልጤ

"ጌታህ በዳዮች የሚሰሩትን ግፍ ዘንጊ አድርገህ አታስብ"

የዛሬ በዳዮች ከዚህ ክስተት ተማሩ!

የትላንት በዳይ ዛሬ ሲዋረድ ስታይ የዛሬ በዳይ ነገም ይህ እጣ እንደሚገጥመው እውቅ!

በጌታዬ አላህ ይሁንብኝ በደልን የፈፀመ ማንም ይሁን ማን አላህ ጀዛውን ሳይከፍለው አይቀርም!

በደል እና ግፍ መፈፀም ለጊዜው የበላይ ቢያደርገንም መጨረሻው ግን ውርደት ነው!

Читать полностью…

ABU DAWD OSMAN

ቋሚ የቂርዓት ፕሮግራም በአል አቅሷ መስጂድ

የኪታብ ቂርኣት በኡስታዝ መሐመድ ፈረጅ!
እንዳያመልጦ!

📖 ኡሱሉል ኢማን

በኡስታዝ መሐመድ ፈረጅ

ዘውትር ጁምዓ

ከመግሪብ እስከ ዒሻእ

አድራሻ ፦ ስድስት ኪሎ አፍንጮ በር ጋር ባለው አል አቅሷ መስጂድ

Читать полностью…

ABU DAWD OSMAN

የአለማቱ ጌታ እንዲህ ይለናል:-
በል"እርሱ አላህ አንድ ነው። አላህ (የሁሉ) መጠግያ ነው።
አልወለደም፤አልተወለደምም።ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።"(ቅዱሥ ቁርዓን 112፥ከ1-4)

Читать полностью…

ABU DAWD OSMAN

ሳኡዲ አረቢያ እና ኳታር የአየር እና የየብስ ድንበራቸው ክፍት ለማድረግ ተስማሙ!ትራምፕ ሲመጣ ለያያቸው መሄዱ ሲታወቅ ወደ እርቅ ቀረቡ! ሁለቱ ወንድማማች የሆኑ ጎረቤት ሃገራቶችን አላህ ይበልጥ ያስማማቸው!

Читать полностью…

ABU DAWD OSMAN

ታላቅ የምስራች ለእውቀት ፈላጊዎች በሙሉ

አሰላሙዐለይኩም ወረሕመቱላሂ ወበረካቱህ

በስልጢ ወረዳ ሰነና ገሬራ የሚገኘው የኑራሀ መስጂድና የቁርኣን ት/ቤት በቅበት ከተማ 01 ቀበሌ የቁርኣንና ሐዲስ ሒፍዝ ማዕከል ቅርንጫፍ በመክፈት ተማሪዎችን ተቀብሎ በማስተማር ለይ መሆኑ ይታወቃል። በመሆኑም መርከዙ ባሉት ክፍት ቦታዎች ተጨማሪ አዲስ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል።

ማዕከሉ የሚሰጣቸው የት/ት ዘርፎች
① አዲስ የቁርኣን ሒፍዝ
② ሐፍዘው ለረሱ የሙራጀዓ ፕሮግራም
③ የቁርኣን ኢጃዛ ፕሮግረም
④ አጫጭር የዐቂዳ ኪታቦች ፣ የአርበዒን ሐዲስ ሒፍዝና ትንታኔ
⑤ የፊቅህ ትምህርቶች
⑥ የቱሕፈቱል አጥፋል መትን ሒፍዝ እና ሌሎችም በዚህ ዘርፍ ተያያዥነት ያላቸው ትምህርቶች በመስጠት ላይ ስለሚገኝ ፈጥነው ይመዝገቡ።

የምዝገባ ቀን ከ22/04/2013 ዓል እስከ 26/04/2013 ዓል

የምዝገባው ቦታ ቅበት ከተማ 01 ቀበሌ ስታዲየም አካባቢ ከሚገኘው ዑመር መስጂድ ጀርባ ከሚገኘው የመርከዙ ቅርንጫፍ

ት/ት የሚጀምርበት ቀን ጥር 04 2013 ዓል

Читать полностью…
Subscribe to a channel