abudawd | Unsorted

Telegram-канал abudawd - ABU DAWD OSMAN

-

Subscribe to a channel

ABU DAWD OSMAN

ይህን ለማድረግ የሚከተለውን Step ይከተሉ፡-

-በቲውተር አካውንታችን Setting የሚለው ውስጥ ይግቡ

--በመቀጠልም በSetting ውስጥ ከተዘረዘሩት ምርጫዎች መካከል ወደታች በመሄድ Apps የሚለውን ይጫኑ

-በመቀጠልም Apps የሚለውን ስንከፍት Facebook Connect የሚል ምርጫ እናገኛለን፡፡ እሱን ምርጫ በመጫን የፌስቡክ አካውንታችንን በማስገባት የቲውተር አካውንታችንን ከፌስብከ አካውንታችን ጋር በቀላሉ ማገናኘት እንችላለን ማለት ነው፡፡

- አስፈላጊ ከሆነም ሁለቱንም በማገናኘት በፌስቡክ ፖስት ያደረግነውም በቲተር ፖስት እንዲሆን እንዲሁም በቲውተር ፖስት ያደረግነውም ደግሞ በፌስቡክ ፖስት እንዲሆን ማድረግ ይቻላል፡፡

- የፌስቡክ አካውንታችንን ከቲውተር ጋር ማገናኘታችን በዋነኝነት በቲውተር ከ140 ፊደላት በላይ የያዘ መልዕክት ማስተላለፍ ስለማይቻል በፌስቡክ የፈለግነውን መልዕክት ስንፅፍ በቲውተር ላይም ለሚገኙ ሰዎች የፅሁፉን ሙሉ መልዕክት በሊንክ ስለሚያስቀምጥልን በቀላሉ እንዲደርሳቸው ማድረግ ያስችለዋል፡፡

ከላይ የተዘረዘሩት አጠር ያሉ የቲውተር አጠቃቀም መግለጫዎች ማንኛውንም የቲውተር ጀማሪ ተጠቃሚ መጠነኛ ግንዛቤ በአላህ ፈቃድ ያስጨብጣሉ፡፡

አንብበው ሲጨርሱ ሼር በማደረግ ለሌሎች አጠቃቀሙን ያካፍሉ

You Can Follow Me On Tiwtter :- @Abudawdosman

۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩
በቴሌ ግራም መረጃዎች እንዲደርሳችሁ ካስፈለገ የሚከተለውን ሊንክ በመጫን ይቀላቀሉን
t.me/ABUDAWD

መረጃዎችን እና መልዕክቶችን በቀላሉ ወደኔ ለመላክ ካስፈለጋችሁ በዚህ የቴሌግራም አድራሻዬ በቀጥታ ልታደርሱኝ ትችላላችሁ.

/channel/abudawdosmann

በፌስቡክ ለመከታተል ገፁን ላይክ ያድርጉ
Click and Like ➤➤ @ https://www.facebook.com/abudawdosman

Читать полностью…

ABU DAWD OSMAN

መስጂድ አል ሐረም

የሮቦት ኻዲሞች

Читать полностью…

ABU DAWD OSMAN

በሒጅራ የጨረቃ አቆጣጠር የነገ ሐሙስ የሙሐረም 10 የአሹራ ፆም እንዳያልፈን!
ለራሳችንም ለሃገራችንም ሰላም ዱኣ ማድረግ አንዘንጋ!

Читать полностью…

ABU DAWD OSMAN

በሒጅራ አቆጣጠር አዲሱ አመት የፊታችን ማክሰኞ (Aug 10) ሙሐረም 1 ይገባል!
1443 አመተ ሒጅራ የኸይር አመት አሏህ ያድርግልን!

Читать полностью…

ABU DAWD OSMAN

ሼር በማድረግ ለሌሎችም እናጋራው

የወንድማችን ነጃ ዋበላ ሰዒድ የባንክ አካውንት ተከፍቷል

ወንድማችንን ለመርዳት የባንክ አካውንት የጠየቃችሁ በሃገር ውስጥም ሆነ ከሃገር ውጪ ያላችሁ በስሙ
አካውንት ስለከፈተ በአካውንቱ ድጋፍ ማድረግ ትችላላችሁ

የአካውንት ስም:— ነጃ ዋበላ ሰኢድ
የሒሳብ ቁጥር:— 1000399619533
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

Читать полностью…

ABU DAWD OSMAN

ወንድማችንን በስልክ አግኝቼዋለው!

አቡ ዳውድ ኡስማን

ይህ ወንድማችን ነጃ ወበላ ይባላል:: መርካቶ ጣና እና ምዕራብ አካባቢ ነው የሚሰራው::በዚህ ጠዋትም መርካቶ ምዕራብ አካባቢ በስራ ላይ ነው:: መኖሪያ ቤቱም አሸዋ ሜዳ አካባቢ መሆኑን አካፍሎኛል:: የራሱ የባንክ አካውንትም እንዳለው ገልፆልኛል::

በአካል ወንድሞች አግኝተውታል:: ቪዲዮ እና የባንክ አካውንቱንም ያካፍሉናል ኢን ሻ አሏህ

አድራሻውን ላደረስከኝ ወንድም አቡበከር አላህ ኸይር ጀዛህን ይክፈልህ

Читать полностью…

ABU DAWD OSMAN

ኧረ በአሏህ እያለ ቢማፀናቸውም ልጆቼ እያለ ቢለምናቸውም ሽጦ ልጆቹን የሚያኖርበትን ነጥቀው ወስደውበታል::
ህግ ማስከበር ተገቢ ነው ቢባል እንኳን አንድ ሚስኪን ደሃን እንዲህ አበሻቅጦ በጭካኔ ንብረቱን መውረስ ያሳዝናል:: በዚህ መጨካከናችን አላህ ሌላ በላእ በኛ ላይ አለማውረዱም አዛኝነቱ ነው
አላህ እጥፉን እና የተሻለውን ይተካልህ ወንድሜ

Читать полностью…

ABU DAWD OSMAN

ኑር የቁርዓን ባንክ

ውድ የመላካም ስራ ቤተሰቦች ላለፉት አመታት ከበጎ አድራጊ ግለሰቦች፣ወዳጆቻችንና ጓደኞቻችን
ቁርዓን በመሰብሰብ ወደ ተለያዩ ገጠራማ አካባቢዎች ስናሰራጭ ቆይተናል።ለዚህም በዚህ መልካም ስራ ለተሳተፋችሁ ሁሉ የአላህን እዝነት እንለምነዋለን።

ነገር ግን በየአመቱ ለተወሰነ ጊዜ ብቻ ቁርአንን ሰብስበን በበቂ ሁኔታ ማዳረስ አልቻልንም።
ከየገጠሩ አከባቢና ከየመድረሳው ጠያቂ ከቀን ወደቀን እየጨመረ ነው።
ገጠር አከባቢ ያሉ መድረሳዎች ላይ በዚሁ ምክንያት ቂርዓት እንዳቋረጡ መረጃዎች ይደርሱናል።

ስለዚህም ዘላቂ መፍትሄ አስበን በተደራጀ መልኩ በቋሚነት ለመስራት እንቅስቃሴ የጀመርን ስለሆነ መላው ሙስሊም ማህበረሰብ ፕሮጀክቱ እውን በሚሆንበት ሂደት ላይ
ከጎናችን እንድትቆሙ በአላህ ስም እንጠይቃለን!!

0913382025 ኑረዲን ነስሮ
0952461303 Fuad Hussein
0935086914 Abas
0913708282 temr

Читать полностью…

ABU DAWD OSMAN

የኦሮሚያ ክልል መጅሊስ ላቀዳቸው ግዙፍ ፕሮጀክቶች ማስፈፀሚያ የሚውል ኡስታዝ አቡበክር አህመድ 100ሺህ ብር ድጋፍ አድርገዋል::

የአዲስ አበባ መጅሊስ የስራ አመራር ቦርድ አባል የሆኑት ኡስታዝ ሱፍያንም በተመሳሳይ 100ሺህ ብር ድጋፍ አድርገዋል::

አላህ ልገሳቸው ይቀበላቸው!

Читать полностью…

ABU DAWD OSMAN

የወንድማችንን ህይወት እንታደግ!

ውዱ ወንድማችን አብዱሰታር ናስር በኩላሊት ህመም እየተሰቃየ የሚገኝ ወንድማችን ነው::

የባዩሽ መስጂድ የጀርባ አጥንት የነበረ ጠንካራ ወንድም የነበረ ሲሆን አሁን ላይ በህመም ምክንያት አልጋ ላይ ወድቆ ይገኛል::

በዚህ በተከበረ ወር ህይወቱን ለመታደግ ያቅማችንን በመደገፍ ትልቅ የአኼራ ስንቅ እንሸምት!

የበጎ ሥራ ዋጋ በጎ እንጅ ሌላ ነውን?

የኢ/ንግድ ባንክ ፦1000381947808 አብዱሰታር ናስር 0911161131

https://chat.whatsapp.com/HfF9gmWwVDP1veYAAq53Dn

Читать полностью…

ABU DAWD OSMAN

ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን

የታላቁ አንዋር መስጂድ ምክትል ኢማም ሼይኽ ሁሴን ወደ አኼራ ሄዱ!

አቡ ዳውድ ኡስማን

የታላቁ አንዋር መስጂድ ምክትል ኢማም በመሆን ለረጅም አመት ህዝበ ሙስሊሙን ሲያገለግሉ የቆዩት ሼይኽ ሁሴን በድንገት ወደ አኼራ ሄደዋል::

ሼይኽ ሁሴን እጅግ ተወዳጅ፣አላህን ፈሪ፣የሙስሊሙን አንድነት አጥበቀው የሚሹ ታላቅ ኢማም ነበሩ::

በአንዋር መስጂድ እሳቸው ኢማም በሚሆኑበት ወቅት ጀምዓው በደንብ ተሰባስቦ ይሰግድ እንደነበር ሁሉም የሚመሰክረው ሲሆን ሙስሊሙን ኡማ የሚጠቅም ትምህርቶችን በመስጂዱ ከማስተማር ውጪ አንዳችም ክፉ ቃል በአላህ ቤት ውስጥም ሆነ ውጪ ተናግረው የማያውቁ አላህን ፈሪ የሆኑ ኢማም ነበሩ::

ሼይኽ ሁሴን ህዝበ ሙስሊሙ የመንግስትን ጣልቃ ገብነት በመቃወም ሰላማዊ ትግል በሚያካሂድበት ወቅት "አብሽሩ አላህ ይረዳናል፣ በርቱ አላህ ከተበዳዮች ጎን ነው እያሉ ያበረታቱ ነበር:: በኢድ ቀንም የመንግስት የፀጥታ ሃይሎች ሙስሊሙ ላይ የበቀል እና የሃይል እርምጃ በወሰዱበት ወቅት ከፍተኛ ድብደባ ተፈፅሞባቸው የነበረ ሲሆን እሳቸው ግን "ቀደምት ሙስሊሞች በመጋዝ ሁለት ቦታ አናታቸው እየተሰነጠቀ ለዲኑ መስዋት ከፍለዋል ይህ ለኢስላም ምንም ማለት አይደለም" በማለት ለሚጠይቃቸው ሰው ይናገሩ ነበር::

እኚህን የመሰለ ሃቀኛ፣ለስልጣን እና ለገንዘብ ሲሉ ከሙስሊም ጠላቶች ጋር የማያብሩ፣በተንኮል ላይ ፈፅሞ የማይተባበሩ ፣የሙስሊሙ ጭቆና እና ህመም እጅግ የሚያሳምማቸው፣ ልታይ ልታይ የማይሉ፣ከአንደበታቸው መጥፎ ቃል የማይወጣ ተወዳጅ ኢማምን በዚህ ወቅት ማጣት ልብ ይሰብራል::

ሼይኽ ሁሴን በዱንያ ላይ በነበሩበት ወቅት በዲናቸው ለነበራቸው አቋም ሁሉም የሚመስክርላቸው ኢማም ነበሩ!

አላህ ይዘንላቸው፣ ማረፊያቸውን በጀነተል ፊርዶስ ያድርግላቸው!

አላህ ሆይ እኛ እንደ ሰው የምናውቀውን መስክረናል አንተ ደግሞ ውስጥ አዋቂ ነህና ታላቅ ደረጃን በጀነት አጎናፅፋቸው!

አሚንን

Читать полностью…

ABU DAWD OSMAN

ጌታችን ሆይ በዚህ በተከበረው ወር ውስጥ ሆነን እንማፀንሃለን፤ በመላ ሃገራችን እየፈሰሰ ያለውን የንፁሃን ደም መቆሚያው ቅርብ ይሆን ዘንድ እርዳን! ማቆሚያ ወደሌለው እልቂት እንዳንገባም በራህመትህ ታደገን!

Читать полностью…

ABU DAWD OSMAN

የረመዳን ስጦታ ዳዕዋ ቲቪ!

ለኢትዮጵዬያ ሙስሊሞች ዲናዊ ጣብያዎች እየተበረከቱለት ይገኛሉ! አልሃምዱሊላህ

በታላቁ አሊማችን በዶ/ር ሼይኽ መሐመድ ሐሚዲን የተቋቋመው ዳዕዋ ቲቪም የሙከራ ቅርጭቱን ጀምሯል!

ይህን አስመልክቶም ሼይኽ መሐመድ ሐሚዲን ይህን መልዕክት አስተላፈዋል:-

"እነሆ ቃል በገባነው መሠረት፣ የሕዝባችንን የዒልም ጥማት ለመቁረጥ በማለም፣ ዳዕዋ ቲቪን ኢትዮ ሳት ላይ ይዘንላችሁ መጥተናል። በአሁኑ ወቅትም የሙከራ ሥርጭታችንን እያስተላለፍን ሲሆን፣ አላህ ከፈቀደ በቅርብ ጊዜ ውስጥ መደበኛ ሥርጭታችንን የምንጀምር ይሆናል። እስከዚያው መልዕክቱን ላልደረሳቸው በማዳረስ ከጎናችን እንድትሆኑ በአክብርዎት እጠይቃለሁ።

#ዳዕዋ_ቲቪ
«ጉዞ ስንቅን ይዞ!»

Читать полностью…

ABU DAWD OSMAN

በሳኡዲ አረቢያ የረመዳን ወር መግቢያ አዲስ ጨረቃ በዛሬው እለት ሰኞ በመታየቷ የታላቁ የረመዳን ወር ፆም በነገው እለት 1 ብሎ ይጀምራል!
ረመዳን ሙባረክ!
አላህ ወሩን ከሚጠቀሙበት ያድርገን

Читать полностью…

ABU DAWD OSMAN

ሳኡዲ አረቢያ በረመዳን ወር መስጂዶች የኢሻ እና የተራዊህ ሰላቶችን በ30 ደቂቃ ውስጥ እንዲያጠናቅቁ መመሪያ አውጥታለች!

በመካ እና በመዲናም የተራዊህ ሰላት 10ረከዓ ብቻ እንዲሰገድ ንጉሱ አዘዋል!

ውሳኔው ለምዕመናኑ የኮሮና ቫይረስ ተጋላጭነትን ለመቀነስ በማሰብ የተወሰደ እርምጃ መሆኑ ታውቋል!

Читать полностью…

ABU DAWD OSMAN

የቲውተር አጠቃቀም አጭር ማብራሪያ

በድጋሚ ተለጠፈ

ቲውተር መጠቀም ይፈልጋሉ?? እንግዲያውስ ይህን አጭር ማብራሪያ ያንብቡ

በአቡ ዳውድ ኡስማን በ2015 የተዘጋጀ አጭር ማብራሪያ

ቲውተር በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተጠቃሚ ያሉት የማህበራዊ ድህረገፅ አንዱ ነው፡፡በሃገራችን ኢትዬጲያ በርካታ ተጠቃሚዎች ባይኖሩትም በውጪው አለም ግን በሚሊዬን የሚቆጠር ተጠቃሚዎች አሉት፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሃገራችንም የቲውተርን ድህረገፅ ተጠቃሚዎች ቁጥር እየጨመረ ይገኛል፡፡

ህዝበ ሙስሊሙም ከፌስ ቡክ በተጨማሪ ቲውተር መጠቀሙ በርካታ ጥቀሞች የሚያስገኙለት በመሆኑ ሁሉም አጠቃቀሙን ይረዳው ዘንድ እንደሚከተለው በአጭሩ ማብራሪያ ተዘጋጅቶለት ቀርቧል፡፡

1. ቅድሚያ የቲውተር አድራሻ እንዲኖረን አካውንት መክፈት ያስፈልጋል፡፡

ይህንንም ለማድረግ

- ይህን ድህረገፅ www.twitter.com ይክፈቱ

-በመቀጠልም sign up የሚለውን በመጫን የሚጠይቀውን ሙሉ ስም፣ የኢሜል አድራሻ፣የይለፍ ቃል(password)፣ Username መሙላት

- የሚጠይቀውን መጠይቅ ሞልተን ማጠናቀቃችንን ካረጋገጥን ቡሃላ Agree to the Twitter Terms of Service የሚለውን መጫን

-በመጨረሻም Sign up for Twitter. የሚለውን በመጫን የቲውተር አካውንት በቀላሉ መክፈት ቻልን ማለት ነው፡፡

-አንዳንዴ ለማረጋገጥ በሚል የስልክ ቁጥር እንድናስገባ ሊጠይቀን ይችላል፡፡ ስልክ ቁጥራችን ያለበትን የሃገር ስም በመምረጥ ስልክ ቁጥራችንን እናስገባለን፡፡ በመቀጠልም የማረጋገጫ ኮድ በስልክ ቁጥራችን ይላክልናል፡፡ እሱን በቲውተር አከውንታችን ላይ በማስገባት የቲውተር አካውንት በቀላሉ መክፈት እንችላለን ማለት ነው፡፡

2. የቲውተር አካውንታችን ሙሉ መረጃዎችን እንዲይዝ መሙላት

ሌሎች የቲውተር ተጠቃሚ ሰዎች በቀላሉ ከኛ ጋር ለመገናኘት ያስችላቸው ዘንድ ልክ በፌስቡክ ፕሮፋይል እንደምንሞላው ሁሉ በቲውተር ላይም በመሙላት በቀላሉ ከሌሎች ጋር መገናኘት ያስችለናል፡፡

3. ከሌሎች ሰዎች፣ተቋሞች እና ሚዲያዎች ጋር ለመገናኘት የሚከተለውን ማድረግ

- የቲውተር አካውንት መጠቀም ስንጀምር የቲውተር ድህረገፅ የራሱን ጥቆማ ያደርግልናል፡፡ ይህንንም Suggestions. የሚለውን በመጫን የምንፈልገውን መርጠን follow ማድረግ እንችላለን፡፡

- በራሳችን ለመፈለግም Search. የሚለው ቦታ ላይ የምንፈልገውን ሰው፣ድርጅት ወይም ሚዲያ በመፃፍ ፍለጋ ማድረግ እንችላለን፡፡ የፈለግነውን ስናገኝም ምርጫችንን በመጫን follow ማድረግ እንችላለን፡፡

4. ቲውተር ላይ ፖስት ለማድረግ

-በቲውተር ላይ ፖስት ማድረግ የሚቻለው በ 140 ቃላቶች ብቻ የተዋቀረን መልዕክት ነው፡

-ሃሳባችንን ወይም መልዕክታችንን ባጭሩ በፌስቡክ ፖስት ለማድረግ የምንጠቀምበትን አይነት ሳጥን ጋር በመጻፍ Tweet የሚለውን በመጫን ፖስት ማድረግ እንችላለን

-በፌስቡክ ፖስት ስናደርግ ታግ እንደምናደረገው ሁሉ በቲውተር ላይም “@” የሚለውን ፊደል ከምንፈልገው የሰው ስም ወይም ተቋም ስያሜ ቀድመን በመፃፍ ታግ ማድረግ እንችላለን

-በቱውተር ላይም በፎቶ የተሰሩ ነገሮችን ፖስት ማድረግ የሚቻል ሲሆን ይህንንም ለማድረግ ፖስት እንድናደርግበት በተዘጋጀው ሳጥን ስር በግራ በኩል ADD PHOTO የሚል እናገኛለን፡፡ እሱን በመጫን ከምንፈልግበት ቦታ ፎቶውን በመምረጥ ማስገባት እንችላለን፡፡ ታግ ማድረግ ከፈለግንም ወይንም ከፎቶ በተጨማሪ ፖስት ከምናደርገው ፎቶ ጋር መልዕክት ማስገባት ከፈለግን ፖስት ለማድረግ በተዘጋጀው ሳጥን ላይ በመፃፍ አንድ ላይ TWEET የሚለውን በመጫን ፖስት ማድረግ እንችላለን

-በቀላሉ መልዕክቶች አንድ ቦታ እንዲሰባሰቡ ከተፈለገም ሃሽታግ መጠቀም እንችላለን፡፡ የምንፈልገውን መልዕክት ወይም ቃላት ፊት ይህን የመሰላል ምልክት (#) በማስገባት መልዕክቶቻችን በአለም ዙሪያ አንድ ቦታ ተሰባስበው እንዲቀመጡ ማድረግ ይቻላል፡፡

5. ቲውተርን ላይ የምናገኛቸው ቃላቶች እና አጠቃቀማቸው

- Follow፡ ይህ ማለት ልክ በፌስቡክ ፖስት የሚደረጉ ነገሮችን ለመከታተል አድ ፍሬንድ ለማድረግ የምንጠቀምበት ሲሆን follow የሚለውን በመጫን ብቻ የፈለግነውን ሰው ወይም ተቋም የሚለቃቸውን መረጃዎች እና መልዕክቶች በቀላሉ መከታተል ያስችለናል፡፡

- Following:- ይህ ማለት Follow እያደርግናቸው ያሉ ሰዎችን እና ተቋማትን የማናገኝበት ምርጫ ነው፡፡

- Followers:-ይህ ማለት እኛን Follow እያደረጉ የሚገኙ ሰዎችን ዝርዝር የምናገኝበት ምርጫ ነው፡፡

- Replies.፡- ይህን የምናገኘው አንድ ሰው ፖስት ወይም ቲውት ባደረገው ነገር
ላይ ሲሆን ምልክቱም ወደ ግራ የታጠፈ የቀስት ምልክት ነው፡፡ አገልግሎቱም ልክ በፌስቡክ ኮሜንት እንደምንለው ነው፡፡ አስተያየት ወይም ምላሽ ለመስጠት Replies. የሚለውን በመጫን ምላሽ ወይም አስተያየት መስጠን እንችላለን፡

- TWEET፡-ይህ በፌስቡክ ፖስት ለማድረግ ስንፈልግ Post የሚለውን ምርጫ እንደምንጫን ሁሉ በቲውትር ላይም ፖስት ለማድረግ ስንፈልግ TWEET የሚለውን በመጫን ይሆናል፡፡

- Retweets.፡- ይህንም የምናገኘው አንድ ሰው ፖስት ባደረገው ነገር ላይ ከስር በኩል መሃል ላይ ሲሆን ምልክቱም ሁለት ቀስቶች ወደላይ እና ወደታች ያሉበት ነው፡፡ አገልግሎቱም በፌስቡክ ሼር ለማድረግ እንደምንጠቀመው ነው፡፡ አንድ ሰው ፖስት ያደረገውን ሼር ለማድረግ ስንፈልግ Retweet የሚለውን በመጫን ሼር ማድረግ እንችላለን

- Favorites.፡ ይህንንም የምናገኘው አንድ ሰው ፖስት ባደረገው ነገር ላይ ከስር በቀኝ በኩል ሲሆን ምልክቱም የኮከብ ምልክት ነው፡፡ አገልግሎቱም በፌስቡክ ላይክ ለማድረግ እንደምንጠቀመው ነው፡፡ ፖስት የተደረገውን ነገር ላይክ ለማድረግ Favorit የሚለውን በመጫን ላይክ ማድረግ እንችላለን፡፡

- More:- በዚህ ስር ደግሞ ፖስት የተደረገውን ነገር በግል የቲውተር ሜሴጅ ለመላክ፣ በኢሜል ለመላክ እንዲሁም ፖስት ያደረገውን ሰው ብሎክ ለማድረግ የምንጠቀምባቸውን ምርጫዎች የያዘ ነው፡፡

- Messages.፡ ይህ ምርጫ በቲውተር Follow እያደረግነው ከምንገኘው ሰው ጋር በውስጥ በኩል መልዕክት ለመለዋወጥ የምንጠቀምበት ምርጫ ነው፡፡

6. የፌስቡክ አካውንታችንን እና የቲውተር አካውንታችን አንድ ጊዜ በጋራ እንዴት እንጠቀም

ይህን ለማድረግ በቀላሉ የፌስቡክ አካውንታችንን ከቲውተር አካውንታችን ጋር በማገናኘት በአንድ ፖስት ሁለቱም ጋር ፖስት ማድረግ ያስችለናል፡፡ ይህ ለማድረግ ሁለት ምርጫዎች ይኖሩናል

ሀ. በፌስቡክ ፖስት የምናደረገውን ነገር በቲውተራችንም ላይ ፖስት እንዲሆን ማድረግ፡፡

ይህን ለማድረግም የሚከተለውን Step ይከተሉ፡

-በቅድሚያ በፌስቡክ Setting የሚለው ውስጥ ይግቡ

-በመቀጠልም በSetting ውስጥ የተዘረዘሩት መካከል Followers የሚለውን ይጫኑ

-በመቀጠልም Followers የሚለውን ሲከፍቱ ከተዘረዘሩት ምርጫዎች መካከል አምስተኛውን "Link my Profile to Twitter. የሚለውን በመጫን የቲውተር አድራሻችንን በማስገባት በቀላሉ ከፌስቡክ አካውንታችን ጋር ማገናኘት እንችላለን፡፡

-ከላይ የተጠቀሰውን በቀላሉ ለማግኘት ይህን ሊንክ http://www.facebook.com/twitter በመጫን ማግኘት ይችላሉ

ለ. በቲውተር ፖስት የምናደረገው በፌስቡክ አካውንታችን ፖስት እንዲሆን ማድረግ፡፡

Читать полностью…

ABU DAWD OSMAN

በሳዑዲ አረቢያ የኮሮኖ ክትባት ሁለት ዙር ወስደው ለእረፍት ወደ ኢትዮጵያ የመጡ የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸው ነዋሪዎች ወደ ሳኡዲ እንዲመለሱ ለነሱ ብቻ የበረራ እገዳው መነሳቱን ሳዑዲ አስታውቃለች!

Читать полностью…

ABU DAWD OSMAN

📢 ለክረምት ኮርስ ፈላጊዎች በሙሉ

📍በባዮሽ መስጂድ የተለያዮ የዲን ትምህርቶችን
📚 የአቂዳ ፣ የፊቂህ እንዲሁም የንፅፅር ኮርሶችን ለመስጠት ተዘጋጅተዋል ።
✅ ትምህርቱን የሚሰጡት ኡስታዞች
ሸይኸ አብዱሰላም አንዋር ፣
በኡስታዝ ሳዲቅ መሓመድ ( አቡ ሓይደር) እና በኡስታዝ ኻሊድ መሀመድ ኑር

⏰ ትምህርቱ የሚሰጥባቸው ጊዜያቶች

ከሰኞ እስከ ሓሙስ ከጥዋቱ ከ4 እስከ 6 ሰዓት

☎️ የመመዝገቢያ አድራሻ :— በባዮሽ መስጂድ ቢሮ
ስልክ 0913667826
0979274717
0960280404

ምዝገባ ከነሓሴ 10 — ነሓሴ 15 ብቻ

Читать полностью…

ABU DAWD OSMAN

3ኛው ዙር የነሲሓ በጎ አድራጎት ኮልፌ ቀብርን እናስተካክል ዘመቻ!

የፊታችን እሁድ ነሐሴ 2 ከጠዋቱ 1:00 ላይ ነገ ብቻችንን የምንገባበትን ቀብር እናስተካክለ የኸይር ስራ ዘመቻ በአላህ ፍቃድ ይከናወናል።

በመሆኑም በተለያየ አካባቢ በመስጂድና መድረሳ እንዲሁም በግል በዚህ ኸይር ስራ እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል።

ኑ! ለነገ ለጨለማ ቤታችን የሚሆነንን ኸይር ስራ ተባብረን እንስራ!

ሼር በማድረግ ላልደረሳቸው እናድርስ!

ኸይር ስራ ከነሲሓችን ጋራ!

@NesihaCharityMain

Читать полностью…

ABU DAWD OSMAN

ወንድማችን ነጃ ዋበላ ሰኢድ ነገ አዲስ የባንክ አካውንት ይከፍታል

አቡ ዳውድ ኡስማን

የሚደረግለትን ድጋፍ ቋሚ ነገር ላይ ለማዋል ይረዳው ዘንድ የግሉን የባንክ አካውንት በመተው በራሱ፣ በወንድም ፉዓድ ሁሴን ( Fuad Hussein ) እና ቪዲዮውን በቀረፀው ወንድም ሁሴን አረቦ ስም አካውንት ለመክፈት ተስማምቷል::

ነገ አካውንቱን ከፍተው ያሳውቁናል::

የወንድማችን ነጃ ዋበላ የትላንት ለቅሶው ዛሬ በተስፋ እና በፈገግታ ተቀይሯል!

እሱን ለመርዳት ከ600ሺህ ብር በላይ የነየታችሁ ወንድም እና እህቶች አካውንቱ ሲከፈት ገቢ ማድረግ አትዘንጉ!

ድጋፍ ማድረግ የምትፈልጉም ከነገ ጀምሮ በአላህ ፈቃድ በሚከፍተው የባንክ አካውንት ድጋፍ ማድርግ ትችላላችሁ

"በእርግጥም ከችግር ቡሃላ ምቾት አለ"

አልሐምዱሊላህ

Читать полностью…

ABU DAWD OSMAN

አልሐምዱሊሏህ!!

የዚህ ወንድማችንን አድራሻ ተገኝቷል:: በአካል ወንድሞች አግኝተውት የባንክ አካውንቱን ተቀብለው ይፋ እስኪያደርጉ ድረስ እንጠብቃቸው::

ከትላንት ማታ ጀምሮ ይህን ወንድማችንን ለመርዳት ገንዘብ የነየታችሁ እና አሁንም መርዳት የምትፈልጉ የባንክ አካውንቱ እስኪገለፅ በሰብር ጠብቁ!

ይህን ሚስኪን ወንድማችን በስሙ የተማፀናቸው ጌታችን አሏህ ፈፅሞ አይተወውም! አሰቃይተውት ንብረቱን እንደወረሱበት ለነሱም የሚተርፍ ባለፀጋ አሏህ ያደርገዋል ኢንሻ አሏህ

۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩
በቴሌ ግራም መረጃዎች እንዲደርሳችሁ ካስፈለገ የሚከተለውን ሊንክ በመጫን ይቀላቀሉን
t.me/abudawd

መረጃዎችን እና መልዕክቶችን በቀላሉ ወደኔ ለመላክ ካስፈለጋችሁ በዚህ የቴሌግራም አድራሻዬ በቀጥታ ልታደርሱኝ ትችላላችሁ.

/channel/abudawdosmann

በፌስቡክ ለመከታተል ገፁን ላይክ ያድርጉ
click and like ➤➤ @ https://www.facebook.com

Читать полностью…

ABU DAWD OSMAN

ኩኑዝ... የማንነት እነፃ

በተለያዩ መስጂዶች የተዘጋጀ ልዩ የሙሓደራ ፕሮግራም

እሁድ ረመዳን 20 | ሚያዝያ 24/2013

✔ ነጃሺ መስጅድ / ቢሾፍቱ
▶ ወንድማማችነት በተውሒድ
ኡስታዝ መሀመድ አረብ

▶ ጀነትና ፀጋዎቿ
ኡስታዝ ቶፊቅ ራህመቶ


✔ ሰላም መስጅድ / ቱሉ ዲምቱ
▶ ሱና እና ወጣትነት
ኡስታዝ ጂብሪል አክመል

✔ ኢማም አህመድ መስጂድ/ አለምባንክ
▶ ሁለቱ የጀነት በሮች
ኡስታዝ ሱልጣን ኸድር

▶ በአላህ ብቻ መመካት (ተወኩል)
ኡስታዝ ጀማል ያሲን

✔ ረህማ መስጅድ/ ቻይና ካምፕ
▶ የዱኣ አደቦች
ዶ/ር አብዱ ኸይሬ

▶ በቁርአን ህያው እንሁን!
ኡስታዝ አብዱረህማን ከማል

✔ አሊ መስጅድ / ስልጤ ሰፈር
▶ አላህን የመታዘዝ አርአያ
ኡስታዝ መሀመድ ሀሰን ማሜ

▶ ወጣቶችን ለመታደግ
ኡስታዝ ዳውድ ያሲን

✔ ሸህ ደሊል መስጂድ
▶ ከረመዳን በኋላስ?
ኡስታዝ መሀመድ ኸድር

▶ ተውሂድ የስኬት ጎዳና
ኢብራሂም ሙሳ

✔ ፈትህ መስጅድ / ንፋስ ስልክ 54
▶ የመስጅድ ታላቅነት
ኢንጂነር ከማል ኸድር

▶ የካዕብ ኢብኑ ማሊክ የተውበት ጉዞ
ኡስታዝ አብዱሰላም አህመድ

✔ ቢላል መስጂድ (ኮካ)
▶ የዲን ምሰሶ
ኡስታዝ አብዱረዛቅ ፈረጃ

▶ ከዋሻው ሰዎች ታሪክ ምን እንማራለን
ኡስታዝ ኸድር አብደላህ

Http://www.facebook.com/merkezuna

Читать полностью…

ABU DAWD OSMAN

የቱን ያክል ከባድ ወንጀል ብትሰራ ወደ አላህ ከመመለስ አታመንታ! በወንጀል ላይ ሆነህ የደበቀህ ጌታ በተውበት ላይ ሆነህ አያዋርድህም!

Читать полностью…

ABU DAWD OSMAN

የኦሮሚያ ክልል መጅሊስ ታላቅ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ማዘጋጀቱን አስታወቀ

ታላላቅ ፕሮጀክቶችን ነድፎ እየተንቀሳቀሰ ነው

የኦሮሚያ መጅለስ የዛሬ ሁለት አመት አከባቢ ተሃድሶ ከተደረገለት ጊዜ ጀምሮ አያሌ ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል። ወደፊት የሚሰሩ ብዙ ስራዎችም አሉ። እነዚህ ስራዎች ወደኋላ እንዲጓተቱ ምክንያት የሆኔ ትልቁ ማነቆ የፋይናንስ/የበጀት እጥረት ነው። ይህን ችግር ለመቅረፍ የኦሮሚያ መጅሊስ የገቢ ማሰባሰቢያ ዘመቻ ፕሮግራም አዘጋጀ።

የፕሮግራሙ ዋና ዓላማ
1- የመጅሊስ ማዕከል ለመስሪያ ቤትነት የሚያገለግሉ ክፍሎች፣ የገቢ ምንጭ፣ እና የመሰብሰቢያ
አደራሽ ያለዉ በድዛይኑ ላይ የሚታየውን ህንጻ መገንባት።

2- የሙስሊሙን ህብረተሰብ አደረጃጀት እስከታች አውርደው ስራ ላይ ማዋል። በዚህ አመት ሶስት ሚሊዮን ሙስሊምን የኦሮሚያ መጅሊስ አባል ለማድረግ አቅደን በቂ መታውቂያ አዘጋጅተናል።

3- በየእርከኑ ያሉትን መዋቅሮችንና የተለያዩ ኮሚቴዎችን፣ ለምሳሌ የእማሞችና የዳዕዋ ኮሚቴ፣ የምሁራን ኮሚቴ፣ የወጣቶች፣ የፈትዋ ኮሚቴ እና የሴቶች ዶክቶሬትን በተለዬ መልኩ ወደ ስራ ማስገባት
4- በየእርከኑ ባለዉ መዋቅር በቂ የሆኔ የሰዉ ሃይል ማደራጀትን አንግበን ተነስቴናል።

መርኃ ግብሩ እንደሚከተለው ይሆናል
******************
የመጅሊሱን ማነቆዎች ለመቅረፍና ስራዎችን በተፈለገ አቅጣጫ ለማስኬድ የምክር ቤቱ
ቁልፍ ችግር የሆነዉን የፋይናንስ/የበጀት ችግር ላይ ርብርቦሽ አድርጎ አስቀድሞ መፍታት ተገቢ
እና አማራጭ የሌለዉ ስራ በመሆኑ ጁምዓ ረመዳን 18/1442ሂ ወይም ሚዚያ 22/2013 የገቢ ማሰባሰብያ ዘመቻ በሚከተለው መርኃግብር እንዲደረግ ም/ቤቱ አፅድቋል።

በመላዉ የሃገራችን መሳጅዶች የ”ኦሮሚያ መጅሊስ ድጋፍ ማሰባሰቢያ ሳምንት ፕሮግራም”ን ማከናወን፤
1- በኦሮሚያ ክልልና በመላው አገርቷ ዉስጥ የሚገኙ መሳጂዶች በኢማሞችና በታዋቂ ዳዒዎች በመታገዝ ለኦሮሚያ መጅሊስ ገቢ እንዲያሰባስቡ ማድረግ።

2- በዲየስፖራ መሳጂዶች ዉስጥም ሆነ በሙስሊም ኮሚዩኒቲ በኩል ድጋፎችን የማሰባሰብ ሂደትን ማከናወን።

3- ሙስሊም ባለሃብቶች ነጋዴዎችና መላዉ ሙስሊም ማህበረሰብ በፕሮገራሙ ላይ ጉልህ ሚና እንዲጫወቱ ጥሪ እናቀርባለን።

4- በመስጅድ ከሚደረግ አስተዋፅኦ ጎን ለጎን ለዚሁ ዓላማ በተከፈቱ የባንክ ሂሳብ ቁጥሮች ገቢ በማድረግ መጅሊሱ አንግቦ ለተነሳዉ ዓላማ ግብ መምታት የበኩሉዎን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ በአላህ ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡

የኦሮሚያ መጅሊስ የባንክ ህሳቦች
1. CBE (Commercial Bank of Ethiopia) 1000396921999
2. CBO (Cooperative Bank of Oromia) 1042200017968
3. OIB (Oromia International Bank) 4192080
4. AIB (Awash International Bank) 01410449821400
5. Nib Bank 7000023371249
6. Wegegen Bank 0878202815401
7. Buna Bank 2779691000002

Читать полностью…

ABU DAWD OSMAN

እሁድን በሼይኽ ሆጀሌ ሰፈር መስጂድ ያሳልፉ

ተወዳጁ ኡስታዝ አቡበክር አህመድ" ይህ ነው እስልምናህ" በሚል ጣፋፅ ዳዕዋ ያቀርባል

ሌሎች ፕሮግራሞችን ይኖራሉ

ከእርሰዎ ብቻ ከነቤተሰብዎ 3:30 ላይ ሼህ ሆጀሌ መስጂድ ይገኙ ።

Читать полностью…

ABU DAWD OSMAN

አብሽሪ እህቴ ይህም ያልፋልን!

አቡ ዳውድ ኡስማን

የራሳቸውን እና የቤተሰባቸውን ህይወት ለመቀየር ከቤተሰባቸው እና ከሃገራቸው ተሰደው በአረብ ሃገራት በስራ ላይ የሚገኙ እህቶቻችን በተለይ በዚህ ባለንበት የረመዳን ወር እጅግ ስራ የሚበዛባቸው እና የሚደክሙበት ወቅት ነው::
ሌላው ፆሙን በተለያዩ ኢባዳዎች ለማሳለፍ ሲጥር እህቶቻችን ግን በማድቤት ስራ ለኢፍጣር ምግብ ሲያዘጋጁ፣ከተፈጠረም ቡሃላ ሲያነሳሱ እና ሲያጣጥቡ አምሽተው ከዛም አልፎ ለሱሁር እየተነሱ ሌላውን ፆም ያሲዛሉ::

ይህን ሁሉ ልፋት በሃገር ቤት ላሉት ለቤተሰቦቻቸው ህይወት መቃናት በማሰብ ነው!

አብሽሪ እህቴ ይህም ያልፋል!

እህቶቻችንን የድካማቸውን እና የልፋታቸውን ውጤት የሚያገኙበት ፣ሃሳባቸው ተሳክቶ ለሃገራቸው የሚበቁበት ፣እየለፉ ያሉትን ልፋትም ኒያቸው አምሮ ታላቅ ምንዳ ከአላህ የሚያገኙበት ረመዳን ፆም አላህ ያድርግላቸው!

አሚን

Читать полностью…

ABU DAWD OSMAN

ነሲሓ ቲቪን ተባብረን እናሻግር!

የቴሌቭዥን ስርጭት በቋሚነት ከፍተኛ በጀት እንደሚፈልግ የታወቀ ነው። የነሲሓ ቲቪ አስተዳደርም ለዚህ የፋይናንስ ተግዳሮት ዘላቂ መፍትሄ በማሰብ ዳሩ-ተውሒድ የወቅፍ ፕሮጀክትን ቀርፆ ለተግባራዊነቱ በመስራት ላይ ይገኛል። አልሐምዱሊላህ ሂደቱም እጅግ አበረታች ነው። ፕሮጀክቱ በታለመለት መልኩ እውን ሲሆን በአላህ ፈቃድ የነሲሓ ቲቪ እና ተያያዥ የዳዕዋ ስራዎችን በቋሚነት ይደጉማል።

አንሷር ጀማዓ ከሌሎች ስብስቦች ጋር በመተባበር ዳሩ ተውሒድ እውን እስኪሆን ድረስ የነሲሓ ቲቪን ወርሐዊ ወጪዎች ለመሸፈን ተባብረው የሚሰሩ በጎ ፍቃደኞች ስብስብ ነው፡፡ የዚህ ልዩ ስብስብ አባል በመሆን ነሲሓ ቲቪን በቁርጠኝነት ይደጉሙ፡፡

🤝 አጋር ይሁኑ
http://nesiha.tv/ansuar/

☎ ለበለጠ መረጃ +251972757575

T.me/nesihatv

Читать полностью…

ABU DAWD OSMAN

ተንዚል247 ኦንላይን የቁርአን ት/ቤት
ከፈጅር ቡሃላ 12:30 ላይ ቁረአንን በጋራ አንቅራ በማለት ይጋብዞታል
Www.tanzil247.com በመግባት በነፃ መመዝገብ ይችላሉ!!!
0975327070
0911559605

Читать полностью…

ABU DAWD OSMAN

ለሶመን ሀበይ በወገሬት አጄጄሙ አጄጄና!!

Читать полностью…

ABU DAWD OSMAN

ረመዳን ሙባረክ!

የታላቁ የረመዳን ፆም ማክሰኞ 1 ብሎ እንደሚጀመር ተገለፀ!

አቡ ዳውድ ኡስማን

እንኳን ለታላቁ የረመዳን ወር በሰላም አደረሰን

በሳኡዲ አረቢያ ዛሬ እሁድ ሚያዝያ 3/2013/ አፕሪል 11/2021 የረመዳን ወር መግቢያ አዲስ ጨረቃ ሊታይ ባለመቻሉ ነገ ሰኞ ሚያዝያ 4 የሻዕባን 30 እንደሚሆን እና የረመዳን የመጀመሪያ ቀን ማክሰኞ ሚያዝያ 5 መሆኑ ታውቋል!

የሳኡዲ አረቢያ ጠቅላይ ሸሪኣ ፍርድ ቤት ዛሬ ምሽት እና ሰኞ ምሽትን የረመዳን ወር መግቢያ አዲስ ጨረቃ መውጣቱ እንዲጠባበቅ ህዝበ ሙስሊሙን አሳስቦ ነበር::

ነገ ሰኞ የሻዕባን የመጨረሻ 30ኛ ቀን እንደሆነ ተገልፆል፡፡

ረመዳን ሙባረክ!

አላህ ሃቁን ጠብቀው የሚፆሙት ያድርገን!

۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩
በቴሌ ግራም መረጃዎች እንዲደርሳችሁ ካስፈለገ የሚከተለውን ሊንክ በመጫን ይቀላቀሉን
t.me/ABUDAWD

መረጃዎችን እና መልዕክቶችን በቀላሉ ወደኔ ለመላክ ካስፈለጋችሁ በዚህ የቴሌግራም አድራሻዬ በቀጥታ ልታደርሱኝ ትችላላችሁ.

/channel/abudawdosmann

በፌስቡክ ለመከታተል ገፁን ላይክ ያድርጉ
Click and Like ➤➤ @ https://www.facebook.com

Читать полностью…
Subscribe to a channel