አስቸኳይ የድጋፍ ጥሪ
በሰጋጆች ድርቅ የተመታውን የዱራሜውን ቢላል መስጂድ ሁላችንም ለመታደግ እንረባረብ
አቡ ዳውድ ኡስማን
መዕክቱን አንብበው ሲጨርሱ ለሌሎችም ሼር ያድርጉት
በደቡብ ክልል በከምባታ ጠምባሮ ዞን በዱራሜ ከተማ በካሻ ቀበሌ አሮጌ ሰፈር የሚገኘው ቢላል መስጂድ አካባቢው የነበሩ ሙስሊሞች እንዲሁም የመስጂዱ ኢማም ሚስታቸው እና ልጃቸው ሳይቀር ከፍረው የመስጁዱ ሙዓዚን እና ኢማም የሆኑት ሼይኽ መሐመድ ኑር ብቻቸውን በመስጂዱ እየሰገዱ እንደሚገኙ መገለፁ ይታወሳል::
በዚህ ትልቅ መስጂድ ውስጥ ብቻቸውን አዛን እያወጡ ብቻቸውን ኢቃም ብለው እንደሚሰግዱ መገለፁን ተከትሎ ከፍተኛ ቁጭት እና ሀዘን በሁላችንም ላይ ተፈጥሯል::
መስጁዱ በእድሳት እጥረት በመጎዳቱ ዝናብም እያፈሰሰ እንደሚገኝ እንዲሁም ሌሎች እድሳቶችም እንደሚያስፈልገው ተገልፆ ነበር::
የአካባቢውን ሙስሊሙ ማህበረሰብ ወደ ዲናቸው እንዲመለሱ፣ ባዶ የሆነው መስጂድም በጀምዓ እንዲሞላ፣ የከፈሩትንም ለመመለስ ህዝበ ሙስሊሙ በአንድነት ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቦ ነበር::
ይህን አሳሳቢ ጉዳይ ቀድሞ መረጃው የደረሳቸው በደቡብ ክልል የአክፍሮት ሃይላትን የኩፍር ዘመቻ ለመመከት መሬት ላይ የወረዱ በርካታ ፕሬጀክቶችን፣ መስጂዶችን እና መድረሳዎችን እያሰሩ የሚገኙት ተወዳጁ ኡስታዛችን ኡስታዝ ሷዲቅ መሐመድ(አቡ ሐይደር) ይህንንም የዱራሜ መስጂድ ጉዳይ መፍትሄ እንዲያገኝ እየለፉ ይገኛሉ::
በዚህም መሰረት ይህን መስጂድ ለመታደግ እና የአክፍሮት ሃይላትን እንቅስቃሴ በመመከት የአካባቢውን ህዝበ ሙስሊም ወደ ዲኑ ለመመለስ ይቻል ዘንድ ሁሉም ህዝበ ሙስሊም ያቅሙን ያህል ድጋፍ የሚያደርግበት ሁኔታ ተመቻችቷል::
በኡስታዝ ሷዲቅ መሐመድ (አቡ ሃይደር ) አስተባባሪነት
በዱራሜ ከተማ በካሻ ቀበሌ አሮጌ ሰፈር የሚገኘው በዚሁ የቢላል መስጂድን ማዕከል የሚያደርግ እንቅስቃሴ ተጀምሯል::
በቀዳሚነት ለመስጂዱ ቋሚ ኡስታዝ መቅጠር እንዲሁም መስጂዱ በሚገኝበት በዱራሜ ከተማ በዱራሜ ዩኒቨርሲቲ ለሚገኙ የዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች በዚህ መስጁድ ላይ ታላቅ የዳዕዋ ኮንፍረንስ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል::
ይህ ኮንፍረንስ ከነሐሴ 13-15/2014 ለሶስት ቀናት ኢማሙ ብቻቸውን ሲሰግዱበት በነበረው ቢላል መስጂድ የሚሰጥ ይሆናል::
ይህ ታላቅ ኮንፍረስ ሙስሊም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ማዕከል በማድረግ በአካባቢው ያለውን የኩፍር ዘመቻ ለመመከት እና ሰዎች ወደ ዲናቸው እንዲመለሱ እንዲሁም የመስጁዱን ጀምዓ በማጠናከር ሰፊ ስራዎችን ለመስራት የሚያግዝ ነው::
አሁን ላይ የሁላችንንም ርብርብ እና ድጋፍ የሚሹ ወጪዎች ያሉ ሲሆን እነዚህም:-
1/ ቋሚ የኢማም ደሞዝ ክፍያ
2/ የመሰጂዱ አጥርን ማሳጠር
3/ መስጁዱ የጎደለውን ነገር ሁሉ ማሟላት እና
4/ ለታሰበው ታላቅ የዳዕዋ ኮንፍራንስ ወጪውን መሸፈን ይገኝበታል:
በአሁኑ ሰዓት ብቸኛ የነበሩትን ሼይኽ መሐመድኑርን የሚያግዝ በመስጁዱ በቋሚነት ሊያገልግል የሚችል ብቁ ኡስታዝ የተገኘ ሲሆን በዋናነት ኡስታዙም የመስጁዱ ኢማም በቋሚነት በመሆን እንዲያገለግል፣ ከዐሱር በኋላ ልጆችን እንዲያቀራ እንዲሁም ለካምፓሱ ተማሪዎች ኪታብ እንዲያቀራ ታስቧል::
እነዚህን አስቸኳይ ስራዎች በመስጂዱ ለመስራት በሀገር ውስጥም ሆነ ከሃገር ውጪ ያላችሁ የበኩላችሁም ድጋፍ ታደርጉ ዘንድ በአላህ ስም እንጠይቃለን::
በተከሰተው ነገር ከንፈር መምጠት እና ማዘን ብቻ ሳይሆን የመፍትሄ ሃሳብ ሲቀርብም ሁላችንም በቻልነው ያህል ማገዝ ይጠበቅብናል:: መፍትሄው በአንድነት መሬት ላይ ሊወርድ የሚችል ስራ መስራት ስንችል ብቻ ነው::
ለተዘረዘሩት ወጪዎች ድጋፍ ማድረግ ለምትፈልጉ ሁሉ በኡስታዝ ሷዲቅ መሐመድ ስም በተከፈተው አካውንት ድጋፍ ማድረግ ትችላላችሁ
1. COMMERCIAL BANK OF ETHIOPIA
1000317507589
SADIK MOHAMMED AHMED
2. ABYSSINIA BANK
83047178
SADIK MOHAMMED AHMED
3. ኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ
1011300008645
SADIK MOHAMMED AHMED
ለበለጠ መረጃ በዚህ ስልክ መደወል ትችላላችሁ
0911103231
ይህን መልዕክት ሁላችንም ሼር በማድረግ እናዳርስ!
የነገር የአረፋ ቀን የዙልሒጃ 9 ፆም እንዳያልፈን
ነብዩ ሙሀመድ ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ፐአረፋን ፆም አስመልክተው እንዲህ ብለዋል:-
የአረፋ ቀን ፆም ያለፈን የአንድ አመት ሀጥያት እና ወደፊት የሚመጣን የአንድ አመት ሀጥያት ያስምራል"ብለዋል
ይህ ቀን ነገ ጁምዓ ነው እንዳያልፈን
በሳኡዲ የመጅሊሱ አካውንት ተቀምጦ የነበረው የሶማሌ ክልል ሁጃጆጅ ገንዘብ
አቡ ዳውድ ኡስማን
ከ 3 አመት በፊት ሀጅ ሳይሄዱ የቀሩት 423የሶማሌ ክልል ሁጃጆች ገንዘብ በወቅቱ በባንክ በኩል ተልኮ 3.4 ሚሊዮን ሪያል በሳኡዲ የመጅሊሱ አካውንት ገቢ ተደርጎ ነበር!
ሁጃጆቹ መሄድ ሳይችሉ ሲቀር ገንዘባቸው ከሳኡዲ የሐጅ ሚኒስተር የመጅሊሱ አካውንት ወጪ ሆኖ እንዲመለስ ደብዳቤ እንዲፅፉ የተጠየቁት ሐጂ ኡመር ኢድሪስ ዘለቀ ተመላሽ እንዲሆን ደብዳቤ አልፅፍም አሻፈረኝ በማለታቸው ላለፉት ሶስት አመታት ገንዘባቸው በሳዑዲ የሐጅ ሚኒስተር የመጅሊሱ አካውንት ውስጥ በዝግ ሂሳብ ተቀምጦ ቆይቷል::
አሁን የሀጅ ዉቅት በመድረሱ አካውንቱ ወደ ተንቀሳቃሽ ሂሳብ በመዞሩ ገንዘባቸው ተበልቷል እያሉ ሲቀጥፉ የነበሩት ቀጣፊዎች አይናቸውን በጨው አጥበው ብራችሁ ቢበላም አሁን ከራሳችን አውጥተን የሱማሌ ክልል ሀጃጆች ሀጅ እንዲያደርጉ ወስነናል ብለው በራሳቸው ምላስ ያጡትን ገፅታ ህፃን ልጆችን እንኳን ማሳመን የማይችል አመክንዬ በማቅረብ ገፅታቸውን ለመገንባት ውድቅ ሙከራ ለማድረግ ሞክረዋል!
አስቡት የሰራተኛ ደሞዝ እንኳን መክፈል አቅቶት የነበረ ተቋም፣ ላስገነባው ህንፃ ከመቶ ሚሊዮን ብር በላይ እዳ ያለበት ተቋም፣ ከሚስኪኑ ህዝብ የአገልግሎት እያለ ከ8እስከ 12ሽህ ብር እየያስከፈለ ያለ ተቋም፣ በዘንድሮ አመት እንኳን ሀጅ መሄድ ሳይችሉ ቀርተው ገንዘባችንን መልሱልን እያሉ ቀን እና ማታ አፈር ላይ እየተኙ ሲንገላቱ ለከረሙ ሚስኪን አዛውንት እናት እና አባቶች የተቋሙን መስታወት በድንጋይ እየመቱ ኑው በማለት ለፖሊስ በሀሰት በመወንጀል ከግቢው አስደብድበው ለማባረር የሚጥሩ ክብር የማያውቁ ክብር ቢስ ሰዎች፣ ሶስት አመታት ሲያንገላታቸው ለነበሩ ሁጃጆች አዝኖ ከኪሱ አውጥቶ ሐጅ ሲያስደርግ አስቡት ?
የሱማሌ ክልል ሁጃጆች ገንዘባቸውበወቅቱ ከሳኡዲ እንዳይመለስ ማን እንዳደረገው ጠንቅቀው ያውቃሉ::/በክልሉ መንግስት በኩል ሳይቀር በኡለሞች እና በሽማግሌዎች በኩል ገንዘቡ ከሳኡዲ እንዲመለስ መጅሊሱ እንዲያደርግ ተጠይቋል:: አሻፈረኝ ተብሎ እስካሁን ቢቆይም::ይህን እውነታ የሶማሌ ክልል ኡለሞች በይፋ ለህዝባቸው አሳውቀዋል::
የሶማሌ ክልል ሁጃጆች የሰጡትን ምስክርነት በሀሩን ሚዲያ መመልከት ትችላላችሁ
https://youtu.be/vFvlVFZBNzo
አሁን ላይ የሶማሌ ክልል ሁጃጆች ሀጅ ከሄዱም ለሶስት አመታት ገንዘባቹ ተበልቷል እየተባሉ ሲዋሹት በነበረው በራሳቸው ገንዘብ ነው:: በዘንድሮ አመት ሐጅ መሄድ ያልቻሉ ካሉም ገንዘባቸውን የሚቀበሉት የማንም ቀጣፊ በግል ችሮታው የሚመልስላቸው ሳይሆን ሶስት አመታት በሳኡዲ በመጅሊሱ አካውንት ተቀምጦ ከነበረው የራሳቸው ገንዘብ ነው::
ሶስት አመታት ሙሉ ኦዲት አንደርግም እየተባለ ሲሸሽ የነበረው የሱማሌ ክልል ሀጃጆች ገንዘብ በቦርዱ ተበልቷል እያሉ ሲሰብኩ የነበሩት ቅጥፈት ስለሚጋለጥባቸው ነበር::
ዞሮ ዞሮ ሶስት አመት ሲቀጥፉ ቢሰነብቱም የሱማሌ ክልል ሁጃጆች ገንዘብ ተበልቷል እያሉ መቆየት በኦዲት የሚረጋገጥ መሆኑ አይቀሬ በመሆኑ አሁን ላይ ገንዘባቸው ከተቀመጠበት ወጥቶ አገልግሎት ላይ ውሏል::
የሚገርመው ግን ከ 40ሚሊዬን ብር በላይ የሀጃጆቹ ገንዘብ ተበልቷል እያሉ ሶስት አመታት ሙሉ እየሰበኩ ሲቆዩ ይህን ሁላ ሶስት አመት በኦዲት ገንዘቡ መበላቱን አረጋግጦ ለህዝብ ማሳወቅ እና በህግ እንዲጠየቁ አለማድረጋቸው እራሳቸውን በወንጀል የሚያስጠይቅ መሆኑን አለማወቃቸው/ነው::የህዝብ ገንዘብ ተዘርፎ ዘራፊውን በህግ ሳይጠይቁ ሶስት አመት ዝም ማለት ዘርፈዋል ከተባሉት ጋር እኩል የወንጀሉ ተባባሪነት መሆኑን ዘንግተውታል:: ሌባ ሲዘርፍ እያዩ ዝም ማለት በህግ ያስጠይቃል:: እነሱስ ገንዘቡ ሲዘረፍ የማንን ጎፈሬ ሲያበጥሩ ነበር መባላቸው አይቀርም::
እውነታው ግን ገንዘቡ ተበልቶ ሳይሆን በሳኡዲ የመጅሊሱ አካውንት በዝግ አካውንት እስካሁን ተቀምጦ ስለነበር እና አሁን ሲከፈት ገንዘቡን አውጥተው ለሁጃጆቹ አገልግሎት ላይ እንዲውል ማድረጋቸው ነው::
መጅሊሱ በህጋዊ የውጪ ኦዲተር ይመርመር እና እውነታው ይውጣ በተባለ ቁጥር መጅሊሱ ለሁለት ይከፈል እያሉ ሲሸሹ የነበሩት እነማን እንደሆኑ ሁሉም ያውቀዋል!
የኦዲት ሽሽት በዱኒያ ቢያመልጡት በአኼራ ግን ማምለጫ የለውም!
ነገም አላህ ውሸታሞችን እና ቀጣፊዎችን እንዲህ ያዋርዳቸዋል!
ያበደ ውሻን ይሩቁታል እንጂ አይታገሉትም
አቡ ዳውድ ኡስማን
የአማራ ክልል የእስልምና ጉዳዮች ፅ/ቤት የከተራ በኣልን ለማክበር በወጡ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ጥቃት ተፈፅሞበታል::
ይህን ነውረኛ ድርጊትን ሲፈፅሙም አስነዋሪ ስድብ እየተሳደቡ እንደነበር ተገልፆል::
ይህን አሳፋሪ ድርጊት የፈፀሙ ፅንፈኞች አላማቸው በውስጣቸው ያለውን የእስልምና ጥላቻ ለማንፀባረቅ ቢሆንም ቢሳካላቸው ይህን ትንኮሳ በመፈፀም ሰላማዊ የበዓሉን ታዳሚያን ከሙስሊሙ ማህበረሰብ ጋር ለማጋጨት ነበር::
ይህን ድርጊት በመፈፀማቸው በሃይማኖታቸው ምን አይነት መንፈሳዊ ጥቅም ያገኙበት ይሆን???
ጌታችን አላህ ለኛ ያላቸውን ጥላቻ ቀድሞ በቅዱስ ቃሉ ስለነገረን ድርጊታቸው አዲስ አይሆንብንም!
እቺ ሃገር በሙስሊሙ ታጋሽነት እና ቻይነት እስካሁን መዝለቅ ቻለች እንጂ እንደ አክራሪ ደብተራዎች ምኞት ቢሆን እርስ በእርስ በተላለቅን ነበር::
ዛሬም ትንኮሳቸው ግጭት መፍጠር ቢሆንም በአርቆ አስተዋዩ ህዝበ ሙስሊም በትዕግስት እና ንቆ በማለፍ ሴራቸውን እያከሸፈ የሃገሩን ሰላም እያስጠበቀ ይቀጥላል
የክልሉ የፀጥታ ሃይሎች ይህን ትንኮሳ የፈፀሙ ፅንፈኞችን ይዞ ለህግ ማቅረብ ግዴታው ነው:: እንደተለመደው ባልሰማ እና ባላየ ያልፉታል ወይስ ሃላፊነታቸውን ይወጣሉ የሚሉውን አብረን የምናይ ይሆናል!
የክልሉ ሙስሊሞች አብሽሩ:-
ውሻ ተናከሰ ተብሎ እሱን መልሶ ለመንከስ እንደማይሞከረው ሁሉ በጥላቻ በታወሩ ደብተራዎች ድርጊትም ብዙ አትሸበሩ:: ሁሌም በጥበብ እና በትዕግስት ትንኮሳዎችን እንደምታልፉት ሁሉ አሁንም በትዕግስት እለፉት:: ያበደ ውሻን ይሩቁታል እንጂ አይታገሉትም
ነሲሓ ቲቪን ለማስቀጠል የ1000ብር የድጋፍ ዘመቻ ይፋ ተደርጓል!አንድ ሺህ ብር ያለው ሁሉ ድጋፍ በማድረግ ዳዕዋውን በማስቀጠል የማይቋረጥ አጅር ያግኙ!
የንግድ ባንክ
1000145615929 ኢብኑ መስዑድ
ዳዕዋ ቲቪ
ለ3ቀን ኘሮፋይሎን #የደዕዋ ቲቪን ሎጎ በማድረግ ለሙስሊሙ ማህበረሰብ ተደራሽ ያድርጉ
የፊታችን ሰኞ መደበኛ ስርጭቱን ይጀምራል
በናይል ሳት ፍሪኪዌንሲ 12521
ሲቦል ሬት 47000
ፖላራይዜሽን ቨርቲካል
አርገው ይከታተሉን ።
#እንዲሁም በማህበራዊ መገናኛ ፦
በፌስቡክ 🔗https://www.facebook.com/daewatv/
ቴሌግራም 🔗
http://t.me/daewatv2013
ዩትዩብ 🔗
https://www.youtube.com/channel/UCrF8wiLRD4IIE1-5-73zdAg
||ደዕዋ ቲቪ /daewa tv ቢሉ ያገኙናል
#ደዕዋ ቲቪ
ጉዞ ስንቅን ይዞ!
የዳእዋ ቲቪን የማህበራዊ ሚዲያ አድራሻዎችንም ይከታተሉ
#ደዕዋ _ቲቪ ሰፊ ተደራሽነት ወዳለው ናይል ሳት ገባ
DAEWA TV
Satellite:- E8WB
Frequency :- 12521 MHz,
Symbol rate 27500
Polarization:- vertical
FEC :- 7/8
በማህበራዊ ሚድያዎች ይከታተሉን፡
በቴሌግራም | daewa tv
http://t.me/daewatv2013
በፌስቡክ | daewa tv
https://www.facebook.com/daewatv/
እንዲሁም በዩቲዩብ| daewa
https://www.youtube.com/channel/UCrF8wiLRD4IIE1-5-73zdAg
like.like .like.share...share...share
#ደዕዋ ቲቪ
ጉዞ ስንቅን ይዞ!
============
አባት ከአራት ሴት ልጆቹ ጋር በእሳት አደጋ ህይወታቸው አለፈ
የአላህ መልዕክተኛ(ሰዓወ) እውነት ተናገሩ!
አቡ ዳውድ ኡስማን
በቀራንዬ አካባቢ ባለፈው ጁምዓ መብራት ጠፍቶ በመቆየቱ በአንድ ቤተሰብ ውስጥ ለብርሃን በሚል መኖሪያ ቤታቸው ላይ የለኮሱት ሻማ ረስተውት በመተኛታቸው መኖሪያ ቤታቸው በእሳት ተቀጣጥሎ አባት ከአራት ህፃናት ልጆቹ ጋር በእሳት ቃጠሎ ህይወታቸው አልፏል:: እናታቸው እና የ8ወር ህፃን ልጃቸው ብቻ በህይወት ሊተርፉ ችለዋል:: ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን
የአላህ መልዕክተኛ(ሰዓወ) በሐዲሳቸው ላይ "ይህች እሳት ለእናንተ ጠላታችሁ ናትና በምትተኙ ስዓት አጥፏት" ብለዋል
የዚህን ሃዲስ ማስጠንቀቂያ በተግባር ተከስቶ ስመለከት ለእናንተም ላስታውሳችሁ ዉደድኩኝ
የአላህ መልዕክተኛ (ሰዓወ) እውነትን ተናገሩ!
አላህ ከዚህ አይነት ከባድ በላዕ ይጠብቀን
አልሐምዱሊላህ
ኡስታዝ ጀማል ያሲን ከእስር ተፈተዋል
አቡ ዳውድ ኡስማን
በግፍ እስር ላይ የነበሩት ኡስታዝ ጀማል ያሲን በአሁኑ ሰአት ከእስር ተፈተዋል::አልሐምዱሊላህ
ከእስር እንዲፈቱ ትልቁን ድርሻ በመውሰድ የኦሮሚያ መጅሊስ ጉዳያቸውን በቡራዩ መጅሊስ አማካኝነት አስፈላጊውን ክትትል በማድረግ ዛሬ የቡራዩ መጅሊስ ቦርድ ሰብሳቢ ወንድም ናስር አብደላህ ዋስትና በመውስድ ኡስታዝን አስፈትተዋል::
ኡስታዝ ጀማል በግፍ ከታሰሩበት ጊዜ ጀምሮ ኡስታዝ አቡበክር አህመድ ከሃገር ውጪ ሆነውም የሚመለከታቸውን አካላት በስልክ ሲያናግሩ፣ ኡስታዝ አህመዲን ጀበል እና ኡስታዝ ካሚል ሸምሱም በተመሳሳይ ለሚመለከታቸው አካላት ሲያናግሩ ቆይተዋል::
በአላህ እርዳታ እና ፈቃድ፣ በሙስሊሙ ዱዓ፣ በኦሮሚያ መጅሊስ ፣የቡራዩ መጅሊስ አመራሮች እና በኡስታዞች እንቅስቃሴ ኡስታዝ ጀማል ከእስር ተፈተዋል:: አልሃምዲሊላህ
ኡስታዝ ጀማል ያሲን በግፍ እስር እንዲለቀቁ ከፍተኛ ርብርብ ላፈረጋችሁ ሁሉ አላህ ኸይር ጀዛችሁን ይክፈላችሁ
ኡስታዝ ጀማል ያሲን አስቸኳይ ፍትህን ይሻሉ!
አቡ ዳውድ ኡስማን
ኡስታዝ ጀማል አሁንም በግፍ እስራት ላይ ናቸው:: ኡስታዝ ጀማል በመታሰራቸው በኢማምነት ሲያገለግሉበት በነበረው መስጂድ ለህዝበ ሙስሊሙ በቋሚነት ሲያቀሩት የነበሩት የተፍሲር እና ሌሎች የቂርዓት ፕሮግራሞች ተቋርጠዋል::
ኡስታዝ ጀማል በአሸዋ ሜዳ በወረዳ 2 ኖኖ ፖሊስ ጣብያ ነው ታስረው የሚገኙት::
የታሰሩበት እስር ቤት ከግቢው ጀምሮ ያለው ገፅታ ልብ የሚሰብር ነው:: በእስር ቤቱ በተለያዩ ወንጀሎች ተከሰው የታሰሩ በርካታ እስረኞች አሉ:: ኡስታዝ ጀማልን በውንብድና፣ በዝርፊያ እና በተለያዩ ፀያፍ ወንጀሎች ተይዘው ከታሰሩ እስረኞች ጋር አብረው እንዲታሰሩ መደረጉ እጅግ ያበሳጫል::
እስረኞቹ ኡስታዝ ጀማልን ለመዘየር የመጣን ሰው ገና ሲመለከቱ "ሼይኽ ጀማል ፣ሼይኽ ጀማል" እያሉ እየጮኹ ይጣራሉ:: ምንም እንኳን እሳቸውን ዝቅ ለማድረግ ከነዚህ እስረኞች ጋር እንዲታሰሩ ቢደረጉም ኡስታዝ ጀማል ግን በእስረኞች ዘንድ አላህ የሰጣቸው ሃይባ እንዲከበሩ አድርጓቸዋል::
ፊታቸው ላይ ያለው ኑር እና ፈገግታ እስር ላይ ሆነውም እጅግ ጨምሯል:: ምንም እንኳን እሳቸውን ለመዘየር ሲጠሩ በትንሽየዋ መስኮት አጮልቀው ብቻ እንዲዘየሩ ቢደረግም በፈገግታ የተሞላ ፊታቸው በታላቅ መረጋጋት እና ጥንካሬ ላይ እንዳሉ ያሳብቃል::
ኡስታዝ ጀማል ለምን እንደታሰሩም፣ ምን አጥፍተው ለእስር እንደተዳረጉም እስካሁን አልተገለፀላቸውም:: ፍርድ ቤትም አልቀረቡም:: ምርመራም አልተካሄደባቸውም:: ከቤተሰባቸውን ተነጥለው ለእስር ከተዳረጉ ሁለት ሳምንታት አልፏል::
የተጠረጠሩበት ወንጀል ካለም በግልፅ ተነግሯቸው ምርመራ ይካሄድባቸው:: ፍርድ ቤት ቀርበውም ጉዳያቸው በህግ ይታይላቸው:: ይህ ሳይሆን አንድን ንፁህ ሃገር ወዳድ የሃይማኖት መምህር በእስር እንዲማቅቁ ማድረግ ግን የግፍ ግፍ ነው::በግለሰብ የግል ቂም ጥቆማ ለእስር መዳረጋቸው እውነት ከሆነ ደግሞ እጅግ የከፋ በደል ይሆናል::
የሚመለከተው የመንግስት አካል እኚህን ተወዳጅ ኢማም እና ኡስታዝ ባስቸኳይ ፍትህን ሊያሰፍንላቸው ይገባል::
#በሁለት_መቶ_ብር_የወገን_እምባ_እናብስ
እዚሁ መንደር ላይ በደንብ አድርገን የምናውቃቸው ወንድሞቻችን የአራት ወር የቤት ኪራይ አለባቸው አከራዮቹ ለቃቹ ውጡልን ብለው የሶስት ቀን ጊዜ ሰቱዋቸዋል 😢 የቤቱን ዕቃ እስከመሸጥ ምናምን ነበር😭 ይከፍሉ የነበሩት የሰው ልጆች ነን እና ችግር ያጋጥመናል። ቤት ውስጥ ማናቸውም ስራ ላይ አይደሉም ጎዳና ላይ ሊወድቁብን ነው። እዚሁ መንደር ላይ ያለነው በደንብ አድርገን ነው የምናውቃቸው እናም ለአላህ ብለን እንድረስላቸው።
ለቤት ኪራይ የሚሆን መቶ ሰዎች እያንዳንዳችን 2መቶ ብር ብንለግስ 20ሺ ብር ሆነ ማለት ነው እነሱንም ከጭንቀት ገላገልናቸው ማለት ነው !
ወንድሞቻችንን በ200 ብር ከስጋት ነፃ እናድርጋቸው
ፋጡማ ሙሃመድ አወል
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ :- 1000100599647
አቢሲኒያ:- 35240136
ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን
የሃገራችን የኢልም ዋርካ የነበሩት ሼይኽ ሰዒድ ወደ አኼራ ሄዱ
በአዲስ አበባ የሱመያ መስጂድ ኢማም የነበሩት ታላቁ አሊም ሼይኽ ሰዒድ ወደ አኼራ ሄደዋል::
ሼይኽ ሰዒድ ሃቅን በመናገር እና በማስተማር ማንንም የማይፈሩ፣ በማንም ወገን ጥፋቶች እና በደሎች ሲፈፀሙ በግልፅ በአደባባይ ጥፋቱን በማውገዝ ትምህርት የሚሰጡ የነበሩ የሃገራችን የእውቀት ዋርካ ነበሩ::
ሙስሊሙ ማህበረሰብ በሃገሩ ትልቅ ቦታ እንዲኖረው የሚመኙ እና ለዛ አላማም ሁሌም ጠንክሮ እንዲሰራ ይለፉ የነበሩ አባት ነበሩ::
የሼይኽ ሰዒድ ማለፍ ለሃገራችን ሙስሊም ትልቅ ኪሳራ ነው:: የግለሰብ ሞት ሳይሆን የኡማ ሞት ነው::
የሳቸው አይነት የእውቀት ባለቤት፣ ቆራጥ እና የሃቅ ጠበቃ በሞት መነጠቅ መተኪያ የማይገኝለት ትልቅ ኪሳራ ነው::
በውስጣችን በመኖራቸው በሃገራችን የሚከሰቱ በላዎችን እና ፈተናዎችን አላህ እንዲያነሳልን አላህን እንዲማፀኑልን እና ምክር እንዲለግሱን የምንሻቸው የእውነት አባታችን ነበሩ::
በዚህ ከባድ ወቅት ሼይኽ ሰዒድን የመሰሉ የሃገር ዋርካ የሆኑ አሊምን በሞት ማጣት ድርብርብ ሙሲባ ነው::
ሁላችንም ወደ አላህ ልንመለስ፣ ፈተናውንም በቃችሁ እንዲለን አልቀሰን ዱዓ ልናደርግ ይገባል::
የሼይኽ ሰዒድ ስርኣት ቀብርም ዛሬ ጁምዓ የሚፈፀም በመሆኑ ሁላችንም በቀብራቸው ላይ በመገኘት ልንሸኛቸው ይገባል::
አባታችንን እና መካሪያችንን ሼይኽ ሰዒድን አላህ ይዘንላቸው
ማረፊያቸውንም በጀነተል ፊርዶስ ያድርግላቸው
ለቤተሰቦቻቸው እና ለመላው ሙስሊም ማህበረሰብም አላህ መፅናናቱን ይወፍቅ
እነዚህ ፖሊስ ተብዬዎች ለህግ ይቅረቡ!
ህግ ማስከበር ማለት ተጠርጣሪን መደብደብ አይደለም!
ሴትን ልጅ በአደባባይ በጠረባ እና በጥፊ እየመቱ የህግ አስከባሪ ናቸው ለማለት እንቸገራለን::
እቺን የልጆች እናት ልጇቿ ፊት ሁለት የፖሊስ ልብስ የለበሱ ህግ አስከባሪ ነን የሚሉ ፖሊሶች እየተቀባበሉ በጠረባ እና በጥፊ መሬት ላይ ጥለዋት እየተፈራረቁ ሲመቷት በቪዲዮ ላይ ተመልክተናል::
ባቅራቢያቸው ያሉ ሰዎች "ኧረ ሴት ልጅ እንዲህ አትመታም" እያሉ ቢማፀኑም እናትየውን ከመምታት አልተቆጠቡም::
የፈለገ ህግ ተላልፋ የተገኘች ተጠርጣሪ ብትሆን እራሱ ፖሊስ ሃላፊነቱ ወደ ህግ ቦታ እሷን ማቅረብ እና በህግ እንድትዳኝ ማድረግ እንጂ እንዲህ ሴትን ልጅ መቀጥቀጥ አይደለም::
ይህን ነውረ ቢስ ድርጊት የፈፀሙ ፣የፖሊስን ሃላፊነት ያልተገነዘቡ ነውረኛ ፖሊሶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ለህግ ሊያቀርባቸው ይገባል::
ይህን ህገ ወጥ ድርጊት የፈፀሙ ፖሊሶች ለህግ ይቀርቡ ዘንድ ሁላችንም ይህን ቪድዮ ሼር በማድረግ ለሚመለከታቸው የህግ አካላት እንዲደርስ የበኩላችንን እንወጣ!
ተመሳሳይ ሰብዓዊ ተግባር በተመሳሳይ ቦታ ተፈፅሞ እውቅናው ግን እምነት እየለዩ ብቻ የሚሰጥባት ሀገር
በሀገራችን ያለመድሎ በእኩልነት መልካም የሰሩ ሰዎችን እኩል የምናመሰግንበት፣ ያጠፉትንም እኩል የምንኮንንበት ሚዛን መቼ ይሆን የምናገኘው??
ሁሌም እምነት እና ብሄር እየለዩ ማሞገስ እና
እውቅና. መቸር የት ያደርሰን ይሆን??
በድሮ አስተሳሰብ ተቸንክሮ ለቀረ አካል መች ይሄ ይገባቸዋል?
©አቡ ዳውድ ኡስማን
በዛሬው የአረፋ ቀን በብዛት ማለት የሚወስድ ዚክር
لاَ إِلَـهَ إِلاَّ اللهُ وَحْدَهُ لاَ شَرِيْكَ لَهُ، لَهُ الْمُلْكُ وَلَهُ الْحَمْدُ، وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيْرٌ
‹ላኢላሀ ኢልለሏሁ ዋህደሁ ላሸሪከለህ፣ ለሁል ሙልኩ፣ ወለሁል ሐምድ ወሁወ ዐላ ኩልሊ ሸይኢን ቀዲር።
› «ከአላህ ውጭ በእዉነት የሚገዙት አምላክ የለም፡፡ አንድ ነው፡፡ አጋር የለውም፡፡ ንግሥና የርሱ ብቻ ነው፡፡ ምስጋናም ተገቢነቱ ለረርሱ ነው፡፡ እርሱ በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነው››
በሳኡዲ የመጅሊሱ አካውንት ተቀምጦ የነበረው የሶማሌ ክልል ሁጃጆጅ ገንዘብ
አቡ ዳውድ ኡስማን
ከ 3 አመት በፊት ሀጅ ሳይሄዱ የቀሩት 423የሶማሌ ክልል ሁጃጆች ገንዘብ በወቅቱ በባንክ በኩል ተልኮ 3.4 ሚሊዮን ሪያል በሳኡዲ የመጅሊሱ አካውንት ገቢ ተደርጎ ነበር!
ሁጃጆቹ መሄድ ሳይችሉ ሲቀር ገንዘባቸው ከሳኡዲ የሐጅ ሚኒስተር የመጅሊሱ አካውንት ወጪ ሆኖ እንዲመለስ ደብዳቤ እንዲፅፉ የተጠየቁት ሐጂ ኡመር ኢድሪስ ዘለቀ ተመላሽ እንዲሆን ደብዳቤ አልፅፍም አሻፈረኝ በማለታቸው ላለፉት ሶስት አመታት ገንዘባቸው በሳዑዲ የሐጅ ሚኒስተር የመጅሊሱ አካውንት ውስጥ በዝግ ሂሳብ ተቀምጦ ቆይቷል::
አሁን የሀጅ ዉቅት በመድረሱ አካውንቱ ወደ ተንቀሳቃሽ ሂሳብ በመዞሩ ገንዘባቸው ተበልቷል እያሉ ሲቀጥፉ የነበሩት ቀጣፊዎች አይናቸውን በጨው አጥበው ብራችሁ ቢበላም አሁን ከራሳችን አውጥተን የሱማሌ ክልል ሀጃጆች ሀጅ እንዲያደርጉ ወስነናል ብለው በራሳቸው ምላስ ያጡትን ገፅታ ህፃን ልጆችን እንኳን ማሳመን የማይችል አመክንዬ በማቅረብ ገፅታቸውን ለመገንባት ውድቅ ሙከራ ለማድረግ ሞክረዋል!
አስቡት የሰራተኛ ደሞዝ እንኳን መክፈል አቅቶት የነበረ ተቋም፣ ላስገነባው ህንፃ ከመቶ ሚሊዮን ብር በላይ እዳ ያለበት ተቋም፣ ከሚስኪኑ ህዝብ የአገልግሎት እያለ ከ8እስከ 12ሽህ ብር እየያስከፈለ ያለ ተቋም፣ በዘንድሮ አመት እንኳን ሀጅ መሄድ ሳይችሉ ቀርተው ገንዘባችንን መልሱልን እያሉ ቀን እና ማታ አፈር ላይ እየተኙ ሲንገላቱ ለከረሙ ሚስኪን አዛውንት እናት እና አባቶች የተቋሙን መስታወት በድንጋይ እየመቱ ኑው በማለት ለፖሊስ በሀሰት በመወንጀል ከግቢው አስደብድበው ለማባረር የሚጥሩ ክብር የማያውቁ ክብር ቢስ ሰዎች፣ ሶስት አመታት ሲያንገላታቸው ለነበሩ ሁጃጆች አዝኖ ከኪሱ አውጥቶ ሐጅ ሲያስደርግ አስቡት ?
የሱማሌ ክልል ሁጃጆች ገንዘባቸውበወቅቱ ከሳኡዲ እንዳይመለስ ማን እንዳደረገው ጠንቅቀው ያውቃሉ::/በክልሉ መንግስት በኩል ሳይቀር በኡለሞች እና በሽማግሌዎች በኩል ገንዘቡ ከሳኡዲ እንዲመለስ መጅሊሱ እንዲያደርግ ተጠይቋል:: አሻፈረኝ ተብሎ እስካሁን ቢቆይም::ይህን እውነታ የሶማሌ ክልል ኡለሞች በይፋ ለህዝባቸው አሳውቀዋል::
የሶማሌ ክልል ሁጃጆች የሰጡትን ምስክርነት በሀሩን ሚዲያ መመልከት ትችላላችሁ
https://youtu.be/vFvlVFZBNzo
አሁን ላይ የሶማሌ ክልል ሁጃጆች ሀጅ ከሄዱም ለሶስት አመታት ገንዘባቹ ተበልቷል እየተባሉ ሲዋሹት በነበረው በራሳቸው ገንዘብ ነው:: በዘንድሮ አመት ሐጅ መሄድ ያልቻሉ ካሉም ገንዘባቸውን የሚቀበሉት የማንም ቀጣፊ በግል ችሮታው የሚመልስላቸው ሳይሆን ሶስት አመታት በሳኡዲ በመጅሊሱ አካውንት ተቀምጦ ከነበረው የራሳቸው ገንዘብ ነው::
ሶስት አመታት ሙሉ ኦዲት አንደርግም እየተባለ ሲሸሽ የነበረው የሱማሌ ክልል ሀጃጆች ገንዘብ በቦርዱ ተበልቷል እያሉ ሲሰብኩ የነበሩት ቅጥፈት ስለሚጋለጥባቸው ነበር::
ዞሮ ዞሮ ሶስት አመት ሲቀጥፉ ቢሰነብቱም የሱማሌ ክልል ሁጃጆች ገንዘብ ተበልቷል እያሉ መቆየት በኦዲት የሚረጋገጥ መሆኑ አይቀሬ በመሆኑ አሁን ላይ ገንዘባቸው ከተቀመጠበት ወጥቶ አገልግሎት ላይ ውሏል::
የሚገርመው ግን ከ 40ሚሊዬን ብር በላይ የሀጃጆቹ ገንዘብ ተበልቷል እያሉ ሶስት አመታት ሙሉ እየሰበኩ ሲቆዩ ይህን ሁላ ሶስት አመት በኦዲት ገንዘቡ መበላቱን አረጋግጦ ለህዝብ ማሳወቅ እና በህግ እንዲጠየቁ አለማድረጋቸው እራሳቸውን በወንጀል የሚያስጠይቅ መሆኑን አለማወቃቸው/ነው::የህዝብ ገንዘብ ተዘርፎ ዘራፊውን በህግ ሳይጠይቁ ሶስት አመት ዝም ማለት ዘርፈዋል ከተባሉት ጋር እኩል የወንጀሉ ተባባሪነት መሆኑን ዘንግተውታል:: ሌባ ሲዘርፍ እያዩ ዝም ማለት በህግ ያስጠይቃል:: እነሱስ ገንዘቡ ሲዘረፍ የማንን ጎፈሬ ሲያበጥሩ ነበር መባላቸው አይቀርም::
እውነታው ግን ገንዘቡ ተበልቶ ሳይሆን በሳኡዲ የመጅሊሱ አካውንት በዝግ አካውንት እስካሁን ተቀምጦ ስለነበር እና አሁን ሲከፈት ገንዘቡን አውጥተው ለሁጃጆቹ አገልግሎት ላይ እንዲውል ማድረጋቸው ነው::
መጅሊሱ በህጋዊ የውጪ ኦዲተር ይመርመር እና እውነታው ይውጣ በተባለ ቁጥር መጅሊሱ ለሁለት ይከፈል እያሉ ሲሸሹ የነበሩት እነማን እንደሆኑ ሁሉም ያውቀዋል!
የኦዲት ሽሽት በዱኒያ ቢያመልጡት በአኼራ ግን ማምለጫ የለውም!
ነገም አላህ ውሸታሞችን እና ቀጣፊዎችን እንዲህ ያዋርዳቸዋል!
ሼይኽ ያህያ ኡስማን አል ሙደሪስ ወደ አኼራ ሄደዋል
አቡ ዳውድ ኡስማን
በመስጂደል ሀረም ለ70 አመታት ኢልም ሲያቀሩ ያሳለፉት ታላቅ አሊም እና ሙሀዲስ ሼይኽ ያህያ ኡስማን አል ሙደሪስ ወደ አኼራ ሄደዋል:: ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን
እኚህ አሊም ለ 70አመታት ሳያቋርጡ በሳምንት ሰባቱንም ቀን በቋሚነት በተከበረው መስጂደል ሃረም ኢልም ያቀሩ ነበር::
እውቅ ከሆኑ የሳቸው ተማሪዎች መካከል የመስጂደል ሀረም ኢማም የነበሩት ሼይሕ ኡመር ቢን ሙሐመድ ሱቤይል (ረሂመሁላህ) ተጠቃሽ ናቸው::
ምንኛ መታደል ነው በተከበረው ቤቱ ውስጥ ለ70 አመታት የአላህን እና የመልእክተኛውን ቃል እያስተማሩ ማሳለፍ?
ሞት በሁሉም ነፍስ ላይ የሚወድቅ ግዴታ ነውና እኚህ ታላቅ አሊምም የዱንያ ቆይታቸውን አጠናቀው ወደ አኼራ ሄደዋልል::
አላህ ይዘንላቸው፣ ማረፊያቸውንም በጀነተል ፊርዶስ ያድርግላቸው፣ መልካም ስራቸውን ሁሉ ይቀበላቸው
አሚንንን
ኢባዳችንን(መልካም ስራችንን) ለፌስብክ እይታ??
አቡ ዳውድ ኡስማን
መልካም ስራዎች በሙሉ በአላህ ዘንድ ተቀበቀይነት የሚያገኙት የተስተካከለ ኒያ ሲኖረው፣ለአላህ ተብሎ ጥርት ተደርጎ ሲሰራ (በኢኽላስ) እና የምንሰራው ኢባዳ በሱናው በተደነገገው መሰረት ከሆነ ብቻ ነው፡፡ ሰዎች እንዲያዩልን ብለን የምንሰራቸው መልካም ስራዎች ሁሉ በአላህ ዘንድ ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡
ሞኝነታችን በዝቶ የምንሰራቸውን መልካም ስራዎች ሰዎች አይተው እንዲያደንቁን ስንል ስራችንን ሰዎች እንዲያዩልን እንጥራለን፡፡ ሰዎች ሰላት ሲሰግዱ ሰው እያያቸው ከሆነ አሳምረው ይሰግዳሉ፡፡ ሰው ከሌለ ግን በሩጫ ሰግደው ይጨርሳሉ፡፡ የሚሰሩትን መልካም ስራ ሁሉ በአደባባይ እንዲታይላቸው ይፈልጋሉ፡፡
በአሁኑ ወቅት ደግሞ ሰዎች መልካም ስራቸውን ሰው እንዲያውቅላቸው ከሚያደርጉበት መንገዶች ፌስቡክ ቀዳሚውን ስፍራ ወስዷል፡፡ ሌሎች በኸይር ስራ ላይ እንዲበረታቱ ለማድረግ ተብሎ ለማነሳሳት ከሚተላለፉ መልዕክቶች ውጪ የግል መልካም ስራዎች ጎልተው እንዲወጡ ይደረጋሉ፡፡
ዛሬ እዚህ መስጂድ ገብቼ የመጀመሪያ ሰፍ ጀምዓ ሰገድኩኝ፣ዛሬ ሱና ፆም ፆምኩኝ፣ ሃጅ አደረኩኝ፣ኡመራ አደረኩኝ፣ሰደቃ ስሰጥ ዋልኩኝ፣ ዳዕዋ በየቦታው ሳደርግ ነበር፣እንዲህ አይነት ኢባዳ ስሰራ አደርኩኝ፣ ይህን ያህል ጁዝ ቁርዓን ዛሬ ቀራሁኝ፣ ለይል ስሰግድ አደርኩኝ ወዘተ … እየተባለ ፖስት ይደረጋል፡፡ ከዚህ ሲብስም ለምሳሌ ሰዎች ኡመራ ወይም ሃጅ እንዳደረጉ ሰው እንዲያወቅላቸው ወይም ለሰው ለማሳየት ጠዋፍ ሲያደርጉ ካዕባ ጋር ሆነው ፎቶ ተነስተው በፌስቡ ይለቃሉ፡፡አንዳንዱ ደግሞ አረፋ ተራራ ላይ ሆኖ እያለቀሰ አላህን እየለመነ ሌላኛው ጓደኛው ፎቶ እንዲያነሳው አድረጎ በፌስቡክ ላይ ይለቃል፡፡
ይህን ኢባዳ ፈፅመን ለሰዎች ለማሳየት መጣርም ጉረኝነትም ነው፡፡ ጉረኛ ሰውን ደግሞ አላህ አይወደውም፡፡
إِنَّ اللَّـهَ لَا يُحِبُّ مَن كَانَ مُخْتَالًا فَخُورًا
አላህ ኩራተኛ ጉረኛ የኾነን ሰው አይወድም፡፡(4:36)
ብዙ መልካም ስራዎች ተሰርተው በፌስቡክ እዩልኝ እና ስሙልኝ በሚል ፎቶዎች እና መልዕክቶችን በመልቀቅ የሰራነው መልካም ስራ አመድ ሆኖ እንዲቀር ይደረጋል፡፡
አላህ በቁርአኑ ለሰዎች ተብሎ ኢባዳን የሚያሳምሩትን፣እዩልኝ ይስሙልኝ ብለው የሚሰሩ ሰዎችን ወዮላቸው ሲል አስጠንቅቋል፡፡
فَوَيْلٌ لِّلْمُصَلِّينَ ﴿٤﴾ الَّذِينَ هُمْ عَن صَلَاتِهِمْ سَاهُونَ ﴿٥﴾ الَّذِينَ هُمْ يُرَاءُونَ ﴿٦﴾
ወዮላቸው ለሰጋጆች፡፡ለእነዚያ እነርሱ ከስግደታቸው ዘንጊዎች ለኾኑት፤ (ሰጋጆች)፡፡ለእነዚያ እነርሱ ይዩልኝ ባዮች ለኾኑት፡፡(107፡3-6)
ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ከሃሰተኛ ነብይ ይልቅ የምፈራላችሁ ድብቁን ሽርክ ነው ብለዋል፡፡ ድብቁ ሽርክ ምንድነው ተብለው ሲጠየቁ አንድ ሰው ሰላት ለመስገድ ይቆማል፡፡ ሌላ ሰው እየተመለከተው መሆኑ ሲያውቅ ሰላቱን እጅግ አሳምሮ ይፈፅማል ብለዋል፡፡(ኢማሙ አህመድ ዘግበውታል)
ለእዩልኝ እና ይስሙልኝ ብሎ መልካም ስራ መስራት ትንሹ ሽርክ ነው፡፡ ከሽርክ(በአላህ ላይ ከማጋራት) ተግባራት ትንሹ ይሁን እንጂ ከወንጀሎች ሁሉ ግን ትልቁ መሆኑን ኡለሞች ይናገራሉ፡፡
ለሰዎች እዩልኝ እና ይስሙልኝ ብለን መልካም ስራዎችን ከመስራት አላህ ይጠብቀን!!
አሚን!!
አሚን!!
۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩
ወቅታዊ መረጃዎችን እና ኢስላማዊ ትምህርቶችን ለማግኘት ይህን ገፅ ላይክ ያድርጉ
Click and Like ➤➤ @ https://www.facebook.com/abudawdosman
በቴሌግራም ለመከታተል ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ በመጫን መቀላቀል ይችላሉ
Click and Like ➤➤ @ /channel/abudawdosman
Gammachu gudda muslima hundaf !
Satellite:- E8WB
Frequency :- 12521 MHz,
Symbol rate 27500
Polarization:- vertical
FEC :- 7/8
በፌስቡክ 🔗https://www.facebook.com/daewatv/
ቴሌግራም 🔗
http://t.me/daewatv2013
ዩትዩብ 🔗
https://www.youtube.com/channel/UCrF8wiLRD4IIE1-5-73zdAg
||ደዕዋ ቲቪ /daewa tv ቢሉ ያገኙናል
#ደዕዋ ቲቪ
ጉዞ ስንቅን ይዞ!
የዳዕዋ ቲቪን የቴሌግራም ቻናል Join ያድርጉ
ሌሎችም Join ያደርጉት ዘንድ ሊንኩን ሼር በማድረግ ያግዙ
በቴሌግራም | daewa tv
http://t.me/daewatv2013
#ደዕዋ ቲቪ
ጉዞ ስንቅን ይዞ!የዳዕዋ ቲቪን የቴሌግራም ቻናል Join ያድርጉ
ሌሎችም Join ያደርጉት ዘንድ ሊንኩን ሼር በማድረግ ያግዙ
በቴሌግራም | daewa tv
http://t.me/daewatv2013
#ደዕዋ ቲቪ
ጉዞ ስንቅን ይዞ!የዳዕዋ ቲቪን የቴሌግራም ቻናል Join ያድርጉ
ሌሎችም Join ያደርጉት ዘንድ ሊንኩን ሼር በማድረግ ያግዙ
በቴሌግራም | daewa tv
http://t.me/daewatv2013
#ደዕዋ ቲቪ
ጉዞ ስንቅን ይዞ!የዳዕዋ ቲቪን የቴሌግራም ቻናል Join ያድርጉ
ሌሎችም Join ያደርጉት ዘንድ ሊንኩን ሼር በማድረግ ያግዙ
በቴሌግራም | daewa tv
http://t.me/daewatv2013
#ደዕዋ ቲቪ
ጉዞ ስንቅን ይዞ!
ኢና ሊላሂ ወዒና ኢለይሂ ራጂዑን
ሼይኽ መሐመድ ቢን ሷሊህ አል ሉሄይዳን ወደ አኼራ ሄዱ
አቡ ዳውድ ኡስማን
የሳኡዲ አረቢያ የታላላቅ ኡለሞች ምክር ቤት አባል የነበሩት ታላቁ የሃገርቱ አሊም ሼይኽ መሐመድ ቢን ሷሊህ አል ሉሄይዳን ወደ አኼራ ሄደዋል:: ሊላሂ ወዒና ኢለይሂ ራጂዑን
ትምህርቶቻቸው ለሃገራቸው ብቻ ሳይሆን ለመላው አለም ተደራሽ ሆኖ ብዙዎች ከሳቸው እውቀት ተጠቃሚ ይሆኑ ነበር::
በመስጂደል ሀረም ትምህርት ሲሰጡም ከፍተኛ ህዝብ ዙሪያቸው ተቀምጦ የሚሰጡትን ትምህርት ይከታተል ነበር::
ሼይኽ መሐመድ ቢን ሷሊህ አል ሉሄይዳን በሳዑዲ አረቢያ በቡኻይሪያ ከተማ ቃሲም በተባለ አካባቢ በ 1350 አመተ ሒጅሪያ ነበር የተወለዱት::
እኚህ ታላቅ የእድሜ ባለፀጋ እና የእውቀት ቀንዲል በ93 አመታቸው የዚህን ምድር ቆይታቸውን አጠናቀው ወደ ጌታቸው አልፈዋል!
ምድራችን ትልቅ አሊም በሞት ተነጥቃለች::
አላህ ይዘንላቸው! መልካም ስራቸውን ሁሉ ይቀበላቸው! ማረፊያቸውንም በጀነት ያድርግላቸው
መልዕክት ለኸጢቦች፣ ለዳዒዎች እና ለዐሊሞች!
እንደሚታወቀው እየኖርን ያለነው ብልሹነት በተንሰራፋበት፤ ፈተናና መሀይምነት በበዛበት፤ ሙስሊሞች መካከለኛና ሚዛናዊ በሆነው የእምነታቸው አስተምህሮ ላይ ጥርጣሬ እንዲያድርባቸው በከፍተኛ ሁኔታ በተዘመተበት ዘመን ላይ ነው፡፡
በተለይ ደግሞ ሙስሊም ሴቶች ላይ ያነጣጠሩ ውዝንብሮችና ጥቃቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ በአደገኛ ሁኔታ እንደ አሸን እየፈሉ እንደ ሰደድ እሳት እየተስፋፉ ይገኛል፤ በመሆኑም ሙስሊሙን ማሕበረሰብን በጠራ ኢስላማዊ ማንነት የማነፅ ሥራ በፅናት መሠራት ያለበት ወሳኝ ጊዜ ላይ ነው የምንገኘው! "ጊዜው አሁን ነው!" ሁላችንም ለዚህ ታላቅ ኃላፊነት በቻልነው አቅም ራሳችንን አዘጋጅተን "አለሁ" ልንል ይገባል። በአቅማችን ልክ ማበርከት ያለብንን ልናበረክት ይገባል።
በዋናነት ደግሞ ሴት እህቶቻችንን የማህበረሰቡ ምሰሶና ከፍተኛ ኃላፊነት የተጣለባቸውን እንደመሆናቸው መጠን በኢስላማዊ ማንነት እንዲታነፁ፣ ዲናቸውን እንዲያውቁ፣ የትክክለኛ ሙስሊም ሴት ስብዕና እንዲረዱ፤ የመልዕክተኛውን ﷺ ፈለግ አውቀው በሕይወታቸው ላይ ተግባራዊ እንዲያደርጉ ማገዝ ያስፈልጋል፡፡ ኢስላምን ከዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያቸው ጋ የተቆራኘ ሆኖ የሕይወት መንገዳቸው አድርገው እንዲጓዙ ማድረግ ያስፈልጋል።
ከጊዜ ወደ ጊዜ ለሴቶች ጠቃሚ ማስታወሻዎችን እንዲሁም ሙስሊም ሴት ልትላበሰው ስለሚገባ ስብዕና የሚያስታውሱ ተግሳፆች እና ስለ አለባበስ ስርዓቷ ሒጃብ የሚያስተምሩ ዱዓቶችና ዳዕዋዎች በማነሳቸውና በመመናመናቸው የተነሳ ብዙሃኑ ሴቶች ዘንድ የኢማን ድክመትና ውድቀት ፣ የሐያእ (ሀፍረት) እጦትና ከዲን መራቅ እንዲስፋፋ፣ ሒጃብ በአግባቡ ያለበሱት ይቅርና ቀደም ባሉ ጊዜያት መስፈርቱን አሟልተው ይለብሱ የነበሩ እህቶች እንኳ ሳይቀር ከአቋማቸው እየተንሸራተቱና አውልቀው እስከመጣል የደረሱበት አደገኛ ሁኔታ እንዲፈጠር አድርጓል፤ በተጨማሪም ከሙስሊም እህቶች ጋ የተያያዙ ዘርፈ ብዙ ጉድለቶች በስፋት እንዲፈጠሩና በተለያየ መንገድ የሸሪዓ ትዕዛዛት መጣስና መተላለፍ እንዲከሰት ይህም በጠራራ ፀሐይ በአደባባይ ግልጽ ወጥቶ እንዲታይ አድርጓል::
የሒጃብ ጉዳይ ሁሉንም የማሕበረሰብ የሚመለከት ጉዳይ በመሆኑ ሁሉ በቻለው አቅም ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል፤ አባት ልጁን፤ ወንድም እህቱን፤ ባል ሚስቱን በሒጃብ ላይ አደራ ሊል ይገባል፤ ሴቶች ለሴቶችም ሊመካከሩ ግድ ይላል።
በዋናት ደግሞ ማሕበረሰቡን በኢስላማዊ ማንነት የማነጽ ኃላፊነት የተጣለባችሁ በምድር ላይ እጅግ የተከበረውን የሥራ ዘርፍ የያዛችሁ ዐሊሞች፣ ኸጢቦች፣ ዳዒዎችና በጥቅሉ የዲን አስተማሪዎች ለዚህ ጉዳይ ተገቢውን ትኩረት ሰጥታችሁ ስለ ሒጃብ በሰፊው ትምህርት ልትሰጡ፣ ማሕበረሰቡን ልታስታውሱና ልትገስጹ የሚገባበት ወሳኝ ሰዓት ላይ በመሆናችን አላህ የጣለባችሁን ግዳጅ እንድትወጡ ታናሾቻችሁ! ተማሪዎቻችሁ! ከአክብሮት ጋ ለማስታወስ እንወዳለን!
በመሆኑም የፊታችን ጁሙዓ በሳምንታዊ ዒዳችን ስለ ሙስሊም ሴት ሒጃብና አብረው ሊላበሱት ስለሚገባው ስብዕና የሚዳስሱ ኹጥባዎችን በማድረግ ዒዳችንን እንድታደምቁልን በአክብሮት እንጠይቃለን!
﴿ وَتَعَاوَنُوا عَلَى الْبِرِّ وَالتَّقْوَى ٢﴾ [المائدة: 2]
“በበጎ ነገርና አላህን በመፍራትም ተረዳዱ፡፡” (5:2)
“ሴትን ካዘጋጀህ ታላቅ ማህበረሰብ አዘጋጀህ!”
//// ሼር እና ሜንሽን በማድረግ እንዲሁን ኮሜንት በመስጠት /////
መልዕክቱ ብዙዎች ዘንድ እንዲደርስ ኃላፊነቶን ይወጡ! አናውቅም በመልካም ሥራ መዝገባችን ላይ ተጽፎ ጀነት መግቢያ ሰበብ ሊሆነን ይችላል!
©Haider Khedir
#ዝምታው_ይብቃ
#ከተኛንበት_እንንቃ
#ኹጥባን_ለሂጃብ
#ትኩረት_ለሂጃብ
እውን የረሱል(صلى الله عليه وسلم) ሱናቸውን መከተል እያፈርን እንወዳቸዋለን ማለት ያስችለን ይሆን?
ፊዳከ አቢ ወኡሚ ያ ሃቢበላህ
አቡ ዳውድ ኡስማን
ይህን አጭር ልብ የሚነካ ሙሃደራ በማድመጥ እራሳችንን እንፈትሽ
ቪዲዬን መመልከት ላልቻላችሁ መልዕክቱ እንደሚከተለው በፅሁፍ ቀርቧል
"ነብዩ፤ (صلى الله عليه وسلم) ላንተ ሲሉ አልቅሰዋል፣ ላንተ ሲሉ ተደብድበዋል፣ ላንተ ሲሉ ተባረዋል፣ ላንተ ሲሉ ጥቃት ደርሶባቸዋል፣ ላንተ ሲሉ የልጆቻቸው ትዳር ፈርሷል።
አንተ ግን፤―
ሱናቸውን ለመከተል ታፍራለህ! አንዲት ሱና በግልፅ መተግበር ያሳፍርሃል፣ ሰዎች ምን እየሰራህ ነው እንዳይሉህ ታፍራለህ፣ ፂማችንን ለማሳደግ እናፍራለን፣ ልብሳችንን ለማሳጠር፣ እንደሳቸው ለመናገር፣እንደሳቸው ለመሄድ፣ ንግግራቸውን ለመሃፈዝ፣በካፊሮች ፊት ማንነታቸውን ለመግለፅ እና ለማሞገስ እናፍራለን፣ጥሪ ያደርጉ እንደነበረው በይፋ መጣራት እናፍራለን፣አላህን በይፋ ያወሱ እንደነበረው ማውሳት እናፍራለን፣ሰዎች ፈለጋቸውን እንዲከተሉ መምከር እናፍራለን፣ እኛ በነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ሱና እናፍራለን፡፡
እሳቸው ግን ላንተ ብለው በተደጋጋሚ ሊገደሉ ነበር፣ በመሰረቱም ከዱኒያ የተሰናበቱት በመረዝ ተገድለው ነው፣ይህ ሁሉ ላንተ ሲሉ ላንቺ ሲሉ ነው፡፡
ከዱኒያ ሊሰናበቱ ሲሉ አለቀሱ፡፡ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ ለምን ያለቅሳሉ ሲሉ ተጠየቁ እሳቸውም "ወንድሞቼ ባየዋቸው ኖሮ......" አሉ::
አንተን ማየት ይመኙ ነበር፡ ነገር ግን እኛ ግን ሱናቸውን እግራችን ውስጥ ወርውረን፣ በግልፅ ሱናቸውን መተግበር እያፈርን፣ በግልፅ ማሞገስ እያፈርን፣ የምናጌጠው እና የምንዋበው በካፊሮች ሱና ሆኖ ቢያዩን እንዴት ያሳፍራል?????? የነሱን ሱና በልባችን የተሟላ አድርገን አሰብነው፣ በእኛ እይታችንም ከምርጡ ከነብዩ(ሰ.ዐ፣ወ) የተሻለ ሱና ሆነ !!
የተከበራችሁ ወንድሞቼ ለምሳሌ ስለ ፂም ስንናገር አንዳንድ ሰዎች ያ ሼህ ይህ እኮ ሱና ነው ይላሉ፡፡ እኔም እኮ እንዳንተው ሱና ነው እያልኩኝ ነው .....
ለምን አንዳንድ ወጣቶች ልብሳቸው ላይ በአላህ ቤት ውስጥ ስሙን ልጠራው የማልፈልገው ሰው ፎቶ ይለጥፋሉ????? ለምን የዚህን ጸጉራም ባለኮፍያ ሰው ፎቶ ትለጥፋለህ ስትለው ይህማ የነፃነት ተምሳሌት ነበር ይልሃል እውን ይህ የነፃነት ተምሳሌት ነበር????? እውነታው ግን የዝሙት እና የመጠጥ ተምሳሌት ነበር ፡፡ ይህ ሰው ኩራታችሁ ነው፡፡ ለምን ታዲያ ነብዩ(ሰ.ዐ፣ወ) ሱና አትኮራም ???? ለምን ፂምህን አታሳድግም????"ይህ ፂም ምንድነው ከተባልክ"፣ ይህማ የነፃነት እና የክብር ተምሳሌት የመሃመድ ኢብኑ አብዱላህ መገለጫ ነው ለምን አትልም????
***********//*********************
ሱናን መከተል እንደሚገባን በቁርአን ላይ ከተቀመጡ የተወሰኑትን አንቀፆች እንመልከት
ن يُطِعِ الرَّسُولَ فَقَدْ أَطَاعَ اللَّـهَ ۖ وَمَن تَوَلَّىٰ فَمَا أَرْسَلْنَاكَ عَلَيْهِمْ حَفِيظًا
﴿
መልክተኛውን የሚታዘዝ ሰው በእርግጥ አላህን ታዘዘ፡፡ ከትእዛዝም የሸሸ ሰው (አያሳስብህ)፡፡ በእነሱ ላይ ጠባቂ አድርገን አልላክንህምና፡፡(4፡80)
لَّا تَجْعَلُوا دُعَاءَ الرَّسُولِ بَيْنَكُمْ كَدُعَاءِ بَعْضِكُم بَعْضًا ۚ قَدْ يَعْلَمُ اللَّـهُ الَّذِينَ يَتَسَلَّلُونَ مِنكُمْ لِوَاذًا ۚ فَلْيَحْذَرِ الَّذِينَ يُخَالِفُونَ عَنْ أَمْرِهِ أَن تُصِيبَهُمْ فِتْنَةٌ أَوْ يُصِيبَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ ﴿٦٣
በመካከላችሁ የመልክተኛውን ጥሪ ከፊላችሁ ከፊሉን እንደ መጥራት አታድርጉት፡፡ ከእናንተ ውስጥ እነዚያን እየተከለሉ በመስለክለክ የሚወጡትን አላህ በእርግጥ ያውቃቸዋል፡፡ እነዚያም ትዕዛዙን የሚጥሱ መከራ እንዳትደርስባቸው ወይም አሳማሚ ቅጣት እንዳያገኛቸው ይጠንቀቁ፡፡(24፡63)
يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اسْتَجِيبُوا لِلَّـهِ وَلِلرَّسُولِ إِذَا دَعَاكُمْ لِمَا يُحْيِيكُمْ ۖ وَاعْلَمُوا أَنَّ اللَّـهَ يَحُولُ بَيْنَ الْمَرْءِ وَقَلْبِهِ وَأَنَّهُ إِلَيْهِ تُحْشَرُونَ ﴿٢
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! (መልክተኛው) ሕያው ወደሚያደርጋችሁ እምነት በጠራችሁ ጊዜ ለአላህና ለመልክተኛው ታዘዙ፡፡ አላህም በሰውየውና በልቡ መካከል የሚጋርድ መኾኑን ወደርሱም የምትሰበሰቡ መኾናችሁን እወቁ፡፡(8፡24)
አንብበን ስንጨርስ ለሌሎች ሼር በማድረግ ይህንን ጠቃሚ ምክር ላልደረሳቸው እናዳርስ
አላህ በሱና ላይ ዘውታሪዎች ያድርገን!!!
አሚን!!
۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩
ወቅታዊ መረጃዎችን እና ኢስላማዊ ትምህርቶችን ለማግኘት ይህን ገፅ ላይክ ያድርጉ
Click and Like ➤➤ @ https://www.facebook.com/abudawdosman
Click and Like ➤➤ @ https://www.facebook.com/abudawdosman
በግፍ እስር ላይ የሚገኙትን ኡስታዝ ጀማል ያሲንን በዱዓችን እናስታውሳቸው! በአካልም በታሰሩበት አሸዋ ሜዳ ወረዳ 2 ኖኖ ፖሊስ ጣብያ በመሄድ እንዘይራቸው!
አላህ ከእስሩ ነጅ ያውጣቸው አሚንን!
የአላህ እርግማን ይውረድብህ አቶ አጉማ ባይሳ
አቡ ዳውድ ኡስማን
ይህ በአሜሪካ ነዋሪ የሆነው አጉማ ባይሳ የተባለ ግለሰብ የፍጥረታት ቁንጮ የሆኑትን የአላህ ነብይ ነብዩ መሐመድ(ሰዓወ) ተሳድቧል::
ይህ ግለሰብ ለኦሮሞ ህዝብ መብት እታገላለው የሚለው የዚህ መሰሉን ጥላቻ በልቡ ይዞ ነው :: ከግማሽ በላይ ህዝቡ ሙስሊም የሆነበትን የኦሮሞ ማህበረሰብ ከነፍሱ በላይ የሚሳሳላቸውን እና መስዋት የሚሆንላቸውን ነብይ እያንቋሸሹ እና እየሰደቡ ለህዝብ መብት ታጋይ ነኝ ማለት አይቻልም::
ይህ ግለሰብ የተሳደበው አንድን ግለሰብ አልያ የአንድ ፓርቲን መሪ ሳይሆን በመላው አለም ከ2 ቢሊዮን በላይ ሙስሊሞችን መሪ እና አለቃን ነው::
ከንብረታችን፣ከቤተሰባችን ከምንሳሳላት እናታችን አልፎ ከውድ ነፍሳችን በላይ የምንወዳቸውን እና መስዋት የምንሆንላቸውን ነብይ መሳደብ እና ማንቋሸሽ በምንም መልኩ በዝምታ የሚታለፍ አይደለም!
ከማንም ብሄር ፣ከማንም ሃገር ዜጋ ቢኮን ለአለማት እዝነት ከአላህ የተላኩት ነብያችንን መሳደብ ለመላው አለም ሙስሊም ቀይ መስመር ነው::
ነብያችን እና እስልምናችን ከብሔራችንም፣ ከሃገራችንም፣ ከቤተሰባችንም፣ ከደም እና ከአጥንታችንም በላይ ለኛ ለሙስሊሞች ውድ ናቸው!
ፊዳከ አቢ ወ ኡሚ ያረሱለሏህ
እናቴም አባቴም መስዋት ይሁንሎት አንቱ የአላህ መልዕክተኛ
የአላህ እርግማን በዚህ ቆሻሻ ግለሰብ ላይ ይሁን!
ወንድሜ Haider Khedir ለመፅሃፍ ስጦታህ ከልብ አመሰግናለሁ
አቡ ዳውድ ኡስማን
በወንድሜ ሐይደር ከድር ወደ አማርኛ ተተርጉሞ ለንባብ የቀረበው"የመልካም ሚስት ስብዕና" የተሰኘውን መፅሃፍ ወንድሜ ሃይደር እንዳነበው በስጦታነት አበርክቶልኛል:: ጀዛከላሁ ኸይር
መፅሃፍ ለሁሉም ሰው አንብብቶ መረዳት እንዲችል በቀላል አቀራረብ የተተረጎመ ሲሆን ለሴት እህቶቻችን ብቻ ሳይሆን ለወንዶችም እጅግ ብዙ ግንዛቤ የሚሰጡ ትምህርቶችን የያዘ ምጥን መፅሃፍ ነው::
ስለመፅሃፉ ባጭሩ ለመግለፅ በመፅሃፉ ላይ ያለውን ማብራሪያ ላጋራችሁ:-
ይህ መጽሐፍ...
📄 እናቶች፣ እህቶች እና ሚስቶች ራሳቸውን በተሻለ መልካም ስብዕና ለመገንባት እንዲረዳቸው፤
📄 ባሎች፣ አባቶችና ወንድሞች በስራቸው ያሉ ሴቶችን ለማስተካከል አጋዥ እንዲሆናቸው፤
📄 እንዲሁም እጅግ እየተዳከመ የመጣውን ሴቶችን በኢስላማዊ ማንነት የማነፅ ሥራ ለማነቃቃትና ዱዓቶችንም ከተዘናጉበት ለመቀስቀስ የሕዳሴ በር ከፋች ይሆን ዘንድ ነው! (ከመጽሐፉ የተወሰደ)
ይህን መፅሃፍ ባለትዳሮችም፣ ለማግባት ሃሳቡ ያላቸውም ቢያነቡት ብዙ ይማሩቡታል::
ሌሎቻችሁም ታነቡት ዘንድ ግብዣዬ ነው::
መፅሃፉን በአል ተውባ፣አል ቁድስ፣ ያሲን እና ቤተል ተቅዋ መስጂድ በር ላይ (ኩብራ ) መፅሃፍት መደብር ያገኙታል!
ወንድሜ ሃይደር ብዕርህን አላህ ይባርክልህ! መልካም ስራህንም ይቀበልህ፣ይህን ስራህንም ሰደቀተ ጃሪያ የሚሆን አላህ ያድርግልህ !
አሚን