ምዕራፍ-5 : #ጋብቻ_መፅሐፍ_ቅዱሳዊ_ግንዛቤ
ከመጽሀፍ ቅዱስ አንጻር የጋብቻ ምንነት
ጋብቻ አንድ ክርስቲያን ወንድና አንዲት ክርስቲያን ሴት በፍቅር ተሳስረው ባልና ሚስት በመሆን እስከ እለተ ሞታቸው ድረስ በአንድነት የሚኖሩበት ሕይወት ነው::
ጋብቻ ከፍጥረት መጀመሪያ በእግዚአብሔር የተመሰረተ ነው (ዘፍ2-:-18-25)፡፡ መጽሀፍ ቅዱስም ስለጋብቻ በቂ መረጃ ይሰጣል::
በሰው፣ በተፈጥሮና ስለወንጌል ጃንደረቦች ከሆኑት በቀር ሁሉም ያገባል::(ማቴ19-:-7-12,1ቆሮ7)
ከቤተ-ክርስቲያን (ከቤተሰብ) ፈቃድ ውጪ ጋብቻን መፈጸም አይፈቀድም::(ዘፍ2-:-22)
ሁለቱም አማኞች መሆን አለባቸው(ዘፍ2-:-25,ዘዳ7-:-1-4,1ቆሮ7-:-39)
ከቤተሰብ ጣልቃ ገብነት ነፃ መሆን (መተው) አለባቸው::(ዘፍ2-:-24,24-:-57)
ጌታ ኢየሱስ አፅንቷል (ዮሐ2-:-11) አስተምሯልም (ማቴ19-:-3-6)፡፡ ጋብቻን የሚያጸኑም ሦስት ዋና ነጥቦች አሉ:: እነሱም የመንፈስ፣ የአእምሮና የአካል አንድነት ናቸው::
ከሞት በቀር የሚለያቸው የለም:: (ዘፍ2-:-24,ማቴ19-:-6)
የክርስቶስና የቤተ-ክርስቲያን የፍቅር ትስስር ምሳሌ ነው:: (2ቆሮ11-:-2,ኤፌ5-:-23)
ፍቺና መለያየት ፈጽሞ አይፈቀድም:: (ሚል2-:-12-15)
እግዚአብሔር ይባርካችሁ !!!
👇👇👇👇👇
👉@Addishiwet
👉@Addishiwet
👉@Addishiwet
👉@Addishiwet
👉@Addishiwet
👉@Addishiwet
👆👆👆👆👆
👆👆👆👆👆
ምዕራፍ-5 : #ሞት_ቀብርና_ትንሳኤ
. #መግቢያ
መግቢያ
ሞት፣ ቀብርና ትንሳኤ በአንድ ሰው የምድራዊ ሕይወት መጨረሻና መንፈሳዊ አለም መጀመሪያ ላይ የሚከሰቱ የሕይወት ክንውኖች ናቸው:: ይህም ሰው ሁሉ የሚያልፍባቸውና በማንኛውም ዕድሜ ክልል ውስጥ የሚከሰት ሂደት ነው::
በጻድቃንም ሆነ በኃጢአተኛ ሰው ላይ ይፈጸማሉ፤ የራሳቸው የሆነ ሥርአትና የአፈጻጸም ግንዛቤ ሲኖራቸው ለክርስቲያን ለተሻለ ኑሮ መሸጋገሪያ ሲሆኑ ለኃጢአተኛ ለባሰ ኑሮ መሸጋገሪያ ናቸው::
ሞት፣ ቀብርና ትንሳኤ የየራሳቸው ትርጓሜ አላቸው::
ሞት ማለት መለየት
ቀብር ማለት መሰወር
ትንሳኤ ማለት ለአዲስ ኑሮ መነሳትን ያመለክታል::
ሞት በአዳም አለመታዘዝ ምክንያት የመጣ ቅጣት ሲሆን (ዘፍ2-:-17,3-:-8,19,ሮሜ5-:-17) ሶስት አይነት ነው:-
መንፈሳዊ ሞት - ከእግዚአብሔር መለየት (ዘፍ3-:-8,4-:-3-15,ኢሳ59-:-1-2,ኤፌ2-:-5,12,ኤፌ4-:-18-19,ሮሜ3-:-9-18)
የአካል (የሥጋ) ሞት - የሥጋና ነፍስ መለያየት (ዘፍ35-:-18-19,ያዕ2-:-26,መክ3-:-2-20) ይህ ሞት ለአማኞችም ለኃጢአተኞችም መሸጋገሪያ ነው::
ዘላለማዊ ሞት - ይህ ሞት ክርስቶስን እንደ ግል አዳኝ አድርገው ባልተቀበሉት ላይ የሚመጣ ሞት ነው:: (ማቴ25-:-41,1ተሰ1-:-9-10,ራዕ14-:-9-11,ራዕ21-:-8,14)
እግዚአብሔር ይባርካችሁ !!!
👇👇👇👇👇
👉@Addishiwet
👉@Addishiwet
👉@Addishiwet
👉@Addishiwet
👉@Addishiwet
👉@Addishiwet
👆👆👆👆👆
👆👆👆👆👆
Music : Tesfaye Gobisso
Enbayen ayte geta......
Meshaten stegnina eyesus lamesgnh❗️
👉@Tehadso_Join👈
👉@Tehadso_Join👈
👉@Tehadso_Join👈
ውድ ቅዱሳን የጌታ ኢየሱስ ሰላም ይብዛላችሁ.!!!
ክፍል ሁለትን ከጀመርን ስድስተኛው ክፍል(መለየት) እየተመለከትን የቆየን ሲሆን በዚህም ክፍል ውስጥ ለእግዚአብሔር የምንለያቸው ነገሮች በዋናነት ምን እነደሆኑ አይተናል....
አሁን ደግሞ ቀጣዮቹን ምዕራፎች ስለ , #ሞት, #ጋብቻ, #ትንሳኤ በእግዚአብሔር ቃል አንፃር በቀጣይ የምንመለከት ይሆናል።
የክፍል አንድን ሙሉ ዝርዝር የያዘ bot አዘጋጅተን እንድትጠቀሙ በተመቻቸው መሠረት በትምህርቱ ላይ ያለፉትን ሙሉ ክፍሎች እያያቹና ዕለት ዕለት በፈለጋቹት ሰዓት እያነበባችሁ እንድትከታተሉን በአክብሮት እንጠይቃለን።
በተጨማሪም ይህ ትምህርት አሰልቺነቱን ለመቀነስ ሲባል በጣም በትንሹ የተዘጋጀ እና በውስጡም ቡዙ ጥቅሶችን የያዘ ስለሆነ ብዙ ለመረዳት ከበድ ያሉ እና ግልፅ ያለሆኑ ነገሮች ካሉ ሃሳብ/አስተያየት የሚለውን በመንካት መጠየቅ ይቻላል።👇👇👇👇👇👇👇
እግዚአብሔር ይባርካችው....!!!
በዚህ ዙሪያ ማንኛውም አይነት ጥያቄ፣ ሀሳብ፣ መጨመር ያለበት ማንኛውም አይነት ነገር (አዲስ ነገር) ካልሆት ይህን ከታች ያለውን👇👇👇 Bot በመጠቀም ይላኩልን....
👇👇👇👇👇👇
👉@Addishiwetbot👈
👉@Addishiwetbot👈
👉@Addishiwetbot👈
👉@Addishiwetbot👈
👉@Addishiwetbot👈
👉@Addishiwetbot👈
ምዕራፍ-5 : #መለየት
. #መግቢያ
መለየት ማለት አገልጋዮችን፣ ሕፃናትን፣ ንብረትን፣ ስፍራንና ጊዜን ወይም ማንኛውንም ነገር በንጽህና ለእግዚአብሔር ክብር እንዲውል በጸሎትና እጅ በመጫን ለእግዚአብሔር አሳልፎ መስጠት ነው::
ሰዎች እንስሳት ቦታዎችና ቀኖች ሁሉ ለእግዚአብሔር እንዲለዩ ተደርጓል:: (ዘፀ3-:-5,13-:-2,28-:-41,ዘፍ2-:-3,ኢያ6-:-19)
የእግዚአብሔር አገልጋዮችና ከእግዚአብሔር አገልግሎት ጋር የተያያዘ ነገር ሁሉ ተለይቷል:: (1ነገ18-:-21,መዝ78-:-8,ዕዝ4-:-3,ሐዋ2-:-40,ዕብ14-:-23,ዘሌ19-:-2,14-:-20-21,ዘፀ40,1ጴጥ1-:-15,1ነገ8-:-56-58,ነህ12-:-27)
#መለየት_የተጠራባቸው_ሌሎች_ስያሜዎች
በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ መለየት ከተጠራባቸው ሌሎች ተዛማች ቃላት ውስጥ ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው::
መቀደስ (ዘኁ7-:-10,84,መሳ17-:-3)
ማስመረቅ (ዘዳ20-:-5)
መቀባት (ዘኁ26-:-84-88)
መመረጥ (ዘፀ19-:-5)
በጌታ ፊት መቆም (ሉቃ1-:-22-24)
እግዚአብሔር ይባርካችሁ !!!
👇👇👇👇👇
👉@Addishiwet
👉@Addishiwet
👉@Addishiwet
👉@Addishiwet
👉@Addishiwet
👉@Addishiwet
👆👆👆👆👆
👆👆👆👆👆
ምዕራፍ-5 : #መስጠት
. #በቤተ_ክርስቲያን_ውስጥ_የስርአቱ_አፈጻጸም
የምንሰጠው ስጦታ እንደገቢያችን መጠን ሆኖ በፈቃደኝነት፣ በልግስናና በደስታ ሊሆን ይገባል::(ሉቃ21-:-1-4,2ቆሮ8-:-1-5,9-:-7)
የሚሰጠው በቀጥታ ለቤተ-ክርስቲያን መሆን አለበት:: (ሚል3-:-8-10,1ቆሮ16-:-2,2ቆሮ8-:-2-3)
መባና አስራት ሲሰበሰብ ለራሱ ጊዜ ተሰጥቶት አምልኮ መሆኑን ማሳወቅ ያስፈልጋል::
በአዲስ ኪዳን በበለጠ ከጉድለት በልግስና፣ በደስታ መስጠት እንዳለብን መግለጹ አስፈላጊ ነው::
ስለስጦታ ያስተማረንና አስቀድሞ ያሳየን ራሱ እግዚአብሔር ነው:: ከስጦታዎች በላይ የሆነውን ስጦታ ለሰው ልጅ ሰጥቷልና (ዮሐ3-:-16,ሮሜ8-:-32)፡፡ ይህ በምድራዊ ቃላት ሊገለጥ የማይችል ስጦታ ላመኑት ሁሉ የዘላለም ሕይወትን እንዲያገኙ አድርጓል::
ቤተ-ክርስቲያን ይህንን የምስራች ለአለም ሁሉ ለማድረስ እንድትችልና የእግዚአብሔርን ቤት ስራ እንድትሰራ አማኞች የታዘዙትንና የፈቀዱትን ስጦታ ለወንጌል መስጠት አለባቸው:: ይህም ደግሞ በሕይወታቸው ላይ በረከትን ያበዛላቸዋል::
እግዚአብሔር ይባርካችሁ !!!
👇👇👇👇👇
👉@Addishiwet
👉@Addishiwet
👉@Addishiwet
👉@Addishiwet
👉@Addishiwet
👉@Addishiwet
👆👆👆👆👆
👆👆👆👆👆
#ይህ_ወቅታዊ_ድምፅ_ነው ❗️❗️❗️
#ይህ_ወቅታዊ_ድምፅ_ነው ❗️❗️❗️
#ይህ_ወቅታዊ_ድምፅ_ነው ❗️❗️❗️
©🅾⚔🆔-1⃣9⃣
➕
➕ ➕
➕ ➕
ያልሰማ ይስማ ➕ @Tehadso_Join ➕
የሰማ ላልሰማ V➕ @Tehadso_Join ➕
ያሰማ❗️ V➕ ➕
ይነበብ❗️ ➕🛑#COVID_19🛑➕
ይነበብ❗️ ➕🛑 #COVID_19 🔴➕
ይነበብ❗️ ➕🛑#COVID_19🛑➕
➕➕➕➕➕➕➕
👇🏾ይህን መልህክት እርሶ ጋር እንዳይቀር SHARE👇🏾
#ስለ_COVID_19_የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል❓
ይህ Covid 19 ወይንም ደግሞ ኮሮና ተብሎ የሚጠራው በሽታ ሁላችንም እንደምናውቀው ዓለምን ሙሉ በሙሉ በእድሜ ሳይለይ፣ በፆታ ሳይለይ፣ በቀለም ሳይለይ....ታዳጊ ሀገርችን ብቻ ሳይሆን ኃያላን በሆኑት ሀገሮች ላይም ጭምር ትልቅ ጭንቀት እየጣለ ያለ መላው የሰውን ልጅን ዓይን፣ ጆሮን....ምዕናብን ሳይቀር ወደ አንድ ቦታ የሰበሰበ ወረርሽኝ ነው።
እናሳ ይህ ክስተት በዚች ዓለም ላይ ላለችው ከእግዚአብሔር ለታላቅ ተልዕኮ ለተጠራችውና ሙሽራዋን በናፍቆት ለምትጠብቅ የኢየሱስ ክርስቶስ ሙሽሪት ለሆነችው ቤተ-ክርስቲያን ምንን ያመለክትታታል ❓❓❓
በእውነት ይህ ክስተት ከእግዚአብሔር ዘንድ ጊዜያዊ ቁጣ ብቻ የመጣ ነውን❓❓❓
የእግዚአብሔር ቃል የዘመን መልካም እንደሌለ እና እያንዳንዱ ዘመን ለሰው ልጆች የየራሳቸውን ክፉ ነገሮችን ይዘው እንደሚመጡ ይናገራል፤ ስለዚህም ደግሞ ከኃጥያት ሁሉ የሚርቅ አስተዋይ ሰው ዘመንን ደግሞ ይዋጅ እንጂ ሞኝ እንዳይሆን መፅሐፍ ቅዱስ አጥብቆ ይነግረናል።(ኤፌ5÷15-17)
#ዘመኑን_ዋጁ_ሲል_ምን_ማለቱ_ነው🤷♂❓
ከእግዚአብሔር ተልዕኮ ያላት ቤተ-ክርስቲያን በየዘመኑ ሰይጣን ከእግዚአብሔር ተልዕኮ ፈቀቅ ሊያደርጋት እና በራሱዋ መንገድ ውስጥ አስገብቶ ሊያንከራትታት ሳይታክት ይተጋል ከዚህም የተነሳ የእግዚአብሔር ቤተ-ክርስቲያን በየዘመኑ ሰይጣን የሚያስቀምጠውን የባህር ወጥመድ በማስተዋል እራሱዋን እና ህልውናዋን ነቅታ ከተስፋዋ ጋር እንድትጠብቅ ይረዳት ዘንድ ዘመንን ልትዋጅ ይገባታል፤ ከዚህም በተጨማሪ ይህቺ የእግዚአብሔር ቤተ-ክርስቲያን በየዘመኑ ለሚያጋጥሙአት እንቅፋት እና ውድቀት እንደ ማንቂያ ደውል ይሆናት ዘንድ ዘመንን ልትመረምር ይገባታል።(1ኛተሰ2÷3፣ ዕብ3÷10-11፣ ሉቃ21÷25-28፣ ኤፌ5÷15-17፣ ራዕ22÷12-13 2ኛዜና16÷9)
ከዚህም የተነሳ ይህ ዘመን አመጣሽ ወረርሽኝ ደዌ ለአለም የእግዚአብሔር ቁጣ ቢሆንም ለቤተ-ክርስቲያን ግን የማንቂያ ደውል ነው❗️❗️❗️
#ስለዚህ_COVID_19_የማንቂያ_ደወል_ነውን_እንዴት❓
የእግዚአብሔር ቤተ-ክርስቲያን ከተላከችው ተልዕኮ በስተ መጨረሻ በትንቢት ከተፃፉት መካከል አንድ ነገር ትጠብቃለች እርሱም የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ዳግም ምፃት ነው።.....ይህች የምፅአት ዘመን እና ቀን ማንም እንደማያውቃትና ድንገተኛ እንደሆነች መፅሐፍ ቅዱስ ይነግረናል።(2ጴጥ 3÷10፣ ማቴ24፤42-44፣ 1ተሰ5፤1-6)
ይህ ሲሆን ግን በዓለም ላይ ከሚገኙ ሰዎች መካከል አዕዛብን እና ያንቀላፉ ክርስቲያኖች ጭምር የኢየሱስ መምጫ ቀን ስለሚያመልጣቸው ለሰይጣን እና ለታላቁ መከራ አልፈው ይሰጣሉ❗️
ለዚህም የአስሩ ቅነጃጂቶችን ታሪክ እንደ ምሳሌ መውሰድ እንችላለን(ማቴ 25)(መብራታቸውን በርቶ እንዲቆይ ያልጠበቁቱ ብርሃን እንደሌላቸው ሰዎች ተቆጠሩ እግዚአብሔርም አላውቃችሁም አላቸው)
ነገር ግን እግዚአብሔር በመሃል ላይ ልታንቀላፋ ለምትችለው ቤተ-ክርስቲያን እንደ ማንቂያ ደውል ይሆን ዘንድ የማትታወቀዋ ዘመን መድረሷን የምናረጋግጥበት የተለያዩ ምልክቶችን አስቀምጧል። (ማቴ24÷4-31)
ከእነዚህም ከብዙ ምልክቶች መካከል አንዱ የዓለምን ህዝብን የሚያስጨንቁ ነገሮች መከሰት ነው። ኢየሱስም ይህን ሲናገር በሉቃስ ወንጌል 21÷25 ላይ..............
¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁵ በፀሐይና በጨረቃም በከዋክብትም
ምልክት ይሆናል፤ በምድር ላይም አሕዛብ
ከባሕሩና ከሞገዱም ድምፅ የተነሣ እያመነቱ
ይጨነቃሉ፤
²⁶ ሰዎችም ከፍርሃትና በዓለም የሚመጣበት
ከመጠበቅ የተነሣ ይደክማሉ፤ የሰማያት
ኃይላት
ይናወጣሉና።
²⁷ በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ በኃይልና በብዙ
ክብር በደመና ሲመጣ ያዩታል።
²⁸ ይህም ሊሆን ሲጀምር ቤዛችሁ ቀርቦአልና
አሻቅባችሁ ራሳችሁን አንሡ።........
#እንግዲያውስ_ይህ_የማንቂያ_ደውል_ከሆነ_ከእኛ_ከቅዱሳን_ምን_ይጠበቃል❓🤷♂
እግዚአብሔር አዋቂ ነው ምድር ላይ ከሚከሰቱ ክስተቶች አንዳች እንኳን ከእግዚአብሔር ዕውቀትና ፍቃድ ውጪ የሚሆን ነገር የለም።(ዮሐ1÷3)
ስለዚህም በዚህ ሰሃት ዓለም ላይ እየሆነ ያለው ነገር ሁሉ እግዚአብሔር የሚያውቀውና የፈቀደው ነው። በመሆኑም እግዚአብሔር ያስቀመጠውን እግዚአብሔር ብቻ ነው የሚያነሳውና እኛ የቤተ-ክርስቲያን አባል የሆንን ቅዱሳን እንደ ዓለም ሰው ከመጨነቅና ከመረበሽ ይልቅ የማንቂያ ደውልን ሰምተንና ነቅተን እግዚአብሔር ሁሉን ይመልስ ዘንድ ወደ እግዚአብሔር በእርጋታ መጮህ ነው የሚገባን።
#ወደእግዚአብሔር_ለመጮህ_እግዚአብሔር_ማንን_ይሰማል❓❓❓
የእግዚአብሔር ቃል ሲናገር እግዚአብሔር ሁሉም ሰው ስለ ዓለም የሚጮሁትን ጩኸት ሁሌም እንደማይሰማ ይናገራል።(ኤር14÷12) የኃጥያተኞችን ልመና ደግሞ ስለ ዓለም ከሆነ እግዚአብሔር አይሰማም፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር አስቀድሞ የኃጢአተኛውን ነብስ በንስሐ እንዲመለስ ስለሚፈልግ ነው።
በዚህ ሁሉ ግን እግዚአብሔር ህዝቡን በሚፈልገው የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ ውስጥ ካገኘ የእነርሱን ፀሎትና ምልጃ ስለመከራቸውም ያላቸውን ተማፅኖ እንደሚሰማ መፅሐፍ ቅዱስ ይነግረናል።(2.ዜና 7÷12-16)
#እግዚአብሔር_በሚፈልገው_ቤተ_መቅደስ_ውስጥ_እንዴት_እንሆናለን🤷♂❓
የእግዚአብሔር ቤተ-መቅደስ ማለት የእግዚአብሔር ማደሪያ ማለት ሲሆን እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ለማግኘት እና ከፍቅሩ የተነሳ ከሰው ልጅ ጋር በቅርበት ለመገናኘት የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ የሚያድርበት ቦታ ሲሆን እግዚአብሔር እራሱ በፈለገው፣ በፈቀደውና ባቀደው ቅዱስ ቦታ የሚዘጋጅ ነው።
ይህም በብሉይ ኪዳን በዳዊት አስጀምሮ በሰለሞን ያስገነባው ቤተ መቅደስ ነበር።
በአዲስ ኪዳን ግን አንድ ቅዱስ ቦታ ስላገኘ ከሰው ውድቀት በኃላ ለመጀመርያ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ከሰማይ በዮርዳኖስ ወንዝ ወረደ በሰውም ላይ(በኢየሱስ) ላይ አደረ። ስለዚህም የእግዚአብሔር ቤተ-መቅደስ ሊሆን የሚችል አንድ ብቻ ሰው ተገኘ ያህ ሰው የእግዚአብሔር መንግሥት ማደሪያ ሆነ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ነገር ግን ኢየሱስ ይህን ቅዱስና ፃዲቅ የእግዚአብሔር ማደሪያ የሆነውን ማንነት ይዞ ይቀመጥ ዘንድ አልወደደም፤ ይልቁንም ለሚቀበሉና በእርሱም ለሚያምኑ ሁሉ ይሆን ዘንድ የእርሱን ፃዲቅ እና የእግዚአብሔር ማደሪያ የሆነውን ማንነት ለዓለም ህዝብ በሞት አሳልፎ ሰጠ(በምትኩ የዓለምን ማንነት እርሱ ወሰደ)።
ምዕራፍ-5 : #መስጠት
. #የስጦታዎቹ_አይነቶችና_ትርጉማቸው
#በኩራት-
የመጀመሪያ ስለሆነ በኩራት መስጠት ማለት እግዚአብሔርን በነገሮቻችን ሁሉ ማስቀደም ማለት ነው::
በኩራት የእግዚአብሔር ነውና (ዘፀ23-:-19,ዘሌ23-:-10-11,18-:-12,ዘፀ13-:-14-16,ዘኁ3-:-13,ዘዳ15-:-19)
የበኩራት ስጦታ ትዕዛዝ ነው::(ዘፀ13-:-2,ዘዳ26-:-2)
የመጀመሪያውን ስንሰጥ ያለን ነገር ይባረክልናል::(1ሳሙ2-:-20-21)
#አስራት-
ከአስር አንድ እጅ ማለት ነው::(ዘፍ28-:-22)
አስራት የእግዚአብሔር ንብረት ስለሆነ አስራትን መክፈል የእግዚአብሔርን ንብረት በታማኝነት መመለስ ነው:: (ሚል3-:-10,ዘዳ14-:-22-23)
አስራት የእግዚአብሔር አገልጋዮች መብል ስለሆነ የሚከፍል ሁሉ በረከቱን ያስለቅቃል:: (ዘዳ26-:-22,ሚል3-:-10)
#መባ
እግዚአብሔር ለእኛ ከሰጠን ንፁህ ድርሻችን ላይ ለወንጌል ስራ፣ ለድሆች መርጃ፣ ለቤተ-ክርስቲያን አጠቃላይ እንቅስቃሴ የምንሰጠው ወሰን የሌለው ስጦታ ነው:: ይህ ስጦታ በልብ ደስታና በራሳችን ውሳኔ በአቅማችን መጠንና ከዚያም በላይ የምንሰጠው ይሆናል:: (ዘፀ25-:-1-5,2ቆሮ8-:-1-5)
#ልዩ_ልዩ_ስጦታዎች
የነቢያት (የአገልጋዮች) ስጦታ - (1ነገ17-:-8-10,ማቴ10-:-40-42,ሕዝ44-:-28-31)
የፍቅር ስጦታ - በእርዳታ የሚሰበሰብና ፍቅርን ለመግለጽ የሚሰጥ ሲሆን በተለያዩ ጊዜያቶች ሊደረግ ይችላል:: (ሐዋ11-:-27,30,2ቆሮ8-:-1-5)
እግዚአብሔር ይባርካችሁ !!!
👇👇👇👇👇
👉@Addishiwet
👉@Addishiwet
👉@Addishiwet
👉@Addishiwet
👉@Addishiwet
👉@Addishiwet
👆👆👆👆👆
👆👆👆👆👆
ውድ ቅዱሳን የጌታ ኢየሱስ ሰላም ይብዛላችሁ.!!!
#መሠረታዊ_የመፅሐፍ_ቅዱስ_ትምህርት
ክፍል ሁለትን ከጀመርን አራተኛ ምዕራፍ #የአገልግሎት_ስርዓት የሚለውን ክፍል ተመልክተናል........ አሁን ደግሞ ቀጣዮን ምዕራፍ-5 ስለ #መስጠት እንመለከታለን።
ቀደም ሲል ያየናቸውን ሙሉ ክፍሎች ዝርዝር የያዘ bot አዘጋጅተን እንድትጠቀሙ በተመቻቸው መሠረት በትምህርቱ ላይ ያለፉትን ክፍሎች እያያቹና እያነበባችሁ እንደቆያችሁ እናስባለን።
በተጨማሪም ይህ ትምህርት አሰልቺነቱን ለመቀነስ ሲባል በጣም በትንሹ የተዘጋጀ እና ዘግየት አያልን እያልን እያቀረብን ሲሆን በውስጡም ቡዙ ጥቅሶችን የያዘ ስለሆነ ብዙ ለመረዳት ከበድ ያሉ እና ግልፅ ያለሆኑ ነገሮች ካሉ ሃሳብ/አስተያየት የሚለውን በመንካት መጠየቅ ይቻላል።👇👇👇👇👇👇👇
እግዚአብሔር ይባርካችው....!!!
በዚህ ዙሪያ ማንኛውም አይነት ጥያቄ፣ ሀሳብ፣ መጨመር ያለበት ማንኛውም አይነት ነገር (አዲስ ነገር) ካልሆት ይህን ከታች ያለውን👇👇👇 Bot በመጠቀም ይላኩልን....
👇👇👇👇👇👇
👉@Addishiwetbot👈
👉@Addishiwetbot👈
👉@Addishiwetbot👈
👉@Addishiwetbot👈
👉@Addishiwetbot👈
👉@Addishiwetbot👈
#ቤተ_ክርስቲያን_ስርአቷን_በመጠበቋ_ያላት_በረከት
እውነትን ታውቃለች እውነትም ነፃ ያወጣታል::(ዮሐ8-:-31-32)
የምትለምነው ሁሉ ይሆንላታል::(ዮሐ15-:-7)
እግዚአብሔር ይገለጥላታል::(1ነገ3-:-4-14)
ለምድራዊ ነገሮች(ለስጋ ፍላጎት) የሞተች ትሆናለች::(2ቆሮ5-:-14-17,ዕብ4-:-12)
መንገዷን አውቃ እንድትሄድ ቃሉ ብርሃን ይሆናታል::(መዝ119-:-100-105,67-:-1-2)
ክፉን ለማፍረስና መልካምን ለመገንባት ጉልበታም ትሆናለች::(ኤር1-:-9-10,ኤፌ2-:-10)
ስለዚህ ቤተ-ክርስቲያን መጽሀፍ ቅዱስ በምድር ዘመኗ መኖርና መመራት የሚገባትን ሰማያዊ ሕግና ስርአትን ስለሚሰጣት ከምድራዊ ስርአት ተለይታ በዚሁ መጽሀፍ ቅዱስ በሚሰጣት ሰማያዊ ስርአት መመራት አለባት(ኤር6-:-16,ኢሳ30-:-19-21,መዝ37-:-1-3)፡፡ በዚሁ መሰረት ወንዶችም ሴቶችም መጽሀፍ ቅዱስ በሚሰጠን ስርአትና ደንብ መሰረት ቤተ-ክርስቲያን ውስጥ ማገልገል አለብን::
ከዚህም የተነሳ ማንም በክርስቶስ ቢያምን የእግዚአብሔር ቤተ-መቅደስ የሆነን ማንነት ከእየሱስ ይቀበላል፤ ይህንም ማንነት በቅድስና ሊጠብቅ ኃላፊነት አለበት። ምን አልባት ይህን ማንነት ባልጠበቀበትና ባልተጠነቀቀበት ጊዜ ይህ ሰው ይህን የእግዚአብሔር ቤተ-መቅደስ የሆነውን ማንነት ላለማጣት በንስሐ ሊመለስ ይገባዋል።
🔴🛑🔴🛑🔴🛑🛑🔴🛑🛑🔴🛑🔴🛑🔴🔴
🔴ስለዚህ ይህ ጊዜ ለዓህዛብ የጭንቅ ጊዜ ለእኛ 🔴
🔴ክርስቲያኖች ግን የእየሱስ ክርስቶስን ማንነት 🔴
🔴የምንፈልግበት እና በንስሐ የእግዚአብሔር 🔴
🔴ቤተ-መቅደስ የምንሆንበት ጊዜ ነው❗️❗️❗️🔴
🔴🔴🛑🔴🛑🔴🛑🔴🛑🔴🛑🔴🛑🔴🔴🔴
⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️
እግዚአብሔር ቤተ-ክርስቲያን ያንቃ❗️
አሜን❗️❗️❗️
⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️
#የኢየሱስ_ክርስቶስ_ሞትና_ትንሳኤ
1_____የኢየሱስ_ክርስቶስ_ሞት
የኢየሱስ ክርስቶስ መሞት በድንገት የሆነ ክስተት ሳይሆን እግዚአብሔር አስቀድሞ ያሰበው የሰውን ልጅ የማዳን እቅድ ነበር ይህም አስቀድሞ መነብያት ተነግሮ ነበር..... (ኢሳ53-:-8,ዳን9-:-26,ዘካ13-:-7)፤ ተወስኖ ነበር (ኢሳ53:6-10፣ ሐዋ2-:-23)
የሞተበትም ምክንያቶች........👇👇👇
ለጠፉት ቤዛ ለመሆን ነው (ሮሜ5-:-11፣ዮሐ2-:-2፣ 10-:-10)
የኃጢአትን መርገም ለማስወገድ ሲባል በመስቀል ላይ ሞተ (ዘሁ21-:-8፣ ዮሐ3:-14፣ ገላ3-:-13)
የአብርሃምን በረከት ለአሕዛብ ለማድረስ ነው (ገላ3-:-14)
2_____የኢየሱስ_ክርስቶስ_ትንሳኤ
የመነሳቱ ማስረጃዋች ምን ነበሩ?
ባዶ መቃብር መሆኑ... (ማቴ28-:-6፣ ሉቃ24-:-3)
የመልአክቱ ምስክርነት (ማቴ28-:-46፣ ሉቃ24-:-5-7)
ከትንሳኤ በኋላ ያናገሩት ሰዎች ጴጥሮስ፣ ማርያም፣ ቶማስ ምስክሮች ናቸው ለእነሱም የተወጋውን ሰውነቱን ማሳየቱ....
ለ500 ሰዎች በአንድ ጊዜ መታየቱ (1ቆሮ15-:-6)
ለእስጢፋኖስ መታየቱ (ሐዋ7-:-56)
#እንዴት_ከሙታን¥ተነሳ?
በአባቱ በአብ ኃይል (ሐዋ2-:-23-24,ሮሜ8-:-11)
በክርስቶስ(መለኮት በመሆኑ) በራሱ ኃይል (ዮሐ2-:-19፣ 10-:-18)
በመንፈስ ቅዱስ ኃይል (1ጴጥ3-:-18)
#የትንሳኤው_ውጤት_ምንድነው?
የእግዚአብሔርን መኖር ያረጋግጥልናል (ሮሜ1-:-16-23)
የክርስቶስን ታላቅ ፍቅር እና መሰጠት ያሳየናል (ሮሜ1-:-4)
ሙታን በእግዚአብሔር ሃይለ መነሳት እነደሚችሉ ያመለክታል (1ቆሮ15-:-12-17)
የነብያት ትንቢት መፈጸምን ያሳውቀናል (ሉቃ24-:-44-47)
3_____የኢየሱስ_ክርስቶስ_ወደቀድሞ_ሥፍራ_ማረግ
አባት ሆይ ዓለም ሳይፈጠር በአንተ ዘንድ በነበረኝ ክብር አንተ በራስህ ዘንድ አክብረኝ.........
ብሎ በመናገሩ ኢየሱስ ማረጉን እና ወደ ቀደመው ስፍራ መመለሱን ያመለክተናል...(ሐዋ1-:-9-11፣ ዮሐ17-:-5፣ ፊል2-:-6-10)
በነብያት ትንቢት መነገሩ (መዝ68-:-18፣ 110-:-1፣ ሉቃ9-:-51፣ ዮሐ6-:-62,14-:-28፣ 20-:-17፣ መዝ16-:-10፣ 49-:-15፣ ማር16-:-19)
በእርጋቱም ጊዜ በዓይን እየተመለከቱት ደመና ሰውራ እንደተቀበለችው መፅሐፍ ቅዱስ ይነግረናል ....... (ሐዋ1-:-9-11)
#የዕርጋቱ_ዓላማ
ወደቀደመው ክብር ለመመለስ.... (ዮሐ17-:-1-5)
በሰማይ ፈራጅ፣ አለቃና አዳኝ ለመሆን..... (ሐዋ5-:-31)
የፍጥረት ሁሉ ቀዳሚ ስለሆነ..... (ዕብ6-:-20)
ለልጆቹ የሚሆንን ዘላለማዊ መኖሪያ ቤት ሊያዘጋጅልን..... (ዮሐ14-:-2,ዕብ10-:-12-13)
በአሁኑ ጊዜ የክርስቶስ ሥራ ለቤ/ክ (ለአማኞች) እና ለሚድኑት ሁሉ መማለድ(በእግዚአብሔር እና በሰው ፊት መቆም እና ማስታረቅ) ነው:: (ዕብ7-:-25,9-:-24,ሮሜ8-:-34)
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም አምላክነት ባሕርዩና ፍጹም ሰው የመሆኑ ሚስጥር በጣም ታላቅ ነው:: የመጽሐፍ ቅዱሳችንም አብይ ርዕስ ነው::
ሐዋ/ዮሐንስ በመጀመሪያ መልዕክቱ ላይ ሲፅፍ ኢየሱስ ክርስቶስ በስጋ እንደመጣ የሚታመን መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው ይላል በሏል። (1ዮሐ4-:-2)፡፡ የእግዚአብሔር ፍቅርም ለሰው ልጆች የተገለጠው በዚሁ መልክ ነው:: ስለወደደን እኛኑ መስሎ በመምጣት ልንከፍለው የማንችለውን የሞት ዕዳ ከፈለልን::
❗️❗️❗️ክብር ሁሉ ለታላቅ ስሙ ይሁን። አሜን !!!❗️❗️❗️
ጌታ ይባርካችው !!!!
ጥያቄና አስተያየት 👇👇👇👇👇
👇👇👇👇👇
👉@Addishiwet
👉@Addishiwet
👉@Addishiwet
👉@Addishiwet
👉@Addishiwet
👉@Addishiwet
👆👆👆👆👆
👆👆👆👆👆
ከዚህም የተነሳ ማንም በክርስቶስ ቢያምን የእግዚአብሔር ቤተ-መቅደስ የሆነን ማንነት ከእየሱስ ይቀበላል፤ ይህንም ማንነት በቅድስና ሊጠብቅ ኃላፊነት አለበት። ምን አልባት ይህን ማንነት ባልጠበቀበትና ባልተጠነቀቀበት ጊዜ ይህ ሰው ይህን የእግዚአብሔር ቤተ-መቅደስ የሆነውን ማንነት ላለማጣት በንስሐ ሊመለስ ይገባዋል።
🔴🛑🔴🛑🔴🛑🛑🔴🛑🛑🔴🛑🔴🛑🔴🔴
🔴ስለዚህ ይህ ጊዜ ለዓህዛብ የጭንቅ ጊዜ ለእኛ 🔴
🔴ክርስቲያኖች ግን የእየሱስ ክርስቶስን ማንነት 🔴
🔴የምንፈልግበት እና በንስሐ የእግዚአብሔር 🔴
🔴ቤተ-መቅደስ የምንሆንበት ጊዜ ነው❗️❗️❗️🔴
🔴🔴🛑🔴🛑🔴🛑🔴🛑🔴🛑🔴🛑🔴🔴🔴
⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️
እግዚአብሔር ቤተ-ክርስቲያን ያንቃ❗️
አሜን❗️❗️❗️
⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️
ምዕራፍ-አራት: #የአገልግሎት_ስርዓት
#የወንድና_የሴት_የአገልግሎት_ስፍራቸው
በብሉይ ኪዳን ዘመን ከነበሩ ሰዎች መካከል እስራኤላውያን ማለትም ከአብርሃም ጀምሮ እግዚአብሔር ለአብርሀም በገባለት ቃልኪዳን ውስጥ ሆነው ከአመጸኛ አለም ወደ እግዚአብሔር ስርአት የተመለሱ ሰዎች ሁሉ እግዚአብሔር ወደ ፈጠረበት ወደ መጀመሪያው ስርዓት ማለትም ከአዳም ውድቀት በፊት መጀመርያ ወደ ነበረው ወደ እግዚአብሔር ስርዓት የተመለሱ ሰው ናቸው(እስራኤላውያን)፤ ከእዚህም የተነሳ ቀደም ባለው ክፍል እንደተመለከትነው በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ወንዶች ኃላፊዎች(የእግዚአብሔር ተጠሪዎች) ሲሆኑ ሴቶች ረዳቶች ነበሩ። (ዘሌ8-:-1-36, ዘጸ29-:-1-37, ዘሌ10-:-12-15, ዘኁ3-:-1-49)፡፡
ለዚህም ማሳያ ይሆነን ዘንድ የአሮንን ልጆች ብንመለከት ከሴቶችና ወንዶች መካከል ወንዶች ነበር ኪነቱን የሚረከቡት፣ ሴቶች ደግሞ በተፈጠሩበት ትልቅ ስፍራ ረዳቶች ነበሩ። (ዘሌ8-:-1-36,10-:-12-15)
እግዚአብሔር ለብሉይ ኪዳን ህዝቡ (ለእስራኤል) የሰጣቸው አገልግሎት አይነት #የቤት_ብቻ_አገልግሎት የሚባል የአገልግሎት አይነት ስለነበር አንድ ወጥ ነው([ስለዚህና ስለሌሎች የአገልግሎት አይነቶች በእግዚአብሔር ቃል እውነት መኖር በሚለው ትምህርት ላይ ለወደፊት በዝርዝር እናየዋለን)]::
ይህ የአገልግሎት አይነት የእስራኤል በእግዚአብሔርና በአሕዛብ መካከል መቆምን ብቻ እንደ አንድ አላፊነት የያዘ ሲሆን የአገልጋዮች ኣላፊነት ደግሞ በእግዚአብሔርና በእስራኤል (በሕዝቡ) መካከል መቆም ነበር:: (ዘፍ12-:-1-3,ዘጸ29-:-1-37,ዘኁ3-:-1-49)
ወደ አዲስ ኪዳን ስንመጣ ደግሞ ቤተ-ክርስቲያን ከአለም ተለይታ ወደ እግዚአብሔር ስርአት የተመለሰች የእግዚአብሔር አንድ አካል ከመሆኗ የተነሳ በቤተ-ክርስቲያን (በቤቱ) ውስጥ ወንዶች ኃላፊዎች(ተጠሪዎች) ሲሆኑ ሴቶች ደግሞ ረዳቶች ናቸው::
ለዚህም ደግሞ ማሳያ የሚሆነን ጌታ ኢየሱስ ከወለዳቸው ከወንዶችና ከሴቶች ልጆቹ መካከል የቤቱን ኃላፊነት አስረክቦ የሄደው ለወንዶች ልጆቹ መሆኑ ሲሆን ሴቶች ልጆች ደግሞ እረዳቶች ነበሩ። (ማቴ10-:-1-4,ሉቃ6-:-12-16,ዮሐ17-:-12-18)፡፡
የአዲስ ኪዳን አገልግሎት አይነት ደግሞ #የቤትና_የውጪ_አለግሎት የሚባል ስለሆነ ሁለት ፌዝ ነው ያለው::
#አንደኛው፥ በእግዚአብሔርና በአለም መካከል መቆም ሲሆን በዚህ አገልግሎት ቤተክርስቲያን ወደ አለም የእርቅ መልዕክተኛ ሆና ትሄዳለች። (ማር16-:-14-20,ዮሐ20-:-21-23,ሐዋ1-:-8,2ቆሮ5-:-19-20,ሐዋ2-:-14-42)
የዚህ አገልግሎት ዋና ግብ ቅዱሳን የትንሳኤው ምስክር ሆነው ከእስራኤል ሰፈር ውጪ ወደ አለም ሁሉ መሮጥ ማለትም እግዚአብሔር ወደሌላቸው ወደ አህዛብ በረት መሮጥ ከመሆኑ የተነሳ በዚህ አገልግሎት (ክህነት) እግዚአብሔር ወንዶችም ሴቶችም ሁሉ ያለልዩነት ይጠቀማል::
(ማቴ28-:-11-15,ዮሐ10-:-17,20-:-1-18,ማቴ28-:-1-10)
#ሁለተኛው ፌዝ ደግሞ በእግዚአብሔርና በሕዝቡ መካከል መቆም ሲሆን አገልግሎቱ በቤተ-ክርስቲያን ውስጥ ያሉትን ምዕመናን ማገልገልን እና ማነፅን ያጠቃልላል::
የዚህ የአገልግሎት ባህርይ በብሉይ ኪዳን ከነበረው ባለአንድ ፌዝ አገልግሎት አይነት ጋር ተመሳሳይ ስለሆነ አገልግሎቱ ከብሉይ ኪዳን ጀምሮ የመጣው የእስራኤል ቤት አገልግሎት ነው።
ስለዚህም ቀደም ባለው ክፍል ላይ እንዳየነው እግዚአብሔር አስቀድሞ ባስቀመጠው ስርዓት መሠረት ወንዶች የአገልግሎቱ ኃላፊዎች(ተጠሪዎች) ሲሆኑ ሴቶች ደግሞ የአገልግሎቱ ረዳቶች ናቸው:: (ዘፍ3-:-4-20,ኤፌ2-:-10,ዘፍ2-:-18-24,ዮሐ19-:-28-30)
ስለዚህ ጌታ የመጣው አስቀድሞ የነበረው ስለተበላሸ ለማደስ ነውና የወንድ እንደራሴነትና የሴት ረዳትነት በቤተ-ክርስቲያን ውስጥ የተጠበቀ ይሆናል፡፡
ስለዚህም
#ወንዶች እግዚአብሔር ካስቀመጣቸው ቦታ ውጪ ሌላ ቦታ የላቸውም
#ሴቶችም እግዚአብሔር ካስቀመጣቸው የረዳትነት ቦታ ውጪ ኤጲስ ቆጶስነት (የቤተ-ክርስቲያን መሪነት) ውስጥ አትገባም።
ፓውሎስ በመልህክቱ ሴት ወንዶች ባሉበት ጉባኤ ውስጥ ዝም ይበሉ፣ አያስተምሩም(አይሰለጥኑም) ያለው ይህ የአገልግሎት አይነት ለወንዶች ብቻ የተሰጠ ስለሆነና ሴት ልጅ ደግሞ እግዚአብሔር ለራሷ ያስቀመጠበት የረዳትነት ስፍራ ስላለ ነው::
#እንደ_አጠቃላይ ስናየው ሴቶች እንደ ወንዶች፣ ወንዶችም እንደ ሴቶች እግዚአብሔር ባስቀመጣቸው ቦታ እና ሃላፊነት እግዚአብሔርን ለማገልገል የተጠሩ ሲሆኑ ከላይ እስከአሁን ባየነው መልክ ማገልገል አለባቸው::(ኤፌ2-:-10,ማቴ19-:-6,22-:-30,ማር12-:-25)
በአገልግሎት ጊዜም አለባበስ ከቅድስና መካከል አንዱ ስለሆነ ማስተካከል ይገባቸዋል(1ቆሮ11-:-1-16)
ጌታ ይባርካችው !!!!
ጥያቄና አስተያየት 👇👇👇👇👇
👇👇👇👇👇
👉@Addishiwet
👉@Addishiwet
👉@Addishiwet
👉@Addishiwet
👉@Addishiwet
👉@Addishiwet
👆👆👆👆👆
👆👆👆👆👆
ምዕራፍ-5 : #ሞት_ቀብርና_ትንሳኤ
. #የአካል(የሥጋ) ሞት
በሁሉም ላይ ተወስኖአል (ዘፍ3-:-19,መክ3-:-2,ዕብ9-:-27)፤ ለሁሉም ሰው አስደንጋጭ ነው (መዝ23-:-4,55-:-4,73-:-19,ኢዮ24-:-17) ስጋ ሲሞት ነፍስ አይሞትም::(ሉቃ16-:-23-24,ፊል1-:-21-23,ራዕ6-:-9-11)፡፡
ለአማኞች ጥቅም ያለው ነው:: (ፊል1-:-21) ከእግዚአብሔር ጋር ለዘላለም መኖርን ያመጣልና (ዮሐ14-:-1-2,ሉቃ23-:-43,2ቆሮ5-:-8)፤ ከዚህ አለም መከራና ድካም ማረፊያ ነውና (ራዕ14-:-13,6-:-11)፤ ሠላምና ደስታ ወደበዛበት ኑሮ መግቢያ ነውና (ኢሳ57-:-1-2)፤ ውድ ጌታችንን በሙላት ለማየት ያስችላልና (ፊል1-:-23)፤ ከቀደሙት እምነት አባቶች ጋር መገናኛ ነውና (ዕብ11-:-13-16)፤ ሰላማዊ አካል መልበሻ ነውና (2ቆሮ5-:-1-5)፤ በሙላት እግዚአብሔርን ማምለክ ያስችላልና:: (ራዕ14-:-1-5,ራዕ15-:-3-4)
#ቀብር
ነፍስ ስትለይ ስጋን ወደ ግባተ መሬት መክተት ነው::
የሰውን አካል አክብሮ አንድ ቦታ ማስቀመጥ ነው::(ዘፍ19-:-3-6,50-:-13,25,ዮሐ11-:-33)
ሥጋ አፈር ስለሆነ ወደ አፈር መመለስ ነው:: (ዘፍ3-:-19)
በጸሎትና በመልካም ነገር የተጉ ሰዎች በአማኝ ቀብር ላይ ማገልገል ይችላሉ:: (ሐዋ8-:-2,ሉቃ13-:-50-53)
#ትንሳኤ
በክርስቶስ ለተገኘው አዲስ ሕይወት ለመነሳት የሚያገለግል ጉልበት ነው(ሙሉ ሰው ሆኖ በስጋና በነፍስ አንድነት መነሳት ነው)(1ቆሮ15-:-12-22)
ከሞት በኋላ ትንሳኤ አለ::(1ነገ2-:-10,ሐዋ7-:-60,1ቆሮ15-:-6,18-20,1ተሰ4-:-15-18)
ከትንሳኤ በኋላ ሞት ይሻራል:: (ራዕ21-:-4)
በክርስቲያኖች ይፈለጋል:: (1ቆሮ15-:-51-57)
በቤተ-ክርስቲያን ውስጥ የስርአቱ አፈጻጸም መመሪያ
በኃዘን ያለውን ቤተሰብ በእግዚአብሔር ቃልና ጸሎት ማጽናናት፤ በቀብር ቦታ ተገኝተው ለኃዘኑ ተካፋዮች ሰለሞትና ትንሳኤ መግለጽ፤ ግብአተ መሬቱን በጸሎት ማስፈጸም:: የኢየሱስ ትንሳኤም የስብከታችን መሰረት ሊሆን ይገባል::
እግዚአብሔር ይባርካችሁ !!!
👇👇👇👇👇
👉@Addishiwet
👉@Addishiwet
👉@Addishiwet
👉@Addishiwet
👉@Addishiwet
👉@Addishiwet
👆👆👆👆👆
👆👆👆👆👆
ውድ ቅዱሳን የጌታ ኢየሱስ ሰላም ይብዛላችሁ.!!!
ክፍል ሁለትን ከጀመርን ስድስተኛው ክፍል(መለየት) እየተመለከትን የቆየን ሲሆን በዚህም ክፍል ውስጥ ለእግዚአብሔር የምንለያቸው ነገሮች በዋናነት ምን እነደሆኑ አይተናል....
አሁን ደግሞ ቀጣዮቹን ምዕራፎች ስለ , #ሞት, #ጋብቻ, #ትንሳኤ በእግዚአብሔር ቃል አንፃር በቀጣይ የምንመለከት ይሆናል።
የክፍል አንድን ሙሉ ዝርዝር የያዘ bot አዘጋጅተን እንድትጠቀሙ በተመቻቸው መሠረት በትምህርቱ ላይ ያለፉትን ሙሉ ክፍሎች እያያቹና ዕለት ዕለት በፈለጋቹት ሰዓት እያነበባችሁ እንድትከታተሉን በአክብሮት እንጠይቃለን።
በተጨማሪም ይህ ትምህርት አሰልቺነቱን ለመቀነስ ሲባል በጣም በትንሹ የተዘጋጀ እና በውስጡም ቡዙ ጥቅሶችን የያዘ ስለሆነ ብዙ ለመረዳት ከበድ ያሉ እና ግልፅ ያለሆኑ ነገሮች ካሉ ሃሳብ/አስተያየት የሚለውን በመንካት መጠየቅ ይቻላል።👇👇👇👇👇👇👇
እግዚአብሔር ይባርካችው....!!!
በዚህ ዙሪያ ማንኛውም አይነት ጥያቄ፣ ሀሳብ፣ መጨመር ያለበት ማንኛውም አይነት ነገር (አዲስ ነገር) ካልሆት ይህን ከታች ያለውን👇👇👇 Bot በመጠቀም ይላኩልን....
👇👇👇👇👇👇
👉@Addishiwetbot👈
👉@Addishiwetbot👈
👉@Addishiwetbot👈
👉@Addishiwetbot👈
👉@Addishiwetbot👈
👉@Addishiwetbot👈
#የጳጉሜ_ፆም_ፀሎት
/channel/Tehadso_Join/43
ሰላም ለእናንተ ይሁን !
በክርስቶስ የተወደዳቹ ውድ ቅዱሳን በያላችሁበት የእግዚአብሄር ሰላምና ጸጋ ይብዛላችሁ።
እነሆ ዛሬ ጳጉሜ ከገባን ሁለተኛውን ቀን ይዘናል...
ለእግዚአብሔር ከእስራኤል ቀጥላ ሁለተኛ የተስፋ ሃገር ለሆነችው ኢትዮጵያ ብቻ የተጠ... ምን አልባትም በሌሎች ሃገሮች የማናስተውለው እነዚህ የጳጉሜ ቀናት እግዚአብሔር ለኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ዓመቱን ሙሉ በ 360 ቀናት ውስጥ ያሳለፈቻቸውን ህውንቶች በእግዚአብሔር ፊት እንድታቀርብና፣ በእነዚሁ ቀናት ውስጥም ደግሞ እግዚአብሔር አምላኳን የበደለችበትን እና ያሳዘነችበትን ሁሉ እያሰበች እራሷን በእግዚአብሔር ፊት አሰቀምጣ ንስሀሰ መግባት እንድትችል እና በተጨማሪ ደግሞ ቤተክርስቲያኗ ስላለችበት ዓለም፣ሀገር እና ቦታ የወንጌል አገልግሎቶቿንም ጭምር በእግዚአብሔር ፊት አቅርባ እንድትማፀንና ከእግዚአብሔርም የተስፋ መሪ ቃል መቀበል እንድትችል እና ለአዲሱ ዓመት መንደርደሪያ እንዲሆናት እግዚአብሔር ለእርሷ ብቻ ይሰጣት ታላቅ በረከት ነው።
ስለዚህም እኛም እንደ ቤተክርስቲያን ቅዱሳን ስላሳለፍነው ዓመት ለእግዚአብሔር በዙ ምንለው እንዳለ ሁሉ እንዲውም ደግሞ እግዚአብሔር ለኛ ብዙ ሚለን ነገሮች በመኖሩ እነዚህን ቀናት በከንቱ ለናሳለፍ አይገባንም....ሁላችንም እግዚአብሔር እንደረዳን፤ በቤታችን ያለንም በስራ ቦታም ቢሆን፣ የምንችል በፃም ያልቻልን ደግሞ እየበላንም ቢሆን፣ የቻልን ሙሉ ቀን የማንችል ደግሞ እግዚአብሔር እንደረዳን ጥቂትም ሰአታት ቢሆን ሁላችንም ከእግዚአብሔር ጋር የምናሳልፍበት ወቅት ነው።
ከእርሱ ጋር በመንፈስ የምንገናኝበት ጥሩ የፀሎት ጊዜ ይሆንልን ዘንድ እግዚአብሔር ሁላችንንም ይርዳን እያልን ለመላው የክርስቶስን አካል የምትወክለው ቤተክርስቲያን ብልቶች ሁሉ እግዚአብሔር የሚከብርበት መልካም የፀሎት ጊዜን እንመኛለን።
እግዚአብሔር ይባርካችሁ ...!!!
👇👇👇👇👇👇
👉@Tehadso_Join👈
👉@Tehadso_Join👈
👉@Tehadso_Join👈
👉@Tehadso_Join👈
👆👆👆👆👆👆
ምዕራፍ-5 : #መለየት
. #እንደ_መጽሀፍ_ቅዱስ_ምሳሌነት_ለእግዚአብሔር_መለየት
#ሕፃናት
ልጆች የእግዚአብሔር ስጦታዎች ናቸው (መዝ127-:-3)፡፡ የስጦታነትን ምስጢር አውቆ በእግዚአብሔር እንክብካቤና ጥበቃ ስር እንዲያድጉ መስጠት::
ሕፃናትን ለእግዚአብሔር አገልግሎት ለይቶ መስጠት(1ሳሙ1-:-11-12,1-:-28,2-:-11,17,21,26)ሳሙኤል የተለየበት
የእግዚአብሔር አላማ ያለባቸውን ሕፃናት የወደፊት አገልግሎት ተረድቶ መልሶ ለእግዚአብሔር መለየት(ሉቃ1-:-13-17,2-:-57-59,80,2-:-21-24,40)
#አገልጋዮች
እግዚአብሔር ለስራው የሚለያቸውና የሚጠራቸው ሰዎች ተለይተው ይሰጣሉ::(ኢሳ42-:-7)
በእግዚአብሔር ጥሪና ዓላማ መሰረት እራሱ እግዚአብሔር ይለያቸዋል:: (ዘፀ28-:-40,29-:-9,ማር3-:-13-19,መሳ13-:-5,1ሳሙ1-:-27-28,ሉቃ2-:-22-24)
የእግዚአብሔርን ሐሳብ ተረድተው ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ስራ ይለያሉ (1ሳሙ16-:-12,ሉቃ2-:-22-24)
የቤተ-ክርስቲያን መሪዎች በተጠራው አገልጋይ ላይ ያለውን የእግዚአብሔር ዓላማ ተረድተው ለአገልግሎት ይለዩታል::(ሐዋ13-:-1-3)
#ንብረትና_ገንዘብ :
ስጦታ ያመጡልኝ ዘንድ ለእስራኤል ልጆች ተናገር:: (ዘፀ25-:-1-9)
የገንዘብና የንብረት ባለቤት እግዚአብሔር ብቻ እንደሆነ አውቆ ለስራው የሚያስፈልገውን መለየት ያስፈልጋል::(ሐጌ2-:-8)
ከእግዚአብሔር የተቀበለውን ለእግዚአብሔር መለየት አስፈላጊ ነው::(1ዜና28-:-11-19)
እግዚአብሔር የሚፈልገውን ታዝዞ መስጠት ወደ ተጨማሪ በረከት መግባት ነው::(ማር13-:-29-30)
#ቦታና_ስፍራ :
(ዘፍ22-:-2) ወደ ሞራ ምድር ሂድ::
እግዚአብሔር በፈጠረበት ምድር ላይ ለራሱ ክብር መገለጫ የሚሆን ቦታ ይለያል::(2ዜና7-:-12)
የእግዚአብሔር ሕዝብ ተሰብስቦ የሚያመልክበት ቦታ ተለይቶ ለእግዚአብሔር ይሰጣል:: (ዘፍ28-:-18-22)
በቤተ-ክርስቲያን ውስጥ የሥርአቱ አፈጻጸም
አገልጋይ ከሆነ መብቱና ግዴታው አብረው እንደሚሄዱ አውቆ ቃል እንዲገባ ማስደረግ::
ሕፃናት ከሆኑ እጅ ጭኖ በመጸለይ በአካል በአዕምሮና በመንፈስ እንዲያድጉ መባረክ::
ንብረት ከሆነ አይነቱና አገልግሎቱ ተገልጾ በፀሎት ማስረከብ::
እግዚአብሔር ይባርካችሁ !!!
👇👇👇👇👇
👉@Addishiwet
👉@Addishiwet
👉@Addishiwet
👉@Addishiwet
👉@Addishiwet
👉@Addishiwet
👆👆👆👆👆
👆👆👆👆👆
ከዚህም የተነሳ ማንም በክርስቶስ ቢያምን የእግዚአብሔር ቤተ-መቅደስ የሆነን ማንነት ከእየሱስ ይቀበላል፤ ይህንም ማንነት በቅድስና ሊጠብቅ ኃላፊነት አለበት። ምን አልባት ይህን ማንነት ባልጠበቀበትና ባልተጠነቀቀበት ጊዜ ይህ ሰው ይህን የእግዚአብሔር ቤተ-መቅደስ የሆነውን ማንነት ላለማጣት በንስሐ ሊመለስ ይገባዋል።
🔴🛑🔴🛑🔴🛑🛑🔴🛑🛑🔴🛑🔴🛑🔴🔴
🔴ስለዚህ ይህ ጊዜ ለዓህዛብ የጭንቅ ጊዜ ለእኛ 🔴
🔴ክርስቲያኖች ግን የእየሱስ ክርስቶስን ማንነት 🔴
🔴የምንፈልግበት እና በንስሐ የእግዚአብሔር 🔴
🔴ቤተ-መቅደስ የምንሆንበት ጊዜ ነው❗️❗️❗️🔴
🔴🔴🛑🔴🛑🔴🛑🔴🛑🔴🛑🔴🛑🔴🔴🔴
⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️
እግዚአብሔር ቤተ-ክርስቲያንን ያንቃ❗️
አሜን❗️❗️❗️
⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️
#ወቅታዊ_መልዕክት
👉#ትንቢተ_ኤርሚያስ 7 ÷1-14
(ዘፀ15÷26)
እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ከመፍጠሩ አስቀድሞ ለስድስት ቀናት እንዳላረፈ እና በስራ ላይ እንጀቆየ መፅሐፍ ቅዱስ ያመለክተናል ....
በስድስተኛውም ቀን ደግሞ ሰውን ፈጠረ ፤ በሰባተኛውም ቀን ከስራው ሁሉ አረፈ፤
እግዚአብሔር አስቀድሞ በስድስት ቀናት ውስጥ የፈጠረውን እና ውብ እንደሆነ የተመለከተውን ዓለም "ታበጅና ትጠብቅ ዘንድ" ብሎ ለሰው ልጅ ዓለምን የመንከባከብንና የማበጀትን ኃላፊነትን ከስልጣን ጋር ሰጠው።
ሰው ግን ይህን ኃላፊነት ባለመጠበቁ የተነሳ ከእግዚአብሔር የተሰጠውን ስልጣን ለሰይጣን አሳልፎ ሰጠ፤ እግዚአብሔር ደግሞ ይህን ስልጣን ለማስመለስ ዳግም ስራ ጀመረ እስከዛሬም በስራ ላይ ነው፤ እኛም በዚህ ዘመን ከአባታችን ከእግዚአብሔር ተልከን በስራ ላይ ነን !!!
#መግቢያ
የእግዚአብሔር ነብይ ኤርምያስ እግዚአብሔር በብሉይ ኪዳን ዘመን ካስነሳቸው ታላላቅ ነብያት መካከል አንዱ ነው። ነገር ግን ኤርሚያስ እግዚአብሔር ለኪነትና ለነብይነት ከመረጣቸው ከሌዊ ዘር መካከል አንዱ አልነበረም፤ በመሆኑም እግዚአብሔር ኤርሚያስን ለነብይነት
ሲመርጠውና ሲጠራው ከተለመደው የመጠራት ስርዓት ውጪ ነበረ፤ ከዚህም የተነሳ ኤርሚያስ "እኔ በነቢያት ቤትና ስርዓት ውስጥ አላደኩምና ገና ማደግ የሚገባኝ ብላቴና ነኝ" በማለት የእግዚአብሔርን ጥሪ የልቀበልም ብሎ አምፆ እንደነበር መፅሐፍ ቅዱስ ያስተምረናል።
ኤርሚያስ በዘሩ ከካህናትና ቤተሰብ አንዱ ቢሆንም... በሰው ዓይን ደግሞ ለነብይነት ጥሪ የማይበቃ ብላቴና ቢመስልም እግዚአብሔር ኤርሚያስን ገና ከእናቱ ሆድ ሳይወጣ በማእፀን ውስጥ ሳይሰራው አስቀድሞ መርጦታልና "በአፍህ ቃሌን አስቀምጣለው" በማለት ለነብይነት ለየው(ቀባው)።
#መልዕክት
ነብዩ ኤርምያስ በተነሳበት ዘመን የነበረው ትውልድ ወደ እግዚአብሔር ቤት የሚመላለስ እና አምልኮ ያለው ነገር ግን የሳተና ከእግዚአብሔርም መንገድ ፈቀቀ ብሎ የነበረ፣
እንደፈለገ ዘባች ሆኖ የእግዚአብሔር ህዝብ ነኝ የሚል፣
ጠማማ የሆነ ነገር ግን የቀናው ነኛ ብሎ የሚያስብ፣
ካልዘራበት ለማጨድ የሚሄድ፣
ድንበር የሌለው (ከእግዚአብሔርም ጋር ከዓለምም ጋር ሊሆን የሚፈልግ)፣
የራሱን ማንነት ያላገኘና ያለበትን የማያውቅ ህዝብ ነበር። ከዚህም የተነሳ እግዚአብሔር ለህዝቡ የተሃድሶ መልዕክቱን ይልክ ነበር።(ኤር 6÷16)
ነገር ግን እነርሱ የእግዚአብሔርን ድምፅ ሰምተው አይመለሱም ነበና ኤርሚያስ ምዕራፍ 7 ላይ ያለውም መልዕክት ለእነሱ የተላከ ነበር።
በዚህም ክፍል እግዚአብሔር እኔ የምልክላቹን የተሃድሶ መለዕክት ብትቀበሉ፣ መንገዳችሁንና ስራችሁን ብታሳምሩ በዚች ምድራችሁ አሳድራችዋለው ብሎ......
የእግዚአብሔርን ቃል አጥብቀው ቢሰሙና ቢታዘዙ ፣
ለእግዚአብሔር የሚበጀውን ነገር ቢያደርጉ(ለእግዚአብሔር የሚበጀውን ነገር ማድረግ ለስጋ ፍላጎትና ሁኔታ የማይመች ቢመስልም እግዚአብሔርን ለሚታዘዙት የበረከት ፍሬ እንደሚያወርሳቸው መፅሐፍ ቅዱስ ያስተምረናል #1ነገ 17÷8-16 ) ፣
ለራሳቹ ማሰብ አቁማችሁ ለኔ ብታስቡ ፣(ሁል ጊዜ የምትመላለሱበት መንገድ እግዚአብሔርን የሚያስደስት ቢሆን (እንደ ዳዊት በእግዚአብሔር ልብ ብትመላለሱ)) ፣
ስለዚህ ይህን ሁሉ ቢያደርጉ በአገራቸው እንደሚያቆያቸውና ለጠላት ምርኮ አሳልፎ እንደማይሰጣቸው ያስታውቃቸው ነበር።
ፈ)
ስለዚህም በዚህ ዘመን ያለን እኛ ህለት ከህለት የእግዚአብሔር ቃል እንደሚያዘን እግዚአብሔርን እየፈራን እና ደስ የሚያሰኘውን ብቻ እያደረግን ማሳለፍ ያስፈልጋል፣ እግዚአብሔርን የምንታዘዝና የምናስደስት ሆነን እራሳችንን ከጠበቅን በኃላ...
ስለ ዓለም እንፀልያለን፣
ስለ ሀገራችን እንፀልያለን፣
ስለ ኑሮ መፀለይ እንችላለን፣
ስለ በሽታ መፀለይ እንችላለን፣
የዲያቢሎስን ጉልበት መስበር እንችላለን፣
እግዚአብሔርም ፀሎታችንን ይሰማል።
ስለዚህም በዚህ ዘመን እግዚአብሔርን ለመታዘዝና ደስ ሚያሰኘውን ነገር ለማድረግ መጀመሪያ
ለእግዚአብሔር የሚበጀውን ብቻ በማድረግ ፣
ሁለተኛ ጉረቤትን(ከእናንተ ጋር ያለውን የቅርብ ሰው) ማሰብ ቀጥሎ መበለትን አለመግፋት፣ ቀጥሎ ስለ ችግረኛው ማሰብ ወዘተ እየቀጠልን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘውን ሁሉ እናደርጋለን፤
ነገር ግን በዋናነት ማስተዋል ያለብን ይህን ሁሉ ከማድረጋችን በፊት እራሳችንን በእግዚአብሔር ፊት አቅርበን ለእግዚአብሔር በሚበጀው መንገድ፣ ህይወት ፣ አገልግሎት፣ ኑሮ ላይ መሆናችንን ማስተዋል አለብን ! ይህን ሳይሆን ግን ምንም ብናደርግ ዋጋ የለውም።
ስለዚህ ለእግዚአብሔር የሚበጀውንና የሚያስደስተውን እያደረግን ለዓለም በረከትና ፈውስ ምክንያት ሆነን የመፍትሔ ሰው እንድንሆን እግዚአብሔር ይርዳን !
አሜን !!!
እግዚአብሔር ይባርካችሁ ...!!!
👇👇👇👇👇👇
👉@Tehadso_Join👈
👉@Tehadso_Join👈
👉@Tehadso_Join👈
👉@Tehadso_Join👈
👉@Tehadso_Join👈
👉@Tehadso_Join👈
. ምዕራፍ-5 : #መስጠት
. #መግቢያ
መስጠት ማለት በኩራት፣ አስራት፣ መባና ልዩ ልዩ ስጦታን ለእግዚአብሔር ቤት አገልግሎት እንዲሆን ማቅረብ ነው:: ይኸውም ያለንን ሁሉ ነገር ከእግዚአብሔር እንደተቀበልንና የተሰጠንንም እንደሚባርክልን ማመናችንን መግለጫ መንገድ ነው:: መስጠት ሁሉንም ክርስቲያን ይመለከታል (2ነገ12-:-9-10,2ዜና31-:-5)
የመስጠት ዋና አላማ
እግዚአብሔር አዟል (ዘፀ25-:-1-5,ዘሌ27-:-30-31,ዘኁ18-:-21,ዘዳ14-:-22-29,ማቴ5-:-15,ሉቃ19-:-10)
እግዚአብሔር እንጂ ገንዘብ አምላክ እንዳልሆነ ማረጋገጫ ነው:: (ማቴ6-:-19-24,ቆላ3-:-5)
የእግዚአብሔርን መንግስት ለማስፋፋት (1ቆሮ9-:-4-14,ፊል4-:-15-18)
አስራትን አለመስጠት እግዚአብሔርን መስረቅ ስለሆነ (ሚልክ3-:-8-10)
በመስጠት ውስጥ ያለውን በረከት ለመውረስ (ዘዳ15-:-4,26-:-13-15,ሚልክ3-:-10-12,2ቆሮ9-:-6,ማቴ19-:-21,ማር10-:-29, ሉቃ6-:-38,1ጢሞ18-:-19)
እግዚአብሔር ይባርካችሁ !!!
👇👇👇👇👇
👉@Addishiwet
👉@Addishiwet
👉@Addishiwet
👉@Addishiwet
👉@Addishiwet
👉@Addishiwet
👆👆👆👆👆
👆👆👆👆👆
. #ሀጥያት_እንዴት_በሰው_ላይ_ስልጣን_አገኘ❓
እግዚአብሔር ሰውን ሲፈጥር ጻዲቅ አድርጎ በራሱ መልክ አምሳያ እንጂ ሀጥያት የሚያደርግ ማንነት አልፈጠረም፤ ነገር ግን ሰውን ሲፈጥር የሰውን እውቀት የሚቀይር(ክፉን እና ደጉን እንዲያውቅ የሚያደርግ ወይንም ደግሞ ጽድቅን እና ኩነኔን እንዲለይ የሚያደርግ) ዛፍ እና የሰውን ስጋ እንዳይሞት የሚያደርግ ዛፍ(የሕይወት ዛፍ) በገነት ውስጥ ነበሩ
(#ዘፍ-2÷9 ፣ #ዘፍ-2÷17 & #ዘፍ-3÷22)።
ሁለቱም ዛፎች በገነት ውስጥ ነበሩ ከዚህም የተነሳ ብዙ ሰዎች እግዚአብሔር ለምን አዳምና ህይዋንን ይፈትናቸው ዘንድ እነዚን ዛፎች በገነት አስቀመጠ? ይላሉ ምክንያቱ ግን አንድ ነው፥
እግዚአብሔር ሰውን ሲፈጥር እንደ ሌሎቹ ፍጥረታት በአንድ በተከበበ ህይወት ውስጥ እንዲኖሩ ሳይሆን በተፈጠሩበት ዓለም የፈለጉትን፣ የመረጡትን እና የፈቀዱትን እያደረጉ በፈቃዳቸው ያሰኛቸውን እያደረጉ እንዲኖሩ ነው።
(ስለዚህም ነው ሁሉ ተፈቅዶልናል የምንለው...አንዳች እንኳን ማድረግ እንዳንችል የተደረግነው ነገር የለም.1ቆሮ10÷23)
ስለዚህም እነዚህ ሁለት ዛፎች ስለ ሰው ስለተፈጠሩ እግዚአብሔርም ከውድ ፍጡሩ ከሰው የሚደብቀው ነገር ስለሌለ(#ዘፍ-18÷17) ነው እንጂ ሰውን ፈጥሮ ሁለቱን ዛፎች ከሰው ዘንድ መሠወር ይችል ነበር ግን እግዚአብሔር ሰውን በፈቃዱ የፈቀደውን እያደረገ እንዲኖር ፈጥሮታልና የወደደውን እንዲያደርግ ዛፎቹን አስቀመጠ።(#1ቆሮ-10÷23)
እነዚህም ዛፎች ሁለት ታላላቅ መንግሥትን ይወክላሉ [የእግዚአብሔር እና የሰይጣን መንግሥት]
ስለዚህም ሰው ልጅ በምርጫው እንዲኖር ተፈጥሯልና የፈቀደውን መንግሥት እንዲመርጥ ምርጫ ቀረበለት...
አሁን ሁሉ ስለተፈቀደለት የፈቀደውን ያደርጋል ነገር ግን ሁሉ ስለማይጠቅመው የማይጠቅመውን ማድረግ ስለሌለበት እግዚአብሔር የቱ እንደማይጠቅመው አስታወቀው(ዘፍ-2÷17)።
ብዙ ሰዎች የአዳምና የይዋን ሀጥያት ፍሬ መስረቅ አድርገው ይወስዳሉ ያ ግን ፈፅሞ ስእተት ነው!!!
የሀጥያት አባት ሰይጣንም! ብቻውን ከእግዚአብሔር መንግስት ተጥሎ የሚኖር ስለሆነ...ሰውን ወደ እርሱ ወዳለበት ወደ ስቃይ መንግስት ለመቀላቀል ስለሚያስብ... ምርጫቸውን ሊያሳስት ወደ ሔዋን መጣ....
ሀሳብም አቀረበ ሔዋንም ተቀበለችው ሀሳቡም ከባድ ሀጥያት ነበር ሀሳቡ ይህ ነበር፦ "...ሞትን አትሞቱም" የሚል ነበር፣ ነገር ግን ይህሃሳብ ሲተነተን ...እግዚአብሔር ውሸታም ነው ማለት ነው።
"....ዓይናቹ እንዲከፈት ስለሚያውቅ ነው" ይህ ደግሞ ሁለተኛው ሃሳብ ነው... ያህ ማለት ደግሞ እግዚአብሔር ስለ እናንተ አያስብም እናም ለእናንተ ጥሩ እንዳይሆን ብሎ ስለሚያስብ ነው ማለት ነው።(#ዘፍ-3÷1-6)
ይህን ሁሉ ሀሳብ ሔዋን ተቀብላለችና በላች አዳምም በላ(የሚስቱን ቃል ከሰይጣን የመጣውን ተቀበለ)(#ዘፍ3÷17)።
ከዚህም የተነሳ ሁለቱም ምርጫቸውን ወደ ህይወት ዛፍ ከማድረግ ይልቅ ወደ ሰይጣንና ኃጥያት መንግስት አደሰጉ ስለዚህም ሀጥያተኞች ሆኑ ነገር ግን ጥያቄው ከነሱ በኃላ ያለው ሰውስ ነው?
እግዚአብሔር የእነርሱ ሀጥያት ከእነርሱ በኃላ ወደ እነሱ ልጆች እንዳያልፍ እና ለልጆቹ አዲስ የህይወት ምርጫ እንዲኖራቸው ለማድረግ ስላሰበ፤ እንዲመለሱ እና መሳታቸውን እንዲያምኑ(እንዲፀፀቱ) ለማድረግ ሁለቱንም አናገራቸው ነገር ግን አዳም በዘሩ ሀጥያት(አመጽ) እንዳያልፍ ሀጥያቱን አልተናዘዘምና የአለም ሀጥያት(ሞት) ምክንያት ሆነ።(#1ቆሮ-15÷22-23)።
ሔዋን ግን ሀጥያቷን በመናዘዟ ዘሯን ለሀጥያት አልሰጠችም።
ነገር ግን የሚወልዱት ልጆች ሁሉ ከአዳም ዘር ስለሚደርሳቸው ሀጥያትን ሞትንም ሁሉ ይወስዳሉ ስለዚህም እነሱም ልጆቻቸውም ከኃጥያት መንግስተ ነፃ ስለማይሆኑ ለፈቃዳቸው መንግስት አሳልፎ ሰጣቸው በገነት የሚቆዩበት ምክንያት ስለሌለ ከገነት ተባረሩ።
የሰው ልጅ ሁሉ ከሴት ብቻ መወለድ ስለማይችል ወደደም! ጠላም በአባት በኩል የአዳም ሀጥያትን(ሞትን) ወይም አመጽን ይቀበላል ለዚህ ነው ኢየሱስ ሁሉ ከአዳም የተነሳ ሙት(የሀጥያት ዘር) ነው ያለው።
ለዚህም ነው አሁን የምንመለከተውን የሰው ልጅ የሀጥያት ዘቅት ውስጥ መግባት የሆነው። ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ከሴት ብቻ የተወለደ ሰው የለምና ከኢየሱስ በቀር ሀጥያት የሌለበት(ጻዲቅ) ሰው የለም(#ሮሜ-3÷11-20)፤ ይህም ነው የኢየሱስ ከድንግል ብቻ የመወለድ ሚስጥር።
አሁን ግን ከአዳም በኩል የሚመጣውን ወይም ደግሞ ሀጥያተኛ የሚያደርገውን ዘር መጣስ... እና ከሀጥያት ተላቆ ጻዲቅ መሆን ይቻላል፤ እርሱም የሚገኘው በማመን ብቻ ነው።
እየሱስን ስናምን ደግሞ ከአዳም የኃጢአት መንግስት እንዳመለጥንና ወደ ክርስቶስ የህይወት መንግስት እንደገባን ደግሞ እናምናለን። (ሮሜ-3÷21-24)
ያመነውን ያክል ፅድቅ በህይወታችን ይታያል.....
Amen !
ለማንኛውም ጥያቄ ወይ አስተያየት 👇👇
@Addishiwetbot
እግዚአብሔር ይባርካቹ ...!!!
👇👇👇👇👇
👉 @Addishiwet
👉 @Addishiwet
👉 @Addishiwet
👆👆👆👆👆
#የሕይወት_መንገድ_የመቀየር ሚስጥር
የሰው ልጅ በእግዚአብሔር በመጀመርያ በትልቅ እና በከበረ ስፍራ በገነት ተፈጥሮ ነበር፤ በዚህም ስፍራ ደስተኛ እና በትልቅ ሀሴት እግዚአብሔርን እያመሠገኑ እንዲኖሩ አዳምና ሒዋን ለእግዚአብሔር ክብር ተፈጠሩ፡፡
ለምድርም ውበት ሆኑ....እግዚአብሔር ሰውን ከፈጠረ በኃላ መልካም የነበረው ምድር ሁሉ እጅግ መልካም እንደሆነ ተመለከተ ይህም የሆነው ሰው ከመፈጠሩ የተነሳ ነው፡፡(#ዘፍ 1÷31)
ነገር ግን የሰው ልጅ ከፈጠረው ከእግዚአብሔር ጋር ተጣላ ለምድር በረከት የነበረው ሰው ለምድር እርግማን ሆነ፡፡(#ዘፍ 3÷17)
እግዚአብሔር ግን ከፍቅሩ የተነሳ ሰውን አልረገመም የዚህም ዋነኛ ምክንያት ሰው በሰይጣን ተታሎ እንጂ እራሱ በራሱ ሀጥያተኛ አልሆነምና ነው፤ ለዛም ነው እግዚአብሔር ሄዋንን ሄዶ ያታለለሽን ሰይጣን(እባብ) ተበቀይ በጭንቅም የበቀልን ልጅ ውዉጂ ያላት፡፡(#ዘፍ 3÷14-16)
አውን የሰው ልጅ ሁሉም የሞተ ከእግዚአብሔርም ጋር ተጣልቶ የሚኖር ሆነ ከዚህም የተነሳ ገነት ተዘጋች ምክንያቱም ገነት ለመግባት የበቃ ፅድቅ ያለው ሰው የለም ነበር፡፡
ነገር ግን እግዚአብሔር በብሉ ኪዳን ለአምስት ሺ አመታት በአጥያት ባርያ ሆኖ የኖረውን ሰው ከዚህ የኃጢአት ባርነት ለማዳን እራሱ እግዚአብሄር ወልድ ሰው ሆነ(ቃሉ ስጋ ሆነ){ዮሐ 1÷14} "ቃል ደግሞ እግዚአብሔር ነው"(ዮሐ 1÷1).....ይህም ደግሞ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው....!
ስለ ሰው ልጅ ፍቅር ሰው ከመሆንም በላይ ከሰው ዝቅ ብሉ የእንስሳት በረት ውስጥ ተወለደ...!!! ይህም ሳያንስ በሰው ተገፍቶ በከተማ ለሙታን ወይም ከእግዚአብሔር ተጣልተው ላሉ ሰዎች ያስተምር፣ ይናገርም ነበር ለዛ ነው "ሙታን የእግዚአብሔርን ድምፅ የሚሰማበት ጊዜ ይመጣል እርሱም አውን ነው" ያለው እርሱ እግዚአብሔር ስለሆነ ነው፡፡(ዮሐ 5÷25).........በመጨረሻም ስለሰው ፍቅር በሰው ልጅ ተደብድቦ፣ ደሙን አፍስሶ ሞተ ግን ይህን ሁሉ የሆነው የእግዚአብሔር ዓላማ ስለነበረ ነው......እርሱም ዓላማው ይህ ነበር..... የሰውን ልጆች ሁሉ ሙሉ ሀጥያት (ሰውን ባሪያ ያደረገው ሀጥያት በሙሉ) በቀራኒየው መስቀል ላይ እንደ መስዋት በክርስቶስ ላይ ሆነ( አስቀድሞ በትንቢት እንደተነገረው እግዚአብሔር የዓለምን ሀጥያት በሙሉ በእየሱስ ላይ አኖረው፡፡(ኢሳ 53÷6) እርሱንም አደቀቀው ገደለውም (ስለዚህ የዓለም ሀጥያት ሙሉ በሙሉ ከኢየሱስ ጋር ሞተ)
ከዚህም የተነሳ የሰው ልጅ ከሀጥያት ባርነት ነፃ ወጣ አርነትም ሆነለት...ስለዚህም ለአምላክ ምስጋና ይሁን፡፡(ሮሜ 6÷17)
ከአሁን በኃላ የሰው ልጅ ከሀጥያት ባርነት ነፃ የመውጣት ትልቅ እድል መድሀኒት አገኘ መዳኛም ምክንያት ሆነ ይህም በክርስቶስ እየሱስ በማመን ብቻ ነው የሚገኘው፡፡ ይህም ከሞት መንገድ ወደ ሕይወት መሻገሪያ እድል ነው(ዕብ 10÷19) ይህም በክርስቶስ የሚገኝ አዲስ እና ህያው መንገድ ነው፡፡(በዚህም መንገድ ከሀጥያት ባርነት ነፃ እንወጣለን) ነገር ግን ችግሩ የሰው ልጅ በአቅሙ መበርታት ስለማይችል(አቅመ ቢስ ስለሆነ) ድጋሚ ሰይጣን አሳስቶት በሀጥያት እንዳይኖር በሶስተኛው ቀን ሞትን ድል አድርጎ እየሱስ ተነሳ....!!!
ስለዚህም ህያው የሆነው ኢየሱስ እረዳቴ ነው ብለን በኢየሱስ በማመን የእግዚአብሔር ብቻ የነበረውን ፅድቅ መውሰድ እንችላለን፡፡(#ሮሜ 3÷22-24)
#ዋና_ጭብጥ
በአውኑ ጊዜ ብዙ ክርስቲያኖች በፅድቅ መኖር አቅቷቸው በብዙ ሀጥያት ውስጥ ይኖራሉ ለዚህም ዋና ተጠያቂ ሰይጣን ነው፡፡
ሰይጣንም የሚጠቀምበት መንገድ ይሄ ነው፡፡ ሰው የእግዚአብሔርን ፅድቅ በራሳቸው እየራቁ መኖር እንደሚችሉ በውስጣቸው ያሳምናቸዋል....ስለዚህ በራሳቸው ከተለያዮ ሀጥያቶች(ከውሸት፣ ከስርቆት፣ ከቅናት፣ ከምኞት፣ ከሱስ ወዘተ...) ለመውጣት እንዲሞክሩ ያደርጋቸዋል ነገር ግን እነሱ ይህን ማድረግ ስለማይችሉ ድል የሚቀናጀው ሰይጣን ነው፡፡
ምክንያቱም ሰው በኃይሉ አይበረታምና የእግዚአብሔርን ሀይል ግን እንዳያገኙ ያሳውራቸዋል፡፡
ሌላው የሰይጣን መንገድ አንዳንድ ክርስቲያኖች ደግሞ ከሕይወት ሙከራ ብቻ ሰው በአቅሙ ከሀጥያት መራቅ እንደማይችል ይረዳሉ ስለዚህም ከሀጥያት መላቀቂያ መንገድ እግዚአብሔርን እንዳይፈልጉ ተስፋ ያስቆርጣቸዋል(ሰው ሁሉ ሀጥያተኛ እንደሆነ ቃል በመጥቀስ፤ ፃዲቅም መሆን እንደማይቻል፣ የሰውም ፃዲቅ እንደሌለ ያሳምናቸዋል) ያኔ ፃዲቅ እንድንሆን የሚያስችለንን የእግዚአብሔር ኃይል እንዳናገኝ ያደርገናል፡፡
ስለዚህ የሰው ልጅ በራሱ አቅም ላይ ብቻ ተስፋ ቆርጦ እና የራሱን አቅም በመጣል ደካማ ባሪያ መሆኑን አምኖ ነገር ግን በእግዚአብሔር ኃይል ታምኖ እለት ተእለት በእግዚአብሔር ፀጋ ለመኖር ራሱን አሳምኖ እግዚአብሔርን ቢለምን እግዚአብሔር ራሱ በራሱ አቅም ሕይወቱን በቅፅበት ይለውጠዋል ፃዲቅም ያደርገዋል፡፡ ግን በእግዚአብሔር ኃይል ብቻ ይቻላል......!!!
አሜን....!
ለማንኛውም ጥያቄ ወይ አስተያየት 👇👇
@Addishiwetbot
እግዚአብሔር ይባርካቹ ...!!!
👇👇👇👇👇
👉 @Addishiwet
👉 @Addishiwet
👉 @Addishiwet
👆👆👆👆👆
ውድ ቅዱሳን የጌታ ኢየሱስ ሰላም ይብዛላችሁ.!!!
ክፍል ሁለትን ከጀመርን አራተኛውን ትምህርት #የአገልግሎት_ስርዓት እየተመለከትን የቆየን ሲሆን በዚህም ክፍል ውስጥ አገልግሎት ምን ማለት ነወ፣ ከሚለው እስከ አገልግሎት የሚያገለግሉ አገልጋዮች እነማን ናቸው፣ እነርሱስ በምን አይነት ስርዓት እግዚአብሔርን ያገለግሉታል እና የመሳሰሉትን ሃሳቦች አንስተን መማራችን ይታወቃል።
እንዲሁም ደግሞ ሁሉ ክርስቲያን ከእግዚአብሄር ጋር በልጁ በኢየሱስ በኩል የተታረቀ አማኝ በዚህ ምድር ሲኖር ከሁሉ በፊት የሚያስቀድመው እና እራሱን የሰጠለት አገልግሎት ከወንዶች እና ከሴቶች አንፃር መፅሐፍ ቅዱስ እንዴት ያስተምረናል የሚለውን ሃሳብ እንደ መነሻ በጥቂቱ ተመልክተናል።
በዛሬው ዕለት ደግሞ የምዕራፍ አራት የመጨረሻ ክፍል የሆነውን #ቤተ-ክርስቲያን ከእግዚአብሔር የተቀበለችውን የአገልግሎት ስርዕት በመጠበቋ የምታገኘውን በረከት በመመልከት የምናጠቃልል ሲሆን በሚቀጥሉት ሁለት ምዕራፎች ደግሞ ስለ #መስጠት እና #መለየት እናቀርባለን፣ እንማራለን።
የክፍል አንድን ሙሉ ዝርዝር የያዘ bot አዘጋጅተን እንድትጠቀሙ በተመቻቸው መሠረት በትምህርቱ ላይ ያለፉትን ሙሉ ክፍሎች ከታች👇👇👇👇 "መሠረታዊ ክርስትና እምነት ት/ት" የሚለውን በመንካት ወደ bot በመሄድ እያያቹና ዕለት ዕለት በፈለጋቹት ሰዓት እያነበባችሁ እንድትከታተሉን በአክብሮት እንጠይቃለን።
በተጨማሪም ይህ ትምህርት አሰልቺነቱን ለመቀነስ ሲባል በጣም በትንሹ የተዘጋጀ እና በውስጡም ቡዙ ጥቅሶችን የያዘ ስለሆነ ብዙ ለመረዳት ከበድ ያሉ እና ግልፅ ያለሆኑ ነገሮች ካሉ ሃሳብ/አስተያየት የሚለውን በመንካት መጠየቅ ይቻላል።👇👇👇👇👇👇👇
እግዚአብሔር ይባርካችው....!!!
በዚህ ዙሪያ ማንኛውም አይነት ጥያቄ፣ ሀሳብ፣ መጨመር ያለበት ማንኛውም አይነት ነገር (አዲስ ነገር) ካልሆት ይህን ከታች ያለውን👇👇👇 Bot በመጠቀም ይላኩልን....
👇👇👇👇👇👇
👉@Addishiwetbot👈
👉@Addishiwetbot👈
👉@Addishiwetbot👈
👉@Addishiwetbot👈
👉@Addishiwetbot👈
👉@Addishiwetbot👈
#ይህ_ወቅታዊ_ድምፅ_ነው ❗️❗️❗️
#ይህ_ወቅታዊ_ድምፅ_ነው ❗️❗️❗️
#ይህ_ወቅታዊ_ድምፅ_ነው ❗️❗️❗️
©🅾⚔🆔-1⃣9⃣
➕
➕ ➕
➕ ➕
ያልሰማ ይስማ ➕@Addishiwet➕
የሰማ ላልሰማ V➕@Addishiwet➕
ያሰማ❗️ V➕ ➕
ይነበብ❗️ ➕🛑#COVID_19🛑➕
ይነበብ❗️ ➕🛑 #COVID_19 🔴➕
ይነበብ❗️ ➕🛑#COVID_19🛑➕
➕➕➕➕➕➕➕
👇🏾ይህን መልህክት እርሶ ጋር እንዳይቀር SHARE👇🏾
#ስለ_COVID_19_የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል❓
ይህ Covid 19 ወይንም ደግሞ ኮሮና ተብሎ የሚጠራው በሽታ ሁላችንም እንደምናውቀው ዓለምን ሙሉ በሙሉ በእድሜ ሳይለይ፣ በፆታ ሳይለይ፣ በቀለም ሳይለይ....ታዳጊ ሀገርችን ብቻ ሳይሆን ኃያላን በሆኑት ሀገሮች ላይም ጭምር ትልቅ ጭንቀት እየጣለ ያለ መላው የሰውን ልጅን ዓይን፣ ጆሮን....ምዕናብን ሳይቀር ወደ አንድ ቦታ የሰበሰበ ወረርሽኝ ነው።
እናሳ ይህ ክስተት በዚች ዓለም ላይ ላለችው ከእግዚአብሔር ለታላቅ ተልዕኮ ለተጠራችውና ሙሽራዋን በናፍቆት ለምትጠብቅ የኢየሱስ ክርስቶስ ሙሽሪት ለሆነችው ቤተ-ክርስቲያን ምንን ያመለክትታታል ❓❓❓
በእውነት ይህ ክስተት ከእግዚአብሔር ዘንድ ጊዜያዊ ቁጣ ብቻ የመጣ ነውን❓❓❓
የእግዚአብሔር ቃል የዘመን መልካም እንደሌለ እና እያንዳንዱ ዘመን ለሰው ልጆች የየራሳቸውን ክፉ ነገሮችን ይዘው እንደሚመጡ ይናገራል፤ ስለዚህም ደግሞ ከኃጥያት ሁሉ የሚርቅ አስተዋይ ሰው ዘመንን ደግሞ ይዋጅ እንጂ ሞኝ እንዳይሆን መፅሐፍ ቅዱስ አጥብቆ ይነግረናል።(ኤፌ5÷15-17)
#ዘመኑን_ዋጁ_ሲል_ምን_ማለቱ_ነው🤷♂❓
ከእግዚአብሔር ተልዕኮ ያላት ቤተ-ክርስቲያን በየዘመኑ ሰይጣን ከእግዚአብሔር ተልዕኮ ፈቀቅ ሊያደርጋት እና በራሱዋ መንገድ ውስጥ አስገብቶ ሊያንከራትታት ሳይታክት ይተጋል ከዚህም የተነሳ የእግዚአብሔር ቤተ-ክርስቲያን በየዘመኑ ሰይጣን የሚያስቀምጠውን የባህር ወጥመድ በማስተዋል እራሱዋን እና ህልውናዋን ነቅታ ከተስፋዋ ጋር እንድትጠብቅ ይረዳት ዘንድ ዘመንን ልትዋጅ ይገባታል፤ ከዚህም በተጨማሪ ይህቺ የእግዚአብሔር ቤተ-ክርስቲያን በየዘመኑ ለሚያጋጥሙአት እንቅፋት እና ውድቀት እንደ ማንቂያ ደውል ይሆናት ዘንድ ዘመንን ልትመረምር ይገባታል።(1ኛተሰ2÷3፣ ዕብ3÷10-11፣ ሉቃ21÷25-28፣ ኤፌ5÷15-17፣ ራዕ22÷12-13 2ኛዜና16÷9)
ከዚህም የተነሳ ይህ ዘመን አመጣሽ ወረርሽኝ ደዌ ለአለም የእግዚአብሔር ቁጣ ቢሆንም ለቤተ-ክርስቲያን ግን የማንቂያ ደውል ነው❗️❗️❗️
#ስለዚህ_COVID_19_የማንቂያ_ደወል_ነውን_እንዴት❓
የእግዚአብሔር ቤተ-ክርስቲያን ከተላከችው ተልዕኮ በስተ መጨረሻ በትንቢት ከተፃፉት መካከል አንድ ነገር ትጠብቃለች እርሱም የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ዳግም ምፃት ነው።.....ይህች የምፅአት ዘመን እና ቀን ማንም እንደማያውቃትና ድንገተኛ እንደሆነች መፅሐፍ ቅዱስ ይነግረናል።(2ጴጥ 3÷10፣ ማቴ24፤42-44፣ 1ተሰ5፤1-6)
ይህ ሲሆን ግን በዓለም ላይ ከሚገኙ ሰዎች መካከል አዕዛብን እና ያንቀላፉ ክርስቲያኖች ጭምር የኢየሱስ መምጫ ቀን ስለሚያመልጣቸው ለሰይጣን እና ለታላቁ መከራ አልፈው ይሰጣሉ❗️
ለዚህም የአስሩ ቅነጃጂቶችን ታሪክ እንደ ምሳሌ መውሰድ እንችላለን(ማቴ 25)(መብራታቸውን በርቶ እንዲቆይ ያልጠበቁቱ ብርሃን እንደሌላቸው ሰዎች ተቆጠሩ እግዚአብሔርም አላውቃችሁም አላቸው)
ነገር ግን እግዚአብሔር በመሃል ላይ ልታንቀላፋ ለምትችለው ቤተ-ክርስቲያን እንደ ማንቂያ ደውል ይሆን ዘንድ የማትታወቀዋ ዘመን መድረሷን የምናረጋግጥበት የተለያዩ ምልክቶችን አስቀምጧል። (ማቴ24÷4-31)
ከእነዚህም ከብዙ ምልክቶች መካከል አንዱ የዓለምን ህዝብን የሚያስጨንቁ ነገሮች መከሰት ነው። ኢየሱስም ይህን ሲናገር በሉቃስ ወንጌል 21÷25 ላይ..............
¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁵ በፀሐይና በጨረቃም በከዋክብትም
ምልክት ይሆናል፤ በምድር ላይም አሕዛብ
ከባሕሩና ከሞገዱም ድምፅ የተነሣ እያመነቱ
ይጨነቃሉ፤
²⁶ ሰዎችም ከፍርሃትና በዓለም የሚመጣበት
ከመጠበቅ የተነሣ ይደክማሉ፤ የሰማያት
ኃይላት
ይናወጣሉና።
²⁷ በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ በኃይልና በብዙ
ክብር በደመና ሲመጣ ያዩታል።
²⁸ ይህም ሊሆን ሲጀምር ቤዛችሁ ቀርቦአልና
አሻቅባችሁ ራሳችሁን አንሡ።........
#እንግዲያውስ_ይህ_የማንቂያ_ደውል_ከሆነ_ከእኛ_ከቅዱሳን_ምን_ይጠበቃል❓🤷♂
እግዚአብሔር አዋቂ ነው ምድር ላይ ከሚከሰቱ ክስተቶች አንዳች እንኳን ከእግዚአብሔር ዕውቀትና ፍቃድ ውጪ የሚሆን ነገር የለም።(ዮሐ1÷3)
ስለዚህም በዚህ ሰሃት ዓለም ላይ እየሆነ ያለው ነገር ሁሉ እግዚአብሔር የሚያውቀውና የፈቀደው ነው። በመሆኑም እግዚአብሔር ያስቀመጠውን እግዚአብሔር ብቻ ነው የሚያነሳውና እኛ የቤተ-ክርስቲያን አባል የሆንን ቅዱሳን እንደ ዓለም ሰው ከመጨነቅና ከመረበሽ ይልቅ የማንቂያ ደውልን ሰምተንና ነቅተን እግዚአብሔር ሁሉን ይመልስ ዘንድ ወደ እግዚአብሔር በእርጋታ መጮህ ነው የሚገባን።
#ወደእግዚአብሔር_ለመጮህ_እግዚአብሔር_ማንን_ይሰማል❓❓❓
የእግዚአብሔር ቃል ሲናገር እግዚአብሔር ሁሉም ሰው ስለ ዓለም የሚጮሁትን ጩኸት ሁሌም እንደማይሰማ ይናገራል።(ኤር14÷12) የኃጥያተኞችን ልመና ደግሞ ስለ ዓለም ከሆነ እግዚአብሔር አይሰማም፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር አስቀድሞ የኃጢአተኛውን ነብስ በንስሐ እንዲመለስ ስለሚፈልግ ነው።
በዚህ ሁሉ ግን እግዚአብሔር ህዝቡን በሚፈልገው የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ ውስጥ ካገኘ የእነርሱን ፀሎትና ምልጃ ስለመከራቸውም ያላቸውን ተማፅኖ እንደሚሰማ መፅሐፍ ቅዱስ ይነግረናል።(2.ዜና 7÷12-16)
#እግዚአብሔር_በሚፈልገው_ቤተ_መቅደስ_ውስጥ_እንዴት_እንሆናለን🤷♂❓
የእግዚአብሔር ቤተ-መቅደስ ማለት የእግዚአብሔር ማደሪያ ማለት ሲሆን እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ለማግኘት እና ከፍቅሩ የተነሳ ከሰው ልጅ ጋር በቅርበት ለመገናኘት የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ የሚያድርበት ቦታ ሲሆን እግዚአብሔር እራሱ በፈለገው፣ በፈቀደውና ባቀደው ቅዱስ ቦታ የሚዘጋጅ ነው።
ይህም በብሉይ ኪዳን በዳዊት አስጀምሮ በሰለሞን ያስገነባው ቤተ መቅደስ ነበር።
በአዲስ ኪዳን ግን አንድ ቅዱስ ቦታ ስላገኘ ከሰው ውድቀት በኃላ ለመጀመርያ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ከሰማይ በዮርዳኖስ ወንዝ ወረደ በሰውም ላይ(በኢየሱስ) ላይ አደረ። ስለዚህም የእግዚአብሔር ቤተ-መቅደስ ሊሆን የሚችል አንድ ብቻ ሰው ተገኘ ያህ ሰው የእግዚአብሔር መንግሥት ማደሪያ ሆነ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ነገር ግን ኢየሱስ ይህን ቅዱስና ፃዲቅ የእግዚአብሔር ማደሪያ የሆነውን ማንነት ይዞ ይቀመጥ ዘንድ አልወደደም፤ ይልቁንም ለሚቀበሉና በእርሱም ለሚያምኑ ሁሉ ይሆን ዘንድ የእርሱን ፃዲቅ እና የእግዚአብሔር ማደሪያ የሆነውን ማንነት ለዓለም ህዝብ በሞት አሳልፎ ሰጠ(በምትኩ የዓለምን ማንነት እርሱ ወሰደ)።
“በዘጠኝ ሰዓትም ኢየሱስ፦ ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ? ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህም፦ አምላኬ አምላኬ፥ ስለ ምን ተውኸኝ? ማለት ነው።”
— ማቴዎስ 27፥46

ምዕራፍ-አራት: #የአገልግሎት ስርዓት
#ስለ_ወንድና_ሴት_መጽሐፍ_ቅዱሳዊ_ግንዛቤ
ወንድ የእግዚአብሔር ምሳሌና እንደራሴ (ወኪል) ሲሆን ሴት ደግሞ ረዳቱ ናት::
ከዚህም የተነሳ ወንድ ያለሴት ሴትም ያለወንድ ሙሉ ሊሆኑ አይችሉም፤ ምክንያቱም በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ የወንድ እራስነትን(ወኪልነትን) ከእግዚአብሔር ሲቀበል ብቻውን ሙሉ ሊሆን እንደማይችል ተነግሮታል፤ ስለዚህም ዓለምን ለማስተዳደርና ወኪል ለመሆን እንደራሱ ያለች ረዳት እንደምታስፈልገው ስለዚህም ከጎኑ አውጥቶ ሴትን እንደሰራት መፅሐፍ ቅዱስ ይነግረናል። (ዘፍ2-:-18-24,1ቆሮ11-:-7-9)
ይህም ማለት መጽሀፍ ቅዱስ ሴት የወንድ (የባል) ረዳት መሆኗን እንጂ የአንዱን በላይነትና የአንዱን በታችነት አያስተምርም::
ሴትም በረዳትነት በመፈጠሯ ወንድ ደግሞ በእራስነት(በወኪልነት) በመፈጠሩ በሚታይ ማንነት ማለትም (Physical Fitness) በአካል ብቃት ወይንም ደግሞ በጉልበት (በአቅም) ወንድ ከሴት በልጦ እንመለከታለን። ይህ ወንድ ለወኪልነት መፈጠሩን የሚያረጋግጥልን ሲሆን፤ ሴት ደግሞ በአብዛኛው እንደሚስተዋለው በውስጣዊ ማንነት ማለትም (Mental maturation) ከወንድ ቀድማ የምትገኝ መሆኑ ሴት ደግሞ የተፈጠረችው የወንድን ወኪልነትን ልትረዳ(ልትደግፍ, ልታቆም, ሙሉ ልታደርግ) እንደሆነ ያረጋግጥልናል። (1ጴጥ3-:-7)፡፡
ነገር ግን በስብዕናዋ ከወንድ ጋር እኩል ናት፤ ወንድም ደግሞ ከሴት ጋር እኩል ነው:: እርሷም እንደ ወንድ ነፃ ምርጫ አላት፤ ወንድም እንደ ሴት ነፃ ምርጫ አለው(1ቆሮ11-:-10)፡፡
#ሴት_ረዳት_ስለመሆኗ
በእግዚአብሔር ቤት ስርአት ውስጥ ወንድ የእግዚአብሔር ተጠሪ ሲሆን ሴትን ደግሞ የወንድ ረዳት አድርጎ አስቀምጧል:: ለዚህም ማስረጃ:-
ሴት ረዳት በመሆኗ ፍሬ እንደበላች ራቁት አልሆነችም::(እግዚአብሔር ወኪል አድርጎ የፈጠረው ወንድ ሂዋንን የማስቆምና የመገፀፅ ኃላፊነት የእርሱ ስለሆነ የእርሱን ድርጊት(ምላሽ) እግዚአብሔር ይጠብቅ ነበር) (ዘፍ3-:-4-6)
ወንድ የቤቱ ተጠሪና ኃላፊ በመሆኑ ፍሬውን እንደበላ ሁለቱም ራቁት ሆኑ:: (ዘፍ3-:-6-8)
እግዚአብሔር ስለጥፋቱ አዳምን በመጠየቅ ጀመረ እንጂ ወደ ሄዋን በመሄድ አልጀመረም ወይም ሁለቱንም በመጠየቅ አልጀመረም ቅጣትንም አልሰጠም፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሔር ወንድን እንደ ወኪል ፈጥሮታልና ለጥፋት ሁሉ መጀመርያ ተጠያቂ የሆነው እሱ ነበር) (ዘፍ3-:-10-19,ዘፍ3-:-22-24,ዘኁ30-:-1-16)
አዳም ለፍጥረቱ ሁሉ ለሴትም ጭምር ስም ማውጣቱና ሴትም ስጋንና እስትንፋስን ከአዳም መቀበሏ በቤቱ የወንድ ኃላፊነትንና የሴትን ረዳትነት አምነን እንድንቀበል ያደርገናል:: (ዘፍ2-:-18-25,3-:-20)
መጽሀፍ ቅዱስ ከብሉይ እስከ አዲስ ኪዳን ማንኛውንም ጉባኤ በወንድ ጾታ መጥራቱ የወንድን ውክልናና (ኃላፊነትና) የሴትን ረዳትነት ያመለክታል:: (መዝ133-:-1-3,ሐዋ1-:-12-16,6-:-1-3)
ሴቶች ረዳቶች ስለሆኑ ወንዶች ባሉበት ጉባኤ እንዳይሰለጥኑም ይገድባል::ይህ ማለት ሴት ልጅ ለወንድ ወይንም ደግሞ ለባልዋ ረዳት እንድትሆን ስለተፈጠረች ባሏን ከማጠንከር እና ከመርዳት ባለፈ እንደወኪል ወይንም እንደ እራስ ሆና በቤተክርስቲያን ልትሰለጥን ብትሞክር እግዚአብሔር ባልፈጠራት ቦታ ተቀምጣለችና የእግዚአብሔር መንፈስን አብሯት አይሆንም ስለዚህም የፀና ውክልና አይኖርም። እንዲውም ደግሞ ወንድ ከተፈጠረበት የአላፊነት ቦታ ወቶ እንደ አጋዥ (እረዳት) ይህ ማለት ደግሞ የሴትን ቦታ ይዞ የቤተክርስቲያንን መቆምና በእግዚአብሔር መንፈስ መጠንከር ሊያበረታ(ሊረዳ) ቢቆም ከተፈጠረበት ዓላማ ውጪ ስለሚሆንና ይህን ሊያደርግ የሚችል ፀጋ እርሱ ጋር ስለሌለ የእግዚአብሔር መንፈስ ከእርሱ ጋር አይሆንም ረዳትም አይኖረውም። (1ጢሞ2-:-8-15,ዘፍ3-:-16,ቲቶ1-:-5-8,1ቆሮ14-:-34-38)
ጌታ ይባርካችው !!!!
ጥያቄና አስተያየት 👇👇👇👇👇
👇👇👇👇👇
👉@Addishiwet
👉@Addishiwet
👉@Addishiwet
👉@Addishiwet
👉@Addishiwet
👉@Addishiwet
👆👆👆👆👆
👆👆👆👆👆