ስድስት ተጨማሪ ሰዎች የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው ተረጋግጧል፡፡
____
ባለፉት 24 ሰዓት የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 74 ሰዎች ውስጥ 6 ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ ሲሆን ይህም በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር 35 ደርሷል፡፡
በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጡት ውስጥ አምስቱ ከአዲስ አበባ ሲሆን አንድ ከድሬዳዋ ነው።
በአዲስ አበባ ከተያዙት ውስጥ ሁለቱ የጉዞ ታሪክ ያላቸው ሲሆን የመጀመሪያው የ35 ዓመት ወንድ መጋቢት 10 ቀን 2012 ዓ.ም ከዱባይ የመጣ ነው፡፡
ሁለተኛው የ30 ዓመት ወንድ በተመሳሳይ ከዱባይ መጋቢት 8 ቀን 2012 ዓ.ም የመጣ መሆኑን ገልጸዋል።
ሁለቱም አስገዳጅ የለይቶ ማቆያ ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት የገቡ ናቸው።
ሶስተኛው የ28 ዓመት ወንድ፤ አራተኛውም የ56 ዓመት ወንድ፣ አምስተኛው የ30 ዓመት ወንድ የጉዞ ታሪክ የሌላቸው ናቸው።እነዚህ ሰዎች ያላቸው ግንኙነት እየተጣራ ይገኛል፡፡
ስድስተኛዋ ሰው የ33 ዓመት ሴት ስትሆን በድሬዳዋ ከዚህ በፊት በኮሮናቫይረስ መያዙ ከተገለጸው ሰው ጋር ግንኙነት የነበራት መሆኑ ታውቋል።
Watch ""አዲስ ድባብ" ድራማ ክፍል 3 / Addis Debab Ethiopian Sitcom Drama Part 3" on YouTube
https://youtu.be/FrfYZrigwpQ
ተወዳጁ ተዋናይ ሳምሶን ታደሠ (ቤቢ) ስለ አዲስ ድባብ እና ወቅታዊ ጉዳይ ስለሆነው COVID 19 ከ EthioInfo ጋር የነበረው ቆይታ!!!
Читать полностью…