አሐዱ ራድዮ 94.3 Your source for top local and international news and analysis. "Voice of Ethiopian" የአሐዱ የቴሌግራም ቻናል ቤተሰብ በመሆን ወቅታዊና እውነተኛ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ
ፓስፖርት ለማውጣት "የአምስት ሺሕ ብር ሲስተም የለም" እየተባልን ነው ሲሉ ተገልጋዮች ቅሬታ አቀረቡ
ጥቅምት 15/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት 20 ሺሕ እና 25 ሺሕ ብር ከሚያስከፍሉት የአስቸኳይ አገልግሎቶች በስተቀር በመደበኛ ከፍያ እያስተናገደን አይደለም ሲሉ ተጋልጋዮች ቅሬታቸውን ለአሐዱ አቅርበዋል፡፡
ቅሬታ አቅራቢዎቹ፤ "5 ሺሕ ብር ከፍለን በመደበኛው ጊዜ ፓስፖርታችንን መውሰድ አልቻልንም" ያሉ ሲሆን፤ "ለዚህም የሚሰጠን ምክንያት ‹‹ሲስተሙ አይሰራም›› የሚል ነው" ብለዋል፡፡
አክለውም "የፓስፖርት አገልግሎት ክፍያውን መምረጥ ያለበት ተጠቃሚው ነው፡፡" ያሉ ሲሆን፤ "በ2 ቀን እንዲደርስላችሁ 25 ሺሕ ብር በ10 ቀን እንዲደርስላችሁ ደግሞ 20 ሺሕ ብር ክፈሉ መባላችን ትክክል አይደለም፡፡ በመረጥነው ክፍያ ልንስተናገድ ይገባል" ሲሉ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ አዲስ የማክሮ ኢኮኖሚይ ማሻሻ ማድረጓን ተከትሎ፤ የክፍያ መሻሻሎች ካደረጉ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች መካከል አንዱ፤ የኢትዮጵያ ኤምግሬሽን የዜግነት አገልግሎት መሆኑ ይታወቃል።
የኢምግሬሽን የዜግነት አገልግሎት ለዜጎች ፓስፖርት ለመስጠት ሲል የክፍያ እና የጊዜ ቀነ ገደብም አስቀምጧል፡፡
ዜጎች በሁለት ወራት ውስጥ ፓስፖርት ለማግኘት ዝቅተኛው ክፍያ አምስት ሺሕ ብር መሆኑን አገልግሎቱ በወቅቱ ያሳወቀ ቢሆንም፤ ተገልጋዮች "አምስት ሺሕ ብር ከፍሎ ፓስፖርት የማግኘት ሲስተም ለጊዜው የለም እየተባለን እየተመለስን ነው" ሲሉ ተናግረዋል።
ሌላኛው ሥማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ተገልጋይ በበኩላቸው፤ "የፓስፖርት አገልግሎት ለማግኘት ወደ ኢምግሬሽን የዜግነት አገልግሎት የሄድን ቢሆንም፤ ከመጉላለት በዘለለ በፓስፖርት ወረፋ ወቅት ያለው ወከባ እና ግርግር ለደህንነታችን አስግቶናል" ብለዋል፡፡
አሐዱ "ለአስቸኳይ ከፍተኛ ከፋዮች የሚሰራው ሲስተም ለዝቅተኛ ከፋዮች የማይሰራበት ምክንያት ግልጽ አይደለም" የሚለውን የተገልጋዮች ቅሬታ በመያዝ ከኢትዮጵያ የኢምግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ምላሽ ለማግኘት በተደጋጋሚ ያደረገው ሙከራ፤ የአገልግሎቱ የሥራ ሃላፊዎች ስልክ ባለማንሳታቸው እንዲሁም አንስተው "ጉዳዩ አይመለከተንም" በማለታቸው ምክንያት ምላሹን ማካተት አልቻለም፡፡
ተቋሙ ለቅሬታው ምላሽ በሚሰጥበት ጊዜ ግን ምላሹን ይዘን እንቀርባለን፡፡
በደረጄ መንግሥቱ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ርዕሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደ ለ34 የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ሹመት ሰጡ
ጥቅምት 15/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደ፤ ለ34 የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ሹመት ሰጥተዋል።
በዚህ መሠረት፦
1. አማኑኤል ፈረደ አያሌው (ዶ.ር) በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የአብክመ ርእሰ መሥተዳደር ልዩ አማካሪ
2. መስፍን አበጀ ተፈራ (ዶ.ር) - በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የርእሰ መሥተዳደሩ የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ አማካሪ
3. ወ/ሮ መሰሉ ብርሃኑ ካሳው - የአብክመ ቆላና መስኖ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ
4. አቶ ደረጀ ማንደፍሮ ዳመነ - የአብክመ ግብርና ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ
5. አቶ ፈንታሁን ስጦታው ፈለቀ - በምክትል ቢሮ ኃላፊ ደረጃ የአብክመ ግብርና ጥራትና ደህንነት ባለስልጣን ኃላፊ
6. አቶ ደምስ እንድሪስ ይማም - የአብክመ ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ
7. አቶ ጥላሁን ፈንታው ተሾመ - የአብክመ ፕላን ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ
8. ወ/ሮ ትብለጥ መንገሻ አማረ - የአብክመ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ
9. አቶ ሙሉነህ ዘበነ ሳህሌ - የአብክመ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ
10. ወ/ሮ አትክልት አሳቤ ታምሩ - የአብክመ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ
11. አቶ ዘላለም አረጋ መኮነን - የአብክመ ወጣትና ስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ
12. ወ/ሮ ሃናን ይመር አሊ - በምክትል ቢሮ ኃላፊ ደረጃ የአብክመ ሴ/ህ/ማ/ጉ ቢሮ ረዳት አማካሪ
13. አቶ አባይነህ ጌጡ ያሬድ - በምክትል ቢሮ ኃላፊ ደረጃ የህዳሴ ግድብ ማስተባባሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ
14. አቶ አታላይ ክብረት ማሩ - በኤጀንሲ ኃላፊ ደረጃ የርዕሰ መስተዳደር ጽ/ቤት የክልል ተቋማት ክትትል አማካሪ
15. አቶ ይርጋ አላምነህ ወርቅነህ - በምክትል ቢሮ ኃላፊ ደረጃ የርዕሰ መስተዳደር ጽ/ቤት የኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ረዳት አማካሪ
16. ወ/ሮ ውዴ እውነቱ አዳምነው - በምክትል ኤጀንሲ ኃላፊ ደረጃ የካቢኔ ሴክረታሪያት ኃላፊ
17. አቶ ዳዊት አቡ አለሙ - የጣና ሐይቅና ሌሎች ውሃ አካላት ጥበቃና ልማት ኤጀንሲ ምክትል ኃላፊ
18. አቶ ወርቁ ኃ/ማርያም ጌጡ - የአብክመ በየነ መንግስታት ግንኙነት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ
19. አቶ ዮናስ ይትባረክ አበበ - በምክትል ቢሮ ኃላፊ ደረጃ የአማራ ሆቴሎችና ሪዞርቶች ልማትና ማስፋፊያ ድርጅት ስራ አስኪያጅ
20. አቶ ፋሲል ሰንደቁ አደመ - በም/አስተዳዳሪ ማዕረግ የማዕከላዊ ጎንደር ዞን አስተዳደር የህዝብ ግንኙነት እና አደረጃጀት ዋና አማካሪ
21. አቶ ሙሉጌታ ንጋቱ ለገሰ - የማዕከላዊ ጎንደር ዞን አስተዳደር ዉሃና ኢነርጂ መምሪያ ኃላፊ
22.አቶ ስጦታው ሰጤ ነጋሽ - የማዕከላዊ ጎንደር ዞን አስተዳደር ገቢዎች መምሪያ ኃላፊ
23. ወ/ሮ ካሳየ ስመኝ ዋሴ - የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ደንና አካባቢ ጥበቃ ተጠሪ ጽ/ቤት ኃላፊ
24. አቶ ሙሉጌታ አለም አድገህ - የምዕ/ጎጃም ዞን አስተዳደር ሰላም እና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ
25. አቶ አግማስ አንተነህ ውቤ - የምዕ/ጎጃም ዞን አስተዳደር ምክትል አስተዳዳሪና ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ
26. አቶ መንግስቱ አየለ ደምለዉ - የሰሜን ጎጃም ዞን አስተዳደር መንገድና ትራንስፖርት መምሪያ ኃላፊ
27. አቶ ስጦታው መርሻ አጆነህ - የሰሜን ጎጃም ዞን አስተዳደር ማዕድን መምሪያ ኃላፊ
28. አቶ ንብረት አበጀ አለሙ - የሰሜን ጎጃም ዞን አስተዳደር ስራና ስልጠና መምሪያ ኃላፊ
29. አቶ ዘውዱ ላቀው ሞገስ - በም/አስተዳደሪ ማዕረግ ለሰሜን ጎጃም ዞን አስተዳደር ኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር አማካሪ
30. ወ/ሮ የሽወርቅ ድረስ ተሰማ - የሰሜን ጎጃም ዞን አስተዳደር ትምህርት መምሪያ ምክትል ኃላፊ
31. ወ/ሮ ፀሐይነሽ ተፈራ በላይነህ - የሰሜን ጎጃም ዞን አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ መምሪያ ምክትል ኃላፊ
32. አቶ ዘነበ ሀይሉ ተ/ፃዲቅ - የሰሜን ሽዋ ዞን አስተዳደር ህብረት ስራ ማህበራት ተጠሪ ጽ/ቤት ኃላፊ
33. ወ/ሮ ተዋባች ጌታቸው ዘዉዴ - የሰሜን ሽዋ ዞን አስተዳደር ዞን ባህል ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ
34. አቶ ዋሲሁን ብርሀኑ ሰብስቤ - የሰሜን ሽዋ ዞን አስተዳደር ዞን ትምህርት መምሪያ ምክትል ኃላፊ በመሆን መሾማቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡
ተሿሚዎች በተለያዩ የመንግሥት የሥራ ኃላፊነቶች የሠሩ ሲሆን የላቀ ዕውቀት፣ ብቃት፣ ቁርጠኝነት እና ታታሪነት ያላቸው ስለመሆኑም ተገልጿል።
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
በአማራ ክልል አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ 13 ዳኞች መታሰራቸው ተገለጸ
👉 ሦስት ዳኞች በታጣቂ ሃይሎች መገደላቸውም ተነግሯል
ጥቅምት 15/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በአማራ ክልል ከመስከረም 26 ጀምሮ እስከ አሁን ባለው መረጃ 13 የፍርድ ቤት ዳኞች ባልታወቀ ምክንያት መታሰራቸውን የክልሉ ዳኞች ማህበር ፕሬዝዳንት ብርሃኑ አሰፋ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
ማህበሩ በክልሉ የሚካሄደው የዳኞች ጅምላ እስር እንዳሳሰበው የገለጹ ሲሆን፤ በባህርዳር ከተማ በአንድ ቀን ብቻ አራት ዳኞች እንደታሰሩ ተናግረዋል፡፡
ይህ አካሄድ በዚህ ከቀጠለ በሌሎች ዳኞች ላይም ከፍተኛ ስጋት የሚፈጥር መሆኑንም የማህበሩ ፕሬዝዳንት ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪም "ይህ አካሄድ የዳኝነት ነጻነትን የሚጥስ ነው" ያሉ ሲሆን፤ "የታሰሩ ዳኞች እንዲፈቱና ነጻነታቸው እንዲከበር በተደጋጋሚ ለሚመለከተው አካል ጥያቄ ብናቀርብም ምላሽ አላገኘንም" ብለዋል፡፡
በክልሉ ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ አሁን በተደረገው ጥናት መሰረት፤ የትኛው ታጣቂ ሃይል እንደገደላቸው ሳይታወቅ ሦስት ዳኞች መገደላቸውንም ፕሬዝዳንቱ አመላክተዋል፡፡
በዚህም "የምዕራብ ጎጃም ደንበጫ ወረዳ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ በቤታቸው በተኙበት በጥይት የተገደሉ ሲሆን፤ የቡሬ ወረዳ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛም በቤታቸው ላይ በተጣለ ከባድ መሳሪያ ከነልጆቻቸው ተገድለዋል" ብለዋል፡፡
እንዲሁም "የደሴ ከተማ አስተዳደር ወረዳ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት በመኪናቸው ላይ በተጣለ ቦንብ ሕይወታቸውን ያጡ ናቸው" ሲሉ፤ የአማራ ክልል ዳኞች ማህበር ፕሬዝዳንት ብርሃኑ አሰፋ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
በዚህም በክልሉ የሚካሄደው አፋና፣ እስርና እንግልት መቆም እንዳለበትና የዳኞች ነጻነትና የዳኝነት ስርአቱ ሊከበር እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡
በአለምነው ሹሙ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
በኢትዮጵያ በዓመት ከ5 ሺሕ 900 በላይ ሴቶች በማህፀን በር ካንሰር ምክንያት እንደሚሞቱ ተገለጸ
ጥቅምት 15/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ በዓመት ከ5 ሺሕ 900 በላይ ሴቶች በማህፀን በር ካንሰር ምክንያት እንደሚሞቱ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
አሁን ባለው ሁኔታ የማህፀን በር ካንሰር ቅድመ ምርመራ 20 በመቶ ብቻ መሆኑን የገለጸው ሚኒስቴሩ፤ በ2030 ቅድመ ምርመራውን 70 በመቶ ለማድረስ እየተሰራ እንደሚገኝም ገልጿል።
በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር መሪ ሥራ አስፈፃሚ ሲስተር ታከለች ሞገስ፤ በአሁን ሰዓት ይህንን አገልግሎት የሚሰጡ 1 ሺሕ 500 የሕክምና ተቋማት ብቻ መኖራቸውን ለአሐዱ ተናግረዋል።
ሲሰተር ታከለች "አሁን ያለውን 20 በመቶ የቅድመ ምርመራ በቀሩት 6 ዓመታት በ2030 ወደ 70 በመቶ ለማድረስ እየተሰራ ነው" ብለዋል።
በማህፀን በር ካንሰር የበርካታ እናቶች ሕይወት እየቀጠፈ ሲሆን፤ በየዓመቱ ቁጥራቸው 8 ሺሕ 168 የሚጠጋ እናቶች በበሽታው እንደሚያዙም ተናግረዋል።
በበሽታው ከተያዙት ሴቶች መካከልም ከ5 ሺሕ 975 በላይ የሚሆኑት ሕይወታቸውን እንደሚያጡ መሪ ሥራ አስፈፃሚዋ አስረድተዋል።
የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር በኢትዮጵያ ከጡት ካንሰር ቀጠሎ ሁለተኛው የእናቶች ገዳይ በሽታ ነው።
እ.ኤ.አ በ2020 በተደረገ ጥናትም፤ በኢትዮጵያ ከ3 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ከ15 ዓመት በላይ የሆናቸው ሴቶች ለማህፀን በር ካንሰር ተጋላጭ መሆናቸው ተገልጿል።
ጤና ሚኒስቴር የማህፀን በር ካንሰርን ለማጥፋት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝም አስታውቋል።
በአቤል ደጀኔ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
በኢትዮጵያ ሕገ-ወጥ የሕጻናት ዝውውር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱ ተነገረ
ጥቅምት 14/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ ሕገ-ወጥ የሕጻናት ዝውውር እየጨመረ መምጣቱ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ሚኒስቴሩ ይህንን ያለው ከደቡብ የአገሪቱ ክፍል ወደ መሐል አገር የሚደረገውን የሕጻናት ፍልሰት እየተበራከተ መምጣቱን ተከትሎ ያስጠናውን ጥናት መሰረት አድርጎ ነው፡፡
በጥናቱ እንዳመለከተው ወደመሀል ከተማ የሚፈልሱ ሕጻናት ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን ለአሐዱ የተናገሩት በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሕገ-ወጥ የሕጻናት ዝውውር ቁጥጥር ኃላፊ አቶ በለጠ ሰውአለ ናቸው፡፡
ኃላፊው እሕጻናቱ የሚፈልሱበት ምክንያት ሲያስረዱ፤ ዋነኛው በክልልሉ እየተባባባሰ የመጣውን ድህነትና ሥራ ማጣት መሆኑን ይገልጻሉ።
ከዚህ በተጨማሪም በደቡብ ክልል የተዘረጋ ሕገ-ወጥ የደላሎች መስመር መኖሩን ጠቅሰው፤ የችግሩ ስፋት አስረድተዋል።
ይሁንና መንግሥት ይህንኑ እንቅስቃሴ ለመግታት ክልሎችን ጨምሮ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍል የሚገኙ ሕጻናት ፍልሰታ ላይ የሚሰሩ ተቋማትን እየመከረበት መሆኑን ኃላፊው በለጠ ሰውአለ ለአሐዱ ገልጸዋል።
ኃላፊው አክለውም፤ የሕጻናት ዝውውርን ለመቆጣጠር በአገራቀፍ ደረጃ መመርያ ወጥቶለት ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴዎችን እየተደረጉ ቢሆንም በአፈፃፀሙ ረገድ ክፍተቶችን መኖራቸውን ነግረውናል።
በተያዘው በጀት ዓመትም የሚኒስቴር መስርያቤቱ የትኩረት አቅጣጫዎች መካከል አንዱ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ይሁንና ከደቡብ ኢትዮጵያ ክፍል የሚፈልሱና ለሕገወጥ ስደት ሰለባ የሆኑ ሕፃናት ቁጥር እያሻቀበ መምጣቱን ከተለያዩ ተራድኦ ተቋማት የተገኘውን መረጃ ጠቅሰው ሐላፊው ለአሐዱ ገልፀዋል።
ደቡብ ኢትዮጵያ የአገሪቱ ክፍልን ጨምሮ ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚነሱ ህፃናት መዳረሻቸው አዲስአበባ እንደሚያደርጉም ከሚኒስቴር መስርያ ቤቱ ያገኘነውን መረጃ ተመልክተናል ።
ይህንኑ ችግር ለመፍታት በሚልም
በቅርቡም የአዲስአበባ ከተማ መስተዳድር ከተለያዩ ክልሎች ጋር በህፃናት ፍልሰት ዙርያ ምክክር መድረኮችን ሲደረግ መቆየቱ የሚታወስ ነው።
በርከት ያሉ መረጃዎች እንደሚያሳዮት ከሆነም
ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎ ወደ አዲስ አበባ የሚጎርፉ ህፃናትን በርካታ ሲሆኑ ኑሯቸውን በጎዳና ያደረጉ ህፃናት ቁጥር ከ60 ሺ እንደሚበልጥ ተገልጿል።
በርካቶቹ ወላጅ አልባ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ባስጠናው አንድ ጥናት ላይ ተጠቅሷል።
በአማኑኤል ክንደያ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
የ2017 ዓ. ም የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ተደረገ
ጥቅምት 14/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው በመደበኛው ፕሮግራም ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ተደርጓል።
ተማሪዎች ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ምደባውን ማየት የሚችሉ መሆኑም ተገልጿል።
በተጨማሪም ትምህርት ሚኒስቴር የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄዎችን የማያስተናግድ መሆኑን አስታውቋል።
የምደባ ተቋም ለማየት የቀረቡ አማራጮች👇
lWEBSITE:
https://placement.ethernet.edu.et
TELEGRAM
/channel/moestudentbot
Via_atc
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
መንግሥት በዶሮ መኖ ላይ የጣለው ተጨማሪ እሴት ታክስ የውጭ ኩባንያዎች ከገበያው እንዲወጡ እያደረገ ነው ተባለ
ጥቅምት 14/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) መንግሥት በቅርቡ ከውጭ የሚገቡ የተቀነባበሩ የዶሮ መኖዎች ላይ በጣለው ተጨማሪ እሴት ታክስ የተነሳ፤ በኔዘርላንድ ያሉ የዶሮ መኖ አቅራቢያ ድርጅቶች ከገበያ እየወጡ መሆናቸውን አንድ የኔዘርላንድ ኩባንያ ለአሐዱ ተናግሯል።
ትሮው ኒውትሮን የተሰኘው ይኸው የዶሮ መኖ አቅራቢ የኔዘርላንድስ ኩባንያ፤ ውሳኔውን ተከትሎ ወደ ኢትዮጵያ የሚልካቸው ምርቶቹን መቀነሱን ገልጿል።
በትሮው ኒውትሮን ኩባንያ የመኖ ገበያ ጥናትና ሽያጭ ሐላፊ ዶክተር ደመቀ ወንድማገኝ ለአሐዱ እንደነገሩት፤ መንግሥት አደረኩት ባለው ማሻሻያ መሰረት የተቀነባበሩ የዶሮ መኖዎች ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ መጣሉን ተከትሎ በኔዘርላንድ መሰረታቸውን ያደረጉ ላኪዎች ላይ ተፅእኖ መፍጠሩን ጠቁመዋል።
ከዚህ ቀደም በርካታ የኔዘርላንድስ ኩባንያዎቹ ለኢትዮጵያ ገበያ የተቀነባበረ የዶሮ መኖ ሲያቀርቡ የቆዩ ሲሆን፤ አሁን ላይ ገበያቸውን እየቀየሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በዚህ ዙርያ የኔዘርላንድስ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጋር ውሳኔው ማሻሻያ እንዲደረግበት ጥያቄ እያቀረቡ መሆኑን ገልጸው፤ ገበያው በእጅጉ መቀዛቀዙን ኃላፊው ለአሐዱ ገልጸዋል።
ይህም በኢትዮጵያ ያለውን የእንስሳት መኖ አቅርቦት ችግር የሚባብስ ሲሆን ዘርፉንም በእጅጉ እየጎዳው መሆኑ ተነግሯል።
ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ የዶሮ መኖ የሚልኩ ኩባንያዎችን ስታፈላልግ እንደነበር የሚታወስ ነው።
በአማኑዔል ክንደያ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
#UPDATE
ያለበቂ ምክንያት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳልሰጥ ታግጃለው ሲል የንጋት ኮከብ ለኢትዮጵያ ፓርቲ አስታወቀ
ጥቅምት 14/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ፓርቲው የንጋት ኮከብ ለኢትዮጵያ በሚል ጊዚያዊ ስያሜ ከምርጫ ቦርድ ያገኘውን ቅድመ እውቅና በማስመልከትና ቀጣይ የትግል አቅጣጫዎቻችን በይፋ ለማሳወቅ በትናንትናው ዕለት ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት ጥሪ ማቅረቡን ገልጿል፡፡
ይሁን እንጂ ለመንግሥትና ለግል መገናኛ ብዙሃን ይፋዊ ጥሪ በማድረግ በዋቢ ሸበሌ ሆቴል መግለጫ ለመስጠት በተዘጋጀንበት ወቅት ያለበቂ ምክንያት በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳይሰጥ ክልክላ ተደርጎብኛል ሲል ፓርቲው ለአሐዱ ጠቁሟል፡፡
አሐዱ በጉዳዩ ላይ ያነጋገራቸው የፓርቲው የዶክመንት ዝግጅት ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ቸርነት ሰዒድ፤ የቅድመ ፖርቲ ምስረታ መግለጫ ለመስጠት ፓርቲው ጥሪ ቢያደርግም መከልከሉን ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም መግለጫው ይሰጥበታል ለተባለው ዋቢ ሸበሌ ሆቴል ከመንግሥት አካል የደረሰው ደብዳቤ አለመኖሩን የጠቆሙ ሲሆን፤ ̎ከደህንነት መስሪያ ቤት ነው የመጣሁ̎ በሚል ግለሰብ ሳይካሄድ መቅረቱን ለአሐዱ ገልጸዋል፡፡
ፓርቲው ከ50 ሰው በታች ከሆነ የሚሰብሰብው ፍቃድ እንደማያስፈልገው ከሆቴሉ ጋር በተደረገ ውይይት የተገለጸለት መሆኑን ያነሳ ሲሆን፤ ̎በስፍራው ግን ተቃራኒው ገጥሞኛል̎ ብሏል፡፡
የቅድመ ዕውቅና ሰርተፍኬቱን ይዘው የመጡ መሆኑን የገለጸት ቡድን መሪው፤ ̎የፀጥታ አካላት ናቸው̎ የተባሉት ግለሰቦች ይህንን ሳይፈቅዱ ቀርተዋል ብለዋል፡፡
"እንዲህ አይነቱ ሁኔታ መከሰቱ በቀጣይ ትግላችሁ ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ ይኖረው ይሆን?" ሲል አሐዱ ፓርቲውን ጠይቋል፡፡
"የኢትዮጵያ ሰላማዊ ትግል ሰፊ አፈና ከጊዜ ወደ ጊዜ ወደቁልቁለት እየተንደረደረ ቢገኝም ለሀገር አንድነት፣ ሕዝባችን የተነፈገውን መሠረታዊ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ መብቶች ለማስከበር የጋራ ትግል ለማድረግ ቁርጠኛ ነን" ሲሉም አቶ ቸርነት አክለው ተናግረዋል፡፡
በአቤል ደጀኔ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
የኢትዮጵያ እና ሩሲያ የሁለትዮሽ ግንኙነት እያደገ መቀጠሉን ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ገለጹ
ጥቅምት 14/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ እና ሩሲያ ታሪካዊ ቁርኝት ላይ የተመሠረተው የሁለትዮሽ ግንኙነት እያደገ ቀጥሏል ሲሉ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገልጸዋል፡፡
ከ16ኛዉ የብሪክስ አገራት የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን፤ ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በሁለትዮሽ መድረክ ውይይት አካሂደዋል፡፡
ውይይቱን አስመልክቶም ጠ/ሚ ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ "በሁለትዮሽ መድረካችን ወቅት ላደረግነው ጥልቅ ውይይት ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንን አመሰግናለሁ" ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሁለቱ ሀገራት ታሪካዊ ቁርኝት ላይ የተመሠረተው የሁለትዮሽ ግንኙነት እያደገ መቀጠሉንም አመላክተዋል፡፡
በተጨማሪም የጋራ የሆነው የብሪክስ መድረክ ሰፋ ላለ የኢኮኖሚ ትብብር እንድንሰራ በር ከፍቶልናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ ለመጀመርያ ጊዜ እንደ አባል ሀገር በምትሳተፍበት በ16ኛው የብሪክስ (BRICS) የመሪዎች ጉባኤ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እየተሳተፉ የሚገኝ ሲሆን፤ ከጉባዔው በተጨማሪ ከተለያዩ ሀገራት መሪዎች ጋር ውይይት በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡
በዚህም ከኢራኑ ፕሬዚዳንት መስዑድ ፔዥሺካን፣ ከደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ እንዲሁም ከዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ ፕሬዝዳንት መሃመድ ዛይድ አልናህያን ጋር በሁለትዮሽ ግንኙነት ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና እየተጠቀመች አይደለም ተባለ
ጥቅምት 14/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና ኢትዮጵያ ፈርማ እየተንቀሳቀሰች ቢሆንም እስካሁንም ምንም ዓይነት ምርት መላክ አለመጀመሯን የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ወንድምአገኘሁ ነገራ ገልጸዋል፡፡
"አፍሪካውያን እርስ በእርስ የንግድ ልውውጥ ማድረግ መጀመር ይኖርባቸዋል" ሲሉ አንስተው፤ "ከተወሰኑ የአፍሪካ ሀገራት ጋር ከምናደርገው የንግድ ልውውጥ ውጪ በአብዛኛው ግብይቶች ከሌሎች የአለም ሀገራት ጋር በመሆኑ ተጠቃሚነቱ ግዜ የሚወስድ ነው" ብለዋል፡፡
ዋና ሥራ አስፈፃሚው ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና በተጨማሪ የዓለም የንግድ ድርጅት አባል ሀገር እንድትሆን ለማድረግ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ጥረት እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
ነፃ የንግድ ቀጠናው የ3 ነጥብ 4 ትሪሊዮን ዶላር ዓመታዊ ምርት ድርሻ ይኖረዋል ተብሎ የተቋቋመ ሲሆን፤ ለ1.3 ቢሊዮን ሕዝብ መገበያያ ይሆናል ተብሏል፡፡
ምርት ገበያው ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ወንድምአገኘሁ የአፍሪካ ሀገራት እርስ በርስ ለመገበያየት እንዲረዳን መገበያያ ዘዴዎች እየተፈጠሩ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
የአፍሪካ ሕብረት በመጋቢት ወር 2010 ዓ.ም በሩዋንዳ በተካሄደ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ነበር የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና ስምምነት የተፈረመው፡፡
ከ55 የህብረቱ ሀገራት ውስጥ 44 ሀገራት ፊርማ የተቋቋመው ይህ የንግድ ቀጠና አሁን ላይ ከኤርትራ ውጪ ሁሉም የአፍሪካ ሀገራት ፈርመውታል፡፡
አሁን ላይ ከ15 በመቶ በታች የሆነውን የአፍሪካ አገራት የእርስ በእርስ የንግድ ልውውጥ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2040 ከ15 እስከ 25 በመቶ እንደሚያሳድገው የመንግሥታቱ ድርጅት የአፍሪካ የኢኮኖሚ ኮሚሽን (ኢ.ሲ.ኤ) ባወጣው መረጃ አመላክቷል።
የንግድ ቀጠናው በተለያየ መንገድ ዘግይቶ በ2021 ዓ.ም ይጀመራል ተብሎ የተጠበቀ ቢሆንም፤ በኮሮናና በሌሎች ጉዳዮች አሁንም ድረስ ሳይተገበር ቆይቷል፡፡
በአቤል ደጀኔ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
#የአሐዱ_ዕለታዊ_ዜናዎች!
ዜናዎቹን ለመከታተል ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👇
https://youtu.be/99KH0NnLghw?si=KvysF5AULnWt42H2
#አሐዱ_ትንታኔ
ትንታኔውን ለመከታተል ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👇
https://youtu.be/jtzD6HXCQhY?si=fZv5pit9-oWWjF-r
በቻን የማጣሪያ ጨዋታ ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር የምታደርጋቸው የደርሶ መልስ ጨዋታዎች በደቡብ ሱዳን ጁባ ይከናወናሉ
👉አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋሊያዎቹ) ጊዜያዊ ዋና አሰልጣኝ ሆኗል
ጥቅምት 13/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ (ቻን) ማጣርያ ኢትዮጵያ ከ ኤርትራ ጋር የምታደርጋቸው የደርሶ መልስ ጨዋታዎች በደቡብ ሱዳን ጁባ ብሔራዊ ስታዲየም የሚከናወኑ ሲሆን የጨዋታ ቀኖቹ ላይም ለውጥ መደረጉ ተነግሯል፡፡
በዚህም ጥቅምት 21 ቀን 2017 እና ጥቅምት 24 ቀን 2017 የሁለቱ ሀገራት የደርሶ መልስ ጨዋታ እንደሚከናወን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ ማጣርያ የሚያደርጋቸው ጨዋታዎችን በአሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ጊዜያዊ ዋና አሰልጣኝነት እየተመራ እንዲያከናውን የፌደሬሽኑ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ወስኗል፡፡
አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ላለፉት 12 ወራት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ምክትል አሰልጣኝ ሆኖ አገልግሏል።
ከዚሁ ጋር ተያያዞም አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከኤርትራ ጋር ለሚያከናውናቸው የቻን ማጣሪያ ጨዋታዎች ዝግጅት ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ አቅርቧል፡፡
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ተሳፋሪዎች ጥቆማዎችን ባለመስጠታቸው አለአግባብ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ አሽከርካሪዎችን ለመቆጣጠር አስቸጋሪ መሆኑ ተነገረ
ጥቅምት 13/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ሰሞኑን ተግባራዊ ከተደረገው የነዳጅ ዋጋ ማሻሻያ ጋር ተያይዞ አለአግባብ የዋጋ ጭማሪ ስለሚያደርጉ አሽከርካሪዎች ተሳፋሪዎች ጥቆማዎችን ባለመስጠታቸው፤ ጉዳዩን ለመቆጣጠር አስቸጋሪ መሆኑ የትራንስፖርትና ሎጀስቲክ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
በሚኒስቴሩ የላምበረት ተርሚናል ተወካይ ኃላፊ የሆኑት አቶ አረጋ አዲስ ለአሐዱ እንደተናገሩት፤ ሰሞኑን የነዳጅ ዋጋ ማሻሻያ ጋር በተያያዘ ሀገር አቋራጭ ተሸከርካሪዎች የትራንስፖርት የዋጋ ጭማሪ ተደርጓል፡፡
ከዚህም ጋር በተያያዘ አላግባብ የታሪፍ ጭማሪ በማድረግ ተሳፋሪዎችን ለከፋ ችግር የሚያጋልጡ አሽከርካሪዎች መኖራቸውን ገልጸዋል።
ይህንንም ሕገ-ወጥ አሰራር ለመቆጣጠር የተሳፋሪው መረጃ አለመሰጠትና ለተቆጣጣሪ ሰራተኞች እገዛ አለማድረግ ቁጥጥሩን አስቸጋሪ ማድረጉን ጠቁመዋል።
የዋጋ ጭማሪ አድርገዋል ተብለው ለስምሪት ባለሙያዎች ጥቆማዎች ደርሰው ባለሙያዎች የማጣራት ሥራን በሚሰሩበት ወቅት፤ ተሳፋሪው ጭማሪ መደረጉን ከመናገር መቆጠቡ ችግሩ እንዲስፋፋ በምክንያትነት ከሚጠቀሱ ጉዳዮች መካከል መሆኑንም አክለው አስረድተዋል፡፡
ኃላፊው አያይዘውም የላምበረት አሽከርካሪዎች ይህንን ሕገ-ወጥ ሥራ የሚያከናውኑት ከመናኸሪያ ወጥተው መሆኑን አውስተው፤ ችግሩን ለመቅረፍ ተሳፋሪው ጥቆማዎችን በመስጠት መቀረፍ እንደሚቻልም ነግረውናል።
"አሽከርካሪዎቹ ተጓዦች ወደሚፈልጉት መዳረሻ እንግልት ሳይገጥማቸው ተመጣጣኝ በሆነ ታሪፍ እንዲሄዱ ማድረግ ይገባቸዋል" ያሉ ሲሆን፤ ይህን በማያደርጉት ላይ ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር እንደሚደረግ አሳስበዋል፡፡
ሀገር አቋራጭ ተሸከርካሪዎች ከተቀመጠው ታሪፍ ዉጭ አላግባብ የዋጋ ጭማሪ አድርገው ሕብረተሰቡን ለከፋ ችግር እየዳረጉት እንደሚገኝ በተደጋጋሚ እየተገለጸ ይገኛል፡፡
በወልደሀዋርያት ዘነበ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
የንጋት ኮከብ ፓርቲ መግለጫ እንዳይካሄድ ተከለከለ
ጥቅምት 13/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በምርጫ ቦርድ ተመዝግቦ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ የሚገኘው አዲሱ የንጋት ኮከብ ለኢትዮጵያ ፓርቲ ዛሬ ማለዳ በዋቢሸበሌ ሆቴል ሊያካሂድ ያቀደው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳይካሄድ ተከልክሏል፡፡
በፓርቲው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ለመታደም በርካታ የሚዲያ አካላት የተገኙ ቢሆንም፤ የፓርቲው አመራሮች ጋዜጣዊ መግለጫውን ‹‹ከላይ በመጣ ትዕዛዝ ምክንያት›› ማካሄድ እንደማይችሉ ተናግረዋል፡፡
አሐዱም የፓርቲውን መግለጫ ለመዘገብ በቦታው ተገኝቶ የነበረ ሲሆን፤ የፓርቲው አመራሮች "የመንግሥት የደህንነት አካላት ጋዜጣዊ መግለጫውን እንዳንሰጥ ከልክለውናል" በማለታቸው መግለጫው መቋረጡን ለመታዘብ ችሏል፡፡ በቀጣይ የፓርቲውን አመራሮች በማናገር ዝርዝር መረጃዎችን ይዞ የሚቀርብ ይሆናል፡፡
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢ.ዜ.ማ) አመራር እና አባል የነበሩ ፖለቲከኞችን ጨምሮ ሌሎች አባላትን ያካተተው የንጋት ኮከብ ለኢትዮጵያ ፓርቲ፤ በቅርቡ የምርጫ ቦርድን እውቅና አግኝቶ የፖለቲካውን መድረክ የተቀላቀለ ፓርቲ መሆኑ ይታወቃል፡፡
በአቤል ደጀኔ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
የእንስሳት ክትባት የሚያመርቱ አራት የውጭ አገር ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ፋብሪካቸውን ሊተክሉ መሆኑን ተሰማ
ጥቅምት 15/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በቅርቡ የእንስሳት ክትባት የሚያመርቱ አራት የውጭ አገር ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ፋብሪካቸውን ሊተክሉ መሆኑን የግብርና ባለስልጣን አስታውቋል።
በኢትዮጵያ የሚስተዋለውን የእንስሳት ክትባት ችግር የተነሳ የእንስሳት ጤና አጠባበቅ ላይ ክፍተት ሲስተዋል መቆየቱን ባለስልጣኑ ተናግሯል።
ወደ ኢትዮጵያ ገብተው ክትባት ለማምረት የተስማሙት ኩባንያዎች፤ የችግሩን ስፋት ያጠቡታል የሚል እምነት እንዳለ በግብር ባለስልጣን የእንስሳት መድሀኒት ቁጥጥር ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር ሰለሞን ከበደ ለአሐዱ ተናግረዋል።
ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ደረጃ የእንስሳት ክትባት የሚያመርት ድርጅት የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእንሰሳት ጤና ጥበቃ ኢንሰቲትዩት ብቻ እንደነበር የገለጹት ኃላፊው፤ "የውጭ ኩባንያዎችን ወደ አገር ውስጥ እንዲገቡ መፈቀዱ ክፍተቱን መድፈን ያስችላል" ብለዋል።
ወደ ሀገር ይገባሉ የተባሉት ክትባት አምራች ኩባንያዎች የማምረተ አቅምና የጥራት ደረጃቸውን በተመለከተ ሰፊ ግምገማ ሲደረግለት መቆየቱን ዶክተር ሰለሞን አስታውሰዋል።
መንግሥት የያዘው የእንስሳት ጤና ጥበቃ እንቅስቃሴ አካል መሆኑን ኃላፊው ጨምረው ለአሐዱ ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ በብቸኝነት የእንስሳት ክትባት በማምረት የሚታወቀው የመንግሥት የልማት ድርጅት የሆነው ብሔራዊ የእንሰሳት ጤና ጥበቃ ኢንሰቲትዩት ሲሆን፤ የተቋቋመው በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ እንደነበር ይታወቃል።
በርካታ የውጭ ምንዛሪ ከሚጠይቁ የግብርና ምርቶች መካከል አንዱ የእንስሳት ክትባት ተጠቃሽ መሆኑን በግብርና ባለስልጣን የእንስሳት መድኃኒት ቁጥጥር ኃላፊው ከዶክተር ሰለሞን ለማወቅና ችለናል።
በአማኑኤል ክንደያ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
#UPDATE
አቶ ታዲዮስ ታንቱ በ6 ዓመት ከ3 ወራት ጽኑ እስራትና በገንዘብ ተቀጡ
ጥቅምት 15/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የጥላቻ ንግግር ማሰራጨት እና ግጭት መቀስቀስ ወንጀል የተከሰሱትን አቶ ታዲዮስ ታንቱ፤ በ6 ዓመት ከ3 ወራት ጽኑ እስራትና በገንዘብ እንዲቀጡ ተወስኖባቸዋል፡፡
የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ የህገ መንግስትና ሕገ-መንግሥታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት አቶ ታዲዮስ ታንቱን በተከሰሱበትና ጥፋተኝነት በተባሉባቸው 3 ክሶች አማካኝነት የጽኑ እስራትና የገንዘብ ቅጣት እንደተጣለባቸው ተመላክቷል፡፡
አቶ ታዲዮስ ታንቱ በሰኔ 20 ቀን 2014 ዓ.ም የጥላቻ ንግግር በማሰራጨት እና የእርስ በርስ ግጭት መቀስቀስ ወንጀል ፈጽመዋል ተብለው በፍትህ ሚኒስቴር በተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ዐቃቤ ሕግ በኩል ተደራራቢ አራት ክሶች ቀርቦባቸው እንደነበር ይታወሳል።
በአጠቃላይ ዐቃቤ ሕግ ባቀረበባቸው አራት ክሶች ላይ የተጠቀሱትን የወንጀል ድርጊት አለመፈጸማቸውን ገልጸው፤ የሰጡትን የዕምነት ክህደት ቃል ተከትሎ ዐቃቤ ሕግ ለወንጀሉ መፈጸም ያስረዳሉ ያላቸውን ምስክሮችን አቅርቦ አሰምቷል።
ፍርድ ቤቱም የዐቃቤ ሕግ ምስክርን መርምሮ እንዲከላከሉ በሙሉ ድምጽ ብይን መስጠቱ ይታወሳል።
አቶ ታዲዮስ እንዲከላከሉ በተሰጠ ብይን መነሻ የተለያዩ የመከላከያ ምስክሮችን አቅርበው አሰምተው የነበሩ ቢሆንም ባቀረቡት የመከላከያ ማስረጃ ግን የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን በተገቢው መከላከል (ማስተባበል) አለመቻላቸው ተገልጾ በ3 ክሶች የጥፋተኝነት ፍርድ ተላልፎባቸዋል።
ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኝ የቅጣት አስተያየትን ለመጠባበቅ ጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረ ቢሆንም፤ አቶ ታዲዮስ በዚህ ዕለት የቅጣት ማቅለያ ማቅረብ እንደማይፈልጉና የጥፋተኝነት ፍርዱን እንደማይቀበሉ ለችሎቱ አስታውቀው ነበር።
ይሁንና ፍርድ ቤቱ ግን የ6 ልጆች አባት መሆናቸውንና የ70 ዓመት አዛውንት መሆናቸውን ከግምት ውስጥ አስገብቶ ሁለት የቅጣት ማቅለያ በመያዝ፤ በዕርከን 24 መሰረት በ6 ዓመት ከ3 ወራት ጽኑ እስራትና በ20 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ወስኗል ሲል ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል፡፡
የአ/አ ማረሚያ ቤት ተከሳሹ ላይ የተጣለውን ቅጣት እጃቸው ከተያዘበት ጊዜ ጀምሮ ታሳቢ በማድረግ እንዲያስፈጽም ታዟል።
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
በባህልና በልማድ ተፅዕኖ ምክንያት የሴቶች የመሬት ባለቤትነት ሕግ የአተገባበር ክፍተት የሚስተዋልበት ነው ተባለ
ጥቅምት 15/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ሴቶች ከወንዶች እኩሌ የመሬት ባለቤትነታቸውን የሚያረጋግጥ የሕግ ሥርዓት ቢኖርም፤ አተገባበሩ በባህልና በልማድ ተፅዕኖ ሳቢያ በርካታ ክፍተቶች ይታዩበታል ተብሏል።
በዚህም የሴቶቸ የመሬት ባለቤትነት በተግባር እንረጋገጥ ሀቢታት ፎር ሂውማኒቲ የተባለው መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት፤ "ስታንድ ፎር ኸር ላንድ" በተሰኘ ፕሮግራም እየሠራበት መሆኑን ገልጿል።
"በተለይም ቀደም ሲል የነበረው የገጠር መሬት አስተዳደር አዋጅ የሴቶችን የመሬት ባለመብትነትን በግልጽ ያስቀመጠ አልነበረም" ያሉት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሕግ ትምህርት መምህር ዶ/ር መለሰ ዳምጤ ናቸው።
ሕጉ በግልጽና በተሻሻለ ሁኔታ ቢቀመጥም አሁንም መሬት ወርዶ የሴቶችን ተጠቃሚነት ያረጋገጠ አይደለም ብለዋል።
“ሀቢታት ፎር ሂውማኒቲ” በአንጻሩ "አዋጁ ተግባራዊ እንዳይሆን ያደረጉት የባህል እና የሕግ ልዩነቶች መኖር ነው" ብሏል፡፡
በዚህም "ማህበረሰቡ በተለምዶ የመሬት ውርስን በቅድሚያ ለወንዶች የሚሠጥ በመሆኑ የሴቶችን የባለቤትነት መብት የሚነፍግ ነው" ሲል አመላክቷል።
በተለይም በገጠር አካባቢ የሚኖሩ ሴቶች የመሬት ባለቤትነትና ተጠቃሚነት መብትን በተመለከተ ያላቸው እውቀት አናሳ መሆኑ ሌላው ምክንያት መሆኑ ተገልጿል።
በተጨማሪም ሴቶች በቂ ግንዛቤ እና እውቀት ኖራቸውም ሕጉ በተግባር ተፈጻሚ አለመደረጉ ሌላኛው የሚስተዋል ችግር ነው ተብሏል።
ስለሆነም የሴቶችን የመሬት ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ እኩል የመሬት ባለቤትነትና የውርስ መብቶችን ማረጋገጥና አድሎአዊ ሕጎችና አሰራሮችን ማስወገድ እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።
በፍርቱና ወልደአብ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
#አሐዱ_ትንታኔ
ትንታኔውን ለመከታተል ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👇
https://youtu.be/igf_R4LuKIM?si=Akf15DOVTpwnm8ES
አሰሪዎች የሚደርሱ አደጋዎች ለመከላከል የደህንነት ቁሳቁሶች የሟሟላት ግዴታ እንዳለባቸው ተገለጸ
ጥቅምት 14/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) አሰሪዎች በሥራ ቦታ ላይ ድንገተኛ አደጋዎች ሲከሰት ኃላፊነት እንዲወስዱ የሚያስገድድ ሕግ ቢኖርም፤ ተግባራዊ እየተደረገ አለመሆኑ ተገልጿል፡፡
ማንኛውም ተቋም ለሠራተኞቹ የሥራ ደህንነት የማስጠበቅ ኃላፊነት እንዳበት እና ሠራተኞችም በሥራ ቦታ ላይ የሚደርሱ አደጋዎች ለመከላከል የደህንነት ቁሳቁሶች የሟሟላት ግዴታ እንዳለባቸው አሐዱ ያነጋገራቸው የሕግ ባለሙያዎች ተናግረዋል፡፡
አሰሪዎች በሥራ ቦታ ላይ አደጋዎች እንዳይከሰቱ ቀድሞ ለመከላከል የሚረዱ ቁሳቁሶችን ለሠራተኛ የማቅረብ እንዲሁም ሊደርሱ የሚችሉ አደጋዎችን በቀዳሚነት የመከላከል ኃላፊነት እንዳለባቸው የሕግ ባለሙያ የሆኑት አቶ ሳሂብ መደድ ገልጸዋል፡፡
ባለሙያው አክለውም ̎በመጀመሪያ ሠራተኛው የድርጅቱ ወይን የቀጣሪው ግለሰብ ሠራተኛ ስለመሆኑ በሕግ ሊያቋቁም የሚችል ግንኙነት መመስረት አለበት̎ ያሉ ሲሆን፤ ያንን ግንኙነት ተከትሎ ለደረሰበት ጉዳትም ይሁን ሌሎች ተያያዥነት ያላቸው በሕግ የተቀመጡ ክፍያዎችን ሠራተኛው የመጠየቅ መብት እንዳለው አስረድተዋል፡፡
ለዚህም የደረሰው አደጋ በሥራ ቦታ ላይ ስለመሆኑ የሚረጋገጥበት አሰራር መኖሩን ገልጸው፤ የካሳ ክፍያ መጠኑ የሚወሰነውም ሠራተኛው በደረሰበት የጉዳት መጠን እና የደሞዙ መጠን ላይ ተመስርቶ ስለመሆኑ አክለዋል፡፡
በሥራ ቦታ ላይ የሚደርሱ አደጋዎችበን በተመለከ የሚቀርቡ ክርክሮች የተለመዱ መሆናቸውን የተናገሩት ደግሞ፤ የሕግ ባለሙያው ፍቃዱ መደድ ናቸው፡፡
የሕግ ባለሙያው ̎የአሰሪና ሠራተኛ አዋጅ ላይ በሕግ እንደተቀመጠው አሰሪው በቅድሚያ በሥራ ቦታው ላይ አደጋ እንዳይከሰት የሚያደርጉ የቅድመ ጥንቃቄ ሥራዎች እንዲያሟላ ይጠበቃል̎ ያሉ ሲሆን፤ ይህ ሆኖ አደጋው ከደረሰ ግን አስፈላጊ ካሳ የሚሰጥበት አሰራር በሕጉ በዝርዝር መቀመጡን አብራርተዋል፡፡
ነገር ግን ጉዳት የደረሰበት ሠራተኛ በተቋሙ ስለማገልገሉ እና ስለደረሰበት የሥራ ቦታ ላይ አደጋ የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ እንደሚጠበቅበት ጨምረው ተናግረዋል፡፡
ተቋማት ለሰራተኞች ምቹ የሥራ ሁኔታን የመፍጠር እና ለሚሰሩት ሥራ አገልግሎት እንዲሰጡ ቁሳቁሶችን የማሟላት ግዴት በአሰሪዎች ላይ እንደሚጣል የሕግ ባለሙያዎቹ የተናሩ ሲሆን፤ ሠራተኞችም ይህን የመጠየቅ መብት እንዳላቸው አመላክተዋል፡፡
ሠራተኞች በሥራ ቦታ ላይ በሚደርስባቸው ድንገተኛ አደጋዎች ምክንያት የአካል ጉዳት የደረሰባቸው እና ሕይወታቸው ያለፈ ስለመኖሩ በርካታ ጊዜያት ሲገለጽ ቆይቷል፡፡
በእሌኒ ግዛቸው
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
የኢትዮጵያ ዲጂታል ኢኮኖሚ በፈረንጆቹ 2028 1 ነጥብ 3 ትሪሊዮን ብር ለጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ተመላከተ
ጥቅምት 14/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ዲጂታል ኢኮኖሚ እ.ኤ.አ. በ2028 ከ1.3 ትሪሊዮን ብር በላይ በጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) ላይ አስተዋጽዖ ሊያደርግ እንደሚችል ጂ.ኤስ.ኤም.ኤ በተባለ አለም ዓቀፍ ድርጅት የቀረበ አዲስ ሪፖርት አመላክቷል።
በኢትዮጵያ ዲጂታል ሽግግር ላይ ትኩረት ያደረገውና በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ይፋ የሆነው ሪፖርት፤ የቴሌኮም ማሻሻያ እና የሞባይል ቴክኖሎጂ ኢንቨስትመንቶች በግብርና፣ በማኑፋክቸሪንግ እና በህዝብ አገልግሎቶች በመሳሰሉት ቁልፍ ዘርፎች እድገትን እንዴት እንደሚያበረታቱ ጠቁሟል።
ከእነዚህ እድገቶች የተነሳም በፈረንጆቹ 2028 ከ 1 ሚሊዮን በላይ አዳዲስ ሥራዎች እንደሚፈጠሩ እንዲሁም ለመንግሥት ተጨማሪ 57 ቢሊዮን ብር ከታክስ ገቢ ያስገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ እድገት ፕሮግራም የሆነው የኢትዮጵያ የቴሌኮም ማሻሻያ በዘርፉ ለሚስተዋለው እመርታ ትልቅ አስተዋጽዎ እያበረከተ መሆኑንም ይህ ሪፖርት አመላክቷል።
በተጨማሪም በፈረንጆቹ በ2023 ዘርፉ 700 ቢሊዮን ብር ለጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት አበርክቶ 57 ቢሊዮን ብር ከታክስ ገቢ ማስገኘቱም የተገለጸ ሲሆን፤ የሞባይል ኢንተርኔት ግንኙነቶች በ65 በመቶ ማደጉና የ4ጂ ሽፋን በስምንት እጥፍ ጨመሩን ሪፖርቱ ጠቁሟል።
ይህንን እድገት በማስገኘት ረገድ በተለይም የሞባይል ኢንተርኔት ተጠቃሚነት እና በቴሌኮም ገበያ ላይ ያለው ውድድር እንዲጨምር ኢትዮ ቴሌኮም እና ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ትልቅ ሚና እንደነበራቸው ተገልጿል።
በተጨማሪም በፈረንጆቹ 2028 ከ50 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን ከሞባይል ኢንተርኔት ጋር ይገናኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ ሪፖርቱ አመልክቷል።
የግንኙነቶች መጨመር በ2028 በግብርና ዘርፉ ላይ 140 ቢሊየን ብር እና በማኑፋክቸሪንግ ላይ የ114 ቢሊየን ብር አስተዋፅኦ ያደርጋልም ተብሏል።
ነገር ግን ከፍተኛ የአጠቃቀም ክፍተት እንዳለ በመቀጠሉ፣ በኔትወርክ ሽፋን ውስጥ ቢኖሩም 76 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ አሁንም የሞባይል ኢንተርኔት እንደማይጠቀም ተነግሯል፡፡
ይህንን ክፍተት በተለይም በሞባይል ኢንተርኔት አጠቃቀም ላይ ያለውን የ40 በመቶውን የፆታ ልዩነትን ማስተካከል ለኢትዮጵያ ዲጂታል የወደፊት እጣ ፈንታ ወሳኝ መሆኑ ተመላክቷል።
በታለመው የፖሊሲ ማሻሻያ ይህ ክፍተት በ2028 ወደ 66 በመቶ ሊያሽቆለቁል እንደሚችል የተገለጸ ሲሆን፤ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን የኢንተርነት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ታምኖበታል።
እንዲሁም የሞባይል ገንዘብ እና የገንዘብ ዝዉውር ስርዐት አካታችነት የሞባይል ገንዘብ አሁን ኢትዮጵያ በደረሰችበት የ 90 ሚሊዮን የተንቀሳቃሽ ስልክ ተጠቃሚዎች እና የ 70 በመቶ የስርዓት ምጣኔ፣ ለሀገሪቱ የገንዘብ ዝዉውር ስርዐት አካታችነት ወሳኝ አንቀሳቃሽ ነው ተብሏል።
እነዚህ አገልግሎቶች እያደጉ ሲሄዱ ዲጂታል እና የገንዘብ ዝዉውር ስርዐት አካታችነትን በማሳደግ ለአገሪቱ ኢኮኖሚ እድገት የበለጠ አስተዋፅዖ እንደሚያደርጉም በሪፖርቱ ተመክቷል፡፡
በጂ.ኤስ.ኤም.ኤ ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ ሀገራት ኃላፊ አንጄላ ዋሞላ "ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ዲጂታል መሪ ለመሆን ጥሩ አቋም ላይ ነች" ያሉ ሲሆን፤ "ስትራቴጂካዊ ማሻሻያዎችን በመተግበር እና የዲጂታል መሳሪያዎችን እና አገልግሎቶችን ተደራሽነት በማሻሻል፣ ኢትዮጵያ ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ የኢኮኖሚያዊ እና የማህበራዊ ልማት እድሎችን መክፈት ትችላለች" ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ይህም ኢኮኖሚውን ብቻ ሳይሆን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን በዲጂታል አካታችነት ተጠቃሚዎች እንደሚያደርግም አመላክተዋል።
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ዜጎችን ከአስገድዶ መሰወር ለመጠበቅ የወጣውን አለማቀፍ ስምምነት ኢትዮጵያ እንድታጸድቅ ኢሰመኮ ጥሪ አቀረበ
ጥቅምት 14/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአዲስ አበባ ከተማ፣ እንዲሁም በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች የሚፈፀሙ የአስገድዶ መሰወር ሁኔታን ሊያቋቁሙ በሚችሉና ያሉበት ሳይገለጽ በተራዘመ እስር ላይ የሚገኙ ሰዎችን ሁኔታና በተመለከተ መግለጫ አዉጥቷል።
ጉዳዩን በሚመለከት ጥብቅ ክትትል አድርጌያለሁ ያለዉ ኮሚሽኑ ከሐምሌ ወር 2015 ዓ.ም ጀምሮ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ተወስደው ያሉበት ቦታ ሳይታወቅ የቆዩ መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን፤ ከ50 በላይ ሰዎችን የተመለከቱ አቤቱታዎችን መመርመሩን አስታውቋል፡፡
ኢሰመኮ አያይዞም "ይህ ሪፖርት እስከወጣበት ቀን ድረስ 44 ሰዎች ከ1 ወር እስከ 9 ወር በተለያዩ መደበኛ ባልሆኑ ቦታዎች ከቆዩ በኋላ መለቀቃቸውን አረጋግጫለሁ" ብሏል።
ሆኖም ያሉበት ቦታ ሳይታወቅ በተራዘመ እስር፣ መደበኛ ባልሆኑ ማቆያ ቦታዎች፣ ብሎም በአስገድዶ መሰወር ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ሰዎች ሁኔታ አሳሳቢ ሆኖ መቀጠሉን ገልጿል፡፡
በዚህም አዲስ አበባን ጨምሮ በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች መደበኛ ባልሆኑ ማቆያ ቦታዎች ሰዎችን የማቆየትና የማሰር ተግባር እንዲቆም ሁሉም የሚመለከታቸው የሕግ እና የጸጥታ አካላት ተገቢውን ትኩረት እንዲሰጡ ኢሰመኮ ጠይቋል፡፡
አሁንም ያሉበት ቦታ በማይታወቅ፣ ብሎም የአስገድዶ መሰወርን ሊያቋቁም በሚችል ሁኔታ ውስጥ ያሉ ሰዎችን የመንግሥት የጸጥታ አካላት አፋጣኝ ምላሽ ሊሰጡ ይገባልም ብሏል።
ይህን መሰሉ የመብት ጥሰት እንዲቆም በአለማቀፍ ደረጃ ሁሉንም ሰዎች ከአስገድዶ መሰወር ለመጠበቅ የወጣው ስምምነት ድርጊቱን ለመከላከል በመንግሥት ሊወሰዱ የሚችሉ እርምጃዎችንም የሚያካትት በመሆኑ ስምምነቱን ኢትዮጵያ ልታፀድቅ ይገባል ብሏል፡፡
በፅዮን ይልማ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
የውጪ ምንዛሬ ዋጋ ጭማሪ አሳየ
ጥቅምት 14/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአሜሪካ ዶላርን ጨምሮ የውጭ ሀገራት የገንዘብ ምንዛሬ ዋጋ ተመን ላይ ጭማሪ አድርጓል።
በዚህም መሠረት ባለፉት ቀናት በንግድ ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ113 ብር ከ1308 ሳንቲም እየተገዛ በ115 ብር 3934 ሳንቲም ሲሸጥ የነበረ ሲሆን፤ ዛሬ ይፋ በተደረገው የምንዛሬ ዋጋ ተመን አንድ ዶላር መግዣው ከ3 ብር በላይ ጨምሮ 116 ብር ከ6699 ሳንቲም ገብቷል።
የመሸጫ ዋጋው ደግሞ፤ ከ3 ብር በላይ ጭማሪ ተደርጎበት 119 ብር ከ0033 ሳንቲም ሆኗልል።
በተጨማሪም ባንኩ ፓውንድን ጨምሮ በሌሎች የውጭ ሀገር የገንዘብ ምዛሬዎች ላይ ጭማሪ አድርጓል።
👉የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የውጪ ምንዛሬ የመሸጫና መግዣ ዋጋ ዝርዝር ከላይ ተያይዟል
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
"ኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ተግዳሮቶች ተጋርጠውባታል" ካርድ
ጥቅምት 13/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የመብቶች እና ዴሞክራሲ እድገት ማዕከል (ካርድ) በኢትዮጵያ ውስጥ በግጭትም ሆነ ከግጭት ውጪ ባሉ አካባቢዎች የሚገኙ ሁሉም ተዋናዮች የዜጎችን መብት እንዲያከብሩ እና ተጠያቂነት እንዲሰፍን ጥሪ አቅርቧል፡፡
"እንዳለመታደል ሆኖ ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ እነዚህ መሰረታዊ መብቶች ከፍተኛ ፈተናዎች እየገጠሟቸው ይገኛል" ያለው ካርድ፤ ጾታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች፣ የአፈና መስፋፋት፣ የዘፈቀደ እስራት እና ያለ ፍርድ ግድያን ጨምሮ እየተካሄዱ የሚገኙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች አስቸኳይ ትኩረት ተሰጥቷቸው ሊታረሙ፤ አጥፊዎችም ለፍርድ ሊቀርቡ ይገባል ብሏል፡፡
ማዕከሉ አሳሳቢ ባለው የመረጃ አሃዝ መሠረት በ2015 ዓ.ም ብቻ 5 ሺሕ 411 የሚሆኑ የዘፈቀደ እስሮች መፈጸማቸውን የገለጸ ሲሆን፤ አብዛኞቹ ያለ መደበኛ ክስ የተፈጸሙ መሆናቸውን አስታውቋል።
እንዲሁም ከመስከረም 2016 ዓ.ም ጀምሮ ከ100 በላይ ግለሰቦች ፣ ምሁራን እና ማህበረሰብ አንቂዎች በጅምላ መታሰራቸውንና 1 ሺሕ 351 ግድያዎች መመዝገባቸውን በመግለጽ፤ ከዚህ ውስጥ 70 በመቶ የሚሆነው በመንግሥት ሃይሎች ተፈጸመ መሆኑን አመላክቷል።
ካርድ በኢትዮጵያ ውስጥ በግጭትም ሆነ ከግጭት ውጭ ያሉ አካባቢዎች ላይ የሚገኙ ሁሉም ተዋናዮች የዜጎችን መብት እንዲጠብቁ ጥሪውን ያቀረበ ሲሆን፤ በተጨማሪም ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተጠያቂነትን እንዲያሰፍኑ ጠይቋል።
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
የውጭ ባለሀብቶች ወደ ሀገር ዉስጥ መግባት ጥቅም እንጂ ጉዳት የለውም ሲል የኢትዮጵያ ምርት ገበያ አስታወቀ
ጥቅምት 13/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢኮኖሚው ዘርፍ ለውጭ ባለሀብት ክፍት መደረጉ እንደ ምርት ገበያ ለሀገር የሚጠቅሙ ነገሮችን ይዞ የሚመጣ ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወንድምአገኘሁ ነገራ ለአሐዱ ገልጸዋል።
ዋና ሥራ አስፈፃሚው አክለውም "የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና እንደፈረመ ሀገር፤ ኢኮኖሚው ለውጭ ባለሀብት ክፍት መደረግ አለበት" ብለዋል፡፡
የውጭ ባለሀብቶች ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡበት ሁኔታን በተመለከተ መስፈርቱ በግልፅ የተቀመጠ መሆኑን በማንሳትም፤ ወደ ሥራ ሲገቡ ትልልቅ መደብሮችን በማቋቋም እንዲሆን ታስቦ ክፍት መደረጉንም ጨምረው ተናግረዋል፡፡
"ወደ ሀገር ዉስጥ የሚገቡት ባለሀብቶች ኢትዮጵያ ላይ ምርቶችን ከሀገር ውስጥ የገዙ እንዲሁም፤ ቡና ላይ ከ10 ሚሊዮን ዶላር በላይ ወደ ውጪ የላኩ መሆን እንዳላባቸው በግልፅ ተቀምጧል" ሲሉም አስረድተዋል፡፡
አክለዉም፤ ኢትዮጵያ ቦሎቄና በቆሎ ወደ አፍሪካ ሀገራት የመላክ ሥራ እየሰራች እንደምትገኝ በማንሳት፤ ወደ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራትም ቡና የመላክ ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪም የውጭ ባለሀብቶች ዘመናዊ የመገበያያ መንገድን ወደ ሀገር ይዘው እንደሚመጡና አስገዳጅ ሕጎችን ተግባራዊ እንደሚያደርጉም ገልጸዋል፡፡
ባለሀብቶቹ ወደ ሀገር ሲገቡ የምርት ገበያው የመመዘን እንዲሁም የተገበያዮችን ጥራት የመቆጣጠር ሀላፊነት ከተሰጠ ደርበዉ መስራት እንደሚፈልጉም አቶ ወንድምአገኘሁ ጨምረው ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
ባሳለፍነው የ2016 ዓመት ሚያዚያ ወር ላይ ለሀገር ውስጥ ባለሀብቶች ብቻ ተከልለው የቆዩት የወጪ፣ የገቢ፣ የጅምላና የችርቻሮ የንግድ ሥራ ዘርፎች ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት እንዲሆኑ መደረጉ ይታወሳል፡፡
በአቤል ደጀኔ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
በእርሻ መሳሪያዎች እጥረት ምክንያት ሰብሎችን ለመሰብሰብ ተቸግሪያለሁ ሲል የትግራይ ክልል የእርሻና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ አስታወቀ
ጥቅምት 13/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ሜትሮሎጂ ኢንስቲትዩት ባወጣው መግለጫ፤ በቀጣይ ቀናት በሚጥለው ዝናብ ጉዳት እንዳያደርስ የደረሱ ሰብሎች እንዲሰበሰቡ ማስጠንቀቂያ መስጠቱ ይታወሳል፡፡
አሐዱም የደረሱ ሰብሎችን ከመሰብሰብ አንጻር ምን እየሰራችሁ ነው? ሲል የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የእርሻና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አለምብርሀን ሃሪፈዮን ጠይቋል፡፡
ኃላፊው በምላሻቸው በዝናብ ምክንያት ምርቶችን ለመሰብሰብ እና የሚያስከትለዉን ዉድመት ለመቀነስ ከግብርና ባለሙያዎች ጋር በመነጋገር የዕቅድ መተግበሪያ ተዘጋጅቶ በክልሉ የተጀመሩ እንቅስቃሴዎች መኖራቸውን ገልጸዋል፡፡
ነገር ግን ሰብል የመሰብሰብ ሥራዎችን ለማከናወን ዘመናዊ የእርሻ መሳሪያዎች እጥረት እንዲሁም አርሶ አደሩን ለመደገፍ የሰዉ ሀይል እጥረት በመኖሩን የሰብል መሰብሰቡን ሥራ አስቸጋሪ አድርጎታል ብለዋል፡፡
አክለውም፤ ሰብሎች ለመሰብሰብ ባለመድረሳቸውም እና ከፌደራል መንግሥት የኬሚካል አቅርቦት አነስተኛ መሆን ተግዳሮት እንደሆነም ተናግረዋል።
በክልሉ ከነበረው የጸጥታ ችግር አንጻር ምርቶችን በቶሎ ለመሰብሰብ በሌሎች ክልሎች የሚታየዉ ዘመናዊ የእርሻ ቁሳቁስ እና ሌሎች ድጋፎች እየተደረገልን አይደለም ሲሉም ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ሜትሮሎጂ ኢንስቲትዩት በመጪው ቀናቶች በአንድ አንድ አንድ የኢትዮጵያ ክፍሎች በተለይም በደቡብ ትግራይ፣ በአማራ ክልል፣ በደቡብ አፋር፣ በምስራቅ ኦሮሚያ ዞኖች፣ በአዲስ አበባ እና በመካከለኛው የሀገራችን ከተሞች ሊከሰት እንደሚችል መግለጹ አይዘነጋም።
በፅዮን ይልማ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
የእንስሳት ሐብት ልማት ያሉበትን ችግሮች በምርምር ደረጃ ለማሻሻል በብርቱ እየሰራ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ገለጸ
ጥቅምት 13/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ ያለውን የእንስሳት ሐብትና የእንስሳት ምርት ተዋፅኦ ያሉባቸውን ችግሮች በመቅረፍ የሚያስችል ስትራቴጂዎችን ተግባራዊ እያደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን አስታውቋል።
ይህን የሰማነው ፕራና ኤቨንትስ ያዘጋጀውን 9ኛ የአፍሪካ እንስሳት ዓውደርእይ ለአገር ውስጥ ጋዜጠኞች በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው።
9ኛ የአፍሪካ እንስሳት አውደ ርዕይና ጉባኤ በመጪው ጥቅምት 21 እስከ 23 2017 ዓ.ም በአዲስአበባ ሚሊንየም አዳራሽ የሚካሄደድ መሆኑን ከመግለጫው ላይ ሰምተናል።
በአውደ ርዕዩና ጉባዔው ላይ በእንስሳት መኖ፣ በእንስሳት ጤና፣ በዶሮ እርባታ፣ በወተት፡ በስጋ እንዲሁም በንብ እና በአሳ ሃብት ልማት ላይ ያተኮሩ ከ17 ሀገራት የተወጣጡ ከ100 በላይ ዓለም ዓቀፍ የቴክኖሎጂ እና ግብዓት አቅራቢዎች ይሳተፋሉ ተብሏል፡፡
በተጨማሪም የተለያዩ ስመጥር የሀገር ውስጥ ኩባንያዎች የሚሳተፉበት ዓመታዊው አውደ ርዕይ እና ጉባኤ እንደሚካሄድ ተነግሯል።
የግብርና ሚኒስቴር በአገራቀፍ ደረጃ የጀመረውን የሌማት ትሩፋት እንቅስቃሴ አካል ይሆናል የሚል እምነት እንዳላቸው፤ የግብርና ሚኒስቴር ተወካይ ወይዘሮ ፅጌሬዳ ፍቃዱ ተናግረዋል።
በአዲስ አበባ ይካሔዳል የተባለው ይኸው አውደ ርዕይና ጉባዔ ከኔዘርላንድ ኤምባሲ ባደረገው ድጋፍ የተዘጋጀ መሆኑን መረዳት ችለናል።
በአሁኑ ጊዜ የእንስሳት ሐብት ልማት እያደገና እየዘመነ የመጣ ጉዳይ ቢሆንምኢትዮጵያ በዘርፉ ከሌሎች ጎረቤት አገራት ጋር ሲነፃፀር አየስተኛ አሐዝ እንዳለው ተገልጿል።
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ደረጃ ከፍተኛ ቁጥር የእንስሳት ሐብት እንዳላት ቢነገርም፤ ነገር ግን እንዳልተጠቀመችበት ይነገራል።
በአማኑኤል ክንደያ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
እስራኤል አዲሱን የሂዝቦላህ መሪ ሀሽም ሳፊይዲንን መግደሏን አስታወቀች
ጥቅምት 13/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የእስራኤል መከላከያ ኃይል (አይ.ዲ.ኤፍ) በሟቹ የሂዝቦላህ መሪ ሀሰን ናስራላህ ምትክ ወደ ቡድኑ ኃላፊነት መጥቶ የነበረውን የቡድኑን መሪ ሀሽም ሳፊይዲንን ባደረገው የአየር ጥቃት መግደሉን አስታውቋል፡፡
መከላከያ ኃይሉ የቀድሞው የሂዝቦላህ መሪ ሀሰን ናስራላህ የአጎት ልጅ የሆነው ሀሽም ሳፊይዲን ከሦስት ሳምንት በፊት እስራኤል በደቡባዊ ሊባኖስ በወሰደችው የአየር ጥቃት መገደሉን ገልጿል።
በሊባኖስ ዋና ከተማ ቤይሩት ደቡባዊ ዳርቻዎች በሚገኘው የድርጅቱ ዋና የስለላ ዋና መስሪያ ቤት ላይ በደረሰው ጥቃት፤ ከሀሽም ሳፊይዲን በተጨማሪ የሂዝቦላህ ኢንተለጀንስ ዳይሬክቶሬት ሃላፊ አሊ ሁሴን ሃዚማ እና የቡድኑ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦች በጥቃቱ መገደላቸው ተነግሯል፡፡
ግድያውን አስመልክቶ ሂዝቦላህ የሰጠው ምላሽ አለመኖሩ ተገልጿል።
ቀደም ሲል በፈረንጆቹ ጥቅምት 8 ቀን 2024 የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ የእስራኤል መከላከያ ሀይል ሀሰን ሳፊይዲንን ጨምሮ በሺዎች የሚቆጠሩ የሂዝቦላህ መሪዎችና ታጣቂዎች መገደላቸውን ተናግረው ነበር።
በወቅቱም ሀሰን ነስራላህን በመተካት ወደ ሂዝቦላህ መሪነት የመጣው ሀሽም ሳፊይዲን ሳይገደል እንዳልቀረ ሲነገር ቆይቷል፡፡
ይሁን እንጂ በእስራኤል ጥቃት የመሪውን መገደል የእስራኤል መከላከያ ሃይል አዛዥ ሌተና ጄኔራል ሄርዚ ሃሌቪ በሰጡት መግለጫ አረጋግጠዋል።
ከሀሽም ሳፊይዲን ለዓመታት በእስራኤል መንግሥት ላይ የሽብር ጥቃቶችን በመምራት እንዲሁም በሂዝቦላ ማዕከላዊ የውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶች ውስጥ በመሳተፍ ውንጀላ ይቀርብበት እንደነበር ተነግሯል፡፡
በተጨማሪም ግለሰቡ እ.ኤ.አ. በ2017 በአሜሪካ እና በሳውዲ አረቢያ “ዓለም አቀፋዊ አሸባሪ” ተብሎ ተፈርጆ ነበር፡፡
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ