አሐዱ ራድዮ 94.3 Your source for top local and international news and analysis. "Voice of Ethiopian" የአሐዱ የቴሌግራም ቻናል ቤተሰብ በመሆን ወቅታዊና እውነተኛ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ
ቱርክ ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ የነበራት ተሳትፎ አሉታዊ በመሆኑ አሁንም ብሔራዊ ጥቅምን ለማስጠበቅ ቁርጠኛ መሆን ይገባል ተባለ
ጥቅምት 18/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ኢትዮጵያ በባህር በር ስምምነት ጉዳይ በቀጠናው ከጎረቤት ሀገራት ጋር በተለይም ከሶማሊያ ጋር በገባችው ዉዝግብ ቱርክ የአደራዳሪነት ሚና ይዛ መምጣቷ አይዘነጋም።
ይህ በእንዲህ እያለ "ግብፅ የአባይን ወንዝ በበላይነት ለመጠቀም እና በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማሳደር በሚመስል መልኩ ለሶማሊያ ብሎም በሌሎች የጎረቤት ሀገራት ወታደራዊ እንቅስቃሴ መጀመሯ በቱርክ የአደራዳሪነት እንቅስቃሴ ላይ ተጽዕኖ አያሳድርም ወይ?" ሲል አሐዱ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ጠይቋል።
የእናት ፓርቲ የአመራር አባል አቶ ጌትነት ወርቁ የግብፅ በቀጠናዉ መንቀሳቀስ ተለምዷዊ መሆኑን አንስተዋል፡፡
ቱርክ በኢኮኖሚ ጠንካራ በመሆኗ በምስራቅ አፍሪካ ላይ በስፋት እንቅስቃሴ ብታደርግም ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ነባራዊ ፖለቲካ ላይ በጎ ተጽእኖ ያልነበራት በመሆኗ፤ በድርድር ሂደቱ ግብፅን ብቻ ሳይሆን ቱርክንም በጥንቃቄ መመልከት እንደሚገባ ለአሐዱ ተናግረዋል።
ግብፅ ከአባይ ጋር ተያይዞ ከዚህ ቀደምም በተዘዋዋሪ መሰል ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን በምስራቅ አፍሪካ ቀጠና ላይ ስታደርግ መቆየቷን የተናገሩት ደግሞ፤ የነጻነት እና እኩልነት ፓርቲ የአደረጃጀት እና አቅም ግንባታ ሀላፊ አቶ ሙባረክ ረሺድ ናቸው።
አቶ ሙባረክ፤ "ኢትዮጵያ በማንኛውም ሁኔታ ዉስጥ የሌሎችን ብሔራዊ ጥቅም በማይነካ እና እንደ ሀገር ሉአላዊነቷን በማይጋፋ መልኩ አቋሟን ልታስከብር እና ብሔራዊ ጥቅሟን ማስቀደም ተገቢ ነዉ" ሲሉ አሳስበዋል፡፡
አክለውም "በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል የተፈጠረውን ዉጥረት ለማርገብ ቱርክ የምታደርገው ጥረት የሚበረታታ ቢሆንም፤ ካለዉ ነባራዊ ሁኔታ አንጻር ሂደቱን በጥንቃቄ መመልከት ይገባል" ብለዋል።
በፅዮን ይልማ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ከ56 በላይ በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ ተሸከርካሪዎች መያዛቸው ተገለጸ
ጥቅምት 18/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በ2017 በሩብ ዓመት ብቻ ከ56 በላይ ተሸከርካሪዎች ኢ-መደበኛ በሆነ መንገድ ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው በጉምሩክ ኮሚሽን መያዛቸውን የኮሚሽኑ ኮምኒኬሽን ዳይሬክተር ዘሪሁን አሰፋ ለአሐዱ ተናግረዋል።
አክለውም "ከተያዙት ውስጥ በቱሪስት ፍቃድ ገብተው ከተፈቀደላቸው ጊዜ በላይ ሕገ-ወጥ ሰሌዳዎችን የለጠፉ 15 ሲሆኑ፤ ቀሪዎቹ 41 ደግሞ በድንበር በኩል የገቡ ናቸው" ብለዋል።
ባሳለፍነው በ2016 በጀት ዓመት ደግሞ በጠቅላላ ከአንድ መቶ 34 በላይ ተሸከርካሪዎች መያዛቸውን ተናግረዋል፡፡
ዳይሬክተሩ አያይዘውም በዚህ በሕገ-ወጥ ሥራ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች በሕግ ተጠያቂ መደረጋቸውን ገልጸዋል።
ኢ-መደበኛ ንግድ ሀገርን የሚጎዳ በመሆኑ በዘርፉ የተሰማሩ ነጋዴዎች በሕጋዊ መንገድ በመስራት ለሀገር ዕድገት የበኩላቸውን እንዲወጡም የኮምኒኬሽን ዳይሬክተሩ አሳስበዋል፡፡
ከሌሎች ጊዜያቶች በተለየ መልኩ በየኬላው የሚደረጉ ቁጥጥሮች መጠንከራቸውን ገልጸው፤ "የተለያዩ እቃዎች በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ ሀገር ውስጥ ሲገቡ እና ሲወጡም ይስተዋላል" ብለዋል።
በወልደሀዋርያት ዘነበ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
#አሐዱ_መልህቅ
ጥንቅሩን ለመከታተል ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👇
https://youtu.be/2LsI3elAMks?si=vKFOxJ4gGTtZ1pRB
https://youtu.be/zsvl8nQ6PzY?si=7ErAos4GtsCp42Y5
Читать полностью…የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ አዲሱን የመቐለ ከንቲባ ከሥራ አገዱ
ጥቅምት 16/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ አዲሱን የመቐለ ከተማ ከንቲባ ዶ/ር ረዳኢ በርሀ ከሥራ ማገዳቸው ተሰምቷል።
በፕሬዝዳንቱ ትላንት ጥቅምት 15/2017 ዓ.ም በተፃፈ ደብዳቤ፤ አዲሱ የመቐለ ከተማ ከንቲባ ዶ/ር ረዳኢ በርሀ ሕጋዊ ያልሆነ ተግባራቸውን እንዲያቆሙ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።
"የመቐለ ከተማ ምክር ቤት መጠቀምያ በማድረግ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ሥራ የሚፃረር ተግባር መፈፀም አይቻልም " ያለው የፕሬዝዳንቱ ደብዳቤ፤ የአዲሱ ከንቲባ ሹመት በጊዚያዊ አስተዳደሩ ተቀባይነት እንደሌለው አስረድቷል።
አቶ ጌታቸው በደብዳቤው "የጊዚያዊ አስተዳደሩን የሚፃረር አቋም በመያዝ በጊዚያዊ አስተዳደሩ ሥር ያለን መዋቅር መምራት አትችሉም" ያሉ ሲሆን፤ "ጊዚያዊ አስተዳደሩም ከእርስዎ ጋር መሰራት አይችልም" ሲሉም አሳስበዋል።
በመቐለ ከተማ የሚገኙ የመንግሥት መዋቅሮች "ሕጋዊ አይደሉም" የተባሉት ከንቲባ የሚሰጡዋቸው አመራሮች እና ትዕዛዞች ተቀብለው እንዳይፈፅሙም ፕሬዝዳንቱ አስጠንቅቀዋል።
አዲሱ የመቐለ ከንቲባ ዶ/ር ረዳኢ በርሀ፤ ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በሚመሩት ህወሓት የሥራ አስፈፃሚ ሆነው መመረጣቸው ይታወሳል።
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
በሩብ ዓመቱ ከታቀደው 100 ሺሕ ዩኒት ደም ውስጥ 94 ሺሕ ዩኒት ደም መሰብሰቡ ተገለጸ
ጥቅምት 16/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በተያዘው ሩብ ዓመት ሦስት ወራት፤ በደም ማሰባሰብ ሂደት ከታቀደው 100 ሺሕ ዩኒት ውስጥ 94 ሺሕ የሚሆን ዩኒት ደም መሰብሰብ መቻሉን የኢትዮጵያ ደም ባንክ አገልግሎት አስታውቋል።
የደም ማሰባሰቡ እንደ ሀገር ሲከናወን የቆየ ሲሆን፤ በሩብ ዓመቱ የተሰበሰው በአንጻሩ ካለፈው የተሻለ መሆኑን የአገልግሎቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሀብታሙ ታዬ ለአሐዱ ተናግረዋል።
እቅዱን ሙሉ ለሙሉ ለማሳካት የደም ለጋሽ በጎ ፈቃደኞች በሚፈለገው ልክ አለመሳተፍ፣ በአንዳንድ የጸጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ላይ ለመሰብሰብ አዳጋች መሆን እንዲሁም በበዓላት ወቅት ደም የመለገስ ሂደቱ አነስተኛ መሆንና መሰል ተግዳሮቶች እንዳጋጠሙ ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አስረድተዋል።
ለቀጣይ ክፍተቶችን በማረም የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብ ተቋሙ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝም ተናግረዋል።
ኅብረተሰቡም በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ አደባባዮች በሚገኙ ማዕከላት፣ በትምህርት ቤቶች፣ ቀይ መስቀል ግቢና በሁሉም የደም ባንክ መስሪያ ቤቶች ደም በበጎ ፈቃደኝነት መለገስ እንደሚችል አቶ ሀብታሙ አመላክተዋል።
በአለምነው ሹሙ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ባለሐብቶች ከገበሬዎች የሚያስመርቱት የእርሻ ምርት በገቡት ውል መሰረት ተግባራዊ እንዲያደርጉ ተጠየቀ
ጥቅምት 16/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በቅርቡ የተሻሻለው በኢንቨስተሮችና ገበሬዎች መካከል የውል እርሻ ምርት መመርያ ተፈፃሚ እንዲሆን በብርቱ እየሰራበት እንደሚገኝ ግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል።
ሚኒስቴሩ መመርያውን ያሻሻለው በኢንቨስተሮችና በገበሬዎች መካከል የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን በዘላቂነት ለመፍታት በማለም መሆኑን ገልጿል።
በግብርና ሚንስቴር የእንስሳትና አሳ ሀብት ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ፅጌሬዳ ፍቃዱ የገበሬን እርሻ በውል የሚያስመርቱ ባለሐብቶች በኩል የሚስተዋለውን ችግር ለመቅረፍ ሲባል፤ አንዳንድ ሕጎች እንዲሻሻሉ መደረጋቸውን ለአሐዱ ተናግረዋል።
ሚኒስቴሩ የውል እርሻ ወይንም ኮንትራት ፋርሚንግ መመርያ አውጥቶ ተግባራዊ ሲያደርግ የቆየ ቢሆንም፤ በሕጉ ላይ መሻሻል ያለባቸው ጉዳዮች በመኖራቸው እንዲሻሻል መደረጉንም ገልጸዋል።
ዘርፉ በርከት ያሉ ቅሬታዎች ሲነሱበት የቆየ መሆኑን ገልጸው፤ በዚህም ምክንያት ማሻሻያ ማድረግ ማስፈለጉን ተናግረዋል።
የተሻሻለው ሕግ በዘርፉ የሚሳተፉ ባለሐብቶች እንዲሳተፉበት የሚያበረታታ መሆኑን የገለጹት ኃላፊዋ፤ ኢንቨስተሮችን ለመሳብ መንግሥት ጥረት እያደረገ እንደሚገኝም ለአሐዱ አስረድተዋል።
ሕጉ የውል እርሻ የሚል ስያሜ ተሰጥቶች ከዓመታት በፊት ተግባራዊ ቢደረግም የታለመለትን ያህል እንዳልተፈጸመ ተነግሯል። በዚህ የተነሳም ማሻሻያ አስፈልጓል ተብሏል።
በአማኑኤል ክንደያ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
በሐሰተኛ ሰነድ የሙያ ፈቃድ ዕድሳት የሚጠይቁ ባለሙያዎች መበራከታቸው ተገለጸ
ጥቅምት 16/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ሐሰተኛ ሰነድ በማቅረብ የሙያ ፈቃድ ዕድሳት የሚጠይቁ ባለሙያዎች ከጊዜ ወደጊዜ እየተበራከቱ መምጣታቸውን የአዲስ አበባ አስተዳደር የምግብና መድሐኒት ባለስልጣን አስታውቋል።
በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች እና ተቋማት የፍቃድ ዕድሳት በመድረግ ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል።
በከተማዋ የምግብና መድሐኒት ባለስልጣን የጤና ተቋማትና ባለሙያዎች ብቃት ማረጋገጫ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ታደሰ ወርዶፋ፤ ባለሙያዎች የሙያ ፍቃዳቸውን ዕድሳት ከማድረጋቸው በፊት እንዲሁም በሙያ ማህበራት አቅም ማጎልበቻ ሥልጣናን ሳያጠናቅቁ ሐሰተኛ መረጃዎችን ከየማህበራቸው በመውስድ ወደ ተቋሙ እንደሚመጡ ገልጸዋል።
እስካሁን ባለው ሂደት በ30 ባለሙያዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን አንስተው፤ ይህ ሐሰተኛ ሰነድ የማቅረብ ሁኔታ በቁጥጥር ሂደቱ ላይ ተግዳሮት መሆኑንም ነግረውናል።
ሀላፊው አክለውም፤ ባለሙያዎች የፍቃድ ዕድሳት አድርገው የህብረተሰብ ሕይወት ላይ ስለሚሰሩ ስልጠናው አጠናቅቀው የዕውቅና ሰርተፍኬት መቀበል እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
በመሆኑም ማህበራቱ ይህንን ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ስልጠናውን መስጠት እንዳለባቸው ጠቁመው፤ "ከጤና ሚኒስትር የሚላክ መረጃን ታሳቢ በማድረግ በተያዘው የጥቅምት ወር ላይ ሙሉ በሙሉ የማጣራት ሥራዎች ይከናወናሉ" ብለዋል።
ባለስልጣኑ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ዕድሳት ያላደረጉ የጤና ባለሙያዎችን ከህዳር 1 ጀምሮ የጤና ሚኒስተር ባወጣው መመሪያ መሰረት በቅጣት እንደሚስተናገዱ ማስታወቁን መዘገባችን ይታወሳል።
በወልደሀዋርያት ዘነበ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
"በ1 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ያልተሰበሰበ ዱቤ ምክንያት የጥሬ ገንዘብ እጥረት አጋጥሞኛል" የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት
ጥቅምት 16/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ክልሎች 1 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ያልተሰበሰበ ዱቤ ምክንያት የጥሬ ገንዘብ እጥረት እንደተፈጠረበት ገልጿል፡፡
አገልግሎቱ በተለያዩ ክልሎች በሚገኙ 19 ቅርንጫፎቹና ለመንግሥት የጤና ተቋማት የመድኃኒት ግብአቶችን ያቀርባል፡፡
በዚህ ሂደት ወስጥ በአዲስ አበባ፣ ትግራይ፣ አማራ፣ ደቡብ፣ ኦሮሚያና ሌሎችም ክልሎች የሚገኙ ተቋማት ያልተሰበሰበ 1 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ዱቤ መኖሩን ገልጿል፡፡
ገንዘቡ በወቅቱ ባለመመለሱ የጥሬ ገንዘብ እጥረት እንዲኖር ማድረጉንና በአፋጣኝ መደበኛ መድኃኒቶች እንዳይቀርብ እንቅፋት መሆኑን የመድሀኒት አቅራቢ አገልግሎት አስታዉቋል፡፡
በ2016 በዱቤ የተሸጠ 6 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ሲሆን፤ ከዚህ ዉስጥ 4 ነጥብ 6 ወይም 71 ነጥብ 4 ከመቶ መሰብሰብ መቻሉንና 1 ነጥብ 8 ቢሊየን ብሩ ያልተሰበሰበ ነዉ ተብሏል፡፡
እነዚህ ችግሮች እንዳሉ ሆኖ በሰሜኑ ክፍል በነበረዉ ግጭት በሽሬና መቀሌ ቅርንጫፍ አማካኝነት ከ1 ቢሊየን 135 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸዉ የሕክምና ግብአቶች ማሰራጨት መቻሉን ለማወቅ ተችሏል፡፡
በሃይማኖት የተሻ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
"የድጎማ ፖለቲካ ፖርቲዎችን መፍጠር ማቆም አለብን" ምርጫ ቦርድ
ጥቅምት 16/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በመንግሥት ድጎማ ላይ ተንጠልጥሎ ፖርቲ መመስረት መቆም አለበት ሲል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።
ተመዝግበዉ ለሚገኙ 53 ፖርቲዎች ከመንግሥት ያገኘዉን 65 ሚሊዮን ብር ማከፋፈሉን የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ዉብሸት አየለ ተናግረዋል።
ቦርዱ በዛሬዉ ዕለት በቅርቡ ያደረገዉን አገልግሎት ክፍያ ማሻሻያ አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።
በመግለጫውም ምክትል ሰብሳቢዉ "ፖርቲዎች የቆየ ልማድ አላቸዉ" ያሉ ሲሆን፤ "በኢትዮጵያ የመድብለ ፖርቲ ምስረታ ከተጀመረበት 1984 ዓ.ም በመንግሥት ድጋፍ ላይ ተንጠልጥሎ ቆይቷል" ብለዋል።
በዚህም ፖርቲዎች በመንግሥት ድጎማ ላይ ተንጠልጥለዉ የቆዩ መሆናቸውን አመላክተዋል።
"የመንግሥት የገንዘብ ድጋፍ ዓላማዉ ተጨማሪ ድጋፍ ሰጥቶ ፖርቲዎች ከፍ የሚሉበት እንጂ፤ የሥራ መፍጠሪያ አይደለም" ሲሉም ምክትል ሰብሳቢዉ ተናግረዋል።
"የድጎማ ፖለቲከኛ አንድ ቦታ ላይ መቆም ይኖርበታል" ያሉት አቶ ውብሸት፤ "ይህ በዋናነት አዲስ ለሚመጡት ፖርቲዎች ነው" ብለዋል።
አክለውም፤ "የአዛዉንቶች ክበብ ዓላማ ይዘዉ የሚመጡ ፖለቲከኞች ዓላማን ለማስቆምም የተሻሻለ ጭማሪ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።
ቦርዱ አዲስ የሚመሰረቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከዚህ በፊት የሙሉ ዕዉቅና ለማግኘት ሲከፍሉ የነበረዉን 2 መቶ ብር ወደ 30 ሺሕ ከፍ ማድረጉን ማስታወቁ አይዘነጋም።
ይህንን ዉሳኔን የፖለቲካ ፖርቲዎችና የጋራ ምክር ቤቱን ጨምሮ ቅሬታ ማቅረባቸዉን አሐዱ መዘገቡ ይታወሳል።
በአቤል ደጀኔ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
እስራኤል ለሊቱን በኢራን ወታደራዊ ዒላማዎች ላይ የአየር ጥቃት ፈጸመች
ጥቅምት 16/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) እስራኤል በዚህ ወር መጀመሪያ በኢራን ለተፈጸመባት የባለስቲክ ሚሳይል ጥቃት ምላሽ የሚሆን የአየር ጥቃት ዛሬ እኩለ ለሊት ላይ አካሂዳለች።
እስራኤል በኢራን ወታደራዊ ተቋማት ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት የሰነዘረች ሲሆን፤ ጥቃቱ "ኢራን እና በመካከለኛው ምሥራቅ የሚገኙ አጋሮቿ ለፈጸሙት ጥቃት ምላሽ ነው" ሲል የእስራኤል መከላከያ ኃይል አስታውቋል።
ኢራን በበኩሏ በዋና ከተማዋ ቴህራን፣ ኹዜስታን እና ኢላም በተባሉ ግዛቶቿ ውስጥ የሚገኙ ወታደራዊ ሰፈሮች የእስራኤል ጥቃት እንደተፈጸመባቸው አስታውቃለች።
በወታደራዊ ይዞታዎቿ ላይ በእስራኤል ጥቃት እንደተፈጸመባት ያረጋገጠችው ኢራን፤ ጥቃቱ ውስን ጉዳት ቢያደርስም በተሳካ ሁኔታ ማክሸፏን ተናግራለች።
ጥቃቱን ተከትሎም ሁሉንም የአየር ክልሏን ዝግ ማድረጓን ገልጻለች።
የኢራን መገናኛ ብዙሃን በበኩላቸው፤ በኢራን ዋና ከተማዋ ቴህራን እና በአቅራቢያዋ በሚገኙ ወታደራዊ የጦር ሰፈሮች ላይ ለበርካታ ሰዓታት የቆየ ፍንዳታ መከሰቱን ዘግበዋል።
ነገር ግን እስካሁን በጥቃቱ የተጎዳ ሰው ስለመኖሩ እና ስለደረሰው ውድመት የተገለጸ ነገር የለም።
የእስራኤል መከላከያ ኃይል ጥቃቱን የፈጸመው “በተመረጡ ወታደራዊ ዒላማዎች” ላይ መሆኑን ያስታወቀ ሲሆን፤ ኢራን ካለፈው ዓመት መስከረም 23/2016 ዓ.ም. ጀምሮ “ያለማቋረጥ እስራኤል ላይ ጥቃት ስትፈጽም ቆይታለች” ሲል ወንጅሏል።
የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስትር ዮአቭ ጋላንት፤ "በኢራን ላይ ጥቃት ከፈጸምን በኋላ አለም ኃያልነታችንን ይረዳል" ሲሉ ተናግረዋል።
ይህ የእስራኤል ጥቃት የተፈጸመው ቴህራን ውስጥ በሐምሌ ወር የሐማስ ፖለቲካ መሪ በመገደላቸው ኢራን ከ200 በላይ ባሌስቲክ ሚሳዔሎችን መስከረም 21/2017 ዓ.ም. በእስራኤል ላይ ከተኮሰች በኋላ ነው።
የእስራኤል አየር ኃይል ሌሊቱን የፈጸመው ጥቃት ኢራን በእስራኤል ላይ የተኮሰቻቸውን ሚሳኤሎች የሚያመርቱ ተቋማትን፣ የአየር ጥቃት መከላከያ እና የሚሳዔል ማስወንጨፊያ ሥርዓቶችን ዒላማ መደረጋቸው መገለጹን የቢቢሲ ዘገባ አመላክቷል።
አሜሪካ በበኩሏ እስራኤል በኢራን ወታደራዊ ይዞታዎች ላይ ስላደረሰችው ጥቃት መረጃው እንደነበራት የገለጸች ሲሆን፤ ነገር ግን በጥቃቱ ላይ እጇን እንዳላስገባች ተናግራለች።
የመካከለኛው ምስራቅ ተቀናቃኝ በሆኑት እስራኤል እና ኢራን መካከል ውጥረት የተጀመረው፤ የፍልስጤሙ ታጣቂ ቡድን ሀማስ ባለፈው ጥቅምት ወር የእስራኤልን ድንበር ጥሶ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ ነው።
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
#አሐዱ_ትንታኔ
ትንታኔውን ለመከታተል ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👇
https://youtu.be/kJ8Lz_vtwKQ?si=t3RQ-baX-WkE40cH
ከካማላ ሀሪስ በተሻለ የዶናልድ ትራንፕ መመረጥ ለአፍሪካና አፍሪካውያን የተሻለ ነው ተባለ
ጥቅምት 15/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በመጪዉ ጥቅምት 26 ለሚደረገዉ ምርጫ በተለይ ለፕሬዝዳንትነት በሚወዳደሩት በቀድሞዉ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕና በምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሐሪስ መካከል ጠንካራ ፉክክር እየተደረገ ነው።
የምርጫዉ ዉጤት ዩናይትድ ስቴትስ እንደ አብዛኛዉ ዓለም ሁሉ ከአፍሪካ ጋር በሚኖራት ግንኙነት ላይ ተፅዕኖ እንደሚያሳርፍም በሰፊዉ ይታመናል።
ዶናልድ ትራንፕ ፕሬዝዳንት በነበሩበት ወቅት የአፍሪካ የመሠረተ ልማት አዉታር እንዲሻሻልና የአፍሪቃና የዩናይትድ ስቴትስ ፖለቲካዊ ግንኙነት እንዲዳብር አድርገዋል የሚሉት አለም አቀፍ ፖለቲካ ተንታኞች ናቸው።
በተለይ በጤና ጥበቃ ሁኔታዎች ላይ የተሻለ አበርክቶ የነበራቸው ትራንፕ በሌላዉም መስክ አፍሪቃን ረድተዋል የሚለው ጉዳይ የሳቸው መመረጥ ለአፍሪካና አፍሪካውያን መልካም ስለመሆኑ ይታመናል መባሉን የሮይተርስ ዘገባ አመላክቷል፡፡
አሁን ላይ ለኋይት ሀውስ የሚደረገው ውድድር የመጨረሻዎቹ ሳምንታት ላይ ሲሆን፤ እንደ አሪዞና እና ጆርጂያ ያሉ ቁልፍ ግዛቶችን ጨምሮ በተለያዩ ግዛቶች ላይ ቀደም ብሎ ድምጽ የመስጠት ሂደቱ ተጀምሯል።
ኹለቱ የከፍተኛ ፓርቲ እጩዎች፣ የዴሞክራቲክ ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሃሪስ እና የሪፐብሊካኑ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በመዘዋወር ገንዘብ የማሰባሰብ እና መራጮችን የመቀስቀስ ሥራን በማከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡
ዶናልድ ትራምፕ ወደ ሥልጣን ይመለሳሉ ወይንስ፤ የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዘዳንት ሊሆኑ የሚችሉት ካማላ ሃሪስን ይመረጣሉ የሚለው ብዙዎችን እያነጋገረ ይገኛል፡፡
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
20 ከመቶ የሚሆነዉ የኤሌክትሪክ ሀይል ለብክነት እንደሚዳረግ ተገለጸ
ጥቅምት 15/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ 20 ከመቶ የሚሆነዉ የኤሌክትሪክ ሀይል ለብክነት እንደሚዳረግ የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ሀይል አስታውቋል።
በተያዘው ሩብ ዓመት ከተመረተው 6 ሺሕ 4 መቶ 56 ጊጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሃይል ውስጥ 6 ሺሕ 4 የሚሆነው መሸጡን የተቋሙ የኮምኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
በኢትዮጵያ የሚመረተው የኤሌክትሪክ ሀይል እና ያሉት መሰረተ ልማቶች አለመጣጣም የኤሌክትሪክ ሀይል በሚፈለገው ልክ ለተጠቃሚዎች እንዳይደርስ ችግር መሆኑ በተደጋጋሚ የሚነሳ ጉዳይ ነው።
አሐዱም ይህን መነሻ በማድረግ ባለፉት ሦስት ወራት ምን ያክል ሀይል ተመርቶ ምን ያክሉስ ጥቅም ላይ ዋለ? በማለት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን ጠይቋል፡፡
የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተሩ "ባለፈው ሩብ ዓመት አጠቃላይ የተመረተው የኤሌክትሪክ ሀይል 6ሺ 4መቶ 56 ጊጋ ዋት ነዉ" ያሉ ሲሆን፤ "ቀሪው 452 ኪጋ ዋት ተቋሙ ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚጠቀምበትን እና የባከነን ሃይልም አንድ ላይ የሚይዝ ነው" ሲሉ ገልጸዋል፡፡
እንደተቋም ይባክናል ተብሎ የሚታሰበዉ የሃይል መጠን 7 ከመቶ ያክል ነው ያሉት አቶ ሞገስ፤ እንደ ሀገር ያለው የብክነት መጠን 20 ከመቶ እንደሆነና "ይህ መጠን ከፍተኛ ነው ለማለት የአለማቀፍ ደረጃዎችን ማየት ያስፈልጋል" ሲሉም አክለዋል፡፡
በእመቤት ሲሳይ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡ https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
"የኢኮኖሚ ማሻሻያ የአገሪቱን ኢኮኖሚ ለማዘመን እና የኢኮሚውን እድገት ምንጭ ከመንግሥት-መር ወደ ግል-መር ኢኮኖሚ በሚያሸጋግር መልኩ የተቃኘ ነው" አህመድ ሺዴ
ጥቅምት 18/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የሚመራው የኢኮኖሚ ማሻሻያ፤ የአገሪቱን ኢኮኖሚ ለማዘመን እና የኢኮሚውን እድገት ምንጭ ከመንግሥት-መር ወደ ግል-መር ኢኮኖሚ በሚያሸጋግር መልኩ የተቃኘ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ ገለጹ፡፡
በኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ የሚመራው ከፍተኛ የልኡካን ቡድን ከአለምአቀፉ የገንዘብ ድርጅት እና የአለም ባንክ 2024 ዓመታዊ ስብሰባ ጎን ለጎን በተካሄደው የቡድን 7 ሀገራት የሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ተሳትፎ አድርጓል።
በወቅቱ የቡድን-7 አገራት ፕሬዝዳንት በሆነችው ጣልያን የተመራው ስብሰባ ላይ የአፍሪካ አገራት የገንዘብ ሚኒስትሮችን፣ የዓለም-አቀፉ የገንዘብ ድርጅት፣ የዓለም ባንክን እና የአፍሪካ ልማት ባንክ የተሳተፉበት ሲሆን፣ እዳ የመክፈል አቅም እና የጥሬ ገንዘብ እጥረት ዙሪያ ተወያይቷል።
እንዲሁም በአፍሪካ የመድኃኒት ምርት ልማት የደረሰበት ደረጃ፣ በአረንጓዴ መሰረተ-ልማት እና ጠንካራና አካታች የአቅርቦት ሰንሰለት በሚጠናከርበት ዙሪያ መምከራቸው ተነግሯል።
አህመድ ሺዴ የጣልያኑ ገንዘብ ሚኒስትር ላደረጉላቸው ግብዣ አመስግነው፤ በኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ስለሚመራውና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የማህበረሰብ ክፍል ማዕከል አድርጎ እየተካሄደ ስላለው የኢኮኖሚ ማሻሻያ ለተሳታፊዎች ገለጻ አድርገዋል።
ይኸው የኢኮኖሚ ማሻሻያ የአገሪቱን ኢኮኖሚ ለማዘመን እና የኢኮሚውን እድገት ምንጭ ከመንግሥት-መር ወደ ግል-መር ኢኮኖሚ በሚያሸጋግር መልኩ የተቃኘ መሆኑን አስረድተዋል።
ሚኒስትሩ የሪፎርም ዋና ዋና መስኮች የገለጹ ሲሆን፣ የአገር ውስጥ ገቢ፣ አስተማማኝ የገንዘብ አቅም ከመፍጠር አኳያ ምክንያታዊ የመንግሥት ወጪን ማስፈን፣ አቅምን ያገናዘበ የብድር አስተዳደር፣ የተዛባ ኢኮኖሚን ከማስተካከል አኳያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሪ ስርአትን ተግባራዊ ማድረግ፣ ተቋማዊ እና የዘርፍ ማዕቀፎችን ማሳደግ ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ መሆኑ ተናግረዋል።
ይሄም የኢኮኖሚ እድገትን ለማረጋገጥ፣ ምርታማነትን ለማሳደግ እና የሥራ እድሎችን ለመፍጠር ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጸዋል፡፡
በዚሁ ስብሰባ ላይ አቶ አህመድ ሺዴ፤ ለኢትዮጵያ እና ሌሎች በማደግ ላይ ላሉ ሀገራት፤ እያደገ ያለውን የፋይናንስ ፍላጎታቸውን በሚመጥን መልኩ የተራዘመና አነስተኛ ወለድ ያለው የፋይናንስ አቅርቦት እንዲያገኙ ለማድረግ ቀጣይነት ያለው አለምአቀፍ ትብብር አስፈላጊ እንደሆነ ገልጸዋል።
ስብሰባው ፈጣን መፍትሄ የሚሹ የአፍሪካ የፋይናንስ ተግዳሮቶችን ጨምሮ እያደገ በመጣው የዕዳ ስቶክ፣ መድሃኒት ማምረት አቅም ማጠናከር አስፈላጊነትን እንዲሁም በአረንጓዴ መሰረተ ልማት ዙሪያ ውይይት አድርጓል።
የአፍሪካ አገራትን ዘላቂ እና አስተማማኝ ልማትን ከማረጋገጥ አኳያ በራስ አቅም ሀብት ማሰባሰብን ጨምሮ አፍሪካ መር የሆነ አገራቱ በራሳቸው የሚመሩት የኢኮኖሚ ሪፎርም እና የኢንቨስትመንት ፕላን እንዲኖራቸው የአለምአቀፉ ማህበረሰብ ትብብሩን ማጠናከር ያለበት መሆኑን ተሰብሰቢዎቹ መስማማታቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
ስብሰባውን የቤኒን፣ የግብፅ፣ የኢትዮጵያ፣ የማላዊ፣ የሞሪሺየስ እና የዛምቢያ ገንዘብ ሚኒስትሮች፣ የቡድን 7 ሀገራት ገንዘብ ሚኒስትሮች፣ የቀድሞ፣ የወቅቱ እና የሚቀጥለው የቡድን 20 ፕሬዝዳንት (ህንድ፣ ብራዚል እና ደቡብ አፍሪካ) ተወካዮች እንዲሁም የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አኪንዉሚ አዴሲና፣ የአለምአቀፉ ገንዘብ ድርጅት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ሚስ ክሪስታሊና ጂዎርጄቫ እና የአለም ባንክ ፕሬዝዳንት ሚ/ር አጄ ባንጋ ተካፍለዋል።
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
በእንቅልፍ ወቅት የምናያቸውን ሕልሞች እንደፊልም ደግመን ለማየት የሚያስችለን ቴክኖሎጂ ይፋ ሆነ
ጥቅምት 18/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የጃፓን ተመራማሪዎች በእንቅልፍ ወቅት የሚከሰቱ ሕልሞችን በመቅረፅ በፊልም መልክ የሚያጫውት መሣሪያ ይፋ አድርገዋል፡፡
ተመራማሪዎቹ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እና የአዕምሮ ምስልን መውሰድ የሚችሉ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም፤ ሕልምን የሚመዘግብና በፊልም መልክ የሚያሳይ መሣሪያ መፍጠር ችለዋል፡፡
ቴክኖሎጂው ከሕልም ጋር ተያይዞ የሚከሰቱ የነርቭ እንቅስቃሴዎችን ለመመዝገብ ኤም.አር አይ (magnetic resonance imaging) እንደሚጠቀም ተገልጿል፡፡
ይህ ፈጠራ የአንጎል እንቅስቃሴን በመጠቀም አንዳንድ የሕልም ገጽታዎችን የመግለጽ አቅም እንዳለውም ነው የተነገረው።
በቴክኖሎጂው ላይ በተደረገ ሙከራ ያለሙትን ሕልም ይዘት ሳይቀይር የመተንተን አቅሙ ከ70 በመቶ በላይ ትክክል ሆኖ መገኘቱን ኒውስ18 የተባለው ድረ ገጽ ዘግቧል፡፡
ቴክኖሎጂው የአዕምሮ ጤናን ለማሻሻል፣ የግለሰቦችን ስብዕና ለመተንተን እና ከሥነ-ልቦና ጋር ተያያዥ በሽታዎችን ለመመርመር ጥቅም ላይ እንደሚውል ተመላክቷል፡፡
መሣሪያው ዕውን መሆን የቻለው በኪዮቶ በሚገኘው የኤ.ቲ.አር (ATR) ኮምፒውቲሽናል ኒውሮሳይንስ ላቦራቶሪዎች ውስጥ በተደረገ ጥናት መሆኑን ከኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡ https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ: http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ፡ www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ፖለቲካን እንደ ገቢ ማግኛ ዘዴ የሚመለከቱ በመኖራቸው ከፓርቲ ፓርቲ የሚቀያይሩ ፖለቲከኞች በዝተዋል ተባለ
ጥቅምት 16/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ፖለቲከኞች ፍላጎታቸው ስልጣን በመሆኑ አንድ ፓርቲ ላይ የመፅናት ፍላጎት የላቸውም ሲሉ፤ የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ተንታኝ እና ዲፕሎማት አቶ ጥላሁን ሊበን ተናግረዋል፡፡
"በሀገራችን ያሉ ፖለቲከኞች ለአቋቋሙት ፓርቲ ተማኝ የመሆን ብሎም የሚቋቋሙትን ፓርቲ መጠቀሚያ እያደረጉት በመሆኑ አንድ ፓርቲ ላይ መፅናት አይችሉም" ሲሉ ነው አቶ ጥላሁን የገለጹት፡፡
"የዘር ፖለቲካ ላይ የሚያተኩሩ ፓርቲዎች ጭምር ለቆሙለት ብሔር ሳይሆን ለስልጣን እና ጥቅም ያደሉ በመሆናቸው ለፓርቲዎቻቸው ታማኝነት የላቸውም" ሲሉም ተናግረዋል፡፡
"ጥያቄው የስልጣን ነው" የሚሉት አቶ ጥላሁን፤ በዚህ መንገድ አንዱ መንገድ ሲዘጋባቸው ሌላኛውን መንገድ እንደሚፈልጉ አስረድተዋል፡፡ ለዚህም በመንግሥት መዋቅር ውስጥ እየሰሩ ያሉ ተቃዎሚ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችን ጠቅሰዋል፡፡
"ለዚህ መፍትሄው ስልጣንን የሀብት ምንጭ እንዳይሆን ተደርጎ መሰራት አለበት" ያሉት አቶ ጥላሁን፤ ማንኛውም ፖለቲከኛ ፖለቲካን ከጥቅም አኳያ እንዳይመለከት መደረግ እንዳለበትም አመላክተዋል፡፡
ፖለቲካን ንግድ አድርጎ ከማሰብ የሚደረግ ሥራዎች ማስተካከል የሚገባ መሆኑንም የዓለም ዓቀፍ ግንኙነት ባለሙያው ጨምረው ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
"በፖለቲካ ፓርቲ ውስጥ የውስጥ ፖለቲካ ልዩነት ካለ እንዲሁም የርዕዮት ዓለም ልዩነት ከተደረገ ከፓርቲ ፓርቲ መቀየር ግዴታ ሊሆን ይገባል" የሚሉት ደግሞ የንጋት ኮከብ ለኢትዮጵያ ፓርቲ የዶክመንት ዝግጅት ቡድን መሪ አቶ ቸርነት ሰዒድ ናቸው፡፡
ይሁን እንጂ የርዕዮተ ዓለም ልዩነት ብቻ ፓርቲ ለመቀየር ምክንያት አይሆንም የሚሉት አቶ ቸርነት፤ "የምትቆይበት ፓርቲ ከመርህ እየወጣ ከሆነና የመታገያ ቦታው እየጠበበ ከሆነ የተሻለ ምህዳር ወዳለው ፓርቲ መዞር ችግር አይኖረውም" ሲሉም ገልጸዋል፡፡
የንጋት ኮከብ ለኢትዮጵያ ፓርቲ ከሌሎች የተለያዩ ፓርቲዎች የተሰባሰቡ ፖለቲከኞች የሚገኙበት መሆኑን የሚያነሱት አቶ ቸርነት፤ "በፓርቲዎች ላይ የነበሩ ችግሮችን ቀርፎ በአዲስ መንገድ ለመምጣት እየሰራ ያለ ፓርቲ ነው" ሲሉ ከአሐዱ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል፡፡
በአቤል ደጀኔ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
የጊዳ አያና ወረዳ አንዶዴ ዲቾ ቀበሌ ነዋሪዎች "ማንነትን ማዕከል ያደረገ የከፋ እልቂት ከፊታችን ተደቅኗል" ማለታቸው ተገለጸ
ጥቅምት 16/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በምሥራቅ ወለጋ ዞን፣ ጊዳ አያና ወረዳ አንዶዴ ዲቾ ቀበሌ "ማንነትን ማዕከል ያደረገ የከፋ እልቂት ከፊታችን ተደቅኗል፤ ድምፃችንን አሰሙልን" ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች መማጸናቸውን እናት ፓርታ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
ጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም ከአንድ የፀጥታ ኃይል አዛዥ ጋር ከጠዋቱ 4 ሰዓት እስከ 11 ሰዓት ድረስ እንደ ተደረገ በተገለጸ እጅግ ውጥረት የተሞላበት ውይይት፤ የቀበሌው ነዋሪዎች መሣሪያቸውን እንዲያወርዱ ካልሆነ ግን የከፋ ነገር እንደሚጠብቃቸው መገለጹን ፓርቲው መረጃ ደርሶኛል ብሏል።
አዛዡ "ካላወረድክ ... ትታረሳለህ" ማለታቸው የተገለጸ ሲሆን፤ ይህም ነዋሪዎቹ ላይ እጅግ ሥጋት እንዳሳደረባቸው ነው ፓርቲው የገለጸው።
ሥጋቱ ይህ ብቻ ሳይሆን "እኛ መሣሪያ ካወረድን በሰዓታት ልዩነት ሸኔ መጥቶ ይጨፈጭፈናል፤ ይህ ደግሞ ያለፉ ዓመታት የቀን ተቀን ሰቀቀናችን እንደሆነ ማንም ያውቃል" ሲሉም ነዋሪዎቹ መግለጻቸው ተመላክቷል።
"መተማመን በሌለበትና እስከዛሬ ማን አሳልፎ እንደሚሰጠን ባወቅንበትና አሁን በጥቂቱ በመንግሥት ጥረትም፣ በሬያችንን እየሸጥንም ገዝተን በታጠቅነው መሣሪያ ራሳችንን ለማትረፍ የአልሞት ባይ ተጋዳይ በምናደርግበት ወቅት እንዲህ መባሉ እጅግ አስገርሞናል" ብለዋል።
በአካባቢው በግምት 20 ኪ.ሜ ርቀት ላይ መንግሥት ሸኔ ብሎ የሚጠራውና ራሱን ኦ.ነ.ሰ የሚለው ኃይል ከፍተኛ እንቅስቃሴ የሚያካሂድበት ቦታ መሆኑንና እስከ አሁንም በጥቂቱም ቢሆን በዚሁ መንገድ ራሳቸውን እየተከላከሉ እንደቆዩም ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።
በጭንቀት ያሉት እነዚሁ የአንዶዴ ዲቾ ቀበሌ ነዋሪዎች ለሞት አሳልፎ የሚሰጠንን ውሳኔ "ብትቀበሉ ተቀበሉት" መባሉ አስገራሚ ነው ማለታቸውን እናት ፓርታ በመግለጫው አመላክቷል።
"እጅግ ውጥረት የተሞላበት ውይይት ነበር። እባካችሁ መሐል ላይ ያለ የእኛን ደህንነት የሚያስጠብቅ መፍትሔ ስጡን" እያልን ብንማጸናቸውም ሊረዱን ዝግጁ አልነበሩም፤ ብቻ 'ታወርዳለህ ታወርዳለህ' እያሉ ይዝቱ ነበር" የሚሉት ነዋሪዎች "በመጨረሻም ባለመግባባት ሕዝቡም አዳራሹን ጥሎ ወጥቷል" ብለዋል።
"በሰሜኑ ጦርነት ወቅት መላው የጸጥታ ኃይል አካባቢውን ሲለቅ መንግሥት እኛን አምኖ ራሳችንን እየተከላከልን አካባቢውንም እንድንጠብቅ ያደረገ ቢሆንም አሁን ምን ተገኝቶ ቃሉን አጠፈ" ሲሉ መጠየቃቸውም በመግለጫው ተመላክቷል።
ፓርቲው ውይይቱን የመሩት የጸጥታ ኃይል ሥምና ማዕረግ እንደደረሰው የገለጸ ሲሆን፤ "በብዙ ምክንያቶች ለጊዜው መጠቀም አላስፈለገንም" ብሏል።
ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለው መሆኑን የገለጸው እናት ፓርቲ፤ የባሰ ዘግናኝ እልቂት ከመፈጸሙ በፊት በተለይ የመከላከያ ሠራዊት አመራሮች ጉዳዩን በገለልተኝነትና ከነባራዊ ሁኔታ ጋር የተገናዘበ መፍትሔ እንዲሰጡት አሳስቧል።
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
በመዲናዋ 120 የሚሆኑ የመድሀኒት መደብሮች ላይ ፈቃድ እስከመዘረዝ የደረሰ እርምጃ መወሰዱ ተገለጸ
ጥቅምት 16/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ከ1 ሺሕ 6 መቶ የመድሀኒት መደብሮች ዉስጥ 120 የሚሆኑት ላይ ፈቃድ እስከመዘረዝ የደረሰ እርምጃ እንደተወሰደባቸዉ የአዲስ አበባ ከተማ ምግብ እና መድሃኒት ባለስልጣን አስታውቋል፡፡
ባለስልጣኑ በ50 መድሃኒት መደብች ላይ ጊዜያዊ እግድ እንዲሁም በ70 መድሃኒት መደብሮች ላይ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ እርምጃ መወሰዱን ለአሐዱ ገልጿል።
ጊዜያቸው ያለፈ መድሃኒቶችን መሸጥ እንዲሁም ከመድሃኒት አቀማመጥ እና የመድሃኒቶች አያያዝ ላይ ቁጥጥር በማድረግ በመድሃኒት መደብሮች ላይ እርምጃ እንደተወሰድባቸው ተነግሯል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ ከ1 ሺሕ 6 መቶ በላይ መድሃኒት መደብሮች ሕጋዊ ሆነው አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ ለአሐዱ የተናገሩት፤ በባለስልጣኑ የጤና ተቋማት እና ባለሙያዎች ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ ገልገሎ ኦልጅራ ናቸው፡፡
ተቋሙ የመድሃኒት አቀማመጥ፣ የመድሃኒት መደብሩን የክፍሉ የሙቀት መጠን፣ ፍቃድ ያለው ግለሰብ ስለመኖሩ እንዲሁም ስለሚሸጡት መድሃኒት ለደንበኛ በግልጽ የማስረዳት እና ሌሎችን ጉዳዮች እንደሚከታተሉ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡
በቅድሚያ ለመድሃኒት መደብሮች የማስተማር እንዲሁም በክትትል ወቅት የሚስተዋሉ ስህተቶችን የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥራ እንደሚሰጥም ጨምረው አስረድተዋል፡፡
በማስጠንቀቂያ የማይታረሙ መድሃኒት መደብሮች ላይ እስከ ፈቃድ የመሰረዝ አስተዳደራዊ እርምጃ የሚከናወንበት ሁኔታ ስለመኖሩ ተመላክቷል።
በእሌኒ ግዛቸው
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
የ12 ዓመት ታዳጊን ጫካ ውስጥ በማገት 500 ሺሕ ብር የጠየቁ ግለሰቦች እጅ ከፈንጅ መያዛቸው ተገለጸ
ጥቅምት 16/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የ12 ዓመት ታዳጊን ጫካ ውስጥ በማገት 500 ሺሕ ብር የጠየቁ ግለሰቦች እጅ ከፈንጅ ተይዘው ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሚገኝ ፖሊስ አስታውቋል።
በአዊ ብሔ/አስ/በአየሁ ጓጉሳ ወረዳ የቻጃ ክብርታ ቀበሌ ነዋሪ የሆነ ወጣት ጥሩነህ ይግዛውና የጓንጓ ወረዳ ነዋሪ ወጣት ግዛቸው ወርቅነህ የተባሉ ግለሰቦች በቻግኒ ከተማ የ05 ቀበሌ ነዋሪ የሆነውን የ12 ዓመት ህፃን ታጁ የሱፍን ጥቅምት 04/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 በባጃጅ በመውሰድ መሰወራቸው ተገልጿል።
ከዛም በማስከተል ወደ ታጋች ቤተሰብ ስልክ በመደወል 500 ሺሕ ብር እንዲከፍሉ ቢጠይቁም፤ የታጋች ቤተሰብ ከሀያ ሺሕ ብር በላይ የመክፈል አቅም እንደሌላቸው ይገልጻሉ።
በዚህም ምክንያት አጋቾቹ ታዳጊውን በጓንጓ ወረዳ ሰሜን ደገራ በተባለው ጫካ ውስጥ ለ8 ቀናት እንዲቆይ ማድረጋቸውን፤ የአየሁ ጓ/ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት የወንጀል ምርማራ ክፍል ኃላፊ ዋና ሳጅን አዳነ ጥላሁን ተናግረዋል።
"አጋቾቹ ታጋቹን ሕፃን ከ8 ቀናት የጫካ ቆይታ በኋላ ከጥቅምት 11_15/2017 ዓ.ም ድርስ በአየሁ ጓ/ወረዳ በቻጃ ክብርታ ቀበሌ ከጥሩነህ ይግዛው ቤተሰብ ጋር እንዲቆይ አድርገዋል" ሲሉ ያብራሩት የምርመራ ክፍል ኃላፊው፤ ማህበረሰቡ ባደረሰው ጥቆማና የወረዳው ፖሊስ ባደረገው ክትትል ጥቅምት 15/2017 ዓ.ም በቦታው ድርስ በመሄድ እጅ ከፈንጅ በመያዝ በወረዳው ፖሊስ ፅ/ቤት ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል ።
"የድርጊቱ ፈፃሚዎች ለገንዘብ ሲሉ ድርጊት መፈፃማቸውን አምነዋል" ያሉት ዋና ሳጅን አዳነ፤ በዚህ ድርጊት የተሳተፉ ሌሎች ተባባሪ አካላትንም በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ እየሠሩ መሆኑን አብራርተዋል።
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
#አሐዱ_ትንታኔ
ትንታኔውን ለመከታተል ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👇
https://youtu.be/Xo8iHCyL6cY?si=7rX0zPZUPWgw2CAR
"ህወሓት ከሦስት ወራት በኃላ ጉባኤ አዘጋጅቶ እንዲጠራን እንጠብቃለን" ምርጫ ቦርድ
ጥቅምት 16/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ነሐሴ 3/2016 ዓ.ም. በቁጥር አ1162/11/15180 ለህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) በጻፈው ደብዳቤ ፖርቲው በልዩ ሁኔታ በመመዝገብ የህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀትም መስጠቱ ይታወሳል፡፡
በመሆኑም ሰርተፍኬቱ ከሰጠበት ቀን ጀምሮ ታሳቢ በማድረግ በቀጣይ ሦስት ወራት ለጉባኤ እንዲጠሩን እንጠብቃለን ሲሉ የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ዉብሸት አየለ ለአሐዱ ተናግረዋል።
ሰርተፍኬቱ ሁለት መሰረታዊ ሃላፊነት ህወሓት ላይ ይጥላል ያሉት አቶ ውብሸት፤ የመጀመሪያው በ6 ወራት ውስጥ ጉባኤ እንዲያደርጉ መሆኑን ለአሐዱ ተናግረዋል። ጉባኤ ከማድረጋቸው ቀደም ብሎ ከ21 ቀን በፊት ለቦርዱ ማሳወቅም ይገባቸው ነበር ብለዋል።
ጉባኤ አድርገው አመራሮቻቸውን የምርጫ ቦርድ ታዛቢዎች ባሉበት መመርጥ ይጠበቅባቸው ነበር ሲሉም ነግረውናል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ጠቅላላ ጉባዔውን ሊያደርግ መሆኑን በመገናኛ ብዙኃን መነገሩን ተከትሎ፤ ቦርዱ ለፓርቲው የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ጽፎ እንደነበር መዘገቡ ይታወሳል፡፡
ህወሓት የቦርዱን ማሳሰቢያ ወደ ጎን በመተው ጉባኤውን ካደረገ፣ ለጉባኤው እና በጉባኤ ለሚተላለፉ ውሳኔዎች እውቅና እንደማይሰጥ ቦርዱ አሳስቦ ነበር፡፡
ነገር ግን ህወሓት የምርጫ ቦርድን ማሳሰቢያ ወደ ጎን በመተው 14ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን አካሂዷል፡፡
ከዚህም ጉባዔው ማብቂያ ላይ የድርጅቱን ምክትል ሊቀመንበር እና የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ረዳን ጨምሮ 17 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ከስልጣን ማንሳቱን ማስታወቁ ይታወሳል፡፡
አሁን ላይ የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ዉብሸት፤ "ህወሓት የዕውቅና ሰርተፍኬቱን ካገኘበት ቀን ጀምሮ ታሳቢ በማድረግ በቀጣይ ሦስት ወራት ውስጥ አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎችን አሟልቶ ለጉባኤ እንዲጠራን እንጠብቃለን" ሲሉ ነው የተናገሩት፡፡
በአቤል ደጀኔ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ኢትዮጵያ ከኤርትራ ሊያደርጉት የነበረው ጨዋታ ተሰረዘ
ጥቅምት 16/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በቻን ማጣርያ የመጀመርያ ዙር ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጨዋታ ሊያደርጉ መርኃ ግብር ወጥቶላቸው የነበረ ቢሆንም፤ ኤርትራ ከውድድሩ ራሷን በማግለሏ ጨዋታው መሰረዙን ካፍ አስታወቀ።
ኢትዮጵያ በቀጣይ ዙር የሱዳን እና ታንዛንያ አሸናፊን እንደምትገጥም ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።
በአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ (ቻን) ማጣርያ ኢትዮጵያ ከ ኤርትራ ጋር የምታደርጋቸው የደርሶ መልስ ጨዋታዎች በደቡብ ሱዳን ጁባ ብሔራዊ ስታዲየም ጥቅምት 21 እና 24/2017 ይካሄዳል መባሉ ይታወሳል።
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
በጎንደር ከተማ የሚገኙ ከ2 ሺሕ 850 በላይ ተፈናቃዮች በመድሃኒት እጥረት መቸገራቸው ተገለጸ
ጥቅምት 16/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በጎንደር ከተማ ቀበሮ ሜዳ ካምፕ የሚገኙ ተፈናቃዮች የመድሃኒት እጥረት መከሰቱን፤ የጎንደር ከተማ ተፈናቃዮች አስተባባሪ አቶ መላኩ ገብሬ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
በመድሃኒት እጥረቱ ምክንያትም በዚህ ሳምንት ብቻ ሁለት ሰዎች መሞታቸው የተገለጸ ሲሆን፤ በካምፑ ከትግራይ፣ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ እና ከኦሮሚያ ክሌልች የመጡ ተፈናቃች የሕክምና አገልግሎት ለማግኘትና በሪፈር ለመታከም የሚፈቀድላቸው እስከ አዘዞ ጤና ጣቢያ ብቻ መሆኑን አስተባበሪው ተናግረዋል፡፡
ችግሩን ለማስተካከል በሚል በጎ አድራጊዎች ሁሉም ተፈናቃዮች የጤና መድህን አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ቢያደርጉም፤ ጎንደር ሆስፒታል ለመታከምም ይሁን ሌሎች የጤና ተቋማት ሲሄዱ “መድሃኒት የለም” እንደሚባሉ ጠቁመዋል፡፡
"ከዚህ በተጨማሪም 'ከውጪ ግዙ' በመባላቸውና መድሃኒት ባለማግኘታቸው የሚሞቱ ተፈናቃዮች እየበዙ ነው" ሲሉ አስተባባሪው ለአሐዱ ተናግረዋል
አሐዱ ስለ ጉዳዩ ለመጠየቅ ወደ አማራ ክልል ጤና ቢሮ ቢደውልም ምላሽ ማግኘት አልቻለም፡፡
ሆኖም በጎ ፈቃደኞች ባመቻቹላቸው የጤና መድህን አማራጭ ለምን መድሃኒት ማግኘት እንዲችሉ አልተደረገም? ሲል የኢትዮጵያ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ተስፋዬ ወርቁን ጠይቋል፡፡
"ተጠቃሚዎች የመድሃኒት አቅርቦት ችግር ሲያጋጥማቸው ከክልሉ ጤና ቢሮ ጋር በቅርንጫፎቻችን አማካኝነት እንነጋገራለን" ያሉት ዲይሬክተሩ፤ "ያለውን ችግር ለመፍታት የድርሻችንን እንወስዳለን። እስካሁን ግን የደረሰን መረጃ የለም" ሲሉ ለአሐዱ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
በክልሉ ባለው የፀጥታ ችግር መድሃኒቶች ከባህርዳር ማዕከል ወደ ሰሜን ጎንደር እና ሌሎች አካባቢዎች መንቀሳቀስ አለመቻላቸውን አሐዱ ከዚህ በፊት መዘገቡ የሚታወስ ነው፡፡
በእመቤት ሲሳይ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ከሞሪንጋ ወይም ሽፈራው ተክል ዘይት ማምመረት የሚያስችል ፋብሪካ ሥራ ሊጀምር መሆኑ ተገለጸ
ጥቅምት 15/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አርባ ምንጭ ከተማ ዘይሴ ቀበሌ፤ ከሞሪንጋ ወይም ሽፈራው ተክል ዘይት ማምመረት የሚያስችል ፋብሪካ ሥራ ሊጀምር መሆኑ ተገልጿል።
ፕሮጀክቱ በዋናነት ተግባራዊ የተደረገው እና ፋብሪካው የተገነባበት ተክሉ በስፋት የሚበቅልበት አርባ ምንጭ ከተማ ዘይሴ ቀበሌ ነው፡፡
የጣሊያን መንግሥት፣ የተባበሩት መንግሥታት የኢንዲስትሪ ልማት ድርጅት እና የደቡብ ኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ልማት ኮርፖሬሽን ከ6 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ያስገነቡት መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል፡፡
በተባበሩት መንግሥታት የኢንደስትሪ ልማት ድርጅት ተወካይ እና የፕሮጀክቱ ቴክኒካል አማካሪ ዶክተር ለምለም ሲሳይ፤ "የሞሪንጋ ተክል ወይም ሽፈራው በአካባቢው ማህበረሰብ "አለኮ" በመባል የሚታወቅ ቢሆንም ከምግብነት ባለፍ በሀገር አቀፍ እና በአለም ገበያ ላይ ተፈላጊ መሆኑ ባለመታወቁ ብዙ ትኩረት አልተሰጠው" ብለዋል፡፡
"የፕሮጀክቱ ዋና አላማ ማህበረሰቡ የሚያውቀውን ተክል በማምረት እና በማቀነባበር ወደ አለም ገበያ እንዲቀርብ ማድረግ ነው" ሲሉም አንስተዋል፡፡
ተክሉ ማህበረሰቡ ለዕለት ተእለት ከሚጠቀምበት ምግብ ባለፈ በፋብሪካ በማቀነባበር የሻይቅጠል ምርት፣ ዘይት እንዲሁም በኪኒኒ መልክ መጠቅም እንደሚቻል በውስጡም የተለያዩ ቫይታሚኖች እንዳሉት፤ በአርባ ምጭ ዩንቨርስቲ በተደረገው ጥናት እና ምርምር መረጋገጡን ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
የሞሪንጋ ወይም የሽፈራው ተክልን በዘመናዊ መልኩ አቀነባብሮ እና አምርቶ ለገበያ ማቅረብ ለኢኮኖሚው ከሚያበረክተው አስተዋጾ በተጨማሪ የጤና ጠቀሜታ እንዳለው የተናገሩት ደግሞ፤ በተባበሩት መንግሥታት የኢንደስትሪ ልማት ድርጅት የምግብ ዋስትና እና የመሰረተ ልማት ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ፌሪድ ኮንጎ ናቸው፡፡
ተክሉ በወቅቶች መፈራረቅ የማይደርቅ በመሆኑ የምግብ ዋስትናን በማረጋጋጥ አስተዋጾ እንዳለው አቶ ፌሪድ ገልጸዋል፡፡
"ፕሮጀክቱ በገጠር የሚገኙ ሴቶች ራሳቸውን ከማብቃት ባለፍ ቤተሰባቸውን በኢኮኖሚ እንዲደግፉ ያስችላቸዋል" ነው ያሉት፡፡
ሞሪንጋን ወይም ሽፈራውን ለምግብነት ከመጠቅም ባለፈ የተለያዩ የብስኩት አይነቶችን መስራት እንደሚቻልም አንስተው፤ "ከሌሎች ምግቦች ጋር በመቀላቀል ለተማሪዎች ምግባ ላይ መጠቀም ይቻላል" ሲሉም ለአሐዱ አስረድተዋል፡፡
መሠረተ ልማቶችን በማሟላት እና ፖሊሲ በማውጣት የሀገር ውስጥ ገበያ ትስስርን ከመፍጠር አንጻር የክልሉ መንግሥት የሚያደርገው ትብብርም የሚበረታታ መሆኑን ተናግረው፤ ፋብሪካው በቅርቡ ሥራ እንደሚጀምርም ጠቁመዋል፡፡
በፍቅርተ ቢተው
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
በጋምቤላ ክልል ኮንዶም በውድ ዋጋ እየተሸጠ ነው በሚል የተሰራጨው መረጃ ከእውነት የራቀ ነዉ ተባለ
ጥቅምት 15/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በጋምቤላ ክልል የኮንዶም ስርጭት የለም እንዲሁም በውድ ዋጋ እየተሸጠ ነው በሚል የተሰራጨው መረጃ ከእውነት የራቀ ነዉ ሲል የክልሉ ጤና ቢሮ አስታውቋል፡፡
በጋምቤላ ክልል ኮንዶም ከመቶ ብር በላይ በሆነ ዋጋ እየተሸጠ እንደሚገኝና፤ በክልሉ ከፍተኛ የሆነ የኤች አይ ቪ ኤድስ ስርጭት ስለመኖሩ ከዚህ በፊት መዘገቡ ይወሳል።
ከዚህ ጋር ተያይዞም የጤና ቢሮው ኃላፊ ዶክተር አቤል አሰፋ፤ በክልሉ የኮንዶም ስርጭት የለም፣ በከፍተኛ ዋጋ እየተሸጠ ነው ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ሃሰተኛ ነው ሲሉ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
ኃላፊው አክለውም፤ በተለይም ኤች አይ ቪ ኤድስን ለመከላከል የሚያስችሉ ተግባራት በስፋት እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸው፤ በዚህም በክልሉ የበሽታው ተጠቂ ቁጥር ከ3.69 ወደ 3.2 በመቶ ዝቅ ማለቱን ተናግረዋል፡፡
በዚህም መሰረት የክልሉ ጤና ቢሮ ኮንዶምን በነፃ እያሳራጨ እንደሚገኝ ጠቅሰው፤ ያልተረጋገጠ መረጃን የሚያሰራጩ አካላት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አሳስበዋል፡፡
በተጨማሪም ሌሎች አካላትም ለገበያ በሚቀርቡት ኮንዶም ላይ የዋጋ ንረት እንዲይኖር ቁጥጥር እንደሚያደርጉም ጠቁመዋል።
በፅዮን ይልማ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
"አብያተ እምነት ተቋማት የሰማያዊ መንግሥት ተልዕኮ ማስፈጻሚያ ኤምባሲዎች በመሆናቸው ጥበቃ ሊደረግላቸው ይገባል" እናት ፓርቲ
ጥቅምት 15/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) እናት ፓርቲ አብያተ እምነት ተቋማት የሰማያዊ መንግሥት ተልዕኮ ማስፈጻሚያ ኤምባሲዎች በመሆናቸው ጥበቃ ሊደረግላቸው ይገባል ሲል፤ በወቅታዊ ጉዳዮች እና የኮሊደር ልማትን በተመለከተ በሰጠዉ መግለጫ አሳስቧል።
ፓርቲዉ በመግለጫው፤ "ከኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ ከተማና ዙሪያዋ በሚገኙ ከተሞች የአምልኮ ሥፍራዎች ሕጋዊ ይዞታዎች ድንበር በማን አለብኝነት እየፈረሰ እንዳለ መረጃዉ ደርሶኛል" ብሏል።
የአብያተ እምነት ተቋማት ለሰው ልጅ አጠቃላይ መንፈሳዊና አእምሯዊ ልዕልና ያላቸው ሚና አይተኬ እንደሆነም ገልጿል።
"እየፈረሱ ካሉት በዋቢነት የሰበታ ጌቴሴማኒ ቤተደናግል ጠባባት የሴቶች ገዳም ይዞታ ከክብር በወረደ አኳኋን እንዲፈርስ የተደረገ ሲሆን፤ ከየካቲት አስራ ሁለት አደባባይ ከፍ ብሎ ያለውና ከአምስቱ ዓመት የፋሽስት ጣልያን ወረራ ወቅት ጋር ቀጥተኛ ተያያዥ ታሪክ ያለው የአገር ባለውለታው የምስካዬ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ይዞታም ጠባብ የሆነውን ዐውደ ምሕረት የበለጠ በማጥበብ ከፊት ለፊቱ የገዳሙና የገዳሙ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ፈረሳ እንደሚከናወንባቸው ፓርቲያችን መረጃ ደርሶታል" ብሏል።
እነዚህን በዋቢነት ተጠቀሱ እንጂ ፈረሳው ያነጣጠረባቸው በአዲስ አበባ ከተማና አካባቢው የሚገኙ አብያተ እምነት ቁጥር ብዙ እንደሆነ መረዳቱን ፓርቲው ገልጿል።
ስለሆነም "መንግሥት ከዚህ ነባር ሃይማኖት አካሄድ እንዲታቀብና የአብያተ እምነት ቅጥሮችን ማፍረሱን በአፋጣኝ እንዲያቆም በጽኑ እናሳስባለን" ሲልም በመግለጫው አስታዉቋል፡፡
በፅዮን ይልማ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ