ahaduradio | Unsorted

Telegram-канал ahaduradio - AHADU RADIO FM 94.3

19349

አሐዱ ራድዮ 94.3 Your source for top local and international news and analysis. "Voice of Ethiopian" የአሐዱ የቴሌግራም ቻናል ቤተሰብ በመሆን ወቅታዊና እውነተኛ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ

Subscribe to a channel

AHADU RADIO FM 94.3

ሁዋዌ በሚያዘጋጀው የአይሲቲ ውድድር አሸናፊ የሆኑ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ሸለመ

👉ኩባንያው
2024-2025 ውድድርን በይፋ አስጀምሯል

ጥቅምት 21/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በሁዋዌ የአይሲቲ ውድድር ሀገር አቀፍ እና አህጉር አቀፍ የፍጻሜ ውድድሮች የተሳተፉ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን በዛሬው ዕለት ሸልሟል።

ኩባንያው ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በሚያዝጋጀው በዚህ ውድድር በዚህ ዓመት ብቻ ከ2 ሺሕ 500 በላይ ተማሪዎች ውድድሩን ለመቀላቀል የተመዘገቡ ሲሆን፤ 120 ያህሉ ለሀገር አቀፍ የፍፃሜ ውድድር አልፈው የተሳትፎ ሰርተፍኬት ወስደዋል፡፡

ከእነዚህም ውስጥ ዘጠኙ ኢትዮጵያን ወክለው በቱኒዚያ በተካሄደው ክፍለ አህጉራዊ ውድድር በመሳተፍ የሦስተኛ ደረጃን ሽልማት ማግኘታቸው ይታወሳል። በተጨማሪም ሦስት ተማሪዎች ያሉት ቡድን በቻይና ሼንዘን ከተማ በተካሄደው አለም ዓቀፍ የፍፃሜ ውድድር አስደናቂ ስኬት አስመዝግቧል።

በሽልማት ሥነ ሥርዓቱ ላይ የሁዋዌ ኢትዮጵያ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሚስተር ሊሚንግ የ፤ የአይሲቲ ውድድሩን አስፈላጊነት ሲናገሩ “የሁዋዌ አይሲቲ ውድድር ለወጣቶቻችን በዋጋ የማይተመን ጠቀሜታ ያለው በመሆኑ ለግል እና ለሙያ እድገታቸው አጋዥ ሆኖ ያገለግላል።” ብለዋል፡፡

አክለውም፤ በዚህ ውድድር ላይ በመሳተፍ፣ ተማሪዎች ቴክኒካል ክህሎቶቻቸውን በማጎልበት እና ለተለዋዋጭ የሥራ ገበያ በማዘጋጀት በዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ልምድ እንደሚያገኙበት ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም ሁዋዌ ቀጣዩን ትውልድ በመሰል የቴክኖሎጂ ክህሎት ለማገዝ የሚያዘጋጃቸውን ፕሮግራሞች አጠናክሮ ለመቀጠል ያለውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩን በመወከል የተገኙት ዶ/ር ሰሚነው ቀስቅስ በበኩላቸው፤ “እንደ ሁዋዌ አይሲቲ ውድድር ያሉ ውድድሮች ወጣቶችን በወሳኝ ቴክኒካል ክህሎት ከማስታጠቅ ባለፈ ሂሳዊ አስተሳሰብን፣ የቡድን ሥራን፣ ችግር አፈታትን፣ እና ፈጠራን ያዳበሩ በቴክኖሎጂ መልክዓ ምድር ውስጥ የሚበለጽጉ የወደፊት መሪዎችን እና ፈጣሪዎችን ለማፍራት ያግዛሉ።” ብለዋል።

በዝግጅቱ ሁዋዌ 9ኛውን ዓለም አቀፍ የ2024-2025 የአይሲቲ ውድድርን በይፋ ያስጀመረ ሲሆን፤ ምዝገባው እስክ ታህሳስ 2017ዓ.ም መጨረሻ ድረስ ክፍት እንደሚሆን ተነግሯል።

በስነ ስርዓቱ ላይ በሀገር አቀፍ የፍፃሜ ውድድር ባስመዘገቡት ውጤት በክላውድ ትራክ፣ በኮምፒውቲንግ ትራክ እና በኔትወርክ ትራክ የተወዳደሩ ዘጠኝ ተማሪዎች፤ በደረጃቸው የተለያዩ ሽልማቶችን አግኝተዋል። ኩባንያው ተማሪዎችን ለውጤታማነት ላበቁ የዩኒቨርሲቲ መምህራንም እውቅና ሰጥቷል።

የሁዋዌ አይሲቲ ውድድር በመረጃና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ (ICT) መስክ የተማሪዎችን ክህሎት ለማሳደግ እና ለማሳየት የተነደፈ ዓመታዊ ውድድር ነው።

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በስፔን በተከሰተ የጎርፍ መጠለቅለቅ የሟቾች ቁጥር 95 መድረሱ ተገለጸ

ጥቅምት 21/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) “ቀዝቃው ጠብታ” ወይም በሀገሪቱ ቋንቋ ጎታ ፍሬያ በመባል የሚታወቀው ክስተት በፈጠረው ከባድ ዝናብ ሳቢያ ሀገሪቱ በጎርፍ መጥለቅለቋን ተከትሎ የሟቾች ቁጥር 95 መድረሱ ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች ጠፍተዋል የተባለ ሲሆን፤ ሌሎች በሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ መብራት እና የስልክ አገልግሎት ማጣታቸው ተነግሯል፡፡

ከዚህ በኋላም ደመናዎቹ በአንድ ቦታ ላይ ለሰዓታት ሊቆዩ ስለሚችሉ፤ ከዝናብ ጎን ለጎን ኃይለኛ በረዶዎችን እና አውሎ ነፋሶች ሊፈጠሩ እንደሚችል የተገለጸ ሲሆን፤ ይህም ከፍተኛ የሆነ የሰው ሕይወት ሊቀጥፍ እንደሚችል እየተዘገበ ይገኛል፡፡

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ሳይንቲስቶች የሜዲትራኒያን ባህር ውሃ በፍጥነት እየሞቀ እና ከመደበኛው የሙቀት መጠን ከፍ ብሎ እንደሚወጣ እያስጠነቀቁና ከሞቃታማ አየር ተጨማሪ እርጥበትን ሊይዝ ስለሚችል ይህም ለከባድ ዝናብ መፈጠር እድሉ ከፍተኛ ነው እያሉ ይገኛሉ፡፡

እንደ ዘጋርዲያን ዘገባ ከሆነ የሟቾች ቁጥር አሁን ካለውም በከፍተኛ ሁኔታ ሊያሻቅብ ይችላል፡፡

ስፔን ለሦስት ቀናት የሚቆይ ብሄራዊ ሀዘን ቀንም ያወጀች ሲሆን፤ የነፍስ አድን ሰራተኞችም በተጎዱት አካባቢዎች ነብስ የማዳን ሥራቸውን አጠናክረው መቀጠላቸው ተገልጿል፡፡

የአደጋ ጊዜ አገልግሎት ወደ አንዳንድ አካባቢዎች ለመድረስ እየታገሉ ባሉበት ወቅት፤ በጎርፍ በተጥለቀለቀባቸው ስፍራዎች የጠፉ ሰዎችን አፋጉን የሚሉ የሬዲዮና የቴሌቭዥን ጣቢያዎች በመቶዎች የሚቆጠሩ የእርዳታ ጥሪዎችን እየደረሳቸው ነው ተብሏል።

የስፔን የአየር ሁኔታ አገልግሎት በቫሌንሲያ ክልል በምትገኘው ቺቫ ማክሰኞ ዕለት በስምንት ሰዓት ውስጥ የጣለው 491 ሚ.ሜ. የዝናብ መጠን በአንድ ዓመት ውስጥ ሊጥል ከሚችለው ዝናብ ጋር እኩል የሆነ መጠን ያለው ዝናብ መጣሉን በመግለጽ፤ የጎርፍ አደጋው የ51 ሰዎችን ሕይወት መቅጠፉን ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በአማራ ክልል እየተስፋፋ በመጣው የወባ በሽታ ምክንያት የመድሐኒት ዕጥረት ሊያጋጥም ይችላል ተባለ

👉በክልሉ በየሳምንቱ ከ75 ሺሕ በላይ የወባ ታማሚዎች መኖራቸው ሪፖርት ይደረጋል


ጥቅምት 21/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በአማራ ክልል በሁሉም አካባቢዎች በሚባል ደረጃ የወባ በሽታ ስርጭት እየተስፋፋ ስለመሆኑ መገለጹ ይታወሳል፡፡

አሐዱም "ከበሽታው ቁጥጥር ጋር በተያያዘ ምን እየተሰራ ነው?" ሲል፤ የክልሉን የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጠይቋል።

የኢንስቲትዩቱ የወባ በሽታ አስተባባሪ አቶ ዳምጤ ላንክር እንደገለፁት ከሆነ፤ በየሳምንቱ ከ75 ሺሕ በላይ የወባ ታማሚዎች መኖራቸው ሪፖርት እየተደረገ ነው፡፡

"ከዚህ አንፃር የበሽታውን ስርጭት መቆጣጠር ካልተቻለ በክልሉ ከፍተኛ የመድሐኒት ዕጥረት ማጋጠሙ አይቀሬ ሊሆን ይችላል" ሲሉ ያለውን ስጋት ጠቁመዋል።

"በአማራ ክልል 80 ወረዳዎች የወባ በሽታ ሥርጭት ተከስቷል" ያሉት አስተባበሪው፤ እነዚህ 80 ወረዳዎች የክልሉን 90 በመቶ የሚሸፍኑ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ከ80ዎቹ ወረዳዎች ውስጥ በ40 ወረዳዎች በሽታው በከፍተኛ ሁኔታ እየተሰራጨ መሆኑንም አቶ ዳምጤ ላንክር ለአሐዱ ተናግረዋል።

አያይዘውም ስርጭቱን ለመግታት እስከ ታህሳስ 30 የሚቆይ ጤና ጣቢያ መር የማህበረሰብ አቀፍ የወባ መከላከል ዘመቻ መጀመሩን ተናግረዋል፡፡

በዚህም በሳምንት አንድ ቀን ነዋሪዎችን ያሳተፈ የአካባቢ ጥበቃ ቁጥጥር እንደሚደረግ በመግለጽ፤ ማህበረሰቡም በነቂስ ወጥቶ እንዲሳተፍ አስተባባሪው ጠይቀዋል።

በወልደሀዋርያት ዘነበ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በመዲናዋ መኪኖች በሚያመነጩት በካይ ጋዝ የተነሳ በዓመት ከ1 ሺሕ 600 በላይ ሰዎች ሕይወት ያልፋል ተባለ

ጥቅምት 21/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በአዲስ አበባ ከተማ መኪኖች በሚያመነጩት በካይ ጋዝ የተነሳ በዓመት ከ1 ሺሕ 600 በላይ ሰዎች ሕይወት እንደሚያልፍ አንድ ጥናት አመላክቷል።

ጥናቱ እንዳመለከተው ነዳጅ በሚጠቀሙ  ተሽከርካሪዎች የሚመነጨው በካይ ጋዝ የሕብረተሰቡ ስጋት እየሆነ መጥቷል።

ጥናቱ የአዲስ አበባ ከተማ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ከሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን የተጠና መሆኑን ከባለስልጣን መስርያቤቱ ሰምተናል።

በአዲስ አበባ ከተማ ከተሽከርካሪዎች የሚመነጨው በካይ ጋዝ ምክንያትም የበርካቶችን ሕይወታቸው የሚቀጥፍ መሆኑንና፤ በዓመት ቢያንስ ከ1 ሺሕ 600 የመዲናዋ ነዋሪዎች ሕይወታቸውን እንደሚያጡ የአዲስ አበባ ከተማ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ለአሐዱ ተናግሯል።

ባለስልጣኑ ከተለያዩ ተራድኦ ድርጅቶች ጋር በመሆን ባደረገው ጥናት መሰረት፤ ከተሽከርካሪዎች የሚመነጨው በካይ ጋዝ በመዲናዋ ኗሪዎች ላይ ከፍተኛ የጤና እክል እየፈጠረ መሆኑንም ተነግሯል።

በዚህ የተነሳም "በርካቶች የመተንፈሻ ችግር ጋር በተያያዘ የጤና እክል እየገጠማቸው ይገኛል" ተብሏል።

በአዲስ አበባ ከተማ ያለው ከተሽከርካሪዎች የሚመነጭ በካይ ጋዝ ልቀትም፤ አስጊ በሚባል ደረጃ ላይ መድረሱን የባለስልጣኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዲዲ ዲሪባ ለአሐዱ ተናግረዋል።

አቶ ዲዲ ዲርባ ለችግሩ መላ እየተፈለገለት መሆኑን ጠቅሰው፤ አሁን ላይ በከተማ መስተዳድሩ የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎችን እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በዚህ ረገድ እያደረገው ያለውን እንቅስቃሴ ለውጥ እየመጣ መሆኑንም አስረድተዋል።

የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ በዓለም አቀፍ ደረጃ አንገብጋቢ ከሚባሉ ጉዳዮ መካከል አንዱ መሆኑን የጠቀሱት ዋና ሥራ አስኪያጁ፤ ኢትዮጵያ ችግሩን ለመቅረፍ በብርቱ እየሰራች እንደምትገኝ ለአሐዱ ተናግረዋል።

ከችግሩ ስፋት አንፃር በአዲስ አበባ ላይ ያለው ችግር አሳሳቢ መሆኑን መረዳት ችለናል።

በአማኑዔል ክንደያ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

"አሁንም ለድርድር እና ምክክር ዝግጁ ነን" ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

ጥቅምት 21/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት 3ኛ መደበኛ ስብስባውን በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ አብን አባል የሆኑት አቶ አበባው ደሳለኝ ጥያቄ አቅርበው ነበር፡፡

በጥያቄያቸውም "በአማራ ክልል በሁለት ወራት ውስጥ የጸጥታውን ሁኔታ ለመቆጣጠር የታሰበ ቢሆንም፤ ከአንደ ዓመት በላይ ቆይቷል" ብለዋል፡፡

አባሉ "መንግሥት የሰላምና የጸጥታ ችግሩን ለመፍታት እየሄደበት ያለው ርቀት ወታደራዊ ብቻ ነው ስለምን ፖለቲካዊ መፍትሄ ማምጣት አልተቻለም?" ሲሉም ጠይቀዋል፡፡

ይህንን በተመለከተ ለምክር ቤት አባላት ምላሽ ለመስጠት በምክር ቤት የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሲመልሱ፤ "ሰው አመዛዛኝ ፍጡር ነው" ያሉ ሲሆን፤ "ለዲሞክራሲ ስርዓት መነጋገሩ የተሻለ ነው" ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒሰትር ዐቢይ ጥያቄ ያቀረቡላቸውን የምክር ቤት አባል "እርሶ ካገዙን አሁንም ከድርድር እና ምክክር ዝግጁ ነን" ብለዋል፡፡

"ከዚህ ቀደም ሽማግሌዎች ልከን ነበር ግን በእንብርርክክ ሄደው የመጣው ውጤት የምትመለከቱት ነው በዚህ ምክንያት ሊሳካልን አልቻለም" ብለዋል፡፡

"ሰላም እንፈልጋለን" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፤ ጦርነት በፍጹም መንግሥታቸው የሚፈልገው ጉዳይ እንዳልሆነ ለጥያቄው ምላሽ ሲሰጡ ተናግረዋል፡፡

በአቤል ደጀኔ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በኢትዮጵያ 3 ወታደራዊ ፋብሪካዎችን ወደ ሥራ እንደሚገቡ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ገለጹ

ጥቅምት 21/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ኢትዮጵያ በዚህ ዓመት 72 ፋብሪካዎች ወደ ሥራ የሚገቡ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ተገኝተው በሰጡበት ማብራሪያ ተናግረዋል፡፡

ከነዚህ ውስጥ ዘጠኝ የጨርቃ ጨረቅ ፋብሪካ፣ 41 የምግብና መጠጥ ፋብሪካ፣ አራት ኮንስትራክሽንና ኬሚካል ፋብሪካዎች እንዲሁም ትልቅ እምርታ ሊያመጡ ይችሏሉ ያሉት ትልቅ ሦስት የወታደራዊ ፋብሪካዎች ወደ ሥራ ይገባሉ ብለዋል፡፡

በዚህም ዓመት ከኢንዱስትሪ 12 ነጥብ 8 ዕድገት እንደሚጠበቅ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ የኮንስትራክሽን ዘርፉ 12 ነጥብ 3 ዕድገት እንደሚጠበቅበትም ተናግረዋል፡፡

"በዚህ ዓመት ኢንዱስትሪ የተሻለ አፈፃፀም ይኖረዋል ተብሎ የተጠበቀው፤ ከኢትዮጵያ ታምርት በተገኘው የተሻለ ማሳያ በመሆኑ ነው" ብለዋል፡፡

ከኢንዱስትሪ ጋር ተያይዞ ይነሱ የነበሩ ችግሮችን በተለይም እንደ መብራት ያሉትን ችግሮች ለመፍታት የተሻለ ሥራ መሰራቱንም ለምክር ቤቱ አባላት ገልጸዋል፡፡

ከመከላከያ ጋር ተያይዞ በርካታ ምርቶች ከውጪ እየተገዙ የቆዩ መሆኑን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ "ይህ ፋብሪካ ከውጪ የሚገቡ የመካለከያ ግብዓቶችን በሀገር ውስጥ ማምረት ያስችላል" ብለዋል፡፡

በአቤል ደጀኔ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

ከቅርቡ ፍራንኮቫሎታን በሚመለከት ማስተካከያ እንደሚደረግ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር ዐብይ አህመድ አስታወቁ

ጥቅምት 21/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ስብሰባውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት እያካሄደ ነዉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከምክር ቤት አባላት ለተነሳላቸዉ ጥያቄ ምላሽ እና ማብራሪያ በመስጠት ላይም ይገኛሉ።

ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ማብራሪያ ከሰጡባቸው ጉዳዮች ውስጥ በቅርቡ ከማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ጋር ተያይዞ ስለተፈቀደዉ ፍራንኮቫሉታ ሲሆን፤ "ለሀገሪቱ ከሚያስገኘዉ ገቢ በላይ ለመጭበርበር የተመቸ በመሆኑ ከቅርቡ ፍራንኮቫሎታን በሚመለከት ማስተካከያ ይደረጋል" ብለዋል፡፡

በሌላ መልኩ "የኢንዱስትሪ ዘርፉን ለማነቃቃት ከፍተኛ ሥራ ተከናዉኗል፣ የኢንዱስትሪ ዘርፉም በተያዘዉ በጀት አመት 12 ነጥብ 8 በመቶ እንደሚያድግ ይጠበቃል ያሉ ሲሆን፤ በተለይ ከኋይል አቅርቦት ጋር ተያይዞ ሲነሱ የነበሩ ችግሮችን በመፍታት ረገድ የተሻለ ስራ ተከናዉኗል"ብለዋል።

አክለዉም የኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም 67 በሞቶ ማድረስ ተችሏል ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

"አዲስ አየር መንገድ ለመገንባት ጥናት ተደርጎ ተጠናቋል" ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

ጥቅምት 21/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ 124 አዳዲስ አውሮፕላኖችን ማዘዙን ገልጸዋል።

"124 አውሮፕላኖችን ማዘዝ ቀላል ነገር አይደለም" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ "ትልቅ ስኬት ነው" ሲሉ ገልጸውታል።

እንዲሁም "አየር መንገዱ በዓመት ከ20 እስከ 25 ሚሊየን ተጓዦችን ያስተናግዳል" ሲሉ ለምክር ቤት አባላቱ ተናግረዋል።

አክለውም፤ "በአፍሪካ ትልቁን የአውሮፕላን ማረፊያ ለመገንባት እንቅስቃሴ ተጀምሯል፡፡" ብለዋል

የተጓዦችን ቁጥር ከፍ ለማድረግ ከ100 ሚሊየን እስከ 130 ሚሊየን ተጓዦችን ማስተናገድ የሚችል አየር መንገድ ለመገንባት የሚያስችል ጥናት ተደርጎ መጠናቀቁን ገልጸዋል።

"ይህም የኢትዮጵያ አየር መንገድን በአፍሪካ ትልቁ የአውሮፕላን ባለቤት ብቻ ሳይሆን፤ ግዙፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ያለው ተቋም ያደርገዋል፡፡" ብለዋል።

"ይሔ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዕድገት አንዱ ማሳያ ነው" ሲሉም ተናግረዋል።

በፍርቱና ወልደአብ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

"መንግሥት የሰላም እና ጸጥታ ችግር ለመፍታት እየሔደ ያለው አካሔድ ወታደራዊ ነው ለምን ፖለቲካዊ አካሄድን አልደፈረም " ዶ/ር አበባው ደስአለው

ጥቅምት 21/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) መንግሥት የሰላም እና ጸጥታ ችግር ለመፍታት እየሔደ ያለው አካሔድ ወታደራዊ ነው እስካሁን ለምን ፖለቲካዊ አካሄድን አልደፈረም ሲሉ የምክር ቤት አባሉ ዶ/ር አበባው ደስአለው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት 3ኛ መደበኛ ስብስባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የተገኙበት በመካሄድ ላይ ይገኛል።
በስብሰባውም የምክር ቤት አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥያቄዎች እየቀረቡላቸው ይገኛል

ጥያቄዎችን ካቀረቡት አባላት መካከል የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት እና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) አባል የሆኑት ዶ/ር አበባው ደሳለው ይገኙበታል፡፡

ዶ/ር አበባው በጥያቄያቸው "በባለፈው ዓመት መጨረሻ የበጀት ዓመቱ መዝጊያ ሰኔ 28 ወቅት ያነሳናቸው በርካታ ከህዝብ ጥያቄዎች ነበሩ። ነገር ግን እነዛ ጥያቄዎች ስላልተመለሱ ከዛ ብዙም ለየት ያለ ጥያቄ አይደለም የምንጠይቀው ምክንያቱም ችግሮቹ እየተባባሱ ስለመጡ ብለዋል፡፡

"በመላው ሀገሪቱ ያለው ጅምላ የንጻሃን ግድያ፣ ህገወጥ ጅምላ እስር፣ እገታ፣ ጾታዊ ጥቃት ፣ መፈናቀል፣ ከፍተኛ ከኑሮ ውድነት፣ አግባብ ያልሆነ የቤቶች ፈረሳ ያኔም ነበረ አሁንም ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው።" ብለዋል

"በአሁን ሰዓት በመላ ሀገሪቱ ከፍተኛ የህዝብ ብሶት አለ።" ያሉት ዶ/ር አበባው፤ በተለይ በአማራ ክልል ያለው ችግር ደግሞ አጠቃላይ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ህይወት ምስቅልቅል እንዲሆን ያደረገ ነው። ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በአማራ ክልል የመንግስት ኃይሎች ፀጥታውን በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ ለመቆጣጠር ነበር ዘመቻ የጀመሩት ነገር ይኸው ከአንድ ዓመት በላይ ሆነ እንጂ ችግሩ ይበልጥ እየከፋ ሄደ እንጂ እየተሻሻለ አይደለም። አሁንም ንጹሃን ዜጎች በከባድ መሳሪያ እና በድሮን እየሞቱ ነው፣ ሲቪል ተቋማት የሆኑ ጤና ጣቢያዎች ፣ ትምህርት ቤቶች እየወደሙ ነው።

በአዲስ አበባ፣ በአማራ ክልል እና በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች እስር ቤቶች የተጨናነቁት ያለ ፍርድ በታጎሩት አማራዎች ነው። ሲሉም ተናግረዋል፡፡

አክለውም፤ "የኛ የምክር ቤት አባል አቶ ክርስቲያን ታደለን ጨምሮ የክልል ምክር ቤቶች አባላት ሳይቀሩ ከአንድ ዓመት በላይ ሆነ ተብሎ በሚመስል ሁኔታ ያለ ፍርድ እየተመላለሱ ነው ያሉት። ፍርድ ሳያገኙ ከአንድ ዓመት በላይ አስቆጥረዋል።" ያሉ ሲሆን፤ "ከዚህም የሚብሱ አሉ። ፖለቲከኞች ፣ ጋዜጠኞች፣ አንቂዎች ለሁለት ዓመት ያክል ያለ ፍርድ የተቀመጡ አሉ በወይኒ ቤቶች።" ሲሉ ገልጸዋል፡፡

"ከፍተኛ የኑሮ ውድነቱን ስናይ የኢኮኖሚ ማሻሻያ አድርገናል፣ የብር የመግዛት አቅምን አዳክመን ኢኮኖሚው እንዲንሰራራ እናድረጋለን በሚል የተለያዩ ድጎማዎችን ተደርገዋል የደመወዝ ጭማሪ እስካሁን መንግስት ሰራተኛው ክሲ ውስጥ አልገባም ኑሮ ውድነቱ ግን እጅግ በጣም አሻቅቧል።" ሲሉም አንስተዋል፡፡

በኮሪደር ልማት ሰበብ በብዙ ሺዎች በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶች ፈርሰው የተለያየ አቤቱታ በተለያየ መገናኛ ብዙሃን ዜጎች እያሰሙ ነው በተለይ አዲስ አበባ ችግሩ በጣም የገዘፈ ነው። ሲሉም ዶክተር አበባው ተናግረዋል፡፡

"በአጠቃላይ እነዚህን ችግሮች ስናይ ከሰላምና ፀጥታው ጋር አብረው የሚሄዱ ናቸው።" ያሉም ሲሆን፤ "ቅድሚያ የሰላምና ፀጥታ ችግሩን ብንፈታው ሌሎች ችግሮችን አብረን እናስወግዳለን። እዛ ላይ ማተኮር አለብን።" ብለዋል፡፡

አክለውም መንግስት የሰላምና ፀጥታ ችግሩን ለመፍታት እየሄደ ያለው አካሄድ እስካሁን ወታደራዊ ነው፤ ፖለቲካዊ አካሄድ ለምን አልደፈረም? ለምንድነው ፖለቲካዊ መፍትሄ ላይ የደከመው? ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

እንዲሁም ለእውነተኛ ድርድርና ውይይት በይፋ ጥሪ አቅርቦ ችግሩን ለምንድነው ለመፍታት የማይጠጋው?፣ የሰላም መፍትሄ አካል አንዱ የጅምላ እስር፣ የጅምላ ግድያ ማቆም ነው። ይሄ መቼ ነው የሚቆመው? የሚሉ ጥያቄዎችን አንስተዋል፡፡

በመጨረሻም የኢኮሮሚ ችግሩን ለመፍታት ዜጎች ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሰው መስራት አለባቸው፡፡ ያን ላለፉት በርካታ ዓመታት ማድረግ አልተቻለም፡፡ ዜጎች በነጻነት እና በሰላም ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሰው እንዲሰሩ መንግስት የሚያስችለው መቼ ነው?" ሲሊ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዶ/ር አበባው ደስአለውን ጥያቄ ጨምሮ ሌሎች፤ ከምክር ቤቱ አባላት ለሚቀርብላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩን ምላሽና ማብራሪያ ተከታትለን ይዘን የምንመለስ ይሆናል፡፡

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

መልካም ቀን!
አሐዱ ሬድዮ 94.3  የኢትዮጵያውያን ድምፅ!

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የመኖ የዋጋ ጭማሪ ወደ ውጭ አገራት የሚላከው የስጋ ንግድ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ አሳድሯል ተባለ

ጥቅምት 20/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኢትዮጽያ ከዓመታት በፊት ጥሩ የገቢ ምንጭ የነበረው የስጋ ምርት አሁን ላይ በተለያዩ ችግሮች ሳቢያ እየተቀዛቀዘ መምጣቱን ተገልጿል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከስጋ ምርት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያለው የመኖ አቅርቦት በአገር ውስጥ አቅርቦት መቀዛቀዙና ዋጋው አልቀመስ እያለ መምጣቱን ተከትሎ፤ የወጪ ንግድ ላይ አሉታዊ ጫና ማሳደሩን ተነግሯል።

ለዚህም እንደምክንያት የሚነሳው የአቅርቦች ችግር መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል።

ተፈጠረ የተባለውን ችግር ለማቃለል በብርቱ እየተሰራበት መሆኑን የሚታወቅ ቢሆንም፤ ችግሩን መፍታት አዳጋች እንደሆነበት ሚኒስቴር መስርያ ቤቱ ገልጿል።

በግብርና ተረፈ ምርትን ተጠቅመው መኖ የሚያመርቱ ድርጅቶችና ወደ ዘርፉ የሚገቡ የምጣኔ ሐብት አከናዋኞች ማግኘት እየተቻለ ባለመሆኑ ችግሩ መከሰቱንም ሚኒስቴሩ እንደምክንያት አንስቷል።

በዋነኝነት መኖ ማቀነባበርን ጨምሮ ተረፈ ምርትን ወደ ጥቅም የሚያውሉ አጋዥ የግሉ ዘርፍ ተዋናያን ችግር ከመሆኑ በተጨማሪም፤ በቅርቡ ደግሞ በእንስሳት መኖ ላይ የተስተዋለውን የዋጋ ጭማሪ ከኢትዮጵያ ወደ ውጭ አገራት የሚላከው የስጋ ንግድ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ እያሳደረ መምጣቱ ተገልጿል።

ሚኒስተሩ ይህንን እየተስተዋለ ያለውን ችግር ለማሻሻል በርካታ ሥራዎች እየሰራ ቢሆንም፤ ችግሩን በሚፈለገው ልክ ማቃለል እንዳልተቻለ አስታውቋል።

ይህንን ለአሐዱ የነገሩት፤ በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳትና አሳ ልማት ሀብት መሪ ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ፅጌሬዳ ፍቃዱ ናቸው።

መሪ ሥራ አስፈፃሚዋ ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ ወደ ውጭ አገራት የምትልከው የሥጋ ምርት መልካም በሚባል ደረጃ የነበረ ቢሆንም፤ አሁን ላይ እየተቀዛቀዘ መሆኑን ለአሐዱ ተናግረዋል ።

ችግሩን ለመቅረፍም እየተሰራበት መሆኑን ጨምረው ተናግረዋል።

ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ስጋ ላኪዎች ማህበር "በስጋ አቅቦት እጥረት የተነሳ ሥራችን ላይ ተፅእኖ እየፈጠረብን ነው" ሲሉ መቆየታቸውም አይዘነጋም።

ኢትዮጵያ በርካታ የእንስሳት ሐብት የበለፀገች መሆንዋን በተደጋጋሚ ሲነገር ቢቆይም፤ ዘርፉን ከገጠመው ከችግር መላቀቅ እንደተሳነው እየተነገረ ይገኛል።

በአማኑዔል ክንደያ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በግጭቶች እና በተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት 5 ሺሕ 568 ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸውን ተገለጸ

ጥቅምት 20/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ በሚገኙ የተለያዩ ክፍሎች በተከሰቱ እና በቀጠሉ ግጭቶች እንዲሁም በተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት 5 ሺሕ 568 ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ገለጸ፡፡

ኮሚሽኑ ዛሬ ጥቅምት 20 ቀን 2017 ዓ.ም የማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ መብቶች ሁኔታ ላይ ያተኮረ ባለ 25 ገጽ ዓመታዊ ሪፖርት አውጥቷል።

በሪፖርቱም በትግራይ ክልል 105 ገደማ ትምህርት ቤቶች በጦርነት በመውደማቸውና የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች መጠለያ ጣቢያ በመሆናቸው ምክንያት ተገቢውን አገልግሎት እየሰጡ አለመሆኑን ገልጿል።

እንዲሁም ተፈናቃዮች በሚገኙባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ትምህርት ቤቶች፤ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 52፣ በአፋር ክልል 17፣ በአማራ ክልል 14፣ በኦሮሚያ ክልል 11፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል 11 እና በጋምቤላ ክልል 11 ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸውን አስታውቋል።

ኢሰመኮ በሰኔ ወር እና ሐምሌ ወር 2016 ዓ.ም. ባሰባሰበው መረጃ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በተከሰቱ እና በቀጠሉ ግጭቶች እንዲሁም በተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት፤ በአማራ ክልል 4 ሺሕ 178፣ በትግራይ ክልል 648፣ በኦሮሚያ ክልል 420፣ በሶማሊ ክልል 195፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 50፣ በጋምቤላ ክልል 40፣ በአፋር ክልል 26 እንዲሁም በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል 8 ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸውን በሪፖርቱ አመላክቷል፡፡

የጸጥታ ሁኔታው አንጻራዊ መሻሻል ባሳየባቸው አካባቢዎች ደግሞ መምህራን አካባቢውን ለቀው የሄዱ በመሆናቸው የመምህራን እጥረት መኖሩን የገለጸው ኮሚሽኑ፤ በአካባቢዎቹ አስተማማኝ ጸጥታ ባለመኖሩ ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት እንደማይልኩ አስታውቋል።

በተጨማሪም "በአንዳንድ አካባቢዎች መምህራን ትምህርት ቤት ውስጥ ለመገኘት በተለይም ሴት መምህራን የመደፈር እና የመዘረፍ ሥጋት ያለባቸው በመሆኑ ትምህርት ላይ ተጽዕኖ አሳድሯል" ሲል ገልጿል።

ኮሚሽኑ በተጨማሪ የጤና ጉዳዮችንም በሪፖርቱ ያነሳ ሲሆን፤ "ባለሙያዎች ደመወዝ ወቅቱን ጠብቆ በአግባቡ ባለመከፈሉ ሳቢያ በአንዳንድ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሕክምና አገልግሎት እንዲስተጓጎል ምክንያት ሆኗል" ብሏል።

በተጨማሪም "የመድኃኒት እጥረት እና በግጭት ምክንያት የጤና ተቋማት በቂ አገልግሎት እየሰጡ ባለመሆናቸው ችግሩ ተባብሶ ቀጥሏል" ሲል ገልጿል፡፡

ኮሚሽኑ አክሎም በአማራ ክልል ያለው የትጥቅ ግጭት ምክንያት የተለያዩ የጤና ተቋማት ሥራቸውን በአግባቡ እንዳይሠሩ ከማድረጉ በተጨማሪ፤ የሕክምና መሣሪያ፣ መድኃኒት፣ ደም፣ ኦክስጂን እና ሌሎች ግብአቶች አቅርቦት እጥረት እንዲፈጠር ምክንያት መሆኑንም አመላክቷል።

ኢሰማኮ በሪፖርቱ መንግሥት በትጥቅ ግጭትም ሆነ በተፈጥሮ አደጋ ምክንያት ከትምህርት ገበታ ውጪ የሆኑ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ አስቻይ ሁኔታዎችን ለመፍጠር እርምጃዎችን እንዲወስድ ጠይቋል።

የወደሙ ትምህርት ቤቶች እንዲገነቡ እና መልሰው እንዲቋቋሙ ለማድረግ በቂ በጀት ተይዞላቸው በዕቅድ ውስጥ መካተታቸውን እንዲያረጋግጥ የጠየቀው ኢሰመኮ፤ ትምህርት ቤቶቹ መደበኛ አገልግሎት መስጠት እስኪጀምሩ መንግሥት ጊዜያዊ የመማሪያ አማራጮችን ጨምሮ የተለያዩ መፍትሔዎችን እንዲያመቻች እንዲሁም አስፈላጊ የትምህርት ቁሳቁሶችን እንዲያሟላሜ አሳስቧል።

በተጨማሪም በትጥቅ ግጭት ሳቢያ የወደሙትን መሠረተ ልማቶች በመጠገንና አገልግሎቶችን በፍጥነት ወደ ሥራ በማስገባት ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ መብቶች በተሻለ ሁኔታ የሚረጋገጡበትን መንገድ እንዲያመቻች ኮሚሽኑ ምክረ ሃሳቡን ሰጥቷል፡፡

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የጸጥታ አካላት ትዕዛዝ ባለመቀበላቸዉ ሕገ-ወጥ የነዳጅ ንግድን መቆጣጠር አልተቻለም ተባለ

ጥቅምት 20/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በሁሉም ዞኖችና ከተማ አስተዳደሮች በሚባል ደረጃ አንድ ሊትር ቤንዚን በሕገወጥ መንገድ ከ250 እስከ 300 ብር እየተሸጠ መሆኑን መዘገባችን ይታወሳል።

አሐዱም ለምን በዘላቂነት ችግሩን መቅረፍ እና ሕገወጥነትን መቆጣጠር አልተቻለም ሲል፤ የክልሉን ንግድና ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊና የኮምኒኬሽን ዳይሬክተር ሳሙኤል ሳዲሁን ጠይቋል።

በምላሻቸውም መሰል ችግሮች በክልሉ ብቻ ሳይሆን ሀገር አቀፍ ደረጃ መሆኑን ተናግረዋል።

በዋነኛነትም የጸጥታ አካላት የቁጥጥር ባለሙያዎችን ትዕዛዝ አለመቀበል እንዲሁም፤ በሕገወጥ ሥራው ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች ጋር በጋራ በመስራታቸው እና በሌሎች ምክንያቶች ሕገወጥ እግዱን መቆጣጠር እንዳልተቻለ ተናግረዋል።

ኃላፊው አያይዘውም ችግሩ አሽከርካሪዎችንና የህብረተሰብ ክፍሎችን ለእንግልት እየዳረገ መሆኑን ተናግረዋል።

ከሚመለከታቸው ከፌዴራል መስሪያ ቤቶች ጋር በቅንጅት በመሥራት ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት እየሰራ ነው ሲሉም ገልጸው።

የቁጥጥር ሥራዎችን በማጠናከር በክልሉ የተከሰተውን ሕገወጥ ተግባር በቅርብ ጊዜ ውስጥ ይቀረፋል ሲሉም ጠቁመዋል።

በወልደሀዋርያት ዘነበ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

"የፍርድ ሂደቶች የፖለቲካ በቀል መፈፀሚያ መሆን የለባቸውም" የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል

ጥቅምት 20/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ እየተካሄዱ የሚገኙ የፍርድ ሂደቶች የፖለቲካ በቀል መፈፀሚያ መሆን የለባቸውም ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል አሳስቧል።

ሕጉ የዋስትና መብት ጭምር የማይነፍግባቸው ክሶች ለተራዘመ የእስር ቆይታና እንግልት እየተዳረጉ መሆኑን የሕግ ባለሙያዎችና ሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ገልጸዋል፡፡

ከፖለቲካ ጋር የተያያዘ ነው የሚባሉ ክሶችን የተቀመጠውን ሕግ በመጣስ ጭምር ያላግባብ ዜጎችን ለእንግልት እየዳረገ መሆኑም ተነስቷል፡፡

"ከዚህ ባለፈም በተደጋጋሚ ግዜ የ14 ቀን ጊዜ ቀጠሮ እየተባለ የማጉላላትና እና ማራዘም ተገቢ አይደለም" ሲሉ ለአሐዱ የተናገሩት የሕግ ባለሙያውና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ማዕከል ዋና ዳይሬክተር አቶ ያሬድ ሃይለማርያም ናቸዉ፡፡

"ሕጉን ለማስተማሪያነትና ፍትህን ለማስረፅ ሳይሆን ሕጉን የመንግሥት ባለስልጣናት በበቀል ተነስሳተው እንደሚጠቀሙበት ማድረግም ተገቢ አይደለም" ብለዋል፡፡ አክለውም በአሁኑ ወቅት እንደሚስተዋለው የፍርድ ሂደቶች የፖለቲካ በቀል መፈፀሚያ መሆን የለባቸውም ሲሉም ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅን ምክንያት በማድረግ ጋዜጠኞች እና ፖለቲከኞችን ጨምሮ የተለያዩ አካላት በሕገ ወጥ መንገድ በእስር ላይ እንደሚገኙ በበርካታ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት ሲገለጽ ቆይቷል፡፡

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ባሳለፍነው ሳምንት ባወጣው ሪፖርት፤ በአዲስ አበባ ከተማ፣ እንዲሁም በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች የተለያዩ አካባቢዎች የአስገድዶ መሰወር እና ያሉበት ሳይገለጽ በተራዘመ እስር ሁኔታ ውስጥ የሚቆዩ ሰዎች መበራከታቸውን ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

በአቤል ደጀኔ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በወላይታ ዞን በደረሰ የመሬት ናዳ የ7 ሰዎች ሕይወት አለፈ

ጥቅምት 20/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በወላይታ ዞን ካዎ ኮይሻ ወረዳ በትናንትናው ዕለት ማታ ላይ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት የሰባት ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰምቷል፡፡

በወረዳው ኮይሻ ላሾ ቀበሌ ሞግሳ ቀጠና በተከሰተው መሬት ናዳ የአራት ሰው ሕይወት ያለፈ ሲሆን፤ በ01 ቀበሌ ደግሞ ሦስት ሰው በአጠቃላይ የ7 ሰው ሕይወት ማለፉን አሐዱ ለማወቅ ችሏል።

አደጋው የአንድ ቤተሰብ አባላት ሙሉ በሙሉ እንዲሁም ሌሎች ሰዎች ላይ አደጋ ማድረሱ የተገለጸ ሲሆን፤ በንብረት ላይም ጉዳት አድርሷል።

ከዚህ ቀደም በካዎ ኮይሻ ወረዳ ጤፓ ቀበሌ በመሬት ናዳ ምክንያት የተፈናቀሉትን መልሶ ለማቋቋም ስሰራ ቢቆይም፤ ተደጋጋሚ አደጋ በመከሰቱ ችግሩ እያባባሰው መምጣቱ ተመላክቷል፡፡

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

"ኢትዮጵያን በሃይል ማንም መውረር አይችልም፤ በቂ የሆነ አቅም አለን" ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

ጥቅምት 21/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) እንደ ሀገር ከተቻለ ከሁሉም ጋር በሰላም መኖር ነው የምንፈልገው ነገር ግን ድሃ ናቸው፣ በውስጣቸው ችግር አለባቸው እና እንዳሻቸው ፍላጎታቸውን አያደርጉም ብለው የሚያስቡ አካላት መታረም አለባቸው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ አሕመድ ገለጸዋል።

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ጥንካሬ መሆኑን በመገንዘብ መነጋገር እንጂ "አናንቆ፣ አራክሶና ድሃ ናቹ" ብሎ ማሰብ ዋጋ የለውም ብለዋል።

"ኢትዮጵያን ከሰፈር፣ ፓርቲ እኛ ክልል በላይ መመልከት ከተቻልን ማንም ሰው ኢትዮጵያን በሃይል ማንበርከክ አይችልም" በማለት ምላሻቸውን ሰጥተዋል።

"ነገር ግን አሁን ያለው ሁኔታ 'እንታገላለን እና እንቃወማለን' የሚሉ አካላት ከጠላት ጋር እየሰሩ ነው" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ከዚህ ተግባራቸው እንዲታቀቡ ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

"በተመሳሳይም ሌሎች ሀገራትም ቢሆኑ ኢትዮጵያን እየነጣጠሉ እና እያጣሉ መዝለቅ አይችሉም" በማለት፤ ኢትዮጵያን አክብሮ ጉርብትናውን ወዶ መኖር መቻል አለበት ሲሉ ገልጸዋል።

ከምክር ቤቱ አባላት ከኤርትራ እና ሶማሊያ ጋር ስላለው ግንኙነት ጥያቄ የቀረብላቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ "ከኤርትራ ጋር የሚነሱ ነገሮች ቢኖሩም እኛ የምንፈልገው ሰላም ነው፡፡ ማንም ገፍቶ እስካልመጣ ድረስ፤ በኤርትራውይን ወንድሞቻችን ላይ ምን አናደርግም" ብለዋል።

በሶማሊያ በሺሕ የሚቆጠሩ ዜጎችችን ሕይወት አልፏል ያሉ ሲሆን፤ "ይኼን ያድረግነው ለጋራ ሰላም ስንል ነው" ይላሉ።

ለዚህም አሁን ለሶማሊያ "ጊዜ ሰጥተናል እንዲረጋጉና ቀልብ እንዲገዙ" በማለት፤ አለም ሊያውቀው የሚገባው ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ተጠቃሚነት ያስፈልጋታል። ይኼ የሚታፈርበት ጉዳይ አይደለም" ሲሉም ገልጸዋል።

"የውጊያ ፍላጎት የለንም" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፤ "ኢትዮጵያን ማንም ሰው በሀይል መውረር አይችልም። በቂ የሆነ አቅም አለን። ሰው አለን። ጀግኖች ነን። ማንንም አንነካም ከነኩን ግን ለማንም አንመለስም። ስጋት የለብንም" ሲሉ ለምክር ቤት አባላት ምላሻቸውን ሰጥተዋል።

በፍርቱና ወልደአብ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

"አየር መንገዱ በኤርትራ የአየር ክልል እንዳይበር እንደተከለከለ የተሰራጨው መረጃ የተሳሳተ ነው" የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ጥቅምት 21/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኤርትራ የአየር ክልል እንዳይበር እንደተከለከለ የተሰራጨው መረጃ የተሳሳተ እንደሆነ አየር መንገዱ ለመረጃ አጣሪው ድረ-ገጽ ለኢትዮጵያ ቼክ ተናግሯል፡፡

በርካታ የኢትዮጵያ፣ የኤርትራ እና የሶማልያ ኦንላይን ሚድያዎች ኤርትራ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኤርትራ የአየር ክልል ውስጥ እንዳይበር መከልከሉን እየዘገቡ ይገኛሉ።

እንደ 'Eritrean Press' ያሉ እነዚህ ሚድያዎች ለዚህ ክስተት አስረጂ ነው ያሉትን ማስረጃ ባያቀርቡም፤ ጉዳዩ አየር መንገዱ በቅርቡ ወደ ኤርትራ እንዳይበር ከመታገዱ ጋር የተያያዘ እንደሆነ አመላክተዋል።

በዚህ ዙርያ ኢትዮጵያ ቼክ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ማብራርያ ጠይቋል።

"አየር መንገዳችን አሁንም በኤርትራ አየር ክልል እየበረረ ነው፣ መረጃው የተሳሳተ ነው" ብለው አንድ ከፍተኛ የአየር መንገዱ ሀላፊ መረጃ ሰጥተዋል።

"በኤርትራ አየር ክልል ለመብረር አሁንም ፈቃድ አለን፣ ይህ ፍቃድ እንደተነሳ ምንም አይነት ከኤርትራ አልደረሰንም" ብለው ያስረዱት ኃላፊው፤ ከበፊቱ የተቀየረ ነገር እንደሌለ ጠቁመዋል።

ይሁንና Flight Radar 24 የተባለው የበረራ መከታተያ ድረ-ገፅ እና መተግበርያ አንዳንድ አውሮፕላን የኤርትራን አየር ክልል በመተው በሱዳን በኩል እየበረሩ እንደሆነ በ X ላይ ምላሽ ሰጥቷል።

ይሁንና በርካታ የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች አየር መንገዱ አሁንም በረራውን በኤርትራ የአየር ክልል እያደረገ እንደሆነ የሚያሳዩ የስክሪን ቅጂዎችን እያጋሩ ይገኛሉ።

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

"ኮሪደር የሚጠላ ኢትዮጵያዊ ያለ አይመስለኝም" ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

ጥቅምት 21/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) "ኮሪደር ዓለም እያደነቀው እያለ እኛ የምንጠላበት ምንም ምክያት የለም" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስተር ዐቢይ አሕመድ፤ "እኔ ካልሰራሁት ካልሆነ የሚጠላ አይደለም" ብለዋል፡፡

"ኮሪደርን ከዲሞግራፊ ጋር ያይዙታል። ይሁን አዲስ አበባ እንደዛ ይሁን ሌሎች የኢትዮጵያ ክልልች ምን ሊባል ነው? ይሄ ፍፁም ስህተት አስተሳሰብ ነው፡፡" ሲሉም ተናግረዋል።

አክለውም፤ "ኮሪደር ልማት ማለት ፒያሳ እና ቦሌ ማለት ናቸው ይሄን የሚጠላ ኢትዮጵያዊ ያለ አይመስለኝም" ብለዋል፡፡

"ኮሪደር ማለት ኢትዮጵያን የሚመጥን ልማት መገንባት ማለት ነው" ሲሉም የተናገሩ ሲሆን፤ "ኢትዮጵያ ውስጥ የነበረው ከተማ ፎቅ የነበረበት ገጠረ ነበር" ብለዋል፡፡

"የነበረው ከተማ ሽንት ቤት የለውም፣ የእግረኛ መንገድ የለውም፣ መብራት የለው በርካታ ችግር የነበረበት ስለነበር መቀየር ነበረበት" ሲሉም ተናግረዋል፡፡

"አንድአንዶች እንደፋሽን ላስቲክ መሃል መንገድ ላይ በማድረግ መንገድ ማጣበብ፤ ካልጠፋ ቦታ ይሄን የሚያህል ሀገር እያለን ይህን መጥፎ ልማድ ተጋፍጠን በብዙ ችግር ውጤት አምጥተንበታል" ሲሉም አክለዋል፡፡

"በ2050 ከተሜነት ወደ 60 በመቶ ያድጋል" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ ከላስቲክ ላይ ላስቲክ ያለውን ሁኔታ ቀይረን ለዛ ዕድገት መዘጋጀት አለብን ብለዋል፡፡

"ከዚህ ቀደም ገጠር ተኮር ብለን አርሶ አደሩን ረሳነው፤ አሁን ደግሞ ሁለቱን በጋራ ከተሜነትንና ገጠሩን አዋህደን እንሂድ ነው እያልን ያለነው" ብለዋል፡፡

"ሁለተኛው ኮሪደር ማለት በየሰፈሩ ትናንሽ ስቴድየሞች እየገነባን ነው ይሄን የሚረዳው አካል ይረዳዋል ምን ያህል ለውጥ እንዳመጣንበት" ሲሉም ተናግረዋል።

"የትኛውም ቦታ ኪስ ቦታ እየተባለ ይሸጥ ነበር። ኪስ ቦታ እየተባሉ የሚሸጡ ቦተታዎችን እናስቁምና ለወጣቱ እናውልው ፓርክ እንስራበት ብለን ነው የተነሳነው" በማለት አክለዋል፡፡

"ሰፋፊ የእግርኛ መንገድ መገንባት ነበረብን። በኢትዮጵያ ከ1 ሚሊዮን ያላነሰ ሰው ነው መኪና ያለው ይህንን በመመልከት ሰፋፊ እግረኛ መንገድ ገንበተናል" ብለዋል፡፡

"ስለዚህ ኮርደር ልማት ለህዝቡ የተሻለ አኗኗር መፍጠሪያ ነው ሌላ አይደለም ይሄ ደግሞ ሊጠላ አይችልም" ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለምክር ቤቱ አባላት ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

በአቤል ደጀኔ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

"መንግሥት አማራን አሳሪ ተብሎ መፈረጅ የለበትም" ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

ጥቅምት 21/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት እያከናወነው በሚገኘው መደበኛ ስብስባው ላይ፤ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱ በርካታ ጥያቄዎች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡

በዚህም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) አባል የሆኑት ዶ/ር አበባው ደሳለኝ ጥያቄ አቅርበው ነበር፡፡ በጥያቄያቸውም "ሰላም መፍትሄ አካል አንዱ የጅምላ እስር፣ የጅምላ ግድያ ማቆም ነው ይሄ መቼ ነው የሚቆመው?" ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

ለዚህም ምላሽ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ "መንግሥት ለአማራ ክልል በርካታ ልማት እየሰራ ነው" ያት ሲሆን፤ "መንግሥት አማራን አሳሪ ተብሎ መፈረጅ የለበትም" ብለዋል፡፡

"ሁሉም ቢጠየቅ የእኔም ሕዝብ ታሰረብኝ የሚል ቅሬታ ያነሳል ነገር ግን መንግሥት ማንም በዘፈቀደ አያስርም፡፡ ይሄ ስህተት ነው" ብለዋል፡፡

"በአማራ ክልል ብልፅግና መንግሥት ከዚህ ቀደም ማንም ባልሰራው መልኩ በርካታ ፋብሪካዎች በደብረ ብርሃን እና ኮምቦልቻ ተሰርቷል" ሲሉም ተናግረዋል፡፡

"ጎንደር ዞርብሎ የሚመለከተው መንግሥት አልነበረም" ያሉም ሲሆን፤ "በብልፅግና ጊዜ ግን ወደ ልማት መጥታለች ይሄ መረሳት የለበትም" ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናግረዋል፡፡

"መንገዶች፣ ትልቅ ውብ ድልድይ ኮሪደር እየሰራን እንገኛለን ይህንን የአማራ ሕዝብ ጠንቅቆ ያውቀዋል" ብለዋል፡፡

"ነገር ግን ልማቱን የሚያደናቅፉትን እኛ እና እናንተ በጋራ በመሆን ወደ ሰላም እንዲመጡ ማድረግ አለብን" ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለአብን ተወካዩ ዶ/ር አበባው ደስለው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

"ብልፅግና አሳሪ አይደለም ማንንም ያለግብሩ አያስርም" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ "በዘፈቀደ የሚያስር ቢሆን እርሶንም ያስር ነበር ግን ዝም ብሎ መንግሥት አያስርም" ብለዋል፡፡

በአቤል ደጀኔ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

ከምክር ቤት አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የቀረቡ ጥያቄዎች!

ጥያቄዎቹን ለመከታተል ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👇
www.youtube.com/live/Wblp2N4fjz8?si=3wzbEE29x6WiCEm6

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የኢትዮጵያን ሐብት ለመዝረፍ ያሰፈሰፉ ኤምባሲዎች መኖራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ገለጹ

ጥቅምት 21/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በማብራሪያቸው በአገር ውስጥ ሆነው ጥቁር ገበያን የሚያቀለጣጥፉ ኤምባሲዎችና የኤምባሲ ሰዎች መኖራቸውን መንግሥት መረጃው እንዳለው ተናግረዋል።

በጥቁር ገበያ መስፋፋት ረገድ ኤምባሲዎች የነበራቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለፓርላማው ሲናገሩ ተደምጠዋል::

በአገር ውሰጠ ካሉ ባንኮች ጋር በመመሳጠርም ጥቁር ገበያውን ሲያሯሩጡ እንደነበር መንግሥት መረጃ እንዳለው ገልጸዋል።

"አገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ኤምባሲዎች የሀገሪቱን የፋይናንስና የፓለቲካ ሕጎችን አክብረው መንቀሳቀስ አባቸው" ብለዋል፡፡

በተማሪም ባንኮች ሕገወጥ ገንዘብ ከሚያስተላልፉት ኮሚሽን በመቁረጥ መክበር የሚፈልጉ እንዳሉም ገልጸዋል።

አንዳንድ ፍራንኮቫሉታ በተሳሳተ መልኩ የሚጠቀሙና የውጭ ምንዛሪ ለማሸሽ የሚሞክሩ ኩባንያዎች መኖራቸውንም አንስተዋል ።

የወርቅ ላይ የሚስተዋውወን ሕገወጥ ዝውውርን በማስቀረት ረገድ መንግሥታቸው ማሻሻሉን ጠቅሰው፤ ይህም ምክርቤቱ እንደትልቅ ውጤት እንዲመለከትላቸውም ጠይቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከሕገ የወርቅ ዝውውር ኢትዮጵያ በርከታ ሐብቶ እያጣች መቆየቷንም ጠቅሰው፤ በርካታ መሻሻሎች እንዳሉ ዛሬ ለምክር ቤቱ በሰጡት ማብራሪያ ላይ ገልጸዋል።

በአማኑዔል ክንደያ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

"ኢትዮጵያ ከብራዚልና ቬትናም በመቀጠል በአለም ሦስተኛዋ ቡና አምራች አገር ሆናለች" ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

ጥቅምት 21/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ኢትዮጵያ የቡና ምርት የተመዘገበው ውጤት ካለፉት ሁለትና ሦስት ዓመታት ጋር ሲመሳከር እጥፍ በሚባል ደረጃ እድገት ማሳየቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ የግብርናው ዘርፍ በከፍተኛ ደረጃ እድገት ከተመዘገበባቸው ዘርፎች መካከል ዋነኛው ሆኖ መመዝገቡን ጠቅሰው፤ ግብርና 6 ነጥብ 1 በመቶ እድገት መታየቱንም አንስተዋል።

ግብርናው ከሌሎች ዘርፎች እድገት ከተስተዋለባቸው መካከል ቀዳሚው ሆኖ መመዝገቡን በመግለጽም፤ በቀጣይም 6 ነጥብ 8 በመቶ እድገት ያስመዘግባል ተብሎ እቅድ መያዙንም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያነሱት።

ሌላኛው ከፍተኛ እድገት ከተመዘገበባቸው የግብርና ክፍለ ኢኮኖሚ መካከል የሆልቲካልቸር ዘርፍ መሆኑን በማብራርያቸው ላይ ተናግረዋል።

የሰሊጥና ሌሎች የቅባት እህሎች ላይ ከፍተኛ ለውጥ እያታየ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የገለጹ ሲሆን፤ ዘርፉን እንዲዳከም ያደረገውም በየአካባቢው ያለውን የፀጥታ ችግሮች መሆናቸውን እንደምክንያት አንስተዋል።

ከግብርናው በመቀጠልም የኢንዱስትሪውና የአገልግሎት ዘርፉ በሁለተኝነትና ሶስተኝነት ተርታ የተሰለፉ ዘርፎት እድገት የተመዘገበባቸው ዘርፎች መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ለምክር ቤቱ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በአማኑዔል ክንደያ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

"ኢትዮጵያ 8 ነጥብ 1 በመቶ ዕድገት አስመዝግባለች" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

ጥቅምት 21/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ስብሰባውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት እያካሄደ ነዉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከምክር ቤት አባላት ለተነሳላቸዉ ጥያቄ ምላሽ እና ማብራሪያ በመስጠት ላይ ይገኛሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምላሻቸው፤ "ኢኮኖሚያችን በአፍሪካ ብቻም ሳይሆን በዓለም ደረጃ ከፍተኛ ዕድገት ከሳመዘገቡ ጥቂት የዓለም ሀገራት መካከል አንዷ ናት" ብለዋል፡፡

አክለውም "ብዙዎች ግን ምን አግታችሁ ነው ነዳጅ አገኛችሁ ወይ እያሉ ጭምር እየጠየቁን ነው" ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ዓምና 8 ነጥብ 4 የተመዘገበ ዕድገት መገኘቱን የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስቴሩ፤ በዚህም ዓመት ከዓምናው የተሻለ ዕድገት እንደሚመዘገበ ጨምረው ገልጸዋል፡፡

ለዕደገቱ ዋነኛ ማሳሪያ የሆነው የግብርናው ዘርፍ 6 ነጥብ 1 በመቶ ዕድገት ያስመዘገበ መሆኑም አንስተዋል፡፡

በዚህ ዓመትም 30 ሚሊየን ሔክታር በክረምትና በበበጋ በማረስ 1 ነጥብ 4 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ መታቀዱን ገልጸዋል።

ለዚህም በሰብል ምርቶች 6 ነጥብ 6 በመቶ እንድሁም በሌማት ትሩፋት 5 ነጥብ 4 በመቶ ዕድገት ይመዘገባል ብለዋል።

በተመሳሳይም በቡና ምርት ኢትዮጵያ ሶስተኛዋ ሀገር ሆናለች ያሉ ሲሆን በ2016 በጀት ኦኣመት 1 ሚሊየን ኩንታል መሰብሰቡን አንስተው በተያዘው ዓመት 450 እስከ 500 ሺህ ለውጭ ገበያ ማቅረብ መታቀዱን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ 8 ነጥብ 1 በመቶ ዕድገት አስመዝግባለች" ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናግረዋል።

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

አምራች ኢንዱስትሪዎች ከሀገር ውጪ ያሉ የገበያ ዕድሎችን እንዲጠቀሙ ጥሪ ቀረበ

ጥቅምት 21/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢንዱስትሪ ልማቱን ለማፋጠንና አቅሙን ለማጎልበት፤ ኩባንያዎች ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ በማድረግ ተጠቃሚነትን የማጎልበት ሥራዎችን ማከናወን እንደሚገባ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የሚኒስቴሩ የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር አበባ ታመነ፤ አምራች ኢንዱስትሪዎች ውጭ ያሉ የገበያ ዕድሎችን ለመጠቀም በተደራጀና በተቀናጀ ሁኔታ መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።

አክለውም፤ የኢንዱስትሪ ልማትና ተወዳዳሪነትን ለማረጋገጥ ከውጭ ሐገር የሚገቡ ኩባንያዎችን ወደ ሀገር እንዲገቡ በማድረግ ተጠቃሚነቱን ማስፋትና ማዘመን አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል፡፡

"አምራች ኢንዱስትሪዎች ከፍተኛ የመግዛት አቅም ያላቸውን የውጭ ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ በመጋበዝ ሀገራችን ያላትን ምቹ የገበያ ሁኔታ ለማሳደግና ለማዘመን በትኩረት መስራት ይገባል" ሲሉም ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሐብቶች በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ እንዲሳተፉ በማድረግ እንዲሁም በሥሩ ያሉ ተጠሪ ተቋማት በዋናነት በሀገር ውስጥ በኢንቨስትመንቱ ላይ እንድሳተፉ በማድረግ ሥራዎችን ማከናወን እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡

የውጭ ገዢዎችን ለመሳብ በሚያደርጉት ሂደት ከአቅም በላይ የሆነ ችግር በሚገጥማቸው ወቅት መንግሥት አስፈላጊውን ሁሉ እገዛ እንደሚያደርግ የተገለጹት የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተሯ፤ ኢንዱስትሪዎች በበረቱ ቁጥር የሚደረግላቸው ድጋፍ በዚያው መጠን እያደገ እንደሚሄድ አስረድተዋል፡፡

በአለምነው ሹሙ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

#አሐዱ_ስንክሳር

ኢትዮጵያ በተለያዩ ወቅቶች የተከሰቱ የታሪክ ምዕራፋትን አልፋለች። እነዚህን የታሪክ እጥፋቶች እየተከታተሉ የሚከትቡ ጸሐፊያንም አሉ።

አሁን ያለችው ኢትዮጵያም ከባለፈችው ኢትዮጵያ የተወለደች በመሆኗ ከቀደመችው ኢትዮጵያ የምትወርሳቸው አያሌ ባሕሪያት አሉ። እነዚህ ባሕሪያት ከወቅታዊዉ የኢትዮጵያ ሁኔታ ጋር ሆነውም ዛሬ የምናያትን ኢትዮጵያ ይገልፃሉ።

ታሪክ ግን፣ የኋላ ማንነትን ማሳያ መስታወት ሆኖ በማገልገል ወደ ፊት እንዴት መጓዝ እንዳለብን ያሳስበናል።

ታሪክ ዘጋቢዎች የተከሰቱ እና የተፈፀሙ ዕውነቶችን በስርአት ጽፈው እንዲያሻግሩም ኃላፊነት አለባቸው። በዛሬው ኢትዮጵያዊ ስንክሳራችን የሐገሪቱን ታሪካዊ ጉዞዎችን ከጸሐፊያን አንፃር እንቃኘዋለን።

በጥበብ በለጠ
ጥንቅሩን ለመከታተል ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👇
https://youtu.be/1vQQTb6A2OE?si=gM3EI1JcBfCFXb5A

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በነዳጅ ታንከር ተደብቆ በሕገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበረ 11 ክላሽንኮቭ ጠመንጃ መያዙን ተገለጸ

ጥቅምት 20/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በነዳጅ ታንከር ውስጥ ተደብቆ በሕገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበረ 11 ክላሽንኮቭ ጠመንጃ ከመሰል ዘጠኝ ካዝና እና ከሁለት ተጠርጣሪዎች ጋር መያዙን ገልጿል።

ሕገ-ወጥ የጦር መሣሪያው ሊያዝ የቻለው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ባገኘው መረጃ መሰረት መሆኑ ተመላክቷል።

በዚህም ጥቅምት 19 ቀን 2017 ዓ.ም መነሻውን ጋምቤላ ክልል አድርጎ ወደ አማራ ክልል ለማስገባት ታስቦ በሕገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበረ 11 ክላሽንኮቭ ጠመንጃ ከመሰል ዘጠኝ ካዝና ጋር ከፋ ዞን ቦንጋ ከተማ ሲደርስ በተደረገው ጥብቅ ክትትል የተጠረጠረው ተሽከርካሪ አካል ተፈትሾ ሊገኝ ባለመቻሉ የፖሊስ ሙያተኛን በመጨመር የነዳጅ ታንከር ወርዶ ውስጡ እንዲፈተሽ በመደረጉ መያዙ ተነግሯል።

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

#አሐዱ_ትንታኔ

አሜሪካ በታይዋን ጉዳይ ጣልቃ መግባቷን እንድታቋርጥ ቻይና አስጠንቅቃለች፡፡ ቤጂንግ በበኩሏ እንደራሷ አንድ አካል በምትቆጥራት ታይዋን ላይ አሜሪካ ጣልቃ መግባቷ ተቀባይነት የለውም ብላለች፡፡ 

አሜሪካ ለምን ታይዋንን ፈለገች የሚለውን በዛሬው የዓለም አቀፍ ትንታኔያችን ተመልክተነዋል።

ትንታኔውን ለመከታተል ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👇
https://youtu.be/sZdWUTv7JOg?si=yBztf_zKV9D1ouAe

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

ሶማሊላንድ ከየትኛውም ወገን ተቃውሞ እና ጫና ቢመጣ ከኢትዮጵያ ጋር የገባችውን ስምምነት ተግባራዊ ከማድረግ ወደ ኋላ እንደማትል ገለጸች

ጥቅምት 20/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ሶማሊላንድ ከየትኛውም ወገን ተቃውሞ እና ጫና ቢመጣ ከኢትዮጵያ ጋር የገባችውን ስምምነት ተግባራዊ ከማድረግ ወደ ኋላ እንደማትል የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ሙሳ ቢሂ ተናግረዋል።

ፕሬዝዳንት ሙሳ ቢሂ ይህን የተናገሩት ከሁለት ሳምንት በኋላ በሶማሊላንድ ከሚካሄደው ምርጫ ጋር በተያያዘ ከቢቢሲ ሶማሊኛ አገልግሎት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ነው።

በቃለ ምልልሱ ላይም አገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር በደረሰችው የመግባቢያ ስምምነት እና በቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

በዚህም የመግባቢያ ስምምነቱ "ምንም ነገር ሳይቀየር በነበረበት እንዳለ ነው።" ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ "በመግባባት ደረጃ ላይ ነው ያለው። ሁሉም ወገን የተግባራዊነት ሰነዱ መቼ እንሚፈረም እየተጠባበቀ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።

የመግባቢያ ስምምነቱ ከተፈረመ በኋላ ውዝግብ መፈጠሩን ያመለከቱት ቢሂ፤ "ኢትዮጵያ ለምን ከሶማሊላንድ ጋር ስምምነት ተፈራረመች" በሚል የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ኢትዮጵያ ላይ ዘመቻ መክፈታቸውን ተናግረዋል።

ስምምነቱ ከሶማሊያ ግዛት ጋር ሳይሆን ራሷን ከቻለች አገር ሶማሊላንድ ጋር የተደረገ መሆኑን በመግለጽም፤ "ፕሬዝዳንት ሐሰን "የእኛ ነው" ወደሚሉት መሬት መሄድም ሆነ መቆጣጠር እንደማይችሉ ያውቁታል" ብለዋል።

"ለ34 ዓመታት ሁለት የተለያየን ነጻ አገራት ነን፤ ሁለት መንግሥታት ነን፤ ሁሉም ያውቀዋል" ሲሉም ተናግረዋል።

አክለውም፤ ከስምምነቱ በኋላ አለመግባባቱ መካረሩን በመጥቀስ “ጦርነት ታቅዶ ነበር። ግብፅ እንድትገባበት ተደረገ፤ ውዝግብ ተፈጠረ። ይህ ተጨማሪ ነገር ነው፤ መፍትሄም አይሆንም" ብለዋል።

"ፕሬዝዳንት ሐሰን ሁለት የተለያየን መንግሥታት መሆናችንን ከተረዳ እና ከእኛ ጋር ንግግር ከፈለገ መልካም ነው" ሲሉም፤ ሶማሊያ አገርነታቸውን ከተቀበለች ለንግግር በራቸው ክፍት መሆኑን አመልክተዋል።

ፕሬዝዳንቱ ጨምረውም ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ መሐሙድ በሶማሊላንድ መሬት የሚመለከታቸው ነገር አለመኖሩን ጠቅሰው፤ "ለኢትዮጵያ መሬት ሰጡ" በማለትም የሚናገሩት የማይመለከታቸውን ጉዳይ ነው" ሲሉ አጣጥለውታል።

"ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ሶማሊዎች አሉ፤ በመንግሥት ውስጥም ቦታ ያላቸው ናቸው። ታዲያ ከኢትዮጵያ ጋር ስምምነት ተፈራረማችሁ በማለት ሶማሊያ ለምንድን ነው የምትከሰን?" ሲሉም ጠይቀዋል።

"ሶማሊያ ከግብፅ ጋር የደረሰችው የወታደራዊ ትብብር ስምምነቱ የሶማሊላንድ ሕዝብ የነጻ አገርነት ፍላጎትን ለማስቆም የታለመ ነው" ብለው እንደሚያምኑም ተናግረዋል።

በአንድ ወር ውስጥ ተግባራዊ መሆን ይጀምራል የተባለው የኢትዮጵያ እና የሶማሊላንድ ስምምነት አንድ ዓመት ሊሞላው ሁለት ወራት ቀርተውታል።

ነገር ግን የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት እንደሚሉት መዘግየቱ ጉዳዩ ሰፊ ጊዜን የሚጠይቅ እና ዓለም አቀፍ ስምምነቶች ወደ ተግባር ለመቀየር በርካታ ዓመታትን የሚጠይቁ መሆናቸውን በምሳሌነት አንስተዋል።

በሶማሊያ በኩል የተደረገ ጫና በስምምነቱ መዘግየት ላይ ምንም ሚና እንደሌለው የገለጹም ሲሆን፤ "የመግባቢያ ስምምነቱ የራሱን ጊዜ እየተከተለ ነው። የመጨረሻውን ሁለቱ አገራት የሚወስኑት ይሆናል" በማለት፤ ጉዳዩ በኢትዮጵያ እና በሶማሊላንድ እጅ ላይ ያለ መሆኑን ተናግረዋል።

አክለውም ከሶማሊያ ጋር የወታደራዊ ትብብር ስምምነት የተፈራረመችውን ግብፅን በተመለከተ፤ "ግብፅ ከኢትዮጵያ ጋር ባለባት የአባይ ውሃ ውዝግብ ውስጥ ሶማሊያን በማስገባት እየተጠቀመችባት ወደ ጦርነት ልታስገባት ነው" ብለዋል።

"የራሷ ችግር አለባት ያሏትን ግብፅ የሶማሊያ መንግሥት ወደ ቀጣናው ውዝግብ ማስገባቱ ትክክል አይደለም" ያሉት ቢሂ፤ "የወታደራዊ ስምምነቱ ግብፅ ከኢትዮጵያ ጋር ካለባት ውዝግብ በተጨማሪ በሶማሊላንድ ላይ ጭምር ያነጣጠረ ነው" ሲሉ ከሰዋል።

ፕሬዝዳንቱ ከኢትዮጵያ ጋር ስምምነት ከመፈራረማቸው በፊት ከሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ መሐሙድ ጋር በተገናኙበት ጊዜ ይህንኑ አስረግጠው እንደነገሯቸው ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ነጻ አገርነቷን ካወጀችው ሶማሊላንድ የባሕር በር፣ ሶማሊላንድ ደግሞ የአገርነት ዕውቅናን ለማግኘት የመግባቢያ ስምምነት ከተፈራረሙ በኋላ በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ያለው የፖለቲካ ትኩሳት ከተጋጋለ አንድ ዓመት ሊሞላው ነው።

ስምምነቱ ከተደረሰ በኋላ ሶማሊያ ተቃውሟዋን እያሰማች ሲሆን፣ ኢትዮጵያንም ሉዓላዊነቷን በመጣስ ከመክሰስ ባሻገር ከኢትዮጵያ ጋር ውዝግብ ውስጥ ከምትገኘው ግብፅ እና ግንኙነታቸው እየሻከረ ካለው ከኤርትራ ጋር ዘርፈ ብዙ የትብብር ስምምነት መፈራረሟ ይታወሳል።

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ነገ በፓርላማ ከምክር ቤት አባላት ለሚነሱላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ ይሰጣሉ

ጥቅምት 20/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ነገ ጥቅምት 21 ቀን 2017 ዓ.ም. በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለሚነሱላቸው ጥያቄ ምላሽ እንደሚሰጡ ታውቋል፡፡

በዚህም በመስከረም 2017 ዓ.ም. መጨረሻ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አራተኛ ዓመት የመጀመሪያ ስብሰባ፣ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፕሬዚዳንት ሆነው የተሰየሙት ታዬ አጽቀሥላሴ በመንግሥት የዘንድሮ ዕቅድ ላይ ባደረጉት ንግግር ላይ የምክር ቤት አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥያቄ ያቀርባሉ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እንደሚሰጡ ይጠበቃል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለከፍተኛ የመንግሥት ሃላፊነት ቦታዎች ሹመት እንዲፀድቅላቸው በደብዳቤ ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት፤ ትናንት በተከናወነው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ የ5 ሚኒስትሮች ሹመት መጽደቁ ይታወሳል፡፡

ነገር ግን ይህ ሹመት በተለይም በቀድሞ የፍትህ ሚኒስትር ጌድዮን ጢሞትዬስ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሆኖ መሾም፤ በምክር ቤት አባላቶች በኩል ከግልጽነት እና ከተጠያቂነት መርህ አንጻር ከፍተኛ ጥያቄ ተነስቶበታል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ የምክር ቤቱ አባላት ጥያቄ ላይም ምላሽ ይሰጡበታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

ሶማሊያ የኢትዮጵያ ዲፕሎማት በ72 ሰዓታት ውስጥ ሀገሪቷን ለቀው እንዲወጡ አዘዘች

ጥቅምት 20/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በሶማሊያ የኢትዮጵያ ኢምባሲ ውስጥ በአማካሪነት የሚሰሩት አሊ መሀመድ አደም በ72 ሰዓት ውስጥ ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ መታዛቸውን የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ሚኒስቴሩ ትናንት ባወጣው መግለጫ "ዲፕሎማቱ ከሀገር እንዲወጡ የታዘዙት ከዲፕሎማሲ ሥራዎች የሚጣረስ ተግባር ውስጥ ተሰማርተው በመገኘታቸው ነው" ብሏል።

በዲፕሎማቱ ተፈፅሟል የተባለውን ድርጊት ያላብራራው ሚኒስቴሩ መግለጫ፤ ነገር ግን የዲፕሎማቱ ድርጊት ዲፕሎማቶች ያሉባቸውን ሀገር ህግ ማክበር እና በውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ከመግባት መቆጠብ አለባቸው የሚለውን "የቬናን የዲፕሎማቲክ ድንጋጌ የሚጥስ ነው" ብሏል፡፡

በመሆኑንም ሉኣለዊነትን ለመጠበቅ ሲባል ይህ እርምጃ መወሰዱን መግለጫው አስታውቋል።

ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ጋር የመግባቢያ ስምምነትን ከተፈራረመች በኋላ ሶማሊያ እና ኢትዮጵያ የከረረ የዲፕሎማሲያዊ ውዝግብ ውስጥ ገብተዋል፡፡

ይህን በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን አለመግባባት በንግግር ለመፍታትም፤ ቱርክ የሁለቱን ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በተናጠል በሁለት ዘር አነጋግራለች፡፡ ባለፈው መስከረም ወር ሊካሄድ የነበረው ሦስተኛ ዙር ንግግርም ሳይካሄድ ቀርቷል።

ኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ የተፈራረሙት የመግባቢያ ሰነዱ ተግባራዊ ከሆነ ኢትዮጵያ 20 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለውን የባህር በር ለ50 ዓመታት ከሶማሌላንድ በሊዝ እንድትከራይ ይፈቅዳል። በተመሳሳይ ማንም ሀገር እውቅና ሰጥቷት የማታውቀው ሶማሊላንድ ደግሞ ከኢትዮጵያ ሙሉ እውቅና እንድታገኝ ያደርጋታል።

ሶማሊያ ይህ ስምምነት "ሉዓላዊነቴን የሚጥስ ነው" ያለች ሲሆን፤ ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያን አምባሳደር ሙክታር መሀመድ ዋሬን ከሀገሯ ማባረሯን አሐዱ መዘገቡ ይታወሳል።

በሌላ በኩል የናይል ወንዝን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ጋር የተለየ ውዝግብ ያላት ግብፅ ደግሞ፤ ሶማሊያን በጽኑ የመደገፍ አዝማሚያን እያሳየች ትገኛለች።

የግብፅ እና የሶማሊያ መሪዎች በነሀሴ ወር የመከላከያ ስምምነት የተፈራረሙ ሲሆን፥ በዚህም ስምምነት መሰረት በሁለት ዙር የግብፅ ወታደራዊ አውሮፕላኖች የጦር መሳሪያ ጭነው ሞቃዲሾ መግባታቸው መገለጹ ይታወሳል፡፡

ይህን ተከትሎም የወቅቱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር የአሁኑ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፕሬዝደንት አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ፤ "ባልተረጋጋ የደህንነት ሁኔታ ውስጥ በውጭ ኃይላት የሚደረግ የጦር መሣሪያ አቅርቦት መጨረሻው አሸባሪዎች እጅ ላይ ሊወደቅ ይችላል" ሲሉ ለሶማሊያ ያላቸውን ስጋት ገልጸው ነበር፡፡

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…
Subscribe to a channel