ahaduradio | Unsorted

Telegram-канал ahaduradio - AHADU RADIO FM 94.3

19349

አሐዱ ራድዮ 94.3 Your source for top local and international news and analysis. "Voice of Ethiopian" የአሐዱ የቴሌግራም ቻናል ቤተሰብ በመሆን ወቅታዊና እውነተኛ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ

Subscribe to a channel

AHADU RADIO FM 94.3

#አሐዱ_ትንታኔ

ትንታኔውን ለመከታተል ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👇
https://youtu.be/GVxMVIhWU0A?si=DQyqvG1j_hHo-KL1

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በአዲስ አበባ ሲ.ኤም.ሲ ሚካኤል አካባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአንድ ሰው ሕይወት አለፈ

ሕዳር 23/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በአዲስ አበባ ከተማ ሲ.ኤም.ሲ ሚካኤል አካባቢ ዛሬ ከረፋዱ 5:30 ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአንድ ሰው ሕይወት አልፏል።

አደጋው የሲኖ ትራክ ተሽከርካሪ ከሞተር ሳይክል ጋር በመጋጨቱ በተከሰተ ሲሆን፤ በግጭቱ ምክንያት ሞተር ሳይክል የሚያሽከረክረው ግለሰብ በአሰቃቂ ሁኔታ ሕይወቱ ማለፉን አሐዱ በቦታው ተገኝቶ ማረጋገጥ ችሏል፡፡

በአካባቢው የተገኙት የትራፊክ ፖሊስ እና የጸጥታ አካላት ጉዳዩን እያጣሩት መሆኑን ለአሐዱ አስታውቀዋል፡፡ ጉዳቱን ያደረሰው አሽከርካሪም እጁን ለጸጥታ አካላት መስጠቱን አረጋግጠናል።

በሲ.ኤም.ሲ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ወደ ወሰን በሚወስደው መንገድ ላይ የተፈጠረውን የትራፊክ አደጋን በተመለከተ የሚመለከተውን አካል አነጋግረን እንመለስበታል፡፡

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!

ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የፌደራል መንግሥት ኤርትራ ጦሯን ከኢትዮጵያ ግዛት እንድታስወጣ ይፋዊ ጥያቄ መቅረብ አለበት ተባለ

ሕዳር 23/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ኤርትራ በኢትዮጵያ ይዛቸዉ ካለችዉ አካባቢዎች መዉጣት ይኖርባታል ሲሉ ከአሐዱ ጋር ቆይታ ያደረጉ ዲፕሎማቶች እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ተናግረዋል።

"በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ዘላቂ ሰላም ማምጣት የሚቻለዉ ሕዝቡም ከስቃይ መዳን የሚችለዉ ኤርትራ ጧሯን ከኢትዮጵያ ማስወጣት ስትችል ነው" ሲሉ የተናገሩት፤ የኢሮብ አኒና ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት የቦርድ አባል የሆኑት አቶ ተስፋዬ አዉዓላ ናቸዉ።

"ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ የፌደራል መንግሥት ኤርትራ ጧሯን ከኢትዮጵያ ግዛት ለቃ እንድትወጣ ይፋዊ የሆነ ጥሪ ማድረግ ሲችል ነው" ብለዋል፡፡

የድንበር ኮሚሽን ውሳኔንም በተመለከተ በሁለቱ ሀገራት መንግሥታት እንዲሁም በድንበር አካባቢ ያሉ የማህበረሰብ ክፍሎች በውይይት መፍታት እንዳለባቸውም አቶ ተስፋዬ አሳስበዋል።

"ነገር ግን ማንኛዉም ዉይይት ከመደረጉ ቀድሞ የኤርትራ ሰራዊት ከኢትዮጵያ ግዛት መዉጣት አለበት" ሲሉ አክለዋል።

"ከሰሜኑ ጦርነት ወዲህ የኤርትራ ሰራዊት ግማሽ ወረዳ ያህሉን የኢሮብ አካባቢን ጨምሮ ይዞ ይገኛል። በአልጀርሱ ስምምነት መሠረት የድንበር አካላይ ኮሚሽን በአየር ላይ ማስመሩ አሳውቆ ነበር" የሚሉት ደግሞ የቀድሞው ዲፕሎማት ዳያሞ ዳሌ ናቸዉ።

"ይህንን ለብዙ ጊዜ ሲንከባለል የመጣዉን ችግር መፍታት ወሳኝ ነው" ያሉት የቀድሞ ዲፕሎማቱ፤ "መሬት ላይ ድንበር ማካለል ባልተደረገበት የራስ አድርጎ መዉሰድ ተገቢ አይደለም" ብለዋል፡፡

የኤርትራ ሠራዊት 6ዐ በመቶ የሚሆነዉን የኢሮብ ማህበረሰብ መቆጣጠሩን የኢሮብ አኒና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ለአሐዱ ገልጿል።

በአቤል ደጀኔ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

አሜሪካ በታይዋን ጉዳይ ላይ ጣልቃ ከመግባት እንድትታቀብ ቻይና አስጠነቀች

ሕዳር 23/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) አሜሪካ በታይዋን ጉዳይ ላይ ጣልቃ ከመግባት መታቀብ አለባት ሲል የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስጠንቅቋል፡፡

ቻይና ማስጠቀቂያዉን ለማዉጣት የተገደደችዉ፤ አሜሪካ ባሳለፍነው ቅዳሜ 385 ሚሊዮን ዶላር የሚገመቱ ኤፍ 16 የጦር ጄቶች እና መለዎወጫዎችን ለታይዋን ለመሸጥ መወሰኗን ተከትሎ መሆኑ ተነግሯል።

"የአሜሪካ ያልተገናዘበ እና መርህን የጣሰ ዉሳኔ የአንድ ቻይናን ፖሊስ የሚጥስ ስለሆነ ቤጂንግ አትጋስም" ሲሉ የቻይና የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር አስጠንቅቀዋል።

"ዋሽንግተን ታይዋን የቻይና አንድ አካል መሆኗን መቀበል አለባት" ሲሉ ያሳሰቡት ሚኒስትሩ፤ "ይህን አሜሪካ በዝምታ የምታልፈዉ ከሆነ ግን ቻይና ሉአላዊነቷን ለማስጠበቅ ቁርጠኛ ናት" ማለታቸውን ኢንዲያን ታይምስ ዘግቧል።

ነገር ግን እራሷን እንደ ሉዓላዊ ሀገር የምትቆጥረዉ ታይዋን፤ ለኢኮኖሚ እድገት በጣም ወሳኝ በሆነ ግዛት ውስጥ እንደምትገኝ ተነግሯል።

በተጨማሪ ወደ ደሴቷ አሜሪካ የምትቀርብ ከሆነ ከምዕራብዊያን አጋሮቿ ጋር ጥብቅ የሆነ ትስስር ይፈጥርላታል ነዉ የተባለዉ።

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በመንግሥት የተደረገው የበጀት ጭማሪ የዋጋ ግሽበት ሊያስከትል እንደሚችል የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች ተናገሩ

ሕዳር 23/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከሚንስትሮች ምክር ቤት የተላከለትን ተጨማሪ 582 ቢልዮን ብር በጀት ማጽደቁ፤ ማህበረሰቡ ላይ አሉታዊ ጫና ሊፈጥር እንደሚችል ተነግሯል፡፡

የምጣኔ ሃብት ባለሙያው እንዳይላሉ ሰለሞን እንደተናገሩት ከሆነ፤ መንግሥት ከበጀተው ተጨማሪ በጀት ተመላሽ ገቢ ሊያሰገኝ የሚችል ኢንቨስትመንት ላይ ያዋለው የብር መጠን አነስተኛ በመሆኑ የዋጋ ግሽበቱን ሊያባብሰው ይችላል፡፡

ባለሙያው አክለውም፤ መንግሥት ደሞዝተኛውን በደምወዝ ጭማሪ ብቻ ሳይሆን በአገልግሎትም ሊደግፈው እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

"በተጨማሪም መንግሥት ተጨማሪ በጀት ሲበጅት ከታክስ ገቢ ለማግኘት አቅዶ ከሆነ፤ ይህ የማህበረሰቡን አቅም የሚያዳክም ነዉ" ሲሉ ለአሐዱ ተናግረዋል።

የቢዝነስና ኢንቨስትመንት አማካሪው ከፈለኝ ሃይሉ በበኩላቸው፤ የተደረገው የበጀት ጭማሪን በዶላር ቢሰላ ካለፈው ዓመት ሊያንስ እንደሚችል ገልጸው፤ "በተደረገው ጭማሪ ሳቢያ መንግሥት በሚሰበስበው ግብር ምክንያት ግብር ከፋዩ ማህበረሰብ ላይ ጫና ያሳድራል" ብለዋል፡፡

ባለሙያው አክለውም፤ ኢኮኖሚው የወጣውን ያክል ገንዘብ የመሰብሰብ አቅም እንዳለውም ሊጠና እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም የበጀት ጭማሪ መደረጉ አሉታዊ ብቻ ሳይሆን አዎንታዊ ተጽዕኖ እንዳለው የተናገሩ ሲሆን፤ "የበጀት ጭማሪ መኖሩ የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎቶች እንዲስፋፉ ያደርጋል" ብለዋል፡፡

የቢዝነስና ኢንቨስትመንት ባለሙያው አክለውም፤ "ተጨማሪ በጀት መፅደቁ የተለያዩ የድንገተኛ አደጋዎችን በፍጥነት ለመመለስ እንዲሁም የተለያዩ የመህበረሰቡን ጥያቄዎች ባስቸኳይ ሊመልስ ይችላል" ሲሉ ገልጸዋል።

ባለሙያዎቹ የበጀት ጭማሪ መደረጉ የዋጋ ንረቱን እንደሚያባብስ በመግለጽ፤ "የተሻለ አተገባበር ተፈፃሚ የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት እንዲሁም ድንገተኛ አደጋ ቢፈጠር ለመቆጣጠር ይጠቅማል" ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት ሕዳር 17 ቀን 2017 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለ2017 በጀት ዓመት የቀረበለትን የ582 ቢሊየን ብር የበጀት ጭማሪ በአብላጫ ድምጽ በ3 ተቃውሞ እና በአምስት ድምጸ ታቅቦ ማፅደቁ ይታወሳል። በዚህም መሠረት የ2017 አጠቃላይ በጀት 1 ነጥብ 55 ትሪሊዮን ብር ደርሷል።

በዳግም ተገኝ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

መልካም ቀን!
አሐዱ ሬድዮ 94.3  የኢትዮጵያውያን ድምፅ!

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በኢትዮጵያ በየዓመቱ መከላከል በሚቻሉ በሽታዎች ምክንያት 95 ሺሕ ሕጻናት እንደሚሞቱ ተነገረ

ሕዳር 21/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ የሳምባ ምችን ጨምሮ መዳን በሚችሉና ቀላል በሆኑ በሽታዎች ሳቢያ፤ በየዓመቱ ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ 95 ሺሕ ሕጻናት እንደሚሞቱ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

በተለይም መከላከል የሚቻሉ ሆነው ሕጻናት ከሚሞቱባቸው ዋና ዋና ምክያቶች መካከል፤ በቀዳሚነት የሚቀመጠው የሳምባ ምች መሆኑን በጤና ሚኒስቴር የጨቅላ ሕጻናትና ሕጻናት ዴስክ ኃላፊ መለስ ሰለሞን ለአሐዱ ተናግረዋል።

መዳን የሚችሉ በሽታዎች ሆነው ነገር ግን የሕጻናት ሕይወት እየነጠቁ ከሚገኙ በሽታዎች መካከል የሳምባ ምች 17 በመቶውን የሞት ምጣኔ እንደሚይዝ ገልጸዋል። "ነገር ግን የሳምባ ምችን ክትባት ከማስከተብ ጀምሮ ክትትል ከተደረግ መከላከል የሚቻል ሆኖ እያለ፤ ለሕጻናት ሞት ምክንያት ሆኗል" ብለዋል።

ከሳምባ ምች በመቀጠል በሁለተኛው ደረጃ መዳን የሚችል ሆኖ ሳለ ለሕጻናት ሞት መንስኤ በመሆን የተቀመጠው ተቅማጥ ሲሆን፤ በሌላ በኩልም ከተወለዱ እስከ 28 ቀን ላሉ ጨቅላ ህፃናት ዋና ዋና ገዳይ ከሚባሉት መካከል ቀናቸው ሳይደርስ መወለድ፣ ኢንፌክሽን እና መታፈን መሆናቸውን ኃላፊው አክለዋል።

ለዚህም በምክንያትነት ከሚጠቀሱት መካከል የግንዛቤ እጥረት፣ በቅርቡ ጤና ጣቢያ ማግኘት አለመቻል፣ የመንገድ ችግር፣ መድኃኒትን ጨምሮ ባለሙያ የሚፈልገውን ያህል አለማግኘት ተጠቃሽ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ከኢትዮጵያ ሕዝብ ከ83 በመቶ በላይ የሚሆነው ነዋሪነቱ ገጠር ከመሆኑ አንፃር፤ ከጤና ተቋም ተደራሽነት አኳያ የራሱ የሆነ ተፅዕኖ አለው ያሉት ኃላፊው፤ ይሁን እንጂ በትክክል መታከም ከቻሉ መዳን የሚችሉ በሽታዎች በመሆናቸው የጤና አቅርቦት፣ ስልጠና እና የማህበረሰብ የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራዎችን በመስራት እንዲቀንስ ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ምንም እንኳን ሕጻናት የሚለው ትርጓሜ እንደ ዓለም ጤና ድርጅት ከተወለደ እስከ 18 ዓመት መሆኑን ያስታወሱት አቶ መለስ፤ "እንደ ኢትዮጵያ ትኩረት ተሰጥቶ የሚሰራው ግን ከአምስት ዓመት በታች ባሉ ሕጻናት ላይ ነው" ብለዋል።

ለዚህም ምክንያቱ "ከሕዝብ ብዛት አንፃር ተደራሽነት ከግምት ውስጥ መግባት ዋነኛው ይሁን እንጂ፤ ሕጻናት አምስት ዓመት ከተሻገሩ በሌሎች ነገሮች ካልሆነ በስተቀር የሳንባ ምችን ጨምሮ መዳን በሚችሉ በሽታዎች የተነሳ ለሞት የሚዳረጉበት ሁኔታ አስጊ ባለመሆኑ ነው" ሲሉ አስረድተዋል።

የጨቅላ ሕጻናትና ሕጻናት ፕሮግራም በተለየ መልኩ ትኩረት ተሰጥቶ ከሚሰራባቸው ፕሮግራሞች መካከል አንዱ እንደሆነም ተመላክቷል። ነገር ግን አሁን ድረስ መዳን በሚቻሉና ቀላል በሆኑ በሽታዎች የተነሳ በርካታ ሕጻናት ለህልፈት እንደሚዳረጉ ይገለጻል።

በአበረ ስሜነህ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

ሙስና እና ብልሹ አሰራር በኢምግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት የአሰራር ስርዓት ላይ ስጋት መደቀኑ ተገለጸ

ሕዳር 21/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኢምግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት የአሰራር ስርዓት ላይ ሙስና እና ብልሹ አሰራር እየተስፋፋ ነው ሲል የፌዴራል የሥነ ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

በተደጋጋሚ በሙስና እና ብልሹ አሰራር ክስ ሲቀርብበት የሚታየው የኢምሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ለዜጎች የሚሰጠውን አሰራር እያዘመነ መሆኑን ቢያሳውቅም፤ አሁንም ድረስ ቅሬታ እየቀረበበት ይገኛል፡፡

በቅርቡ እንኳን ከፓስፖርት ቅጣት የተሰበሰበ ወደ 18 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ገንዘብ በግለሰብ አካዉንት ገቢ ሲደረግ እንደነበር በኦዲት መረጋገጡና በምክር ቤት መቅረቡ የሚታወስ ነው፡፡

ይህን ሕገ-ወጥ አሰራራ ሲሰራ የቆየው ደግሞ ተቋሙ ባላወቀው መመሪያ እና ሕግ እንደሆነ የፊደራል ዋና ኦዲተር ገልጿል፡፡

አሐዱም "በተደጋጋሚ በተቋሙ ላይ የሚታዩ የሙስና እና ብልሹ አሰራሮችን ለምን መቅረፍ አልተቻለም? እናተስ እንደተቋም ምን እየሰራችሁ ነው?" ሲል የፌዴራል የሥነ ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽንን ጠይቋል፡፡

የኮሚሽኑ የሥራ አመራር ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተስፋዬ ሸሜቦ በሰጡት ምላሽ፤ "ተቋሙ ለዜጎች በሚሰጣቸው የአሰራር ሂደቶች ላይ ስጋት እንዳለ መመልከት ችለናል" ብለዋል፡፡

ኮሚሽኑ በቀጣይ በይበልጥ መሰራት አለባቸው በሚባሉ ጉዳዮች ላይ እንደተቋም እንደዚህ አይነት ለዜጎች አስጊ የሆኑ አሰራሮችን ለመከታተል የሚያስችል ቴክኖሎጂ እያስተዋወቀ መሆኑንም ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

"በኢትዮጵያ በሚገኙ በሁሉም ተቋማት ላይ ሙስና እና ብልሹ አሰራር አለ" ያሉት አቶ ተስፋዬ፤ "ነገር ግን ይህንን ለመቀርፍ የሥነ ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን መከላከያ ሚኒስቴርን ጨምሮ በሌሎች ተቋማት የሚገኙ አመራሮችን ስልጠና እየሰጠን ነው" ብለዋል፡፡

የፌዴራል ዋና ኦዲተር የ2015 እና 2016 በጀት ዓመት የፓስፖርት አገልግሎት አሰጣጥና ውጤታማነትን በተመለከተ የክዋኔ የኦዲት ሪፖርት ላይ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውይይት ባደረገበት ወቅት፤ የኤምግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ስልጣን ሳይሰጠዉ ከፓስፖርት የሚገኝ የቅጣት ገንዘብ ሲሰበስብ መቆየቱ መገለጹ ይታወሳል፡፡

በዚህም አገልግሎቱ የገንዘብ ሚኒስትርን ሳያስፈቅድ የራሱን አካዉንት በመክፈት 17 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር ገደማ ገቢ ስለማድረጉ ተነግሯል።

አሐዱ ለተጨማሪ መረጃ የኢምግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ኮሚኒኬሽን ቢሮ ተደጋጋሚ ስልክ ሙከራ ያደረገ ቢሆንም ማግኘት አልቻለም። ነገር ግን ተቋሙ ምላሽ ለመስጠት ፍቃደኛ ከሆነ ምላሹን ወደእናንተ የምቀርብ ይሆናል።

በደረጄ መንግስቱ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የቤት ውስጥ ጾታዊ ጥቃት እየተባባሰ መምጣቱ ተገለጸ

ሕዳር 21/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በቤት ውስጥ የሚፈጸም ጾታን መሠረት ያደረገ ጥቃቶት እየጨመረ መምጣቱን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳይ ቢሮ አስታውቋል።

በክልሉ በሕጻናትና አፍላ ወጣቶች ላይ በቅርብ ሰዎች አማካኝነት አስገድዶ መድፈር፣ ግድያ እና ጾታን መሠረት ያደረገ ጥቃት መፈጸም እየተስፋፋ መምጣቱን ለአሐዱ የገለጹት፤ የክልሉ ሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳይ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኩሪባቸው ታንቶ ናቸው።

አሐዱም "የችግሩ መስፋፋት ከታወቅ ለምንስ መቆጣጠር እና መከላከል አልተቻለም?" ሲል ኃላፊዋን ጠይቋል።

በምላሻቸው ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች መበራከት፣ የሕግ ክፍተትና መላላት እንዲሁም የግንዛቤ ማነስ ጥቃቱ እንዲስፋፋ ምክንያት መሆኑን የገለጹ ሲሆን፤ በርካታ ሥራዎች ቢሰሩም የሚፈለገውን ያክል ለውጥ ማምጣት አለመቻሉን ተናግረዋል።

በተጨማሪም ባለትዳር ሴቶች ለቤት ውሰጥ ፆታዊ ጥቃት ተጋለጭነታቸው የሰፋ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ኃላፊዋ አክለውም ከፌዴራል አካላት ጋር በመሆን ችግሩን ለመቅረፍ እየተሰራ እንደሚገኝ ለአሐዱ ገልጸዋል።

ለቤት ውሰጥ ጾታዊ ጥቃት ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች የተለያዩ ኢኮኖሚያዊና ሥነልቦናዊ ድጋፎች እየተደረጉ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

የችግሩን ግዝፈትና የሚያስከትለውን ጉዳት በመረዳትም ማሕበረሰቡ መሰል ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ከመፈጸም መቆጠብ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

በወልደሀዋርያት ዘነበ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

#ADVERTISMENT
#ጊፍትሪልስቴት
ታላቅ የምስራች!

**
ጊፍት ሪል ስቴት ከ10% ቅድመ ክፍያ ጀምሮ በ22 ሳይቶቹ ቅንጡ አፓርትመንቶችን እና የንግድ ሱቆችን ለሽያጭ አቅርቧል፡፡

ይህ ሳይት ለአፓርትመንትና ንግድ ሱቆች የሚውሉ G+25 ሶስት መንታ ህንጻዎች ያሉት ሲሆን የዚህ 6ኛ መንደር መለያዎች፡-
•ከባለአንድ እስከ ባለአራት መኝታ ክፍሎች ያሉት፣
•ለመኖሪያም ሆነ ለንግድ ተመራጭ አካባቢ የሆነ፣
•በአንድ ወለል ሶስት ቤቶች ብቻ ያሉት፣
•በእያንዳንዱ ወለል ስድስት አሳንስር ያለው፣
•አራት ቤዝመንት ያሉት በቂ የመኪና ማቆሚያ የተዘጋጀለት፣
•24 ሰዓት የኤሌክትሪክ፣ ኢንተርኔትና ውሃ አቅርቦት አሉት፣

ጊፍት ሪል ስቴት
ማህበረሰብን እንገነባለን!
ለበለጠ መረጃ፡-
Website: https://www.giftbusinessgroup.com                                                                                             
Twitter: https://twitter.com/GIFTBusinessG                                                     
YouTube: www.youtube.com/channel/UCcqr7cpVv9ski-F7haxXx4w                                                     
Facebook: www.facebook.com/profile.php?id=100090918391017...                                                       
Telegram: /channel/giftbusinessgroup

Short Code: 8055

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

#አሐዱ_መድረክ

"የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች ፖለቲካ ምን እንደሆነ አያውቁም" ከ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ዋና ጸሀፊ ደስታ ዲንቃ ጋር የተደረገ ቆይታ (ክፍል ሁለት)

ቆይታውን ለመከታተል ከሥር ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ!
👇
https://youtu.be/aOHBNUAYkys?si=lTr_V7G_0NjeN5HQ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

#አሐዱ_ትንታኔ

ትንታኔውን ለመከታተል ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👇
https://youtu.be/Ty9eHXNTCTE?si=6vCwD7jfbapTEW1E

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

"በደባርቅ ከተማ በረዶ ቀላቅሎ በጣለው ዝናብ ለተጎዱ አርሶ አደሮች በቂ ድጋፍ እየተደረገ አይደለም" የሰሜን ጎንደር ዞን ግብርና መምሪያ

ሕዳር 20/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ከተማ፤ በርዶ ቀላቅሎ በጣለው ዝናብ ምክንይት ጉዳት የደረሰባቸው አርሶ አደሮች በቂ ድጋፍ እንዳልተደረገላቸው የዞኑ ግብርና መምሪያ ገልጿል።

የሰሜን ጎንደር ዞን ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ጌትነት አዳነ ሕዳር 14 2017 ዓ.ም በደባርቅ ከተማ በረዶ ቀላቅሎ የጣለው ዝናብ ወደ 5 ሺሕ 500 ሄክታር የሚሆን ማሳ ማውደሙን የገለጹ ሲሆን፤ በወረዳው 3 ቀበሌዎች ማለትም፤ ክራር፣ ምቃራ እና ኪኖ በተባሉ ቀበሌዎች ላይ ከባድ ጉዳት ማድረሱን ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

በዚህም ከ7 መቶ በላይ አርሶ አደሮች የጉዳቱ ሰለባ መሆናቸውን የጠቆሙ ሲሆን፤ ሰብላቸው ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ መውደሙን ተናግረዋል።

የመምሪያው ኃላፊ አቶ ጌትነት "ተጎጂዎችን የመለየት፣ መረጃ የማጥራትና ማህበረሰቡን የማረጋጋት ሥራ እሰራን ነው" ያሉ ሲሆን፤ "በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ለጊዜው ከማገገም አንፃር አቅም ያላቸውን ቀበሌዎች የመስኖ ዘርና በቴክኖሎጂ የታገዘ የውሀ መሣቢያ ሞተር የማቅረብ ሥራዎችን እየሰራን ነው" ብለዋል ።

በቀጣይ በዘላቂነት ድጋፍ ከማድረግ አኳያ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ስለመሆኑም ለአሐዱ ገልጸዋል፡፡

"የቅርብ ጊዜ ጉዳይ ስለሆነ ኮሚቴ የማደራጀት፣ መረጃዎችን የማጥራት፣ የመለየት ሥራዎችን እየተከታተልን በቀጣይ እናሳውቃለን" ሲሉም ተናግረዋል።

በመጨረሻም መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች መረጃውን ተደራሽ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልጸው፤ "ነገር ግን እስካሁን ምንም አይነት ድጋፍ አልተደረገም" ያሉ ሲሆን፤ በቀጣይ ሁሉም አካላት ድጋፍ እንዲያደርግ የመምሪያ ኃላፊ ጥሪ አቅርበዋል።

በከተማዋ ሕዳር 14/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ ለ30 ደቂቃ ያህል የጣለው ከባድ የበረዶ ዝናብ በተለያዩ የሰብል አይነቶች ላይ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን፤ ከነዚህም ውስጥ ስንዴ፣ ገብስ፣ ጤፍና ጥራጥሬ ሰብሎች ይገኙበታል ተብሏል።

በአንማው በሪሁን
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ ዘጠኝ ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ በታጣቂዎች መገደላቸውን እናት ፓርቲ ገለጸ

ሕዳር 20/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኦሮሚያ ክልል፣ አርሲ ዞን፣ ሽርካ ወረዳ፣ ሶሌ ፈረንቀሳና ሶሌ ጡጃ ቀበሌ ትናንት ሕዳር 19 ለሕዳር 20 አጥቢያ ከሌሊቱ 8፡00 ገደማ፤ በአንድ ቤተሰብ ዙሪያ ያሉ ዘጠኝ ሰዎች በታጣቂዎች መገደላቸውን እናት ፓርቲ አስታውቋል።

ከሟቾቹ መሐል 70 ዓመት ያለፋቸው ኹለት አረጋውያንን አባቶች እንዳሉ የገለጸም ሲሆን፤ "በእድሜ የገፉ እናቶችና ወጣቶችም አሉበት" ሲል ፓርቲዉ ዛሬ በሰጠዉ ጋዜዊ መግለጫ አስታውቋል፡፡

ግዳያዉ የተፈጸመዉ በአከባቢዉ በሚንቀሳቀሱ የታጠቁ አካላት (ሸኔ) መሆኑን ከአካባቢው ነዋሪዎች ማረጋገጡን የገለጸው ፓርቲዉ፤ "ነዋሪዎች ሌሊት ላይ መጥተውና እየመረጡ ወንዝ ዳር ከወሰዱ በኋላ አስተኝተው ጭካኔ በተሞላበት መልኩ እንደፈጇቸው ገልጸውልናል፡፡" ብሏል።

ከሟቾች በተጨማሪ ቀደም ሲልም አራት ግለሰቦች ታግተው እንደተወሰዱና እስካሁን ድረስ በምን ኹኔታ ላይ እንደሚገኙ እንደማያቁ ከነዋሪዎች መረዳቱን ገልጿል።

ፓርቲው አክሎም ከሰሞኑ በዚሁ አካባቢ 2 ሰዎች ተገድለው ሌሎች 8 ሰዎች ታግተው እንደተወሰዱ የአካባቢው ነዋሪዎች መስማቱን በመግለጽ፤ ታጋቾቹ የትና በምን ኹኔታ እንዳሉ ምንም ዓይነት መረጃ እንደሌላቸውም በመግለጫው አመላክቷል፡፡

"አርሲ ውስጥ ባለፉት 5 ዓመታት በተለይ ማንነትና ሃይማኖት ተኮር ዘግናኝ ግድያዎች እንደሚፈጸሙ ገልጸዉልኛል" ያለዉ እናት ፓርቲ፤ በቅርብ ጊዜያት ደግሞ "የመንግሥት የጸጥታ አካላት ነን" ያሉ ገብተው ከነዋሪው በግዳጅ መሣሪያ እያስወረዱ እንደነበር ነዋሪዎች መረዳቱን አስታውቋል።

በተደጋጋሚ ተጠያቂነት ከሌለ መግደል ቀላል እንደሚሆን በመግለጽም፤ በንጹሓን እልቂት ታጣቂዎችም መንግሥትም እኩል ተጠያቂነት እንዳለባቸው አምነው እንዲህ ካለው አገርን ወደ ሁለንተናዊ ቀውስ ከሚመራ ድርጊት እንዲታቀቡ አሳስቧል።

የጸጥታ ኃይሉም የፓርቲ ጉዳይ አስፈጻሚ ሳይሆን የሕዝብ ልጅነቱን እንዲህ ባለው እልቂት ፈጥኖ በመድረስና በማስቆም እንዲያስመሰክርም ፓርቲው ጥሪውን አቅርቧል።

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

ኮንዶም ከቀረጥ ነጻ እንዲገባ መፈቀዱ ተነገረ

ሕዳር 20/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ ያለውን የኤች አይቪ ስርጭት ለመግታት የገንዘብ ሚንስቴር በአዋጅ ቁጥር 1341/2024 መሰረት ኮንዶም ከቀረጥ ነጻ ሆኖ ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገባ ፈቅዷል፡፡

በሀገሪቱ 278 ሚልዮን ኮንዶም የሚያስፈልግ ሲሆን፤ ወደ ሀገር ለመግባት በሂደት ላይ ያለ የኮንደም ቁጥር 111 ነጥብ 8 ሚልየን ብቻ በመሆኑ እንዲሁም፤ ኮንዶም ወደ ሀገር ውስጥ የሚያስገቡ ነጋዴዎችና ረጂ ድርጅቶች ቁጥር በማሽቆልቆሉ ምክንያት ከታክስ ነጻ እንዲሆን መደረጉን የገንዘብ ሚንስቴር የታክስ ጉዳዮች አማካሪ አቶ አብረሃም ረጋ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

ከዚህ በፊት የኮንዶም ምርት 35 በመቶ የታክስ ክፍያ ተከፋፍሎ እንዲገባ የሚስያገድድ ፖሊሲ እንደነበር ያነሱት አማካሪው፤ ከሰኔ 13 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ግን የመመሪያ ማሻሻያ ተደርጎ ከታክስ ክፍያ ነጻ እንዲሆን መደረጉ አስረድተል።

አማካሪው አክለውም፤ ለማምረት በፍቃድ የሚወስዱ ተቋማትና ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት ሃሳብ ያላቸው ድርጅቶች ከታክስ ነጻ ማስገባት እንደሚችሉ እንዲሁም የተለያዩ ማበረታቻዎች እንደሚሰጣቸውም ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ ከግማሽ ሚልዮን በላይ ሰዎች የኤች አይቪ ቫይረስ በደማቸው ውስጥ እንደሚገኝ መገለጹ የሚታወስ ነው፡፡

በዳግም ተገኝ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

ከእናቶቻቸው ጋር በማረሚያ ቤት የሚገኙ ሕጻናት መብቶች እየተከበሩ አደለም ተባለ

ሕዳር 23/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ ከእናቶቻቸው ጋር በማረሚያ ቤት የሚገኙ ሕጻናት የሰብዓዊ መብቶች እየተከበሩ አለመሆኑን አሐዱ ያነጋገራቸው የሕግ ባለሙያዎች ገልጸዋል፡፡

የኢትጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ባለፈው ዓመት የኢትዮጵያ ዓመታዊ የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርትን ይፉ ባደረገበት ወቅት የሴቶችና የሕፃናት ሰብአዊ መብቶች ሁኔታን በተመለከተ እንዳቀረበው፤ ከእናቶቻቸው ጋር በማረሚያ ቤት የሚገኙ ሕጻናት የወላጆቻቸውን እንክብካቤ ማግኘት እንዳልቻሉ መግለጹ ይታወሳል።

ሆኖም በአሁኑ ወቅት በማረሚያ ቤቶች ከእናቶቻቸው ጋር ያሉ ሕጻናት የሰብዓዊ መብት አያያዝ በምን አይነት ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ አሐዱ ኢሰመኮን የጠየቀ ሲሆን፤ ኮሚሽኑ በምላሹ ጥናት እየተደረገ ስለመሆኑና አለመጠናቀቁን ገልጿል፡፡

የሕግ ባለሙያ የሆኑት አቶ ካሳሁን ሙላት ከአሐዱ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ የሕጻናት መብት በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት እውቅና ያለው ከመሆኑም ባለፈ ሰፊ ጥበቃና ሽፋን የሚሰጠው መሆኑን በማስታወስ፣ በርካታ ሕጻናት ከወላጆቻቸው ጋር በማረሚያ ቤት እንደሚገኙ ተናግረዋል።

"ነገር ግን በማረሚያ ቤት ከእናቶቻቸው ጋር የሚገኙ ሕጻናት በበቂ ሁኔታ ትምህርት፣ ለአዕምሮ እና አካላዊ እድገታቸው የሚመጥን የመጫወቻ ቦታ፣ የጤና አገልግሎትና እንክብካቤ ያገኛሉ ወይ ሲባል፤ የማረሚያ ቤትች ሁኔታ ይህን ያሟላ አይደለም" ብለዋል።

ሌላኛዉ የሕግ ባለሙያ ፍፁም አብርሃም በበኩላቸው፤ ከፍርደኛ እናቶቻቸው ጋር አብረው እንዲቆዩ የሚደረገው በአብዛኛው እድሜያቸው 24 ወር ያልሞላቸው ሕጻናት መሆናቸውን ገልጸዋል።

ነገር ግን ከዚያ በላይ ሆነው ሌላ የሚንከባከባቸውና ተቀብሎ የሚያሳድጋቸው ቤተሰብ የሌለ እንደሆነ፤ ከእናታቸው ጋር በማረሚያ ቤት እንዲቆዩ የሚደረግ መሆኑን ተናግረዋል። በፌደራል ማረሚያ ቤቶች አዋጅም የማረሚያ ቤት አስተዳደሩ ለሕጻናቱ እንክብካቤና ድጋፍ የማድረግ ግዴታ አለበት በማለት የሚደነግግ መሆኑን አስታውሰዋል።

"በማረሚያ እንዲቆዩ ሲደረግ የሕጻናት መብቶች ተጠብቀው ነው" ያሉት ባለሙያው፤ "ነገር ግን በተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተግዳሮቶች የተነሳ ሕጻናቶች ማግኘት ያለባቸውን እንክብካቤ እያገኙ አይደለም" ብለዋል።

ከእናቶቻቸው ጋር በማረሚያ ቤት የሚገኙ ሕጻናት ማግኘት ያለባቸውን መብቶች እያገኙ እንዳልሆነ የሚናገሩት የሕግ ባለሙያዎቹ፤ "የሚመለከተው አካል በሙሉ በርብርብ በማድረግ በማረሚያ ቤት የሚገኙ ሕጻናት ማግኘት ያለባቸውን መብቶችና ጥበቃዎች እንዲያገኙ መደረግ አለበት" ሲሉ አፅንኦት ሰጥተዋል።

አሐዱ የፌደራል ማረሚያ ቤትን ለማነጋገር ያደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡ በቀጣይ ምላሹን ይዞ በሌላ ዘገባ የሚመለስ ይሆናል፡፡

በአበረ ስሜነህ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የአየር መንገድ ባልደረባ ወድቆ ያገኙትን 50 ሺሕ ዶላር ለባለቤቱ አስረከቡ

ሕዳር 23/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሴኪዩሪቲ ክፍል ባልደረባ ፍሬዘር በቀለ ወድቆ ያገኙትን 50 ሺሕ የአሜሪካ ዶላር ለባለቤቱ ማስረከባቸውን አየር መንገዱ አስታውቋል፡፡

አቶ ፍሬዘር ገንዘቡን በሕዳር 16 ቀን 2024 ዓ.ም ከመንገደኛ ወድቆ ማግኘታቸው ነው የተገለጸው፡፡

ግለሰቡ በኢትዮጵያዊ ጨዋነትና ሲቀጠሩ በገቡት ቃል መሰረት አየር መንገዱ የሚመራበትን መርህና ሥነ-ምግባር እንዲሁም ሙያዊ ታማኝነታቸውን በብቃት መወጣታቸውንም አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ "አየር መንገዳችን ዓለም-አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ እና ስነ-ምግባር የተላበሰ የደንበኞች አገልግሎት ምንግዜም ያላሰለሰ ጥረት ያደርጋል" ሲልም ገልጿል።

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በመቶዎች የሚቆጠሩ የሶማሊያ ኮማንዶዎች በቱርክ መመረቃቸዉ ተሰማ

ሕዳር 23/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ከ30 ዓመታት በላይ በአፍሪካ የሰላም አስከባሪ ልዑክ እየተጠበቀች የምትገኘው ሞቃዲሾ፤ በመቶዎች የሚቆጠሩ ልዩ ኮማንዶች በአንካራ ማስመረቋን አስታዉቃለች።

"የኮማንዶዎቹ መመረቅ ዋናኛ አላማ የአልሸባብን ጥቃት ለመመከት ነው" ሲል በተርኪ የሶማሊያ ኢምባሲ አስታውቋል።

በሶማሊያ እና በቱርክ መካከል ያለውን ጠንካራ ግንኙነት በሁሉም መስክ ለማሳደግ እና ወንድማማችነትን የበለጠ ለማጠናከር ሞቃዲሾ በቁርጠኝነት መሥራቷን እንደምትቀጥል የሶማሊያ የመከላከያ ሚኒስትር አብዱልቃድር መሀመድ ኑር አስታዉቀዋል።

አክለውም፤ አንካራን "በተለይ ለሶማሊያ ሰላም እና ደህንነት እንዲሁም በአጠቃላይ ለምስራቅ አፍሪካ ለሚያደርገው ጠቃሚ ድጋፍ" ማመስገናቸውን አናዶሎ ዘግቧል።

ተርኪዬ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከሶማሊያ ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እያጠናከረች ሲሆን፤ የትምህርት፣ የመሰረተ ልማት እና የጤና አጠባበቅ ዘርፎች ላይ ኢንቨስት አድርጋለች።

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከታጠቁ ሃይሎች ጋር አሁንም ውይይት ማድረግ እንደሚፈልግ ገለጸ

ሕዳር 23/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ነፍጥ አንግበው ከመንግሥት ጋር ግጭት ውስጥ የሚገኙ ቡድኖች ወደ ምክክር መድረኩ እንዲገቡ ጥሪ ሲያደርግ ቆይቷል።

የተፈጠረውን እድል ሁሉም የማኅብረተሰብ ክፍሎች ሊጠቀሙበት እንደሚገባም በተደጋጋሚ ተጠይቋል።

ኮሚሽኑ "ማንኛውም 'ሀሳብ አለኝ' የሚል አካል ወደ ውይይት መምጣት አለበት" ብሎ እንደሚያምን የሚገልጹት የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ናቸው።

የኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች በምክክሩ ለሚሳተፉት የታጠቁ አካላት ኮሚሽኑ ተገቢውን የጥበቃ ዋስትና እንደሚያመቻችና ከኢትዮጵያም ውጪ በፈለጉት ቦታ ውይይት ለማድረግ ፍቃደኛ መሆኑን ለአሐዱ ተናግረዋል።

ኮሚሽነሩ "ደጋግመን እንደምንገልጸው የሀገራዊ ምክክር ኮሚሸን አንዱ ዓላማ ታጥቀው ያሉ ወገኖች ትጥቃቸውን አስቀምጠው ወደ ንግግር እንዲመጡ ማድረግ ነው" ብለዋል። "አሁንም በምዕራብ ኦሮሚያም ሆነ በአማራ ክልል ያሉ ከመንግሥት ጋር በግጭት ውስጥ ያሉ አካላት ወደ ድርድር እንዲመጡ ጥረት እያደረግን ነው" ሲሉም ተናግረዋል።

ኮሚሽኑ ከታጣቂ ሀይሎች ጋር ቀጥታ ግንኙነት እንደሌለው ገለጸ ሲሆን፤ የመገናኛ ብዙሃን አካላት እገዛ እንዲያደርጉለትም ጥሪውን አቅርቧል።

የቆይታ ግዜው ሊጠናቀቅ ሦስት ወር ያላነሰ ግዜ የቀረው የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከታጣቂዎች ጋር በተደጋጋሚ ውይይት ለማድረግ አጀንዳ ለመሰብሰብ ያደረገው ሙከራ ሳይሳካ ቀርቷል፡፡

ኮሚሽኑ ከዚህ በተጨማሪም በአማራ፣ በከፊል ኦሮሚያ እና በትግራይ ክልል ሙሉ ለሙሉ የአጀንዳ ስበሰባ ማድረግ አለመቻሉ ይገለጻል፡፡

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዋጅ ቁጥር 1265/2014 ዓ.ም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጸደቀ ሲሆን፤ ታህሳስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ሦስተኛ ዓመቱ የሚሞላ በመሆኑ ጊዜው በምክር ቤቱ ካልተራዘመለት ይጠናቀቃል፡፡

በአቤል ደጀኔ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

#ADVERTISMENT
#AmharaBank
የአማራ ባንክ አ/ማ የባለአክሲዮኖች 3ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ማክሰኞ ታህሳስ 01 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ በሚሊኒየም አዳራሽ ስለሚካሄድ ባለአክሲዮኖች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጉባዔው እንድትገኙ ጥሪ እናስተላልፋለን፡፡

የጉባዔው አጀንዳዎችን እና ተጨማሪ መረጃዎችን ጥቅምት 06 ቀን 2017 ዓ.ም በወጡት አዲስ ዘመን እና ሪፖርተር አማርኛ እትም ጋዜጦች ላይ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ለበለጠ መረጃ ነፃ የጥሪ ማዕከል 690 ወይም
የባንኩን ድረ ገጽ www.amharabank.com.et ይጎብኙ፡፡

አማራ ባንክ
ከባንክ ባሻገር!

የአማራ ባንክ ትክክለኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾች
Website: www.amharabank.com
Facebook: www.Facebook.com/amharabanksc1
Telegram: /channel/Amhara_Banksc
Instagram: https://instagram.com/amhara_bank
Twitter: https://twitter.com/Amharabanksc
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/amharabank/
YouTube: https://youtube.com/channel/UC73x9uuGYV0Uxw0EkpVZN8g
TikTok: amharabanks.c" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@amharabanks.c

#አማራባንክ #AmharaBank

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

#አሐዱ_ስንክሳር

የፅላተ-ሙሴ መቀመጫ አክሱም ፅዮን (በጥበቡ በለጠ)

ሙሉ ጥንቅሩን ለመከታተል ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👇
https://youtu.be/gDsImnNlkx8?si=YwyXOibMO68dilSD

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

"ብልፅግና ከሀሳብ እንጂ ከሰዎች ጋር ግጭት ውስጥ አይገባም" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

ሕዳር 21/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የብልጽግና ፓርቲ አምስተኛ ዓመት የምስረታ በዓል የማጠቃለያ መርኃ ግብር፤ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዝደንት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ተካሄዷል።

በዓደዋ መታሰቢያ በተካሄደው መርኃ ግብር ላይም ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ፤ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት ተመስገን ጥሩነህ፣ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ አገኘሁ ተሻገር፣ የክልል ርዕሰ መስተዳደሮች እና የከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች እንዲሁም የፓርቲውና የመንግሥት ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

በመርኃ ግብሩ ላይም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ፓርቲው ወደ ስልጣን ከመጣበት ጊዜ አንስቶ እስከ ዛሬ ድረስ ያከናወናቸውን የዲፕሎማሲ፣ የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ እንቅስቃሴ ያብራሩ ሲሆን፤ በዚህም "በፖለቲካው ዘርፍ የብልጽግና ፓርቲ አዲስ የፖለቲካ ልምምድ በኢትዮጵያ አስጀምሯል" ብለዋል።

ከዚህ ቀደም ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር መስራት እንዳልነበር ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በጠላትነት የመተያየት ባህልን ማስቀረት መቻሉን ገልጸዋል።

"ብልፅግና ከሀሳብ እንጂ ከሰዎች ጋር ግጭት ውስጥ አይገባም" ያሉም ሲሆን፤ "የሀሳብ ልዕልና የብልጽግና ፓርቲ ባህሉ ነው" ሲሉም መናገራቸውን ከፓርቲው ማኅበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

በተጨማሪም የብልፅግና ፓርቲ ከ 15 ሚሊዮን በላይ አባላት ያሉት የአፍሪካ ግዙፉ ፓርቲ መሆኑን የገለጹ ሲሆን፤ በኢኮኖሚው ዘርፍም ባለፉት 5 ዓመታት ኢትዮጵያ የበጋ ስንዴ ማምረት የጀመረችበት፣ ሥራ አቁመው የነበሩ ኢንዱስትሪዎች ወደ ሥራ የገቡበት፣ ሜጋ ፕሮጀክቶች የተመረቁበት እንደነበር አንስተዋል።

በዲፕሎማሲ በኩልም ባለፉት 5 ዓመታት ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር እየሰራች ያለችው በወዳጅነት እና በትብብር መሆኑን ጠቁመዋል።

በመርሐ ግብሩ መልዕክት ያስተላለፉት የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ በበኩላቸው፤ "የበዓሉ ዓላማ ፓርቲው ከምሥረታው ጀምሮ እስካሁን ያደረገውን ጉዞ ለመዘከር እና ቃላችንን ለማደስ ነው" ብለዋል።

ፓርቲው በርካታ ፈተናዎች ቢያጋጥሙትም ፈተናዎችን ወደ ድል በመቀየር ድል ማስመዝገቡን ጨምረው ተናግረዋል፡፡

የብልጽግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓል "የሀሳብ ልእልና ለሁለንተናዊ ብልጽግና" በሚል መሪ ሀሳብ በተለያዩ ሁነቶች ሲከበር መቆየቱ ይታወሳል።

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት ከሦስት እስከ አራት ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙ ተገለጸ

ሕዳር 21/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በአፋር ክልል በተከታታይ በተከሰቱ የመሬት መንቀጥቀጦች ምክንያት ከሦስት እስከ አራት ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙ ተገልጿል፡፡

በክልሉ በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ከስድስት መቶ በላይ ተማሪዎች ከትምህርት መማሪያ ክፍል ውጭ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ እንደሚገኙ፤ የአፋር ክልል አዋሽ ፈንታሌ ወረዳ የትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሙሳ ሀሰን ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

ኃላፊው ባለፉት ጊዜያት በተከሰቱ የመሬት መንቀጥቀጦች ምክንያት፤ ከሦስት እስከ አራት ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ላይ ውድመት መድረሱን አስረድተዋል፡፡

ከክልል ትምህርት ቢሮ እና አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት የትምህርት ስርዓቱን ከመማሪያ ውጪ ለሚከታተሉ በመቶች ለሚቆጠሩ የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ድጋፍ እየተሰባሰበ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

የትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊው አክለውም፤ በክልሉ ከዚህ በፊት ከአራት ነጥብ ስምንት በላይ ሬክተር ስኬል መጠን ሲከሰት የነበረው የመሬት መንቀጥቀጥ፤ በአሁኑ ወቅት እየተስተዋለ እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡

ነገር ግን በወረዳው የሚስተዋለው የመሬት መንቀጥቀጥ በድንገት የሚከሰት መሆኑን ተከትሎ፤ ጥንቃቄ እንደሚያስፈልግ እና ተማሪዎቹ ትምህርታቸውን በድንኳን እና ከመማሪያ ክፍል ውጭ እየተከታተሉ ስለመሆኑ ተነግሯል፡፡

አክለውም በመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት በመማሪያ ሕጻዎች ላይ የደረሱ ውድመቶች ለመጠገን ተጨማሪ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡

በእሌኒ ግዛቸው
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የዝቅተኛ የደሞዝ ወለል ውሳኔ መዘግየቱ አሳስቦኛል ሲል ኢሰማኮ አስታወቀ

ሕዳር 21/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) መንግሥት የዝቅተኛ የደሞዝ ወለል ለመወሰን የየያዘውን ዕቅድ ሊያዘገየው ይችላል መባሉ አሳስቦኛል ሲል የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን አስታውቋል።

መንግሥት የዝቅተኛ ደሞዝ ወለልን ለመወሰን ጥናት አጥንቶ የጨረሰ ቢሆንም፤ "ችግር ያመጣብኛል በሚል ስጋት አዝግይቼዋለው" ማለቱን ተገቢ አይደለም ሲሉ የኮንፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ካሳሁን ፎሎ ለአሐዱ ተናግረዋል።

ፕሬዝዳንቱ "ይህንን በሚመለከት ለሚመለከተው የፌደራል የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ምላሽ እንዲሰጠን ስንል ጠይቀናል" ብለዋል።

"በተጠና ጥናት መሠረት ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል" የሚል ነገር መነገሩን የገለጹት አቶ ካሳሁን፤ "ጥናት በትክክል ተደርጎ ከሆነ በጥናቱ ላይ መሳተፍ ነበረብን" ብለዋል።

አቶ ካሳሁን አክለውም "እንደተባለው ኮሚሽኑን ሳያካትቱ ተጠንቶም ከሆነ ጥናቱን እንዲሰጡን ስንል በደብዳቤ ጠይቀናል" ሲሉም ተናግረዋል።

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ከኑሮ ውድነት ጋር ተያይዞ የስራ ግብር እንዲቀነስ እና የዝቅተኛ ደመወዝ ወለል የሚወስን የደመወዝ ቦርድ እንዲቋቋም ሲጠየቅ ይሰማል።

በኢትዮጵያ የሚገኘው የኑሮ ሁኔታ በቋሚ ደምወዝ በሚኖሩ ተቀጣሪ ሠራተኞች ላይ እየፈጠረ ያለው ተጽእኖ ከጊዜ ወደጊዜ እየተባባሰ እንደሆነ ይገለጻል፡፡

"የኑሮ ውድነቱ ሠራተኛው ከሚያገኝው ገቢ ጋር ሊመጣጠን ባለመቻሉ ዜጎች በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ኑሯቸውን እንዲገፉ አስገድዷል" ያለው የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን፤ ማስተካካያዎች እንዲደረጉ በተደጋጋሚ ጥያቄ ሲያቀርብ መቆየቱን አስታውቋል፡፡

ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል እንዲወሰን እና የግብር ቅነሳ እንዲደረግ ኢሰማኮ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር በነበረው ውይይት ጥያቄ ማቅረቡ የሚታወስ ሲሆን፤ ተደጋጋሚ ጥያቄዎችን በደብዳቤ ቢጠይቅም ተገቢውን ምላሽ አለማግኘቱ ይገለጻል፡፡

በአቤል ደጀኔ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

መልካም ቀን!
አሐዱ ሬድዮ 94.3  የኢትዮጵያውያን ድምፅ!

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በክፍያ መንገዶች ላይ የሚስተዋሉ የአሰራር ችግሮችን ለመፍታት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

ሕዳር 20/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የመንገድ ፈንድ ክፍያን አስመልክቶ በርካታ ችግሮች ሲነሱ እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን፤ አሁን ላይ ችግሮቹን ለመፍተታት እንቅስቃሴዎች መጀመራቸውን የኢትዮጵያ መንገድ ፈንድ ኢንተርፕራይዝ አስተዳደር አስታወቋል።

ኢንተርፕራይዙ ከአዲስ አበባ አዳማ ያለውን ጨምሮ ሌሎች የክፍያ መንገዶች አገልግሎት እየሰጡ መሆናቸውን በመጥቀስ፤ ያሉበትን ክፍተቶች ለሙላት አሰራሩን እያዘመነ መሆኑን ለአሐዱ ገልጿል።

የኢትዮጵያ መንገድ ፈንድ ኢንተርፕራይዝ በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሥር የሚተዳደር መንግሥታዊ የልማት ድርጅት ሲሆን፤ አሰራሩን ለማዘመን እየሰራ መሆኑን የድርጅቱ የኮሙኒኬሽን ኃላፊ ስንታየሁ መኮንን ተናግረዋል።

መንግሥት የልማት ድርጅቶችን ለማዘመን ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ በርከት ያሉ ማሻሻያዎች እያደረገ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው፤ የክፍያ መንገዶች ለተሸከርካሪዎች ምቹ ከማድረግ በተጨማሪ አጠቃላይ የአገልግሎት ስርዓቱን ዘመናዊና ቀልጣፋ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የክፍያ መንገዶች አገልግሎት ከተጀመረ ወዲህ በርካታ ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑንም የኮሙኒኬሽን ኃላፊው ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ መንገድ ፈንድ ኢንተርፕራይዝ የተፈቀዱ ሦስት የክፍያ መንገዶችን የሚያስተዳድር ሲሆን፤ እነርሱም የአዲስ አበባ - አዳማ፣ የድሬዳዋ ዳዋሌ እና የሞጆ - ባቱ የክፍያ መንገዶች ናቸው፡፡

ኢንተርፕራይዙ የአገልግሎት ስርዓቱን ከማዘመን በተጨማሪ፤ የክፍያ መንገዶችን ደህንነት ለመጠበቅ እና የመንገድ መሰረተ ልማት እንዳይወድም ከተፈቀደላቸው የጭነት በላይ በሚጭኑት ተሽከርካሪዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እያደረገ መሆኑን አስታውቋል።

በዚህም መሰረት ከዛሬ ሕዳር 20 ቀን 2017ዓ.ም ጀምሮ ትርፍ በክፍያ መንገዶች ላይ ከክብደት በላይ ለጫኑ ተሸከርካሪዎች የጫኑትን ጭነት እንዲቀነሱ በማስደረግ በተፈቀደለት የክብደት መጠን ብቻ እንዲንቀሳቀሱ እንደሚያደርግ የገለጸ ሲሆን፤ በጫኑት የትርፍ መጠን መሰረት ቅጣቱን ተግባራዊ የሚያደርግ መሆኑን ገልጿል።

በተጨማሪም ልዩ ሀገራዊ ጠቀሜታ እና ባህሪ ያላቸውን ጭነት ለሚጭኑ ተሽከርካሪዎች እና የሚጭኑት ጭነት ከተፈቀደው የክብደት መጠን በላይ ከሆነ ከመጫናቸው በፊት በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር በኩል ልዩ ፍቃድ ሲያገኙ ብቻ እንደሚስተናገዱ አስታውቋል፡፡

በአማኑኤል ክንደያ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ብዙ ሄክታር የአገዳ ምርት በእሳት መቃጠሉ ተገለጸ

👉በአደጋው አንድ ዶዘር መቃጠሉም ተገልጿል


ሕዳር 20/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በምዕራብ ኦሮሚያ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ሱሉላ ፍንጫ ወረዳ የሚገኘው የፍንጫ ስኳር ፍብሪካ የአገዳ ምርት ትናንት መቃጠሉን የፋብሪካዉ ሠራተኞችና ነዋሪዎች አስታውቀዋል።

ትናንት ከቀኑ 8 ሰዓት አካባቢ የተነሳዉ እሳት፤ በአምስት ማሳዎች ላይ የነበረዉን የሸንኮራ አገዳ ማቃጠሉን የፋብሪካዉ ሠራተኞች ገልጸዋል።

የፍንጫ ስኳር ፍብሪካ በሚሊዩን ኩንታል የሚቆጠር ስኳር ያመርት የነበረ ሲሆን፤ ከ2015 ዓ.ም ወዲህ በተለያየ ጊዜ በደረሰበት ጥቃት ምርቱ መቀነሱ ተነግሯል፡፡

የትናንትናው ቃጠሉ በማን እንደተለኮሰ ባይታወቅም፤ ከዚህ ቀደም በፋብሪካው ይዞታ ውስጥ በሕገ ወጥ መንገድ የሚያርሱ ግለሰቦች ያመረቱትን ምርት የአካባቢው የወረዳ አስተዳደር መውረስ መጀመሩን ተከትሎ፤ በቂም በቀል ያደረጉት ሳይሆን እንዳልቀረ ሠራተኞች መናገራቸውን ዶይቼ ቬለ ዘግቧል፡፡

"ትናንት አገዳ ተቃጥሎብን ነበር፡፡ አንድ ዶዘርም ተቃጥሏል፡፡ ከቀኑ 8፡00 እስከ ምሽቱ 1፡30 የእሳቱን እያጠፋን ነበር፡፡ ብዙ ሄክታር የሚሆን አገዳ የተቃጠለ ሲሆን፤ መንደር 2 የተባለ ቦታ ብቻ ከ50 እስከ 60 ሄክታር ይሆናል የተቃጠለው፡፡ ሰክሽን ‹ዲ እና ኢ‹ የሚባሉ ቦታዎች አሉ እዛም ተቃጥሏል፡፡" ሲሉ ሠራተኖቹ ገልጸዋል።

የፍንጫ ስኳር ፍብሪካ በግንቦት 2015 ዓ.ም በደረሰበት ጥቃት በቢሊዩን ብር የሚገመት ውድመት ደርሶበት እንደነበር ከዚህ ቀደም መዘገቡ ይታወሳል፡፡

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በአዲስ አበባ የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ በእጥፍ የታሪፍ ጭማሪ ተደረገ

ሕዳር 20/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ታሪፍ ጭማሪ መደረጉን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

በዚሁ መሠረት ከታሕሣስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በመዲናዋ ተግባራዊ የሚደረግ የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር አገልግሎት ታሪፍ አሁን እየተሰጠበት ካለው 10 ብር ወደ 20 ብር ማሻሻያ መደረጉን ቢሮው አስታውቋል፡፡

የታሪፍ ማሻሻያው ከታሕሣስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ ታውቆ ተፈፃሚ እንዲደረግም ቢሮው አሳስቧል፡፡

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት ከሰሜን ወደ ደቡብ (ከጊዮርጊስ - ቃሊቲ) እና ከምስራቅ ወደ ምዕራብ (ከአያት - ጦር ኃይሎች) የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት፤ በየቀኑ በ10 ሺሕዎች የሚቆጠሩ መንገደኞች እንደሚያጓጉዝ ተገልጿል፡፡

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

#አሐዱ_መድረክ

"የፖለቲካ ፓርቲዎች ብሄር ተኮር ሆነዋል" ከ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ዋና ጸሀፊ ደስታ ዲንቃ ጋር የተደረገ ቆይታ (ክፍል አንድ)

ቆይታውን ለመከታተል ከሥር ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ!
👇
https://youtu.be/KvXwScYVFHE?si=U0ErY-51eABdqXo8

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

ዲሽታ ጊና ወይንም የአሪ ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ በዓል በሚቀጥለው ታሕሳስ ወር ላይ ይካሄዳል

ሕዳር 20/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ዲሽታ ጊና ወይንም የአሪ ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ በዓል በብሔረሰቡ የቆየ አከባበር መሰረት፤ በሚቀጥለው ታሕሳስ ወር ላይ በጂንካ ከተማ እንደሚከበር ተገልጿል።

የአሪ ብሔረሰብ ወይንም ዲሽታ ጊና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ሥር ዞን ሆኖ መቋቋሙን የሚታወስ ሲሆን፤ የዘመን መለወጫ በዓሉን ቅድመ ዝግጅትን አስመልክቶ በዛሬው ዕለት የባሕልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ሸዊት ሻንካን ጨምሮ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በተገኙበት በብሔራዊ ትያትር መግለጫ ተሰጥተዋል፡፡

በተጨማሪም ከጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤትና የፌደሬሽን ምክርቤት ተወካዮች መገኘታቸውንም ተገልጿል።

የአሪ ብሔረሰብ ወይንም ዲሽታ ጊና ብሔረ ሰቡ በሕገ መንግሥቱ መሰረት ዞን ሆኖ ለመቋቋም የሚያስችለውን መሰፈርት አሟልቶ በደቡብ ኢትዮጵያ መንግሥት ሥር ዞን ሆኖ መመስረቱ ተገልጿል።

በዚህም መሰረት በብሔረሰቡ የዘመን ቀመር አቆጣጠር "ሎንጋ'' በተሰኘው ታህሳስ ወር ላይ በዓሉ በተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚከበር በዝግጅቱ አስተባበሪዎች አስታውቀዋል።

በሚቀጥሉት ወራት በደቡብ ኢትዮጵያ የሚገኙ ብሔረሰቦች እንደየ ባህላቸው የዘመን መለወጫ የሚያከብሩበት ወር መሆኑንም በመድረኩ ተመላክቷል፡፡

በአማኑኤል ክንደያ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ:www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…
Subscribe to a channel