ahaduradio | Unsorted

Telegram-канал ahaduradio - AHADU RADIO FM 94.3

19349

አሐዱ ራድዮ 94.3 Your source for top local and international news and analysis. "Voice of Ethiopian" የአሐዱ የቴሌግራም ቻናል ቤተሰብ በመሆን ወቅታዊና እውነተኛ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ

Subscribe to a channel

AHADU RADIO FM 94.3

ኢትዮጵያ በምግብ ንጥረ ነገሮች እጥረት ምክንያት በዓመት 5 ቢሊየን ዶላር እንደሚታጣ ተገለጸ

ሕዳር 25/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ኢትዮጵያ የንጥረ ነገር እጥረት በጤና ላይ የሚያስከትለውን ችግር ለማከም እና ለመርዳት ብቻ፤ በዓመት ከአጠቃላይ ኢኮኖሚው ላይ 5 ቢሊየን ዶላር እንደምታጣ ሚለር ፎር ኒውትሬሽን ኢትዮጵያ ገለጸ።

መቀመጫውን በቨርጂኒያ አርሊንግተን ያደረገውና የተመጣጠነ ምግብ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የማማከር፣ የቴክኒክ እና የፋይናንስ ድጋፍ ማቅረብ ላይ የሚሰራው ሚለር ፎር ኒውትሬሽን፤ በኢትዮጵያ በይፋ ሥራ መጀመሩን አስታውቋል።

የሚለር ፎር ኒውትሬሽን ኢትዮጵያ ፕሮግራም ማናጀር ኢያቄም አምሳሉ፤ ይህን ችግር ለመቅረፍ ከመንግሥትና የኢንዱስትሪው ዘርፍ ጋር ለመስራት መስማማታቸውን ገልጸዋል።

"የንጥረ ነገር እጥረት ችግር ለቤተሰብ፣ ለማህበረሰብ ከፍ ሲልም ለሀገር ትልቅ ተፅዕኖ እያሳደረ ነው" ያሉም ሲሆን፤ በዚህ የተጎዳው ማህበረሰብ ለአንድ ሀገር ያበረክት የነበረው አስተዋፅዖ ቀላል አለመሆኑን ጠቁመዋል።

ለዚህም የስንዴ ዱቄት በበርካታ የሕብረተሰብ ክፍል ዘንድ ጥቅም ላይ የሚውል በመሆኑ፤ ከ25 እስከ 30 በመቶ የስንዴ ዱቄት አምራች ፋብሪካዎች የበለፀገ (fortified) ዱቄት እንዲያመርቱ ግብዓትና ማሽኖች መግዛታቸውን ተናግረዋል።

እንዲሁም ሚለር ፎር ኒውትሬሽን በጀመረው እንቅስቃሴ በሦስት ወራት ውስጥ እስከ 60 በመቶ ለሚሆኑ የስንዴ ዱቄት አምራቶች አስፈላጊውን የግብዓትና ማሽን ድጋፍ ለማድረግ እቅድ መያዙን ጠቁመዋል።

በተመሳሳይም 38 የሚሆኑ ማጣሪያ ያላቸው የዘይት ፋብሪካዎች አስፈላጊ ግብዓቶችን ማሟላላታቸውን ገልጸዋል።

የንጥረ ነገር እጥረት ምክንያት 30 በመቶ የሚሆነው የአለም ሕዝብ አካላዊና አዕምራዊ አቅሙን እንዳይጠቀም ማድረጉን ከዚህ ቀደም የተደረጉ ጥናቶች ያሳያሉ።

በፍርቱና ወልደአብ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

ለካንሰር ሕክምና የሚውል መሳሪያ ከአራት ዓመታት በፊት በ2 መቶ ሚልየን ብር ግዥ ቢደረግም እስካሁን ሥራ ላይ አለመዋሉ ተገለጸ

ሕዳር 25/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በጎንደር እና መቀሌ ለካንሰር ሕክምና ይውላል ተብሎ በ2 መቶ ሚልየን ብር ወጪ የጨረር ሕክምና መስጫ መሳርያ ግዢ ቢደረግም ለአራት አመታት ሥራ ላይ አለመዋሉን የማቲዮስ ወንዱ የኢትዮጵያ ካንሰር ሶሳይቲ አስታውቋል።

የማቲዮስ ወንዱ የኢትዮጵያ ካንሰር ሶሳይቲ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወንዱ በቀለ የሕክምና መሳሪያውን ለመትከል ውስብስብ በመሆኑ አለመተከሉን በመግለጽ፤ ለ1 ሚልየን ሰው አንድ መሳሪያ ቢያስፈልግም ከቁጥሩ ጋር ያለዉ መሳሪያ ብዛት እንደማይመጣጠን ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ የካንሰር የጨረር ሕክምና በአዲስ አበባ በሃዋሳ እና ሀሮማያ እየተሰጠ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው፤ "እንደሀገር ብዙ የካንሰር ሕክምና መሳርያ በብዛት ያስፈልጋል" ብለዋል፡፡

ሕብረተሰቡ ወደ ጨረር ሕክምና ወይም 'ኬሞ ቴራፒ' ከመግባቱ በፊት አስቀድሞ መከላከል እንዲሁም ምርመራ ተደርጎ የተገኘባቸው ሰዎችም ሕክምና በማድረግ ማገገምና መዳን እንደሚችል ኃላፊው አጽንዖት ሰጥተውበታል፡፡

አሐዱ "ለካንሰር ሕክምና የሚውልው መሳሪያ ለምን ተገዝቶ ሥራ ላይ አልዋለም?" የሚለውን የጤና ሚንስቴርን ምላሽ ለማግኝት ጥረት ቢደረግም አልተሳካም። ምላሹን ባገኝነበት አፍታ በዘገባ የምንመለስበት ይሆናል፡፡

በዳግም ተገኘ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

"6 ማደያዎች ላይ እርምጃ ሲወሰድ ሁለት ማደያዎች በጊዜያዊነት ሥራ አቁመዋል" የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ

ሕዳር 25/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በ2017 ሁለት ወራት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ 6 ማደያዎች ላይ እርምጃ ሲወሰድ ሁለት ማደያዎች በጊዜያዊነት ሥራ ማቆማቸውን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታውቋል።

የነዳጅ እንቅስቃሴ በአዲስ አበባ ንድግ ቢሮ ሥር እንዲተዳደር ከተደረገ በኋላ በአንጻራዊነት የተረጋጋ መሆኑን የገለጸው ቢሮው፤ ማደያዎች ነዳጅን በመደበቅ እንደሌላቸው የሚያስመስሉበትን አሰራር ማስቀረት መቻሉን ተናግሯል፡፡

የንግድ ቢሮው የገበያ መረጃ ጥናት እና ማስተዋወቅ ዳይሬክተር አቶ ሙሰማ ጀማል ለአሐዱ በሰጡት ቃል፤ 'የማሽን ብልሽት አጋጠመ'፣ 'ነዳጅ አለቀ' እና ሌሎችንም ምክንያቶች የሚያቀርቡ ማደያዎች በባለሙያዎች ፍተሻ እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡

በዚህም አሰራሩ ከተጀመረ ባለፉት 39 ቀናት ውስጥ 6 ማደያዎች ሕገ ወጥ ተግባር ፈፅመዉ መቀጣታቸውን እና በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍል ከተማ የሚገኙ ሁለት ማደያዎች ነዳጅ የሚያቀርብላቸው ተቋም ጋር ያላቸው ውል በመቋረጡ ሥራ ማቆማቸውን አስታውቀዋል፡፡

"እርምጃ የተወሰደባቸው ስድስት ማደያዎች ነዳጅ እያለ 'የለም' በማለታቸው፤ የማስጠንቀቂያ እና በሕግ ተጠያቂ እንዲሆኑ የማድረግ ሥራ ተሰርቷል" ሲሉ ለአሐዱ ገልጸዋል፡፡

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የነዳጅ ማደያዎች ዕለታዊ የነዳጅ አቅርቦት መጠንን ጥቅምት ወር ላይ ይፋ ማድረግ መጀመሩ ይታወቃል፡፡

ለአብነትም የዛሬ ሕዳር 25 ቀን 2017 ዓ.ም ጠዋት ማደያዎች ሥራ ሲጀምሩ የነበራቸው የነዳጅ መጠን ሲታይ፤ ቤንዚን 3 ሚሊየን 167 ሺሕ 210 ሊትር፤ ናፍጣ ደግሞ 3 ሚሊየን 820 ሺሕ 464 ሊትር እንደነበር መረጃው ያሳያል፡፡

በተያያዘ ዜና በትናንትናው ዕለት በተካሄደው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስምንተኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ የሰጡት የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)፤ በአዲስ አበባ አንድ ቀን በተደረገ አሰሳ ከ120 ማደያዎች ስድስቱ ብቻ አገልግሎት ሲሰጡ መገኘታቸውን ተናግረዋል፡፡

አክለውም በነዳጅ የአቅርቦት እና የስርጭት ችግር መኖሩን ገልጸው፤ ይህን ችግርን ለመቅረፍ የተለያዩ ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

68 የሚሆኑ ነዳጅ ማደያዎች ነዳጅ እያላቸው 'የለም' ሲሉ መገኘታቸውንም ያብራሩት ሚኒስትሩ፤ ከ105 ሺሕ በላይ ነጋዴዎች ላይ በመላው ሀገሪቱ እርምጃ መወሰዱንና ከዚህ ወስጥ ከአንድ ሺሕ በላይ የሚሆኑት በእስራት አንዲቀጡ መደረጉን አስታውቀዋል።

በእመቤት ሲሳይ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበት በሚቀጥሉት ወራት ወደ 26 ነጥብ 1 ከፍ ሊል እንደሚችል ተመላከተ

ሕዳር 25/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ ያለዉ የዋጋ ንረት በሚቀጥሉት ወራት ከነበረዉ 16 ነጥብ 1 በመቶ በ10 በመቶ ጨምሮ፤ 26 ነጥብ 1 በመቶ ሊደርስ እንደሚችል የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ባለሙያዎች ማህበር ያወጣው የፖሊሲ ጥናት አመላክቷል።

ሸቀጦች ላይ እየተደረገ ያለዉ የዋጋ ጭማሪ ፈጣን በመሆኑና የኢትዮጵያ ብር የመግዛት አቅሙ መዳከም ጋር መጣጣም ባለመቻሉ፤ የዋጋ ንረቱ እንደሚከሰት በጥናቱ ተገልጿል።

በተጨማሪም የዋጋ ንረቱ የማህበረሰቡን የአኗኗር ዘይቤ እንደሚቀይረዉና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸዉ ማህበረሰቦች ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ስለማሳደሩም ተመላክቷል።

እንዲሁም የውጭ ምንዛሬ እጥረቱና ኢኮኖሚው የተመጣጠነ አለመሆኑን የተቆመው ማህበሩ፤ የገበያ መር ስርዓት ሊያረጋጋው እንደማይችልም ገልጿል።

ሌላዉ በጥናቱ እንደታየዉ ከሆነ ለኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ መሻሻል ማነቆ ከሆኑት ውስጥ፤ የሰላም መደፍረስ፣ በቂ ጥሬ እቃ አለመኖር፣ ደካማ የሆነ መሰረተ ልማትና ቢሮክራሲ መብዛት ዋነኞቹ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

እንደ መፍትሔ ሀሳብ መንግሥት በረጅም ጊዜ የልማት ዕቅዶቹ ላይ የሚያወጣውን ወጪ በመቀነስ አነስተኛ ገቢ ላላቸው ዜጎች የማኅበራዊ ድጋፍ ማድረግ እንዳለበት ተመላክቷል።

በዳግም ተገኘ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

መልካም ቀን!
አሐዱ ሬድዮ 94.3  የኢትዮጵያውያን ድምፅ!

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በኢትዮጵያ ከአስር ሴቶች መካከል አንዷ አካላዊ ጥቃት ይደርስባታል ሲል የአውሮፓ ህብረት አስታወቀ

ሕዳር 24/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ኢትዮጵያ ውስጥ ከአስር ሴቶች መካከል አንዷ አካላዊ ጥቃት እንደሚደርስባት የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ አስታውቋል።

የፆታ ተኮር ጥቃት አድራሾች በብዛት የተጠቂዎች የቅርብ ሰዎች ሲሆኑ፤ ከእነዚህም የትዳር አጋሮች በቀዳሚነት የጥቃቱ አድራሽ ሆነው ይታያሉ ብሏል።

የሕግ ማሻሻያዎችን በማደረግ እና ለተጎጂዎች ድጋፍ በመስጠት በቅርብ አጋሮች የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ማስቆም የበለጠ ደህንነቱ የተጠበቀ ማህበረሰብ ለመፍጠር አስፈላጊ ስለመሆኑም ህብረቱ ጠቁሟል።

የፆታ ጥቃት አካላዊ ብቻ አለመሆኑም ያመላከተም ሲሆን፤ ኢትዮጵያ ውስጥ 13 ነጥብ 3 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች ስነ-ልቦናዊ ጥቃቶች ደርሶባቸዋል ብሏል።

"ይህም ስድብ፣ ማስፈራራት እና አምባገነናዊ ተቆጣጣሪነትን ይጨምራል" ያለው ህብረቱ፤ በሰሃራ ዙሪያ ባሉ የአፍሪካ አካባቢዎች ደግሞ ወደ 29 ነጥብ 9 በመቶ ከፍ እንደሚል አስታውቋል።

በተጨማሪም ኢትዮጵያ ውስጥ ከአስር ሴቶች አንዷ አካላዊ ጥቃት እንደሚደርስባት ያስታወቀ ሲሆን፤ በመላው አፍሪካ ደግሞ ቁጥሩ ወደ አንድ ሦስተኛ የቀረበ መሆኑን ገልጿል።

"አላማ ተኮር የሆኑ ጣልቃ ገብነቶች ደግሞ ለዚህ አንገብጋቢ ጉዳይ መልስ ለመስጠት እንዲሁም፤ ወደፊት ሁሉም ሰው በተሻለ ደህንነትና እኩልነት የሚኖርበትን ሁኔታ ለመፍጠር  ቁልፍ ድርሻ አለው" ሲል አክሏል።

በተለይም በኢትዮጵያ ዝቅተኛ ገቢ ባለው የህብረተሰብ ክፍል ውሰጥ የሚኖሩ ሴቶች ለፆታ ተኮር ጥቃት የበለጠ ተጋላጭ ሲሆኑ፤ "ከእነዚህም ውስጥ 11 ነጥብ 3 በመቶ የሚሆኑት አካላዊ ጥቃት ይደርስባቸዋል" ብሏል።

በአንፃሩ ይህ ቁጥር ከፍተኛ ገቢ ባላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ውስጥ ወደ 8 ነጥብ 2 በመቶ ዝቅ ይላል ያለው የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ፤ ለሴቶች የኢኮኖሚ አቅም መፍጠር ጥቃትን ለመቀነስ የሚረዳ ስለመሆኑም ገልጿል፡፡

በአበረ ስሜነህ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

#አሐዱ_ትንታኔ

ለአሜሪካ ማስጠንቀቂያ የላኩት ኪም ጆንግ ኡን

ትንታኔውን ለመከታተል ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👇
https://youtu.be/NSpRLdxAL1g?si=utDM14VsxnzCZNbQ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አባላት ወደ ተዘጋጀላቸው ካምፕ መግባት መጀመራቸው ተገለጸ

ሕዳር 24/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኦሮሚያ ክልል መንግሥት እና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አመራሮች የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ፤ የሠራዊቱ አባላት ወደ ተዘጋጀላቸው ካምፕ መግባት መጀመራቸው ተገልጿል፡፡

የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት አመራር የነበሩት ጃል ሰኚ ነጋሳ መንግሥት ያቀረበላቸውን የሰላም ጥሪ በመቀበል ከኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ጋር በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ፅህፈት ቤት አዲስ አበባ ላይ ባሳላፍነው ሳምንት የሰላም ስምምነት መፈራረማቸው ይታወሳል፡፡

ይህንኑ ተከትሎ በተለያዩ አካባቢዎች ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አባላት ወደ ተዘጋጀላቸው ካምፕ እየገቡ መሆኑን፤ በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡

ሰሞኑን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አመራር ጋር ተፈራረምኩት ያለውን የሰላም ስምምነት የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ያጣጣለው ሲሆን፤ "የክልሉ መንግሥት የሰላም ስምምነት ተፈራረምኩ ያለው ከወራት በፊት ከቡድኑ ከተባረሩ አንድ ግለሰብ ጋር ብቻ ነው ሲል" መግለጹ ይታወሳል።

ከመንግሥት ጋር የጀመረውም ሆነ ያቀደው አዲስ የሰላም ድርድር እንደሌለ የጠቀሰው ቡድኑ፤ "መንግሥት ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ጋር እየተደራደርኩ ነው በማለት የሚናገረው "ሕዝብን ለማወናበድ" ሲል ብቻ ነው" በማለት ከሶም ነበር።

ይህንን ሥምምነት ተከትሎም በዛሬው ዕለት በምዕራብ ሸዋ ዞን ኮቢ ወረዳ የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት አመራር አባላት በሕዝብ አቀባበል እንደተደረገላቸው ተነግሯል።

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በኦሮሚያ ክልል ሁለት ሕገወጥ የነዳጅ ቦቴዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገለጸ

ሕዳር 24/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኦሮሚያ ክልል ዱከም ከተማ በሕገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ሁለት ሙሉ የነዳጅ ቦቴ በቁጥጥር ሥር መዋሉን የኦሮሚያ ንግድ ቢሮ አስታውቋል።

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ገሾ ሕገወጥ ነዳጁ ቢፍቱ በሚባል ካምፓኒ በኩል ሲዘዋወር መቆየቱንና ከ 3 ቀን በፊት ለሊት ዱከም ከተማ ላይ በበርሜል ሲቀዳ መያዙን ለአሐዱ ገልጸዋል።

አክለውም፤ "ከሕግ ውጪ በሆነ መንገድና መቀዳት ካለበት በላይ በመቅዳቱ እንዲሁም ለምን አላማ እንደሚውል የማናውቅ በመሆኑ በቁጥጥር ሥር ውሏል" ብለዋል።

ምክትል ኃላፊው በኦሮሚያ ክልል በ2017 የመጀመሪያው በጀት ዓመት እስከ ትላንትናው ዕለት ድረስ በአጠቃላይ 133 ሺሕ 857 ሊትር ግምቱ 13 ሚሊዮን 781 ሺሕ 423 ብር የሆነ ሕገወጥ ነዳጅ በቁጥጥር ሥር ውሎ፤ 1 ሚሊዮን 559 ሺሕ 11 ብር ለመንግሥት ገቢ መደረጉንም ለአሐዱ ተናግረዋል።

የተያዘው ሕገወጥ ነዳጅ መፍትሄ እስከሚያገኝ ድረስ ምን ያክል መጠን እንደያዘ ተለክቶ በመታሸጉ ምን እናድርገው? በሚል ውይይት ተካሂዶ ዛሬ ጠዋት ለነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን እንዳስታወቁ ገልጸዋል።

በዚህም መሰረት "ወደ ዲፖ እንዲገባ አልያም እነሱ በሚያስቀምጡልን አቅጣጫ መሰረት በመሄድ አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወሰድበት እየተሰራ ነው" ብለዋል።

የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰሀረላ አብደላሂ ሕገወጥ ነዳጁን የኦሮሚያ ክልል በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ዛሬ መረጃው እንዳደረሷቸው ገልጸው፤ ከሁለቱ የነዳጅ ቦቴ አንደኛው የቤንዚን ሲሆን ሌላኛው የናፍጣ እንደሆነ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

ነዳጅ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ የሚዘውር ትልቅ ጉዳይ በመሆኑ በተለይም ከማክሮ ኢኮኖሚው ማሻሻያ በኋላ ጥብቅ የሆነ ቁጥጥርና ክትትል እየተደረገበት እንደሚገኝ ጠቅሰው ፣ "ማንም ግለሰብ ተነስቶ የነዳጅ ነጋዴ መሆን አይችልም" ሲሉ አሳስበዋል።

በስፍራሽ ደመላሽ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በኢትዮጵያ ከ17 ነጥብ 6 በመቶ በላይ ሰዎች የአካል ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ተገለጸ

ሕዳር 24/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ ከ17 ነጥብ 6 በመቶ በላይ ሰዎች የአካል ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው የአለም ጤና ድርጅትና አለም ባንክ ያጠናው ጥናት መጠቆሙ ተገልጿል፡፡

ይህ የተነገረው ዓለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች ቀን በማስመልከት በሀዋሳ ከተማ በተካሄደው የፓናል ውይይት ላይ ነው።

አለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች ቀን ዛሬ ታህሳስ 3 በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ33ኛ ተከብሮ ይውላል። በኢትዮጵያ ደግሞ ለ32ኛ ጊዜ "የአካል ጉዳተኞችን የመሪነት ሚና በማጉላት አካታችና ዘላቂ ልማትን እናረጋግጥ!" በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ይገኛል፡፡

በሀዋሳ ከተማ ቀኑ በማስመልከት በተካሄደው የፓናል ውይይት ላይም ከጤና፣ ከትምህርት፣ ከማህበራዊ ድጋፎች፣ ማህበራትን ከማደራጀት፣ አጋዥ መሣሪያዎችን ከማቅረብ፣ ማህበራዊ ተሀድሶ ተቋማትን ከማስፋፋት፣ አስገዳጅ ሕግ ማዕቀፍ ከማዘጋጀት አንፃር የተሰሩ ሥራዎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

በውይይቱ አንደ ተግዳሮት ከተነሱት መካከል፤ ተደራሽ አለመሆን፣ የአካል ጉዳተኞች አሁናዊ ዳታ አለመኖር፣ የመንገዶችና ሕንፃዎች ግንባታ አካል ጉዳተኞችን በበቂ ሁኔታ ያገናዘበ አለመሆን እንዲሁም የአካል ጉዳተኞች የተጠቃለለ ሕግ አለመፅደቅ እንደሚገኙበት ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ዓለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች ቀን እ.ኤ.አ በ1992 በተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ በተወሰነ ውሳኔ መሰረት መከበር የጀመረ ሲሆን፤ ዕለቱ የአካል ጉዳተኞችን መብትና ደህንነት በሁሉም ዘርፎች ለማስከበር እንዲሁም የፖለቲካ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ እና ግንዛቤን ለማሳደግ ታስቦ ይከበራል።

በአሁኑ ወቅት በዓለም ላይ ከ1 ቢሊዮን የሚበልጡ ሰዎች የአካል ጉዳት እንዳለባቸው የዓለም ጤና ድርጅት ሪፖርት ያመላከተ ሲሆን፤ ከእነዚህ ውስጥ ከ100 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ አካል ጉዳተኞች ሕጻናት መሆናቸውን ገልጿል፡፡

እንዲሁም አካል ጉዳተኛ የሆኑ ሕጻናት ላይ የሚደርሰው ጥቃት የአካል ጉዳት፤ ከሌለባቸው ሕጻናት በአራት እጥፍ እንደሚበልጥም በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በሰሜን ምዕራብ ሶሪያ በተፈጸሙ የአየር ጥቃቶች ቢያንስ 25 ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ

ሕዳር 24/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የሩስያ እና የአሳድ መንግሥት ተዋጊ ጄቶች በሰሜን ሶሪያ በአማፂያኑ ቁጥጥር ሥር በምትገኘው ኢድሊብ ከተማ በፈጸሙት ጥቃት 25 ሰዎች መሞታቸው ተገልጿል፡፡

ከዚህ በፊት የሶሪያው ፕሬዝዳንት በሽር አል አሳድ አማፂ ቡድኑን ለመደምሰስ ሃሳብ እንዳላቸው ሲገልጹ እንደነበር ተነግሯል፡፡

አራት ሚሊዮን የሚጠጉ ሶሪያውያን ተፈናቅለው በተሠሩ ድንኳኖች ውስጥ የሚኖሩባት በቱርክ ድንበር አቅራቢያ በምትገኘው ኢድሊብ የሶሪያ መንግሥት ጥቃት መፈጸሙን በቦታው የነበሩ የነፍስ አድን ሠራተኞች መግለጻቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

በዚህም የአማፂያኑ ጦር አሌፖን ተቆጣጥረው በምዕራብ እና ሰሜን ምዕራብ በኩል ሐማ ወደ ተባለች ከተማ ሲገሰግሱ፤ ሶርያ እና ሩሲያ ከፍተኛ የአየር ላይ ጥቃት መፈጸማቸው ተገልጿል።

የሶሪያ መንግሥት ሚዲያ እና የሶሪያ የሰብአዊ መብቶች ታዛቢዎች የሩስያ እና የሶሪያ ተዋጊ ጄቶች በሰሜናዊ ምዕራብ ሶሪያ በአማፂያን በተያዙ ቦታዎች ላይ ኢላማዎችን እየመቱ መሆናቸውን ዘግቧል፡፡

በሌላ በኩል መቀመጫውን በብሪታንያ ያደረገው የተቃዋሚዎች የሶሪያ የሰብዓዊ መብት ተከታታይ ቡድን፤ ጥቃቱ ሰላማዊ ሰዎች እና ተዋጊዎች ተገድለዋል ብሏል።

የሩሲያ እና የኢራን ባለስልጣናት በበኩላቸው ትናንት ሰኞ በሰጧቸው መግለጫዎች፤ ከፕሬዝዳንት በሽር አል አሳድ ጎን በመቆም ወታደራዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ዕርዳታዎችን ማድረጋቸውን እንደሚቀጥሉ ጠቁመዋል።

የሶሪያ የእርስ በርስ ጦርነት ላለፉት አስርት ዓመታት የቀጠለ ሲሆን፤ የአሳድ መንግሥት እና አጋሩ ሩሲያ በጋራ አማጺያኑን እየተፋለሙ ይገኛሉ፡፡ አሁን ላይ የሶርያ አማጽያን በበሽር አል አሳድ መንግሥት ላይ የከፈቱት ጥቃት ተከትሎ፤ እንደ አዲስ በሀገሪቱ የእርስ በእርስ ጦርነት ስጋት ተፈጥሯል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሶሪያ ልዩ መልዕክተኛ ገይር ፔደርሰን እሁድ ዕለት በሰጡት መግለጫ፤ በግጭቱ ውስጥ ያሉ ሁሉም አካላት በአስቸኳይ ፖለቲካዊ መፍትሄ እንዲፈልጉ ጥሪ አቅርበዋል።

ባለፈው ሳምንት እንደአዲስ ያገረሸውና እስካሁን እየተካሄደ የሚገኘው ይህ ጦርነት፤ በንጹሃን ላይ ከፍተኛ ሞት፣ ጉዳትና መፈናቀልን ማስከተሉም ተገልጿል፡፡

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!

ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

#ADVERTISMENT
#ጊፍትሪልስቴት
ታላቅ የምስራች!

**
ጊፍት ሪል ስቴት ከ10% ቅድመ ክፍያ ጀምሮ በ22 ሳይቶቹ ቅንጡ አፓርትመንቶችን እና የንግድ ሱቆችን ለሽያጭ አቅርቧል፡፡

ይህ ሳይት ለአፓርትመንትና ንግድ ሱቆች የሚውሉ G+25 ሶስት መንታ ህንጻዎች ያሉት ሲሆን የዚህ 6ኛ መንደር መለያዎች፡-
•ከባለአንድ እስከ ባለአራት መኝታ ክፍሎች ያሉት፣
•ለመኖሪያም ሆነ ለንግድ ተመራጭ አካባቢ የሆነ፣
•በአንድ ወለል ሶስት ቤቶች ብቻ ያሉት፣
•በእያንዳንዱ ወለል ስድስት አሳንስር ያለው፣
•አራት ቤዝመንት ያሉት በቂ የመኪና ማቆሚያ የተዘጋጀለት፣
•24 ሰዓት የኤሌክትሪክ፣ ኢንተርኔትና ውሃ አቅርቦት አሉት፣

ጊፍት ሪል ስቴት
ማህበረሰብን እንገነባለን!
ለበለጠ መረጃ፡-
Website: https://www.giftbusinessgroup.com                                                                                             
Twitter: https://twitter.com/GIFTBusinessG                                                     
YouTube: www.youtube.com/channel/UCcqr7cpVv9ski-F7haxXx4w                                                     
Facebook: www.facebook.com/profile.php?id=100090918391017...                                                       
Telegram: /channel/giftbusinessgroup

Short Code: 8055

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

እየተስፋፋ የመጣው የበይነ መረብ ንግድ በምጣኔ ሐብቱ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ እያሳደረ መምጣቱን ተገለጸ

ሕዳር 23/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ እንደቴሌግራም፣ ኢንስታግራምና ፌስቡክ በመሳሰሉት የበይነ መረብ አውታሮች በመጠቀም የሚሸጡ የሚለውጡ ነጋዴዎች እየተበራከቱ መምጣታቸውን ተከትሎ፤ ከግብይቶች መንግሥት ማግኘት ያለበትን ታክስ እያሳጡት መሆኑን የፓሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት አስታውቋል።

የፓሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩቱ በዘርፉ አደረኩት ባለው ጥናት መሰረት፤ የበይነ መረብ አውታር ግብይቶች የመንግሥት ገቢ ላይ ተፅእኖ እየፈጠሩ መምጣታቸውን አረጋግጫለሁ ብሏል።

በኢትዮጵያ እየተስፋፉ የመጣውን የበይነ መረብ ንግድ ለወደፊቱ በአግባቡ ካልተያዘ በምጣኔ ሐብቱ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ መፍጠሩ እንደማይቀር ኢንስቲትዩቱ በጥናቱ ገልጿል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢ-መደኛ መልኩ የሚንቀሳቀሱ የበይነ መረብ ነጋዴዎች ተመዝግበው እንዲሰሩ ጥሪ ቢቀርብም፤ የሚመዘገቡና ግብር የሚከፍሉ ነጋዴዎች በቁጥር ደረጃ አነስተኛ መሆናቸውንም ተናግሯል።

በተለይም ከታክስ ስወራ ጋር ተያይዞ ዘርፉ ተግዳሮት እየሆነ መምጣቱን ከግብር ሰብሳቢ መስርያ ቤትን ጨምሮ ከሚመለከታቸው አካላት የተገኘው መረጃ ጥናቱ የዳሰሰበት መሆኑንና፤ ለዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ እንቅፋት ሊሆን ይችላል የሚል እምነት መኖሩን የኢንስቲትዩቱ የምጣኔ ሐብት ተመራማሪ አቶ ሰለሞን አክሊሉ ለአሐዱ ገልጸዋል።

ኢንስቲትዩቱ የበይነ መረብ ንግድን በተመለከተ ለዘርፉ የሕግ ማእቀፍ እንዲዘጋጅ ውትወታ እያደረገ መሆኑንና የፓሊሲ ግብአቶችንም በማቀናጀት ላይ መሆኑን ተናግረዋል።

ከጎረቤት አገራት ጋር ተወዳዳሪ የበይነ መረብ ሕግ እንዲዘረጋና የንግዱ ስርዓትም በዚሁ ልክ እንዲስፋፋ ያስፈልጋል መባሉን የምጣኔ ሐብት ተመራማሪው አቶ ሰለሞን አክሊሉ ለአሐዱ ገልጸዋል።

ጥናቱ በሌሎች አገራት ያለውን ተሞክሮ እየተዘጋጀ መሆኑን ጠቅሰው፤ በአገር ዓቀፍ ደረጃ እየተዘጋጀ ባለው ፓሊሲ ለማካተት ጥረት እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በኢትዮጵያ የበይነ መረብ ንግድ እየተስፋፋ መምጣቱን ተከትሎ ህግና መመርያ ሊደረግለት መሆኑ እየተነገረ ይገኛል፡፡ ሆኖም ይህ የበይነ መረብ ንግድ በትክክል ግብር የሚከፍሉ የንግድ ማሕበረሰቦች ላይ አሉታዊ ተፅእኖ እያሳደረ መሆኑ ተነግሯል።

ከውጭ አገራት የሚገቡ የምርቶች ጥራት ጉዳይ ያልተረጋገጡ በመሆናቸው በተጠቃሚው ላይ ተፅእኖ እየፈጠሩ መሆናቸውን በፓሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት በጥናቱ አሳስቧል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ያልተረጋገጡ መድኃኒቶች እየተበራከቱ መሆናቸውን ጠቅሶ፤ በሕብረተሰቡ ጤናን ጨምሮ አጠቃላይ ማሕበረ- ኢኮኖሚያዊ ቀውስ እየፈጠሩ እንደሚገኙም አደረኩት ባለው ዳሰሳ አመላክቷል።

ኢ-መደበኛ የበይነ መረብ ነጋዴዎች ወደ መደበኛው የንግድ ስርዓት እንዲመጡና ከሚመለከተው የመንግሥት መስርያቤት ፍቃድ ወስደው እንዲሰሩ የሕግ አካላት የበኩላቸውን ማድረግ ይኖርባቸዋል ሲል ኢንስቲትዩቱ አሳስቧል።

በአማኑኤል ክንደያ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!

ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በታዳጊ ማህሌት ተክላይ ላይ የግድያ ወንጀል የፈፀመው ተከሳሽ የሞት ፍርድ ተፈረደበት

👉2ኛ ተከሳሽ በዕድሜ ልክ እስራት እንዲቀጣ ተወስኗል


ሕዳር 23/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በትግራይ ክልል ዓደዋ ከተማ በታዳጊ ማህሌት ተክላይ ላይ የግድያ ወንጀል የፈፀመው አንደኛ ተከሳሽ ላይ የሞት ፍርድ ውሳኔ ተሰጥቷል።

በትግራይ ክልል የመቀሌ ከተማ መካከለኛ ፍርድ ቤት በታዳጊ ማህሌት ተክላይ ላይ የግድያ ወንጀል የፈፀሙ ተከሳሾች ላይ ዛሬ የፍርድ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡

የ16 ዓመት ታዳጊዋ የዓድዋ ከተማ ነዋሪ ማህሌት ተክላይ መጋቢት 10 ቀን 2016 ወደ ትምህርት ቤት እየሄደች ከነበረበት ታግታ ተወስዳ ሰኔ 12 ቀን 2016 ዓ ተገድላ መገኘቷ ይታወሳል፡፡

አንደኛ ተከሳሽ አንገቷን አንቆ በመያዝ፣ ሁለተኛ ተከሳሽ ደግሞ በባጃጅ አግቶ በመውሰድ ለ30 ደቂቃ ያክል በጫማ ማሰሪያ ገመድ አሰቃይተው እንደገደሏት የመቀሌ ከተማ ዐቃቤ ሕግ ገልጿል።

አንደኛ ተከሳሽ ግድያውን ከፈጸመ በኋላ ወደ ሥራ እንደገባ፤ ገድለው ከቀበሯት ከሦስት ቀናት በኋላም አባቷ ተክላይ ግርማይን 3 ሚሊየን ብር እንደጠየቀው ተገልጿል።

ሁለተኛ ተከሳሽም ከአንደኛ ተከሳሽ እኩል የወንጀሉ ተባባሪ መሆኑን ያስረዳው ዐቃቤ ሕግ፤ ይህ የግድያ ወንጀል ጭካኔ የተሞላበት በመሆኑን ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል።

ዐቃቤ ሕግ ያቀረበውን ማስረጃ የመረመረው ፍርድ ቤቱ ተከሳሾች የፈጸሙት የወንጀል ድርጊት ጭካኔ የተሞላበት መሆኑን በማረጋገጥ የፍርድ ውሳኔ ሰጥቷል።

በዚህም ታዳጊዋ ላይ የግድያ ወንጀል የፈፀመው 1ኛ ተከሳሽ በሞት፣ 2ኛ ተከሳሾች ደግሞ በዕድሜ ልክ እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ አሳልፏል።

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

ከገጠራማ አካባቢዎች ወደ ከተማ የሚደረጉ የሰዎች ሕገ ወጥ ዝውውር እየጨመረ መምጣቱን ተነገረ

ሕዳር 23/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወደተለያዩ ከተሞች ሥራ እናገናኛለን በሚሉ ደላሎች ሴቶችን ጨምሮ ለአቅም ያልደረሱ ሕጻናት ሕገወጥ ዝውውር ቁጥር መጨመሩን የሴቶችና ሕጻናት ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ አደረኩት ባለው ዳሰሳና በከተሞች ባደረገው ምልከታ መሰረት፤ የተዘረጋ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር መኖሩን ገልጿል።

ይህን ሕገወጥ እንቅስቃሴ ለመግታትና በሕጻናት ላይ የሚደርሰው የመብት ጥሰት ለመከላከል ከክልሎች ጋር የሚሰራ ግብረሐይል ማቋቋሙን በሚኒስቴሩ የሕጻናት መብትና ስብእና ቀረፃ ኃላፊ አቶ በለጠ ዳኜ ለአሐዱ ተናግረዋል።

በተለይም ከደቡብ ኢትዮጵያ ወደ መሀል በሕገ-ወጥ መልኩ ሴቶችና ሕጻናት የሚያስኮበልሉ መኖራቸውን ኃላፊው ገልጸዋል።

የሕጻናት መብት ጥበቃ ለማስከበር ከዚህ ቀደም የተፈረመው የሆሳእና ስምምነት በመባል የሚታወቀውን ስምምነት ለማስጀመር እንቅስቃሴዎች መጀመራቸውንም አቶ በለጠ ተናግረዋል።

የሕጻናትና ሴቶች መብት ጥበቃን በተመለከተ ከተለያዩ አለማቀፍ ተቋማት ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ገልጸው፤ ችግሩን ለመግታት የመጀመርያ ስምምነት ከአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር ጋር መደረጉን አስረድተዋል።

አዲስ አበባ ከተማ ዋና መዳረሻ በመሆኗም የከተማ መስተዳድሩ ጋር ውይይት እየተደረገበት መሆኑን ተገልጿል።

በወልደሀዋርያት ዘነበ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

ከጎረቤት ሀገራት እየተስተዋለ ያለዉን የብሄራዊ ደህንነት ስጋት ለመግታት የውስጥ ሰላምን ማስጠበቅ እንደሚገባ ተገለጸ

ሕዳር 25/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በቅርቡ የኤርትራዉ ፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከሀገራቸዉ የቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር በነበራቸዉ ቃለመጠይቅ፤ "ዋናዉ ትኩረታችን ሁሌም ጦርነትን ማስወገድ ነው" ሲሉ ተደምጠዋል።

"በአካባቢው መረረጋጋት እና ትብብር እንዲመጣ እንሰራለን" ያሉም ሲሆን፤ ኤርትራ ኢትዮጵያን ከሚጎዱ ሀገራት ጋር ትሰራለች መባሉን አስተባብለዋል፡፡

ይህንን የፕሬዝዳንቱን ንግግር በሚመለከት አሐዱ ያነጋገራቸው የፖለቲካ ሳይንስ መምህሩ አቶ ጥላሁን ሊበን፤ "ለሁሉም ነገር ኢትዮጵያ ቅድሚያ የውስጥ ችግሯን መፍታት እንዳለባት ብዙዎችን የሚያስማማ ነው" ብለዋል፡፡

"የፕሬዝዳንቱን ሀሳብ እጋራዋለው" የሚሉት የፖለቲካ ተንታኙ አቶ ጥላሁን፤ በተቃራኒው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ንግግርን ተችተውታል፡፡

ተንታኙ "ኢትዮጵያ በሁሉም አቅጣጫ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ውጥረት ውስጥ በገባችበት ሁኔታ፤ 'ሰላም ነን ምንም ችግር የለብንም' ብለው መናገራቸው ተገቢ አይደለም" ሲሉ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

በተመሳሳይ በብልፅግና ፖርቲ አምስተኛ ዓመት ምስረታ ማጠቃለያ ፕሮግራም ላይ የተገኙት የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ "ኢትዮጵያ ያለፉትን አምስት ዓመታት ከጎረቤት ሀገራት ጋር በትብብር እየሰራች ነው" ያሉ ሲሆን፤ "ኢትዮጵያን ሊያፈርስ የሚችል አንዳች ሀይል የለም" ሲሉም አክለዋል።

ይህንን በሚመለከት ሀሳባቸውን ያጋሩን እናት ፓርቲ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር አሰፋ አዳነ በበኩላቸው፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቀጠናው ጉዳይ ላይ የሰጡን ሀሳብ "ተገቢ ያልሆነ ሀሳብ" ሲሉ ገልጸውታል፡፡

በተለይም 'ከማንኛውም የውጭ አካል ጋር ምንም ዓይነት ችግር የለብንም' መባሉን የገለጹት የፓርቲው የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ፤ "መሬት ላይ ያለውን እውነታ ይሄንን አያሳይም" ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስተሩ ይህንን ይበሉ እንጂ ኢትዮጵያ በግልፅ ባይገለፅም ከኤርትራ ጋር እንዲሁም ከሶማሊያ ጋር ይፋዊ እሰጣ ገባ ዉስጥ መግባቷ ግልጽ መሆኑን የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ተንታኞች ለአሐዱ ገልጸዋል፡፡

በአቤል ደጀኔ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የፓለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት 7 የሚሆኑ አጀንዳዎቹን ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስረከበ

ሕዳር 25/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ከተለያዩ ፓርቲዎች የሰበሰበውን ወደ 7 የሚሆኑ ዋና አጀንዳዎችንና 64 የሚሆኑ ንዑስ አጀንዳዎችን ሰብስቦ ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስረክቧል።

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ ኮሚሽኑ ሥራውን ሲጀምር አብሯቸው ለመስራት ከመረጣቸው አምስት አካላቱ አንዱ ፓለቲካ ፓርቲዎች መሆኑን ገልጸዋል።

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር የጋራ ምክር ቤቱ ሌሎች ከመጀመሪያው ጀምሮ የኮሚሽኑን ሥራ ያልተቀበሉትን ወደ ኮሚሽኑ እንዲመጡ ጠይቀዋል።

የጋራ ምክር ቤቱን ወክለው የተገኙት የፓለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ ሰለሞን አየለ፤ ከኮሚሽኑ ጋር በትብብር ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል።

የጋራ ምክር ቤቱ ከፓርቲዎች የሰበሰበውን ወደ 7 የሚሆኑ አጀንዳዎችን ያሰረከበ ሲሆን፤ በተለይም በሀገረ መንግሥት ምሰረታ፣ በታሪክ ትርክት፣ የውጭ ግንኙነቶችን ጨምሮ 64 ንዑስ አጀንዳዎችን ለኮሚሽኑ አስረክቧል።

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከተለያዩ አካላት አጀንዳዎች የመሰብሰብ ሥራውን በመቀጠል በ9 ክልሎችና 2 ከተማ አስተዳደሮችን ሥራዎችን ማጠናቀቁም ተገልጿል።

በአቤል ደጀኔ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ ላይ ሲፈጸም ለነበረዉ ሕገ ወጥ ተግባር መፍትሄ መሰጠቱ ተገለጸ

ሕዳር 25/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በደቡብ ኢትዮጵያ በጋሞ ዞን የሚገኘው የነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ አዋሳኝ አካባቢ የሚኖሩ ማሕበረሰቦች ወደ ፓርኩ ዘልቀው በመግባታቸው እና በፓርኩ ውስጥ የሚገኘው የዱር እንስሳት አደን በመደረጉ ፓርኩ ስጋት ላይ መሆኑ በተደጋጋሚ ሲገለጽ ቆይቷል፡፡

አሐዱም ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ "የነበረውን ችግር መፍትሄ መስጠት አልተቻለም ወይ?" ሲል የጋሞ ዞን መንግሥት ኮሚኒኬሽን ቢሮን ጠይቋል።

የቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ገዛኸኝ ጩባ በሰጡት ምላሽ፤ በፓርኩ ድምበር ጥሰው ከገቡ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር በመወያየትና ሌሎች ቦታዎችን በማመቻቸት እንዲወጡ ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ጋር በጋራ መሠራቱን ገልጸዋል።

አክለውም በባሕላዊ መንገድ የዱር እንስሳትን በሚያድኑ ግለሰቦች ላይ አስተማሪ እርምጃዎችን በመውሰድ የታየውን ችግር መቅረፍ መቻሉን አስረድተዋል።

ሆኖም ግን አሁንም የተወሰኑ ችግሮች እንዳሉ አብራርተው፤ "ፓርኩ በፀጥታ ምክንያት ዝግ ነው ተብሎ በማሕበራዊ ሚዲያዎች የሚሰራጨው መረጃም ሀሰተኛ ነው" ሲሉ የቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ገዛኸኝ ጩባ ለአሐዱ ተናግረዋል።

ኃላፊው አክለውም አካባቢው የቱሪስት መዳረሻ በመሆኑ ሊጎበኙ የሚችሉ ቦታዎችን የማስፋፋት ሥራ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

ወደ ፓርኩ በሚኬድበት ወቅት አልፎ አልፎ የሚከሰት የፀጥታ ችግር መኖሩን ያልደበቁት አቶ ገዛኸኝ፤ "አካባቢውን ሙሉ በሙሉ ሰላማዊ ለማድረግ እየተሰራ ነው" ብለዋል፡፡

በነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ ከሚገኘው 52 ነጥብ 2 ሜዳማ የግጦሽ መሬት ውስጥ 51 በመቶውን ማለትም ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በፓርኩ ውስጥ ነዋሪ በሆኑ የምዕራብ ጉጂ ገላና ወረዳ ኤርጌንሳ ቀበሌ አርብቶ አደሮች፤ በመቶ ሺሕ በሚቆጠሩ ከብቶቻቸው በመጋጡ በፓርኩ ያሉ የዱር እንሰሳት ህልውና አደጋ ውስጥ መውደቁ ሲገለጽ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

በወልደሐዋርያት ዘነበ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

#ADVERTISMENT
#AmharaBank
የአማራ ባንክ አ/ማ የባለአክሲዮኖች 3ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ማክሰኞ ታህሳስ 01 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ በሚሊኒየም አዳራሽ ስለሚካሄድ ባለአክሲዮኖች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጉባዔው እንድትገኙ ጥሪ እናስተላልፋለን፡፡

የጉባዔው አጀንዳዎችን እና ተጨማሪ መረጃዎችን ጥቅምት 06 ቀን 2017 ዓ.ም በወጡት አዲስ ዘመን እና ሪፖርተር አማርኛ እትም ጋዜጦች ላይ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ለበለጠ መረጃ ነፃ የጥሪ ማዕከል 690 ወይም
የባንኩን ድረ ገጽ www.amharabank.com.et ይጎብኙ፡፡

አማራ ባንክ
ከባንክ ባሻገር!

የአማራ ባንክ ትክክለኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾች
Website: www.amharabank.com
Facebook: www.Facebook.com/amharabanksc1
Telegram: /channel/Amhara_Banksc
Instagram: https://instagram.com/amhara_bank
Twitter: https://twitter.com/Amharabanksc
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/amharabank/
YouTube: https://youtube.com/channel/UC73x9uuGYV0Uxw0EkpVZN8g
TikTok: amharabanks.c" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@amharabanks.c

#አማራባንክ #AmharaBank

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

#አሐዱ_ትንታኔ

ትንታኔውን ለመከታተል ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👇
https://youtu.be/yx3unkSA7zw?si=YVH8pSZb5SloK9j2

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በመዲናዋ በርበሬ ከባዕድ ነገር ጋር ተቀላቅሎ የሚመረትበት መጋዘን ላይ እርምጃ መወሰዱ ተገለጸ

ሕዳር 24/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በአዲስ አበባ ከተማ ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የሚገኝ አንድ በርበሬ ከባዕድ ነገር ጋር ተቀላቅሎ የሚመረትበት መጋዘን ላይ እርምጃ መወሰዱ ተገልጿል።

በክፍለ ከተማው ወረዳ 07 ሚካኤል ቤተክርስቲያን ጀርባ በአንድ መጋዘን በሕገወጥ መልኩ በርበሬን ከባዕድ ነገር ጋር በመቀላቀል ምርት ሲመረት በቁጥጥር ሥር መዋሉን ነው፤ የክፍለ ከተማው የሕገ ወጥ ንግድ ቁጥጥር ግብረ ሃይል ያስታወቀው።

የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የንግድ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አሸናፊ ፍቅሬ፤ በኅብረተሰቡ ጤናን ደህንነት በሚጎዳ መልኩ በርበሬን ከባዕድ ነገር ጋር በመቀላቀል ለገበያ ለማዋል ሲመረት በቁጥጥር ሥሩ መዋሉን የገለጹ ሲሆን፤ ወደ ገበያ ቢገባ በኅብረተሰቡ ላይ ከፍተኛ የጤና ጉዳትም ሊያስከትል እንደሚችል ተናግረዋል።

አክለውም ጽ/ቤታቸው በእንደዚህ አይነት ሕገወጥ ተግባር ላይ ተከታታይነት ያለው እርምጃ እየወሰደ እንደሚገኝና በሕገወጦች ላይ የሚወሰዱ አስተዳደራዊና ሕጋዊ እርምጃዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል፡፡

ኅብረተሰቡም እንደዚህ አይነት ሕገወጥ ተግባራት ሲመለከት፤ ለሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበዋል።

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ:www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በኢትዮጵያ በየዓመቱ ከ3 ሺሕ በላይ ሴቶች በማህፀን በር ካንሰር በሽታ ሕይወታቸው እንደሚያልፍ ተገለጸ

ሕዳር 24/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ በየዓመቱ 5 ሺሕ ሴቶች በማህፀን በር ካንሰር በሽታ የሚያዙ ሲሆን፤ 3 ሺሕ የሚሆኑት ደግሞ ሕወታቸው እንደሚያልፍ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ የዘርፉ አስተባባሪ አቶ ወንድወሰን በርሄ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

"እድሜቸው ከ30 እስከ 40 የሆኑት በኤች አይቪ ቫይረስ የተያዙ እና በወሲብ ንግድ ላይ የተሰማሩ ሴቶች የበለጠ ተጋላጭ ናቸው" ያሉት አቶ ወንደሰን፤ ጥንቃቄ ካልተደረገ ከ 18 ዓመት በታች ያሉትንም እንደሚያጠቃ አንስተዋል፡፡

አክለውም "የማህፀን በር ካንሰር ምንም አይነት ምልክት ሳያሳይ ከ10 እስከ 20 ዓመት ይቆያል" ሲሉ ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በ1 ሺሕ 453 የጤና ተቋማት የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር ቅድመ ልየታ እየተሰጠ እንደሚገኝም ተናግረዋል።

የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር በሽታ "ሂውማን ፓፒሎማ ቫይረስ" በሚባል ረቂቅ ተዋህስ የሚከሰት በሽታ መሆኑንም አመላክተዋል፡፡

በአለም አቀፍ ደረጃ በበሽታው የሚያዙ ሰዎች 5 መቶ 30 ሺሕ ሲሆኑ፤ ከ2 መቶ 70 ሺሕ በላይ የሚሆኑ ሴቶች እንደሚሞቱ ተገልጿል፡፡

በሽታው በሴቶች ላይ ከሚከሰቱ የካንሰር ዓይነቶች ከጡት ካንስር ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ በሽታ መሆኑም ተነግሯል።

በህይወት ጌትነት
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ:www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የራስ ደስታ ዳምጠው የወርቅ ሜዳሊያ ለጨረታ መቅረቡን ተከትሎ ቤተሰቦቻቸው ሜዳልያው እንዲመለስ ጠየቁ

ሕዳር 24/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በጣልያን ዳግም ወረራ ወቅት የተገደሉት የራስ ደስታ ዳምጠው የኮከብ ቅርጽ ያለው የወርቅ ሜዳሊያ ለጨረታ መቅረቡን ተከትሎ፤ ቅርሱን ለማስመለስ እንደሚፈልጉ ቤተሰቦቻቸው ገልጸዋል።

በጎርጎሮሳውያኑ 1937 ራስ ደስታ ዳምጠው በተያዙበት ወቅት በስፍራው በነበረ የጣልያን ወታደር ተወስዷል የተባለው ይህ የወርቅ ሜዳልያ፤ 'ላይቭኦክሽነርስ' በተሰኘ የድረ-ገጽ ላይ ለጨረታ ከቀረቡ ቅርሶች ዝርዝር ውስጥ መካተቱ ተነግሯል፡፡

በዚህም የኮከብ ቅርጽ ያለው የወርቅ ሜዳሊያ ከ60 ሺሕ እና 90 ሺሕ ዩሮ መካከል ግምታዊ ዋጋ ተሰጥቶታል።

በአሜሪካን ሀገር የሚኖሩት እና የራስ ደስታ ዳምጠው የልጅ ልጅ የሆኑት አማሃ ካሳ “ከአያታችን አስከሬን ላይ የተወሰደ ሜዳሊያ ነው" ያሉ ሲሆን፤ በጨረታ ካታሎጉ ላይ ያለውን ጽሑፍ ማንበባችን "ደማችን እንዲፈላ አድርጓል" ማለታቸውን ዘ አርት ጋዜጣ ስለ ቅርሱ በሰራው ዘገባ አመላክቷል።

የራስ ደስታ የልጅ ልጆቹ ሜዳልያው ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ሙዝየም እንደሰሚጥ ተስፋ እንደሚያደርጉም መናገራቸው ተመላክቷል።

ትኩረቱን በተሰረቁ ቅርሶች እና ልዩ ልዩ የጥበብ ሥራዎች ላይ አድርጎ በሚንቀሳቀሰው 'አርት ሪከቨሪ ኢንተርናሽናል' በበኩሉ ሜዳሊያውን ለኢትዮጵያ ሙዚየም ተላልፎ እንዲሰጥ ፍላጎት ቢኖረውም፤ ነገር ግን የጨረታው ቤት እቃውን ለማንሳት ፈቃደኛ አለመሆኑ ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ አበባው አያሌው ከጨረታው በፊት ለጨረታ ቤቱ በፃፉት ደብዳቤ ሽያጩ እንዲሰረዝ እና ይህ የተዘረፈ ጠቃሚ ቅርስ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለስ መጠየቃቸውም ተነግሯል፡፡

ራስ ደስታ ዳምጠው በጣልያን ዳግም ወረራ ወቅት በአርበኝነት ከሚጠቀሱት መካከል አንዱ ሲሆኑ፤ በፋሽስት ወረራ ወቅት የሲዳማን ጦር በመምራት ታግለውና አታግለው በጀግንነት አልፈዋል።

እኚህ ጀግና የሀገር ባለውለታ በሥማቸው በአዲስ አበባ ሆስፒታል እንደተሰየመላቸውም ይታወቃል።

በተመሳሳይ በተያዘው ዓመት ጥቅምት ወር ላይ እ.ኤ.አ 1868 በመቅደላ ጦርነት ወቅት የተወሰደው የአጼ ቴዎድሮስ ያጌጠ ጥንታዊ ጋሻ፤ ከብሪታኒያው አንደርሰን እና ጋርላንድ የጨረታ ቤት ጨረታው ተሰርዞ፤ ከ156 ዓመታት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ መመለሱ ይታወሳል።

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የፕላስቲክ ምርቶችን የሚጠቀሙ ኢንዱስትሪዎች አጠቃቀማቸውን እንዲያስተካክሉ ማሳሰቢያ መሰጠቱ ተገለጸ

ሕዳር 24/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙና የፕላስቲክ ምርቶችን በመጠቀም ምርት የሚያሽጉ፣ መሸጫ መለወጫ የሚደደርጉ ኢንዱስትሪዎች፤ ማስጠንቀቂያ እንደደረሳቸው የከተማ አስተዳደሩ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ለአሐዱ ተናግሯል።

ባለስልጣኑ ኢትዮጵያ በአዘርባጃን በተካሄደው የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ላይ ተፈፃሚ ለማድረግ ቃል ከገባችባቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ የፕላስቲክ ብክለት መከላከል መሆኑን ጠቅሶ፤ የአዲስ አበባ ከተማ ተግባራዊ እንዲያደርግ መጠየቁን አስታውቋል። 

ለዚህም ኢንዱስትሪዎች ከሚያመነጩት በተጨማሪም በህብረተሰቡ ያለውን የፕላስቲክ አጠቃቀም መስተካከል ካልተቻለ፤ ከተማዋ ካላት የሕዝብ ብዛት አንፃር ጉዳቱ አደገኛ የሚባል መሆኑን የባለስልጣኑ ከፍተኛ ተመራማሪ አቶ ሙላቱ ወሰን ለአሐዱ ተናግረዋል።

በአዲስ አበባ ያሉ አምራች ኢንዱስትሪዎች ለአካባቢ ብክለት የሚወስዱት ሚና ከፍተኛ መሆኑን የገለጹት ተመራማሪው፤ ተደጋጋሚ ማሳሰቢያ ሲሰጣቸው መቆየቱን አንስተዋል።

የከተማ መስተዳድሩ የአለም የጤና ድርጅትን ጨምሮ  ሌሎች ረጂ ተቋማት ጋር በተደረሰው ስምምነት መሰረትም፤ ማስተካከል እንደሚያስፈልግ መወሰኑን ነው የገለጹት።

ከዚህ በመነሳትም የአየር ንብረት ተርቋሪዎች የተሰጠውን ምክረ ሐሳብ በመጥቀስ፤ የቅድሚያ ቅድሚያ መሰራት ያለባቸው ጉዳዮች መሆናቸውን አፅንኦት ሰጥተውበታል።

ኢትዮጵያ ኮፕ 29 ጨምሮ የተለያዩ አለም ዓቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ የተመለከቱ ጉባኤዎች ላይ ስትሳተፍ መቆየቷን ይታወቃል።

ባለፈው ጊዜም በተሳተፈችበት ጉባኤ የፕላስቲክ ብክለት ለማስወገድ ቃል ከተገቡ ጉዳዮች መካከል እንደሚገኙበት ከባለስልጣኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በአማኑኤል ክንደያ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የብልፅግና ፓርቲ የአምስት ዓመት ጉዞ በተገለጸው ልክ የስኬት ዓመታት አልነበሩም ሲሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ገለጹ

ሕዳር 24/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የብልፅግና ፓርቲ አመስተኛ ዓመት የምስረታ በዓል ላይ የፓርቲውን ጉዞ አስመልክቶ በተገለጸው ልክ፤ ያለፋት አምስት ዓመታት የስኬት ዓመታት አልነበሩም ሲሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሀሳባቸውን ለአሐዱ ገልጸዋል፡፡

ፓርቲዎቹ ያለፉትን አምስት ዓመታት አስመልክቶ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቀረበው ንግግር ዙሪያ ሀሳባቸውን ለአሐዱ የሰጡ ሲሆን፤ በተለያዩ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይም ትችታቸውን ሰንዝረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒሰትሩ በፓርቲው ምስረታ አምስተኛ ዓመት የማጠቃለያ ፕሮግራም ላይ ባደረጉት ንግግር፤ "ባለፉት አምስት ዓመታት ብልፅግና ያሳካቸው ድሎች ታፈሰው የማያልቁ ናቸው" ሲሉ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡

ያለፉትን አምስት ዓመታት የኢኮኖሚ ጉዞ በሚመለከት  ሀሳባቸውን ለአሐዱ ያጋሩት የእናት ፓርቲው የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር አስፋ አዳነ፤ እናት ፓርቲ የኢኮኖሚ ዕድገቱን ከመንግሥት በተቃራኒ መልኩ እንደሚመለከተው ተናግረዋል፡፡

"የመንግሥት ተቀዳሚ ሥራ መሆን ያለበት የዜጋው በሰላም ወጥቶ መግባት ነው" የሚሉት ዶክተር አሰፋ፤ "ዜጋው ግብር የሚከፍለው መሰረተ ልማት እንዲሟላለትና በሰላም ወጥቶ ለመግባት ነው። ይህ ባልሆነበት ሁኔታ የኢኮኖሚ ዕደገት አለ ብሎ ማሰብ ተገቢ አይደለም" ብለዋል፡፡

"ኢኮኖሚው ከሚገባው በላይ የመውደቅ አደጋ የተጋረጠበት ሆኖ፣ የዩኒቨርሲቲ መምህራን ተርበው መመገብ የተሳናቸው እና ሌሎች በርካታ የሚነሱ ጉዳዮች ባሉበት በዚህ ጊዜ ስለ ኢኮኖሚ ዕደገት መነጋገር ተገቢ አይደለም" ሲሉም ተናግረዋል፡፡

"በተደጋጋሚ ባለፉት አምስት ዓመታት ዕድገት መመዝገቡ በተለያየ አጋጣሚ ሲገልጽ ቆይቷል" ያሉም ሲሆን፤ ነገር ግን ለህብረተሰቡ እዚህ ግባ የሚባል ነገር ያልታየበት እንደነበር ገልጸዋል፡፡

መንግሥት የህብረተሰቡን ቅድሚያ የሚሰጠውን ጉዳይ ችላ በማለት የሚፈልገውን ጉዳይ ብቻ እየሠራ እንደሆነም፤ ዶክተር አሰፋ ከአሐዱ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል፡፡

በብፅግና ፓርቲ ምስረታ ማጠቃለያ ፕሮግራም ላይ በበርካታ ጉዳዮች ላይ ሰፋ ያለ ንግግር ያደረጉት የፓርቲው ፕሬዝዳንት ዐቢይ አሕመድ በተለይም በፖለቲካ ምህዳሩ ዙሪያ እና ከጎረቤት ሀገራት ጋር በተያያዘ ንግግር ያደረጉ ሲሆን፤ "ያለፉትን አምስት ዓመታት ከቃላት በዘለለ ይህ ነው የሚባል ግጭት ውስጥ አልገባንም" ብለዋል፡፡

ይህንን በሚመለከት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር ሙላት ገመቹ ሲገልጽ፤ "ከሶማሊያ ጋር ያለው ግንኙነት በሚታወቅበት ሁኔታ ላይ ሆነን እንዲሁም ከተለያዩ የሀገሪቱ ድንበሮች ጋር በተያያዘ ውዝግብ ውስጥ በሆንበት ጊዜ ላይ 'ምንም ግጭት የለም' ብሎ መግለጽ ተገቢ አይደለም" ይላሉ፡፡

ዓለም አቀፍ ሕግ በሚፈቅደው መሰረት ድንበር መከበር አለበት የሚሉትና ሀሳባቸውን ለአሐዱ የሰጡት የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮቹ፤ "በድንበር አካባቢ የሚገኙ የሀገሪቱ ይዞታዎች በወራሪዎች እጅ ባለበት ሁኔታ ሰላማዊ ግንኙነት ውስጥ ነው ያለነው የሚል ሀሳብ ተቀባይነት የለውም" ሲሉ ገልጸዋል፡፡

"ከሁሉም በላይ ግን ብልፅግና ፓርቲ ባለፉት አምስት ዓመታት 'አሳክቼዋለው' ካለው የውጭ ጉዳይ አስቀድሞ በውስጥ ያሉ ችግሮችን ሊፈታ ይገባል" ሲሉም አክለዋል፡፡

በፓርቲው አምስተኛ ዓመት ምስረታ ማጠቃላይ ፕሮግራም ላይ ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ "ብልፅግና ፓርቲ በቀጣይ አምስት ዓመታት ከአሁኑ በላቀ አዳዲስ ድሎችን ያስመዘግባል" ሲሉ መግለጻቸው የሚታወስ ነው፡፡

በአቤል ደጀኔ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

10 ኢንዱስትሪ ፓርኮች ወደ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን አደጉ

ሕዳር 24/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከሚያስተዳድራቸው 13 ኢንዱስትሪ ፓርኮችና የድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠና መካከል፤ 10ሩ ወደ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ማደጋቸውን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ቦርድ ፓርኮቹ ያሉበትን ደረጃ በመገምገም ወደ ልዩ ኢኮኖሚ ዞንነት ለማደግ 10ሩ አስፈላጊውን መስፈርት በማሟላታቸው፤ ወደ ልዩ ኢኮኖሚ ዞንነት እንዲያድጉ መወሰኑን ለኮርፖሬሽኑ በላከው ይፋዊ ደብዳቤ ገልጿል።

ኢንዱስትሪ ፓርኮቹ ወደ ልዩ ኢኮኖሚ ዞንነት ማደጋቸው የግል ዘርፉ በኢኮኖሚ፣ በንግድ፣ በአገልግሎት እና ሌሎች ልማታዊ ኢንቨስትመንቶች ላይ እንዲሳተፉ ለማበረታታትና የሀገሪቱን የውጪ ባለሀብት ቀጥታ ኢንቨስትመንት የመሳብ እንቅስቃሴ ለማጠናከር ጠቀሜታ እንዳለው ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር፣ ንግድን፣ ዕቃን ወደ ውጭ የመላክ አፈፃፀም እና ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ዕቃዎችን በሀገር ውስጥ ምርቶች የመተካት አቅም ለማሳደግ፣ በዓለም ዓቀፍ የንግድ ሰንሰለት የሚኖር ቁርኝትን ለማስፋፋት እና ዘላቂ ዕድገት ለማምጣት የሚኖራቸው ሚና ከፍተኛ ይሆናል ተብሎም ታምኖበታል፡፡

በዚህም መሰረት ወደ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ያደጉት አዳማ፣ ባህርዳር፣ ቦሌ ለሚ፣ ደብረ ብረሃን፣ ሀዋሳ፣ ጅማ፣ ቂሊንጦ፣ ኮምቦልቻ፣ መቀሌ እና ሰመራ ኢንዱስትሪ ፓርኮች መሆናቸውን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!

ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

መልካም ቀን!
አሐዱ ሬድዮ 94.3  የኢትዮጵያውያን ድምፅ!

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

ምርጫ ቦርድ ለምክር ቤቱ ዕዉቅና ከመስጠት ውጪ አማራጭ የለዉም ሲል የፖለቲካ ፖርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ገለጸ

ሕዳር 23/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለምክር ቤቱ ዕዉቅና ከመስጠት ዉጪ አማራጭ የለዉም ሲል የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፖርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ገልጿል፡፡

የፖለቲካ ፖርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በምርጫ ቦርድ የተመዘገበ ተቋም ለማድረግ የሕግ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴዉ በርካታ ጥረቶች ሲያደርግ መቆየቱ ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፖርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አዲሱ ሊቀመንበር የሆኑት የከፋ ሕዝቦች አረንጓዴ ፖርቲ ፕሬዝዳንት ሰለሞን አየለ፤ ዕዉቅና ያለዉ ተቋም እንዲሆን ከፍተኛ ጥረት መደረጉን ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

ሊቀመንበሩ "ሕግ የለም ማለት አይቻልም" ያሉ ሲሆን፤ የተለያዩ ማዕቀፎችና መተዳደሪያ ደንቡ ለጋራ ምክር ቤቱ ቀርቦ መጽደቁን ገልጸዋል።

"ብሔራዊ ምርጫ ቦርድም ለጋራ ምክር ቤቱ እዉቅና ከመስጠት ዉጪ አማራጭ የለውም" ሲሉ የምክር ቤቱ ሊቀመንበር ተናግረዋል።

አክለውም፤ አዲሱ አመራርም ሆነ ሥራ አስፈፃሚ ከቦርዱ ጋር በመሆን ያሉበትን ችግሮች ለመፍታት በጋራ እንደሚሰራ አስረድተዋል፡፡

ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፖርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ምርጫ ቦርድ የቤት ኪራይ ተከራይቶ እንደሚያስተዳድረዉ ቢገልፅም "እዉቅና ነፍጎኛል" ሲል ግን ተደምጧል።

ይህንንም በተደጋጋሚ በደብዳቤ ቢያሳውቅም ምላሽ ማግኘት አለመቻሉንም መግለፁ ይታወሳል። ይህንን በሚመለከት ከዚህ ቀደም ጥያቄ አንስተንላቸዉ የነበሩት የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ ዉብሸት አየለ፤ "ቦርዱ እዉቅና መስጠት ኃላፊነቱ አደለም" ብለዋል፡፡

"ምክር ቤቱ አሁን ባለበት መንገድ የሚቀጥል እንጂ፤ ፖርቲዎችን የማስተዳደር ኃላፊነት የተሰጠዉ ለምርጫ ቦርድ ብቻ ነው" ሲሉም ምክትል ሰብሳቢዉ ተናግረዋል።

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ "እውቅና የመስጠት ኃላፊነት የለኝም" እያለ ቢገልጽም፤ የጋራ ምክር ቤቱ ሊቀመንበር "አማራጭ የለውም" ሲሉ ለአሐዱ ተናግረዋል።

በአቤል ደጀኔ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!

ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

#አሐዱ_አንቀፅ

"ላይደማመጡ የተማማሉ የሃገራችን ጎምቱ ልሂቃን"

ሙሉ ጥንቅሩን ለመከታተል ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👇
https://youtu.be/Be3y73UCENA?si=jYIO1v4FUHkyNKIZ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

አቶ ብናልፍ አንዱዓለም ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው ተሾሙ

ሕዳር 23/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የቀድሞው የሰላም ሚኒስትር የነበሩት አቶ ብናልፍ አንዱዓለም ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው ተሹመዋል።

የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት አቶ ብናልፍ አንዱዓለም ከሕዳር 23 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው መሾማቸውን አስታውቋል ሲል የኢዜአ ዘገባ አመላክቷል።

ከቀናት በፊት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ መሐመድ እድሪስ የሰላም ሚኒስትር ሆነው መሾማቸው ይታወሳል።

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…
Subscribe to a channel