የኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ የአክሲዮን ሽያጭ 100 ሚሊዮን ብር መሆኑን አስታወቀ
ጥቅምት 6/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ግዙፉና መንግሥታዊዉ የቴሌኮም አቅራቢያ ድርጅት ኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ አክስዮን ሽያጭ 100 ሚሊዮን ብር መሆኑን አስታውቋል፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም ለኢትዮጵያውያን ክፍት የተደረገው የአክሲዮን ሽያጭ ዝቅተኛው የሼር ወይም የአክሲዮን መጠን 33 እንዲሆን የአንዱ አክሲዮን ዋጋም 300 ብር እንዲሆን መወሰኑን የገለጸ ሲሆን፤ 100 ሚሊዮን መደበኛ አክሲዮኖች ለሽያጭ መቅረባቸውን ገልጿል፡፡
ከፍተኛው የክሲዮን ወይንም የሼር መጠን 3 ሺሕ 333 እንደሆነና የአንዱ አክሲዮን ዋጋም 300 ብር እንደሆነ የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ተናግረዋል።
የአክሲዮን ሽያጩ ከዛሬ ጥቅምት 06 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እሰከ ታህሳስ 25 ቀን 2017 ዓ.ም የሚከናወን ሲሆን፤ በአክስዮን ሽያጩ ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው ዜጎች ለሽያጩ ከማመልከታቸው በፊት ሊያሟሏቸው የሚገቡ ቅደመ-ሁኔታዎች መካከል፤ ኢትዮጵያዊ ዜጋ መሆን እንደግዴታ ተቀምጧል።
ኢትዮ ቴሌኮም በኢትዮጵያ 130 ዓመታት ገደማ በመንግሥት በብቸኝነት ተይዞ መቆየቱ ይታወቃል።
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
በግል ጤና ተቋማት ለአንድ ጊዜ የኩላሊት እጥበት ከአንድ ሺሕ እስከ 2 ሺሕ ብር ድረስ ጭማሪ እየተጠየቀ ነው ተባለ
ጥቅምት 6/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በግል የጤና ተቋማት ላይ ለአንድ ጊዜ የኩላሊት እጥበት ከ3 ሺሕ እስከ 4 ሺሕ ብር ድረስ እየተጠየቀ መሆኑን የኩላሊት ሕመምተኖች እጥበት በጎ አድራጎት ድርጅት አስታውቋል፡፡
ከዚህ ቀደም ለአንድ ጊዜ የሚሆን የኩላሊት እጥበት 2 ሺሕ ብር የነበረ ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት ከ3 ሺሕ ብር እስከ 4 ሺሕ ብር ድረስ እየተጠየቀ እንደሚገኝ የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን አሰፋ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
ወደ 4 ሺሕ የሚጠጉ ዜጎች በግል ጤና ተቋማት የኩላሊት እጥበት እያከናወኑ እንደሚገኙ አቶ ሰለሞን ገልጸዋል፡፡
የኩላሊት እጥበት በሳምንት ሦስት ቀን ሊደረግ የሚገባ ቢሆንም፤ ለአገልግሎቱ በሚወጣ ወጪ ምክንያት በሳምንት አንድ ቀን እያከናወኑ የሚገኙ ስለመኖራቸውም አንስተዋል፡፡
ለኩላሊት እጥበት የሚጠየቀው ገንዘብ እየጨመረ በመሆኑ፤ እጥበቱን የሚያደርጉ አንዳንድ ዜጎች አገልግሎቱን ለማቆም እየተገደዱ መሆናቸው ተነግሯል፡፡
በግብዓት ጭማሪ ምክንያት በአገልግሎቱ ላይ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ የግል የጤና ተቋማት መኖራቸው የገለጹት ዋና ሥራ አስኪያጁ፤ በተጨማሪም ሰው ሰራሽ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ ተቋማት ስለመኖራቸውም አንስተዋል፡፡
በመሆኑም ይህ ሁኔታ ቁጥጥር እንዲደረግበት ለሚመለከተው አካል ማሳወቃቸውን የገለጹት የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የክትትል ክትትል ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
በእሌኒ ግዛቸው
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ከአዲስ አበባ ወደ ድሬዳዋ በመጓዝ ላይ የነበረ አውሮፕላን ለማረፍ በዝግጅት ላይ ሳለ በውስጡ ጢስ መታየቱ ተገለጸ
ጥቅምት 6/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በዛሬው ዕለት ከአዲስ አበባ ወደ ድሬዳዋ በመጓዝ ላይ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር ET248 ድሬዳዋ አየር ማረፍያ ለማረፍ በዝግጅት ላይ ሳለ በአውሮፕላኑ ውስጥ ጢስ መታየጡን አየር መንገዱ ገልጿል።
አውሮፕላኑ በድሬዳዋ አየር ማረፍያ በሰላም በማረፍ መንገደኞችን በተለመደው መልኩ ከአውሮፕላኑ ማውረድ መቻሉን የገለጸው የኢትዮጵያ አየር መንገድ፤ ጢሱ የተነሳበትን ምክንያት በማጣራት ላይ እንደሚገኝም አስታውቋል።
አየር መንገዱ ለተፈጠረው ክስተት መንገደኞቹን ይቅርታ ጠይቋል።
ከወራት በፊት ከሀዋሳ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ የነበረ አውሮፕላን ውስጥ ጭስ መታየቱን ነገር ግን አውሮፕላኑ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፍያ በተመደበለት የመንገደኞች ማስተናገጃ በር ያለ ምንም እክል መቆሙ መንገዶኞቹም ከአውሮፕላን ላይ ደህንነታቸው እንደተጠበቀ መወርዳቸውን መገለጹ ይታወሳል፡፡
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
የሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች የግጭት ቀጠናዎችን ለቀው መውጣታቸው አግባብነት የሌለው ውሳኔ ነው ተባለ
ጥቅምት 6/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ግጭት ባለባቸው የተለያዩ አካባቢዎች ተሰማርተው የዕለት ደራሽ እና የሰብአዊ ድጋፍ በማከናወን ላይ የነበሩ የሲቪል ማኅበራት ድጋፋቸውን አቋርጠው የግጭት ቀጠናዎችን ለቀው መውጣታቸው አግባብነት የሌለው ውሳኔ እንደሆነ፤ በኢትዮጵያ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ምክርቤት አስታወቀ፡፡
ድርጅቶቹ በግጭት ቀጠናዎቹ እንደልብ ተንቀሳቅሰው እንዳይሰሩ አስቸጋሪ ጉዳዮች ቢገጥሟቸውም ዓለም አቀፉን የሰብአዊ እርዳታ ሕግ ማክበር ይጠበቅባቸው ነበር ተብሏል፡፡
̎የሲቪክ ማኅበራት ድርጅቶች በግጭት ለተጎዱ እና ለተፈናቀሉ ዜጎች እርዳታ ለማቅረብ ፈታኝ ቢሆንባቸውና አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ቢገቡም እንኳን፤ የጸጥታ ችግር አለ በሚል ምክንያት አካባቢውን ለቀው መውጣታቸው አሳማኝ አይደለም̎ ያሉት የምክር ቤቱ የኘሮግራም ልማት አማካሪ እና የሰላም ግንባታ ጉዳዮች ባለሙያ ዶክተር ቃለወንጌል ምናለ ናቸው፡፡
በአጠቃላይ የዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችንና ሕግጋትን በመከተል ሰብአዊ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ወገኖች ድጋፍ እንዳይቋረጥባቸው መጣር እንደሚገባ የገለጹት ባለሙያው፤ ̎የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን ከሚመለከተው አካል ጋር መፍታት፣ የግጭቱ ተሳታፊዎች ወደ ሰላም እንዲመጡ መጣር ይጠበቅባቸው ነበር̎ ሲሉ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
በኢትዮጵያ ያሉ ችግሮችን ለመፍታትና ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች የሰብአዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች ተደራሽ ለማድረግ የተጠና ስልታዊ መንገድ መጠቀም እንደሚገባ ባለሙያው አንስተዋል፡፡
በአለምነው ሹሙ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
#የአሐዱ_ዕለታዊ_ዜናዎች!
ዜናዎቹን ለመከታተል ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👇https://youtu.be/z6x7EL-6xws?si=bvLtB5w0t-eNXOPl
ዩኤስኤድ በኢትዮጵያ በ5 ቢሊየን ብር የሚተገበር የአደጋ ሥጋት አመራር ፕሮግራም ይፋ አደረገ
ጥቅምት 5/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የአሜሪካ አለም አቀፍ የተራድኦ ድርጅት (ዩኤስኤድ) በኢትዮጵያ 9 ክልሎች የሚተገበርና 5 ቢሊየን ብር ድጋፍ የተደረገበትን የአምስት ዓመት የአደጋ ሥጋት አመራር ፕሮግራም በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጓል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አርባምንጭ ከተማ ይፉ የተደረገው ይህ ፕሮግራም፤ በአሜሪካ መንግሥት በሚገኝ የ49 ሚሊዮን ዶላር ወይንም ከ5 ቢሊዮን ብር በላይ ድጋፍ የሚተገበር ሲሆን፤ በኢትዮጵያ በሚገኙ 9 ክልሎችና 120 ወረዳዎች ላይ ከ14 ሚሊዮን በላይ ሕዝቦችን ማዕከል አድርጎ እንደሚሰራ ተነግሯል፡፡
የድርጅቱ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ ድጋፍ ቢሮ ምክትል ዳይሬክተር ሄኖክ ሁንበላይ፤ ለፕሮግራሙ የ5 ዓመታት ጊዜ መያዙን ገልጸው፤ ሦስት መሰረታዊ ትላልቅ አላማዎች በውስጡ መያዙን ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
እነርሱም አንደኛ የአገሪቱ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ሥራዎች በተፋጠነ እና በተቀላጠፈ መልኩ በተሻለ ዝግጁነት እንዲሰሩና ከአሁን በፊት በተደረጉ ሥራዎች ላይ ተመስርቶ የተሻለ ትንበያ እንዲሁም የአደጋ ምላሽ እንዲሰጥ ማስቻል መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ሁለተኛው ደግሞ በየክልሎቹ ያሉ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ተቋማትን አቅም የማጎልበት ሥራ ነው ብለዋል፡፡
በሦስተኛው ደረጃ ደግሞ የግሉ ዘርፍ አደጋ ከተከሰተ በኋላ ሳይሆን፤ አደጋ ከመከሰቱ በፊት አስተዋጽዖ እንዲያደርግ ማስቻል እና ማስተባበር የፕሮግራሙ ዋና አላማዎች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ በየክልሎቹ የሚገኙ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽኖች የተሻለ የአደጋ ትንበያ እንዲሰጡ፣ ያላቸውን ሀብትና ሌሎች ግብዓቶችን በአግባቡ እንዲጠቀሙ እንዲሁም አደጋው ችግር ከማስከተሉ በፊት ከማህህረሰቡ ጋር እንዲሰሩ የሚያደርግ የአቅም ግንባታ ሥራዎች እንደሚሰሩም አቶ ሄኖክ አስረድተዋል፡፡
በዚህም መሰረት ፕሮግራሙ የሶማሌ ክልል፣ የደቡብ ክልል፣ የአፋር ክልል፣ የኦሮሚያ ክልል፣ የአማራ ክልል፣ የትግራይ ክልል፣ የደቡብ ምእራብ እና ማዕከላዊ ደቡብ ክልሎችን ማዕከል አድርጎ እንደሚሰራ የገለጹ ሲሆን፤ በዚህም እንደየክልሎቹ የአደጋ ተጋላጭነት የክልሎቹን አቅም የመገንባት ሥራ ይሰራል ሲሉ ለአሐዱ ገልጸዋል፡፡
የአሜሪካ አለም አቀፍ የተራድኦ ድርጅት በዚህ ፕሮጀክት ከፌደራል አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን፣ ከገንዘብ ሚኒስትር እንዲሁም ከሌሎች የመንግሥት አካላትና የልማት አጋር ድርጅቶች ጋር በትብብር እንደሚሰራ የገለጹት ምክትል ዳይሬክተሩ፤ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበርን ጨምሮ ሦስት አለም ዓቀፍ እና የአገር ውስጠ ተቋሟት ፕሮግራሙ በማስፈጸም ደረጃ አብረው እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡
ይህ ድጋፍ በአደጋ ሥጋት አመራር ዘርፍ በዩኤስኤድ እስካሁን ከተደረጉ ድጋፍ ከፍተኛ መሆኑ የተነገረ ሲሆን፤ በዚህም ምክንያት ፕሮግራሙ በአግባቡ ተግባራዊ ስለመደረጉ ትልቅ አጽዕኖት ተሰጥቶበት የቁጥጥር ሥራ እንደሚሰራ ተመላክቷል፡፡
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ኔቶ የኒውክሌር ልምምዶችን መጀመሩን አስታወቀ
ጥቅምት 5/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት(ኔቶ) ከ60 በላይ አሜሪካ ሰራሽ አውሮፕላኖች የተሳተፉበትን የአቶሚክ የጦር መሳሪያዎች በማሰማራት የኒውክሌር ልምምዶችን መጀመሩን አስታውቋል፡፡
ድርጅቱ ይህንን ልምምድ የጀመረው በሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት ውጥረት ውስጥ መሆኑ በሚነገርበት በአሁኑ ወቅት ነው፡፡
በስልጠናውም አሜሪካን ጨምሮ 13 የሚደርሱ የኔቶ አባል ሃገራት እየተሳተፉ እንደሚገኝ ሲሆን፤ ልምምዱ በቤልጂየም እና በኔዘርላንድስ የጋራ አስተናጋጅነት ለሁለት ሳምንታት የሚሰጥ ይሆናል ተብሏል።
ጥምር ጦሩ አክሎም በጋራ ወታደራዊ ልምምዱ ላይ ቦምቦች፣ ተዋጊ ጄቶች፣ የበረራ ታንከሮች እና የኤሌክትሮኒክስ የጦር አውሮፕላኖችን እንደሚካተቱ ማስታወቁን አልጂዝራ ዘግቧል::
ይህንንም ተከትሎ ሩሲያ ̎ኔቶ ውጥረቱን እያባባሰ ነው̎ ስትል ክስ አቅርባለች፡፡ ልምምዱ የሚካሄደው ከሩሲያ 900 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ መሆኑን ተከትሎ ጉዳዩ እንዳሳዘናትም ገልጻለች::
የሩሲያ መንግሥት ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ፤ "በዩክሬን ግጭት ማዕቀፍ ውስጥ እየተካሄደ ባለው ሞቃት ጦርነት፤ በእርግጥ እንደዚህ ያሉ ልምምዶች የበለጠ ውጥረትን ከማባባስ በስተቀር ምንም አያመጡም" ማለታቸውን የአገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
ቃል አቀባዩ አክለውም፤ ዋሽንግተን በዩክሬን ግጭት ውስጥ በጣም ስለተሳተፈች ሞስኮ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ አጠቃቀምን በተመለከተ፤ ከአሜሪካ ጋር ምንም አይነት ውይይት እንደማታደርግ ተናግረዋል።
በደረጄ መንግስቱ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
የፌደራል ፍርድ ቤት የሽግግር ፍትሕ ስርአትን ተግባራዊ በማድረግ ልዩ ችሎቶችን በማቋቋምና በማደራጀት እንደሚሰራ አሰታወቀ
ጥቅምት 5/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የፌደራል ፍርድ ቤት የሽግግር ፍትሕ ስርአትን ተግባራዊ በማድረግ ልዩ ችሎቶችን በማቋቋምና በማደራጀት ሊሰራባቸው የሚገባ ጉዳዮችን ላይ በትኩረት እንደሚሰራ፤ የፌደራል ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ቴዎድሮስ ምህረት ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
ፕሬዝዳንቱ የሽግግር ፍትሕ እንደ ፍርድ ቤት በዋናነት የተከላካይ ጠበቆች ላይ በትኩረት የሚሰራ መሆኑን አንስተዉ፤ የልዩ ችሎቶችን በተመለከተ የሕግ ማዕቀፍ ያለው መሆኑንና ከአደራጃጀት ጋር በተያያዘ የሰው ሐይልና ፋሲሊቲ የተሟላ እንዲሆን ለማድረግ ይሰራል ብለዋል፡፡
የሽግግር ፍትሕ ብዙ ለውጦችን ያመጣል ተብሎ የታሰበ ሲሆን፤ የሕግ ማዕቀፉን በተመለከተ የመጀመሪያ ረቂቅ መዘጋጀቱን ያነሱት ፕሬዝዳንቱ፤ በቀጣይ በሕዝቡ ወይይት እንደሚደረግበት አንስተዋል፡፡
የማደራጅት ሥራውን ደግሞ የውስጥ ኮሚቴዎችን በማዋቀር የጥናት ሥራ መጀመሩን የገለጹ ሲሆነ፤ ፖሊሲው ባስቀመጠው መሰረት ለችሎት የሚመጥኑ ዳኞችን እንደሚሰየሚም አስረድተዋል፡፡
በሽግግር ፍትሕ ስርአቱ መሰረት ምን ያክል ልዩ ችሎቶች ይቋቋማሉ በሚል አሐዱ ላነሳላቸው ጥያቄ አቶ ቴዎድሮስ ገና ዝርዝር ሥራ እንደሚጠይቅ የገለጹ ሲሆን፤ "በሚደረገው ጥናት መሰረት ምን ያክል ጉዳዮች እንደሚኖሩ ከጥናት በኋላ ይፋ ይደረጋል" ብለዋል፡፡
ጥናቱ ከባለድርሻ አካላት በጋራ በመሆን የሚሰሩ መሆኑን በማንሳትም፤ በተለይ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ከዚህ በፊት ባደረገው ጥናት መሰረት የሚያከናውኑ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
በአለምነው ሹሙ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
በቻድ በጣለ ከባድ ዝናብ ከ550 በላይ ሰዎች ሕይወታቸዉ አለፈ
ጥቅምት 5/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በማዕከላዊ አፍሪካዊቷ አገር ቻድ በጣለ ከባድ ዝናብ 550 በላይ ሰዎች ሕይወታቸዉ ማለፉ ተሰምቷል።
ሀገሪቱ 23 ግዛቶች እንዳሏት የሚታወቅ ሲሆን፤ በሁሉም ግዛቶች ላይ በተከሰተው ከፍተኛ ጎርፍ ምክንያት 210 ሺሕ ቤቶች መወሰዳቸው ተገልጿል፡፡
በተጨማሪም ከ550 በላይ ሰዎች እንዲሁም 72 ሺሕ የቤት እንስሳት በጎርፉ ምክንያት ሕይወታቸው ማለፉ ተነግሯል፡፡
በአደጋዉ 400 ሺሕ ሄክተር መሬት የወደመ ሲሆን፤ በዚህም ምክንያት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ቻዳዊያን ለረሃብ አደጋ ሊጋለጡ ይችላል የሚል ስጋት መፈጠሩን የአፍሪካ ኒዉስ ዘገባ አመላክቷል።
የተባበሩት መንግሥታት የስነ ህዝብ ፈንድ (UNFPA) በሀገሪቱ ከተጎዱት 1.9 ሚሊዮን ሰዎች መካከል 85 ሺሕ ያህሉ ነፍሰ ጡር እናቶች መሆናቸውን ያስቀመጠ ሲሆን፤ እነዚህ ነፍሰ ጡር እናቶች መሰረታዊ የጤና እንክብካቤ እጥረት አጋጥሟቸዋል ብሏል።
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
በኢትዮጵያ ለሚገኙ ችግር ያለባቸው የሱዙኪ SPRESSO ተሽከርካሪዎች ጥሪ ቀረበ
ጥቅምት 4/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ሱዙኪ ኩባንያ የሚያመርታቸው ስፕሬሶ (SPRESSO) በሚል መጠሪያ የሚታወቁ የተወሰኑ ተሽከርካሪዎች ላይ የመሪ ዘንግ ክፍል አካባቢ ችግር መኖሩ በመታወቁ፤ በኢትዮጵያ ይህ ችግር ያጋጠማቸው የተጠቀሱት ዓይነት ተሽከርካሪዎች ተሰብስበው ማስተካከያ እንዲደርግባቸው ጥሪ ቀርቧል።
በኢትዮጵያ ውስጥ የሱዙኪ ተሽከርካሪዎች ሕጋዊ አከፋፋይ ድርጅት የሆነው ታምሪን ኩባንያ ዛሬ በሪፖርተር ላይ ባወጣው ይፋዊ መረጃ፤ በተወሰኑ የ SPRESSO የምርት ባች ላይ በተደጋጋሚ ለጉዳት ሊጋለጥ የሚችል የመሪ ዘንግ ክፍል አካባቢ እክል ስለመኖሩ አምራች ኩባንያ ሱዙኪ መረጃ እንደደረሰው አስታውቋል።
"በመሆኑም ከላይ የተገለጽው ችግር ይኖርባቸዋል ተብለው የታሰቡ የምርት ባች ላይ ያሉትን SPRESSO መኪናዎች በሙሉ ጥሪ በማድረግ ሊያጋጥም ከሚችል እክል ማስወገድ አስፈላጊ ሆኗዋል" ብሏል፡፡
በዚህም ምክንያት በኢትዮጵያ የ SPRESSO መኪና ባለቤት የሆኑ ባለንብረቶች ይፋ የተደረገውን የምርት ዘመን ዝርዝርና የሻንሲ ቁጥር በማየት ተሽከርካሪዎቻቸው ለጥሪ እና ጥገና የሚፈለጉ መሆኑን እንዲያረጋገጡ ታምሪን ኩባንያ አሳስቧል።
ይፋ በተደረገው ዝርዝር ውስጥ የሻንሲ ቁጥራቸውን ያገኙ ባለቤቶች፤ ተሽከርካሪዎቹን በታምሪን ኩባንያ የአገልግሎት ማዕከል በማቅረብ ችግር እንዳለበት የተለየውን ክፍል (የመሪ ዘንግ አካላት) በኦርጂናል የሱዙኪ መለዋወጫዎች በማስቀየር ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን ለማስወገድ እንዲተባበሩን ጥብቅ ጥሪውን አቅርቧል።
"በመሆኑም የ SPRESSO መኪና ባላቤት የሆናችሁ ባለንብረቶች ከላይ ባለው ዝርዝር የሻንሲ ቁጥር በማየት ተሽከርካሪያችሁ ለጥሪ እና ጥገና የታሰበ መሆኑን እንድታረጋገጡ በጥብቅ እናሳስባለን" ብሏል።
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው ወንጀሎች ጥፋተኛ ተባሉ
ጥቅምት 4/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የጥላቻ ንግግር ማሰራጨት እና የዕርስ በዕርስ ግጭት መቀስቀስ ወንጀሎች የተከሰሱት አቶ ታዲዮስ ታንቱ በፍርድ ቤት ጥፋተኛ ተባሉ፡፡
አቶ ታዲዮስ በተከሰሱበት ሦስት ክሶች በዛሬ ቀጠሮ የጥፋተኝነት ፍርድ የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የሕገ-መንግስትና ሕገ-መንግሥታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።
ከሳሽ ዐቃቤ ሕግ የዋስትና ጥያቄያቸው ውድቅ እንዲደረግ የመከራከሪያ ነጥቦችን አቅርቦ ክርክር መደረጉ ይታወቃል።
የግራ ቀኙን ክርክር መርምሮ ፍርድ ቤቱ ዋስትና ላይ ብይን ለመስጠት ለዛሬ በሰጠው ተለዋጭ ቀጠሮ መሰረት ችሎቱ ተሰይሞ የአቶ ታዲዮስ ታንቱ የዋስትና ጥያቄያቸውን በሙሉ ድምፅ ውድቅ አድርጎታል።
አቶ ታዲዮስ ዝርዝር የሠነድ መከላከያ ማስረጃዎች ካሏቸው ማቅረብ እንዲችሉ ለታኅሣስ 21 ቀን የተቀጠረ ሲሆን፤ የሚቀርቡ የመከላከያ ማስረጃዎችን አሰማምን በሚመለከት በዕለቱ ሌላ የቀጠሮ ቀን የሚሰጥ ይሆናል ተብሏል።
ተከሳሹ ሰኔ 20 ቀን 2014 ዓ.ም የጥላቻ ንግግር በማሰራጨት እና የእርስ በርስ ግጭት መቀስቀስ ወንጀል ፈጽመዋል በሚል በፍትሕ ሚኒስቴር በተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ዐቃቤ ሕግ በኩል ተደራራቢ አራት ክሶች ቀርቦባቸው እንደነበር ይታወሳል።
ዐቃቤ ሕግ ያቀረበው 1ኛው ክስ እንደሚያመላክተው በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32/(1)ሀ እና አንቀጽ 257/ሀ ስር የተደነገገውን ድንጋጌ በመተላለፍ ታዲዮስ ታንቱ ግንቦት 11 ቀን እና መጋቢት 22 ቀን 2014 ዓ.ም እና በተለያዩ የዩቲዩብ ቻናሎች ሕዝባዊ አመጽ መቀስቀስ ወንጀል ተከሰው ነበር።
በ2ኛ ክስ ደግሞ የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ ቁ 1185/2012 አንቀጽ 4 እና 7/4 በመተላለፍ ታዲዮስ ታንቱ ታኅሣስ 3 ቀን 2014 ዓ.ም በአንድ የዩቲዩብ ቻናል ሐሰተኛ መረጃ አሰራጭተዋል የሚል ክስ በዐቃቤ ሕግ ቀርቦባቸው ነበር፡፡
እንዲሁም በ3ኛ ክስ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32 /1ሀ እና አንቀጽ 337 በመተላለፍ የመከላከያ ሰራዊትን እንቅስቃሴ ለማሰናከልና የመከላከል አደጋ እንዲደርስ ለማድረግ በማሰብ ሐሰተኛ ወሬ በመንዛት ቅስቀሳ ማድረግ ወንጀል መከሰሳቸው ይታወቃል፡፡
በ4ኛ ክስ ደግሞ የኮምፒዩተር ወንጀል አዋጅ ቁ 958/2008 አንቀጽ 14 በመተላለፍ ሕዝባዊ አመጽ እንዲፈጠር ቀስቃሽ መልዕክት በድምጽና በተንቀሳቃሽ ምስል ተሰራጭቷል የሚል ክስ በዐቃቤ ሕግ በኩል ቀርቦባቸው እንደነበር ይታወሳል።
ዐቃቤ ሕግ ባቀረበባቸው አራት ክሶች ላይ የተጠቀሱትን የወንጀል ድርጊት አለመፈጸማቸውን ገልጸው፤ የሰጡትን የእምነት ክህደት ቃል ተከትሎ ዐቃቤ ሕግ ለወንጀሉ መፈጸም ያስረዳሉ ያላቸውን ምስክሮችን አቅርቦ አሰምቷል።
ፍርድ ቤቱም የዐቃቤ ሕግ ምስክርን መርምሮ እንዲከላከሉ በሙሉ ድምጽ ብይን መስጠቱ ይታወሳል።
አቶ ታዲዮስ እንዲከላከሉ በተሰጠ ብይን መነሻ የተለያዩ የመከላከያ ምስክሮችን በማቅረብ አሰምተው የነበሩ ቢሆንም፤ ባቀረቡት የመከላከያ ማስረጃ ግን የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን በተገቢው መከላከል አለመቻላቸው ተገልጾ የጥፋተኝነት ፍርድ እንደተላለፈባቸው ኤፍቢሲ ዘግቧል፡፡
ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኝ የቅጣት አስተያየትን ለመጠባበቅ ለጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱም ታውቋል፡፡
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
የፕሮግራም ጥቆማ!
የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ም/ቤት በአውሮፓ ሕብረት የገንዘብ ድጋፍ የሚያዘጋጀውና የሰላም ግንባታ ላይ የሚያተኩረው ልዩ ፕሮግራም ዘወትር ማክሰኞ ከምሽቱ 11፤ 30 ጀምሮ በአሐዱ 94.3 ላይ ወደ እናንተ ውድ ቤተሰቦቻችን ያደርሳል፡፡
ፕሮግራሙን እንድትከታተሉና ሃሳብ እንድታደርሱን በአክብሮት እንጋብዛለን፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ፣ ይደውሉልን፡፡
በ2016 ከቀረቡ ከ2 መቶ ሺሕ በላይ መዝገቦች ውስጥ 176 ሺሕ 722 መዝገቦች እልባት ማግኘታቸው ተገለጸ
ጥቅምት 4/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በ2016 በጀት ዓመት ከቀረቡ 2 መቶ 12 ሺሕ 495 መዝገቦች ውስጥ፤ 176 ሺሕ 722 መዝገቦች እልባት ማግኘታቸውን የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለአሐዱ ገልጿል።
በበጀት ዓመቱ ከመዝገብ አፈጻጸም አኳያ ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከቀረቡ 24 ሺሕ 591 መዛግብት መካከል ለ16 ሺሕ 636 መዛግብት እልባት መሰጠቱን እንዲሁም፤ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 31 ሺሕ 989 መዛግብት ቀርበው 24 ሺሕ 853 መዛግብቶች እልባት ማግኘታቸውን የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ቴዎድሮስ ምህረት ለአሐዱ አስታውቀዋል፡፡
በተመሳሳይም በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤቶች 155 ሺሕ 915 መዛግብት ቀርበው 135 ሺሕ 233 መዛግብት እልባት ማግኘታቸውን ተናግረዋል።
ፕሬዝደንቱ አክለውም፤ በ2017 በጀት ዓመት ትኩረት ተሰጥቷቸው ከሚከናወኑ ተግባራት መካከል ተቋማዊ ነጻነትን የጠበቀ ገለልተኛ የዳኝነት አገልግሎት መስጠት የሚያስችሉ የሕግና አሰራር ማዕቀፎችን ማጠናከር አንዱ መሆኑን የገለጹ ሲሆን፤ የፍርድ ቤት እና ሌሎች የመንግሥት አካላት የእርስ በእርስ ግንኙነት መድረኮችን በማመቻቸት የቅንጅት ሥራዎችን የማስፋት ሥራም እንደሚሰራ አስረድተዋል።
በተጨማሪም የዳኞችን ሁለንተናዊ ደህንነት በማረጋገጥ ነጻ፣ ገለልተኛ፣ ጥራት ያለውና ቀልጣፋ የዳኝነት አገልግሎት መስጠት የሚችሉበት አሰራርን በመዘርጋት ላይ በትኩረት እንደሚሰራም ፕሬዝዳንቱ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
በአለምነው ሹሙ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
#የአሐዱ_ዕለታዊ_ዜናዎች!
ዜናዎቹን ለመከታተል ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👇
https://youtu.be/51hOR1rCBug?si=z6ibC0_m73oPB8np
በተያዘው ወር ስንዴ አምራች በሆኑ አካባቢዎች ላይ ብቻ የጸረ-አረም ርጭት ይከናውናል ተባለ
ጥቅምት 6/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የግብርና ሚኒስቴር በተያዘው ወር ስንዴ አምራች በሆኑ አከባቢዎች ላይ ብቻ የጸረ-አረም ርጭት እንደሚከናወን አስታውቋል፡፡
ሚኒስቴሩ የአረም መከላከል እና ርጭት ሥራው በስንዴ ምርት ላይ ብቻ እንዲከናወን የወሰነው የፀረ-አረም መከላከያ ኬሚካል አቅርቦት እጥረት በመኖሩ ነው ተብሏል።
ከዚህ በፊት የጸረ-አረም ርጭት የሚከናወነው በሁሉም የአዝዕርት ማሳ ላይ እንደነበር ያስታወሰው ሚንስትር መስሪያቤቱ፤ በዚህ ዓመት ባጋጠመው እጥረት ምክንያት ስንዴ ምርት ላይ ብቻ ለማተኮር መገደዱን አስታውቋል።
በግብርና ሚንስቴር የአዝዕርት ጤና ክትትል ኃላፊ አቶ በላይነህ ንጉሤ፤ የርጭት ሂደቱ በወረፋ እንዲሆን እና እንደ ጤፍ ያሉ ሌሎች አዝርእቶች ተራቸውን ጠብቀው በተያዘላቸው መርሀ-ግብር የጸረ-አረም ርጭት እንደሚከናወንላቸው ለአሐዱ ተናግረዋል።
በተለይም በምእራብ ኦሮምያ የጸረ-አረም ርጭቱ እንዲዳረስ ከፍተኛ ጥረት በመደረግ ላይ መሆኑን መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል፡፡
ለአረም መከላከል እና ርጭት ሥራው የማሳው ባለቤት አርሶ አደር የበኩሉን አስተዋጽኦ እያደረገ እንደሚገኝ የገለጹት ኃላፊው፤ የክልል ግብርና ቢሮዎችም የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የሚያስችላቸውን ስልጠና በመውሰድ ላይ እንደሚገኙ ነግረውናል፡፡
የግብርና ግብዓት አቅርቦት ኮርፓሬሽን የፀረ-አረም ግብአቶች በዋጋ ንረት ምክንያት አቅርቦታቸው በመቀነሱ እጥረት እንዳጋጠመው በተደጋጋሚ ቢገልጽም፤ መንግሥት እጥረቱ የጎላ ችግር እንደማያደርስበት ገልጾ አብቃቅቶ ለመጠቀም እንደሚጥር ምላሽ ሲሰጥ መደመጡ አይዘነጋም፡፡
በአማኑኤል ክንደያ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
#UPDATE
"አቤት ሆስፒታል 'የፍርድ ቤት ክርክር አሸንፌ ቦታዬን ተረክቢያለሁ' ቢልም የፍርድ ቤት ክርክሩ ገና አልተጀመረም" የሦስቱ አብያተ ክርስቲያናት ጠበቃ
ጥቅምት 6/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) አቤት ሆስፒታል 'የፍርድ ቤት ክርክር አሸንፌ ቦታዬን ተረክቢያለሁ' ቢልም የፍርድ ቤት ክርክሩ ገና አለመጀመሩን የደብረ ሲና ቅዱስ እግዚአብሔርአብ፣ የደብረ መድሐኒት ድል በር መካነ ጎሎጎታ መድሐኒዓለም እንዲሁም የመንበረ ክቡር አቡነ ተክለሀይማኖት እና ቅዱስ ሚካዔል ገዳም አብያተ ክርስቲያናት ጠበቃ ሳምራዊት አሰፋ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
አቤት ሆስፓታል ለግንባታ ማስፋፊያ የተሰጠው ቦታ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስምንት በተለምዶ አጠራሩ አዲሱ ገበያ አካባቢ የሚገኝ ሲሆን፤ ቦታው ሦስት አብያተ ክርስቲያናት ለባህረ ጥምቀት ማክበሪያነት የሚገለገሉበት የነበረ ቦታ እንደሆነ ይታወቃል።
ይህንን ቦታ በተመለከተ አቤት ሆስፒታልን በበላይነት በሚያስተዳድረዉ ቅዱስ ጷውሎስ ሆስፒታል እና በሦስቱ አድባራት በኩል የፍርድ ቤት ክርክር እየተደረገ እንደሆነና ጷውሎስ ሆስፒታል ክርክሩን አሸንፊያለሁ ማለቱን አሐዱ መዘገቡ ይታወሳል።
ነገር ግን የፍርድ ቤት ሂደቱ ገና አለመጀመሩን የተናገሩት የሦስቱ አድባራት ጠበቃ፤ በፍርድ ቤት ያለው ሂደትም "ስድስት ሚሊዮን ብር ለፍርድ ቤት ክፈሉ ጉዳዩ ይታይ" የሚል መሆኑን ለአሐዱ አስረድተዋል።
ጠበቃዋ ይህን ገንዘብ አንከፍልም̎ በሚል በሰበር ሰሚ ፍርድ ቤት ጉዳዩ ክርክር ላይ መሆኑን የገለጹም ሲሆን፤ ጉዳዩን ፍርድ ቤት ማየት የጀመረው በ2013 ዓ.ም እንደሆነም አስታውሰዋል።
ተቋሙ አሁን ላይ የሕንፃው ግንባታ እንዲጀመር የጨረታ ሰነዱን አዘጋጅቶ ማስረከቡ የተነገረ ሲሆን፤ በቀጣይ ሦስት ዓመታት ውስጥም የግንባታ ሥራውን ለማጠናቀቅ እቅድ መያዙን የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የግንባታ ክፍል ባለሙያ አቶ ገብረጊዮርጊስ ዘሩ ለአሐዱ መግለፃቸው ይታወሳል።
እግዱን አውጥቶ የነበረው አካል ማረጋገጫ ካርታ የሌለው መሆኑ የፍርድ ቤቱን ክርክር እንዲያሸንፉ ዕድል እንደሰጠው፤ በዚም መሰረት ጳውሎስ ሆስፓቲል የማረጋገጫ ካርታ እንደተሰጠው መግለጹን አሐዱ መዘገቡ አይዘነጋም።
በሚኪያስ ሃይሌ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ዲጂታል የጤና የመረጃ ቋት ለመዘርጋት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ
ጥቅምት 6/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ ብሔራዊ የሆነ ዲጂታል የጤና የመረጃ ቋት ለመዘርጋት እየተሰራ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
ሚኒስቴሩ በኢትዮጵያ እየተስተዋለ ያለውን የተበታተነ የጤና መረጃ አያያዝ ማሻሻል አስፈላጊ መሆኑ እንደታመነበት ገልጿል።
ይዘጋጃል የተባለው የመረጃ ቋት የመድኃኒት አያያዝንና ቁጥጥርን ጨምሮ የበሽታ አይነቶች የሚመዘገቡበት እንዲሆን ውጥን መያዙን የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ ገልጸዋል።
አክለውም፤ ዲጂታል የጤና መረጃ ለማደራጀት፣ ለመጠቀም እንዲሁም ወደ ዲጂታል አገልግሎቶች መግባት የሚችሉ የጤናው ዘርፍ ሥራዎችን በዲጂታል ለመተካት bጤና ሚኒስቴር በርካታ ሥራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ለአሐዱ ተናግረዋል።
ዲጂታል የጤና የመረጃ ቋት በተለያዩ ጊዜያቶች የሚፈጠሩ በሽታዎችን ለመለየት የሚያስችል መሆኑን የገለጹት ሚንስተሯ፤ የተያዘው ውጥን እንዲሳካ ከተለያዩ ተቋማት ጋር በትብብር መስራት አስፈላጊ መሆኑን አሳስበዋል።
"የዲጂታል የጤና መረጃ ስርአት መዘርጋቱ የጤና አገልግሎት አሰጣጡን ለማቀላጠፍ ይረዳል፡፡" የተባለ ሲሆን፤ ስርዓቱ መረጃን በፍጥነት ተደራሽ ለማድረግ፣ እንግልትን ለመቀነስ እንዲሁም፤ ቶሎ ውሳኔ በመስጠት ወረርሽኝን ለመግታት እና ለመሳሰሉት አስፈላጊ መሆኑን ተነግሯል።
በኢትዮጵያ ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚከሰቱ በሽታዎች ዙርያ በሰነድ ደረጃ የሚያዝ መረጃ እንዳልነበረ ሲገለፅ ቆይቷል።
በአማኑዔል ክንደያ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
በአዲስ አበባ የህዝብ ትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ ጭማሪ ተደረገ
ጥቅምት 5/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ ለተሰማሩ ሚኒ-ባሶች፣ ሚዲ-ባስ ታክሲዎችና የከተማ አውቶብሶች ላይ ተግባራዊ የሚደረግ አዲስ ታሪፍ ይፋ አድርጓል፡፡
አዲሱ ታሪፍ ከነገ ጥቅምት 06 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል የተባለ ሲሆን፤ በአዲሱ ታሪፍ ዝቅተኛው 10 ብር ከፍተኛው 65 ብር ገብቷል።
በዚህም መሰረት የሚኒባስ ታክሲ ጭማሪ
👉 4 ብር ከ50 ሳንቲም የነበረው 10 ብር
👉 8 ብር ከ50 ሳንቲም የነበረው 15 ብር
👉 13 ብር የነበረው 20 ብር
👉 17 ብር የነበረው 25 ብር
👉 21 ብር ከ50 ሳንቲም የነበረው 30 ብር ሆኗል::
ቀድሞ አገልግሎት ሲሰጥበት የነበረው የታሪፍ ተመን ከጥቅምት 20/2016 ዓ.ም ጀምሮ አገልግሎት ላይ የዋለ እንደነበረና ስሌቱም የነዳጅ ጭማሪ ዋጋን ብቻ ታሳቢ ያደረገ እንደነበር ቢሮው አስታውቋል።
አሁን የተደረገው የታሪፍ ማሻሻያ ደግሞ ወቅታዊ የነዳጅ የችርቻሮ ዋጋ እና ሌሎች አስተዳደራዊ ወጪዎችን ያማከለ መሆኑን ቢሮው ገልጿል፡፡
የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች አዲስ በተሻሻለው ህጋዊ የታሪፍ ተመን ብቻ አገልግሎት እንዲሰጡ ማሳሰቢያ የሰጠው በቢሮው፤ ይህንን በሚተላለፉት አካላት ላይ ጥብቅ እርምጃ እንደሚወሰድም አስታውቋል፡፡
👉የታሪፍ ጭማሪው ሙሉ መረጃ ከላይ ተያይዟል!
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
ኢትዮጵያ የወጭ ጉዳይ ሚኒስትር በአስቸኳይ መሾም እንዳለባት ምሁራን አሳሰቡ
ጥቅምት 5/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ.ም 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን መክፈቻ ላይ፤ የቀድሞ የዉጭ ጉዳይ ሚንስትር የነበሩት አምባሳደር ታዬ ሀጽቀስላሴ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፕሬዝዳንት ሆነው መመረጣቸው ይታወሳል፡፡
አሐዱም ኢትዮጵያ አሁን ካለችበት ነባራዊ ሁኔታ አንጻር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯን ሳትመርጥ ለምን ያህል ጊዜ ቦታው ክፍት መሆን ይችላል? በማለት ሕጉን በተመለከተና የሚያመጣውን ተጽዕኖ ጠይቋል፡፡
ኢትዮጵያ አሁን ባለችበት ሁኔታ የዉጪ ግንኙነቷን ማጠናከር እንደሚያስፍልግ የተናገሩት የቀድሞ ዲፕሎማት ዳያሞ ዳሌ ናቸው፡፡
በዚህም ምክንያት የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ የሰዉ ሀይል በሙሉ የቀጠናውን እንቅስቃሴ በንቃት መከታተል ያለበት ወቅት መሆኑን ዳያሞ አሳስበዋል።
በመሆኑም የወጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከሌሎች ሀገራት ጋር መደበኛ ግንኙነቶችን ከማድረግ አንጻር ከፍተኛ ተጽዕኖ እንደሚኖረው አንስተው፤ "ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለቦታዉ የሚመጥን ሚኒስትር ሊተካ ይገባል" ሲሉም ተናግረዋል።
አክለውም ርዕሰ ብሔሮች ከፓርቲ ፖለቲካ ነጻ እና ገለልተኛ ስለሆኑ፤ ከሌሎች የዉጭ ሀገራት ጋር መደበኛ ግንኙነቶችን ኢ-መደበኛ ግንኙነት ከማድረግ አንጻር ከፍተኛ ተጽዕኖ እንደሚኖረው ገልጸው፤ በአገሪቱ ሚኒስትር የመሾሙ ሥራ በአስቸኳይ ሊከናወን እንደሚገባ አጽዕኖት ሰጥተዋል።
"የሚንስቴር መስሪያ ቤቶች ከፍተኛ ባለስልጣናት ከቦታው በሚነሱበት ጊዜ ወዲያው ቦታዉን በሓላፊነት የሚመራ አካል መተካት እንዳለበት አጠቃላይ ግንዛቤ ቢኖርም፤ በምን ያህል ጊዜ መተካት አለባቸው የሚለዉ ጉዳይ ሕጉ በግልጽ ያስቀመጠዉ ነገር የለም" ያሉት ደግሞ የሕግ ባለሙያዉ አቶ ካሳሁን ሙላት ናቸው፡፡
ኢትዮጵያ ካለችበት ነባራዊ ሁኔታ አንጻር አሁን ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሾም ይገባታል ያሉት የሕግ ባለሙያዉ፤ ሕገ መንግሥቱ ላይ ለሀገሪቱ ፕሬዚዳንት የተሰጡት ስልጣኖች ለብቻ የተቀመጡ እንደሆኑ እና ሁለት ቦታዎች ላይ ደርበው ለመስራት የሚያስችል የሕግ አግባብ እንደሌለ አስረድተዋል።
አሁንም ቀጥተኛ ባልሆነ መልኩ የዉጭ ጉዳይ ዘርፉ ላይ አስተዋጽኦ ይኖራቸዋል ተብሎ እንደሚጠበቅ አሐዱ ያነጋገራቸው ባለሙያዎች አንስተው፤ በቶሎ መፍትሄ የሚያሻው ጉዳይ ነው ሲሉም ጠቁመዋል፡፡
በፅዮን ይልማ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
የከተማ ልማት ሥራው በሊዝ ሽያጭ “የአየር ባየር ባለሃብቶች” ማበልጸጊያ ሆኗል ሲሉ የትብብር ፓርቲዎች ገለጹ
ጥቅምት 5/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በመንግሥት የሚሰራው የከተማ ልማት በዘርፉ ባለሙያዎች ያልተመዘነ፣ በፕሮግራም ያልተያዙ የአጭር ጊዜ ትርፍ ብቻ ያላቸው የኑሮ ውድነት፣ የቤት/የቦታ እጥረትና ዋጋ መናር፣ የመጓጓዣ፣ የውሐና መሰል መሠረተ ልማት ችግር ጠፍሮ ለያዛቸው ከተሞች የእግረኛ መንገድ፣ የሕንጻ ላይ መብራትና ቀለም፣ ሣርና ዘንባባ ተከላ እና መሰል ነገሮች ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ ጉዳዮች አይደሉም ሲሉ ተባባሪ ፓርቲዎች ገልጸዋል።
በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መኢአድ፣ ኢሕአፓ፣ ዐማራ ግዮናዊ ንቅናቄና እናት ፓርቲ ትናንት ጥቅምት 4 ቀን 2017 ዓ.ም በጋራ ባወጡት መግለጫ ነው ይህን የገለጹት።
ተባባሪዎቹ አክለውም፤ ̎የሚሰሩት የከተማ ማስዋብ ሥራዎች የወረት ያህል ለጊዜው ከላይ ሲታይ ያማረ ቢመስል የከተማውን ነዋሪ ማኅበረ ኢኮኖሚያዊ ችግር ቢያወሳስበው እንጂ እሴት ጨምሮ ችግራቸውን አይፈታውም̎ ሲሉ ገልጸዋል።
በአንጻሩ አዲስ አበባ በዓለም ሦስተኛዋ ድፕሎማቲክ ከተማ በመሆኗ ንፁሕ መሆን፣ የበለጠ ማማርና መዘመን እንዳለባት እሙን ነው ሲሉ ተባባሪ ፓርቲዎች ገልጸዋል።
ሆኖም ግን የኮሪደር ልማት በሚል “መጠኑንና አድማሱን አስፍቶ ሙሉ ከተማ ወደማፍረስ የተሸጋገረው ሥራ አሻራ የመቶ ሺህዎችን ሕይወት እያመሰቃቀለ ነው” ብለዋል።
በዚህም በድንገት ቤታቸው የፈረሰባቸውና የይፈርሳል መርዶው ሲነገር ለጠና ሕመም የተዳረጉ፣ ከለመዱት ማኅበራዊ መሠረት የተናጠቡ፣ ሥራቸው ሙሉ ለሙሉ የተቋረጠና ለከፋ ችግር የተዳረጉ፣ ቍጥሩ በውል ያልታወቀ በድንጋጤም የሞቱ ሰዎች መኖራቸውን አንስተዋል።
አሁን ላይ በአዲስ አበባ በ4ኪሎ፣ 5ኪሎ፣ ፒያሳ፣ ቤላ፣ አምባሳደር፣ ፈረንሳይ፣ ቦሌ፣ ካዛንችስ፣ ገርጂ እና በኹሉም ወንዝ አለባቸው በሚባሉ የከተማዋ አካባቢዎችና በሌሎችም አካባቢዎች በዋና ዋና መንገዶች ዳርቻ ከፍተኛ ፈረሳዎች እየተካሄዱ/እንደሚካሄዱ ገልጸዋል።
በኑሮ ውድነትና ሰላም እጦት ውስጥ ያለ ማኅበረሰብ ባለበት ልማት ሳይሆን መንግሥት የገጠመውን በጀት እጥረት ከሊዝ ሽያጭ መሰብሰብ፣ ሥርዓቱን ተጠግተው ለሚገኙ የተወሰኑ አካላት ሁነቱ "የአየር ባየር ባለሀብቶች" ማበልጸጊያ ሆኗል ብለዋል።
ይህ ተግባር በሕገ መንግሥት (አንቀጽ 40፣ 41፣ 89፣ 90፣ 91፣ 92) እና አዋጅ ቍ. 1161/2011 ዓ.ም በመሠረታዊነት የጣሰ ነው ሲሉም ፓርቲዎቹ በጋራ መግለጫቸው አሳስበዋል።
ስለሆነም መንግሥት በሕገ መንግሥቱ የተደነገገውን የዜጎች መብት እንዲያከብርና ማኅበረሰቡን መሠረታዊ በሆነ መልኩ የሚያስተጓጉል ተግባር ሊያቆም እንደሚገባ ተባባሪ ፓርቲዎቹ ገልጸዋል።
እንዲሁም የፈረሳው ሰለባ የሆነው የአዲስ አበባ ነዋሪ ድርጊቱን በሰላማዊ መንገድ በመቃወም ሕገ መንግሥታዊ መብቱን እንዲያስከብር ሲሉ ጠይቀዋል።
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
የውጭ ምንዛሬ መግዣ እና መሸጫ መካከል ያለው ልዩነት ከሁለት በመቶ እንዳይበልጥ ማሳሰብያ ተሰጠ
ጥቅምት 5/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ንግድ ባንኮች የውጭ ምንዛሬ በሚገዙበት እና በሚሸጡበት ዋጋ መካከል ያለው ልዩነት እንዲቀራረብ በማሰብ፤ ቢበዛ ከሁለት በመቶ መብለጥ እንደሌለበት አሳስቧል።
ይህንን በተመለከተም ለንግድ ባንኮች በደብዳቤ ማሳወቁን ብሔራዊ ባንክ ገልጿል።
አዲሱ የምንዛሬ ተመን አሰራር ይፋ መሆኑን ተከትሎ በውጭ ምንዛሬ ገበያው ላይ ያሉ ሂደቶችን ሲከታተል መቆየቱን የገለጸው ብሔራዊ ባንኩ፤ የንግድ ባንኮች የውጭ ምንዛሬ መግዣ እና መሸጫ መካከል ያለው ልዩነት በዓለም አቀፍ አሰራር መሰረት መሆን እንዳለበት አመላክቷል።
አሁንም ቢሆንም ባንኮች የምንዛሬ መግዣ እና መሸጫ ዋጋቸውን በራሳቸውና ከደንበኞቻቸው ጋር ባላቸው ስምምነት ማድረጋቸውን እንደሚቀጥሉም ጠቁሟል።
በተጨማተሪም ንግድ ባንኮች የምንዛሬ መግዣ እና መሸጫ ዋጋቸውን በተናጠል በየቀኑ ማሳወቃቸውን መቀጠል እንዳለባቸው ያሳሰበ ሲሆን፤ ባንኮች ከውጭ ምንዛሬ ሽያጭ ጋር በተያያዘ የሚጠይቋቸውን ኮሚሽኖች ከምንዛሬ መሸጫ ጋር ሳይሆን በተናጠል ለደንበኞቻቸው እንዲያሳውቁሞ ትዕዛዝ አስተላልፏል።
እስካሁን በነበረው አሰራርም ንግድ ባንኮች የምንዛሬ መሸጫ ዋጋቸውን ከኮሚሽኑ ጋር ደምረው ያስታውቁ እንደነበር ያስታወሰብ ባንኩ፤ ንግድ ባንኮች ሁለቱን ጉዳዮች እስከነገ ባለው ባለው ጊዜ ተግባራዊ እንዲያደርጉት አሳስቧል፡፡
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
በአዲስ አበባ ከ2.5 ሚሊዮን በላይ ነዋሪን የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ተጠቃሚ ለማድረግ ዕቅድ መያዙ ተገለጸ
ጥቅምት 5/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ በ2017 ዓ.ም ከ2.5 ሚሊዮን በላይ የከተማዋን ነዋሪ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህ ተጠቃሚ እንዲሆን ለማድረግ ዕቅድ መያዙን አስታውቋል።
ቢሮው ለዘርፉ በሰጠው ትኩረት ምክንያት ባለፉት ዓመታት በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎችን የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን የገለጸ ሲሆን፤ በዚህም በ2016 ዓ.ም ከ2.3 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የጤና መድህን አባል መሆናቸውን ተናግሯል።
እንዲሁም ከ2.5 ሚሊዮን በላይ አባላትና ቤተሰቦቻቸው በተመላላሽ እና በተኝቶ ሕክምና ከጤና ጣቢያ ጀምሮ እስከ ፌደራል ሆስፒታሎች ባሉ የጤና ተቋማት ተጠቃሚ ሆነዋል ብሏል።
የከተማ አስተዳደሩ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዩሐንስ ጫላ ትናንት ጥቅምት 4 ቀን 2017 በሰጡት መግለጫ፤ በ2017 ዓ.ም የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ነባር እና አዲስ አባላቶችን ሙሉ ለሙሉ እድሳታቸውን እንዲጨርሱ የጠየቁ ሲሆን፤ ከ10 በመቶ በላይ አዲስ አባላቶችን በመቀበል በአጠቃላይ ከ2.5 ሚሊዮን በላይ የከተማውን ነዋሪ ተጠቃሚ ለማድረግ ዕቅድ ተይዞ ወደ ሥራ መገባቱን ተናግረዋል።
አክለውም፤ የዘንድሮው የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን የነባርና የአዲስ አባላት ምዝገባ ከጥቅምት 1 እስከ ሕዳር 30 በሁሉም ክፍለ ከተሞች በሚገኙ ጤና ጣቢያዎች መጀመሩን ተናግረዋል።
የፀደቀው መዋጮ፦
👉 መደበኛ መዋጮ 1500 ብር ሲሆን፤ የድሀደሀ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ሙሉ በሙሉ በከተማ አስተዳደሩ መዋጮውን የሚሸፈን ይሆናል ተብሏል።
ይህም ማለት ነባር አባል መዋጮ 1500 ብር፣ በአዲስ አባል መዋጮ 1500 ብር እና የመመዝገቢያ 200 ብር በአጠቃላይ 1700 ብር ዓመታዊ መዋጮ ይከፍላል።
👉 ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ ለሆኑ ልጆች እና በአባሉ ጥላ ስር ለሚኖሩ ተጨማሪ ቤተሰብ 750 ብር የሚከፈል መሆኑም ተነግሯል።
በኢ-መደበኛ ክፍል ኢኮኖሚ የተሰማሩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተቀመጠውን መዋጮ በመክፈል ዓመቱን ሙሉ በሁሉም ውል በተገባባቸው የጤና ተቋማቶች አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ ተብሏል።
ሕብረተሰቡ የምዝገባ ጊዜው አጭር መሆኑን ተረድቶ ዛሬ ነገ ሳይል በሚኖርበት ወረዳ ጤና ጣቢያ በመሄድ ምዝገባ እንዲያደርግም የቢሮው ኃላፊ አሳስበዋል።
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
"የአዲስ አበባ ከተማ ሕዝብ በተጎሳቆለበት ሁኔታ ከተማይቱን ማስዋብ ፋይዳ የለውም" ኢህአፓ
👉ሕዝብን ወደ ቁጣ ከሚወስድ ድርጊት መንግሥት ሊቆጠብ ይገባል ሲልም ፓርቲው አሳስቧል
ጥቅምት 4/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ)፣ የአዲስ አበባ ኮሚቴ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ በዛሬው ዕለት መግለጫ ሰጥቷል፡፡
መግለጫው ሁለተኛው ዙር የኮሪደር ልማት በስፋት በሚካሄድባትና ከሰሞኑ በፈረሳ ምክንያት ቅሬታ ሲነሳበት በነበረው ካዛንቺስ አካባቢ በሚገኘው በፓርቲው ፅህፈት ቤት ነው የተሰጠው።
በመግለጫውም ሕዝቡ የሀገሩ ባለቤት መሆኑም ታውቆ፣ ሰብዓዊ መብቱ ተከብሮ መኖር መቻል አለበት የተባለ ሲሆን፤ ፓርቲው የሕዝቡ መብት ሊከበር ይገባል ሲል በጽኑ አሳስቧል፡፡
ከልማትና መዋብ በፊት የአዲስ አበባ ኗሪዎችም ሆኑ መላው የሀገራችን ዜጎች በልቶ ማደር እና ሠላምን ይፈልጋሉ ያሉት የኢህአፓ የአዲስ አበባ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አበበ አካሉ ናቸው።
ሰብሳቢው የሀገር ባለቤትነታቸውን አክብሮ፣ የከተማዋ ኗሪዎችን የተለያዩ ድጋፎች እያደረጉ ሠርተው እንዲበለጽጉ በማስቻል ፈንታ፣ ቤታቸውን አፍርሶ እያፈናቀሉ ሕዝብን ማማረር ተገቢ አይደለም ብለዋል፡፡
አዲስ አበባ ከሀገራችን ዋና ከተማነት በዘለለ የአፍሪካ ህብረት እንዲሁም የበርካታ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ድርጅቶችና ከፍተኛ ዲፕሎማቶች መቀመጫ በመሆኗ ዓለም አቀፍ ደረጃዋን ጠብቃ የመልማቷ ጉዳይ ለድርድር የሚቀርብ ጉዳይ አይደለም ያለው ፓርቲው፤ ይሁን እንጂ የከተማዋ ልማትና እድገት ከኗሪው ሕዝብ መብት መከበር፣ ከጥቅሞቹ መጠበቅ፣ ተነጥሎ የሚታይ ሊሆን አይገባም ብሏል።
በአሁኑ ወቅትም ሌላኛው ዙር የኮሪደር ልማት ከቀደመው ኗሪዎችን እጅግ የጎዱ ስሁትና ጎጂ ተግባሮችና አካሄዶች አንጻር በሚገባ ሳይጠናና የነዋሪውን ማህበረሰብ መብት በሚገፍ፣ ጥቅምና ፍላጎት ባላገናዘበና የኗሪዎችን ስምምነት ባላረጋገጠ መልኩ የሚደረግ ሊሆን አይገባም ሲልም በመግለጫው አስስቧል፡፡
ሕዝብን ወደ ቁጣ ከሚወስድ ድርጊት መንግሥት ሊቆጠብ ይገባል ያለው ኢህአፓ፤ ባለ አራት ነጥብ የአቋም መግለጫም አውጥቷል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሁለተኛው ዙር የኮሪደር ልማት በቅርቡ ወደ ስራ መግባቱንና በዚህኛው ዙር የኮሪደር ልማት 132 ኪሎ ሜትር እንደሚሸፍን መገለፁ አይዘነጋም፡፡
በአቤል ደጀኔ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
"ሀሰተኛ ማስረጃዎች ችግር ፈጥረውብኛል" የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
ጥቅምት 4/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ለዜጎች ፖስፖርት በመስጠት ሂደት ውስጥ፤ መሰረታዊ ማስረጃዎች ሀስተኛ ሰነድ እየቀረበባቸው እንደሚገኝ የኢሜሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ገለጸ።
የኢሜሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በትግራይ ተወላጆች ፓስፖርት ለማውጣት በሚሄዱበት ወቅት ከፍተኛ እንግልት እየደረሰባቸው ይገኛል̎ በሚል ለቀረበበት ክስ ምላሽ ሰጥቷል፡፡
ከዚህ ቀደም ቅድሚያ ለሰብዓዊ መብቶቸ በኢትዮጵያ የተሰኘ ሀገር በቀል የሰብዓዊ መብት ድርጅት በምርመራዬ አገኘሁት̎ ባለው የስድስት ወራት ሪፖርት ላይ፤ "የትግራይ ተወላጅ የሆኑ ዜጎች ፓስፖርት ለማውጣት ለእንግልት ተዳርገዋል" ሲል ገልጿል፡፡
"ፓስፖርት ለማውጣት የሚያስፈልገው መታወቂያ እና የልደት ካርድ ብቻ ቢሆንም፤ የትግራይ ተወላጅ የሆኑ ዜጎች ፓስፖርት ለመከልከል በሚመሰል መልኩ በርካታ ጥያቄዎቸ እየቀረበባችዉ ይገኛል" ሲሉም የድርጅቱ ምልክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ መብሪህ ብርሃኔ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
ይህንን በተመለከተ አሐዱ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊትን ጠይቋል፡፡
ዳይሬክተሯ በምላቸው፤ "ፓስፖርት ፈላጊዎች ኢትዮጵያዊ መሆናቸውንና አለመሆናቸውን ለማጣራት ዓለም አቀፍ ሕግጋትን በተከተለ መንገድ ማስረጃዎች አሟልቶ ያለመገኘት ሲኖር፤ ተጨማሪ ምርመራዎች ይደረጋሉ" ብለዋል፡፡
እነዚህ የሚያስፈልጉ መሰረታዊ ማስረጃዎች ሀሠተኛ ሰነድ እየቀረበባቸው ስለሆነ፤ ይህ ለሥራችን እንቅፋት ሆኖብናል ሲሉም ተናግረዋል፡፡
ዳይሬክተሯ አክለውም "የኢትዮጵያን ፓስፖርት የማይፈልግ የጎረቤት ሀገር የለም" ያሉ ሲሆን፤ "በተለምዶ ኤርትራዊ ይባላል እንጂ የሁሉም ጎረቤት ሀገራት ዜጎች የኢትዮጵያን ፓስፖርት ይፈልጉታል" ብለዋል፡፡
በመሆኑም እነዚህን ማጣሪያ ማድረግ አስፈላጊ ቢሆንም በወከባ መሆን የለበትም፡፡ ነገር ግን ጥራት ያለው ማስረጃ መቅረብ አለበት̎ ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በተቋሙ አገልግሎት ፈልገው ለሚሄዱ የትግራይ ተወላጆች "7 ቁጥር የተባለ ቢሮ ውስጥ ዜግነት እየተበየነበት ነው" ተብሎ መነሳቱም ይታወሳል። ይህንንም በተመለከተ ዋና ዳይሬክተሯ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
ተጨማሪ ማስረጃዎችን ለማቅረብ አንድ አንድ ቦታዎች የጸጥታ ችግር ሊኖር ይችላል̎ ያሉት ዳይሬክተሯ፤ እነዚህን ሲገጥሙ በምን መንገድ መፍታት አለበት የሚለውን እየሰራንበት እንገኛል ሲሉ አስረድተዋል፡፡
ቅድሚያ ለሰብዓዊ መብቶች በኢትዮጵያ ከትግራይ ተወላጆች በተጨማሪ ከሶማሌ ክልል የሚመጡ ላይም በቋንቋ ምክንያት እንግልት እንደሚያደርስ ገልጿል፡፡
ቅድሚ ለሰብዓዊ መብቶች ይህንን የዜግነት መብት የሚገፍ አሰራር እንዲታረም ካልሆነ ግን ጉዳዩ መሰረታዊ የዜጎች መብት ጥሰት በመሆኑ በፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 መሰረት ወደ ፍ/ቤት እንደሚወስደው ለአሐዱ መግለጹም አይዘነጋም፡፡
በተያያዘ ዜና ቤት ለቤት ፖስፖርት አገልገሎት መስጠትን በዚህ ዓመት እንደሚጀመር የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት ተናግረዋል፡፡
ተቋማቸው ከእጅ ንክኪ ነፃ የሆነ አገልግሎት ለመስጠት እየሰራ መሆኑን ገለጸው፤ እስካሁን ባለዉ ከክፍያዎች ጋር በተያያዘ በዲጂታል መንገድ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
ነገር ግን ይህ መተግበሪያዎችን ተጠቅሞ ክፍያዎችን መፈፀም ላይ ክልሎች ላይ ክፍተት መኖሩን ሰላማዊት ዳዊት አስታዉቀዋል።
ቤት ለቤት ፖስፖርት የማሰረጨቱ ሂደት ግን ሲስተም ላይ የገባ ሲሆን፤ በዚህ ዓመት ወደ ሥራ ይገባል ብለዋል።
ይህንን አገልግሎት ለመጠቀምም ስልክ ቁጥርና አድራሻ በማስገባት አገልግሎቱን መጠቀም ይቻላል ብለዋል።
በተጨማሪም የኢ-ፖስፖርት ምርትንም ያነሱት ዳይሬክሯ ምርት መጀመሩን በመግለጽ በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት ወደ ሥራ እንደሚገባ ለአሐዱ ተናግረዋል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ ህብረተሰቡ ተመሳሰለዉ ከተሰሩ ዌብሳይቶችና ማህበራዊ ሚዲያ ፕላትፎርሞች እራሱን መጠበቅ አለበት ያሉት ዋና ዳይሬክተሯ፤ ̎በርካታ ሀሰተኛ መረጃዎች እየተሰራጩብን ነዉ̎ ሲሉም ገልጸዋል።
በአቤል ደጀኔ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
እነ ዮሃንስ ዳንኤል የቀረበባቸው የክስ ዝርዝር እንዲሻሻል የክስ መቃወሚያ አቀረቡ
ጥቅምት 4/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ አየር መንገድን ደህንነት አደጋ ላይ ለመጣል በመንቀሳቀስ የተከሰሱ ስድስት ግለሰቦች ክሱ እንዲሻሻል የመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያ አቀርበዋል።
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሕገ መንግሥትና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት የቀረበውን የክስ መቃወሚያ መርምሮ ብይን ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
በዛሬው ቀጠሮ የክስ መቃወሚያቸውን በጠበቆቻቸው አማካኝነት ያቀረቡት ተከሳሾቹ፤ ዮሃንስ ዳንኤል (ጆን ዳንኤል)፣ አማኑኤል መውጫ፣ ናትናኤል ወንድወሰን፣ ኤልያስ ድሪባ፣ ይዲድያ ነጻነት እና እሌኒ ክንፈ ናቸው።
የፍትህ ሚኒስቴር የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ዐቃቤ ሕግ በነ ዮሃንስ ዳንኤል መዝገብ በስድስት ተከሳሾች ላይ አውሮፕላንን ያለአግባብ መያዝ ወንጀል፣ የመንግሥት ሰራተኛ የሥራ ግዴታውን እንዳይፈጽም መቃወምና አለመታዘዝ ወንጀል ክስ በተጨማሪም በ1ኛ ተከሳሽ ብቻ ደግሞ የአየር መንገዱን መልካም ሥም ለሚያጎድፍ በተንቀሳቃሽ ምስል በኮምፒዩተር ስርዓት አማካኝነት ማሰራጨት ወንጀል የሚል ክስ ማቅረቡ ይታወሳል።
ተከሳሾቹ የክሱ ዝርዝር ከደረሳቸው በኋላ ያቀረቡት የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ተደርጎ በማረሚያ ቤት ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ በተሰጠ ትዕዛዝ መሰረት ዛሬ ከማረሚያ ቤት ቀርበው ጉዳያቸውን ተከታትለዋል።
በዚህም የተከሳሽ ጠበቆች የክስ ዝርዝሩ እንዲሻሻል የመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያ በጽሁፍ አቅርበዋል።
ፍርድ ቤቱ በተከሳሾች በኩል በቀረበው የክስ መቃወሚያን በሚመለከት ዐቃቤ ሕግ ከቀጠሮ በፊት መልሱን (አስተያየቱን) በሬጅስትራር በኩል እንዲያቀርብ በማለት በአጠቃላይ በመቃወሚያው ላይ መርምሮ ብይን ለመስጠት ለጥቅምት 21 ቀን 2017 ዓ.ም መቀጠሩን ኤፍቢሲ ዘግቧል።
ተከሳሾቹ ከዚህ ቀደም በስር ፍርድ ቤት የዋስትና ጥያቄያቸው ውድቅ መደረጉን ተከትሎ፤ ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ይግባኝ ጠይቀው ጉዳያቸው በሂደት ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል።
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ኢትዮጵያ በውስጥ ችግሮቿ በተጠመደችበት ወቅት አጋጣሚውን ለመጠቀም የሚጥሩ ሀገራት እንደሚኖሩ መገንዘብ ያስፈልጋል ተባለ
ጥቅምት 4/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ኢትዮጵያ በውስጥ ችግሮቿን ለመፍታት በተጠመደችበት በአሁኑ ወቅት፤ ይህን አጋጣሚ ለመጠቀም ጥረት የሚያደርጉ ሀገራት እንደሚኖሩ መገንዘብ ያስፈልጋል ሲሉ የሕግ ባለሙያዎች ለአሐዱ ገልጸዋል፡፡
ከቀናት በፊት የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሃሰን ሼክ መሃመድ እንዲሁም የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አል ሲሲ በአስመራ ተገኝተው ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ውይይት ማድረጋቸው ይታወቃል።
በውይይታቸውም የሶማሊያን ሉዓላዊነት፣ የግዛት አንድነትን እና ነፃነትን በማስጠበቅ ትብብራቸውን ማጠናከር እንደሚገባ አንስተዋል።
ኢትዮጵያ ቀድሞም ከግብጽ ጋር የነበራት ቅራኔ፤ እንዲሁም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ከሶማሊያና ኤርትራ ያላት ግንኙነት መሻከሩ ይታወቃል።
̎ኢትዮጵያ በበርካታ የውስጥ ችግሮቿ በተጠመደችበት ወቅት የሦስቱ ሀገራት ግንኙትና ጥምረት መጥበቁ በተለይም ግብጽ ከድሮም የነበራት ቅሬታ ጋር ተያይዞ አጋጣሚውን ለመጠቀም ይመስላል̎ የሚሉት የቀድሞ ዲፕሎማት እና የሕግ ባለሙያው ዶክተር ተሻለ ሰብሮ ናቸው።
̎የኤርትራ መንግሥት ካለፈው ስህተቱ መማር ይገባዋል̎ የሚሉት ዶ/ር ተሻለ የኢትዮጵያ መንግሥት የሀገራቱን ጎረቤትነት ጠብቆ ለማቆየት ነገሮችን በአንክሮ መመልከትና መታገስ አስፈላጊ ነው ብለዋል።
̎አንድ ሀገር ከሌላ ሀገር ጋር ግንኑነት ማድረግ መብታቸውም ነው፡፡ መከልከልም አይቻልም̎ የሚሉት የፖለቲካ ሳይንስ እና አለማቀፍ ግንኙነት መምህር ፕሮፌሰር አለሙ አራጌ ሲሆኑ፤ አሁን ባለው ሁኔታ ግን የሦስቱ ሀገራት ግንኙነት አሉታዊ ተጽዕኖ ይኖረዋል ይላሉ።
̎የኢትዮጵያ መንግሥት በኤርትራና ሶማሊያ መካከል ያለው ዲፕሎማሲያዊ ግንኑነት እንዲጠናከር ያበረከተችው አስተዋጽጾ መረሳት የለበትም ሲሉም አክለዋል፡፡
በቀደመው ጊዜ ኤርትራ ከኢትዮጵያ እንድትገነጠል በማድረጉ ረገድ የግብጽ ሚና እንደነበረት ያነሱት ምሁራኑ፤ ዛሬም ነገሮችን ከዝምታ ባሻገር በትኩረት መመልከተና መፍትሔ መፈለግ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።
በፍርቱና ወልደአብ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ