በድርቅ ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚደረገው ድጋፍ በቂ አለመሆኑ ተገለጸ፡፡
ይህንን ያለው የሶማሌ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሲሆን ካለፈው 2014ዓ.ም አንስቶ በክልሉ 7 ወረዳዎች የተከሰተውን ድርቅ ተከትሎ በርካታ ዜጎች መፈናቀላቸውን በመጥቀስ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ነዋሪዎችም ተረጂ ለመሆን ተገድደዋል፡፡
በቢሮው የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሃላፊ የሆኑት አቶ አብዱልቃድር ኢብራሂምም ምንም እንኳን በድርቁ ምክንያት የተፈናቀሉ ወገኖች መሰረታዊ ሰብአዊ እርዳታዎች እየተደረጉላቸው ቢሆንም በቂ አለመሆኑን ነው የገለጹት፡፡
ተፈናቃዮችን ለመደገፍ ከክልሉና ከፌደራሉ መንግስት እንዲሁም በርካታ አለማቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች በኩል ድጋፍ እየተደረገ ነው ያሉት ሃላፊው አሁን ላይ ድርቁ ያለባቸው ወረዳዎች አሃዝ ወደ 4 ዝቅ ያለ ቢሆንም በርካታ እርዳታ ፈላጊ ወገኖች አሉ ነው ያሉት፡፡
አሁን ላይ የእርዳታውን መጠን ለማሳደግ ሰፊ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነም ገልጸው ድርቁን ተከትሎ በክልሉ ሲቲ ዞን የተከሰተውን የኮሌራ ወረርሽኝም ክትባት በመስጠትና የንጽህና አጠባበቅ ሁነትን በማሻሻል የመቆጣጠር ስራ እየተሰራ እንደሆነም አክለዋል፡፡
የሶማሌ ክልልን ጨምሮ በሃገሪቱ በአፋር ፣ ኦሮምያ 4 ዞኖች እንዲሁም የደቡብ ክልል 2 ዞኖች ካለፈው አመት አጋማሽ አንስቶ ድርቅ የታየባቸው አካባቢዎች መሆናቸው ይታወቃል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/ahadutelevision
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቴሌግራም፡- /channel/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en