የቡርኪናፋሶ ወታደራዊ መንግሥት ኢዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር መሾሙ ተገለጸ
ሕዳር 30/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የቡርኪናፋሶ ወታደራዊ መንግሥት የሀገሪቱን ጊዜያዊ ጠቅላይ ሚኒስትር አፖሊኒየር ጆቺም ኬለም ደ ታምቤላ ከስልጣናቸው በማንሳት ዣን ኢማኑኤል ኦውድራጎን ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ መሾሙ ተገልጿል።
ሀገሪቱን በወታደራዊ አገዛዝ እያስተዳደሩ የሚገኙት ኢብራሂም ትራኦሪ፤ "እርምጃዉ ቀጣይነት እና ታአማኒነት ያለዉ መንግሥት ለመመስረት ያለመ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።
በጠቅላይ ሚኒስትርነት ማዕረግ የተሾሙት ኦውድራጎ ከዚህ ቀደም፤ በጋዜጠኛነት እና የዜና አዘጋጅ፣ እንዲሁም በወታደራዊ መንግሥቱ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ላይ ሚኒስትር ዴኤታ ሆነዉ ማገልገላቸዉ ተነግሯል።
በተደጋጋሚ ጊዜያት የመንግሥት ግልበጣ በተደረገባት ቡርኪናፋሶ በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጡት ፕሬዝዳንት ሮች ማርክ ካቦሬ በሌተናል ኮሎኔል ፖል ሄንሪ ሳንዳጎ ከስልጣናቸው መነሳታቸው ይታወሳል።
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን ተወሰነ
ሕዳር 30/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተውጣጡ ባለሙያዎች የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን የምግብ ሜኑ ተቀራራቢ እንዲሆን እየሰሩ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።
ወቅታዊውን የምግብ ዋጋ መጨመር መነሻ በማድረግ ትምህርት ሚኒስቴር ጥናት ማድረጉን የገለጸ ሲሆን፤ በጥናቱ ውጤት መነሻነትም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ በጀት በቀን ወደ 100 ብር ከፍ እንዲል መደረጉን አስታውቋል።
በተደረገው የበጀት ማሻሻያ መሰረት በተቋማቱ የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን በባለሙያዎች ሥራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ ተገልጿል።
በትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳደርና መሰረተ ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ሰለሞን አብርሃ፤ ወቅታዊ የምግብ ዋጋ ንረትን ግምት ውስጥ በማስገባት የምግብ በጀት ማሰተካከያ መደረጉን ገልጸዋል።
ዶ/ር ሰለሞን አክለውም በሀገሪቷ ባሉ ዩኒቨርስቲዎች ያለው የምግብ ሜኑ ተቀራራቢ እንዲሆን እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው፤ በአዲሱ የበጀት ተመን መሰረት ለዩኒቨርስቲዎቹ ባላቸው ተማሪ ቁጥር ልክ ገንዘቡ እንደሚለቀቅላቸው ጠቁመዋል።
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ለካዛንችስ የልማት ተነሺዎች በገላን ጉራ የተገነባው የመኖሪያ መንደር አገልግሎት መስጠት ጀመረ
ሕዳር 30/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ለካዛንችስ የልማት ተነሺዎች በገላን ጉራ የተገነባውና በ1200 መኖሪያ ቤቶች 6500 ነዎሪዎችን የያዘው የመኖሪያ መንደር አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታውቀዋል፡፡
"አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ አበባ እናደርጋታለን" የሚለው አባባል የነዋሪዎቿን ሕይወት ማሳመርንም ያካትታል ያሉት ከንቲባ አዳነች፤ የከተማዋ አስተዳደር ለካዛንችስ የልማት ተነሺዎች በገላን ጉራ የገነባውን የመኖሪያ እና የተቀናጀ የልማት መንደርን በማሳያነት ጠቅሰዋል።
ይህ ዛሬ አገልግሎት መስጠት የሚጀምረው የገላን ጉራ የመኖሪያ እና የተቀናጀ የልማት መንደር በውስጡ፦
👉 በ1200 መኖሪያ ቤቶች 6500 ነዎሪዎችን የያዘ የመኖሪያ መንደር ነው።
👉 1.6 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የአስፋልት መንገድ፣
👉 ከ20 በላይ አውቶቡሶችን በአንድ ጊዜ ማስተናገድ የሚያስችል ተርሚናል፣
👉 በ2 ወር ጊዜ ውስጥ የተገነቡ ከቅድመ አንደኛ ደረጃ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ያሉ ትምህርት ቤቶች ከምገባ ማዕከል፣
👉 በ3 ሺፍት ለ270 እናቶች የሥራ ዕድል የፈጠረ የእንጀራ መጋገሪያ ፋብሪካ፣
👉 500 አረጋውያን እና አቅመ ደካሞችን በቀን አንድ ጊዜ መመገብ የሚያስችል የምገባ ማዕከል፣
👉 በቀን 60 ሺሕ ዳቦ የማምረት አቅም ያለው የዳቦ ፋብሪካ እና የእህል ወፍጮዎች፣
👉 ደረጃውን የጠበቀ የሕጻናት መጫወቻ እና የሕጻናት ማቆያ፣
👉 ሁለት የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እንዲሁም አረንጓዴ ቦታዎችና መናፈሻዎች ተገንብውለታል።
👉 የተቀናጀ የልማት መንደሩ በቋሚነት እና በጊዜያዊነት ለ1 ሺሕ 646 ነዋሪዎች የሥራ ዕድል መፍጠሩንም ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው አስታውቀዋል።
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
በሶማሌ ክልል 450 ሺሕ የሚሆኑ ሕጻናት ክትባት አለመውሰዳቸውን የክልሉ ጤና ቢሮ ገለጸ
ሕዳር 30/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በሶማሌ ክልል 450 ሺሕ የሚሆኑ ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ሕጻናት ክትባት አለመውሰዳቸውን የክልሉ ጤና ቢሮ ለአሐዱ ገልጿል።
የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ማህሙድ መሃመድ፤ "ሕጻናቱ ክትባቱን እንዳያገኙ ካደረጓቸው ምክንያቶች ውስጥ አንዱ የማህብረሰቡ አኗኗር ዘይቤ ተንቀሳቃሽ በመሆኑ ነው" ብለዋል።
ስለሆነም ቢሮው ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ ሕጻናት ክትባት ተደራሽ ለማድረግ የተለያዩ እቅዶችን መያዙን ምክትል ኃላፊው ገልጸዋል።
በዚህም የክትባት አገልግሎትን ከጤና ጣቢያዎች እና የጤና ኬላዎች ባላቸው ርቀት ምክንያት ተድራሽ ባለመሆኑ፤ ከማዕከሎቹ ውጪ አገልግሎት ለመሰጠት አርሶ አደር ለሆነው ማህበረሰብ ተከታታይ በሆነ ዘመቻ ክትባት መሰጥቱን አንስተዋል።
በዚህ መንገድ ከ400 ሺሕ ሕጻናት ውስጥ 100 ሺሕ የሚሆኑ ሕጻናትን መከተብ መቻሉን ምክትል ኃላፊው ማህሙድ ገልጸዋል።
የተቀሩትን ሕጻናትን ለመከተብ እቅዶች መያዛቸውን ጠቁመው፤ በአጠቃላይ የጤና አገልግሎት አሰጣጡ የአካባቢውን አኗኗር ባገናዘበ መልኩ ተንቀሳቃሽ የሕክምና ቡድኖች መኖራቸውንም ለአሐዱ ተናግረዋል።
የዓለም አቀፍ ተራድዓ ድርጅት የሆነው ሴቭ ዘ ችልድረን ይፋ ባደረገው መረጃ፤ ኦሮሚያ፣ አማራ እና ሶማሊያ ክልሎች ከሌሎቹ ክልሎች ከፍ ባለ መልኩ ያለተከተቡ ሕጻናት ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን መግለጹ ይታወሳል።
የጤና ሚኒስቴር በሀገር አቀፍ ደረጃ በተደረገው ጥናት ባለፈው ዓመት ብቻ 1 ሚሊየን ሕጻናት ምንም አይነት ክትባት አለመውሰዳቸውን ገልጿል።
በፍርቱና ወልደአብ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
#ADVERTISMENT
#AmharaBank
የአማራ ባንክ አ/ማ የባለአክሲዮኖች 3ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ማክሰኞ ታህሳስ 01 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ በሚሊኒየም አዳራሽ ስለሚካሄድ ባለአክሲዮኖች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጉባዔው እንድትገኙ ጥሪ እናስተላልፋለን፡፡
የጉባዔው አጀንዳዎችን እና ተጨማሪ መረጃዎችን ጥቅምት 06 ቀን 2017 ዓ.ም በወጡት አዲስ ዘመን እና ሪፖርተር አማርኛ እትም ጋዜጦች ላይ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ለበለጠ መረጃ ነፃ የጥሪ ማዕከል 690 ወይም
የባንኩን ድረ ገጽ www.amharabank.com.et ይጎብኙ፡፡
አማራ ባንክ
ከባንክ ባሻገር!
የአማራ ባንክ ትክክለኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾች
Website: www.amharabank.com
Facebook: www.Facebook.com/amharabanksc1
Telegram: /channel/Amhara_Banksc
Instagram: https://instagram.com/amhara_bank
Twitter: https://twitter.com/Amharabanksc
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/amharabank/
YouTube: https://youtube.com/channel/UC73x9uuGYV0Uxw0EkpVZN8g
TikTok: amharabanks.c" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@amharabanks.c
#አማራባንክ #AmharaBank
#አሐዱ_ሳድስ
"የኢራን ጦር ዝግጅት" በአብይ ይልማ
ሙሉውን ለመከታተል ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👇
https://youtu.be/C_NWSre4vro?si=BLcSD-Q94LN7iquZ
የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ሌላ የጋራ ምክር ቤት ለመመስረት ማሰቡን አስታወቀ
👉 ፓርቲው "የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ፈርሷል" ብሎ እንደሚያምን ገልጿል
ሕዳር 29/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ሕዳር 7 እና 8 ቀን 2017 ዓ.ም. ጠቅላላ ጉባኤውን አድርጎ መሪዎቹን የመረጠውን የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት 'ፈርሷል' ብሎ እንደሚያምንም አስታውቋል፡፡
ኢሕአፓ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች ላይ ያለውን ቅሬታ በተደጋጋሚ ሲገልፅ የቆየ ሲሆን፤ ጠይቋቸውና እንዲስተካከሉ የሚፈልጋቸው ነገሮች ካለተሳኩ በቀጣይ የሚደርስበትን ውሳኔ እንደሚያሳወቅ ገልጿል፡፡
የኢሕአፓ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት መጋቢ ብሉይ አብርሃም ሐይማኖት ከአሐዱ መድረክ ጋር በነበራቸው ቆይታ "ከዚህ ቀደም በምክር ቤቱ ሥር በመሆን ብዙ ጥረቶችን አድርገናል" ያሉ ሲሆን፤ "ነገር ግን በምንፈልገው መንገድ ሊመጣ አልቻለም" ሲሉ ተናግረዋል፡፡
"ይህንን በመገንዘብና የተለያዩ የሕግ ጥሰቶች የነበሩ በመሆኑ፤ ምክር ቤቱ አላግባብ ስልጣን ላይ በመቆየትና የምርጫ ጊዜውን በማራዘም ተጉዟል" ያሉት ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበሩ፤ "ለዚህ እንደ ምክንያት የቀረበው የፋይናስ ጉዳይ ተቀባይነት የሌለው ነው" ሲሉ ገልጸዋል፡፡
"የጋራ ምክር ቤቱ በምንፈልገው መንገድ ባለመሄዱና ጉዳዩንም ወደ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በመውሰድ ምክር ቤቱን እዲያድነው ጥረት ቢደረግም መፍትሄ ሳይሰጥ ጠቅላላ ጉባኤው መካሄዱ አግባብነት የለውም" ሲሉም ተናግረዋል፡፡
የኢትጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ)ን ጨምሮ አምስት የሚሆኑ ፓርቲዎች በጋራ ምክር ቤቱ ላይ ቅሬታ ከሚያነሱበት ጉዳይ አንዱ፤ የጋራ ምክር ቤቱ ያለምንም ምርጫ የብልፅግና ፓርቲ በሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ላይ መካተቱ መሆኑንም መጋቢ አብርሃም በቆይታቸው አንስተውታል፡፡
"የጋራ ምክር ቤቱ ለጋዜጠኞችና ለፖቲከኞችም ድምፅ መሆን አልቻለም" የሚሉት ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበሩ፤ በተለይም እርሳቸውን ጨምሮ የፓርቲያቸው ሊቀመንበር 'ሰላም ይሰፈን ጦርነት ይቁም' በሚል በጠሩት ሰልፍ መታሰራቸውን በማንሳት ምክር ቤቱ ደምጽ መሆን አለመቻሉን ኮንነዋል፡፡
አሐዱም "በኢትዮጵያ የጋራ ምክር ቤት ላይ ያላችሁን ቅሬታ መነሻ በማድረግ ሌላ የተቃዋሚዎች የጋራ ምክር ቤት ታቋቋማላችሁ ወይ?" ሲል ጠይቋል፡፡
በምላሻቸውም በቀጣይ በሚደረግ ውይይት የሚወሰን መሆኑን በማንሳት፤ ነገር ግን ሀሳብ እንዳላቸው ሳይሸሽጉ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
"ኢሕአፓም ሆኑ ሌሎች ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤቱ እንዲፈርስ ፍላጎት የላቸውም" ያሉም ሲሆን፤ "አሁን ግን ፈርሷል ብለን የምናምነውን የጋራ ምክር ቤት ለማዳን ነው እየሰራን የምንገኘው" ብለዋል፡፡
👉 መጋቢ ብሉይ አብርሃም ሐይማኖት ከአሐዱ መድረክ ጋር ያደረጉትን ሙሉ ቆይታ ለመከታተል ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👇https://youtu.be/2QzAwsNg6co?si=tRQ6aWwyZLrXFNQO
በአቤል ደጀኔ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
አዲስ አበባን ጨምሮ በመላው የሀገሪቱ አካባቢዎች የኤሌትሪክ ኃይል መቆራረጥ ማጋጠሙ ተገለጸ
ሕዳር 28/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ዛሬ ምሽት ከ12 ሰዓት በኃላ አዲስ አበባን ጨምሮ በመላው የሀገሪቱ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጧል።
አሐዱም በክልሎች ባደረገዉ ማጣራት ሀዋሳ፣ ጅማ ባህርዳር፣ ትግራይ፣ በጉራጌ ዞን እና ሌሎች አካባቢዎች ላይ በተመሳሳይ ሰዓት ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ የሃይል አቅርቦቱ መቋረጡን ለማወቅ ችላሏ።
የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ አገልግሎት ማምሻውን ባወጣው መረጃ፤ "ዛሬ ማምሻውን በሲስተም አለመረጋጋት በተፈጠረ ችግር የተነሳ በመላው ሀገሪቱ የኃይል መቋረጥ" ማጋጠሙን አስታውቋል።
የተቋረጠውን ኃይል ወደነበረበት ለመመለስ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል በኩል ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ መሆኑንም ገልጿል።
አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
#አሐዱ_መድረክ
"ከብልፅግና በላይ ብልፅግና እንሁን የሚሉ ፓርቲዎች አሉ" ከኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር መጋቢ ብሉይ አብርሃም ሐይማኖት ጋር የተደረገ ቆይታ (ክፍል 1)
ቆይታውን ለመከታተል ከሥር ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ!
👇
https://youtu.be/A2MVQiNKxl4?si=hB0cfdjYzEs4feQZ
ኮሚሽኑ በትግራይ ክልል ሀገራዊ የምክክር ሥራ ለመጀመር ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፍቃድ ማግኘቱን አስታወቀ
ሕዳር 28/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በትግራይ ክልል ለውይይትም ሆነ የተሳታፊ ልየታ ለማድረግ ተደጋጋሚ ሙከራዎችን ሲያደረግ ቢቆይም፤ ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ፍቃድ አለማግኘቱን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን መግለጹን አሐዱ መዘገቡ ይታወሳል፡፡
አሁን ላይ ከጊዜያዊ ከአስተዳደሩ ፍቃድ መገኘቱንና በቅርቡ ሥራ እንደሚጀር የተናገሩት የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ናቸው፡፡
ክልሉ ምክክር ለማድረግ ፍላጎት እንዳለው የገለጹት ፕሮፌሰር መስፍን፤ ምክክሩ ከፕሪቶሪያው የሰላምም ስምምነት ጋር በተያያዘ ተፈፃሚ እንዲሆን ጥያቄዎች መኖራቸውን ተናግረዋል፡፡
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ሲገለጽ እንደቆየው፤ ከታጣቂ ሃይሎች ጋር ውይይት ለማድረግ ፍላጎት እንዳለውና ሥራዎችን እየሰራ ቢሆንም ሳይሳካለት መቅረቱን ለአሐዱ ገልጸዋል፡፡
ዋና ኮሚሽነሩ አክለውም፤ በቤንሻንጉል ጉምዝ እና በጋምቤላ ክልል አጀንዳ የማሰባሰቡ ሥራ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ቢሆን ኮሚሽኑ ሂደቱን ማሳካቱን በመግለጽ፤ በምዕራብ ኦሮሚያም መሰል ሥራ የመስራት ፍላጎት እንዳለው ተናግረዋል፡፡
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአማራ ክልል አጀንዳ የማሰባሰብ ሥራውን የሚያግዙ አካላትን መረጣ ያካሄደ ሲሆን፤ በትግራይ ክልል ግን ምንም ዓይነት ሥራ አለመጀመሩ ይታወቃል፡፡
በአቤል ደጀኔ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ:www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡-https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
ቲክቶክ ለአሜሪካ ኩባንያ እንዲሸጥ ወይንም በሀገሪቱ አገልግሎት ከመስጠት እንዲታገድ የሚስገድድ ሕግ ወጣ
ሕዳር 28/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የአሜሪካ የፌደራል ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በቻይና በተመሰረተው ባይትዳንስ ኩባንያ ሥር የሚገኘው የቲክ ቶክ መተግበሪያ፤ በሚቀጥለው ዓመት መጀመሪያ ላይ እንዲሸጥ ወይም እገዳ እንዲጣልበት የሚያስገድድ ውሳኔ አፅድቋል።
ውሳኔው ለአሜሪካ የፍትህ ሚኒስቴር እና ለመተግበሪያው ተቃዋሚዎች ትልቅ ድል እንደሆነና ለቲክቶክ ደግሞ፤ ከባድ ኪሳራን ሊያስከትል እንደሚችል ተመላክቷል፡፡
ውሳኔውን ተከትሎም የፍትህ ሚኒስቴሩ ኃላፊዎች "ውሳኔው ቻይና በአሜሪካ ብሔራዊ ደህንነቶች ላይ የደቀነቻቸውን ስጋቶች ለመዋጋት ዴሞክራት እና ሪፐብሊካኖች ተመሳሳይ አቋም እንዳላቸው አመላካች ነው" ማለታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
በአሜሪካ 170 ሚሊዮን የሚደርሱ ተጠቃሚዎች ያሉት ቲክ ቶክ፤ "የዜጎችን ግላዊ መረጃዎች ለቻይና መንግሥት አሳልፎ ይሰጣል" በሚል ለቀረበበት ክስ ያቀረበው ይግባኝ ውድቅ በመደረጉ ውሳኔው መተላለፉ ነው የተነገረው፡፡
ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ሜሪክ ጋርላንድ ውሳኔው "የቻይና መንግሥት ቲክቶክን በመሳሪያነት እንዳይጠቀም ለማድረግ አስፈላጊ እርምጃ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።
በዋሽንግተን የሚገኘው የቻይና ኤምባሲ በበኩሉ፤ "አይን ያወጣ የንግድ ዘረፋ ነው" ሲል ውሳኔውን የተቃወመው ሲሆን፤ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን መተማመንና ግንኙነት እንዳይጎዳ አሜሪካ ጉዳዩን በጥንቃቄ መያዝ እንዳለባት አስጠንቅቋል።
የቲክ ቶክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሾው ዚ ቼው ለሮይተርስ በላኩት ኢሜል፤ "የዛሬው ዜና ተስፋ አስቆራጭ ቢሆንም የመናገር ነፃነትን ለመጠበቅ ትግሉን እንደምንቀጥል ለማረጋገጥ እንወዳለን" ማለታቸውን ዘገባው አመላክቷል፡፡
መተግበርያው ለአሜሪካ ኩባንያዎች ከመሸጥ ይልቅ መታገድ መምረጡን ተከትሎም፤ በሚቀጥሉት 6 ሳምንታት ውስጥ በአሜሪካ መስራት ሊያቆም እንደሚችል ተነግሯል፡፡
የባይት ዳንስ ኩባንያ ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዓለ ሲመታቸው ከመከናወኑ አንድ ቀን በፊት ውሳኔውን ካላሳወቀ የእግድ አደጋ እንደተጋረጠበት የተገለጸ ሲሆን፤ ኩባንያው በመጪዎቹ ቀናት ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ለማለት ማቀቀዱም ተነግሯል፡፡
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ቱርክ በአፍሪካ ቀንድ የምታደርገው እንቅስቃሴ ለኢትዮጵያ ስጋት ሊሆን አይገባም ሲሉ ምሁራን ገለጹ
ሕዳር 28/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በአለም ዓቀፍ ግንኙነት ላይ የመደራደር አቅምን ማሳደግ እንጂ፤ ቱርክ በአፍሪካ ቀንድ የምታደርገው እንቅስቃሴ ለኢትዮጵያ ስጋት ሊሆን እንደማይገባ ምሁራን ገልጸዋል።
ቱርክ በኢትዮጵያ እና ሱማሊያ መሀከል የተፈጠረውን የባሕር በር ውዝግብ እንዲሁም ኢትዮጵያ ከሶማሌ ላንድ ጋር የተፈራረመችውን የመግባባቢያ ስምምነት ተፈጻሚነት እና ውጥረትን በተመለከተ መፍትሄ የማፈላለግ ጥረቷን እንደምትገፋበት ማስታወቋ አይዘነጋም።
ይሁን እንጂ ቱርክ ከቀጠናው አባል ሀገራት ጋር የተለያዩ ወታደራዊ ግንኙነቶችን ስታደርግ ይስተዋላል። "በተለይም ለሶማሊያ የጦር መሳሪያ የማቅረብ እንዲሁም ወታደርን እስከ ማሰልጠን መድረሷ የኢትዮጵያ ደህንነት እና የወደብ ጥያቄ ላይ ተጽዕኖ አይፈጥርም ወይ?" ሲል አሐዱ የአለም ዓቀፍ ግንኙነት ምሁራንን ጠይቋል።
ከዚህ ጋር ተያይዞ ቱርክ በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መሀከል ያለዉን የባህር በር ዉዝግብ ለማደራደር ብትሞክርም፤ ከሁለቱም ሀገራት ጋር የቆየ ወታደራዊ እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ግንኙነቶች ያላት መሆኑን የገለጹት የቀድሞ ዲፕሎማት ዳያሞ ዳሌ ናቸው።
አክለውም ቱርክ እንደ ማንኛዉም ሀገር ጥቅሟን ከማስከበር አንጻር እንደምትመለከተው ሁሉ፤ እንዲሁ ኢትዮጵያም የዲፕሎማሲ ጥቅሟን እና ግንኙነቷን ማጠናከር እና የቀጠናውን እንቅስቃሴ በትኩረት ልታየው እንደሚገባ ገልጸዋል።
በተጨማሪም ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅምን ለማስከበር የምትከተለውን የውጭ ፓሊሲ እንደየአካሄዳቸዉ ማስተካከል እና ማሻሻል እንደሚገባት የቀድሞ ዲፕሎማት ዳያሞ ዳሌ አሳስበዋል።
የቀድሞ አምባሳደር ጥሩነህ ዜናዉ በበኩላቸው፤ "ኢትዮጵያ የወደብ ጥያቄዋን ለማስመለስ ከቀጠናው ሀገራት እንዲሁም ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያላትን መልካም ግንኙት ከማጠናከር እና የተለያዩ ኢኮኖሚያዊ ፓለቲካዊ እና ቀጠናዊ ትስስርን ከመፍጠር አንጻር 'እንዴት የመደራደር አቅምን ማሳደግ እንዲሁም ቀጠናዊ ትስስርን እንዴት መፍጠር እችላለሁ' የሚለዉ እንጂ ቱርክ በቀጠናው እያደረገች ያለዉ እንቅስቃሴ ሊያሳሳስበን አይገባም" ብለዋል።
ምሁራኑ አክለውም ቱርክ በአፍሪካ ቀንድ እና በቀጠናው የምታደርገው እንቅስቃሴ እና የማደራደር ሚናዎች ከኢኮኖሚያዊ እና ፓለቲካዊ ጥቅም አንጻር ቢታዩም ኢትዮጵያም የጦር መሳሪያዎችን ስታቀርብ የነበረች ሀገር ከመሆኗ አንጻር እንዲሁም ከሁሉም ሀገራት ጋር የቆየ ታሪካዋ ወዳጅነት አላት ያሉ ሲሆን፤ "ከሶማሊያ ጋር ወታደራዊ ግንኙነት መፍጠሯ የሚጠበቅ ነው። ነገር ግን በጥንቃቄ ነገሮችን ማጤን ያስፈልጋል" ብለዋል።
በፅዮን ይልማ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
በመዲናዋ 2 ሺሕ 400 ያለ አግባብ የዋጋ ጭማሪ አድርገው የሸጡ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መውሰዱ ተገለጸ
ሕዳር 27/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በተያዘው የ2017 ዓ.ም ሩብ ዓመት የዋጋ ዝርዝር ሳይለጥፉና ምርትን በፍጥነት ወደ ገበያ ባለማስገባታቸው ምክንያት፤ 2 ሺሕ 400 በሚሆኑ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ አስታውቋል፡፡
በቢሮው የገበያ መረጃ ጥናትና ማስተዋወቅ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሙሰማ ጀማል ለአሐዱ እንደገለጹት፤ ቢሮው በነጋዴዎች ላይ ቁጥጥር በማድረግ አስተዳደራዊና ሱቆችን የማሸግ እርምጃ እየወሰደ ይገኛል፡፡
በዚህም መሰረት በሩብ ዐመቱ እርምጃ ከተወሰደባቸው መካከል 634 ሱቆች መታሸጋቸውን የገለጹ ሲሆን፤ እንዲሁም የዋጋ ዝርዝር ያለጥፉ 1 ሺሕ 800 በሚሆኑ ነጋዴዎች ላይ ሌሎች አስተዳደራዊ እርምጃዎች መውሰዳቸውን ተናግረዋል፡፡
የታሸጉ ሱቆች ወደ ሥራ ገበታቸው እንዲመለሱ ከማድረግ አንጻር አስተዳደራዊና የጹሁፍ ማስጠንቀቂያ በመውሰድ እንዲሁም ስህተታቸውን በማመን የመግባባት ሥራ ተፈጥሮ ወደ ሥራ እንዲመለሱ የተደረገበት ሁኔታ መኖሩንም አቶ ሙሰማ አክለው ገልጸዋል፡፡
የእርምጃ አወሳሰድ ሁኔታ በተመለከተ ነጋዴዎች የጹሑፍ ማስጠንቀቂያ፣ አስተዳደራዊ እርምጃ፣ ሱቆችን ማሸግ እንዲሁም በሕግ የተቀጡ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ሕገ ወጥ ንግድን እና ከተቀመጠው መመሪያ ውጭ የሚያካሄዱ ነጋዴዎችን ለመቆጣጣር ከሚመለከተው አካል በጋራ እየሰሩ እንደሚገኙ ጠቁመው፤ ማህበረሰቡም በተለጠፈው የዋጋ ተመን ልክ ብቻ እንዲገዛ ቁጥጥር እያደረጉ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
በአለምነው ሹሙ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ሲቪል ማህበራት የሚያከናውኑትን ሥራ ያህል ተገቢው እውቅና አልተሰጣቸውም ተባለ
ሕዳር 27/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ዓመታዊው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሳምንት ለ4ኛ ጊዜ ዛሬ አርብ ሕዳር 27 ቀን 2017 በአዲስ አበባ ግዮን ሆቴል በይፋ ተከፍቷል።
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሳምንቱ "ለዘላቂ ሰላም እና ፍትሐሃዊ ልማት ቃልኪዳናችንን እናድስ" በሚል መሪ ቃል ነው በመከበር ላይ የሚ።
በፕሮግራሙ መክፈቻ ላይ በኢትዮጵያ የሲቪል ማህበራት ሰፊ ሥራዎችን ቢሰሩም የተሰጣቸው እውቅና ውስን መሆኑ ተነስቷል።
የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ዋና ዳይሬክተር ተረፈ ደግፌ በሲቪል ማህበራቱ ሰላም እንዲሰፍን የዲሞክራሲ ግንባታ ጨምሮ በርካታ ሥራዎች መሠራታቸውን ገልጸዋል።
አክለውም ባለፉት ጊዜያት ከተለያዩ መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት ጋር በጥምረት መሠራቱን አንስተዋል።
ነገር ግን የሲቪል ማህበራት ስለሚሰጡት አገልግሎት በቂ ግንዛቤ ባለመኖሩ "የሚሰጡ አስተያየቶች ዘርፉን የሚያሳንሱ ሆነው አግተናቸዋል" ብለዋል።
ስለሆነም ምክር ቤቱ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ጋር በመሆን በዘርፉ የሚሠሩ ሥራዎችን ለማህበረሰቡ የማስተዋወቅ ሥራዎች ተሰርተዋል ሲሉ ተናግረዋል።
በመድረኩ የክብር እንግዳ ሆነው የተገኙት የትራንስፓስትና ሎጂስቲክ ሚኒስቴር ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የሕዝብን ተጠቃሚነት ማዕከል አድርገው መስራት ይኖርባቸዋል ሲሉ አሳስበዋል።
በዘርፉ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን እንዲሁም በቀጣይ የሚሠሩ ሥራዎች ላይ ውይይት ሊደረግ እንደሚገባም አመላክተዋል።
በዚህ የሲቪል ማህበረሰብ ሳምንት ከ85 በላይ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የተሳተፉበት አውደ ርዕይ እና የፓናል ውይይት መኖሩ ተመላክቷል።
በርካታ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ይሳተፉበታል የተባለው ዓመታዊ ዝግጅት ከዛሬ ሕዳር 27 እስከ እሁድ ሕዳር 29 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ ነው።
በፍርቱና ወልደአብ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
በኦሮሚያ ክልል በቀጣይ ሳምንት የአጀንዳ ማሰባሰብ ሥራው ይጠናቀቃል ተባለ
ሕዳር 30/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኦሮሚያ ክልል በሀገራዊ ምክክር አስተባባሪነት የሚካሄደው የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ፤ ከታህሳስ 7 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡
ይህንንም በማስመልከት ኮሚሽኑ በአዳማ ከተማ ለመገናኛ ብዙሃን እና ለተሳታፊዎች በዛሬው ዕለት ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል።
በዚህ ስልጠና ላይ የተገኙት የኮምሽኑ ምክትል ኮሚሽነር መሀሙድ ድሪር፤ "በኦሮሚያ ክልል በቀጣይ ሳምንት የአጀንዳ ማሰባሰቡ ሥራ ይጠናቀቃል" ብለዋል።
ከዚህ ቀደም ህብረተሰቡ በተሳታፊ ልየታ ውስጥ የመረጣቸው 7 ሺሕ ተወካዮች፤ አጀንዳ የመለየት ሥራን እንደሚሰሩም ገልጸዋል።
"በክልሉ እስካሁን ድረስ ያለፉት ዓመታት የኮሚሽኑን ሥራዎች የማስተዋወቅ ሥራ ሲሰራ ቆይቷል" ሲሉም ምክትል ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።
በሁለተኛው ምዕራፍ ደግሞ ከክልሉ የተለያዩ ዞኖችና ወረዳዎች የተወጣጡ ተሳታፊዎችን የመለየት ሥራ ሲሰራ መቆየቱን አስታውሰዋል።
በመሆኑም በክልሉ የሚጀመረው 7 ሺሕ አካላት የሚሳተፍበት የአጀንዳ ማሰባሰብ ሥራ በቀጣይ ሳምንት ይጠናቀቃል ሲሉ ገልጸዋል።
ባለፉት ሦስት ዓመታት በ9 ክልሎች እና 2 ከተማ መስተዳደሮች አጀንዳ ልየታው ያጠናቀቀዉ ኮሚሽኑ በቀጣይ ሳምንት በኦሮሚያ ሥራውን ያጠናቅቃል ሲሉም አስታውቀዋል።
በአካባቢው የተገኘውን ሰላም ለማስጠበቅ ይህ ውይይት አስፈላጊ መሆኑንም ጨምረው ተናግረዋል።
ግጭት ያለባቸው አካባቢዎች የነበሩ አካላት በተለይም በምዕራብ ኦሮሚያ የነበሩ ተወካዮች ጅማ ላይ መጥተው አጀንዳቸው አስረክበው መመለሳቸውንም የኮምሽኑ ምክትል ኮሚሽነር መሀሙድ ድሪር ለአሐዱ ገልጸዋል።
በአቤል ደጀኔ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
በአማራ ክልል መንግሥት በሚለው ልክ ሰላምና ፀጥታው የተረጋገጠ አለመሆኑን ፓርቲዎች ገለጹ
ሕዳር 30/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የአማራ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ በክልሉ ያለው የሰላም ሁኔታ ከጊዜ ወደጊዜ እየተሻሻለ ስለመምጣቱን ገልጿል።
የእናት ፓርቲ ፕሬዝደንትና የትብብር ፓርቲዎች የወቅቱ ሊቀመንበር ዶ/ር ሰይፈስላሴ አያሌው እንደገለጹት ደግሞ፤ "ዓመታትን ያስቆጠረው የሰላም እጦት አሁንም እንደቀጠለ መሆኑንና ከጊዜ ወደጊዜ እየተባባሰ መምጣቱ የሚታይ ነው" ብለዋል።
"በምንም አይነት መልኩ ኢትዮጵያ ውስጥ ሰላም መስፈን አለበት፣ ሰላም ብቸኛው አማራጭ ነው" የሚሉት ፕሬዝደንቱ፤ "በክልሉ እየተካሄደ ስላለው ነገር ገለልተኛ ሆኖ የሚገልፅ አካል በሌለበት ሁኔታ እውነታው ይሄ ነው ማለት ቢከብድም፤ በተለያዩ መንገዶች በሚገኝው መረጃ መሰረት ግን መንግሥት በሚለው መልኩ በአማራ ክልል ሰላም እየሰፈነ እንዳልሆነ እርግጠኛ ሆኖ መናገር ይቻላል" ሲሉ ገልጸዋል።
"ሰላም እንዲሰፍን ፍላጎት መኖር አለበት" ያሉም ሲሆን፤ አሁን ያለው ነባራዊ ሁኔታ ከፕሮፖጋንዳና በአፍ ከሚነገረው በዘለለ መንግስት አለ የሚለውን ሰላም እንደማያሳይ ገልጸዋል።
ሀገር ኢኮኖሚዋ የተሳሰረ በመሆኑ በአማራ ክልል ያለው ውጊያ ክልሉን ብቻ ሳይሆን ሁሉንም የሚመለከት እንደሆነም አፅንኦት ሰጥተዋል።
"መንግሥት በአማራ ክልል ያሉ ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሄደው ርቀት ይህ ነው የሚባል አይደለም" ያሉት ደግሞ የኢሕአፓ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀ መንበር መጋቢ አብርሃም ሀይማኖት ናቸው።
"በዚህ መሀል የንፁሃን እልቂት ከቀን ወደቀን እየተስፋፋ ነው ያለው" ሲሉም ተናግረዋል።
"ዜጎች ወጥቶ መግባት ቅንጦት ሆኖባቸዋል ያሉት ተቀዳሚ ፕሬዝደንቱ "ትምህርት ቤት፤ ጤና ተቋማትና ሌሎች መሰረታዊ ነገሮች ሁሉ በሚገባ አገልግሎት አለመስጠታቸው ሰላማዊ አለመሆኑን የሚያሳይ ነው" በማለት በክልሉ እየደረሰ ስላለው በደል ገልጸዋል።
የነፃነትና እኩልነት ፓርቲ አደረጃጀትና አመራር ዘርፍ ሀላፊ አቶ ሙባረክ ረሺድ በበኩላቸው፤ በአጠቃላይ በክልሉ ከሚታየው ነገር የሰላሙ ሁኔታ አሁንም ድረስ ጥሩ አለመሆኑን ገልጸው፤ "መንግሥት ያሉ ግጭቶችን ለማስወገድ የሚረዳ ሁሉንም ባለድርሻ አካል የሚያሳትፍ ፓለቲካዊ የሰላም ፍኖተ ካርታ ማዘጋጀትና በግልፅ ለማህበረሰቡ መንገር ያስፈልጋል" ሲሉ አሳስበዋል።
በአማራ ክልል በመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች እና በክልሉ ታጣቂዎች መካከል እያተካሄደ ያለው ግጭት፤ ከፍተኛ የሆነ የሰብዓዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ቀውስ እያስከተለ እንደሚገኝ ይታወቃል።
በስፍራሽ ደመላሽ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
በሕገ ወጥ መንገድ ሊሸጥ የነበረ 28 ሺሕ ሊትር ነዳጅ በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የትግራይ ክልል ንግድ ቢሮ አስታወቀ
ሕዳር 30/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በትግራይ ክልል 28 ሕሺ ሊትር የሚሆን ነዳጅ ባልተፈቀደ መልኩ ከነዳጅ ማደያ ቦታዎች ተወስዶ በሕገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር መያዙን የክልሉ ንግድ ኤጀንሲ የቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ ጉኡሽ ወልደገሪማ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
በክልሉ በ3 ወራት ዉስጥ በአጠቃላይ 27 ሚሊየን 500 ሺሕ ሊትር ነዳጅ የገባ ሲሆን፤ ቤንዝል ደግሞ 6 ሚሊዮን ሊትር መግባቱን አስታውቀዋል።
ይሁን እንጂ አሁንም እየገባ ያለዉ ነዳጅ በቂ አለመሆኑን የገለጹት አቶ ጉኡሽ "ለክልሉ በየወሩ መግባት የሚጠበቅበት ናፍጣ 13 ሚሊዮን ሊትር ሲሆን፤ እየገባ ያለዉ ግን 9 ሚሊዮን ሊትር ነው" ብለዋል።
በሕገ ወጥ መንገድ ሲሸጡ የተገኙት ግለሰቦችም ንብረታቸውን በመውረስና የጹሁፍ ማስጠንቀቂያ በመስጠት እርምጃ የተወሰደባቸው መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል።
አክለውም በክልሉ እየገባ ያለዉ የነዳጅ አቅርቦት አነስተኛ ቢሆንም ለተጠቃሚዉ ማህበረሰብ በአግባቡ ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው፤ ሕገ ወጥ ንግድን ለመከላከል ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል።
በአለምነዉ ሹሙ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ኢትዮጵያ ከዓለም ዓቀፍ የገንዘብ ተቋማት ያገኘችው ብድር የአከፋፈል ሂደት ግልፅ መደረግ አለበት ሲሉ የምጣኔ ሐብት ባለሙያዎች ተናገሩ
ሕዳር 30/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ኢትዮጵያ ከአይ.ኤም. ኤፍና ከዓለም ባንክ ያገኘችውን ተመላሽ ብድር አከፋፈል እና ገንዘቡ የሚውልበት ቦታ ግልፅ አለመደረጉ የምጣኔ ሐብቱን ትንተና አስቸጋሪ እንዳያደርገው የዘርፉ ባለሙያዎች ስጋታቸውን ገልጸዋል።
ከዚህ ቀደም ዮሮ ቦንድ አበዳሪ አገራት የተወሰደው ብድር 'ለኢንዱስትሪ ፓርኮች' በሚልና ግልፅነት የጎደለው መንገድ መወሰዱ አሁን ድረስ መመለስ ያልተቻለበት ሁኔታ መኖሩን የምጣኔ ሐብት ባለሙያው ቆስጠንጢንዮስ በርኸ ተስፋ (ዶ/ር) ተናግረዋል።
መንግሥት ከዩሮ ቦንድ አበዳሪ አገራት የተበደረውን ብድር ያልመለሰበት ምክንያት ሲያስዳም፤ 'ሁሉም አበዳሪ አገራት በእኩል ማስተናገድ ስለሚጠበቅብን ነው' ማለቱ አይዘነጋም።
"ሆኖም ብድሩ የተወሰደበት አላማ ግልፅነት የጎደለው ስለነበር ጥቅም ላይ አልዋለም" ሲሉ ዶክተር ቆስጠንጢንዮስ ለአሐዱ ተናግረዋል።
ሌላኛው አሐዱ በዚሁ ዙርያ ያነጋገራቸው የምጣኔ ሐብት ባለሙያው አቶ ክቡር ገና በበኩላቸው፤ አሁንም ቢሆን ከአለም ዓቀፍ አበዳሪ ተቋማት የተገኘውን ብድር አጠቃቀም በተመለከተ መንግሥት እቅዱን ይፋ አለማድረጉን እንደ ክፍተት ያነሳሉ።
በቅርቡ የኢኮኖሚክስ ማሕበር ጥናት ዋቢ በማድረግ የግሽበቱ ምጣኔና አጠቃላይ የአገር ምርት የቀረቡ ሪፖርቶ፤ ከብሔራዊ ባንክ (ፋይናንሻል ስቴብልቲ ሪፖርት) ጋር ፍፁም የተራራቀ ሪፖርት በመሆኑ ሪፖርቱ ሲተች ሰምተናል።
ለዚህም የፌደራል በጀት 1 ነጥብ 5 ትሪሊዮን ብር የደረሰበት ምክንያት በማንሳት፤ በዚሁ ልክ የመንግሥት የበጀት ብክነት እንዳይጨምር የምጣኔ ሐብት ባለሙያው ክቡር ገና ስጋታቸውን ገልጸዋል።
"የመንግሥት በጀት ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር በእጥፍ ጭማሪ ማሳየቱ ላይ የሸማቹ ሕብረተሰብ የመግዛት አቅም መዳከም ተደማምሮ የሸቀጦች ዋጋ ላይ ግሽበት ሊፈጥር ይችላል" ሲሉም አሳስበዋል።
በቅርቡም የፌደራል መንግሥት በጀት ጭማሪ ያደረገው ከአበዳሪ አገራት የተገኘው ብድር ጭማሪ በማሳየቱ ምክንያት እና ለካፒታል ወጪ የሚውል መሆኑን የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መግለጻቸውን የሚታወስ ነው።
የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ አክለውም ይህ የበጀት ጭማሪ አጠቃላይ በሕብረተሰቡ ላይ የሚያሳድረው ተፅእኖ እንደማይኖር በመግለጽ፤ ከምክር ቤቱ የቀረበላቸውን ጥያቄዎች ሲያስተባብሉ ተደምጠዋል።
የፌደራል መንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት ከ1 ነጥብ 5 ትሪልዮን ብር በላይ ሆኖ የተመዘገበ ሲሆን፤ ይህም በኢትዮጵያ በጀት አመዳደብ ታሪክ ከፍተኛ ሆኖ ተመዝግቧል።
በአማኑኤል ክንደያ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ለ24 ዓመታት ሶሪያን የመሩት በሽር አል-አሳድ ሀገር ጥለው ሸሹ
ሕዳር 29/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የሶሪያ አማጺያን መዲናዋ ደማስቆን መቆጣጠራቸውን ተከትሎ ፕሬዝዳት ባሽር አል-አሳድ ከሀገሪቱ መሸሻቸው ተነግሯል።
የሶሪያ መንግሥት ኃይሎች እና መሪው ባሽር አል አሳድ ከዋና ከተማዋ እንደሸሹ እና አማጽያን በቁጥጥራቸው ሥር እንዳዋሏት ገልጸዋል።
አላሳድ ከደማስቆ ሸሽተው ወዳልታወቀ ሥፍራ በአውሮፕላን እንደሄዱ የሚጠቁሙ ሪፖርቶች ወጥተዋል ነው የተባለው።
የታጠቁ የሶሪያ ተዋጊዎች የፕሬዚዳንት በሽር አል አሳድን የ24 ዓመት አገዛዝ ለመደምሰስ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ የተጠናከረ ወታደራዊ ዘመቻ እያካሄዱ ነበር።
በተለይም በሰሜናዊ ክፍል የሚገኙ የታጣቁ ተቃዋሚዎች ከረዥም ዓመታት በኋላ የአገሪቱ ጦር ላይ ድንገታዊ ጥቃት ከከፈቱ በኃላ ብዙ ቦታዎችን በፍጥነት ይዘዋል። ከሳምንት በፊት ነው አሌፖን ዘልቀው የገቡት።
ከዛ በኃላ በመላ ሀገሪቱ ውስጥ ያሉ የመንግሥት መከላከያዎች በአስደናቂ ፍጥነት ፈራርሰዋል።
በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች የአማጽያኑን ምት መቋቋም ከብዷቸው ድንበር አቋርጠው ኢራቅ ለመግባትና ጥገኝነት ለመጠየቅ መገደዳቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ይህንንም ተከትሎ የታጠቁት ተቃዋሚዎች በሀገሪቱ የቴሌቭዥን ጣቢያ ቀርበው ባወጡት መግለጫ፤ "ጨቋኙ በሽር አላሳድ ከደማስቆ ለቀው ሄደዋል" ያሉ ሲሆን "ደማስቆን ከጨቋኙ በሽር አላሳድ ነጻ አውጥተናል " ሲሉም አስታውቀዋል።
ተቃዋሚዎቹ በቀናት ውስጥ እጅግ በርካታ ቁልፍ ከተሞችን እና ቦታዎችን ከአል-አሳድ አገዛዝ ነጻ ያደረጉ ሲሆን፤ ለሊቱን የአሳድ መቀመጫ ወደ ሆነችው ደማስቆ መግባታቸው ታውቋል።
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
የብሔር ብሔረሰቦች ቀንን ለማክበር ቅድመ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸው ተገለጸ
ሕዳር 28/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ከተማ 19ኛው የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓልን ለማክበር ቅድመ ዝግጅት መደረጉን የዞኑ መንግሥት ኮምዩኒኬሽን ገልጿል።
የቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ገዛኸኝ ጩባ ለአሐዱ እንደተናገሩት፤ በዓሉ በይዘትም ሆነ በዝግጅት ደረጃ የተሻለ እንዲሆን በቅድመ ዝግጅት ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸዋል።
አክለውም በዓላት ሲቃረቡ በተለያዩ ነገሮች ላይ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ ነጋዴዎችና አሽከርካሪዎች ላይ ቅድመ መከላከል እና መቆጣጠር ሥራዎች እንደተሰሩም ጠቁመዋል።
በተጨማሪም የሚከሰቱ የወንጀል ጉዳዮችን የሚመለከት ጊዜያዊ ችሎት መጀመሩን አብራርተዋል።
በከተማው እየተከበረ የሚገኘውን ሀገራዊ ሁነት ተከትሎ የሚከሰቱ የወንጀል ጉዳዮችን የሚመለከት በዋናው፣ በሼቻ እና በልማት ቀበሌ ባሉ ምድብ ችሎቶች እስከ በዓሉ ፍጻሜ የሚቆይ ጊዜያዊ ችሎት መጀመሩንም ለአሐዱ ተናግረዋል።
አያይዘውም በዓሉን ለማክበር የሚመጡ እንግዶችን ባህላዊ እሴቶቻችንን በጠበቀ መልኩ ነዋሪዎች መቀበል እንዳለባቸውና "በዓሉን የዞኑን ገፅታ በሚያጎላ መልኩ ለማክበርና በስኬት እንዲጠናቀቅ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እና የዞኑ ሕዝብ የድርሻውን ሊወጣ ይገባል" ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
19ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን "ሀገራዊ መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት" በሚል መሪ ቃል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት፤ ነገ ሕዳር 29 ቀን 2017 ዓ.ም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አርባ ምንጭ ከተማ ይከበራል።
በደረጄ መንግስቱ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
በሩብ ዓመቱ በብልሹ አሰራር ተሳትፈዋል የተባሉ 46 ባለሙያዎች እና ተገልጋዮች ላይ እርምጃ መወሰዱ ተገለጸ
ሕዳር 28/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የአዲስ አበባ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በ2017 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት ከማዕከል እስከ ወረዳ ድረስ በብልሹ አሰራር ተሳትፈዋል ያላቸውን ባለሙያዎች እና ባለጉዳዮች ተጠያቂ ማድረጉን አስታውቋል።
ኤጀንሲው ከሚሰጣቸው የመታወቂያ የልደት ካርድ እና ሌሎችም የኩነት ምዝገባ አገልግሎቶች ጋር በተያያዘ በተፈጸሙ የሌብነት፣ የሥነ-ምግባር ጉድለት እንዲሁም ከሃሰተኛ ሰነድ ጋር በተያያዘ 46 ባለሙያዎች እንዲሁም ግለሰቦችን ከቀላል እስከ ከባድ የሥነ-ምግባር እና የወንጀል ተጠያቂነት እርምጃዎች እንደተወሰደባቸው ነው የገለጸው፡፡
ከእነዚህም መካከል በቀላል ዲሲፕሊን 17፣ በከባድ 9 እና ጉዳያቸው በፍርድ ቤት የተያዘ 9 እንዲሁም፤ በማዕከሉ የማረጋገጥ አገልግሎት ለማግኘት የመጡ 11 ባለጉዳዮች በጥቅሉ 46 ባለሙያዎችና ባለጉዳዮች በሩብ ዓመቱ እርምጃ እንደተወሰደባቸው ተነስቷል።
የአዲስ አበባ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ከክፍለ ሀገር በመሸኛ የሚመጣን ነዋሪ በተመለከተ፤ "መረጃዎች ተጣርተው ወረፋ እየጠበቁ ካሉት ከ42 ሺሕ በላይ አገልግሎት ፈላጊዎች መካከል ትክክለኛ መረጃ ያላቸውን ከሕዳር አንድ ጀምሮ አስተናግዳለሁ" ያለ ቢሆንም እስካሁን አለመጀመሩም ይታወቃል።
አሐዱም "ይህን አገልግሎት ለምን ሕዳር አንድ ማስጀመር አልተቻለም?" ሲል የኤጀንሲውን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ወይዘሮ ጀሚላ ረዲን ጠይቋል፡፡
"አገልግሎቱን ለማስጀመር የተገልጋዮችን ማስረጃ የማጣራቱ ሠራ እየተሰራ ነው። ተጣርተው የመጡ ማስረጃዎችም አሉ" ብለው፤ ነገር ግን በተባለበት ቀን ለማስጀመር የሲስተም ብልሽት እንዳጋጠመ እና አዳዲስ ተመዝጋቢዎችን አሻራ መውሰድ ባለመቻሉ እንደዘገየ ገልጸዋል፡፡
"ከብሔራዊ መታወቂያ ጋር በተያያዘም እንደ ሀገር እየተሰራበት ያለ ነው። ከእኛ ጋርም በጋራ እየሰራን ቢሆንም፤ መታወቂያው ግን የእኛን የቀበሌ መታወቂያ አይተካም" ሲሉም የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተሯ ተናግረዋል፡፡
በእመቤት ሲሳይ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ለዜጎች በቂ ሆነ የሥራ ዕድል እስካልተፈጠረ ድረስ ሙስና እና ብልሹ አሰራር ስጋት መሆናቸው እንደማይቀር ተገለጸ
ሕዳር 28/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ 70 በመቶ የሚሆነው ወጣት ቢሆንም ሙስናን እና ብልሹ አሰራርን በጋራ ከመከላከል አንፃር በወጣቱ ላይ እየተሰራ ያለው ሥራ ዝቅተኛ መሆኑን የፌደራል ሥነ ምግባር እና ጸረ ሙስና ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
ይህንን ችግር ለመቅረፍ በስብዓናው መልካም የሆነ ወጣትን ማፍራት የአቅም ግንባት መሰጠት እንዳለበት፤ በኮሚሽኑ የአስቸኳይ ሙስናን መከላከል መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ገዛኸኝ ጋሻው ተናግረዋል፡፡
መሪ ሥራ አስፈጻሚው በዘንድሮው ዓመት በአለም ዓቀፍ ደረጃ ለ21ኛ ጊዜ የሚከበረውን የጸረ ሙስና ቀንን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ፤ ኢትዮጵያ ከ1999 ጀምሮ በተባበሩት መንግሥትታት ድርጅት የጸረ ሙስና ኮሚሽን የጸደቀውን ስምምነት ተቀብላ ተግባራዊ በማድረግ ላይ እንደምትገኝ ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም ይህ ስምምነት በርካታ ነጥቦችን የያዘ መሆኑን ገልጸው፤ አባል ሀገራትም በየ አምስት ዓመቱ ግምገማ ስለሚያቀርቡ ኢትዮጵያም ኃላፊነቷን እየተወጣች እንደምትገኝ አስረድተዋል፡፡
አክለውም "ለሙስናና ብልሹ አሰራር ተጋላጭነት ስጋት የሚሆኑ ችግሮችን ለመቀነስ ወጣቱን ባሳተፈ መልኩ በጋራ እና በተቀናጀ ስልት መግታት ካልተቻለ፤ ወጣቱ በመንግሥት አስተዳደር ላይ የሚያነሳው ቅሬታ ሊጨምር ይችላል" ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡
ይህን ታሳቢ በማድረግ በሀገር አቀፍ ደረጃ ስጋት ደቅኖ የሚገኘውን ሙስና እና ብልሹ አሰራር ለመቀነስ ወጣቱን በአቅም ግንባታ ማሳደግ እንደሚያስፈልግ የፌደራል ሥነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን መከላከል ሥራ አስፈጻሚ አቶ ገዛኸኝ ጋሻው ተናግረዋል፡፡
ነገር ግን ኢትዮጵያ አሁን ባለችበት ሁኔታ ለዜጎች በቂ ሆነ የሥራ ዘርፍ እስካልፈጠረች ድረስ እንዲሁም በቂ የሆነ ገቢ እንዲኖራቸው እስካልተመቻች ድረስ ሙስና እና ብልሹ አሰራርን ለመቀነስ ተግዳሮት እንደሚሆን ተጠቁሟል፡፡
በደረጄ መንግስቱ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል 700 የሚጠጉ የማዕድን አልሚዎች መኖራቸው ተገለጸ
ሕዳር 28/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ወደ 700 የሚሆኑ የማዕድን አልሚዎች በሥራ ላይ እንደሚገኙ የክልሉ የማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ደርበው ዘንቶ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
ከእነዚህም ውስጥ በድንጋይ ከሰል ዘርፍ 450 ተቋማት ተሰማርተው በክልሉ በሥራ ላይ እንደሚገኙ ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡
ቀሪዎቹ 250 ተቋማት ደግሞ በእምነበረድ ዘርፍ ፈቃድ ወስደው እየሰሩ መሆኑን የገለጹት ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተሩ፤ 10 ግራናይት አምራች ተቋማትም በክልሉ መኖራቸን ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም በማዕድን ልማት ዘርፍ ተሰማርተው ሥራ ለመጀመር በሂደት ላይ ያሉ ሌሎች ተቋማት መኖራቸውንም አክለው ገልጸዋል፡፡
ከዚህ ባሻገርም በክልሉ የማዕድን ሀብት የሚገኝበት ቦታ ድንበር አካባቢ እንደመሆኑ በተለይም የወርቅ ማዕድን በሔገወጥ መንገድ እንደሚወጣ የተገለጹት ዳይሬክተሩ፤ ፈቃድ የተሰጣቸው አካላት ብቻ እንዲሰማሩ በማድረግ የመከላከል ሥራ እየተሰራ ስለመሆኑ ተናግረዋል፡፡
በዚህም በክልሉ ከዚህ በፊት 6 ነጥብ 6 ኪሎ ግራም የሚገመት ወርቅ በሕገ-ወጥ መንገድ ሊወጣ ሲል መያዙ ነው የተገለጸው፡፡
በእመቤት ሲሳይ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
#ADVERTISMENT
#ጊፍትሪልስቴት
ታላቅ የምስራች!
**
ጊፍት ሪል ስቴት ከ10% ቅድመ ክፍያ ጀምሮ በ22 ሳይቶቹ ቅንጡ አፓርትመንቶችን እና የንግድ ሱቆችን ለሽያጭ አቅርቧል፡፡
ይህ ሳይት ለአፓርትመንትና ንግድ ሱቆች የሚውሉ G+25 ሶስት መንታ ህንጻዎች ያሉት ሲሆን የዚህ 6ኛ መንደር መለያዎች፡-
•ከባለአንድ እስከ ባለአራት መኝታ ክፍሎች ያሉት፣
•ለመኖሪያም ሆነ ለንግድ ተመራጭ አካባቢ የሆነ፣
•በአንድ ወለል ሶስት ቤቶች ብቻ ያሉት፣
•በእያንዳንዱ ወለል ስድስት አሳንስር ያለው፣
•አራት ቤዝመንት ያሉት በቂ የመኪና ማቆሚያ የተዘጋጀለት፣
•24 ሰዓት የኤሌክትሪክ፣ ኢንተርኔትና ውሃ አቅርቦት አሉት፣
ጊፍት ሪል ስቴት
ማህበረሰብን እንገነባለን!
ለበለጠ መረጃ፡-
Website: https://www.giftbusinessgroup.com
Twitter: https://twitter.com/GIFTBusinessG
YouTube: www.youtube.com/channel/UCcqr7cpVv9ski-F7haxXx4w
Facebook: www.facebook.com/profile.php?id=100090918391017...
Telegram: /channel/giftbusinessgroup
Short Code: 8055
በመንግሥትና በኦነግ ሸኔ ከፍተኛ አመራር መካከል የተደረገው ድርድር የስምምነት ነጥቦች ይፋ ሊደረጉ እንደሚገባ ፓርቲዎች ገለጹ
ሕዳር 27/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ሽመልስ አብዲሳ እና የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ከፍተኛ አመራር የነበሩት ጃል ሰኚ ነጋሳ በአዲስ አበባ ከተማ የሰላም ስምምነት መፈራረማቸው መገለጹ ይታወቃል።
ጃል ሰኚ ነጋሳ መንግሥት ያቀረበላቸውን የሰላም ጥሪ በመቀበል ነው ከአቶ ሽመልስ አብዲሳ ጋር የሰላም ስምምነቱን መፈረማቸው የተጠቆመው።
"ስምምነት መደረጉ ለረጅም ጊዜ የሰላም ጥያቄውን ሲያቀርብ ለኖረ ማህበረሰብ እፎይታን የሚሰጥ እና የሚበረታታ ነው" ያሉት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ (ኢፌኮ) ተቀዳሚ ምክትል ሊቀ-መንበር አቶ ሙላቱ ገመቹ ናቸው።
ነገር ግን የዚህ ቡድን አመራር አስቀድሞ ወደ ጫካ የገባው 'ያልተመለሱ ጥያቄዎች ስላሉኝ ነው' ማለቱን አስታውሰው፤ "አሁን ምላሽ አግኝቶ ነው" ወይ ሲሉ ይጠይቃሉ።
አክለውም፤ "የተደረገው ስምምነት በምን በምን ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት ተደርሶ መሆኑን፣ ከዚህ በኋላ መተዳደሪያ የሚሆኑ ነገሮች ተመቻችተዋል፣ ታጥቀው የነበሩ አካላትስ በምን ሁኔታ ነው የሚታዩት የሚለውን ግልጽ መድረግ ነበረበት" ሲሉ ለአሐዱ ገልጸዋል።
"ስምምነቱን የፈረመው አመራር ቡድን አስቀድሞ እጁን ሰጥቶ የነበረ ነው" ያሉት ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበሩ፤ ከዚህ ቀደም እጃቸውን የሰጡ አመራሮችም እንዲሁም ተዋጊዎች እንደነበሩ አንስተዋል።
በመንግሥትና በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት አመራር መካከል የተደረገውን ድርድር "የሰላም መጥፎ የጦርነት ጥሩ የለውም" በማለት የቀደመውን ሃሳብ የሚጋሩት የነጻነት እና እኩልነት ፓርቲ አደረጃጀት እና አመራር ዘርፍ ኃላፊው ሙባረክ ረሺድ በበኩላቸው፤ "ድርድሩ መደረጉ በጎ ነው" ብለዋ።
ይኼው ስምምነት በመርህ እና በተግባር ውጤት የሚታይበት ሊሆን እንደሚገባም ገልጸዋል።
"በመንግሥት በሽብረትኝነት የተፈረጀው የአሮሞ ነጻነት ሠራዊት ከስምምነቱ ይፋ መደረግ በኃላ ባወጣው መግለጫ 'ከቡድኑ የተሰናበተና እኛን የማይወክል ነው' ማለቱ የራሱን ጥላ አጥልቷል" ያሉም ሲሆን፤ መንግሥት ዘላቂ ሰላም ማምጣት የሚችልበትን መንገድ መከተል እንዳለበት አሳስበዋል።
እንዲሁም "ኅብረተሰቡ ከስምምነቱ የሚጠብቃቸው በርካታ ነገሮች አሉ" በማለት፤ "ስምምነቱ ምን ምን ነገሮችን ይዟል ከምን ምን ይጠበቃል የሚለው ይፋ መደረግ አለበት" ሲሉ ገልጸዋል።
"ኅብረተሰቡም በተለያዩ ክልሎች ሰላም በማጣት ሰርቶ በመብላት ችግር ውስጥ ነው" ያሉት ፖለቲከኞቹ፤ መንግሥት ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የሚያስችሉ ስምምነቶችን በተገቢው መንገድ መከተል አለበት ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።
የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር እና በጃል ሰኚ ነጋሳ መካከል የተፈረመውን ስምምነት አስመልክቶ፤ የስምምነት ሰነዱ ምን ይዟል፣ ምን ምን ጉዳዮች ላይ መግባባት ተደርሷል እንዲሁም የሰላም ስምምነቱ ተፈጻሚነት እስከምን ድረስ ነው የሚለው ጉዳይ በይፋ አለመገለጹ በብዙዎች ዘንድ ጥያቄ እየፈጠረ መሆኑ እየተገለጸ ይገኛል፡፡
ስምምነቱን ተከትሎም የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ይህ የሰላም ስምምነት ለዜጎች እረፍትን የሚሰጥ ሰላም የሚያሰርጽ መሆኑን የገለጸ ሲሆን፤ የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፤ "ክልሉን ወደ መደበኛ ሁኔታ ለማምጣት እንዲህ ያሉ እምርጃዎች ይበረታታሉ" ብለዋል።
የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ከፍተኛ አመራር የነበሩት ጃል ሰኚ ነጋሳ በዛሬው ዕለት በሰጡት መግለጫ፤ የሰላም ጥሪውን የተቀበሉት የሕዝብና የመንግሥትን ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪዎች ተከትሎ መሆኑን የገለጹ ሲሆን፤ እየደረሰ ያለውን ጉዳት ለመቀነስ እና የሰላም አማራጭን መቀበል 'ብልህነትና አዋቂነት' መሆኑን በመረዳታቸው መሆኑን አስረድተዋል፡፡
በፍርቱና ወልደአብ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
የታሕሳስ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት እንደሚቀጥል ተገለጸ
ሕዳር 27/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የታሕሳስ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በሕዳር ወር በነበረበት እንዲቀጥል መወሰኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
የነዳጅ ማደያዎችና ኩባንያዎች ያልተገባ የነዳጅ ክምችት ከመያዝና የዋጋ ጭማሪ ከማድረግ ተቆጥበው ውሳኔውን ተግባራዊ በማድረግ ህብረተሰቡን በቅንነትና በታማኝነት እንዲያገለግሉም ሚኒስቴሩ አሳስቧል፡፡
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
#አሐዱ_ትንታኔ
ከባይደን የአንጎላ ጉዞ ጀርባ ምን አለ?
ትንታኔውን ለመከታተል ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👇
https://youtu.be/OYFXoAcfHvk?si=ed4wLtZH0w6regL-