ahaduradio | Unsorted

Telegram-канал ahaduradio - AHADU RADIO FM 94.3

19349

አሐዱ ራድዮ 94.3 Your source for top local and international news and analysis. "Voice of Ethiopian" የአሐዱ የቴሌግራም ቻናል ቤተሰብ በመሆን ወቅታዊና እውነተኛ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ

Subscribe to a channel

AHADU RADIO FM 94.3

የሽግግር ፍትሕ ሂደቱ ላይ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጎጂዎች ማህበራት ማቋቋም አስፈላጊ መሆኑ ተገለጸ

መስከረም 14/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን እና የምስራቅ አፍሪካ የሰብዓዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር ጽሕፈት ቤት በጋራ ያዘጋጁት አዉደ ጥናት ተጠናቋል።

አውደ ጥናቱ ዓላማ የተለያዩ የክልል ማህበራትን አቅም፣ ተግዳሮቶች እና እድሎች መገምገም እንዲሁም በአገር አቀፍ ደረጃ የተጎጂዎች ማህበራት እና ቡድኖችን በማቋቋም የማህበራት ጥምረት መመስረት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መወያየት መሆኑ ተገልጿል፡፡

በዚህም የተጎጂዎች እና ከጥቃት የተረፉ ሰዎች እራሳቸውን ማደራጀትን በተመለከተ የሌሎቹ ሀገራት ተሞክሮዎች ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን፤ ይህ በሂደቱ ላይ የሚኖራቸውን ሚና የጎላ እንዲሆን ያግዛል ተብሏል።

እንዲሁም ተጎጂዎች ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ተወካዮች ጋር በመሆን የየራሳቸውን ሁኔታ እና የሲቪል ማህበራትን ብሔራዊ ህግ ግምት ውስጥ በማስገባት በሽግግር ፍትህ ሂደት ውስጥ ጥያቄያቸው ለመመለስ እና እራሳቸውን ማደራጀት የሚችሉበት መሆኑ ተገልጿል።

የማህበራቱ የጥምረት ምስረታ እጅግ አስፈላጊው አማራጭ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ ይህንን ድርጅታዊ ማዕቀፍ ከማቋቋም ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን የሚመልስ መሆኑ በመድረኩ ተነስተዋል።

የሽግግር ፍትሕ ትግበራ ፍኖተ-ካርታ ዝግጅት ተጠናቅቆ ወደ ሥራ መገባቱን የፍትሕ ሚኒስቴር ማስታወቁ ይታወሳል።

በፍርቱና ወልደአብ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡-www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በደቡብ ሊባኖስ በሚገኙ ሦስት ከተሞች በደረሰባቸው ጥቃት የተነሳ ትምህርት መስጠት ማቆማቸው ተገለጸ

መስከረም 14/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በመካከለኛው ምስራቅ እየተባባሰ የመጣውን ጦርነት ተከትሎ፤ በደቡብ ሊባኖስ በሚገኙ ሦስት ከተሞች ከእስራኤል ኃይሎች በደረሰባቸው ጥቃት የተነሳ ትምህርት መስጠት ማቆማቸው ተገልጿል።

ዩኒቨርስቲዎቹ ሲዶና፣ ናባቲህ እና ጢሮስ ከተሞች የሚገኙ ሲሆን፤ የዩኒቨርሲቲ ካምፓሶች ክፉኛ ጥቃት እንደረሰባቸው ተናግሯል።

የሊባኖስ የትምህርት እና የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር የሆኑት አባስ አል-ሃላቢ፤ ዩኒቨርስቲዎቹ ከፍተኛ ጉዳት ስለደረሰባቸው ተማሪዎቹ እንዲበተኑ መደረጉ አስታውቀዋል።

በአከባቢው ያሉ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችም ወደ ቅጥር ጊቢዎቹ ዝር እንዳይሉም መልዕክታቸውን አስተላለልፈዋል ሲል ሚዲል ኢስት ሞኒተር ዘግቧል።

ከሰሞኑ ተባብሶ የቀጠለውን የሊባኖስና የእስራኤል ጦርነት ከወዲሁ ኪሳራ እያስከተ መሆኑን ታዛቢዎች እየገለጹ ይገኛሉ።

ሁለቱ ኃይሎች በቀሰቀሱት ነውጥም፤ መካከለኛ ምስራቅ በባሩድ ክፉኛ እየተናጠች ትገኛለች።

በአማኑኤል ክንደያ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በህወሓት አመራሮች መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት የፌደራል መንግሥቱ ጣልቃ ገብቶ መፍታት አለበት ተባለ

መስከረም 14/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በትግራይ ክልል በህወሓት አመራሮች መካከል የተፈጠረውን መከፋፈል እና አለመግባባት፤ የፌደራል መንግሥቱ ጣልቃ ገብቶ መፍታት አለበት ሲሉ አሐዱ ያነጋገራቸው የሕግ ባለሙያዎች ግልጸዋል፡፡

በክልል በአመራሮቹ መካከል የተፈጠረውን ይህን መከፋፈል እና አለመግባባት በተመለከተ የፌደራል መንግሥቱ ሚና ምን መሆን አለበት? ሲል አሐዱ የሕግ ባለሙያዎችን ጠይቋል፡፡

"የህወኃት አመራሮች እያደረጉት ያለው እንቅስቃሴ ከሕግ እና መመሪያ ውጭ በመሆኑ ምርጫ ቦርድ እርምጃ መወሰድ ይችላል" ያሉት የህግ ባለሙያው አቶ ካሳሁን ሙላቱ ናቸው፡፡

የተደረገውም የስልጣን ሹም ሽር ተቀባይነት የለውም" ያሉት አቶ ካሳሁን፤ በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት ውይይት መደረግ እንዳለበት አንስተዋል፡፡

"ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ውይይት ማድረግ ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር ደግሞ የፌደራል መንግሥቱ ሀላፊነት ነው" ብለዋል፡፡

በአመራሮቹ መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ክልሉን መልሶ ለማቋቋም እንዲሁም ለሚሰራው የሰላም እና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ተግዳሮት እንደሆን የተናገሩት ደግሞ ሌላኛው የህግ ባለሙያው አቶ ጥጋቡ ደሳለኝ ናቸው፡፡

"እንዲህ አይነት እንቅስቃሴዎችን የፌደራል መንግሥቱ በዝምታ ማለፍ እና ማየት የለበትም" ያሉት አቶ ጥጋቡ፤ ችግሮቹ መውይይት እንዲፈቱ ጣልቃ መግባት አለበት ብለዋል፡፡

"በህወሓት አመራሮች መካከል የተፈጠረው አለመግባባት የሚያመጣው ዳፋ ለሕዝቡ እንዳይተርፍ ልዩነቶታቸውን በውይይት መፍታት አለባቸው" ሲሉም የሕግ ባለሙያዎቹ መክረዋል፡፡

በፍቅርተ ቢተዉ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

"በሶማሊያ በውጭ ሃይላት የሚደረግ የጦር መሣሪያ አቅርቦት ሀገሪቷ አሸባሪዎች እጅ ላይ እንድትወድቅ በር የሚከፍት ነው" አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሤ

መስከረም 14/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በሶማሊያ ባልተረጋጋ የደህንነት ሁኔታ ውስጥ በውጭ ሃይላት የሚደረግ የጦር መሣሪያ አቅርቦት በመጨረሻ ሀገሪቷ አሸባሪዎች እጅ ላይ እንድትወድቅ በር ሊከፍት ይችላል ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሤ ተናግረዋል፡፡

ሚኒስትሩ በኒውዮርክ እየተካሄደ ከሚገኙው 79ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ጎን ለጎን ከተመድ የሰላም ግንባታ እና ፖለቲካ ጉዳዮች ረዳት ዋና ፀሐፊ ሮዝማሪ ዲካርሎ ጋር የጋራ ተወያይተዋል፡፡

አምባሳደር ታዬ በ.ተ.መ.ድ. ጥላ ሥራ የሚገኙ የተለያዩ ኤጀንሲዎች ከኢትዮጵያ ጋር ጠንካራ የሥራ ግንኙነት ፈጥረው እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን በማድነቅ፤ ቀጣይነት ያላቸው መደበኛ ምክክሮችን አስፈላጊነት አንስተዋል።

ሚኒስትሩ ለረዳት ዋና ፀሐፊዋ በሱዳን ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ገለጻ በማድረግ እና በአገሪቱ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት የተቀናጀ ጥረት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለሱዳን ቀውስ መፍትሔው ፖለቲካዊ ነው የሚል አቋም እንዳላትም አንስተዋል።

አምባሳደር ታዬ ሶማሊያን በተመለከተ ከሮዝማሪ ጋር በነበራቸው ውይይት፤ ኢትዮጵያ በሽብርተኞች ለመዋጋት ላይ የምታደርገውን ጥረት አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል።

በሶማሊያ ድህረ የአፍሪካ ህብረት ሽግግር ተልዕኮ በሶማሊያ የሚኖረው የኃይል ስምሪት ተገቢውን ጊዜ ወስዶ የተልዕኮዎን የኃላፊነትን መጠን፣ የፋይናንስ ምንጭ እና ቅንጅት በአግባቡ መሠራት እንዳለበትም አሳስበዋል።

ሚኒስትሩ ባልተረጋጋ የደህንነት ሁኔታ ውስጥ በውጭ ኃይላት የሚደረግ የጦር መሣሪያ አቅርቦት መጨረሻው አሸባሪዎች እጅ ላይ ሊወደቅ እንደሚችል ያላቸውን ስጋት ገልጸዋል።

የተመድ የሰላም ግንባታ እና የፖለቲካ ጉዳዮች ረዳት ዋና ፀሐፊ ሮዝማሪ ዲካርሎ በበኩላቸው፤ በቀጣናው እና ከቀጣናው ባሻገርም ተ.መ.ድ. ከኢትዮጵያ ጋር በሰላም ግንባታ ዙሪያ የሚያደርገውን ሥራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ማረጋገጣቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

ሁለቱ አካላት በቀጣይም ኢትዮጵያ እና ተመድ በጋራ የሚያከናውኗቸውን ሥራዎች የበለጠ አጠናክረው በሚቀጥሉበት አግባብ ላይ መምከራቸውም ተነግሯል፡፡

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

ለሴት አካል ጉዳተኞች የርቀት ትምህርትን ለማዳረስ የፋይናንስ እና ቴክኖሎጂ እጥረት መኖሩ ተነገረ

መስከረም 14/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የርቀት ትምህርትን በጥራት ለአካል ጉዳተኛ ሴቶች ማዳረስ እንዳይቻል፤ የቴክኖሎጂ እና የፋይናንስ እጥረት መኖሩ ተመላክቷል፡፡

ይህ ሐሳብ የተነሳው፤ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን እና የትምህርት ጥራትን በሚለከት በተዘጋጀ አውደ-ጥናት ላይ ነው፡፡

በዚህ አውደ-ጥናት ላይ የቅድስት ማርያም፣ የደብረ-ብርሃን እና የወለጋ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ባቀረቡት የጥናት ወረቀት፤ የርቀት ትምህርትን ጥራት፣ የተማሪዎችን ውጤታማነትና የመማር ማስተማሩን ተግዳሮቶች ተዳሰዋል፡፡

በጥናቱም መንግሥት የርቀት ትምህርትን በሚመለከት ግልጽ ፖሊሲ አለማስቀመጡ እንዲሁም የፋይናንስ እና የቴክኖሎጂ እጥረት በመኖሩ፤ ለሴት አካል ጉዳተኞች የርቀት ትምህርትን በሚፈለገው ልክ ለማዳረስ አለመቻሉ ተጠቁሟል።

በመሆኑም ሴት አካል ጉዳተኞች የሚያጋጥማቸውን የፋይናንስ እና የቴክኖሎጂ እጥረት ለመቅረፍ እና ተግዳሮቶቻቸውን ለመቃለል እንዲቻል፤ መንግሥም ሆነ የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩበት እንደሚገባ ተመላክቷል፡፡

በተጨማሪም እንደ አጠቃላይ የርቀት ከፍተኛ ትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅና የተማሪዎችን ዉጤታማነት ለማሳደግ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅባቸውን ሊወጡ ይገባል ተብሏል፡፡

የቅድስተ ማርያም ዮኒቨርስቲ ላለፉት 11 ዓመታት ዓመታዊ የ“ኦፕን”ና የርቀት ትምህርት ጉባኤ ሲያካሂድ መቆየቱ ይታወቃል።

በፅዮን ይልማ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

"በኦሮሚያ ክልል ያለው ግጭት ትኩረት ተነፍጎታል" ኦፌኮ

መስከረም 13/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኦሮሚያ ክልል ያለው ግጭት  ትኩረት ተነፍጎታል ሲል የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ (ኦፌኮ) አስታወቀ፡፡

"ኦሮሚያ ክልል ውስጥ ከአንድ ቦታ ወደሌላ ቦታ ተንቀሰቅሶ ነገሮችን መከወን አለመቻል፣ መታገት ከዛም አለፍ ሲል መገደል የተለመደ ሆኗል" ሲልም ነው ፓርቲው የገለጸው፡፡

"ንጹሃን ዜጎች እየተገደሉ፣ ቤቶች በየዕለቱ እየተቃጠሉና እንስሳት እየተዘረፉ ያለበት ሁኔታ ቢኖርም፤ ይህንን መንግሥት ትኩረት ሊሰጠው አልቻለም" ሲሉ የፓርቲው ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሙላት ገመቹ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

"በክልሉ ውስጥ ሰላም ለማምጣት ለምን አትሰሩም" ተብለን እንወቀሳለን" ያሉት የፓርቲው ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር፤ "ከቦታ ቦታ መንቀሰቃስ በማይቻልበት ሁኔታ በጠላትነት በተፈረጅንበት እንዲሁም ታች ወረዳ ድረስ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ መደረግ በማይቻልበት  ሁኔታ ላይ መሆናችን መዘንጋት የለበትም" ብለዋል፡፡

ገዢው ፓርቲና መንግሥት ስለ ኢትዮጵያ የሚገልጹትና ነባራዊ ሀቁ ፈፅሞ የተለያየ እንደሆነ የገለጹት አቶ ሙላት "ይህ እውነታን የካደ ነው" ብለዋል፡፡

"ኦሮሚያ ክልል ከዛሬ ስድስት ዓመት ጀምሮ ከሚዲያ እይታ ውጪ ሆኗል። ክልሉ ላይ የሚፈጠረው ችግር ተመልካች ካጣም ቆይቷል" ሲሉም ቅሬታቸውን አሰምተዋል፡፡

እነዚህን ሁሉ ችግሮች የማቆም ወሳኝ ሚና መወጣት ያለበት መንግሥት መሆኑ የተገለጹም ሲሆን፤ "ነፍጥ አንግበው እየታገሉ ያሉትን አካላት በንጹህ ልብ ቀርቦ ማነጋገር አለበት" ብለዋል፡፡

"መንግሥት ግጭቶችና ጦርነትን ለማስቆም ቁርጠኛ መሆን አለበት" የሚሉት ደግሞ፤ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ደስታ ዲንቃ ናቸው፡፡

ሰብሳቢው አንድ አንድ ጉዳዮች በርግጥ ውስብስብ በመሆናቸው ነገሮችን በቶሎ ለመፍታት አስቸጋሪ መሆኑንም ጨምረው ተናግረዋል፡፡

"የመገንጠል ጥያቄ የሚያነሱ መኖራቸው መዘንጋት የለበትም" የሚሉት ሰብሳቢው፤ መንግሥት ቁርጠኛ በመሆን የውስጥ ችግሮችን መፍታት ይኖርበታል ብለዋል፡፡

በአቤል ደጀኔ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የትምህርት ስርዓቱን በማሻሻል ብቻ ለውጥ መጠበቅ አይቻልም ሲሉ ባለሙያዎች ገለጹ

መስከረም 13/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ በተለያዩ ጊዜያት የሚወጡ የትምህርት ስርዓት ፖሊሲ ለውጦችና ማሻሻያዎች መልካም ቢሆኑም፤ መሬት ላይ ወርደው ወደ ተግባር አለመምጣታቸው ማነቆ ሆኖ መቀጠሉን አሐዱ ያነጋገራቸው ባለሙያዎች ገልጸዋል።

"ኢትዮጵያ ውስጥ ትልቁ ችግር የተጠያቂነት አለመኖር ነው" የሚሉት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የስነ ትምህርትና ባህሪ ጥናት ኮሌጅ ባልደረባ ዶ/ር ካሳ ሚካኤል፤ የተቀመጠው መመሪያ በአፈጻጸም ክፍተት ምክንያት ባለመተግበሩ ለተፈጠረው ችግር ሃላፊነቱን የሚወስድ አካል አለመኖሩ ችግር ሆኖ መቀጠሉን አንስተዋል።

አክለውም " እኛ የመመሪያና የአዋጅ ችግር የለብንም" ያሉ ሲሆን፤ "ለምን መመሪያዎችን መሬት አውርዶ መስራት አልተቻለም? እንዲሁም እንዴት እና መቼ ወደ ተግባር እናምጣው? የሚለው ሊጤን የሚገባው ነው" ብለዋል።

አክለውም፤ በትምህርቱ መስክ ለሚታዩ ውድቀቶች የትምህርት ስርዓቱ ሳይሆን የትምህርት ስርዓቱን የሚያስፈጽሙ አካላት የሚኖራቸው ድርሻ ጉልህ መሆኑን ገልጸዋል።

ጠንካራ የትምህርት ስርዓት መገንባት ብቁ ተማሪዎችና እና መምህራንን ከመፍጠር አንጻር ያለው ሚና ጉልህ ነው የሚሉት ደግሞ ፕሮፌሰር ጥሩሰው ተፈራ ናቸው።

ለዚህም ከስርዓተ ትምህርቱ ተግባራዊነት ባሻገር የመምህራን ጥራት፣ የተማሪዎች እና የወላጆች ዝግጁነትም ለሚመጣው ውጤት የራሱ የሆነ አስተዋጾ እንዳለው ገለጸዋል።

ባለሙያዎቹ እንደ ሀገር የሚወጡ አዋጆች እና መመሪያዎች ላይ ችግር ባይኖርም፤ መመሪያዎችን ወደ ተግባር አውርዶ ለሚመጣው ውጤም ሃላፊነቱና እና ተጠያቂነትን የሚወስድ አካል ሊኖር እንደሚገባ አጽንዖት ሰጥተዋል።

እንዲሁም በችኮላ ያልተጤኑ፣ መቅደም ያለባቸው ነገሮችን ወደኃላ የሚያስቀሩ ውሳኔዎችን ከመወሰን መቆጠብ እንደሚገባም ለአሐዱ ገልጸዋል።

በፍርቱና ወልደአብ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በአሜሪካ በሰዎች መሃል በተነሳ ተኩስ 4 ሰዎች ሲገደሉ አስራ ስምንት ሰዎች መቁሰላቸው ተገለጸ

መስከረም 13/2017 (አሐዱ ራዲዮ) በአሜሪካ በርሚንግሃም፤ አላባማ ግዛት በሰዎች መሃል በተደረገ የተኩስ ልውውጥ አራት ሰዎች ሲሞቱ አስራ ስምንት ሰዎች መቁሰላቸው ተገልጿል።

በበርካታ ሰዎች መሃል የተነሳውን ተኩስ ተከትሎ፤ ፖሊስ በአካባቢው ላይ ደርሶ ግጭቱን ለማብረድ ጥረት ማድረጉን ኤቢሲ ኒውስ ዘግቧል፡፡

የበርሚንግሃም ፖሊስ ዲፓርትመንት ተኩሱን ለማብረድ በርካታ የፖሊስ መኮንኖች ቦታው ላይ መገኘታቸውን አስታውቋል፡፡

በተኩስ ልውውጡ አራት ሰዎች ሲሞቱ 18 የሚሆኑት መቁሰላቸውን የገለጸው ፖሊስ፤ በስፍራው በርካታ ሰዎች ሲተኩሱ ስለነበርና አካባቢውም በሰዎች የተጨናነቀ ስለነበር ማንንም በቁጥጥር ሥር ማዋል አለመቻሉን አስታውቋል፡፡

አሁንም ድረስ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር ለማዋል በመንቀሳቀስ ላይ እንደሚገኝም ነው ፖሊስ ያስታወቀው።

ተኩስ ልውውጡ ከተመቱት ከአራቱ ተጎጂዎች መካከል ሦስቱ እዛው ሕይወታቸው ሲያልፍ፤ አራተኛው ሰው ሆስፒታል ከገባ በሗላ መሞቱ ተነግሯል፡፡

በገነነ ብርሃኑ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

ሕገ-ወጥ ንግድ ላይ ማደያዎችም ሰለሚሳተፉበት ለመቆጣጠር አዳጋች መሆኑ ተገለጸ

መስከረም 13/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በሕገ-ወጥ የነዳጅ ንግድ ላይ ማደያዎችም ሰለሚሳተፉበት ለመቆጣጠር አዳጋች ሆኗል ሲል የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን ለአሐዱ ገልጿል።

በኢትዮጵያ ያለው ነዳጅ አቅርቦት ጉዳይ በተለይም የቤንዚን አቅርቦት ችግር በተደጋጋሚ የሚነሳ ሲሆን፤ በክልሎች ላይ ደግሞ ችግሩ ይበልጥ አሳሳቢ ሆኗል።

አሐዱም በዚህ ልክ ችግሩ ጎልቶ እንዲታይ ያደረገው ምንድን ነው? ሲል የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣንን ጠይቋል።

ባገኘው ምላሽም በክልሎች ያለው የነዳጅ የጥቁር ገበያ ሁኔታ እየተባባሰ እና የቁጥጥር አቅምን እየፈተነ መሆኑን ለማወቅ ችሏል።

"ወደ ክልሎች ነዳጅ ይላካል! ነገር ግን የጥቁር ገበያው ሥራ ላይ ማደያዎችም ስለሚሳተፉበት ችግሩን መቅረፍ አልተቻለም" ሲሉም የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሳህረላ አብዱላሂ ተናግረዋል፡፡

በነዳጅ ምርቶች ላይ የሚካሄደው የጥቁር ገበያ ንግድ የምርት አቅርቦትና ስርጭትን እያስተጓጎለ እንደሚገኝም አስረድተዋል፡፡

"የቁጥጥር ሥራውን በቅርበት ለመከታተል ሥራውን ወደ ክልሎች ያወረደው ቢሆንም፤ አሁንም ችግሩ አለ" ሲሉም ነው ዋና ዳይሬክተሯ ያነሱት፡፡

አክለውም የቁጥጥር ሥራው ላይ የእኔነት ስሜትን መፍጠር እና ህብረተሰቡ እንዲከላከል ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከሰሞኑ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የክልል ከተሞች በተለያዩ ማድያዎች ረጃጅም ሰልፎች እየተስተዋሉ ነው፡፡ ይህንንም ተከትሎ አሽከርካሪዎችና ሹፌሮች ቀናቸውን በሙሉ በቤንዚን ሰልፎች ላይ ለማሳለፍ በመገደዳቸው ሥራቸውን በአግባቡ ለመስራት መቸገራቸውን እየገለጹ ይገኛሉ፡፡

በእመቤት ሲሳይ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በሰሜን ወሎ ዞን ትናንት ምሽት በተነሳ የእሳት ቃጠሎ 31 የንግድ ሱቆች ሙሉ በሙሉ መውደማቸው ተገለጸ

መስከረም 13/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በሰሜን ወሎ ዞን መርሳ ከተማ ውስጥ በተለምዶ ሥሙ መናኸሪያ አካባቢ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ትናንት ምሽት 05:00 ገደማ በተነሳ የሳት ቃጠሎ 31 የንግድ ሱቆች ሙሉ በሙሉ በቃጠሎው መውደማቸው ተገልጿል።

ሱቆቹ የአልባሳት፣ የሸቀጣሸቀጥ፣ የኤሌክትሮኒክስ፣ ማተሚያ ቤትንና የመሳሰሉትን ያካተቱ ሲሆን፤ ባለቤትነታቸው የአካባቢው ወጣቶች መሆናቸው ተነግሯል።

የቃጠሎውን መንስኤ፣ አጠቃላይ የወደመውን ንብረት ግምትና ወደፊት ሰለሚወሰዱ የመፍትሄ እርምጃዎች ከመንግሥትና ከንግዱ ማህበረሰብ የተውጣጣ ኮሚቴ ተዋቅሮ መረጃዎችን በማጠናቀር ላይ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ በቀጣይ ሲጠናቀቅ ይፋ ይደረጋል ተብሏል።

ቃጠሎው ወደሌሎች ንግድ ቤቶችና ድርጅቶች ተስፋፍቶ የበለጠ ውድመት እንዳያደርስ፤ የአከባቢው ነዋሪዎች፣ የጸጥታ አካላት፣ የውሃ አገልግሎት ተቋማት ባለሙያዎችና ውሃ አቅራቢ ግለሰቦች ሚናቸው ትልቅ እንደነበር የከተማዋ ኮምዩኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል፡፡

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

Update
የካሳንቺስ የልማት ተነሺዎች 239 የኮንዶሚኒየምና 110 የመንግሥት መኖሪያ ቤቶችን ዕጣ አወጡ


መስከረም 13/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቂርቆስ ክ/ከተማ የካዛንቺስ አካባቢ የልማት ተነሺ ነዋሪዎች የመንግሥትና የኮንዶሚኒየም መኖሪያ ቤቶች ዕጣ የማውጣት ሥነ ስርዓት ተካሂዷል።

በስድስት ቀናት ውስጥ 742 የካሳንቺስ የልማት ተነሺዎች የመንግሥትና የኮንዶሚኒየም መኖሪያ ቤት ዕጣ በማውጣት ቤታቸውን እየተረከቡ መሆኑንም የአስተዳደሩ ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል፡፡

ከወጣው ዕጣ መካከል 503 ባለ አንድ እና ባለ ሁለት መኝታ የመንግሥት መኖሪያ ቤቶችን እንዲሁም 239 ስቱዲዮ የኮንዶሚኒየም ቤቶች መሆናቸው ተነግሯል።

በዚሁ መሰረት በአቃቂ፣ በቦሌ አራብሳ፣ ገላን፣ ፈረንሳይ ጉራራ እና ጃርሶ ሳይት የመኖሪያ መንደሮች ለባለእድለኞች ተደራሽ እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል።
የዕጣ ማውጣት ሥነ ስርዓቱ በቀጣይ ቀናትም እንደሚከናወን ተጠቁሟል።

የልማቱ ተነሺዎች ማንኛውም አይነት ቅሬታ ካላቸው ከባንቢስ ወደ ደንበል በሚወስደው የቤቶች ኮርፖሬሽን ወይም በክፍለ ከተማው አስተዳደር 10ኛ ፎቅ ወደተቋቋመው የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ በአካል በመቅረብ ወይም በ9065 ነፃ የስልክ መስመር ማቅረብ እንደሚችሉም ተነግሯል።

በኮሪደር ልማቱ ምክንያት ከመስከረም 20 ቀን 2017 በፊት ከመኖሪያቸው እንደሚነሱ የተነገራቸው የካዛንቺስ አካባቢ ነዋሪዎች ቅሬታቸውን ለአሐዱ ማሰማታቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

በቅሬታቸውም "የመኖርያ መንደራችን እንደሚፈርስ በአዲስ አበባ ከንቲባ ተነግሮን በውይይት ላይ ሳለን፤ ውይይታችን ሳይቋጭ ከመስከረም 20 በፊት “ንብረታችሁን ሰብስባችሁ፣ ቤታችሁን ለቃችሁ ውጡ” እየተባልን በፖሊስ መገደዳችን ቅር አሰኝቶናል" ብለው ነበር፡፡

ይህ የመንግሥትና የኮንዶሚኒየም መኖሪያ ቤት እጣ የማውጣት ስነ ስርዓት፤ ለዚሁ የነዋሪዎች ቅሬታ ምላሽ ይሆናል ተብሎ ታምኖበታል፡፡

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

መልካም ቀን!
አሐዱ ሬድዮ 94.3  የኢትዮጵያውያን ድምፅ!

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

አምራች ኢንዱስትሪዎች የውጭ ምንዛሪ እጥረት እንዳይገጥማቸው ከባንኮች ጋር ድርድር መጀመሩ ተገለጸ

መስከረም 11/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ የሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎች ለጥሬ እቃ ማስመጫ የሚውል የውጭ ምንዛሪ እጥረት እንዳይገጥማቸው፤ ከባንኮች ጋር ድርድር መጀመሩን የኢንዱስትሪ ሚኒሰቴር አስታወቀ።

ቀደም ባሉ ጊዜያቶች አምራች ኢንዱስትሪዎች በግብአት እጥረት ምክንያት ሥራቸውን ያቋረጡ መኖራቸውን የሚታወቅ ሲሆን፤ አሁን ላይ ችግሩ እንዳይደገም በብርቱ እየተሰራበት መሆኑን ሚኒስቴሩ ተናግሯል።

በተያዘው በጀት ዓመትም በርካታ ባለሐብቶች ፋብሪካዎቻቸውን ሥራ እንዲያስጀምሩ መንግሥት እንቅስቃሴዎች መጀመሩን በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የመሰረተ ልማትና የግብአት ዘርፍ አማካሪ ዳንኤል ኦላኔ ለአሐዱ ገልጸዋል።

ባለፈው ዓመት በርከት ያለ ብድር ከልማት ባንክ የቀረበላቸው ቢሆንም፤ ከግል ባንኮች እየቀረበ ያለው የብድር ምጣኔ አነስተኛ መሆኑን ነው አማካሪው የገለጹት።

ይህንንም ለማበረታታት የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴ ጋር እየተመከረበት እንደሚገኝ አስረድተዋል።

አሁን ላይ ለአምራች ኢንዱስትሪዎች እየተደረገ ያለው ድጋፍ እንዲቀጥልም አስቻይ ሁኔታዎች እየተዘረጉ ይገኛሉ ሲሉ አማካሪው ዳንኤል ኦላኔ ለአሐዱ ተናግረዋል።

ባለፉት ሦስት ዓመታት የአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ብድር ችግር እየተፈተነ መቆየቱን የሚታወቅ ነው።

በአማኑኤል ክንደያ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የሀንጋሪው ጠ/ሚኒስትር አገራቸው በምትሸጠው የጦር መሳርያ ለተገደሉት ሰዎች ይቅርታ ጠየቁ

መስከረም 11/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የሀንጋሪው ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶር ኦርባን አገራቸው በምትሸጠው የጦር መሳርያ ለተገደሉት ሰዎች ይቅርታ መጠየቃቸውን ተሰምቷል።

የሀንጋሪ ጦር አምራች ምርት ኩባንያ በሊባኖስ የግድያው ጋር ሥሙ በመያያዙ የተነሳ በአገሪቱ ቁጣ ቀስቅሷል ተብሏል።

ጦሩን የተኮሰችው እስራኤል መሆንዋን አረጋግጠናል ሲሉ የሀንጋሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶር ኦርባን ተናግረዋል።

የሌላ ሀገር ነዋሪዎች በሀገራቸው በተመረቱ መሳሪያዎች መገደላቸውንና በግድያው የሀገራቸው ሥም መጠቀሱ እንዳሳዘናቸውም ገልጸዋል።

የእስራኤል ድርጊቶች ዓለም አቀፍ ህግን የሚጥሱ ናቸው መባሉን አናዱሉን ጠቅሶ ሚዲል ኢስት ሞኒተር ዘግቧል።

በአማኑኤል ክንደያ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በቤንዝል እጥረት ምክንያት ሥራ መስራት አልቻልንም ሲሉ አሽከርካሪዎች ቅሬታ አቀረቡ

መስከረም 11/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በአዲስ አበባ ትናትን ጨምሮ በተለያዩ ማድያዎች ረጃጅም ሰልፎች መኖራቸውን አሐዱ ለመታዘብ ችሏል፡፡

"ሰሞኑ በተከሰተ የነዳጅ እጥረት ምክንያት የበቤንዝል እጥረት በመኖሩ ሥራችንን መስራት አልቻልንም" ሲሉ አሽከርካሪዎች ቅሬታቸውን ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

ለተማሪዎች የሰርቪስ አገልግሎት ለመስጠት፣ ህሙማንን ለማድረስ፣ እንዲሁም ለሌሎች እንቅስቃሴዎችን ለማድረግ መገደባቸውን የተናገሩት ቅሬታ አቅራቢዎቹ፤ እንዲህ አይነት ችግሮች ሲያጋጥም ቀድሞ ማሳወቅ እንደሚያስፍልግም አንስተዋል፡፡

የአቅርቦት እጥረት እንደሌለ መንግሥት በተደጋጋሚ ቢናገርም፤ በብዙ ቦታዎች ላይ እጥረት መኖሩንም አሽከርካሪዎቹ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

ቅሬታውን አስመልክቶ አሀዱ የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣንን ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡ በቀጣይ ምላሽ በሰጡን ሰዐት ይዘን እንመለሳለን፡፡

በዳግም ተገኘ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የግብፅ መንግሥት ወደ ሶማሊያ የጦር መሳሪያ መላኩን አረጋገጠ

መስከረም 14/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ኢትዮጵያ ከሱማሌላንድ ጋር ባደረገችው ስምምነት ምክንያት የግብፅ መንግሥት ወደ ሶማሊያ የጦር መሳሪያ መላኩን አረጋግጧል።

ኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ በፈረንጆቹ ጥር ወር 2024 የተፈራረሙት የመግባቢያ ሰነድ ኢትዮጵያ 20 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለውን የባህር በር ለ50 ዓመታት ከሶማሌላንድ በሊዝ እንድትከራይ የሚፈቅድ ሲሆን፤ ይህን ተከትሎ ሶማሊያ "ስምምነቱን ሉዓላዊነቴን የሚጥስ ነው" ማለቷ ይታወሳል፡፡

በዚህም ምክንያት ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ጋር የገባችውን ስምምነት እንድትሰርዝ እና የሶማሊያን ሉዓላዊነት እንድታከብር ጠይቃለች።

በሌላ በኩል የናይል ወንዝን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ጋር የተለየ ውዝግብ ያላት ግብፅ ደግሞ፤ ሶማሊያን በጽኑ የመደገፍ አዝማሚያን እያሳየች ትገኛለች።

የግብፅ እና የሶማሊያ መሪዎች በነሀሴ ወር የመከላከያ ስምምነት የተፈራረሙ ሲሆን፥ በዚህም ስምምነት መሰረት ከሳምንታት በፊት ሁለት የግብፅ ወታደራዊ አውሮፕላኖች የጦር መሳሪያ ጭነው ሞቃዲሾ መግባታቸው ተገልጾ ነበር፡፡

ከቀናቶች በፊት እሁድ ዕለት ደግሞ ሁለት የግብፅ ወታደራዊ አውሮፕላኖች የጦር መሳሪያ ጭነው ሞቃዲሾ መግባታቸው ተገልጿል፡፡

እነዚህ በግብፅ ወታደሮች በሚተዳደሩ የጭነት መርከቦች የጦር መሳሪያ ጭነው ሞቃዲሾ መግባታቸው፤ የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ታሚም ካላፍ በሰጡት መግለጫ አረጋግጠዋል።

“ግብፅ በሶማሊያ ጸጥታንና መረጋጋትን ለማስፈን፣ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት እና ሉዓላዊነቷን፣ የግዛት አንድነቷን ለማስጠበቅ የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ፤ የግብፅ ወታደራዊ የጭነት መርከቦች የጦር መሳሪያዎችን ጭነው ወደ ሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ ደርሰዋል።” ሲሉም ነው ቃል አቀባዩ በመግለጫቸው የተናገሩት።

በጉዳዩ ላይ እስካሁን ከሶማሊያ መንግሥት የተሰጠ ይፋዊ መግለጫ ባይኖርም፤ የመከላከያ ሚኒስትሩ አብዱልቃድር መሀመድ ኑር እና የሶማሊያ ጦር አዛዥ ጄኔራል ኢብራሂም ሼክ ሙህያዲን፤ በግብፅ ባንዲራ ከታጠቀች መርከብ የጦር መሳሪያዎችን በሞቃዲሾ ወደብ ሲያወርዱ የሚያሳዩ ፎቶግራፎች በማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ ሲዘዋወሩ ታይተዋል፡፡

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት ሰላም ማስከበር ተልዕኮ አካል ሆኖ በሶማሊያ በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች እንዳሏት የሚታወቅ ሲሆን፤ ሶማሊያ ከሶማሌላንድ ጋር የተደረሰውን ስምምነት እስካልሰረዘ ድረስ እነዚህ ወታደሮች አገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ ማስተላለፏ ይታወሳል።

በቦታውም የግብፅ ሰላም አስከባሪ ኃይል እንዲተካ ለማድረግ መጠነ ሰፊ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ ላይ ትገኛለች፡፡

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሤ ከተመድ የሰላም ግንባታ እና ፖለቲካ ጉዳዮች ረዳት ዋና ፀሐፊ ሮዝማሪ ዲካርሎ ጋር ባደረጉት ውይይት፤ "ባልተረጋጋ የደህንነት ሁኔታ ውስጥ በውጭ ኃይላት የሚደረግ የጦር መሣሪያ አቅርቦት መጨረሻው አሸባሪዎች እጅ ላይ ሊወደቅ ይችላል" ሲሉ ለሶማሊያ ያላቸውን ስጋት መግለጻቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

እናት ባንክ ለእነ ሕፃን ሶሊያና የትምህርት ቤት ወጪ የሚሆን የገንዘብ ድጋፍ አበረከተ

መስከረም 14/2017 (አሐዱ ራዲዮ) እናት ባንክ ለሕፃን ሶሊያና፣ ለሕፃን ሄራን እና ለሕፃን አናኒያ የትምህርት ቤት ወጪ የሚሸፍን የሦስት መቶ ሺህ ብር የገንዘብ ድጋፍ በዛሬው ዕለት አበርክቷል።

እናት ባንክ አዲሱን ዓመትና በቀጣይ የሚከበረውን የመስቀል በዓልን ምክንያት በማድረግ ስጦታውን ያበረከተ ሲሆን፤ የሕጻናቱ እናት ወይዘሮ ትግስት ካሳ እና ሕጻናቶቹ እናት ባንክ ላደረገላቸው የገንዘብ ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ሕፃን ሶሊያና እና ሕፃን ሄራን በቅርቡ ህብረተሰቡ ባደረገው እርብርብ ለአይን ህክምና ወደ ባንኮክ ያቀኑ ሲሆን፤ ዐይናቸው ታክሞ ማየት እንደማይችሉ ተነግሯቸው ወደሀገራቸው መመለሳቸው ይታወሳል።

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የመስቀል በዓል ሃይማኖታዊ እሴቱን ጠብቆ እንዲከበር ከባለድርሻ አካላት ጋር በቂ ዝግጅት መደረጉ ተገለጸ

መስከረም 14/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የመስቀል ደመራ በዓል ሃይማኖታዊ ቱውፊቱን ጠብቆ በሰላም እንዲከበር ከኃይማኖት አባቶች ጋር በመሆን በቂ ዝግጅት መደረጉን የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ አስታውቋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የደመራና የመስቀል አከባበርን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሃይማኖት አባቶች ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሃላፊ ሊዲያ ግርማ እንደገለጹት፤ የደመራና የመስቀል በዓል ሃይማኖታዊ እሴቱን ጠብቆ በድምቀትና በሰላም እንዲከበር ከባለድርሻ አካላት ጋር በቂ ዝግጅት ተደርጓል።

የመስቀል ደመራ በዓል በዓለም ቅርስነት የተመዘገበና ከሃይማኖታዊ እሴቱ ባሻገር የኢትዮጵያዊያን አብሮነት መገለጫ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በመሆኑም በዓሉ ሃይማኖታዊ ትውፊቱን ጠብቆ በሰላም እንዲከበር በትብብርና በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።

በተለይ የሃይማኖት አባቶችና የእምነቱ ተከታዮች በዓሉ በድምቀትና በሰላም እንዲከበር ሚናቸው የጎላ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የአዲስ አበባ ሃይማኖት ጉባኤ ዋና ፀሀፊ መጋቢ ታምራት አበጋዝ በበኩላቸው፤ የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በዓሉ ሃይማኖታዊ ትውፊቱን ጠብቆ በሰላም እንዲከበር ከሚመለከታቸው የሃይማኖት አባቶችና ከመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመተባበር ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል።

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!

ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

"ጀነራል ፃድቃን የቆየ ቂም በመወጣት፤ ስልጣን ለመጠቅለል አቅዷል" ደብረፅዮን ገብረሚካኤል

መስከረም 14/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዝደንት የሆኑት ጀነራል ፃድቃን ገብረትንሳኤ "የቆየ ቂም በመወጣት ስልጣን ለመጠቅለል በማቀድ ላይ ናቸው" ሲሉ ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ከሰዋል፡፡

ህወሓት ባለፉት ቀናት መቐለን ጨምሮ በተለያዩ የትግራይ ከተሞች ህዝባዊ የተባሉ ስብሰባዎች ያካሄደ ሲሆን፤ በእነዚህ መድረኮች ላይ የፖርቲው አመራሮች ክፍፍል በስፋት መነሳቱ ተገልጿል፡፡

በመድረኮቹም ህወሓትን ለማጥፋት፣ ስልጣን ለመጠቅለል የሚንቀሳቀሱ ተብለው የተገለጹ አመራሮች በሥም እየተጠቀሱ ወቀሳ እንደተሰነዘረባቸው ተሰምቷል፡፡

ባሳለፍነው ቅዳሜ በመቐለ በተካሄደ መድረክ ላይ ንግግር ያደረጉት የህወሓት ሊቀመንበሩ ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል፤ የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዝደንት የሆኑት ጀነራል ፃድቃን ገብረትንሳኤን፥ ስልጣን ለመጠቅለል በማቀድ፣ የቆየ ቂም በመወጣት እና ሌሎች በርካታ ጉዳዮች በማንሳት እንዲሁም ከዚህ በፊት በይፋ ያልተሰሙ መረጃዎች በመግለፅ ሲተቹም ተደምጠዋል።

በዚሁ ንግግራቸው እርሳቸው የሚመሩትን ህወሓት ሰላም የማይፈልግ አድርጎ የማቅረብ የተሳሳተ ፍረጃ ከትግራይ ባለስልጣናት በኩል እየቀረበበት መሆኑ ገልጸው፤ "ይህ ውሸት ነው" በማለት ወቀሳውን ማጣጣላቸውን ዶቼቨለ ዘግቧል፡፡

ደብረፅዮን አክለውም፤ "ለምሳሌ በደቡባዊ ዞን በተደረገ መድረክ ጀነራል ፃድቃን እኛ ሰላም እንፈልጋለን፣ እነሱ የሚሹት ጦርነት ነው" ሲል ሰምታችሁታል" ብለዋል።

"በጦርነቱ ወቅት ደሴ ተሻግረን ሰሜን ሸዋ ስንጠጋ፥ "ድርድር ያስፈልጋል ወይ?" ሲባል እኔ አዎን ያስፈልጋል ነው ያልኩት። በሰላም ሊፈታ ስለሚገባው። እሱ ግን "ከማን ጋር ነው የምንደራደረው፣ ውጊያው አልቋል" ሲል የነበረ ነው። አሁን ግን እኔ ሰላም ነኝ እነሱ ጦርነት ናቸው የሚፈልጉ ማለት ጀመረ" ሲሉ ጀነራል ፃድቃን ተችተዋል።

በተያያዘ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ካቢኔ ካደረገው መደበኛ ስብሰባ በኃላ ትላንት በክልሉ ኮምኒኬሽን ቢሮ በኩል ባሰራጨው መግለጫ፤ "በክልሉ ያለው ፖለቲካዊ ችግር በህወሓት እና የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር መካከል የተፈጠረ አለመግባባት አድርጎ ማቅረቅ የተሳሳተ ነው" ያለ ሲሆን፤ ችግሩ በህወሓት ከፍተኛ አመራሮች መካከል የተፈጠረ መሆኑን ገልጿል፡፡

ነገር ግን ይህ በህወሓት አመራሮች መካከል የተፈጠረው ክፍፍል የአስተዳደር ሥራዎችን እያደናቀፈ ስለመሆኑ ገልጿል፡፡

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

መልካም ቀን!
አሐዱ ሬድዮ 94.3  የኢትዮጵያውያን ድምፅ!

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በሰቆጣ ተፈናቅለው የሚገኙ ከ17 ሺሕ በላይ ዜጎች ለከፋ ረሀብ መዳረጋቸውን ገለጹ

መስከረም 13/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በአማራ ክልል በዋግ ኽምራ ዞን ሰቆጣ ከተማ የሚገኙ ተፈናቃዮች፤ የሚደረግላቸውን ድጋፍ በቂ ባለመሆኑ ምክንያት ለከፋ ረሃብና ለተለያዩ ችግሮች እየተጋለጡ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በዋግ ኽምራ ዞን ሰቆጣ አካባቢ ብቻ 17 ሺሕ 8 መቶ 40 የሚሆኑ ተፈናቃዮች እንደሚገኙ የተገለጸ ሲሆን፤ ተፈናቃዮቹ አሁን ካሉበት አስከፊ ሁኔታ ለማውጣት ዘላቂ መፍትሔ ሊሰጥ እንደሚገባ ተመላክቷል፡፡

ተፈናቃዮቹም በቂ ድጋፍ እየተደረገላቸው እንዳልሆነ ገልጸው፤ ወደቀያቸው እንዲመለሱ "የሚመለከተው አካል መፍትሔ ይሰጠን" ሲሉ ቅሬታቸውን አንስተዋል፡፡

እስከ አሁን የተወሰኑ የግብረ ሰናይ ድርጅቶችና በዞኑ በኩል የሚደረግ የምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ድጋፎች እንደነበሩም ገልጸው፤ በአሁኑ ወቅት ግን ያ ድጋፍ መቋረጡን ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

አክለውም፤ "ይህንን ችግር የሚመለከተው አካል ትኩረት ሰቶ ዘላቂ መፍትሔ ይሰጠን" ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

አሐዱም የዋግ ኽምራ ዞን አደጋ ስጋትና ምግብ ዋስትና አስተባባሪ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ምህረት መላኩን ስለጉዳዩ ጠይቋል፡፡

ኃላፊው በምላሻቸውም በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ዞን ሰቆጣ ከተማ ብቻ 17 ሺሕ 8 መቶ 40 የሚሆኑ ተፈናቃዮች እንዳሉ አንስተው፤ ዞኑ በሚችለው አቅም ድጋፍ እያደረገላቸው እንዳለና ከተፈናቃዮች ብዛት አንጻር ግን የሚደረገው እርዳታ ድጋፍ በቂ እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡

ከዚህ በፊት በአንዳንድ የግብረ ሰናይ ድርጅቶችም ድጋፍ እየተደረገላቸው እንደነበረ ያነሱት ኃላፊው፤ በክልል ደረጃ ይመጣል ተብሎ ታስቦ የነበረ ድጋፍ ባለው የጸጥታ ችግርና የመንገድ መዘጋት ምክንያት መግባት አለመቻሉን ገልጸዋል፡፡

አክለውም፤ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍና ለተፈናቃዮች ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት ከሚመለከተው አካል በጋራ በመሆን መፍትሔ ለመስጠት ጥረት እየተደረገ መሆኑን አንሰተዋል፡፡

በአለምነው ሹሙ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የቁም እንስሳትን በባቡር ወደ ጅቡቲ ማጓጓዝ ጀመረች

መስከረም 13/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ከአዳማ ወደ ጂቡቲ የቁም እንስሳት የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ይፋ መሆኑን የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር አክሲዮን ማኅበር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ታከለ ኡማ አስታውቀዋል፡፡

የባቡር ትራንስፖርት ከዚህ በፊት ወደ ሀገር ውስጥ ገቢ ምርቶችን ለማስገባት ብቻ የሚያገለግል እንደነበር ያስታወሱት ኢንጂነር ታከለ ኡማ፤ "ይህን አገልግሎት በመጀመራችን አቅማችን ከፍ ያደርገዋል" ብለዋል፡፡

በአዳማ በኩል የኢትዮ-ጂቡቲ የባቡር ትንስፖርትን ወደ ውጭ ሀገራት ጥራት ያለውን የስጋ ምርት የመላክ አቅምን ከመጨመሩም ባሻገር የትራንስፖርት መጨናነቅን ይቀንሳል ሲሉም ኢንጂነር ታከለ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ገልጸዋል፡፡

አክለውም፤ "የአገልግሎቱ ይፋ መሆን ኢትዮጵያ በዘርፉ ውጤታማና ቀጣይነት ያለው ንግድ ለማካሄድ ቁርጠኛ መሆኗን ያሳየችበት ነው" ብለዋል፡፡

በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በበኩሉ፤ "በቀንድ ከብት ከአፍሪካ ቀዳሚ አገር የሆነችው ኢትዮጵያ የውጭ ንግድን ለማስፋት ከሚሌ ኳረንቲ ቀጥሎ ዛሬ በባቡር ከአዳማ ወደ ጅቡቲ የቁም እንስሳትን የመላክ ሥራ ተጀምሯል" ብሏል፡፡

ይህም ተግባር ድንበር ላይ ያለውን ህገወጥ ንግድ ከመቀነሱ ባሻገር የአገር ገቢ በአግባቡ እንዲሰበሰብ እንደሚረዳም ተመላክቷል።

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

እስራኤል እና ሄዝቦላህ ላለፉት ሁለት ቀናት ከባድ ተኩሶችን መለዋወጣቸው ተገለጸ

መስከረም 13/2017 (አሐዱ ራዲዮ) ከቀናት በፊት ሄዝቦላህ ወደ እስራኤል ያስወነጨፋቸውን በመቶዎች የሚቆጠሩ ሮኬቶች ተከትሎ፤ እስራኤል የአጸፋ እርምጃ በመውሰድ ላይ እንደምትገኝ ተገልጿል፡፡

በዚህም በሊባኖስ ዋና ከተማ ቤሩት ላይ በፈጸመችው የአየር ጥቃት፤ የሄዝቦላህ ከፍተኛ ጦር አዛዥ ኢብራሂም አቂልን ጨምሮ፤ ከ30 በላይ ሰዎች እንደሞቱ ተነግሯል፡፡

የእስራኤል መከላከያ ሚንስትር ዮአቭ ጋላንት "ከሰሜን እስራኤል የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀያቸው ለመመለስ አስተማማኝ እስኪሆን ድረስ ጥቃቱ ይቀጥላል" ብለዋል፡፡

ሄዝቦላ በተመሳሳይ እስራኤል በጋዛ የምታደርገው ወረራ እስካልቆመ ድረስ መዋጋቱን እንደሚቀጥል አስታውቋል፡፡

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚንስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ በሰጡት የቪዲዮ መግለጫ፤ "ከቅርብ ቀናት ወዲህ ሄዝቦላህ ያላሰበውን ተከታታይ ድብደባ ፈጽመንበታል" ያሉ ሲሆን፤ "አሁንም ሄዝቦላህ መልዕክቱን ካልተረዳው ወደፊት እንዲረዳው እንደምናደርገው ቃል እገባላችሗለሁ" ብለዋል፡፡

የእስራኤል ጦር ቅዳሜ ዕለት የሄዝቦላን በሺዎች የሚቆጠሩ የሮኬት ማስወንጨፊያ በርሜሎችን ማውደሙን የገለጸ ሲሆን፤ እረምጃው እንደሚቀጥልም አስታውቋል፡፡

እስራኤል በሰሜናዊ ክፍሏ ያሉ ትምህርት ቤቶችን እንደዘጋችና ስብሰባዎችንም ለጊዜው እንደከለከለች የሮይተርስ ዘገባ አመላክቷል።

በገነነ ብርሃኑ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በፓኪስታን የኢትዮጵያ አምባሳደር ጀማል በኽር የሚገኙበት የዲፕሎማቲክ ኮንቮይ ላይ የሽብር ጥቃት ተፈጸመ

መስከረም 13/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በፓኪስታን በከይበር ፓክቱንክዋ ግዛት የኢትዮጵያ አምባሳደር ጀማል በኽር የሚገኙበት የዲፕሎማቲክ ኮንቮይ ላይ የሽብር ጥቃት መፈጸሙ ተገልጿል፡፡

የዲፕሎማቲክ ኮንቮዩ የኢትዮጵያ አምባሳደር ጀማል በኽርን ጨምሮ፣ ሩዋንዳ፣ ዚምባብዌ፣ የኢንዶኔሲያ እና የሌሎች ሀገራት አምባሳደሮችን አካቷል ተብሏል፡፡

እነዚህ ከ11 አገራት የተውጣጡ ዲፕሎማቶች በደረሰው የሽብር ጥቃት ጉዳት ባይደርስባቸውም የአንድ ፖሊስ ህይወት ሲቀጥፍ ሦስት ፖሊሶችን ማቁሰሉ ተነግሯል፡፡

ኢትዮጵያ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል፤ የተፈጸመውን የሽብር ጥቃት አውግዛ፤ ዲፕሎማቶቹን ሲያጅብ ለነበረው የሟች ፖሊስ ቤተሰብም መጽናናትን ተመኝታለች፡፡

የሽብር ጥቃቱን በጽኑ ያወገዘችው ኢትዮጵያ ለፓኪስታን ሕዝብና መንግሥትም መጽናናትን መመኘቷን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር የምታደርገው የንግድ ልውውጥ በንግድ ባንክ ብቻ እንዲፈጸም የቀረበው ሕግ በግል ባንኮች ላይ ተፅዕኖ ይፈጥራል ተባለ

መስከረም 13/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር የምታደርገው የንግድ ልውውጥ በንግድ ባንክ ብቻ እንዲፈጸም የቀረበው ሕግ፤ በግል ባንኮች ላይ ተፅዕኖ እንደሚያሳድር የምጣኔ ሐብት ባለሞያዎች ለአሐዱ ገልጸዋል።

ይህም ውሳኔ የፋይናንስ ስርዓቱን ሚዛን የሚያዛባ መሆኑን ነው ባለሞያዎቹ የተናገሩት።

ውሳኔው የግል ባንኮች ደንበኞች ላይ የፋይናንስ  ነፃነትና አማራጭ የመጠቀም መብት የሚያሳጣ ነው ሲሉም አስተያየታቸውን ሰጥተዋልል ።

መንግሥት "በንግድ ባንክ ብቻ እንድትጠቀሙ" ሲል ያሳለፈው ውሳኔ፤ የተነቃቃውን የፋይናንስ ስርዓት እንቅፋት የሚፈጥር መሆኑን የተናገሩት፤ በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ማሕበር ተመራማሪው ዶክተር ደግዮ ጎሹ ናቸው።

በቅርቡም ኢትዮጵያና ቻይና በየገንዘቦቻቸው እንዲገበያዩ የገቡት ስምምነት በንግድ ስርዓቱ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ ማሳደሩ እንደማይቀር ዶክተር ደግዮ ተናግረዋል።

መንግሥት ተግባራዊ እያደረገው ካለው የፋይናንስ ስርዓት አንፃር የባንኮችን ውድድር የሚገድብ መሆን እንደሌለበትም ገልጸዋል።

ልላኛው የምጣኔ ሀብት ባለሙያ ዶክተር ቆስጠንጢንዮስ በርኸተስፋ በበኩላቸው፤ መንግሥት ያሳለፈው ውሳኔ የእዳ ጫና ማቃለያ ስልት መሆኑን ጠቅሰው፣ ይህም ከውጭ ምንዛሪ አተገባበሩ ላይ ያላቸው ተፅዕኖ ሊኖረው ይችላል ብለዋልል።

ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር የምታከናውን የንግድ ስርአት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሽቆለቆለ መምጣቱ ሲገለፅ ቆይቷል።

ለዚህም መንግሥት የግል ባንኮች ላይ ያሳየው ተፅዕኖ ሳይሆን እንዳልቀረ የምጣኔ ሐብት ባለሞያዎቹ ነግረውናል።

ቻይና ከኢትዮጵያ ትላልቅ የንግድ አጋር አገራት መካከል አንዷ ነች። ኢትዮጵያ በዋነኛነት አበባ፣ የዘይት ዘር፣ ቡናና ስጋን ወደ ቻይና የምትልክ ሲሆን፤ ሰፊ ምርቶችንም ወደ አገር ውስጥ ታስገባለች።

በአማኑኤል ክንደያ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

መልካም ቀን!
አሐዱ ሬድዮ 94.3  የኢትዮጵያውያን ድምፅ!

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

ምርጫ ቦርድ ዕውቅና አልሰጠኝም ሲል የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አስታወቀ

መስከረም 11/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዕውቅና አልሰጠኝም ሲል የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ለአሐዱ አስታውቋል፡፡

"ለቦርዱ ተደጋጋሚ የዕውቅና ማረጋጋጫ ሰርተፍኬት እንዲሰጠን የጠየቅን ቢሆንም ጥያቄያችንን ውድቅ አድርጓታል" ሲልም ነው ምክር ቤቱ የገለጸው፡፡

"ምክር ቤቱ ለመክሰስም ሆነ ለመከሰስ እንዲሁም ከሌሎች ሦስተኛ ባለድርሻዎች ጋር ግንኙነት ለመፍጠር ዕውቅናው አስፈላጊ ነው" ሲሉ የምክር ቤቱ ሰብሳቢ ደስታ ዲንቃ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

ምርጫ ቦርድ ፖለቲካ ፖርቲዎችን፣ ጥምረቶችንና ቅንጅቶችን የሚመዘግብ በመሆኑ፤ ፓርቲዎችን ጠቅለል አድርጎ ለያዘው ለምክር ቤቱም የምስክር ወረቀቱ ሊሰጠው ይገባል ብለዋል፡፡

"ተደጋጋሚ ጥያቄዎች በምናቀርብ ወቅት በደብዳቤ አይሆንም የሚል ምላሽ ተሰጥቶናል" ሲሉም ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ከምርጫ ቦርድ ዕውቅና የተሰጠው ባይሆንም፤ ዕውቅና የላቸውን ፖለቲካ ፓርቲዎች ሰብስቦ ይዟል፡፡

በተጨማሪም ምክር ቤቱ ምንም እንኳን ዕውቅና ባይሰጠውም የግለሰብ ቤት ተከራይቶ የሚኖረው ቦርዱ የኪራይ ክፍያ እየከፈለለት መሆኑን ተረድረናል፡፡

"መንግሥት የጋራ ምክር ቤቱን መንከባከብ አለበት" የሚሉት አቶ ደስታ ዲንቃ፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች በአንድ ላይ ሰብሰቦ ከመያዝ ጀምሮ ለመንግሥት እፎይታ የሚሰጥ ሥራ መስራቱን ተናግረዋል፡፡

በአቤል ደጀኔ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ:www.facebook.com/ahaduradio
ዩትዩብ፦shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡-tiktok.com/@ahadutv.official

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የኢጋድ መስራች ሀገራት የዉስጥ ችግሮቻቸውን አለመፍታታቸው የድርድሩ ዉጤታማነት ላይ ተጽዕኖ ያመጣል ተባለ

መስከረም 11/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ) ኢትዮጵያና ሶማሊያ በባሕር በር ውዝግብ ዙሪያ የገቡበትን ውጥረት በድርድር ለመፍታት ጥረት መጀመሩ አይዘነጋም።

ኢጋድ ሁለቱ አገሮች ውጥረቱን በውይይት እንዲፈቱ ለማስቻል ከተጀመረው ጥረት ጀርባ፣ የጂቡቲ፣ የኬንያና የአሜሪካ መንግሥታት ድጋፍ እንዳለም አመልክቷል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም ኢጋድ ከዚህ ቀደም በምስራቅ አፍሪካ ካከናወናቸዉ ተግባራትና በሁለቱ ሀገራት የተፈጠረዉን ዉጥረት ከማርገብ አንጻር በማደራደር ሂደቱ ምን ያህል ዉጤታማ ይሆናል ሲል አሐዱ ምሁራን ጠይቋል።

በምስራቅ አፍሪካ የኢጋድ መስራች ሀገራት ቅራኔ ዉስጥ ከገቡ ጊዜ ጀምሮ ኢጋድ ቀጠናዉ ላይ ተጽዐኖ ፈጣሪነቱ እምብዛም መሆኑን የገለጹት የቀድሞ ዲፕሎማት አቶ ዳያሞ ዳሌ ናቸው።

አቶ ዳያሞ ኢጋድን ጨምሮ ሌሎች አህጉር አቀፍ ድርጅቶች በሀያላን ሀገራት ተጽዕኖ እንደሚደረግባቸው እና የድርድር ዉጤቱ ላይም ተጽዕኖ እንደሚኖረው ጨምረው ገልጸዋል።

የፖለቲካ ተንታኝ የሆኑት አቶ ጉተማ ዳንኤል በበኩላቸው፤ ኢጋድ በደቡብ ሱዳንን እንዲሁም በሶማሊያ ዉጤማ ሥራዎች መሰራታቸዉን አስታዉሰዉ፤ አሁን ላይ በኢጋድ መስራች ሀገራት መሀል የተፈጠሩ ችግሮችን መፍታት ከተቻለና ጠንካራ የድርድር ሀሳቦችን ይዞ ከቀረበ ዉጤታማ ይሆናል ብለዋል።

ምሁራኑ አክለዉም፤ ኢጋድ በሁለቱ ሀገራት የሚንጸባረቁ አቋሞችን ከግምት ያስገባ ጠንካራ የሆነ የድርድር ሀሳቦችን ሊያቀርብ ይገባል ሲሉ ገልጸዋል።

በፅዮን ይልማ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በትግራይ ክልል ከ12 ሚሊየን በላይ የመመሪያ መጽሀፍት መውደማቸው ተገለጸ

መስከረም 11/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በትግራይ ክልል በነበረው ጦርነት ምክንያት ከ12 ሚሊየን በላይ የተማሪዎች የመመሪያ መጽሀፍት መውደማቸውን የክልሉን ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

2017 ዓ.ም የተማሪዎች የመመሪያ መጽሀፍቶችን በተመለከተ ምን ያህል ተደራሽ ተደርጓል ሲል፤ አሐዱ የክልሉን ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ኪሮስ ጉዑሽን ጠይቋል።

በምላሻቸውም በጦርነቱ ከ12 ሚሊየን በላይ የተማሪዎች መመሪያ መጽሀፍት መውደማቸውን ገልጸው፤ ለአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ሙሉ ለሙሉ የመመሪያ መጽሀፍትን ማዳረስ እንዳልተቻለ ተናግረዋል።

የመምህራኖች መጽሀፍትንም ቢሆን፤ ለእያንድ አንዳቸው መስጠት ባለመቻሉ አንድ ለሁለት ተደራሽ እንደተደረገ ተናግረዋል፡፡

ሀላፊው አክለውም፤ የትግራይ ክልል የመጀመሪያ ደረጃ ተማሪዎች በአዲስ ሳይሆን ቀድሞ በነበረው የትምህርት ስርዓት እና የመማሪያ መጽሀፊት እየተማሩ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

ለሁለተኛ ደረጃ የተማሪዎች ግን መጽሀፊትን የመስጠት ወይም የማሰራጨት ሥራ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በሚኪያስ ኃይሌ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የጊኒ ቢሳው ፕሬዝዳንት በመጪው ህዳር በሚካሄደው የአገሪቱ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እንደማይወዳደሩ ገለጹ

መስከረም 11/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የጊኒ ቢሳው ፕሬዝዳንት ኡማሮ ሲሶኮ ኢምባሎ በመጪው ሕዳር ወር በሚካሄደው የአገሪቱ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ለመወዳደር ፍላጎት እንደሌላቸው ገልጸዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ ከምርጫ ውድድሩ ራሳቸውን ለማግለል የወሰኑት በባለቤታቸው ግፊት መሆኑን አስታውቀዋል።

እርሳቸው የስልጣን ዘመን ሁለት ጊዜ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ተካሂዶባቸው የነበረ ሲሆን፤ መፈንቅለ መንግሥቱ ሳይሰምር እንደቀረ ይነገራል ።

ጊኒ ቢሳኦ ለአመታት ፓለቲካዊ መረጋጋት እንደራቃት ነው። ይሁንና ፕሬዝዳንት ኡማሮ ሲሶኮ ሕገመንግሥታዊ ስርአቱን ጨምሮ ፕሬዚዳንታዊ ስርአቱን ለማሻሻል ጥረት ሲያደርጉ መቆየታቸውን አፍሪካ ኒውስ ዘግቧል።

በአማኑኤል ክንደያ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…
Subscribe to a channel