ahaduradio | Unsorted

Telegram-канал ahaduradio - AHADU RADIO FM 94.3

19349

አሐዱ ራድዮ 94.3 Your source for top local and international news and analysis. "Voice of Ethiopian" የአሐዱ የቴሌግራም ቻናል ቤተሰብ በመሆን ወቅታዊና እውነተኛ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ

Subscribe to a channel

AHADU RADIO FM 94.3

በሩዋንዳ ማርበርግ በተባለ ቫይረስ ስድስት ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ

መስከረም 20/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በሩዋንዳ ማርበርግ በተባለው ቫይረስ ስድስት ሰዎች ሲሞቱ 20 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች የመሞት እድል 88 በመቶ ድረስ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን፤ ማርበርግ ቫይረስ ከኢቦላ ቫይረስ አይነት ጋር የሚመደብ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ቫይረሱ በዋናነት በበሽታው ከተያዙ ሰዎች የሰውነት ፈሳሽ ከሰው ወደሰው የሚተላለፍ መሆኑም ተነግሯል፡፡ ምልክቶቹም ትኩሳት፣ የጡንቻ ህመም፣ ተቅማጥ፣ ማስመለስና በአንዳንድ የሰውነት ክፍሎች ላይ መድማትን በማስከተል ለሞት ያበቃል ተብሏል፡፡

እስካሁን ለቫይረሱ ተብሎ የተዘጋጀ ክትባትም ሆነ ህክምና እንደሌለ የተገለጸ ሲሆን፤ ነገርግን መድሃኒቶች እና የበሽታ መከላከያ ህክምናዎች በመዘጋጀት ላይ መሆናቸውን የአለም ጤና ድርጅት አስታውቋል።

ሩዋንዳ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት የተያዙት ሰዎች ከሌሎች ሰዎች ጋር ያላቸውን ግንኙነት እየመረመረች መሆኑ ተገልጿል፡፡

የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር ህብረተሰቡ እንዲጠነቀቅና የእጁን ንጽህና እንዲጠብቅ በተጨማሪም የበሽታው ምልክት የታየባቸውን ሰዎች እንዲጠቁም ማሳሰቡን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ለመጀመሪያ ጊዜ የማርበርግ ወረርሽኝ እአአ በ1967 ጀርመን ውስጥ የተከሰተ ሲሆን፤ በወቅቱ ሰባት ሰዎች በቫይረሱ ሕይወታቸውን አጥተዋል።

እአአ በ2005 አንጎላ ውስጥ በቫይረሱ ምክንያት ከ200 በላይ ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል። በተጨማሪም 2017 ላይ በዩጋንዳ ተከስቶ ሦስት ሰዎች መሞታቸው የተገለጸ ሲሆን፤ በ2023 ደግሞ በታንዛኒያም ተቀስቅሶ እንደነበርም ተነግሯል፡፡

ቫይረሱ ወደ ሰዎች የሚተላለፈው ከሌሊት ወፍ ዝርያዎች ሲሆን፤ በሰዎች መካከል ደግሞ ከሰውነት ከሚወጣ ፈሳሽ ጋር በሚኖር ንክኪ አማካኝነት በቀላሉ የሚተላለፍ መሆኑ ተነግሯል።

በገነነ ብርሃኑ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሙዳ ቅዱስ ገብርኤል አጥቢያ 8 ሰዎች በታጣቂዎች መገደላቸው ተገለጸ

መስከረም 20/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በሉሜ ወረዳ ቤተ ክህነት በሙዳ ቅዱስ ገብርኤል አጥቢያ፤ ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች 8 የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በግፍ መገደላቸው ተገልጿል።

በሙዳ ሰንቀሌ ቀበሌ በሙዳ ቅዱስ ገብርኤል አጥቢያ የሚገኙትን የእምነቱን ተከታዮች የታጠቁ ኃይሎች ቅዳሜ በ18/2017 ዓ.ም ሌሊት ከየቤታቸው በመልቀም ይዘዋቸው የሄዱ ሲሆን፤ ጀቢሳ በሚባል አነስተኛ ወንዝ ሥር በግፍ እንደገደሏቸው ተነግሯል፡፡

በቦታው የደረሰው መከላከያ ሠራዊትም የሟቾችን አስክሬን በማንሳት በቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን እንዳሳረፏቸው ሐመረ ተዋሕዶ ሚዲያ ዘግቧል፡፡

የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ በክስተቱ የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸው፤ በሀገረ ስብከቱ እየተበራከተ የመጣውን የንጹሐን ግድያ በማስመልከት ከሚመለከታቸው የምሥራቅ ሸዋ ዞን አስተዳዳሪዎችና ከዞኑ የጸጥታ መዋቅር ጋር ሰፊ ውይይት ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

አክለውም፤ ለአካባቢው ምዕመናንና ለአደጋ ተጋላጭ ናቸው ተብለው በሚታሰቡ ቦታዎች ሁሉ ጥበቃና ከላላ እንዲደረግ በአጽንዖት ጠይቀዋል፡፡

የዞኑ አስተዳደርና የዞኑ የጸጥታ መዋቅር ይህ ዜና ከተሰማበት ጊዜ ጀምሮ ለዞኑ የጸጥታ ኃይል ስምሪት በመስጠት በአካባቢው የሚገኙ የጸጥታ ኃይሎችን ለጊዜው በማሠር የማጣራት ሥራና በአካባቢው የኦፕሬሽን ሥራ እያካሄደ እንደሚገኝም ተገልጿል፡፡

ብፁዕነታቸው ከዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አንድነት ገዳም አባቶች ግድያ ጀምሮ፤ ያለ እረፍት ከሚመለከታቸው የፌደራልና የክልል እንዲሁም የዞን አመራሮች ጋር ሰፊ ውይይት እያካሄዱ እንደሚገኙም ተነግሯል፡፡

በሀገረ ስብከቱ ከከተማ ወጣ ባሉ አካባቢዎች እየተፈጸመ የሚገኘው በደልና ግፍ ታሪክ ይቅር የማይለው በመሆኑ የሚመለከተው ሁሉ ለሰላም ጠንክሮ እንዲሠራና ይህን መሠል ድርጊት ያለ ርኅራኄ የሚፈጽሙትን መቃወምና ድርጊቱን ማውገዝ እንደሚገባም አሳስቧል።

ባሳለፍነው ሐሙስ መስከረም 16 ቀን 2017 የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በሞጆ ሉሜ ወረዳ ቤተ ክህነት አገልጋይ የነበሩ መ/መ/ቀ/ወልደ ኢየሱስ አያሌው የተባሉ ካህን ከባለቤታቸውና ከሦስት ልጆቻቸው ጋር በአንድ ቀን በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በደብረብርሃን እና ዙሪያ በሚገኙ ወረዳዎች ላይ የኤሌክትሪክ የኃይል አቅርቦት መቋረጡ ተነገረ

መስከረም 20/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በደብረብርሃን ቁ.1 የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ላይ ባገጠመ ብልሽት ምክንያት፤ በከተማዋና ዙሪያዋ በሚገኙ ወረዳዎች ላይ የኤሌክትሪክ የኃይል አቅርቦት መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል።

በዚህም በደብረብርሃን ከተማ ቀበሌ1፣ 2፣ 3፣ 4፣ 5፣ 6፣ 8 እንዲሁም በከተማዋ ዙሪያ የሚገኙ ወረዳዎች ሰላድንጋይ፣ ባሶና ወረና፣ አንኮበር ፣ዳሽን ቢራ ፋብሪካ፣ጫጫ ሮራንክ ቢዝነስ፣ሐበሻ ቢራ ፋብሪካ፣ አልዩ አምባ እና ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ እና የጤና ሳይንስ ኮሌጅ አካባቢዎቻቸው ኃይል መቋረጡ ተገልጿል፡፡

ስለሆነም በተጠቀሱት አካባቢዎች የሚገኙ ደንበኞች የጥገና ባለሙያዎች ጥገናውን እያከናወኑ መሆኑን ተገንዝበው፤ ጥገናው ተጠናቆ አገልግሎቱ እስኪመለስ በትዕግስት እንዲጠባበቁ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጠይቋል።

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

ሩሲያ ከ100 በላይ የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መትታ መጣሏ ተገለጸ

መስከረም 20/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የሩስያ መከላከያ ሚኒስቴር በሰባት ግዛቶች 125 የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መትቶ መጣሉን አስታውቋል፡፡

በተለይም ወደ ደቡብ ምዕራብ የሚገኘው የቮልጎ ግራድ ክልል ከዩክሬን የተተኮሱ 67 ሰው አልባ አውሮፕላኖች በሩሲያ አየር መከላከያ ተመትተው መውደቃቸው ተገልጿል፡፡

ሌሎች 17 ሰው አልባ አውሮፕላኖችም በሩሲያ ቮሮኔዝ ክልል ላይ ቢታዩም፤ የሩሲያ አየር ሃይል እንደጣላቸው ነው የተነገረው፡፡

በዚህ በቮሮኔዝ ክልል ሰው አልባ አውሮፕላኖቹን በመጣሉ ሂደት በእሳት የተያያዙ ስብርባሪዎች በአንድ አፓርታማ ላይ ወድቀው እሳት ተነስቶ እንደነበር የተነገረ ሲሆን፤ በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት የለም ተብሏል፡፡

በተጨማሪ 18 የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖች በሩሲያዋ የሮስቶቭ ግዛት ላይ ተመተው እንደወደቁ ተነግሯል፡፡ በዚህ ግዛትም በድሮኖቹ ስብርባሪ አማካኝነት ሰደድ እሳት ተከስቶ እንደነበር የግዛቱ አስተዳዳሪ ቫሲሊ ጎሉቤቭ መናገራቸውን ኒውስ ታይምስ ዘግቧል።

የተከሰተው ሰደድ እሳት ህዝብ የሚበዛባቸው ቦታዎች ላይ ባይደርስም፤ 20 ሄክታር ደን በእሳት መያያዙንና እሳቱን ለማጥፋት የእሳ አደጋ ቡድኖች ከፍተኛ ርብርብ ማድረጋቸው ተገልጿል፡፡

በገነነ ብርሃኑ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በአሜሪካ ሰሜን ካሮላይና በሚገኝ ኤርፖርት ላይ በደረሰ የአውሮፕላን አደጋ የሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገለጸ

መስከረም 20/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በአሜሪካ ሰሜን ካሮላይና በራይት ብራዘርስ ብሄራዊ መታሰቢያ ኤርፖርት ላይ በደረሰ የአውሮፕላን አደጋ የሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገልጿል፡፡

የአይን እማኞች እንደገለጹት ባለ አንድ ሞተር አውሮፕላን በኤርፖርቱ ለማረፍ እየሞከረ በነበረበት ወቅት መከስከሱ የተነገረ ሲሆን፤ ለጊዜው ቁጥራቸው ያልተገለጸ ሰዎች ሕወታቸው ማለፉ ተገልጿል፡፡

የአውሮፕላን አደጋው ከተከሰተ በኋላ ከፍተኛ እሳት መነሳቱ የተገለጸ ሲሆን፤ የአካባቢው የእሳት አደጋ ቡድኖች ባደረጉት ከፍተኛ ርብርብርብ እሳቱን መቆጣጠር ተችሏል ተብሏል፡፡

የብሔራዊ ትራንስፖርት ደህንነት ቦርድ የአደጋውን መንስኤ ለማወቅ ምርመራ ጀምሪያለው ማለቱን ኤቢሲ ኒውስ ዘግቧል፡፡

በአደጋውም ምክንያት አውሮፕላን ማረፊያው ለጊዜው ሥራ በማቆም ቀጣይ በረራዎችን የሰረዘ ሲሆን፤ መቼ ወደሥራው እንደሚመለስ በቀጣይ ይገለጻል ተብሏል፡፡

በገነነ ብርሃኑ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የሃማስ መሪ ፋትህ ሻሪፍ አቡ አል-አሚን በእስራኤል ጥቃት ተገደሉ

መስከረም 20/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የፍልስጤም ታጣቂ ቡድን ሃማስ መሪ የሆኑት ፋትህ ሻሪፍ አቡ አል-አሚን እስራኤል በሊባኖስ ላይ በፈጸመችው የአየር ጥቃት መገደሉን ቡድኑ አስታውቋል፡፡

ፈትህ ሸሪፍ አቡ አል-አሚን ከባለቤታቸው፣ ወንድ ልጃቸው እና ሴት ልጃቸው ጋር ዛሬ ማለዳ በደቡብ ሊባኖስ በሚገኘው የፍልስጤም የስደተኞች ካምፕ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ላይ ባነጣጠረ ጥቃት መገደላቸውን ሃማስ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

የእስራኤል ጦር የሃማስ መሪ ግድያንም ሆነ የተደረገውን ጥቃት አስመልክቶ እስካሁን ምንም አይነት አስተያየት አልሰጠችም።

የእስራኤል ጦር ባለፈው አርብ የሂዝቦላህ መሪ ሀሰን ነስራላህን ከገደለ በኋላ፤ በየመን በሚገኙ የሁቲ ሚሊሻዎች እና በመላው ሊባኖስ በሚገኙ በደርዘን የሚቆጠሩ የሂዝቦላህ ኢላማዎች ላይ ያነጣጠረ የአየር ጥቃትን ትናንት እሁድ ጀምሯል።

እስራኤል በትናትናው ዕለት ማዕከላዊ ቤሩት በሚገኘው ኮላ አካባቢ ለመጀመሪያ ጊዜ ድብደባ የፈጸመች ሲሆን፤ በዚህም የአየር ድብደባ የፍሊስጤም ህዝባዊ ነጻ አውጪ ግንባር (PFLP) ሦስት አመራሮች መገደላቸውን ቡድኑ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

እስራኤል በበኩሏ እሁድ ምሽት በተደረገው ጥቃት ብቻ 120 የሄዝቦላህ ኢላማዎችን ማጥቃቷን አስታውቃለች።

በዚህም ጥቃት 20 በላይ የሂዝቦላ አመራሮችን መግደሏን የገለጸች ሲሆን፤ የሊባኖስ ጤና ሚኒስቴር ደግሞ በጥቃቱ እስካሁን 50 ሰዎች መሞታቸውን ገልጿል፡፡ በጥቃቱ ከተገደሉት ውስጥ 17ቱ ከአንድ ቤተሰብ መሆናቸውንም አስታውቋል።

እስራኤል በሊባኖስ በሚገኘው የሂዝቦላህ ቡድን እና በየመን የሁቲ ሚሊሻዎች ላይ በምታደርሰው ተደጋጋሚ ጥቃት፤ የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ከቁጥጥር ውጭ ሊሆን ይችላል የሚል ስጋት እየፈጠረ ይገኛል፡፡

በእዮብ ውብነህ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

መልካም ቀን!
አሐዱ ሬድዮ 94.3  የኢትዮጵያውያን ድምፅ!

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የተሽከርካሪ አገልግሎት ክፍያ ላይ የዋጋ ጭማሪ ተደረገ

መስከረም 19/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ላይ የአገልግሎት ክፍያ ታሪፍ ጭማሪ አድርጓል።

ባለስልጣኑ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በማስደገፍ ቀልጣፋ እና ፈጣን አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ገልጾ፤ በተቋሙ ከሚሰጡ አገልግሎቶች ውስጥ በአንዳንዶቹ ላይ የክፍያ ታሪፍ ማሻሻያ ማድረጉን አስታውቋል።

በዚህም መሰረት፤ የክፍያ ዋጋ ጭማሪ ከተደረገባቸው አገልገሎቶች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፦

=> የተሽከርካሪ አገልግሎት ለውጥ ምዝገባ 10,000 ብር የነበረው 12,000 ብር ተደርጓል።

=> የተሽከርካሪ የዋጋ ግምት ማሳወቅ አገልግሎት 500 ብር የነበረው 1,000 ብር ሆኗል።

=> የተሽከርካሪ የዋጋ ግምት ለሽያጭ አገልግሎት 2,310 ብር የነበረው 4,000 ብር ሆኗል።

=> የተሽከርካሪ የባለቤትነት ሥም ዝውውር አገልግሎት 3,000 ብር የነበረው 5,000 ብር ተደርጓል።

=> ከገቢዎች እና ከጉምሩክ ባለስልጣን በሚፃፍ ደብዳቤ ከቀረጥ ነፃ ለገባ ተሽከርካሪ ቀረጥ ማንሳት አገልግሎት 1,000 ብር የነበረው 5,000 ብር ተደርጓል።

=> ለዓመታዊ ምርመራ ተለጣፊ ምልክት (ቦሎ) ግልባጭ ለመጀመሪያ ጊዜ 1,010 ብር የነበረው 2,500 ብር ሆኗል።

=> የተሽከርካሪ የቴክኒክ ብቃት ምርመራ በተሽከርካሪ 150 ብር የነበረው ወደ 700 ብር አድጓል።

=> የተሽከርካሪ ባለቤት ማረጋገጫ ሊብሬ 300 ብር የነበረው 1200 ብር ተደርጓል።

=> ሊብሬ  ሲበላሽ ወይም ሲጠፋ ምትክ ፣ የማደሻ ቦታው ሲያልቅ መስጠት 3,000 ብር የነበረው 3,500 ብር ሆኗል።

=> መረጃ መስጠት 300 ብር የነበረው 700 ብር ተደርጓል።

=> አዲስ መንጃ ፍቃድ መስጠት 680 ብር የነበረው 1,500 ብር ተደርጓል።

=> ለጠፋ መንጃ ፍቃድ ማፈላለጊያ ለፖሊስ ወይም ለፕሬስ የሚሰጥ መረጃ 100 ብር የነበረው 700 ብር ሆኗል።

=> ከ3 ጊዜ በላይ የፅሁፍ ፈተና ለወደቁ በየወሩ ለመፈተን የሚሰጥ አገልግሎት 100 ብር የነበረው 300 ተደርጓል።

=> የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፍቃድ እድሳት 620 ብር የነበረው 1,000 ብር ተደርጓል።

=> ለጠፋ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ምትክ መስጠት 620 ብር የነበረው 5,000 ብር ሆኗል።

=> ከ3 ጊዜ በላይ የተግባር ፈተና ለወደቁ በየወሩ ለመፈተን የሚሰጥ አገልግሎት 300 ብር የነበረው 600 ብር ተደርጓል።

=> የአሽከርካሪ የብቃት ማረጋገጫ እግድ ለማንሳት 1,000 ብር የነበረው 2,000 ብር ተደርጓል።

=> የተሽከርካሪ የዋጋ ግምት ማፍረስ 1,500 ብር የነበረው 5,000 ብር መደረጉን፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን አስታውቋል።

👉 በተጨማሪ ተቋሙ በሌሎች የተለያዩ አገልግሎቶች ላይ የታሪፍ ጭማሪ ያደረገ ሲሆን፤ ሙሉ መረጃውን የያዘው ዝርዝር ከላይ ተያይዟል።

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

#Update
ሂዝቦላህ መሪው ሀሰን ናስረላህ መሞቱን አረጋገጠ


መስከረም 18/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) እስራኤል በቤሩት ላይ ባደረሰችው ጥቃት ሂዝቦላህ መሪው ሀሰን ናስረላህ መሞቱን አረጋግጧል።

ሂዝቦላህ ከደቂቃዎች በፊት በለቀቀው መግለጫ፤ መሪው ሀሰን ናስረላህ መሞቱን አስታውቋል።

የእስራኤል መከላከያ ባወጣው መግለጫ፤ በኢራን የሚደገፈውን የሂዝቦላ ታጣቂ ቡድን መሪ እና ሌሎችም ከፍተኛ የሂዝቦላህ አመራሮችን በትላንትናው ዕለት በቤሩት በፈጸመው ጥቃት መግደሉን መግለጹ ይታወሳል።

ሀሰን ናስረላህ ከአውሮፓውያኑ 1992 ጀምሮ የሂዝቦላህ መሪ ነበሩ። 

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የፋሲል ግንብ መጠነኛ ጥገና ብቻ እንደሚደረግለት ተገለጸ

መስከረም 18/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በጎንደር የሚገኘው የፋሲል ግንብ መጠነኛ ጥገና ብቻ እንደሚደረግለት የኢትዮጽያ ቅርስ ባለስልጣን አስታውቋል፡፡

"የፋሲል ግንብ ጥገና ተጀምሯል" መባሉን ተከትሎ፤ የሚደረግለት እድሳት ወይም ጥገና የቀድሞ ይዘቱን በጠበቀ መልኩ እንዲሆን ምን ያህል ጥንቃቄ ወይም ጥናት ተደርጓል ሲል አሐዱ ጠይቋል፡፡

በዚህ ረገድ ምላሽ የሰጡት የኢትዮጽያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌ፤ ግንቡ በ2013 እና 2014 በታሪክ ሙህራን እና በአከባቢዉ የመሀንዲስ ባለሙያዎች ጥናት ተደርጎ ታሪካዊ ይዘቱን በጠበቀ መልኩ አነስተኛ እድሳት እንደሚደረግለት ተናግረዋል፡፡

ቅርሱ ከ1980 ጀምሮ ምንም እድሳት እና ጥገና እንዳልተደረገበትም አንስተዋል፡፡

አክለዉም እድሳቱ 3 አይነት ሥራዎችን ያካተተ መሆኑን ገልጸው፤ የመጀመሪው ሙሉ ጥገና፣ ሁለተኛው ግቢውን ማስዋብ እና ሦስተኛው የኤሌትሪክ ሀይል የመስመር ዝርጋታን ያካተተ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በ16ኛው ክፍለ ዘመን በተቆረቆረችው በጎንደር ከተማ የሚገኘው የአፄ ፋሲለደስ ቤተ መንግሥት እድሳት መጀመሩን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ መናገራቸው ይታወሳል፡፡

በ1628 ዓ.ም. የተሠራው የአፄ ፋሲለደስ ቤተ መንግሥት ፋሲል ግቢ፤ በውስጡ ቤተ መዛግብት፣ የአፄ ፋሲል መዋኛ፣ ቁስቋም ማርያም ቤተ ክርስቲያን፣ ራስ ግምብና ደረስጌ ማርያምን የያዘ ሲሆን፤ ቤተ መንግሥቱ በዓለም ቅርሶች መዝገብ በ1979 ዓ.ም. መስፈሩ ይታወቃል፡፡

በፅዮን ይልማ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

እስራኤል የሂዝቦላህ መሪ ሀሰን ናስራላህ መግደሏን አስታወቀች

መስከረም 18/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት ትናንት አርብ በደቡባዊ ቤይሩት ክፍል ባደረሰው ጥቃት፤ የሂዝቦላህ መሪ ሀሰን ናስራላህ መገደሉን አስታውቋል፡፡

እስራኤል ደቡባዊ የቤይሩት ክፍልን በአየር ጥቃት ኢላማ ያደረገችው ትላንት አርብ ሲሆን፤ ከፍተኛ የሂዝቦላ አመራሮችንና የጦር ካንፖችን ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እንደነበር ተገልጿል፡፡

ይህም በደቡባዊ ቤይሩት እየተደረገ ያለው የእስራኤል የአየር ድብደባ እስከ ዛሬ ማለዳ ድረስ የቀጠለ ሲሆን፤ በዚህም ድብደባ የሂዝቦላህ መሪ ሀሰን ናስራላህ መገደሉን የአገሪቱ መከላከያ ሠራዊት አስታውቋል፡፡

አርብ ዕለት በነበረው ከፍተኛ ጥቃት የሊባኖስ ጤና ሚኒስቴር 6 ሰዎች መሞታቸውን እና 91 ሰዎች መጎዳታቸውን ይፋ አድርጓል። በአጠቃላይ እስራኤል ካለፈው ሰኞ ጀምሮ በፈጸመችው ጥቃት 800 የሚጠጉ ሰዎች ሕይወት ማለፉም ተነግሯል።

ከዚህ ቀደም እስራኤል የሄዝቦላህን የሚሳኤል ክፍል ሃላፊ ሙሀመድ አሊ ኢስማኤል እና ምክትሉን ሆሴን አህመድ ኢስማኤል መግደሏን ማስታወቋ ይታወሳል፡፡

ሂዝቦላህ የመሪውን ግድያ አስመልክቶ እስካሁን አስተያየት አልሰጠም።

በእዮብ ውብነህ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

"ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር የፈረመችው የመግባቢያ ስምምነት በሶማሊያ ውስጥ ያለውን ተጨባጭ የፖሊካ ሁኔታ ከግምት ውስጥ ያስገባ ነው" አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ

መስከረም 18/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር የፈረመችው የመግባቢያ ስምምነት በሶማሊያ ውስጥ ያለውን ተጨባጭ የፖሊካ ሁኔታ ከግምት ውስጥ ያስገባ እና በቀጣናው የተሳሰር ዕድገት እና ብልጽግና ለማምጣት ያለመ ነው ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ገለጹ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ በኒዮርክ እየተከናወነ በሚገኘው 79ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ንግግር አድርገዋል።

በንግግራቸውም ኢትዮጵያ ለዓለም ሰላም እና ደህንነት ያላትን ቁርጠኝነት እና የባለብዙ ወገን ግንኙነት መርሆችን አክብራ የምትጓዝ መሆኗን ገልጸዋል።

አክለውም፤ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በአሁኑ ወቅት በርካታ ፈተናዎች እያጋጠሙት እንደሚገኝ አንስተው፤ እነዚህን ችግሮች ለመፍታት ወደ ቀደመ የባለብዙ ወገን ግንኙነት መርሆች መመለስ እና አባል አገራቱ በመካከላቸው ያለውን የትብብር መንፈስ ማጠናከር እንደሚገባ ተናግረዋል።

የጦር መሣሪያ እሽቅድድም፣ አስከፊ ድህነት፣ ኢ-ፍትሐዊነት፣የ አየር ንብረት ለውጥ እና ዘላቂ የልማት ግቦችን ለማሳካት የገጠሙ መሠናክሎች የተመድ እና አባል አገራቱን ትኩረት የሚሹ መሆናቸውንም ሚኒስትሩ በንግግራቸው አንስተዋል።

አገሪቱ ወደ ሙሉ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራ መግባቷ፣ የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ኢኒሼቲቭ በሆነው የአረንጓዴ ዓሻራ ትግበራ የአገሪቱ የደን ሽፋን ከ3 በመቶ ወደ 24 በመቶ ከፍ ማለቱን እና ይህም የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ጉልህ ሚና እንደሚኖረውም ተናግረዋል፡፡

አምባሳደር ታዬ በቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ባተኮረው የንግግር ክፍላቸው፤ ኢትዮጵያ ከናይል ወንዝ ተፋሰስ አባል አገራት ጋር በትብብር ለመሥራት ያላትን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።

"የናይል ወንዝ ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት ኮረሙ በሚደነግገው መሠረት በፈራሚ አባል አገራት ፓርላማ ጸድቆ ወደ ናይል ወንዝ ተፋሰስ ኮሚሽን ትግበራ ሊገባ መሆኑ አንዱ ማሳያ ነው" ብለዋል።

ሚኒስትሩ በቀይ ባሕር እና ሕንድ ውቅያኖስ ያለው ደህንነት አስተማማኝ እንዲሆን በመሥራት እና እንደ አልሽባባ ያሉ አሸባሪ እና ፅንፈኛ ቡድኖችን በመዋጋት ኢትዮጵያ ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር ለመሥራት ያላትን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።

አክለውም በሶማሊያ አሸባሪነትን በመዋጋት ረገድ ለሶማሊያ ሕዝብ ፅናት እና ዋጋ ለከፈሉ የቡሩንዲ፣ ጂቡቲ፣ ኬንያ፣ ኡጋንዳ እና ኢትዮጵያ ልጆች ምስጋና አቅርበዋል።

የሶማሊያ መንግሥት ለተከፈለለት ዋጋት ምስጋና መቸር እንዳለበት ጥሪ ያቀረቡት አምባሳደር ታዬ፥ ከአፍሪካ ቀንድ ውጭ ያሉ ኃይላት በቀጣናው ውጥረት ከመፍጠር እንዲታቀቡ መጠየቃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትቴር መረጃ ያመላክታል።

አምባሳደር ታዬ አክለውም፤ "ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር የፈረመችው የመግባቢያ ስምምነት በሶማሊያ ውስጥ ያለውን ተጨባጭ የፖሊካ ሁኔታ ከግምት ውስጥ ያስገባ እና በቀጣናው የተሳሰር ዕድገት እና ብልጽግና ለማምጣት ያለመ ነው" ሲሉ ገልጸዋል።

ተመሳሳይ ስምምነቶች በሌሎች አገራት ከአሁን በፊት የተፈረሙ መሆናቸውን በማስታወስ፤ "የሶማሊያ መንግሥት ውስጣዊ የፖለቲካ ችግሩን ለመሸፈን ካልሆነ በስተቀር ግጭት ቀስቃሽ ሥራዎችን እንዲሠራ የሚገፋፋ አንዳች የተለየ ነገር የለም" ብለዋል።

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

አርቲሜተር የተባለው የወባ መድኃኒት ጥቅም ላይ እንዳይውል ታገደ

መስከረም 18/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አርቲሜተር የተባለውን በመርፌ የሚሰጥ የወባ መድኃኒት ጥቅም ላይ እንዳይውል አግዷል፡፡

በተደረገ የገበያ ቅኝት መድኃኒቱ መገኘቱን፣ በባለስልጣኑ ያልተመዘገበ እንዲሁም ናሙናው ተወስዶ በላብራቶሪ ሲፈተሽ አርቲሜተር (Artemether) የተባለው ንጥረ ነገር በውስጡ አለመገኘቱ መረጋገጡን ባለስልጣኑ ገልጿል፡፡

በመሆኑም፤ ይህን መድኃኒት የጤና ባለሙያዎች እንዳይጠቀሙት እና በየደረጃው ያሉ የክልል ተቆጣጣሪዎች በየአካባቢያቸው ጥብቅ ክትትል በማድረግ እርምጃዎች እንዲወስዱ ባለስልጣኑ አሳስቧል፡፡

መድኃኒቱ ሻይን ፋርም በተባለ የቻይና የመድኃኒት አምራች የተመረተ ሲሆን፤ አርቲሜተር (Artemether 80mg/1ml) የሚል ስያሜ ያለው እና በመርፌ የሚሰጥ የወባ መድኃኒት መሆኑን፤ የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን መረጃ አመልክቷል፡፡

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

ካህኑ ከባለቤታቸውና ከሦስት ልጆቻቸው ጋር በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ

መስከረም 18/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በሞጆ ሉሜ ወረዳ ቤተ ክህነት አገልጋይ የነበሩ መ/መ/ቀ/ወልደ ኢየሱስ አያሌው የተባሉ ካህን ከባለቤታቸውና ከሦስት ልጆቻቸው ጋር በአንድ ቀን በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው ተገልጿል።

መልአከ /መ/ቀሲስ ወልደ ኢየሱስ አያሌው በላስታ ላሊበላ ልዩ ቦታው ጥል አስፈሬ ቅዱስ ገብርኤል አካባቢ የተወለዱ ሲሆን፤ በቢቃ ደ/መ/ቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ከ1976 ዓ.ም ጀምሮ ለ 41 ዓመታት ያህል ከዲቁና እስከ ደብር አስተዳዳሪነት ድረስ በትኅትና ሲያገለግሉ መቆየታቸው ተነግሯል።

ካህኑ ሐሙስ መስከረም 16 ቀን 2017 ባለቤታቸውን ጨምሮ ከሦስት ልጆቻቸው ጋር በግፍና በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው የተገለጸ ሲሆን፤ ለረጅም ጊዜ ባገለገሉበት በቢቃ ደ/መ/ቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ ቀብራቸው መፈጸሙን የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሕዝብ ግንኙነት አስታውቋል።

ልጃቸው ዲ/ን መልአክ ወልደ ኢየሱስ የአባቱን ፈለግ በመከተል በድቁና ያገለግል እንደነበርም ተገልጿል።

ከግድያው ጋር በተያያዘ ድርጊቱ በማን እንደተፈጸመ  የተነገረ ነገር ባይኖርም፤ ሀገረ ስብከቱ ግድያው "ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቀ ኃይሎች" መፈጸሙን  አስታውቋል።

የመልአከ /መ/ቀሲስ ወልደ ኢየሱስ አያሌውና ቤተሰቦቻቸው ጸሎተ ፍትሐት፤ ትላንት መስከረም 17 ቀን 2017 ዓ/ም መ/ሰ/ቆ/አባ ሰይፈ ገብርኤል ገረመው የወረዳው ቤተክህነት ሥራ አስኪያጅ  የአድባራትና የገዳማት አስተዳዳሪዎች በተገኙበት በሞጆ ደ/ብ/ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን  ተከናውኗል።

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

እንኳን አደረሳችሁ!
መልካም የመስቀል ዳመራ በዓል!


አሐዱ ሬድዮ 94.3 የኢትዮጵያውያን ድምፅ!

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

ኢትዮጵያ ከአለም ባንክ ጋር የ70 ሚሊየን ዶላር ስምምነት ተፈራረመች

መስከረም 20/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የገንዘብ ሚኒስቴር እና የዓለም ባንክ ለዘመናዊ አስተዳደር ሥርዓት ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የሚውል፤ የ70 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት ተፈራርመዋል።

በስምምነቱ መሰረት ገንዘቡ በረጅም ጊዜ የሚከፈል ሲሆን፤ የመንግሥት የፋይናንስ እና የሰው ሃይል የማሰባሰብ እንዲሁም የማስተዳደር አቅምን በመጨመር እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎችን ለማሳደግ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ተገልጿል፡፡

በዚህም መሰረት የፕሮጀክቱ የመጀመሪያ አካል በመረጃ ላይ የተመሰረተ የሰው ሃብት አስተዳደር አሰራርን በማሻሻል፣ በብቃት ላይ የተመሰረተ የቅጥርና የአመራር ሂደቶችን ማጎልበት እንዲሁም፤ የመንግሥት ሰራተኞችን የአቅም ግንባታ ሥራዎችን ለመስራት ይረዳል ተብሏል።

ሁለተኛው አካል ደግሞ፤ የአገር ውስጥ ገቢ አሰባሰብን ለማሻሻልና ለመደገፍ የተነደፈ ሲሆን፤ በተሻሻለ የግብር ከፋይ አገልግሎት የቴክኖሎጂ እና የመረጃ ትንተናዎችን በመጠቀም ክፍተቶችን መዝጋት ላይ ትኩረቱን እንደሚያደርግ ተነግሯል፡፡

በሦስተኛው አካልም የህዝብ ፋይናንስ አስተዳደርን የዲጂታል መፍትሄዎች በማስፋት፣ በህዝብ ፋይናንስ አስተዳደርን ዑደት ውስጥ ያሉ ወሳኝ የሂደት ጉድለቶችን ለመፍታት እንደሚውል የተገለጸ ሲሆን፤ የኤሌክትሮኒክስ የመንግሥት ግዥ (ኢ-ጂፒ) ስርዓት መዘርጋት እና ማሻሻልን በመደገፍ የሂሳብ አያያዝ እና ግዥን ሙያዊ ብቃትን ይደግፋል መባሉን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገነኘው መረጃ ያመላክታል።

ስምምነቱ በገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ እና በአዲሷ በአለም ባንክ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ማርያም ሳሊም መካከል ተፈርሟል፡፡

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በመዲናዋ ያለንግድ ፈቃድ፣ ባልታደሰ ንግድ ፈቃድና በተሰረዘ ንግድ ፈቃድ ሲነግዱ የተገኙ 1 ሺሕ 441 የንግድ ድርጅቶች መታሸጋቸው ተገለጸ

መስከረም 20/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ከነሀሴ 27/2016 ጀምሮ ባካሄደው የንግድ ቁጥጥር ተግባር፤ ያለንግድ ፈቃድ፣ ባልታደሰ ንግድ ፈቃድና በተሰረዘ ንግድ ፈቃድ ሲነግዱ የነበሩ 1 ሺሕ 441 የንግድ ድርጅቶችን ማሸጉን አስታውቋል፡፡

ቢሮው ከነሀሴ 27 /2016 ጀምሮ እስከ መስከረም 18/2017 ድረስ በ69 ሺሕ 50 የንግድ ድርጅቶች ላይ ክትትል ለማድረጉን፤ በቢሮው የንግድ ሪጉላቶሪና ኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ አሰፋ ተናግረዋል።

በዚህም 1 ሺሕ 400 የንግድ ድርጅቶች ያለ ንግድ ፈቃድ፣ 71 ባልታደሰ ንግድ ፈቃዶችና 2 በተሰረዘ ንግድ ፈቃድ ሲነግዱ በመገኘታቸው፤ በአጠቃላይ 1 ሺሕ 441 የንግድ ድርጅቶች መታሸጋቸውና ለ32 የንግድ ድርጅቶች ማስጠንቀቂያ መሰጠቱ ገልጸዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ በተደረገው ክትትልና ቁጥጥር ከንግድ ፈቃድ ውጭ ባሉ 703 የንግድ ድርጅቶች ልዩ ልዩ ጥፋቶች ፈጽመው በመገኘታቸው፤ እንዲያርሙ መደረጉን ከቢሮው ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የቀሲስ ወልደ ኢየሱስ አያሌው እና ቤተሰባቸው ግድያ ተራ ግድያ ሳይሆን በእምነት ተቋማት ላይ ያነጣጠረ ጭፍጨፋ ነው ሲል እናት ፓርቲ ገለጸ

መስከረም 20/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) መስከረም 16 ቀን 2017 በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን ሞጆ ወረዳ የቢቃ ደ/መ/ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህን የነበሩት ቀሲስ ወልደ ኢየሱስ አያሌው እና 4 ቤተሰባቸው በአሰቃቂ ኹኔታ መገደል፤ ተራ ግድያ ሳይሆን በእምነት ተቋማት ላይ ያነጣጠረ፣ ቤተሰብን በሙሉ በአንድ ላይ በመፍጀት ዘር እንዳይተርፍ ጭምር የተወሰደና ቀደም ሲል ከተፈጸሙ መሰል ግድያዎች የጥፋት ደረጃውን ከፍ አድርጎ ያሳየ ጭፍጨፋ ነው ሲል እናት ፓርቲ ገልጿል።

ፓርቲው "የሰቆቃው ዘመን ማብቂያ በሥርዓቱ ሳይሆን በሕዝብ እጅ ነው።" በሚል ርዕስ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ አውጥቷል፡፡

በመግለጫውም "በኢትዮጵያ ሥርዓታዊ የሆነ በእምነት ተቋማት፣ በሃይማኖት አባቶችና ምእመናን ላይ የሚደርስ ጥቃት አቻ በሌለው መልኩ ከዳር ዳር ሲያምሳት ማየትና ምንም እንዳልተፈጠረ በዝምታ ማለፍ የተለመደና በተዘዋዋሪ ይሁንታ የመስጠት የሚመስል ክስተት ከሆነ ዓመታት ተቆጥረዋል" ብሏል፡፡

"የግፉ መጠን ከዕለት ዕለት እየቀነሰ ከመሄድ ይልቅ መልኩንና ቦታውን እየቀያየረ አሰቃቂነቱንም በየወቅቱ የከፋ እያደረገ ቀጥሏል።" ያለው ፓርቲው፤ "አንዱን ሰቆቃ ማን፣ እንዴት፣ ለምን እንዳደረገው በበቂ ሳይጠናና ጠያቂም፣ ተጠያቂም ሳይኖር ለጥቂት ጊዜያት ዝም ያለና የቆመ ካስመሰለ በኋላ ያለፈውን በሚያስንቅ እልቂቱ ይቀጥላል"ሲል ገልጿል፡፡

አክሎም እንደማኅበረሰብ ጣት መቀሳሰርና አሁን አሁን ደግሞ እልቂትን በጥንቃቄ በመለማመድ ላይ ያለን ይመስላል። ብሏል፡፡

ፓርቲው ይህንና ቀደም ሲል በተለያዩ ጊዜያት የደረሱ ጥቃቶችና የጅምላ ፍጅቶች በአጋጣሚና በዘፈቀደ እየሆኑ ያሉ ሳይሆን በተጠና መልኩ ሀገርን አጽንተው ባቆሙ ሃይማኖታዊ እሴቶቻችን ላይ ያነጣጠሩና ፈርጀ ብዙ አንድምታ ያላቸው በመጣህብኝ ሰበብ የተጠና ዘር ማጽዳትና ማሳሳት፣ በቀል፣ ማዋረድ፣ የአዲሱን ዓለም አስተዳሰብ ትግበራ አካል መሆኑን በጽኑ እንደሚያምንም አስታውቋል፡፡

"እንዲህ ያሉ ድርጊቶች በጥንቃቄና አሻራ በማይተው መልኩ፣ ገፋ አድርጎ ቢሄድም በማዳፈን የሚፈጸሙ ናቸው" ያለው እናት ፓርቲ፤ "የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር የዚህም ሆነ የቀደሙ ጅምላ ጭፍጨፋዎች ተዋንያን ለፍርድ አደባባይ መቅረባቸው አይቀሬ ነው።" ብሏል፡፡

ፓርቲውን ጨምሮ መሰል ተቋማትና ግለሰቦች በቀደሙት ጊዜያት በተደጋጋሚ ያሰሟቸው ዜጎችና ተጋላጭ የሆኑ የሃይማኖት ተቋማት ጥበቃ እንዲደረግላቸው ያስተላለፏቸው ጥሪዎች ሰሚ በማጣቱ ወይም ሆነ ተብሎ በመታለፉ፤ ዛሬም ጭፍጨፋውና ግድያው በከፋ መልኩ መቀጠሉንም አንስቷል፡፡

በመሆኑም "ኢትዮጵያውያን አንዳችን የአንዳችንን ደህንነት እየጠበቅን የእምነት ተቋማቶቻችንን ከሥርዓታዊ ጥቃት ለመታደግ እጅ ለእጅ ተያይዘን እንድንቆምና ለተሻለ ጊዜ እንትጋ" ሲል እናት ፓርቲ በጽኑ አሳስቧል።

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ በካርቱም የሚገኘው የአምባሳደሯ መኖሪያ ቤት ላይ ጥቃት መፈጸሙን ገለጸች

መስከረም 20/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ዛሬ ሰኞ ማለዳ በሱዳን ካርቱም በሚገኘው የአምባሳደሯ መኖሪያ ቤት ላይ የሱዳን ወታደራዊ አውሮፕላን ጥቃት መፈጸሙን ገልጻለች፡፡

የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፤ በአምባሳደሩ መኖሪያ ቤት ላይ በደረሰው ጥቃት ምክንያት በህንፃው ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል ብሏል።

የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶችን በሚቆጣጠሩት ስምምነቶች መሰረት የዲፕሎማቲክ ሕንጻዎችን እና የኤምባሲ ሰራተኞችን መኖሪያ የመጠበቅን አስፈላጊ መሆኑን የገለጸው ሚኒስቴሩ፤ ጥቃቱን “አሳፋሪ ጥቃት” ሲል ማውገዙን ሮይተርስ ዘግቧል።

የሱዳን ጦር የቀረበበትን ክስ አስመልክቶ እስካሁን የሰጠው ምላሽ የለም፡፡

ለ17 ወራት በዘለቀው የሱዳን ጦርነት የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ በሄምቲ ለሚመሩት ለፈጣን ድጋፍ ሃይሎች ( አር ኤስ ኤፍ) የጦር መሳሪያ ታቀርብ ነበር ሲል የሱዳን ጦር ማስታወቁ ይታወሳል፡፡ የኤምሬትስ ባለስልጣናትም በሱዳን ጦር በኩል የቀረበው ክስ ከእውነት የራቀ ነው ሲሉ ውድቅ አድርገውታል፡፡

ነገር ግን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የማዕቀብ ተቆጣጠሪዎች ቡድን፤ በሱዳን እየነደደ ባለው እሳት አቡ-ዳቢ ቤንዚን ከሚያርከፈክፉ ተዋናዮች መካከል አንዷ ናት ሲል በሪፖርቱ ማመላከቱ ይታወሳል፡፡

በሱዳን ጦር እና ለፈጣን ድጋፍ ሃይሎች ( አር ኤስ ኤፍ) መካከል በተቀሰቀሰው ጦርነት ምክንያት፤ በርካቶች ሕይወታቸውን ሲያጡ፣ ወደ 25 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ለከፍተኛ ችግር እና ረሃብ መጋለጣቸውን እንዲሁም 8 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታውቋል፡፡

በእዮብ ውብነህ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በአፍሪካ አገራት መካከል ለሚደረገው የንግድ ልውውጥ ነጋዴዎች የጉዞ ቪዛ ማግኘት እየቻሉ አደለም ተባለ

መስከረም 20/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያን ጨምሮ በመላው አፍሪካ ይተገበራል ተብሎ የሚጠበቀው የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና፤ ከወዲሁ ችግር እንዳይገጥመው ስጋት እንዳደረበት ፓን አፍሪካ ንግድና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት አስታውቋል።

በዘርፉ የተቀመጡ ስጋቶችን በቅድምያ መፈታት ያለበት ችግር እንደሆነ ሲነገር የቆየ ጉዳይ ቢሆንም፤ እስካሁን ድረስ መፍትሔ መስጠት እንዳልተቻለ የምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት ክቡር ገና ተናግረዋል።

ፕሬዝዳንቱ ክቡር ገና ከአሐዱ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና ሥምምነት በቀጠናው ያለውን የጸጥታ ችግርን ጨምሮ የትራንስፖርትና የሎጂስቲክስ ችግር እንዳይገጥመው ያላቸውን ስጋት ገልጸዋል።

አክለውም፣ የአፍሪካ ነፃ የንግድ የቀጠና ስምምነት ተግባራዊነትን በተመለከተ እንደገና መፈተሽ ያለባቸው ጉዳዮች መኖራቸውን በመግለጽ፤ በአገራቱ መካከል ለሚደረገው የንግድ ልውውጥ ነጋዴዎች የጉዞ ቪዛ ማግኘት እየቻሉ አለመሆኑን አመላክተዋል፡፡

የንግድ ስርአቱን ከመዘርጋት በዘለለ ለኢንቨስትመንት የተሰጠው ቦታ አናሳ መሆኑን የገለጹት ክቡር ገና፤ አብሮ መሄድ ያለባቸው ጉዳዮች መሆናቸውንም አንስተዋል።

የአፍሪካ የንግድ ቀጠና 1 ነጥብ 2 ቢሊየን የአህጉሪቱን ህዝቦች ገበያ እና 3 ቢሊየን ዶላር የሚገመተውን የሀገር ውስጥ ምርት የያዘ ሲሆን፤ ወደ 3 ነጥብ አራት ትሪሊየን የአገራቱን አጠቃላይ ምርት ያንቀሳቅሳል ተብሎ ይገመታል፡፡

በአፍሪካ ይተገበራል ተብሎ የሚጠበቀው ይኸው የንግድ ስርአት በርካታ ጥቅሞች እንዳሉት ሁሉ፤ በአተገባበሩ በኩል ክፍተት እየተስተዋለበት እንደሚገኝ አሐዱ ያነጋገራቸው አፍሪካዊያን ነጋዴዎች መስክረዋል።

በኢትዮጵያ መንግሥት በኩልም በስምምነቱ አተገባበር ላይ ማስተካከል ያለበባቸው ጉዳዮች መኖራቸውን አስተያየት ሲሰጥበት ሰምተናል።

የአፍሪካ አህጉር ነፃ የንግድ ቀጠና የአፍሪካ ህብረት የ2063 አጀንዳ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፤ በስምምነቱ ላይ ከኤርትራ በስተቀር 54ቱ የአፍሪካ ሀገራት ፊርማቸውን ማስቀመጣቸው ይታወቃል።

በአማኑኤል ክንደያ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን 98 በመቶ የአንድ ፓርቲ አባላት ለሆኑበት ምክር ቤት ተጠሪ መሆኑ ተዓማኒነት ያሳጣዋል ተባለ

መስከረም 20/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ መንግሥት ያደራጀውና ሪፖርትም የሚያደረገው ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መሆኑ እንዲሁም፤ 98 በመቶ የአንድ ፓርቲ የበላይነት ላለበት ምክር ቤት ተጠሪ መሆኑ ተዓማኒነቱን ያሳጣዋል ሲል የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) አስታውቋል፡፡

"ፓርቲዊች ሁልጊዜ እንወያይ መነገጋር መቅደም አለበት! የሚል ሀሳብ ታነሳላችሁ፡፡ ነገር ግን የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከመሳሰሉት ትወጣላችሁ ተብለን እንወቀሳለን" የሚሉት የኦፌኮ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሙላት ገመቹ፤ "ይሄ የውይይቶችን ዓላማ ካለመረዳት የሚመጣ ነው" ብለዋል፡፡

"ከሁሉም ቀድሞ ውይይቱ ሳይጀመር ጀምሮ የህግ ማዕቀፉ ላይ እንዲሁም ከማንም ንክኪ የሌለው ውይይት እንዲካሄድ እንደ ፓርቲ ተደጋጋሚ ጥያቄዎች ስንጠይቅ ነበር" ብለዋል፡፡

ይሁን እንጂ መንግሥት የጉዳዩ ባለቤት ሆኖ እራሱ እያደራጀና ካልመራሁት ማለቱ የውይይቱን ተዓማኒነት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

"የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማንኛውንም ጥያቄ የሚያሰተናግድ ነው የተባለ ቢሆንም፤ የሽግግር መንግሥት ጥያቄ ማንሳት ግን ሀገር ማፍረስ ነው" ተብለናል ሲሉም አቶ ሙላት ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

ኮሚሽኑ እንደ ከዚህ ቀደም ዓይነቶቹ ተመስርተዉ እንደደበዘዙ ኮሚሽኖች መዋቅር ውስጥ ያለ በመሆኑ፤ ያሉ ችግሮችን ይፈታል የሚል ዕምነት እንደሌላቸዉ የገለጹት የፓርቲው ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር፤ እራሳቸውን ከኮሚሽኑ ማግለላቸውን ጨምረው አስታውቀዋል፡፡

ከዚህ ቀደም ወደ 13 የሚጠጉ ፓርቲዎች እራሳቸውን ከኮሚሽኑ ማግለላቸው የሚታወስ ሲሆን፤ በሂደት የተወሰኑት ንግግር በማድረግ እንደተቀላቀሉ የሚታወቅ ነው፡፡

በዚህ ጉዳይ ላይ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ከፓርቲዎች ጋር ውይይት በማድረግ ፓርቲዎችን የማሳመን ሥራ እየሰራ እንደሚገኝ በተደጋጋሚ መግለጹ ይታወሳል፡፡

በአቤል ደጀኔ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

መልካም ቀን!
አሐዱ ሬድዮ 94.3  የኢትዮጵያውያን ድምፅ!

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

ብሔራዊ የአእምሮ ጤና ስትራቴጂክ እቅድ በትክክል አለመተግበሩ ተገለጸ

መስከረም 18/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ኢትዮጵያ ከ2013 ጀምሮ እስከ 2017 ዓ.ም ድረስ ለመፈጸም ያቀደችው ብሔራዊ የአእምሮ ስትራቴጂክ እቅድ አስፈጻሚ አካል ባለመኖሩ ምክንያት በትክክል መተግበር አለመቻሉን የአዕምሮ ህሙማን ፎረም አስታወቀ፡፡

የፎረሙ መስራችና ፕሬዝዳንት እሌኒ ይታገሱ ለአሐዱ እንደገለጹት፤ "በመንግሥት ደረጃ ጥሩ የሚባል እቅድ የተቀመጠ ቢሆንም፤ ነገር ግን እስካሁን እቅዱን በሙሉ አቅም ተግባራዊ ማድረግ አልተቻለም።

እቅዱ የአእምሮ ጤናን በተመለከተ ግንዛቤ ማስጨበጥ፣ የአእምሮ ጤና ላይ የሚሰራ የሰው ሃይል ማፍራት፣ የህክምና ማዕከላት ማጠናከር እንዲሁም የመድሃኒት አቅርቦትን ጨምሮ በርካታ እቅዶችን በውስጡ መያዙን ያነሱት እሌኒ፤ "ነገር ግን እቅዱን የሚከታተልና የሚያስፈጽም አካል ባለመኖሩ ምክንያት እስካሁን በትክክል ተግባራዊ እየተደረገ አይደለም" ብለዋል።

እንደ አብነትም ባለፉት ዓመታት ጠቅላላ ለጤናው ዘርፍ ከተበጀተው በጀት፤ 0 ነጥብ 9 በመቶ ብቻ ለአእምሮ ጤና መሰጠቱን ገልጸው፤ ይህም በዘርፉ ላይ መሰራት የነበርባቸው በርካታ ነገሮች እንዳይሰሩ እንቅፋት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ 

አክለውም፤ በጤና ሚኒስቴር በተሰራው አዲስ መዋቅር ቀድሞ የነበሩ የአእምሮ ጤና የባለሙያዎችን ብዛት በመቀነስ፤ ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች ሥር የአዕምሮ ጤና ዴስክ ክፍል እንዲሆን መደረጉን ገልጸዋል፡፡

በአንጻሩ "የአዕምሮ ጤና በዳይሬክቶሬት መልኩ መቋቋም ነበረበት" ያሉት ፕሬዝዳንቷ፤ "ለእቅዱ ትኩረት ተሰጥቶት በርከት ያሉ ባለሙያዎች ሊመደቡለት ይገባ ነበር" ሲሉም አንስተዋል።

ጤና ሚኒስቴር በሐምሌ ወር 2013 ብሔራዊ የአእምሮ ጤና ስትራቴጂክ ዕቅድ (2021-2025)ን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። በወቅቱም የአእምሮ፣ የነርቭ እና የአደንዛዥ ዕፅ ችግሮችን በመቅረፍ የህብረተሰብ ጤናን ማሻሻል ላይ እቅዱ ትኩረቱን ማድረጉ ተገልጾ ነበር።

በአለም ላይ 40 በመቶ የሚሆኑ ሀገራት የአእምሮ ጤና ፖሊሲ የሌላቸው ሲሆን፤ 20 በመቶ የሚሆኑት ሀገራት ደግሞ የአዕምሮ ጤና የህግ ማእቀፍ እንደሌላቸው ይነገራል።

በፍርቱና ወልደአብ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በኦሮሚያ ክልል በጸጥታ ችግር ምክንያት ፈተና ያልወሰዱ ተማሪዎች መኖራቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ

መስከረም 18/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኦሮሚያ ክልል በጸጥታ ችግር ምክንያት የመማር ማስተማር ሥራ ያልጀመሩ ትምህርት ቤቶች መኖራቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምሪያ አስታውቋል፡፡

የመምሪያው ኃላፊ አቶ ወርቅነህ ነድኣሳ ለአሐዱ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ በክልሉ በጉጂ እና በምዕራብ ኦሮሚያ ባለው ግጭት አንዳንድ ትምህርት ቤቶች የተዘጉበት ሁኔታ መኖሩን አንስተዋል፡፡

አክለውም፤ ባለው የሰላም እና የጸጥታ ችግር ምክንያት ፈተና ያልወሰዱ የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች መኖራቸውን ገልጸው፤ ተማሪዎቹን በዚህ ዓመት ለማስፈተን እቅድ መያዙን ተናግረዋል፡፡ የመማር ማስተማር ሥራ ለማስጀመር እየተሰራ እንደሚገኝም አመላክተዋል፡፡

መስከረም 7/2017 ለማስጀመር የታቀደው ትምህርት እስካሁን ያልተጀመረባቸው ቦታዎች መኖራቸውን ያነሱት ኃላፊው፤ ከመስቀል በዓል በኋላ መደበኛው ሥራ ይቀጥላል ተብሎ እንደሚጠበቅም ጨምረው ገልጸዋል።

የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ በዚህ ዓመት 12 ነጥብ 5 ሚሊየን ተማሪዎችን ለመመዝገብ እቅድ መያዙ የሚታወስ ነው፡፡

በእመቤት ሲሳይ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ከፍተኛ አመራር አባል ጃል ሰኚ ነጋሳ ከድርጅቱ መነጠላቸውን አስታወቁ

መስከረም 18/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በጃል መሮ ወይም ኩምሳ ድሪባ ከሚመራው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ራሳችንን አግልለናል ሲሉ የድርጅቱ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የማዕከላዊ ዞን የቀድሞ አዛዥ ጃል ሰኚ ነጋሳ አስታውቀዋል።

ጃል ሰኚ ነጋሳ መሆናቸውን ያስተዋወቁት የድርጅቱ አመራር፣ ከተመረጡ መገናኛ ብዙሀን ዘጋቢዎች በስልክ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች የት እንደሆኑ ባልተገለጸ ቦታ ሆነው ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ረቡዕ መስከረም 15 ቀን 2017 ዓ/ም የወጣውና የማዕከላዊ ዞን ዕዝ፣ በጃል መሮ ወይም ኩምሳ ድሪባ ከሚመራው ቡድን መለየቱን የሚገልፀው መግለጫ፣ የእሳቸውና የቡድናቸው መሆኑንም ጠቅሰዋል።

በኦሮሚያ የቀጠለውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ዝግጁ ነን ሲሉም ጃል ሰኚ መሰከረም 16 ቀን 2017 በሰጡት በዚሁ መግለጫ መናገራቸውን ቪኦኤ ዘግቧል።

ጃል ሰኝ ከድርጅቱ ተለይተው የወጡበትን ምክንያት ሲያስረዱ "ህግና ደንብ የሌለበት እንዲሁም መተዳደሪያ ደንብ የሌለው ድርጅት ነው፣ ጥፋት ሲሰራም ተጠያቂነት የሌለበት ድርጀት ነው፤ በአንደ ሰው የሚመራ መሆኑን አይተንና ተረድተን ወደ ድርጀቱ ደንብና ህግ ተመልሰን እርስ በርሳችን እናሰተካክል ብለን ነው የምንቀሳቀሰው" ሲሉ ተናግረዋል።

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

ኢትዮጵያ እና አይ.ኤም.ኤፍ በተራዘመ የብድር አቅርቦት ላይ የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት ላይ ደረሱ

መስከረም 18/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ.ኤም.ኤፍ) ሠራተኞች ከኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ጋር የተራዘመ የብድር አቅርቦትን በተመለከተ የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተገልጿል።

አይ.ኤም.ኤፍ ባወጣው መግለጫ፤ ድርጅቱ በአራት ዓመታት የሚያቀርበው የ3.4 ቢሊዮን ዶላር የተራዘመ የብድር አቅርቦትን በተመለከተ የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት ላይ ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋር መደረሱን አስታውቋል።

ስምምነቱ በይፋ በዓለም አቀፉ ገንዘብ ተቋም ዋና የአመራር ቦርድ ከታየ በኋላ ኢትዮጵያ ወደ 345 ሚሊዮን ዶላር ገደማ እንደምታገኝ ተገልጿል።

“በገበያ ሥርዓት ላይ የተመሠረተ የውጭ ምንዛሪ ግብይት ተመንን ጨምሮ ኢትዮጵያ አገር በቀል የምጣኔ ሃብት ፖሊሲ ማሻሻያ ማድረጓ በጥሩ ሁኔታ ውጤት እያሳየ ነው” ብሏል ድርጅቱ በመግለጫው።

በገበያ ሥርዓት ላይ የተመሠረተ የውጭ ምንዛሪ ግብይት ተመን መተግበሩ በትይዩና በይፋዊ ገበያ መካከል ያለውን ልዩነት በስፋት እያጠበበ እንደሆነም ተገልጿል።

የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ሠራተኞች ቡደን የተመራው በአልቬሮ ፒሪስ ሲሆን፤ እአአ ከመስከረም 17 እስከ 26፣ 2024 በኢትዮጵያ ቆይታ ማድረጋቸውን መግለጫው ጠቁሟል።

በኢትዮጵያ በኩል ደግሞ፤ የብሔራዊ ባንክ ገዢ አቶ ማሞ ምሕረቱ፣ ከገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሽዴ እና ከገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ ከቡድኑ ጋር ንግግሩን ማድረጋቸው ተመላክቷል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ያለፈው ዓመት ሐምሌ ላይ በገበያ ሥርዓት ላይ የተመሠረተ የውጭ ምንዛሪ ግብይት ተመንን ለመተግበር ውሳኔ አሳልፎ ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩ ይታወሳል።

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ትናንት መስከረም 18፣ 2017 ዓ. ም. ባወጣው መግለጫ፤ ኢትዮጵያ “ስኬታማ ለውጦችን ማድረጓ የማክሮ ኢኮኖሚ መረጋጋትን የሚፈጥር፣ የውጭ ምንዛሬ አቅርቦትን አስተማማኝ የሚያረግና ለዘለቄታዊ የምጣኔ ሃብት እድገት የሚረዳ ነው” ማለቱን ቢቢሲ ዘግቧል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያለፈው ዓመት ሐምሌ ላይ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ የብድር ስምምነት ሊያጸድቅ መሆኑ መዘገቡ ይታወሳል።

ምክር ቤቱ የሚያጸድቀው የብድር ስምምነት የትኛው እንደሆነ ይፋ ባይደረግም፤ በወቅቱ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ለኢትዮጵያ በተራዘመ የብድር አቅርቦት የ3.4 ቢሊዮን ዶላር ብድር ማጽደቁን አስታውቆ ነበር፡፡

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የሱዳን ጦር በዋና ከተማይቱ ካርቱም ላይ የመድፍ እና የአየር ድብደባ መፈጸሙ ተገለጸ

መስከረም 18/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የሱዳን ጦር በካርቱም ያጣቸውን ቦታዎች መልሶ ለመያዝ በተቀናቃኙ የፈጥኖ ደራሽ ሃይሎች ላይ ከፍተኛ የመድፍ እና የአየር ድብደባ መፈጸሙ ተገልጿል፡፡

የሱዳን መከላከያ ጦር ካርቱምን መልሶ ለመያዝ በማሰብ ጥቃቱን ማድረሱም ተነግሯል፡፡

በዚህም ጥቃት በጄነራል አልቡርሃን የሚመራው የሱዳን ጦር ታጣቂ ቡድኑ በሚገኝባቸው የካርቱም ሰፈሮች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን የቢቢሲ ዘገባ አመላክቷል፡፡

ሱዳን በሚያዚያ 2023 የመንግሥት ጦርና የልዩ ሃይሉ ቡድን ወደጦርነት ከገቡ ጀምሮ 150 ሺሕ የሚደርሱ ሰዎች ሲሞቱ፤ ከ10 ሚሊየን በላይ ሰዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል፡፡

የሱዳንን የእርስ በርስ ጦርነት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከአለም አስከፊ የሰብአዊ ቀውሶች አንዱ ሲል ገልጾታል፡፡

ሁለቱ የሱዳንን ሃይሎች ለማደራደር አሜሪካ ተደጋጋሚ ሙከራዎችን ብታደርግም እስካሁን ሊሳካ እንዳልቻለ ተሰምቷዋል፡፡

የሱዳን ጦር ዋና አዛዥ ጀነራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን ታጣቂ ቡድኑ የያዛቸውን ቦታዎች ለሱዳን መንግስት ሲያስረክብ ብቻ ለድርድር እንደሚቀመጡ ገልጸዋል፡፡

በገነነ ብርሃኑ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

ዩክሬን በረጅም ሚሳኤሎች ሩሲያን የምትመታ ከሆነ ሩሲያ በኒኩለር ምላሽ እንደምትሰጥ ፑቲን አስጠነቀቁ

መስከረም 18/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ዩክሬን በረጅም ሚሳኤሎች ሩሲያን የምትመታ ከሆነ ሩሲያ በኒኩለር ምላሽ ትሰጣለች ሲሉ ቭላድሚር ፑቲን አሜሪካንና አጋሮቿን አስጠንቅቀዋል።

ፑቲን ለዩክሬን የረጅም ርቀት ሚሳኤሎችን ሊያቀርቡ ላሰቡ ምእራባውያን ሀገራት ቀይ መስመር ማስመራቸውን ገልጸዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ "ዩክሬን በረጅም ርቀት ሚሳኤሎች ሩሲያን የምትመታ ከሆነ የመሳሪያ አቅራቢዎቹም የጦርነቱ አካል ይሆናሉ፡፡ ለዚህም ደግሞ በኒኩለር መሳሪያ ምላሽ እንሰጣለን" ብለዋል፡፡

የቀድሞዋ ሶቪየት እና የሩሲያ ዲፕሎማት ኒኮላይ ሶኮቭ፤ "ፕሬዝዳንቱ ያስተላለፉት ግልጽ መልዕክት ነው። ጦርነቱ ወደ ኒኩለር መሳሪያ ሊያመራ ይችላል" ሲሉ ስጋታቸውን መግለጻቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

የሩሲያ ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያና በምዕራባዊያኑ ቸልተኝነት የሩሲያና ዩክሬን ጦርነት ከዚህም በላይ እየባሰ ሄዶ ሦስተኛውን የአለም ጦርነት ሊቀሰቅስ እንደሚችል እየተገለጸ ይገኛል፡፡

በገነነ ብርሃኑ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

እንኳን አደረሳችሁ!

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች፤ እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳቹህ!

አሐዱ በዓሉ የሰላም፣የፍቅር የደስታ ይሆንላችሁ ዘንድ መልካም ምኞቱን ይገልጻል።

አሐዱ ሬድዮ 94.3  የኢትዮጵያውያን ድምፅ!

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የመስቀል ደመራ በዓል በተለያዩ ሀይማኖታዊ ሥነ-ስርዓቶች በመከበር ላይ ነው

መስከረም 16/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የመስቀል ደመራ በዓል አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በተለያዩ ሀይማኖታዊ ሥነ-ስርዓቶች በመከበር ላይ ይገኛል፡፡

በዓመቱ መስከረም16 በኢትዮጵያ የክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት የሚከበረው ይህ በዓል፤ ከዋዜማው አንስቶ በታላቅ በድምቀት ከሚከበሩ የአደባባይ በዓላት ውስጥ አንዱ ነው።

በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ እየተከናወነ በሚገኘው የደመራ አከባበር ሥነ-ስርዓት ላይም፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካን ጨምሮ ሚኒስትሮች፣ የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ አምባሳደሮች እንዲሁም ከተለያዩ ሀገራት የመጡ ቱሪስቶች ታድመውበታል፡፡

በዓሉን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ፓትሪያሪክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በቡራኬ በጾሎት አስጀምረዋል።

በበዓሉ ላይ በስምንት ቋንቋዎች የተዘጋጁ መዝሙሮች የሚቀርቡ ሲሆን፤ የሰንበት ትምህርት ቤቶችም የተለያዩ መዝሙሮችን እና ትርዒቶችን ያቀርቡበታል፡፡

በተጨማሪም ላለፈው አንድ ዓመት ዝግጅት ሲያደርግ በነበረው የደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን መሪነት የመስቀል ደመራ ሥነ ስርዓት እንደሚከናወን ተነግሯል።

የመስቀል ደመራ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት(ዩኔስኮ) እውቅና ተሰጥቶት በዓለም አቀፍ ቅርስነት የተመዘገበ በዓል መሆኑ ይታወቃል።

ፎቶ፡- ማህበራዊ ሚዲያ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…
Subscribe to a channel