አሐዱ ራድዮ 94.3 Your source for top local and international news and analysis. "Voice of Ethiopian" የአሐዱ የቴሌግራም ቻናል ቤተሰብ በመሆን ወቅታዊና እውነተኛ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ
ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ይዘዉ የሚቀርቡት የድርድር አቋም ተለዋዋጭ አለመሆኑ ዉጤት እንዳይመጣ አድርጓል ተባለ
መስከረም 22/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ኢትዮጵያ ራሷን እንደነጻ አገር ከምትቆጥረው ሶማሊላንድ ጋር በባህር ዳርቻ አጠቃቀም ዙርያ የመግባቢያ ሰነድ ከተፈራረሙ በኋላ በሞቃዲሾ እና በአዲስ አበባ መካከል ያለው ግንኙነት መበላሸቱን ተከትሎ፤ ቱርክ ሁለቱን ሀገራት ለማደራደር ጥረት እያደረገች ትገኛለች።
ቱርክ ለዚህ የኢትዮጵያ እና ሱማሊያ የባሕር በር ውዝግብ መፍትሄ የማፈላለግ ጥረቷን እንደምትገፋበት አስታውቃለች።
የቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ይህን ያለው፤ የአገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ኒውዮርክ ውስጥ ከኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ እና ከሱማሊያው ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አሕመድ ፊቂ ጋር በተናጥል ከተወያዩ በኋላ ነው።
አሐዱም ከዚህ ቀደም በቱርክ አደራዳሪነት የተካሄዱት ዉይይቶች ለምን ዉጤታማ መሆን አልቻሉም? ምክንያቱ ምን ሊሆን ይችላል? ሲል የዲሎማሲዉ ዘርፍ ባለሙያዎችን ጠይቋል።
ቱርክ በአፍሪካ ሀገራት ካላት ጠንካራ የኢኮኖሚ እና ፖለቲካዊ ተሳትፎ አንጻር በሶማሊያ እና በኢትዮጵያ የተፈጠረዉን ዉጥረት ለማርገብ እና ለማደራደር ብቃቱ እንዳላት የገለጹት፤ የቀድሞው የሰብዓዊ መብት ኮሚሽነር አምባሳደር ጥሩነህ ዜና ናቸው።
አምባሳደር ጥሩነህ ከዚህ በፊት በነበሩት ዉይይቶች በተለይም የሶማሊያ አቋም አለመሻሻሉ ድርድሩ ዉጤት አልባ እንዲሆን አድርጓታል ብለዋል።
አክለዉም፤ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ለድርድር ይዘዉ የሚቀርቡት አቋም ተለዋዋጭ አለመሆኑ ዉጤት እንዳይመጣ ካደረጉት ምክንያቶች ውስጥ አንዱ መሆኑን ገልጸዋል።
"ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያላትን መልካም የሆነ ግንኙነት ለማስቀጠል በዲፕሎማሲ መጠንከር እና መስራት ይገባታል" ሲሉም አምባሳደር ጥሩነህ ጠቁመዋል፡፡
የቀድሞ ዲፕሎማት አቶ ዳያሞ ዳሌ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ ከሶማሊ ላንድ ጋር በተፈራረመችዉ የመግባቢያ ሰነድ ዙሪያ ሁለቱ ሀገራት ያላቸው አቋም አለመቀየሩ ያለፉት ድርድሮች ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩን አንስተዋል።
በቱርክ የተያዘዉ ሦስተኛ ዙር የአደራዳሪነት ሚና ለዉጥ ያመጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጸዋል።
ባለሙያዎቹ አክለዉም ቱርክ በቀጠናው በተለይም በሶማሊያ የግብፅን ተጽዕኖ ፈጣሪነት ስለማትፈልገዉ ለኢትዮጵያ መልካም አጋጣሚ ይሆናል ብለዋል።
ቱርክ እስካሁን በሁለቱ ጎረቤት ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ለማስተካከል ሁለት ዙር የጋራ የንግግር መድረኮችን ማዘጋጀቷ የሚታወስ ሲሆን፤ በመስከረም ወር መጀመሪያ ላይ በአንካራ ሊካሄድ የነበረው ሦስተኛው ዙር ድርድር መሰረዙ ይታወሳል።
ይህንንም ተከትሎ ለሦስተኛ ጊዜ አዲስ ድርድር ከመደረጉ በፊት ቱርኩ ሁለቱን አገራት በተናጥል ለማወያየት ማቀዷን አስታውቃለች።
በፅዮን ይልማ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ ከአፋር ክልል ፕሬዝዳንት አወል አርባ ጋር ተወያዩ
መስከረም 22/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ የትግራይ እና የአፋር ህዝብ ግንኙነት ለማጠናከር ከአፋር ክልል ፕሬዝዳንት አወል አርባ ጋር ዛሬ መስከረም 22 ቀን 2017 ዓ.ም በሰመራ ከተማ ተወያይተዋል፡፡
ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ የተመራው የትግራይ ልዑካን ቡድን አፋር ሲደርስ፤ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ እና ካቢኔያቸው በሰመራ አውሮፕላን ማረፊያ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
በፕሬዝዳንቱ የሚመራው የትግራይ ልዑካን ቡድን፤ የደቡብ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ምስራቅ ዞኖችን ርእሰ መስተዳድሮች ያቀፈ መሆኑን ድምጸ ወያኔ ዘግቧል::
የርዕሰ መስተዳድሮቹ ውይይት የሁለቱን አጎራባች ከተሞች የቀድሞ ግንኙነት ማደስ ላይ ያተኮረ መሆኑም ተገልጿል፡፡
ሰኞ መስከረም 20 ቀን 2017 ዓ.ም በመቐለ ከተማ በተደረገ ስብሰባ ላይ፤ የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት አቶ ጌታቸው ረዳ ኤርትራን ጨምሮ ከሌሎች ሁሉም አጎራባች ህዝቦች ጋር ዘላቂ ሰላም ለመፍጠር እንደሚሰሩ መግለጻቸው ይታወሳል።
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
"ሕዝባዊ ክብረ በዓላት ለየትኛውም አይነት የፖለቲካ አጀንዳ ማራመጃነት መጠቀምን አይገባም" ኢዜማ
መስከረም 22/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ሕዝባዊ ክብረ በዓላት ለየትኛውም አይነት የፖለቲካ አጀንዳ ማራመጃነት መጠቀምን አይገባም ሲል የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) አሳሰበ፡፡
ፓርቲው ዛሬ ባወጣው መግለጫ፤ "ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በተለይም ኢሬቻን በማክበር ሒደት በመንግሥት መዋቅሮች እና በመንግሥታዊ ኃላፊነት ቦታ ላይ የተቀመጡ ባለሥልጣናት ባሕሉ ካለው ሕዝባዊ እሴት ባፈነገጠ መልኩ ባሕሉን ከሕዝቡ ባለቤትነት ነጥቆ ፖለቲከኞቹ ዋነኛ አጋፋሪ ሆነው መምጣታቸው በሌሎች ዘንድ የመገለል እና የስጋት ስሜት ይፈጥራል" ሲል ገልጿል፡፡
አክሎም፤ ገዢው ፓርቲ በዚህ መልኩ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት በሚመስል መልኩ መንቀሳቀሱ ተገቢ አይደለም ብሎ እንደሚያምንም አስታውቋል፡፡
"ፓርቲው በመርሆዎቹ ካስቀመጣቸው መሠረታዊ ሐሳቦች መካከል አንዱ “ኢትዮጵያ ልንንከባከበው የሚገባን ባለ ብዙ ባሕል፣ ታሪክ እና ቅርስ ባለቤት የሆነች ሀገር መሆኗን ከልብ እናምናለን” የሚል ነው።" ያለው ኢዜማ፤ እነዚሕን ባሕል፣ ታሪክ እና ቅርሶች በተሻለ ደረጃ ለመጠበቅ ለማቆየት እና ለማጎልበት የመንግሥት፣ የማኅበረሠቡ እና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ኃላፊነት መሆኑን አመላክቷል፡፡
እነዚህ የጋራ ማንነትን በመፍጠር ሚናቸው ከፍተኛ የሆኑ ባሕሎችን በእኩል መንከባከብ እና ማሳደግ ተገቢ እና የሚበረታታ መሆኑንም አንስቷል።
ነገር ግን "ሀገራችን ባላት ፌደራላዊ የመንግሥት ስሪትን በመንተራስ መሠል ባህሎችን የጋራ ማንነት ማጠንከሪያ ምሰሶዎች ከማድረግ ይልቅ፤ የፖለቲካ ውግንና እና ትርፍ መሸቀጫነት ለማድረግ ሲሞከሩ ማየት የሚያሳዝን ነው" ሲል ገልጿል፡፡
"መንግሥት ከባሕል፣ ታሪክ እና ቅርሶች ጉዳይ ጋር በተያያዘ ዋነኛ ኃላፊነቱ የሆነውን እነኚህን ለማሳደግ፣ ለመጠበቅ እና ለማጎልበት የሚረዱ የሕግ ማዕቀፎችን እና ፖሊሲዎችን ማውጣትና መተግበር፣ ግንዛቤ መፍጠር እና ለቅርሶቹ አስፈላጊውን ጥበቃ ማድረግ እንዲሁም ባሕሎቹ ሲከበሩ ያለምንም ስጋት ተከብረው እንዲጠናቀቁ የጸጥታ እና ደኅንነት ሥራን መሥራት ብቻ ነው።" ሲልም አሳስቧል፡፡
በተለይ ለባሕሉ ተብሎ በመንግሥት መስሪያ ቤቶች ደብዳቤ የንግድ ማኅበረሠቡን በሚያስጨንቅ እና ከአቅም በላይ የሆነ ከፍተኛ አስገዳጅ የገንዘብ መዋጮ መጠየቅ ማኅበረሠቡን ከፍተኛ ምሬት ውስጥ በመክተት ባሕሉን በስጋት እንዲመለከተው እያደረገ እንደሚገኝ ፓርቲው በመግለጫው አመላክቷል፡፡
"የባሕሉ ባለቤት የሆነው ሕዝብም ተቋማትን እና ግለሰቦችን አስጨንቃችሁ መዋጮ በመሰብሰብ በዓሉን አድምቁልኝ አይልም" ያለው ኢዜማ፤ "ይህንንም ሕገወጥ ተግባር የሚጠየፈው መሆኑን አንዳች ጥርጥር የለንም።" ብሏል፡፡
"በመሆኑም የየትኛውንም ማኅበረሠብ ባሕላዊም ሆነ ሃይማኖታዊ በዓል ለፖለቲካ ፍጆታ ማዋል ባሕሉን መበረዝ እንደሆነ ሊታወቅ ይገባል።" ያለው የኢዜማ መግለጫ፤ ይህን መሰል የአደባባይ ክብረ በዓላት ለየትኛውም አይነት የፖለቲካ አጀንዳ ማራመጃነት መጠቀምን እንደሚያወግዝም አስታውቋል፡፡
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ዶክተር አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ የፍርድ ቤት ዕግድ በመጣስ ሌላ ክስ ቀረበባቸው
👉በኦሎምፒክ ኮሚቴ ላይ የተጣለው ዕግድ እንዲፀናም ተወስኗል
መስከረም 22/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደ ጊዮጊስ፣ የኦሊምፐክ ኮሚቴ የባንክ ሒሳቦች እንዳይንቀሳቀሱ በፍርድ ቤት የተጣለውን ዕግድ በመጣስ ሌላ ክስ ቀርቦባቸዋል፡፡
የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ፍትሐ ብሔር ምድብ ችሎት፤ እነ አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ ያቀረቡትን የክስ አቤቱታ፣ ችሎቱ ትናንት ማክሰኞ መስከረም 21 ቀን 2017 ተመልክቶ ትዕዛዝ ሰጥቶበታል፡፡
በእነ ኃይለ ገብረ ሥላሴ የቀረበው ክስም ‹‹ይግባኝ ሰሚ ችሎቱ መስከረም 8 ቀን 2017 በኦሎምፒክ ኮሚቴ የባንክ ሒሳብ እንዳይንቀሳቀስ ዕግድ መሰጠቱ እየታወቀ፣ ሁለተኛ መልስ ሰጪ ዶክተር አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ እግድ በተሰጠ በማግሥቱ መስከረም 9 ቀን በአዲስ አበባ ማሪዮት ሆቴል ለሚዲያ አካላትና "እሸልማቸዋለሁ" ላሏቸው አካላት ጥሪ አድርገው፣ ከታገደው ገንዘብ ላይ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ በአደባባይ ሲሸልሙ ውለዋል›› የሚል ነበር።
ከዚህም ባለፈ ዶክተር አሸብር ባዘጋጁት የሽልማት ፕሮግራም ላይ ባደረጉት ንግግር፣ ‹‹ምንም እንኳን ሽልማት እንዳንሰጥ በእነ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ የታገድን ቢሆንም እኛ ግን ሽልማቱን እንሰጣለን፤›› በማለት፣ የተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ባሉበት መናገራቸውን የቀረበው ክስ ያስረዳል።
‹‹በመሆኑም ሆነ ብለው በአደባባይ የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ ባለማክበር የፈጸሙትን የዕግድ ጥሰት ፍርድ ቤቱ አጣርቶ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 443 መሠረት ዕርምጃ እንዲወስድ በአክብሮት እናመለክታለን፤›› ሲሉ ከሳሾች እነ አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ (አራት ሰዎች) ጠይቀዋል።
የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ፍትሐ ብሔር ምድብ ችሎት በእነ አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ የቀረበውን የዕግድ ጥሰት አቤቱታና እነ አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ (ዶ/ር) በጽሑፍ የሰጡትን ምላሽ ተመልክቶ፣ መስከረም 21 ቀን 2017 ዓ.ም. ትዕዛዝ ሰጥቷል።
ችሎቱ በሰጠው ትዕዛዝም፣ ዕግዱ መጣስ አለመጣሱን አስመልክቶ የቀረበው ክርክር መደበኛው የችሎት ጊዜ ሲጀምር በመደበኛው ችሎት የሚታይ ይሆናል በማለት ትዕዛዝ የሰጠ ሲሆን፣ የመደበኛ ክርክሩን ቅሬታ ለመስማት ለጥቅምት 1 ቀን 2017 ዓ.ም. ቀጠሮ መስጠቱን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል።
ከዚሁ አቤቱታ ጋር ተያይዞ ለችሎቱ የቀረበው ሌላው ጉዳይ፣ የኦሎምፒክ ኮሚቴ የባንክ ሒሳብና የኦሎምፒክ ኮሚቴው ያካሄደው ምርጫ ታግዶ መቆየት አለበት ወይስ የለበትም የሚል ነው።
የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ፍትሐ ብሔር ምድብ ችሎት የሁለቱን አካላት ክርክር ከተመለከተ በኋላ፣ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቀደም ሲል የሰጠውን ዕግድ ያነሳበት አግባብ ስህተት በመሆኑ ሊታረም ይገባል አይገባም የሚለው ክርክር በመደበኛው የችሎት ጊዜ ታይቶ ዕልባት እንደሚያገኝ ገልጿል፡፡
ይህ የይግባኝ ክርክር ዕልባት እስኪያገኝ ድረስም የተሰጠው ዕግድ ትዕዛዝ ጸንቶ እንዲቆይ ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
"በአማራ ክልል እየተፈጸመ ያለው የጅምላ እስር በአስቸኳይ ማቆም አለበት" አምነስቲ ኢንተርናሽናል
መስከረም 22/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ የአማራ ክልል ዋና ዋና ከተሞች ከቅዳሜ መስከረም 17/2017 ዓ.ም ጀምሮ የአካዳሚክ ማህበረሰብ አባላትን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በዘፈቀደ እየታሰሩ እንደሚገኙ አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ።
የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ አምነስቲ "የክልሉ ባለስልጣናት ይዘው በመጡት “የሥም ዝርዝር” መሠረት፤ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሲቪል ሰዎችን በቁጥጥር ሥር ማዋላቸውን የዓይን እማኞች ገልጸውልኛል" ሲል ትናንት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
ባለስልጣናቱ ሰዎቹን በቁጥጥር ሥር ባዋሉበት ወቅት የብርበራም ሆነ የእስር ትዕዛዝ አለማቅረባቸውን የአይን እማኞቹ የገለጹ ሲሆን፤ የተወሰኑት እስራት በምሽት መከናወናቸውን ለድርጅቱ ተናግረዋል፡፡
የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምስራቅ እና ደቡባዊ አፍሪካ ቀጣና ዋና ዳይሬክተር ቲጌሬ ቻጉታህ፤ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ግለሰቦች በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት እንዲሆም በሌሎች ሕጎች በተደነገገው መሰረት በ48 ሰዓት ውስጥ ፍርድ ቤት አለመቅረባቸውን ገልጸው፤ "ይህም “የዘፈቀደ የጅምላ እስር” የኢትዮጵያ መንግሥት የሕግ የበላይነትን ሙሉ ለሙሉ ቸል ለማለቱ ተጨማሪ ማሳያ ነው” ብለዋል፡፡
ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም "የኢትዮጵያ ባለስልጣናት እነዚህን የዘፈቀደ እስራት በአስቸኳይ ማቆም አለባቸው!" ያሉ ሲሆን፤ "በእስር ላይ ያሉ ሰዎች ላይ በአለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ባላቸው ወንጀሎች ክስ መመስረት እና ህጋዊ ሂደቶችን መከተል ወይም ያለ ምንም ተጨማሪ መዘግየት ከእስር ሊለቀቁ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
በዚህ እስር ላይ ከክልሉ ፖሊስ አባላት በተጨማሪ መከላከያ ሰራዊት አባላትም መሳተፋቸውን የገለጸው ድርጅቱ፤ "የመንግሥት ባለስልጣናት በዘፈቀደ ማሰርን እንደ "የጭቆና መሣሪያ" መጠቀማቸውን ሊያቆሙ ይገባል" ሲል አሳስቧል፡፡
የአማራ ክልል እና የኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት በትላንትናው ዕለት በጋራ በሰጡት መግለጫ፤ በክልሉ ከሰሞኑ የተካሄደው እርምጃ “ህግ ማስከበር” መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
የሀገር መከላከያ ሰራዊት የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነ፤ “የኦፕሬሽኑ ዓላማ ሁከትን እና ብጥብጥን አስወግዶ ለክልሉ መንግሥት እና ህዝብ ሰላምን ማስፈን” መሆኑን የገለጹ ሲሆን፤ ይህንን ሥርዓት ለማስያዝ የመከላከያ ሠራዊቱ ከክልሉ መንግሥት ጋር በመሆን በጥናት ላይ የተመሰረተ የሕግ ማስከበር ሥራ እያካሄደ መሆኑን ተናግረዋል።
የአማራ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሀላፊ ዶክተር መንገሻ ፈንታው በበኩላቸው፤ በክልሉ የሚስተዋለውን የፀጥታ ችግር ለመቅረፍ በርካታ ጥረቶች መደረጋቸውን ገልጸው፤ ችግሩን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ባለፉት ወራት የመንግስት የሥራ ሀላፊዎች የመሯቸው በርካታ የውይይት መድረኮች ቢካሄዱም አለመሳካታቸውን ተናግረዋል፡፡
የአሁኑ እርምጃ በሰው እገታ፣ ግድያ እና መሰል ሕገወጥ ተግባራት ላይ የሚሳተፉ፣ በመንግስትና በተለያዩ መዋቅሮች የሚገኙ አካላትንም ተጠያቂ እንደሚያደርግ የገለጹት ዶክተር መንገሻ፤ "ለሰላም የተዘረጋን እጅ ያልተቀበለ ኃይል ላይ መንግሥት የሚወስደው እርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል" ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የአማራ ክልል መንግሥት ችግሮችን በውይይት እና በምክክር ለመፍታት ቢሞክርም ምላሹ ግን በሚፈለገው መንገድ እንዳልሆነ እየተገለጸ ይገኛል።
በእዮብ ውብነህ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ኢራን በእስራኤል ላይ ከፍተኛ የሚሳዔል ጥቃት ከፈተች
👉 ጆ ባይደን የአሜሪካ ጦር የኢራንን ሚሳዔሎች መትቶ እንዲጥል ትዕዛዝ ሰጥተዋል
መስከረም 21/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ኢራን በእስራኤል ላይ ከፍተኛ የባላስቲክ ሚሳዔል ጥቃት መክፈቷን የእስራኤል መከላከያ ኃይል አስታውቋል።
መከላከያ ኃይሉ ከኢራን የሚተኮሱ ሚሳዔሎች ወደ እስራኤል ግዛት መግባታቸውን ባወጣው መግለጫ የገለጸ ሲሆን፤ ከ180 በላይ ሚሳዔል መተኮሳቸውን አረጋግጧል።
የሚሳኤል ጥቃቶቹ ወደ እስራኤል ዋና ከተማ ቴላቪቭ ያነጣጠሩ መሆናቸውም ተነግሯል፡፡
ዛሬ አመሻሽ ላይ በአብዛኛው የእስራኤል ግዛቶች ውስጥ የሚሳዔል ጥቃት ማስጠንቀቂያ ደውሎች ሲደወሉ መሰማታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
አሁን ላይ የሚሳኤል ተኩሱ መቆሙ የተነገረ ሲሆን፤ በጥቃቱ ኢራን ቢያንስ 250 የሚደርሱ የባላስቲክ ሚሳኤሎችን ወደ እስራኤል ማስወንጨፏን የእስራኤል መገናኛ ብዙሃን ማምሻውን እየዘገቡት ይገኛሉ።
የአሁኑ የኢራን ጥቃት እስራኤል በሄዝቦላህ መሪ ሃሰን ናስራላህ ላይ ለፈፀመችው ግድያ አጸፋ ነው ተብሏል።
የእስራኤል መከላከያ ኃይል በበኩሉ ጥቃቱ መጀመሩን ተከትሎ ለዜጎቹ ባስተላለፈው መልዕክት፤ “የሚወጡ መመሪያዎችን በንቃት እንዲከታተሉ” አሳስቧል። ጥቃቱ ያደረሰው ጉዳት መጠንን አስመልክቶ ያለው ነገር የለም።
አሜሪካ ኢራን ዛሬ ሌሊት ጀምሮ እስራኤልን ልታጠቃ እንደምትችል አስጠንቅቃ የነበረ ሲሆን፤ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የአሜሪካ ጦር ኢራን ወደ እስራኤል የተኮሰቻቸውን ሚሳዔሎች መትቶ እንዲጥል ትእዛዝ መስጠታቸውን ዋይት ኋውስ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
በትግራይ ክልል የሸቀጦች ዋጋ እንዲጨምር ነጋዴዎች "የኮቴ" ክፍሉ እየተባሉ መሆኑ ተገለጸ
መስከረም 21/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በትግራይ ክልል የሸቀጣሸቀጥና በመሰረታ ፍጆታ ዋጋ እንዲጨምር እና እጥረት እንዲከሰት በየኬላው ነጋዴዎችን "ለኮቴ" ወይንም እቃ ያወረዱበትን ክፍያ ክፈሉ እየተባሉ መገደዳቸውን የክልሉ ንግድና ኤክስፖርት ኤጀንሲ አስታወቀ።
የኤጀንሲው የንግድ ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ ዳይሬክተር አቶ ካሳሁን ክንደያ "በመንገዱ የሚደረጉ ሕገ ወጥ ክፍያዎችን መቆጣጣር ከአቅማች በላይ ነው" ያሉ ሲሆን፤ ይህ ሁኔታ የተለያዩ ምርቶች ወደ ክልሉ እንዳይገቡ ጫና እየፈጠረ እንደሚገኝ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
አክለውም ነዳዴዎች ላይ የሚደረጉ ጫናዎች ማህበረሰቡን እንደሚጎዱ ገልጸው፤ የሚደረጉ የዋጋ ጭማሪዎችን በተመለከተ የፌደራል መንግሥቱ የዋጋ ተመኑን በትክክል እየላከ አለመሆኑን አንስተዋል፡፡
የፌደራል ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የዋጋ ተመኑን ጉዳይ እንዲስተካከል በተደጋጋሚ በደብዳቤ መጠየቃቸውንና ምላሽ አለማግኘታቸውንም ጨምረው ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም በየኬላው የሚደረጉ ሕገ ወጥ ክፍያዎችን በተመለከተ የፌደራል መንግሥት ትኩረት እንዲሰጥ በተደጋጋሚ ቢጠይቁም ምንም ምላሽ እንዳልተሰጣቸው አስረድተዋል፡፡
ኤጀንሲው ትክክለኛውን ዋጋ ባለማወቁ ምክንያት ነጋዴውን ለመቆጣጠር እንዳልተቻለ የገለጹት አቶ ካሳሁን፤ ችግሩን በተመለከተም የክልሉ ቢሮ ከሚመለከተው አከካል ጋር በጋራ በመሆን ውይይት ማድረጉን ገልጸዋል፡፡
በክልሉ የሚገኙ ነጋዴዎች በየኬላው ከ5 ሺሕ እስከ 8 ሺሕ ብር ድረስ እየተጠየቁ እንደሚከፍሉም ተመላክቷል።
በአለምነው ሹሙ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ከቅንጡ የግንባታ መመሪያዎች በፊት መሰረታዊ ጥያቄዎች ምላሽ ሊሰጣቸው እንደሚገባ ባለሙያዎች ተናሩ
መስከረም 21/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን በቅርቡ ባስተላለፈው የመንገዶች እና የግንባታ መመሪያ መሰረት፤ 15 ሜትር ስፋት ያላቸው መንገዶች በሚያዋስኗቸው ይዞታዎች ዝቅተኛው የቦታ ስፋት ቢያንስ 500 ሜትር ካሬ መሆን እንደሚገባው ደንግጓል።
ውሳኔውን ተከትሎ አሐዱ ያነጋገራቸው ባለሙያዎች "መሰረታዊ ጥያቄዎች አስቀድሞ ምላሽ ሊያገኙ ይገባል" ይላሉ።
የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ዶ/ር አጥላው ዓለሙ፤ አሁን ባለንበት ሁኔታ ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገባቸው ጉዳዮች እንዳሉ ገልጸዋል።
የሥራ እድል የፈጠሩ ቦታዎችን ማፍረስ፣ በባንክ ብድር እና በዜጎች አቅም የሚገነቡ ግንባታዎችን ማቋረጥ ጉዳቱ የጥቂት ግለሰቦች ብቻ አይሆንም ሲሉም ተናግረዋል።
አክለውም "አሁን እኛ ማድረግ ያለብን ሰዎች ሥራ ፈጥረው እራሳቸውን እንዲለውጡ፣ ባለው አቅም ተጠቅመው ሌላ ተጨማሪ አቅም እንዲፈጥሩ ማድረግ እንጂ እንዲህ አይነት ቅንጡ ነገሮች ማድረግ አለብን ብዬ አላምንም" ብለዋል፡፡
ይህ ህግ የወጣበት ምክንያት በግልጸ አልተነገረም የሚሉት ዶ/ር አጥላው፤ "ቢገለጽም ከጀርባው ያለው ምክንያት እና ፊት ለፊት ያለው ምክንያት ላይጣጣም ይችላል" ሲሉ ተናግረዋል፡፡
"ትናንሽ ሥራዎች ቢፈጠሩ ለብዙ ሰዎች መኖሪያ ናቸው፡፡ እነዚህን ሥራዎች ስንከለክል በብዙ ሰዎች ላይ ፈርደን ነው፡፡ ይህ ለምን እንደማይታይ አይገባኝም" ሲሉም ተገልጸዋል፡፡
የመሬት ባለቤትነት ከመንግሥት እጅ እንዲወጣ ማድረግ ከመመሪያው መቅደም የሚገባው ጉዳይ እንደሆነ የሚያብራሩት ደግሞ የምጣኔ ሐብት ባለሙያው አቶ መቆያ ከበደ ናቸው።
ግለሰቦች የመሬት ባለቤት መሆን እስካልቻሉና መሬት በመንግሥት እጅ እንስካለ ድረስ፤ የሚፈለገውን ያህል ውጤት ይመጣል ተብሎ እንደማይጠበቅ ባለሙያው ለአሐዱ ተናግረዋል።
"የግንባታው መመሪያ እና የኮሪደር ልማቱ በርካታ ቦታዎችን እያፈረሰ ነው" ያሉት ባለሙያው፤ የንግድ እንቅስቃሴዎች የሚኖሩት መንገድ በሚገነቡ ሕንጻዎች መሆኑን አንስተዋል።
"ይህ ደግሞ መንግሥት የግብር ተጠቃሚ ያደርገዋል" ያሉ ሲሆን፤ እነዚህ የገቢ ምንጮች ላይ ያደረጉ ስራዎችን መከልከል እራሱ መንግሥትን የሚጎዳ ነው ብለዋል።
በዚህ መመሪያ መሠረት በርካታ ግንባታዎች እየተቋረጡ ሲሆን፤ ይሄም ከጊዜና ከገንዘብ አንፃር ለኪሳራ እንደሚዳርግ አሐዱ ያነጋገራቸው ባለሙያዎች ተናግረዋል።
በፍርቱና ወልደአብ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ኢራን የፖሊስ አባል በመግደል የተከሰሱ ሁለት ሰዎችን በስቅላት ቀጣች
መስከረም 21/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኢራን በጦር መሳሪያ በመታገዝ ዝርፊያ ሲፈጽሙ የነበሩ ሁለት ሰዎች አንድ የፖሊስ አባል በመግደላቸው በስቅላት መቀጣታቸውን የአገሪቱ የፍትህ አካላት ገልጸዋል፡፡
ሁለቱ ወንጀለኞች ከአራት አመት በፊት ከሕግ አስከባሪዎች ጋር በተፈጠረ ግብግብ መሐል ለማምለጥ ሲሞክሩ፤ አንድ የፖሊስ አባል በጥይት መግደላቸው የተነገረ ሲሆን፤ በመጨረሻው የፍርድ ቤት ውሳኔ በስቅላት መቀጣታቸው የሲቢ ኤስ ዘገባ አመላክቷል፡፡
አምነስቲ ኢንተርናሽናልን ጨምሮ የመብት ተሟጋቾች ኢራን ከቻይና ቀጥላ በየዓመቱ ከፍተኛ የሞት ቅጣት እንደምትፈጽም ገልጸዋል፡፡
እንደ ሂዩማን ራይትስ ዎች ዘገባ ኢራን ባለፈው ወር ብቻ ቢያንስ 87 ሰዎችን በሞት የቀጣች ሲሆን፤ በአንድ ቀን 29 ሰዎችን በሞት ቀጥታ ታውቃለች ተብሏል።
በገነነ ብርሃኑ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ዩትዩብ፦ shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
"ያስመዘገቡትን አዕምሯዊ ንብረት ሥራ ላይ የማያውሉ ሰዎች አሰራሩ ላይ ችግር እየፈጠሩ ነው" የአዕምሯዊ ንብረት ጥበቃ ባለስልጣን
መስከረም 21/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የፈጠራ ሥራቸውን ካስመዘገቡ በኋላ ጥቅም ላይ የማያውሉ እና የአዕምሯዊ ንብረታቸውን የማያስመዘግቡ ሰዎች ለሥራው እንቅፋት እንደሆኑበት የፈጠራ ውጤቶችን የሚመዘግበው እና ዕውቅና የሚሰጠው የአዕምሯዊ ንብረት ጥበቃ ባለስልጣን አስታውቋል።
የፈጠራ ባለሙያዎች “ፓተንት” ወይም የዕውቅና ምዝገባ የወሰዱባቸውን ፈጠራዎች ወደ ሥራ አለመቀየራቸው፤ ተመሳሳይ ጥያቄዎች በተደጋጋሚ እንዲቀርቡ እያደረገ እንደሚገኝ በባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኤልያስ መሀመድ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡ ኃላፊው ተቋማቸው ችግሩን ለመቅረፍ በቴክኖሎጂ የታገዘ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝም ገልጸዋል።
አክለውም በቅርቡ ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር ያካሄደችው የሁትዮሽ ስምምነት የተቋማቱን ትብብር ከፍ ከማድረግ ባለፈ የአዕምሯዊ ንብረት ጥበቃ ስርዓትን ለማሳደግና ለማጠናከር ከፍተኛ ኣስተዋፅኦ እንደሚኖረው ጠቁመዋል።
የአዕምሯዊ ንብረት ጥበቃ ባለስልጣን፤ የአዕምሯዊ ንብረት የፓተንት፣ የመገልገያ ሞዴል፣ ኢንዱስትሪያዊ ንድፍ፣ የንግድ ምልክት እንዲሁም የቅጅና ተዛማጅ መብቶች ጥበቃ ላይ እየሰራ ይገኛል።
በኢትዮጵያ ከ30 ሺሕ በላይ የአዕምሯዊ ንብረት መብቶች ተመዝግበው ጥበቃ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ባለስልጣኑ አስታውቋል።
በፅዮን ይልማ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
የባሮ ወንዝ በመሙላቱ በአምቡላንስ አደጋ ሕይወታቸው ያጡ 7 ሰዎችን አስክሬን የመፈለጉን ሥራ አስቸጋሪ ማድረጉ ተገለጸ
👉እስካሁን የአንድ ሰው አስክሬን ብቻ ነው የተገኘው
መስከረም 21/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በጋምቤላ ክልል በኑዌር ብሔረሰብ ዞን ጂካዎ ወረዳ መስከረም 15/2017 ምሽተ አንድ ሰዓት አካባቢ በደረሰ የመኪና አደጋ የ7 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ይታወሳል፡፡
አደጋው የደረሰው ከጋምቤላ ከተማ ወደ ኑዌር ብሔረሰብ ዞን በመጓዝ ላይ የነበረ አምቡላንስ በጂካዎ ወረዳ የባሮ ወንዝ ጊዜያዊ ድልድይ ጥሶ በወንዝ ውስጥ መሆኑንም አሐዱ መዘገቡ አይዘነጋም፡፡
በክልሉ ኑዌር ዞን የሚገኝው ኒን ያንግ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሠራተኞች የሆኑት 7 ሰዎች በጉዞ ላይ በነበሩበት ሰዓት ሰምጠው ሕይወታቸው ያለፈ ሲሆን፤ ከሟቾቹ ውስጥ እስካሁን የአንድ ሰው አስክሬን ብቻ መገኘቱን የሆስፒታሉ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ኬክ ሪያን ኬር ለአሐዱ ገልጸዋል፡፡
በወንዙ መሙላት አምቡላንስ ውስጥ የነበሩ የሆስፒታሉ ሠራተኞች እስካሁን ከወንዙ ውስጥ ማውጣት አለመቻሉን የገለጹት የህዝብ ግንኙነት ባለሙያው፤ "ሁኔታው የከፋ ነው" ሲሉም ተናግረዋል፡፡
አምቡላንሱ ከጋምቤላ ከተማ መነሻውን ያደረገ ሲሆን፤ ላሬ እና ኑዌርን የሚያገናኘው ድልድይ አቅራቢያ ወንዝ ውስጥ መግባቱን ነው የገለጹት፡፡
በአሁን ሰዓት ምንም ዓይነት ዝናብ የሌለ ቢሆንም ባሮ ወንዝ በመሙላቱ ከፍተኛ ችግር ላይ መውደቃቸውንም የህዝብ ግንኙነት ባለሙያው ጨምረው ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
የክልሉ እንዲሁም ከፌደራል የመጡ አካላት የተለያየ ጥረት ቢያደርጉም፤ አምቡላንሱን ለማውጣት እንዲሁን ሟቾችን ለማግኘት አለመቻላቸውን አስረድተዋል፡፡
በ2016 ዓ.ም በተመሳሳይ የባሮ ወንዝ በመሙላቱ የተነሳ ከ25 ሺህ በላይ ዜጎች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸው አይዘነጋም፡፡
በአቤል ደጀኔ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
የሚኒስትሮች ምክር ቤት የታክስ ፖሊሲዎች እና አስተዳደራዊ ሪፎርምን ጨምሮ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ
መስከረም 21/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 39ኛ መደበኛ ስብሰባ የታክስ ፖሊሲዎች እና አስተዳደራዊ ሪፎርምን ጨምሮ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡
1. በቅድሚያ ምክር ቤቱ የተወያየው ብሔራዊ የመካከለኛ ዘመን 2017-2020 የገቢ ስትራቴጂ ላይ ነው፡፡ ስትራቴጂው የታክስ ሥርዓቱን ለማዘመን እና ለግል ኢንቨስትመንቱ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር የታለመ ሲሆን አጠቃላይ የታክስ ፖሊሲዎችን እና አስተዳደራዊ ሪፎርሞችን እንዲሁም ማሻሻያዎችን ለመተግበር የሚያስችል ነው፡፡ ሰትራቴጂው ከ10 ዓመቱ የልማት ዕቅድ ጋር የተጣጣመ እንዲሆን ተደርጎ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በስትራቴጂው ላይ በዝርዝር ከተወያየበት በኋላ በምክር ቤቱ ውሳኔ ካገኘበት ቀን ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ በሙሉ ድምጽ ወስኗል።
2. በመቀጠል ምክር ቤቱ የተወያየው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት ከማልታ ሪፐብሊክ መንግስት እና ከቻድ ሪፐብሊክ መንግስት ጋር የተፈረማቸውን የአየር አገልግሎት ስምምነቶችን ለማጽደቅ የቀረቡ 2 ረቂቅ አዋጆች ላይ ነው፡፡ ስምምነቶቹ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ማንኛውም የማልታ ከተማ እና ወደ እንጃሜና ከተማ በ3ኛና 4ኛ ትራፊክ መብት የመንገደኛ እና የጭነት የበረራ ምልልስ ለማድረግ፣ ተወካይ አየር መንገዶችን በሽርክና ለማሰራት፣ በ5ኛ ትራፊክ መብት ወደ ተመረጡ መዳረሻዎች በረራ ለማድረግ የሚያስችል እና አገራችን ከሁለቱ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር፣ ለንግድና ኢንቨስትመንት፣ ለወጪ ንግድ፣ ለቱሪዝም፣ ለስራ እድል ፈጠራ እና ለውጭ ምንዛሪ ግኝት ትልቅ አስተዋጽኦ ያላቸው ስምምነቶች ናቸው፡፡ ምክር ቤቱ በረቂቅ አዋጆቹ ላይ ከተወያየ በኋላ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፉ ወስኗል።
3. በመቀጠል ምክር ቤቱ የተወያየው የፓሪስ ኢንዱስትሪያዊ ንብረት ኮንቬንሽን ለማጽደቅ በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ የፓሪስ ኢንዱስትሪያዊ ንብረት ኮንቬንሽን በአባል አገራት መካከል ሕብረት በመፍጠር የኢንዱስትሪ ንብረትን ለመጠበቅ፣ የፈጠራ ባለቤትነት፣ የግልጋሎት ሞዴሎች፣ የኢንዱስትሪ ንድፎች፣ የንግድ ምልክቶች፣ የአገልግሎት ምልክቶች፣ የንግድ ስሞች፣ የምርቶች ምንጭ አመልካች ምልክቶች ለመጠበቅ እንዲሁም ተገቢ ያልሆነ ውድድር ለመከላከል እና ለግብርና እና ሁሉንም የተመረቱ ወይም ተፈጥሯዊ ምርቶች የሚያካትት ነው፡፡ የኮንቬንሽኑ መጽደቅ ሀገራችን ለምታደርገው የአለም ንግድ ድርጅት አባልነት ጥያቄ ድጋፍ የሚሆን ሲሆን ከአባል ሀገራቱ ለሚነሱ የኢንዱስትሪያዊ ንብረት ጥበቃን ለሚመለከቱ ጥያቄዎች አዎንታዊ መልስ ለመስጠት ያስችላል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ ከተወያየ በኋላ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል።
4. ሌላው ምክር ቤቱ የተወያየው የዓለም አቀፍ ምልክቶችን ከሚመለከተው የማድሪድ ስምምነት ጋር የተዛመደውን ፕሮቶኮል ለማጽደቅ በወጣ ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ ፕሮቶኮሉ የንግድ እና የአገልግሎት ምልክቶች በአገር ውስጥ ሕግ ከሚደረግላቸው ጥበቃ አልፈው በዓለም አቀፍ ደረጃ ጥበቃ እንዲኖራቸው ለማድረግ የሚያስችል ከመሆኑም በተጨማሪ ምርቶች እና አገልግሎቶች ያላግባብ ለሌሎች ጥቅም እንዳይውሉ በቂ ጥበቃ የሚደረግበትን ሁኔታ የሚፈጥር፣ ጥራታቸውን የጠበቁ ምርቶችና አገልግሎቶች እንዲኖሩና የሀብት ምንጭ እንዲሆኑ ትልቅ ጠቀሜታ ያለው በመሆኑ ምክር ቤቱ በፕሮቶኮሉ ላይ ከተወያየ በኋላ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ ወስኗል።
5. በመጨረሻም ምክር ቤቱ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ደንብ እና የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ሰራተኞች ደንብ ላይ ነው፡፡ አገልግሎት መስሪያ ቤቱ በአዋጅ የተሰጠውን ተግባር እና ሀላፊነት ለመወጣት፤ የተቀላጠፈ አገልግሎት ለደንበኞች ለመስጠት እንዲሁም ከፓስፖርት የቆይታ ጊዜ ጋር በተያያዘ ያሉ ጥቄዎችን መፍታት እንዲችል የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ረቂቅ ደንቡ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ በተጨማሪም የጀመረውን ሪፎርም ውጤታማ ለማድረግ፣ ሪፎርሙ በተሟላ ሁኔታ እንዲተገበር ለማስቻል የአገልግሎቱን ልዩ ባህሪይ ከግምት ውስጥ ያስገባ ሰራተኞች መተዳደሪያ ደንብ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ ደንቦቹ ላይ በዝርዝር ከተወያየባቸው በኋላ ግብዓቶችን በማከል በነጋሪት ጋዜጣ ታትመው ከወጡበት ቀን ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረጉ በሙሉ ድምጽ መወሰኑ ተገልጿል፡፡
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ንግድ ባንክ የአገልግሎት ክፍያ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ ታሪፍ ተግባራዊ አደረገ
መስከረም 21/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ ታሪፍን ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚያደርግ አስታዉቋል።
መንግሥት በቅርቡ ባወጣው አዲስ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሕግ ቁጥር 1341/2016 መሠረት ባንኮች በሚሰጧቸው አገልግሎቶች ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲጣል መታወጁን የገለጸው ባንኩ፤ ለሚያቀርባቸው ምርት እና አገልግሎቶች ያስከፍል በነበረው የአገልግሎት ክፍያ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲከፈልባቸው መወሰኑን ገልጿል።
በዚህም መሠረት ከዛሬ መስከረም 21 ቀን 2017 ዓ. ም ጀምሮ የባንኩ ምርትና የአገልግሎት ዓይነቶች ላይ በሚከፈል የአገልግሎት ክፍያ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ ታሪፍ የተጨመረባቸው መሆኑን አስታውቋል።
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
የኢትዮ ቴሌኮም የታሪፍ ማሻሻያ ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል
መስከረም 20/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ግዙፉ መንግሥታዊ የቴሌኮም አቅራቢ ድርጅት የሆነዉ ኢትዮ ቴሌኮም፤ ከነገ መስከረም 21 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ በተወሰኑ ምርትና አገልግሎቶቹ ላይ ማሻሻያ የሚያደርግ መሆኑን አስታዉቋል።
ተቋሙ የሚደረገው የዋጋ ማሻሻያ አብዛኛውን የህብረተሰብ ክፍል እንደማይነካ የገለጸ ሲሆን፤ ተመጣጣኝ እና የዲጅታል አካታችነትን መርህ በጠበቀ መልኩ ተግባራዊ ይደረጋል ማለቱን ካፒታል ጋዜጣ ዘግቧል።
ተቋሙ የሚደረገዉ ማሻሻያዉ 22 ፓኬጆችን የማይነካ እንደሆነ ቢገልፅም፤ በምን ያህል ፐርሰንት የሚለዉን እና በየትኞቹ አገልግሎቶቹ ላይ ተግባራዊ እንደሚደረግ አላሳወቀም።
ተግባራዊ ከተደረገ አንድ ወር ያለፈዉ የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያ ተከትሎ፤ ኢትዮ ቴሌኮም በተወሰኑ ምርትና አገልግሎቶቹ ላይ የደበንኞችን የመክፈል አቅም ያገናዘበ የታሪፍ ማሻሻያ ለማድረግ መታሰቡን ተቋሙ ማስታወቁ ይታወሳል።
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ለካንሰር ታካሚዎች ሕክምና የሚውለው የደም አይነት እጥረት ማጋጠሙ ተገልጿል
መስከረም 22/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ ለካንሰር ታካሚዎች አገልግሎት የሚውለው (ፕሌትሌት) የደም አይነት እጥረት ማጋጠሙን የኢትዮጵያ ደም እና ህብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት አስታውቋል።
የካንሰር ታካሚዎች በቀን 120 የፕሌትሌት የደም አይነትን ይፈልጋሉ እንደሚፈልጉ አገልግሎቱ ለአሐዱ ገልጿል።
በዚህመ ሦስት አይነት የደም ተዋዕጾ መኖራቸውን እና የመጠቀሚያ ጊዜያቸው የሚለያይ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ ቀይ የደም ሴል ለ42 ቀናት፣ ፕላዝማ የደም አይነት ለአንድ ዓመት እንደሚቆይ እና በከፍተኛ ሁኔታ እጥረት ያጋጠው የፕሌትሌት የደም አይነት ግን ለአምስት ቀናት ብቻ የሚቆይ መሆኑ ተነግሯል።
7 መቶ 41 ለሚሆኑ የህክምና ተቋማት የደም አቅርቦት እንደሚሰጥ የገለጹት የደም እና ህብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ታዩ፤ በአሁኑ ወቅት የደም ለጋሾች ቁጥር መቀነሱን ለአሐዱ ገልጸዋል።
የህፃናት እና የአዋቂዎች የካንሰር ህክምና ማዕከላት ላይ የፕሌትሌት የደም አይነት እጥረት በከፍተኛ ሁኔታ እየታየ ይገኛልም ብለዋል፡፡
በአዲስ አበባ ለካንሰር ታካሚዎች ህክምና በሚሰጡት በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እና በጳውሎስ አጠቃላይ ሆስፒታል የፕሌትሌት የደም አይነት እጥረት ማጋጠሙም ተነግሯል።
በእሌኒ ግዛቸው
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ከአዲስ አበባ ደራ የሚወስደው መንገድ መፍትሔ ባለማግኘቱ ችግር ላይ መውደቃቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ
መስከረም 22/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ከተቋረጠ 2 ዓመታት ያለፈው ከአዲስ አበባ ደራ የሚወስደው መንገድ መፍትሔ አለማግኘቱ ችግር ላይ እንደጣላቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ለአሐዱ ተናግረዋል።
ነዋሪዎቹ ለአሐዱ ባስገቡት ቅሬታ እንዳሳወቁት፤ በተለይ አፋጣኝ የህክምና አገልግሎት የሚያስፈልጋቸው ጽኑ ታካሚዎች፣ ነፍሰጡር ሴቶች እና ጨቅላ ሕጻናት ተገቢውን ሕክምና በፍጥነት ባለማግኘታቸው ለከፋ ሕመም እና ለሞት እየተዳረጉ እንደሆነ አስረድተዋል።
ቅሬታ አቅራቢዎቹ በተጨማሪም ታማሚዎችን በቃሬዛ በመሸከም በእንስሳት እና በእግር ለመጓዝ የሚያደርጉት ጥረት ለዕገታ እና ለዘረፋ ወንጀል እየተዳረጉ እንደሆነ ነግረውናል።
ከፍቼ ወደ ደራ የትራንስፖርት አገልግሎት አለመኖሩን አንስተው፤ አልፎ አልፎ የሚመጡ ተሸከርካሪዎችም የሚጠይቁትን ክፍያ ከአቅማችን በላይ ነው ብለዋል።
ከ2 ዓመት በላይ አገልግሎት ያቋረጠው የከተማዋ መግቢያ እና መውጫ ዋና መንገድ ወደ አግልገሎት እንዲመለስ ለወረዳ እና ለዞን መስተዳድሮች ያቀረቡት ተደጋጋሚ ጥያቄ ፍሬ ያለው ምላሽ እንዳላገኙም ጨምረው ነግረውናል።
የነዋሪዎቹን ቅሬታ ያደመጠው አሐዱ የደራ ወረዳ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮን ምላሽ በዚህ ዘገባ ላይ ለማካተት ያደረገው ሙከራ አልተሳካም።
በአለምነው ሹሙ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ኢሬቻን በተመለከተ በውጭ አካላት ሲደረግ የነበረው ጥናት ታሪኩን አዛብቷል ተባለ
መስከረም 22/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የሰላምና የአንድነት በዓል የሆነውን ኢሬቻ ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ እንዲከበር በብዙ መልኩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸውን የኦሮሚያ ክልል አስታውቋል፡፡
መስከረም 25 እና 26 የሚከበረው ኢሬቻ አለም ዓቀፍ በዓል እንዲሆን እና በዩኔስኮ እንዲመዘገብ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ መሆኑም ተገልጿል፡፡
አሐዱም የኢሬቻ በዓል ካለው ባህላዊ እና ሀገራዊ ፋይዳ አንጻር በአከባበሩ ላይ ለምን የሚፈለገውን ያህል ለውጥ ማምጣት አልተቻለም? ሲል የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ደራራ ከተማን ጠይቋል፡፡
በምላሻቸውም "የሚፈለገውን ያህል ትኩረት ባለመሰጠቱ እና በውጭ አካላት ሲደረግ የነበረው ጥናትም የባህሉ ታሪክ እንዲዛባ በማድረጉ ነው" ብለዋል፡፡
አሁን ላይ የምስጋና ባህል የሆነው ኢሬቻ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲሸጋር ለማድረግ ሲደረግ የነበረው ጥናትም መጠናቀቁን የተናገሩት ምክትል የቢሮ ኃላፊው፤ "ያለ ሀይማኖት እና የፖለቲካ ልዩነት የሚከበር በዓል ነው" ሲሉም ገልጸዋል፡፡
ኢሬቻ በሌሎች ቦታዎች እንደሚከበሩ በዓላት የሚፈለገዉን ያህል ትኩረት ሊሰጠዉ እንደሚገባ የተገለጹ ሲሆን፤ ጎረቤት ሀገራትን ጨምሮ "የምስጋና ቀን" በሚል እንደሚከበር ገልጸዋል።
ኢሬቻ የምስጋናና የኦሮሞ ሕዝብ አንድነት መገለጫ ከመሆኑም ባለፈ ለፈጣሪ ምስጋና የሚያቀርብበት ነው። በበዓሉ ላይ የዉጭ እና የሀገር ዉስጥ ጎብኚዎች ስለሚገኙበት የቱሪዝም ዘርፉን ከመደገፍ ባለፈ ለበርካቶች የሥራ እድል እንደሚፈጥርም የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ኮምዩንኬሽን አስታዉቋል።
በዓሉ ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ በሰላም እንዲከበር መገናኛ ብዙሀንን ጨንሮ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ለማድረግ የቅድመ ዝግጅት ሥራ መጠናቀቁን የክልሉ መንግሥት መግለጹ ይታወሳል፡፡
በፍቅርተ ቢተው
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ኢትዮጵያ የሥራ ቦታ ጥቃትና ትንኮሳን ለመከላከል የወጣውን ዓለም አቀፍ ስምምነት እንድታጸድቅ ተጠየቀ
መስከረም 22/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ኢትዮጵያ የዓለም የሥራ ድርጅት (I.O.L) ስምምነት ቁጥር 190 ማጽደቅ እንደሚገባት የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌደሬሽን አሳስቧል።
የስምምነቱ ዓላማ የስራ ቦታ ጥቃትን ማስቀረት፣ ግለሰቦች ከማንኛውም ጥቃት ነጻ በመሆን ሥራቸው ላይ የሚያተኩሩበትን የሥራ አካባቢ መፍጠር እንደሆነ የኮንፌደሬሽኑ ፕሬዝዳንት ካሳሁን ፎሎ ተናግረዋል።
የሥራ ቦታ ደህንነትን በተመለከተ የአሠሪና ሰራተኛ አዋጁ መመሪያ እንዳስቀመጠ ያስታወሱት ፕሬዝዳንቱ፤ አዲሱ የዓለም የሥራ ድርጅት (I.O.L) ስምምነት መደበኛ ያልሆነ የሥራ ቦታንም እንደሚያካትት አንስተዋል።
ፕሬዝዳንቱ አክለውም፤ ‹‹ስምምነቱን አለማጽደቅ የሰዎች መብት አይከበር እንደማለት ነው›› ብለዋል።
በ2017 ዓ.ም. ከተያዙ የሦስትዮሽ እቅዶች መካከል አንዱ ይኼንን ስምምነት የተመለከተ እንደሆነና ከውይይትና ጥናት በኋላ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት እንደሚላክ አንስተውም፤ ሕጉ እዲጸድቅ በተቻለውን ሁሉ ግፊት እንደሚያደርጉ አሳውቀዋል።
ስምምነቱ እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ2019 ከጸደቀ በኋላ ሁለት የአረብ ሀገራትን ጨምሮ 36 ሀገራት ከ2021 ጀምሮ ተግባራዊ አድርገውታል። ስምምነቱን ካጸደቁት የአፍሪካ ሐገራት መካከል ሶማሊያ አንዷ ናት።
ኢትዮጵያ የዓለም ሥራ ድርጅት አባል ከሆነች መቶ ዓመታትን ማስቆጠሯ ይታወቃል፡፡
በፍርቱና ወልደአብ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
በራያ አላማጣ ሕዝብ በተሰበሰበበት ቦታ ላይ በተከፈተ ተኩስ 2 ሰዎች ሲገደሉ ሌሎች 11 ሰዎች መቁሰላቸው ተገለጸ
መስከረም 21/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የትግራይ ታጣቂዎች ዛሬ ራያ አላማጣ ከተማ ውስጥ ሕዝብ በተሰበሰበበት ቦታ ላይ በከፈቱት የእሩምታ ተኩስ ኹለት ወጣቶችን ሲገደሉ ሌሎች 11 ሰላማዊ ሰዎችን ማቁሰላቸው ተሰምቷል።
ታጣቂዎቹ እሩምታ ተኩስ የከፈቱት፣ በከተማዋ ቀበሌ 03 ምድረ ገነት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ ሆነው ውጭ በተሰበሰቡ ሰዎች ላይ መሆኑን የዐይን እማኞች ለዋዜማ ተናግረዋል፡፡
በጥቃቱ ከቆሰሉት 11 ሰዎች መካከል ሰባቱ ሰዎች ከባድ የመቁሰል ጉዳት እንደደረሰባቸው ተነግሯል።
ታጣቂዎቹ ተኩስ የከፈቱት፣ በከተማዋ "ትምህርት እናስጀምራለን" በማለት ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት እንዲልኩ ማስገደዳቸውንና ነዋሪዎችም ከእናንተ ትዕዛዝ አንቀበልም በማለት መቃወማቸውን ተከትሎ እንደሆነም የዋዜማ ዘገባ አመላክቷል፡፡
የፌደራል ጸጥታ ኃይሎች "ትዕዛዝ አልተሰጠንም" በማለት፤ የታጣቂዎቹን ርምጃ አላስቆሙም ተብሏል፡፡
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ይደረጋል የተባለው የደሞዝ ጭማሪ የውሃ ሽታ ሆኗል ሲሉ የመንግሥት ሠራተኞች ቅሬታቸውን አሰሙ
መስከረም 21/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ለመንግሥት ሠራተኞች 300 ፐርሰንት የደሞዝ ጭማሪ ይደረጋል ከተባለ ወዲህ፤ ከማህበራዊ ሚዲያ በዘለለ መረጃ ማግኘት አለመቻላቸውን ሠራተኞች ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
ቅሬታቸውን ለአሐዱ የገለጹት የመንግሥት ሠራተኞቹ፤ "ከመስከረም 1 ጀምሮ የደሞዝ ጭማሪው ተግባራዊ መሆን እንደሚጀምር ተሰፋ አድረገን የነበረ ቢሆንም የውሃ ሽታ ሆኖብናል" ብለዋል፡፡
ሠራተኞቹ ደሞዝ ሳይሻሻል ኑሮ መጨመሩ እንዳሳሰባቸው የገለጹ ሲሆን፤ "የኑሮው ውድነቱ በከፍተኛ ሁኔታ ተባብሶ በመቀጠሉ የተነሳ ለከፍተኛ ችግር በመጋለጣችን መንግሥት በአስቸኳይ መፍትሄ ይስጠን" ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
መንግሥት ለደሞዝ ጭማሪ ከ90 ቢሊዮን በላይ ብር እንደመደበ ያስታወቀ ቢሆንም ጭማሪው ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ እንዲጸድቅ አልተደረገም፡፡
በተጨማሪ በጀቱ ለዝቅተኛ ደሞዝ ተከፋይ ለሆኑ የመንግሥት ሠራተኞች እንዲሁም ለነዳጅ፣ ለዘይትና ለማዳበሪያ እና መድሃኒት ድጎማ የሚውል መሆኑ መገለጹ ይታወሳል፡፡
አሐዱም የመንግሥት ሠራተኞች ቅሬታን በመያዝ የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽንን የጠየቀ ሲሆን፤ ባገኘው ምላሽ "በተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ ባለጸደቀ ጉዳይ ላይ ዘገየ ማለት አይቻልም" ሲል አስታውቋል፡፡
በዚህ ረገድ መግለጫ እና መረጃ እስከሚሰጥ መታገስ ያስፈልጋልም ሲል ኮምሽኑ ገልጻል፡፡
በአቤል ደጀኔ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ:www.facebook.com/ahaduradio
ዩትዩብ፦http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ፡ www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
በደቡብ አፍሪካ ሦስት ሕጻናት ከሱፐርማርኬት የተገዛ ገንፎ በልተው ለሞት በመዳረጋቸው የገንፎ ምርቱ ከሁሉም መደብሮች እንዲወጣ ተደረገ
መስከረም 21/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በደቡብ አፍሪካ ከአንድ ሱፐርማርኬት የተገዛ ገንፎ በልተው ሦስት ሕጻናት ለሞት በመዳረጋቸው ተከትሎ፤ የገንፎ ምርቱ ከሁሉም መደብሮች እንዲወጣ መደረጉ ተገልጿል፡፡
የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ እድሜያቸው ከ18 ወራት እስከ 4 ዓመት የሚሆናቸው ሕጻናቱ ገንፎውን ከበሉ በኋላ በተከሰተባቸው ከባድ የሆድ ህመም ቤተሰቦቻቸው ለፖሊስ እንዳመለከቱ ገልጿል፡፡
በኋላም ሦስቱ ሕጻናት ሕወታቸው ማለፉ የተገለጸ ሲሆን፤ ገንፎው የተገዛበት ሱፐርማርኬትን ጨምሮ በሁሉም መደብሮች የገንፎው ምርት ከመደርደሪያ እንዲወርድ ተደርጓል ተብሏል፡፡
ገንፎውን ያመረተው የናሚቢያ ኩባንያ ከዚህ አሳዛኝ ክስተት ጋር የሚያገናኘው ምንም አይነት መረጃ ባይኖርም ጉዳዩን እናጣራለን ማለቱን ዘ ሳውዝ አፍሪካን ዘግቧል፡፡
ለሞቱት ሕጻናት እና ሃዘን ለደረሰባቸው ቤተሰቦች ኩባንያው መፅናናትን የተመኘ ሲሆን፤ ምርመራው ሲቀጥል ውጤቱን ተከትሎ ቀጣይ ሊደረጉ የሚገባቸው እርምጃዎች እንደሚደርግም ገልጿል፡፡
በገነነ ብርሃኑ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ዩትዩብ፦ shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ከፍቺ በኋላ ለሕጻናት የሚቆረጥ ቀለብን በተመለከተ ከ7 ሺሕ በላይ ጥያቄዎች መቅረባቸው ተገለጸ
መስከረም 21/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በ2016 ዓ.ም ከፍቺ በኋላ ለሕጻናት ልጆች የሚቆረጥ ቀለብን በተመለከተ ከ7 ሺሕ በላይ ጥያቄዎች ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህጻነት ፍትህ ፕሮጀክት መቅረባቸው ተነግሯል፡፡
ከትዳር ፍቺ በኋላ ለልጅ ከሚቆረጥ ቀለብ ጋር በተያያዘ የሚነሱ ቅሬታዎች በፍርድ ቤት የሚመለሱ ቢሆንም፤ የጠቅላይ ፍርድ ቤት የሕጻናት ፕሮጀክት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ጠበቃ የመመደብ እና የሕግ ማማከር አገልግቶችን ለቅሬታ አቅራቢዎች እንደሚሰጥ ተገልጿል፡፡
በፕሮጀክቱ የሚነሱ ጥያቄዎች በስምምነት እንዲፈቱ የማድረግ ሥራ የሚከናወን ሲሆን፤ ይህ የማይሆንበት ሁኔታ ሲፈጠር ግን አቤቱታ የማጻፍ እና ጠበቃን የመመደብ ሥራ ያለምንም ክፍያ እንደሚከናወን የፕሮጀክቱ ዳይሬክተር ዳኛ ተክለሀይማኖት ዳኜ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
በዚህም መሰረት በ2016 7 ሺሕ ለሚሆኑ ሕጻናት ከፍቺና ቀለብ ጋር በተያያዘ አገልግሎት እንዲያገኙ መደረጉን የገለጹት ዳይሬክተሩ፤ በተጨማሪም 100 ለሚሆኑ ሕጻናት ጠበቃ በመመደብ ያለምንም ክፍያ ሙሉ ክርክር መደረጉን ተናግረዋል፡፡
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሕጻናት ፕሮጀክት አገልግሎት መስጠት ከጀመረ 25 ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን፤ ሕገ መንግሥቱን መሰረት በማድረግ የሕጻናትን መብት በማስጠበቅ ላይ የተለያዩ ሥራዎች እያከናወነ እንደሚገኝ ተነግሯል፡፡
በእሌኒ ግዛቸው
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ:www.facebook.com/ahaduradio
ዩትዩብ፦ shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
አገር በቀል ኩባንያዎች የውጭ ገበያ በማፈላለጉ በኩል ድክመት እየተሰተዋለባቸው ነው ተባለ
መስከረም 21/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) መሠረታቸውን አገር ውስጥ ያደረጉ ኩባንያዎች ከሌሎች አገራት ድርጅቶች ጋር በጥምረት እንዲሰሩ ከመንግሥት የቀረበላቸውን ጥሪ እየተገበሩት አለመሆኑ ተገልጿል።
የውጭ ኩባንያዎች በአገር ዉስጥ ገብተው እንዲሰሩ በቀረበላቸው ጥሪ መሰረት ኢትዮጵያዉን ኩባንያዎች በውጭ አገራት ገበያ እንዲያፈላልጉ የሚጠበቅባቸው መሆኑን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታው አቶ እንዳለው መኮንን ገልጸዋል።
በቅርቡም በጅምላና ችርቻሮ ዘርፍ የውጭ አገራት ነጋዴዎች ጥሪ የተደረገበት ምክንያትም ይህንኑ ለማበራታትና የንግዱ ዘርፍ ለማነቃቃት እንደሆነ ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል።
ነገር ግን አሁን ላይ የአገር ውስጥ ኩባንያዎች በውጭ አገራት ገበያ በማፈላልግ ላይ ያላቸው ሚና ዝቅተኛ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡
የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዉን ተከትሎ በወጭ ንግድ ዘርፍ በርካታ ተግዳሮቶች እየገጠሙት እንደሚገኙም ሚኒስትር ዲኤታው ለአሐዱ ተናግረዋል።
ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ የውጭ ኢንቨስተሮችን በተወሰኑ የሥራ ዘርፎች ብቻ እንዲሰሩ ፍቃድ ትሰጥ የነበረ ሲሆን፤ አሁን ግን ባለሀብቶቹ ከማዳበሪያ እና ነዳጅ በስተቀር በሁሉም የገቢና ወጪ ንግድ ላይ በጅምላ እና በችርቻሮ እንዲሳተፉ መፈቀዱ ይታወቃል፡፡
በተፈቀዱት ዘርፎች ላይ የውጪ ባለሀብቶችን በማሳተፍ እና ገበያውን ክፍት በማድረግ የሀገሪቱ የግብይት ሥርዓትን በማስተካከል በወጪ ንግድ ዘርፍ ያላትን ተወዳዳሪነት እንደሚጨምር ታምኖበታል፡፡
በአማኑኤል ክንደያ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
በኢትዮጵያ ከ4 ሚልየን በላይ ህፃናት ከትምህርት ገበታቸዉ ተሰናክለዋል" በኢትዮጵያ የአሜሪካው አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ
መስከረም 21/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በተፈጠረ ግጭት ምክንያት፤ ከ 4 ሚልየን በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸዉ መሰናከላቸዉንና 4 ሺሕ 178 የሚሆኑ ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸዉን ገለጹ፡፡
አምባሳደሩ ይህን ያሉት ትናንት ሰኞ መስከረም 20 ቀን 2017 ዓ.ም አመሻሹን በሸራተን አዲስ ሆቴል በተዘጋጀው የዩኤስ ኤድ መዝጊያ ፕሮግራም ላይ ሲሆን፤ በሥነ-ስርዓቱ ላይ በኢትዮጵያ ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች የወንጀል ድርጊቶች እየጨመሩ መምጣታቸውን ተገልጿል፡፡
የመርሃ ግብሩ ቁልፍ ተናጋሪ የነበሩት አምባሳደር ማሲንጋ፤ በትግራይ ክልል በጦርነቱ ለችግር የተጋለጡ ሰዎች የድህረ ጦርነት የዓዕምሮ ማገገም እንዲያገኙ ጥረት መደረጉን ገልጸው፤ ግጭቱ በሕፃናት ሕይወት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማስከተሉን ተናግረዋል፡፡
አክለውም፤ በቅርቡ በአማራ ክልል የደረሰውን የከፋ ሁኔታ እና በክልሉ 4 ሺሕ 178 ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸው ሪፖርት መደረጉን ያነሱ ሲሆን፤ ሰላም ሕፃናትን ወደ ትምህርት ቤት እና ወደ ጤናቸው እንደሚመለሱ ቁልፍ ጉዳይ ስለመሆኑ አፅንዖት ሰጥተዋል።
በኢትዮጵያ ከአስር ዓመት በፊት ለተከታታይ ዓመታት ይመዘገብ የነበረው የኢኮኖሚ እድገት በባለፈው የፈረንጆቹ 2023 ዓመት መቀነሱን አስረድተዋል። ለዚህ የኢኮኖሚ መቀዛቀዝ በሀገሪቱ ያለው ግጭት “ዋነኛ ሚና” መጫወቱንም አስገንዝበዋል።
አምባሳደር ማሲንጋ በንግግራቸው የሰላም እና የውይይትን አስፈላጊነትን በተደጋጋሚ አንስተዋል። ግጭቶችን ለማስቆም፣ የጋራ መግባባት እና መፍትሔን ለማበጀት “ብቸኛው መንገድ” ውይይት ማድረግ መሆኑንም አበክረው ገልጸዋል።
አምባሳደሩ ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር ላይ ባደረጉት የፖሊሲ ንግግር፤ ተመሳሳይ ሀሳብ አንጸባርቀው እንደነበር ይታወሳል። አምባሳደሩ በወቅቱ በኢትዮጵያ ያሉ ሁሉም የታጠቁ ኃይሎች “ጊዜያዊ ሀገር አቀፍ የተኩስ ማቆም” እንዲያደርጉ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል።
በዚህ የዩኤስ ኤድ የመዝጊያ ፕሮግራም ላይ በኢትዮጵያ የአሜሪካን አምባሳደርን ጨምሮ የዩስ ኤድ በኢትዮጵያ ሰራተኞች፣ የመንግሥት ባለስልጣናት፣ የ"ምን ሆኛለሁ" መፅሐፍ ደራሲ እና የስነ ልቦና አማካሪ ትዕግስት ዋልተንጉስ እንዲሁም ሌሎች የስነልቦና አማካሪዎች ተሳትፈዋል። የሥነ ልቦና አማካሪዎቹም ከግጭት ጋር ተያይዞ ስለሚፈጠሩ የሥነ-ልቦና እክሎች የፓናል ዉይይት አድርገዋል።
በዳግም ተገኝ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
"በትግራይ ክልል የነዋሪነት መታወቂያ ምዝገባ እና የማረጋገጫ ሂደት መስከረም 26 ይካሄዳል" የትግራይ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ
መስከረም 21/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደሩ በሚቆጣጠራቸው አካባቢዎች ላይ የመታወቂያ ካርዶችን ለመስጠት እንዲቻል፤ የምዝገባ እና የማጣራት ሂደት በተመሳሳይ ጊዜ መስከረም 26 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚካሄድ የትግራይ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ አስታወቀ።
ቢሮው የመታወቂያ ካርዶች ስርጭትን በመደበኛነት ለማስጀመር እንቅስቃሴ መጀመሩን የገለጸ ሲሆን፤ በዚሁ መሰረት ራሱን የቻለ እቅድ በማዘጋጀት እስከ ክልል ጣቢያዎች ድረስ ገለጻዎችን መስጠቱን ገልጿል።
በመሆኑም "የሚመለከታቸው ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ለዚህ ዓላማ የተዘጋጀውን ቅጽ በመሙላትና ለሚመለከተው የልማት ቡድን አመራር በማቅረብ መታወቂያ የማግኘት መብታቸውን ሊጠቀሙበት ይገባል።" ብሏል፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ የሚመለከታቸው አካላት የነዋሪነት መረጃዎችን የማረጋገጥ እና የማጣራት ሥራ ላይ ተገቢውን ትኩረት እንዲሰጡ የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ አሳስቧል።
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ኮርፖሬሽኑ የጋራ መኖሪያ ቤት ባለቤቶች እስከ ጥቅምት 30/2017 ድረስ ወደ ቤታቸው የማይገቡ ከሆነ ውላቸው እንደሚቋረጥ ገለጸ
መስከረም 21/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በተለያዩ ጊዜያት በዕጣ እና በጨረታ ተላልፈው ነዋሪ ያልገባባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ላይ እስከ ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም ድረስ የቤት ባለቤቶቹ የማይገቡበት ከሆነ፤ ውሉ ተቋርጦ ቤታቸው በዕጣ ወይ በሽያጭ ለሌላ ነዋሪ እንደሚተላለፍ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን አስታወቀ።
ኮርፖሬሽኑ በተለያዩ ጊዜያት ገንብቶ በዕጣ እና በጨረታ ያስተላለፋቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ላይ እስከ አሁን ነዋሪ ባለመግባቱ ምክንያት፤ በመኖሪያ ቤቶቹ ውስጥ የተለያዩ ሕገ ወጥ ተግባራት እየተፈጸሙ እንደሚገኝ ገልጿል።
በመሆኑም ነዋሪ ያልገባባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ላይ እስከ ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም ድረስ ባለቤቶቹ እንዲገቡ ኮርፖሬሽኑ ጥብቅ ማሳሰቢያ አስተላልፏል።
የቤት ባለቤቶቹ በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ወደ ቤቶቹ የማይገቡ ከሆነ፤ የሽያጭ ውላቸው ተቋርጦ በዕጣ እና በሽያጭ ለሌላ ነዋሪ የሚተላለፉ መሆኑንም ኮርፖሬሽኑ ገልጿል።
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሚና ውስን በመሆኑ በትግራይ ክልል የፖለቲከኞች ውዝግብ ላይ የመፍትሄ አካል መሆን አለመቻላቸው ተገለጸ
መስከረም 20/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በትግራይ ክልል እየተካረረ የመጣው የክልሉ ፖለቲከኞች ጉዳይን በተመለከተ የሲቪል ማህበረስብ ድርጅቶች ሚና ውስን በመሆኑ የመፍትሄ አካል መሆን እንዳልቻሉ የኢሮብ ኣኒና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት አስታዉቋል፡፡
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሚናቸው ማህበረሰብን ማንቃትና ማስተማር ቢሆንም፤ በተለያዩ ጊዜያት ጥሪዎች በማድረግ ላይ እንደሚገኙ ለአሐዱ የገለጹት የድርጅቱ የቦርድ አባል የሆኑት አቶ ተስፋዬ አውኣላ ናቸው፡፡
አቶ ተስፋዬ አክለውም፤ እነዚህ ድርጅቶች የዜጎች መፈናቀል፣ የኢኮኖሚ እንዲሁም የድንበር ጉዳዮች ቅድሚያ እንዲሰጣቸው የማስገንዘብ ሥራዎችን እንደሚሰሩ አንሰተዋል፡፡
"የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች መሪዎች ሕዝብን እንዲሰሙ የማስገንዘብ ሥራዎችን በስፋት ስለሚሰሩ ከዚህ ያለፈ ነገር መስራት አልተቻለም" ሲሉም ገልጸዋል፡፡
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በትግራይ ክልል ያለውን ሁኔታ በተመለከተ ጎራ ለይቶ ዉሳኔ ሰጭ መሆን ባይችልም፤ በተወሰነ ደረጃ የእርቅ ጉዳዮች ተጀምረው እንደነበር አንስተዋል፡፡
እየተደረገ ያለው ጥረት የሕዝቡን መከራ የሚቀንስበት፣ የሕዝቡን ፍላጎት መሠረት ያደረገና ቅድሚያ መሰጠት ያለበት ጉዳይ ቅድሚያ እንዲሰጠው የማድረግ ጥረቶች አሁንም እየተደረጉ መሆኑን አቶ ተስፈዬ ገልጸዋል፡፡
"የጊዜያዊ አስተዳዳሩ ሰልጣኑን በአግባቡ እንዲወጣ የማድረግ እና የፓርቲውም ጉዳይ ወደ ሕዝቡ እንዳይወርድ የማድረግ ሥራዎች እየተሰራባቸው ይገኛል" ሲሉም ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
የሲቪል ማህበሰርብ ድርጅቶች በመንግሥት ላይ የሚደረገውን ጫና አጠናክረው እንዲቀጥሉ የማድረግ ሥራዎች እየተሰሩ ስለመሆኑም ጨምረው ገልጸዋል።
በአቤል ደጀኔ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
የትግራይ መምህራን ማህበር የ17 ወራት ደመወዝ ለመምህራን እንዲከፈል ጠየቀ
መስከረም 20/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የትግራይ መምህራን ማህበር ለ17 ወራት የተቋረጠው የመምህራን የደመወዝ ክፍያን ጨምሮ ሌሎች የተለያዩ ጥያቄዎችን አቅርቧል።
ማህበሩ በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ፤ በምዕራብ ትግራይ ዞን ከኢሮብ፣ ጉሎ መኸዳ፣ ዛላንበሳ፣ እገላ እና ታሕታይ ኣድያቦ ወረዳዎች የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቤታቸው አልተመለሱም ያለ ሲሆን፤ ወደ ደቡብ ጸለምት የተመለሱት ዜጎችም ተረጋግተው መኖር አለመጀመራቸውን እና በከፍተኛ ችግር ውስጥ መሆናቸውን ገልጿል።
ማኅበሩ የፈረሱ ትምህርት ቤቶች ሳይጠገኑና መሰረተ ልማቶች ሳይገነቡ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት እንደማይመለሱ በመግለጽ፤ በአዲሱ የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማሩ ሂደት ስኬታማ እንዲሆን የትግራይ ትምህርት ቢሮም ሆነ ሌሎች ባለድርሻ አካላት እነዚህን አበይት ችግሮች እንዲፈቱ ጥሪውን አስተላልፏል።
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ