አባትነትን የሚገልጽ የዘረመል ምርመራ ይደረግልኝ ጥያቄዎች እየጨመሩ መሆኑ ተገለጸ
መስከረም 24/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ አባትነትን የሚገልጽ የዘረመል ምርመራ እንዲረግላቸው የሚፈልጉ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሕጻናት ፍትህ ፕሮጀክት አስታውቋል።
በ2016 ዓ.ም. 95 የሚሆኑ የአባትነት የሚገልጽ የዘረመል ምርመራ (DNN) ጥያቄዎች እንደቀረቡላቸው እና ምላሽ መስጠታቸውን፤ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሕጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክተር ዳኛ ተክለሃይማኖት ዳኜ ተናግረዋል።
ምርመራ በፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ በኩል መከናወኑን የገለጹት ዳይሬክተሩ፤ ከቀረቡት 95 የአባትነት የሚገልጹ ጥያቄዎች ውስጥ 61 ለሚሆኑት ምርመራ መከናወኑን ለአሐዱ ገልጸዋል።
ይህም ካለፉት ዓመታት የዘረመል ምርመራ ጥያቄዎች ጋር ሲስተያይ፤ ቁጥሩ እየጨመረ መሆኑን እንደሚያሳይ ተናግረዋል።
ከዚህ ቀደም በውጪ አገራት ይከናወን የነበረው የዘረመል ምርመራ ከቅርብ ዓመታት በፊት በአገር ውስጥ መከናወን መጀመሩ የሚታወቅ ሲሆን፤ ምርመራው በግል 35 ሺሕ ብር በላይ በመንግሥት ደግሞ 13 ሺሕ ብር እንደሚፈጅ ተነግሯል።
በዚህም መሠረት ከ95 የአባትነት ምርመራ መካከል 52 የሚሆኑ ጥያቀቴዎች አባትነታቸው የተረጋገጠ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ 9 ጥያቄዎች በምርመራ ላይ እንደሚገኙ እና 6 የሚሆኑት በዘረመል ምርመራ ላይ አባት አለመሆናቸው ተረጋግጧል ተብሏል።
በዘረመል (DNA) ምርመራ በዋናነት፤ ከወንጀል ስፍራ የተገኙ ማስረጃዎችን ከተጠርጣሪዎች ጋር በማገናኘት ምንጫቸውን ለመለየት፣ የስጋ ዝምድናን ለመለየት እንዲሁም ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎችን ወይም የሰው አካላትን ማንነት ለመለየት ሥራ እንደሚሰራበት ይታወቃል።
በእሌኒ ግዛቸው
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
እስራኤል በደቡባዊ ቤሩት ከባድ ፍንዳታ ያስከተሉ 11 ተከታታይ ጥቃቶችን ሰነዘረች
መስከረም 24/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) እስራዔል ትናንት ለሊቱን በደቡባዊ ቤይሩት በሚገኘው የሂዝቦላህ ቡድን ጠንካራ ይዞታ ላይ፤ ከባድ ፍንዳታ ያስከተሉ 11 ተከታታይ ጥቃቶችን አድርጋለች።
በዚህም የአየር ጥቃት የእስራኤል ሃይሎች የሂዝቦላህ የሚዲያ ግንኙነት ጽህፈት ቤት በሚገኝበት ህንፃ ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን ኤፍፒ ዘግቧል።
ከጥቃቶቹ አንደኛው ከቤሩት ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አጠገብ መፈጸሙ የተገለጸ ሲሆን፤ አየር ማረፊያው በዋና ከተማው የሂዝቦላ ጠንካራ ምሽግ ከሆነው ዳሂህ ጋር ይዋሰናል ተብሏል፡፡
እስካሁን የትናንቱ ጥቃት ኢላማ በውል ባይገለጽም፤ የሊባኖስ ሚዲያዎች ግን የሐሰን ነስረላህ ተተኪ ይሆናሉ ተብሎ የሚጠበቁትን የሐሺም ሰይፉዲ መሸሸጊያ ምሽግ ለመምታት የተሰነዘረ ነው ሲሉ ዘግቧል፡፡ ሐሺም ሰይፉዲን በዚህ ጥቃት ስለመገደላቸው ከሁለቱም ባላንጣ አገራት እስካሁን የተባለ ነገር የለም።
የሊባኖስ የህዝብ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በበኩሉ ባወጣው መግለጫ፤ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 37 ሰዎች በምድር እና በአየር ጥቃት ሲገደሉ ሌሎች 151 ሰዎች መቁሰላቸውን አስታውቋል።
የእስራኤል ጦር በሂዝቦላህ ላይ ወረራውን በቀጠለበት ወቅት፤ ከድንበር አካባቢ በቅርብ ርቀት የሚገኙ 20 ከተሞች ነዋሪዎች መንደሮቹን ለቀው በአስቸኳይ እንዲወጡ ትዕዛዝ ተላልፏል፡፡
በሌላ በኩል የእስራኤል ሠራዊት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ሌተናንት ኮሎኔል ሄርዚ ሃሌቪ፤ ወታደሮቹ በሊባኖስ ቤይሩት እና ቤቃ ሸለቆ ላይ የቦምብ ድብደባ እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል፡፡
በእዮብ ውብነህ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
የመንግሥት ሰራተኞች የደመወዝ ጭማሪ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ጸደቀ
👉የጭማሪው ዝርዝር በቅርቡ በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በኩል ይፋ ይደረጋል ተብሏል
መስከረም 24/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ከመስከረም ወር ጀምሮ ታሳቢ የሚደረግ የመንግሥት ሰራተኞች የደመወዝ ጭማሪ በሚኒስትሮች ምክር ቤት መጽደቁን፤ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ አስታውቀዋል።
ጭማሪው ዝቅተኛ ደመወዝ ተከፋይ የሆኑ የመንግሥት ሰራተኞችን የሚመለከት ሲሆን፤ ከመስከረም ወር ጀምሮ ታሳቢ እንዲደረግ ማክሰኞ መስከረም 21 ቀን 2017 በተካሄደው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ መጽደቁን ተናግረዋል።
የገንዘብ ሚኒስትሩ ከፋና ጋር በነበራቸው ቆይታ "የተወሰነ የደመወዝ ጭማሪ ለኑሮ ድጎማ ጭምር እንዲሆን ታሳቢ ተደርጎ በካቢኔ ጸድቋል። ከመስከረም ወር ጀምሮ ታሳቢ ይደረጋል።" ያሉ ሲሆን፤ የደመወዝ ጭማሪው ከ91 እስከ 92 ቢሊዮን ብር መካከል ተጨማሪ በጀት መጠየቁን ገልጸዋል።
ሚኒስትሩ አክለውም በነባሩ በጀት የተወሰነ መግባቱን ገልጸው፤ ተጨማሪ ደግሞ በተጨማሪ በጀትነት የሚታወጅ መሆኑን አስረድተዋል።
"ይሄኛው አጠቃላይ የመንግሥት ሰራተኛው በሁሉም መስክ በፀጥታም በሌሎችም ዘርፍ ያሉትን የኑሮ ጫና ለመቋቋም የሚያስችለውን ድጋፍ ለማድረግ መንግሥት በከፍተኛ ቁርጠኝነት የገባበት ነው" ሲሉም አቶ አህመድ ተናግረዋል።
"የባለፉት ሁለት ወራት የኢንፍሌሽን አፈጻጸም በሚታይበት ጊዜ እንደተሰጋው አይደለም። የተረጋጋ የዋጋ ሁኔታ ነው ያለው። የተወስነ ጭማሪ በአንዳንድ እቃዎች ላይ እንጂ በአብዛኛው የተረጋጋ ሁኔታ ነው ያለው።" ሲሉ አክለዋል።
"ሆኖም የደመወዝ ጭማሪው እጅግ አስፈላጊ ስለሆነ የሰራተኛውን ቋሚ ደመወዝተኛ ገቢ ያለውን ዝቅተኛውን ትኩረት አድርገን የዝቅተኛውን በጣም ከፍተኛ ጭማሪ አድርገናል" ያሉ ሲሆን፤ የላይኛውን ዝቅተኛ ጭማሪ ተደርጎ መሰራቱንም አብራርተዋል።
የገንዘብ ሚኒስቴር ከዚህ ቀደም "ዝቅተኛ ደሞዝ ተክፋዮች በኑሮ ውድነት እንዳይጎዱ ለማድረግ አስጠናሁት" ባለው ጥናት መሠረት፤ ለደመወዝ ጭማሪው የሚያስፈልገው ተጨማሪ የወጪ በጀት ከነመጠባበቂያው 91 ቢሊየን 439 ሚሊየን 368 ሺሕ 14 ብር መሆኑን አስታውቆ እንደነበር አሐዱ መዘገቡ ይታወሳል።
በጭማሪው ዝቅተኛው የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ 4 ሺሕ 760 ብር ሲሆን፤ ቀድሞ ከነበረው 1 ሺሕ 100 ብር በመቶኛ የ332.7 በመቶ ጭማሪ ተደርጎበታል። ከፍተኛው 20 ሺሕ 468 ብር ደመወዝ በ5 በመቶ ጭማሪ 21 ሺሕ 491ብር መድረሱ በጊዜው ተገልጾ ነበር፡፡
የገንዘብ ሚኒስትሩ በአሁኑ ማብራሪያቸው፤ ጭማሪው "ለኑሮ ድጎማ ጭምር እንዲሆን" በማሰብ የተተገበረ መሆኑን የገለጹ ሲሆን፤ የጭማሪው ዝርዝር በቅርቡ በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በኩል ይፋ እንደሚደረግ አመላክተዋል።
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
የእንስሳት ጤና አጠባበቅ ላይ ክፍተቶች መኖራቸው ተገለጸ
መስከረም 23/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ እንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት፤ የእንስሳት ጤና አጠባበቅ ላይ ክፍተቶች መኖራቸውን አስታውቋል፡፡
ኢንስቲትዩቱ በገጠርም ሆነ በከተማ የእንስሳት ጤና ጥበቃን ጨምሮ በእንስሳት አያያዝ ረገድ መሻሻል ያለባቸው ጉዳዮች መኖራቸውን ገልጾ፤ ለዚህም ምክንያቱ በአገር ውስጥ የእንስሳት ክትባት መድኃኒት አምራች ተቋማት ባለመኖራቸው መሆኑን ገልጿል።
በተለይም ከመስከረም አንስቶ እስከ ሕዳር ባሉ ወራት የፍየል፣ በግ እንዲሁም የቀንድ ከብቶች የጤና እክል የሚገጥማቸው በመሆኑ በቂ የመድሐኒት ስርጭት ማዘጋጀት አስፈላጊ መሆኑን የኢንስቲትዩቱ የገበያ ስርጭት ዳይሬክተር አቶ መስፍን ታደሰ ለአሐዱ ተናግረዋል።
አክለውም፤ ተቋሙ በአሁኑ ወቅት 25 አይነት ክትባቶችን እያመረተ እንደሚገኝ አመላክተዋል፡፡
በዚሁ ወቅት ተመሳስለው የሚመረቱ የእንስሳት ክትባት መኖራቸውን ተከትሎ የግብርና ሚኒስቴር አስፈላጊውን ክትትል ሊያደርግ ይገባል ሲሉም ተናግረዋል።
አቶ መስፍን በእንስሳት ጤና አጠባበቅ ጉድለት የተነሳ በርካታ እንስሳት ላይ ችግር መድረሱን አስታውሰው፤ የሚመለከታቸው አካላት ይህንን ታሳቢ አድርገው እንዲንቀሳቀሱም ጠይቀዋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት የእንስሳት ሕክምና የሚውል ክትባት ለአርብቶ አደሩ የሚያቀርብ መንግሥታዊ የልማት ድርጅት ነው።
ኢንስቲትዩቱ ከተቋቋመበት ከ1956 ዓ.ም ጀምሮ የክትባት ምርት፣ የበሽታ ምርምርና ምርመራ እንዲሁም የእንስሳት መድሀኒት ማቀነባበር ሥራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል።
በአማኑኤል ክንደያ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
በጅቡቲ ባህር ዳርቻ በደረሰ አደጋ ሕይወታቸውን ያጡ 48 ዜጎች በሙሉ ኢትዮጵያዊያን መሆናቸው ተረጋገጠ
መስከረም 23/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ባሳለፍነው ማክሰኞ መስከረም 21/2017 ዓ.ም ማምሻውን ከየመን ወደ ጅቡቲ በሚጓዝ የስደተኞች ጀልባ ላይ በደረሰ አደጋ ሕይወታቸውን ያጡ 48 ዜጎች በሙሉ ኢትዮጵያዊያን መሆናቸው መረጋገጡን፤ በጅቡቲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል፡፡
320 መደበኛ ያልሆኑ ፍልሰተኞች ይዘው የተነሱት ሁለት የስደተኞች ጀልባዎች በጅቡቲ ባህር ዳርቻ አከባቢ ሲደርሱ በደረሰው አደጋ የዜጎች ህይወት ማለፉ ይታወሳል።
አደጋውን ተከትሎ 48 ፍልሰተኞች ህይወታቸው ሲያልፍ፣ 197 ፍልሰተኞች ከአደጋው ተርፈው ኦቦክ የሚገኘው ዓለም አቀፉ የስደተኞች ካምፕ መድረሳቸው ተነግሯል።
የተቀሩት 75 ፍልሰተኞችን አካል የማፈላለጉ ሥራ በነፍስ አድን ሠራተኞች መቀጠሉን ተገልጿል፡፡
እስከአሁን በስፍራው በተደረገው የዜጎች ማጣራት ሂደት፤ ሁሉም ፍልሰተኞች ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውን ከሚመለከተው አካላት በተገኘው መረጃ ማወቅ መቻሉን ኤምባሲው አስታውቋል።
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የመመረቂያ አዳራሹን "ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ አዳራሽ" ተብሎ እንዲጠራ ተወሰነ
መስከረም 23/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት ትናንት መስከረም 22 ቀን 2017 ዓ.ም ባደረገው መደበኛ ስብሰባ፤ የቀድሞ የተማሪዎች መመረቂያ አዳራሽ በፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ሥም እንዲሰየም ውሳኔ አስተላልፏል።
ሴኔቱ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ ከዚህ በፊት "የተማሪዎች መመረቂያ አዳራሽ" ተብሎ የሚጠራው የዩኒቨርሲቲውን የመመረቂያ አዳራሽ፤ ከመስከረም 22/2017 ዓ.ም ጀምሮ "ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ አዳራሽ" ተብሎ እንዲጠራ ውሳኔ ማስተላለፉን ከዩንቨርስቲው የህዝብ ግንኙነት እና ዓለም ዓቀፍ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ በህይወት ዘመናቸው በኢትዮጵያ በሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ተምሳሌት የሚታወቁ፣ መምህርና ተመራማሪ፣ የሀገር ባለውለታ በመሆናቸው፤ አሁን በሥማቸው የተሰየመው አዳራሽ እሳቸውን በሚመጥን መልኩ እድሳት ተደርጎ እሳቸው የሰሩትን ሥራዎች ያካተተ ማስታወሻ እንዲቀመጥ እና በትውልድ መካከል ቅብብሎሽ እንዲኖር ሲል ሴኔቱ መወሰኑም ተገልጿል።
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
በትግራይ ክልል የመከላከያ ሲቪል ሠራተኞች ከ2013 ጀምሮ ደሞዝ አልተከፈለንም ሲሉ ቅሬታቸውን ገለጹ
መስከረም 23/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በትግራይ ክልል በመከላከያ ማሰልጠኛ ካንፕ ውስጥ የሚገኙ ሲቪል ሠራተኞች፤ ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ ደሞዝ እንዳልተከፈላቸው ለአሐዱ ገልጸዋል፡፡
ሠራተኞቹ አብዛኛው ዝቅተኛ የወር ደሞዝ ተከፋይ መሆናቸውን የገለጹ ሲሆን፤ ነገር ግን አሁን ላይ ዝቅተኛውንም ክፍያ ቢሆን ባለማግኘታቸው በችግር ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡
በክልሉ የሚገኙ የመከላከያ ማሰልጠኛ ካንፕ ውስጥ የሚሰሩ ሠራተኞች የደሞዝ ክፍያቸውን ጉዳይ ከሁለት ዓመት በላይ ሲጠይቁ መቆየታቸውን አንስተው፤ ለሚመለከተው አካል እስከ አዲስ አበባ ዋና መስሪያ ቤት ድረስ ቅሬታ ቢያቀርቡም ምላሽ እንዳላገኙ ገልጸዋል፡፡
በአጠቃላይ በኮንትራትና በቋሚ ተቀጣሪ ሠራተኛ ከ600 በላይ እንደሚሆኑ የገለጹት ቅሬታ አቅራቢዎቹ፤ ቅሬታቸውን በተደጋጋሚ ለሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የትግራይ ክልል ቅርንጫፍ ቢያቀርቡም እስከ አሁን ድረስ ምንም መፍትሔ እንዳልተሰጣቸው አስረድተዋል፡፡
አሐዱም ለምን መፍትሄ አልሰጣችሁም? ሲል የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ የትግራይ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጽሐዬ እንባዬን ጠይቋል፡፡
ኃላፊው በምላሻቸው፤ ቅሬታው በትክክል በተደጋጋሚ የሚቀርብ መሆኑን አንስተው፤ ነገር ግን ተጠሪ መስሪያ ቤቱ ትግራይ ውስጥ ስለሌለ አዲስ አበባ ለሚገኘው ዋናው መስሪያ ቤት ጉዳያቸው መላኩን አስረድተዋል፡፡
በዚህም መሰረት መርማሪ ተመድቦ ከቅሬታ አቅራቢ ተወካዮች ጋር ንግግር እንደተጀመረ መረጃው እናዳላቸው የገለጹት አቶ ጸሐዬ፤ "እኛ መሸኛ እና የሠራተኞቹን ዝርዝር ሥም እና ፊርማ አድርገን ልከናል፡፡ ክፍያው በዋናው ቢሮ ነው የሚፈጸመው" ብለዋል፡፡
"የቅሬታ አቅራቢ ተወካዮች እና የተመደበው መርማሪ መረጃ መለዋወጥ ጀምረዋል" ያሉም ሲሆን፤ ጉዳዩ በሂደት ላይ እንደሚገኝና መፍትሄ ይገኛል ብለው እንደሚያስቡም ተናግዋል፡፡
ሠራተኞቹ ደሞዛቸው ባለመከፈሉ ምክንያት እነርሱና ቤተሰቦቻቸው በከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደሚገኙ በመግለጽ ትኩረት ሊሰጣቸው እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
በአለምነው ሹሙ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
እድሜ ልክ የሚወሰዱ መድኃኒቶች ዋጋ በእጥፍ ስለመጨመሩ የተናፈሰው ወሬ ሐሰተኛ ነው ተባለ
መስከረም 23/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) እድሜ ልክ በሚወሰዱ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች መድኃኒቶች ዋጋ በእጥፍ ስለመጨመሩ እየተናፈሰ የሚገኘው ወሬ ሐሰተኛ ነው ሲል የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት አስታውቋል።
በአዲስ አበባ ከተማ የስኳር በሽታ መድሐኒት ዋጋ በእጥፍ መጨመሩን የሚገልጽ ቅሬታ ለአሐዱ ቀርቦለታል፡፡
ከስኳር በተጨማሪ የደም ግፊት እና ኮሌስትሮል መድኃኒቶችም መጠነኛ የዋጋ ጭማሪ እንዳሳዩ የተናገሩት ቅሬታ አቅራቢዎቹ፤ መድኃኒቶቹ እድሜ ልክ የሚወሰዱ እና የማይቋረጡ በመሆናቸው መቸገራቸውን አስረድተዋል፡፡
አሐዱ ቅሬታውን መሰረት በማድረግ የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎትን ጠይቋል፡፡
የአገልግሎቱ የህዝብ ግኑኙነት ዳይሬክተር አቶ አወል ሀሰን፤ በተጠቀሱት መድኃኒቶች ላይ ምንም ዓይነት የዋጋ ጭማሪ እንዳልተደረገና የአቅርቦት እጥረት እንዳላጋጠመ ነግረውናል፡፡
የደም ግፊት፣ ኮሌስትሮል እና የስኳር በሽታ መድኃኒቶች በመንግሥት መድኃኒት መሸጫዎች ላይ ቀድሞ በነበረበት ዋጋ እየተሸጠ እንደሚገኝ የገለጹት ዳይሬክተሩ፤ "በመድኃኒቶቹ ላይ በእጥፍ ጭማሪ ተደርጓል ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ፍጹም የተሳሳተ ነው" ሲሉም ተናግረዋል፡፡
አክለውም የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የህብረተሰቡን የመድኃኒት አቅርቦት ፍላጎት ለማርካት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸው፤ የጤና ተቋማት ከአገልግሎቱ ጋር ዉል በመግባት ዓመታዊ የመድኃኒት ፍላጎታቸውን በተመጠነ መልኩ የሚያገኙበት እና ተጠቃሚዉን ማህበረሰብ የሚያገለግሉበት ስርዓት ከዚህ ቀደም መዘርጋቱን አንስተዋል፡፡
ዳይሬክተሩ ባስተላለፉት መልዕክት፤ የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ የግል መድኃኒት መደብሮችን፣ ‹‹መድኃኒቱ አልቋል›› ወይም ‹‹የለም›› የሚሉ የመንግሥት መድኃኒት ቤቶችን በመጠቆም ማኅበረሰቡ እንዲተባበር ጠይቀዋል፡፡
በሚክያስ ኃይሌ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
የ10 ወር ሕፃን በማገት 500 ሺሕ ብር የጠየቀችው ግለሰብ በ13 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣች
መስከረም 23/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በባህርዳር ከተማ ቀበሌ 14 ኤፍራታ የተባለ አካባቢ በቤት ሰራተኝነት ከተቀጠረችበት ቤት የ10 ወር ሕፃን በማገት ይዛ የተሰወረችው ግለሰብ በ13 ዓመት ፅኑ እስራት መቀጣቷ ተሰምቷል፡፡
ወጣት ትዕግስት አለነ የተባለች ግለሰብ መስከረም 7 ቀን 2017 ዓ.ም በባህርዳር ከተማ ቀበሌ 14 ኤፍራታ የተባለ አካባቢ በቤት ሰራተኝነት ሥራ ለመቀጠር በደላላ አማካኝነት ከአቶ ወርቁ ሰማ ቤት ከጧቱ 3:00 ገደማ የገባች ሲሆን፤ በዚሁ በመጣችበት ቀንም አሰሪዎቿ ሆኖን ወርቁ የተባለ የ10 ወር ሕፃን ልጃቸውን አምነው ለእርሷ በመተው ወደሥራ ይሄዳሉ።
በቤት ውስጥ ከነበረው ከሕፃኑ አጎት ስልክ በመለመን ወደማይሰራ የራሷ ስልክ ትደውልና ስልኩን የመለሰች ሲሆን፤ ከዛም የሕፃኑ አጎት ከቀኑ 9:00 ገደማ ከቤት መውጣቱ ተነግሯል።
ሰራተኛዋ ትዕግስት ግን አደራዋን በመብላት እና ያልተፈለገ ጥቅም ለማገኘት በማሰብ በዛው ሥራ በጀመረችበት ቀን ከቀኑ 10:00 አካባቢ ሰው አለመኖሩን ካረጋገጠች በኋላ ሕፃኑን ይዛ ትሰወራለች።
ቀጥሎም የሕፃኑ ወላጆችና ዘመዶች ጉዳዩን ያውቁና አዳሩን ሙሉ ሲፈልጉት ያመሻሉ ግን ምንም አየን ወይም ሰማን የሚል ሰው አላገኙም።
የሕፃን ሆኖን ወርቁ ወላጅ አባት አቶ ወርቁ ሰማ እንደተናገሩት "ልጄ መጥፋቱን እንደሰማሁ ለፖሊስ ከጠቆምኩ በኋላ በማህበራዊ ሚዲያ አፋልጉኝ በማለት የልጄን ፎቶ አጋራሁ፤ ቀጥዬም ከወንድሞቸ ጋር በመሆን ምሽቱን ሙሉ የተለያየ ቦታ ሁነን ማፈላለግ ጀመርን ግን ምንም ማግኘት አልቻልንም ከምሽቱ 3:00 ገደማ ደረሰ ባለቤቴ በጣም አዝናና ደንግጣ ነበር።" ብለዋል፡፡
ከዛም ከምሸቱ 3:00 አካባቢ ደውላበትበት በነበረው ስልኳ ለሕፃኑ አጎት ደውላ የ100 ብር ካርድ እንድልክላትና ሕፃኑም ከሷ ጋር መሆኑን የገለጸች ሲሆን፤ የሕጻኑ አባት አቶ ወርቁ ሰማ ካርዱን ይሞሉላታል፡፡
በፅሁፍ መልዕክት 500,000 (አምስት መቶ ሽህ ብር) ዛሬውኑ ካላመጣ ህፃኑን እንደማያገኘው ትናገራለች፡፡ አባትም "ይሄን ያህል ብር የለኝም ለጊዜው ያለኝን ልስጥ" እያለ ሲማጸን እምቢተኛ ሆነች።
በሚቀጥለው ቀን ቤተሰቡ ከፖሊስ ጋር በየኬላው በመበተተን ፍተሻ ሲደረግ ይቆያል። ዘንዘልማ አካባቢ ከገበሬዎች ቤት አድራ የዘንዘልማ ኬላን በእግሯ አልፋ የትራንስፖርት ገንዘብ ስላልነበራት ኬላ የሚፈትሹ የአድማ መከላከል ፖሊሶችን ገንዘብ ለመጠየቅ ወደ ኬላው መጥታ ስትጠይቅ ቀድሞ የህፃኑ ፎቶ የደረሳቸው አድማ መከላከል ፖሊሶች እና እዛው የነበረ የህፃኑ አጎት ደርሰው ይይዟታል።
በዚህ ሂደት ክስ ተመስርቶባት ለምን እንዳደረገችው ስትጠየቅ "ወደ ውጭ ሀገር ለመሄድ ገንዘብ ስላጣሁ ለሱ የሚሆን ገንዘብ ለማግኘት ፈልጌ ነው" በማለት የእምነት ቃሏን ሰጥታለች።
ፖሊስም የተለያዩ ማስረጃዎችን በማጠናከር ምርመራውን አጣርቶ ለሰሜን ጎጃም ዞን ፍትህ መምሪያ ይልካል።
በመጨረሻም የባህርዳርና አካቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት መስከረም 21 በዋለው ችሎት ትዕግስት አለነ በ13 ዓመት ፅኑ እስራት እንድትቀጣ መወሰኑን ከክልሉ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
በባንኮች ያለው የውጭ ምንዛሬ ክምችት በ80 በመቶ መጨመሩን የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ አስታወቁ
👉በ2017 በጀት ዓመት ከወርቅ ወጪ ንግድ 488 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር መገኘቱ ተገልጿል
መስከረም 23/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ አፈጻጸምን ተከትሎ በባንኮች ያለው የውጭ ምንዛሬ ክምችት በ80 በመቶ መጨመሩን የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ አስታውቀዋል፡፡
የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ አፈጻጸም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በትናንትናው ዕለት ተገምግሟል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ፤ "በተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራ አማካኝነት ላለፉት አምስት አስርት ዓመታት ሥራ ላይ የቆየውን የውጭ ምንዛሪ ፖሊሲ መሰረታዊ በሆነ መልኩ ማሻሻል ተችሏል" ብለዋል፡፡
ይህም በሀገር አቀፍ ደረጃ የነበረውን የውጭ ምንዛሬ እጥረት ትርጉም ባለው መልኩ እንዲቀረፍ ማድረጉን ነው የተናገሩት፡፡
ለአብነትም ማሻሻያውን ተከትሎ ባለፉት ሁለት ወራት በባንኮችና በትይዩ ገበያ ያለውን የውጭ ምንዛሬ ልዩነት ወደ 3 በመቶ ዝቅ ማድረግ መቻሉን አንስተዋል፡፡
በዓለም አቀፍ ስታንዳርድ መሰረት በባንክና ትይዩ ገበያ መካካል ያለው የውጭ ምንዛሬ ልዩነት ከመቶ በታች ከሆነ አፈጻጸሙ ጤናማ መሆኑንም አንስተዋል።
በሌላ በኩል የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራውን ተከትሎ በወጪ ንግድ አፈጻጸም የተሻለ ስኬት መመዝገቡን ተናግረዋል፡፡
ለአብነትም በተያዘው መስከረም ወር የተመዘገበው የወጪ ንግድ አፈጻጸም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ53 በመቶ ብልጫ እንዳለው ነው የተናገሩት፡፡
ከሃዋላ የተገኘው የወጪ ንግድ ገቢም ካለፈው በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ145 በመቶ ብልጫ እንዳለው አብራርተዋል።
በከፍተኛ ሁኔታ ለኮንትሮባንድ ተጋልጦ የነበረው የወርቅ ወጪ ንግድም እጅግ መሻሻል ማሳየቱን ጨምረው ገልጸዋል፡፡
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ከወርቅ ወጪ ንግድ የተገኘው ገቢ 58 ሚሊዮን ዶላር ብቻ እንደነበር ጠቅሰው፤ በ2017 በጀት ዓመት እስካሁን ባለው ሂደት ከወርቅ ወጪ ንግድ 488 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር መገኘቱን ጠቁመዋል፡፡
የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ አፈጻጸምን ተከትሎ በባንኮች ያለው የውጭ ምንዛሬ ክምችት በ80 በመቶ መጨመሩን ጠቁመው፤ ይህም ማሻሻያው ስኬታማ አፈጻጸምን እያስመዘገበ መሆኑን ያሳያል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ስርዓቱን ጤናማነት ለመጠበቅ የጀመራቸውን ጥብቅ ቁጥጥሮች አጠናክሮ እንደሚቀጥልም የገለጹት ገዢው፤ ባንኩ ከውጭ ምንዛሬና ብድር አሰጣጥ ጋር ተያያዝ ተገቢና ህጋዊ ያልሆነ አካሄድ በሚከተሉ ባንኮች ላይ ጠንካራ ቁጥጥርና የእርምት እርምጃ እንደሚወስድም ተናግረዋል፡፡
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
በኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ በተፈጸመ ሥርቆት በምሥራቅ ኢትዮጵያ በርካታ አካባቢዎች ኃይል መቋረጡን ተገለጸ
መስከረም 23/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፣ ከቆቃ ወደ ሁርሶ በተዘረጋ በባለ 230 ኪሎ ቮልት ጥምር የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ በተፈጸመ ሥርቆት በምሥራቅ ኢትዮጵያ በርካታ አካባቢዎች ኃይል መቋረጡን ትናንት ምሽት አስታውቋል።
የተቋሙ የማዕከላዊ ሁለት ሪጅን የኃይል ማስተላለፊያዎችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽንና ጥገና መምሪያ ዳይሬክተር አቶ አለማየሁ ዘበርጋ እንደገለጹት፤ ኃይል የተቋረጠው በአፋር ክልል አዋሽ ፈንታሌ ወረዳ በንቲ ቀበሌ ልዩ ሽሙ አዋሽ ፓርክ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በአንድ የኃይል ተሸካሚ ምሰሶ ላይ በተፈጸመ ስርቆት ምክንያት ነው።
የኃይል ማስተላለፊያ መስመሩ በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍል ለሚገኙ ከተሞችና አካባቢዎች፣ ለአዲስ አበባ- ጅቡቲ የባቡር መስመር እንዲሁም ለጅቡቲ የኤሌክትሪክ ኃይል እያቀረበ እንደነበረ የገለጹት ዳይሬክተሩ፤ በደረሰው ጉዳት ምክንያት በተጠቀሱት ቦታዎች የኃይል አቅርቦት መቋረጡን ጠቅሰዋል።
በስርቆት ምክንያት ከወደቀው አንድ ምሰሶ በተጨማሪ ሰባት የኃይል ተሸካሚ ምሰሶዎች በአስጊ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙም አቶ አለማየሁ ተናግረዋል።
ስርቆት የተፈጸመበት የኃይል ተሸካሚ ምሰሶ ጥምር የኤሌክትሪክ መስመሮችን የያዘ በመሆኑ የጥገና ሥራው ከ20 ቀን ያላነሰ ጊዜ ሊወስድ እንደሚችልም አስታወቀዋል።
የጥገና ሥራው ሙሉ በሙሉ እስከሚጠናቀቅ ድረስም ከመስመሩ ኃይል ሲያገኙ ለነበሩ ከተሞችና አካባቢዎች በፈረቃ ኤሌክትሪክ እንዲያገኙ ለማድረግ ጥረቶች ይደረጋሉ ያሉት ዳይሬክተሩ፤ ህብረተሰቡ የተፈጠረውን ችግር ተረድቶ በትዕግስት እንዲጠብቅም ነው መልዕክት ያስተላለፉት።
በሌላ በኩል፤ ከመተሃራ - አዋሽ ባለ 132 ኪሎ ቮልት የባቡር መስመር ላይ በሚገኙ ዘጠኝ የኃይል ተሸካሚ ምሰሶዎች ላይ ጉዳት በመድረሱ የጥገና ሥራዎችን ለማከናወን ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝም ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል።
በተመሳሳይ በአዲስ አበባ ከቃሊቲ አንድ- መካኒሳ የተዘረጋው ባለ 132 ኪሎ ቮልት የኃይል ማስተላለፊያ መስመር አንደኛው ፌዝ በመበጠሱ ትናንት ከምሽቱ 2 ሰዓት ሰዓት ጀምሮ ጎፋ ገብርኤል፣ በቄራ፣ በጀርመን አደባባይ፣ በሃና ማሪያም፣ ጀሞ አንድ ኮንዶሚኒየም፣ በለቡ አርሴማ በአካባቢው ኃይል መቋረጡ ተገልጿል፡፡
የደረሰውን ጉዳት በአፋጣኝ በመጠገን አገልግሎቱን ለመመለስ እንቅስቃሴ የተጀመረ ሲሆን፤ ከሰበታ አንድ- መካኒሳ የሚገባውን ተጨማሪ መስመር በመጠቀም ለተወሰኑ አካባቢዎች ኃይል መስጠት መጀመሩን አሐዱ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ያገኘው መረጃ ያመላክታል።
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ባልተፈቀደ ስፍራ ተሽከርካሪ በሚያቆሙ ላይ የሚጣለው ቅጣት ሊጨምር መሆኑ ተሰማ
መስከረም 22/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ባልተፈቀደ ስፍራ ተሽከርካሪያቸውን በሚያቆሙ አሽከርካሪዎች ላይ የሚጥለውን ቅጣት ሊጨምር መሆኑን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ለአሐዱ ገልጿል፡፡
ቢሮው "አሽከርካሪዎች ላይ የሚጣለው የቅጣት መጠን የሚጨምረው፤ "ቅጣቴ አስተማሪ ባለመሆኑ ነው" ብሏል፡፡
የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዳኛቸው ሸፈራው ለአሐዱ እንደተናገሩት፤ ለፓርኪንግ አገልግሎት ተብለው የሚገነቡ መኪና ማቆሚያዎችን መጠቀም የማይፈልጉ አሽከርካሪዎች ባልተፈቀደ ስፍራ ተሸከርካሪያቸውን እያቆሙ በመሆኑ የቅጣት እርከኑን ከፍ ማድረግ አስፈልጓል፡፡
ከፍ ይላል የተባለው የቅጣት እርከን ከተማ መስተዳድሩ ከመከረበት በኋላ ለሕዝብ ይፋ እንደሚደረግም ከኃላፊው ሰምተናል፡፡
አቶ ዳኛቸው አክለውም፤ በከተማዋ እየጨመረ ለመጣው የትራፊክ መጨናነቅ ምክንያት ባልተፈቀደ ስፍራ ተሽከርካሪን ማቆም አንዱ ምክንያት ነው ብለዋል።
የመስቀል አደባባይ የምድር ቤት፣ መገናኛ፣ መርካቶ እና በተለያዩ የከተማዋ መዳረሻዎች ላይ ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያዎች ተገንብተው ወደ ሥራ ቢገቡም በአሽከርካሪዎች ዘንድ የመጠቀም ልምዱ ዝቅተኛ መሆኑን ገልጸው፤ ይህ ልምድ መዳበር እንደሚገባውም አቶ ዳኛቸው ጨምረው አሳስበዋል፡፡
በአማኑኤል ክንደያ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ብሔራዊ ባንክ ለአምስት ባንክ ላልሆኑ የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች የስራ ፈቃድ ሰጠ
መስከረም 22/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለአምስት ባንክ ላልሆኑ የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች የሥራ ፈቃድ መስጠቱን አስታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አገልግሎትና ተደራሽነትን ለማስፋፋትና የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሪ ግኝት ለማዳበር አሁን በሥራ ላይ ካሉት ከባንክ ጋር ከተያያዙ የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች በተጨማሪ ከባንክ ጋር ዝምድና የሌላቸው የግል የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎችን ለመክፈት የሚያስችል የውጭ ምንዛሪ መመሪያ ማውጣቱ ይታወሳል፡፡
በዚሁ መሠረት፣ ከዚህ የሚከተሉት አምስት የግል የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች ተፈላጊውን መስፈርት ማሟላታቸው ተረጋግጦ በመመሪያው ንኡስ አንቀጽ 4.2 መሠረት እንዲንቀሳቀሱ የሥራ ፈቃድ እንደተሰጣቸው ተገልጿል፡፡
1. Dugda Fidelity Investment PLC
2. Ethio Independent Foreign Exchange Bureau
3. Global Independent Foreign Exchange Bureau
4. Robust Independent Foreign Exchange Bureau
5. Yoga Forex Bureau መሆናቸውን ባንኩ ገልጿል፡፡
በዚህም መሰረት፤ የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች በሙሉ ተቀባይነት ያላቸው የውጭ ሀገር ጥሬ ገንዘቦችን በመግዛትና በመሸጥ እንዲሁም ከባንኮች ጋር በመቀናጀት ለወጪና ገቢ ንግድ የሚውል የውጭ ምንዛሪ በማመቻቸት የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሪ ገበያ ለማስፋፋትና ለማዳበር የሚረዳ ሚና ይኖራቸዋል ተብሏል፡፡
የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች በዋናነት የሚያካሂዱት የውጭ ምንዛሪ ሽያጭም ሆነ ግዥ ወዲያውኑ የሚፈጸም (spot transaction) ብቻ እንደሚሆንም ተነግሯል፡፡
የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች ያለ ጉምሩክ ዴክላራሲዮን ከደንበኞች እስከ 10 ሺሕ የአሜሪካን ዶላር፣ የጉምሩክ ፈቃድ ከሚያቀርቡት ደግሞ ከዚያ በላይ የውጭ ምንዛሪ በጥሬ ገንዘብ መግዛት እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡
እንዲሁም ተፈላጊ የጉዞ መረጃ ላላቸው የግል ተጓዦች እስከ 5 ሺሕ የአሜሪካን ዶላር፣ ለንግድ ሥራ ተጓዦች ደግሞ እስከ 10 ሺሕ የአሜሪካን ዶላር በጥሬ ገንዘብ መሸጥ ይችላሉ፡፡
የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የወጡ የአሠራር፣ የደህንነት፣ ሪፖርት አደራረግና የመዝገብ አያያዝ መስፈርቶችን በአግባቡ ተግባራዊ ስለማድረጋቸው ባንኩ ጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል የሚያደርግ መሆኑን አስታውቋል፡፡
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
የቻይና ባለሃብቶች ከኢትዮጵያ መውጣታቸው ያለውን ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት እንደሚጎዳው ተገለጸ
መስከረም 22/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ የሚገኙ የቻይና ባለሃብቶች በኢትዮጵያ እያጋጠሙን ነው ባሉት ችግር ምክንያት፤ ከኢትዮጵያ ወደ ጎረቤት ሀገራት ታንዛኒያ፣ ኬንያ፣ ኡጋንዳ እየሄዱ መሆኑ ተሰምቷል፡፡
ይህን ጉዳይ በተመለከተ አስተያየታቸዉን የሰጡት የምጣኔ ሃብት ባለሙያው እና የቢዝነስ እና ኢንቨስትመንት አማካሪው አቶ ከፈለኝ ሀይሉ፤ "ከዚህ ቀደም የቻይና ባለሃብቶች ከሌሎች ሀገራት ባለሃብቶች ይልቅ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ የሚሰሩ ናቸው" ብለዋል፡፡
ነገር ግን አሁን ላይ በኢትዮጵያ ባለው የውጭ ምንዛሬ እጥረት በግብር እና በሌሎችም ምክንያቶች ተማረው ምርጫቸውን ጎረቤት ሀገራት ማድረጋቸው የሥራ እድል የተፈጠረላቸውን ዜጎች ሥራ አጥ ከማድረግ ባለፈ የውጭ ኢንቨስተሮችን ለመሳብ የሚደረገውን ጥረት እንደሚያደበዝዘው ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
አክለውም፤ ሌሎች ሀገራት የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ የግብር ቅነሳ እና ሌሎችንም ማበረታቻዎች ሲጠቀሙ የኢትዮጵያ መንግሥት ግን በሁሉም ሴክተር ላይ እየጣለ ያለው ግብር እና ተጨማሪ እሴት ታክስ ምጣኔ ሀብቱን አጣብቂኝ ውስጥ የሚከት መሆኑን አመላክተዋል፡፡
የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ዶክተር ሲሳይ ደበበ በበኩላቸው፤ "ሙሉ በሙሉ ለማለት በሚቻል ደረጃ የኮንስትራክሽን ዘርፉ የተያዘው በቻይናውያን ኢቨስተሮች በመሆኑ እና ትልልቅ ኢንቨስትመንቶች ላይ የሚሳተፉ በመሆናቸው የሚያስከትለው ችግር አንድ አቅጣጫ ብቻ ያለው አይደለም" ብለዋል፡፡
"የባለሃብቶቹ ከኢትዮጵያ ለቆ መውጣት በተለይም የሌሎች ሀገራት ኢንቨስተሮች በዘርፉ እንዳይሳተፉ ያደርጋል" ሲሉም አክለዋል፡፡
በተጨማሪም በሀገር ኢኮኖሚ ላይ የሥራ አጥ ቁጥርን በመጨመር ወጣቶችን ሥራ አጥ ያደርጋል ሲሉም ነው የተናገሩት፡፡
ከ6 መቶ ሺሕ በላይ ሰራተኞችን በስራቸው ቀጥረው እንደሚያሰሩ የሚገመቱት በኢትዮጵያ ያሉ የቻይና ኩባንያዎች ባለቤቶቻቸው ወደ ሌሎች ሀገራት ማማተር ኢትዮጵያን የሚያስከፍላት ዋጋ ከፍተኛ ነው ያሉት ባለሙያዎቹ፤ መንግሥት ጉዳዩን ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባው እና የሌሎች ሀገራትን ልምድ ማየት እንደሚያስፈልግም አንስተዋል፡፡
የቻይና ባለሀብቶች በኢትዮጵያ በኮንስትራክሽን፣ በኢንዱስትሪና በግብርና ዘርፎች በስፋት በመሰማራት ለበርካታ ዜጎች የሥራ እድል የፈጠሩ ሲሆን፤ በግንቦት 2024 በኢትዮጵያ ከ2 ሺሕ በላይ ፕሮጀክቶች ላይ በመሳተፍ እስከ 5 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ ኢንቨስትመንት ማምጣታቸውን የቅርብ ጊዜ መረጃዎች አመላክተዋል፡፡
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ለካንሰር ታካሚዎች ሕክምና የሚውለው የደም አይነት እጥረት ማጋጠሙ ተገልጿል
መስከረም 22/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ ለካንሰር ታካሚዎች አገልግሎት የሚውለው (ፕሌትሌት) የደም አይነት እጥረት ማጋጠሙን የኢትዮጵያ ደም እና ህብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት አስታውቋል።
የካንሰር ታካሚዎች በቀን 120 የፕሌትሌት የደም አይነትን ይፈልጋሉ እንደሚፈልጉ አገልግሎቱ ለአሐዱ ገልጿል።
በዚህመ ሦስት አይነት የደም ተዋዕጾ መኖራቸውን እና የመጠቀሚያ ጊዜያቸው የሚለያይ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ ቀይ የደም ሴል ለ42 ቀናት፣ ፕላዝማ የደም አይነት ለአንድ ዓመት እንደሚቆይ እና በከፍተኛ ሁኔታ እጥረት ያጋጠው የፕሌትሌት የደም አይነት ግን ለአምስት ቀናት ብቻ የሚቆይ መሆኑ ተነግሯል።
7 መቶ 41 ለሚሆኑ የህክምና ተቋማት የደም አቅርቦት እንደሚሰጥ የገለጹት የደም እና ህብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ታዩ፤ በአሁኑ ወቅት የደም ለጋሾች ቁጥር መቀነሱን ለአሐዱ ገልጸዋል።
የህፃናት እና የአዋቂዎች የካንሰር ህክምና ማዕከላት ላይ የፕሌትሌት የደም አይነት እጥረት በከፍተኛ ሁኔታ እየታየ ይገኛልም ብለዋል፡፡
በአዲስ አበባ ለካንሰር ታካሚዎች ህክምና በሚሰጡት በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እና በጳውሎስ አጠቃላይ ሆስፒታል የፕሌትሌት የደም አይነት እጥረት ማጋጠሙም ተነግሯል።
በእሌኒ ግዛቸው
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ከሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ በለቀቁ ኩባንያዎች ምክንያት 15 ሺሕ ሰራተኞች ከሥራ ተሰናብተዋል ተባለ
መስከረም 24/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ ተቀጥረው ከሚሰሩ 35 ሺሕ በላይ ሰራተኞች መካከል፤ 15 ሺሕ ሰራተኞች መቀነሳቸውን የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማኅበራት ኮንፌደሬሽን ፕሬዝደንት ካሳሁን ፎሎ ለአሐዱ እንደተናገሩት፤ ሰራተኞቹ የተሰናበቱት በኢንዱስትሪ ፓርኩ የነበሩ ኩባንያዎች ለቀው በመውጣታቸው ነው።
በአሁን ሰዓት በኢንደስትሪ ፓርኩ በሥራ ላይ ያሉ ሰራተኞች 20 ሺሕ መሆናቸውን ገልጸው፤ የለቀቁት ሰራተኞች ከመሰናበታቸው በፊት ጥቅማ ጥቅማቸው እንደተከበረላቸው ነግረውናል።
በኢንዱስትሪ ፓርኩ ውስጥ ያሉ አምራቾችን የሚያበረታታ አሰራር የማይዘረጋ ከሆነ እና ኩባንያዎች መውጣታቸው ከቀጠለ ግን የተሰናባች ሰራተኞቹ ቁጥር ከዚህ ሊጨምር እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።
በፓርኮቹ ውስጥ ፆታዊ ጥቃት ስለሚያጋጥማቸው ሴቶች ጉዳይ አሐዱ ላነሳው ጥያቄ ፕሬዝዳንቱ አቶ ካሳሁን ሲመልሱ፤ እስከ አሁን ጾታዊ ጥቃትን የተመለከተ ጥቆማ እንዳልደረሳቸው ጠቅሰው፤ የሴት ማኅበራትን የማደራጀት እና ክትትል የማድረግ እቅድ ስለመኖሩ ነግረውናል።
ኢንዱስትሪ ፓርኮች በኢትዮጵያ ኢኮኖሚን በማሳደግ፣ ኢንቨስትመንትን በማስፋት፣ የሥራ ዕድል በመፍጠርና የውጭ ምንዛሪ በማስገኘት በኩል ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡
በእመቤት ሲሳይ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ደራርቱ ተስፋዬ ''የሚስ ቱሪዝም ኦሮሚያ'' ውድድር አሸናፊ ሆነች
መስከረም 24/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን አዘጋጅነት በየዓመቱ የሚካሄደው ''ሚስ ቱሪዝም ኦሮሚያ'' ውድድር ዘንድሮም 15 ቆነጃጅቶችን በማሳተፍ ተካሂዷል።
በውድድሩ 5 ተወዳዳሪዎች ለፍጻሜ የደረሱ ሲሆን ደራርቱ ተስፋዬ በወድድሩን አንደኛ በመውጣት የ350 ሺሕ ብር ተሸላሚ ሆናለች።
በተጨማሪም ኤደን ሰለሞን 2ተኛ በመውጣት የ300 ሺሕ ብር እንዲሁም ሮቤኑስ አብዲሳ 3ተኛ በመውጣት 250 ሺሕ ብር ተሸላሚ ሆነዋል።
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
የሰሜን ጎንደር ዞን ጃንአሞራ ወረዳ ከ8 ሺሕ በላይ ዜጎች የዕለት ጉርስ ጠባቂ መሆናቸው ተገለጸ
መስከረም 23/2017 (አሐዱ ሬዲዮ)የሰሜን ጎንደር ዞን ጃንአሞራ ወረዳ በ2016 ዓ.ም በተከሰተው ድርቅ ምክንያት፤ በአካባቢው የሚኖሩ ከ8 ሺሕ በላይ ዜጎች የእለት ጉርስ እንደሚያስፈልጋቸውና በወረዳው ከፍተኛ የንጹሕ የመጠጥ ውሃ እጥረት መኖሩ ተገልጿል፡፡
የወረዳው ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሸጋው ተሰማ፤ በወረዳው በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ከዚህ ቀደም የሰው እና የእንስሳት ሞት መከሰቱን አንስተዋል፡፡
አሁንም ከድርቁ ጉዳት ሙሉ ለሙሉ ማገገም ባለመቻሉ በነዋሪዎችና በእንስሳት ላይ ከፍተኛ ችግር እየፈጠረ መሆኑን ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
የዕለት ጉርስ የሚጠብቁ ከ8 ሺህ ዜጎች መካከል ህጻናት እና አቅመ ደካሞች እንደሚገኙ ያነሱት ምክትል ዋና አስተዳዳሪው፤ ኩፍኝ እና ኮሌላ ወረርሽኝ ዳግም እያገረሸ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
የተከሰተውን ወረርሽኝ ለመቆጣጠር የተለያዩ ሥራዎች እየተሰሩ ቢሆንም፤ የሚፈለገውን ያህል ለውጥ ማምጣት አለመቻሉንም ተናግረዋል፡፡
በወረዳው ዘንድሮ መጠነኛ ዝናብ ቢኖርም፤ በቆላማ አካባቢዎች ግን የምርት እጥረት መኖሩንም አመላክተዋል፡፡
በወረዳው የሰው እና የእንስሳት መድሃኒት እጥረት መኖሩን ገልጸው፤ ክትባት የሚያስፈልገው ወረርሽኝ መከሰቱንም ተናግረዋል፡፡
ስለሆነም መንግሥትም ሆነ የሚመለከታቸው ድጋፍ ሰጪ አካላት አፋጣኝና ተከታታይ እርዳታ ማድረግ እንደሚገባቸው ገልጸው፤ ይህ ካልሆነ ግን ጉዳቱ የከፋ ሊሆን እንደሚችል አመላክተዋል፡፡
በ2015 ዓ.ም ሰኔ፣ ሐምሌ እና ነሃሴ ወራት በጃንአሞራ ወረዳ ውስጥ በሚገኙ በ13 ቀበሌዎች ላይ ምንም አይነት ዝናብ ባለመዝነቡ ምክንያት ነዋሪዎች ለከፍተኛ ለድርቅ መጋለጣቸው ይታወሳል፡፡
በእሌኒ ግዛቸው
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
Update
ለልማት ተነሺዎች የጋራ መኖሪያ ቤት የሚሰጥበት እድል ዝቅተኛ መሆኑ ተገለጸ
መስከረም 23/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በአዲስ አበባ ከተማ ለኮሪደር ልማት እና ለመልሶ ማልማት ተነሺ ነዋሪዎች የጋራ መኖሪያ ቤት የሚሰጥበት እድል ዝቅተኛ መሆኑን የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ፡፡
በቢሮ የቤት ማስተላለፍ ብድር አስተዳደር ዘርፍ ምክትል ዳይሬክተር ኢንጂነር ቶማስ ደበሌ፤ በከተማዋ ከተለያዩ አካባቢዎች በልማት ምክንያት ለሚነሱ ዜጎች፤ የጋራ መኖሪያ ቤት የሚሰጥበት እድል ዝቅተኛ መሆኑን ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
ኢንጂነር ቶማስ አሁን ላይ ያሉ ቤቶች ስቱዲዮ መሆናቸውን ገልጸው፤ "ከ ባለ 1 እስከ 3 መኝታ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጥረት በመኖሩ ለመስጠት አስቸጋሪ ነው" ብለዋል፡፡
ነገር ግን ብዙ ቤተሰብ ላላቸው ሰዎች ለመስጠት ጥረት ይደረጋል ሲሉ አንስተዋል፡፡
ከካሳንቺስ አካባቢ የልማት ተነሺዎች "ከባለ 1 እስከ ባለ ሦስት የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ብንጠይቅም፤ የተሰጠን ግን ስቱዲዮ ነው" በማለት ለአሐዱ ቅሬታቸውን መግለጻቸው ይታወሳል፡፡
በሚኪያስ ኃይሌ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ኬንያና ናይጄሪያ ዜጎቻቸውን ከሊባኖስ እንዲወጡ ሊያደርጉ ነው ተባለ
መስከረም 23/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የእስራኤልና ሂዝቦላህ ውጥረት እየተባባሰ መምጣቱን ተከትሎ፤ ኬንያ እና ናይጄርያ በሊባኖስ የሚኖሩ ዜጎቻቸው አገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የእስራኤል የምድር ጦር በትላንትናው ዕለት የሊባኖስን ድንበር አቋርጦ መግባቱ የተገለጸ ሲሆን፤ ይህም ሀገራት ዜጎቻቸውን እንዲያስወጡ ምክንያት ሆኗል ተብሏል፡፡
በዚህም የኬንያ የውጭና ዳያስፖራ ጉዳዮች ሚኒስቴር ትናንት ባወጣው መረጃ፤ እየተባበሰ በመጣው ወቅታዊ ሁኔታ በሊባኖስ የሚገኙ ኬንያዊያንን ደህንነት ለማስጠበቅ ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጧል፡፡
ሚኒስቴሩ አያይዞም "ምንም እንኳን መሰል ተደጋጋሚ ጥሪ ብናቀርብም በሊባኖስ የሚገኙ በርካታ ዜጎች ለቀው ለመውጣት እስካሁን አለመመዝገባቸው በእጅጉ ያሳስበናል" ብሏል፡፡
በተመሳሳይም የናይጀሪያ ፕሬዝዳንት የማህበራዊ ትስስር ልዩ ረዳት፤ "ሁሉም በሊባኖስ የሚገኙ ናይጀሪያውያን ወደ ኤምባሲ በመሄድ እንድትመዘገቡና ለቃችሁ እንድትወጡ" ሲሉ አሳስበዋል፡፡
የእሰራኤልና ሂዝቦላህን ፍጥጫ ተከትሎ እንደጀርመን፣ ካናዳ ፣እንግሊዝና ቻይና ያሉ ሀገራት ቀደም ሲል ዜጎቻቸው ከሊባኖስ እንዲወጡ ጥሪ ያስተላለፉ ናቸው፡፡
በሊባኖስ የኢትዮጵያ ቆንስል ጄነራል ጽሕፈት ቤት በሀገሪቱ በተከሰተው ጦርነት ምክንያት ወደ ሀገራቸው መመለስ የሚፈልጉ ዜጎች ከሊባኖስ መውጣት የሚችሉበትን መንገድ እያመቻቸ መሆኑን ባወጣው መግለጫ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡
በዚሁ መሠረት ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ የሚፈልጉ እና እስከ አሁን ያልተመዘገቡ ወገኖች አስፈላጊውን መረጃ በማዘጋጀት እንዲመዘገቡ ጥሪ አቅርቧል፡፡
በታሪኩ ጋሹ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
"ምዕመናን ገንዘባቸውን የሚሰጡት ለሃይማኖት ማስፋፊያ እንጂ ለዘረፋ አይደለም።" ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ
መስከረም 23/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፤ ምዕመናን ገንዘባቸውን የሚሰጡት ለሃይማኖት ማስፋፊያ እንጂ ለዘረፋ አይደለም ሲሉ አሳሰቡ።
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሚስተዋለውን የሙስናና ብልሹ አሰራር በዝርዝር በማጥናት የመፍትሔ ሐሳብ እንዲያቀርብ በጠቅላይ ቤተክህነት ጽሕፈት ቤት የተቋቋመው አጥኚ ኮሚቴ፤ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖትና ከብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የባህር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ጋር ከተቋቋመ ጀምሮ እስካሁን የሠራቸውን ሥራዎች ሪፓርት አቅርቧል።
በተጨማሪም በቀጣይ በሚያከናውናቸው ተግባራት ዙሪያ በመወያየት የሥራ መመሪያ ተቀብሏል።
ኮሚቴው በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሚስተዋለው የመልካም አስተዳደር ችግር ከውስጥ አልፎ በአደባባይ መነጋገርያ በመሆኑ በጥናት ላይ በተመሠረተ አግባብ ተቋማዊ ለውጥ ማምጣት የሚያስችልና የቤተ ክርስቲያናችንን ክብር በሚመጥን መልኩ እንዲደራጅ የሚያደርግ የመፍትሔ ሐሳብ ለማቅረብ የሚያስችለውን ዕቅድ በማውጣት ወደ ተግባር መግባቱን የኮሚቴው ሰብሳቢ መ/ሰ ቆሞስ አባ ቃለጽድቅ ሙሉጌታ (ዶር)
እና ዲ/ን ስንታየሁ ምስጋናው ባቀረቡት ሪፖርት ገልጸዋል።
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በሰጡት አባታዊ የሥራ መመሪያ "ምዕመናን ገንዘባቸውን የሚሰጡት ለሃይማኖት ማስፋፊያ እንጂ ለዘረፋ አይደለም። ያሉ ሲሆን ስለሆነም ሕግና ሥርዓትን አክብራችሁ፣ በእውነተኝነት ለቤተክርስቲያን፣ለእግዚአብሔርና ለራሳችሁ ብላችሁ ሳታፍሩና ሳትፈሩ ሥራችሁን ሥሩ። ሥራው ታማኝነት"ጥብዓት" ያስፈልጋል ብለዋል።
"ከብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ጋር ሆናችሁ በጋራ ሥሩ" ያሉት ቅዱስ ፓትርያርኩ፤ጠንከር ያለ መድኅኒት ሊሆን የሚችል ጥናት ከመፍትሔ ሐሳብ ጭምር እንደምታቀርቡ እምነቴ የጸና ነው" ሲሉም ተናግረዋል።
አያይዘውም "የተላካችሁበት ሥራ ያለ ውጤት የሚቀር መሆን የለበትም። ቤተክርስቲያን የተዋረደችበት ጊዜ ማብቃት አለበት" ያሉት ቅዱስነታቸው፤ "ቤተክርስቲያናችን ራሷን አንጽታ ለሌሎች መልካም አብነት መሆን አለባት" በማለት አሳስበዋል።
አክለውም፤ "ዓለማዊያን የሚሰሩት ሥህተት እንዳይኖር በተግባር የምታስተምር ተቋም እንጂ በሙስና የምትታማ መሆን የለበትም" ብለዋል።
"ልጆቼ እውነቱን ለማውጣት ታጥቃችሁ ሥሩ በሙስና ህመም ለምትሰቃየው ቤተክርስቲያን መድኃኒት ፈልጉላት" በማለት አባታዊ መልዕክታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው፤ "አንመረመርም ማለት ራሱን ችሎ ወንጀል ነው" ካሉ በኋላ "ይህ ሥራ ለእናንተም ታሪክ ነው። እውነትን መሰረት አድርጋችሁ በመሥራት ታሪክ አስመዝግቡ" ብለዋል።
በመልዕክታቸው ማጠቃለያ ላይም "ወደ እዚህ ተቋም የሚገቡ ሁሉ ይህን ያህል ጊዜ ቆይተን ይህን ያህል ይዘን እንውጣ የሚሉ እንጂ ለቤተክርስቲያን የሚቆረቆሩና የሚያስቡ እንዳልሆኑ ይታወቃል ካሉ በኋላ የተሰጣችሁን ኋላፊነት በትጋት ፈጽሙ" በማለት አሳስበዋል።
በመጨረሻም "ሥራችሁ ሁሉ የተሳካና ውጤታማ እንዲሆን እንጸልያለን እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን" በማለት፤ አባታዊ መልዕክታቸውን ማጠናቀቃቸውን ከቤተክርስቲያኒቱ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
አሜሪካ በሀገሯ ከፍተኛ ዝናብ በቀላቀለው አውሎ ነፋስ የተጎዱ ዜጎችን እንዲያግዙ 1 ሺሕ ወታደሮችን አሰማራች
መስከረም 23/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በአሜሪካ ሰሜናዊ ካሮላይና ግዛት ባለፈው ሳምንት በተከሰተው ከፍተኛ ዝናብ የቀላቀለና አውሎነፋስ የ179 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተነግሯል፡፡
በዚህም የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን በግዛቷ በርካቶች መሞታቸውን ተከትሎ፤ 1 ሺሕ ወታደሮች እርዳታ እንዲያደርጉ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል፡፡
ድጋፎችን ማቅረብ፣ ምግብ እናውሃ በአውሎነፋስ ለተጎዱ ማህበረሰቦች ማድረስ ላይ በትኩረት እንደሚሰራም አስታውቀዋል።
"ሀሪኬን ሔሊን" የተሰኘው አውሎነፋስ በቅድሚያ ፍሎሪዳን የመታ ሲሆን፤ ወደ ሰሜን ተሻግሮ ጆርጂያን፣ ሁለቱን ካሮላይናዎች እና ቴኔሲን ማዳረሱ ተገልጿል።
በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በጎርፍ መጥለቅለቁ መወሰዳቸው የተገለጸ ሲሆን፤ በደረሰው ጉዳት እስካሁን በርካታ ሰዎች የደረሱበት አልታወቀም ተብሏል።
አውሎነፋሱ ካደረሰው ሰብዓዊ ቀውስ በተጨማሪ ከፍሎሪዳ እስከ ቨርጂንያ ድረስ ባሉት አካባቢዎች ከ1.3 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የሃይል አቅርቦት እንዲቋረጥባቸው አድርጓል መባሉን ኤንቢሲ ዘግቧል፡፡
በአደጋው በጥቅሉ ከ95 እስከ 110 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ንብረት መውደሙም የተገለጸ ሲሆን፤ እስካሁን ከፍተኛ የሟቾች ቁጥር የተመዘገበው በሰሜን እና ደቡብ ካሮላይና መሆኑም ተነግሯል።
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓል ተከብሮ እስከሚጠናቀቅ ነገ ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ጀምሮ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ተደረጉ
መስከረም 23/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓል አከባበር ወቅት የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር፤ ከነገ መስከረም 24 ቀን 2017 ዓ/ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ለተሽከርካሪ ለጊዜዉ ዝግ እንደሚሆኑ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስ በዓሉ በሠላም እንዲከበር የፀጥታ አካላት ትኩረት ሰጥተው ወደ ተግባር በመግባት እየሰሩ መሆኑን ጠቅሶ፤ በተለይ በዓሉ ወደሚከበርበት ስፍራ የሚመጡ ታዳሚዎች ለጋራ ደህንነት ሲባል ፍተሻ መኖሩን ተገንዝበው አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ጠይቋል፡፡
በዓሉ በሠላም እንዲከበርም የበዓሉ ታዳሚዎች እና የከተማው ነዋሪ የተለመደውን ትብብር እንዲያደርጉ በፀጥታ አካላት ሥም ጥሪውን አስተላልፏል፡፡
በመሆኑም የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓል ተከብሮ እስከሚጠናቀቅ
• ከቅዱስ ኡራኤል አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ኡራኤል አደባባይ ላይ
• ከቦሌ አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ኦሎምፒያ አደባባይ ላይና ታች እንዲሁም ግራና ቀኝ
• ከመስቀል ፍላወር ወደ ኦሎምፒያ የሚወስደው መንገድ ጋዜቦ አደባባይ ላይ
• ከአጎና ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ ለከባድ ተሽከርካሪ አጎና ሲኒማ አጠገብ እንዲሁም ለቀላል ተሽከርካሪ ጥላሁን አደባባይ (አራተኛ ክፍለ ጦር ላይ)
• ከለገሀር መብራት ወደ መስቀል አደባባይ ለገሀር መብራት ላይ
• ከቴሌ ማቋረጫ ወደ ስታድዮም ለሚጓዙ ቴሌ ማቋረጫ
• ከራስ ሆቴል ወደ ስታድዮም ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ራስ ሆቴል ላይ
• ከሃራምቤ መብራት ወይም ከአምባሳደር ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ ሃራምቤ መብራት ላይ
• ከብሔራዊ ቤተ መንግሥት ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ብሔራዊ ቤተ መንግሥት አጠገብ
• ከካዛንቺስ ሼል ወደ ባምቢስ የሚወስደው መንገድ ካዛንቺስ ሼል አጠገብ እንዲሁም
• ከጁፒተር ሆቴል ወደ ECA የሚወስደው መንገድ ባምቢስ ሳልኮት ህንፃ አጠገብ ያሉ መንገዶች ከነገ መስከረም 24 ቀን 2017 ዓ/ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ለተሽከርካሪ ለጊዜዉ ዝግ እንደሚሆኑ አስታውቋል፡፡
በዚህም መሠረት በዓሉ በሚከበርበት ዙሪያ እና በአካባቢው በግራና በቀኝ ለረጅምም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል፡፡
ህብረተሰቡ ለፀጥታ ስጋት የሆኑ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት በ011-1-11-01-11 እንዲሁም በ991 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ በመስጠትና አስፈላጊውን ትብብር በማድረግ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ ተላልፏል፡፡
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
የኢሬቻ በዓል አዲስ አበባን የቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ ከፍ ያለ ሚና ይጫወታል ተባለ
መስከረም 23/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢሬቻ በዓል የአዲስ አበባን የቱሪዝም ፍሰት ከለወጡ የአደባባይ በዓላት ዋነኛው ወሆኑን፤ የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ባሕል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ገልጿል።
የመስተዳድሩ የባሕል፣ ኪነ-ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊዋ ዶክተር ሒሩት ካሳው መንግሥት አዲስ አበባን የቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ እየሰራ እንደሚገኝ አንስተው፤ ኢሬቻን ጨምሮ ጥምቀት፣ መስቀልና ሌሎች የአደባባይ በዓላት ላይ ትኩረት እየተደረገ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል፡፡
በከቅርብ ጊዜ ወዲህ በመዲናዋ እየተተገበሩ የሚገኙ የልማት ሥራዎች ለቱሪዝም ኢንዱስትሪው ከፍ ያለ አስተዋጽኦ እንዳላቸው ዶክተር ሒሩት ተናግረዋል።
በማይዳሰሱ ቅርሶች ዘርፍ ዓለም አቀፍ እውቅና የተሰጣቸው ባህላዊ እና ሀይማኖታዊ በዓላትን በቁሳዊና ባሕላዊ እሴቶች ለማዳበር እየተሰራ መሆኑን ገልፀው፤ "ኢሬቻ በዓል ደግሞ ዋነኛው የኢትዮጵያ ባሕላዊው በረከት ነው" ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተመዘገቡ በርካታ የማይዳሰሱ ቅርሶች ያላት ቢሆንም፤ እስካሁን በበቂ ሁኔታ ተመዝግበዋል ለማለት እንደማያስደፍር የገለጹት ዶክተር ሒሩት፤ በቅርስነት የተመዘገቡትን ተንከባክቦና አክብሮ መያዝ እንደሚገባ አሳስበዋል።
የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል “ኢሬቻ ለባህል ሕዳሴያችን” በሚል መሪ ሐሳብ፤ በመጪው ቅዳሜ መስከረም 25 በአዲስ አበባ ሆራ ፊንፊኔ መስከረም 26 እሁድ ደግሞ በቢሾፍቱ ሆራ አርሰዲ ይከበራል።
በአማኑኤል ክንደያ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
የሽሮ ሜዳ አካባቢ የወንዝ ዳር ልማት ተነሺዎች ቃል የተገባላቸው የካሳ ክፍያ እንዳልተከፈላቸው ተናገሩ
መስከረም 22/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ጉለሌ ክፍለ ከተማ፤ ሽሮ ሜዳ በሚገኘው የቀበና ወንዝ አካባቢ ነዋሪዎች፤ በወንዝ ዳር ልማት ምክንያት ከመኖሪያ አካባቢያችን ስንነሳ ቃል የተገባልን የካሳ ክፍያ አልተፈጸመልንም የሚል ቅሬታ አሰምተዋል።
የልማት ተነሺዎቹ ለአሐዱ በተናገሩት ቅሬታ፤ ከ90 ሺሕ ብር በላይ እንደሚከፈላቸው ቃል የተገባላቸው ቢሆንም የተከፈላቸው 60 ሺሕ ብር ብቻ መሆኑን ተናግረዋል።
ቅሬታ አቅራቢዎቹ በተጨማሪም መንግሥት የፈቀደላቸውን የካሳ ክፍያ የቀነሱት የክፍለ ከተማው ኃላፊዎች መሆናቸውን ነግረውናል።
ወደ ክፍለ ከተማው ቤቶች ልማት በማምራት ቅሬታቸውን ባሰሙበት ወቅት፤ "ለእቃ ማንሻ የሚሆን ክፍያ እንዲፈጸም ለክፍለ ከተማው ኃላፊዎች ትእዛዝ እንዳስተላለፉ" መረዳታቸውን ገልጸው፤ ነገር ግን የክፍለ ከተማው ኃላፊዎች ክፍያውን ለመፈጸም ፈቃደኛ እንዳልሆኑ ለአሐዱ አስረድተዋል።
አሐዱም የሽሮሜዳ አካባቢ የወንዝ ዳር ልማት ተነሺዎችን ቅሬታ በመያዝ ምላሽ ለማግኘት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን ጠይቋል፡፡
የከተማ አስተዳደር ቢሮው "ለልማት ተነሺዎች ይከፈላል" የተባለው የእቃ ማንሻ ክፍያ የዘገየበት ምክንያት ተጣርቶ በትዕዛዙ መሰረት የማስተካከያ እርምጃ እንደሚወሰድ አስታውቋል፡፡
ሥማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉት ኃላፊው ችግሩ በአስቸኳይ ይፈታል ሲሉ ለአሐዱ ተናግረዋል።
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
በኢትዮጵያ የሚገኙ የንግድ ምክር ቤቶች የንግድ ስርአቱ እንዲቀላጠፍ አስተዋጽኦ እያበረከቱ አለመሆኑ ተገለጸ
መስከረም 22/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በኢትዮጵያ የሚገኙ የንግድ ምክር ቤቶች የግሉ ክፍለ ኢኮኖሚ እንዲነቃቃና በመንግሥት ስርዓት እንዲመራ መወጣት የነበረባቸውን ሚና አለመወጣታቸውን ገለጸ፡፡
የሚኒስቴሩ ሚኒስትር ዲዔታ እንዳለ መኮንን እንደተናገሩት፤ ተቋማቸው መካከለኛ እና አነስተኛ ኢንዱስትሪዎች የሚሳተፉበት ገበያ እያፈላለገ ቢሆንም ንግድ ምክር ቤቶች እገዛ እያደረጉለት አይደለም፡፡
በተለይም ከታሪፍ ነፃ የንግድ ስርአት ለመዘርጋት እየተደረገ ያለውን ጥረት ለንግድና ኢንዱስትሪው ዘርፍ ከፍተኛ እገዛ እንደሚኖረው ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የንግዱን ስርአት ለማስፋፋትና የመዳረሻ አገራትን ቁጥር ለመጨመር በትኩረት እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝም ለአሐዱ ተናግረዋል።
በተጨማሪም ሚንስትር ዴኤታው የንግዱ እንቅስቃሴ እንዲስፋፋና እንዲጎለብት የንግድ ምክር ቤቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑን አስረድተዋል።
በአዲስ አበባ የሚገኙ ንግድ ምክርቤቶች በአንፃራዊነት የተሻሉ ቢሆኑም ከዚህ በበለጠ መንቀሳቀስ እንደሚገባቸው ተጠቁሟል፡፡
በአማኑኤል ክንደያ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ይዘዉ የሚቀርቡት የድርድር አቋም ተለዋዋጭ አለመሆኑ ዉጤት እንዳይመጣ አድርጓል ተባለ
መስከረም 22/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ኢትዮጵያ ራሷን እንደነጻ አገር ከምትቆጥረው ሶማሊላንድ ጋር በባህር ዳርቻ አጠቃቀም ዙርያ የመግባቢያ ሰነድ ከተፈራረሙ በኋላ በሞቃዲሾ እና በአዲስ አበባ መካከል ያለው ግንኙነት መበላሸቱን ተከትሎ፤ ቱርክ ሁለቱን ሀገራት ለማደራደር ጥረት እያደረገች ትገኛለች።
ቱርክ ለዚህ የኢትዮጵያ እና ሱማሊያ የባሕር በር ውዝግብ መፍትሄ የማፈላለግ ጥረቷን እንደምትገፋበት አስታውቃለች።
የቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ይህን ያለው፤ የአገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ኒውዮርክ ውስጥ ከኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ እና ከሱማሊያው ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አሕመድ ፊቂ ጋር በተናጥል ከተወያዩ በኋላ ነው።
አሐዱም ከዚህ ቀደም በቱርክ አደራዳሪነት የተካሄዱት ዉይይቶች ለምን ዉጤታማ መሆን አልቻሉም? ምክንያቱ ምን ሊሆን ይችላል? ሲል የዲሎማሲዉ ዘርፍ ባለሙያዎችን ጠይቋል።
ቱርክ በአፍሪካ ሀገራት ካላት ጠንካራ የኢኮኖሚ እና ፖለቲካዊ ተሳትፎ አንጻር በሶማሊያ እና በኢትዮጵያ የተፈጠረዉን ዉጥረት ለማርገብ እና ለማደራደር ብቃቱ እንዳላት የገለጹት፤ የቀድሞው የሰብዓዊ መብት ኮሚሽነር አምባሳደር ጥሩነህ ዜና ናቸው።
አምባሳደር ጥሩነህ ከዚህ በፊት በነበሩት ዉይይቶች በተለይም የሶማሊያ አቋም አለመሻሻሉ ድርድሩ ዉጤት አልባ እንዲሆን አድርጓታል ብለዋል።
አክለዉም፤ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ለድርድር ይዘዉ የሚቀርቡት አቋም ተለዋዋጭ አለመሆኑ ዉጤት እንዳይመጣ ካደረጉት ምክንያቶች ውስጥ አንዱ መሆኑን ገልጸዋል።
"ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያላትን መልካም የሆነ ግንኙነት ለማስቀጠል በዲፕሎማሲ መጠንከር እና መስራት ይገባታል" ሲሉም አምባሳደር ጥሩነህ ጠቁመዋል፡፡
የቀድሞ ዲፕሎማት አቶ ዳያሞ ዳሌ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ ከሶማሊ ላንድ ጋር በተፈራረመችዉ የመግባቢያ ሰነድ ዙሪያ ሁለቱ ሀገራት ያላቸው አቋም አለመቀየሩ ያለፉት ድርድሮች ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩን አንስተዋል።
በቱርክ የተያዘዉ ሦስተኛ ዙር የአደራዳሪነት ሚና ለዉጥ ያመጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጸዋል።
ባለሙያዎቹ አክለዉም ቱርክ በቀጠናው በተለይም በሶማሊያ የግብፅን ተጽዕኖ ፈጣሪነት ስለማትፈልገዉ ለኢትዮጵያ መልካም አጋጣሚ ይሆናል ብለዋል።
ቱርክ እስካሁን በሁለቱ ጎረቤት ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ለማስተካከል ሁለት ዙር የጋራ የንግግር መድረኮችን ማዘጋጀቷ የሚታወስ ሲሆን፤ በመስከረም ወር መጀመሪያ ላይ በአንካራ ሊካሄድ የነበረው ሦስተኛው ዙር ድርድር መሰረዙ ይታወሳል።
ይህንንም ተከትሎ ለሦስተኛ ጊዜ አዲስ ድርድር ከመደረጉ በፊት ቱርኩ ሁለቱን አገራት በተናጥል ለማወያየት ማቀዷን አስታውቃለች።
በፅዮን ይልማ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ ከአፋር ክልል ፕሬዝዳንት አወል አርባ ጋር ተወያዩ
መስከረም 22/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ የትግራይ እና የአፋር ህዝብ ግንኙነት ለማጠናከር ከአፋር ክልል ፕሬዝዳንት አወል አርባ ጋር ዛሬ መስከረም 22 ቀን 2017 ዓ.ም በሰመራ ከተማ ተወያይተዋል፡፡
ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ የተመራው የትግራይ ልዑካን ቡድን አፋር ሲደርስ፤ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ እና ካቢኔያቸው በሰመራ አውሮፕላን ማረፊያ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
በፕሬዝዳንቱ የሚመራው የትግራይ ልዑካን ቡድን፤ የደቡብ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ምስራቅ ዞኖችን ርእሰ መስተዳድሮች ያቀፈ መሆኑን ድምጸ ወያኔ ዘግቧል::
የርዕሰ መስተዳድሮቹ ውይይት የሁለቱን አጎራባች ከተሞች የቀድሞ ግንኙነት ማደስ ላይ ያተኮረ መሆኑም ተገልጿል፡፡
ሰኞ መስከረም 20 ቀን 2017 ዓ.ም በመቐለ ከተማ በተደረገ ስብሰባ ላይ፤ የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት አቶ ጌታቸው ረዳ ኤርትራን ጨምሮ ከሌሎች ሁሉም አጎራባች ህዝቦች ጋር ዘላቂ ሰላም ለመፍጠር እንደሚሰሩ መግለጻቸው ይታወሳል።
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ