ahaduradio | Unsorted

Telegram-канал ahaduradio - AHADU RADIO FM 94.3

19349

አሐዱ ራድዮ 94.3 Your source for top local and international news and analysis. "Voice of Ethiopian" የአሐዱ የቴሌግራም ቻናል ቤተሰብ በመሆን ወቅታዊና እውነተኛ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ

Subscribe to a channel

AHADU RADIO FM 94.3

አምባደር ታዬ አጽቀሥላሴ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾሙ

መስከረም 27/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ም/ ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን መክፈቻ ሥነ- ሥርዓት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት መካሄድ ጀምሯል።

በመክፈቻው ላይም የፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ የሥራ ጊዜ መጠናቀቁን ተከትሎ፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑት አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፕሬዚዳንት እንዲሆኑ በእጩነት ቀርበዋል።

ምክር ቤቱም ሹመታቸውን በ5 ተቃውሞ በአብላጫ ድምጽ አጽድቆታል።

በዚህም መሠረት አምባሳደር ታዬ የሁለቱን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ በንግግር ከፍተዋል።

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

"በአማራ ክልል የተዘጉ መንገዶችን በአስገዳጅነት ከጸጥታ ሐይል በጋራ በመሆን መከፈት ይገባቸዋል" የክልሉ ትራንፖርት ቢሮ

👉ቢሮው ከታሪፍ በላይ የሚጭኑ አሽከርካሪዎችን ለመቆጣጠር መቸገሩን ገልጿል


መስከረም 27/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በአማራ ክልል ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት የተዘጉ መንገዶችን ለመክፈት ከጸጥታ ሐይል በጋራ በመሆን የማስከፈት ሥራ እንደሚሰራ የአማራ ክልል መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

በቢሮው የትራፊክ ደህንነት የግንዛቤና ስልጠና ባለሙያ አቶ አበበ አላምረው ከአሐዱ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ በክልሉ የተዘጉ መንገዶችን ለመክፈት እንቅስቃሴዎች መጀመራቸውን የገለጹ ሲሆን፤ አሽከርካሪዎችም የተሰጣቸውን ስምሪት በአግባቡ ሊወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

የስምሪት ሁኔታዎችን ክትትል ለማድረግ በየወሩ የውይይት መርሐ ግብር በማካሄድ መስመሮችን ለመሸፈን በእንቅስቃሴ ላይ መሆናቸውን የገለጹት አቶ አበበ፤ በስምሪታቸው መሰረት መስመራቸውን የማይሸፍኑ አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ እየተወሰደ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡

በሚሰጠው መመሪያ መሰረት ግዳጃቸውን የማይወጡ ወይም መስመሮችን የማይሸፍኑ አሽከርካሪዎች ከስምሪት እንዲታገዱና እንደየጉዳዩ ታይቶ እስከ ሁለት ሳምንት ለሚሆን ጊዜ አሽከርካሪው ታስሮ እንዲቆይ የሚደረግበት ሁኔታ መኖሩንም ለአሐዱ ገልጸዋል፡፡

ባለፈው ዓመት ከ70 በላይ የሚሆኑና በተለያዩ ምክንያቶች ስምሪታቸውን ወይም ሐላፊነታቸውን ባልተወጡ አሽከርካሪዎች ላይ ከስምሪታቸው እንዲታገዱ የተደረገበት አግባብ እንዳለም አንስተው፤ የተሰጠውን ሐላፊነት የማይወጣ አሽከርካሪ ላይ እርምጃ የመውሰዱ ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስረድተዋል፡፡

በሌላ በኩል ቢሮው በክልሉ ከታሪፍ በላይ የሚጭኑ አሽከርካሪዎችን ለመቆጣጠር ያለው የጸጥታ ችግር እንቅፋት እየሆነበት እንደሚገኝ አቶ አበበ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

በጸጥታው ችግር ምክንያት ከታሪፍ በላይ የሚጭኑ አሽከርካሪዎችን ከቦታ ቦታ ባለሙያዎች ተንቀሳቅሰው መከታተል እንዳልቻሉ አንስተው፤ ይህም ማህበረሰቡ ላይ ከባድ ጫና እየፈጠረ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

እንደ ክልል በተደረገው ጥናት መሰረት በአጠቃላይ በትራንስፖርቱ የሚታዩ ጥፋቶች 30 በመቶ ከታሪፍ በላይ መጫን እንደሆነም አቶ አበበ ጨምረው ገልጸዋል፡፡

በክልሉ የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ ሁኔታን በተመለከተ ከታሪፍ በላይ ማስከፈልና ትርፍ በመጫን የሚሰሩ አሸከርካሪዎች ላይ ቁጥጥር እየተደረገ ቢሆንም፤ በበቂ ሁኔታ ሥራውን ለማከናወን የጸጥታው ችግር እንቅፋት እንደሆነባቸው አንስተዋል፡፡

በአለምነው ሹሙ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ የመጀመሪያውን ኤርባስ A350-1000 በጥቅምት ወር ሊረከብ መሆኑ ተገለጸ

መስከረም 27/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ አኅጉር የመጀመሪያውንና ከ350 እስከ 410 መንገደኞች ማሳፈር የሚያስችለውን ግዙፍ ኤርባስ A350-1000 አውሮፕላን በጥቅምት ወር እንደሚረከብ ተሰምቷል።

አውሮፕላኑ ET-BAW በሚል የተመዘገበ ሲሆን፤ 46 የቢዝነስ ደረጃ እና 349 የኢኮኖሚ ደረጃ መቀመጫዎች በአጠቃላይ 395 መቀመጫዎች እንዳሉት ተነግሯል፡፡ ከሌሎች አውሮፕላኖች ጋር ሲወዳደርም ከፍተኛ የቢዝነስ ደረጃ መቀመጫዎችን ያሉት ነው።

ኤ350-1000 የመጀመሪያ በረራውን ከአዲስ አበባ ወደ ሄትሮው ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ህዳር 3 ቀን 2024 በማድረግ ሥራ ይጀምራል ተብሎ እንደሚመጠበቅ ተነግሯል።

እነዚህ አውሮፕላኖች ከ777-300ER በመቀጠል ሁለተኛው ከፍተኛ ሰው የመጫን አቅም ያላቸው እንደሚሆኑም ተመላክቷል።

በሐምሌ ወር 2014 የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሚያደርገውን የኤርባስ A350-1000 ትዕዛዝ ከኤርባስ አውሮፕላን አምራች ኩባንያ ጋር መፈራረሙ ይታወቃል፡፡

አየር መንገዱ ከዚህ በፊት ከኩባንያው 22 ኤርባስ A350-900 አውሮፕላን በማዘዝ 16ቱን ተረክቦ ሥራ ላይ ያዋለ ሲሆን፤ ከተቀሩት የኤርባስ A350-900 አውሮፕላን ትዕዛዞች አራቱ ወደ ኤርባስ A350-1000 እንዲቀየሩ ከኤርባስ አውሮፕላን አምራች ኩባንያ ጋር ስምምነት ማድረጉ ይታወሳል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኤርባስ A350-1000ን አገልግሎት ላይ ያዋለ የመጀመሪያው የአፍሪካ አየር መንገድ ያደርገዋል፡፡

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

"በአማራ ክልል የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌዎችን እና መርሖችን ያልተከተሉ እስሮች በአፋጣኝ ሊቆሙ ይገባል" ኢሰመኮ

መስከረም 27/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በአማራ ክልል በበባህር ዳር፣ ጎንደር ከተሞች እና በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች ከያዝነው ዓመት የመስከረም ወር አጋማሽ ጀምሮ “በአዲስ መልክ” በርካታ ሰዎች “ያለ ፍርድ ቤት ትእዛዝ” እየታሰሩ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ።

ኮሚሽኑ በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች የሚፈጸመውን የበርካታ ሰዎች እስር በተመለከተ ክትትል ማድረጉን እንደሚቀጥል የገለጸ ሲሆን፣ በማናቸውም ወቅት ቢሆን የሚፈጸም እስር ተገቢውን የሕግ እና የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌዎች ሊከተል የሚገባ መሆኑን አሳስቧል።

በክልሉ የመንግሥት ሠራተኞች፣ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት እና የሚዲያ እና የሲቪክ ማኅበረሰብ አባላትን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ወደ ጊዜያዊ ማቆያዎች እየተወሰዱ እንደሚገኝም አስታውቋል፡፡

እስሮቹ በሕግ አግባብ በፍርድ ቤት ትእዛዝ ያልተፈጸሙ፣ ተጠርጣሪዎቹ ፍርድ ቤት ያልቀረቡ መሆናቸው እንዲሁም ከመካከላቸው ቋሚ የሕክምና ክትትል የሚያስፈልጋቸው ሰዎች መኖራቸውን ማወቅ መቻሉንም ገልጿል።

የጊዜያዊ ማቆያዎቹን ሁኔታ እንዲሁም የተያዙ ሰዎችን ሰብአዊ መብቶች አያያዝ በተመለከተ የሚመለከታቸውን የክልሉን የአስተዳደር እና ጸጥታ አካላት ለማነጋገር እና ምላሽ ለማግኘት የሚደረገው ጥረት የሚቀጥል መሆኑን አመላክቷል።

እንዲሁም ኢሰመኮ መስከረም 24 ቀን 2017 ዓ.ም. በባሕር ዳር ከተማ የሚገኘውን አድቬንቲስት ትምህርት ቤትን ጨምሮ በተለያዩ የከተማው አካባቢዎች ላይ ለጊዜው ማንነታችው ባልታወቁ ሰዎች የተፈጸሙት የቦንብ ፍንዳታዎች ያደረሱትን የሰብአዊ ጉዳት እና አንድምታ እየተከታተለ እንደሚገኝም አስታውቋል፡፡

ኮሚሽኑ አክሎም፤ ማንኛውም አካል በሲቪል ሰዎች እና በሲቪል ተቋማት ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ከማድረስ እንዲሁም የነዋሪዎችን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ከሚያውክ ተግባር ሊቆጠብ እንደሚገባ አሳስቧል።

የኢሰመኮ ተጠባባቂ ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ፣ “በትጥቅ ግጭት እና በጸጥታ መደፍረስ ወቅትም ቢሆን ሲቪል ሰዎችን ለመያዝ የሚያበቃ/በወንጀል ለመጠርጠር የሚያበቃ በቂ ሕጋዊ ምክንያት መኖሩን ማረጋገጥ ያገባል" ብለዋል፡፡

አክለውም፤ የተወሰኑ ልዩ ሁኔታዎች እንደተጠበቁ ሆነው በፍርድ ቤት የተሰጠ የመያዣና የብርበራ ትእዛዝ መኖሩን፣ በወንጀል ተጠርጥረው የተያዙ ሰዎች በመደበኛ ማቆያ ቦታዎች ብቻ እና መብቶቻቸውን ባከበረ ሁኔታ መያዛቸውን እንዲሁም በተያዙ በ48 ሰዓት ውስጥ ፍርድ ቤት መቅረባቸውን ማረጋገጥ ይገባል” ሲሉም አሳስቧል።

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በአዋሽ ፈንታሌ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ የተወሰኑ ቤቶችን ማፍረሱ ተገለጸ

መስከረም 27/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በአዋሽ ፈንታሌ እና አካባቢው ትናንት ምሽት የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ የተወሰኑ መኖሪያ ቤቶችን ማፍረሱን ሰመራ ዩኒቨርሲቲ አስታውቋል፡፡

በመሬት መንቀጥቀጡ መሬት መሰንጠቁንም ዩኒቨርቲው ዛሬ ሰኞ ማለዳ ባወጣው መግለጫ ተናግሯል።

በፈንታሌ ተራራ ላይ ተከስቶ ንዝረቱ አዲስ አበባ ከተማ ድረስ የተሰማው የመሬት መንቀጥቀጥ፣ ከሁለት ሳምንታት በላይ በተለያየ አጋጣሚ መከሰቱን ባለሞያዎች ገልጸዋል።

ትናንት መስከረም 26/2017 ምሽት 2፡10 ገደማ የተከሰተው በሬክተር ስኬል 4 ነጥብ 9 የተመዘገበበት ነበር።

"የሰሞኑ የመሬት መንቀጥቀጥ በአዋሽ ፈንታሌ እና አካባቢው ከፍተኛ ሥጋት ፈጥሯል" ያለው ዩኒቨርሲቲው፤ አደጋው በተከሰተበት ሳቡሬ ቀበሌ ተገኝቶ መረጃ የመሰብሰብ እና ለማህበረሰቡ ጥንቃቄ የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራ መሥራቱን ገልጿል።

የአካባቢው ነዋሪዎች የትናንቱ መንቀጥቀጥ ተወሰኑ ቤቶችን እንዳፈረሰ፣ መሬትን እንደሰነጠቀ እና በተለይ እንስሳት ከፍተኛ መደናገጥ ውስጥ እንደገቡ ገልጸዋል::

የዩኒቨርሲቲው ጂኦሎጂስቶች ነዋሪዎች ከፈንታሌ ኮረብታማ ቦታ እና ከከሰም ግድብ ርቀው እንዲቆዩ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል።

ትናንት እሑድ ምሽት የተከሰተውና በአዲስ አበባ በነዋሪዎች ላይ መደናገጥ የፈጠረው የመሬት መንቀጥጠጥ ለ18 ሴኮንድ የቆየ እንደነበረ ባለሞያዎች ተናግረዋል።

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

#ለጥንቃቄ
የመሬት መንቀጥቀጥ ሲያጋጥም ምን ማድረግ ይጠበቅብናል?


መስከረም 26/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦ ፊዚክስ እና ስፔስ ሳይንስ ተቋም ዳይሬክተር ዶክተር ኤሊያስ ሌዊ የመሬት መንቀጥቀጥ ሲያጋጥም ምን ማድረግ ይጠበቅብናል? በሚለው ዙሪያ የሚከተለውን ብለዋል።

ዛሬ አዲስ አበባ የተሰማው የመሬት መንቀጥቀጥ ከአዲስ አበባ በሰሜን ምስራቅ 165 ኪ.ሜ ፈንታሌ አካባቢ የተፈጠረ የመሬት መንቀጥቀጥ ነው።

የመሬት መንቀጥቀጥ ሲያጋጥም

👉 የህንፃ ኮለኖች አካባቢ መሆን

👉 ጠረጴዛ ወይም መሰል ነገር ስር መደበቅ

👉 መሬት ላይ ያለ ሰው የመብራት ፖል አካባቢ በሌለበት ቦታ መቆም

👉 ከፎቅ ለመውረድ ሊፈት አለመጠቀም

👉 እሳት ሊያስነሱ የሚችሉ ነገሮችን ማጥፋት ይገባል

ዶክተር ኤሊያስ ሌዊ ይህ መንቀጥቀጥ ድጋሚ ሊከሰት ይችላል ወይ? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ፤ "መሬት መንቀጥቀጥ መተንበይ የሚባል ነገር የለም፤ የት አካባቢ እንደሆነ እንጂ መቼ ይከሰታል የሚባለውን መተንበይ አይቻልም። " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

"ለጊዜው መናገር የምችለው ከበድ ያለ ነገር አይመጣም ብለን ነው የምንገምተው። ከመጣ ግን መደረግ ስላለበት ጥንቃቄ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።

በቀጣይ የመሬት መንቀጥቀጥ የመከሰት ዕድሉ በተለይም በአዲስ አበባ ላይ መኖሩን የገለጹ ሲሆን፤ "ስምጥ ሸለቆና የስምጥ ሸለቆ አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ነቅተን የምንጠብቀው ነገር መሆን አለበት" ሲሉም አሳስበዋል።

የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በበኩሉ፤ የመሬት መንቀጥቀጥ በሚያጋጥም ጊዜ መደረግ የማገባቸዉ የጥንቃቄ እርምጃዎች አመላክቷል።

እነርሱም፦

👉  ከቤት ውጭ ከሆኑ - ከዛፎች፣ ከሕንፃዎች፣ ከኤሌትሪክ ምሶሶዎች እና ሌሎች ወድቀው ጉዳት ሊያደርሱ ከሚችሉ ነገሮች መራቅ እና ገላጣ ሜዳ አካባቢ መቆየት።

👉  በቤት ውስጥ ከሆኑ - በበር መቃኖች፣ በኮርነሮች እና ኮሪደሮች ተጠግቶ ማሳለፍ። ከእሳት ምድጃዎች፣ ከተሰቀሉ ፍሬሞች እና የግድግዳ ጌጦች፣ ከመጽሐፍ መደርደሪያዎች እንዲሁም ከመስኮት አካባቢ መራቅ። የጋዝ ምድጃዎችን በተቻለ ፍጥነት ማጥፋት ካልሆነም ከአካባቢው መራቅ።

👉 በትልልቅ ሕንጻዎች ውስጥ ከሆኑ- ከሕንጻዎቹ ለመውጣት አለመሞከር፣ አሳንሰር (ሊፍት) በፍፁም አለመጠቀም። ከደረጃዎች አካባቢ መራቅ።

# መኪና እያሽከረከሩ ከሆኑ- የኤሌትሪክ መተላለፊያ ምሶሶዎችን፣ ዛፎችና ሽቦዎች አካባቢ አለመቆም፣ የኤሌትሪክ መስመር ምሶሶዎች እና ሽቦዎች ተሽርካሪው ላይ ከወደቁ ከመኪናው ለመውጣት አለመሞከር፣ በተቻለ ፍጥነት ገላጣ ወደሆነ አካባቢ መኪናን ማቆም ይገባል ብሏል።

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በአዲስ አበባ እና አካባቢዋ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ

መስከረም 26/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ዛሬ ምሽት ከ2:00 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ እና አካባቢዋ ላይ ብዙዎችን ያስደነገጠ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት ተከስቷል።

የመሬት መንቀጥቀጡ በለሚኩራ ክፍለ ከተማ፣ ሰሚት፣ አያት 49፣ ጀሞ፣ ኮዬ ፈጬ፣ ጎፋ ካምፕ፣ ዊንጌት፣ ጋርመንት፣ መስቀል አደባባይ፣ ካሳንችስ፣ ጉለሌ የካ አባዶ እንዲሁም በሌሎች አካባቢዎች ላይ የተከሰተ ሲሆን፤ በንዝረቱ በርካታ ነዋሪዎች ተደናግጠው ቤታቸውን ጥለው መውጣታቸውን በአየአካባቢው የሚገኙ የአሐዱ ጋዜጠኞች ተናግረዋል።

በተጨማሪም በድሬደዋ፣ በደሴ፣ ሸዋሮቢት ከተማ፣ ደብረብርሃን እንዲሁም በሌሎች የሀገሪቷ ክፍሎች ተመሳሳይ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱ ታውቋል።

የመሬት መንቀጥቀጡ በርዕደ መሬት መለኪያ ምን ያህል እንደሆነ እና ያደረሰው ጉዳት አስመልክቶ እስካሁን የተባለ ነገር የለም። በቀጣይ ዝርዝር መረጃዎችን ይዘን የምንቀርብ ይሆናል።

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

ቱርክ የብሪክስ አባል አገር ልትሆን እንደምትችል የሩስያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተናገሩ

መስከረም 25/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በመጪው ወር በሩስያ ይካሄዳል ተብሎ ቀን የተቆረጠለት ሰብሰባ የቱርክ አባልነት ይፋ እንደሚደረግ የሩስያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ገልጸዋል።

ሰርጌ ላቭሮቭ፣ በሩስያ በሚካሄደው የብሪክስ ስብሰባ ላይ ሰላሳ አገራት እንደሚሳተፉ የገለጹ ሲሆን፤ ሉዕካኑን ለመቀበል ዝግጁ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

በዚህ ሰብሰባ ላይ በርካታ አዳዲስ ውሳኔዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ ላቭሮቭ ፍንጭ መስጠታቸውንም ስፑትኒክ ዘግቧል።

ቱርክ በተደጋጋሚ ጥያቄ ስታቀርብ ብትቆይም ጥያቄዋ ተቀባይነት ሳያገኝ የቆየበትን ምክንያት በተመለከተ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ፤ ሰርጌ ላቭሮቭ መልስ ከመስጠት መቆጠባቸውንም ዘገባው አመላክቷል።

እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በፈረንጆቹ 2009 በሩሲያ የመጀመሪያ ጉባኤውን ያደረገው "ብሪክ" በ2010 ወደ "ብሪክስ"ነት ያደገ ሲሆን፤ በዋናነት ብራዚል፣ ሩሲያ፣ ህንድ እና ቻይና መመስረቱ ይታወቃል።

በፈረንጆች 2011 ደቡብ አፍሪካ የመጀመሪያዋ ብሪክስ የተቀላቀለች አፍሪካዊት ሀገር ስትሆን፤ ጉባኤው ኢትዮጵያ፣ ግብፅ፣ ኢራን እና የተባበሩት አረብ ኢምሬቶችን በዚህ ዓመት መጀመርያ ላይ በአባልነት መቀበሉ ይታወሳል፡፡

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

"በዓሉ ያለምንም ጸጥታ ችግር በሰላም ተጠናቋል" የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ

መስከረም 25/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የ2017 ዓ.ም የ ‘ሆረ ፊንፊኔ’ ኢሬቻ በዓል ያለምንም ጸጥታ ችግር በሰላም መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታውቋል።

ፌደራል ፖሊስ ባወጣው መግለጫ፤ "ሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብና አባገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎች፣ ከተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች እና ከጎረቤት ሀገራት የመጡ እንግዶች እንዲሁም የውጭ ሀገራት ቱሪስቶች  የታደሙበት የሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል ያለምንም የጸጥታ ችግር በሰላም ተጠናቋል" ብሏል።

የበዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ድርሻቸውን ለተወጡ ለአባገዳዎችና ሀደ ሲንቄዎች፣ ለበዓሉ ታዳሚዎች፣ ለአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች፣ ለበዓሉ አዘጋጅ ኮሚቴዎች እና ለሰላም ሠራዊት ወጣቶች እንዲሁም ኃላፊነታቸው በብቃትና በትጋት ለተወጡ የፀጥታና ደኅንነት አካላት ምስጋና አቅርቧል፡፡

በአሁኑ ሰዓት በአዲስ አበባ ከበዓሉ ጋር በተያያዘ ተዘግተው የነበሩ መንገዶች የተከፈቱ ሲሆን፤ የተሽከርካሪ እንቅስቃሴዎችም መጀመራቸውን አሐዱ ለማወቅ ችሏል።

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

"የሆራ ፊንፊኔ" የኢሬቻ በዓል በመከበር ላይ ነው

መስከረም 25/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የ2017 ሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል ባህላዊ እሴቱንና ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ በአዲስ አበባ በመከበር ላይ ይገኛል።

በክብረ በዓሉ ላይ አባ ገዳዎች፣ አባ መልካዎች፣ አባ ሙዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎች፣ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ሀላፊዎች እንዲሁም ከተለያዩ የኦሮሚያ ዞኖች የመጡ በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተውበታል።

ኢሬቻ የምስጋና በዓል እንደመሆኑ፤ አባገዳዎች የኢሬፈና ሥነ- ሥርዓት በማካሄድ በዓሉን በይፋ አስጀምረውታል።

የበዓሉ ታዳሚዎችም በተለያዩ ባህላዊ አልባሳት፣ መዋቢያ ጌጦችና ጭፈራዎች ታጅበው በዓሉን በታላቅ በድምቀት በማክበር ላይ ይገኛሉ።

በተጨማሪም የሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል ነገ መስከረም 26 ቀን 2017 በቢሾፍቱ ሆራ ሃርሰዴ ይከበራል።

ኢሬቻ የኦሮሞ ሕዝብ የክረምቱን መጠናቀቅ ተከትሎ ለፈጣሪ ምሥጋና የሚያቀርብበትና መጪው ዘመን መልካም እንዲሆን የሚለምንበት የምስጋና በዓል ነው፡፡

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

መከፋፈል ውስጥ የሚገኙ የህወሓት አመራሮች በቀጣይ ሳምንት ለውይይት እንደሚቀመጡ ተገለጸ

መስከረም 24/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የትግራይ ሲቪል ማህበራት ህብረት በቀጣይ ሳምንት በትግራይ ክልል በውዝግብ ውስጥ የሚገኙት የህወሓት እና የጊዚያዊ አስተዳደር ቡድኖችን ሊያወያይ መሆኑን ገልጿል፡፡

ህብረቱ በፖለቲከኞቹ መካከል ያለውን ልዩነት ለመፍታት በምሁራን ጥናቶች እያቀረበ ዉይይት ሲያደርግ መቆየቱን የገለጹት የህብረቱ ፕሮግራም ማናጀር አቶ በሪሁ ገብረመድህን፤ "ይሁን እንጂ ይህ መፍትሄ ይዞልን ሊመጣ አልቻለም" ብለዋል፡፡

"በዚህም ምክንያት አጀንዳዎችን በጋራ በመቅረፅ፣ በሁለቱም ወገን ያሉ አካላት በማገናኘትና ችግሩን እንዲያቀርቡ በማድረግ ህዝቡ ሳይጎዳ ችግሩን ለመፍታትና ምን መደረግ አለበት የሚለው ጉዳይ ላይ እየሰራን እንገኛለን" ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በዚህም በቀጣይ ሳምንታት ሁለቱንም ወገኖች በማሰባሰብ የውይይት መድረክ ለማዘጋጀት ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን ኃላፊዉ ተናግረዋል፡፡

"በፖለቲከኞቹ መካካል በአቋም ደረጃ ተመሳሳይ ነገር አለ፤ በሌላ በኩል ደግሞ የስልጣን ፍላጎት ይስተዋላል" ያሉት አቶ በሪሁ፤ ይሁን እንጂ ሁለቱም ለሰላም ፍላጎት እንዳላቸው ሲገልጹ መቆየታቸውን አንስተዋል፡፡

ነ"ገር ግን በተግባር እታየ ያለው ሁኔታና በየስብሰባው ያለው ሁኔታ በክልሉ ውጥረት እንዲፈጠር እያደረገ ነው" ሲሉ ለአሐዱ ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል በቅርቡ ቅንርጫፉን በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ የከፈተው የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢህአፓ) በትግራይ ያለውን ፖለቲካዊ ውዝግብ አሳሳቢ መሆኑን ገልጿል፡፡

የፓርቲው የአዲስ አበባ ኮሚቴ አባልና በመቀሌ የተከፈተውን ቅርጫፍ በማደራጀት የታሳተፉት አቶ ይሳቅ ወልዳይ፤ በህወሓት መካከል የተፈጠረው ፖለቲካዊ ውጥረት የፓርቲው ችግር መሆኑን ያነሳሉ፡፡

ይሁን እንጂ በፓርቲው ብቻ የሚቆም ጉዳይ ባለመሆኑ፤ በክልሉ ያለውን ውጥረት ለማርገብ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ማድረግ እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡

ኢህአፓ እንደ ፓርቲ ሁለቱም መካረር ዉስጥ መግባታቸዉ ተገቢ ነው ብሎ እንደማያምን የገለጹ ሲሆን፤ ህዝቡ ያለበት ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

የትግራይ ህዝብ ከዚህ ወዲህ ወደ ጦርነት የሚወስድ ማንኛውንም ሁኔታ እንደማይፈቅድ የገለጹት አቶ ወልዳይ፤ "ሁለቱም አካላት በጠረጴዛ ዙሪያ ንግግር እንዲያደርጉ" ሲሉ ምክረ ሀሳብ ሰጥተዋል፡፡

በተያያዘ ዜና የህወሓትን ህጋዊነትን ለማስመለስ ከፌደራል መንግሥት እና ከአፍሪካ ህብረት ፓነል ጋር የሚወያይ ልዑክ እንደ አዲስ እንደሚደራጅ በህወሓት ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራ ህወሓት በዛሬው ዕለት ገልጿል፡፡

ህወሓት ይሄን ያለው ከመስከረም 20 እስከ 22 /2017 ዓ.ም ለሦስት ቀናት ያካሄደውን የማእከላዊ ኮሚቴ እና የከፍተኛ ካድሬዎች ስብሰባ ማጠቃለሉ በማስመልከት ባወጣው የአቋም መግለጫ ላይ ነው፡፡

በመግለጫውም ውይይቱን የሚያስቀጥል የትግራይ የሰላም ልዑክ አንደ አዲስ እንዲደራጅና በሰው ሃይል እንዲጠናከር እንደሚደረግ አስታውቋል፡፡

በትግራይ ክልል ያለው ፖለቲካ መካረር እየታየበት በመሆኑ ብዙዎች ስጋታቸውን እየገለጹ ሲሆን፤ የፌደራል መንግሥት ጣልቃ ገብነት እንዲኖር ጥሪ እያደረጉ ይገኛል፡፡

በአቤል ደጀኔ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የሁለቱ ምክር ቤቶች 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን መክፈቻ ሥነ- ሥርዓት በመጪው ሰኞ ይካሄዳል

መስከረም 24/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) 6ኛው የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን መክፈቻ ሥነ- ሥርዓት ሰኞ መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚካሄድ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታውቋል።

በኢፌዴሪ ሕገ መንግስቱ አንቀፅ 58 ንዑስ አንቀፅ (2) እና በምክር ቤቱ የአሰራርና የአባላት የሥነ-ምግባር ደንብ ቁጥር 6/2008 አንቀፅ 24 ንዑስ አንቀፅ (1) መሰረት የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአንድ ዓመት ስራ ጊዜ ከመስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት ሰኞ ጀምሮ እስከ ሰኔ 30 ቀን ድረስ መሆኑ ተደንግጓል፡፡

በዚሁ ድንጋጌ መሰረት የ6ኛው ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን የተጠናቀቀ ሲሆን 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓትም የሪፐብሊኩ ፕሬዚዳንት በተገኙበት ሰኞ መስከረም 27 ከቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ እንደሚካሄድ ተጠቁሟል፡፡

በመክፈቻ ሥነ-ስርዓቱ ላይ የሪፐብሊኩ ፕሬዚዳንት ለሁለቱ የፌደራል መንግሥት ምክር ቤቶች (የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት) ዓመታዊ ሥራቸውን መጀመራቸውን በማብሰር የፌደራል መንግሥቱን ዓመታዊ ዕቅድ ያቀርባሉ።

የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችና የዓለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች፣ የሐይማኖት አባቶች፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው ተጋባዥ እንግዶች በሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ እንደሚገኙ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታውቋል፡፡

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

"ህወሓት እያራመደ የሚገኘው ፖለቲካ የትግራይ ሕዝብን የማይመጥን ነው" አረና ፓርቲ

መስከረም 24/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሰው አረና ትግራይ ፓርቲ "በአሁን ሰዓት በትግራይ ክልል እየተስተዋለ የሚገኘው የፖለቲካ አሰላለፍ፣ ክፍፍል እና እንቅስቃሴ የትግራይ ሕዝብን የማይመጥን ነው" ሲል ለአሐዱ ተናግሯል።

ክልሉን እያስተዳደረ በሚገኘው ጊዜያዊ አስተዳደር እና በህወሓት መከከል የተፈጠረው የፖለቲካ ሽኩቻ የስልጣን ፍላጎት የፈጠረው ነው ያሉት የአረና ፖርቲ መስራች አቶ ገብሩ አስራት፤ ህወሓት በ50 ዓመታት የፖለቲካ እንቅስቃሴው መሰረታዊ ለውጥ ማምጣት አለመቻሉን አንስተዋል።

"ከጦርነቱ በኋላም ቢሆን በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት የትግራይን ህዝብ ወደ ቀድሞ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ማንነቱ ለመመለስ አለመቻሉ ያረጀ የፖለቲካ አካሄድ እንደተከተለ ማሳያ ነው" ብለዋል።

አክለውም፤ በህወሓት አመራሮች መካከል የተፈጠረው ክፍፍል እና አለመረጋጋት በሰከነ መልኩ ሊታይ እንደሚገባ ጠቁመው፤ በክፍፍል ውስጥ ያሉት አመራሮች ለትግራይ ሕዝብ መሰረታዊ ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ቅድሚያ እንዲሰጡ መክረዋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም የትግራይ ሕዝብ ችግር የመላው ኢትዮጵያዊ ሕዝብ ችግር መሆኑን አንስተው፤ ተፈናቃዮችን ወደነበሩበት የመመለስ እንዲሁም የወደሙ የመሰረተ ልማትቶችን መልሶ የማቋቋም ጉዳይ ለትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ብቻ የሚተዉ አለመሆኑን ለአሐዱ ገልጸዋል።

በዚህም "የትግራይ ክልል እንዲሁም ለሌሎች በጦርነት የተጎዱ አከባቢዎችን መልሶ ለማቋቋም የማዕከላዊ መንግሥቱ ከሌሎች ክልልሎች በተለየ መልኩ በጀት መመደብ አለበት" ሲሉም ጠቁመዋል።

በፅዮን ይልማ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የጠበቆች ማኅበር 5ኛ የፍትሕ አካል ተደርጎ መቆጠር እንዳለበት ተገለጸ

መስከረም 24/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ከአራቱ የፍትሕ አካላት በተጨማሪ የጠበቆች ማኅበር እንደ 5ኛ አካል መቆጠር እንደሚገባው የፌደራል ጠበቆች ማኅበር አስታውቋል፡፡

የፌደራል ጠበቆች ማኅበር መሪና የአፍሪካ ጠበቆች ምክትል ፕሬዝዳንት ቴዎድሮስ ጌታቸው ለአሐዱ እንደተናሩት፤ ሁሉም ክርክሮች በጠበቃ የሚካሄዱ እንደመሆናቸው ፍትሕን ለማስፈን የጠበቆች ሚና ከፍተኛ ነው፡፡

ባለፉት 2 ዓመታት ጠበቆች የሕግ ጉዳያቸውን በነጻነት እንዳያስኬዱ በአንዳንድ የጸጥታ አካላት እርምጃና የማስፈራራት ሁኔታ የነበረ ሲሆን፤ እነዚህን ችግሮች ተጠያቂ ለማድረግ በቀጣይ ሥራዎች እንደሚሰሩ አቶ ቴዎድሮስ ተናግረዋል።

ከዚህ በፊት አስር የሚሆኑ ጠበቆች በአንዳንድ የጸጥታ አካላት ያለምንም ምክንያት እርምጃ እንደተወሰደባቸው አስታውሰዋል።

የነበሩ ችግሮችን ለመቅረፍ በአፍሪካ ደረጃ የተቋቋመው የጠበቆች ማኅበር መቀመጫውን በአዲስ አበባ በማድረግ ብዙ ሥራዎችን ለመስራት መታቀዱን ገልጸው፤ በዚህም አዳዲስ መመሪያዎችን ተግባራዊ ለማድረግ እንዲሁም በጠበቆች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ተጠያቂነት የሚያደርግ አሰራሮችን ለመተግበር ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ አክለው ተናግረዋል።

የጠበቆች ማኅበር ፍትሕን ከማስፈን አኳያ ከፍተኛውን ድርሻ የሚወጣ መሆኑን አንስተውም፤ ማኀበሩ 5ኛ የፍትሕ አካል መሆን እንዳለበት አብራርተዋል፡፡
የጠበቃ ሥራ አንድኛ የፍትሕ አካል መሆን አለበት የሚል እንቅስቃቄ እየተደረገ እንደሚገኝም አስረድተዋል፡፡

የፌደራል ጠበቆች ማኅበር ከአፍሪካ ሀገራት ከተውጣጡ አባላቱ ጋር ለሦስት ተከታታይ ቀናት ያካሄደ ሲሆን፤ ውይይቱ ማኅበረሰቡ በነጻነት ጠበቆች እንዲመደብላቸውና ጠበቆችም ሐሳባቸውን በነጻነት እንዲራመዱ የታሰበ መሆኑን አቶ ቴዎድሮስ ጨምረው ለአሐዱ ገልጸዋል።

በአለምነው ሹሙ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ግዜ ገደቡ በመጠናቀቁ ጉባኤ ይጠራ ሲሉ ፓርቲዎች ጠየቁ

መስከረም 24/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ግዜ ገደቡ በመጠናቀቁ ጉባኤ ይጠራ ሲሉ ኢህአፓን ጨምሮ አምስት ፓርቲዎች ጠይቀዋል፡፡

ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በደብዳቤ ያሳወቁት ፓርቲዎቹ፤ ቦርዱ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፖርቲዎች የጋራ ም/ቤት አስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠራ በዛሬው ዕለት ባወጡት መግለጫ አሳስበዋል፡፡

ፓርቲዎቹ ምክር ቤቱ የግዜ ገደቡ ቢጠናቀቀም የምክር ቤቱ አመራር በተቃራኒውና የአመራር ዘመኑ ካለፈበት በኋላ ዕድሜውን ወደ ሁለት ዓመት ለማራዘም፤ የጋራ ምክር ቤቱ አባላት የማያውቁትን የማሻሻያ ጥያቄ ለምርጫ ቦርድ ማስገባቱ ተገቢ አይደለም" ሲሉ ገልጸዋል፡፡

አሐዱ በዛሬው ዕለት በተላከለት መግለጫ ኢህአፓ፣ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ)፣ የወላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ፣ ህብር ኢትዮጵያ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር በጋራ የሰጡትን መግለጫ ተመልክቷል፡፡

በኢትዮጵያ የምርጫ ሕግ መሰረት ቦርዱ ባመቻቸው ጉባኤ፤ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፖርቲዎች የጋራ ምክር ቤት መቋቋሙና በተዘጋጀው የአሰራር ሥርዓት ቃል-ኪዳን መሰረት እስካሁን ሲሰራ መቆየቱ በመግለጫው ተጠቅሷል፡፡

"ይሁን እንጂ ይህ ጊዜዉን የጨረሰዉ አመራር በመተዳደሪያ ደንቡ የተጣለበትን ተግባርና ኃላፊነት በአግባቡ ሊወጣ አልቻለም የሚል ቅሬታ ቢቀርብበትም፤ ለማድመጥና ለማሻሻል ፍቃደኛ አይደል" ሲሉ ፓርቲዎቹ ከሰዋል፡፡

አክለውም፤ ግንቦት 21/2016 ዓ.ም አርባ ፖርቲዎች ምክር ቤቱ ጉባኤ ጠርቶ ችግሮች እንዲቀረፉ የቀረበዉ ጥያቄ ተገቢ መልስ ባላገኘበትና ይሄዉ የጋራ ምክር ቤት ወቅቱን የጠበቀ ስብሰባ አድርጎ ሪፖርት ሳይቀርብና ምርጫም ሳይደረግ የአመራር ዘመኑ መጠናቀቁ በግልጽ የሚታወቅ ነው" ብለዋል፡፡

ከላይ ጥያቄ ያቀረቡትን ፖርቲዎች ተንተርሶ፤ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ጉባኤ እንዲጠራ ለጋራ ምክር ቤቱ ደብዳቤ ቢጽፍም ባለመፈጸሙ ስብሰባወ አልተደረገም ሲል ቅሬታውን መግለጹንም አመላክተዋል፡፡

ስለዚህም፤ "ምርጫ ቦርድ ይህንን ሕገ ወጥና በፖርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አሰራርና በፓርቲዎች መካከል ያለው የጋራ ጉዳያቸውን በመተማመን መንፈስ የማስፈፀም ፍላጎት የሚጎዳ ተግባርና አካሄድ ጣልቃ በመግባት ማስቆም አለበት" ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

የጋራ ምክር ቤቱ አመራር የሥራ ዘመኑ ከተጠናቀቀ ከወር በላይ ያለፈው በመሆኑ ስብሰባ መጥራት እንደማይችል ታዉቆ ቦርዱ የጋራ ምክር ቤቱን አባል ፖርቲዎች በአስቸኳይ ስብሰባ በመጥራት ለቀጣይ አመራር ምርጫና አጀንዳ ቀረጻ ሁኔታዎችን እንዲያመቻች ሲሉም ፓርቲዎቹ በመግለጫቸው አስታውቀዋል፡፡

ይህንን የፓርቲዎች ቅሬታ በተመለከተ የኢትጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤትን ምላሽ በቀጣይ የምናካትት ይሆናል፡፡

በአቤል ደጀኔ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

ህወሓት 12 የእነ ጌታቸው ረዳ ቡድን አባላትን በማንሳት 13 ሌሎች አመራሮችን ተክቻለሁ አለ

መስከረም 27/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በእነ ዶ/ር ደብረፅዮን የሚመራው የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ቡድን በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ ውስጥ የአመራር ማሻሻያ እንዲደረግ መወሰኑን አስታውቋል፡፡

ህወሓት ዛሬ ባወጣው መግለጫ የውስጥ ችግሮቹን ለመፍታት ከፍተኛ ህዝባዊ ንቅናቄ እያደረገ እንደሚገኝ ያስታወቀ ሲሆን፤ በማዕከላዊ ኮሚቴው ውሳኔ መሰረት በመላው ህዝብ፣ አባላትና በሁሉም ተዋጊ ሃይሎች አካሄዱ እንደ አስፈላጊነቱ እውቅና ያገኘ ህጋዊ እና ዲሞክራሲያዊ ኮንግረስ በማዘጋጀት የድነት መንገድን በመከተል ላይ መሆኑን ገልጿል፡፡

በዚህም መሰረት ከዛሬ መስከረም 27/2017 ዓ.ም ጀምሮ 12 የእነ ጌታቸው ረዳ ቡደን አባላት በጊዚያዊ አስተዳድሩ የነበራቸውን ሹመት በማስነሳት 13 ሌሎች አመራሮችን ተክቻለሁ ብሏል፡፡

ፓርቲው ከአስተዳደራዊ ኃላፊነታቸው የተነሱ ሰዎች ከዚህ ቀን ጀምሮ በተሰጣቸው ኃላፊነት እንዲወጡ ያዘዘ ሲሆን፤ ከዚህ በኋላ ትግራይን መምራት፣ መወሰንና መወከል አይችሉም ሲልም ገልጿል።

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ በተመለከተም፤ ከኃላፊነታቸው ተነስተው እንዴት እና በማን እንደሚተኩ የፌደራል መንግሥት ጋር እየተነጋገረ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡

በዚህም መሰረት በየደረጃው ያለው አስተዳደር፣ የትግራይ የጸጥታ ሃይሎች፣ የፌዴራልና የክልል መንግሥታት፣ አለም አቀፉ ማህበረሰብ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ይህንን ውሳኔ እንዲያውቁት ጠይቋል፡፡

👉በእነ ዶ/ር ደብረፅዮን የሚመራው ህወሓት በመግለጫው፤ ከሃላፊነት አነሳኋቸው ያላቸው እና በቦታቸው የተካቸው አመራሮች ሥም ዝርዝር ከላይ ከዚህ ዜና ጋር ተያይዟል፡፡

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

አዲስ የተመረጡ የምክር ቤት አባላት ቃለ-መሐላ ፈጸሙ

መስከረም 27/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በ6ኛው ዙር ቀሪና እና ድጋሚ ምርጫ ያሸነፉ አዲስ የምክር ቤት አባላት በዛሬው ዕለት በምክር ቤቱ ተገኝተው ቃለ-መሐላ ፈጽመዋል፡፡

አባላቱ በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ አፋር፣ ሶማሌ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች ሰኔ 16 ቀን 2016 ዓ.ም በተካሄደው ምርጫ የተመረጡ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

አባላቱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ታገሰ ጫፎና የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) በተገኙበት ነው ቃለ-መሐላ የፈጸሙት፡፡

በዕለቱ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ቴዎድሮስ ምህረት ቃለ-መሐላውን እንዳስፈጸሙ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

በተያያዘ ዜና 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመናቸውን ዛሬ ከሰዓት ከቀኑ 8 ሰዓት በሚያካሂዱት የጋራ ስብሰባ ይጀምራሉ።

በመክፈቻ ሥነ-ሥርዓቱ ላይም የሪፐብሊኩ ፕሬዚደንት ለሁለቱ የፌዴራል መንግሥት ምክር ቤቶች ዓመታዊ ሥራቸውን መጀመራቸውን በማብሰር የፌዴራል መንግሥቱን ዓመታዊ ዕቅድ ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የቆይታ ጊዜ ሊጠናቀቅ ከአምስት ወራት ያነሰ ጊዜ እንደሚቀረዉ ተገለጸ

መስከረም 27/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በአዋጁ መሠረት ለሦስት ዓመት የሥራ ጊዜ የተቋቋመዉ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የተሰጠጠዉ ጊዜ ሊጠናቀቅ አምስት ወራት ያልሟላ ጊዜ እንደሚቀረዉ ተገልጿል፡፡

በማቋቋሚያ አዋጁ ላይ ተደንግጎ እንዳለዉ ተጠሪነቱ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሆነዉ ኮሚሽኑ፤ ምክር ቤቱ ጊዜዉ የሚያራዝምለት ከሆነ እንደሚቀጥል የኮሚሽኑ ቃል አቀባይ አቶ ጥበቡ ታደሠ ለአሐዱ ተናግረዋል።

በዚህም ከተሰጠዉ ሦስት ዓመታት ዉስጥ የቀረዉ ጊዜ ከአምስት ወራት እንደማይበልጥ የገለጹ ሲሆን፤ በዚህም መሠረት በቀሩት ወራት ያልተጠናቀቁ ሥራዎችን ለማጠናቀቅ እየተሰራ እንደሚገኝ አስረድተዋል።

በቀሩት ወራት ተሳታፊ ተለይቶ በተጠናቀቀባቸዉ ክልሎች ላይ አጀንዳ የማሰባሰብ ሂደቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የገለጹት የኮሚሽኑ ቃል አቀባይ፤ ባሉት ጊዜ ዉስጥ በአማራና ትግራይ ክልሎች ሁኔታዎች አመቺ ሲሆኑ በፍጥነት ወደ ሥራ ለመግባት እየተሰራ መሆኑንም አንስተዋል።

"ጊዜዉ ከተጠናቀቀ በኃላ የሚመለከተዉ አካል የሚያራዝምለት ከሆነ ሥራዉ ይቀጥላል" ሲሉም ተናግረዋል፡፡

አሐዱም ለመሆኑ ሦስት ዓመታት ገዳማን የቆየዉ ኮሚሽኑ የቆይታዉ ጊዜ የሚራዘምለት ከሆነ የበጀቱ ሁኔታ በምን መልኩ ነዉ የሚቀጥለዉ? ብሎ ላነሳንላቸዉ ጥያቄ ቃል አቀባዩ ተከታዩን ሀሳብ ሰጥተዋል።

የበጀት ምንጩ ሁለት መሆኑን ያነሱት አቶ ጥበቡ፤ ከህዝብ የሚገኝን ገንዘብ በመንግሥት የሚመድበዉ ሲሆን ሁለተኛዉ ደግሞ ዓለም አቀፍ ተቋማት የሚገኝ በመሆኑ አስረድተዋል፡፡ "በዚህም መሰረት ኮሚሽኑ የሥራ ዘመኑ የሚራዘም ከሆነ ተያይዞ የሚነሳ ይሆናል" ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ የተፈጠረዉ ፖለቲካዊ ችግር በምርጫ ብቻ የሚፈታ እንዳልሆነ በመታመኑ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቀቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1265/2014 ሆኖ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸድቋ መቋቋሙ የሚታወስ ነዉ።

በአቤል ደጀኔ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በአዲስ አበባ በኮሊደር ልማት ምክንያት 8 የሚሆኑ ማደያዎች መፍረሳቸው ተገለጸ

👉ማደያዎቹ 13 ነጥብ 66 ሚሊዮን ሊትር ያስጠቅሙ ነበር ተብሏል


መስከረም 27/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በአዲስ አበባ በኮሊደር ልማት ምክንያት 8 የሚሆኑ የነዳጅ ማደያዎች መፍረሳቸውን የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሳህረላ አብዱላሂ ለአሐዱ እንደገለጹት፤ ማደያዎቹ በቀን 1500 የሚሆኑ መኪናዎችን ያስተናግዱ የነበረ ሲሆን፤ 13 ነጥብ 66ሚሊዮን ሊትር ለተጠቃሚው ማህበረሰብ አገልግሎት ሲሰጡ እንደነበር ተናግረዋል፡፡

የፈረሱት ማደያዎች 4 ኪሎ፣ ቦሌ ብራስ፣ ሜክሲኮ፣ ካሳችስ እንዲሁም መገናኛ አካባቢ ይገኙ የነበረ ሲሆን፤ በዋናነት ግን 4ኪሎ አካባቢ የሚገኙ 5 ማደያዎች ሙሉ በሙሉ መፍረሳቸውን ገልጸዋል፡፡

እነዚህ የፈረሱ ማደያዎች የኮሊደር ልማቱ እንደተጠናቀቀ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምሩም አንስተዋል፡፡

በዚህም መሰረት የኮሊደር ልማቱ ሲጠናቀቅ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ አገልግሎት የሚሰጡበት አግባብ እንደሚኖር ያነሱት ዋና ዳይሬክተሯ፤ ማደያዎቹን ወደ ሥራ ለመመለስ በሂደት ላይ መሆናቸውን ለአሐዱ አስረድተዋል፡፡

ለልማት ተነሽ የሆኑ ማደያዎችን በተመለከተ ለቀጠይ የአኗኗር ዘይቤን የሚመጥንና ደረጃቸውን የጠበቀ የሚሆን ሥራ እንደሚሰራና ፈርሰው የሚቀሩ ሳይሆን መልሰዉ የሚቋቋሙበት ሁኔታ እንደሚፈጠርም ወ/ሮ ሳህረላ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

በአለምነው ሹሙ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ዩትዩብ፦http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

መልካም ቀን!
አሐዱ ሬድዮ 94.3  የኢትዮጵያውያን ድምፅ!

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

"የመሬት መንቀጥቀጡ በአዋሽ ፈንታሌ ተራራ አካባቢ የተከሰተ ነው" ዶክተር ኤልያስ ሌዊ

👉 በሬክተር ስኬል 4.9 ተዝግቧል


መስከረም 26/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በአዲስ አበባ ያጋጠመው የመሬት መንቀጥቀጥ የተከሰተው በአዲስ አበባ ሳይሆን በአዋሽ ፈንታሌ ተራራ አካባቢ መሆኑን የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጂኦ ፊዚክስና ስፔስ ሳይንስ ተቋም አስታውቋል።

ዛሬ መስከረም 26/2017 ዓ.ም ከምሽቱ 2:00 ሰዓት አካባቢ በአዲስ አበባ እና አካባቢዋ ላይ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት በከተማዋ በርካታ አካባቢዎች ላይ መስተዋሉ እየተነገረ ይገኛል።

መንቀጥቀጡም በአዲስ አበባ ሳይሆን ፈንታሌ ከሚባል ተራራ መተሃራ አካባቢ የተከሰተ ሲሆን፤ በሬክተር ስኬል መለኪያ 4.9 ሆኖ መመዝገቡን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦ ፊዚክስና ስፔስ ሳይንስ ዳይሬክተር ዶክተር ኤልያስ ሌዊ ለኢቢሲ ተናግረዋል

ንዝረቱ መሬት ለመሬት ተጉዞ በአዲስ አበባ በተለይ ሰሜን እና ሰሜን ምስራቅ አካባቢዎች መሰማቱን የገለጹም ሲሆን፤ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ጉዳት የማድረስ አቅሙ ዝቅተኛ መሆኑን ተናግረዋል።

ይህ መተሃራ አካባቢ የተነሳው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት አዲስ አባባን ጨምሮ በድሬደዋ፣ በደሴ፣ በሸዋሮቢት፣ በደብረብርሃን፣ በኮምቦልቻ፣ በአዳማ፣ በደብረዘይት እንዲሁም በሌሎች የሀገሪቷ የክልል ከተሞች እና አካባቢዎች ላይም መስተዋሉ ተነግሯል።

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የጤና ሚኒስቴር በሕክምና ስህተት የሚከሰቱ ችግሮችን መፍታት የሚያስችል አዲስ መመርያ ይፋ ማድረጉ ተሰማ

መስከረም 25/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ እየተደጋገመ ያለው በሕክምና ስህተት የሚከሰተውን የሰዎች ሞት ለማሻሻል፤ አዲስ መመርያ ተግባራዊ ሊያደርግ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር ተናግሯል።

መመርያው በሕሙማንና ሐኪሞች መካከል የሚከሰቱት አለመግባባቶችን ለመፍታት ያለመ መሆኑን ከሚኒስቴሩ ሰምተናል።

መረጃውን ለአሐዱ የተናገሩት በጤና ሚኒስቴር የህሙማን ክትትል አስተባባሪ አቶ እዮቤድ ካሊብ ናቸው።

"በሕክምና ስህተት የሚከሰቱ ችግሮችን አስመልክቶ ተደጋጋሚ ቅሬታዎች መሰማታቸው የተለመደ እየሆነ መጥቷል" ያሉት አቶ እዮቤድ፤ ይህንን ችግር ለመፍታት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ በመሆን መመርያውን ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን አስረድተዋል።

በዘርፉ በተደረገ የዳሰሳ ጥናት መሰረትም፤ በኢትዮጵያ ችግሩ እየከፋ መምጣቱን ነግረውናል።

በአለም የጤና ድርጅት መስፈርት መሰረት በኢትዮጵያ ያለው የሕክምና አሰጣጥ ስርዓት በርካታ ክፍተቶች ያሉበትና አስቸኳይ መፍትሔ የሚያስፈልገው ጉዳይ መሆኑ ሲገለጽ ቆይቷል።

በመሆኑም ክፍተቶቹን ለመሙላት የሚያስችል መፍትሔ ሳያገኝ በዚሁ ከቀጠለ፤ የሚያደርሰው ችግር ከፍተኛ በመሆኑ መመርያውን ማውጣት አስፈላጊ ሆኗል ተብሏል።

ይህንን ክፍተት ለመድፈንና በጤናው ዘርፉ ያለው ተአማኒነት ለመጨመርም በጤና ሚኒስቴር በኩል መመርያው መዘጋጀቱ ነው የተገለጸው።

በሰነዱ ላይ ከሰፈሩት መመርያዎች መካከል "ሕሙማን ላይ ይደርሳል" የተባለውን እንግልት የማስቀርና የሕክምና አሰጣጥ ደረጃውን ለማሻሻል ይረዳል የተባለለት መመሪያ መካተቱን አቶ እዮቤድ ጨምረው ነግረውናል።

በቀጣይም በኢትዮጵያ ያለው የጤና ዘርፍ ክፍተት ለማሻሻል የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን እንዲያደርጉ ተጠይቋል።

ችግሩን ለማሻሻልም ከአለም የጤና ድርጅት የተሰጡ ምክረ ሐሳቦችን ለመተግበርና በጤናው ዘርፍ ፈጣን ለውጥ ለማምጣት እየተሰራ እንደሚገኝ ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በአማኑኤል ክንደያ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የደቡብ አፍሪካ ሕገ-መንግሥታዊ ፍርድ ቤት በፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎዛ ላይ ክስ ሊመሰርት መሆኑን ተሰማ

መስከረም 25/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የደቡብ አፍሪካ ሕገ-መንግሥታዊ ፍርድ ቤት የአገሪቱን ሐብት ለግል ጥቅማቸው አውለዋል በማለት በፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎዛ ክስ ላይ ሊመሰርትባቸው መሆኑ ተሰምቷል።

ራማፎዛ ፓርቲያቸው በፓርላማው ላይ ያለውን አብላጫ ድምጽ በመጠቀም ወንጀሉን እያድበሰበሱት ይገኛሉ ሲሉ ባላንጣዎቻቸው ተቃውሞ እያሰሙ እንደሚገኙም ነው የተገለጸው።

ገዢው ኤኤንሲ ፓርቲ ደቡብ አፍሪካን ለማስተዳደር ከሌሎች ዘጠኝ ፓርቲዎች ጋር መድብለ ፓርቲ መስርቶ በማስተዳደር ላይ እንደሚገኝ አፍሪካ ኒውስ ዘግቧል።

ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎዛ በፈረንጆቹ 2018 በተመሳሳይ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ከስልጣን የተነሱትን ጃኮብ ዙማ ተክተው ወደ ስልጣን መምጣታቸው ይታወሳል፡፡

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

አቶ ዘሪሁን ተሾመ የደህንነት ቢሮ ሀላፊው አማካሪ ሆነው መሾማቸው ተሰማ

መስከረም 25/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) መንግሥትን በመተቸት የሚታወቁት የፖለቲካ ተንታኙ እና የቀድሞው የዛሚ ኤፍ ኤም ሬድዮ ጣብያ ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘሪሁን ተሾመ የመንግሥት ሹመት ማግኘታቸው ተሰምቷል።

አቶ ዘሪሁን የደህንነት ቢሮ ሀላፊ የሆኑት የአቶ ሬድዋን ሁሴን አማካሪ ሆነው ከጥቂት ወራት በፊት ሹመት እንደተሰጣቸው መሠረት ሚድያ አረጋግጫለሁ ሲል ዘግቧል። 

የዛሬ ሰባት ዓመት ገደማ የአሁኑ መንግሥት ስልጣን በያዘበት ወቅት የሰላ ትችት በመሰንዘር የሚታወቁት እና የጋዜጠኛ ሚሚ ስብሀቱ ባለቤት የሆኑት አቶ ዘሪሁን ለቀድሞው የኢህአዴግ ባለስልጣናት እና ለስርዐቱ አራማጆች እጅግ ቅርብ እንደነበሩ ብዙዎች ይናገራሉ።

ለውጥ መጣ የተባለበትን ወቅት "የጎበዝ አለቆች ወጥቶ መግባትን ከባድ ያደረጉበት ግዜ ነው" በማለት በመተቸት የሚታወቁት ግለሰቡ ወቅቱ መደማመጥ የሌለበት ስለሆነ በጥሞና ዝም ለማለት በመፈለጋቸው ከሚድያ እይታ ርቀው እንደነበር ተናግረዉ ነበር። ዛሚ ኤፍ ኤም ከተዘጋ በኋላም አብዛኛ ግዜያቸውን በአሜሪካ እንዳሳለፉ ታውቋል።

አሁን ግን በአዲስ ሹመት መንግስትን የተቀላቀሉ ቢሆንም እስከዛሬ ድረስ ሹመቱ በመንግሥት ይፋ አልሆነም፣ ይሁንና ከሰሞኑ በዋልታ ሚድያ ላይ ቀርበው ስለ ወቅታዊው የሶማልያ፣ ግብፅ እና ኢትዮጵያ ውጥረት ትንታኔ ሰጥተዋል።

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ:-www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

እንኳን ለ2017 የኢሬቻ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
Baga Ayyaana Irreechaa bara 2017!


አሐዱ በዓሉ የሰላም፣የፍቅር የደስታ ይሆንላችሁ ዘንድ መልካም ምኞቱን ይገልጻል።

አሐዱ ሬድዮ 94.3  የኢትዮጵያውያን ድምፅ!

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

ከቤንሻንጉል ወደ አዲስ አበባ የሚላኩ የኤች አይ ቪ ቫይረስ ናሙናዎች ዉጤቱ ሳይደርስ እየጠፉ መሆኑ ተገለጸ

መስከረም 24/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የቫይረስ መጠን መለኪያ ማሽን ባለመኖሩ ለምርመራ ወደ አዲስ አበባ የሚመጡ ናሙናዎች ዉጤቱ ሳይደርስ እየጠፋ መሆኑን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታውቋል፡፡

በክልሉ የኤች አይ ቪ ኤድስ በሽታ የቫይረስ መጠን ለማወቅ የሚያስችለው ማሽን ባለመኖሩ፤ ከዚህ በፊት ናሙናዎች ለምርመራ የሚላኩት ወደ ነቀምት እንደነበር ተገልጿል፡፡

ነገር ግን አሁን ላይ ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት ናሙናዎችን መላክ ባለመቻሉ ወደ አዲስ አበባ ለመላክ መገደዱን የክልሉ ጤና ቢሮ ለአሐዱ አስታውቋል፡፡

በቢሮው የዘርፈ ብዙ ምላሽ የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከል እና መቆጣጠር ዳይሬክተር አቶ ታረቀኝ ወዲ፤ ናሙናዎቹ ወደ አዲስ አበባ በሚላኩበት ጊዜ በቶሎ ካለመድረስም ባለፈ የናሙናዉ ዉጤት ባለቤቱ ጋር ሳይደርስ እየጠፉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በዚህም ምክንያት የታካሚዎችን የጤና ሁኔታ በትክልል ለመከታተል አስቸጋሪ እንዳደረገው ገልጸዋል፡፡

ማሽኑን በክልሉ ለማስገባት ተደጋጋሚ ጥያቄዎች ቢቀርብም የተጠቂ መጠኑ ከ 5 ሺሕ ሰዎች በታች በመሆኑ "ማግኘት አትችሉም" እንደተባሉም ነው የተናገሩት፡፡
በክልሉ በ2016 ዓ.ም ብቻ 292 አዳዲስ የኤች አይ ቪ ተጠቂዎች መገኘታቸው ታዉቋል፡፡

በእመቤት ሲሳይ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

ለጾታዊ ጥቃት የፍትሕ ጥያቄ ሽልማት እና ስጦታ መልስ አይሆንም ተባለ

መስከረም 24/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሴቶች ላይ የሚደርስን አካላዊ እና ጾታዊ ጥቃት መኖሪያ ቤት እና ሌሎች ስጦታዎች በመስጠት ሐዘኔታ እና ድጋፍን ማሳየት እየተለመደ መጥቷል ያለው ሴታዊት ጾታዊ ንቅናቄ፤ ድርጊቱ የፍትሕ ስርአቱን የሚያዛባ፣ ጥፋተኞች ተገቢውን ቅጣት እንዳያገኙ የሚያደርግ ነው ብሏል።

የንቅናቄው መስራችና ሥራ አስኪያጅ ዶክተር ስህን ተፈራ ከአሐዱ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ጥቃት ለደረሰባቸው ሴቶች እና ቤተሰቦቻቸው ስጦታ መስጠት በራሱ ችግር ባይሆንም ለተንዛዛ የፍትሕ ስርአት እየዳረገ እንደሚገኝ ነግረውናል።

"የስጦታዎቹ ትልቅነት ጉዳት ያልደረሰባቸው ሴቶችም ጉዳት እንደደረሰባቸው በማስመሰል እንዲዋሹና እንዲያስመስሉ የማድረግ ዕድሉ ከፍ ያለ ነው" ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት እየተበራከተ ለሚገኘው ፆታዊ ጥቃቶች ተጠያቂው ማን ነው? ማኅበረሰብ ወይስ የሕግ መላላት ሲል ከአሐዱ ለቀረበላቸው ጥያቄም "የሕግ አስተዳዳር ዘርፉ ላይም በርካታ ችግሮች አሉ፡፡ የፀጥታ አካላት ስልጠና ማነስ ጥቃት አድራሾችን እስከ መጨረሻው ተከታትለው ለፍርድ እንዳያቀርቡ እንቅፋት ሆኗል" ብለዋል፡፡

ይህም ደግሞ ከበጀት እጥረት እና በቂ መረጃ ተደራጅቶ ካለመምጣት እርስ በርስ የመካሰስ ሁኔታ ቢኖረውን ይህ የሕግ ክፍትት 30 በመቶውን ቢውስድ ነው ሲሉም አክለዋል።

በኢትዮጵያ ለሚፈጠሩ ፆታዊ ጥቃቶች 70 በመቶውን ኃላፊነት የሚወስደው ማኅበረሰቡ ነው የሚሉት ዶክተር ስህን፤ "ማኅበረሰቡ አጥቂዎችን መሸሸጉ ጥቃቶችን መላመዱ ተደማምሮ አሁን ላለንበት ችግር ዳርጎናል" ብለዋል።

በፊት የሰዎች ሞትም ሆነ ፃታዊ ጥቃቶች አስደንጋጭ ነገሮች እንደነበሩም በማንሳት፤ "ይሁን እንጂ አሁን ላይ ማኅበራዊ ሚድያው ይበልጥ እያጋለጠ ተሰምቶ የማይታወቅ ነገሮች እየተሰማ ነው" ሲሉም ተናግረዋል።

አሁን ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን መስማት ምንም የማያስደነግጥ መሆኑን የሚያነሱት የሰብዓዊ መብት ተሟጋቿ ሁሉንም ችግር ሕግ መላላት ነው ብሎ መውሰድ ግን አያስችልም ብለዋል።

በኢትዮጵያ ከ4 ሴቶች ውስጥ አንዷ ከ15 ዓመቷ ጀምሮ ጾታዊ ጥቃት እንደሚያጋጥማት በ2016 ዓ.ም የተካሄደው የስነ- ህዝብና ጤና ዳሰሳ ያመላክታል፡፡

በአቤል ደጀኔ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በአማራ እና በኦሮምያ ክልል ባሉ ግጭቶች የሚሳተፉ አካላት ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ጥሰት እንዳይፈጽሙ ተጠየቀ

መስከረም 24/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የፌደራል እና የክልል መንግሥታት በክልላቸው የሚፈጸመውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ለማስቆም ተግባራዊ እንቅስቃሴ ባለማድረጋቸው የሚፈጸመው ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋና እየተባባሰ መምጣቱን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) አስታወቀ።

ይህም የሰብዓዊ መብት ጥሰት ማኅበረሰቡን ለከፍተኛ ምሬት እና እንግልት እየዳረገው መሆኑን ገልጿል፡፡

ኢሰመጉ "በሕይወት የመኖር መብት ይከበር" በሚል ርዕስ ባወጣው መግለጫ፤ በኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች አሁንም እየቀጠለ ያለው የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች እልባት ሊያገኙ ይገባል ብሏል።

በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ አርሲ ዞን በአስኮ ወረዳ ጢዮ ቀበሌ ጠሎታ ጫፋ ከተማ የጠሎታ ቅ/ገብርኤል ቤተክርስቲያን አገልጋይ ካህናትን ጨምሮ፤ 6 ምዕመናን በታጠቁ አካላት ነሐሴ 07/2016 ዓ.ም. ግድያ መፈጸሙን ጉባኤው አስታውሷል።

በተመሳሳይም በአማራ ክልል ያለው ግጭት አንድ ዓመት ያለፈው እና አሁንም በአሳሳቢ ሁኔታ ተስፋፍቶ የቀጠለ ሲሆን፤ ይህ ግጭትም በስፋት ዜጎች በሚኖሩበት እና በከተሞች አካባቢ የሚካሄድ መሆኑን ገልጿል፡፡

በዚህም ምክንያት "በሁለቱም ወገን በሚደረግ የተኩስ ልውውጥ እንዲሁም በመንግሥት በሚደረጉ የድሮን እና ከባድ መሳሪያ ጥቃት ንጹሃን ዜጎች ላይ ሞት፣ የአካል ጉዳት እና የንብረት ውድመት እና መፈናቀል እያስከተሉ ይገኛሉ" ብሏል፡፡

ስለሆነም በአማራና በኦሮምያ ክልል በግጭቱ ተሳታፊ የሆኑ ሁሉም አካላት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተኩስ ለማቆም በመስማማት ልዩነቶች በሰላማዊ መንገድ የሚፈቱበትን መንገድ እንዲያመቻቹ ጠይቋል፡፡

የፌደራል መንግስቱም በክልሎች ያለውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት በትጥቅ ግጭቱ ተሳታፊ ከሆኑ አካላት ጋር ውይይት የሚያደርግበትን ሁኔታ ሊያመቻች ይገባል ብሏል።

በአማራና በኦሮሚያ ክልል በግጭቱ ተሳታፊ የሆኑ ሁሉም አካላት በማንኛውም ግጭት ሂደት ዓለም አቀፋዊ የሰብዓዊ መብቶችን ጥሰት ከመፈጸም እንዲቆጠቡ፣ የፌደራል መንግስት የዜጎችን በሕይወት የመኖር መብት የማስከበር፣ የማክበር እና የዜጎችን ደህንነት የመጠበቅ ሕገ-መንግስታዊ ግዴታውን ሊወጣ ይገባል ሲልም ኢሰመጉ በመግለጫው አሳስቧል።

በፍርቱና ወልደአብ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

ከተመረመሩ 2 ሺሕ 500 ሴቶች መካከል 7 በመቶዎቹ የጡት ካንሰር እንደተገኘባቸው ተነገረ

መስከረም 24/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ፓዮኔር ዲያግኖስቲክ ማዕከል በፈረንጆቹ ወር ኦክቶበር ማለትም ከመስከረም 21 እስከ ጥቅምት 21 በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ7ኛ ጊዜ የሚከበረውን የጡት ካንሰር ቀን ምክንያት በማድረግ ‹‹ማሞግራፊ›› በተሰኘ የጡት ካንሰር መመርመሪያ ማሽን የምርመራ ዘመቻ መጀመሩን አስታውቋል።

ተቋሙ ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ፤ በፈረንጆቹ የዘመን አቆጣጠር 2023 በተቋሙ ከተመረመሩ 2 ሺሕ 500 ሰዎች መካከል 7 በመቶ የሚሆኑት የጡት ካንሰር እንደተገኘባቸው መረጋገጡን ገልጿል።

ማዕከሉ በሰጠው መግለጫ የቅድመ ካንሰር እና የካንሰር ምርመራ ግንዛቤ ማስጨበጥ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጾ፤ በተጠቀሰው ቀን የጡት ካንሰር ምርመራ ለሚያካሂዱ ሴቶች 50 በመቶ የዋጋ ቅናሽ አደርጋለሁ ብሏል።

የጡት ካንሰር መንስኤ በትክክል ባይታወቅም፤ የሆርሞን ቴራፒ፣ ለጨረር መጋለጥ፣ በዘር ወይም በቤተሰብ ታሪክ ተጠቃሽ ምክንያቶች እንደሆኑ ተነግሯል።

ምርመራውን ለማድረግ በዋነኛነት ማሞግራፊ፣ አልትራሳውንድ ፣ እና ፒኢቲ (PET) የተሰኙት ምርመራዎች የሚታዘዙ ሲሆን፤ አጠራጣሪ ውጤቶች ሲገኙ ናሙና ተወስዶ ምርመራ ይደረግበታል፡፡

ሕክምናውም ቀዶ ጥገና ፣ ኪሞቴራፒ፣ የጨረር ሕክምና፣ የሆርሞን ቴራፒን ጨምሮ በበርካታ አማራጮች ይሰጣል።

በተጨማሪም በሽታውን ቀድሞ ለመከላከልም በየጊዜው ምርመራ ማድረግ፣ ከወሊድ በኋላ ጡት ማጥባት እና የአልኮል መጠጥ መቀነስ እንደሚገባ ተገልጿል፡፡

የጡት ካንሰር ዘግይቶ በመታወቁ ምክንያት በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣት ሴቶችን እና እናቶችን ህይወት በመንጠቅ ላይ እንደሚገኝም ተመላክቷል፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሴቶችን ለሞት ከሚዳርጉ ምክንያቶች መካከል የጡት ካንሰር በቀዳሚነት ተቀምጧል።

በዳግም ተገኝ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

ከዛሬ አርብ እስከ ሰኞ በአዲስ አበባ ከተማ የሞተር ብስክሌት ማሽከርከር ተከለከለ

መስከረም 24/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ለኢሬቻ በዓል አከባበር የመንገድ ትራንስፖርት ደህንነት ሲባል፤ ዛሬ ዕለተ ዓርብ መስከረም 24 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 6:00 እስከ ሰኞ መስከረም 27 ቀን 2017 እስከ ንጋቱ 12:00 ድረስ በአዲስ አበባ ከተማ የሞተር ብስክሌት የትራንስፖርት አገልግሎት መከልከሉ ተገልጿል፡፡

ይህንን ክልከላም የትራንስፖርትና የትራፊክ ተቆጣጣሪዎች እና የትራፊክ ፖሊሶች አፈፃፀሙን ተግባራዊ እንዲያደርጉ ሲል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…
Subscribe to a channel