አሐዱ ራድዮ 94.3 Your source for top local and international news and analysis. "Voice of Ethiopian" የአሐዱ የቴሌግራም ቻናል ቤተሰብ በመሆን ወቅታዊና እውነተኛ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ
"የጸጥታ ኃይሉን ጭምር የከፈለ ልዩነት ነው የተከሰተው" በትግራ ክልል የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች
መስከረም 29/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በትግራይ ክልል ያለው ልዩነት እየሰፋ መጥቶ ከፓርቲዎች ወደጸጥታ ኃይሎች ጭምር በመከፋፈል የዶክተር ደብረፅዮን እና የአቶ ጌታቸው ረዳ የሚል ታማኝ ኃይል አዘጋጅተዋል ሲሉ ፓርቲዎች ገለጹ፡፡
ከአሐዱ ጋር ቆይታ የነበራቸው የአረና ትግራይ ፓርቲ ዋና ሊቀመንበር አቶ አምዶም ገብረስላሴ፤ "የሁለቱም አካሄድ የስልጣን የሚመስሉ አካሄዶች አሉት" ብለዋል፡፡
እንደእርሳቸው ገለፃ፤ "ሁሉም የጸጥታ ኃይሎች በአንድ ዕዝ የመመራት ችግር አለባቸው" ያሉ ሲሆን፤ ይህ ደግሞ የፖለቲካውን ውድቀት የሚያሳይ ነው" ሲሉ ገልጸዋል፡፡
አክለውም በክልሉ መካረር ውስጥ የጸጥታ ኃይሎች እንዲሳተፉ የሚያደርግ እንቅስቃሴ መኖሩን ገልጸው፤ "ከፍተኛ እና መካካለኛ አመራሮች ወደ አንዱ አካል የመወገን ሁኔታ ይታይባቸዋል" ብለዋል፡፡
ይሁን እንጂ የሠራዊቱ አባላት ጦርነት ዉስጥ የቆዩ በመሆኑ ምንም ዓይነት ግጭት ውስጥ የመግባት ፍላጎት የላቸውም ሲሉም ተናግረዋል፡፡
"ለመሆኑ ይህ የመከፋፈል ሁኔታ ዳግም በክልሉ ግጭትን አያስነሳም ወይ?" ሲል አሐዱ ላነሳላቸው ጥያቄ፤ ይህ ሁኔታ ወደ ጦርነት እንደማይገባ ዕምነት እንዳላቸው ገልጸው፤ እንደ ምክንያትም "ፖለቲከኞቹ ወደ ለየለት ሁኔታ ውስጥ ገብተው ስልጣናቸውን የማጣት ፍላጎት የላቸውም" ብለዋል፡፡
የባይቶና አባይ ትግራይ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ዮሴፍ በርሄ በበኩላቸዉ፤ "ሁለቱ ቡድኖች እያደረጉት ያለው ሁኔታ ከስልጣን አልፎ ወደ አካባቢያዊ ሁኔታ ውስጥ እየቀየሩት ይገኛሉ" ብለዋል፡፡
በዚህም "ልዩነቱ ሰፍቶ ወደ ሕዝብ ለማጋባት እየተሰራ ያለው ሁኔታ ተገቢነት የሌለው ነው" ሲሉም አሳስበዋል፡፡
"የጸጥታ ሃይሉ የጊዚያዊ አስተዳደር ሥር የተቋቋመ አንድ ካቢኔ ነው እንጂ የፓርቲ አይደለም" ያሉት አቶ ዮሴፍ፤ "ገለልተኝነት ለማሳየት የሚደረገው ጥረት ተገቢ አይደለም" ብለዋል፡፡
አክለውም፤ "ጸጥታ አስተዳደሩ የጊዚያዊ አስተዳደር የሚመጣን ሥራ የመስራት ሃላፊነት ያለበት በመሆኑ፤ ይህንን ሊያርም ይገባል" ሲሉ አቶ ዮሴፍ ከአሐዱ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል፡፡
ባሳለፍነው ሰኞ መስከረም 27/2017 በዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል የሚመራው ህወሓት ባወጣው መግለጫ፤ ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የሚገኙባቸው 13 የጊዚያዊ አስተዳደሩ የሥራ ሃላፊዎች በማንሳት በሌሎች 14 የድርጅቱ አባላት እንዲተኩ መወሰኑን ማስታወቁ ይታወሳል።
ይህን ተከትሎ የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ባወጣው መግለጫ የህወሓቱ ቡድን በግልፅ "መፈንቅለ ስልጣን እንዲደረግብኝ አውጇል" ያለ ሲሆን፤ "የጥፋት ኃይል" ባለው ቡድን ላይ ሕጋዊ እርምጃ መውሰድ እንደሚጀምር አስታውቋል።
የትግራይ ጸጥታ ኃይል በበኩሉ በህወሓት አመራሮች መከፋፈል ምክንያት ከሁለቱም አካላት የሚወጡ መግለጫዎች በሕዝቡ ውስጥ የመረበሽ ስሜት መፍጠራቸውን ገልጾ፤ "መግለጫዎቹ ምክንያት የሚፈጠር ማንኛውንም አይነት ስርዓት አልበኝነት ተቀባይነት የለውም" ማለቱ ይታወሳል፡፡
በአቤል ደጀኔ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
በመዲናዋ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ4 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ 7 ሰዎች ከባድ ጉዳት ደረሰባቸው
መስከረም 29/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ ከጎሮ ወደ ኮዬ ፈቼ በሚወስደው መንገድ ላይ አርሴማ በተባለ አካባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ፤ የ4 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ 7 ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ፤ ኮድ 3 ታርጋ 69867 ቱርቦ ገለባጭ መኪና በአይሱዙና በከተማ አውቶቢስ ላይ ባስከተለው የመኪና አደጋ የሰዎች ሕይወት ማለፉንና በአካል ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
በአደጋውም የአውቶቢስ ትኬት ለመቁረጥ የቆሙ 3 ሴቶችን እና በአካባቢው ላይ በጉሊት ንግድ የምትተዳደር ነጋዴ ሕይወት ያለፈ ሲሆን፤ ሹፌሩን ጨምሮ ሌሎች በአካባቢው የነበሩ 7 ሰዎች ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል ብለዋል፡፡
ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው 7 ሰዎችም በጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ጨምረው ለአሐዱ አስታውቀዋል፡፡
በዳግም ተገኝ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ:www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
አሐዱ አፋላጊ!
ተፈላጊያችን ሮናልዶ የማነ መሃሪ ይባላል፡፡
ፈላጊ አክስቱ ፋሲካ ሀጂ የእህታቸውን ልጅ እናፋልጋቸው ዘንድ ወደ አሐዱ መጥተዋል፡፡
ተፈላጊ ሮናልዶ የማነ መሃሪ የተወለደው ጅማ አጋሮ ከተማ ነው፡፡ በተወለደ በ4 ዓመቱ እናቱ በመኪና አደጋ ሕይወታቸው በማለፉ እና አባቱ በድንገተኛ ሞት በመለየታቸው ምክንያት ከእናቱ እህት ፋሲካ ሀጂ ጋር ይኖር ነበር፡፡
"ለ4 ዓመታት ካሳደግኩት በኋላ፤ የአባቱ እህት ማለትም ፍሬወይኒ መሃሪ እኔ ላሳደገው ብላ በ1997 የስምንት ዓመት ህፃን እያለ ወሰደችው" ይላሉ አክስቱ ፋሲካ ሐጂ፡፡
"አክስቱ ከወሰደችው ከቀናት በኋላ ስደውል 'ትምህርት ቤት ሄዷል' እያለች ተደጋጋሚ ምክንያት ስትሰጠኝ፤ ከጅማ ወደ አዲስ አበባ መጥቼ ስጠይቃት 'ወደ ትምህርት ቤት ሄዷል' የሚል የውሸት መረጃ ብትሰጠኝም፤ አባቷ ለጉድፈቻ እንደሰጠችው እና ካመጣችው በኋላ ሁለት ቀንም ቤቷ እንዳላሳደረችው ነገሩኝ፡፡
በስተመጨረሻም ከረጅም ጊዜ በኋላ ደግሜ ስጠይቃት ወደ ጣሊያን ሀገር በተሰጠበት አልማዝ አሽኔ ማሳደጊያ ተቋም በኩል ቢሄድም እኔ አላገኘውም ሚል ምላሽ ሰጠችኝ፡፡
ነገር ግን እንደምትገናኝ እና ያለበት ሁኔታ መረጃዎች እንደሚደርሷት ተቋሙን ሄጄ ስጠይቅ ባረጋግጥም፤ ልታገናኘኝ ፈቃደኛ ባለመሆኗ እና ልጁ 18 ዓመት ሞልቶት ከማሳደጊያ ድርጅቱ ጋር ያለው ግንኙነት በመቋረጡ ምክንያት የእህቴን ልጅ አድራሻ በማፈላለግ አግዙኝ" ሲሉ ፈላጉ አክስት ፋሲካ ሀጂ ጠይቀውናል፡፡
በመሆኑም አሐዱ ሬዲዮ በሚደመጥባቸዉ አካባቢዎች ያላችሁ ቤተሰቦቻችን እና የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን ተከታታዮች በሙሉ፤ እንዲሁም የተፈላጊ ቤተሰቦች ወይንም በሌሎች አጋጣሚዎች ተፈላጊ ሮናልዶ የማነ መሃሪን የምታዉቁና ወደ ጣሊያን ሀገር ጉዞ የምታደርጉ፣ የማግኘት እድሉም ያላችሁ ቤተሰቦቻችን ሮናልዶ የማነ መሃሪን በማፈላለግ እና በማገናኘት እንድትተባበሯቸው በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡
ፈላጊ ፋሲካ ሀጂ 09 13 04 82 53
አሐዱም ፈላጊ እና ተፈላጊ ይገናኙ ዘንድ ከወዲሁ መልካም ምኞቱን ይገልፃል፡፡
ዉድ ቤተሰቦቻችን #አሐዱ_አፋላጊ መሰናዷችን አሐዱ ሬዲዮ ማህበራዊ ኃላፊነቱን የሚወጣበት መሰናዶ ሲሆን፤ ወደ ጣቢያችን መጥታችሁ ማመልከት የምትፈልጉ ዘወትር በሥራ ቀናት እስከ 11 ሰዓት ድረስ ሲኤምሲ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አጠገብ በሚገኘው የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ማህበር ሕንፃ 1ኛ ፎቅ ላይ በአካል በመምጣት ማመልከት ትችላላችሁ፡፡
ለዚህ ጉዳይ ምንም አይነት ክፍያ የማንጠይቅ መሆኑን በዚሁ አጋጣሚ ለመግለፅ እንወዳለን፡፡
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
የትግራይ ክልል በምክር ቤቶች ውክልና ማጣቱ የሕዝቡን ችግር ለማመላከት አስቸጋሪ ሆኗል ተባለ
መስከረም 29/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በትላትናው ዕለት የተከፈተው 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የህዝብ ተወካዮችና ፌደሬሽን ምክር ቤት ውስጥ የትግራይ ክልል በማንም አለመወከሉ ይታወቃል፡፡
ይህንንም በተመለከተ ውክልና ያጣው ሕዝብ እስከመቼ በመገለል ይቆያል እና ምን መደረግ አለበት የሚለውን የሕግ ባለሙያዎች ጠይቀናል፡፡
"በትግራይ ክልል ያለው ሁኔታ ባለፉት ዓመታት ያለውን ዕድገት እና ከሌሎች ክልሎች አንፃር ሲታይ ወደ ኃላ መቅረቱ የሚታይ ነው" የሚሉት የሕግ ባለሙያው አቶ አበባው አበበ፤ "ዕዉቅና የተሰነረዘበት ክልል ከድጎማ ከሌሎች ጥቅማጥሞችም ወደ ኃላ እንዲቀር ያደርጋል" ብለዋል፡፡
የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ ምርጫ ለማድረግ የሚል ሀሳብ ቢኖርም፤ በክልሉ አስቻይ ሁኔታ ባለመኖሩ አሁን ያለውን ችግር እንዲከሰት ማድረጉንም ተናግረዋል፡፡
ስምምነቱም "በሁለቱ የህወሓት ሃይሎች የተለያየ ሀሳብን የያዘና በትክክል የትግራይን ህዝብ ጥቅም ያላስከበረ ነው" በሚል ልዩነቶች መኖራቸውን የሚያነሱት የሕግ ባለሙያው፤ ይህም የህብረተሰቡን ችግር የሚያራዝም መሆኑን አንስተዋል፡፡
የትግራይ ሕዝብ ባለፉት ዓመታት ተወካይ አለመኖሩን አስመልክቶም አቶ አበባው ሲያስረዱ፤ "ሕጋዊ ሰውነትን በተመለከተ የፌደራል መንግሥት ዕውቅና የማይሰጥ ከሆነ ምንም መፍትሄ የለውም" ሲሉ ገልጸዋል፡፡
"በሕገ-መንግሥቱ መሰረት በምክር ቤቶች ላይ ውክልና ለመስጠት በቅድሚያ ምርጫ ማከናወን የሚቀደም ነው" የሚሉት ደግሞ ጠበቃና የሕግ ባለሙያ አቶ ታምራት ኪዳነማርያም ናቸው፡፡
ከዚህ ቀደም በትግራይ ክልል ምርጫ መከናወኑን ተከትሎ የተከሰተዉ ጦርነት በርካታ ውድመትን እንዲፈጥር ማድረጉን የገለጹ ሲሆን፤ "ይህ ትዕግስት ማጣት ለአሁኑ ችግር ዳርጓል" ይላሉ፡፡
አሁንም ቢሆን "በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት ምርጫ እንዲካሄድ" የሚል ከተቀመጡ ነጥቦች ዉስጥ የተቀመጠ መሆኑን ያነሱም ሲሆን፤ የስምምነቱ አተገባበር እንደታሰበው ባለመቀጠሉ ምክንያት እስካሁን ምርጫ ማካሄድ አለመቻሉን ገልጸዋል፡፡
በሕገ-መንግሥቱ የተመረጠ አካል ብቻ ምክር ቤት እንደሚገባ የሚያነሱት የሕግ ባለሙያው፤ "ካለው ችግር አንፃር ትግራይን ሊወክል የሚችል አባል በተለየ መንገድ እንዲሳተፍ ሊደረግ ይገባልም" ሲሉም አስረድተዋል፡፡
በትግራይ ክልል በተደረገው ምርጫ ምክንያት በማድረግ በተፈጠረው ጦርነት፤ በሺሕዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ሲሞቱ በርካታ ንብረት መውድሙ የሚታወስ ጉዳይ ነው፡፡
ይህንንም ተከትሎ በ6ተኛው ዙር ሀገር ዓቀፍ ምርጫ በትግራይ ክልል ምርጫ ባለመከናወኑ፤ ላለፉት በርካታ ዓመታት የትግራይ ሕዝብ በፌዴሬሽን ምክር ቤትም ሆነ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምንም ተወካይ ሳይኖረው ቆይቷል፡፡
በአቤል ደጀኔ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
በቤንች ሸኮ ዞን ንፋስ ቀላቅሎ በጣለዉ ከባድ ዝናብ እናትና የ2 ወር ልጅን ጨምሮ የሦስት ሰዎች ሕይወት አለፈ
መስከረም 29/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በቤንች ሸኮ ዞን ደቡብ ቤንች ወረዳ፤ ከበርታ ቀበሌ ልዩ ስፍራዉ ቆንጨልቃ መንደር ትናንት መስከረም 28 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 11 ጀምሮ በጣለዉ ከባድ ዝናብ አማካኝነት ትልቅ ዛፍ በመኖሪያ ቤት ላይ በመዉደቁ፤ አንዲት እናት ከወለደቻት ከሁለት ወር ሕፃን ልጇ ጋር ሕይወታቸዉ ማለፋን የቤንች ሸኮ ዞን ፖሊስ አስታውቋል።
በተመሳሳይ በወረዳው ቂጤ ቀበሌ ልዩ ሥሙ ጋራ መንደር ተብሎ በሚጠራ ሥፍራ ከቀኑ 11:30 ሰዓት አካባቢ ንፋስ ቀላቅሎ በጣለዉ ከባድ ዝናብ ምክንያት ዝናቡን ለመጠለል ዛፍ ሥር የነበረች አንዲት ግለሰብ ዛፋ ወድቆባት ሕይወቷ ማለፏን የቤንች ሸኮ ዞን ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኢንስፔክተር አዳነ አለማየሁ ተናግረዋል።
በአደጋዉ ቡና ለመልቀም የተሰማሩ ሠራተኞች በተሰራላቸዉ ዳስ ዉስጥ እያሉ ዛፍ ወድቆባቸዉ በአንድ ሰዉ ላይ ከባድ ጉዳት እና በሰባት ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን፤ ወደ ሕክምና ተወስደዉ ሕክምና እየተደረገላቸዉ እንደሚገኝም ገልጸዋል።
"ሕብረተሰቡ ዝናብ በሚዘንብበት ወቅት ዛፍ ስር ከመጠለል እንዲቆጠብና አደጋ ሊያስከትሉ የሚችሉ ዛፎችን ከመኖሪያ ቤቶች አካባቢ በመቁረጥ መሰል አደጋዎችን መከላከል ይኖርበታል" ሲሉ ኢንስፔክተር አዳነ መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል።
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ባንኮች ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት ከሚያበረክቱት አስተዋጾ አንጻር የሚፈለገውን ያህል ትኩረት አልተሰጣቸውም ተባለ
መስከረም 28/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ባንኮች ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት የሚያበረክቱት አስተዋጾ አንጻር የሚፈለገውን ያህል ትኩረት እየተሰጣቸው አለመሆኑን የኢትዮጵያ ባንኮች ማህበር ገለጸ።
የማህበሩ ዋና ጸሀፊ አቶ ደምሰው ካሳ "የሀገራችን ባንኮች ማህበራዊ ሀላፊነታቸውን ከመወጣት ባለፍ ለሀገሪቱ ሁለንተናዊ እድገት አስተዋጾ እያበረከቱ ይገኛሉ" ያሉ ሲሆን፤ ነገር ግን መገናኛ ብዙሀንን ጨምሮ በሚመለከታቸው አካላት አስተዋጾ ስለማበርከታቸው እውቅና እየተሰጣቸው አለመሆኑን ለአሐዱ ገልጸዋል፡፡
"ባንኮች ለግብርናና ለግንባታው ዘርፍ እንዲሁም ለአስመጪ እና ላኪ ነጋዴዎችም ጭምር የጀርባ አጥንት ናቸው" ያሉት ዋና ጸሀፊው፤ ኢንዱስትሪን ጨምሮ ከመንግሥት በሚመጣ ሰነድ እና ጥሪ ላይ የላቀ ተሳትፎ እንደሚደርጉ ተናግረዋል፡፡
ነገር ግን ለዚህ አበርክቷቸው ምንም አይነት እውቅና እየተሰጣቸው አለመሆኑን ገልጸው፤ "አልሰሩም ብሎ ከመውቅስ ይልቅ አስቀድሞ ለሰሩት ሥራ እውቅና መስጠት ያስፈልጋል" ሲሉ አሳስበዋል፡፡
"ባንኮች ከአገር ውስጥ ባለፈ ከዓለም አቀፍ ባንኮች ጋር ተወዳዳሪ ለመሆን መዘጋጀት አለባቸው እየተባለ በሚገኝበት በዚህ ወቅት፤ ለሥራቸው እውቅና መስጠትና ማበረታታት ሥራቸውን ይበልጥ አጠንክረው እንዲሰሩ ይረዳቸዋል" ሲሉም አክለዋል፡፡
የሀገሪቱ እድገት እና የባኮች አስተዋጾ ተነጣጥሎ መታየት እንደሌለበት በማንሳትም፤ በሚፈለገው ልክ ለሰሩት ሥራ ትኩረት መስጠጥ ይገባል ብለዋል፡፡
ለቀጣይ ሥራ ባንኮች የሚያበረክቱት አስተዋጾ እንደሀገርም እንደማህበረሰብም መታወቅ እንዳለበት ጨምረው አመላክተዋል፡፡
በኢትዮጵያ ያሉ ባንኮች በ2014 ዓ.ም 32 የደረሱ ሲሆን፤ እነዚህ ባንኮች በመላ ሀገሪቱ ከ8 ሺሕ 900 በላይ ቅርንጫፎች አሏቸው።
አዲሱ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀስላሴ በትናንትናው ዕለት በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ባደረጉት የመጀመሪያ የመክፈቻ ንግግር ላይ፤ የእነዚህ ባንኮች ጠቅላላ የሀብት መጠን 2 ነጥብ 5 ትሪሊየን ብር መድረሱን መናገራቸው ይታወሳል፡፡
በፍቅርተ ቢተው
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
የ12ኛ ክፍል ሬሚዲያል ፕሮግራም ገቢዎች ዉጤት ይፋ ተደረገ
መስከረም 28/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የትምህርት ሚኒስቴር የ2016 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) ፕሮግራም የመቁረጫ ነጥብን ይፋ አድርጓል።
በዚህም መሰረት፡-
1. የተፈጥሮ እና የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ጠቅላላ ውጤት 600 የመግቢያ ውጤት 204
2. የተፈጥሮ እና የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 600 ጠቅላላ ውጤት የመግቢያ ውጤት 192
3. ታዳጊ ክልልና አርብቶ አደር አካባቢ የተፈጥሮና ማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ጠቅላላ ውጤት 600 የመግቢያ ውጤት 192
4. ታዳጊ ክልልና አርብቶ አደር አካባቢ የተፈጥሮና ማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ጠቅላላ ውጤት 600 የመግቢያ ውጤት 186
5. ማህበራዊ ሳይንስ ዓይነስውራን ወንድ ተማሪዎች ጠቅላላ ውጤት 500 የመግቢያ ውጤት 160
6. ማህበራዊ ሳይንስ ዓይነስውራን ሴት ተማሪዎች ጠቅላላ ውጤት 500 የመግቢያ ውጤት 155
7. በፕሪፓራቶሪ ፕሮግራም የተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ጠቅላላ ውጤት 700 የመግቢያ ውጤት 238
8. በፕሪፓራቶሪ ፕሮግራም የተፈጥሮ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ጠቅላላ ውጤት 700 የመግቢያ ውጤት 224 መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡
👉ዝርዝር መረጃዉ ከላይ ተያይዟል!
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ለአርሶ አደሮችና ላኪዎች እውቅና ሊሰጥ መሆኑን አስታወቀ
መስከረም 28/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን "ቡናችን ለብልጽግችን!" በሚል መሪ ቃል ለዚህ ስኬት እንድንበቃ ያስቻሉንን ጀግና አርሶ አደሮች፣ ላኪዎች እና ሌሎች የዘርፉ ተዋንያን ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽዖ እውቅና ልሰጥ ነው ብሏል፡፡
ባለስልጣኑ ይሄን ያስታወቀው በዛሬው ዕለት በዋና መስሪያ ቤቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው።
የእውቅና ከሚሰጣቸው ዘርፎች መካከልም ቡናቸውን በከፍተኛ ጥራት ያመረቱ፣ ቡናቸውን አምርተው በቀጥታ ለውጭ ገበያ ማቅረብ የቻሉ በመጠን ከፍተኛ የሆነ የቡና ምርት ወደ ውጭ የላኩ፣ በከፍተኛ ዋጋ ቡናቸውን ለውጭ ገበያ መሸጥ የቻሉ እንዲሁም በሌሎችም የተለያዩ ዘርፎች ውጤት ያስመዘገቡ አካላት ሽልማት እንደሚበረከትላቸው ተገልጿል።
እንዲሁም በዘንድሮው ዓመት ለየት ባለ ሁኔታ ደግሞ በከፍተኛ መጠን እና በጥሩ ዋጋ መግዛት የቻሉ አገራትም ለሽልማቱ ከታጩት መካከል ይገኙበታል ተብሏል።
በመድረኩ ላይ ከ1000 በላይ የሚሆኑ የቡና ቤተሰቦች እንደሚገኙ ይጠበቃል፡፡
አጋጣሚው አጋርነትና ህብረት ለመፍጠር የሚያግዝ ሲሆን፤ ለንግዱ ህብረተሰብ እና ለመላ ባለድርሻ አካላት የእርስ በእርስ ግንኙነት ማጠናከሪያ መድረክ እንደሚሆንም ነው የተገለጸው።
ኢትዮጵያ ወደ ውጭ ከምትልካቸው የግብርና ምርቶች ውስጥ ቡና በአማካይ ከ25-35 በመቶውን የሚሸፍን ሲሆን፤ ለኢኮኖሚው ቀላል የማይባል የውጭ ምንዛሬን ያስገኛል፡፡
በቡና አምራችነቷ በዓለም በአምስተኛ ደረጃ የምትገኘው ኢትዮጵያ፤ ከሰባት እስከ አስር በመቶ ቡና ለዓለም ገበያ በማቅረብ ትታወቃለች፡፡
ይሁን እንጂ የቡና መገኛ ከመሆኗ እና ከምርቱ ተፈላጊነት አንፃር የተፈለገውን ያህል ለመጠቀም አልቻለችም፡፡
ሆኖም ግን በ2016 በጀት ዓመት 300 ሺሕ ቶን ቡና ተልኮ 1 ነጥብ 43 ቢሊየን ዶላር እንደተገኘበት ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ማስታወቁ አይዘነጋም።
እንዲሁም የባለልዩ ጣዕም ቡናዎች ውድድርም ተካሂዶ፤ አንድ ኪሎግራም ቡና በ103 ሺሕ ብር ተሸጦ ሪከርድ የተሰበረበት ዓመት በመሆኑ ከሌሎች ዓመት የተሻለ እንደሚያደርገው ነው የተገለጸው።
በፍርቱና ወልደአብ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
በትግራይ ክልል 3 ሺሕ 500 የሚሆኑ ነባር የፖሊስ አባላት ያለ ምንም ምክንያት ከሥራ ታግደናል ሲሉ ቅሬታ አቀረቡ
መስከረም 28/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በትግራይ ክልል የሚገኙ 3 ሺሕ 500 የሚሆኑ ነባር የፖሊስ አባላት ያለ ምንም ምክንያት ከሥራ ታግደናል ሲሉ በክልሉ ለሚገኘው የህዝብ እንባ ጠባቂ ቅሬታ ማቅረባቸው ተገልጿል።
በትግራይ ክልል ነባር የፖሊስ አባላት ከሰሜኑ ጦርነት በኃላ ያለ ምንም ምክንያት ከሥራ መታገዳቸውን እና ከ3 ሺሕ 500 ፖሊሶች መካከል 300 የሚሆኑትን ወደ ሥራ እንዲመለሱ መደረጉን የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ትግራይ ክልል ቅርንጫፍ ኃላፊ አቶ ጸሐዬ እንባዬ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
ከሥራ ከታገዱ የፖሊስ አባላት መካከል የተመለሱበት ምክንያት ባይታወቅም፤ ለምን ሁሉም እንዳልተመለሱና ይህ አካሄድ አድሏዊ አሰራር በመሆኑ ቀሪዎቹ ወደ ሥራ እንዲመለሱ የቀረበውን ጥያቄ በመቀበል፤ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ውሳኔ አስተላልፎ ለሚመለከተው አካል ሪፖርት መላኩንም ጨምረው ገልጸዋል።
የፖሊስ አባላቱ "ወደ ሥራችን እንመለስ፣ ጥቅማ ጥቅማችንና ያለፈ የወር ደሞዛችን ይሰጠን" የሚል ቅሬታ ማቅረባቸውን ነው ኃላፊው የተናገሩት።
ከ3 ሺሕ 500 የፖሊስ አባላት ውስጥ 440 የሚሆኑት በአካል በመቅረብ ቅሬታ ያቀረቡ ሲሆን፤ በአጠቃላይ ግን ብዛት እንዳላቸው ገልጸዋል።
ቅሬታውን በተመለከተ በ1 ወር ውስጥ ምላሽ እንዲሰጥበትና ምላሹ አጥጋቢ ካልሆነ፤ ይግባኝ የሚሉበት ሁኔታ እንዲመቻች ለጊዜያዊ አስተዳደሩ ሪፖርት መደረጉንም ኃላፊው ጨምረው ተናግረዋል፡፡
"ነባር የፖሊስ አባላት ከሥራ የሚያስባርራቸው ምክንያት ስላልተገኘ፤ ወደ ሥራቸው መመለስ አለባቸው" የሚል ውሳኔ የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ያስተላለፈ ሲሆን፤ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ምላሽ እስኪሰጡበት እየተጠበቀ ስለመሆኑም ተናግረዋል፡፡
የፖሊስ አባላቱ "በፌደራል መንግሥቱና በህወሓት መካከል በተደረገው ጦርነት አልተሳተፋችሁም" በሚል ከሰኔ 21 ቀን 2013 ዓ.ም በኋላ ከሥራም ከደሞዝም ታግደናል ሲሉ መግለጻቸው መዘገቡ ይታወሳል፡፡
በአለምነው ሹሙ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
በአማራ ክልል ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት ሥራ መስራት አስቸጋሪ ሆኖብኛል ሲል የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታወቀ
መስከረም 28/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በአማራ ክልል ለአስተባባሪ ስልጠና የተሰጠ ቢሆንም፤ በሁሉም ወረዳዎች የልየታ ሥራ ለመስራት ግን የጸጥታው ሁኔታ አስቸጋሪ ሆኖብኛል ሲል የሀገራዊ የምክክር ኮምሽን አስታውቋል፡፡
በክልሉ ያለው የጸጥታ ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መምጣቱን ለአሐዱ የገለጹት የኮምሽኑ ቃል አቀባይ አቶ ጥበቡ ታደሠ፤ በዚህ ምክንያት ሂደቱን በተመሳሳይ ጊዜ ማካሄድ አለመቻሉን ተናግረዋል፡፡
አክለውም፤ በየወረዳው ተሳታፊዎችን የመለየት ሥራ ለመስራት ጥረት ተደርጎ እንደነበር አንስተው፤ "ነገር ግን የኮሚሽኑ ሠራተኞች እና አስተባባሪዎች እንደልብ መንቀሳቀስ ባለመቻላቸው ሂደቱን ማጠናቀቅ አልተቻለም" ብለዋል።
"ዜጎች በግጭትና በሠላም እጦት ውስጥ ሆነው እንዲሁም የደህንነት ስጋት በሚሰማቸው ሁኔታ ላይ ሳሉ የሀገራዊ ምክክር ሂደትን ማሳካት አይቻልም" ያሉት አቶ ጥበቡ፤ "በዚህም ምክንያት በክልሉ ምክክሩን ለማካሄድ በቅድሚያ የዜጎችን ደህንነት ለማስጠበቅ ዘላቂ መፍትሔን በጋራ መፈለግ ይገባል" ብለዋል፡፡
በተመሳሳይ በኦሮሚያ ክልል የተሳታፊዎች ልየታ መካሄዱ የገለጹ ሲሆን፤ በቀጣይ የአጀንዳ የማሰባሰብ ሥራ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡
አሐዱም ለመሆኑ በአሮሚያ ክልል ያለውስ የምክክር ሂደት አልዘገየም ወይ? ሲል ላነሳላቸው ጥያቄ የኮምሽኑ ቃል አቀባይ ተከታዩን ብለዋል፡፡
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዲስ አበባ የጀመረውን የምክክር ሂደት በማስቀጠል አሁን ላይ በአፋር የምክክር ሂደት ያደረገ ሲሆን፤ በቀጣይ በሶማሌ፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ እና የታሳታፊ ልየታ በተደረገባቸው የኦሮሚያ ክልሎች የምክክር ሂደቱ እንደሚከናወን ገልጸዋል፡፡
በአማራ ክልልን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች ለምክክር ሂደቱ ምቹ ሁኔታዎች እንዲፈጠሩ ኮሚሽኑ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር እየመከረ መሆኑንም አቶ ጥበቡ ጨምረው ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአገሪቱ ያሉ አለመግባባቶችና ግጭቶችን በሕዝባዊ ውይይት ለመለየት እና መፍትሔ ለማፈላለግ ከተቋቋመ ሁለት ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን፤ በእነዚህ ሁለት ዓመታት ውስጥ ሥራዎቹን ‘ቅድመ ዝግጅት፣ ዝግጅት እና የምክክር ምዕራፍ’ በሚል ከፋፍሎ እየሠራ ይገኛል፡፡
በአቤል ደጀኔ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
እስራኤል በቤሩት በተፈጸመ የአየር ጥቃት የሄዝቦላህ ከፍተኛ አዛዥን መግደሏን አስታወቀች
👉የእስራኤል እና ሄዝቦላህ ግጭት ከጀመረ ዛሬ አንድ ዓመት ሞልቶታል
መስከረም 28/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የእስራኤል ጦር በቤሩት በተፈጸመ የአየር ጥቃት የሄዝቦላህ የበጀት እና ሎጂስቲክ ክፍል ሃላፊ የሆኑትን ሱሄል ሁሴኒን መግደሉን አስታውቋል፡፡
የእስራኤል ጦር በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ፤ ሁሴኒ ከኢራን የሚላኩ ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎችን ለሄዝቦላህ የተለያዩ ወታደራዊ ክፍሎች የማከፋፈል ሃላፊነት ነበራቸው ያለ ሲሆን፤ የሄዝቦላህ ወታደራዊ ምክርቤት አባል እንደነበሩም አመላክቷል።
የእስራኤል ጦር ሄሁሴኒ በቤሩት ተገድለዋል በማለት ያወጣውን መረጃ አስመልክቶ እስካሁን ሄዝቦላህ ያለው ነገር የለም፡፡
በሌላ በኩል የሄዝቦላህ ቡድን ትናንት ምሽት በእስራኤል የስለላ ድርጅት (ሞሳድ) ዋና ቢሮ አቅራቢያ ለተፈጸመው የሮኬት ጥቃት ሃላፊነቱን እወስዳለሁ ማለቱን ዩሮ ኒውስ ዘግቧል።
ከፍተኛ ውድመት እያስከተለ የሚገኘው እስራኤል እና የሄዝቦላህ ግጭት ከጀመረ ዛሬ መስከረም 28 አንድ ዓመት ሆኖታል።
ግጭቱ ሄዝቦላህ ለፍልስጤማውያን አጋርነቱን በማሳየት ወደ እስራኤል መተኮሱን ተከትሎ የተጀመረ ሲሆን፤ ግጭቱ ወደ ጦርነት አድጎ በተለያዩ የሊባኖስ አካባቢዎች እየተቀጣጠለ ይገኛል።
እስራኤል በጋዛ ሰርጥ እና ሊባኖስ የቀጠለውን ጦርነት መነሻ በማድረግ፤ እ.ኤ.አ በጥቅምት 7/2023 በሃማስ የተፈፀመውን የጅምላ ግድያ እና አፈና ሰለባዎችን የማስታወስ ሥነ-ስርዓት አድርጋለች።
ከጥቅምት 7 ጀምሮ እስራኤል በጋዛ ላይ ባካሄደችው ጥቃት ወደ 42 ሺሕ የሚጠጉ ሰዎች መገደላቸውን፤ በሃማስ የሚመራው ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
በ19ኛው ክፍለ ዘመን በእንግሊዝ ወታደሮች የተዘረፈ ያጌጠ ጥንታዊ የኢትዮጵያ ጋሻ ወደ ሀገር ቤት ሊመለስ መሆኑ ተገለጸ
መስከረም 28/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የመቅደላ ጦርነትን ተከትሎ በ19ኛው ክፍለ ዘመን በእንግሊዝ ወታደሮች የተዘረፈ ያጌጠ ጥንታዊ የኢትዮጵያ ጋሻ፤ በቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ የልጅ ልጅ ልዑል ኤርሚያስ ሳህለ-ሥላሴ ኃይለ ሥላሴ ተገዝቶ ወደ ሀገር ቤት ሊመለስ መሆኑ ተሰምቷል፡፡
ጋሻው ከግል ስብስብ ውስጥ ተወስዶ በፈረንጆቹ የካቲት ወር በዩናይትድ ኪንግደም የጨረታ ቤት ለሽያጭ የቀረበ ሲሆን፤ ልዑል ኤርሚያስ ጋሻውን በመግዛት ወደ አገር ቤት እንዲመለስ የተሳካ ንግግር ማድረጋቸው ተገልጿል፡፡
ጥንታዊ ጋሻውን የኢትዮጵያን ዘውድ ትዉፊትና ታሪክ ለማስቀጠል፣ የኢትዮጵያዊያንን ባህል ለማስታዋወቅና የኢትዮጵያንም ሕዝብ በትምህርትና በኢኮኖሚ ለማበልጸግ በተቋቋመው፤ የኢትዮጵያ ንጉሣዊ በጎ አድራጎት ባለ አደራ ድርጅት (Royal Ethiopian Trust) በኩል ወደ ሀገር ለማስመለስ እንደሚሰራም ተመላክቷል፡፡
"ይህ ጋሻ ታሪካዊ ቅርስ ብቻ አይደለም፡፡ የኢትዮጵያ ታሪክ እና የጽናት ምልክት ነው" ያሉት ልዑል ኤርሚያስ፤ "ይህንን ውድ ሀብት ለማግኘት ያደረግነው ጥረት እና ስኬት ቅርሶቻችንን ለመጠበቅ እና ለሀገራችን ሉዓላዊነት የታገሉትን ቅድመ አያቶቻችንን ለማክበር ያለንን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው።" ማለታቸውን ዘ ቮይስ ዘግቧል፡፡
የመቅደላ ጦርነትን ተከትሎ በብሪታንያ ወታደሮች ከተያዙት በርካታ ቅርሶች መካከል አንዱ የሆነው ይህ ጋሻ፤ እጅግ በጣም ጥሩ ባህላዊ እሴት ያለው ሲሆን፤ ለጨረታ ከቀረበበት የአንደርሰን እና ጋርላንድ የጨረታ ቤት ጋር በተደረገ ድርድር ወደ አገር ቤት እንዲመለስ መወሰኑ ተነግሯል፡፡
ጋሻው ወደ ኢትዮጵያ ከመመለሱ በፊት ወደ ቶሌዶ ኦሃዮ እንደሚወሰድ የተነገረ ሲሆን፤ እስከ ጥቅምት 17 ድረስ በቶሌዶ የስነ ጥበብ ሙዚየም እንደሚታይ ተገልጿል፡፡
ጋሻው የመጨረሻውን ጉዞውን በህዳር ወር የሚያደርግ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም ውስጥ ተቀምጦ ከተለያዩ የአለም ሀገራት ለሚመጡ ኢትዮጵያውያን እና ጎብኚዎች ለእይታ እንደሚቀርብም ተነግሯል።
አንደርሰን እና ጋርላንድ የጨረታ ቤት የ19 ኛው ክፍለ ዘመኑን የኢትዮጵያ ጋሻ ለጨረታ ባቀረበበት ወቅት በድረ-ገጹ ላይ ከ800 እስከ1,200 የእንግሊዝ ዩሮ ይሸጣል ብሎ ነበር፡፡ ጨረታውም በፈረንጆቹ የካቲት 29 ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ ሊካሄድ ታቅዶ የነበረ ቢሆንም፣ የጨረታው ቤት ግን እቃው መነሳቱን አረጋግጧል።
እ.አ.አ በ1868 የተካሄደው የመቅደላ ጦርነት በኢትዮጵያና በእንግሊዝ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ክስተት እንደነበር ይታወቃል።
የእንግሊዝ ጦር የዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ ተራራ ምሽግ የሆነውን መቅደላን ከተያዙ በኋላ የንጉሠ ነገሥቱን ዘውድ፣ የሥርዓት መስቀሎች፣ ጽዋዎችና የጦር መሣሪያዎችን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ ቅርሶችን ዘርፈዋል።
ዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ እ.አ.አ በ1818 እና 1868 በንጉሠ ነገሥትነት የነገሡ ሲሆን፤ ጋሻው የሟቹ ንጉሠ ነገሥት ሊሆን ይችላል ተብሎም ተገምቷል፡፡
እንዲሁም ኤክስፐርቶች እቃው በእርግጥም የመቅደላ ዕቃ እንደሆነ እና ከፍተኛ ጥራት ያለው ጋሻ መሆኑን ያረጋገጡ ሲሆን፤ "በጣም በሚያምር ሁኔታ የተመረተው ይህ ጋሻ በራሳቸው የአጼ ቴዎድሮስ ንብረት ካልሆነም ደግሞ የቅርብ ሰው ነው” ብለዋል።
በእዮብ ውብነህ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡-https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
በሊባኖስ የነበሩ 51 ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው ተመለሱ
መስከረም 28/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በሊባኖስ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 51 ኢትዮጵያውያን በዛሬው ዕለት በሁለት በረራዎች ወደ አገራቸው ተመልሰዋል።
ተመላሾቹ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ሴቶች እና ማኀበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር እና ከኢትዮጵያ አደጋ ሥጋት አመራር ኮሚሽን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው፤ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ከዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ ሥራዎች ቀዳሚ ትኩረቱን በሊባኖስ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን በማድረግ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
"ከሊባኖስ ዛሬ የተመለሱት ዜጎቻችንም አንዱ የተግባር የእንቅስቃሴው መገለጫ ነው" ብለዋል።
በቀጣይም ሌሎች ለችግር ተጋላጭ የሆኑ ዜጎቻችንን ወደ አገራቸው ለመመለስ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር እየተሠራ መሆኑን መናገራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
"በመግለጫዎቹ ምክንያት የሚፈጠር ማንኛውንም አይነት ስርዓት አልበኝነት ተቀባይነት የለውም" የትግራይ ጸጥታ ሃይል
መስከረም 28/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በተጻራሪ መግለጫዎች ምክንያት በትግራይ ክልል የሚፈጠር ማንኛውንም አይነት ስርዓት አልበኝነት እና የጸጥታ ችግር ተቀባይነት አይኖረውም ሲል የትግራይ ጸጥታ ሃይል አስታወቀ።
የጸጥታ ሃይሉ ትናንት መስከረም 27 ቀን 2017 ማምሻውን ባወጣው አጭር መግለጫ፤ በህወሓት አመራሮች መከፋፈል ምክንያት ከሁለቱም አካላት የሚወጡ መግለጫዎች በህዝቡ ውስጥ የመረበሽ ስሜት መፍጠራቸውን ገልጿል።
በዚህም ምክንያት የትግራይን ሰላምና ጸጥታ ለማረጋገጥ፤ በመግለጫዎቹ ምክንያት የሚፈጠር ማንኛውንም አይነት ስርዓት አልበኝነት እና የጸጥታ ችግር አይፈቅዱም ብሏል።
በትናንትናው ዕለት በዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል የሚመራው ህወሓት፤ ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የሚገኙባቸው 13 የጊዚያዊ አስተዳደሩ የሥራ ሃላፊዎች በማንሳት በሌሎች 14 የድርጅቱ አባላት እንዲተኩ መወሰኑን ባወጣው መግለጫ ማስታወቁ ይታወሳል።
ይህን ተከትሎ የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ባወጣው መግለጫ የህወሓቱ ቡድን በግልፅ "መፈንቅለ ስልጣን እንዲደረግብኝ አውጇል" ያለ ሲሆን፤ "የጥፋት ኃይል" ባለው ቡድንከ ላይ ሕጋዊ እርምጃ መውሰድ እንደሚጀምር አስታውቋል።
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
"በደብረጽዮን የሚመራውን አመራር ላይ ሕጋዊ እርምጃ መውሰድ እጀምራለው" የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር
መስከረም 27/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር "የጥፋት ሃይል" ባለውና በዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል በሚመራውን አመራር ላይ ሕጋዊ እርምጃ መውሰድ እንደሚጀምር አስታውቋል።
በህወሓት አመራር ውስጥ የተፈጠረውን ክፍፍል ተከትሎ አንድ ቡድን ሕገወጥ ስብሰባ አድርጓል ያለው መግለጫው፤ "ከዚህ ሕገ ወጥ ስብሰባ በኋላ ይህ ሃይል በትግራይ ሕግና ስርዓት እየጣሰ ነው" ብሏል።
"ይህ ሃይል የትግራይን ህዝብ አንድነት በማደፍረስ ላይ ይገኛል" ሲልም የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር በመግለጫው ከሷል።
አክሎም "ቡድኑ በትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር አመራርና በትግራይ ሰራዊት ላይ ያላሰለሰ የሥም ማጥፋት ዘመቻ እና ውንጀላ እያካሄደ ነው" ብሏል።
አንድ ጊዜ “ሠራዊቱ ከእኛ ጋር ነው” በሌላ ጊዜ ደግሞ “ከፌዴራል መንግሥት ጋር ተስማምተናል” በማለት ህዝብ እያሳሳተ ይገኛል ሲልም ገልጿል።
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በዚህ የጥፋት ሃይል አመራር ላይ ሕጋዊ እርምጃ መውሰድ ይጀምራል ሲል በመግለጫው አስታውቋል።
"በዚህ ሂደት ለሚደርስ ማንኛውም ጉዳት ይህ ቡድን እና አመራሩ ብቻ ተጠያቂ ናቸው" ሲል መግለጫው አሳስቧል።
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የፕሪቶሪያ ስምምነትን በአግባቡ ተግባራዊ ለማድረግ አቅሙን በማደራጀት መሰረታዊ ጥያቄዎችን ለመመለስ እንደሚሰራ ይታወቅልኝም ብሏል።
በዛሬው ዕለት በዶክተር ደብረፅዮን የሚመራው ህወሓት ባወጣው መግለጫ፤ ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ ጨምሮ ሁሉም በጊዚያዊ አስተዳደሩ ሥር የሚገኙ በጉባኤ ያልተሳተፉ የሥራ ሃላፊዎች ከሃላፊነት በማንሳት በጉባኤ በተሳተፉ ሹማምንት መቀየሩን መግለጹ ይታወሳል።
በአቤል ደጀኔ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ኢትዮጵያ ባሳለፍነው ዓመት ከ8 ነጥብ በላይ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት አስመዝግባለች መባሉ የተጋነነ ነው ተባለ
መስከረም 29/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ሰኞ መስከረም 27 ቀን 2017 የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ለሁለቱ ምክር ቤቶች የመንግሥትን የ2016 በጀት ዓመት አፈጻጸምና የ2017 በጀት ዓመት ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ባቀረቡበት ወቅት፤ በ2016 በጀት ዓመት 8 ነጥብ 1 በመቶ ጥቅል ሀገራዊ እድገት መመዝገቡን መግለጻቸው ይታወሳል፡፡
አሐዱም ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ይህን ያህል ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ለማስመዝገብ በሀገሪቱ ምቹ ኹኔታዎች አሉ ወይ? ሲል የምጣኔ ሐብት ባለሞያዎችን አነጋግሯል።
እንደ ሐገር ካልንበት ኹኔታ አንፃር ለዚህ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ለማደግ አዳጋች መሆኑንና በተለያዩ አካባቢዎች የሚከሰቱ ግጭቶች ትልቅ ማነቆ መሆናቸው የተናገሩት የምጣኔ ሀብት ባለሞያው አቶ እንዳይላሉ ሰለሞን ናቸው።
አቶ እንዳይላሉ፤ በሀገሪቱ በሁሉም አካባቢዎች በሚባል ደረጃ ግጭቶች በመኖራቸው፣ የሥራ አጥ ቁጥር በመጨመሩ፣ የዋጋ ግሽበት በመናሩ እንዲሁም በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በሠላም እጦት ምክንያት በበቂ ደረጃ ምርት ባለመስጠታቸው ምክንያት ይሄን እድገት ማስመዝገብ አይቻልም" ሲሉ ተናግረዋል፡፡
አክለውም፤ "በሀገሪቱ ማምረት ከሚችሉ አካባቢዎች በጣም ጥቂቱ ናቸው የሚያመርቱት፡፡ ያሉትም ምርት በአግባቡ እየሰበሰቡ ነው የሚለው አጠያያቂ ነው" ያሉ ሲሆን፤ "የተባለው እድገት ቢመዘገብም ያን ያህል አስደናቂ አይደለም፡፡ ነገር ግን ብዙ ነገሮች እያሽቆለቆሉ ባለበት ሁኔታ የወጣው ሪፖርት በየትኛውም መልኩ ተቀባይነት የለውም" ብለዋል፡፡
ሥማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ሌላይኛው የምጣኔ ሐብት ባለሞያ፤ ከ 8 ነጥብ በላይ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት እንደ ሀገር ማስመዝገብ ካሉብን ችግሮች አንፃር አስቻይ አለመሆኑን ገልጸው፤ ዕድገቱ በገለልተኛ አካል አለመጣራቱን አንስተዋል፡፡
አክለውም "አጣሪውም ሪፖርት አቅራቢው መንግሥት ራሱ በመሆኑ ቁጥራዊ መረጃው የተጋነነ ያድርገዋል "ሲሉ ጠቁመዋል።
ባለሞያዎቹ ኢትዮጵያ የተባለውን ዕድገት የማስመዝገብ የአቅም ውስንነት እንደሌላት ታውቆ ኢኮኖሚ ላይ ዘርፈ ብዙ ሥራዎች መሰራት እንዳለበት አሳስበዋል።
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀስላሴ ባቀረቡት ሪፖርት፤ ኢትዮጵያ በ2017 የበጀት ዓመት የ8 ነጥብ 4 በመቶ የኢኮኖሚ ዕድገት ለማስመዝገብ ጥረት እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡
በወልደሀዋርያት ዘነበ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ:www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
"የሥራ ጊዜያቸው ተጠናቆ ከስልጣን የተነሱት ሣኅለወርቅ ዘውዴ የስንብት ንግግር አለማድረጋቸው ጥያቄ ፈጥሮብናል" ዶ/ር አበባው ደሳለዉ የአብን ተወካይ የምክር ቤት አባል
መስከረም 29/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ባሳለፍነው ሰኞ መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ.ም 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት መካሄዱ ይታወቃል፡፡
በዚህም የፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ የሥራ ጊዜ መጠናቀቁን ተከትሎ፤ አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፕሬዚዳንት ሆነው ተሹመዋል።
ከዚህ ጋር ተያይዞ ታድያ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የፖርላማ አባላት በፕሬዝዳንቱ ሹመት ላይ ድምጽ ከመስጠት የተቆጠቡ ሲሆን፤ አሐዱም ምክንያት ይኖረዉ ይሆን? ሲል ጠይቋል።
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ተወካይ እና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት ዶክተር አበባው ደሳለዉ፤ ትላልቅ ሀላፊነት ላይ የቆዩ ከፍተኛ አመራሮች በፍጥነት መቀየራቸው በኢትዮጵያ ማህበራዊ፣ ኢከኖሚያዊና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ላይ ጉዳት ያመጣል" ሲሉ ለአሐዱ ገልጸዋል፡፡
ዶክተር አበባው የቀድሞ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር በዲፕሎማሲዉ ረገድ የነበራቸውን ጉልህ ሚና በመጥቀስ፤ ካላቸዉ አስተዋጽኦ አንጻር በቦታው ላይ ቢቆዩ መልካም እንደነበር አንስተዋል፡፡
አክለውም የቀድዋ ፕሬዚዳንት የነበሩት ሳህለወርቅ ዘዉዴ ስልጣን የለቀቁበት ሁኔታ ልክ እንዳልነበር የገለጹ ሲሆን፤ "የስንብት ንግግር አለማድረጋቸው ጥያቄ ፈጥሮብናል" ብለዋል።
"በእነዚህ ምክንያቶች የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አባላት በሹመቱ ውሳኔ ላይ ምንም አይነት ድምጽ ከመስጠት ታቅበናል" ሲሉም ዶክተር አበባው ለአሐዱ ተናግረዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ በምክር ቤቱ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፕሬዚዳንት እንዲሆኑ በእጩነት ቀርበው፤ ሹመታቸው በ5 ተቃውሞ በአብላጫ ድምጽ መጽደቁ ይታወሳል።
በፅዮን ይልማ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ:www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
በአዲስ አበባ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ከነገ ጀምሮ ይካሄዳል
👉ምዝገባው ለአንድ ወር የሚቆይ ነው ተብሏል
መስከረም 29/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በአዲስ አበባ ከተማ ለአንድ ወር የሚቆይ የፋይዳ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ የምዝገባ ዘመቻ በነገው ዕለት እንደሚጀምር ተገለጸ፡፡
የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጽ/ቤት እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ የፋይዳ ብሔራዊ መታወቂያ ምዝገባን በጋራ ለመስጠት መስማማታቸውን አስመልክቶ፤ በዛሬው ዕለት የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም ምዝገባው ከነገ መስከረም 30 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ፤ በኤጀንሲው 119 የወረዳ እና 11 የክፍለ ከተማ ቅርንጫፎች እንደሚካሄድ አስታውቀዋል፡፡
የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ያለምንም ክፍያ በነፃ እንደሚሰጥ የተገለጸም ሲሆን፤ ምዝገባው ካሁን በፊት የተመዘገቡ ኗሪዎችን እንደማይመለከት ተነግሯል።
የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ የዲጂታል ስትራቴጂ 2025 እቅድ አካል ሲሆን፤ የሁሉንም ነዋሪ ረቂቅ ባዮሜትሪክ መረጃን በመውሰድ ወደ ልዩ መለያ ከመቀየር ባለፈ፤ ከተሞችን፣ ክልሎችንና ዞኖችን አጣጥሞ ለማስኬድ የሚያስችል ስርዓት መሆኑም ተገልጿል፡፡
የፋይዳ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ በብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም የተቀመጠውን ቅድመ ሁኔታ ለሚያሟሉ ነዋሪዎች የሚሰጥ ባለ 12 አኀዝ ልዩ መለያ ቁጥር ነው።
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ:www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ተመድ በአማራ ክልል የምግብ ሥርጭትን ጨምሮ የረድዔት ሥራዎቹን ለጊዜው ሊያቆም መሆኑ ተሰማ
መስከረም 29/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በኢትዮጵያ አማራ ክልል፤ የምግብ ሥርጭትን ጨምሮ የሚያከናውናቸውን የረድዔት ሥራዎች ለጊዜው ሊያቆም ማሰቡን ከአንድ የድርጅቱ ሚስጢራዊ ሰነድ ላይ ተመልክቻለሁ ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።
ሮይተርስ ከሰነዱ በተጨማሪ ከሁለት የድርጅቱ ዲፕሎማቶች አረጋግጫለሁ ባለው መረጃ መሰረት፤ ድርጅቱ የረድኤት ሥራውን ለማቆም ያሰበው በክልሉ ውስጥ በረድዔት ሠራተኞች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች መደጋገማቸውን ተከትሎ ነው፡፡
በነሀሴ ወር በወጣውና ሮይተርስ የተመለከተው ሰነድ፤ ካለፈው ዓመት ጥር እስከ ነሃሴ ድረስ በክልሉ አምስት የእርዳታ ሠራተኞች ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች ሲገደሉ፤ 10 ሠራተኞች እንደቆሰሉና 11ዱ ደግሞ እንደታገቱ ያመላክታ ተብሏል፡፡
ይህ ባለ ሦስት ገፅ ሰነድ "ውስጣዊ" የሚል ምልክት የተደረገበት ሲሆን፤ "ድርጅቱ በክልሉ ውስጥ ጊዜያዊ የእርዳታ ሥራዎችን ለማቆም በከፍተኛ ሁኔታ እያሰበ ነው" እንደሚል ተገልጿል።
ይህን የመንግሥታቱን ድርጅት ዕርምጃ በርካታ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና ለጋሽ ድርጅቶች የተቃወሙት ሲሆን፤ "በክልሉ የእርዳታ ሥራዎችን ማቆም ከ2.3 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑና የምግብ እርዳታ በሚጠባበቁ ሰዎች ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ ይኖረዋል" ማለታቸውንም ዘገባው አመላክቷል፡፡
ሰነዱ የተዘጋጀው በመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት (ኦቻ) በኩል መሆኑም ተገልጿል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባስቀመጠው ግምት መሰረት፤ በክልሉ ከተቀሰቀሰ 1 ዓመት ባስቆጠረው ግጭት ምክንያት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሲገደሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ከቀያቸው ተፈናቅለዋል፡፡
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
አየር ላይ ርጭት የሚያከናውኑ የአረም መርጫ መሳርያዎች ሥራቸውን ጀምረዋል ተባለ
መስከረም 28/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የግብርና ሚኒስቴር በቅርቡ በግዥ ከውጭ አገራት ያስገባቸው የአየር ላይ አረም መርጫ መሳርያዎችን በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ማሰማራቱን ተናግሯል።
በዚህም መሰረት በተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች በተላኩት አረሞችን ጨምሮ የእፅዋት ተባዮች ላይ በሚረጩ መሳሪያዎች የአረም መከላከል ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል።
ቀደም ሲል በተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች የአረም ስርጭት እየተስፋፋ መምጣቱንና በሰብሎች ላይ ስጋት መደቀኑ ሲገልፅ እንደነበረ የሚታወስ ሲሆን፤ አሁን ላይ የስርጭት ስርዓቱን በብዛት እየተሳለጠ መሆኑን በግብርና ሚኒስቴር የእፅዋት ጤና ክትትል ኃላፊ አቶ በላይነህ ንጉሴ ለአሐዱ ተናግረዋል።
ኃላፊው አክለውም፤ በተለይ በአማራና በኦሮምያ ክልሎች የእፅዋት ተባይ ስርጭት መታየቱን ገልጸው፤ ሚኒስቴሩ አዝርዕት ላይ የሚከሰተው ጥፋት ለመታደግ አስፈላጊውን ክትትል እያደረገ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
በተለይም ከመስከረም እስከ ሕዳር ባሉ ወቅቶች ውስጥ የግብርና ሥራ የሚሰራበትና ምርት የሚሰበሰብበት ወቅት በመሆኑ፤ አስፈላጊውን ክትትል እየተደረገ እንደሚገኝ አያይዘው ጠቅሰዋል።
ለዚህም ሚኒስቴር መስርያቤቱ የሰለጠኑ ባለሞያዎች ወደተለያዩ ስፍራዎች መሰማራታቸውንና ለችግሩ መላ ለመምታት በብርቱ እየተደከመበት መሆኑን አቶ በላይነህ ገልጸዋል።
ከዚህ ቀደም በርከት ያሉ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በኢትዮጵያ በየዓመቱ በአረምና በተባይ ምክንያት የሚበላሽ የግብርና ምርት ከፍተኛ አሐዝ እንዳለው ከኃላፊው ሰምተናል።
ከተባይና አረም የሚባክነው ምርት በተጨማሪም በምርት አሰባሰብ ላይ የሚስተዋሉ እክሎች ከፍተኛ የሆነ አሐዝ እንዳለው ከዚህ ቀደም የወጡ ጥናቶች ያመልክታሉ።
ሆኖም ችግሩን ለመፍታት የሚደረገው ጥረት ከዓመት ዓመት ችግሩን ሲፈቱ አይስተዋሉም ተብሏል።
በአማኑኤል ክንደያ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ ላይ ከዛሬ ምሽት 12 ሰዓት ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን ጭማሪ ተደረገ
መስከረም 28/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ከዛሬ መስከረም 28/2017 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ በሥራ ላይ የሚውለውን የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ማስተካከያ መደረጉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ታህሳስ 20 ቀን 2014 ባደረገው 3ኛ መደበኛ ስብሰባ ባስተላለፈው የነዳጅ ውጤቶች የዋጋ ግንባታ የአፈጻጸም ውሳኔ መሠረት የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በየጊዜው እየተስተካከለ ሥራ ላይ እንዲውል ሲያደርግ መቆየቱ ይታወሳል፡፡
በዚህም መሰረት በአለም ገበያ የታየውን የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ መነሻ በማድረግ ከመስከረም 28/2017 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ በሥራ ላይ የሚቆይ የሁሉም የነዳጅ ውጤቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ ተደርጓል፡፡
በዚህ መሰረት፦
👉 ቤንዚን- ብር 91.14 በሊትር
👉 ነጭ ናፍጣ- ብር 90.28 በሊትር
👉 ኬሮሲን- ብር 90.28 በሊትር
👉 ቀላል ጥቁር ናፍጣ- ብር 100.20 በሊትር
👉 ከባድ ጥቁር ናፍጣ- ብር 97.67 በሊትር እንዲሁም
👉 የአውሮፕላን ነዳጅ በሊትር 77.76 ብር መደረጉን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡
N.B የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ የዋጋ ማስተካከያ ማድረግ ያስፈለገበትን ምክንያትና ማስተካከያውን አስመልክቶ ያወጣው መግለጫ ከላይ ተያይዟል፡፡
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ:www.facebook.com/ahaduradio
ዩትዩብ፦http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
የመንግሥት ንብረት አወጋገድ በጨረታ ብቻ እንዲከወን የወጣው መመሪያ ተግባራዊ እንደሚደረግ ተገለጸ
መስከረም 28/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በየዓመቱ በመንግሥት በጀት ላይ የሚስተዋለውን ብክነት ለመፍታት እንዲያስችልና ተጨማሪ ገቢ ለመሰብሰብ ሲባል ንብረቶች አወጋገድ በሽያጭ ብቻ እንዲፈጸም እቅድ መያዙንም ተገልጿል።
ባለበጀት የፌደራል መስርያ ቤቶች ላይ የሚስተዋለውን የንብረት አወጋገድ በተመለከተ የጨረታ አወጣጥ ላይ ችግር መኖሩ ሲገለጽ ይደመጣል፡፡
በዚህ ረገድ መሻሻሎች መኖራቸውን የፌደራል መንግስት ንብረት አስተዳደር አገልግሎት የሕዝብ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ጎጃም ታደለ ለአሐዱ ተናግረዋል።
አክለውም፤ የመንግሥት ንብረት አወጋገድ በጨረታ ብቻ እንዲከወን የወጣው መመሪያ በአዲሱ በጀት ዓመት ተግባራዊ እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡
"የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር በርከት ያሉ የንብረት አወጋገድ አይነቶች ሲተገበሩ የቆዩ ቢሆንም፤ አሁን ላይ በጨረታ ከመሸጥ ውጭ ሌላው የአወጋገድ አይነቶች አይተገበሩም" ሲሉም አስረድተዋል።
ሥራ አስፈፃሚዋ የመንግሥት በጀት ብክነት መኖሩን አስታውሰው፤ ይህን ብክነት ለመቆጣጠር የንብረት አስተዳደር እንዲዘምን ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን አመላክተዋል፡፡
የፌደራል መንግሥት ባለበጀት መስሪያ ቤቶች የንብረት አስተዳደር ረገድ ያሉባቸውን ችግሮች እንዲፈቱና ለዘርፉ የሚመጥን የግዥ አስተዳደር እንዲዘረጉም የፌደራል መንግሥት ንብረት አስተዳደር አገልግሎት ጠይቋል።
በአማኑኤል ክንደያ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
በመዲናዋ በሩብ ዓመቱ ከ519 በላይ የሚሆኑ የጤና ተቋማት የፍቃድ ዕድሳት አለማድረጋቸው ተገለጸ
መስከረም 28/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በአዲስ አበባ ከተማ በሩብ ዓመቱ ከ519 በላይ የሚሆኑ የጤና ተቋማት የፍቃድ ዕድሳት አለማድረጋቸውን የከተማ አስተዳደሩ ምግብና መድሐኒት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ፡፡
ምን ያህል የጤና ተቋማት ፍቃዳቸውን ዕድሳት አድርገዋል? ከጥራት ልኬት ጋር በተገናኘ የቁጥጥር ሂደቱ ምን ይመስላል ሲል አሐዱ ባለስልጣኑን ጠይቋል።
በባለስልጣኑ የጤና ተቋማትና ባለሞያዎች ብቃት ማረጋገጫ ዳይሬክቶሬት ዳይረክተር ታደሰ ወርደፋ፤ ከ1 ሺሕ 855 ተቋማት ውስጥ 1 ሺሕ 336 ብቻ የብቃት መለኪያ መስፍርቱን አሟልተዉ ወደ ሥራ መግባታቸውን ገልጸዋል፡፡
ነገር ግን ከ519 በላይ የሚሆኑት መለኪያውን ባለሟሟላት፣ ከልማት ጋር ተያይዞ ተቋማቸው በመፍረሱ እንዲሁም ከገበያ በመዉጣታቸዉ ምክንያትም እድሳት አለማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡
ኃላፊው አክለውም በዘርፉ የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችን ከሌሎች ጊዜያት በተለየ መልኩ የቁጥጥር ሥራዎችን በማዘመን ችግሮችን ለመቅረፍ ፣ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሠራ መሆኑን ጠቁመዋል።
በወልደሃዋሪያት ዘነበ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
በመዲናዋ በሁለተኛ ዙር የኮሪደር ልማት የተካተቱ 8 መስመሮች ይፋ ተደረጉ
መስከረም 28/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የአዲስ አበባ ከተማ የሁለተኛ ዙር የኮሪደር ልማት ሥራ መጀመሩን የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታውቀዋል።
በዚህም መሰረት 132 ኪሎሜትር የሚረዝም እንዲሁም ከ2 ሺሕ 8 መቶ ሄክታር በላይ የቦታ ስፋት ያለው ሁለተኛ ዙር የኮሪደር ልማት የማካሄድ ሥራ መጀመሩን ተናግረዋል።
አክለውም ለተነሺዎች የሚተላለፉ ከ4 ሺሕ በላይ ቤቶች መገንባታቸውን የገለጹ ሲሆን፤ ምትክ ቦታ ለሚያስፈልጋቸው መሬት መዘጋጀቱን እንዲሁም 5 ቢሊዮን ብር ለካሳ መመደቡን ገልጸዋል።
የሁለተኛው ዙር የኮሪደር ልማት 8 መስመሮች የሚከተሉት ናቸው፦
1. ካዛንቺስ፣ መስቀል አደባባይ፣ ሜክሲኮ፣ ቸርችል፣ አራት ኪሎ፣ እስጢፋኖስ ኮሪደር እና መልሶ ማልማት 1000 ሄክታር ቦታ ስፋት እና 40.4 ኪሎሜትር ርዝመት፤
2. ሳውዝጌት፣ መገናኛ ፣ ሃያሁለት፣ መስቀል አደባባይ የኮሪደር ልማት 128.7 ሄክታር የቦታ ስፋት እና 7.1 ኪሎሜትር ርዝመት፤
3. ሲኤምሲ፣ ሰሚት ጎሮ፣ ቦሌ አየር ማረፊያ ቪአይፒ ተርሚናል፣ አዲስ አፍሪካ አለም አቀፍ ኮንቬንሽንና ኤግዚብሽን ማዕከል የኮሪደር ልማት 146 ሄክታር የቦታ ስፋት እና 10.8 ኪሎሜትር ርዝመት፤
4. ሳር ቤት፣ ካርል አደባባይ፣ ብስራተ ገብርኤል፣ አቦ ማዞሪያ፣ ላፍቶ አደባባይ፣ ፉሪ አደባባይ ኮሪደር ልማት 565 ሄክታር የቦታ ስፋት እና 15.9 ኪሎሜትር ርዝመት፤
5. አንበሳ ጋራዥ፣ ጃክሮስ ጎሮ ኮሪደር ልማት 16.58 ሄክታር የቦታ ስፋት እና 3.1 ኪሎሜትር ርዝመት፤
6. አራት ኪሎ፣ ሽሮ ሜዳ እንጦጦ ማርያም፣ ጉለሌ እጸዋት ማዕከል የኮሪደር ልማት 314 ሄክታር የቦታ ስፋት እና 13.19 ኪሎሜትር ርዝመት፤
7. የቀበና ወንዝ ዳርቻ ኮሪደር ልማት 372.5 ሄክታር የቦታ ስፋት እና 20 ኪሎሜትር ርዝመት፤
8. እንጦጦ፣ ፒኮክ ፓርክ የወንዝ ዳርቻ ልማት ኮሪደር ልማት 274 ሄክታር የቦታ ስፋት እና 21.5 ኪሎሜትር ርዝመት መሆናቸው ተገልጿል።
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
በኢትዮጵያ ከግማሽ ሚሊየን በላይ ዜጎች የኤች.አይ.ቪ ኤድስ ተጠቂ መሆናቸው ተረጋግጧል ተባለ
መስከረም 28/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ ከግማሽ ሚሊየን በላይ ዜጎች የኤች.አይ.ቪ ኤድስ ቫይረስ በደማቸው መገኘቱ ተረጋግጧል ሲል ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
በተለይም በአዲስ አበባ ፣አማራ ፣ በጋምቤላ ፣ በትግራይ ፣ በሐረር እና በድሬዳዋ አካባቢዎች ያለው የስርጭት መጠን ወረርሽኝ ነው ሊባል በሚችልበት ሁኔታ ላይ መሆኑን የገለጹት፤ በጤና ሚኒስቴር የኤች.አይ.ቪ ኤድስ መከላከል እና መቆጣተጠር መሪ ሥራ አስፈፃሚ የዘርፈ ዴስክ ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ካሳ ናቸው፡፡
በዚህም በኢትዮጵያ የኤች አይቪ ኤድስ ተጠቂ ይሆናሉ ተብለው ከተገመቱት የማህበረሰብ ክፍሎች ውስጥ 90 ከመቶ የሚሆኑት ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ እንደተገኘባቸውና የተጠቂዎቹ ቁጥርም ከ5 መቶ ሺሕ በላይ እንዳለፈ ኃላፊው ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
በኢትዮጵያ እንደ ሀገር ያለው የስርጭት መጠን ከ1 በመቶ በታች ቢሆንም፤ በአንዳንድ ክልሎች ግን ወረርሽኝ በሚቻል ደረጃ መስፋፋቱን ጨምረው ገልጸዋል፡፡
ኃላፊው አክለውም፤ ማህረሰቡ በኤች.አይ.ቪ ኤድስ ላይ ያለውን ግንዛቤ መቀነስ ለበሽታው መስፋፋት መንስኤ እየሆነ መምጣቱን የገለጹ ሲሆን፤ በበሽታው ተጋላጭ የሆኑ ዜጎች ስለ በሽታው መተላለፊያና የመከላከያ መንገዶች ግንዛቤ የመፍጠር ሥራ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ አሳስበዋል።
ከቫይረሱ መስፋፋት እና መጨመር ጋር ተያይዞ ማህበረሰቡ ንቃተ ህሊና ሊጨምርና ጥንቃቄ ሊያደርግ እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡
በእመቤት ሲሳይ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
በዳውሮ ዞን ቶጫ ወረዳ በተከሰተ የመሬት መንሸራተት አደጋ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ተገለጸ
👉በአደጋው በሰው ሕይወት ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩ ተገልጿል
መስከረም 28/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በዳዉሮ ዞን ቶጫ ወረዳ በሚገኙ በ5ቱ ቀበሌዎች ላይ ትላትና ቀን በጣለው ከፍተኛ ዝናብ ተከትሎ፤ የተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ ከፍተኛ ጉዳት ማስከተሉ ተገልጿል።
በዚህም በወረዳው በተለያዩ ቀበሌዎች፤ ቲማ፣ ደሊ፣ ሻንዳ፣ ኦክሊና ቦቶሪ ላይ ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ በመዝነቡ እና የአካባቢው መልክአ ምድራዊ አቀማመጥ ተጨምሮ የተስተዋለው የአፈር መንሸራተት አደጋ በአርሶ አደሮች ማሳ፣ በእንስሳት፣ በመኖሪያ ቤቶች እና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን ወረዳው አስታውቋል።
በደረሰው ክስተት በሰው ሕይወት ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩ የተገለጸ ሲሆን፤ የተከሰተውን ከፍተኛ የመሬት መንሸራተት አደጋ ተከትሎ ወረዳው ግብረ- ኃይል አቋቁሞ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ እንደሚገኝ ተገልጿል።
አጠቃላይ የጉዳት መጠኑ በቀጣይ ከሚመለከተው ክፍል ጋር በመሆን እንደሚገለጽ የቶጫ ወረዳ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አስታውቋል።
የወረዳው መንግሥት በቀጣይም ከመደበኛ በላይ መጠን ያለው ዝናብ የሚጠበቅ በመሆኑ ማኅበረሰቡ አስፈላጊውን ሁሉ ቅድመ ዝግጅት እና ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስቧል።
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡-https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
መንግሥት በሊባኖስ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ደኀንነታቸው ችግር ላይ እንዳይወድቅ ከፍተኛ ርብርብ እያደርገ እንደሚገኝ አስታወቀ
መስከረም 28/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በሊባኖስ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ደኀንነታቸው ችግር ላይ እንዳይወድቅ ከፍተኛ ርብርብ እያደርገ እንደሚገኝ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ሚኒስቴሩ በሊባኖስ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ደኅንነታቸው የተጠበቀ እንዲሆን የቴክኒክ ኮሚቴ በማቋቋም ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡
ከአሁን በፊት በተለያዩ አገራት ለችግር የተዳረጉ ኢትዮጵያውያንን ወደ አገራቸው ለመመለስ የተቋቋመው ብሔራዊ ኮሚቴ ቀዳሚ ትኩረቱን በሊባኖስ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን በማድረግ እየሰራ መሆኑን ነው የገለጸው።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ቤይሩት የሚገኘው ቆንስላ ጀኔራል ጽ/ቤት የዜጎችን ምዝገባ እና ክትትል በተሻለ ፍጥነት ለማካሄድ የሚያስተባብር አመራር ወደ ሊባኖስ ተልኮ ሥራውን መጀመሩንም ገልጿል፡፡
ቆንስላ ጀኔራል ጽ/ቤቱ ካለበት አገር የአገሪቱን ቋንቋ የሚችሉ ተጨማሪ ሰራተኞችን በመቅጠር እየሠራ እንደሚገኝም የተገለጸ ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅትም ቆንስላ ጀኔራል ጽ/ቤቱ በሊባኖስ የሚገኙ ዜጎቻችንን በአካል እና ዲጂታል ምዝገባ ስርዓት ዘርግቶ እያከናወነ እንደሚገኝ ተገልጿል።
በዚህም በሊባኖስ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በቆንስላ ጀኔራል ጽ/ቤቱ በተጠቀሰው አድራሻ እና በዲጂታል መመዝገቢያ እንዲመዘገቡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጥሪ አቅርቧል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዜጎች አንጻራዊ ደኀንነት ወደ አለበት የሊባኖስ አካባቢ እንዲንቀሳቀሱ ማድረግ እና ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ህጻናት እና ሴቶችን ወደ አገራቸው ለመመለስም ሁሉንም አማራጮች ለመጠቀም ከተለያዩ አካላት ጋር ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝም አስታውቋል።
ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አሁን ላይ በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲው ቅድሚያ በሊባኖስ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን በመስጠት ደኀንነታቸው ችግር ላይ እንዳይወድቅ ከፍተኛ ርብርብ እያደርገ መሆኑንም ገልጿል።
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ለቀድሞው ፕሬዚዳንት ሣሕለ ወርቅ ዘውዴ ምስጋና አቀረቡ
መስከረም 27/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ላለፉት ስድስት ዓመታት ኢትዮጵያን በፕሬዚዳንትነት ላገለገሉት ለሣሕለ ወርቅ ዘውዴ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ "የለውጡ አንዱ ዓላማ ሥርዓትን ማጽናት ነው። የሥራ ኃላፊዎች በሕግ የተሰጣቸውን ኃላፊነት በተሰጣቸው ጊዜ ይወጣሉ። ሲሉ ገልጸዋል፡፡
አክለውም "ሌሎች ደግሞ በተራቸው እነርሱን ተክተው ሀገራዊ ዓላማን በትውልድ ቅብብል ከግብ ያደርሳሉ። የሀገር ግንባታ የሚሳካው በዚህ መንገድ ነው።" ብለዋል፡፡
ላለፉት ስድስት ዓመታት ኢትዮጵያን በፕሬዚዳንትነት ላገለገሉት ሣሕለ ወርቅ ዘውዴ በኢትዮጵያ መንግሥት ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
ዛሬ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሆነው ኃላፊነት ለተቀበሉት ታዬ አጽቀሥላሴ፤ ሀገርና ሕዝብን በላቀ ሁኔታ የሚያገለግሉበት የኃላፊነት ዘመን እንዲሆንላቸው መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ