ahaduradio | Unsorted

Telegram-канал ahaduradio - AHADU RADIO FM 94.3

19349

አሐዱ ራድዮ 94.3 Your source for top local and international news and analysis. "Voice of Ethiopian" የአሐዱ የቴሌግራም ቻናል ቤተሰብ በመሆን ወቅታዊና እውነተኛ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ

Subscribe to a channel

AHADU RADIO FM 94.3

የሞሪንጋ (ሽፈራው) ተክል በሕጻነት ላይ የሚከሰተውን የመቀንጨር ችግር እንደሚከላከል በጥናት መረጋገጡ ተገለጸ

ጥቅምት 13/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ 'ሽፈራው' እየተባለ የሚጠራው የሞሪንጋ ተክል በሕጻነት ላይ የሚከሰተውን የመቀንጨር ችግር እንደሚከላከል በጥናት መረጋገጡ ተገልጿል፡፡

ጥናት እና ምርምሩ ተግባራዊ እንዲሆን የጣሊያን መንግሥት፣ የተባበሩት መንግሥታት የኢንዲስትሪ ልማት ድርጅት እንዲሁም የአርባ ምንጭ ዩንቨርስቲ በጋራ የሰሩትን ፕሮጀክት ይፋ አድርገዋል፡፡

በአርባ ምንጭ ዩንቨርስቲ በምግብ ቴክኖሎጂና ባዮቴክኖሎጂ ተባባሪ ፕሮፌሰር አዲሱ ፍቃዱ፤ የሞሪንጋ ወይም የሽፈራው ተክል በሕጻነት ላይ የሚከሰተውን የመቀንጨር ችግር ጨምሮ ብዙ የጤና ጠቀሜታ እንዳለው በጥናት እና ምርምር መረጋገጡን ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

በተክሉ ውስጥ የተለያዩ ንጥረ ነገሮች የሚገኝበት በመሆኑ ከሌሎች ምግቦች ጋር በመቀላቀል በመጠቀም እንደሚቻል አንስተው፤ የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፍ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ምርቶችንም ማስቀረት እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡

ፕሮጀክቱ በዋናነት ተግባራዊ የተደረገው ተክሉ በስፋት የሚበቅልበት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አርባ ምንጭ ከተማ ዘይሴ ቀበሌ ሲሆን፤ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ገብረመስቀል ጫላ ከተክሉ የተለያዩ ምርቶች እንደሚገኝበት እና ዘርፍ ብዙ ጠቀሜዎች እንዳሉት ተናግረዋል፡፡

በተገኘው ጥናት እና ምርምር መሰረት፤ ተክሉ በብዙ መልኩ የሚቀነባበርበት የፋብሪካ ግንባታ ተጠቀናቆ የተለያዩ ማሽኖችም መግባታቻውን አሐዱ ማረጋገጥ ችሏል፡፡

የተጀመረው ፕሮጀክት ተግባራዊ እንዲሆን ያሉትን የመሰረተ ልማት ችግር ለመቅረፍ ምን እየተሰራ ነው? ሲል አሐዱ ለክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ላነሳው ጥያቄም፤ የመንገድ እና የኤሌትሪክ አገልግሎት ችግሮች እንደሚፈቱም ተናግረዋል፡፡

በተባበሩት መንግሥታት የኢንደስትሪ ልማት ድርጅት ተወካይ እና የፕሮጀክቱ ቴክኒካል አማካሪ ዶክተር ለምለም ሲሳይ በበኩላቸው፤ በገጠር ላሉ ሴቶች የኑሮ ማሻሻያ ያስፈልጋል በሚል ከመንግሥት በቀረበው ጥያቄ መሰረት ፕሮጀክቱ ተግባራዊ መደረጉን አንስተው ከክልሉ መንግሥት ጋር በጋራ እንደተሰራም አስረድተዋል፡፡

የሞሪንጋ ወይም የሽፈራው ተክልን አብዛኛው የኢትዮጵያ የማህበረሰብ ክፍሎች የተለያዩ የካንሰር አይነቶችን እና ደምግፊትን ጨምሮ ሌሎች በሽታዎችን ለመከላከል እንደሚጠቀሙበት የሚታወቅ ነው፡፡

በፍቅርተ ቢተው

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

መልካም ቀን!
አሐዱ ሬድዮ 94.3  የኢትዮጵያውያን ድምፅ!

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በመርካቶ ሸማ ተራ ከደረሰው የእሳት አደጋ ተያይዞ የስርቆት ወንጀል የፈጸሙ 33 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ፖሊስ አስታወቀ

👉ከአደጋው በ7 ሰዎች ቀላል በ2 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት ደርሷል


ጥቅምት 12/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በመርካቶ ሸማ ተራ አካባቢ ከደረሰው የእሳት አደጋ ተያይዞ የስርቆት ወንጀል የፈጸሙ 33 ተጠርጣሪዎችን ይዞ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ የአደጋውን መንስኤ ለማጣራት ከፌዴራል ፖሊስ የፎረንሲክ ምርመራ ቡድን ጋር በመቀናጀት ምርመራ መጀመሩንም ገልጿል።

አደጋውን ለመከላከል እና በአደጋው ምክንያት ሌላ ወንጀል እንዳይፈፀም እንዲሁም የአደጋ ተከላከይ ሰራተኞች ተግባራቸውን በአግባቡ መወጣት እንዲችሉ እና ተጨማሪ ጉዳት እንዳያጋጥም የፌዴራል እና የአዲስ አበባ ፖሊስ፣ የመከላከያ ሠራዊት፣ ሪፐብሊካን ጋርድ፣ ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች፣ የሠላምና ፀጥታ መዋቅር፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ሌሎች ተቋማትም ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ አደጋው እንዳይባባስ ከፍተኛ ጥረት ተደርጓል ብሏል።

አደጋውን እንደ ምቹ ሁኔታ በመጠቀም የስርቆት ወንጀል የፈፀሙ 33 ተጠርጣሪዎችን ይዞ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የገለጸው ፖሊስ፤ ከአደጋው ጋር በተያያዘ በ7 ሰዎች ቀላል በ2ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት መድረሱን አስታውቋል፡፡

አደጋውን ለመከለከል የጸጥታና ሌሎች ተቋማት እንዲሁም የአካባቢው ህብረተሰብ ላደረገው ድጋፍና ተባባሪነት ፖሊስ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ በደረው የእሳት አደጋ የተሰማውን ሃዘን ገልፆ፤ ወደፊት በምርመራ የደረሰበትን ውጤት ለሕዝብ እንሚያሳውቅም ገልጿል፡፡

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

ምርጫ ቦርድ በአስራ አንድ ፓርቲዎች ላይ የዕግድ ውሳኔ ማስተላለፉን አስታወቀ

ጥቅምት 12/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በጠቅላላ ጉባኤ፣ በኦዲት እና በሴት አባላት በሚገኝ የገንዘብ ድጋፍ ምክንያት ቦርዱ በተለያዩ ጊዜ በአስራ አንድ ፓርቲዎች ላይ የዕግድ ውሳኔ መስጠቱን አስታውቋል።

ቦርዱ ለኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በጻፈው ደብዳቤ፤ ዕግድ ውሳኔ የተሰጣባቸው ፓርቲዎች የኦሮሞ ነጻነት ንቅናቄ፣ አንድ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ የጌዲኦ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት፣ የሐረሪ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት፣ የገዳ ሥርዓት ለኦሮሞ ነጻነት ፓርቲ፣ የዎላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ፣ አዲስ ትውልድ ፓርቲ፣ የጋምቤላ ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ፣ የጋምቤላ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ፣ የኢትዮጵያ ዴሞክቲክ ኅብረት እና አገው ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ መሆናቸውን ገልጿል።

በፓርቲዎቹ ላይ የተሰጠው የዕግድ ውሳኔ ውጤት ቦርዱ የተለየ ውሳኔ እስከሚሰጥ ድረስ፤ ለጊዜው ፓርቲዎችን ከማናቸውም ሕጋዊ እንቅስቃሴ ታቅበው እንዲቆዩ የሚያደርግ መሆኑን አስታውቋል።

በመሆኑም ቦርዱ የሰጠውን የዕግድ ውሳኔ እስከሚያነሳ ድረስ፤ በማናቸውም የጋራ ምክር ቤቱ በሚያዘጋጃቸው ጉባኤዎች ላይ ሊገኙ እንዲሁም ሊመርጡም ሊመረጡም ወይም በተለያዩ የኮሚቴ አባልነት ሊያገለግሉ አይችሉም ብሏል።

በዚህም መሠረት የጋራ ምክር ቤቱ በዝርዝር የተገለጹትን ፓርቲዎች ከማናቸውም የምክር ቤቱ ሥራዎችም ሆነ እንቅስቃሴዎች እንዳይካፈሉ ተገቢውን ሁሉ እንዲያደረግ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አጥብቆ አሳስቧል።

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

ዘለቀ ተመስገን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነዉ ተሾሙ

ጥቅምት 12/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽንን በምክትል ኮሚሽነርነት ሲመሩ የነበሩት ዘለቀ ተመስገን (ዶ/ር) ኮሚሽኑን በዋና ኮሚሽነርነት እንዲመሩ በጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ተሹመዋል፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት ጥቅምት 8 ቀን 2017 የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩት ሃና አርዓያስላሴ የፍትህ ሚኒስትር ሆነዉ በጠቅላይ ሚኒስትሩ መሾማቸው ይታወሳል፡፡

ይህንንም ተከትሎ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽንን በምክትል ኮሚሽነርነት ሲመሩ የነበሩት ዘለቀ ተመስገን ( ዶ/ር) የኮሚሽነርነት ቦታን ተረክበዋል።

ዶ/ር ዘለቀ ከጣልያን ቱሪን ዩኒቨርሲቲ በህዝብ አለምአቀፍ ሕግ የዶክትሬት ዲግሪ ያጠናቀቁ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽንን ከመቀላቀላቸዉ በፊት የኢፌዲሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የቢሮ ኃላፊ ሆነው አገልግለዋል።

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

ምርጫ ቦርድ የአገልግሎት ክፍያ ላይ ጭማሪ አደረገ

👉 የፓርቲዎች የሙሉ ዕውቅና ክፍያ ከ200 ብር ወደ 30 ሺሕ ብር አድጓል


ጥቅምት 12/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምዝገባ፣ የሙሉ ዕውቅና እና የሰነድ ማሻሻያ የአገልግሎት ክፍያ መጠን ላይ ጭማሪ ማድረጉን አስታውቋል።

ቦርዱ ባወጣው መግለጫ፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምዝገባና የሰነድ ማሻሻያ አገልግሎት ክፍያ በምርጫ፣ በፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና ሥነምግባር አዋጅ በሥራ ላይ ከዋለበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ያለው የምዝገባ ክፍያ መጠን ለሀገር አቀፍ እና ለክልላዊ ፖለቲካ ፓርቲ ጊዜያዊ ሰርተፍኬት ለማግኘት 100 ብር እንደነበር አስታውሷል፡፡

እንዲሁም ለሙሉ ዕውቅና ለሀገር አቀፍ እና ክልላዊ ፓርቲ 200 ብር እንደነበር በመጥቀስ የተመዘገቡ ፖለቲካ ፓርቲዎች መሰረታዊ ሰነዶቻቸውን በጉባኤ አሻሽለው ሲያቀርቡ 30 ብር የአገልግሎት ክፍያ ሲከፈል መቆየቱን ገልጿል።

ነገር ግን የክፍያ መጠኑን በየጊዜው መሻሻል እንደሚያስፈልግ ቦርዱ በማመን ከጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ተፈጻሚ የሚሆን የአገልግሎት የክፍያ ተመን መሻሻሉን አስታውቋል፡፡

በዚህ በተሻሻለው የክፍያ ተመን መሰረትም የጊዜያዊ ዕውቅና ክፍያ 15 ሺሕ ብር፣ የሙሉ ዕውቅና ክፍያ 30 ሺሕ ብር ሲሆን፤ የሰነድ ማሻሻያ ክፍያ ደግሞ 5 ሺሕ ብር መሆኑን ቦርዱ አስታውቋል፡፡

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በትምህርት ቤቶች አካባቢ የሚስተዋሉ አዋኪ ድርጊቶች ለመቀነስ ለአመራሮች ስልጠና ሊሰጥ መሆኑ ተገለጸ

ጥቅምት 12/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በአዲስ አበባ ከተማ በትምህርት ቤቶች አካባቢ የሚስተዋሉ አዋኪ ድርጊቶች ለመቀነስ፤ ለርዕሳነ መምህራን የወጣቶች ሰብዕና ግንባታን የተመለከተ ስልጠና ሊሰጣቸው መሆኑ ተሰምቷል።

ስልጠና መስጠቱ አስፈላጊ የሆነበት ምክንያት ርዕሳነ መምህራን ትምህርት ቤቶችን ከማስተዳደር ጎን ለጎን በትምህርት ቤቶች አካባቢ የተዘረጉና የመማር ማስተማር ሂደቱን የሚያውኩ ድርጊቶችን የመረዳት አቅም ስለማይስተዋልባቸው ነው ተብሏል።

በአዲስአበባ ያሉ ትምህር ቤቶች የወጣቶች ሰብዕና ጉድለት ዙርያ በርካታ ጥያቄዎች ሲነሳባቸው የቆየ ጉዳይ በመሆኑ ይህንን ችግር ለማስተካከል ስልጠናው ሚና እንደሚኖረው የተገለጸ ሲሆን፤ ርዕሳነ መምህራን ችግሩን የመረዳት ቅልጥፍና እንዲኖራቸውም የሚረዳ መሆኑን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ተናግሯል።

በተያዘው በጀት ዓመትም በትምህርት ቤቶች አካባቢ በሚስተዋሉ በተለይም ከሱስና አዋኪ ተግባራት ጋር በተያያዘ ያሉትን ችግሮች ለመቅረፍ እየሰራበት መሆኑን፤ በትምህርት ቢሮው የአገልግሎት አሰጣጥ ቁጥጥር ዳይሬክተር ዳዊት ከበደ ለአሐዱ ተናግረዋል።

ዳይሬክተሩ አክለውም የተዘረጉትን ሰንሰለቶችን ለመበጠስ ውጥን ተይዞ በብርቱ እየሰራበት መሆኑን ገልጸው፤ ቢሮው በቀጣይም በርካታ እቅዶች እንዳሉት አስታውቀዋል።

በመዲናዋ በየትምህርት ቤቶች እየተስተዋሉ ያሉ አላስፈላጊ እንቅስቃሴዎችንና እክሎችን ለማሻሻል ሁሉም የሚመለከተው ሁሉ የሚቻለውን ሁሉ እንዲያደርግም ጠይቀዋል።

ንግድ ቢሮን ጨምሮ ፓሊስ ኮሚሽንና የደንብ ማስከበር መስርያ ቤቶች ትልቅ ኃላፊነት የሚጠበቅባቸው መሆኑንና ድርሻቸውም ከፍተኛ መሆኑን ዳይሬክተሩ አክለው ገልጸዋል።

ለዚህም ዋነኛ ተዋናዮች የሆኑት የትምህርት ቤቶች ርዕሳነ መምህራን አስተውሎታቸው እንዲጨመር እየተሰራ ነው ብለዋል።

አዋኪ ድርጊቶች እንዲቀንሱ በማድረግ ረገድ በመዲናዋ እየተተገበረ ያለውን የኮሪደር ልማት እንቅስቃሴ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ መሆኑንም አንስተዋል።

ዳይሬክተሩ አክለውም የመንግሥት መስሪያ ቤቶች እቅዶቻቸውን በሚይዙበት ጊዜ የትምህርት ቤቶችን ደህንነት በሚጠብቅ መልኩ መሆን ይኖርበታል ሲሉ ለአሐዱ ተናግረዋል።

በአማኑኤል ክንደያ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

"የእሳት አደጋ መኪና በተሟላ ሁኔታ ለመንቀሳቀስ አስቸጋሪ በመሆኑ ሄሊኮፕተር ለመጠቀም ጥረት እየተደረገ ነው" ከንቲባ አዳነች አቤቤ 

ጥቅምት 11/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በመርካቶ ሸማ ተራ አካባቢ የተከሰተውን የእሳት አደጋ ቶሎ ለመቆጣጠር እየተደረገ ባለው ጥረት፤ የአካባቢው መንገድ የእሳት አደጋ መኪና በተሟላ ሁኔታ ለመንቀሳቀስ አስቸጋሪ በመሆኑ ሄሊኮፕተር ለመጠቀም ጥረት እየተደረገ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት፤ "በመርካቶ ሸማ ተራ አካባቢ በተከሰተው የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ለደረሰው ጉዳት እጅግ አዝነናል" ብለዋል።

"ይህንን አደጋ ለመቀነስ ርብርብ እያደረጋችሁ ያላችሁ አካላት ሁሉ ጥረታችሁን አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ አሳስባለሁ" ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል።

በአዲስ አበባ አዲስ ክ/ከተማ መርካቶ በተለምዶ ሸማ ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ዛሬ ማምሻውን ከፍተኛ የእሳት አደጋ ተነስቷል። እሳቱን ለመቆጣጠር ርብርብ እየተደረገ ቢሆንም የእሳቱ መጠን ከፍተኛ በመሆኑና ከቦታው አለመመቸት ጋር ተያይዞ እስካሁን አደጋውን መቆጣጠር አልተቻለም።

የእሳት አደጋው በንግድ ሱቆች ላይ የተነሳ ሲሆን፤ በርካታ ሱቆች በእሳቱ ሙሉ ለሙሉ ውድመት ደርሶባቸዋል።

እስካሁን እሳት አደጋው በሰው ላይም ሆነ በንብረት ላይ ያደረሰው የጉዳት መጠን አልታወቀም። በቀጣይ መረጃዎች ሲደርሱን ወደእናንተ የምናደርስ ይሆናል።

ቪዲዮ፦ ማህበራዊ ሚዲያ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝ ጭማሪ ከተያዘው የጥቅምት ወር ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ ተፈቀደ

ጥቅምት 11/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ለኑሮ ውድነት መቋቋሚያ የሚሆን የመንግሥት ሠራተኞች የደመወዝ ጭማሪ ተፈቅዶና በጀቱም ጸድቆ፤ ክፍያው ከጥቅምት ወር 2017 ዓ.ም.  ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አስታውቋል።

ከገንዘብ ሚኒስቴር የተፈቀደውን በጀት፣ የአፈጻጸም መመሪያውንና የክፍያ ትዕዛዙን ለ12ቱ ክልሎች፣ ለሁለቱ የከተማ አስተዳደሮችና ለፌደራል ተቋማት ዛሬ መተላለፉን ኮሚሽኑ ገልጿል።

👉 ከጥቅምት ወር 2017 ዓ/ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረገው የደመወዝ እርከን ከላይ ተያይዟል!

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የማክሮ- ኢኮኖሚ ማሻሻያ ከተደረገ በኃላ በግንባታው ዘርፍ ያሉ ፕሮጀክቶች ማጠናቀቅ እየተቻለ አይደለም ተባለ

ጥቅምት 11/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ ከሦስት ወራት በፊት ተግባራዊ የተደረገውን አዲሱን የገንዘብ አስተዳደር መመርያን ተከትሎ፤ በግንባታው ዘርፍ ላይ ተይዘው የነበሩ የግንባታ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ መቸገራቸውን የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማሕበር አስታውቋል።

ማሕበሩ ከማሻሻያው በፊት የተያዙ ፕሮጀክቶች የተገባላቸው ውል አሁን ላይ ካለው ገበያና የግብአት አቅርቦት ዋጋ አንፃር የሚመጣጠን አለመሆኑን ገልጿል።

በዚህ የተነሳም ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ማስረከብ እየተቻለ አለመሆኑን የማሕበሩ ፕሬዚዳንት ለአሐዱ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማህበር ፕሬዝዳንት ኢንጅነር ግርማ ሀብተማርያም፤ በዘርፉ የግብዓት አቅርቦት መኖሩ ብቻ የፕሮጀክቶቹ ችግር የሚፈታው አለመሆኑን ጠቅሰው፤ የፕሮጀክቶች ዋጋ ማስተካከያ ሊደረግ እንደሚያስገድድ ለአሐዱ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ኢንጂነር ግርማ አክለውም፤ የግንባታውን ዘርፍ የሚመራው የመንግሥት አካል ጉዳዩን መርምሮና መክሮበት አስፈላጊውን መፍትሔ እንዲሰጥ ጠይቀዋል።

ጉዳዩ እስካሁን ቸል መባሉን የግንባታው ሥራን ጨምሮ ተያይዘው የሚመጡ ችግሮች እያባባሰ ይገኛል ሲሉም ነግረውናል።

የግንባታ ዘርፍ በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሥራ እድል ፈጥሮ ምጣኔ ሐብቱ ላይ የራሱን አበርክቶ እያበረከተ የሚገኝ ዘርፍ መሆኑንም ገልጸዋል።

ከወራት በፊት ኢትዮጵያ ያደረገችውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ተከትሎ በርከት ያሉ የሥራ ዘርፎች በገንዘብ ፍስት እጥረትና ማሻሻያው ይዟቸው በመጡ ለውጦች አሉታዊ ተፅእኖ አሳድሮ መቆየቱን ጠቅሰው፤ ከእነዚህ ዘርፎች መካከል የግንባው ዘርፍ አንዱ መሆኑን ተናግረዋል።

መንግሥት በዘርፉ ያሉ ችግሮች ተመልክቶ አስፈላጊውን መፍትሔ እንዲሰጥበት ማሕበሩ በመጠየቅ ላይ እንደሚገኝም ለአሐዱ አስረድተዋል።

በተለይም በሲሚንቶና ብረታብረት ግብአቶች ላይ ከፍተኛ የዋጋ ንረት እንዳለም ፕሬዝዳንቱ ከሰጡን ቃለመጠይቅ ለማወቅ ተችሏል።

በአማኑኤል ክንደያ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

#አሐዱ_ትንታኔ

ትንታኔውን ለመከታተል ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👇
https://youtu.be/Z2pt0OfpNW8?si=GdGkWHdz9y56nOfU

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የደሞዝ መቆረጥን የሚቃወሙ መምህራን ላይ ማዋከብና ማንገላታት እየደረሰ መሆኑን የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ገለጸ

ጥቅምት 11/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ያለመምህራን ዕውቅናና ፈቃድ በተለያዩ ምክንያቶች የደሞዝ መቆረጥን የሚቃወሙ መምህራን ላይ ማዋከብና ማንገላታት እየደረሰ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አስታውቋል።

ማህበሩ ከጥቅምት 7 እስከ 9/2017 ዓ.ም ድረስ በአዳማ ከተማ ሲያካሄድ የነበረውን 37ኛ መደበኛ የምክር ቤት ስብሰባ ባለ 11 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት አጠናቋል።

በስብሰባው የማህበሩ የ2016 ዓ.ም የሥራ አፈፃፀምና የኦዲት ሪፖርት ቀርቦ ሰፊ ወይይት የተደረገበት ሲሆን፤ በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ መምህራን ላይ እየደረሱ ያሉ ችግሮች ተነስተዋል።

በዚህም መምህራንን እየተፈታተነ ያለው ከፍተኛ የኑሮ ውድነት፣ ረጅም ጊዜ አገልግሎት ያላቸው መምህራን የደረጃ እድገት ወይም የእርከን ጭማሪ አለመኖር፣ በአንዳንድ ክልሎች የመምህራን ደሞዝ በጊዜ አለመከፈል ብሎም እየተቆራረጠ በፐርሰንት መከፈል እንደ ችግር ተጠቅሰዋል።

በተጨማሪም ያለመምህራን ዕውቅናና ፈቃድ በተለያዩ ምክንያቶች የደሞዝ መቆረጥ፤ ይሄንን የሚቃወሙትን ደግሞ ማዋከብና ማንገላታት መኖሩም ተመላክቷል።

እንዲሁም ቀደም ብሎ የተጀመረው የመምህራን የመኖሪያ ቤት እና የመሥሪያ ቦታ በሚፈለገው ፍጥነት እየተከናወነ ያለመሆን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ደግሞ ጭራሽ አለመጀመሩም እንደችግር ተነስቷል።

በሌላ በኩል የመምህራን በትርፍ ሰዓት ክፍያ ላይ ተደራራቢ ግብር መቆረጡ፣ የመጽሐፍትና ሌሎች ግብአቶች እጥረት፣ የክረምት መምህራን ስልጠናና ያጋጠሙ ችግሮች በተሳታፊዎች በአስተያየት እና በጥያቄ መልክ ተነስተዋል።

በቀረቡት ጥያቄዎች ዙሪያ የኢፌዴሪ ትምህርት ሚንስቴር የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ኮራ ጡሹነ እና በት/ት ሚንስቴር የመምህራንና ትምህርት አመራሮች ዴስክን ጨምሮ ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ምላሽ ሰጥተውበታል፡፡

በምላሻቸውም ከመምህራን ጥቅማ ጥቅም ጋር በተያያዘ እየታየ ያለው ጥያቄ የተጀመረው የትምህርት ሴክተር ሪፎርም ተጠናቆ ተግባራዊ ሲሆን፤ ብዙ ጉዳዮች እንደሚፈቱ ገልጸዋል።

በስብሰባው ላይ በ36ኛው ምክር ቤት ያልተሳተፈዉ የአማራ ክልልን ጨምሮ የሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የማህበሩ የምክር ቤት አባላት፣ የዩኒቨርስቲዎች መምህራን ማህበር፣ ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት፣ ከትምህርት ሚንስቴር፣ ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን፣ ከሥራና ክህሎት ሚንስቴር ተወካዮችና የተማሪ ወላጆች ማህበር ፕሬዝዳንት መገኘታቸውን ከማህበሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የ2017 የቴክኒክና ሙያ የመደበኛ ስልጠና ዘመን መቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደረገ

👉ዘንድሮ በቴክኒክና ሙያ የትምህርት ተቋማት 526 ሺሕ 683 ጠቅላላ ሰልጣኞች ይቀበላሉ ተብሏል

ጥቅምት 11/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች የቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና ዘመን መቁረጫ ነጥብ በዛሬው ዕለት ይፋ ተደርጓል፡፡

በዚህም መሰረት የተፈጥሮ ሳይንስ የመግቢያ ውጤት በስልጠና ደረጃ 1 እና 2 ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 141 እና ከዚያ በታች፤ ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች 137 እና ከዚያ በታች እንደሆነ ተገልጿል፡፡

ለሴት ተማሪዎች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 138 እና ከዚያ በታች፤ ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች 134 እና ከዚያ በታች እንዲሁም፤ ለሁሉም የአካል ጉዳተኞች የመቁረጫ ነጥቡ 124 እና ከዚያ በታች መሆኑ ተነግሯል፡፡

እንዲሁም የስልጠና ደረጀ 3 እና 4 ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 142 እና ከዚያ በላይ ሲሆን፤ ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 138 እና ከዚያ በላይ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም የስልጠና ደረጀ 3 እና 4 ሴቶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 139 እና እና ከዚያ በላይ ሲሆን፤ ሴቶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 135 እና ከዚያ በላይ ሆኗል፡፡ ለሁሉም የአካል ጉዳተኞ የመቁረጫ ነጥቡ 125 እና ከዚያ በላይ መሆኑም ተመላቷል፡፡

የስልጠና ደረጀ 5 ደግሞ፤ ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 179 እና ከዚያ በላይ ሲሆን፤ ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 167 እና ከዚያ በላይ መሆኑ ተነግሯል፡፡

በዚሁ የስልጠና ደረጀ 5 ሴቶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 170 እና እና ከዚያ በላይ፤ ሴቶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 162 እና ከዚያ በላይ ሲሆን፤ ለሁሉም የአካል ጉዳተኞ የመቁረጫ ነጥቡ 154 እና ከዚያ በላይ ሆኗል፡፡

በተጨማሪም የማህበራዊ ሳይንስ የመግቢያ ውጤት በስልጠና ደረጃ 1 እና 2 ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 139 ከዚያ በታች፤ ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች 135 እና ከዚያ በታች ያለ ነጥብ ነው፡፡

ለሴቶች በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 134 እና ከዚያ በታች፤ ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች 124 እና ከዚያ በታች በተመሳሳይ ለሁሉም የአካል ጉዳተኞ የመቁረጫ ነጥቡ 124 እና ከዚያ በታች መሆኑ ተመላክቷል፡፡

እንዲሁም የስልጠና ደረጀ 3 እና 4 ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 140 ከዚያ በላይ ሲሆን፤ ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 136 እና ከዚያ በላይ ሆኗል፡፡

ሴቶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 135 እና እና ከዚያ በላይ፤ ሴቶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 125 እና ከዚያ በላይ ሲሆን፤ ለሁሉም የአካል ጉዳተኞ የመቁረጫ ነጥቡ 125 እና ከዚያ በላይ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በተጨማሪ የስልጠና ደረጃ 5 ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 172 ከዚያ በላይ ሲሆን፤ ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 164 እና ከዚያ በላይ ሆኗል፡፡

ሴቶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 165 እና እና ከዚያ በላይ ሲሆን፤ ሴቶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 160 እና ከዚያ በላይ ለሁሉም የአካል ጉዳተኞ የመቁረጫ ነጥቡ 154 እና ከዚያ በላይ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ዘንድሮ በቴክኒክና ሙያ የትምህርት ተቋማት 526 ሺሕ 683 ጠቅላላ ሰልጣኞች እንደሚቀበል የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በዚህም መሰረት 91 ሺሕ 597 ሰልጣኞች በደረጃ 1 እና 2 የሚሰለጥኑ ሲሆን፤ 343 ሺሕ 489 ሰልጣኞች ደግሞ ደረጃ 3 እና 4 ላይ እንደሚገቡ ተነግሯል፡፡ቀሪዎቹ 91 ሺሕ 597 ሰልጣኞች ደግሞ ደረጃ 5 ላይ እንደሚካተቱ ተገልጿል፡፡

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ተከስተዋል የተባሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን እንዲያጣራ የተቋቋመው አጣሪ ኮሚቴ ሪፖርቱን ለቋሚ ሲኖዶስ አቀረበ

ጥቅምት 11/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ተከስተዋል የተባሉትን የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በተመለከተ በዝርዝር በማጣራት ከመፍትሔ ሐሳብ ጭምር እንደያቀርብ የተሰየመው አጣሪ ኮሚቴ ባለፉት አሥራ አምስት ቀናት ሲያከናውናቸው የሰነበተውን የማጣራት ሥራዎች በማስመልከት ያዘጋጀውን ሪፖርት ዛሬ ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም ለቋሚ ሲኖዶስ አቅርቧል።

አጣሪ ኮሚቴው አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በአካል ተገኝቶ ማጣራት እንዳይችል የተከለከለ መሆኑን በመጥቀስ፤ መረጃውን ለማሰባሰብ ይቻል ዘንድ ተበዳዮች በስልክ፣ በቴሌጌራምና በዋትስ አፕ መልዕክቶች፣ በአካል በመቅረብ፣ በሰነድ ማስረጃ በማስደገፍ፣ በድምጽና 3:30 ርዝማኔ ባለው በቪዲዮ በተቀረጸ ማስረጃ ጭምር መረጃዎችን ማሰባሰቡን፣ መተንተኑን፣ ማደራጀቱንና ጥቅም ላይ ማዋሉን ገልጿል።

በሪፖርቱም ከመልካም አስተዳደርና ከብልሹ አሰራር ጋር ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮች በማስረጃ ተደግፈው መቅረባቸው ተነግሯል፡፡

በዚህም የማጣራት ሥራ የተረጋገጡ ጉድለቶችንና ጥፋቶችን መሰረት በማድረግም በጊዜያዊነትና በቋሚነት ችግሮቹን ለመፍታትና የካህናትና የአገልጋዮችን ቅሬታ ዘላቂነት ሊፈቱ ይችላሉ ተብለው የቀረቡ በሰባት ነጥቦች የተተነተኑ የመፍትሔ ሐሳቦችና በዘጠኝ ነጥቦች የተተነተኑ ችግሮቹን በዘላቂነት ሊፈቱ ይችላሉ ተብሎ የታመነባቸው የመፍትሔ ሐሳቦችን አቅርቧል።

ይኸው የጥናት ሰነድ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ቀርቦ ውሳኔ እንደሚሰጥበት ከኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

ክልከላ ተደርጎባቸው የነበሩ በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ወደ አገር ውስጥ እንዲገቡ ተፈቀደ

ጥቅምት 11/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የገንዘብ ሚኒስቴር የነዳጅ ፍጆታ ለመቀነስ በሚል፤ በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ መከልከሉ የሚታወስ ነው።

ይሁንና ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጣ ኮሚቴ በጉዳዮ ላይ ምክክር ካደረገ በኃላ ክልከላው እንደተነሳላቸውና ከጅቡቲ ወደ አገር ውስጥ እንዲገቡ ከውሳኔ ላይ መደረሱን አስታውቋል።

በዚሁ ዙርያ የገንዘብ ሚኒስቴር እና የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ኃላፊዎች በተናጠል የተለያዩ ሀሳቦችን በማንሳታቸው ልዩነት ታይቶ ቆይቷል።

ከሚመለከታቸው የመንግሥት መስሪያ ቤቶች የተውጣጣ ኮሚቴ በማቋቋም ዝርዝር ግምገማዎች በማድረግ ጥያቄ የተነሳባቸው ነዳጅ የሚጠቀሙ ተሽከርካሪዎች የመፍትሔ ውሳኔ ላይ መደረሱን ተገልጿል፡፡

በተደረሰው ውሳኔ መሰረትም፤ የገንዘብ ሚኒስቴር ከጉምሩክ ኮሚሽን ጋር በመተባበር በጅቡቲና ድሬዳዋ ደረቅ ወደብ ላይ የሚገኙ በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች እንዲገቡ መፈቀዱን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በተጨማሪ ባለፈው ዓመት ከየካቲት 26 ቀን 2016 ዓ.ም በፊት የተገዙና በጉምሩክ ተገቢውን ምዝገባ የተደረገላቸው ተሽከርካሪዎች ጉዳይ እየተመከረበት እንደሚገኝም ተጠቅሷል።

ከጅቡቲ ወደ ድሬዳዋ መጥተው እንዲቆዩም ከውሳኔ ላይ ተደርሷል ተብሏል።

ገንዘብ ሚኒስቴር ከዚህ ቀደም ቱሪዝምን ለማበረታታት በሚል ለቱሪዝም ሥራ የሚውሉ ተሽከርካሪዎች እንዲገቡ ፈቅዶ የነበረ ሲሆን፤ እነዚህ ተሽከርካሪዎች ከተጨማሪ እሴት ታክስ ጋር በተገናኘ ውዝግብ ሲነሳባቸው መቆየቱ የሚታወስ ነው።

በአማኑኤል ክንደያ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

ምርጫ ቦርድ ሆን ብሎ ከመደበኛ እንቅስቃሴ ለመገደብ እየሰራ ያለውን ሥራ ሊያቆም ይገባል ሲሉ ፓርቲዎች ገለጹ

ጥቅምት 13/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በጠቅላላ ጉባኤ፣ በኦዲት እና በሴት አባላት በሚገኝ የገንዘብ ድጋፍ ምክንያት ቦርዱ በተለያዩ ጊዜ በአስራ አንድ ፓርቲዎች ላይ የዕግድ ውሳኔ መስጠቱን ትናንት ጥቅምት 12 ቀን 2017 አስታውቋል።

ቦርዱ ለኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በጻፈው ደብዳቤ፤ ዕግድ ውሳኔ የተሰጣባቸው ፓርቲዎች የኦሮሞ ነጻነት ንቅናቄ፣ አንድ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ጨምሮ 11 የሚሆኑ ንቅናቄ ፓርቲዎችን በጊዜያዊነት አግዷል። በዚህ ጉዳይ ላይም አሐዱ ፓርቲዎችን አነጋግሯል፡፡

አሐዱም የዕግድ ውሳኔው የተላለፈበት አንድ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲን ያነጋገረ ሲሆን፤ ቀድሞ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር በክስ ሂደት ላይ መሆኑንና ዕግድ የተጣለበት እንደነበር አስታውቆ፤ "በድጋሚ ትዕዛዝ ማስተላለፉ አዲስ ነገር ነው" ብሏል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ገለልተኛነቱ ጥያቄ ውስጥ የሚገባ ነው ያለው ፓርቲው፤ ማብቃትና ማደራጀት ኃላፊነቱ እንደነበር ገልጿል።

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አንድ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ሂሳብ ላይ በተደረገ የኦዲት ምርመራ ከቦርዱ በ2015 የተበጀተለትን የ2 ሚልየን 750 ሺሕ 873 ብር በአመራሮቹና አባላቱ መመዝበሩን በመግለጽ፤ ከመጋቢት 4 ቀን 2016 ጀምሮ ፓርቲውን ማገዱ ይታወሳል፡፡ የትናንቱ እግድ ዳግመኛ የተጣለ ነው፡፡

በተመሳሳይም አሐዱ ያነጋገራቸው የጋምቤላ ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ካነሳቸው ነገሮች የሴት አባላት ቁጥርን በተመለከተ እንደሆነ ገልጾ፤ "ያሉንን የሴት አባላት ቁጥር መዝግበን ያስገባን ቢሆንም በዲጂታል ወይም ከወረቀት ነጻ በመሆነ መልኩ አደራጅታቹ ስጡን ብሎ መልሶናል" ሲል አንስቷል።

"የፖለቲካ ድርጅቶች ያላቸውን አቅም እና የአካባቢያዊ ሁኔታ ያላገናዘበ ነው" ያለው ፓርቲው፤ "የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተለይም በጋምቤላ የነበረውን ወቅታዊ ነገሮችን መገንዘብ አቅቶት ሳይሆን ተፎካካሪ ፓርቲዎችን ለመቀነስ የሚመስል ሁኔታ አለው" ሲልም ገልጿል።

ምርጫ ቦርድ ትናንት ለጋራ ምክር ቤቱ በጻፈው ደብዳቤ፤ በፓርቲዎቹ ላይ የተሰጠው የዕግድ ውሳኔ ውጤት ቦርዱ የተለየ ውሳኔ እስከሚሰጥ ድረስ፤ ለጊዜው ፓርቲዎችን ከማናቸውም ሕጋዊ እንቅስቃሴ ታቅበው እንዲቆዩ ትዕዛዝ ማስተላለፉን አሐዱ መዘገቡ ይታወሳል፡፡

በፍርቱና ወልደአብ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

#አሐዱ_ትንታኔ

ትንታኔውን ለመከታተል ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👇
https://youtu.be/0i2ypQpLJew?si=lZiQrLD5CeY1Un0b

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

ኮርፖሬሽኑ በፒያሳ መልሶ ማልማት ዘመናዊ የንግድ ሞሎችንና የመኖሪያ ቤቶችን በ6 ወራት ለመገንባት ከኦቪድ ግሩፕ ጋር ተስማማ

ጥቅምት 12/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በፒያሳ መልሶ ማልማት ዘመናዊ የንግድ ሞሎችንና የመኖሪያ ቤት በ6 ወራት ለመገንባት ከኦቪድ ግሩፕ ጋር መስማማቱ ተገልጿል።

ፒያሳን መልሶ የማልማት አካል በሆነውና በ9 ነጥብ 5 ሄክታር መሬት ላይ የሚያርፈው ይህ የፕሮጀክት ስምምነት የተፈረመው፤ በኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አሰፈጻሚ አቶ ረሻድ ከማል እና በአቪድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዮናስ ታደሰ መካከል ነው፡፡

በስምምነቱ መሠረትም የወርቅ ቤቶች፣ የንግድ ሱቅ ሞል፣ መዝቦልድ ሞል እና ጣይቱ የመኖሪያ አፓርትመንትን ጨምሮ፤ በአልሙኒየም ፎርም ወርክ ቴክኖሎጂ የሚገነቡ ቤቶችን በ6 ወራት ጊዜ ውስጥ ገንብቶ በሚጠናቀቅ ወደ አገልግሎት ለማስገባት እቅድ መያዙ ተገልጿል።

ይህንኑ ተከትሎ ግንባታውን በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ለማጠናቀቅ አስፈላጊው የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መጠናቀቃቸው ታውቋል።

ለአዲሲቷ ፒያሳ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን ጉልህ አስተዋጽዖ አላቸው የተባሉት የንግድ ሞሎችና ኘላዛዎች፤ በአጭር ጊዜ ተገንብተው ለአገልግሎት እንደሚበቁ አቶ ረሻድ ከማል ስምምነቱ በተፈረመበት ወቅት ገልጸዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ዘመናዊ የመኖሪያ ቤት በዚሁ ስፍራ ላይ እንደሚገነባም ዋና ሥራ አስፈጻሚው አስታውቀዋል።

ኮርፖሬሽኑ ፕሮጀክቶቹን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ የሚያስችለውን ዘመናዊ የፕሮጀክት አስተዳደር የዘረጋ በመሆኑ፤ የሳይቶቹን ግንባታ በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ እንደሚያስችለውም አክለዋል።

በኮርፖሬሽኑ ታሪክም በብዛት እና በዘመናዊነቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚገነባ የመጀመሪያው የንግድ ሞሎችና ፕላዛ ግንባታ ፕሮጀክት መሆኑንም ዋና ሥራ አስፈፃሚው ጠቁመዋል።

የአቪድ ግሩኘ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ዮናስ ታደሰ በበኩላቸው ከዚህ በፊት ከኮፖሬሽኑ ጋር በመሆን በ18 ወራት ጊዜ ውስጥ ግዙፍ የመኖሪያ መንደር ገንብተው ማጠናቀቃቸውን አሰታወሰው፤ ውለታ የገቡትን የንግድ ሞሎችን እና የመኖሪያ ቤቶችን በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ኦቪድ አጠናቆ እንደሚያስረክብ ቃል ገብተዋል።

ሳይቶችን በ6 ወራት ለማጠናቀቅ የሚያስችለው የአልሙኒየም ፎርምወርክ ቴክኖሎጂም ለግንባታ ዝግጁ ማድረጋቸውንም ነው አቶ ዮናስ የተናገሩት፡፡

ፕሮጀክቶችን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ አሁን ያለው የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዘመናዊ የፕሮጀክት አስተዳደር ሥርዓት ምቹ እንደሆነም አውስተዋል።

ሞሎቹ እና የመኖሪያ ቤቶቹ የሚገነቡት በፒያሳ መልሶ ማልማት ለልማት ዝግጁ በሆኑት የኮርፖሬሽኑ ይዞታዎች ላይ መሆኑም ተመላክቷል።

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

ጎጎት ፓርቲ ሸማ ተራ በደረሰው ድንገተኛ የእሳት አደጋ ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች ለማቋቋም የተቀናጀ ዘመቻ እንዲጀመር ጠየቀ

ጥቅምት 12/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ትናንት ከምሽቱ 1:00 ሰዓት ገደማ በአዲስ አበባ አዲስ ክ/ከተማ መርካቶ በተለምዶ ሸማ ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በደረሰው ድንገተኛ የእሳት አደጋ ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች ለማቋቋም የተቀናጀ ዘመቻ እንዲጀመር፤ ጎጎት ለጉራጌ አንድነት እና ፍትሕ ፓርቲ ጠይቋል፡፡

ፓርቲው በግምት ከምሽቱ 1:00 አካባቢ በንግድ ማዕከላት ላይ በደረሰው ድንገተኛ የእሳት አደጋ እስካሁን ግምቱ በውል ያልተለየ የንብረት ውድመት መድረሱን ገልጿል።

"አደጋው በቁጥጥር ስለመዋሉ እንጂ በአደጋው ስለደረሰው ዝርዝር ጉዳት እስካሁን ከመንግሥት የተገለጸ ባይሆንም፤ በቦታው ባደረግነው ምልከታ የደረሰው ጉዳት እጅግ ከፍተኛ መሆኑ መመልከት ችለናል" ብሏል፡፡

መንግሥት የእሳት አደጋው መንስኤ፣ ለምን ቶሎ በቁጥጥር ሥር ማዋል እንዳልተቻለ፣ ከአደጋው ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ አካላት ስለመኖራቸው፣ እንዲሁም በአደጋው ስለደረሰው ዝርዝር የንብረትና የአካል ጉዳት ፈጣን ማጣራት አድርጎ ለሕዝብ ይፋ እንዲያደርግም ፓርቲው ጠይቋል።

የደረሰው ጉዳት ላቅ ያለ በመሆኑ የመንግሥትና ህዝብ ትብበር የሚጠይቅ መሆኑን የገለጸው ጎጎት ፓርቲ፤ የተቀናጀ የመልሶ ማቋቋም ሥራ እንዲጀመር መንግሥት ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት በመስጠት የተለያዩ ቴክኒካል ኮሚቴዎችና ገንዘብ ማሰባሰቢያ ቋቶችን ፈጥሮ ሕዝብን እንዲያስተባብርም አሳስቧል፡፡

በደረሰው ውድመትም የተሰማውን ሐዘን የገለጸው ፓርቲው፤ ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች መልሶ ለማቋቋም በሚደረገው ጥረት መንግሥትን ጨምሮ ሁሉም አካላት ያልተቆጠበ ትብብርና ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪውን አቅርቧል።

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በመዲናዋ 14 ነጥብ 3 ሄክታር መሬት ለሊዝ ጨረታ ቀረበ

ጥቅምት 12/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 143 ሺሕ 140 ካሬ ሜትር መሬት ለሊዝ ጨረታ አቅርቧል፡፡

የሊዝ ጨረታው ከጥቅምት 8 እስከ 21 ቀን 2017 ዓ.ም ክፍት መደረጉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

መግለጫውን የሰጡት በቢሮው የለማ መሬት ማስተላለፍና የሊዝ ክትትል ዳይሬክተር ጫሊ አብርሀም፤ ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ ውጭ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ለጨረታው የቀረቡ መሬቶች መኖራቸውን ተናግረዋል።

ይህ ከ2016 ዓ.ም ወዲህ አራተኛው ዙር ሲሆን፤ በዚህኛው ዙር ብቻ አጠቃላይ የቀረበው 143 ሺሕ 140 ካሬ ሜትር ቦታ ነው ተብሏል።

ይህም በከተማ አስተዳደሩ ታሪክ በቁጥር ከፍተኛው መሆኑ ተመላክቷል ሲል ኤፍቢሲ ዘግቧል።

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በብሪክስ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ሩሲያ ካዛን ገቡ

ጥቅምት 12/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ኢትዮጵያ ለመጀመርያ ጊዜ እንደ አባል ሀገር በምትሳተፍበት በ16ኛው የብሪክስ (BRICS) የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ሩሲያ ገብተዋል፡፡

የጉባዔው አዘጋጅ የሩሲያዋ ታታርስታን ግዛት ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ባወጣው መግለጫ፤ "የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በBRICS የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ካዛን ገብተዋል" ያለ ሲሆን፤ በካዛን አለም ዓቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የግዛቷ ፕሬዝዳንት ሩስታም ሚኒካኖቭ አቀባበል እንዳደረጉላቸው አስታውቋል፡፡

በዚህ ኢትዮጵያ ለመጀመርያ ጊዜ እንደ አባል ሀገር የምትሳተፍበት የብሪክስ አባል ሀገራት በሩሲያ ካዛን የሚደረገው የመሪዎች ጉባኤ ላይ በጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ትወከላለች፡፡

የዘንድሮው የብሪክስ ሀገራት ስብሰባ ከዛሬ ማክሰኞ እስከ ሐሙስ ድረስ የሚካሄድ ሲሆን፤ ከመስራቾቹ 5 ሀገራት፣ ማለትም ከብራዚል፣ ሩስያ፣ ህንድ፣ ቻይና እና ደቡብ አፍሪካ በተጨማሪ የአዳዲሶቹ አባል ሀገራት ማለትም የኢትዮጵያ፣ ግብፅ፣ ኢራን እና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በስብሰባው ላይ ለመጀመርያ ግዜ ይካፈላሉ።

በተጨማሪም በስብሰባ ላይ ከ30 ሀገራት በላይ ተወካዮች በጉባዔው ይታደማሉ መባሉን ከሩሲያ የዜና አገልግሎት ታስ ዘግቧል፡፡

የዘንድሮው የመሪዎች ስብሰባ በዋናነት 'BRICS Pay' የተባለ አዲስ አለም አቀፍ የግብይት ስርዐት ላይ እንደሚያተኩር የተገለጸ ሲሆን፤ ይህ የግብይት ስርዓት ስዊፍት (SWIFT) የተባለውን የምዕራባውያን የገንዘብ ዝውውር ስርዐት የሚገዳደር እንዲሆን መታሰቡ ተመላክቷል፡፡

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

መልካም ቀን!
አሐዱ ሬድዮ 94.3  የኢትዮጵያውያን ድምፅ!

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በመዲናዋ መርካቶ ሸማ ተራ አካባቢ ከፍተኛ የእሳት አደጋ ተከሰተ

ጥቅምት 11/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በአዲስ አበባ አዲስ ክ/ከተማ መርካቶ በተለምዶ ሸማ ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከፍተኛ የእሳት አደጋ ተከስቷል።

የእሳት አደጋው ዛሬ ማምሻውን የተከሰተ ሲሆን፤ ቃጠሎውን ለማጥፋት የእሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን እንዲሁም የአካባቢው ማህበረሰብ እርብርብ እያደረገ እንደሚገኝ ተነግሯል። ነገር ግን የእሳቱ መጠን ከፍተኛ በመሆኑ እስካሁን መቆጣጠር አለመቻሉ ተገልጿል።

እስካሁን የእሳት አደጋው መንስዔ ምን እንደሆነ የተረጋገጠ ነገር ባይኖርም፤ የአካባቢው ማህበረሰብ ንብረቱን ከአደጋው ለማትረፍ ወደ ሌላ ቦታ እያሸሸ እንደሚገኝ ታውቋል።

የእሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የእሳት አደጋው በንግድ ሱቆች ላይ መነሳቱን ገልጾ፤ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ሥር ለማዋል የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞችና ባለድርሻ አካላት ርብርብ እያደረጉ እንደሚገኝ አስታውቋል።

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

#አሐዱ_አንቀፅ

ጥንቅሩን ለመከታተል ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👇
https://youtu.be/pRlKMPH6Uh0?si=BXUpAXeLiLC0XM9s

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የካፍ የወዳጅነት የእግር ኳስ ጨዋታ ላይ ተካፈሉ

ጥቅምት 11/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደ የካፍ የወዳጅነት የእግር ኳስ ጨዋታ መካፈላቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡

በኢትዮጵያ አዘጋጅነት እየተደረገ ለሚገኘው የካፍ 46ኛ ጠቅላላ ጉባዔ ማድመቂያ ከሆኑ መርሐግብሮች አንዱ የሆነው የአፍሪካ እግርኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) አባላት እና ከተለያዩ ሀገራት የተወጣጡ የቀድሞ ተጫዋቾች የወዳጅነት ጨዋታ ዛሬ ከ 9 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ስታዲየም ተከናውኗል።

በወዳጅነት ጨዋታውም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ እና የካፍ ፕሬዚዳንት ፓትሪስ ሞትሴፔን ጨምሮ የቀድሞ እውቅ የአህጉሪቱ ተጫዋቾች ሳሙኤል ኤቶ፣ ጄጄ ኦካቻ እና አልሃጂ ዲዩፍ ተሳትፈዋል።

በተያያዘ ዜና ዛሬ ጠዋት ኢትዮጵያ እያስተናገደች ከምትገኘው 46ኛው የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) መደበኛ ጉባኤ አስቀድሞ የካፍ ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ሞትሴፔን እና የካፍ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ከፍተኛ አመራሮችን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በጽሕፈት ቤታቸው መቀበላቸውን ገልጸዋል፡፡

በዚህም በመጠናቀቅ ላይ ያለውን የአደይ አበባ ስታዲየምንም መጎብኘታቸውንና "ኢትዮጵያ ይህ ጠቃሚ ጉባኤ የተሳካ እንዲሆን ለማገዝ በሚገባ ተዘጋጅታለች" ሲሉ መናገራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ምደባ በቅርቡ እንደሚገለጽ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ

ጥቅምት 11/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡና ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች በመደበኛ እና በ 'Remedial' ፕሮግራም ትምህርታቸውን ለሚከታተሉ ተማሪዎች የተቋም ምደባ በቅርቡ እንደሚገለጽ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ከዚህ ቀደም ሚኒስቴሩ የማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም እና የትምህርት መስክ ምርጫቸውን በየትምህርት ቤታቸው በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ መስከረም 30/2017 ዓ.ም ድረስ ሞልተው እንዲጨርሱ ያሳሰበ ቢሆንም፤ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች በሲስተም ችግር ምክንያት የተማሪዎቻችንን የትምህርት መስክ እና የዩኒቨርስቲ ምርጫ መሙላት ተቸግረናል" ባሉት መሰረት የምርጫ መሙያ ጊዜውን እስከ ረቡዕ ጥቅምት 6/2017 ዓ.ም ድረስ ማራዘሙን ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

በዚህም መሰረት ሚኒስቴሩ ዛሬ በይፋዊ የፌስ ቡክ ገፁ ላይ ባወጣው መረጃ "በ2016 የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ምደባ በቅርቡ ይገለፃል" ብሏል። ይህንን በመገንዘብ ተማሪዎች በትዕግስት እንዲጠባበቁ ሚኒስቴሩ ጥሪ አቅርቧል።

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

#UPDATE
በጫሞ ሀይቅ ላይ የተከሰተው አደጋ ለጀልባ በተከለከለ ስፍራ ከመጠን በላይ ሰው ይዞ በመጓዝ የተፈጠረ መሆኑ ተገለጸ

👉በአደጋው የሦስት ሰዎችን ሕይወት ማዳን ቢቻልም 13 ሰዎች ሕይወታቸውን ማጣታቸው ተገልጿል


ጥቅምት 11/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከአቡሎ አርፋጮ ወደ አርባምንጭ ከተማ 16 ሰዎችን እና ሙዝ ጭና ስትጓዝ የነበረች ጀልባ ባሳለፍነው ሐሙስ 10 ሠዓት ከ20 ገደማ ጫሞ ሐይቅ ላይ መስጠሟ ይታወሳል፡፡

ለጊዜው በተለያዩ ስጋቶች በመኖራቸው እንዲሁም በጸጥታ ችግር ሳቢያ የትኛውም አይነት ጀልባ እንዳይጓዝ በተከለከለበት በጫሞ ሐይቅ ላይ 16 ሰዎችን እንዲሁም ሙዝ ጭና ስትጓዝ የነበረች ጀልባ ሰምጣ፤ ከተሳፈሩ 16 ሰዎች ውስጥ ሁለቱ በህይወት ተገኝተው የተቀሩትን 14 ሰዎች የመፈለጉ ሥራ ቀጥሎ መቆየቱን የጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ የሕዝብ ግንኙነት ገጽታ ግንባታ ዲቪዥን ኋላፊ ኮማንደር ረታ ተክሉ አስታውሰዋል፡፡

አሁን ላይ የሦስት ሰዎችን ሕይወት በፍለጋ ማዳን መቻሉን እና 13 ደግሞ ሕይወታቸው ማጣታቸውን ኮማንደር ረታ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

አክለውም የሟቾች አስክሬን ከእልህ አስጨራሽ ፍለጋ በኋላ ሙሉ በሙሉ መገኘቱን አውስተው፤ ወደ ቤተሰቦቻቸው መላኩንም ገልጸዋል።

̎የአደጋው መንስኤ በተከለከለበት ቦታ መጓዛቸው ብቻ ሳይሆን ጀልባዋ ከመጫን አቅሟ በላይ በመጫኗ ነው̎ ያሉት ኮማንደር ረታ፤ የጀልባዋ የመጫን አቅም 35 ኩንታል ቢሆንም በዕለቱ 70 ኩንታል ሙዝ እና 16 ሰዎችን ጭና እንደነበር አስረድተዋል፡፡

አሐዱም አያይዞ በተለያዩ ጊዜያት በአባይና በጫሞ ሐይቅ ላይ በተለያዩ ምክንያቶች እንዲህ አይነት አደጋዎች ሲከሰቱ ይስተዋላል ከዚህ ጋር በተያያዘ ችግሩን ለምን መቆጣጠር አልተቻለም? ሲል ጠይቋል።

ኃላፊው በምላሻቸው አደጋው ለመቆጣጠር ሥራዎች መሰራታቸውን ተናግረው፤ አብዛኛው የሚከሰቱ አደጋዎች ሕገወጥ ጉዞ እንዲሁም ከጀልባዋ የመጫን አቅም በላይ ጭነት ሳቢያ በመሆኑ በሚመጡ ቀናት ችግሩን ሙሉ ለሙሉ የመቆጣጠር ሥራ እንደሚሰራ አስታውቀዋል፡፡

በወልደሀዋርያት ዘነበ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳን እንድተካ በእጩነት ስለመቅረቤ የደረሰኝ መረጃ የለም ሲሉ አምባሳደር ወንድሙ አሳምነው ገለጹ

ጥቅምት 11/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የትግራይ ክልል ግዚያዊ አስተዳዳር ፕሬዝዳነት የሆኑትን አቶ ጌታቸው ረዳን ለመተካት በፌደራል መንግሥት አምባሳደር ወንድሙ አሳምነው በዕጩነት መቅረባቸው እየተዘገበ ይገኛል፡፡

በዚህም አሐዱ በፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ ምትክ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት ዕጩ ስለመሆናቸው የደረሳቸው መረጃ ስለመኖሩ አምባሳደር ወንድሙን ጠይቋል፡፡

አምባሳደር ወንድሙ ይህንን ጥያቄ ሲመልሱ፤ "የተባለውን ነገር ሰዎች ነግረውኛል፤ ይሁን እንጂ እኔ ጋር የደረሰ  ምንም ዓይነት ይፋዊ ነገር የለም" ብለዋል፡፡

"እኔ የጀመርኩትን ሥራ እየሰራው እገኛለው" ሲሉ ለአሐዱ የተናገሩት አምባሳደር ወንድሙ፤ "በቀጥታ በዚህ ላይ ያወራኝ አካል የለም" ሲሉም አክለው ተናግረዋል፡፡

በትግራይ ያለው ችግር የማይፈታ ነው ብለው እንደማያምኑ የተናገሩት አምባሳደር ወንደሙ፤ ሁሉም ወደ ውይይት የሚመጣበትን መፍትሄ መፈለጉ ተገቢ ነው ብለው እንደሚያስቡም ገልጸዋል፡፡

አሐዱም "ለመሆኑ ክልሉን የሚረከቡ ከሆነ በክልሉ በህወሓት መከፋፈል የተፈጠረውን ውጥረት ጨምሮ ከጦርነት ማግስት ያጋጠሙ ሰብዓዊ ቀውሶች፣ የተፈናቃዮች ችግር በምን መልኩ ሊፈቱት ይችላሉ?" ሲል አምባሳደሩን ጠይቋል፡፡

አምባሳደሩ ከጉዳይ ጋር በተያያዘ ግምታቸውን ማስቀመጥ ፍላጎት እንደሌላቸው ገልጸው፤ አሁን የጀመሩትን በህወሓት መካከል ያለውን ውጥረት ለማርግብ ከ7ቱ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር በመሆን ችግሩን ለመቅረፍ ሥራቸውን እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

አምባሳደር ወንድሙ አሳምነው በተለያዩ ሀገራት አምባሳደር ሆነው ያገለገሉ ሲሆን፤ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር  እንዲሁም በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ድርድር ላይ የትግራይ ልዑክ አባል ነበሩ። በአሁን ወቅትም የገርዓላታ ኢንስቲትት ዋና ዳይሬክተር በመሆን እየሰሩ ይገኛሉ፡፡

በእነ ደብረፅዮን የሚመራው የህወሓት ቡድን መስከረም 27 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ 12 የጊዚያዊ አስተዳደሩ ላይ ያሉ በጉባኤ ያልተሳተፉ ያላቸውን አመራሮች ማንሳቱን መግለጹ የሚታወስ ሲሆን፤ የፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳን ጉዳይ ደግሞ ከፌደራል መንግሥት ጋር እየተወያየ መሆኑን መግለጹ ይታወሳል፡፡

በአቤል ደጀኔ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጭ ግንባር (ኦብነግ) በብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን ውስጥ የነበረውን ተሳትፎ ማቆሙን አስታወቀ

ጥቅምት 11/2017 (አሐዱ ሬዲዮ)የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) አሳታፊነትና ግልጸኝነት ስላላየሁበት ከአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተሳታፊነት እራሴን አግልያለሁ ሲል ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

በሶማሌ ክልል ገዢው ፓርቲ በቅርቡ የወሰዳቸው እርምጃዎች ተሳታፊዎችን አንድ ወገንን በመምረጥ፣ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ያለውን ስምምነት በመጣስ እና የተለያዩ ድምፆችን ወደ ጎን በመተው ሂደቱን አግላይ በማድረጉ ምክንያት ራሱን ከምክክር ሂደቱ ማግለሉን ነው የገለጸው፡፡

ሁሉንም ባለድርሻ አካላት በማሰባሰብ የግጭት መንስኤዎችን ለመፍታት የታቀደውን የብሔራዊ ውይይት ዓላማን የሚቃረን፣ ከአማራ፣ ከኦሮሚያ እና ከትግራይ የተውጣጡ ቁልፍ የፖለቲካ ተዋናዮች በሌሉበት እና እየተከሰቱ ያሉ ግጭቶችን ለመፍታት ጥረት እየተደረገ ባልሆነበት ሁኔታ፣ አሁን ያለው ውይይት የአንድ ወገንን ያማከለ በመሆኑ እውነተኛ ሰላም የማምጣት አቅም የሌለው መሆኑን ፓርቲው በመግለጫው አንስቷል።

ኦብነግ ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ማምጣት የሚችል እውነተኛ፣ ሁሉን አቀፍ እና ግልጽ ውይይት ለማድረግ ቁርጠኛ ቢሆንም፤ እንዲህ ያለው ምክክር ሁሉን አቀፍ እና ታእማኒ እስኪሆን ድረስ አሁን ባለው ማዕቀፍ ውስጥ አልሳተፍም ሲል ገልጿል።

የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጭ ግንባር (ኦብነግ) በ2010 ዓ.ም ሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴን ለማድረግ ከመንግሥት ጋር ስምምነት አድርጎ ወደሀገር ውስጥ መግባቱ የሚታወስ ነው፡፡

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

"የቱንም ያክል ኢኮኖሚው ላይ ቢሰራ ሰላም ካልሰፈነ ለዉጥ የለዉም" የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች

ጥቅምት 11/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ የቱንም ያክል ኢኮኖሚው ላይ ቢሰራ ሰላም ካልሰፈነ ለዉጥ የለዉም ሲሉ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ገልጸዋል።

በአገሪቱ አሁን ባለዉ የሰላም እጦት ምክንያት ዜጎች ለተለያዩ ችግሮች እየተጋለጡ መሆኑንና በኢኮኖሚ እድገቱ ላይ ተጽዕኖ እያሳደረ እንደሚገኝ ባለሙያዎቹ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

በአለም ደረጃ ድህነት ውስጥ ከሚኖረው ሕዝብ መካከል ግማሽ ቢሊዮን የሚጠጋው ግጭት ባለበት አካባቢ የሚኖር መሆኑ ይፋ መደረጉ አይዘነጋም።

ይሁን እንጂ እንደ ኢትዮጵያ ሲታይ ደግሞ 86 በመቶ የሚሆነው ድህነት ላይ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በኢትዮጵያ ዘላቂ የኢኮኖሚ እድገትን ለማረጋገጥ የሰላምና ደህንነት ጉዳይ ሊታሰብበት እንደሚገባ የምጣኔ ሀብት ባለሙያው አቶ መሀመድ አብራር ተናግረዋል፡፡

አክለውም ባለዉ የጸጥታ ችግር ምክንይት ዜጎች እየተፈናቀሉ፤ በሰላም ወጥተው እንዳይሰሩ እየተደረገ ባለበት ሁኔታ እድገት ሊመጣ እንደማይችል አመላክተዋል፡፡

ሌላኛው የምጣኔ ባለሙያ ዶክተር አጥላው አለሙ በበኩላቸው፤ ̎ለድህነት እየተጋለጥን ያለው ሰላም ባለመኖሩ ምክንያት፣ ሀብት በአግባቡ ባለመጠቀም፣ እንዲሁም የማክሮ ኢኮኖሚው ኑሮ ውድነትን እንዲባባስ በማድረጉ ወደተባባሰ ድህነት እንዲገባ እያደረገ ነው̎ ሲሉ አንስተዋል፡፡

እንዲሁም ያለውን ሐብት ለግጭትና ጦርነት ግብአት እየሆነ ባለበት ሁኔታ ኢኮኖሚዉን ለማንሰራራት መሞከር አግባብ አደለም ብለዋል።

ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገቷ እያሽቆለቆለ መምጣቱን ተከትሎ፤ ያለውን የኑሮ ውድነት ለመቀነስ እንዲሁም ዜጎች በሰላም ሰርተው እንዲገቡ ያለዉን የሰላም እጦት መንግሥት ማረጋጋት ይገባዋል ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

በአለምነው ሹሙ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…
Subscribe to a channel