ahaduradio | Unsorted

Telegram-канал ahaduradio - AHADU RADIO FM 94.3

19349

አሐዱ ራድዮ 94.3 Your source for top local and international news and analysis. "Voice of Ethiopian" የአሐዱ የቴሌግራም ቻናል ቤተሰብ በመሆን ወቅታዊና እውነተኛ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ

Subscribe to a channel

AHADU RADIO FM 94.3

ባጋጠመ ብልሽት ምክንያት የድሬዳዋ፣ የሀረረ፣ የጅግጅጋ ከተሞች እና አካባቢያቸው የኃይል አቅርቦት መቋረጡ ተገለጸ

ጥቅምት 24/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በሁርሶ ኃይል ማከፋፊያ ጣቢያ ላይ ባጋጠመ ብልሽት ምክንያት በምስራቁ የኢትዮጵያ ክፍል በሚገኙ የድሬ ዳዋ፣ የሀረረ ፣ የጅግጅጋ ከተሞች እና አካባቢያቸው የኃይል አቅርቦት መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል፡፡

በመሆኑም በአካባቢዎቹ የሚገኑ ደንበኞች በኃይል ማከፋፊያ ጣቢያው ላይ የተፈጠረው ችግር በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በኩል ተጠግኖ አገልግሎቱ እስኪመለስ ድረስ በትዕግስት እንዲጠባበቁ ጠይቋል፡፡

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

'ለእርቅ እና ሽምግልና ተስማምተዋል' ተብሎ እየተሰራጨ ያለው መረጃ ከእውነት የራቀ ነው ሲል ህወሓት ገለጸ

ጥቅምት 24/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በትግራይ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት አባቶች አማካኝነት በመቀሌ ከተማ ተዘጋጅቶ፤ በሁለቱ የህወሓት ቡድኖች መካከል የተደረገው የፊት ለፊት ግንኙነት "ከብፁአን የሃይማኖት አባቶች ተግሳፅና ምክር የዘለለ ውጤት የሌለው ነው" ሲል በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ገለጸ።

በህወሓት አመራሮች መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ለመፍታት አርብ ጥቅምት 22 ቀን 2017 ዓ.ም የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ እና የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤልን ያገናኘ የምክክር መድረክ መከናወኑን አሐዱ መዘገቡ ይታወሳል።

ይህንንም ተከትሎ በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ትናንት ማምሻውን አጭር መግለጫ አውጥቷል።

በመግለጫውም፤ የትግራይን ወቅታዊ ሁኔታ በሰለጠነና በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የታለመውን የምክርና የተግሳጽ መርሃ ግብርን ተከትሎ የተፈጠሩ የተለያዩ ብዥታዎች አሉ።" ሲል ገልጿል።

በብፁዓን አባቶች የተዘጋጀው መርሃ ግብር በትግራይ ህዝብ ላይ ጉዳት ሳያደርስ በሰለጠነ እና በሰላማዊ መንገድ ልዩነቶችን ለመፍታት ምክር እና ተግሣጽ ለመስጠት ያለመ እንደነበርም ህወሓት አስታውቋል።

"በመሆኑም ውይይቱ ልዩነቶችን በሰላማዊ፣ ህጋዊ፣ በመርህ እና በስርዓት መፍታት ይገባል የሚለውን መርህ ላይ ያተኮረና አቋማችንን የሚያጠናክር በመሆኑ አባቶች የሰጡት ምክር እንደግፋለን።" ብሏል።

ነገር ግን በተለያዩ አካላት እና ሚዲያዎች "ለእርቅና ሽምግልና ተስማምተዋል" በሚል እየተሰራጨ ያለው መረጃ ከእውነት የራቀ ነው። ሲል በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

#አሐዱ_መድረክ

"ትግራይ አሁን ተወራለች" ከብሔራዊ ባይቶ ዓባይ ትግራይ (ባይቶና) ፓርቲ ሊቀመንበር ክብሮም በረኸ ጋር የተደረገ ቆይታ፤ ክፍል ሁለት!

ሙሉ ቆይታውን ለመከታተል ከሥር ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ!
👇
https://youtu.be/mxgC1nBmuFw?si=uasg2K0A7edc0Lks

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በህብረተሰቡ ዘንድ ያለው የግንዛቤ እጥረት የአእምሮ ዕድገት ውስንነት ያለባቸው ዜጎችን ለፆታዊ ጥቃት አጋላጭ ነው ተባለ

ጥቅምት 23/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ስለ አእምሮ ዕድገት ውስንነት በህብረተሰቡ ዘንድ ያለው የግንዛቤ እጥረት፤ የአእምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ዜጎች ለፆታዊ ጥቃት እንዲጋለጡ ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥር ተገልጿል።

በአዲስ አበባ የአእምሮ እድገት ውስንነት ላለባቸው ዜጎች የትምህርት አገልግሎት የሚሰጡ 22 ትምህርት ቤቶች ስለመሆናቸውም ተነግሯል፡፡

የአእምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸውን ዜጎች በቤት ውስጥ እንዲቀመጡ ማድረግ አሁንም በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች እንደሚስተዋል፤ የፍቅር ኢትዮጵያ የአእምሮ ዕድገት ውስንነት ማህበር ፕሬዝደንት ማህሌት ንጉሱ ለአሐዱ ተናግረዋል።

የትምህርት አገልግሎት እንዲያገኙ የሚደረግበት ሁኔታ አነስተኛ ስለመሆኑን እና ከትምህርት ገበታቸው ተለይተው በቤት ውስጥ እንዲያሳልፉ መደረጋቸውን የገለጹት ማህሌት፤ ይህ ሁኔታ በማህበራዊ ሕይወታቸው ላይ ከፍተኛ ጫናን እንደሚፈጥር አስረድተዋል፡፡

የማህበሩ ፕሬዚደንት አክለውም፤ "ከማህበራዊ ጫና በተጨማሪ ለፆታዊ ጥቃት ተጋላጭ እንዲሆኑ ያደርጋል" ያሉ ሲሆን፤ ፆታዊ ጥቃት ቢደርስባቸው እንኳን ለመናገር የሚቸገሩበት ሁኔታ ስለመኖሩም ጠቁመዋል፡፡

በመሆኑም "ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር ጥብቅ ግንኙነት ሊኖራቸው ይገባል" ብለዋል።

በሌላ በኩል በአሁኑ ወቅት የአእምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ዜጎችን እየተሰጠ ያለው ትኩረት ዝቅተኛ መሆኑን ያነሱት የማህበሩ ፕሬዝዳንት፤ ማንኛውም አገልግሎት አሰጣጥ የአእምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ዜጎችን ያካተተ ሊሆን እንደሚገባው አሳስበዋል።

በዚህም የጤና፣ የትምህርት እና ማንኛውም አገልግሎት አሰጣጥ የአእምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ዜጎችን ያካተተ ሊሆን ይገባል ብለዋል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ15 ሺሕ በላይ የሚሆኑ አባላት ይዞ በ17 ከተሞች ላይ ቅርንጫፍ ማህበራትን የመሠረተው ፍቅር ኢትዮጵያ የአእምሮ ዕድገት ውስንነት ማህበር፤ 30ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ለተከታታይ አስር ቀናቶች እንደሚያከብር አስታውቋል።

የምስረታ በዓሉን በማስመለከትም በኢትዮ ኩባ አደባባይ ከጥቅምት 25 ቀን እስከ 29 ድረስ የአእምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ዜጎችን ምዝገባ እንደሚያከናውንና፤ እስከ ህዳር 5 በተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚከበርም ገልጿል።

የአእምሮ እድገት ውስንነት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከአራት እስከ አምስት ሚሊየን እንደሚደርስ የተገለጸ ሲሆን፤ ይህም በአለም አቀፍ ደረጃ ያለውን የአእምሮ እድገት ውስንነት ሦስት በመቶ ሊደርስ ይችላል ተብሎ እንደሚታሰብ ተነግሯል።

በእሌኒ ግዛቸዉ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

እናት ፓርቲ በንጽሃን ዜጎች ላይ የሚደረግ ግድያ እንዳሳሰበው ገለጸ

ጥቅምት 23/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በሀገሪቱ እየታየ ያለው የዜጎች ግድያ የጊዜ ጉዳይ እንጂ ተጠያቂነት እንደሚያስከትል እናት ፓርቲ አስታውቋል፡፡

"ኢትየጵያ የምትራመደው በጎሳ የፖለቲካ ዘውድ ከፋፍሎ ነው" በሚል እሳቤ እርስ በርስ ማገዳደል ከተጀመረ ከሦስት አስርት ዓመታት በላይ ተቆጥሯል ሲል ፓርቲው ለአሐዱ በላከው መግለጫ ወንጅሏል፡፡

በንጹሃን ዜጎች ላይ እየታያ ያለው ግድያ የጊዜ  ጉዳይ  እንጂ በሕግ እንደሚያስጠይቅ የገለጸው እናት ፓርቲ፤ በሥም ያልጠቀሳቸውን የፖለቲካ ስርዓቶች ሀገርን ወደ ፊት እናራምዳልን ብለው የተነሱ ቢሆንም፤ "ሕዝብን በጎሳ ከፋፍለው እርስር በእርስ እንዳይተማመን አድረገዋል" ሲል ወቅሷል፡፡

"ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ በዜጎች ላይ ሲፈጸሙ የቆዩ የጅምላ ግድያዎች፤ አተገባበራቸውን መላው የሀገራችን ሕዝብም ሆነ የአለም ዓቀፍ ማህብረተሰብ የሚያውቀዋው ጉዳይ ነው" ሲልም በመግለጫው አስታውቋል፡፡

የፖለቲካ አላማን ለማሳካትም ሆነ የመንግሥትን ስልጣን ለማስጠበቅ ከሚደረጉ የሃይል  እርምጃዎች ተወጥቶ ችግሮች በጠረጴዛ ዙሪያ እንዲፈቱ ከዚህ ቀደም በርካታ ጥረቶችን ሲያደርግ እንደቆየ ያስታወሰው ፓርቲው፤ ነገር ግን ኢትዮጵያ ውስጥ እየተፈጠሩ ያሉ ግጭቶች መቀጠላቸው እንዳሳሰበው ገልጿል።

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ የሚያስገኘው የገቢ ምንጭ እጅግ መቀዛቀዙ ተገለጸ

ጥቅምት 23/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ከደባርቅ ከተማ 32 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኘው የሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ፤ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ፣ በሰሜን ጦርነት እና አሁን በክልሉ በተፈጠረው ግጭት ምክንያት ከቱሪስቶች የሚያስገባው የገቢ ምንጭ በእጅጉ መቀዛቀዙ ተገልጿል፡፡

ለዚህ ደግሞ ዋንኛ ምክንያት የሆነው ቱሪስቶች ለመጎብኘት በክልሉ በሚታዩ አልፎ አልፎ ግጭቶች የደህንነት ስጋት ስለፈጠረባቸው መሆኑን፤ የፓርኩ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ማሩ ቢያድግልኝ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

ኃላፊው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ከመስፋፋቱ በፊት የአካባቢው ማህበረሰብ ከቱሪስቶች እስከ 32 ሚሊዮን ብር ያገኝ እንደነበር አንስተው፤ መንግሥትም እስከ ሰባት ሚሊዮን ብር ገቢ እንደሚያገኝ አስታውሰዋል፡፡

"ነገር ግን የወረርሽኙ መከሰት እንዲሁም የሰሜኑ ጦርነት መከሰቱ፤ በፓርኩ የገቢ ምንጭ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ አሳድሯል" ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ውስጥ በርካታ ብርቅዬ እንስሳቶች የሚገኙ ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ ዋልያ አይቤክስ፣ ቀይ ቀበሮ፣ ጭላዳ ዝንጀሮ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ እንዲሁም የተለያዩ ብርቅዬ እፅዋትና አዕዋፍም መገኛ ነው፡፡

ፓርኩ እ.ኤ.አ በ1978 በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት /ዩኔስኮ/ በዓለም የተፈጥሮ ቅርስነት የተመዘገበ ሲሆን፤ 412 ስኩየር ኪሎ ሜትር አጠቃላይ ስፋት አለው፡፡

በኢትዮጵያም ከፍተኛው ስፍራ ሲሆን፤ ከባህር ወለል በላይ በ1 ሺሕ 500 ሜትር ከፍታ ላይ ይገኛል፡፡ በዚህም ተፈጥሯዊ ፓርኩ የበርካታ የሀገር ውስጥም ሆነ የውጪ የተራራ ወጪዎችን ቀልብ ይስባል፡፡

ፓርቱ በቅርብ ዓመታት ውስጥ ተደጋጋሚ የእሳት ቃጠሎ የደረሰበት ሲሆን፤ በዚህ እና በጦርነት ስጋቶች ምክንያት ከጊዜ ወደጊዜ የቱሪስት መስህብነቱ እየቀነሰ እንደሚገኝ ተነግሯል፡፡

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት በትናንትው ዕለት 120 የመንግሥት ወታደሮችን መግደሉን አስታወቀ

👉ታጣቂዎቹ ዕረቡ ሌሊት ባንዲት መንደር በፈጸሙት ጥቃት 40 ያህል ሰላማዊ ሰዎች መግደላቸው ተሰምቷል


ጥቅምት 23/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት፣ ትናንት በሰሜን ሸዋ ዞን ወጫሌ ወረዳ በኹለት ቦታዎች ላይ በፈጸመው ጥቃት 120 የመንግሥት ወታደሮችን መግደሉን አስታውቋል።

ካራ ከተማ በሚገኝ ወታደራዊ ካምፕ ላይ በፈጸመው ጥቃት 67 ወታደሮችን መግደሉን የገለጠው ቡድኑ፣ "ባጮ ፋሉሚ በተባለ ቦታ በወታደራዊና በትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች ላይ በፈጸምኩት ጥቃት ደሞ 53 ወታደሮችን ገድያለሁ ብሏል።

ቡድኑ፣ "ሕዝቡን ያሰቃዩ ነበር ያላቸውን የአካባቢ አስተዳዳሪዎች ጭምር ገድያለሁ" ማለቱን ዋዜማ ዘግባለች።

ታጣቂዎቹ አደረሱት በተባለው ጥቃት የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ ንጉሴ ኮሩ ጨምሮ በርካቶች መገደላቸው ተሰምቷል፡፡

የወጫሌ ወረዳ አጎራባች የሆነው አለልቱ ወረዳ በይፋዊ ማህበራዊ ገጹ እንዳረጋገጠው፤ የቀድሞ የአለልቱ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ የነበሩትና የአሁኑ የወጫሌ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ንጉሴ ኮሩ ጉርሙ “መግደል ዓለማው በሆነ” ባሉት አካል መገደሉን ገልጾ፤ ግድያውንም አውግዞታል፡፡

በሌላ በኩል በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ዱግዳ ወረዳ ከመቂ ከተማ 18 ኪ.ሜ. ግድም ወጣ ብለው በሚገኙ ገጠራማ መንደሮች ተወስዷል በተባለው በዚህ የታጣቂዎች አስደንጋጭ ጥቃት፤ በአካባቢው ባሉ ቤቶች ላይ እሳት በማያያዝ ብዙዎችን ደግሞ የጥይት እራት ስለመደረጉ ተጎጂ የአይን እማኞች ለዶቼቨሌ ገልጸዋል፡፡

ዕረቡ ጥቅምት 20 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 3:00 ገደማ ጀምሮ እስከ እኩለ ለሊት ተራዝሞ ነበር በተባለው በዚህ ጥቃት፤ ሕጻናትን ጨምሮ እናቶችና አረጋውያን በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው ተሰምቷል፡፡

ለደህንነታቸው ሲባል ሥማቸውን እንዳይጠቀስ የጠየቁ አንድ ተጎጂ እንዳሉት፤ በተለይም በሶዶ ወረዳ አዋሳኝ ኤጄርሳ ሌሌ በሚባል ስፍራ የደረሰው ጉዳት እጅጉን አስከፊ ነው፡፡

“ጥቃቱ ያው እሮብ ምሽት ከሦስት ሰዓት ግድም ጀምሮ ነው ቤት በማቃጠል እና በግድያ የተጀመረው፡፡ ለዚህ ጥቃት ደግሞ “ሸኔ የተባሉ ታጣቂዎች” ያቀረቡት ምክንያት ለምን ከመንግሥት ጋር ተባበራችሁ የሚል ሲሆን፤ ማህበረሰቡ ደግሞ ተደጋጋሚ ጥቃት በታጣቂዎቹ ሲደርስበት ስለነበር እራሱን በማደራጀት ለመከላከል በእንቅስቃሴ ላይ የነበረ ነው” ብለዋል፡፡

“ከዚህ በፊትም ብዙ ሰው እያገቱ ለቀዋል፡፡ ብዙ ስቃይ ነው ስደርስ የነበረው፡፡ አሁን ከፋ ሆነና በዚች ምሽት በብዙ አቅጣጫ ገብተው ሰው ቤት እየዘጉ እሳት እያያዙበት ለመሮጥ የሞከረን ደግሞ በጥይት ሲመቱ ነበር፡፡ በአንድ ጉድጓድ ሦስት-አራት ሰው እያደረግን ትናንት ወደ 40 ሰው ቀብረናል” ሲሉም ተናግረዋል፡፡

የሟቾች አስከሬን በዚያው ሐሙስ ዕለት ጎዜና ደረባ ቀበሌ በሚገኙ ሁለት ቤተክርስቲያን ሲቀበር መዋሉንም አስተያየት ሰጪው አክለው ገልጸዋል፡፡
በዕለቱ ከሰው እልቂት በተጨማሪ እንስሳት ከቤቶች ጋር ስቃጠሉና በርካታ ንብረት ሲወድም ታይቷልም ነው የተባለው፡፡

ከዚህ ቀደም የታጣቂ ቡድኑ አመራር የነበረው ጃል ሰኚ የሚያዙት የቡድኑ ክንፍ፣ ከቡድኑ የበላይ አዛዥ ከጃል መሮ መለየቱንና ከመንግሥት ጋር ለመደራደር ፍላጎት እንዳለው ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

ይህንን ተከትሎም የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ሽመልስ አብዲሳ፣ መንግሥታቸው ጃል ሰኚ ከሚያዙት የአማጺው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ክንፍ ጋር ለመደራደር ዝግጁ መሆኑን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል፡፡

ነገር ግን ታጣቂ ቡድኑ የመንግሥትን ጥሪ ባለመቀበል፤ አሁንም በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በስፋት በመንቀሳቀስ ከመንግሥት ኃይሎች ጋር ሲዋጋ እና በንጹሐን ዜጎች ላይ አሰቃቂ ጥቃቶችን እየፈጸመ መሆኑ እየተገለጸ ይገኛል።

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

መልካም ቀን!
አሐዱ ሬድዮ 94.3  የኢትዮጵያውያን ድምፅ!

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በጋምቤላ ክልል የተከስተው ከፍተኛ የወባ ወረርሽኝ የመቀነስ አዝማሚያ ማሳየቱ ተገለጸ

ጥቅምት 22/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ከዚህ በፊት በጋምቤላ ከተማ በመንገሺ እና ጎሬ ወረዳዎች ከፍተኛ የሆነ የወባ ወረርሽኝ መከሰቱን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታዉቆ እንደነበር አይዘነጋም።

ከሰሞኑ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍልች በተለይም በአማራ ትግራይ እና በአንድ አንድ የደቡብ ኢትዮጵያ ክፍሎች ከፍተኛ የሆነ የወባ ወረርሽኝ ተከስቶ እንደነበር መገለጹ ይታወሳል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም በጋምቤላ በሚገኙ መንገሺ እና ጎደሬ ወረዳዎች እንዲሁም በከተማው ተከሰቶ የነበረዉ ከፍተኛ የሆነ የወባ ወረርሽኝ አሁን ላይ መቀነስ ታይቶበታል ተብሏል፡፡

ለዚህ ደግሞ እንደሀገር የወባ በሽታን ለመከላከል በተጀመረው ዘመቻ የአጎበር ስርጭት እና የኬሚካል ርጭት አስተዋፅኦ ማድረጉን የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር አቤል አሰፋ ገልጸዋል።

በተጨማሪም የወባ ተጋላጭ በሆኑ የክልሉ ወረዳዎች የአካባቢ ጽዳትና ቁጥጥር ሥራዎችን በመስራት፤ የቅድመ መከላከልና ጥንቃቄ ሥራ መከናወኑን አስረድተዋል፡፡

ኃላፊዉ አክለውም የወባ ወረርሽኙን ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት የማህበረሰቡን ተሳትፍ ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ገልጸዉ፤ "በሌሎች ወረዳዎችና አካባቢዎችም እንዳይስፋፋ ጥረት እየተደረገ ነዉ" ብለዋል።

በፅዮን ይልማ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በአማራ ክልል ያለው ግጭት ለቀጣናው ስጋት ነው ሲሉ ምሁራን ገለጹ

ጥቅምት 22/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ አማራ ክልል ያለውን ግጭት ተከትሎ ዜጎች መደበኛ የዕለት ተዕለት ኑሯቸውን ለመኖር በሰላም ወጥቶ መግባት እና መደበኛ እንቅስቃሴዎችን መከወን እንዳልቻሉ ይገለጻል።

"ኢትዮጵያ ብቸኛዋ የሰላም ሚኒስቴር ያላት እንዲሁም ሰላም ማግኘት ያልቻለች ሀገር፤ የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም እያላት ህዝብ የሚያለቅስባት ሀገር ነች" የሚሉት የዲፕሎማሲ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ባለሙያ ጥላሁን ሊበን፤ "ከቀደመው ግጭትና ጦርነት ትምህርት መውሰድ አልተቻለም" ይላሉ።

"አራት ዓመታት የእርስ በእርስ ጦርነትና ግጭት ውስጥ ነበርን" የሚሉት ጥላሁን ሊበን፤ በዚህ ውስጥ በርካታ ዜጎችን ሕይወታቸውን እንዲያልፍ ሆኗል ሲሉ ገልጸዋል።

"በአማራ ክልል ያለው ግጭት በዚሁ የሚቀጥል ከሆነም የአፍሪካ ቀንድ ቀጣና ስጋት ይሆናል" ሲሉም ገልጸዋል።

አሁን ላይ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልል ያለው አለመረጋጋት ወደ ሌሎች ክልሎችም ይዛመታል ያሉ ሲሆን፤ "ከጦርነት የምናተርፈው የወጣትን ሞት ብቻ ነው" ብለዋል።

"በክልሉ ከመንግሥት ጋር በግጭት ውስጥ ያሉ አካላት አላማቸው ምን እንደሆነ፣ 'ያለን አቅም ምን ያህል ነው?'፣ 'ከጎናችን ማን አለ?' የሚሉ ጥያቄዎችን በእውኑ መልሰዋል ወይ?" የሚሉት ደግሞ የቀድሞው አምባሳደር ጥሩነህ ዜናው ናቸው።

እንዲሁም በኢትዮጵያ ያለውን ግጭት ለማባባስ ከውጭ በእጅ አዙር ተሳታፊ የሆኑ አካላት ሊኖሩ እንደሚችል ጠቁመው፤ "የዜጎችን ችግርና እንግልት ከማራዘም ይልቅ መፍትሔው ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል" ሲሉ ገልጸዋል።

"አሁን ላለው ችግር ተጠያቂ የሚሆኑ የተለያዩ አካላት ቢኖሩም ህዝቡ ግን እየተጎዳ ነው" ብለዋል።

በቀጣናው ያለውን ግጭት እንደመልካም አጋጣሚ የሚወስዱት መኖራቸውንም ታሰቢ ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል።

የፌደራል መንግሥት የክልል ልዩ ኃይሎች ህልውና አብቅቶ ወደ ፖሊስና እና የመከላከያ መዋቅሮች እንዲካተቱ መወሰኑን ተከትሎ፣ የአማራ ክልል ልዩ ኃይል መፍረስን በመቃውም የተቀሰቀሰው ግጭት ክልሉን ቀውስ ውስጥ መክተቱ ይታወቃል።

በትናንትናው ዕለት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የምክር ቤቱ አባል እና የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ አብን ተወካይ የሆኑት ዶ/ር አበባው ደሳለለኝ በክልሉ ስላለው ሁኔታ ላነሱት ጥያቄ፤ "መንግሥት አሁንም ለድርድር እና ምክክር ዝግጁ ነው" ሲሉ ምላሽ መስጠታቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

በፍርቱና ወልደአብ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

#አሐዱ_ትንታኔ

ሩስያ የኒውክሌር ሃይሏን ዝግጁነት ለመፈተሸ ከሁለት ቀን በፊት የተሟላ ልምምድ ማስጀመሯ ተሰምቷል፡፡ የዩክሬኑ ጦርነት አለምን ወደሚያሰጋት የኒውክሌር ጦርነት እንዳይወስዳት ተፈርቷል፡፡

ሩስያ አሁን ያደረገቸው ልምምድ በሁለት ሳምንት ውስጥ ሁለተኛው ነው፡፡ ጉዳዩን በዛሬው አለማቀፍ ትንታኔያችን ተመልክተነዋል፡፡
ትንታኔውን ለመከታተል ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👇
https://youtu.be/z-RDlBJR6Fg?si=wa_nKbkV8hYhbDdu

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ እና ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የተገኙበት መድረክ በመቐለ ከተማ መካሄዱ ተገለጸ

ጥቅምት 22/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በህወሓት አመራሮች መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ለመፍታት ዛሬ ጥቅምት 22 ቀን 2017 ዓ.ም በሃይማኖት አባቶች የተዘጋጀ መድረክ፤ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳን እና የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ማገናኘቱ ተሰምቷል፡፡

በመቐለ ከተማ በመካሄድ ላይ እንደሚገኘው መድረኩ በህወሓት አመራሮች ላይ የተፈጠር ልዩነት የሕዝብና የሀገርን ጥቅም በሚያስጠብቅ መልኩ ሰላማዊ በሆነ መንገድ አለመግባባቱን እልባት ለመስጠት በማለም የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በመድረኩም ሁለቱም ወገን ጥሩ የሚባል መቀራረብ ማሳየታቸው የክልሉ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል፡፡

ከሁለት ቀናት በፊት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ በተረጋገጠ የX ገጻቸው ላይ፤ ከዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤልጋር ንግግር ማድረጋቸውን በሚመለከት መልዕክት ማጋራታቸው ይታወሳል፡፡

በመልዕክታቸውም፤ "ከሩቅ የሚመጣ ሰው አያስፈልግም ለመቀራረቡ እኛ እንቀርባለን ብላችሁ እኛን ለማገናኘት በመጣር ላይ ያላችሁ ክብር ይስጣችሁ" ያሉ ሲሆን፤ "ተቀራረቦ እንደመነጋገር የመሰለ ነገር የለም" ብለዋል፡፡

በወቅቱም ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ጋር አብረው የተነሱትን ፎቶ ያጋሩ ሲሆን፤ ይህም በሁለቱ መካከል የንግግር ሂደት መጀመሩን አመላካች እንደሆነ ሲገለጽ ቆይቷል፡፡ የዛሬውም የውይይት መድረክ የዚሁ መቀራረብ አንደኛው አካል እንደሆነ ታምኖበታል፡፡

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የመኖሪያ ፈቃድ ሕግን ተላልፈው ለሚገኙ ኢትዮጵያዊያን የሰጠውን የምህረት አዋጅ ለሁለት ወራት አራዘመ

ጥቅምት 22/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መንግሥት የመኖሪያ ፈቃድ ሕግ ተላልፈው ለሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች የሰጠውን የምህረት አዋጅ ለቀጣይ ሁለት ወራት ማራዘሙን በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ አስታውቋል፡፡

ኤምባሲው ባለፉት ሁለት ወራት ከኢትዮጵያውያን ኮሚኒቲ ማህበር ጋር ባደረገው ጥረት ከ10 ሺሕ የሚልቁ ኢትዮጵያውያን ወረቀት አልባ ዜጎች ያለምንም ቅጣት መኖሪያ ፈቃዳቸውን እንዲያስተካክሉ ወይም እገዳ ተነስቶላቸው አገሪቱን በሕጋዊ መንገድ ለቀው እንዲወጡ ድጋፍ ማድረግ መቻሉን በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ልዩ መልዕክተኛና ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ዑመር ሁሴን ገልጸዋል፡፡

ባለፉት ሁለት ወራት በተለያዩ ምክንያቶች ከአዋጁ ተጠቃሚ መሆን ያልቻሉ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ሳይዘናጉ እስከ ፈረንጆቹ ታሕሳስ 31 ቀን 2024 ድረስ ወረቀታቸውን እንዲያስተካክሉም አምባሳደር ዑመር ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

መልካም ቀን!
አሐዱ ሬድዮ 94.3  የኢትዮጵያውያን ድምፅ!

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

ኢትዮ ቴሌኮም የኢ- ኮሜርስ ዘርፍ በኢትዮጵያ እንዲስፋፋ እያደረገው ያለውን አስተዋፅኦ የማይተካ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ

ጥቅምት 21/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ኢትዮ ቴሌኮም በኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ስር የሚተዳደሩት የመንግስት ልማት ድርጅቶች በእግራቸው እንዲቆሙ እያደረገ ያለውን ሚና የማይተካ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ "የመንግሥት ያደረገውን የኢኮኖሚ ለውጥን ተከትሎ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ወደ ግል እንዲዞሩ ያሳለፈውን ውሳኔ ጊዜውን የጠበቀ ነው" ሲሉ ለምክር ቤቱ ገልጸዋል።

መንግሥት የካፒታል ገበያ እንዲከፈት ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ፤ አለማቀፍ ያሉ ኩባንያዎች አይን ማረፍያቸው የኢትዮጵያ ገበያ እየሆነ መምጣቱን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለምክር ቤት አባላት ሲብራሩ ተደምጠዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ኢትዮ ቴሌኮም የመንግሥትን ለውጥ በእጅጉ እየደገፈ እንደሚገኝ አብራርተዋል።

በቅርቡም ኩባንያው ለሕዝብ ይፋ መደረጉን ጠቅሰው፤ መንግሥታቸው የካፒታል ገበያ በኢትዮጵያ ለማስፋፋት ውጥን ይዞ በመንቀሳቀስ ላይ መሆኑን ለፓርላማው ገልጸዋል።

ከዚህ በተጨማሪም የመንግሥት የልማት እቅዶች የመጡ ለውጦችንም አሐዞችን ጠቅሰው ማብራርያ ሰጥተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ያነሷቸው አንዃር ነጥቦች የግብርና፣ ኢንዱስትሪና አገልግሎት ዘርፉ አበረታች ለውጦች እየተስተዋለበት መሆኑን ለምክርቤቱ ከሰጡት ማብራርያ ሰምተናል።

በአማኑዔል ክንደያ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ:www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ:http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡www.tiktok.com/@ahadutv.official

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

ንግድ ባንኮች ለፋብሪኮች ያቀረቡትን ብድር አቅርቦት እየተጠቀሙበት አይደለም ተባለ

ጥቅምት 24/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ንግድ ባንኮች እያቀረቡት ያለውን ብድር ምንም እንኳን መሻሻሉ ቢገለጽም፤ አምራች ኢንዱስትሪዎች የብድር አቅርቦቱን እየተጠቀሙት አለመሆኑ ተገልጿል።

የብድር አቅርቦቱ ለዘርፉ መነቃቃት አስፈላጊ ከሆኑ ጉዳዮች መካከል አንዱ መሆኑ ቢታመንበትም፤ ገበያቸው ላይ አንዳንድ ያልተረጋጉ ነገሮች መኖራቸውን ተከትሎ አምራች ኢንዱስትሪዎች አቅርቦቱ ለመጠቀም እየደፈሩ አለመሆኑ ነው የተነገረው።

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በበኩሉ የብድር አቅርቦቱን እንዲጠቀሙ ውትወታ እያደረገ መሆኑን በመግለጽ፤ ብድሩን የመጠቀም አዝማምያ እንደሌለ አስታውቋል።

ኢትዮጵያ ታምርት እንቅስቃሴ በርካታ ኢንዱስትሪዎች ከልማት ባንክ ብድር አግኝተው እየተንቀሳቀሱ መሆኑን፤ በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የመሰረተ ልማት አማካሪው አቶ ዳንኤል ኦላኔ ለአሐዱ ተናግረዋል።

ሚኒስቴር መስርያ ቤቱ ኢንዱስትሪዎች የመሰረተ ልማት ዝርጋታን ጨምሮ የግብአት እጥረት እንዳይገጥማቸው የተለያዩ ሥራዎችን እየሰራ እንደሚገኝም አማካሪው ጨምረው ገልጸዋል።

ነገር ግን እነዚህ አምራች ኢንዱስትሪዎች እራሳቸውን በአቅም እንዲያጎለብቱ ታስቦ በንግድ ባንኮች የተመቻቸላቸውን የብድር አቅርቦት ለመጠቀም ያላቸው ፍላጎት ዝቅተኛ መሆኑን ተናግረዋል።

የኢንዱስትሪው ዘርፍ በአገር ጠቅላላ ኢኮኖሚ እያበረከተው ያለውን አስተዋፅኦ ከቀዳሚዎቹ ተርታ የሚሰለፍ መሆኑን፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሰሞኑ ለሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ያቀረቡት ሪፖርት ያስረዳል።

በበጀት ዓመቱም 12 በመቶ እድገት ይኖረዋል ተብሎ እቅድ የተያዘለት ሲሆን፤ በዘርፉ የሚሳተፉ ምጣኔ ሐብት አከናዋኞችን ማበረታታት አስፈላጊ መሆኑን እየተገለጸ ይገኛል።

በአማኑዔል ክንደያ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

መልካም ቀን!
አሐዱ ሬድዮ 94.3  የኢትዮጵያውያን ድምፅ!

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በአስገድዶ መሰወር እና ማፈን ላይ የጸጥታ አካላት መሳተፋቸዉ አሳሳቢ ጉዳይ ነው ተባለ

ጥቅምት 23/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኢትዮጽያ  የተለያዩ አካባቢዎች ላይ በሚስተዋሉ የአስገድዶ መሰወር እና አፈናዎች፤ የጸጥታ አካላት መሳተፍቸዉ አሳሳቢ ጉዳይ መሆኑን አሐዱ ያነጋገራቸው ፖለቲከኞችና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ገልጸዋል፡፡

የፍትህ ተቋማት በዚህ ጉዳይ ላይ በአግባቡ ሥራቸውን መስራት ይኖርባቸዋል ሲሉም አሳስበዋል።

"የሰላምና ጸጥታ ተቋማት የፍትህ ተቋማት ሰዎች በምን መልኩ ነው መያዝ ያለባቸው የሚለውን ጉዳይ ላይ፤ በአግባቡ ሥራቸውን ሊወጡ ይገባል" ሲሉ፤ የነፃነትና እኩልነት ፓርቲ የአደረጃጀትና አቅም ግንባታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙባረክ ረሽድ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

"እነዚህ ተቋማት ሥራቸውን በአግባቡ መከወን ባልቻሉ ጊዜ ስርዓት አለበኝነት ይስፋፋል" ያሉት ኃላፊው፤ የሚመለከታቸው ተቋማት ሥራቸውን በአግባቡ መወጣት እንደሚገባቸው ገልጸዋል።

"በተለያዩ ጊዜያት የሚደርሱን ጥቆማዎች እንደሚያሳዩት፤ በአዲስ አበባ እንዲሁም በክልሎች የፓርቲ አባሎች ላይ የዘፈቀደ እስር እንደሚፈጸም ነው። ይህ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ብቻ መሆን አለበት" ሲሉም አክለዋል፡፡

"ይህ ሁኔታ የሚኖረዉ የአንድ ሀገር የሰብዓዊ መብት ሁኔታ እንዲሁም የሕግ የበላይነት ሲላላ ነው" የሚሉት ደግሞ፤ የሕግ ባለሙያውና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አቶ ያሬድ ሃይለማርያም ናቸው፡፡

አቶ ያሬድ አክለውም፤ "የሚደረጉ አፈናዎችና እስሮች በተመለከተ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ያወጣው ሪፖርትም የሚያሳየው አሁን ያለንበት ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑን ነው" ብለዋል፡፡

"ከሪፖርቱ በመነሳት አፈናው እና እስሩ አንዱ በፖለቲካ አመለካከት የሚመጣ ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ አፈናው የጸጥታ አካላት ጭምር የሚሳተፉበት በመሆኑ ሁኔታውን አስቸጋሪ አድርጎታል" ብለዋል።

በመሆኑም የፍትህ ተቋማት ለሕዝብ እንደተቋቋሙ በማሰብ፤ ሥራቸውን ሕግን በተከተለ መንገድ መስራት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል።

ከሰሞኑ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በአዲስ አበባ ከተማ እንዲሁም በአማራ እና ኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የአስገድዶ መሰወር በተመለከተ አሳሳቦኛል ያለውን ሪፖርት ማውጣቱ ይታወሳል፡፡

በአቤል ደጀኔ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

ተሽከርካሪዎች ደረጃና የአገልግሎት ብቃት የሚለኩበት አዲስ መመርያ እየተዘጋጀላቸው መሆኑ ተሰማ

ጥቅምት 23/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በመዲናዋ የሚዘዋወሩት ተሽከርካሪዎች ጤና የሚመረመሩበት አሰራርን ጨምሮ፤ ወደ አገር ውስጥ የሚገቡት አውቶሞቢሎችን ለመገምገም የሚመለከታቸው አካላት ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን ተሰምቷል።

በኢትዮጵያ ያሉ ተሽከርካሪዎች በአየር ጠባይ ላይ እያደረሱት ያለውን ስጋት እየተባባሰ መምጣቱን ተከትሎ፤ የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የሚያስተባብረው አዲስ መመርያ እየተሰናዳ መሆኑ ነው የተገለጸው።

መመርያው የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር፣ የደረጃዎች ምዘና ኤጀንሲን ጨምሮ የአካባቢ ባለስልጣን መስርያ ቤቶች በጋራ የሚያረቁት ነው ተብሏል።

በኢትዮጵያ እስካሁን ባለው የተሽከርካሪዎች ምርመራ እያስከተሉት ያለውን ችግር መቅረፍ ባለመቻሉ ምክንያት የአለም ዓቀፍ ደረጃን የጠበቀ የምርመራ ስልት እንደሚተገበር፤ የአዲስ አበባ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ዳዳ ዲሪባ ለአሐዱ ተናግረዋል።

ዋና ሥራ አስፈፃሚው የግል ተሽከርካሪ ምርመራ የሚሰሩ ድርጅቶችም አሰራሩን እንዲከተሉ የሚያስገድድ መመሪያ መሆኑን ገልጸዋል።

አክለውም፤ ቀደም ሲል የገለጿቸው ችግሮች ኢትዮጵያ አየር ንብረትን በአለም ዓቀፍ ደረጃ ያላትን ተቀባይነት የሚያኮስስ ሆኖ መገኘቱን አስረድተዋል።

ይህንን ችግር ለመቅረፍም የአለም ዓቀፍ ገንዘብ ድርጅትን ጨምሮ የአየር ንብረት ተቆርቋሪዎች ዘንድ የቀረበ ምክረ-ሐሳብ ሊተገበር መሆኑን ነው አቶ ዳዳ ዲሪባ የገለጹት።

የአየር ንብረት ለውጥ ሚዛን መጠበቅ ረገድ ኢትዮጵያ እያበረከተች ያለችውን እንቅስቃሴ የሚያወድሱ ተቋማት በርካቶች ቢሆኑም፤ በተቃራኒው በተሽከርካሪዎች የሚመነጨው አየር ብክለት እንደ ችግር እየተነሳ ነውም ብለዋል።

"ለዚህም ጥረታችንን ውሀቅዳ ውኃ መልስ እያደረገብን በመሆኑ ዘመን አፈራሽ መመዘኛዎችን ለመጠቀም እንገደዳለን" ሲሉም ጨምረው ገልጸዋል።

የግንዛቤ ሥራን በተመለከተ ከሚመለከታቸው የአየር ንብረት ለውጥ ተቆርቋሪዎች ከትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ቤት ጨምሮ የግሉ ክፍለ ኢኮኖሚ ተሳታፊዎች ጋር በመሆንም ምክክር የሚደረግበት መሆኑንም ከባለስልጣን መስርያ ቤቱ ሰምተናል።

በአማኑዔል ክንደያ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

#አሐዱ_መድረክ

"ትግራይ እራሱን የቻለ ሀገር መሆን አለበት" ከብሔራዊ ባይቶ ዓባይ ትግራይ (ባይቶና) ፓርቲ ሊቀመንበር ክብሮም በረኸ ጋር የተደረገ ቆይታ።

ሙሉ ቆይታውን ለመከታተል ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ!
👉https://youtu.be/ESQyBtiJkRs

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

ትናንት ማምሻውን በአዋሽ ፈንታሌ አካባቢ ንዝረቱ እስከ አዲስ አበባ የተሰማ የመሬት መንቀጥቀጥ በድጋሚ ተከሰተ

ጥቅምት 23/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ አካባቢ ትናንት ምሽት የተለያየ መጠን ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ በድጋሚ መከሰቱን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦፊዚክስ፣ ሕዋ ሳይንስና አስትሮኖሚ ኢንስቲትዩት አስታውቋል።

በዩኒቨርሲቲው የሶሲሞሎጂ ትምህርት ክፍል ሃላፊ አታላይ አየለ (ፕ/ር) እንዳሉት፤ በአዋሽ ፋንታሌ ወረዳና አካባቢው ከትናንት ቀን ጀምሮ የተለያየ መጠን ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል።

ከሌሊቱ 6:13 ላይም የዕለቱ ከፍተኛው በሬክተር ስኬል 4 ነጥብ 6 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።

የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረትም አዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች ድረስ መሰማቱን ነው የገለጹት።

በአካባቢው የመሬት መንቀጥቀጥ በተደጋጋሚ እየተከሰተ መሆኑን ጠቁመው፤ ይሁን እንጂ መጠኑ አነስተኛ ስለሆነ ስጋት እንደማይሆን አስረድተዋል።

በሰመራ ዩኒቨርሲቲ የሥነ-ምድር ጥናት ትምህርት ክፍል ኃላፊ ጌታቸው ገብረጻዲቅ በበኩላቸው፤ አዋሽ ፈንታሌ የሚከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ በአካባቢው ካለው የቅልጥ ዓለት እንቅስቀሴ ጋር የተያያዘ መሆኑን መግለጻቸውን ኤፍቢሲ ዘግቧል።

የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቱ የመቀጠል እድል ይኑረው አይኑረው የሚለውን መገመት እንደሚያስቸግር ኃላፊው ገልጸዋል።

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በመዲናዋ አንዳንድ ተርሚናሎች ላይ የመጫኛና ማውረጃ ቦታ ለውጥ መደረጉ ተገለጸ

ጥቅምት 23/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ በአንዳንድ ተርሚናሎች ላይ የመጫኛና ማውረጃ ቦታ ለውጥ ማድረጉን አስታውቋል።

በዚህም መሰረት፦
መገናኛ ውስጥ ተርሚናል አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩት 👉ከመገናኛ - ቃሊቲ
👉ከመገናኛ - ሳሪስ
👉ከመገናኛ - ጋርመንት መስመሮች
ወደ መገናኛ ሙሉጌታ ሕንጻ ዝቅ ብሎ አምቼ ፊት ለፊት መንገድ በጊዜያዊነት ተዛውሯል፡፡

ከቦሌ ክፍለ ከተማ ፊት ለፊት ሲሰጥ የነበረው
👉ከመገናኛ - ቱሉ ዲምቱ እና
👉ከመገናኝ - ኮዬ ፈቼ አገልግሎት ሲሰጥ የነበሩት መስመሮች አምቼ አጠገብ (ቀደም ሲል ከነበረበት ቦታ ትንሽ ዝቅ ብሎ) ወዳለው ቦታ ተዛውሯል፡፡

ከዚህ በፊት ሙሉጌታ ሕንፃ አካባቢ ይሰጡ የነበሩ
👉ከመገናኛ - ገርጂ
👉ከመገናኛ-ጎሮ
👉ከመገናኛ - አያት እና
👉ከመገናኛ - ሰሚት የመጫኛና መውረጃ መስመሮች ወደ ዘርፈሽዋል አካባቢ በተዘጋጀው ጊዜያዊ ተርሚናል ውስጥ በመዛወር በሁሉም ሞዳሊቲ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ቢሮው አስታውቋል።

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

#አሐዱ_አብይ_ጉዳይ!

ጥንቅሩን ለመከታተል ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👇
https://youtu.be/X8v6bnMp3bQ?si=XVn_NBb9ljCWpTyV

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የሀገርን እድገት ከፖለቲካዊ እይታ ነጥሎ ማየት ያስፈልጋል ሲሉ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ገለጹ

ጥቅምት 22/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ኢትዮጵያ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 8 ነጥብ 1 በመቶ እድገት አስመዝግባለች፡፡ በሚቀጥለው ዓመት 8 ነጥብ 4 ከመቶ ማስመዝገብ ትችላለች ሲሉ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በትናንትናው ዕለት በፓርላማ ውሏቸው ገልጸዋል፡፡

አሐዱም የሀገር የምጣኔ ሀብት እድገት የሚለካው በትክክል በምንድን ነው? አስመዘገበች የሚባለው እድገትስ እውን እድገት ነው ብለን መውሰድ እንችላለን ወይ? ሲል የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎችን አነጋግሯል፡፡

የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ዶክተር አጥላው አለሙ፤ "ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት (ጂ.ዲ.ፒ) እድገት ሲመዘገብ የተመጣጠነ ሊሆን አልያም ደሃውን የበለጠ ደሀ አድርጎ ሀብታሙን የበለጠ ሀብታም የሚያደርግ ሊሆን ይችላል" ሲሉ ገልጸዋል፡፡

አክለውም፤ "በኢትዮጵያ ያለውም ደሀውን የበለጠ ደሀ ሀብታሙንም የበለጠ ሀብታም የማድረግ አሰራር ነው" ያሉ ሲሆን፤ "የተመጣጠነ እድገት በሌለበት ሁኔታ እድገት ታየ ብሎ ለፖለቲካ ፍጆታ መጠቀም አግባብ አይደለም" ብለዋል፡፡

"ልማትን እና የሀገር ውስጥ ምርት እድገትን መለየት ያስፈልጋል፡፡ ልማት ሲባል የማህበረሰቡ የጤና፣ የትምህርት እና ሌሎችም ፍላጎቶች መሟላቱ መታየት አለበት፡፡ ከሱ ውጭ ሆነው እንቅስቃሴን ብቻ ይዞ ቁጥር መግለፅ ፋይዳ አይኖረውም" ሲሉም አብራርተዋል፡፡

ሌላኛው የምጣኔ ሀብት ባለሙያ ዶክተር ቆስጠንጢንዮስ በርኸ ተስፊ፤ "የሀገር ውስጥ ምርት እድገት ሲለካ ጥቂት ኩባንያዎች ወይም የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሊያስመዘግቡት ይችላሉ፡፡ ይህ ደግሞ የዜጎችን የምጣኔ ሀብት ጤንነት አያመለክትም" ሲሉ ይገልጻሉ፡፡

"ከ200 ቢሊየን ዶላር በላይ በ10 ዓመት ውስጥ ነዳጅ ኤክስፖርት የምታደርገው አንጎላ በድህነት ከሚጠቀሱ ሀገራት መካከል እንድትሆን ያደረጋት የሚመጣው ገንዘብ ማን ኪስ ውስጥ እንደሚገባ ስለማይታወቅ ነው" ብለዋል፡፡

አክለውም፤ እንደ ኢኳቶሪያል ጊኒ እና ደሞክራቲክ ኮንጎ የመሳሰሉት ሀገራት ያላቸው እድገት ጥሩ ነው ቢባልም፤ በጥቂት ባለሃብቶች እጅ ያለ ገንዘብ ለሀገር እድገት መለኪያ ሊሆን ባለመቻሉ አሁንም የከፋ ድህነት ውስጥ መሆናቸውን የገለጹ ሲሆን፤ በዚህም ምክንያት ጥቂቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግን እድገት እንደ ሀገር አድርጎ መውሰድ እንደማይገባ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም "የሀገር ትክክለኛ እድገት የሚለካው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በሚያወጣው የሰው ልማት መረጃ ጠቋሚ (ኤች ዲ አይ) ነው" ያሉት ባለሙያው፤ "ኢትዮጵያ ያላት እድገት ዝቅተኛ ነው" ሲሉም አስረድተዋል፡፡

"የሀገር ውስጥ ምርት እድገት ግን አካታች ባለመሆኑ በምጣኔ ሀብት አደግን ብለን ልንወስደው አንችልም" ሲሉም አክለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው በኋላ ያስመዘገበችው እድገት ከፍተኛ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ መናገራቸውም አይዘነጋም፡፡

በእመቤት ሲሳይ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በኮንታ ዞን በተከሰተ የመሬት መንሸራተት አደጋ የ6 ሰዎች ሕይወት አለፈ

ጥቅምት 22/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ኮንታ ዞን አመያ ዙሪያ ወረዳ ጫሬ ቀበሌ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ የሥድስት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የክልሉ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በቀበሌው ትናንት ምሽት የጣለው ከባድ ዝናብ ተከትሎ ዛሬ ጠዋት 2 ሠዓት ላይ የመሬት መንሸራተት መከሰቱን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ተናግረዋል፡፡

በአደጋው ሕይወታቸውን ያጡት ሰዎች የሁለት ቤተሰብ አባላት ሲሆኑ፤ ከአንደኛው ቤተሰብ አራት እንዲሁም ከሌላኛው ቤተሰብ ሁለት ሰዎች ሕይወታቸውን እንዳጡ አስረድተዋል፡፡

በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋም ሁለት ቤት የወደመ ሲሆን፤ የነፍስ አድን ሥራው ተጠናክሮ መቀጠሉን ኢንስፔክተር ደጀኔ ለኤፍቢሲ ተናግረዋል፡፡ እስከ አሁን 1 አስከሬን ተገኝቷል ብለዋል፡፡

በአካባቢው አሁንም መሬቱ እየተናደ መሆኑ እና የውኃ ሙላት (ጎርፍ) መኖሩ የነፍስ አድን ሥራውን በሚፈለገው ልክ እንዳይሆን ማድረጉን ተናግረዋል፡፡

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

ብሔራዊ ባንክ በባንኮች እርስ በርሳቸው የሚበዳደሩበት የገንዘብ ገበያ ይፋ አደረገ

ጥቅምት 22/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባንኮች እርስ በርሳቸው የሚበዳደሩበትን የገንዘብ የግብይት ሥርዓት መፍቀዱን አስታውቋል።

ብሔራዊ ባንኩ ዛሬ ጥቅምት 22 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ፤ "በባንኮች መካከል የሚደረግ የገንዘብ ግብይት መጀመር ንግድ ባንኮች የዕለት ተዕለት የገንዘብ ፍሰታቸውን በአግባቡ እንዲያስተዳድሩ ያግዛቸዋል" ብሏል።

በተጨማሪም "የገንዘብ እጥረት ስጋትን በመቀነስና በተረጋጋ የወለድ ተመን ለደንበኞች የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት ያስችላል" ሲል ገልጿል።

ንግድ ባንኮች ብድር መበደር ወይም ማበደር የሚችሉት ለአንድ ቀን ወይም ለሰባት ቀናት ለሚከፈል ገንዘብ ብቻ እንደሆነም አስታውቋል።

ይህም ባንኮች የአጭር ጊዜ የገንዘብ ጉድለትን በመሸፈን ወይም ትርፍ ገንዘብን ለሌሎች ባንኮች በማበደር የገንዘብ ፍሰትን በብቃት እንዲያስተዳደሩ እንደሚያስችል ተመላክቷል።

እንዲሁም በባንኮች መካከል የሚደረግ የገንዘብ ግብይት በኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ የግብይት መድረክ ላይ ብቻ እንዲከናወን የተፈቀደ ሲሆን፤ ግብይቱ ላይ ለመሳተፍም ሁሉም የንግድ ባንኮች ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፍቃድ ማግኘት እና የሚጠበቅባቸውን መስፈርቶች ማሟላት እንደሚገባቸው ተመላክቷል።

በተጨማሪም ይህ በባንኮች መካከል የሚደረግ የገንዘብ ግብይት የባንክ ዘርፉን በማጠናከር በኢኮኖሚው ዉስጥ ቀልጣፋ የገንዘብ ፍሰት እንዲኖርና የኢኮኖሚ ዕድገት እንዲፋጠን እንደሚያግዝ ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል።

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

#UPDATE
የአጼ ቴዎድሮስ ጋሻ ከ156 ዓመታት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሰ


ጥቅምት 22/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) እ.ኤ.አ 1868 በመቅደላ ጦርነት ወቅት የተወሰደው የአጼ ቴዎድሮስ ጋሻ ከ156 ዓመታት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሷል።

የኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አበባው አያሌው (ረ/ፕ)፤ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዝዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን፤ የአርበኞች የልጅ ልጆች፣ በተገኙበት ርክክብ ተደርጓል።

በ19ኛው ክፍለ ዘመን በእንግሊዝ ወታደሮች እንደተወሰደ የተነገረው ይህ ያጌጠ ጥንታዊ የኢትዮጵያ ጋሻ፤ በቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ የልጅ ልጅ ልዑል ኤርሚያስ ሳህለ-ሥላሴ ኃይለ ሥላሴ ተገዝቶ ወደ ሀገር ቤት ሊመለስ መሆኑ አሐዱ ከዚህ በፊት መዘገቡ ይታወሳል፡፡

ጥንታዊ ጋሻው አንደርሰን እና ጋርላንድ የጨረታ ቤት ለጨረታ ባቀረበበት ወቅት በድረ-ገጹ ላይ ከ800 እስከ1,200 የእንግሊዝ ዩሮ ይሸጣል ብሎ የነበረ ሲሆን፤ ጨረታውም በፈረንጆቹ የካቲት 29 ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ ሊካሄድ ታቅዶ ነበር፡፡ ጋሻውን ለማስመለስ ከአንድ ዓመት በላይ የፈጀ ጥረት ተደርጓል ተብሏል።

ጥንታዊ ጋሻውን የቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ የልጅ ልጅ በሆኑት በልዑል ኤርሚያስ ሳህለ-ሥላሴ ኃይለ ሥላሴና የኢትዮጵያ ንጉሣዊ በጎ አድራጎት ባለ አደራ ድርጅት (Royal Ethiopian Trust) በኩል ወደ ሀገር መመለሱ ተነግሯል፡፡

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

ከግንባታ ዘርፍ የሚመነጨው ቆሻሻ የአካባቢ ብክለትን በመፍጠር ከፍተኛውን ድርሻ መያዙ ተገለጸ

ጥቅምት 22/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በግንባታ ወቅትና ከግንባታ በኋላ የሚመነጨው ቆሻሻ የአካባቢን ብክለትን በመፍጠር ረገድ የአንበሳው ድርሻ የሚወስድ መሆኑን የገለጸው የፌደራል አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ነው።

ባለስልጣኑ እንዳስታወቀው ከሆነ፤ ከግንባታ በኋላ ያለው የደረቅና ፈሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ ስልት የተዝረከረከና በሕግ ያልተደገፈ ሆኖ ቆይቷል።

ይህን ችግር ለመፍታትም ባለስልጣኑ የተለያዩ ሥራዎችን እየሰራ ቢሆንም ሂደቱ ቀላል እንዳልሆነ የተናገሩት፤ በፌደራል የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የአከባቢ ብክለትና ቁጥጥር ኃላፊ ሙሉእመቤት ታሪክ ናቸው።

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በአገር አቀፍ ደረጃ የአካባቢ ጥበቃን በተመለከተ በርካታ ንቅናቄዎችን ሲያደርግ መቆየቱን የገለጹት ኃላፊዋ፤ ከችግሩ ስፋት አንፃር አሁንም መሰራት ያለባቸው ሥራዎች መኖራቸውን ተናግረዋል።

በተለይም የድምፅ ብክለትን ጨምሮ የአየር ንብረትና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ አዳዲስ እቅዶችን በማውጣት ወደ ትግበራ ሊገባ መሆኑን ለአሐዱ ገልጸዋል።

አክለውም አሮጌና የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸው ተሽከርካሪዎች እንዲወገዱ ማድረግ በአየር ንብረት የሚመጣውን ችግር ለመከላከል ዋነኛ መፍትሄ መሆኑን አስታውሰዋል።

በቅርቡም መንግሥት በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ወደ አገር ውስጥ ገበያ እንዳይገቡ ከልክሎ እንደነበር የሚታወስ ነው። ይሁንና የውሳኔ ለውጥ በማድረግም በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ወደ አገር ውስጥ እንዲገቡ ይሁንታ መስጠቱን አሐዱ ከዚህ በፊት መዘገቡ ይታወሳል።

በአማኑዔል ክንደያ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

#አሐዱ_ትንታኔ

ትንታኔውን ለመከታተል ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👇
https://youtu.be/z-s4QaE0Nmo?si=vzMck02T0PQiYJbx

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በአዋሽ ፈንታሌ በተደጋጋሚ በሚከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ለአደጋ ታጋላጭ የሆኑ 7 መቶ አባወራዎች መነሳታቸው ተገለጸ

ጥቅምት 21/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በአፋል ክልል በአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ በተደጋጋሚ እየተከሰተ የሚገኘው የመሬት መንቀጥቀጥ በዜጎች ላይ አደጋ እንዳያስከትል 7 መቶ የሚሆኑ አባወራዎች ከስፍራው መነሳታቸው ተገልጿል፡፡

ከመስከረም አንድ ጀምሮ በአፋር ክልል በአዋሽ ፈንታሌ በተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ እየተከሰተ እንደሚገኝ እና ይህም ስጋት መፍጠሩን የአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አባህ አባህ ሁሴን ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

ዋና አስተዳዳሪው፤ እስካሁን የ4 ሰዎች ቤት የመፍርስ አደጋ እና የአንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ ጉዳት መድረሱን ገልጸዋል፡፡

አክለውም "ወደ 11 ኪሎ ሜትር የሚጠጋ የምድር ውስጥ መሰንጠቅ አለ" ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የመሬት መንቀጥቀጡ ሲጀምር ከ4 ነጥብ 6 ሬክቴር ስኬል የነበረ ሲሆን፤ አሁን ላይ 4 ነጥብ 9 ሬክቴር ስኬል ላይ መድረሱ ተነግሯል፡፡

ዋና አስተዳዳሪው ከሦስት ቀናት ወዲህ የመሬት መንቀጥቀጥ እየተስተዋለ አለመሆኑን የገለጹም ሲሆን፤ አሁንም በህብረተሰቡ ዘንድ ስጋት ስለመኖሩ ጠቁመዋል፡፡

"ከዚህ ቀደም የመሬት መንቀጥቀጥ በዓመታት ልዩነት የሚስተዋልበት ሁኔታ ቢኖርም በአሁኑ ወቅት ግን በየቀኑ የሚጨምር የመሬት መንቀጥቀጥ አለ" ብለዋል፡፡

በእሌኒ ግዛቸው

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ:www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ:http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…
Subscribe to a channel