በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ለተፈጸሙት አሰቃቂ ድርጊቶችና የጦር ወንጀሎች ተጠያቂነት እንዲኖር አሜሪካ ጠየቀች
ሕዳር 3/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በዛሬው ዕለት በተካሄደው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት ግምገማ ላይ በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ለተፈጸሙ አሰቃቂ ድርጊቶች፣ የጦር ወንጀሎች፣ በሰው ልጆች ላይ ለተፈጸሙ ሰብዓዊ እና የዘር ማጥፋትን ጨምሮ ተጠያቂነት እንዲኖር አሜሪካ ጠይቃለች፡፡
በአማራ፣ በኦሮሚያ እና በሌሎችም አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰት እና በመላ ሀገሪቱ የመሰረታዊ ነጻነቶች እገዳ በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ መሆኑን የአሜሪካ ተወካይዋ በግምገማው ገልጸዋል።
አክለውም፤ "ለኢትዮጵያ የጸጥታ ኃይሎች የሰብዓዊ መብት ጥሰትን የሚከለክል እና ተጠያቂ የሆኑትን ግልጽነት ባለው፣ ተጎጂዎችን ያማከለ የፍትህ ሂደት ግምት ዉስጥ አስገብቶ ተጠያቂ እንዲሆኑ እናሳስባለን" ብለዋል።
ሃሳብን በነጻነት በመግለጽ ወይም ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ የታሰሩትን የሲቪል ማህበረሰብ መሪዎች፣ ጋዜጠኞች እና ተቃዋሚዎችን ጨምሮ የተለያዩ ዜጎች እንዲፈቱ እና የእስር ቦታዎችን እና የግጭት ቀጠናዎችን ጨምሮ የአለም ዓቀፍ እና የሀገር ውስጥ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች በነጻነት እንዲንቀሳቀሱ ጠይቀዋል።
የኢትዮጵያ መንግሥትን በመወከል ከፍትህ ሚንስቴር ጉባኤውን የታደሙት አቶ የሱፍ ጀማል በበኩላቸው፤ መንግሥት ሰብዓዊ መብቶችን ለማስከበር እና ለማንኛውም የሰብአዊ መብት ጥሰት ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ ቁርጠኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
"የፍትህ ስርዓቱን ነፃነት በማጠናከር፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽንን በማሳደግ፣ የወንጀል ድርጊቱ ተፈጽሟል ወደተባለው ቦታ መርማሪ ባለሙያዎችን እና አቃብያን ህጎችን በፍጥነት ተሰማርተዋል" ብለዋል፡፡
በተጨማሪም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ኮሚሽነር ፅህፈት ቤት በጋራ እንዲሰሩ ማመቻቸትን ጨምሮ ጉልህ እርምጃዎች መወሰዳቸውን ተናግረዋል።
አክለውም በፖሊስ እና ዐቃቢ ሕግ ሰፊ ገለልተኛ ምርመራዎች የተካሄዱ ሲሆን፤ በግጭት ክስ በተመሰረተባቸው 2 ሺሕ 1 መቶ 17 ተከሳሾች ላይ 42 የክስ መዝገብ እንደቀረበ አቶ የሱፍ መናገራቸውን አሐዱ ከስብሰባው ተከታትሏል፡፡
ተከሳሾቹም ከፍተኛ እና መካከለኛ ደረጃ ያላቸው ወታደራዊ ባለስልጣናት የፖሊስ መኮንኖችን እንደሚያካትት ተናግረዋል።
በዳግም ተገኝ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
በ10 ቢሊዮን ብር በጀት የተጀመረው የከርሰ ምድር ውሀ የማውጣት ፕሮጀክት በበጀት እጥረት ምክንያት አለመጠናቀቁ ተገለጸ
👉ፕሮጀክቱ አለመጠናቀቁ ማህበረሰቡን ለድርቅ ተጋላጭ እንደሚያደርገው ስጋት ፈጥሯል
ሕዳር 3/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኦሮሚያ ክልል በቦረና ዞን በ10 ቢሊዮን ብር በጀት የተጀመረው የከርሰ ምድር ውሀ ማውጣት ፕሮጀክት በበጀት እጥረት ምክንያት አለመጠናቀቁ ተገልጿል፡፡
በዞኑ ተከስቶ የነበረው ድርቅ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ጨምሮ በእንስሳት ላይ ጉዳት ማድረሱ የሚታወቅ ነው፡፡
በዚህ ረገድ በአካባቢው ያለውን ችግር ለመፍታት የሚያስችል የውሀ ፕሮጀክት በመንግሥት በኩል ተጀምሯል መባሉ የሚታወስ ነው፡፡
አሐዱም የሚከሰተውን ድርቅ ለመቋቋም በመንግሥት በኩል የተጀመረው ፕሮጀክት ተግባራዊ ስለመደረጉ የቦረና ዞን ጤና መምሪያ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሞሪ ዲሞን ጠይቋል፡፡
ኃላፊው በምላሻውም ከከርሰ ምድር ውሀ ለማውጣት በ10 ቢሊዮን ብር በጀት የተጀመረው ፕሮጀክት በበጀት እጥረት ምክንያት አለመጠናቀቁን ተናግረዋል፡፡
"ፕሮጀክቱ ተግባራዊ ባለመደረጉ የማህበረሰቡ ችግር እንዳይፈታ አድርጎታል" ያሉት ኃላፊው፤ ፕሮጀክቱ ከተጀመረ 10 ዓመት በላይ እንደሆነውም አንስተዋል፡፡
አሁን ላይ በአካባቢው ዝናብ በመኖሩ ችግሩ የተፈታ ቢሆንም፤ ዘላቂ መፍትሄ መስጠት እንደሚያስፍልግም ገልጸዋል፡፡
"ፕሮጀክቱን ሰርቶ ማጠናቅ ቢቻል በድቅር ምክንያት ማህበረሰቡ ላይ የሚደርሰውን ጉዳት መቀነስ ይቻላል" ሲሉም አጽንኦት ሰጥተውበታል፡፡
በኦሮሚያ ክልል በቦረና ዞን ለተከታታይ አምስት ዓመታት በሁሉም የዝናብ ወቅቶች ዝናብ ባለማግኘቱ ምክንያት በከተሰተው ድርቅ 3 ሚሊዮን የቀንድ ከብቶች መሞታቸውንና ከ800 ሺሕ በላይ ዜጎች ዕርዳታ እንደሚሹ የዞኑ የጤና ቢሮ ከዚህ ቀደም ያወጣው መረጃ ያመላክታል፡፡
በፍቅርተ ቢተዉ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
የከባድ የተሽከርካሪዎችን የመጫን ክብደት ለመገደብ የወጣው ደንብ ተግባራዊ ባለመደረጉ የሀገር ኢኮኖሚ ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩ ተገለጸ
👉ባለፉት ሦስት ዓመታት ለመንገድ ጥገና ብቻ 1 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ወጪ ተደርጓል ተብሏል
ሕዳር 3/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ከባድ ተሸከርካሪዎች ከተፈቀደው ልክ በላይ ጭነት በመጫናቸው መሰረተ ልማቶች ላይ ጉዳት እያደረሱ መሆኑን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክ ሚኒስቴር ገልጿል፡፡
መሰረታዊ የግብርና ግብዓቶች፣ መድሀኒኒቶች እና የማኑፋክቸሪንግ እቃዎች 95 በመቶ ከጅቡቲ ወደብ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ምርቶች በጭነት እንደሚገቡም ሚኒስቴሩ ለአሐዱ አስታውቋል፡፡
በዚህ ረገድ የትራንስፓርት እና ሎጂስቲክ እንቅስቃሴን በተመለከተ ከክብደት በላይ የጫኑ ተሽከርካሪዎች በተለያዩ የሀገሪቷ መሠረተ ልማቶች ላይ ጉዳት እያደረሱ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡
ተሽከርካሪዎች ከፍተኛ ጭነት ወይንም ከተፈቀደው ልክ በላይ ሲጭኑ ከፍተኛ የነዳጅ ፍጆታ፣ የድልድይ መሰበር እና የመንገድ መሰነጠቅን እያስከተለ በመሆኑ ጉዳት የደረሰባቸውን መሰረተ ልማቶች መልሶ ለመጠገን የሚወጣው ወጪ የሀገር ኢኮኖሚ ላይ የራሱ ተፅዕኖ ያሳድራል ተብሏል።
በዚህም ምክያት ከ2012 እስከ 2016 ድረስ ባሉት ዓመታት ለመንገድ ጥገና ብቻ 1 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ወጪ መደረጉን ነው የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክ ሚኒስቴር ያስታወቀው።
መንገዶች ያገለግላሉ ተብሎ ከሚታሰበው ጊዜ አስቀድሞ የመሰነጣጠቅ እና መቦርቦር ችግር እንደሚፈጠር የገለጸው ሚኒስቴሩ፤ የከባድ ተሽከርካሪዎች ከመጠን በላይ እቃዎች ማጓጓዝ አንዱ ለመንገዶች መበላሸት ምክንያት መሆኑን አንስቷል።
ከክብደት በላይ የሚጭኑ አሽከርካሪዎችን በመቅጣት የሚገኘው ገቢ መንገዱን ለማደስ ከሚወጣው ጋር ፈጽሞ አይመጣጠንም ሲልም አክሏል።
በዚህም ከጅቡቲ አዲስ አበባ ያለውን መስመር በአንድ ጊዜ ለማደስ 8 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ እንደሚያስወጣ ነው የተገለጸው።
በተመሳሳይም ይሄንን መንገድ ለማደስ በየዓመቱ ከ1 ቢሊየን እስከ ሁለት ሚሊየን ብር ወጪ እንደሚወጣም ሚኒስቴሩ ገልጿል።
ሚኒስቴሩ አክሎም፤ "ኢትዮጵያ አሁን ባለችበት ሁኔታ የተሻለ የመሠረተ ልማት ግንባታ ለማከናወን የሚያስችል የኢኮኖሚ አቅም የላትም" ብሏል።
ስለሆነም መንገዶች ይሰጣሉ ተብሎ የሚታሰበውን አገልግሎት እንዲሰጡ የመንገዶችን ደህንነት መጠበቅ የተሻለው አማራጭ እንደሆነ ገልጿል።
በዚህም መሰረት ተሽከርካሪዎች ከተፈቀደው ልክ በላይ እንዳይጭኑ በ1954 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣው ደንብ እና ለመጨረሻ ጊዜ 2014 ዓ.ም የተሻሻለው ደንብ የተዘጋጀ ቢሆንም፤ የአፈጻጸም ክፍተት መኖሩን ገልጿል፡፡
የወጣው ደንብ በቅርቡ ተግባራዊ እንደሚደረግ፤ ከክብደት በላይ የጫኑ ተሸከርካሪዎች ጭነው ያመጡትን እቃ እስከ መመለስ ድረስ የሚደርስ የቅጣት እርምጃ እንደሚጀመርም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለአሐዱ አስታውቋል፡፡
በፍርቱና ወልደአብ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ግብፅ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሱዳናውያን ስደተኞች መቀበሏ ተገለጸ
ሕዳር 3/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ግብፅ 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን የሚደርሱ ሱዳናዊንን ስደተኞችን መቀበሏን አስታዉቃለች።
በግብፅ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ተወካይ ሃናን ሃምዳን፤ "ካይሮ ይህን ያህል ቁጥር ስደተኞችን ተሸክማ የመቆየት አቅም የላትም ሲሉ" ተናግረዋል።
"የግብፅ መንግሥት አለም አቀፍ ጥበቃን ለማድረግ ቁርጠኛ ቢሆንም፤ የቀውሱ መጠን ግን ከአቅሙ በላይ ሆኗል" ሲሉ ተወካዩ አስታዉቀዋል።
በተጨማሪ የአለም አቀፍ ሃገራት ድጋፍ እንዲያደርግ ሲሉ ጥሪ ማቅረባቸውን ሱዳን ትሪብን ዘግቧል።
የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ባለፈው አርብ እንደተናገረው፤ ግብፅ በሱዳን ያለውን ጦርነት ሸሽተው ለሚሰደዱ ሱዳናውያን ስደተኞች በመቀበል ቀዳሚ ሀገር ሆናለች።
በዚህም የሱዳን ሰብዓዊ ቀውስ መስፋፋት በግብፅ ሃብትና መሰረተ ልማት ላይ ከፍተኛ ጫና መፍጠሩን የመንግሥታቱ ድርጅት አመልክቷል።
የሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ከአንድ ዓመታት በላይ ያስቆጠረ ቢሆንም፤ ተፋላሚ ሃይሎች የተኩስ አቁም ስምምነት የማድረግ ፍላጓት ሲያሳዩ መመልከት አልተቻለም።
እንደፈረንጆቹ አቆጣጠር ከሚያዚያ ወር 2023 ጀምሮ በሱዳን እየተካሄደ ባለው ጦርነት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሕይወታቸው ሲያልፍ፤ ከ11 ሚሊዮን በላይ መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ገልጿል።
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
የዛሬ ፕሮግራም ጥቆማ!
የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ም/ቤት በአውሮፓ ሕብረት የገንዘብ ድጋፍ የሚያዘጋጀውና የሰላም ግንባታ ላይ የሚያተኩረው ልዩ ፕሮግራም ዘወትር ማክሰኞ ከምሽቱ 11፤ 30 ጀምሮ በአሐዱ 94.3 ላይ ወደ እናንተ ውድ ቤተሰቦቻችን ያደርሳል፡፡
ፕሮግራሙን እንድትከታተሉና ሃሳብ እንድታደርሱን በአክብሮት እንጋብዛለን፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ፣ ይደውሉልን፡፡
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት አያያዝ በዛሬው ዕለት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሊገመገም ነው
ሕዳር 3/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ሁኔታ በአራተኛ ዙር የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተ.መ.ድ.) የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት ሁሉን-አቀፍ ወቅታዊ ግምገማ (ዩ.ፒ.አር) መድረክ ላይ በዛሬው ዕለት ግምገማ እንደሚደረግበት ተገልጿል፡፡
የግምገማው ቡድኑ ስብሰባውን ዛሬ ሕዳር 3 ቀን 2017 ዓ.ም በጄኔቭ የሚካሄድ ሲሆን፤ ስብሰባው ከቀኑ 5፡00 ጀምሮ በቀጥታ በድህረ ገጽ (ዌብ ካስት) ይተላለፋል ተብሏል፡፡
በቡድኑ ከጥቅምት 25 እስከ ሕዳር 6 ቀን 2017 ዓ.ም በሚደረገው ስብሰባ ላይ፤ ኢትዮጵያን ጨምሮ የ14 ሀገራት የሰብዓዊ መብት አያያዝ ሁኔታ እንደሚገመገም ምክር ቤቱ አመላክቷል፡፡
የግምገማው ቡድኑ 47 የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት አባል ሀገራትን ያቀፈ ሲሆን፤ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አባል ሀገራትም በግምገማው ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ ተነግሯል፡፡
ይህ የአገራት ሁሉን አቀፍ ወቅታዊ ግምገማው የሚደረገው በሀገራዊ ሪፖርቶች ላይ ተመስርቶ ነው፡፡
እንዲሁም ገለልተኛ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች እና ቡድኖች ሪፖርቶች፣ ሀገራት በተቀበሉት አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ስምምነቶች ዙሪያ የሚያከናውኑ አካላት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅቶች ሪፖርት ውስጥ የተካተቱ መረጃዎችን መሰረት በማድረግ ግምገማው እንደሚካሄድም ተመላክቷል፡፡
በተጨማሪም ሀገር አቀፍ የሰብአዊ መብት ተቋማት፣ አህጉር አቀፍ ድርጅቶች እና የሲቪል ማህበረሰብ ቡድኖችን ጨምሮ ሌሎች አካላት ባቀረቡት መረጃዎች ላይ መሰረት በማድረግ ሪፖርቱ ይቀርባል፡፡
በአራተኛው ሁሉን አቀፍ ወቅታዊ ግምገማ ላይ፤ መንግሥታት ከዚህ ቀደም በተካሄዱ ግምገማዎች ላይ የቀረቡትን ምክረ ሃሳቦች ተግባራዊ ለማድረግ የወሰዷቸውን እርምጃዎች እንዲገልጹ ይጠበቃል፡፡ ይህም በቅርብ ጊዜ በሀገሪቱ ውስጥ የሰብአዊ መብት ለውጦችን ለመከታተል እና ለማጉላት የሚደረግ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
በዚህ ዛሬ በጄኔቫ በሚከናወነው ግምገማ ላይ የኢትዮጵያ መንግሥትን በመወከል የፍትህ ሚኒትር ዲኤታ የሆኑት አቶ ቢልልኝ ይርጋ ክፍሌ በስፍራው እንደሚገኙ አሐዱ ከምክር ቤቱ መግለጫ መረዳት ችሏል፡፡
ከዚህ ቀደም እ.ኤ.አ. በታህሳስ 2009፣ በግንቦት 2014 እና በግንቦት 2019 ላይ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት አያያዝ ላይ ያተኮሩ ተከታታይ ሦስት ግምገማዎች በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት መካሄዳቸው ይታወቃል።
ባሳለፍነው ጥቅምት ወር በተካሄደው 79ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ኢትዮጵያ ለሦስተኛ ጊዜ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት አባል ሆና መመረጧም ይታወሳል፡፡
በዚህም ከፈረንጆቹ 2025-2027 ድረስ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት አባል ሆና ትቆያለች፡፡
በእዮብ ውብነህ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ኢትዮ ቴሌኮም በቢሾፍቱ የስማርት ሲቲ ፕሮጀክትን ለማስጀመር የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ
ሕዳር 3/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ኢትዮ ቴሌኮም የስማርት ሲቲ (ስማርት ቢሾፍቱ) ፕሮጀክትን ዕውን ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት ከከተማዋ አስተዳደር ጋር ተፈራርሟል።
የስማርት ቢሾፍቱ ፕሮጀክት በምዕራፍ ከተማዋን ለማዘመን የሚያስችል የክላውድ፣ ጥሪ ማዕከል፣ ዳታ ሴንተር፣ እጅግ ከፍተኛ ፍጥነት እና ጥራት ያለው ኢንተርኔት፣ የኦፕቲካል ፋይበር እና ሌሎች የዲጂታል መሰረተ ልማቶችን ለመገንባት ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
ፕሮጀክቱ የመዘጋጃ አገልግሎቶችን ጨምሮ ትምህርት፣ ጤና፣ ግብርና፣ ትራንስፖርት እና የግብር አሰባሰብ የመሳሰሉ አገልግሎቶችን ለማዘመን እንዲሁም፤ አስተማማኝ ደህንነት ያላት ከተማን ዕውን ለማድረግ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው አጽንኦት ተሰጥቷል።
በተጨማሪም ሁሉንአቀፍ የዲጂታል ሶሉሽኖችን ተጠቃሚነት ከማሳደግ ባሻገር ክፍያዎችን በቴሌብር በቀላሉ በማስፈጸም ውጤታማነትን በእጅጉ ለማሳደግ የሚያስችል ሲሆን፤ ይህም ተገልጋዮች ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ እና የአኗኗር ዘይቤን ለመቀየር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተብራርቷል።
በተለይም ከተማዋን ለቱሪዝም መዳረሻነት፣ ኢንዱስትሪ (Economic zone) እና ኢንቨስትመንት ያላትን ተመራጭነት በማሳደግ ተወዳዳሪነትን እንደሚጨምር እና የቢዝነስ እንቅስቃሴን በማሳለጥ የማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን እንደሚያሻሽል ተገልጿል።
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
#ADVERTISMENT
#AmharaBank
የአማራ ባንክ አ/ማ የባለአክሲዮኖች 3ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ማክሰኞ ታህሳስ 01 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ በሚሊኒየም አዳራሽ ስለሚካሄድ ባለአክሲዮኖች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጉባዔው እንድትገኙ ጥሪ እናስተላልፋለን፡፡
የጉባዔው አጀንዳዎችን እና ተጨማሪ መረጃዎችን ጥቅምት 06 ቀን 2017 ዓ.ም በወጡት አዲስ ዘመን እና ሪፖርተር አማርኛ እትም ጋዜጦች ላይ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ለበለጠ መረጃ ነፃ የጥሪ ማዕከል 690 ወይም
የባንኩን ድረ ገጽ www.amharabank.com.et ይጎብኙ፡፡
አማራ ባንክ
ከባንክ ባሻገር!
የአማራ ባንክ ትክክለኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾች
Website: www.amharabank.com
Facebook: www.Facebook.com/amharabanksc1
Telegram: /channel/Amhara_Banksc
Instagram: https://instagram.com/amhara_bank
Twitter: https://twitter.com/Amharabanksc
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/amharabank/
YouTube: https://youtube.com/channel/UC73x9uuGYV0Uxw0EkpVZN8g
TikTok: amharabanks.c" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@amharabanks.c
#አማራባንክ #AmharaBank
#አሐዱ_ስንክሳር
"ሥሙ እና ግብሩ የተዋደዱለት ጋዜጠኛ ዜናነህ መኮንን" በጋዜጠኛ ጥበብ በለጠ
ጥንቅሩን ለመከታተል ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👇
https://youtu.be/J-hHeC0iGo4?si=ytF_1MZYOATppUnJ
#አሐዱ_ትንታኔ
በእስራኤልና በሀማስ መካከል እየተካሄደ የሚገኘውን ጦርነት ለማስቆም በአንፃራዊ መልኩ ተስፋ የተጣለባት ኳታር ራሷን ከአደራዳሪነቷ ማግለሏን አስታውቃለች።
ከዚህ ባሻገርም የሀማስ ህልውናን አደጋ ላይ የሚጥል ውሳኔ ማስተላለፏ ተሰምቷል። የእስራኤል አጋር የሆነችው አሜሪካም በሀማስ ላይ ጥብቅ ውሳኔን አስተላልፋለች፡፡ እነዚህን እና ተያያዥ ጉዳዮችን በዛሬው ዓለም አቀፍ ትንታኔያችን እንመለከታለን።
ትንታኔውን ለመከታተል ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👇
https://youtu.be/bXg760RuRsE?si=-YQdHDvC1tZ1GNL0
"ወርቁ ከቀደሙት መንግሥታት እይታ ለ44 ዓመታት ያህል ተሠውሮ ኖረ የሚለው፤ ግልጽ ማብራሪያ የሚሻ ጉዳይ ነው" እናት ፓርቲ
ሕዳር 2/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ በቅርቡ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ በሰጡበት ወቅት፤ “ባደረግነው የብሔራዊ ቤተ መንግሥት እድሳት ተቆልፎበት የተቀመጠ 400 ኪ.ግ. ወርቅ ኮሚቴ አቋቁመን ወደ ብሔራዊ ባንክ አስገብተናል” ማለታቸው ይታወሳል።
ይህንንም ተከትሎ ጉዳዩ በብዙዎች ዘንድ መነጋገሪያ ሆኖ የቆየ ሲሆን፤ እናት ፓርቲም ጉዳዩን አስመልክቶ በዛሬው ዕለት መግለጫ አውጥቷል፡፡
በመግለጫውም፤ "ተቆልፎበት የነበረው የተገኘው ወርቅ ቀደም ሲል በጠቀስነውና በGold Bullion መልክ የተቀመጠ ጥፍጥፍ ወርቅ ነው? ከሆነስ እንዴት ከቀደሙት መንግሥታት እይታ ለ44 ዓመታት ያህል ተሠውሮ ኖረ? የሚለው ግልጽ ማብራሪያ የሚሻ ጉዳይ ነው።" ብሏል፡፡
ከማብራሪያው በኋላ በእንደዚህ ዓይነት መልኩ የተቀመጠና አዲስ የተገኘ ከሆነ፤ በወቅቱ የዓለም ገበያ ዋጋ መዝግቦ መያዙና ለዚሁ በባንኩ በተዘጋጀው ሥፍራ ማስቀመጡ አግባብነት ያለው መሆኑን የገለጸ ሲሆን፤ ወደ ባንክ ማዛወሩም ትክክለኛ እንደሆነ ገልጿል፡፡
"የጠቅላይ ሚንስትሩ ንግግር ግልጽ አይደለም።" ያለው ፓርቲው፤ "ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ወደ ሥልጣን መምጣት አሰቀድሞ 44 ዓመታት ይህ የተጠቀሰው ወርቅ ከእይታ ተሰውሮ ተደብቆ የተገኘ አዲስ ግኝት ወይንስ የአገር ቅርስ በመሆኑ ለጥፋት እንዳይጋለጥ ተጠብቆ የቆየ ነው?" ሲል ጠይቋል፡፡
አክሎም፤ "የተገኘው ወርቅ በዓለም የወርቅ ግብይትና በብሔራዊ ባንክ የሚቀመጠው Bullion (ቡልዮን) በሚባለው ጥፍጥፍ ወርቅ መልክ የተቀመጠ ወርቅ ነው? ወይንስ ይህ ወርቅ የተባለው በነገሥታቱ ዘመን በቤተ መንግሥት አገልግሎት ላይ የነበሩና ለነገሥታቱ ከተለያዩ አካላት የተበረከቱ ከወርቅ የተሠሩ መገልገያዎች የሚለው ግልጽ አይደለም።" ሲልም የጠ/ሚንስትሩ ንግግር ግልጽ እንዲደረግ አሳስቧል፡፡
በአንጻሩ የተጠቀሰው ወርቅ ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንደተነገረው ወርቅ ሳይሆን ከወርቅ የተሠሩ የተለያዩ መገልገያዎች ከሆኑ፤ ወደ ብሔራዊ ባንክ እየተላለፈ ያለው ወርቅ ሳይሆን ከወርቅ በላይ የሆነ የአገር ቅርስ የትላንት እኛነታችን መገለጫ ከሆኑ ነገሮች በግንባር ቀደምነት የሚጠቀስ መሆኑን በመጥቀስ በዚህ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ መጠየቅ አግባብነት ይኖረዋል።" ብሏል፡፡
"ወርቁ በቤተ መንግሥት አገልግሎት ላይ ይውሉ የነበሩ ከወርቅ የተሠሩ መገልገያዎች ወይንም ለነገሥታቱ ከውጭ አገራት መንግሥታት የተበረከቱ ከወርቅ የተሠሩ መገልገያዎች ከሆኑ፤ እነዚህ ወርቅ ተብለው በወርቅ ዋጋ የሚገመቱና ተመዝግበው በብሔራዊ ባንክ የሚቀመጡ ባንኩም አግባብነት አለው ባለው ጊዜ የሚሸጠው ንብረት ሊሆኑ ከቶውንም አይችሉም" ሲልም አሳስቧል፡፡
በዚህ መልኩ ለ47 ዓመታት በኹለት የተለያዩ ሥርዓቶች በምክንያት ተጠብቆ ቆይቶ ዛሬን የደረሰ መሆኑ አዲስ ግኝት ሳይሆን፤ በሚመለከታቸው አካላት የሚታወቅ ከሆነ እየተናገርን ያለነው ስለ ወርቅ ሳይሆን ስለ አገር ቅርስ መሆኑን እናት ፓርቲ አጽንዖት ሰጥቶ ተናግሯል፡፡
በዚሁ መሠረት ለተወካዮች ምክር ቤት የተገለጸው ወርቅ ምን ወርቅ እንደሆነ ባለቤቱና ባለታሪኩ ለሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ግልጽ እንዲደረግ ፓርቲው ጠይቋል፡፡
በተጨማሪም የተጠቀሰው ወርቅ በቤተ መንግሥት ተቀምጦ የነበረ ከወርቅ የተሠሩ መገልገያዎች ሊሆኑ እንደሚችሉ እንደሚያምን የገለጸው ፓርቲው፤ የአገር ቅርስ መሆናቸው ታውቆ በክብር ተጠብቀው የሚቀመጡበት ኹኔታ ሊመቻች እንደሚገባ ገልጿል፡፡
ይህን መሰል የአገር ቅርስ ወደ ተራ ወርቅነት ተለውጦ መልኩን እንዲቀይርና በወርቅም ሆነ በሌላ መልኩ ተሸጦ ወደ ገንዘብ የሚለወጥ ከሆነ፤ የኢትዮጵያ መንግሥት በአጠቃላይና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክና የኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን በተለይ የጋራ ተጠያቂነት እንደሚጠብቃቸው በመረዳት ከዚህ መሰል የጥፋት ሥራ እንዲታቀቡም እናት ፓርቲ በመግለጫው አሳስቧል።
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
በኦሮሚያ ክልል ከዞን እስከ ቀበሌ እየተሰራ ያለው መወቅር ምርጫን ታሳቢ ያደረገ ነው ሲል የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ገለጸ
ሕዳር 2/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በወረዳ ደረጃ የነበረውን 28 የጽ/ቤት መዋቅር ወደ 15 ማጠፉንና አዲስ የቀበሌ አደረጃጀት ማዋቀሩ ከዚህ ቀደም ተገልጾ ነበር፡፡
በክልሉ ዞን የሚለውን መዋቅርም በአዲስ መልክ ክላስተር በሚል አደረጃጀት ለማዋቀርና መምሪያዎችን ለማጠፍ ጥናትና ውይይት እየተደረገ መሆኑም ተገልጿል፡፡
ይህንን በሚመለከትም በክልሉ መዋቅር በተሰራባቸው አንድ አንድ ወረዳዎችና ዞኖች ዜጎች ቅሬታ ሲያሰሙ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡
አሐዱም ይህንን ቅሬታ በመያዝ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ፓርቲን የጠየቀ ሲሆን፤ የፓርቲው ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሙላት ገመቹ "ሀሳቡ 'ሕዝቡን ሩቅ ሆኖ ከመምራት ቀረብ ብሎ ችግሩን መለየት' በሚል የተነገረ ቢሆንም፤ ይህ ፈፅሞ ትክክል ያልሆነ የፌደራሊዝምን ስርዓት የሚያፋልስ አካሄድ ነው" ብለውታል፡፡
"አካባቢውን የሚያስተዳድሩ ሀላፊዎች በምርጫ መመረጥ ሲኖርባቸው የፖለቲካ ሹመኛ መሆናቸው ክልሉን የሚያስተዳደረው ፓርቲ የራሱን ሀሳብ በሕዝብ ላይ ለመጫን ያሰበ መሆኑን ማሳያ ነው" ሲሉም ተናግረዋል፡፡
"ኅብረተሰቡ ጫና ውስጥ ወድቋል" የሚሉት ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበሩ፤ "ይህ እየሆነ ያለው በፍላጎት ሳይሆን ከላይ ወደታች በግዴታ ነው" ሲሉ ይገልጻሉ፡፡
በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ቦረና በሚል ከጉጂ፣ ቦረና እና ባሌ ዞኖች የተወሰኑ ወረዳዎችን ቀንሶ የተመሰረተው አዲስ ዞን ከዚህ ቀደም ተቃውሞን ማስነሳቱ የሚታወስ ነው፡፡
በተለይም በጉጂ ዞን ሥር ይተዳደር የነበረውና አሁን ላይ ምስራቅ ቦረና ሥር እንዲተዳደር በአዲሱ መዋቅር የተወሰነበት ጎሮ ዶላ ወረዳ ከፍተኛ የሕዝብ ተቃውሞ ተፈጥሮ እንደነበርም እንዲሁ ይታወቃል፡፡
ይህንን በሚመለከት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ ምክትል ተቀዳሚ ሊቀመንበርና ፖለቲከኛው ሙላት ገመቹ፤ የሕዝብ ተቃውሞ መመልከታቸውን በማንሳት፤ መንግሥት ለሕዝቡ የሚበጀዉን እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡
በአቤል ደጀኔ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በደቡብ ሱዳን ብሄራዊ አየር መንገድ ሊያቋቁም መሆኑ ተሰማ
ሕዳር 2/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከደቡብ ሱዳን መንግሥት ጋር በሀገሪቱ ብሄራዊ አገልግሎት የሚሰጥ አየር መንገድ ለማቋቋም እና ለማስተዳደር የሚያስችል የአጋርነት ስምምነት መስማማቱ ተገልጿል።
የትብብር ስምምነቱ የተደረሰው በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ነቢል ማህዲም እና የሀገሪቱ የትራንስፖርት ሚኒስትር ማዱት ቢያር ዬል በጁባ ባደረጉት ውይይት መሆኑን የደቡብ ሱዳን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፡፡
በዚህም ውይይታቸው ሁለቱ ሀገራት እ.ኤ.አ. በ2023 በተፈራረሙት የመግባቢያ ሰነድ (MoU) መሰረት፤ አጋርነታቸውን የሚገልጹ ሁኔታዎችን ላይ በድጋሚ መነጋገራቸው ተገልጿል።
በዚህም ዳግመኛ አጋርነታቸውን ለማደስ የተስማሙ ሲሆን፤ ይህም የሁለቱ ሀገራት ሥምምነት ለደቡብ ሱዳን የአቪዬሽን ገጽታ አዲስ ምዕራፍ ይዞ ለማምጣት ያለመ መሆኑ ተነግሯል።
ደቡብ ሱዳን እ.ኤ.አ. በ2011 ከሱዳን ነፃነቷን ከተጎናፀፈች በኋላ ብሔራዊ አየር መንገድ ለማቋቋም በጥረት ላይ የነበረች ቢሆንም፤ በዋነኛነት በሀገሪቱ ያለው ፖለቲካዊ አለመረጋጋት እና የእርስ በርስ ግጭት ይህ ጥረቷን ለማሳካት እንቅፋት ሆኖባት ቆይቷል፡፡
በዚህም ምክንያት ሀገሪቱ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የአቪዬሽን ትራንስፖርትን በግል ይዞታ ሥር ባሉ አየር መንገዶች አገልግሎት ላይ ጥገኛ ሆና ቆይታለች።
ይህ አዲስ ስምምነት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ አቪዬሽን ላይ ያለውን ሰፊ ልምድና አመራር ይዞ ወደ ሥራ ሲገባ፤ ለደቡብ ሱዳን የለውጥ እድል ይፈጥራል ተብሏል።
በዚህም የኢትዮጵያ ሲቪል አቬሽን ባለሙያዎች የደቡብ ሱዳንን የአየር ክልል የመቆጣጠር ሃላፊነት እንደሚኖራቸው የተገለጸ ሲሆን፤ አየር መንገዱ አስፈላጊ የቴክኒክ እና የአስተዳደር ሥራዎችንም እንደሚሰራ ተመላክቷል፡፡
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
በኢትዮጵያ ከአንድ ሚሊየን በላይ ሕጻናት ምንም አይነት ክትባት አለመውሰዳቸውን የጤና ሚኒስቴር ገለጸ
ሕዳር 2/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የጤና ሚኒስቴር በ2016 በጀት ዓመት ብቻ ባደረገው ጥናት፤ በኢትዮጵያ ከ1 ሚሊየን በላይ ሕጻናት ምንም አይነት ክትባት አለመውሰዳቸውን ገልጿል።
ክትባት ካልወሰዱት ሕጻናት በተጨማሪ ጀምረው ያቆሙ 1 ነጥብ 7 ሚሊየን ሕጻናት መኖራቸውን ለአሐዱ የገለጹት በጤና ሚኒስቴር የክትባት ፕሮግራም ከፍተኛ ባለሙያ አቶ መስፍን ካሴ ናቸው።
በተለያዩ አካባቢዎች የሚስተዋለዉ ግጭትና ጦርነት ህብረተሰቡ ሕጻናትን እንዳያስከትብ ካደረጉ ምክንያቶች ውስጥ አንዱ መሆኑን ገልጸዋል።
ራቅ ያለ የገጠር አካባቢ የሚኖሩ እንዲሁም ቋሚ መኖሪያ የሌላቸዉ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ተደራሽ ያለመሆን ችግር እንደሚስተዋልም ባለሙያው አንስተዋል።
በተመሳሳይ ከክትባት አስፈላጊነት ጋር ያለው የግንዛቤ እጥረትም ሌላው ምክንያት መሆኑን ተናግረዋል።
በተለያየ ምክንያት ክትባት ያልወሰዱ ሕጻናትን ተደራሽ ለማድረግ አማራጮችን በመጠቀም ዜሮ ዶዝ ከሚባለዉ ክትባት ወደ 16 በመቶ የሚሆነዉን ተደራሽ ማድረግ መቻሉን ገልጸው፤ 84 በመቶ ገና የሚቀር መሆኑን አስረድተዋል።
የጤና ባለሙያዎች ለህብረተሰቡ ተደራሸ ለመሆን ባላቸው አቅም እየሠሩ መሆኑን የተናገሩት የክትባት ፕሮግራም ከፍተኛ ባለሙያው መስፍን ካሴ፤ ክትባቶችን በጤና ተቋማት፣ ጤና ጣቢያና ሆስፒታሎች እንዲሰጡ እየተደረገ መሆኑንም ለአሐዱ ገልጸዋል።
በፍርቱና ወልደአብ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
#አሐዱ_አሳሩ_በዛብህ
"የሚባለው እና የምንኖረው አልተጣጣመም፡፡ መንግሥት ብቻውን ማደጉ ጥቅም የለውም"
አሳሩ በዛብህ በሳምንቱ አሳሰበኝ ያለውን ጉዳይ በብዕሩ ከትቦ ለወዳጁ ምክረ ሰናይ ልኮለታል፡፡ አሳሩን ያሳሰበው ጉዳይ ምን ይሆን?
ሙሉ ጥንቅሩን ለመከታተል ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👇
https://youtu.be/cjIKl4YvX-Y?si=e8ztx2hy3iANvauW
በኢትዮጵያ የጉበት በሽታ ዘጠኝ መቶ ከፍ ማለቱን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ
ሕዳር 3/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር በሀገር አቀፍ ደረጃ የጉበት በሽታ መድኃኒት እጥረት እንዳለ የገለጠ ሲሆን፤ በዚህም የተነሳ የበሽታው ስርጭት መጠን 9 በመቶ ከፍ ማለቱን አስታዉቋል።
በሽታው የማህብረሰብ የጤና ስጋት እየሆነ መምጣቱ የተገለጸ ሲሆን፤ በአለም ዓቀፍ ደረጃ መድኃኒት ለማግኘት የሚደረግ ድጋፍም እንደሌለ የተናገሩት በሚኒስቴሩ የኤችአይቪ መከላከል እና መቆጣጠር መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፍቃዱ ያደታ ናቸው፡፡
በተጨማሪ በኢትዮጵያ የጉበት በሽታን ለመርመር በቂ የሆኑ ሆስፒታሎች እንደሌሉ ለአሐዱ አስረድተዋል፡፡
በሽታዉ ከእናት ወደ ልጅ በወሊድ ጊዜ የመተላለፍ እድሉ ከፍተኛ እንደሆነ የገለጹት ኃላፊዉ፤ ይህ እንዳይሆን ደግሞ እናቶች በእርግዝና ወቅት አስፈላጊዉን የጤና ክትትል ማድረግ እንደሚያስፈልጋቸዉ አሳስበዋል።
አክለውም "በሽታውን ለመግታት ወቅታዊ ሕክምና እየተሰጠ ቢገኝም፤ ነገር ግን ተደራሽነቱ ውስን ነው" ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የዓለም ጤና ድርጅት ባሳለፈው ዓመት ግንቦት ወር ትኩረቱን በጉበት በሽታ ዙሪያ አድርጎ ባካሄደው ጉባኤ ላይ የዓለም ጉበት በሽታ ስርጭት ሪፖርት የቀረበ ሲሆን፤ በሪፖርቱ በተለይም በሄፓታይቲስ ቢ የሚጠቁ ዜጎች ቁጥር መጨመሩን ማስታወቁ ይታወሳል፡፡
በዚህም በዓለማችን በየዕለቱ 3 ሺሕ 500 ሰዎች በጉበት በሽታ እየሞቱ መሆኑን የገለጸ ሲሆን፤ ከእነዚህ ውስጥም 83 በመቶዎቹ በሄፓታይተስ ቢ በተሰኘው የጉበት በሽታ የሚሞቱ መሆናቸውን አመላክቷል፡፡
63 በመቶ ያህሉ ተጠቂዎች በአፍሪካ የሚገኙ ዜጎች መሆናቸውም በሪፖርቱ የተገለጸ ሲሆን፤ በሽታው እየተሰራጨባቸው ካሉ 10 ሀገራት መካከልም ኢትዮጵያ አንዷ መሆኗን አስታዉቋል፡፡
በደረጄ መንግስቱ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
#አሐዱ_ትንታኔ
የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ላለፉት ዓመታት ለአፍሪካ ብዙም ፋይዳ አልነበረውም ተብሏል፡፡
ዶናልድ ትራምፕም ሆኑ ካማላ ሃሪስ የምርጫ ዘመቻቸው ወቅት አፍሪካን እቅዳቸው ውስጥ አለማካተታቸው አሜሪካ ለአህጉሪቱ ያላት ትኩረት ዝቅተኛ መሆኑን የሚያሳይ ነው መሆኑም እየተነገረ ይገኛል፡፡ ይህንን እና ተያያዥ ጉዳዮችን በዛሬው ዓለም አቀፍ ትንታኔያችን ዳሰነዋል፡፡
ትንታኔውን ለመከታተል ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👇
https://youtu.be/fS5ubWsoIDY?si=FV-jv0OZxz2F-Vth
የሚዲያ ሕግ ረቂቅ ማሻሻያው ሥልጣንን ጠቅልሎ ለአንድ አካል የሚሰጥና በሒደትም ላልተገባ ተፅዕኖ በር የሚከፍት ነው ተባለ
ሕዳር 3/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የሚዲያ ሕግ አዋጁ ማሻሻያ አስፈላጊነት ላይ ገለልተኛ ጥናት ባልተደረገበት፣ በቂ የባለድርሻ አካላት ውይይትም ባልተካሔደበት ሁኔታ ረቂቁ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲፀድቅ መቅረቡ፣ እንዲሁም በአዋጁ ከለላ ተሰጥቷቸው የነበሩ የቁጥጥርና ሚዛን መጠበቂያዎች በረቂቅ አዋጁ ሊሻሩ የሚችሉ መሆናቸው አሳሳቢ ነው ተብሏል።
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥቅምት 19/2017 በ6ኛው ዙር 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን ባካሄደው 2ኛ መደበኛ ስብሰባ፣ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013ን ለማሻሻል የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ለዝርዝር እይታ ለዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መምራቱ ይታወሳል።
ይህንንም ተከትሎ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማህበር፣ የመብቶችና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (CARD)፣ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔን ጨምሮ 14 የሚሆኑ የሲቪክ ማህበራት የጋራ መግለጫ አውጥተዋል፡፡
በመግለጫቸውም "አሁን በአስፈፃሚው አካል ተረቅቆ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲፀድቅ የቀረበው ረቂቅ ማሻሻያ አዋጅ፤ በሥራ ላይ የሚገኘውን የመገናኛ ብዙኃን ሕግ በርካታ አንቀፆች ይዘትና መንፈስ የሚቀይር ነው" ብለዋል።
"ረቂቅ ማሻሻያው የአካሄድና የይዘት ግድፈቶች በስፋት የሚስተዋሉበት ነው" ያሉት ተቋማቱ፤ "በረቂቁ ማሻሻያ ላይ ምንም ዓይነት የሕዝብ ውይይቶች ባለመከናወናቸው የሲቪል ማኅበረሰቡን፣ የሚዲያ ሙያተኞችን እንዲሁም የሌሎች መብቶች ተሟጋቾችንና የማኅበረሰብ ድምፆች እንዳይሰሙ አድርጓል" ሲሉም ተችተዋል።
ማሻሻያውን ለማዘጋጀት የተሔደበት መንገድ ግልጽነትና አሳታፊነት የጎደለው መሆኑንም በመግለጽ፤ የረቂቅ አዋጁ አስፈላጊነት በገለልተኛ አካል በተሠራ ጥናት ስለመለየቱ የቀረበ ማስረጃ አለመኖሩንም አንስተዋል።
በሌላ በኩል "የረቂቅ አዋጁ የተለያዩ አንቀፆች በሥራ ላይ የሚገኘው የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ጥበቃ የሚሰጣችውን ነጻነቶች የሚገድብና የሚዲያ ተቆጣጣሪውን አካል በአስፈፃሚው አካል ተፅዕኖ ውስጥ ይከተዋል የሚል ስጋት አለን" ብለዋል።
ለአብነትም ያህል የነባሩን አዋጅ አንቀጽ 8 (2) ዋና ዳይሬክተሩ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስለሚሾምበት የሚደነግገው ክፍል፤ አንቀጽ 9 (1 እና 2) የቦርዱ አባላት እጩዎች የሚመለመሉበትና የሚፀድቁበት ሒደት ለሕዝብ ግልጽ መሆን እንዳለበት የሚደነግገው ከፍል፤ አንቀጽ 11 (6) የቦርዱ አባላት ከፖለቲካ ፓርቲ አባልነት ወይም ተቀጣሪነት የሚከለከሉበትን ሁኔታ የሚደነግገው ክፍል መሰረዝ ዋና ዋና የይዘት ለውጦች መሆናቸውን አመላክተዋል፡፡
በተያያዘም "በአዲሱ ማሻሻያ የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሹመት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ መሰጠቱ፤ ሥልጣንን ጠቅልሎ ለአንድ አካል ከመስጠትና በሒደትም ላልተገባ ተፅዕኖ በር ከመክፈቱ በተጨማሪ የባለሥልጣኑን ገለልተኝነትና ነፃነት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ረቂቅ አዋጅ ያደርገዋል" ብለዋል።
በተያያዘም "ረቂቅ አዋጁ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሚቀርብበት ወቅት ከተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የምክር ቤት አባላት ጭምር ተቃውሞ ገጥሞት የነበረ ቢሆንም፤ በቂ የባለድርሻ አካላት ውይይት ሳይደረግበት ወደቋሚ ኮሚቴ መመራቱ በጉዳዩ ላይ የሕዝብን ድምፅ በተገቢ ላለማካተቱ ሁነኛ ማሳያ ተደርጎ ይወሰዳል" ሲሉ ተናግረዋል።
ስለሆነም የማሻሻያ ረቂቅ አዋጁ አስፈላጊነት ላይ በጥናት የተደገፈ ማስረጃ እንዲቀርብ እና በባለድርሻ ወገኖች ሰፊ ውይይትና መግባባት እንዲደረስበት፣ እንዲሁም በጥናቱ እና ውይይቱ መሠረት ማሻሻያ ማድረጉ አስፈላጊ መሆኑ ከታመነበት፣ የማሻሻያ ረቂቅ አዋጁ በምክር ቤቱ ከመፅደቁ በፊት ትርጉም ያለውና ሁሉንም ባለድርሻ አካላት ያሳተፈ ውይይት እንዲደረግ ጠይቀዋል።
"ከፍተኛ ጥንቃቄ በማድረግ የማሻሻያ ረቂቅ አዋጁ መንፈስ ዴሞክራሲን ከማስፈንና የመገናኛ ብዙኃንን ነጻነትን ከማረጋገጥ አንፃር የነበረውን አስቻይ የሕግ ማዕቀፍ የሚንድና ወደኋላ የሚጎትት እንዳይሆን" ሲሉም የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶቹና የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማህበር አሳስበዋል።
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
በኢትዮጵያ የሚገኙ መገናኛ ብዙሃን መስማት የተሳናቸውን ዜጎች አካታች እንዲያደርጉ የሚያስገድድ መመሪያ ሊዘጋጅ መሆኑ ተገለጸ
ሕዳር 3/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት መስማት የተሳናቸው ዜጎችን ያካተተ ዝግጅት እንዲያቀርቡ የሚያስገድድ መመሪያ እያዘጋጀ መሆኑን ገልጿል፡፡
የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ፈቃድ ሲወስዱ ልዩ ትኩረት የሚሹ የማህበረሰብ ክፍሎችን አሳታፊ እና ተጠቃሚ የሚያደርጉ የፕሮግራም ይዘት እና አቀራረብ ሊኖራቸው እንደሚገባ የሚያስገድድ ሕግ መኖሩን የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮናስ ፋንታዬ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
ነገር ግን ይህ ሕግ ቢኖርም ተፈጻሚ እየተደረገ አለመሆኑን የተናገሩት ጽ/ቤት ኃላፊው፤ በዚህም ምክንያት ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በቀጣይ መገናኛ ብዙሃኑን የማስገደድ፣ የወጡ ሕጎች እንዲፈጸሙ የማድረግ እንዲሁም እርምጃም የመውሰድ ሥራን እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡
በዚህም መሰረት በመገናኛ ብዙሃን አካል ጉዳተኞችን አካታች ያደረጉ ዝግጅቶች እንዲተላፉ እንደሚደረግ የተገለጸ ሲሆን፤ ለአብነት ያህልም መስማት ለተሳናቸው ልጆች የሚሆኑ የሕፃናት ዝግጅቶች እንዲቀርቡ ለማድረግ በቀጣይ እቅድ መያዙን ኃላፊው አስታውቀዋል፡፡
ይህን ለማድረግ መካተት ያለባቸው አዳዲስ እቅዶች በመመሪያ የሚካተቱበትና ተፈጻሚ የሚሆኑበት ሁኔታ ስለመኖሩም ጠቁመዋል፡፡
በመሆኑም መስማት የተሳናቸውን ልጆች ተደራሽ ያደረጉ እና መረጃን የሚሰጡ ዝግጅቶች እንዲሰሩ ለማድረግ መታቀዱ ተመላክቷል፡፡
በተጨማሪም "በአጠቃላይ አካል ጉዳተኖችን አካታች ያደረገ ዝግጅት በመገናኛ ብዙሃን ላይ እየታዩ ባለመሆኑ፤ በአስገዳጅነት ለአካል ጉዳተኞች ሽፋን እንዲሰጡ ይደረጋል" ሲሉም አቶ ዮናስ ለአሐዱ አስታውቀዋል፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በመገናኛ ብዙኃን ላይ የሚተላለፉ የተለያዩ መረጃዎች አካል ጉዳተኞችን አካታች ያደረጉ እና ግንዛቤ የሚሰጡ እንዲሆኑ በቀጣይ በትኩረት እንደሚሰራም ተናግረዋል።
በመሆኑም "መገናኛ ብዙኃን በአካል ጉዳተኞች ላይ ምን ያህል ሚናቸውን እየተወጡ ነው?" የሚለውን በተመለከ፤ ሕጎችን የማስፈፀም ሥራ የሚከናወንበት ሁኔታ መኖሩ ተጠቁሟል።
በእሌኒ ግዛቸው
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
የሰላም ስምምነቱ በገለልተኛ እና አለም ዓቀፍ ተቋማት ሊረጋገጥና ተጠያቂነት ሊሰፍን ይገባል ሲሉ ሰባት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጠየቁ
ሕዳር 3/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በትግራይ የተካሄደው ጦርነት የፈጠረውን ቀውስና ያለውን ፖለቲካዊ ችግር ለመፍታት የተለያዩ ጥረቶች እየተደረገ መሆኑ ሲገለጽ ቆይቷል።
የዚሁ አካል የሆኑ ሰባት የትግራይ የሲቪክ እና የንግድ ማህበራት እና ጥምረቶችን ያካተተ፤ "ዋዕላ ትግራይ" ወይንም የትግራይ ኮንፈረንስ የተሰኘ መድረክ ከሰሞኑ በመቀለ ከተማ ተካሂዷል፡፡
በክልሉ በተለይም ከህወሓት፣ ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር፣ ከተቃዋሚ የትግራይ ፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት እና የሲቪክ ማህበራት ጋር ሲወያይ መቆየቱን፤ ከጥምረቱ መካከል አንዱ የሆኑትና የገርዓልታ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ወንድሙ አሳምነው ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
የፕሪቶሪያ ስምምነት፣ የትግራይ የፖለቲካ ሽግግር እና የሲቪክ እና የንግድ ሚና እድሎች እና ትግበራን አስመልክቶ በዘርፉ ሰፊ ልምድ ባካበቱ ባለሙያዎችና ማኅበራት ውይይት መደረጉን የገለጹት አምባሳደሩ፤ መፍትሄ የሚለውንም ኮንፈርንሱ እንዳስቀመጠ ገልጸዋል፡፡
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጥምረቱ በአሁናዊ ትግራይ ሁኔታ እና በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት አተገባበር ላይ ውይይቱን ካደረገ በኋላም ባለ አስር ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥቷል፡፡
በዚህም የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ከተፈረመ ሁለት ዓመት ቢሆነውም የስምምነቱ ዋና ዋና ምስሶዎች አለመተግበራቸውን ጥምረቱ ያነሳ ሲሆን፤ "ያልተጠናቀቁ ጉዳዮች ተጠናቀው ተጠያቂነት ይሰፍን" ሲልም ጥሪውን አቅርቧል፡፡
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶቹ በምዕራብ ትግራይ ያሉ ተፈናቃዮች እና በሱዳን የሚገኙ 70 ሺሕ የትግራይ ተወላጆችም ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ጠይቀዋል፡፡
ሁሉም አካላት የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ የተቀናጀ ጥረት እና ግፊት እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በትግራይ ክልል እና በፌደራል መንግሥት መካከል የተቀሰቀሰው ጦርነት በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት የዛሬ ሁለት ዓመት ከተጠናቀቀ በኃላ፤ በትግራይ የተኩስ ድምፅ መሰማት ቢቆምም በርካታ የስምምነቱ ምሶሶዎች እንዳልተገበሩ በቅርቡ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤትን ጨምሮ በርካቶች ወቀሳ ሲያቀርቡ ይሰማል፡፡
በአቤል ደጀኔ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመጀመሪያው ርዕሰ መሥተዳድር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
ሕዳር 3/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመጀመሪያው ርዕሰ መሥተዳድርና የነፃነት ትግል ዓርበኛ የነበሩት አቶም ሙስጦፋ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡
አቶ አቶም በክልሉ ሕዝቦች የነፃነት ትግል ውስጥ እጅግ ውድ የሆነ ዋጋ ከከፈሉ የነፃነት ዓርበኞች መካከል በቀዳሚነት የሚጠቀሱ መሆናቸውን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አሻድሊ ሀሰን ገልጸዋል፡፡
አቶ አሻድሊ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት የሐዘን መግለጫ መልዕክት፤ "አቶ አቶም ዕድሜ ዘመናቸውን ለክልሉ ሠላምና ልማት ሲታትሩ የኖሩ ባለ ራዕይ መሪ ነበሩ" ብለዋል፡፡
በክልሉ ሠላምና መረጋጋትን ለመፍጠር ያበረከቱት አስተዋፅዖ በክልሉ ሕዝብ ታሪክ ውስጥ የላቀ ስፍራ የሚሰጠውና ሲወሳ የሚኖር መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
ርዕሰ መሥተዳድሩ አክለውም በቀድሞ ርዕሰ መሥተዳድር ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን የገለጹ ሲሆን፤ ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸውም መፅናናትን ተመኝተዋል፡፡
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ከከተማ ፕላን ጋር የማይጣጣሙ ሕንፃዎች የመጠቀሚያ መብት ሊነጠቁ ይገባል ተባለ
ሕዳር 3/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ ከተሞች የግንባታ ፍቃድ የሌላቸውና የመጠቀሚያ መብት ያላገኙ ሕንፃዎች እንዲፈርሱ የሚያዝ ረቂቅ አዋጅ ለውይይት መቅረቡ ተሰምቷል።
በረቂቁ ላይ በተለይም በመሬት ላይ እንዲውሉ ከፀደቀው የሕንፃ ካርታ ውጭ ተላልፈው የተገነቡ ሕንፃዎች የመጠቀሚያ መብት እንዲነጠቁ ተጠይቋል።
ቀደም ሲል በሥራ ላይ የቆየውን የሕንፃ አዋጅ "በርካታ ጉደለቶች አሉበት" በሚል መሻርያ ረቂቅ አዋጅ በትናንትናው ዕለት ለከተማ መሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ቋሚ ኮሚቴ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
በውይይቱም በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች የሚገኙ ሕንፃዎች የመጠቀሚያ ሕግ ተላልፈው የተገነቡ ሕንፃዎች መኖራቸውን የተገለጸ ሲሆን፤ አገልግሎት አሰጣጣቸውን ጨምሮ የከተማና መሰረተ ልማት ፕላን ያልተከተሉ በመኖራቸው እንዲፈርሱ የሚያስገድድ ረቂቅ አዋጅ መሰናዳቱ ተነግሯል።
ለዚህም በሚመለከተው የመንግሥት አካል በከተማ የሚገኙ ሕንፃዎችን የመጠቀሚያ መብት እንዲነጥቁ የሚያስገድድና ቀደም ሲል የነበረው የመሻርያ አዋጅ ቀርቦ ውይይት መደረጉን ተገልጿል።
በረቂቅ አዋጁ ዙርያ በርከት ያሉ ሐሳቦች የተነሱበት ሲሆን፤ መሐንዲሶች የሚወጧቸው ፕላኖች ተጠያቂ የሚሆኑበት የሕግ ወሰን በተመለከተም አስተያየት ሲሰጥበት አሐዱ ሰምቷል።
ከተሞች ለመኖርያና ለንግድ የሚውሉ ሕንፃዎች ዙርያ ለይቶ ማስቀመጥና ማስጠቀም እንዳለባቸውም የምክር ቤት አባላቱ አሳስበዋል ተብሏል።
በሌላ በኩል በተለይም ከከተማ ፕላን ጋር የማይጣጣሙ ሕንፃዎች የመጠቀሚያ መብት ሊነጠቁ ይገባል የሚለውን በርካት ያሉ ትችቶች እንደተነሱበት አሐዱ ከቋሚ ኮሚቴው ሰብሰባ መረዳት ችሏል።
በአማኑዔል ክንደያ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
"በመርካቶ “ንብረት ሊወረስ ነው፤ ሱቃችን ሊዘጋ ነው” በሚል የሚናፈሰው ወሬ ሕጋዊ የንግድ ሥርዓት ለመዘርጋት እየተከናወነ ያለውን ሥራ ለማስተጓጎል ነው" የከተማ አስተዳደሩ
ሕዳር 2/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ መርካቶ አካባቢ "ንብረት ሊወረስ ነው፤ ሱቃችን ሊዘጋ ነው" በሚል የሚናፈሰው ወሬ ሕጋዊ የንግድ ሥርዓት ለመዘርጋት እየተከናወነ ያለውን ሥራ ለማስተጓጎል ታስቦ የሚናፈስ ነው ሲል ገልጿል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ "በመርካቶ አካባቢ አንዳንድ ነጋዴዎች “ንብረት ሊወረስ ነው፤ ሱቃችን ሊዘጋ ነው” የሚል መሰረት የሌለው ውዥንብር ውስጥ መግባታቸውን በማኅበራዊ ሚዲያዎች ተመልክተናል፡፡" ብሏል
ውዥንብሩ የመጣው "በደረሰኝ እንዲገበያዩ የሚጠበቅባቸው ነጋዴዎች በዚህ ሂደት ውስጥ እንዲያልፉ በሚደረገው ሥራ" ነው ሲል የገለጸው አስተዳደሩ፤ ይህ እንዲስተጓጎል ሆን ተብሎ የተነዛ አሉባልታ ነው ሲል ገልጿል።
በደረሰኝ እንዲገበያዩ የሚጠበቅባቸው ነጋዴዎችን በመለየት በደረሰኝ ግብይት እንዲፈጽሙ የከተማ አስተዳደሩ በተለያዩ ጊዜያት ጥሪ ሲያቀርብ መቆየቱን የገለጸም ሲሆን፤ "ይሁን እንጂ ይህንን ጥሪ ወደ ጎን በመተው እና ሕጋዊ የንግድ ሥርዓት ለመዘርጋት እየተከናወነ ያለውን ሥራ ለማስተጓጎል የተሰራ ውዥንብር ነው" ብሏል።
የከተማ አስተዳደሩ አክሎም፤ በውዥንብሮች እና የተሳሳቱ መረጃዎች ንብረት የሚያሸሹና ሱቅ የሚዘጉ ነጋዴዎች ተገቢነት ከሌለው ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ያሳሰበ ሲሆን፤ "እንዲሁም አምራች፣ አከፋፋይና ቸርቻሪ ነጋዴዎች ያለደረሰኝ መገበያየት ሕገወጥ ተግባር መሆኑን በአግባቡ በመረዳት ወደ ሕጋዊ መስመር ሊገቡ ይገባል" ብሏል።
በመርካቶ እየተከናወነ የሚገኘው ሕጋዊ የንግድ ሥርዓት እንዲኖር ለማስቻል የንግዱ ማኅበረሰብ ተባባሪ እንዲሆንም አስተዳደሩ ጥሪ አቅርቧል።
አንዳንድ ያለደረሰኝ በመገበያየት ሕዝብና መንግሥት ማግኘት ያለባቸውን ጥቅም እያሳጡ የራሳቸውን ኪስ የሚሞሉ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ያሳሰቡ አስተዳደሩ፤ ከዚህ በፊት ያለደረሰኝ የተገዙ ዕቃዎች ካሉ ሕጉ በሚያዘው መሠረት የማስመዝገብ ሥራ ማከናወን እንደሚጠበቅባቸው በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ አሳስቧል።
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
በሩብ ዓመቱ ብቻ ከ15 ሺሕ በላይ ግለሰቦች የስኳር ሕመም ተጠቂ መሆናቸው ተገለጸ
ሕዳር 2/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በተያዘው 2017 ዓ.ም የመጀመሪያ ሩብ ዓመት 500 ሺሕ በሚሆኑ ሰዎች ላይ የስኳር ሕመም ምርመራ ተደርጎ፤ ከ15 ሺሕ በላይ የሚሆኑት ላይ በሽታው እንደተገኘባቸው መረጋገጡን የጤና ሚኒስቴር ገልጿል፡፡
በኢትዮጵያ የስኳር ሕመምን በተመለከተ በዓመት 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች ምርመራ እንደሚያደርጉና ከነዚህ ዉስጥ ከ50 ሺሕ በላይ የሚሆኑ ሰዎች በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠበት ወቅት እንዳለም ታዉቋል፡፡
ታዲያ በዚህ በተያዘዉ ሩብ ዓመት በስኳር ሕመም 500 ሺሕ የሚሆኑ ሰዎች ላይ ምርመራ ተደርጎ ከ15 ሺሕ በላይ ሰዎች የተረጋገጠባቸዉ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችና የአይምሮ ጤና ባለሙያ አቶ አዲሱ ወርቁ ለአሐዱ ተናግረዋል።
ባለሙያው ስለ ስኳር ሕመም ማህበረሰቡ ጋር በቂ ግንዛቤ ባለመኖሩ ምክንያትና ቅድመ ጥንቃቄና ክትትል ባለመደረጉ ዜጎችን በከፋ ሁኔታ እየጎዳ እንደሚገኝ አንስተዋል።
የስኳር ሕመምን ለመከላከል የግንዛቤ ፈጠራ ሥራ እንዲሁም ታማሚዎችን ደግሞ የክትትልና የሕክምና ሥራዎችን በስፋት እየተሰሩ መሆናቸዉን አቶ አዲሱ ተናግረዋል።
ከስኳር ሕመም ጋር ተያይዘዉ የሚመጡ ተጓዳኝ በሽታዎች በተለይ ከልብ፣ ከአይን እንዲሁም ለኩላሊት በሽታ ተጋላጭ እንደሚያደርግ አንስተዉ፤ ማንኛዉም ሰዉ በየጊዜዉ ምርመራ ማድረግ እንደሚገባዉና በተለይ ከ40 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎች በአመት 1 ጊዜ ግደታ መታየት እንደሚገባቸዉ ገልጸዋል።
የስኳር ሕመም አንድ ሰው በደሙ ውስጥ ያለው የስኳር መጠን መሆን ከሚገባው በላይ ከፍ ሲል የሚከሰት ሲሆን፤ ጤናማ አመጋገብ በመመገብ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ፣ የሰውነት ክብደትን በመቆጣጠር፣ አልኮልን ባለመጠጣትና ሲጋራ ባለማጨስ የስኳር ሕመምን መከላከል እንደሚቻል ተገልጿል፡፡
የጤና ሚኒስቴር የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር ዳይሬክቶሬት እና የኢትዮጵያ ስኳር ሕመም ማህበር በኢትዮጵያ ለ34ኛ ጊዜ ሕዳር 5 ቀን 2017 ዓ.ም በተለያዩ ሁነቶች የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የስኳር ሕመም ቀን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ፤ አሁን ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ 653 ሚሊየን ዜጎች ከስኳር ከሕመም ጋር የሚኖሩ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ ደግሞ 1 ነጥብ 9 ሚሊየን በላይ ዜጎች ከሕምሙ ጋር እንደሚኖሩ ገልጸዋል፡፡
በአለምነው ሹሙ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
አዲሱ "የሕንፃ ረቂቅ አዋጅ" እንዲካተቱ የተሰጡ ሐሳቦች አልተካተቱም በሚል ተቃውሞ ገጠመው
ሕዳር 2/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መስከረም 30 ቀን 2017 ዓ.ም ባካሄደው 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ስብሰባ መርምሮ ለዝርዝር ዕይታ ለከተማ መሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ቋሚ ኮሚቴ የመራው የኢትዮጵያ የሕንፃ ረቂቅ አዋጅ ተቃውሞ ገጥሞታል።
የሕንፃ ረቂቅ አዋጁ ተቃውሞ የገጠመው፤ በዛሬው ዕለት የከተማ መሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ቋሚ ኮሚቴ ባደረገው ስብሰባ ላይ ነው።
በስብሰባው ተቃውሞ ካስነሱ ሐሳቦች መካከል፤ የግንባታ ፍቃድ አሰጣጥ ላይ ያሉ አሰራሮችን በተመለከተ ከቋሚ ኮሚቴው አባላት የተሰጡ ምክረ ሐሳቦችን አላካተተም የሚል ትችት ይገኝበታል።
ከዚህ ቀደም የሕንፃ አዋጅን በተመለከተ ከቋሚ ኮሚቴ አባላት ግብአትና አስተያየት ተሰጥቶበት የነበረ ቢሆንም፤ ለቋሚ ኮሚቴው በቀረበው ሪፖርት አብዛኞቹ አስተያየቶች አልተካተቱም ተብሏል።
በተለይም ከከተማና መሰረተ ልማት ጋር ተያይዘው የሚነሱ በግንባታ ወቅት የሚደርሱ አደጋዎችን ጨምሮ ተያያዥ ጉዳዮች አዋጁ ላይ አልተሻሻሉም የሚል ቅሬታም ተሰምቷል።
እንዲሁም የሕግና መቀጮ በተመለከተ በፍትሐብሔርና በሕግ ጉዳዮች ማለቅ የሚችሉ ነገሮች በአዋጁ ላይ መስፈራቸው የሙያ ደሕንነትን የሚጋፋ መሆኑን ከተለያዩ የሙያ ማሕበራት የተወከሉ የቋሚ ኮሚቴው አባላት ገልጸዋል።
በተጨማሪም የአንድ ሕንፃ ፕላን በሚወጣበት ጊዜ የተሳተፉበት ሙያተኞች የደረጃ ጥራታቸው ጉዳይ አሳሳቢ መሆኑ በስብሰባው ላይ ተነስቷል።
በአማኑዔል ክንደያ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
የሆቴል ባለሙያዎችን አለባበስ እና የመዋቢያ ጌጣጌጥ አጠቃቀም ሥርዓት የሚወስን ደንብ ወጣ
ሕዳር 2/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በአዲስ አበባ ከተማ የሆቴል ባለሙያዎችን አለባበስ እና የመዋቢያ ጌጣጌጥ አጠቃቀም ሥርዓት የሚወስን ደንብ መውጣቱን የከተማ አስተዳደሩ ፍትህ ቢሮ አስታውቋል።
ይህ ደንብ ቁጥር 178/2017 ሆኖ የወጣ ሲሆን በሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ውስጥ ለሚሰሩ ባለሙያዎች ወጥ የሆነ የአለባበስ፣ የጌጣጌጥ እና የመዋቢያ አጠቃቀም ሥርዓት በመዘርጋት የሀገር ባህልና እሴት እንዲጠበቅ ለማድረግ የወጣ ደንብ መሆኑ ተነግሯል፡፡
ከደንቡ የአለባበስ ሥርዓት ውስጥ ለአብነት ደረት ክፍልን ያልሸፈነ ወይም ከአንገት በታች ያለውን የሰውነት ክፍል የሚሸፍን ሸሚዝ ያለበሰ፣ የሴቶች ጉርድ ቀሚስ ቁመቱና ቅዱ ከጉልበት በላይ ከሆነ፣ ከጋብቻ ቀለበት ውጪ ጌጣጌጦችን በሚታዩ የሰውነት ክፍሎች ላይ ከተደረገ እንደሚያስቀጣ ማስቀመጡ ተገልጿል፡፡
ደንቡ በዘርፉ ተሰማርተው የሚሰሩ ሙያተኞች ሊደርስባቸው ከሚችለው አካላዊ፣ ሥነ-ልቦናዊ ጫና እና አላስፈላጊ ጥቃቶችን ለመከላከል ብሎም በከተማው የሚሰጠው የሆቴል አገልግሎት ዓለም አቀፍ መስፈርትን የሚያሟላ እንዲሆን ማድረግ ያለመ መሆኑም ተመላክቷል፡፡
በዚህም መሠረት ይህ ደንብ በሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የተሰማራ ባለሙያ በደንቡ በተደነገገው መሰረት አክብሮ እየሰራ ስለመሆኑ ወቅቱን የጠበቀ ክትትል እንደሚደረግ ተነግሯል።
ለዚህም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል፣ ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ከአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን እና የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ጋር በቅንጅት በመስራት ደንቡ ተፈጻሚ እንዲሆን እንደሚደረግ አሐዱ የከተማ አስተዳደሩ ፍትህ ቢሮ ያገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ኢትዮጵያ ወደ ቻይና እየላከቻቸው ያሉ የወጪ ምርቶች መጠን ከፍ እያለ መምጣቱ ተገለጸ
ሕዳር 2/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ኢትዮጵያ ወደ ቻይና የምትልካቸው የግብርና ምርቶችን ጨምሮ የእደጥበብ ውጤቶች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ ተነግሯል፡፡
የቻይና ባለሀብቶች በግብርና ምርቶች ማቀነባበር እንዲሳተፍ በቀረበላቸው ጥያቄ መሰረት በቀጣይ ሁለት ወራት ውስጥ ወደ አገር ቤት ይገባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገልጿል።
ኢትዮጵያና ቻይና በየገንዘቦቻቸው እንዲገበያዮ በደረሱት ስምምነት መሰረትም በሁለቱም አገራት በሚኖረውን የንግድ ልውውጥ ተግባራዊ ይደረጋልም ተብሏል።
ከዚህ ቀደም በኢንዱስትሪ ፓርኮች ተሰማርተው የነበሩ የቻይና ድርጅቶች ውላቸውን የሚያድሱበት ሁኔታና ሥራቸውን እንዲቀጥሉ ይደረጋል መባሉን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ውሉ የሚታደስበትም የሁለቱም አገራት የንግድ ሚኒስትሮች በተደረሰው ስምምነት መሰረት በየገንዘቦቻቸው ግብይት መፈፀም እንደሚጀምሩ ተነግሯል።
በዚህም መሰረት የቻይና ባለሀብቶች የኢትዮጵያን ምርቶች የመግዛት ፍላጎት እያደገ መምጣቱ የተገለጸ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ ምርቶች ላይ እሴት በመጨመር ለመስራት ፍላጎት ላላቸው ባለሀብቶች ከቻይና መንግሥት የተለያዩ ማበረታቻዎች እንደተዘጋጀላቸውም ተነግሯል።
በአማኑዔል ክንደያ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
#ADVERTISMENT
#ጊፍትሪልስቴት
ታላቅ የምስራች!
**
ጊፍት ሪል ስቴት ከ10% ቅድመ ክፍያ ጀምሮ በ22 ሳይቶቹ ቅንጡ አፓርትመንቶችን እና የንግድ ሱቆችን ለሽያጭ አቅርቧል፡፡
ይህ ሳይት ለአፓርትመንትና ንግድ ሱቆች የሚውሉ G+25 ሶስት መንታ ህንጻዎች ያሉት ሲሆን የዚህ 6ኛ መንደር መለያዎች፡-
•ከባለአንድ እስከ ባለአራት መኝታ ክፍሎች ያሉት፣
•ለመኖሪያም ሆነ ለንግድ ተመራጭ አካባቢ የሆነ፣
•በአንድ ወለል ሶስት ቤቶች ብቻ ያሉት፣
•በእያንዳንዱ ወለል ስድስት አሳንስር ያለው፣
•አራት ቤዝመንት ያሉት በቂ የመኪና ማቆሚያ የተዘጋጀለት፣
•24 ሰዓት የኤሌክትሪክ፣ ኢንተርኔትና ውሃ አቅርቦት አሉት፣
ጊፍት ሪል ስቴት
ማህበረሰብን እንገነባለን!
ለበለጠ መረጃ፡-
Website: https://www.giftbusinessgroup.com
Twitter: https://twitter.com/GIFTBusinessG
YouTube: www.youtube.com/channel/UCcqr7cpVv9ski-F7haxXx4w
Facebook: www.facebook.com/profile.php?id=100090918391017...
Telegram: /channel/giftbusinessgroup
Short Code: 8055