#አሐዱ_ትንታኔ
ዶናልድ ትራምፕ ከቻይና በሚገቡ ምርቶች ላይ የሚጥሉት ከፍተኛ ታሪፍ ቻይናን ሊያጠነክራት እንደሚችል የዘርፉ ባለሙያዎች ገልጸዋል።
አብዛኛው ትኩረቱዋ ወታደራዊ ሃይል ላይ እንደሆነ የሚነገርላት ቻይና የትራምፕ ከፍተኛ ታሪፍ ከዚህ በኅላ ኢኮኖሚዋም ላይ እንድታተኩር ያስገድዳታል ተብሏል፡፡ በዚህ እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የዛሬው ዓለም አቀፍ ትንታኔያችን ትኩረቱን አድርጓል፡፡
ትንታኔውን ለመከታተል ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👇
https://youtu.be/JIb_UAajX3Y?si=HWWMvdu52IZJlmP8
በሸገር ከተማ የ6 ዓመቷን ታዳጊ ሕጻን አስገድዶ የደፈረዉ ግለሰብ በ12 ዓመት እስራት ተቀጣ
ሕዳር 5/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በሸገር ከተማ አስተዳደር ኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ ዉስጥ ጨለማን ተገን በማድረግ ወላጆች በሌሉበት ያገኛትን የ6 ዓመት ሕጻን ልጅ የደፈረዉ ግለሰብ በእስራት መቀጣቱ ተገልጿል።
ተከሳሽ ካብታሙ ጥላዬ የተባለዉ ግለሰብ፤ መስከረም ወር 2017 ዓ.ም ሕጻኗ በረንዳ ላይ እየተጫወተች ባለችበት ሰዓት አባብሎ በመዉሰድ ጥቃቱን መፈፀሙ በማስረጃ መረጋገጡን አሐዱ ከሸገር ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ሕጻኗ በደረሰባት ጥቃት የተነሳ ከፍተኛ ደም ሲፈሳት የተመለከቱት ወላጆቿ ጉዳዩን ወዲያውኑ ለፖሊስ በማሳወቅ የህክምና እርዳታ ማግኘቷም ተገልጿል።
ፖሊስም ከወላጆች ባገኘዉ ጥቆማ መሠረት ባዳረገዉ ክትትል ተከሳሹን በቁጥጥር ሥር በማዋል ባደረገዉ ምርመራ ተከሳሹ ሙሉ በሙሉ ጥፋተኛ መሆኑን አምኗል።
በዚህም መሰረት ፖሊስ የተከሳሹን ቃል እና የሕክምና ማስረጃ በማደራጀት ለዐቃቤ ሕግ የላከ ሲሆን፤ ዐቃቤ ሕግም ማስረጃዉን ከመረመረ በኃላ በሕጻናት ላይ የሚፈፀም የወሲብ ጥቃትን በተመለከተ የተደነገገዉን የወንጀል ህግ 627 ንዑስ አንቀፅ ሁለትን በመተላለፍ የፈፀመዉን ድርጊት ከግምት ዉስጥ በማስገባት ክስ መስርቷል።
ክሱን ሲከታተል የነበረዉ የሸገር ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተከሳሹን በ12 ዓመት እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል።
ወላጆችም ሕጻናትን ለማያዉቁት ሰዉ ጥሎ መሄድ እና ብቻቸዉን መተዉ ለእንደዚህ አይነት ችግሮች ተጋላጭ እንዲሆኑ ስለሚያደርግ፤ አስፈላጊዉን ጥንቃቄ ቢያደርጉ መልካም እንደሆነ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አሳስቧል፡፡
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
በኢትዮጵያ 28 በመቶ የሚሆኑት እናቶች ከጤና ተቋማት ውጭ እንደሚወልዱ ተገለጸ
ሕዳር 5/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ በሁሉም አካባቢዎች በሚባል ደረጃ በተለያዩ ምክንያቶች 28 በመቶ የሚሆኑ እናቶች በጤና ተቋማት በባለሞያዎች ሳይታገዙ እንደሚወልዱ ጤና ሚኒስትር አስታውቋል።
ይህንን ያሉት በሚኒስትር መስሪያ ቤቱ የሕዝብ ግንኙነት ቢሮ ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር ተገነ ረጋሳ ናቸው፡፡
ኃላፊው አክለውም በየአካባቢው ባለው የፀጥታ ሁኔታ፣ በመሠረተ ልማቶች ጉድለት፣ በግንዛቤ ማነስ ሳቢያ እንዲሁም በሌሎች መሰል ችግሮች ምክንያት በባህላዊ መንገድ እናቶች እንደሚወልዱ ተናግረዋል።
በዚህም ከ2016 ጀምሮ እስካሁን በተሰራው ጥናት 72 በመቶ እናቶች ብቻ በጤና ተቋማት እንደሚወልዱ ጠቁመዋል።
አያይዘውም በእናቶች ወሊድ ላይ ዘረፈ ብዙ ሥራዎች ቢሰሩም፤ ችግሮቹ ብዛት አንጻር በቂ አለመሆኑን ለአሐዱ ገልጸዋል።
የሕዝብ ግንኙነት ቢሮ ኃላፊው፤ ጉዳዩ የሚያስከትለውን አሉታዊ ተፅዕኖ በመረዳትና በባለሙያዎች በመታገዝ ልጆችን በመውለድ የልጆችንና የእናቶችን ጤና መጠበቅ እንደሚስፈልግም ተናግረዋል።
በወልደሐዋርያት ዘነበ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
በሞቃዲሾ በተፈጸመ የቦንብ ጥቃት የ3 ሰዎች ሕይወት አለፈ
ሕዳር 5/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ በመንገድ ዳር በተፈፀመ የቦምብ ጥቃት ሁለት የጸጥታ አካላት እና አንድ ሰላማዊ ሰው መገደላቸው ተገልጿል፡፡
በተጨማሪም በፍንዳታው ሌሎች ሦስት ሰዎች ቆስለው ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸው ተነግሯል።
በሞቃዲሾ የደህንነት ባለስልጣን የሆኑት አሊ አህመድ፤ ፍንዳታውን በተመለከተ ፖሊስ እና የፀጥታ አካላት በአካባቢው በመገኘት ምርመራ መጀመራቸውን ለአናዶሉ ገልጸዋል፡፡
ለጥቃቱ እ.ኤ.አ ከ2007 ጀምሮ የሶማሊያ መንግሥትን እና የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪዎችን ሲዋጋ የቆየው አልሸባብ ሃላፊነቱን መውሰዱም ተነግሯል።
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የትምህርት ተቋማት የሰለጠነ ሰው ኃይል ምንጭ እንዲሆኑ ትዕዛዝ ማስተላለፋቸው ተሰማ
ሕዳር 4/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቴክኒክና ሙያ የትምህርት ተቋማት መተግበር አለበት ያሉትን መመርያ ማውረዳቸው የተገለጸ ሲሆን፤ ተቋማቱ መሰረታዊ ለውጥ እንዲደረግባበቸው መታዘዙን የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት አስታውቋል።
ተላለፈ የተባለውን ይኸው መመርያ ከተለያዩ አገራት ልምድ የተቀሰመ የስልጠና አሰጣጥ የትምህርት ሞዴል መሆኑን ተገልጿል።
"ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ላይ አስተላለፉት የተባለው የስልጠና ሞዴል ለመሆኑ ምን መሳይ ነው?" ሲል አሐዱ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድርን (ዶ/ር) ጠይቋል።
የኢንስቲትዮቱ ዋና ዳይሬክተር ላነሳንላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፤ "የስልጠና ሞዴሉ ፐብሊክ ፕራይቬት ኮንኔክሽን ይሰኛል" ብለዋል።
አሐዱም ይኸው የስልጠና ሞዴል በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሥራ ጉብኝት ካደረጉባቸው የሩቅ ምስራቅ አገራት የተቀዳ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ ጋር በነበረው ቃለ ምልልስ ለማወቅ ችሏል።
በኢትዮጵያ በርካታ ቁጥር ያለው ወጣት ኃይል ቢኖርም አብዛኛው የሰለጠነና የክህሎት ባለቤት እንዳልሆነ ዶክተር ብሩክ የገለጹ ሲሆን፤ የትምህርት ሞዴሉ ሁነኛ መፍትሔ መሆኑን ተናግረዋል።
አክለውም፤ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ምክረ ሀሳብ ከፍተኛ ለውጥ ማምጣት የሚችል መሆኑንና ተፈፃሚነቱ እንዲረጋገጥ ብርቱ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም ገልጸዋል።
ይህንን የስልጠና ሞዴል በተመለከተም በሌሎች አገራት ያለውን ልምድ ጠቅሰው፤ "አዋጭነቱን የተረጋገጠለት ነው" ብለዋል።
አሁን ላይ በኢትዮጵያ የሙያ ትምህርት ተቋማትን ለማስፋፋት እየተደረገ ያለውን ጥረት ጨምሮ እየተስተዋለ ያለው ውጤት ጥሩ በሚባል ደረጃ ላይ መሆኑ ተነግሯል።
ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትም ቢሆኑ ከቀለም ትምህርት ባሻገር ሙያ ተኮር የትምህርት ዝግጅት እንዲሰጡ እየተመከረበት መሆኑን ከዋና ዳይሬክተሩ ሰምተናል።
በአማኑዓል ክንደያ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
"ላኪዎች ከነገ ጀምሮ ካመነጩት የውጭ ምንዛሬ 50 በመቶውን በመሸጥ ቀሪውን ላልተወሰነ ጊዜ በአካውንታቸው ማስቀመጥ ይችላሉ" ብሔራዊ ባንክ
ሕዳር 4/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ላኪዎች ያመነጩትን የውጭ ምንዛሬ 50 በመቶ ወዲያውኑ በመሸጥ ቀሪውን 50 በመቶ ላልተወሰነ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ ባለ አካውንታቸው ማስቀመጥ የሚችሉበት አሰራር ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገልጿል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ እንዳሉት፤ ላኪዎች ካመነጩት የውጭ ምንዛሬ 50 በመቶውን ለባንኮች ወዲያውኑ በመሸጥ ቀሪውንም በአንድ ወር ውስጥ መሸጥ ይገደዱ ነበር።
በወቅቱ አሰራሩ በጊዜያዊነት ተግባራዊ ሲደረግ የተረጋጋ የውጭ ምንዛሬ ፍሰት እንዲኖር ከመፈለግ እንደነበር አቶ ማሞ አስታውሰዋል።
ከነገ ጀምሮ ግን ላኪዎች ያመነጩትን የውጭ ምንዛሬ 50 በመቶ ወዲያውኑ በመሸጥ ቀሪውን 50 በመቶ ላልተወሰነ ጊዜ በአካውንታቸው ማስቀመጥ ይችላሉ ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
"ይህም ማለት ያመነጩትን የውጭ ምንዛሬ በአንድ ወር ውስጥ እንዲሸጡ አይገደዱም" ብለዋል።
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ www.tiktok.com/@ahadutv.official
#አሐዱ_ስንክሳር
ኢትዮጵያ ሰሞኑን ታላላቅ አፍሪካዊ ጉዳዮችን አክብራለች።
ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ፣ የባሕል፣ የኪነጥበባት፣ የማሕበረሰብ አንቂዎች፣ የሰላምና የዕርቅ ተቋማት ተወካዮችና የተለያዩ አፍሪካዊ ባሕላዊ መሪዎች በአዲስ አበባ ታድመው ነበር።
በዚሁ በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ ውስጥ የተሰባሰቡት አፍሪካውያን ስለየሀገራቸው እና አሕጉራቸውም ጭምር በጥናትና በምርምር የዳበሩ ውይይቶችን አድርገዋል።
በውይይቶቻቸውም አፍሪካ ትልቅ ተፈጥሮአዊ ሐብት ያላት፣ የባሕልና ሀገር በቀል ዕውቀቶች ያሏት፣ የሰው ሐብትና ምቹ ዕድሎች ኖረዋት፣ ነገር ግን በሰፊው እንዳልተጠቀመችበትም ተወስቷል።
በመጨረሻም ወደ አፍሪካዊያን ውህደት፣ አንድነት፣ ወደ ፓን አፍሪካኒዝም የሚደረገው ጉዞ መፋጠን እንዳለበትም ተገልጿል።
በዛሬው ኢትዮጵያዊ ስንክሳራችን ይሄን ትልቅ ጉባኤ መሠረት በማድረግ ስለ ፓን አፍሪካኒዝም፣ ስለ አፍሪካዊነት ጥቂት ነጥቦችን እናነሳሳለን።
በጥበቡ በለጠ
ጥንቅሩን ለመከታተል ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👇
https://youtu.be/wNhmirMD3Wg?si=HOaXvB4ir2WuClZQ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ገቢ ወጪውን መሸፈን እንደማይችል ተናገረ
ሕዳር 4/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የታሪፍ ጭማሪ በየአራት ዓመቱ የሚደረግ ቢሆንም፤ ለስድስት ዓመታት ምንም አይነት ጭማሪ ሳይደረግ መቆየቱን ገልጿል።
በዚህም ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል እንዲሁም ከእራሱ ከአገልግሎቱ የተውጣጡ ባለሙያዎች የታሪፍ ጭማሪ ማድረግ የሚያስችል ዝርዝር ጥናት ማድረጋቸውን ለአሐዱ የገለጹት፤ የተቋሙ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ መላኩ ታዬ ናቸው።
እንዲሁም "በሦስተኛ ወገን ጥናት ተደርጓል ያሉ" ሲሆን ጥናቶቹን ማዕከል በማድረግ የሚኒስትሮች ምክር ቤት እንዳጸደቀው ገልጸው፤ "የታሪፍ ጭማሪው የህብረተሰቡን አቅም ከግንዛቤ ያስገባ ነው" ብለዋል።
ከአገልግሎቱ ተጠቃሚ ከሆኑ ደንበኞች 60 በመቶ ከ50 ኪሎ ዋት ሰዓት በታች ተጠቃሚ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው፤ በወር ከ200 ኪሎ ዋት ሰዓት የመጠቀመው 80 በመቶው ሲሆን ይህ የሚደጎምበት ስርዓት መኖሩን አንስተዋል።
የኤሌክትሪክ አገልግሎት ግብዓት ከ70 በመቶ በላይ በውጭ ምንዛሬ ተገዝቶ የሚገነባ መሠረተ ልማት ነው ያሉት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው መላኩ፤ "ቢያንስ ተቋሙ የሚያወጣውን ወጪ መሸፈን የሚያስችል ክፍያ ሊኖረው ይገባል" ብለዋል።
ይህ ካልሆነ ግን አገልግሎቱ የሚሰጠውን አገልግሎት ሊቋረጥ እንደሚችል አንስተዋል።
ኢትዮጵያ ካደረገችው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ በፊት ጥናቱ መደረጉንም በመግለጽ፤ አሁንም ማሻሻያውን የሚያመጣውን የገበያ ሁኔታ ምልከታ ሊደረግበት እንደሚችል ጠቁመዋል።
በፍርቱና ወልደአብ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
በትግራይ ክልል ወቅቱን ባልጠበቀ ዝናብ ምክንያት የጤፍ ሰብል ላይ ከፍተኛ ጉዳት መከሰቱ ተገለጸ
ሕዳር 4/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በትግራይ ክልል ባለፉት ሁለት ሳምንታት በጣለው ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ በተለያዩ ሰብሎች ላይ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን፤ በተለይም በጤፍ ሰብል ላይ የከፋ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታውቋል።
ባሳለፍነው ሳምንት በክልሉ ወቅቱን ያልጠበቀና በረዶ የቀላቀለ ዝናብ በመዝነቡ ሳቢያም ያልተሰበሰቡ ምርቶች ላይ ጉዳት መድረሱን ለአሐዱ የተናገሩት፤ በቢሮው የአዝርእት ማሻሻያና አፈር ልማት ዳይሬክተር አቶ አታክልቲ አረፈ ናቸው።
አሁን ላይ አርሶ አደሩን በማነቃቃት በክልሉ ያልተሰበሰቡና ማሳ ላይ ያሉ የግብርና ምርቶች እንዲሰበሰቡ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
ቢሮው በክልሉ የሚገኙ ተራድኦ ድርጅቶችን ጨምሮ የተለያዩ ተቋማትን በማስተባበር ያልተሰበሰቡ ምርቶችን ለመሰብሰብና ሰብል ላይ የበለጠ ጉዳት እንዳይደርስ ጥረት እየተደረገ እንዳለም ገልጸዋል።
በክልሉ የተዘራው ሰብል እስካሁን መሰብሰብ የተቻለው 47 በመቶ መሆኑን ጠቅሰው፤ ቀሪዎቹ በቀጣይ ጊዜ እንደሚሰበሰቡ የክልሉ ግብርና ቢሮ የአዝርእት ማሻሻያና አፈር ልማት ዳይሬክተር አቶ አታክልቲ አረፈ ለአሐዱ ተናግረዋል።
በትግራይ ክልል ካለው የሰብል እርሻ 70 በመቶ በክረምቱ በሰብል መሸፈን እንደቻለ ገልጸው፤ ቀሪው 30 በመቶ እንዳልተዘራበትም ጨምረው ገልጸዋል።
የክልሉ ግብርና ቢሮ ቀደም ባሉ ጊዚያቶች አርሶ አደሩ ምርቱን በጊዜ እንዲሰበሰብ በግብርና ባለሙያዎች በኩል ጥሪ ሲደረግለት እንደነበር ጠቅሰው፤ በተለያዩ ምክንያቶች ምርቱ ሳይሰበሰብ መቅረቱን አስታውቀዋል።
በአማኑዔል ክንደያ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
#UPDATE
በፍራንኮ ቫሉታ ይገቡ የነበሩ መሰረታዊ የፍጆታ ሸቀጦች በመደበኛ የንግድ ባንኮች የመተማመኛ ሰነድ እንዲገቡ መወሰኑ ተገለጸ
ሕዳር 4/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በፍራንኮ ቫሉታ ከውጭ የሚገቡ መሰረታዊ የፍጆታ ሸቀጦች በመደበኛ የንግድ ባንኮች የመተማመኛ ሰነድ /LC/ አማካኝነት እንዲገቡ መወሰኑን የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ገለጹ፡፡
መንግሥት በመሰረታዊ የንግድ ሸቀጦች ላይ የምርት እጥረት እንዳይከሰት በማሰብ ለግል ባለሀብቶች ፍራንኮ ቫሉታ መፍቀዱ ይታወሳል፡፡
የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ እንዳሉት፤ ፍራንኮ ቫሉታ መሰረታዊ ሸቀጦችን ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት የምርት እጥረት እንዳይከሰት የተወሰነ እገዛ አድርጓል፡፡
ይሁን እንጂ የፍራንኮ ቫሉታ ባልተገባ መንገድ ለጥቁር ገበያ በመጋለጡ በውጭ ምንዛሬ ላይ ጫና በማሳደር ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ማመዘኑን ተናግረዋል፡፡
የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፖሊሲ ትግበራው በመደበኛውና በትይዩ ገበያው መካከል ያለውን የውጭ ምንዛሬ ተመን ተቀራራቢ በማድረጉ የፍራንኮ ቫሉታ እንዲነሳ መደረጉን ገልጸዋል፡፡
መሰረታዊ የፍጆታ ሸቀጦችን በፍራንኮ ቫሉታ ወደ ሀገር ውስጥ የማስገባት ውሳኔ ሙሉ በሙሉ እንዲቆም መደረጉንም ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።
በሂደት ላይ ያሉ ከውጭ የሚገቡ ሸቀጦች በሁለት ሳምንታት ውስጥ እንዲገቡ እንደሚደረግም ተናግረዋል፡፡
በውሳኔው መሰረትም ከውጭ የሚመጡ መሰረታዊ የፍጆታ ሸቀጦች በንግድ ባንኮች የመተማመኛ ሰነድ ብቻ እንዲገቡ መወሰኑንና ይህም ወደ ተግባር መግባቱን ገልጸዋል።
የንግድ ባንኮች ለመረሰታዊ ሸቀጦች የሚሆን በቂ የውጭ ምንዛሬ ክምችት እንዳላቸው ጠቅሰው፤ "ባንኮች ለሸቀጦች ትኩረት ሰጥተው የውጭ ምንዛሬ አቅርቦት እንዲያሻሽሉ ይደረጋል" ብለዋል፡፡
መንግሥት የመሰረታዊ ሸቀጦችን አቅርቦትና ዋጋ በማረጋጋት የፖሊሲ ርምጃው ተጠናክሮ እንዲቀጥል እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡
መንግሥት በወሰዳቸው የቁጥጥርና የፖሊሲ ርምጃዎች በትይዩ ገበያውና በመደበኛ ገበያው መካከል ያለው ልዩነት በእጅጉ መጥበቡን አብራርተዋል፡፡
በተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፖሊሲ ትግበራው የውጭ ምንዛሬ ተመን መዋዠቅ አላጋጠመም ያሉት ሚኒስትሩ፤ በቀጣይም በብሄራዊ ባንክ በኩል የተጠናከረ ክትትል ይደረጋል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ከሳምንት በፊት ጥቅምት 29 ቀን 2017 የገንዘብ ሚኒስቴር መንግሥት የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ተከትሎ የዋጋ ግሽበት እንዳይከሰት በሚል ፍራንኮ ቫሉታን ፈቅዶ እንደነበር በመግለጽ፤ "አሁን ላይ ዋነኛውን ምእራፍ የታለፈ በመሆኑ ፍቃዱን አንስቻለሁ" ማለቱን አሐዱ መዘገቡ ይታወሳል።
የፍራንኮ ቫሉታ ፍቃዱን ከጥቅምት 29/2017 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የማይደረግ መሆኑን በሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ ተፈርሞ በወጣ ደብዳቤ መገለጹን ዘግቦ እንደነበርም አይዘነጋም።
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
አወንታዊ አስተሳሰብ ማጣት ለሥራዉ እንቅፋት እንደሆነበት የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ገለጸ
ሕዳር 4/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ሦስት ዓመት ሊሞላ የወራት እድሜ የቀረዉ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክር ኮሚሽን እያከናወነ ባለው የሥራው ሂደት ላይ አወንታዊ አስተሳስብ ማጣት እንቅፋት ሆኗብኛል ሲል ገልጿል፡፡
ይሁን እና በሥራ ሂደት የሚያጋጥሙ ችግሮችን በመቋቋም ባለፉት ሦስት ዓመታት በ11 ክልሎች እና በሁለት የከተማ መስተዳደሮች የአጀንዳ ማሰባሰብ መርሃግብር ማጠናቀቁን የገለጸ ሲሆን፤ ከ100 ሺሕ በላይ ዜጎችን ማሳተፍ መቻሉን አስታውቋል፡፡
አሐዱም "ኮሚሽኑ ሥራዉን ከጀመረ ጀምሮ ምን ያህል አጀንዳ ማሰባሰብ መሰብሰብ ችላችኋል? ምን ያህሉንስ በልየታ አስቀምጣችኋል?" ሲል ጠይቋል፡፡
የሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች ውስጥ አንዱ የሆኑት ዮናስ አዳዬ (ዶ/ር) በሰጡት ምላሽ፤ አሁን ባለው ሁኔታ ይፋዊ ቁጥር መናገር ባይቻልም ነገር ግን በቀጣይ ለሕዝብ ይፋ እንደሚደረግ ገልጸዋል፡፡
የሀገራዊ ምክክር ሂደት በታቀደው ጊዜ ውስጥ እንደሚሳካ ተስፋቸውን የገለጹት ዶክተር ዮናስ፤ "ነገር ግን አውንታዊ አስተሳሰብ በማጣት አሉታዊ አመለካከት ጎልቶ መታየቱ እንዲሁም በማህበራዊ ትስስር ገፆች የሚሰራጩ የሃሰት መረጃዎች በሥራ ሂደቱ ላይ እንከን ሆኗል" ሲሉ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
አክለውም አንዳንድ ችግሮች ቢኖሩም እንኳን የሥራ ሂደቱን በተገቢው ጊዜ ለማጠናቀቅ፤ የሲቪክ ማህበራት ድርጅቶችን በማካተት በጋራ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በተለያዩ አጋጣሚዎች ገለልተኛ እንዳልሆነ ትችት ሲቀርብበት ቢደመጥም፤ በሕዝብ ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት ማግኘት እንደቻለ ኮሚሽነሩ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
በደረጄ መንግስቱ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ዶናልድ ትራምፕ ለቢሊየነሩ ኤለን መስክ ሹመት ሰጡ
ሕዳር 4/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በ2024ቱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ቅስቀሳ ወቅት፤ የተመራጩ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የጀርባ አጥንት የነበረው ቢሊየነሩ ኤለን መስክ የመንግሥትን ብቃት የሚገመግም አዲስ መስሪያ ቤት የኃላፊነት ሹመት ተሰጥቶታል።
ተመራጩ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኤለን መስክ ለሪፐብሊካን እጩ ፕሬዚዳንትነት ተወዳድረው ከነበሩት ቪቬክ ራምስዋሚ ጋር በጋራ ይህንን መስሪያ ቤት ይመራሉ ብለዋል።
መስሪያ ቤቱ በዋነኝነት የመንግሥት ቢሮክራሲን ለማስወገድ እና ወጪን በመቀነስ ላይ ከመንግሥታዊ ሥራ ውጭ ምክር እና መመሪያ ይሰጣል ተብሏል።
መስሪያ ቤቱ መንግሥታዊ ሚና የለውም የተባለ ሲሆን ምን አይነት ቅርጽ እንደሚኖረው እስካሁን ግልጽ አልሆነም።
በተጨማሪም ተመራጩ ፕሬዚዳንት ትራምፕ የፎክስ ኒውስ አቅራቢውን ፒት ሄግስትን የመከላከያ ጸሓፊ እንዲሁም ጆን ራትክሊፍን የብሔራዊ መረጃ ዳይሬክተር አድርገው መምረጣቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
ኤለን መስክ በመንግሥት ብቃት እና የበጀት ቅነሳ ላይ ለመስራት ፍላጎት እንዳለው ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ መናገሩ ይታወሳል፡፡
በቅርቡም በኤክስ ላይ በለጠፈው ጽሁፍ “በመንግሥት ውስጥ ከፍተኛ ማባከን እና አላስፈላጊ ቁጥጥር ያለ ሲሆን ይህ ሊወገድ ይገባል” ሲል መልዕክቱን አስተላልፎ ነበር። አክሎም “እርምጃ ካልተወሰደ በስተቀር የፌደራል መንግሥት ወጪ አገሪቱን ባዶ ካዝና ያደርጋታል” ብሏል።
በተጨማሪም መንግሥት የሚቀጥራቸውን ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እንዲቀንስ በተደጋጋሚ ምክር በመስጠት ይታወቃል።
የዓለማችን ቁጥር አንድ ባለጸጋ የሆነው ኤለን መስክ የትራምፕ የስልጣን ሽግግርን የሙሉ ጊዜ ሥራው እንዳደረገው ሪፖርቶች ወጥተዋል።
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ሰሜን ኮሪያ ከሩሲያ ጋር የጋራ ወታደራዊ ስምምነት ማጽደቋ ተገለጸ
ሕዳር 4/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ሰሜን ኮሪያና ሩሲያ ያጸደቁት ወታደራዊ ስምምነት አንዱ ሀገር ቢጠቃ በጋራ ለመከላከል የሚያስችል እንደሆነ የሰሜን ኮሪያ የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል፡፡
የሁለቱ ሃገራት ስምምነት በምእራባውያኑ ቢተቹም፤ ሰሜን ኮሪያ ከሳምንታት በፊት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን ወደ ሩሲያ መላኳ የሚታወስ ነው፡፡
ይህንንም አሜሪካ፣ ደቡብ ኮሪያ እና ዩክሬን፤ ሩሲያ በዩክሬን ላይ የምታደርገውን ጦርነት ለመደገፍ ሰሜን ኮሪያ በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮቿን መላኳን በመግለጽ ድርጊቱን ተቃውመውታል።
ይህ የአሁኑ ስምምነት ከቀዝቃዛው ጦርነት ማብቂያ በኋላ የሁለቱም ሀገራት ትልቁ የመከላከያ ስምምነት ተደርጎ ተወስዷል።
ሰሜን ኮሪያና ሩሲያ ያጸደቁት አጠቃላይ የስትራቴጂክ አጋርነት ውል ተግባራዊ የሚሆነው፤ ሁለቱም ወገኖች ያጸደቋቸውን ሰነዶች ሲለዋወጡ መሆኑ ተገልጿል።
ቭላድሚር ፑቲን፤ ስምምነቱ ሀገራቱ በሚያጋጥማቸው የሉአላዊነት ጥቃት ሁሉ በየትኛውም መንገድ ደራሽ ለመሆን የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ስምምነቱ የሁለቱን ሀገራት ትብብር ወደተሻለ ደረጃ ከፍ እንደሚያደርገውም ፕሬዝዳንቱ መግለጻቸውን አሶሺየትድ ፕሬስ የዜና ወኪል (ኤፒ) ዘግቧል፡፡
በተጨማሪም ሥምምነቱ ሁለቱ ሀገራት “ፍትሃዊ እና ዘርፈብዙ አዲስ የአለም ስርአት” ለመመስረት በሚደረገው ጥረት በንቃት እንዲተባበሩ እና በተለያዩ ዘርፎች ሰላማዊ የአቶሚክ ኢነርጂ፣ በህዋ፣ በምግብ አቅርቦት፣ በንግድ እና ኢኮኖሚ ያላቸውን ትብብር እንዲያጠናክሩ ጥሪ እንደሚያቀርብ ተመላክቷል።
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ኮሚሽኑ የተቋማት አመራሮች ብልሹ አሰራርን ለመቆጣጠር ቁርጠኛ አለመሆን ፈተና እንደሆነበት ገለጸ
ሕዳር 4/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የፌዴራል ሥነ ምግባር እና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን፤ የተቋማት አመራሮች ብልሹ አሰራርን ለመቆጣጠር ቁርጠኛ አለመሆን ፈተና እየሆነበት እንደሚገኝ ለአሐዱ ገልጿል።
በሁሉም የመንግሥት ተቋማት በሚባል ደረጃ ብልሹ አሰራሮች መኖራቸው ይገለጻል፡፡
አሐዱም "እነዚህን ብልሹ አሰራሮች በመከላከልና በመቆጣጠር ሂደት ያሉ መሰናክሎች ምንድን ናቸው?" ሲል የፌዴራል ሥነ ምግባር እና ፀረ-ሙስና ኮሚሽንን ጠይቋል፡፡
የኮሚሽኑ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ተስፋዬ ሻሜቡን በምላሻቸው ችግሩ በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተንሰራፋ መምጣቱን ገልጸው፤ "በየተቋማቱ የሚገኙ ኃላፊዎች ቁርጠኛ አለመሆን የቁጥጥር ሥራውን ፈታኝ አድርጎታል" ብለዋል፡፡
በተጨማሪም ብልሹ አሰራርን መከላከል የኮሚሽኑ ሥራ ብቻ አድርጎ ማሰብ፣ ቸልተኝነትና ተባባሪ አለመሆን ተግዳሮት እንደሆነባቸው ተናግረዋል።
አክለውም የተቋማት ኃላፊዎች ብልሹ አሰራርን በመከላከል ረግድ ከሥር ያሉ ባለሙያዎችን አለመቆጣጠር የሚስተዋል ችግር መሆኑን ኃላፊው ጠቁመዋል።
ኃላፊው አያይዘውም ይህ ብልሹ አሰራር ዜጎችን ለከፋ እንግልት ከመዳረጉ በተጨማሪ የሀገር ኢኮኖሚ ክፉኛ የሚጎዳ በመሆኑ፤ የበላይ አመራሮች ቁርጠኝነትን እንዲያሳዩ ጥሪ አቅርበዋል።
በወልደሀዋሪያት ዘነበ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
‹‹ኢንሱሊን›› በግል የመድኃኒት መሸጫ መደብሮች የሚከፋፈልበት ሁኔታ እየተመቻቸ መሆኑ ተገለጸ
👉 ለ8 ወራት የሚያገለግል የኢንሱሊን ክምችት መኖሩም ተነግሯል
ሕዳር 5/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ከዚህ ቀደም በመንግሥት የሕክምና ተቋማት ብቻ ይሰጥ የነበረውና የስኳር ህሙማን የሚወስዱት ‹‹ኢንሱሊን››፤ በግል የመድኃኒት መሸጫ መደብሮች የሚከፋፈልበትን ሁኔታ በማመቻቸት ላይ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ የስኳር ህሙማን ማኅበር ገለጸ።
ማህበሩ ለስኳር ህመምተኞች የሚያገለግል በቂ የኢንሱሊን ክምችት መኖሩን አስታውቋል፡፡
ይህ የተነገረው በዛሬው ዕለት በየዓመቱ ታስቦ የሚውለው የዓለም የስኳር ሕመም ቀንን አስመልክቶ በተዘጋጀው መድረክ ላይ ነው፡፡
የኢትዮጵያ የስኳር ህሙማን ማኅበር ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጌታሁን ታረቀኝ የስኳር ህሙማን የሚጠቀሙበት ኢንሱሊን እጥረት እንዳለ በተደጋጋሚ መነገሩን አንስተው፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ8 ወራት የሚበቃ ክምችት መሆሩን ተናግረዋል፡፡
ፕሬዝዳንቱ አክለውም፤ "ከዚህ ቀደም በመንግሥት የሕክምና ተቋማት ብቻ ይሰጥ የነበረው ኢንሱሊን በግል የመድኃኒት መሸጫ መደብሮች የሚከፋፈልበትን ሁኔታ በማመቻቸት ላይ ይገኛል" ብለዋል፡፡
ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች አማካሪ ዶ/ር ውባዬ ዳኘው በበኩላቸው፤ በኢትዮጵያ እስከ 150 ሺሕ የሚጠጉ ሕጻናትና ወጣቶች ከስኳር ህመም ጋር ይኖራሉ ተብሎ እንደሚገመት ተናግረዋል።
ከእነዚህም መካከል 80 ከመቶ የሚሆኑት ግን ህክምና አገልግሎት ለማግኘት ወደ ጤና ተቋም ባለመምጣታቸው ሕክምናውን እያገኙ እንዳልሆነ አስረድተዋልል፡፡
በኢትዮጵያ ካሉ የስኳር ህመምተኞች 10 ከመቶ የሚሆኑት ዓይነት አንድ የሚባለውና አሁን ባለው የሕክምና አቅም የማይታከም ሕመም፤ እንዲሁም 90 ከመቶ የሚሆነው ደግሞ ከዓይነት 2 የስኳር ህመም ጋር ይኖራሉ ብለዋል፡፡
ተደጋጋሚ እና ብዛት ያለው ሽንት፣ የማይረካ ወይም የማያቋርጥ ውሃ ጥም፣ የድካም ስሜት፣ የሰውነት ክብደት መቀነስ እና ይህንን መሰል ምልክቶችን በሰውነቱ ላይ የተመለከተ ግለሰብ ወደ ጤና ተቋማት በማምራት እንዲሁም፤ ያለበትን ደረጃ ማወቅ እንደሚገባውም መክረዋል፡፡
ሕዳር 5 ቀን በየዓመቱ የሚታሰበው የዓለም የስኳር ህመም ቀን በዛሬው ዕለት ለ34ተኛ ጊዜ በተለያዩ ዝግጅቶች እየታሰበ ይገኛል።
በዳግም ተገኝ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
እስራኤል በጋዛ ረሃብን እንደጦር መሳሪያ እየተጠቀመች ነው ስትል ደቡብ አፍሪካ ከሰሰች
ሕዳር 5/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ደቡብ አፍሪካ በዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት እስራኤል ላይ ባቀረበችው የዘር ማጥፋት ወንጀል ክስ እስራኤል በጋዛ ረሃብን እንደ ጦር መሳሪያ እየተጠቀመች ነው ብላለች።
ደቡብ አፍሪካ ከዚህ በተጨማሪም እስራኤል በጋዛ የጅምላ ግድያና በግዳጅ ማፈናቀልን እያደረሰች መሆኑን ገልጻለች።
ሀገሪቱ ክሷን በማስረጃ ስታብራራ፤ በጋዛ የዘር ማጥፋት እንቅስቃሴዎችን እና የዘር ማጥፋት ድርጊቶችን የሚቀሰቅሱ እና የሚፈጽሙትን አካላት መቆጣጠርና መቅጣት አለመፈለጓን አንስታለች።
በዚህም የዘር ማጥፋት ወንጀልን የመከላከል እና የመቅጣት ሁሉም ሀገራት ሀላፊነት እንዳለባቸው የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሮናልድ ላሞላ በዋና ከተማዋ ፕሪቶሪያ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።
"ደቡብ አፍሪካ በእስራኤል ላይ ያቀረበችውን የዘር ማጥፋት ክስ አስመልክቶ የተዛባ መረጃ መስፋፋቱን ታወግዛለች" ያሉት ላሞላ፤ እንዲህ ያለው ጥረት በጋዛ እየታየ ካለው የዘር ማጥፋት ወንጀል የህዝቡን ትኩረት ለመሳብ ያለመ መሆኑን መግለጻቸውን ፕረስ ቲቪ ዘግቧል።
በፈረንጆቹ ጥር ወር በኔዘርላንድስ ሔግ መቀመጫውን ባደረገው የዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት (ICJ) በእስራአል ላይ የተጀመረውን ክስ፤ ቱርክ፣ ኒካራጓ፣ ፍልስጤም፣ ስፔን፣ ሜክሲኮ፣ ሊቢያ እና ኮሎምቢያን ጨምሮ በርካታ ሀገራት ተቀላቅለውታል፡፡
ይህ የዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት (ICJ)፣ የተባበሩት መንግሥታት የሕግ አስፈጻሚ አካል ሲሆን፤ በሀገራት መካከል አለመግባባት ተፈጥሮ ሲቀርብለት ምርመራ አድርጎ ብይን ይሰጣል፤ በዓለም አቀፍ ሕግ ነክ ጉዳዮች ላይም ምክር የሚሰጥ ተቋም ነው።
ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ በፈረንጆቹ ግንቦት ወር እስራኤል በደቡባዊ ጋዛ ራፋህ ከተማ የምታደርገውን ጥቃት እንድታቆም ማዘዙ ይታወሳል።
የሟቾች ቁጥር 44 ሺሕ በላይ በሆነበት በዚህ አካባቢ የሟቾችን ቁጥር ለመቆጣጠር እንዲሁም ሰብአዊ ጉዳትን ለመቀነስ 15 ዳኞችን የያዘው ቡድን የመጀመሪያ ደረጃ ትዕዛዞችን ሲያወጣ ለሦስተኛ ጊዜ ነው።
በገነነ ብርሃኑ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
በመዲናዋ በኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት ላይ ስርቆት የፈፀሙ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ዋሉ
ሕዳር 5/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በአዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ካዛንቺስ አካባቢ፤ 550 ሺሕ ብር የሚገመት የኤሌክትሪክ መስመር ላይ ስርቆት ያደረሱ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል።
በቁጥጥር ሥር የዋሉት ግለሰቦች በኮሪደር ልማት ሥራ ምክንያት ተቆፍረው የተቀመጡ 200 ሜትር የሚደርስ የኤሌክትሪክ መስመሮችን ቆራርጠው ለግል ጥቅማቸው ያዋሉ ሲሆን፤ ተቋሙ ከአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ጋር ባደረገው ከፍተኛ ርብርብ መያዛቸው ተጠቅሷል፡፡
በኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማቶች ላይ ስርቆት መፈፀም በኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት አውታሮች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 464/97 መሰረት ከ5 ዓመት እስከ 20 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት እንደሚያስቀጣ ተገልጿል፡፡
በኤሌክትሪክ መሠረተ-ልማቶች ላይ የሚፈፀምን የስርቆት ወንጀል መከላከል የሁሉም ሃላፊነት በመሆኑ መሰል እኩይ ተግባራትን የሚፈፅሙ አከላትን ሲመለከቱ በአካባቢው ለሚገኙ የፀጥታ አካላት ማሳወቅና ጥበቃ ማድረግ እንደሚገባ ተቋሙ አሳስቧል።
በተያዘው በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ብቻ ከ2 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው ኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ላይ የስርቆት ወንጀል መፈፀሙ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ማስታወቁን አሐዱ መዘገቡ ይታወሳል፡፡
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
ቢሮው ባለፉት አራት ወራት ከ57 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን ገለጸ
ሕዳር 5/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ፤ ከሀምሌ 2017 እስከ ጥቅምት 2017 ዓ.ም ድረስ 70 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ለማሰባሰብ አቅዶ፤ 57 ቢሊዮን 774 ሚሊዮን 280 ሺሕ ብር ለማሰባሰብ መቻሉን አስታውቋል።
በ2016 በጀት ዓመት ተመሳሳይ አራት ወራት የተሰባሰበ ገቢ 44 ቢሊዮን 487 ሚሊዮን 250 ሺሕ ብር እንደነበርም አስታውሷል።
በዚህም የዘንድሮ ገቢ ከዓምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፃር የ13 ቢሊዮን 287 ሚሊዮን 3 ሺሕ ብር ልዩነት እንዳለው ገልጿል።
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
#ADVERTISMENT
#ጊፍትሪልስቴት
ታላቅ የምስራች!
**
ጊፍት ሪል ስቴት ከ10% ቅድመ ክፍያ ጀምሮ በ22 ሳይቶቹ ቅንጡ አፓርትመንቶችን እና የንግድ ሱቆችን ለሽያጭ አቅርቧል፡፡
ይህ ሳይት ለአፓርትመንትና ንግድ ሱቆች የሚውሉ G+25 ሶስት መንታ ህንጻዎች ያሉት ሲሆን የዚህ 6ኛ መንደር መለያዎች፡-
•ከባለአንድ እስከ ባለአራት መኝታ ክፍሎች ያሉት፣
•ለመኖሪያም ሆነ ለንግድ ተመራጭ አካባቢ የሆነ፣
•በአንድ ወለል ሶስት ቤቶች ብቻ ያሉት፣
•በእያንዳንዱ ወለል ስድስት አሳንስር ያለው፣
•አራት ቤዝመንት ያሉት በቂ የመኪና ማቆሚያ የተዘጋጀለት፣
•24 ሰዓት የኤሌክትሪክ፣ ኢንተርኔትና ውሃ አቅርቦት አሉት፣
ጊፍት ሪል ስቴት
ማህበረሰብን እንገነባለን!
ለበለጠ መረጃ፡-
Website: https://www.giftbusinessgroup.com
Twitter: https://twitter.com/GIFTBusinessG
YouTube: www.youtube.com/channel/UCcqr7cpVv9ski-F7haxXx4w
Facebook: www.facebook.com/profile.php?id=100090918391017...
Telegram: /channel/giftbusinessgroup
Short Code: 8055
ሄዝቦላህ በቴላቪቭ በሚገኘው የእስራኤል ወታደራዊ ካምፕ ላይ የአየር ጥቃት መፈጸሙን ገለጸ
ሕዳር 4/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኢራን የሚደገፈው የሊባኖሱ ታጣቂ ቡድን ሄዝቦላ በዛሬው ዕለት በቴላቪቭ "ሃኪሪያ ወታደራዊ ካምፕ" ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ በሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቃት መፈጸሙን ተናግሯል፡፡
ነገር ግን በከተማው በሚገኘው ወታደራዊ ካምፕ አካባቢ ምንም አይነት የማስጠንቀቂያ ድምጽ አለመሰማቱ እንዲሁም፤ በጥቃቱ ምን አይነት ጉዳት እንደደረሰ የተገለጸ ነገር አለመኖሩን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
በሄዝቦላህ መግለጫ ላይ የእስራኤሉ ጦር የሰጠው ምላሽ አለመኖሩም የተገለጸ ሲሆን፤ ከቴል አቪቭ ወታደራዊ ካምፕም ይፋ የተደረገ ነገር የለም።
በቴል አቪቭ የሚገኘው የወታደራዊ እና የመንግሥት ማዕከል የሆነው የጦር ሰፈር፤ የጦር ካቢኔን ጨምሮ የበርካታ ወታደራዊ አካላትን ዋና መሥሪያ ቤት ያስተናግዳል።
ወታደራዊ ካምፑ በከተማው ውስጥ ከትልቅ የገበያ አዳራሽ እና ከባቡር ጣቢያ አጠገብ በተጨናነቀ ቦታ ላይ እንደሚገኝ በዘገባው ተመላክቷል።
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋር የሚኖራት የሁለትዮሽ ግንኙነት ከወቅታዊ ነባራዊ ሁኔታዎች አንጻር የተቃኘ ሊሆን እንደሚገባው ተገለጸ
ሕዳር 4/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) አዲሱ የአሜሪካ ምርጫን ተከትሎ ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋር የሚኖራት የዲፕሎማሲ ግንኙነት ከሀገሪቱ ፖርቲና ከተመራጩ ባህሪ አንጻር ሊቃኝ እንደሚገባ የአለም አቀፍ ግንኙነት ምሁራን ገልጸዋል።
"አሜሪካ ከብሔራዊ ጥቅሟ አንጻር በዉጭ ግንኙነት ፖሊሲዋ ምን ላይ ትኩረቷን ታደርጋለች? የተመራጩ ባህሪስ እንዴት ይቃኛል? የሚለዉን ኢትዮጵያ ታሳቢ ማድረግ አለባት" ያሉት የፖለቲካል ሳይንስ መምህር እና የአለምአቀፉ ግንኙነት መምህሩ አቶ አዲስ አለማየሁ ናቸዉ።
ሀገራት በዋናነት የሚቆሙለት አላማ ላይ ትኩረታቸዉን እንደሚያደርጉ ያነሱት አቶ አዲስ፤ ኢትዮጵያ ከአሜሪካ እንዲሁም ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ጋር ሊኖራቸዉ የሚችለዉን የዉጭ ፖሊሲ ባህሪ በጥንቃቄ ማጤን እንደሚገባ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
በዚህም "የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ በዋናነት ከምጣኔ ሃብት፣ ከንግድ ጉዳዮች እንዲሁም ከቀጠናዊ ሰላም እና ጸጥታ አንጻር ሊቃኝ ይገባል" ብለዋል፡፡
አምባሳደር ጥሩነህ ዜናው በበኩላቸው "የአሜሪካ መሪዎች በየግዜው ቢቀያየሩም ኢትዮጵያ በምትከተለው የዉጭ ፖሊሲ ላይ መሰረታዊ ለዉጥ አታደርግም" ያሉ ሲሆን፤ "ከአሜሪካ ጋር ያላትን ግንኙነት እንደየአመጣጡ በማስተካከል ማስኬድ ይቻላል" ሲሉ ተናግረዋል።
አክለውም፤ "የሁለትዮሽ ግንኙነቱን ለማጠናከር አሜሪካ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የምትወስዳቸዉን እርምጃዎች እና ትግበራዎች እንደየአመጣጣቸው መመለስ ያስፈልጋል" ብለዋል።
ምሁራኑ አክለውም፤ ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም የነበሩ የዲፕሎማሲ ግንኙነቶችን መነሻ በማድረግ በቀጣይ የሚኖራት ምጣኔ ሃብታዊ እና ፖለቲካዊ ግንኙነት በጥንቃቄ መጤን እንዳለበት አመላክተዋል።
በፅዮን ይልማ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ www.tiktok.com/@ahadutv.official
"ባላወቅነው ምክንያት ባንክ ውስጥ ያለ ገንዘባችንን ማንቀሳቀስ አልቻልንም" የንግድ ባንክ ተጠቃሚዎች
ሕዳር 4/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በአማራ ክልል የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደብተር አውጥተው ሲጠቀሙ የቆዩና ከክልሉ ወደ አዲስ አበባ ተንቀሳቅሰው ባለበት ወቅት፤ አገልግሎት ለማግኝት ወደ ባንኩ ሲሄዱ "ሂሳባችሁ ስለታገደ ማንቀሳቀስ አትችሉም" የተባሉ ተጠቃሚዎች ቅሬታቸውን ለአሐዱ አቅርበዋል።
"ለምን እንደታገደ ምክንያቱን የሚያስረዳን አካል አላገኘንም" ያሉት ቅሬታ አቅራቢዎቹ፤ "ቀነ ቀጠሮ ብቻ እየተሰጠን ነው" ሲሉም ተናግረዋል፡፡
በዚህም "ገንዘባችንን ማንቀሳቀስ ባለመቻላችን ችግር ውስጥ ነን" ብለዋል።
አሐዱም በጉዳዩ ላይ ምላሽ እንዲሰጡበት የባንኮች ማህበር ዋና ፀሃፊ አቶ ደምሰው ካሳን ጠይቋል፡፡
ዋና ፀሃፊው "ባንኮች በየትኛውም ቅርንጫፍ የወጣን ደብተር ባለቤት ገንዘብ መከልከልም ይሁን የማገድ ስልጣን የላቸውም" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
"ግለሰቡ በወንጀል ተጠርጠሪ ሆኖ ከሆነ በሚወጣ ትእዛዝ መሰረት ገንዘብ እንዳያንቀሳቅስ ካልታገደ በስተቀር አሰራሩም አይፈቅድም" ያሉት ዋና ጸሃፊው፤ ይህ ችግር ያጋጠማቸው ደንበኞች እስከ ላይኛው የባንኮች እርከን ድረስ ሄደው የመጠየቅ መብት እንዳላቸውም ተናግረዋል፡፡
አሐዱ ቅሬታ አቅራቢዎቹ የጠቀሱትን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በጉዳዩ ላይ ለማነጋገር ያደረገው ሙከራ አልተሳም፡፡ ምላሹን እንዳገኘ ይዞ የሚመለስ ይሆናል።
በእመቤት ሲሳይ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ www.tiktok.com/@ahadutv.official
በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የንጹህ መጠጥ ውኃ ችግርን መፍታት አልተቻለም ተባለ
ሕዳር 4/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል 250 የሚሆኑ የውሃ ተቋማት ጥገና ተደርጎ አገልግሎት እንዲሰጡ ቢደረግም የንጹህ መጠጥ ውኃ ችግርን መፍታት አለመቻሉን የክልሉ ውሃ እና ኢነርጂ ቢሮ አስታውቋል፡፡
በክልሉ ለዜጎች ንጹህ የመጠጥ ውኃ አገልግሎትን ለማቅረበት ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች ጋር እየተሰራ ቢሆንም፤ የንጹህ መጠጥ ውኃ አቅርቦት እጥረት ሊፈታ ያልቻለ ችግር መሆኑን የቢሮ ኃላፊ ሀጂራ ኢብራሂም ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
በዚህም በክልሉ ሙሉ በሙሉ የንጹህ መጠጥ ውሃ ችግር መፍታት ባይቻልም በተደረገ ጥረት ግን በ2016 ዓም በሦስት ወራት ውስጥ በጸጥታ ችግር ምክንያት አገልግሎት መስጠት አቁመው ለነበሩ ለ250 የውሃ ተቋማት አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ሥራዎች ተከናውነዋል ሲሉ ገልጸዋል፡፡
በክልሉ ያለውን የንጹህ መጠጥ ውሃ እጥረ ለመፍታት የተለያዩ ሥራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ የገለጹት ኃላፊው፤ ነገር ግን አሁንም የንጹህ የመጠጥ ውሃ እጥረት ሙሉ ለሙሉ አለመፈታቱን ተናግረዋል፡፡
በመሆኑም ህብረተሰቡ መጠገን የሚችሉትን እንዲጠገኑ እየተደረገ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን፤ ሙሉ በሙሉ የንጹህ መጠጥ ውሃ እንዲያገኙ ለማድረግ ጥረት ይደረጋል ብለዋል፡፡
በእሌኒ ግዛቸው
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
የዶቼ ቬለ ራዲዮ ጣቢያ ሠራተኞች የደመወዝ ጭማሪ ጥያቄያቸው ባለመመለሱ የሥራ ማቆም አድማ ጠሩ
ሕዳር 4/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በዶቼ ቬለ አስተዳደር እና በሠራተኛ ማኅበራቱ መካከል ለቋሚም ሆነ የትርፍ ሰዓት ተቀጣሪዎች የደመወዝ ጭማሪ እንዲደረግ የተጀመረው ድርድር የተፈለገውን ውጤት ባለማስገኘቱ ምክንያት፤ የጀርመን የሠራተኛ እና የጋዜጠኞች ማኅበራት ዛሬ እና ነገ የሥራ ማቆም አድማ ጠርተዋል።
የሠራተኛ ማኅበራቱ ከዋጋ ግሽበት ጋር ተያይዞ ለሚታየው የኑሮ ውድነት መቋቋሚያ ይሆን ዘንድ ለሁሉም ሠራተኞች የ10 ነጥብ 5 በመቶ የደመወዝ ጭማሪ ነው የጠየቁት።
አስተዳደሩ በቀጣይ ሁለት ዓመት ከ2 ነጥብ 4 በመቶ ያላነሰ ጭማሪ እንደሚያደርግ መግለጹ ተነግሯል።
በቀጣሪው አካል እና በሠራተኞች ማኅበራቱ መካከል ስድስት ዙር የወቅቱን የዋጋ ንረት ያገናዘበ ቋሚ የደመወዝ ጭማሪ እንዲደረግ ውይይት መካሄዱን ያመለከቱት ማኅበራት፤ ከዶቼ ቬለ አስተዳደር በኩል የተጠበቀው ምላሽ ማዝገሙን ገልጸዋል።
በዚህም ምክንያት ምንም እንኳን "ለሕዝብ መረጃ የማቅረብ ሥራ መደናቀፍ የለበትም" ብለው ቢያምኑም፤ ያቀረቡት ጥያቄ ትኩረት እንዲሰጠው የሥራ ማቆም አድማ መደረግ እንደሚኖርበት መወሰናቸውን አስታውቀዋል።
ራዲዮ ጣቢያው የመረጃ አቅርቦት ሥራው እንዳይስተጓጎልና የአየር ሰዓቱ ባዶ እንዳይሆን አማራጭ ስልቶችን ለመጠቀም እንዲችል ጋዜጠኞችም ሆኑ የስቱዲዮ ቴክኒክ ባለሙያዎች በአድማው የሚሳተፉ ከሆነ እንዲያሳውቁት ጠይቋል።
ማኅበራቱ በበኩላቸው በአድማው ለሚሳተፉ አባሎቻቸው የአንድ ቀን ደመወዝ ድጎማ እንደሚያደርጉ በመግለጽ የተሳታፊዎች ቁጥር እንዲጨምር ማበረታታቸውን ዶቼ ቬለ ዘግቧል።
በአድማው የሚሳተፉት ሠራተኞች በጀርመን ቦን ከተማ በራይን ወንዝ ዳርቻ በሚገኘው የዶቼ ቬለ ራዲዮ ሕንጻ ደጃፍ እየተካሄደ እንደሚገኝም ተመላክቷል።
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
በዲጂታል ዘርፉ የተማረ የሰው ሃይል እጥረት መኖሩ አሉታዊ ተፅዕኖ እያሳደረ መሆኑ ተገለጸ
ሕዳር 4/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በቴክኖሎጂ ዘርፉ ከሚስተዋሉ ችግሮች ዉስጥ የተማረ የሰው ሃይል እጥረት መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ በተለይም የሰለጠነ የሰዉ ሀይል ወደ ተለያየ ተቋማት መፍለስ አንዱ ችግር መሆኑ ተገልጿል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በየዓመቱ የተማሩ የሰው ሃይል ከዩኒቨርሲቲ ሲወጡ ለዓመታት አሰልጥኖ ወደ ሥራ የማሰማራት ሥራዎች ቢሰራም ባለሙያዎች ወደ ተለያዩ የተቋማት መሄዳቸው አልቀረም ተብሏል፡፡
"በዘርፉ የሰለጠኑ ባለሙያዎች ወደ ተለያዩ ተቋማት ይሄዳሉ" ያሉት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኢንፎርሜሽን ሲስተም ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አማረ አሰፋ ናቸው፡፡
እንደሳቸው ገለጻ፤ "ይህንን ማቆም ስለማይቻል ቁጥሩን ከፍ አድርጎ ማስልጠን ላይ ትኩረት አድርገናል" ብለዋል፡፡
"ይህ እንደ ተግዳሮት ሊነሳ የሚችል ነው" ያሉት አቶ አማረ፤ "ነገር ግን ይህንን ተግዳሮት ለማስወገድ ተተኪ ባለሙያዎችን ከስር ከስር በማዘጋጀት ሥራዎች እየሰራን እንገኛለን" ሲሉ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
"ባለሙያዎቹ ከሰለጠኑ በኃላ ወደ ውጪ ቢወጡም በአንድ ጎኑ ለሀገር ጠቃሚ ነው" ያሉት ምክትል ፕሬዝዳንቱ፤ በሀገር ውስጥ ያሉትም ሀገርን የሚጠቅሙ ስለሆነ ጉዳት እንደማይኖረው አመላክተዋል፡፡
"ሆኖም ግን እንደ ተግዳሮት መታየቱ ተገቢ በመሆኑ ችግሩን መፍትሄ ለመስጠት ቀጣይነት ያለው የባለሙያዎች ብቃት ዕድገት ላይ ስራዎችን እንሰራለን እንገኛለን" ሲሉም ተናግረዋል፡፡
በአቤል ደጀኔ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ
ሕዳር 4/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ከከፈተች ወዲህ የተሳለጠ የካፒታል ገበያ እንቅስቃሴ እያደረገች መሆንዋን የተገለጸ ሲሆን፤ ይህንን ለማጠናከር የሚመለከታቸው አካላት በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ስካይላይት ሆቴል ምክክር ጀምረዋል።
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ከአፍሪካ ልማት ባንክ ጋር በትብብር የተዘጋጀ የምክክር መድረክ መሆኑን ሰምተናል።
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ጀነራል ዳይሬክተር ሐና ተክሉ፤ "አሁን ላይ በርካታ ኢንቨስተሮችና መካከለኛ ባለሐብቶች በመፍጠር ረገድ እያደረግነው ያለውን ጥረት እየተሳካልን ይገኛል" ሲሉ ተናግረዋል ።
ሐና አክለውም፤ "ኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ከከፈተች ወዲህ ምንም እንኳን አጭር ጊዜ ቢሆንም፤ ካለው አገራዊ እምቅ ሐብት አንፃር በተሳካ ሁኔታ እየተጓዘ ነው" ብለዋል።
መድረኩን በመክፈቻ ንግግር የከፈቱት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዋና ገዥ ማሞ ምሕረቱ ናቸው።
ማሞ ምሕረቱ የካፒታል ገበያ መከፈቱ አስፈላጊ የሆነበት ምክንያት ለረጅም ጊዜ ሲጠየቅ የነበረውን የውጭ ባንኮችን ወደ አገር ውስጥ ገበያ እንዲሳተፉ ለማድረግ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
አክለውም፤ አሁን ላይ የተፈጠረው የባንክ ዘርፍ አስተዳደር ለማሻሻል የካፒታል ገበያ መከፈት አስፈላጊነት እንደነበር አንስተዋል።
ሌላኛው የመንግሥትን እቅድ ከጉባኤው ጋር አያይዘው ንግግር ያደረጉት፤ የገንዘብ ሚኒስቴር የፊሲካል ፓሊሲ ዘርፍ ሚኒስትር ድኤታው እዮብ ተካልኝ ናቸው።
እዮብ ተካልኝ በገለጻቸው ላይ የመንግሥት አገር በቀል ኢኮኖሚ በተጠና መንገድ መከፈቱን ገልጸው፤ ከእነዚህ መካከል የካፒታል ገበያ መከፈት ዋነኛው መሆኑን ተናግረዋል።
ሚኒስትር ድኤታው አክለውም፤ የአጠቃላይ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው የፋይናንስ ስርአቱ የአስተሳሰብ ነፃነቱን ተጠብቆ ዘመን አፈራሽ በሆነ አመራር እንዲመራ ማድረግ እንደነበር ጠቅሰዋል።
በዛሬው ዕለት የጀመረው የካፒታል ገበያ ጉባኤ ለተከታታይ ሦስት ቀናት የሚመለከታቸው ምጣኔ ሐብት አንቀሳቃሾች ለምክክር በጠረጴዛ ዙሪያ ይቀመጣሉ ተብሏል።
በአማኑዔል ክንደያ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ተጀመረ
ሕዳር 4/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በራስ ገዟ ሶማሊላንድ በዛሬው ዕለት 4ኛው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ መካሄድ ጀምሯል፡፡
ለምርጫው ከ1 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ መራጮች መመዝገባቸው የተገለጸ ሲሆን፤ በስድስት ክልሎች በተዘጋጁ 2 ሺሕ 648 የምርጫ ጣቢያዎች መራጮች ድምፃቸውን በመስጠት ላይ ይገኛሉ።
በተጨማሪም 13 ሺሕ ምርጫ አስፈጻሚዎች ምርጫውን እያስፈጸሙ እንደሚገኙ የሀገሪቱ ብሔራዊ ምርጫ ኮሚሽን አስታውቋል። እንዲሁም ከ8 ሀገራት የተውጣጡ ታዛቢዎች ምርጫውን እየታዘቡ እንደሚገኙ ተገልጿል።
በሀገሪቱ በየአምስት ዓመቱ ፕሬዚዳንታቸውን ምርጫ የሚከናወን ሲሆን፤ በየአስር ዓመቱ ደግሞ ቀጣይ ለሁለት አምስት አመታት ለፕሬዚዳንትነት ምርጫ እጩ የሚያቀርቡ ሦስት ፓርቲዎችን ይመርጣሉ።
በዚህም መሰረት በአሁኑ ምርጫ የወቅቱ ገዥ ፓርቲ የሰላም፣ የአንድነትና የእድገት ፓርቲ (ኩልምዬ) በመወከል ፕሬዝዳንት ሙሴ ቤሂ፣ ተፎካካሪ ዋዳኒ ፓርቲን በመወከል አብዱሮህማን መሀመድ እና የሰላምና ዊል ፌር ፓርቲን በመወከል ደግሞ ፈይሰል አሊ ፕሬዝዳንታዊ እጩ ሆነው ቀርበዋል።
በተጨማሪም በፓርቲዎች ምርጫ 7 የፓለቲካ ማህበራት እየተሳተፉ ይገኛሉ።
የምርጫ ጣቢያዎች የተከፈቱት ከማለዳው 6፡30 ሲሆን፤ የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን የማንነት ማረጋገጫን ለማሻሻል እና ማጭበርበርን ለመግታት የባዮሜትሪክ የአይን ቅኝት ቴክኖሎጂን በተመረጡ ቦታዎች ተግባራዊ ማድረጉ ተነግሯል።
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ www.tiktok.com/@ahadutv.official
"የቀበሌ ቤት ውል አቋርጣለሁ" በማለት 50 ሺሕ ብር ጉቦ ሊቀበል የነበረ አመራር እጅ ከፍንጅ ተያዘ
ሕዳር 4/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) "የቀበሌ ቤት ውል አቋርጣለሁ" በማለት 50 ሺሕ ብር ጉቦ ሊቀበል የነበረ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 የቤቶች አስተዳደር ፅ/ቤት ኃላፊ እጅ ከፍንጅ መያዙን የክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያና አስተዳደሩ ገልጸዋል።
የጉለሌ ፖሊስ መምሪያና የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ከሕዝብ የመጣላቸውን ጥቆማ መሰረት በማድረግ ባደረጉት ክትትል፤ የጉለሌ ወረዳ 5 ቤቶች አስተዳደር ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሳምሶን ይልማ የተባለው አመራር በቁጥጥር ሥር መዋሉ ነው የተነገረው።
አመራሩ ከግል ተበዳይ የቀበሌ ቤት ከእጅ መንሻ ነፃ በሆነ መንገድና በቤቶች መመሪያ መሰረት ማስተናገድ እየተገባው፤ መንግሥት የጣለበትና ኃላፊነትና የሰጠውን አደራ ወደ ጎን በመተው 50 ሺሕ ብር በመጠየቅና ከግል ተበዳዮች ቤታቸው ድርስ ሄዶ ግቢ በማንኳኳት በማስጨነቅና የጠየቀው ገንዘብ ካልተሰጠው ውል እንደሚሰርዝ ማስፈራራቱ ተገልጿል፡፡
በዚህም ሕዳር 3 ቀን 2017 ከምሽቱ 1ሰዓት አካባቢ ገንዘቡን በጥሬው ሲቀበል መረጃው ቀድሞ የደረሰው ፖሊስና የአስተዳደሩ አካላት እጅ ከፍንጅ በመያዝ ወደ ጉለሌ ፖሊስ መምሪያ በመውሰድ ጉዳዮን እያጣሩ እንደሚገኝ ተነግሯል።
ማንኛውም አገልግሎት ፈላጊ ኅብረተሰብ ያለምንም የእጅ መንሻ እና ጉቦ በተቀመጠው ሕጋዊ አሰራር መሰረት መስተናገድ ሕገ መንግሥታዊ መብቱ መሆኑን የገለጸው አስተዳደሩ፤ መሰል ድርጊት ሲያጋጥም ለሚመለከተው የፀጥታ አካልና ለአስተዳደሩ በመጠቆም ሌቦችን በማጋለጥ ኃላፊነቱን እንዲወጣ አሳስቧል።
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
#ADVERTISMENT
#ጊፍትሪልስቴት
ታላቅ የምስራች!
**
ጊፍት ሪል ስቴት ከ10% ቅድመ ክፍያ ጀምሮ በ22 ሳይቶቹ ቅንጡ አፓርትመንቶችን እና የንግድ ሱቆችን ለሽያጭ አቅርቧል፡፡
ይህ ሳይት ለአፓርትመንትና ንግድ ሱቆች የሚውሉ G+25 ሶስት መንታ ህንጻዎች ያሉት ሲሆን የዚህ 6ኛ መንደር መለያዎች፡-
•ከባለአንድ እስከ ባለአራት መኝታ ክፍሎች ያሉት፣
•ለመኖሪያም ሆነ ለንግድ ተመራጭ አካባቢ የሆነ፣
•በአንድ ወለል ሶስት ቤቶች ብቻ ያሉት፣
•በእያንዳንዱ ወለል ስድስት አሳንስር ያለው፣
•አራት ቤዝመንት ያሉት በቂ የመኪና ማቆሚያ የተዘጋጀለት፣
•24 ሰዓት የኤሌክትሪክ፣ ኢንተርኔትና ውሃ አቅርቦት አሉት፣
ጊፍት ሪል ስቴት
ማህበረሰብን እንገነባለን!
ለበለጠ መረጃ፡-
Website: https://www.giftbusinessgroup.com
Twitter: https://twitter.com/GIFTBusinessG
YouTube: www.youtube.com/channel/UCcqr7cpVv9ski-F7haxXx4w
Facebook: www.facebook.com/profile.php?id=100090918391017...
Telegram: /channel/giftbusinessgroup
Short Code: 8055