ahaduradio | Unsorted

Telegram-канал ahaduradio - AHADU RADIO FM 94.3

19349

አሐዱ ራድዮ 94.3 Your source for top local and international news and analysis. "Voice of Ethiopian" የአሐዱ የቴሌግራም ቻናል ቤተሰብ በመሆን ወቅታዊና እውነተኛ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ

Subscribe to a channel

AHADU RADIO FM 94.3

የኢትዮጵያ አየር መንገድ 'ምርጥ የአፍሪካ ካርጎ አየር መንገድ' ሽልማትን ተሸለመ

ሕዳር 7/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ለሁለተኛ ተከታታይ ግዜ በ “Arabian Cargo Awards” ምርጥ የአፍሪካ ካርጎ አየር መንገድ ሽልማትን ተቀዳጅቷል።

የሽልማት አሰጣጥ መርሐግብሩ በዱባይ ከተማ የተካሄደ ሲሆን፤ በገልፍ ሀገራት ለሚሰጡ ምርጥ የአየር እቃ ጭነት አገልግሎቶች ዕውቅና የሚሰጥበት መድረክ መሆኑን አየር መንገዱ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ትናንት ሕዳር 6/2017 ዓ.ም የ2024 የቢዝነስ ተጓዦች ሽልማት ውድድርን በማሸነፍ፤ ለአምስተኛ ተከታታይ ዓመት ‘ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ’ በመባል መሸለሙን አሐዱ መዘገቡ ይታወሳል፡፡

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በኦሮሚያ ክልል በሕገ-ወጥ መንገድ ሊሸጥ የነበረ 13 ሚሊዮን ብር የሚገመት ነዳጅ መያዙ ተገለጸ

ሕዳር 7/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኦሮሚያ ክልል በ4 ወር ጊዜ ውስጥ በሕገ-ወጥ መንገድ ሊሸጥ የነበረ 13 ሚሊዮን ብር የሚገመት ነዳጅ መያዙን የክልሉ ንግድ ቢሮ አስታውቋል፡፡

በክልሉ ሕገ-ወጥ የነዳጅ ግብይትን በተመለከተ ቁጥጥርና ክትትል በማድረግ ሕገ ወጥ ነዳጁ ሲዘዋወር በቁጥጥር ሥር መዋሉን፤ የክልሉ ንግድ ቢሮ የእንስፔክሽን ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ጉዲሳ ለአሐዱ ገልጸዋል፡፡

ከዚህም ውስጥ 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር የሚገመት ነዳጅ ለመንግሥት ገቢ መደረጉን ገልጸው፤ ቀሪው ደግሞ በሂደት ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በክልሉ የሚስተዋለውን የሕገ-ወጥ የነዳጅ ንግድ ለማስቆም፤ በተለያዩ ዞኖች እና ከተሞች ላይ ቁጥጥርና ክትትል እየተደረገ እንደሚገኝም ገልጸዋል፡፡

የነዳጅ ግብይትን በተመለከተ በሕጋዊ መንገድ አገልግሎቱ እንዲሰጥ የማድረግ ሥራ እየተሰራ መሆኑንም ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

ነዳጅ ከቦታ ቦታ በማዘዋወር እንዲሁም በሕገ-ወጥ መንገድ በመሸጥ ላይ የተገኙ ግለሰቦች የያዙት ነዳጅ እንደሚወረስ የጠቆሙም ሲሆን፤ በተጨማሪም አስተዳደራዊ እርምጃና የጹሁፍ ማስጠንቀቂያ በመስጠት እርምት የማስወሰድ ሥራ እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ቢሮው በሕገ-ወጥ የነዳጅ ንግድ ላይ የሚንቀሳቀሱ ሰዎችን ለመቆጣጠር ከሚመለከተው አካል ጋር እየሰራ መሆኑንና ለማህበረሰቡ ግንዛቤ በመስጠት ጥቆማ እንዲያደርጉ እየተሰራ ስለመሆኑም አቶ ጌታቸው ጨምረው አመላክተዋል፡፡

በአለምነው ሹሙ

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

መልካም ቀን!
አሐዱ ሬድዮ 94.3  የኢትዮጵያውያን ድምፅ!

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የካፒታል ገበያ ስርአት መተዳደሪያ ደንብና የሰነድ መዋእለ ንዋይ ሕግ ፀድቆ ሥራ እንዲጀምር ይሁንታ ማግኘቱን የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ተናገረ

ሕዳር 6/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ የሚተገበረውን ካፒታል ገበያ ስርአት የሕግ ማዕቀፍ ተዘጋጅቶለት ወደ ፍትህ ሚኒስቴር ተልኮ የነበረ ሲሆን፤ የሕግ ማዕቀፉ የመጨረሻ የተባለለትን ውይይት ተደርጎበት መፅደቁን የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ገልጿል።

የሕግ መመርያውና የመተዳደሪያ ሰነዱ የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት በተገኙበት መተማመኛ ሰነድ ተፈርሞ በዛሬው ዕለት ባለስልጣኑ መረከብ መቻሉን የካፒታል ገበያ ባለስልጣን መረጃውን ለአሐዱ ተናግሯል።

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሐና ተኸክሉ፤ የሕግ መመርያውና የመተዳደሪያ ሰነዱ የሰነድ መዋእለ ንዋይ የተመለከቱ አጠቃላይ ሕጎች የተካተቱበት መሆኑን ለአሐዱ ገልጸዋል።

የሕግ ሰነዱ ለሁለት ዓመታት ጥናት የተደረገበት ሲሆን፤ ከተለያዩ አገራት በርካታ ልምዶች የተወሰዱበት መሆኑንም አንስተዋል።

ባለስልጣኑ በአዋጅ በተሰጠው ስልጣን መሰረት የአማካሪነት ፍቃድ ወሰደው የሚሰሩ አካላትን ጨምሮ ሌሎች የሰነድ መዋእለ ንዋይ ተሳታፊዎችን ለመቆጣጠር የሚያስችል መሆኑን ሐና ተኸክሉ ተናግረዋል።

የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲሆን፤ ከተለያዩ አካላት በተሰጠው ምክረ ሐሳብ መሰረት ገበያ ሰርአቱ የሚመራበት ሕጎች እንደተዘጋጁለት ነው ዋና ዳይሬክተሯ የገለጹት።

ባለስልጣኑ ከዚህ ቀደም መምርያውን የሚከታተል የሕግ አርቃቂ ቡድን አቋቁሞ ሲሰራ የቆየ ሲሆን፤ በተደረሰው ስምምነት መሰረትም ሥራውን የሚከታተል ግብረ ኃይል እንደተቋቋመለት ተነግሯል።

የሕግ መመርያው ባሳለፍነው ሳምንት ይፀድቃል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረ ቢሆንም፤ በአዲስ አበባ ከሚካሄደው የካፒታል ገበያ ጉባኤ በኃላ እንዲፀድቅ መደረጉን ባለስልጣኑ ለአሐዱ አስታውቋል።

የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ከአፍሪካ ልማት ባንክ ጋር በመተባበር ለሦስት ቀናት ያካሄደው የምክክር መድረክ፤ በተለያዩ ጉዳዮች ዙርያ ተመክሮበት ዛሬ ማምሻውን ተጠናቋል።

በአማኑዔል ክንደያ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

ኢሰመኮ ከመንግሥታቱ ድርጅት የዘር ማጥፋትን መከላከል ልዩ አማካሪ ቢሮ ጋር በትብብር ለመስራት ተፈራረመ

ሕዳር 6/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዘር ማጥፋትን መከላከል ልዩ አማካሪ ቢሮ፤ በቀጣናው የዘር ማጥፋት ወንጀሎች ላይ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል።

"ከገለልተኛ ብሄራዊ የሰብአዊ መብት ተቋማት (ኤን.ኤች.አይ.ኤስ) ጋር ያለው ትብብር የዘር ማጥፋትን፣ የጦር ወንጀሎችን እና በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ለመከላከል በምናደርገው ጥረት ወሳኝ እርምጃ ነው" ሲሉ የድርጅቱ ዋና ጸሃፊ እና የዘር ማጥፋትን መከላከል ልዩ አማካሪ አሊስ ዋይሪሙ ተናግረዋል።

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ በበኩላቸው፤ "ስምምነቱ የሁለቱ ተቋማት የሰብአዊ መብቶችን በማስተዋወቅ እና በመጠበቅ ላይ ያሉ ተግባራትን የሚያጎላ መሆኑን ያሳያል" ብለዋል።

አክለውም፤ የተፈረመው የትብብር ስምምነት ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ለመከላከል በተዘጋጁ ቀዳሚ እርምጃዎች እና የትብብር ዘርፎች ላይ እንደሚያተኩር ተናግረዋል።

ተጠባባቂ ዋና ኮሚሽነሯ አጋርነቱ ኢሰመኮ ከክልላዊ እና አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት አካላት ጋር ለመስራት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያጠናክር እና ኢትዮጵያ አባል የሆነችበትን አሰራር የሚያጠናክር መሆኑንም አፅንኦት ሰጥተዋል።

ስምምነቱ ሁለቱ ተቋማት የዘር ማጥፋት እና ሌሎች ከባድ አለም አቀፍ ወንጀሎችን የቅድመ ማስጠንቀቂያ ምልክቶችን በመለየት ምላሽ የመስጠት አቅምን ያሳድጋል ተብሎ ይጠበቃል።

በዳግም ተገኝ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በኢትዮጵያ እየተስተዋለ ያለውን የሰነድ መዋእለ ንዋይ እንቅስቃሴ ተስፋ ሰጪ ነገሮች እየታዩበት መሆኑን ተነገረ

ሕዳር 6/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተስተዋለ ያለውን የሰነድ መዋእለ ንዋይ እንቅስቃሴ ተስፋ ሰጪ ነገሮች እየታዩበት መሆኑን የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን አስታውቋል።

ባለስልጣኑ በኢትዮጵያ የአክስዮን ገበያ መተግበር ከጀመረ ሦስት አስርት ዓመታት ቢያስቆጥርም በንግድ ሕጉ ሲመራ መቆየቱን የገለጸ ሲሆን፤ አመርቂ ውጤት ሳይታይበት መቆየቱን ተናግሯል።

አሁን ላይ ባለስልጣን መስርያቤት ተቋቁሞለት ሥራ መጀመሩ ከወዲሁ የተወዳዳሪነት መንፈስን እየፈጠረ እንደሚገኝም ገልጿል።

ይህ የተባለው በአዲስ አበባ ከተማ ለሦስት ቀናት ባለድርሻ አካላት ተሰባስበው በመከሩበት "የካፒታል ጉባኤ" ላይ ነው።

የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሀና ተኸክሉ ምክክሩ አስመልክተው ከአሐዱ እንደተናገሩት፤ "የግሉ ክፍለ- ኢኮኖሚ በሰነድ መዋእለ ንዋይ ግብይት ተሳታፊ ለመሆን ያሳየው በቁርጠኝነትና ሕብረተሰቡ በዘርፉ ተሳትፎ ለማድረግ ያለውን ፍላጎት ጠንክረን እንድንሰራ የሚያደርግ ነው" ብለዋል።

ዋና ዳይሬክተሯ የካፒታል ገበያ መንግሥት የፈጠረው ልዩ እንቅስቃሴ መሆኑንና ምጣኔ ሐብቱም እንዲመራበት ለማስቻል መሆኑን ገልጸው፤ አጠቃላይ የተገኘውን ውጤት በሚገመገምበት ጊዜ መልካም እርምጃ የተጀመረበት መሆኑን አንስተዋል።

"በአዲስ አበባ የተካሄደው የካፒታል ገበያ ጉባኤ የተሳፉ ከሌሎች አገራት የመጡ የሰነድ መዋእለ ንዋይ ተዋናዮችና አንቀሳቃሾች በኢትዮጵያ ያሉ ድርጅቶች ጋር አብሮ ለመስራት ፍላጎት ያሳዩበት ነው" ብለዋል።

የካፒታል ገበያ እሳቤ ኢትዮጵያ ካደረገቻቸው ለውጦች መካከል በግንባር ቀደምነት የሚገለጽ መሆኑን ጠቅሰው፤ እስካሁን የሰነድ መዋእለ ንዋይ ዘርፍ የተለያዩ የአገር ባንኮች ውስጥ ባንኮች እየተሳተፉበት እንደሚገኙም ተናግረዋል።

በተጨማሪም ዋና ዳይሬክተሯ በጉባኤው የተሳተፉት የውጭ ኩባንያዎችና የገንዘብ ተቋማት መዋእለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ከመንግሥት የቀረበላቸውን ጥያቄ በበጎነት እየወሰዱት እንደሚገኙ አስታውቀዋል።

ዳይሬክተሯ የመስርያ ቤቱ ኃላፊ ሆነው ከተሾሙ በኃላም ቢሆን የተለያዩ ሥራዎች ማከናወን መቻላቸውን ገልጸው፤ "የካፒታል ገበያ ከተከፈተ ምንም እንዃን ከሁለት ዓመታት በላይ እየዘለለ እድሜ ባይኖረውም ምጣኔ ሐብቱን የሚያስተካክ በርካታ ሥራዎች ማከናወናቸውን ለአሐዱ ተናግረዋል።

"ኢትዮጵያ ለምትገነባው ኢኮኖሚ የካፒታል ገበያ ጥገኛ ነው" ያሉ ሲሆን፤ የሚሰጠው ጥቅም ከፍተኛ መሆኑን እንደማሳያ በኢትዮ ቴሌኮም የተጀመረውን አክስዮን መሸጥ እንቅስቃሴ በአስረጂነት አንስተዋል።

በቀጣይም የመንግሥት የልማት ድርጅቶች በአክስዮን ለሕዝብ እንዲሸጡ ለሕዝብ መቅረባቸው ቀጣይ የመንግሥት እቅድ መሆኑን ጠቅሰው፤ ኢትዮ በቴሌኮም የታየው ውጤት አበረታች መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን በአዋጅ የተቋቋመ መስርያ ቤት ሲሆን፤ ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትር ፅሕፈት ቤት መሆኑን ይታወቃል።

አጠቃላይ የመስርያ ቤቱ እንቅስቃሴ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የሚገመገም ሲሆን፤ የገንዘብ ሚኒስቴርና ብሔራዊ ባንክ የመስርያ ቤቱ ቦርድ አባላት ናቸው።

በአማኑዔል ክንደያ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!

ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

"በዚህ ሕገወጥ ቡድን የሚተዳደር ህዝብም ሆነ ሃብት አይኖርም" የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር

ሕዳር 6/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ሕጋዊ ያልሆነ ጉባኤ ባካሄደውና ህጋዊ ባልሆነው ቡድን የሚተዳደር ሕዝብም ሆነ ሃብት አይኖርም ሲል ገልጿል።

ጊዚያዊ አስተዳደሩ በፕሬዝዳንት ፅ/ቤቱ በኩል ባወጣው መግለጫ "ሕጋዊ ያልሆነው ቡድን"  ሲል የገለጸው በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት፤ አሁንም ሕገ ወጥ ተግባራቱን እያጠናከረና በግልፅ መፈንቅለ መንግሥት እያደረገ እንደሚገኝ ገልጿል።

አክሎም፤ "ቡድኑ በትግራይ የተለያዩ አካባቢዎች ሕጋዊ ያልሆነ የሥራ ምድባ በማካሄድ የመንግሥት ግልበጣ በማካሄድ የቀን ተቀን ሥራን የማደናቀፍ ኢ-ሕጋዊ ተግባሩ ቀጥሎበታል" ብሏል።

"በእነዚህ ሕገወጥ ቡድኖች የሚተዳደር ሕዝብም ሆነ ሃብት አይኖርም።" ያለው የጊዜያዊ አስተዳደሩ መግለጫ፤ የትግራይ የጸጥታ አካላት፣ የፍትህ አካላትና ባንኮች ይህንን ሁኔታ ተረድተው ሕጋዊ ግዴታቸውን እንዲወጡ አሳስቧል።

በተጨማሪም በየደረጃው ያሉት የጊዜያዊ አስተዳደሩ መዋቅሮች፣ በትግራይ በሕጋዊ መንገድ የሚንቀሳቀሱ አካላትና ተቋማት፣ የፌደራል መንግሥት እንዲሁም የአለም አቀፍ ማህበረሰብ በየትኛውም መድረክ እና ኮንፈረንስ ላይ በቡድኑ የሚመደቡ አካላትን እንዳያሳትፋ ጥሪ አቅርቧል።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ሕዳር 1 ቀን 2017 በሰጠው መግለጫ፤ "ሕገ-ወጥ ጉባኤ አካሂደናል ያለው ሕገ ወጥ ቡድን በጊዜያዊ አስተዳደር ፕሮግራሞችን ከማስተጓጎል ባለፈ ግልፅ መፈንቅለ መንግሥት ማድረጉን አድርጎብኛል" ማለቱ ይታወሳል።

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ2024 የቢዝነስ ተጓዦች ሽልማት ውድድርን ለ5ተኛ ጊዜ በማሸነፍ ተሸለመ

ሕዳር 6/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ2024 የቢዝነስ ተጓዦች ሽልማት ውድድርን በማሸነፍ ‘ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ’ በመባል ተሸልሟል፡፡

ሽልማቱ በዘርፉ ለአምስተኛ ተከታታይ ዓመታት የተገኘ መሆኑን አየር መንገዱ አስታውቋል፡፡

ከሽልማቱ በኋላም አየር መንገዱ ደንበኞቹ ለሰጡት ድጋፍ ምሥጋና አቅርቧል፡፡

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

#ክፍት_የሥራ_መደብ_ማስታወቂያ
#VACANCY

ኢዲ ስቴለር ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ከዚህ በታች በተጠቀሱት ክፍት የሥራ መደቦች ላይ የውጭ አመልካቾችን አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል

1ኛ) የሽያጭ ክፍል ባለሙያ
ብዛት:- 10
ተፈላጊ ችሎታ:- በማርኬቲንግ ወይም ተያያዥ የትምህርት መስክ የመጀመሪያ ዲግሪ ወይም የኮሌጅ ዲፕሎማ ሆኖ 0/2 ዓመት የስራ ልምድ ያለው/ያላት

2ተኛ) የሽያጭ ክፍል ኃላፊ
ብዛት:- አንድ
ተፈላጊ ችሎታ:- በማርኬቲንግ ወይም ተያያዥ የትምህርት መስክ የመጀመሪያ ዲግሪያለው የስራ ልምድ 5 ዓመት እና ከዚያ በላይ ያለው /ያላት

ማሳሰቢያ፡-
1.አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 7(ሰባት) ተከታታይ ቀናት የትምህርት ማስረጃቸውን ዋና እና የማይመለስ ኮፒ በመያዝ ሲኤምሲ ሚካኤል አጠገብ በሚገኘው ኢኮኖሚክስ አሶሴሽን ህንፃ 1ኛ ፎቅ በአካል በመገኘት መመዝገብ ይችላሉ፡፡

2. መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶችና የግል ድርጅቶች የሚቀርቡ የስራ ልምድ ማስረጃዎች የሥራ ግብር የተከፈለበት መሆኑን የተረጋገጠ መሆን ይኖርበታል፡፡

3. የተጠየቁት የስራ ልምዶች ከምረቃ በኋላ የተሰሩ ሆኖ ከየስራ መደቦቹ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት (Relevant) ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

4. በደረጃ (Level) ለሚቀርቡ የትምህርት ማስረጃ በሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት (COC) አብሮ መያያዝ ይኖርበታል፡፡

5. ደሞዝ በስምምነት/በድርጅቱ ስኬል መሰረት

#VACANCY #የሥራ_ማስታወቂያ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በኢትዮጵያ ከ25 እስከ 30 በመቶ ሕጻናት በደም ካንሰር እንደሚጠቁ ተገለጸ

ሕዳር 6/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ አብዛኛውን ጊዜ ሕጻናትን ከሚያጠቁ የካንሰር አይነቶች መካከል ከ25 እስከ 30 በመቶውን የደም ካንሰር እንደሚይዝ ተነግሯል፡፡

ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሕክምና አገልግሎት ለማግኘት ከሚሄዱ ሕጻናት መካከል፤ አብዛኛውን ጊዜ በደም ካንሰር የሚጠቁ መሆናቸውም ተመላክቷል፡፡

በዚህም በቀዳሚነት የደም ካንሰር በምርመራ ወቅት እንደሚገኝ እና በሁለተኛ ደረጃ የአንጎል እጢ የሚገኝ መሆኑን፤ በሆስፒታሉ የሕጻናት ደም እና ካንሰር ሕክምና ክፍል ኃላፊ ዶክተር አብዱልቃድር መሀመድ ለአሐዱ ገልጸል፡፡

የደም ካንሰር በሽታ 80 በመቶ የመዳን እድል እንዳለው ክፍል ኃላፊው ጨምረው ተናግረዋል፡፡

በሆስፒታሉ ለተለያዩ የካንሰር ሕመሞች የሕክምና አገልግሎት የሚሰጥ ክፍል እድሳት ተደርጎለት፤ ትናንት ሕዳር 5 ቀን 2017 ዓ.ም ተመርቋል፡፡

ከዚህ ቀደም የውሃ እጥረት እና የመጸዳጃ ቤት ላይ ብልሽት እንደነበር የተገለጸ ሲሆን፤ በዚህም ምክንያ የሚፈጠረው ኢንፌክሽን ሕጻናቱን ለሞት ያደርስ እንደነበር ተነግሯል፡፡

የተደረገው እድሳት የሕጻናቱን ሕይወት መታደጉን "የተስፋ አዲስ ፓረንትስ ቻይልድ ሁድ" ካንሰር ሥራ አስኪያጅ ሳራ ኢብራሂም የገለጹ ሲሆን፤ "የተከናወነው እድሳት ሕክምና የሚያገኙትን ሕጻናት ቁጥር ይጨምረዋል ብለዋል፡፡

በኢትዮጽያ በዋናነት ብዙ ጊዜ በሕፃናት ላይ በመከሰት የሚታወቀው ‘አኪውት ሊምፎብላስቲክ ሉኪሚያ’ የሚባለው የደም ካንሰር አይነት ሲሆን፤ ሁለተኛው በሕፃናት ላይ የሚከሰት የደም ካንሰር ‘አኪውት ማይሎጂነስ ሉኪሚያ’ በመባል የሚታወቀው ነው።

እነዚህ ሁለት የካንሰር አይነቶች የሚነሱት ከነጭ የደም ህዋሳት ሲሆን፤ አኪውት ሊምፎብላስቲክ ሉኪሚያ የሚነሳው ሊንፎሳይት ከሚባለው ነጭ የደም ህዋስ እንዲሁም፤ አኪውት ማይሎጂነስ ሉኪሚያ ደግሞ ማይሎድ ከሚባለው ነጭ የደም ህዋስ የሚነሳ መሆኑን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ያወጣው መረጃ ያስረዳል።

ሁለቱም በሕጻናት ላይ የሚከሰቱት የደም ካንሰሮች ተመሳሳይ ምልክት ያላቸው ሲሆን፤ ድካም፣ በተደጋጋሚ ለኢንፌክሽንና ለደም ማነስ በሽታ መጋለጥ፣ መድማት፣ ክብደት መቀነስ፣ ትኩሳት፣ የሆድ እብጠት፣ ራስ ምታት የመሳሰሉ ምልክቶች እንደሚስተዋሉም መረጃው አመላክቷል።

በእሌኒ ግዛቸው
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በርካታ "የምርጫ መወዳደሪያ ቦታ ይገባኛል" ጥያቄዎች እንደሚቀርቡለት የሕገ-መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ አስታወቀ

ሕዳር 6/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በተለያዩ ጊዜያት በርካታ "የምርጫ መወዳደሪያ ቦታ ይገባኛል" ጥያቄዎች ከፖለቲካ ፓርቲዎች እንደሚቀርቡለት የሕገ-መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ አስታውቋል፡፡

ጉባኤው "በምርጫ ወቅት በምወዳደርበት አካባቢ መወከል ሲገባኝ አልተወከኩም" የሚሉ አቤቱታዎችን በተደጋጋሚ ማስተናገዱንም ነው ለአሐዱ የገለጸው፡፡

የጉባኤው ዋና ዳይሬክተር ደሳለኝ ወዬሳ በምርጫ ወቅት የመወዳደሪያ ቦታ ይገባኛል ከሚል የዘለለ፤ ጥያቄም ሆነ አቤቱታ ቀርቦለት እንደማያቅ ተናግረዋል፡፡

"የሕገ-መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ሊመለከተው የሚገባው የሕገ-መንግሥት ጉዳዮች ብቻ ቢሆንም፤ በዋናነት የፌዴሬሽን ምክር ቤትን የሚመለከተው ከአስተዳደር ወሰን ጋር የተያያዘ ጥያቄ እየቀረበልኝ ይገኛል" ሲሉም ገልጸዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም፤ "ጉባኤው የሚመለከተው ከፍርድ ቤት ውሳኔ በኋላ የሚመጡ ሕገ-መንግሥታዊ ጉዳዮችን ነው፡፡" ያሉ ሲሆን፤ ጉባኤው እንዲህ ዓይነት ጉዳዮች ሲቀርቡለት አስፈላጊውን ምርመራ ካካሄደ በኃላ ውሳኔ እንደሚሰጥበት አስረድተዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ለጉባኤው የማይመለከቱት ጉዳዮችም እየቀረቡለት እንደሚገኙ ያነሱት ኃላፊው፤ የሕግ ትርጉም እና የሕገ-መንግሥት አተረጓጎም ብዙዎችን ግራ እያጋባ እንደሚገኝ ያነሳሉ፡፡
የሕገ-መንግሥትን የመተርጎም ስልጣን የተሰጠው የሕገ-መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ፤ በግንዛቤ እጥረት ምክንያት የፌደሬሽን ምክር ቤትን የሚመለከቱ ጉዳዮችን ሲጠየቅ ወደሚመለከተው ቢሮ እንደሚመራውም ነግረውናል፡፡

የሕገ-መንግሥት ትርጓሜን በተመለከተ ግን መብቴ ተጥሷል የሚል ማንኛውም አካል አቤቱታውን ማቅረብ እንደሚችል አስረድተዋል፡፡

ጉባኤው ሥራውን ከጀመረበት 1991 ዓ.ም. ጀምሮ ከ9 ሺሕ በላይ አቤቱታዎች እንደቀረቡለት የተገለጸ ሲሆን፤ ከእነዚህ ውስጥ አብዛኛ ከሦስቱም የመንግሥት አካላት የሚቀርቡ ሆነው፣ 90 በመቶ የሚሆነው ግን ከመደበኛ ፍርድ ቤት የሚመጡ ናቸው ተብሏል፡፡

በአቤል ደጀኔ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

#ADVERTISMENT
#AmharaBank
የአማራ ባንክ አ/ማ የባለአክሲዮኖች 3ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ማክሰኞ ታህሳስ 01 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ በሚሊኒየም አዳራሽ ስለሚካሄድ ባለአክሲዮኖች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጉባዔው እንድትገኙ ጥሪ እናስተላልፋለን፡፡

የጉባዔው አጀንዳዎችን እና ተጨማሪ መረጃዎችን ጥቅምት 06 ቀን 2017 ዓ.ም በወጡት አዲስ ዘመን እና ሪፖርተር አማርኛ እትም ጋዜጦች ላይ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ለበለጠ መረጃ ነፃ የጥሪ ማዕከል 690 ወይም
የባንኩን ድረ ገጽ www.amharabank.com.et ይጎብኙ፡፡

አማራ ባንክ
ከባንክ ባሻገር!

የአማራ ባንክ ትክክለኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾች
Website: www.amharabank.com
Facebook: www.Facebook.com/amharabanksc1
Telegram: /channel/Amhara_Banksc
Instagram: https://instagram.com/amhara_bank
Twitter: https://twitter.com/Amharabanksc
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/amharabank/
YouTube: https://youtube.com/channel/UC73x9uuGYV0Uxw0EkpVZN8g
TikTok: amharabanks.c" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@amharabanks.c

#አማራባንክ #AmharaBank

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

#አሐዱ_ወንዞች

ሀገራት ለሕዝባቸው ህልውናና እድገት በገዛ ምድራቸው ፈልቆ በምድራቸው የሚፈስሰውን ውሃ መጠቀም ሁለተኛ የሌለው ቀዳሚ ምርጫ ነው።

የታችኛው ተፋሰስ ሀገሮች ሕዝባቸው በጠኔ፣ በሃይል ዕጦትና በመሰረተልማት እየተቸገሩ በሚገኙባቸው የውሃው አመንጭ ሀገሮች ላይ፤ እነርሱን ባልጨመረና ባላካተተ የቅኝ ግዛት ውሎች ‘አንዲት ጭልፋ ውሃ ካለ እኛ ፈቃድና እውቅና ንክች አታደርግዋትም’ ማለት ፍርደ- ገምድልነት ነው።

የሕዝባቸው ቁጥር በአስደንጋጭ ሁኔታ እየጨመረ የመጣባቸው የላይኛው ተፈሰስ ሀገሮች፤ ውሃ ለተለያዩ የቀን ተቀን ግልጋሎትና ለታናናሽ፣ መካከለኛና ታላላቅ መሰረተ ልማት መጠቀም ግድ ብሏቸዋል።

ከእነዚህ ግንባር ቀደም የችግሩ ሰለባ የናይል ውሃ ሦስት አራተኛውን የምታበረክተውና በዚህ ወቅት ከመቶ ሚልየን ሕዝብ በላይ ያላት ኢትዮጵያ ናት።

የአባይ ወንዝ አጠቃቀም እና የተጎጂነት መጠናችንን ብሎም በእቅድ የነበሩ እና በተግባር ያልታዩ ግድቦችን እናነሳለን፡፡

ሙሉ ጥንቅሩን ለመከታተል ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👇
https://youtu.be/X_ywqAwXjkg?si=ztl243bqHF9t6pk5

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

"ፓርቲያችን በሀገራዊ ምክክሩ ለመሳተፍ ይቸገራል" ሲል የቁጫ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ገለጸ

ሕዳር 5/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የቁጫ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ከጅምሩ አንስቶ ከኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሸን ጎን በመሰለፍ ለምክክር ሂደቱ መሳለጥ ድርሻውን በመወጣት የቆየ ቢሆንም፤ አሁን ላይ በሀገራዊ ምክክሩ ለመሳተፍ ያለው ዕድል በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ መሆኑን ገልጿል፡፡

ፓርቲው "በዚህ ታላቅ ሀገራዊ ፋይዳ በሚኖረው የምክክር ሂደት ላይ ለመሳተፍ ያለው ፅኑ አቋም እና ፍላጎት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት አመራሮች እኩይ ሴራ ሳቢያ ለመደናቀፍ በመቃረቡ፤ በሀገራዊ ምክክሩ ለመሳተፍ ይቸገራል" ሲል ነው በዛሬው ዕለት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ያስታወቀው፡፡

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከጥቅምት 22 እስከ 24 ቀን 2017 ዓ.ም. በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ሶዶ ከተማ ሀገራዊ ምክክር አጀንዳ ማሰባሰብና የተሳታፊ ልየታ መድረክ አዘጋጅቶ፤ ከተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች ጋር ባደረገዉ ውይይት አድርጓል፡፡

"በዚህ የውይይት መድረክ ፓርቲዉን ወክለው በተገኙ አመራሮችና አባላት ላይ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት አካላትና የፊት አመራሮች አቀነባባሪነት የግድያ ዛቻ፣ ማስፈራሪያ እና ከስብሰባው አዳራሽ አፍኖ የመውሰድ የኃይል እርምጃ ተወስዷል" ሲል ገልጿል።

"በምክክር ሂደቱ ተሳትፎ አድርገው በተመለሱ አባላቶቻችንም ላይ እየተፈጸሙ ያሉት ሕገ-ወጥ እስራቶችና አካላዊ ጥቃቶች ፓርቲያችን በሀገራዊ ምክክሩ አባላትን መድቦ በነፃነት እንዳይሳተፍ ስጋት ደቅኖብኛል" ብሏል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በተካሄደው ውይይት ፓርቲውን ወክለው ተሳትፎ ባደረጉ አመራሮችና አባላት ላይ ከመጀመሪያው ቀን ውሎ አንስቶ በተቀናጀ ሁኔታ ወከባዎች እንደተፈጸመባቸውም ገልጿል፡፡

"እነዚህ ወከባዎችም የተቀነባበሩት በዋናነት በክልሉ፣ በጋሞ ዞን፣ በቁጫ ወረዳ፣ በቁጫ አልፋ ወረዳና በሰላም በር ከተማ አስተዳደር የመንግሥት አካላት ነው" ሲልም በመግለጫው ከሷል።

በፅዮን ይልማ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በንጹሃን ዜጎች ላይ የሚደረገው የድሮን ጥቃት እንዲቆም ኢሕአፓ ጠየቀ

ሕዳር 5/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ የዜጎችን ሕይወት የመጠበቅ ሃላፊነት ያለበት መንግሥት በሚያሰማራቸው የጸጥታ ሃይሎችና የአገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ጭምር የዜጎች ሕይወት በበርካታ የሀገሪቷ ክፍሎች እየተቀጠፈ ይገኛል ሲል፤ የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢህአፓ) ገልጿል።

ፓርቲው ይሄን ያለው በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ ላይ ነው።

በመግለጫውም፤ "የኢትዮጵያ ሕገመንግሥት በአንቀጽ 14 ውስጥ፣ “ማንኛውም ሰው ሰብዓዊ (ሰው) በመሆኑ የማይደፈርና የማይገሰስ በሕይወት የመኖር፣ የአካል ደህነንትና የነፃነት መብት አለው” ብሎ ቢያስቀምጥም በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በአፋር ክልሎችና በቅርቡ ደግሞ በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በታጠቁ ወገኖች መጥፋት የዜጎች የሀዘን፣ የብሶትና የምሬት ምንጭ ሆኖ ቀጥሏል" ብሏል።

በጥቅምት 26 ቀን 2017 ዓ.ም. በደቡብ አቸፈር ጎጃም ዉስጥ በምትገኝ፣ “አርጌ” በምትባል ከተማ 46 የሚሆኑ ሰዎች መገደላቸውን፣ ሌሎች እስከ 64 የሚደረሱ ደግሞ መጎዳታቸውን የገለጸው ፓርቲው፤ በአካባቢው የተፈጸመውን ጥቃት በራሱ በማጣራት ማረጋገጥ መቻሉን አስታዉቋል።

"የጦርነቶች መስፋፋት፣ የሠላም መጥፋት፣ የዜጎች የሕይወት ዋስትና ማጣት፣ በፍረጃና በጅምላ የሚደረጉ እስራቶች መቀጠል፣ አምራቹ ሃይል ከማምረት ተግባሮቹ መደናቀፉ፣ የበርካታ አምራች ዜጎች በጦርነት እየተገደዱም ጭምር እንዲማገዱ መደረጉ፣ በሀገር ላይ ውድመትና ጥፋትን ነው የሚያስከትለው" ሲል ፓርቲው አሳስቧል።

ስለሆነም በመንግሥት ኃይሎች በንጹሃን ዜጎች ላይ የሚፈጸሙ የድሮን ጥቃቶች መፈጸም እንዲቆም ጠይቋል።

እንዲሁም ጦርነት እንዲቆም፣ ለችግሮች በሠላማዊ መንገድና በፖለቲካዊ ድርድር መፍትሄዎች እንዲፈለጉም ጥሪውን አቀርቧል።

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና ከ 30 ሺሕ በላይ ለሆኑ ዜጎች የሥራ እድል እንደሚፈጥር ተገለጸ

ሕዳር 7/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ከቀናት በፊት ወደ ትግበራ የገባው የድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና ከ30 ሺሕ በላይ ለሆኑ ዜጎች ቀጥተኛ የሥራ እድልን እንደሚፈጥር፤ የድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አህመድ ረሺድ ለአሐዱ ገልጸዋል።

ከ200 በላይ ባለሀብት ወደ ከተማዋ ይገባል ተብሎ እንደሚጠበቅ የገለጹት ዋና ሥራ አስኪያጁ፤ "ሁሉም የሚገቡ ከሆነ አጠቃላይ የኢትዮጵያን የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) 3 በመቶ ይሸፍናል" ሲሉም አክለዋል።

"ነፃ የንግድ ቀጠናው በድሬዳዋ የተመሰረተው ከተማዋ ለበርበራና ጅቡቲ ወደብ ቅርበት ያላት ከተማ በመሆንዋ ነው" ያሉም ሲሆን፤ በዋናነት ግን ከሌሎች የኢትዮጵያ ከተሞች በተሻለ መልኩ ድሬዳዋ ውስጥ አንፃራዊ ሰላም መኖሩና የከተማው አመሰራረት ንግድ ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ነው" ብለዋል።

የንግድ ትግበራዉ መጀመር የውጭ ምንዛሬ ወጪን የሚቀንስና የገቢና ወጪ ንግድን በፍጥነት የሚያሳልጥ ስለመሆኑም አስረድተዋል፡፡

በነፃ ንግድ ቀጠናው የሚሰጡ አገልግሎቶች በዋናነት ንግድ፣ ሎጀስቲክስ እና ማኑፋክቸሪንግ መሆናቸዉን በመግለጽ፤ አጠቃላይ ክንውኑም 70 በመቶ ንግድ፣ 30 በመቶ ደግሞ ማኑፋክቸሪንግ መሆኑን ተናግረዋል።

ነፃ ንግድ ቀጠናው ውስጥ የትኛውም ኢንቨስተር ይዞት የመጣውን ገንዘብ መቶ በመቶ መጠቀም እንደሚችል ተገልጿል።

ምርት ከውጪ ወደ ሀገር ውስጥ በሚገባበት ሰዓት ከተለመደው የንግድ አሰራር በተለየ መልኩ ባለሀብቱ አንዴ ፈቃድ አግኝቶ ሥራ ሲጀምር፤ ምንም አይነት የባንክ ፈቃድና ቀረጥ መክፈል ሳይጠበቅበት የሚያስገባበት አሰራር መኖሩንም ዋና ሥራ አስኪያጁ አቶ አህመድ አመላክተዋል፡፡

"ከሚልኩበት ሀገር ወደ ድሬዳዋ ዶክመንት ብቻ በመላክ ፍተሻ ሳይደረግበት በቀጥታ እቃውን ማራገፍ ይችላል" ሲሉም አክለዋል።

ለምጣኔ ሀብት ባለሙያው አቶ እንዳይላሉ ሰሎሞን በበኩላቸዉ፤ "ነፃ የንግድ ቀጠናው ድሬዳዋ መጀመሩ በዋናነት ድሬዳዋ ከወደብ ሀገራት ጋር ቅርበት ስላላት መሆኑን መልካም የሚባል ነው" ሲሉ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

ነፃ የንግድ ቀጠናው ለኢኮኖሚው መነቃቃትና እድገት ዘርፈ ብዙ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጸው፤ "ነገር ግን ይህ ሁሉ ሊሰራ የሚችለው የአሰራር ስርዓቱ አመቺ ሲሆን ነው" ብለዋል፡፡

በስፍራሽ ደመላሽ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

#ADVERTISMENT
#ጊፍትሪልስቴት
ታላቅ የምስራች
!
**
ጊፍት ሪል ስቴት ከ10% ቅድመ ክፍያ ጀምሮ በ22 ሳይቶቹ ቅንጡ አፓርትመንቶችን እና የንግድ ሱቆችን ለሽያጭ አቅርቧል፡፡

ይህ ሳይት ለአፓርትመንትና ንግድ ሱቆች የሚውሉ G+25 ሶስት መንታ ህንጻዎች ያሉት ሲሆን የዚህ 6ኛ መንደር መለያዎች፡-
•ከባለአንድ እስከ ባለአራት መኝታ ክፍሎች ያሉት፣
•ለመኖሪያም ሆነ ለንግድ ተመራጭ አካባቢ የሆነ፣
•በአንድ ወለል ሶስት ቤቶች ብቻ ያሉት፣
•በእያንዳንዱ ወለል ስድስት አሳንስር ያለው፣
•አራት ቤዝመንት ያሉት በቂ የመኪና ማቆሚያ የተዘጋጀለት፣
•24 ሰዓት የኤሌክትሪክ፣ ኢንተርኔትና ውሃ አቅርቦት አሉት፣

ጊፍት ሪል ስቴት
ማህበረሰብን እንገነባለን!
ለበለጠ መረጃ፡-
Website: https://www.giftbusinessgroup.com                                                                                             
Twitter: https://twitter.com/GIFTBusinessG                                                     
YouTube: www.youtube.com/channel/UCcqr7cpVv9ski-F7haxXx4w                                                     
Facebook: www.facebook.com/profile.php?id=100090918391017...                                                       
Telegram: /channel/giftbusinessgroup

Short Code: 8055

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

#አሐዱ_ስንክሳር

በኢትዮጵያ ሙዚቃ ውስጥ ደማቅ አሻራ አለው።

ለሀገሩ ኢትዮጵያ ብዙ ታሪክ ያሻገረ ድምፃዊ ነው ጥላሁን ገሠሠ።

ሰሞኑን ይገለገልባቸው የነበሩት የግል ንብረቶቹ፣ አልባሳቱ፣ ሽልማቶቹ፣ ሌሎችም ቁሳቁሶቹ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለሚገኘው ለኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም ተሰጥተዋል።

እነዚህን የጥላሁን ገሠሠን ንብረቶች ለዩኒቨርሲቲው ያስረከቡት ባለቤቱ ወይዘሮ ሮማን በዙ ናቸው።

በርክብክቡ ወቅትም ሲናገሩ፣ የጥላሁን ገሠሠ ንብረቶች ለዩኒቨርሲቲው መሠጠታቸው ሕዝብ እንዲያያቸው፣ እንዲጎበኛቸው፣ ተማሪዎቹም ጥላሁን ገሠሠ ለሀገሩ ኢትዮጵያ ያበረከታቸውን ውለታዎችም እንዲያውቁ እና እንዲማሩበትም ጭምር መሆኑን ገልጸዋል።

በዛሬው ኢትዮጵያዊ ስንክሳራችን ጥላሁን ገሠሠን ከኢትዮጵያዊ ሥራዎቹ አንፃር በጥቂቱ እናነሳሳዋለን።

በጥበቡ በለጠ
ጥንቅሩን ለመከታተል ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👇
https://youtu.be/sNxgvUQyaT0?si=5y-QNDHBrvzTkaxK

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

140 የሕገ መንግሥት ጥሰት የተፈፀመባቸው ጉዳዮችን አግኛቻለሁ ሲል የሕገ-መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ አስታወቀ

ሕዳር 6/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የሕገ-መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ 140 የሚሆኑ ጉዳዮች የሕገ-መንግሥት ትርጉም ተሰጥቶባቸው ለሚመለከተው ፌዴሬሽን ምክር ቤት መላኩን፤ የጉባኤው ፅህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ደሳለኝ ወዬሳ ከአሐዱ መድረክ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል፡፡

አጣሪ ጉባኤው ከተቋቋመበት 1991 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን ከ 9 ሺሕ በላይ አቤቱታዎች እንደቀረቡለትም ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡

ከሚቀርቡለት አቤቱታዎች አብዛኞቹ ፍትህ ከማግኘት ጋር የተያያዙና በተለይም በመደበኛው ፍርድ ቤት ክርክር በተሰጡ ውሳኔዎች ላይ ያተኮሩ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ሌላው የእኩለነት ጋር የተያያዘ አቤቱታ እንደሚቀርብለት ያነሱት ዋና ዳይሬክተሩ፤ በሕገ-መንግሥቱ የእኩልነት መብት በግልፅ የተቀመጠ በመሆኑ ይህንን ልዩነት በፈጠሩ አካላት ላይ ጉባኤው አቤቱታ እንደሚቀርብለት ገልጸዋል፡፡

ንብረት የማፍራት መብትም ሌላኛው በርካታ አቤቱታ የሚቀርበበት ጉዳይ መሆኑን የገለጹ ሲሆን፤ የጋራ መኖሪያ ቤት ዕጣን በሚመለከት ማንኛውም መስፈርቱን የሚያሟላ ዕድሉን እንደሚያገኝ የተቀመጠ መሆኑን አስታውሰዋል፡፡

በዚህም "መቶ በመቶ የከፈሉ ቅድሚያ ይሰጣል" የሚለውን በከተማ ልማት የወጣውን መመሪያ የሕገ መንግሥት መሰረታዊ የእኩልነት መብት የሚጥስ በመሆኑ እንዲስተካከል ተድርጓል ብለዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ የታሳሪዎችን የዋስትና መብት የሚከልከል አዋጅ ወጥቶ እንደ ነበር ያስታወሱት ዋና ዳይሬክተሩ፤ "በአዋጁ ላይ 'ማንኛውም በአደገኛ ቦዘኔነት የተጠረጠረ አካል የዋስትና መብት አይሰጠውም' የሚል በመኖሩ የሕገ መንግሥቱን መሰረታዊ መብት የሚጥስ ሆኖ ተገኝቷል" ብለዋል፡፡

በዚህ ጉዳይ ላይ የወጣው አዋጅ ከሕገ-መንግሥቱ ጋር የሚፃረር በመሆኑ የሕገመንግሥት ትርጉም እንዲሰጠው ከተደረጉ 140 ጉዳዮች ውስጥ መሆኑን ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

ጉባኤው የሚቀርቡለት አቤቱታ ከጊዜ ወደ ጊዜ መጨመሩም የተነሳ ሲሆን፤ በተቻለ መጠን የአሰራር ስርዓት ደንብ በማውጣት መጨናነቅን ለመቀነስ እየተሰራ እንደሆነም ዋና ዳይሬክተሩ ለአሐዱ አስረድተዋል፡፡

የሕገ-መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ፤ በዚህ ዓመት ካለፈው ዓመት የተከማቸ አቤቱታ ስላለበት የሚመለከተው አዲስ አቤቱታ አለመኖሩንም ጨምረው ተናግረዋል፡፡

በአቤል ደጀኔ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

#አሐዱ_ሳድስ

ትራምፕ እና ፑቲን ያስተሳሰራቸው ጥቅም ምንድን ነው?

ሙሉ ጥንቅሩን ለመከታተል ከሥር ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ!
👇
https://youtu.be/pmSz_y5Zo_U?si=JzHIwC5ikiYITLXO

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በጾታዊ ትንኮሳ ወንጀልነት ላይ ያለው ግንዛቤ አናሳ መሆን ለችግሩ መበራከት ምክንያት መሆኑ ተገለጸ

👉 የግንዛቤ ከመፍጠር አንጻር የመንግሥትና የግል መገናኛ ብዙሃን ተሳትፎ ዝቅተኛ መሆኑም ተነግሯል


ሕዳር 6/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በሕብረተሰቡ ዘንድ ያለው የግንዛቤ እጥረት ለጾታዊ ጥቃት መስፋፋት ምክንያት መሆኑን ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ ይህን ያለው "ኢንጀንደር ኸልዝ" ከተባለው የሲቪል ተቋም ጋር በመሆን ከፆታዊ ትንኮሳና ከስነተዋልዶ ጋር በተያያዘ በአዳማ እየተሰጠ ባለው የስልጠና መድረክ ላይ ነው።

በዚህም ፆታዊ ትንኮሳ ፈጻሚዎች ድርጊቱን መፈፀም ወንጀል መሆኑን ባለመረዳት ትንኮሳዎችን እንደሚፈጽሙ ተጠቁሟል፡፡

ከዚህ ባሻገርም የትንኮሳው ሰለባ የሆኑት አካላት ጾታዊ ትንኮሳ ወንጀል መሆኑን አለመረዳትና ፍትህ ፍለጋ ወደ ፍትህ ተቋማት አለመሄድ፤ ለችግሩ መስፋፋት ምክንያት ሆኗል ተብሏል፡፡

በመድረኩ ችግሩ መኖሩ ቢታወቅም የመከላከል ሥራዎች እስካሁን በበቂ ሁኔታ እንዳልተሰሩ ተያይዞ ተነስቷል።

በዚህም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣውን ፆታዊ ትንኮሳ ለመከላከል ከህግ አካላትና ከጤና ሚኒስትርና ከሚመለከታቸው ባለሙያዎች ጋር ምክክር ተደርጓል።

ጤና ሚኒስትር በበኩሉ፤ ሕብረተሰቡ በጾታዊ ትንኮሳ ወንጀልነት ላይ ያለው ግንዛቤ አናሳ መሆኑን በማንሳት፤ እየተባባሰ የመጣውን ፆታዊ ትንኮሳ ቀድሞ ከመከላከል አኳያ የመንግሥትና የግል መገናኛ ብዙሃን ተቋማት ተሳትፎ ዝቅተኛ መሆኑን ገልጿል።

"የመገናኛ ብዙሃን ካላቸው ተሰሚነት አንፃር የፆታዊ ትንኮሳ ቅድመ መከላከል ሥራዎችን ሊሰሩ ቢገባም፤ ያላቸው ተሳትፎ ዝቀተኛ ነው" ሲሉ፤ የጤና ሚኒስትር ሕዝብ ግንኙነት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ተገኔ ረጋሳ ተናግረዋል።

አክለውም፤ ችግሮች መኖራቸው ታምነው የመገኛና ብዙሃን ከግንዛቤ ማስጨበጥ እስከ ጥቆማዎች መስጠት ያሉ ክፍተቶችን መሙላት አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል።

"ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ችግሩን ከመቅረፍ ጋር በተያያዘ ዘረፈ ብዙ ሥራዎችን እየሰራ ይገኛል" ያሉት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው፤ ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት የድርሻቸውን ከተወጡ ችግሩ እንደሚቀረፍ አመላክተዋል፡፡

በኢትዮጵያ 27 በመቶ የሚሆኑ ፆታዊ ትንኮሳዎች በዲጅታል ትስስር አማራጮች እንደሚፈፀሙ በ2015 በተሰራው ጥናት መታወቁ ተነግሯል።

በወልደሐዋርያት ዘነበ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!

ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የግብፅ ከፍተኛ ድፕሎማት ከተባበሩት መንግሥታት ሉዑክ ጋር በሱዳን የተኩስ አቁም ጥረት ዙሪያ ዉይይት ማድረጋቸዉ ተገለጸ

ሕዳር 6/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ባድር አብደላቲ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሱዳን ልዑክ ራምታኔ ላምራ ጋር በሱዳን የተኩስ አቁም ጥረት ላይ በካይሮ መወያየታቸዉን አስታዉቀዋል።

"ግብፅ የሱዳንን ጥቅም ለማስጠበቅ እና የግዛት አንድነቷን ለማስከበር ትፈልጋለች" ሲሉ አብደላቲ ተናግረዋል።

አክለውም፤ የሱዳንን ሕዝብ ስቃይ በማቃለል በሃገሪቱ የተኩስ አቁም እንዲደረግና ዘላቂ እልባት እንዲመጣ፤ ካይሮ በተለያዩ አህጉራዊ እና አለም አቀፋዊ ጥረቶች ላይ በንቃት ለመሳተፍ ቁርጠኛ መሆንዋን ገልጸዋል።

የሱዳንን ፀጥታና መረጋጋት ወደ ነበረበት ለመመለስ ግብፅ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን ሙሉ በሙሉ ለመደገፍ ዝግጁ መሆኗንም ተናግረዋል፡፡

ከፍተኛው ዲፕሎማት በሱዳን እየተባባሰ ያለው የሰብአዊ ቀውስ ሁኔታ እንዳሳሰባቸው ገልጸው፣ ግብፅ “የሱዳንን ጥቅም፣ ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነትን ለማስጠበቅ” ቁርጠኛ አቋም እንዳላትም አብራርተዋል፡፡

በተጨማሪም በሱዳን የሚከሰቱ ለውጦች በሁለቱ ሀገራት መካከል ባለው የጠበቀ ግንኙነት ምክንያት፤ በግብፅ ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም ዲፕሎማቲ መጠቆማቸውን የሱዳን ትሪቡን ዘገባ አመላክቷል፡፡

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በአራት ወራት ውስጥ 62 ሺሕ 384 ሕገ ወጥ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን የኦሮሚያ ንግድ ቢሮ አስታወቀ

ሕዳር 6/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኦሮሚያ ክልል በ2017 ዓ.ም አራት ወራት ውስጥ እንደ አጠቃላይ 1 ሚሊዮን 23 ሺሕ 512 የንግድ ድርጅቶች ላይ ቁጥጥር በማድረግ፤ 62 ሺሕ 384 በሕገ ወጥ ንግድ የተገኙ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን የኦሮሚያ ንግድ ቢሮ አስታውቋል፡፡

የቢሮው የክትትል እና ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ጉዲሳ፤ በክልሉ በዚህ ዓመት በሕገ ወጥ ሥራ ተስማርተው የነበሩ ነጋዴዎች ላይ የተለያዩ እርምጃዎች መወሰዳቸውን ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

በዚህም የዋጋ ዝርዝር ሳይለጥፉ በሚሰሩ እንዲሁም በሕገወጥ መንገድ የንግድ ሥራ በሚያከናውኑ ነጋዴዎች ላይ፤ ከጹሑፍ ማስጠንቀቂያ ጀምሮ ድርጅቶችን እስከ ማሸግ የሚደርስ ሕጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃዎች መወሰዳቸውን ገልጸዋል፡፡

በዚህም መሠረት በክልሉ አራት ወራቶች ውስጥ 26 ሺሕ የሚሆኑ ድርጅቶች የታሸጉ ሲሆን፤ 19 ሺሕ የሚሆኑት ደግሞ የጹሁፍ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ገልጸዋል፡፡ ሌሎቹም ነጋዴዎች እንደየጥፋታቸው ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው እና እርምጃ የተወሰደባቸው መሆኑን አንስተዋል፡፡

እንደ አጠቃላይ በንግድ ዘርፉ ላይ አላስፈላጊ የንግድ ልውውጦችን በተመለከተ ከሚመለከተው አካል በጋራ በመሆን ቁጥጥርና ክትትል የማድረግ ሥራዎች እየተሰሩ ስለመሆኑ አቶ ጌታቸው ገልጸዋል፡፡

በክልሉ የሚካሄዱ ሕገ ወጥ ንግዶችን ለመቆጣጠር ከሚመለከተው አካል ጋር በጋራ በመሆን እየሰሩ እንደሚገኙ የገለጹት ዳይሬክተሩ፤ ለማህበረሰቡም ግንዛቤ በመፍጠር ከሕገ ወጥ ድርጊታቸው እንድቆጠቡ ለማድረግ እንደሚሰሩም ተናግረዋል።

አክለውም፤ የማክሮ ኢኮኖሚ ጭማሪውን ታሳቢ በማድረግ መንግሥት ለማህበረሰቡ ድጋፍ በሚያደርገው የሸቀጣ ሸቀጥ ቁሶችን በአግባቡ ተደራሽ ለማድረግ እየሰሩ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

በአለምነዉ ሹሙ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!

ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የአፋር ፌደራላዊ ዴሞክራሲ ፓርቲ ታጣቂዎች ትጥቃቸውን ለአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ማስረከባቸው ተገለጸ

ሕዳር 6/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የአፋር ፌደራላዊ ዴሞክራሲ ፓርቲ ታጣቂዎች ትጥቃቸውን ለአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት አስረክበው፤ ለክልሉ ሰላም እና ልማት በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት አስታውቋል።

ታጣቂዎቹ በአፋር ክልል አብአላ ከተማ ላይ በተካሄደው ሥነ ስርአት ላይ ለክልሉ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ ትጥቃቸውን ያደረጉ ሲሆን፤ ርዕሰ መስተዳድሩ በሠላም ወደ ክልሉ ለመጡ ወጣቶች የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር አድርገዋል፡፡

በመልዕክታቸውም ሠላም የሁሉም ነገር መሠረት መሆኑን በመጠቆም፤ "ታጣቂዎቹ የሠላምን መንገድ መምረጣቸው ለክልሉ ሠላም መረጋገጥ ከሚያበረክተው አስተዋጽኦ ባሻገር ለሀገራዊ ሠላም እና አንድነት ያለው ጠቀሜታ ከፍተኛ ነው" ብለዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ አክለውም "በክልሉ ሠላም እና ልማት ላይ በንቃት መሣተፍ እንዲችሉ ክልሉ አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል" ካሉ በኃላ፤ የመከላከያ መረጃ ዋና መምሪያ ስምምነቱ በስኬት እንዲጠናቀቅ ላበረከተው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል።

ብርጋዲየር ጄኔራል ጀማል ሻሌ በበኩላቸው፤ የመከላከያ መረጃ ዋና መምሪያ ከዚህ ቀደምም በጋምቤላ እና ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልሎች የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎችም ትጥቃቸውን አስረክበው ወደ ሠላማዊ መንገድ እንዲመጡ መደረጉን አስታውሰዋል፡፡

በአፋር ክልልም ትጥቅ ይዘው ከሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ጋር ተከታታይ ውይይቶችን በማድረግ ከአፋር ፌደራላዊ ዴሞክራሲ ፓርቲ ታጣቂዎች በተጨማሪ፤ ራሱን "የአፋር ነፃ አዉጪ ግንባር" እያለ ከሚጠራዉ ታጣቂ ሀይል ጋርም በተሠራው ዉጤታማ ሥራ ወደ ሠላማዊ መንገድ ማምጣት እንደተቻለ ገልጸዋል።

ብርጋዲየር ጄኔራል ጀማል በአሁኑ ወቅት በአፋር ክልል በሕገ ወጥ መንገድ ትጥቅ ይዞ የሚንቀሳቀስ የተደራጀ ሃይል እንደሌለ ያስታወቁ ሲሆን፤ "ከዚህ ለሀገር አንድነት እና ሠላም ከሚበጅ በጎ ተግባር ሌሎች ክልሎችም ትምህርት ሊወስዱ ይገባል" ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የጸጥታ ዘርፍ ሀላፊ ጋዶ ሐሞሎ፤ ታጣቂዎቹን ወደ ሰላማዊ መንገድ ለማምጣት ተከታታይ ውይይቶች ሲካሔዱ መቆየታቸውን ገልጸው፤ "የሀሳብ ልዩነቶችን በሠለጠነ መንገድ መፍታት እንደ ባህል መለመድ ያለበት አሰራር ሊሆን ይገባል" ብለዋል፡፡

የአፋር ፌደራላዊ ዴሞክራሲ ፓርቲ ታጣቂዎች ሊቀመንበር ሀጂ ስዩም አወል በበኩላቸው፤ ከግጭት እና ጦርነት የሚገኝ ትርፍ እንደሌለ የተናገሩ ሲሆን፤ "ከአሁን በኋላ ሕገ መንግሥታዊ ስርአቱን አክብረን በሠላማዊ መንገድ ሕዝባችንን ለማገልገል በወሳኝ ምዕራፍ ላይ እንገኛለን" ሲሉ ተናግረዋል፡፡

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በኢትዮጵያ በግጭት ምክንያት የሚካሄደው የሀገር ውስጥ መፈናቀል የድህነት ቅነሳ መርሃ ግብሩን እየቀለበሰ መሆኑ ተገለጸ

ሕዳር 6/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ በግጭት ምክንያት የሚካሄደው የሀገር ውስጥ መፈናቀል ለአስርት ዓመታት የዘለቀውን የድህነት ቅነሳ መርሃ ግብር እየቀለበሰው እንደሚገኝ የአለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (አይ.ኦ.ኤም)፣ የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም (ዩ.ኤን.ዲፒ) እና የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኤጀንሲ (ዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር) በጋራ አሳሰቡ።

ከሕዳር 2 እስከ 4/2017 ድረስ ከሦስቱ የተመድ ኤጀንሲዎች የተውጣጡ መሪዎች በዋና ከተማዋ አዲስ አበባ ላይ ተገናኝተው፤ አስቸኳይ እርዳታ ከማሟላት ጎን ለጎን በመንግሥት የሚመራውን የልማት እና የሰላም ግንባታ ጥረቶችን ለማጠናከር ያለመ አዲስ ሀገራዊ ስትራቴጂ ይፋ አድርገዋል።

በጉባኤዉ ላይ በተባበሩት መንግሥታት የአለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት የኦፕሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኡጎቺ ዳኒልስ፣ የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም የአደጋ ቢሮ ዳይሬክተር ሾኮ ኖዳ እንዲሁም የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኤጀንሲ ረዳት ከፍተኛ ኮሚሽነር ራኡፍ ማዙ የተሳተፉ ሲሆን፤ “በኢትዮጵያ እየተደረገ ያለው ሰብዓዊ እርዳታ በቂ አይደለም" ሲሉ ተደምጠዋል።

ኢትዮጵያ 15 ሚሊዮን ዜጎችን ከድህነት ማውጣት ብትችልም፤ በኮቪድ-19፣ በግጭት፣ በድርቅ እና በጎርፍ በተከሰቱ ችግሮች ሳቢያ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በርካታ ተፈናቃዮች ለመኖር አስፈላጊ የሚባሉ ግብአቶችን ማግኘት አለመቻላቸው ተነግሯል።

“በኢትዮጵያ ውስጥ የተፈናቀሉ ዜጎች ችግር የሰብአዊ ጉዳይ ብቻ አይደለም፤ ብዙ ተፈናቃዮች መሰረታዊ የሆኑ ማህበራዊ አገልግሎቶችን፣ ጥበቃን፣ ሥራ እና የመተዳደሪያ እድሎችን ማግኘት ያስፈልጋቸዋል" ሲሉም ሾኮ ኖዳ ተናግረዋል።

የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም ለኢትዮጵያ የሚሰጠው አለም ዓቀፍ የገንዘብ ድጋፍ፣ በ2020 ከ4 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር ወደ 2 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር በ2022 መውረዱን ተቋሙ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በአስተዳደር እና በማህበራዊ አገልግሎቶች፣ በኢኮኖሚያዊ እድሎች ላይ ኢንቨስት በማድረግ እንዲሁም የተፈናቀሉ ዜጎችን በፈቃደኝነት ወደነበሩበት እንዲመለሱ፣ እንዲሰፍሩ እና እንዲዋሃዱ ሁኔታዎችን በመፍጠር ላይ መሆናቸዉ ተነግሯል።

በድርጅቱ ዘላቂ የሰብአዊ እርዳታ ተግባራዊ ለማድረግ ከተመረጡ 15 ሀገራት መካከል፤ ኢትዮጵያ አንዷ ነች።

በዳግም ተገኝ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

ኢትዮጵያ የአቡጃን ስምምነት የፈረመች ቢሆንም ለጤናው ዘርፍ የምትመድበው 8 በመቶ ብቻ መሆኑ ተገለጸ

ሕዳር 6/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ኢትዮጵያ በናይጄሪያ አቡጃ ከተማ ሚያዝያ 23 ቀን 1993 ዓ.ም የአፍሪካን የጤና ዘርፍ ለማሳደግ እንዲሁም በሽታዎች ከመከሰታቸው በፊት ቅድመ ጥንቃቄ ለማድረግ ታስቦ የተፈረመውን ስምምነት ፈራሚ ሀገር ብትሆንም፣ እስካሁን ለጤናው ዘርፍ የምትመድበው በጀት 8 በመቶ ብቻ መሆኑ ተገልጿል።

በዚህ የአቡጃ ስምምነት ከሀገራት አጠቃላይ በጀት ለጤናው ዘርፍ 15 በመቶ እንዲመደብ ውሳኔ ላይ ተደርሶ የነበረ ሲሆን፤ ስምምነቱ ከተፈረመ 23 ዓመታት አልፈውታል።

ነገር ግን ኢትዮጵያ አሁንም ከአጠቃላይ በጀቷ 8 በመቶውን ብቻ ለጤናው ዘርፍ እየመደበች እንደምትገኝ፤ በጤና ሚኒስቴር ብሄራዊ የእናቶች ጤና ፕሮግራም አስተባባሪ ሲስተር ዘምዘም መሀመድ ለአሐዱ ተናግረዋል።

ይህም በእናቶች እና ሕጻናት እንዲሁም በአጠቃላይ የጤና ዘርፉ ላይ ተጽዕኖ እያሳደረ እንደሚገኝ ጨምረው ገልጸዋል።

ለአብነትም በኢትዮጵያ በዓመት 10 ሺሕ እናቶች፣ በወር 833 እና በቀን 28 እናቶች በወሊድ ምክንያት ለሕልፈት እንደሚዳረጉ በመግለጽ፤ ለዚህም እንደምክንያት ከሚነሱ ችግሮች መካከል አንዱ የበጀት እጥረት መሆኑን አስረድተዋል።

ስምምነቱ ከተፈረመ በኋላም በሚደረጉ ክትትሎች እስከ አሁን በበርካታ የአፍሪካ ሀገራት ላይ፤ ተፈጻሚ መሆን አለመቻሉ ተጠቁሟል።

እንዲሁም ስምምነቱ ከተፈረመ ከ 10 ዓመት በኋላ 27 የአፍሪካ ሀገራት ለጤና ዘርፍ የሚመድቡትን በጀት ያሳደጉ ቢሆንም፤ ሩዋንዳ እና ደቡብ አፍሪካ ብቻ የተቀመጠውን 15 በመቶ በጀት መመደብ ችለዋል።

በአውሮፓውያኑ በ2016ም 19 የአፍሪካ ሀገራት ስምምነቱ ሲፈረመ ከነበራቸው የተሻለ እንቅስቃሴ፤ ማሽቆልቆላቸው ተገልጿል።

በፍርቱና ወልደአብ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

መልካም ቀን!
አሐዱ ሬድዮ 94.3  የኢትዮጵያውያን ድምፅ!

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በኢትዮጵያ በወባ በሽታ ከአንድ ሺሕ 157 ሰዎች መሞታቸዉን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ

ሕዳር 5/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ ከታህሳስ 22/2016 እስከ ጥቅምት 10 ቀን 2017 ድረስ ከ7 ነጥብ 3 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በወባ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን፤ አንድ ሺሕ 1 መቶ 57 ሰዎች ደግሞ በበሽታው ምክንያት መሞታቸውን የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) አስታውቋል።

የተባበሩት መንግሥታት የጤና ኤጀንሲ ባወጣው ሪፖርት ባለፉት ሰባት ዓመታት በቫይረሱ የተያዙ ሴት አኖፌልስ ትንኞች ንክሻ ከተመዘገበው ከፍተኛው ነው ብሏል።

ወባ በኢትዮጵያ ከፍተኛ የህብረተሰብ ጤና ተግዳሮት መሆኑን የአለም ጤና ድርጅት የገለጸ ሲሆን፤ 75 ከመቶ የሚሆነዉ የሀገሪቱ አካባቢ የወባ በሽታ በሰፊዉ የሚከሰትበት መሆኑን አመላክቷል።

ሪፖርቱ አክሎም ከጠቅላላ የሀገሪቱ ሕዝብ 69 በመቶ ያህሉ የወባ በሽታ እንደሚያዙ በመግለፅ፤ በየወቅቱ በሚከሰቱት ወረርሽኞች ከአምስት ዓመት በታች ለሆኑ ሕጻናት እስከ 20 በመቶ ለሚሆኑት ሞት መንስኤ ነዉ ሲል ሪፖርቱ ገልጿል።

በ2024 ከተመዘገቡት ኬዞች 81 በመቶው እና 89 በመቶ የሚሆነዉን የወባ ሞት የሚይዙት አራት ክልሎች መሆናቸውን የገለጸው የተባበሩት መንግሥታት የጤና ኤጀንሲ፣ እነዚህም ኦሮሚያ፣ አማራ፣ ደቡብ ምዕራብ እና ደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት መሆናቸውን ገልጿል።

በዳግም ተገኝ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ:www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በእነ መስከረም አበራ መዝገብ የተከሰሱት 51 ተከሳሾች የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ

👉ችሎት ፊት በአካል የቀረቡት ሃያ ሦስት ተከሳሾች “ወንጀሉን አልፈጸንም” ሲሉ ተከራክረዋል


ሕዳር 5/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በእነ መስከረም አበራ መዝገብ የተከሰሱት 51 ተከሳሾች ዛሬ ሕዳር 5 ቀን 2017 ዓ.ም በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት 1ኛ ጸረ-ሽብር ወንጀል ችሎት የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጥተዋል።

ችሎቱ "ሕገ መንግሥቱን በሃይል በመናድ" ወንጀል የተከሰሱትን ተከሳሾች የእምነት ክህደት ቃል ለመቀበል፤ ለዛሬ ቀጠሮ መስጠቱ ይታወቃል፡፡

በዚህም ከሃምሳ አንዱ ተከሳሾች መካከል ሃያ ሦስቱ በዛሬው ዕለት በችሎቱ በአካል በመገኘት፤ "ወንጀሉን አልፈጸምንም" ሲሉ ቃላቸውን ሰጥተዋል።

ከተከሳሾቹ መካከል “ኢትዮ ንቃት” የተሰኘው ማኅበራዊ ሚዲያ መሥራች እና ባለቤት ጋዜጠኛ መስከረም አበራ፣ ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ እንዲሁም ዶ/ር ወንደሰን አሰፋ እንደሚገኙበት የአሐዱ ሬድዮ ሪፖርተር ከችሎት ተገኝቶ ዘግቧል።

ዐቃቤ-ሕግ በበኩሉ ጉዳዩን የሚያስረዱለት 92 ምስክሮችን እንደሚያቀርብ ለችሎቱ አስረድቷል።

ፍርድም ቤቱም ዐቃቢ ሕግ ማስረጃ ያላቸዉን ምስክሮች እንዲያቀርቡ በማዘዝ መዝገቡን ለታህሳስ 7 ቀን 2017 ዓ.ም. ቀጥሯል።

እንደ አጠቃላይ የእስር ቤት አያያዝን በተመለከተ መስከረም አበራ ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ አቅርባለች።

በአቤቱታዋም ቤተሰቦቿ እሷን ለመጠየቅ መቸገራቸዉን አንስታ፤ “ይህ ጉዳይ በተደጋጋሚ ስለሆነ የተከበረዉ ፍርድ ቤት ይህንን ችግር ተገንዝቦ ትዕዛዝ እንድሰጥልኝ” ብላለች።

ፍርድ ቤቱም መስከረም አበራ በቃል ያቀረበችውን አቤቱታ በመቀበል፤ የሚመለተው አካል ማስተካከያ እንዲያደርግ ትዕዛዝ እንደሚሰጥ አስታውቋል፡፡

በአለምነው ሹሙ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በምዕራብ ኦሮሚያ ወለጋ በግጭት ምክንያት የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋርጦባቸው የነበሩ ከ150 በላይ አካባቢዎች ሃይል ማግኘታቸው ተገለጸ

ሕዳር 5/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ግጭት በነበረበት የምዕራብ ኦሮሚያ ክፍል የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋርጦባቸው የነበሩ 150 አካባቢዎች ሃይል ማግኘታቸውን ገልጿል።

የአገልግሎቱ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ መላኩ ታዬ፤ የኤሌክትሪክ አገልግሎቱ ሰራተኞች ግጭት ባለባቸው አካባቢዎችም ጭምር ሥራዎችን እየሰሩ መሆኑን አንስተዋል።

አሁንም ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች (የቦታዎችን ሥም ባይጠቅሱም) "በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ ተቋሙ አገልግሎት እየሰጠ ነው" ብለዋል።

በትግራይ ክልል በነበረው ጦርነት የወደሙ የመሰረተ ልማቶች መልሶ ጥገና ሙሉ ለሙሉ መጠናቀቁንም የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው መላኩ ታዬ አክለዋል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በደረሰባቸው ጥቃት ከአገልግሎት ውጪ የሆኑትን ለትግራይ ክልል የኤሌክትሪክ ኃይል የሚቀርብባቸውን መሠረተ ልማቶች በመጠገን የክልሉ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት እንዲመለስ እየሠራ መሆኑን መግለጹ ይታወሳል።

የኤሌክትሪክ አገልግሎት ከሚሰራቸው ጥገናዎች የሚወጡ ወጪዎች ባሻገር የመስረት ልማት ስርቆት በከፍተኛ ሁኔታ ወጪ እያስወጣው መሆኑንም ገልጿል።

በፍርቱና ወልደአብ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…
Subscribe to a channel