በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳዳር ላይ ክስ መመስረቱን እንዳዘገየው የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም አስታወቀ
ሕዳር 10/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም የትግራይ ቅርጫፍ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳር ላይ ሊመሰርት የነበረውን ክስ ላልተወሰነ ጊዜ እንዳዘገየው አስታውቋል፡፡
የቀድሞ የትግራይ ፖሊስ አባላት "ያለአግባብ ከሥራ ገበታችን ተነስተናል" በሚል ለእንባ ጠባቂ ተቋም ቅሬታ ማቅረባቸው የሚታወቅ ሲሆን፤ ይህንን በሚመለከት ቅርጫፍ ፅ/ቤቱ ግዚያዊ አስተዳደሩ ላይ ክስ ለመመስረት ማሰቡ ተገልጾ ነበር፡፡
የትግራይ ቅርጫፍ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፀሀዬ እምባዬ ለአሐዱ እንደተናገሩት፤ ጊዜያዊ አስተዳደሩ የቀድሞ ፖሊሶችን አቤቱታ በተመለከተ ምላሽ እንዲሰጥ በተደጋጋሚ ተጠይቆ ምላሽ ባለማግኘታችን ወደ ክስ ለመመስረት በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
30 ቀን ጠብቀው ምላሽ ማግኘት ባለመቻላቸውን አምስት ተጨማሪ ማስጠንቀቂያ ቀናት መጠበቃቸውን የሚናገሩት ኃላፊው፤ "በአካል ለመነጋገር ወደ ርዕሰ መስተዳደሩ ቢሮ ያመራን ሲሆን፤ ጉዳዩ ለካቢኔ መመራቱ ተገልጾልናል" ብለዋል፡፡
በዚህም መሠረት ክሱን ለግዜው ማቆማቸውን የተናገሩት አቶ ፀሐዬ፤ "ጉዳዩ ወደ ካቢኔ ስለተመራ ከካቢኔ ውሳኔ በኃላ በፅሁፍ እንዲያስውቁን ተነገጋርን ክሱን አዘግይተነዋል" ሲሉ ተናግረዋል፡፡
አሐዱም "ለመሆኑ ወደ ክስ በድጋሚ ልታመሩ ትችላላችሁ ወይ? ተቋርጧል ማለትስ ይቻላል ወይ? ሲል የዕምባ ጠባቂ የትግራይ ቅርጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊው ፀሀዬ እምባዬን ጠይቋል፡፡
በምላሻቸውም "የካቢኔውን ውሳኔ በሚመለከት ምላሻቸውን ካዳመጥን በኃላ፤ መፍትሄ ከተሰጠ ክሱ ይቋረጣል ካልሆነ ግን ወደ ክስ እንመራለን" ብለዋል፡፡
በጊዜያዊ አስተዳደሩ ላይ የቀረበው ክስ፤ "የቀድሞ የትግራይ ፖሊስ አባላት አለአግባብ ከሥራ ገበታቸው የተባረሩ በመሆኑ ወደ ነበሩበት ቦታ እንዲመለሱና ደሞዛቸውም እንዲከፈላቸው" የሚል ነው፡፡
ከፕሪቶሪያው ስምምነት በኃላ ሁሉም የመንግሥት ሠራተኛ ወደ ሥራ የተመለሰ መሆኑን ያነሱት አቶ ፀሐዬ፤ ፖሊሶቹ ግን ደምወዝ እንዳላገኙና ወደ ሌላ ሥራም እንዳይገቡ (ክሊራስ) ወይም መሸኛ ጭምር እንዳልተሰጣቸው ገልጸዋል፡፡
ኃላፊው አክለውም፤ "በክልሉ ምክር ቤት ባለመኖሩ የሚጠይቅ አካል የለም" ብለዋል፡፡
የቀድሞ የትግራይ ፖሊስ አባላት 'በሰሜኑ ጦርነት ወቅት መንግሥት መቀሌን ሲቆጣጠር አልታገላችሁም' እንዲሁም፤ 'ከመንግሥት ጎን ወግናቹሃል' በሚል ግዚያዊ አስተዳደሩ ወደ ስልጣን ሲመጣ ከሥራ እንዳገዳቸው ይታወሳል፡፡
በአቤል ደጀኔ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2029 በአፍሪካ ትልቅ ኢኮኖሚ ካላቸው ሀገራት ሦስተኛ ደረጃን እንደምትይዝ ተገለጸ
ሕዳር 10/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) አሁን ላይ የኢትዮጵያ ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምረቷ 210 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን፤ በአውሮፓውያን አቆጣጠር 2029 ጠቅላላ ሀገራዊ ምርቷ 369 ቢሊዮን ዶላር ይደርሳል ተብሏል።
ይህ የተገለጸው በዛሬው ዕለት የረጅም ግዜ የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን ፍኖተ ካርታ ላይ በልማት ሚኒስቴር በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ነው።
በመድረኩ ላይ የልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ፍፁም አሰፋን ጨምሮ የገንዘብ ሚኒስቴር አህመድ ሺዴ፣ የብሔራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምህረቱ እንዲሁም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቤ ሳኖ ተገኝተዋል።
የልማት ሚኒስቴር ያዘጋጀው መድረኩ የረጅም ግዜ የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን ምን ይመስላል? የሚለውን ያለፈውን 60 ዓመት እና ቀጣይ 25 ዓመታትን ምን መምሰል አለበት? በሚለው ላይ ያተኮረ ነው።
በዚህ መድረክ ላይ ያለፈውን 60 ዓመት ምን ይመስላል የሚለውን ያቀረቡት የልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ፍፁም፤ ባለፉት 60 ዓመት ኢትዮጵያ 4 ነጥብ 2 በመቶ ዕድገት ማስመዝገቧን ተናግረዋል።
የሕዝብ ቁጥሩም ባለፉት 60 ዓመታት 2 ነጥብ 9 በመቶ ዕድገት ማስመዝገብ መቻሉንም ገልጸዋል።
ይህ የዓለም ባንክ ጥናት መሆኑን የገለፁት ሚኒስትሯ፤ ኢትዮጵያ በቀጣይ 2029 ከአፍሪካ ከግብፅ እና ደቡብ አፍሪካ በመቀጠል ሦስተኛ ትልቁ ኢኮኖሚ እንደሚኖራት መናገራቸውን አሐዱ ሰምቷል።
የነፍስ ወከፍ ገቢም ባለፉት 69 ዓመታት 1 ነጥብ 3 በመቶ ዕድገት መመዝገቡን የገለፁ ሲሆን፤ የዕድሜ ጣሪያውም 68 ዓመት መድረሱን በመድረኩ ላይ ገልጸዋል።
ያለፉት 60 ዓመታት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ጉዞ የተለያዩ የኢኮኖሚ ፓሊሲ ተግባራዊ ቢደረግም ለውጥ ያመጣ ነው ለማለት አያስደፍርም ተብሏል።
በአቤል ደጀኔ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ምክር ቤቱ የአንድ አባሉን ያለመከሰስ መብት አነሳ
ሕዳር 10/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የአዲስ አበባ ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 4ተኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤው የአንድ አባሉን ያለመከሰስ መብት አንስቷል።
የምክር ቤቱ አባል ሰዒድ ዓሊ ከማል ያለመከሰስ መብትን የተነሣው በፍትሕ ሚኒስቴር በቀረበ ጥያቄ መሠረት መሆኑን በምክር ቤቱ የሰላም፣ የፍትሕ እና መልካም አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ አስታውቋል።
ቋሚ ኮሚቴው በሚኒስቴሩ የቀረበውን የሙስና ክስ በመመርመር የደረሰበትን ውጤት ለምክር ቤቱ ዝርዝር ሪፖርት አቅርቧል።
ምክር ቤቱ የቀረበው ሪፖርትን በመመልክት አባሉ በተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል በሕግ እንዲጠየቁ ለማድረግ ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ በሙሉ ድምፅ መወሰኑን የከተማ አስተዳደሩ ኮምዩኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመለክታል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት እያካሄደ በሚገኘው መደበኛ ጉባዔው ላይ የአሥተዳደሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የተገኙ ሲሆን፤ ከምክር ቤት አባላት ለሚነሱላቸው አስተያየትና ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያዎችን እንደሚሰጡ ተመላክቷል፡፡
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ከአዲስ አበባ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ የመጓዝ ላይ የነበረ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተሳፋሪ አየር ላይ ሕይወቱ ማለፉ ተሰማ
ሕዳር 10/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ባሳለፍነው አርብ ሕዳር 6 ቀን 2017 ከአዲስ አበባ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ፣ በበረራ ቁጥር ET 500፣ በኤርባስ ኤ350 አውሮፕላን ተሳፋሮ በመጓዝ ላይ የነበረ፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አንድ መንገደኛ አየር ላይ እንዳለ ባጋጠመው ድንገተኛ ህመም ሕይወቱ ማለፉ ተሰምቷል።
እድሜው ከ45 እስከ 50 ዓመት የሚገመተው አቶ ወንደሰን መኮንን፤ ከእህቱ አጠገብ አብሮ ቁጭ ብሎ በመብረር ላይ እያለ ባጋጠመው ድንገተኛ ህመም ምክንያት ሕይወቱ ማለፉን መዝናኛ መጽሔት ዋሽንግተን ዲሲ ዘግቧል።
በዚህም አውሮፕላኑ ነዳጅ ሞልቶ እና የበረራ ሰራተኞችን ቀፍሮ ከሮም፣ ጣልያን ተነስቶ ወደ አሜሪካ ጉዞ ከጀመረ ከአንድ ሰዓት በኋላ እህቱ ለበረራ አስተናጋጆች ወንድሟ የመተንፈስ ችግር እንዳጋጠመው የነገረቻቸው ሲሆን፤ የበረራ አስተናጋጆቹም "የሕክምና ባለሙያዎች ካላችሁ ለእርዳታ እንፈልጋችኋለን" ብለዉ ጥሪ ማቅረባቸው ተነግሯል።
በበረራው ዉስጥ የነበሩ ወደ 5 የሚጠጉ የሕክምና ባለሙያዎች ወደ ግለሰቡ መጥተው ሕይወቱን ለማትረፍ ተረባርበው የመጀመሪያ የሕክምና እርዳታ ቢሰጡትም ግለሰቡ አየር ላይ ሕይወቱ ሊያልፍ መቻሉን በበረራ ላይ የነበሩ ተሳፋሪዎች ለመዝናኛ ሚዲያው አስታውቀዋል።
የአቶ ወንደሰን መኮንን ፀሎተ ፍትሀት ነገ ሕዳር 11 ቀን 2017 ዓ.ም. ቨርጂኒያ በሚገኘው ደብረ ኀይል ቅዱስ ራጉኤል ካቴድራል የሚከናወን ሲሆን፤ የቀብር ሥነስርአቱም በማግስቱ ሕዳር 12 በበፌርፋክስ ሚሞሪያል ፓርክ እንደሚፈጸም ታውቋል።
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
የነዳጅ ማስተካከያ ባለመደረጉ በሁለት ወራት ብቻ 35 ቢሊዮን ብር እዳ መምጣቱ ተገለጸ
👉የጎረቤት ሀገራትን በነዳጅ ለመቀለብ የተዘጋጁ ማደያዎች መኖራቸውን ተገልጿል
ሕዳር 9/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የነዳጅ ግብይትን እና የነዳጅ ማደያዎችን ተደራሽነት ሕጋዊነት ለማረጋገጥ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር እንዲሁም የነዳጅ እና ኢነርጅ ባለስልጣን ርብርብ ማድረግ እንደሚገባቸው ተመላክቷል፡፡
ይህ የተገለጸው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንግድ እና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፤ የነዳጅ ውጤቶችን የግብይት ሥርዓት ለመደንገግ የወጣ ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ ከአስረጂዎች ጋር በተወያየበት መድረክ ላይ ነው፡፡
በመድረኩም የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በተደረገ ክትትል የጎረቤት ሀገራትን በነዳጅ ለመቀለብ የተዘጋጁ ማደያዎች መኖራቸውን የገለጹ ሲሆን፤ "በሁለት ወራት ብቻ የነዳጅ ማስተካከያ ባለመደረጉ 35 ቢሊዮን ብር እዳ ሊመጣ እንደቻለ" ተናግረዋል፡፡
አክለውም "አሁናዊ የነዳጅ አቅርቦት፣ ስርጭት እና አጠቃቀም ላይ ብክነት ስላለ እና ችግሩን ለመፍታት ረቂቅ አዋጁ የማይተካ ሚና አለው" ብለዋል፡፡
በተጨማሪም 'የዋጋ ማስተካከያ ይደረጋል በሚል እሳቤ' ነዳጅ እያለ 'ነዳጅ የለም' ብለው የሚዘጉ ማደያዎች መኖራቸውን የገለጹት ሚኒስትሩ፤ ረቂቁ በአስመጭዎች፣ አከፋፋይ እና ማደያዎች ላይ ሕጋዊ ስርዓት ለመዘርጋት አስፈላጊ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
ቀደም ሲል የነበረው አዋጅ 838/2006 ላይ የቁጥጥር ክፍተት እንደነበረበት የገለጹት በምክር ቤቱ የንግድ እና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ አሻ ያህያ፤ የረቂቅ አዋጁ መውጣት ብክነትን እና አጠቃላይ በነዳጅ ዘርፉ ለይ የሚታየውን ችግር ለመቅረፍ ድርሻው ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ አቶ አስቻለ አላምሬ በበኩላቸው፤ ነዳጅን ከአስመጭው እስከ ተጠቃሚው ድረስ ዘመናዊ እና በቴክኖሎጂ የታገዘ እንዲሆን ለማድረግ ረቂቅ አዋጁ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው አብራርተዋል፡፡
የነዳጅ እና ኢነርጅ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰሀርላ አብዱላሂ በበኩላቸው፣ እየተስፋፋ የመጣውን የኮንትሮባንድ ተጋላጭነት ለመቀነስ እና ነዳጅን ለተጠቃሚዎች ለማድረስ ረቂቅ አዋጁ አስፈላጊ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
አክለውም፤ በቋሚ ኮሚቴው ተነስተው መቀነስ እና መጨመር ያሉባቸውን አስተያየቶች በግብዓትነት እንደሚወስዱ መግለጻቸውን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
"ተጨባጭ በቂ ምክንያት ያቀረበ ፓርቲ ቀጣይ 7ኛ ዙር ምርጫ እንዲራዘምለት ቢጠይቅ ምርመራ አካሂዳለው" የሕገ-መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ
ሕዳር 9/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ተጨባጭ በቂ ምክንያት የሚያቀርብ አካል ካለ ጉባኤው ነፃ እና ገለልተኛ ሆኖ ምርመራ እንደሚያደርግ፤ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ-መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ለአሐዱ ገልጿል፡፡
ምርጫ ቦርድ ነሀሴ 23 ቀን 2012 ዓ.ም ሊያካሂደው ቀን ቆርጦለት የነበረው 6ተኛው ሀገራዊ ምርጫ “ምርጫ 2012” በአለም ዓቀፍ ደረጃ በተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት፤ "ለምርጫው አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረግ እንደማይችል" በመግለፅ ተራዝሞ እንደነበር ይታወቃል፡፡
በኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት መሰረት ምርጫ በየአምስት ዓመቱ የሚካሄድ ሲሆን፤ 6ተኛው ሀገራዊ ምርጫ መካሄድ ካለበት ጊዜ ሲያልፍ፣ የመንግሥትም ሆነ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እድሜ ያበቃል ማለት ነው፡፡
ይህን የሚደነግገው የሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ በ“ሕገ-መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ” እንዲተረጎም በመንግሥት አቅራቢነት በተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ ትርጉም ተሰጥቶበት የነበረ ሲሆን፤ በዚህም መሰረት ምርጫው እንዲራዘም መደረጉ የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው፡፡
ይህንን በሚመለከት አሐዱም ከአጣሪ ጉባኤው ዋና ዳይሬክተር ደሳለኝ ወዬሳ ጋር በነበረው ቆይታ፤ "ባለፈው ግዜ መንግሥት ጠይቆ ሕገ-መንግሥቱ እንደተተረጎመ ሁሉ ሌላ የፖለቲካ ፓርቲ መጥቶ 'ምርጫ ይራዘምልኝ' የሚል ጥያቄ ቢያቀርብ የማራዘም ቁርጠኝነት አላቹ ወይ?" ሲል ጠይቋል፡፡
የጉባኤው ዋና ዳይሬክተርም፤ "ተጨባጭ በቂ ምክንያት ያቀረበ ፓርቲ ቀጣይ ምርጫ እንዲራዘምለት ቢጠይቅ ምርመራ እናካሂዳለን" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
ጉባኤውን ለመጠናከር በ2005 ዓ.ም በወጣው አዋጅ ቁጥር 789 /2005 አንቀፅ 3 መሰረት፤ "ጉባኤው ማንኛውም ሕግ ልማዳዊ አሰራር ወይም የመንግሥት አካል ውሳኔ ከሕገ-መንግሥቱ ጋር ይቃረናል የሚል ቅራኔ በፅሁፍ ሲቀርብለት ያጣራል" ይላል፡፡
ለመሆኑ በ2012 ዓ.ም በኮቪድ እና በመሳሰሉ ጉዳዮች እንዲራዘም የተደረገው 6ተኛው ሀገራዊ ምርጫ በስልጣን ላይ ያለውን መንግሥት በሚፈልገው መንገድ ነው የተረጎመው? ወይንስ በትክክል ሕገ-መንግሥታዊ አግባብነትን ተከትሎ ነው የተተረጎመው? ስንል ጠይቀናል፡፡
የሕገ-መንግሥቱ ትርጉም ሥራ አንዱ ክፍተቶችን የመሙላት መሆኑን ያነሱት ዋና ዳይሬክተሩ፤ "እንደዚህ ዓይነት ችግር ሲፈጠር ጉባኤው እየሞላ ይሄዳል" ሲሉም ተናግረዋል፡፡
በአንድ ጉዳይ ላይ የሕገ-መንግሥት ትርጉም ውሳኔ ከተሰጠበት ተመሳሳይ ከሆነ ተግባራዊ ይደራጋል እንጂ፤ በድጋሚ የሚታይበት አግባብ የለም" ብለዋል፡፡
በሕገ-መንግሥት ትርጉም የተራዘመው 6ተኛው ሀገራዊ ብሔራዊ ምርጫ 2013 ዓ.ም ከትግራይ ክልል ውጪ ባሉ የሀገሪቱ ክፍሎች መካሄዱ የሚታወስ ነው፡፡
በአቤል ደጀኔ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
በአዲስ አበባ የመምህራን ሆስፒታል እየተገነባ መሆኑን ተሰማ
ሕዳር 9/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ መምህራን ለከተማ መስተዳድሩ ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት፤ ለመምህራን አገልግሎት የሚውል ሆስፒታል ግንባታ ፕሮጀክት መጀመሩን የአዲስ አበባ መምህራን ማሕበር አስታውቋል።
ፕሮጀክቱ ለመምህራን ልዩ ድጋፍ ለማድረግ ያለመ ሲሆን፤ ሆስፒታልን ጨምሮ ለንግድ ሥራ የሚውል ሁለገብ ሕንፃ በግንባታ ላይ መሆኑን የማሕበሩ የኮሙኒኬሽን ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ሙሴ ለአሐዱ ተናግረዋል።
በአዲስ አበባ ይገነባል የተባለውን የመምህራን ሁለገብ ሕንፃ ኡራኤል አካባቢ የሚገነባ ሲሆን፤ ከአዲስአበባ ከተማ መስተዳድር 50 ሚልየን ብር ድጋፍ እንደተደረገለት አቶ ሳሙኤል ሙሴ ገልጸዋል።
ሕንፃው በ36 ሺሕ ካሬ ሜትር መሬት ላይ ያረፈ ስለመሆኑም ተናግረዋል።
የመምህራን ሆስፒታሉ ማስገንብያ መዋእለ ንዋይ ከህብረተሰቡና ከደጋፊ ተቋማት ለማሰባሰብ ውጥን የተያዘለት መሆኑን አሐዱ ከኮሙኒኬሽን ኃላፊው መረዳት ችሏል።
ለመምህራን የቤት ግንባታ አበዳሪ የፋይናንስ ተቋምና አነስተኛ ወለድ የሚያገኙበት ባንክ በማፈላለግ ላይ መሆኑንም ማሕበሩ ገልጿል።
ከመምህራን የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመፍታት ማሕበሩ በብርቱ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን የገለጹት የኮሚኬሽን ኃላፊው፤ ከዚህ በተጨማሪም የመምህራን ባንክ ለማቋቋም ውጥን መያዙንም አንስተዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ መምህራን ማሕበር በሥሩ ወደ 33 ሺሕ የሚጠጉ አባላት ያለው መሆኑንና፤ በየጊዜው ከመምህራን የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመፍታት እየሰራ መሆኑን የኮሙኒኬሽን ኃላፊው ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ተቋቁመው ሥራ ላይ ከሚገኙ የሙያ ማሕበራት መካከል የአዲስ አበባ ከተማ መምህራን ማሕበር ግንባር ቀደሙ ተጠቃሽ መሆኑን ይታወቃል።
በአማኑዔል ክንደያ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
የከባድ ተሽከርካሪዎች የክብደት መጠን ለመወሰን የወጣው ደንብ በዘርፉ በተሰማሩ የግል አገልግሎት ሰጪዎች ቅሬታ ተነሳበት
ሕዳር 9/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የተሽከርካሪዎች ክብደትና መጠን ለመወሰንና ለመቆጣጠር ደንብ ቁጥር 491/2014 የሚኒስትሮች ምክር ቤት ማጽደቁ ይታወቃል።
ይህን ደንብ ተፈጻሚ ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት የተደረገ ሲሆን፤ በደንቡ መሰረት ከባድ አሽከርካሪዎች ከ350 ቶን በላይ እንዳይጭኑ ይከለክላል።
የትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ሚኒስቴር ተሽከርካሪዎች ከፍተኛ ጭነት ወይንም ከተፈቀደው ልክ በላይ ሲጭኑ ከፍተኛ የነዳጅ ፍጆታ፣ የድልድይ መደርመስና የመንገድ መሰንጠቅን እየፈጠረ መሆኑን አንስቷል። ይህንን ለመከላከል ደንብ ወደ ማሻሻል ሥራ ተገብቷል።
አሐዱም የትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ሚኒስቴር ያሻሻለው እና ተግባር ላይ ያዋለውን ደንብ በተመለከተ የተለያዩ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ የአሽከርካሪ ባለንብረቶችን አነጋግሯል።
"ደንብ መውጣቱን አንቃወምም" የሚሉት የኢርባ በቀለ የግል ትራንስፖርት ድርጅት መስራች የሆኑት አቶ ኢርባ በቀለ፤ ከዚህ ቀደም 400 ቶን ይጭኑ የነበሩ ተሸከርካሪዎች አሁን 350 ቶን ብቻ እንዲጭኑ ማስገደዱ አሁን ካላው የዋጋ ንረት ጋር የማይጣጣም መሆኑን ገልጸዋል።
አሁናዊ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ዋጋ ጭማሪ እንዲሁም ከውጭ የሚገቡ ምርቶች ዋጋ መናር ታሳቢ መደረግ አለበት ብለዋል። ይሄም ችግሩ ዞሮ ማህበረሰቡ ላይ የዋጋ ጭማሪን እንደሚያመጣ አንስተዋል።
ይህንኑ ሃሳብ የሚጋሩት የጌት አስ ኢንተርናሽናል ሃላፊነቱ የተወሰነ የትራንስፖር ድርጅት ተወካይ አቶ ሐሰን "ሥራ እንድንሰራበት የተሰጠን ሊብሬ 380 የሚል ተቀምጦበት 350 ቶን ጫኑ የሚል መመሪያ ማውጣት እርስ በእርሱ የሚጋጭ ነው" ብለዋል።
ለዚህም በአንድ ዘመን የገቡ ተመሳሳይ የመጫን አቅም ያላቸው ተሽከርካሪዎች የተለያየ የመጫኛ ሊብሬ እንዳላቸው ጠቁመዋል።
"አዋጁ በ2014 ላይ የተሻሻለ ሆኖ ሳለ ለማስፈጸም እጅግ ዘግይቷል" የሚሉት ደግሞ የፈጣን ሎጂስቲክስ እና ትሬዲንግ አክሲዮን ማኅበር ማኔጂንግ ዳይሬክተር መርሻ ጸጋዬ ሲሆኑ፤ እርሳቸውም ቀደም ብሎ ተጀምሮ እየተሰራበት ቢመጣ የተሻለ ይሆን እንደነበር አንስተዋል።
የአሽከርካሪ ባለንብረቶቹ፤ የወጣው ደንብ በአንዴ መቀየሩ እና በአሽከርካሪዎች ዘንድ አለመታወቁ እንዲሁም፤ የተለያየ ሊብሬ መስጠቱ አሁን ካለው ሁኔታ አንጻር 350 ቶን መጫን አዋጭ አለመሆኑን ለአሐዱ ገልጸዋል።
የትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር አለሙ ስሜ ለአሐዱ በሰጡት ምላሽ፤ "ደንቦች ከመውጣታቸው በፊት ረቂቅ ሳለ ማስተካከያ ሊደረግበት ይችላል ከጸደቀ በኃላ ግን የወጣው ደንብ ተፈጻሚ ይሆናል" ሲሉ ገልጸዋል።
አክለውም፤ "ከግል አሽከርካሪ ባለንብረቶች ለተነሳው የተለያየ የሊብሬ የክብደት መጠን ቅሬታ በጊዜ ሂደት ሊብሬ ላይ ያለውን መጠን የሚስተካከል ይሆናል" ብለዋል።
በተመሳሳይም የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ በበኩሉ፤ ለሚበላሹ መንገዶች ባለፈው ሦስት ዓመት ብቻ ከ1 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ መደረጉን አስታውሶ፤ ተሽከርካሪዎች የተፈቀደላቸውን ብቻ መጫን እንዳለባቸው አሳስቧል።
በፍርቱና ወልደአብ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ለጨረታ ቀርቦ 2 ሺሕ 400 ዶላር የተሸጠው የአትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ ማልያ ፌዴሬሽኑን ለማጠናከር እንደሚውል ተገለጸ
ሕዳር 9/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ለጨረታ ቀረቦ 2 ሺሕ 400 ዶላር ያወጣው የአትሌት ሻለቃ የኃይሌ ገብረሥላሴ ማልያ የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንን ለማጠናከር እንደሚውል ተገልጿል።
የታላቁ ሩጫ ባዘጋጀው የእራት ግብዣ ፕሮግራም ላይ የሻለቃ ኃይሌ ገ/ሥላሴ የሮጠበት ማልያ፤ በእንግሊዛዊ ተጋባዥ እንግዳ 2 ሺሕ 400 ዶላር ማሸነፉ ተነግሯል።
በዝግጅቱ ላይ የተገኘው ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ታዳጊዎችን ለማፍራት እየስራ ያለውን ሥራ በማድነቅ፤ በጨረታ የተሸጠው ማልያ የአትሌቲክስ ስፖርትን ለማነቃቃትና ለሚሰሩ ማዘውተርያ ስፍራዎች እንደሚውል ገልጿል።
ኃይሌ በሩጫው መስክ የአገሩን ገጽታ በታላላቅ የዓለም መድረኮች ላይ ከማስተዋወቁ ባሻገር በተለያዩ የኢንቨሰትመንት መስኮች ውጤታማ መሆኑን የገለጹት የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አትሌት መልካሙ ተገኝ፤ ፌዴሬሽኑን ለማጠናከር ላደረገው ጠቃሚ ተግባር ምስጋና አቅርበዋል።
ፌዴሬሽኑ አትሌቲክሱን ለማሳደግ ከሞሓ ለስላሳ መጠጦች፣ ከጆርካ ኢቨንትና ከጎፈሬ የትጥቅ አምራች ጋር ስፖንሰር ሽፕ ስምምነት መፈራረሙን ያስታወሱት አትሌት መልካሙ፤ ውጤታማ የአትሌቲክስ ውድድሮችን ለማካሄድ እና የማዘውተሪያ ስፍራ ለማስፋፋት የሚሰራው ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መግለጻቸውን ከአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በተጨማሪም በስፖርት ታሪክ በማስታወሻነት የተቀመጡ ማልያዎች፣ ሜዳልያዎች እና ልዩ ልዩ ቁሳቁሶች ለጨረታ በማዋል ስፓርቱን ለማጠናከር በጋራ እንዲሰሩ ፌዴሬሽኑ ጥሪ አቅርቧል።
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
"የጋራ ምክር ቤቱ አያስፈልግም የሚል ፖርቲ መውጣት ይችላል" የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት
ሕዳር 9/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ቅዳሜ እና እሁድ (ሕዳር 7- 8 ቀን 2017 ዓ.ም) ለሁለት ቀናት ሲያካሂድ የነበረውን ጠቅላላ ጉባኤ፤ የምክር ቤቱን ሰብሳቢ፣ ምክትል ሰብሳቢ፣ ፀሀፊ እና ሥራ አስፈፃሚ አባላቱን በመምረጥ አጠናቋል።
በዚህ መሰረትም የምክር ቤቱ ሰብሳቢ የነበሩት አቶ ደስታ ዲንቃ ፀሀፊ ሲሆኑ፤ የከፋ አረጓዴ ፓርቲ ዋና ሊቀመንበር ሰለሞን አየለ የምክር ቤቱ ሰብሳቢ ሆነዋል። በተጨማሪም በምክትል ሰብሳቢነት የነፃነትና እኩልነት ፓርቲ ሊቀመንበር ዶክተር አብዱልቃድር አደም ተመርጠዋል።
ከዚህ ውጪ በፊት አምስት የነበረውን የሥራ አስፈፃሚ ወደ ሰባት በማሳደግ፤ ሰባት የምክር ቤቱ ሥራ አስፈፃሚ አባላትም በጠቅላላ ጉባኤው ተመርጠዋል።
ከአሐዱ ጋር ቆይታ የነበራቸው የቀድሞ ዋና ሰብሳቢ የአሁኑ ፀሀፊ የሆኑት አቶ ደስታ ዲንቃ፤ በጠቅላላ ጉባኤው ለሁለት ዓመት ሲንከባለል የነበረ መተዳደሪያ ደንብ መኖሩን ያነሱ ሲሆን፤ ይህ መተዳደሪያ ደንብ በጉባዔው መፅደቁን ተናግረዋል።
ከቀናት በፊት ስድስት የሚጠጉ ፓርቲዎች የኢትዮጵያ የፓለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ያደረገውን ጠቅላላ ጉባኤ እንዲሁም፤ ሰብሳቢ፣ ምክትል ሰብሳቢ እና ሥራ አስፈፃሚ መረጣውን መቃወማቸውን አሐዱ መዘገቡ ይታወሳል።
አሐዱ 'አንሳተፍም' ያሉና ራሳቸዉን ያገለሉ ፓርቲዎች ቀጣይ ሁኔታን አስመልክቶ አቶ ደስታ ዲንቃን ጠይቋል።
አዲሱ የምክር ቤቱ ፀሀፊ ሲመልሱም፤ "በመተዳደሪያ ደንብና ስርዓት መሄድ ተገቢ ነው። ማኩረፍ ተገቢ አይደለም" ብለዋል።
"በግዜው ይደረጋል ተብሎ የተደረገ ነገር ብዙም ነገር የለም። ይህንን እንደ ምክንያት ማቅረብ ተገቢ አይደለም" ሲሉም አክለዋል።
"የጋራ ምክር ቤቱን እንደ ትምህርት ቤት ማየት አለብን" ያሉት ፀሀፊው፤ "ይህ ውሃ የማያነሳ ተቃውሞ ነው" በማለት የፓርቲዎቹን ጥያቄ አጣጥለውታል።
ሆደ ሰፊ እና መቻቻልን የሚጠይቁ ጉዳዮች መኖራቸዉንም በማንሳት፤ "ምክር ቤቱ አያስፈልግም የሚል ካለ ደግሞ መውጣት ነው የሚሻለው" ሲሉም ከአሐዱ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓን) ጨምሮ ስድስት የሚሆኑ ፓርቲዎች "ሕገወጥ" ያሉትን የጋራ ምክር ቤት ጠቅላላ ጉባኤ እንደማይሳተፉ መግለፃቸውን መዘገባችን ይታወሳል።
የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት፤ በተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና በመንግሥት መካከል ጠንካራ ግንኙነት ለመፍጠር በመጋቢት ወር 2011 ዓ.ም የተቋቋመ ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት ገዢው ብልጽግና ፓርቲን ጨምሮ 59 አባል ፓርቲዎችን በውስጡ ይዟል።
በአቤል ደጀኔ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
#ADVERTISMENT
#AmharaBank
የአማራ ባንክ አ/ማ የባለአክሲዮኖች 3ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ማክሰኞ ታህሳስ 01 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ በሚሊኒየም አዳራሽ ስለሚካሄድ ባለአክሲዮኖች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጉባዔው እንድትገኙ ጥሪ እናስተላልፋለን፡፡
የጉባዔው አጀንዳዎችን እና ተጨማሪ መረጃዎችን ጥቅምት 06 ቀን 2017 ዓ.ም በወጡት አዲስ ዘመን እና ሪፖርተር አማርኛ እትም ጋዜጦች ላይ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ለበለጠ መረጃ ነፃ የጥሪ ማዕከል 690 ወይም
የባንኩን ድረ ገጽ www.amharabank.com.et ይጎብኙ፡፡
አማራ ባንክ
ከባንክ ባሻገር!
የአማራ ባንክ ትክክለኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾች
Website: www.amharabank.com
Facebook: www.Facebook.com/amharabanksc1
Telegram: /channel/Amhara_Banksc
Instagram: https://instagram.com/amhara_bank
Twitter: https://twitter.com/Amharabanksc
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/amharabank/
YouTube: https://youtube.com/channel/UC73x9uuGYV0Uxw0EkpVZN8g
TikTok: amharabanks.c" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@amharabanks.c
#አማራባንክ #AmharaBank
ቢሮው ያለአግባብ ዋጋ የሚጨምሩ ነጋዴዎችን ለመቆጣጠር የምርቶችን ዋጋ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ይፋ እያደረገ መሆኑን አስታወቀ
ሕዳር 7/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ "የቅዳሜና እሁድ ገበያዎች እንዲሁም የንግድ ማዕከላት የምርቶች ዋጋ ተመንን አላወጣም" በሚል የተጋነነ ዋጋ ጨምረው የሚሸጡ ነጋዴዎችን ለመቆጣጠር፤ በየማዕከላቱ የሚሸጡ ምርቶችን የዋጋ ተመን በየሳምንቱ ይፋ እንደሚያደርግ ገልጿል።
የቢሮው የገበያዎች ጥናት እና ማስታወቂያ ዳይሬክተር ሙሰማ ጀማል ለአሐዱ እንደገለጹት፤ በሳምንት ሦስት ቀናት በዋና የገበያ ስፍራዎች የምርቶችን ዋጋ ቅኝት በማድረግ በየሳምንቱ አርብ ከሰዓት በተቋሙ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ላይ የምርቶችን የዋጋ ተመን ይገለጻል፡፡
"ይሄ አሰራር ማህበረሰቡ አስቀድሞ የምርቶቹን ዋጋ ስለሚያቃቸው በሕገወጥ ነጋዴዎች እንዳይጭበረበር ያደርገዋል" ብለዋል፡፡
አክለውም፤ ምርቶች እንደ ጥራታቸው የዋጋ ልዩነት እንዳላቸው አንስተው፤ ሁለተኛ ደረጃውን "አንደኛ ነው" እያሉ የሚሸጡ ነጋዴዎች መኖራቸውንም ተናግረዋል፡፡
በዚህ ረገድ ቢሮው አሰራሩ ከተጀመረ በኃላ ባልተገቡ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ በመወሰድ ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
260 በሚሆኑ ባለሙያዎች በገበያ ስፍራዎች የክትትልና የድጋፍ ሥራዎችን በሁለቱም ቀናት እንደሚሰጡ የተገለጸ ሲሆን፤ በአዲስ አበባ 193 የሚደርሱ የቅዳሜና እሁድ ገበያዎች እንዲሁም 4 የገበያ ማዕከላት መኖራቸውንም አንስተዋል።
በዚህም መሰረት ንግድ ቢሮው፤ በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የግብርና ምርቶች መሸጫ ከሕዳር 7 እስከ 13/2017 ዓ.ም እንዲሁም በዕሁድ ገበያዎች ዛሬ ሕዳር 7 እና ነገ 8/2017 ዓ.ም የሚቀርቡ የአትክልት፣ የፍራፍሬ፣ የሰብል ምርቶች እና የፋብሪካ ምርት ውጤቶች የመሸጫ ዋጋ መረጃ ይፋ አድርጓል፡፡
👉የመሸጫ ዋጋ ዝርዝሩ ከላይ ተያይዟል!
በፍርቱና ወልደአብ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
በአዲስ አበባ የሚያስተምሩ መምህራን ወቅታዊ የኑሮ ሁኔታ ከአቅም በላይ እንደሆነባቸው ተገለጸ
ሕዳር 7/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ለመምህራን ይደረጋል የተባለውን የኑሮ ድጎማና የቤት አቅርቦት የውሃ ሽታ ሆኖል ሲል የአዲስ አበባ መምህራን ማህበር ተናግሯል።
ለመምህራን ይደረጋል የተባለውን ልዮ ጥቅማ ጥቅምን ጨምሮ፤ ቃል የተገባው የቤት አቅርቦት ተግባራዊ እንዲሆን ማህበሩ ጠይቋል።
ሀሳቡ የተነሳው ለሁለት ተከታታይ ቀናት ተከናውኖ በትናንትናው ዕለት በተጠናቀቀው፤ የአዲስ አበባ ከተማ መምህራን ማሕበር 37ኛ መደበኛ የምክር ቤት ጉባኤ ላይ ነው።
የማህበሩ የኮሙኒኬሽን ኃላፊ ሳሙኤል ሙሴ በጠቅላላ ጉባኤው በርካታ ጥያቄዎች እንደተነሱ ገልጸው፤ የኑሮ ውድነቱን ጨምሮ የቤትና ጥቅማ ጥቅሞች ጉዳይ በስፋት መነሳታቸውን ለአሐዱ ተናግረዋል።
አክለውም በአዲስ አበባ ያለውን የኑሮ ጫና በመምህራ ላይ እየበረታ መምጣቱን የገለጹ ሲሆን፤ ይህም በመማር ማስተማር ስርዓቱ ላይ ጫና እያሳደረ መምጣቱን ተናግረዋል።
የመምህራን ማሕበር ከዚህ ቀደም ያነሳቸው ጥያቄዎች መልስ እንዳልተሰጠባቸው የተገለጸ ሲሆን፤ የመምህራን ጥያቄ ቸል እየተባለ መሆኑንም ኃላፊው ጨምረው ለአሐዱ ገልጸዋል።
በአዲስ አበባ የሚገኙ መምህራን ህይወት አስቸጋሪ በሚባል ደረጃ ላይ መድረሱን በመጥቀስ፤ መፍትሔ እንዲሰጥበት መጠየቁን ተነግሯል።
የአዲስአበባ መምህራን ማሕበር በመጪዎቹ ጊዜያቶች የማሕበሩ ፕሬዚዳንት ምርጫ የሚያደርግ መሆኑንም ገልጿል።
በዚህ ጉባዔ የማጠቃለያ መድረክ ላይ የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አሊ ከማል እንዲሁም ከከተማ ጀምሮ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ ያሉ የምክር ቤት አባላትና ሌሎች ከማህበሩ ጋር በጋራ የሚሰሩ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈውበታል።
በአማኑዔል ክንደያ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
"ቴክኖሎጂን በመጠቀም በሰዓታት ውስጥ የስኳር በሽታን ማጥፋት ተችሏል በሚል የተሰራጨው መረጃ ከእዉነት የራቀና አሳሳች ነዉ" ጤና ሚኒስቴር
ሕዳር 7/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ከሰሞኑ ቴክኖሎጂን በመጠቀም በሰዓታት ውስጥ የስኳር በሽታን ማጥፋት ተችሏል በሚል እየተሰራጨ የሚገኘው መረጃ ከእዉነት የራቀና አሳሳች ነዉ ሲል ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
ሚኒስቴሩ በተለያዩ የማህበራዊ መገናኛዎች የስኳር ሕመምን ጨምሮ ሃሰተኛ የጤና መረጃዎች ኃላፊነት በጎደላቸው አካላት እየተለቀቁ እንደሚገኝ ገልጿል።
አክሎም የሕክምና ሙያ ሳይኖራቸውና ለሚሠጡት አገልግሎት ሕጋዊ የሆነ የብቃት ማረጋገጫ ሳይኖራቸው በማህበራዊ ሚዲያ ማህበረሰቡን የሚጎዱ፣ ከእውነት የራቁ ሀሰተኛ መረጃዎችን የሚለቁ አካላት መበራከታቸውን አስታውቋል።
ይህ ተግባር ማህበረሰቡን በእጅጉ እየጎዳና ለአላስፈላጊ ወጪና እንግልት ከመዳረግ አልፎ፤ ፈውስ ፈላጊ ዜጎች ላይ ከፍተኛና የተወሳሰበ የጤና ችግር እየፈጠረ እንደሚገኝም ገልጿል።
ስለሆነም በዚህ መሰል ተግባር ላይ ተሰማርተው የሚገኙ አካላት ይህ ተግባር በሕግ የሚያስጠይቅ መሆኑን ተገንዝበው፤ ከእኩይ ተግባራቸው እንዲታቀቡ ሚኒስቴሩ አሳስቧል፡፡
ማህበረሰቡም ምንጫቸው ካልተረጋገጠ አካላት የሚላኩ መልእክቶችን እንዲመረምር፣ አገልግሎቶችንም ከመጠቀማችን በፊት ጥንቃቄ እንድናደርግ፣ አስፋላጊ ሆኖ ሲገኝም በ"Regulatory.moh@moh.gov.et" ላይ ጥቆማ እንዲሰጥ ተጠይቋል፡፡
ሕዝቡ ሀሰተኛ የጤና መረጃ የሚለቁትን በማጋለጥ፣ የጤና ባለሙያ በማማከር ጤንነቱን እንዲጠብቅም ጤና ሚኒስቴር አሳስቧል።
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
"ባለሙያዎች በተገቢ መልኩ አገልግሎት አለመስጠታቸው ተግዳሮት ሆኖብኛል" ጤና ሚኒስቴር
ሕዳር 10/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ባለሙያዎች በተገቢ መልኩ አገልግሎት አለመስጠት እና የግንዛቤ ማነስ አላስፈላጊ እርግዝና እና ውርጃን መከላከል ላይ ተግዳሮት እንደሆነበት ጤና ሚኒስትር አስታውቋል።
አላስፈላጊ እርግዝና እያደረሰ ያለው የጤና፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች እየጨመረ በመምጣቱ እንዲሁም ተጋላጭ የሆኑ አፍላ ወጣቶች፤ ለደም ግፊትና ማነስ፣ ጊዜውን ላልጠበቀ ምጥ እንዲሁም ለፌስቱላ በሽታ አጋላጭ መሆኑ ይታወቃል፡፡
ይህንን ችግር ለመከላከልና ለመቅረፍ በርካታ ሥራዎች ቢሰሩም፤ ከግንዛቤ እጥረት የተነሳ እንዲሁም የጤና ባለሙያዎች በተገቢ መልኩ አገልግሎት ማለመስጠታቸው ምክንያት የመከላከል ሥራዎች ላይ ተግዳሮቶች እየተፈጠሩ መሆኑን በጤና ሚኒስትር የእናቶች፣ የሕጻናትና የአፍላ ወጣቶች መሪ ሥራ አስፈፃሚ ሰኚ ዱፌራ ለአሐዱ ተናግረዋል።
አክለውም የአፍላ ወጣትነትና አላስፈላጊ እርግዝና ውርጃ ጉዳይ የአንድ አካል ኃላፊነት ሳይሆን የሁሉም ባለድርሻ አካላትና የእያንዳንዱ ሰው የተጠናከረ ተሳትፎን የሚጠይቅ መሆኑን በማንሳት፤ ማህበረሰቡ ግንዛቤ ሊኖረው እንደሚገባ እንዲሁም ባለሙያዎች በተገቢ መልኩ አገልግሎት መስጠት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
ኃላፊው አያይዘውም አፍላ ወጣቶች ለእንደዚህ አይነት ችግሮች ተጋላጭ እንዳይሆኑ በትምህርት ቤቶች አካባቢ ያሉ አዋኪ ድርጊቶች ላይ ቁጥጥር በማድረግ፣ በወጣቶች ስብእና መገንቢያ ማእከላት ላይ የወጣቶች ባህርይ ለውጥ ተግባቦት ላይ ሥራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
በወልደሐዋርያት ዘነበ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ኢትዮጵያ አለም ዓቀፍ ስምምነቶችን ብትፈርምም ተግባራዊ ማድረጉ ላይ አሁንም ብዙ ይቀራታል ሲሉ የሕግ ባለሙያዎች ገለጹ
ሕዳር 10/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ኢትዮጵያ በርካታ አለም ዓቀፍ ስምምነቶችን በተለይም የሰብዓዊ መብት ጥበቃን የተመለከቱ ስምምነቶችን የፈረመች ብትሆንም ስምምነቱን ተግባራዊ ማድረግ ላይ ግን እዚህ ግባ የሚባል እንቅስቃሴ አላደረግችም ሲሉ አሐዱ ያነጋገራቸው የሕግ ባለሙያዎች ገልጸዋል።
የሕግ ባለሙያው ጥጋቡ ደሳለኝ፤ "ስምምነቶችን ለመፈረም ኢትዮጵያ ግንባር ቀደም ሀገር ብትሆንም መሬት ላይ ተፈፃሚ ሲሆኑ አይታዩም" ይላሉ።
ስምምነቶችን ተቀብሎ በፓርላማ ማጽደቅ የሥራ አንድ አካል ተደርጎ ቢመጣም ሰፊ የአፈጻጸም ክፍተት በመኖሩ የዜጎችን ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብት ተግባራዊ ማድረግ እንዳልተቻለ ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ብሎም የዴሞክራሲያዊ ነጻነት ስምምነቶችን በምክር ቤት ጭምር ማፅደቋን የገለጹት ደግሞ የሕግ ባለሙያው ካሳሁን ሙላት ሲሆኑ፤ "በዚህ መልኩ የጸደቁ ስምምነቶች በሕገ መንግሥቱ መሰረት የሀገሪቱ የሕግ አካል ተደርገው የሚታዩ ናቸው" ብለዋል።
ሆኖም ግን "አለም ዓቀፍ ስምምነቶችን ብቻ ሳይሆን በሕገ መንግሥቱ የተካተቱ የሀገር ውስጥ ሕጎችንም ተግባራዊ ማድረግ ላይ ክፍተቶች አሉ" ይላሉ።
አክለውም "የዜጎችን ሰብዓዊ መብት ማስክበር ሃላፊነት የመንግሥት ድርሻ ነው" ያሉ ሲሆን፤ ሕግ ባለመከበሩ ለሚመጡ ችግሮች ኃላፊነቱን መውሰድ ያለበትም መንግሥት መሆኑን አንስተዋል።
አሐዱ ያነጋገራቸው የሕግ ባለሙያዎች ነጻና ገለልተኛ እንዲሁም በሕግ አሰራር የሚያምኑ ጠንካራ ሀገራዊ ተቋማትን መገንባት ያስፈልጋል ብለዋል።
ምክር ቤቶችም ሕግ ሲያወጡ ነጻና ገለልተኛ በመሆን ለሀገርና ለህዝብ የሚጠቅሙ ውሳኔዎችን የማሳለፍና አፈጻጸሙን የመከታተል ኃላፊነት አለባቸው ሲሉ በአጽንዖት ገልጸዋል።
በፍርቱና ወልደአብ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
አብዲራህማን ሞሃመድ አብዲላሂ የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ
ሕዳር 10/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) አብዲራህማን ሞሃመድ አብዲላሂ ሕዳር 4 ቀን 2017 ዓ.ም. የተካሄደውን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በማሸነፍ፤ የራስ ገዟ ሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት በመሆን መመረጣቸውን የሀገሪቱ ምርጫ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
በምርጫ የወቅቱ ገዥ ፓርቲ የሰላም፣ የአንድነትና የእድገት ፓርቲ (ኩልምዬ) በመወከል ፕሬዝዳንት ሙሴ ቤሂ፣ ተፎካካሪ ዋዳኒ ፓርቲን በመወከል አብዲራህማን ሞሀመድ እና የሰላምና ዊል ፌር ፓርቲን በመወከል ደግሞ ፈይሰል አሊ ፕሬዝዳንታዊ እጩ ሆነው መቅረባቸው ይታወቃል።
ይህንም ተከትሎ በተካሄደው ምርጫ የዋዳኒ ፓርቲ እጩ አብዲራህማን ሞሀመድ 63 ነጥብ 92 በመቶ ድምጽ በማግኘት ፤ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሆነው መመረጣቸውን ኮሚሽኑ ይፋ አድርጓል፡፡
የወቅቱ የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴ ቤሂ 34 ነጥብ 81 በመቶ ድምጽ በማግኘት ድል ሳይቀናቸው መቅረቱንም አስታውቋል።
ምርጫው በሶማሊላንድ ዲሞክራሲያዊ ጉዞ ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ መሆኑን የገለጸው የሀገሪቱ ምርጫ ኮሚሽን፤ ሕዝቡ ላሳየው ተሳትፎ ምስጋና አቅርቧል።
በዚህም መሰረት አዲስ የተመረጡት ፕሬዚዳንት በሚቀጥሉት ቀናት ቅድሚያ የሚሰጧቸውን ጉዳዮች ያሳውቃሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ሙስታክባል ሚዲያ ዘግቧል፡፡
በሶማሊላንድ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ከ1 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ መራጮች ተመዝግበው፤ በስድስት ክልሎች በተዘጋጁ 2 ሺሕ 648 የምርጫ ጣቢያዎች ላይ ድምፃቸውን መስጠታቸው መዘገቡ ይታወሳል፡፡
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
#ADVERTISMENT
#ጊፍትሪልስቴት
ታላቅ የምስራች!
**
ጊፍት ሪል ስቴት ከ10% ቅድመ ክፍያ ጀምሮ በ22 ሳይቶቹ ቅንጡ አፓርትመንቶችን እና የንግድ ሱቆችን ለሽያጭ አቅርቧል፡፡
ይህ ሳይት ለአፓርትመንትና ንግድ ሱቆች የሚውሉ G+25 ሶስት መንታ ህንጻዎች ያሉት ሲሆን የዚህ 6ኛ መንደር መለያዎች፡-
•ከባለአንድ እስከ ባለአራት መኝታ ክፍሎች ያሉት፣
•ለመኖሪያም ሆነ ለንግድ ተመራጭ አካባቢ የሆነ፣
•በአንድ ወለል ሶስት ቤቶች ብቻ ያሉት፣
•በእያንዳንዱ ወለል ስድስት አሳንስር ያለው፣
•አራት ቤዝመንት ያሉት በቂ የመኪና ማቆሚያ የተዘጋጀለት፣
•24 ሰዓት የኤሌክትሪክ፣ ኢንተርኔትና ውሃ አቅርቦት አሉት፣
ጊፍት ሪል ስቴት
ማህበረሰብን እንገነባለን!
ለበለጠ መረጃ፡-
Website: https://www.giftbusinessgroup.com
Twitter: https://twitter.com/GIFTBusinessG
YouTube: www.youtube.com/channel/UCcqr7cpVv9ski-F7haxXx4w
Facebook: www.facebook.com/profile.php?id=100090918391017...
Telegram: /channel/giftbusinessgroup
Short Code: 8055
#አሐዱ_አንቀፅ
"ድህነት ለባለፀጎች የሚከፈል ግብር ሆኗል"
ሙሉ ጥንቅሩን ለመከታተል ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👇
https://youtu.be/SQdtHnkqQQs?si=XXZ6rxXAJl4IFdxC
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአለም አራት ኮኮብ አየር መንገድ ደረጃ ሽልማትና ዕውቅና አገኘ
ሕዳር 9/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዓመታዊው አፔክስ የመንገደኞች ምርጫ 2025 (APEX Passenger Choice Awards 2025) የአለም አራት ኮኮብ አየር መንገድ ደረጃ ሽልማትና ዕውቅና ማግኘቱን አስታውቋል።
የአለም አራት ኮኮብ አየር መንገድ ሽልማት ከአንድ ሚሊዮን በላይ ከተረጋገጡ ጉዞዎች ከበረራ በኋላ ከመንገደኞች በተሰጠ ድምፅ መሰረት የተበረከተና በአቪዬሽን ዘርፍ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው አለም አቀፍ ዕውቅና መሆኑ ተመላክቷል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቀናቶች በፊት ሕዳር 6/2017 ዓ.ም የ2024 የቢዝነስ ተጓዦች ሽልማት ውድድርን በማሸነፍ፤ ለአምስተኛ ተከታታይ ዓመት ‘ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ’ በመባል የተሸለመ ሲሆን፤ በተጨማሪም ካርጎና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ለሁለተኛ ተከታታይ ግዜ በ “Arabian Cargo Awards” ምርጥ የአፍሪካ ካርጎ አየር መንገድ ሽልማትን ማግኘቱን አሐዱ መዘገቡ ይታወሳል፡፡
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ኮሚሽኑ አስፈላጊ መሆኑ ከታመነበት በምክክር ሂደቱ ላይ ሦስተኛ ሀገራትን ጣልቃ ሊያስገባ እንደሚችል ገለጸ
ሕዳር 9/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የተሰጠውን የሦስት ዓመት የሥራ ገደብ ሊያጠናቅቅ የወራት እድሜ የቀረው የኢትዮጵያ የሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን፤ በሥራ ክንውኑ ውስጥ ስኬታማ ያደርጋል ተብሎ ከታመነበት ሦስተኛ ሀገራትን ጣልቃ ሊያስገባ እንደሚችል አስታውቋል።
አሐዱ "በምክክር ሂደቱ ላይ ሦስተኛ ሀገራትን ጣልቃ ማስግባት አስፈላጊ ነው ወይ? እናንተ ገለልተኛ ነን ካላችሁ ለምን መታመን አልቻላችሁም?" ሲል የምክክር ኮሚሽኑን ኮሚሽነር ዶክተር ዮናስ አዳዬን ጠይቋል፡፡
ኮሚሽኑሩ በምላሻቸው፤ "ምንም ቢሆንም ችግሩ ከአቅም በላይ ከሆነ የሦስተኛ ሀገራት ጣልቃ ማስገባት የተለመደ ነው" ሲሉ ተናግረዋል፡፡
አክለውም የምክክር ሂደቱ ፈታኝ እንደሆነ ገልጸው፤ ከዚህ ቀደም እንደ ቀይ መስቀል ያሉ የሲቪክ ማህበራት ድርጅቶች እገዛ ተጠይቆ እንደነበር አስታውሰዋል።
እንዲሁም ከዚህ ቀደም 50 የሚደርሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምክክር ሂደቱን መደገፋቸውን ያስታወሱት ዶክተር ዮናስ፤ በተጨማሪም ከ110 ሺሕ ሕዝብ በላይ በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደቱ ላይ ማሳተፍ መቻሉን ገልጸዋል፡፡
ያም ሆኖ ሁሉንም ጫና በመቋቋም በሥም ካልጠቀሷቸው "የታጠቁ አካላት" ጋር ንግግር መጀመራቸውን ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
የሥራ ሂደቱን በተገቢው ጊዜያት ለማጠናቀቅ እንዲቻልም፤ የሲቪክ ማህበራት ድርጅቶችን በማካተት በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በተለያዩ አጋጣሚዎች ገለልተኛ እንዳልሆነ ትችት ሲቀርብበት ቢደመጥም፤ በሕዝብ ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት ማግኘት መቻሉን አስታውቋል፡፡
በደረጄ መንግስቱ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
#አሐዱ_መልህቅ
"ከአሰብ ይልቅ የሃኒሽ ደሴትን ማጣት ያማል"
ጥንቅሩን ለመከታተል ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👇
https://youtu.be/wbN9j0kNHFQ?si=p_CqAZlogwl-TN64
በመርካቶ በትናንትናው ዕለት ለሁለተኛ ግዜ የደረሰው የእሳት ቃጠሎ በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱ ተገለጸ
ሕዳር 9/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በአዲስ አበባ ከተማ መርካቶ አካባቢ በተለምዶ "ድንች በረንዳ" እየተባለ በሚጠራው ቦታ ላይ ትናንት ሕዳር 8 ቀን 2017 ዓ.ም በተከሰተ የእሳት አደጋ፤ በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን የእሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።
ኮሚሽኑ በትናንትናው ዕለት ከቀኑ 6 ሰዓት ከ30 ላይ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ መርካቶ ጃቡላኒ ሕንፃ በተለምዶ "ድንች በረንዳ" እየተባለ በሚጠራው ቦታ ላይ የተነሳውን የእሳት ቃጠሎ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ሥር ማዋል መቻሉን ገልጿል፡፡
በዚህም ኮሚሽኑ ቃጠሎው ሳይዛመትና የከፋ ጉዳት ሳያደርስ አንድ ሰዓት ተኩል በፈጀ ርብርብ መቆጣጠሩን አመልክቷል፡፡
በቅርቡ ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም. ሸማ ተራ ተብሎ ከሚታወቅ ነባር ሕንጻ አካባቢ በተነሳው ከባድ የእሳት አደጋ፤ ከፍተኛ የንብረት ውድመት መከሰቱ ይታወሳል፡፡ የትናንቱ የእሳት አደጋ ያጋጠመበት "ድንች በረንዳ" አካባቢም ከዚህ ብዙም የማይርቅ ስፍራ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
ምንም እንኳ የአደጋው መንስኤው እስካሁን ባይጣራም እሳቱም የተነሳው ተቀጣጥለው ከተሰሩ ሱቆች መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ የእሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ንጋቱ ማሞ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።
“እሳቱ የተነሳው ቆርቆሮ በቆርቆሮ ሆነው ተቀጣጥለው ከተሰሩ የንግድ ሱቆች ነው” ያሉት አቶ ንጋቱ፤ እሳቱ የተነሳበት ስፍራ በብዛት ስኒከር ጫማዎች የሚሸጡበት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ኃላፊው አክለውም እሳቱ እንደተነሳ አብዛኘውን እቃ በማውጣት ከቃጠሎ ማትረፍ መቻሉንም አስረድተዋል፡፡
የትናንቱ አደጋ አጋላጭነቱ ከዚህ በፊት በአከባቢው ከተነሳው ከባድ የእሳት አደጋ ሊከፋ የሚችልበት እድል እንደነበርም አስረድተው፤ ነገር ግን እሁድ በመሆኑ አካባቢው ክፍት በመሆኑ እና በተደረገው ርብርብ እሳቱን መቆጣጠር መቻሉን ገልጸዋል፡፡
የእሳት አደጋውን ለመቆጣጠር ወደ 18 የእሳት አደጋ ተሸከርካሪ ቦቴዎች ከ122 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ጋር መሰማራታቸውንም አክለው ተናግረዋል፡፡
በእሳት አደጋው ስድስት ሰዎች ላይ ቀላል አደጋ ደርሶባቸው ሕክምና ማግኘታቸው የተገለጸ ሲሆን፤ ሁለቱ በዚያው በአምቡላንስ ውስጥ ሲታከሙ አራቱ ደግሞ የቆርቆሮ መቁረጥ አደጋ እንደደረሰባቸው ተነግሯል፡፡
በተጨማሪም በንብረት ላይ ደግሞ ከፍ ያለ ጉዳት መድረሱን አቶ ንጋቱ መናገራቸውን ዘገባው አመላክቷል።
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
የመንግሥት ትምህርት ቤቶች ለማካካሻ ትምህርት በአስገዳጅነት ክፍያ መጠየቃቸዉ ተገቢ አደለም ሲሉ ወላጆች ቅሬታ አቀረቡ
ሕዳር 9/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በአዲስ አበባ ጎሮ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ለማካካሻ ትምህርት በግድ ለእያንዳንዱ ተማሪ 300 ብር ክፈሉ እየተባሉ መሆኑ ቅር እንዳሰኛቸው ወላጆች ለአሐዱ ተናግረዋል።
ወላጆች እንደገለጹት ተማሪዎች ከመደበኛዉ ትምህርት ውጭ ቅዳሜ በማካካሻ ትምህርት እንዲማሩ የታሰበ ቢሆንም፤ ካለዉ የኑሮ ውድነት ጋር ተመጣጣኝ ባለመሆኑና በግዴታ ክፈሉ በመባላቸው ምክንያት ተማሪዎች በነጻነት እንዳይማሩ እያደረጋቸዉ መሆኑን አንስተዋል።
ይሁን እንጂ ጎሮ ትምህርት ቤት ከመዋዕለ ሕጻናት እስከ 8ኛ ክፍል የትምህርት አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ አንስተዉ፤ ለእያንድንዱ ተማሪ 300 ብር የግድ ክፈሉ እየተባሉ መሆኑን ገልጸዋል።
እንዲሁም አንድ ወላጅ 3 ተማሪዎችን የሚያስተምር ከሆነ ግዴታ ለሁሉም በነፍስ ወከፍ እንዲከፍሉ እየተገደዱ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በዚህም ምክንያት ክፍያ የመክፈል አቅም የሌላቸዉ ወላጆች፤ ልጆቻቸዉን ወደ ትምህርት ቤት ለመላክ መቸገራቸውን ነግረዉናል፡፡
ይህንን ችግር በተመለከተ አሐዱ የጎሮ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አቶ ኦላና ተሰማን አነግግሯል። በምላሻቸዉም "ማንኛዉንም ወላጅና ተማሪ በግድ ክፈሉ የተባ የለም" ብለዋል።
"ይሁን እንጂ ክፍያ የተባለዉን በተመለከተ ለተማሪዎች ማጠናከሪያ በሚል ከላይ የወረደ መመሪያ ስላለ በተለይ 6ኛ እና 8ኛ ክፍል የእነሱን ውጤት ለማሻሻል ሲባል ቅዳሜ እንዲማሩ የተደረገበት ሁኔታ አለ" ብለዋል።
"እንደ አጠቃላይ የተማሪዎችን ዉጤት ለማሻሻል ከወላጆች፣ ከመምህራን እና ከሚመለከተዉ አካል በጋራ በመሆን በስምምነት የተደረገ እንጂ፤ በግድ ክፈሉ የሚባል ነገር የለም" ሲሉም ለአሐዱ ገልጸዋል።
በማንኛዉም የመንግሥት ትምህርት ቤት የመክፈል አቅም የሌላቸዉን ተማሪዎች እንዲማሩ ማድረግ እንጂ፤ ከአቅም በላይና በግዳጅ እንዲከፍሉ መደረጉ ተገቢነት የሌለዉ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በአለምነው ሹሙ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
#አሐዱ_አብይ_ጉዳይ
ጥንቅሩን ለመከታተል ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👇
https://youtu.be/p8haUrt9HRQ?si=IwgR5874bU4qHy6B
#አሐዱ_መድረክ
"ሕገ-መንግሥቱን የመተርጎም እንጂ የመሻሻል ስልጣን የለንም" ከሕገ-መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ዋና ዳይሬክተር ደሳለኝ ወዬሳ ጋር የተደረገ ቆይታ (ክፍል 1)
ቆይታውን ለመከታተል ከሥር ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ!
👇
https://youtu.be/_d9b5EF97ds?si=Aqyz0Jrbaitsrg3S
"የፓለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የሚያካሂደዉ ጉባኤ ሕገ-ወጥ በመሆኑ አንሳተፍም" ሲሉ 6 ፓርቲዎች ገለጹ
ሕዳር 7/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ)ን ጨምሮ ስድስት የሚሆኑ ፓርቲዎች ሕገ-ወጥ ያሉትን የኢትዮጵያ የፓለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ጠቅላላ ጉባኤ እንደማይሳተፉ ገልጸዋል።
ፓርቲዎቹ የጋራ ምክር ቤቱ ዛሬ ቅዳሜ ሕዳር 7 እና እሁድ ሕዳር 8/2017 ለማድረግ የጠራውን ጠቅላላ ጉባኤ እንዲሁም ሰብሳቢ፣ ምክትል ሰብሳቢ እና ሥራ አስፈፃሚ ለመመርጥ ማሰቡን በመቃወም ነው በጉባዔው እንደማይሳተፉ የገለጹት።
ግዜው የተጠናቀቀው የጋራ ምክር ቤቱ ምርጫ እና ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያደርግ ከዚህ ቀደም መጠየቃቸውን ያስታወሱት ፓርቲዎቹ፤ "ስብሰባ መጥራት አይችልም" ብለዋል።
በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ)፣ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ)፣ የዎላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ (ዎብን)፣ ህብር ኢትዮጵያ እና የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ህብር- ኢትዮጵያ) ሕገ-ወጥ ነው ባሉት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እንደማይሳተፉ ገልጸዋል።
በጉባኤው የሚወሰኑ ማንኛውም ውሳኔዎችንም እንደማይቀበሉም ፓርቲዎቹ አስታውቀዋል።
ምክር ቤቱ ጠቅላላ ጉባኤውን ያለፈው ነሐሴ ማድረግ ቢኖርበትም፤ በበርካታ ተቃውሞ ዛሬ ቅዳሜ እና እሁድ ያደርጋል።
ኢሕአፓን ጨምሮ ስድስት ፓርቲዎች ከዚህ ቀደም ጠቅላላ ጉባኤ እንዲደረግና ምርጫ እንዲደረግ መጠየቃቸው አሐዱ መዘገቡ ይታወሳል።
ፓርቲዎቹ በዚህ ጉዳይ ላይም ቀጣይ እርምጃዎችን በተመለከተ በቅርቡ እንደሚያሳውቁም ገልጸዋል።
የኢትዩጵያ የፓለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በበጀት እጥረት ጉባኤዉን አለማካሄዱን መዘገባችን ይታወሳል።
በአቤል ደጀኔ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
የአክስዮን ሽያጭ የሚሰሩ ደላሎችን በታሰበው ልክ ማግኘት እየተቻለ አለመሆኑ ተገለጸ
ሕዳር 7/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በድለላ ሥራ የሚሳተፉ ድርጅቶችና ግለሰቦች ለመመዝገብ ተደጋጋሚ ጥሪ እየተደረገ ቢሆንም፤ በታቀደው ልክ እየተገኙ እንዳልሆነ የኢትዮጵያ የሰነድ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ መስርያ ቤት የኦፕሬሽን ኃላፊ አቶ ሚኪኤል ሐብቴ ለአሐዱ ገልጸዋል።
ኃላፊው "የኢትዮጵያ አክስዮን ገበያ መከፈቱን ተከትሎ ገበያው በታቀደለት መልኩ እንዲተገበር በድለላ ሥራ የሚሳተፉ አካላት ሚና ከፍተኛ መሆኑን ሲገለጽ የቆየ ቢሆንም፤ በታለመለት መልኩ እየተጓዘ አይደለም" ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የመዋእለ ሰነድ ግብይት በተሳካ መልኩ እንዲሳለጥ በዋነኝነት የድለላ ሥራ የሚሰሩ አካላት በስርአቱ መሳተፍ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።
ነገር ግን ከታሰቡት ደላሎች ውስጥ፤ አሁን ላይ የተመዘገቡት በቁጥር አነስተኛ ናቸው ብለዋል።
ለዚህም እቅዱ ላይ ተግዳሮት እንደሆነ የተናገሩ ሲሆን፤ "አሁንም አቅሙ ያላቸው አካላት እንዲመዘገቡ ጥሪ ይደረጋል" ብለዋል።
በታሰበው ልክ ደላሎች የማይገኙ ከሆነም ዘርፉን የሚያከናውኑ አካላትን ጨምሮ ተገበያዮች የሚገናኙበት አማራጭ እንደሚፈለግለት አቶ ሚኪኤል ለአሐዱ ገልጸዋል።
የድለላ ሥራን የሚሰሩ ድርጅቶች አስፈላጊነት በተደጋጋሚ ሲነገር የቆየ ጉዳይ ቢሆንም፤ እንደ አገር ካለው ግንዛቤ አንፃር በታቀደው ልክ ማግኘት እየተቻለ አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡
በዚህም መሰረት ኢትዮጵያ የከፈተችው የአክስዮን ገበያ በተሳካ መልኩ እንዲጓዝ፤ እነዚህ ደላሎች ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።
ዘርፉን ለማነቃቃት በርካታ ሥራዎች እየተሰሩ ቢሆንም፤ ከግንዛቤ ውስንነት አንፃር ተግዳሮት እንደገጠመው መስርያ ቤቱ ተናግሯል።
የኢትዮጵያ ሰነድ መዋእሎ ንዋዮች አክስዮን ገበያ ለማሻሻጥ የተቋቋመ መስርያ ቤት መሆኑን ይታወቃል።
በአማኑዔል ክንደያ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ