ahaduradio | Unsorted

Telegram-канал ahaduradio - AHADU RADIO FM 94.3

19349

አሐዱ ራድዮ 94.3 Your source for top local and international news and analysis. "Voice of Ethiopian" የአሐዱ የቴሌግራም ቻናል ቤተሰብ በመሆን ወቅታዊና እውነተኛ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ

Subscribe to a channel

AHADU RADIO FM 94.3

በትግራይ ክልል የቀድሞ ተዋጊዎችን ትጥቅ ማስወረድና ወደ ተሃድሶ ማዕከላት የማስገባት ሥራ ተጀመረ

ሕዳር 12/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የመጀመሪያው ዙር የትግራይ የቀድሞ ተዋጊዎችን ትጥቅ ማስወረድና ወደ ተሃድሶ ማዕከላት የማስገባት ሥራ በዛሬው ዕለት በመቐለ ከተማ በይፋ ተጀምሯል።

በዚህም መሰረት የመጀመሪያው ዙር የነፍስ ወከፍ እና የቡድን ጦር መሳሪያዎች ርክክብ፤ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የትግራይ ክልል የፀጥታ ሃይሎች ከፍተኛ አመራሮች፣ የአፍሪካ ህብረት፣ የመንግሥታቱ ድርጅትና የአውሮፓ ህብረት ተወካዮች በተገኙበት ተከናውኗል።

በመጀመሪያ ዙር በክልሉ 75 ሺሕ የቀድሞ ተዋጊዎች ስልጠናና የማቋቋሚያ ገንዘብ በመስጠት፤ ወደ ኅብረተሰቡ የማቀላቀል ሥራ እንደሚሰራ ተገልጿል።

የብሔራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን በትናንትናው ዕለት በሰጠው መግለጫ፤ በመቐለ፣ እዳጋ ሀሙስ እና ዓድዋ የመጀመሪያ ዙር ተዋጊዎች ስልጠና የሚወስዱባቸው ማዕከላት መዘጋጀታቸውን ማስታወቁ ይታወሳል።

"የቀድሞ ተዋጊዎች በተዘጋጁ ማዕከላት ስልጠናዎችን ከወሰዱ በኋላ፤ የመቋቋሚያ ድጋፍ ተደርጎላቸው ወደ ማህበረሰቡ በመቀላቀል መደበኛ ሕይወታቸውን እንዲመሩ ይደረጋል" ተብሏል።

በፕሪቶሪያ ስምምነት መሰረት በብሔራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን መሪነት የሚከናወነው ተዋጊዎችን ትጥቅ ማስወረድና ወደ ተሃድሶ ማዕከላት ውስጥ የማስገባት ሥራ ዓላማው፤ "ታጣቂዎችን ወደ መደበኛው የሲቪል ሕይወት በመመለስ በሰላማዊ ልማት ውስጥ እንዲሳተፉ ማድረግ ነው" ተብሏል።

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ:https://www.facebook.com/ahaduradio
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

"ኢትዮጵያ በልጆቿ ትታረቅ" በሚል የተጀመረው የእርቅ ሂደት የፋይናንስ እጥረት ተግዳሮት እንደሆነበት ተገለጸ

ሕዳር 12/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የነጻነት እና እኩልነት ፓርቲ ግጭቶችን ለማስቆም "ኢትዮጵያ በልጆቿ ትታረቅ" የሚል የእርቅና የሰላም ሂደት መጀመሩን መጋቢት 9 ቀን 2016 ዓ.ም ይፋ ማድረጉ ይታወቃል።

ይህንንም ተከትሎ፤ መጋቢት 14 ቀን 2016 ዓ.ም ሂደቱን የሚያስፈጽሙ ከተለያዩ ፓርቲዎች የተውጣጡ አባላት ያሉት ጊዜያዊ ኮሚቴ ተቋቁሟል።

አሐዱም "የተጀመረው የእርቅ ሂደት ከምን ደረጃ ደረሰ? ምን ሥራዎችስ እየተሰሩ ነው?" ሲል ፓርቲውን ጠይቋል።

"የሰላምና የእርቅ ሂደቱ አሰራር በተመለከተ ከመንግሥት እና በተለያዩ ክልሎች ታጥቀው የሚገኙ አካላትን በአንድ መድረክ በማምጣት ንግግር እንዲደረጉ ማድረግ ነው" ያሉት የነጻነት እና እኩልነት ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር ዘኑር አብዱል ወሃብ፤ በሂደቱ ከተለያዩ ፓርቲዎች እና የሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት እና መግባባት ላይ መደረሱን ገልጸዋል።

"ሆኖም ግን ሂደቱን ከግብ ለማድረስ እና ሥራው በታሰበው ፍጥነት እንዳይሄድ የፋይናንስ እጥረት ትልቁ ችግር ሆኖብናል" ሲሉም ተናግረዋል።

በምርጫ ቦርድ የሚመድበው በጀት ውስን መሆኑን ያነሱት ምክትል ሊቀመንበሩ፤ ገንዘቡን ለዚህ ሥራ ለማዋል የሚቻልበት ሁኔታ አለመኖሩን ጠቁመዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ሰብስበው ባነጋገሩበት ወቅት ለሂደቱ ድጋፋቸውን ገልጸው የነበረ ሲሆን፤ በግጭቱ ውስጥ መንግሥት አንዱ ተሳታፊ በመሆኑ ከመንግሥት ምንም አይነት ድጋፍ የማይደረግበት መሆኑን አንስተዋል።

ለዚህም "ኢትዮጵያ በልጆቿ ትታረቅ" የሚለው የእርቅ ሂደት ላይ የገለልተኛነት ጥያቄን እንዳይፈጥር በሚል መሆኑን ገልጸዋል።

በአንጻሩ ችግሩን ለመቅረፍ ከተለያዩ የግል እና አለም ዓቀፍ ተቋማት ጋር ንግግር እየተደረገ መሆኑን፤ ምክትል ሊቀመንበሩ ዘኑር አብዱልወሃብ ለአሐዱ ገልጸዋል።

በፍርቱና ወልደአብ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

#ADVERTISMENT
#ጊፍትሪልስቴት
ታላቅ የምስራች!

**
ጊፍት ሪል ስቴት ከ10% ቅድመ ክፍያ ጀምሮ በ22 ሳይቶቹ ቅንጡ አፓርትመንቶችን እና የንግድ ሱቆችን ለሽያጭ አቅርቧል፡፡

ይህ ሳይት ለአፓርትመንትና ንግድ ሱቆች የሚውሉ G+25 ሶስት መንታ ህንጻዎች ያሉት ሲሆን የዚህ 6ኛ መንደር መለያዎች፡-
•ከባለአንድ እስከ ባለአራት መኝታ ክፍሎች ያሉት፣
•ለመኖሪያም ሆነ ለንግድ ተመራጭ አካባቢ የሆነ፣
•በአንድ ወለል ሶስት ቤቶች ብቻ ያሉት፣
•በእያንዳንዱ ወለል ስድስት አሳንስር ያለው፣
•አራት ቤዝመንት ያሉት በቂ የመኪና ማቆሚያ የተዘጋጀለት፣
•24 ሰዓት የኤሌክትሪክ፣ ኢንተርኔትና ውሃ አቅርቦት አሉት፣

ጊፍት ሪል ስቴት
ማህበረሰብን እንገነባለን!
ለበለጠ መረጃ፡-
Website: https://www.giftbusinessgroup.com                                                                                             
Twitter: https://twitter.com/GIFTBusinessG                                                     
YouTube: www.youtube.com/channel/UCcqr7cpVv9ski-F7haxXx4w                                                     
Facebook: www.facebook.com/profile.php?id=100090918391017...                                                       
Telegram: /channel/giftbusinessgroup

Short Code: 8055

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

#አሐዱ_ስንክሳር

ኢትዮጵያ በርካታ ፀሐፊያን ልጆችዋ ብዙ ነገሮችን ለትውልድ አስቀምጠውላት አልፈዋል። እነዚህ ፀሐፊያን ስለ ሀገራቸው የሚጨነቁ፣ የሚጠበቡ፣ የሚያስቡ ናቸው።

በየዘመናቱ ኢትዮጵያ ላይ የሚከስቱት በጎም ይሁኑ አስከፊ ችግሮችን ፅፈው ከማለፋቸውም በላይ፤ መልካሙን መንገድ ለኢትዮጵያ አመላክተዋልም።

እነዚህ ፀሐፊያን መካከል ታላቁ ጋዜጠኛ አሐዱ ሳቡሬ አንዱ ናቸው። "አሐዱ ሳቡሬ አጠገበኝ ወሬ" ይባልላቸው ነበር ድሮ።

ትልቅ የሚዲያ ሰው ነበሩ። በአምባሳደርነትም ሀገራቸውን አገልግለዋል፡፡

ትናንት November 19 አለማቀፍ የጋዜጠኞች ቀን ነበር።

ዛሬ በሕይወት የሌሉትን ትልቁን ጋዜጠኛ አሐዱ ሳቡራን መሠረት አድርገን፤ ስለ ኢትዮጵያ በጥቂቱ እናወጋለን።

በጥበቡ በለጠ
ጥንቅሩን ለመከታተል ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👇
https://youtu.be/JwhMxY-OfGQ?si=tTjqBZFXPlrJoi9X

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በመዲናዋ በሦስት ወራት ብቻ 1 መቶ 50 የሚሆኑ ዜጎች በትራፊክ አደጋ ሕይወታቸው ማለፉ ተገለጸ

ሕዳር 11/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በአዲስ አበባ ከተማ ከሀምሌ አንድ እስከ ሕዳር ዘጠኝ ቀን ድረስ 1 መቶ 38 የትራፊክ አደጋዎች መከሰታቸውን፤ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የትራፊክ አደጋ መርማሪ ኢንስፔክተር ተመስገን ደሳለኝ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

በደረሰዉ የትራፊክ አደጋ 1 መቶ 51 ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉን የገለጹት ኢንስፔክተር ተመስገን፤ ከእነሱም ውስጥ 103 ወንዶች ሲሆኑ 48 ሴቶች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

እንዲሁም ከ5 ዓመት በታች ያሉ 6 ሕጻናት በትራፊክ አደጋ ሕይወታቸው ማለፉ ጠቁመዋል፡፡

አክለውም 55 የሚሆኑት ዜጎች ከ35 ዓመት እድሜ ክልል በታች ያሉ አምራች ዜጎች ናቸው ብለዋል፡፡

ለትራፊክ አደጋዎቹ መከሰት፤ ለእግረኛ ቅድሚያ አለመስጠት፣ የአልኮል ይዘት ያላቸውን መጠጦች ጠጥቶ ማሽከርከር ለሚከሰቱ የትራፊክ አደጋዎች እንደ ምክንያት ተጠቃሽ ናቸው ተብሏል፡፡

በእሌኒ ግዛቸው
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

#አሐዱ_ትንታኔ

ነጩን ቤተ መንግሥት ሊለቁ ጥቂት ጊዜ ብቻ የቀራቸው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ያስተላለፉትን ውሳኔን ተከትሎ ዩክሬን በሩስያ ላይ የረጅም ርቀት የሚሳኤል ጥቃት ሰንዝራለች፡፡

ይህ የዩክሬን የረዥም ርቀት ሚሳኤል ትንኮሳ ፕሬዝደንት ፑቲን ያስቀመጡትን ቀይ መስመር የተላለፈ መሆኑም አለምን ወደ ኒውከሌር ጦርነት ሊያሸጋግር ይችላል እየተባለ ነው፡፡ ይህንንና ተያያዥ ጉዳዮችን በዛሬው አለም ዓቀፍ ትንታኔያችን እንመለከታለን፡፡

ትንታኔውን ለመከታተል ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👇
https://youtu.be/XrcMbxMts_4?si=YPToKQiqEikw_kMk

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በቤት ሠራተኝነት ተቀጥራ ከምትሰራበት ቤት ከ2 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት እና ገንዘብ ሰርቃ የተሰወረች ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር መዋሏ ተገለጸ

ሕዳር 11/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 አያት ዞን1 ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ በቤት ሠራተኝነት ተቀጥራ ከምትሰራበት ቤት ጥቅምት 22 ቀን 2017 ዓ/ም ከ2 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት እና ገንዘብ ሰርቃ የተሰወረች ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር መዋሏን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ተጠርጣሪዋ በደላላ አማካኝነት በቤት ሠራተኝነት ከተቀጠረችበት መኖሪያ ቤት በሦስተኛው ቀን ቆይታዋ የግል ተበዳይ ወደ ሥራ በሄዱበት ወቅት አጋጣሚውን በመጠቀም በቤቱ ውስጥ የተቀመጠውን የተለያዩ ሀገራት ገንዘቦች እንዲሁም የተለያዩ የወርቅ ጌጣጌጦችን ሰርቃ በመሰወሯ የግል ተበዳይ የተፈፀመባቸውን የወንጀል ድርጊት ለመሪ ሉቄ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ አመልክተዋል፡፡

ተጠርጣሪዋ የወንጀል ድርጊቱን ከፈፀመች በኋላ የግል ተበዳይ ጋር ከመቀጠሯ በፊት በክፍለ ከተማው ወረዳ 14 አባዶ አካባቢ ኮንዶሚኒየም ቤት ለሦስት ወራት ተከራይታ በነበረበት ቤት መደበቋ ተነግሯል

የክትትል የፖሊስ አባላትም ከሰረቀቻቸው የተለያዩ አልባሳት፣ የተለያዩ የሴትና የወንድ ጫማዎች፣ 18 ሺሕ የአሜሪካ ዶላርና የህንድ ሩፒ፣ የተለያዩ የወርቅና ልዩ ልዩ ጌጣጌጦች ጋር ከተደበቀችበት ቤት በቁጥጥር ሥር መዋሏን ከክ/ከተማው የተገኘው መረጃ ያስረዳል።

በተጨማሪም ተጠርጣሪዋ በሁለት የተለያዩ ሥሞች የነዋሪነት መታወቂያ እንደተገኘባትም ተገልጿል።

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የመሪ ሉቄ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የወንጀል ምርመራ ማስተባበሪያ ኃላፊ ኢንስፔክተር ሰለሞን አበበ፤ የግል ተበዳይ ተጠርጣሪዋን ለስራ ሲቀጥሯት ያቀረበችው የተያዥ ፎርም የራሷን ፎቶ በትክክል እንዳይለይ አድርጋ የለጠፈች መሆንዋን ተናግረዋል፡፡

የግል ተበዳይም ይህንን ሳያረጋግጡ በእምነት የቀጠሯት መሆኑን የገለጹት ኢንስፔክተር ሰለሞን፤ ህብረተሰቡ የቤት ሰራተኛ በአጋዥነት መቅጠሩ ተገቢ ቢሆንም በህጋዊ መንገድ በቂ ተያዥ በማስቀረብ የተያዣቸውን አድራሻና ማንነት በአግባቡ በማጤን መቅጠር እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

አክለውም ቀጣሪዎች ውድ የሆኑ ንብረቶችንና ገንዘቦችን ደህንነቱ በተጠበቀ ቦታ በማስቀመጥ በተገቢው ሊቆጣጠሩና ንብረታቸውን ከስርቆት ወንጀል ሊታደጉ እንደሚገባም ተናግረዋል።

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በቃሊቲ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ የሚገኙ 270 ናይጄሪያውያን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ትዕዛዝ ተሰጠ

ሕዳር 11/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በናይጄሪያ አቡጃ የሚገኘው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት የሚገኙ ከ270 ያላነሱ ናይጄሪያውያን ወደሀገራቸው እንዲመለሱ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ለናይጄሪያ ዲያስፖራ ኮሚሽን ትዕዛዝ አስተላልፏል።

ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ የታሰሩ ናይጄሪያውያኑ እንዲመለሱ የሚያስገድድበትን ትዕዛዝ ያስተላለፈው፤ የኢትዮጵያ መንግሥት ለእስረኞቹ የሚሆን ምግብ፣ መድኃኒት እና ሌሎች ግብአቶችን ለመሸፈን የሚያስችል በጀት እንደሌለው በመግለጹ መሆኑን ተመላክቷል፡፡

በማረሚያ ቤቱ የሚገኙት ናይጄሪያዊያን በቋንቋ ችግር ምክንያት፤ ፍርድ ቤት እንዳልቀረቡና የአስተርጓሚ አገልግሎት እንዳልተሰጣቸውም በፍርድ ቤቱ ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም ከኢትዮጵያዊያን ታሳሪዎች ጋር የሚደረግ ማንኛውም የቃላት ልውውጥ የጅምላ ድብደባን እያስከተለ መሆኑ በፍርድ ቤቱ የተነሳ ሲሆን፤ "በዚህም ምክንያት በእስር ላይ ለሚገኙ ናይጄሪያውያን እየተደረገ ያለው አያያዝ አስደንጋጭ ነው" መባሉን የናይጄሪያ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ከዚህ ቀደም የናይጄሪያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር በአደገኛ እፅ ዝውውርና ሌሎች ወንጀሎች የተጠረጠሩ ናይጀሪያዊያን በቃሊቲ እስር ቤት እንደሚገኙ መግለጹ ይታወሳል።

በዚህም የሀገሪቱ የመብት ተከራካሪዎች ከ250 በላይ ናይጀሪያዊያን እስረኞች ኢትዮጵያ ውስጥ አግባብ ባለሆነ መንገድ መያዛቸውን ገልፀው የነበረ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ ያሉ ናይጄራዊያን እስረኞችን ሁኔታ የሚያጣራ ኮሚቴ መዋቀሩም ተገልጾ ነበር።

በዚህም መሰረት ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ለሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ዲያስፖራ ኮሚሽን ባስተላለፈው ትዕዛዝ፤ "በማረሚያ ቤቱ የሚገኙ ናይጄሪያውያን ዜጎች ወደሀገራቸው ይመለሱ" ማለቱ ተነግሯል፡፡

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የተሃድሶ ኮሚሽን በመጀመሪያ ዙር 75 ሺሕ የቀድሞ ተዋጊዎችን ወደ ማህበረሰቡ እንደሚቀላቅል አስታወቀ

ሕዳር 11/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የብሔራዊ የተሃድሶ ኮሚሽን የቀድሞ ታዋጊዎችን ወደ ማህበረሰቡ የመመለስ ሥራውን፤ በሥሩ ከመዘገባቸው 3 መቶ 71 ሺሕ 907 የቀድሞ ተዋጊዎች ውስጥ 70 በመቶ የሚሆኑት በሚገኙበት ትግራይ ክልል የሚጀመር መሆኑን አስታውቋል።

በዚህም በመጀመሪያ ዙር 75 ሺሕ፣ በሁለተኛ ዙር 100 ሺሕ እንዲሁም በሦስተኛ ዙር 150 ሺሕ የቀድሞ ተዋጊዎች ወደ ማህበረሰቡ ተሃድሶ ወስደው እንደሚቀላቀሉ ኮሚሽኑ ገልጿል።

የብሔራዊ የተሃድሶ ኮሚሽን በሚኒስትሮች ምክር ቤት ሕዳር 3 ቀን 2015 ዓ.ም በተካሄደ 15ኛ መደበኛ ስብሰባ፤ በደንብ ቁጥር 525/2015 እና በተሻሻለው ደንብ ቁጥር 541/2016 መሰረት መቋቋም ይታወሳል።

በማቋቋሚያ ደንቡ መሠረት የኮሚሽኑ የሥራ ጊዜ ሁለት ዓመት ሆኖ እንደ አስፈላጊነቱ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ሊራዘም እንደሚችልም ተቀምጧል።

ኮሚሽኑም ከተቋቋመ በሁለተኛ ዓመቱ የቀድሞ ታጣቂዎችን ወደ ማህበረሰብ ለመቀላቀል መወሰኑን የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አቶ ተመስገን ጥላሁን ገልጸዋል።

በዚህም ከመቀሌ ሥራው እንደሚጀምር የገለጹት ኮሚሽነሩ፤ በቀጣይ በደጋ ሁሙስ እና በአድዋ የሚቀጥል መሆኑንም ተናግረዋል።

የተሃድሶ ኮሚሽን የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት መሰረት አንቀፅ ስድስት ላይ መሰረት አድርጎ የተቋቋመ ነው።

የተሃድሶ ሥራ ከፍተኛ ገንዘብ የሚጠይቅ መሆኑ የሚታወቅ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ ከ760 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ እንደሚያስፈልግ መገለጹ ይታወቃል።

አሁን ላይ ለመጀመሪያ ዙር ከመንግሥት 1 ቢሊዮን ብር እንዲሁም፤ ከውጭ ለጋሾች 60 ሚሊዮን ዶላር በተገኘ በጀት የሚሰራ ሥራ መሆኑን ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።

የመጀመሪያ ዙር የቀድሞ ተዋጊዎችን ወደ ማህበረሰቡ የመቀላቀል ሥራ በአራት ወራት ውስጥ የሚጠናቀቅ መሆኑንም አሐዱ ከኮሚሽነሩ ሰምቷል።

በአቤል ደጀኔ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በኢትዮጵያ 40 ሺሕ የሚደርሱ የጤና ተቋማት ቢኖሩም በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ አገልግሎት የሚጠቀሙት 10 ብቻ መሆናቸዉ ተገለጸ

ሕዳር 11/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ 40 ሺሕ የሚደርሱ የጤና ተቋማት ቢኖሩም፤ አስሮቹ ብቻ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ አገልግሎት የሚጠቀሙ መሆናቸውን ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ ተመርጠዉ 70 የሚደርሱ የጤና ተቋማት ላይ የዲጂታል የአከፋፈል ስርዓቱን ለማዘመን ሙከራ የተደረገ ቢሆንም፤ ሙሉ ለሙሉ ከወረቀት የክፍያ ስርአት ነፃ ማድረግ ባለመቻሉ 10 ተቋማት ብቻ አገልግሎቱን እየተጠቀሙ መሆናቸዉን በሚኒስቴሩ የዲጂታል የጤና ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ገመችስ መልካሙ ለአሐዱ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ የሚገኙ በርካታ ተቋማት የዲጂላይዜሽን ስርዓት እየተጠቀሙ እንደሆነ የገለጹት አስተባባሪዉ፤ "ነገር ግን በጤናዉ ተቋማት ላይ ሲታይ ትኩረት ተሰጥቶት መሰራት የሚፈልግ ነዉ" ሲሉ ተናግረዋል።

ከዚህ ቀደም ሰዎች የሕክምና አገልግሎት አግኝተዉ የክፍያ ሲስተም ሲተገብሩ ቅሬታ ያቀርቡ እንደነበር በማንሳትም፤ ነገር ግን ይህ ተግዳሮት ሳይፈታ ውሎ ማደሩ ከእንግልት በተጨማሪ ተቋሙ ማግኘት ያለበትን ገንዘብ መሰብሰብ እንዳይችል አሉታዊ ተፅዕኖ አሳድሮበት መቆየቱን ተናግረዋል።

በጤና ተቋማቱን ላይ ያለዉን በቀጣይ ዲጂታላይዜሽን ለማድረግ የታሰበበት አንዱ አላማ ዜጎችን ከአጭበርባሪዎች ለመጠበቅ መሆኑንም አስተባባሪው ጨምረው ለአሐዱ ገልጸዋል።

በተጨማሪም በሀገር አቀፍ ደረጃ 9 ሺሕ ለሚደርሱና በገጠር ቀበሌዎች የሚሰሩ የጤና ባለሙያዎች የዲጂታላይዜሽን የአከፋፈል ስርዓትን ተግባራዊ እንዲያደርጉ ስልጠና መሰጠቱንም አስታውቀዋል።

በደረጄ መንግስቱ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

#ADVERTISMENT
#AmharaBank
የአማራ ባንክ አ/ማ የባለአክሲዮኖች 3ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ማክሰኞ ታህሳስ 01 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ በሚሊኒየም አዳራሽ ስለሚካሄድ ባለአክሲዮኖች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጉባዔው እንድትገኙ ጥሪ እናስተላልፋለን፡፡

የጉባዔው አጀንዳዎችን እና ተጨማሪ መረጃዎችን ጥቅምት 06 ቀን 2017 ዓ.ም በወጡት አዲስ ዘመን እና ሪፖርተር አማርኛ እትም ጋዜጦች ላይ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ለበለጠ መረጃ ነፃ የጥሪ ማዕከል 690 ወይም
የባንኩን ድረ ገጽ www.amharabank.com.et ይጎብኙ፡፡

አማራ ባንክ
ከባንክ ባሻገር!

የአማራ ባንክ ትክክለኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾች
Website: www.amharabank.com
Facebook: www.Facebook.com/amharabanksc1
Telegram: /channel/Amhara_Banksc
Instagram: https://instagram.com/amhara_bank
Twitter: https://twitter.com/Amharabanksc
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/amharabank/
YouTube: https://youtube.com/channel/UC73x9uuGYV0Uxw0EkpVZN8g
TikTok: amharabanks.c" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@amharabanks.c

#አማራባንክ #AmharaBank

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

#አሐዱ_አሳሩ_በዛብህ

"አኗኗራችን ከስደት ሞት ያስመኛል"

አሳሩ በዛብህ በሳምንቱ አሳሰበኝ ያለውን ጉዳይ በብዕሩ ከትቦ፤ ለወዳጁ ምክረ ሰናይ ልኮለታል፡፡ አሳሩን ያሳሰበው ጉዳይ ምን ይሆን?

ሙሉ ጥንቅሩን ለመከታተል ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👇
https://youtu.be/7XUojqn7ZvI?si=0vfdy_BrwwoIwVdr

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

ዩክሬን አሜሪካ ሰራሽ ረጅም ርቀት ሚሳኤል ወደ ሩሲያ አስወነጨፈች

ሕዳር 10/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የባይደን አስተዳደር ሩሲያ ውስጥ ባሉ ኢላማዎች ላይ ረጅም ርቀት ያላቸውን የአሜሪካ ጦር መሳሪያዎች ለመጠቀም ለዩክሬን ፍቃድ ከሰጠ ከሁለት ቀናት በኋላ፤ ዩክሬን አሜሪካ ሰራሽ ሚሳኤሎችን ወደ ሩሲያ ማስወንጨፏን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ዛሬ ማክሰኞ ዩክሬን ወደ ሩሲያ ብራያንስክ ግዛት ስድስት የባላስቲክ ሚሳኤሎችን መተኮሷን ሚኒስቴሩ የገለጸ ሲሆን፤ በጥቃቱ አሜሪካ ሰራሽ ATACMS ሚሳኤሎች ጥቅም ላይ ውለዋል ብሏል።

ከእነዚህም ስድስት ሚሳኤሎች ውስጥ አምስቱ በሩሲያ ጦር የከሸፉ መሆኑን የገለው ሚኒስቴሩ፤ የአንደኛው ሚሳኤል ፍንጣሪ በሩሲያ ጦር አቅራቢያ የእሳት አደጋ ማስከተሉን አስታውቋል። ነገር ግን ፍንጣሪው ምንም አይነት ጉዳት አለማድረሱን ገልጿል፡፡

ይህ የረጅም ርቀት ተምዘግዛጊ የሚሳኤል ጥቃት ወደ ሩሲያ ሲወነጨፍ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑም የተነገረ ሲሆን፤ ዩክሬን ስላስወነጨፈቻቸው ሚሳይሎች እስካሁን ይፋ ያደረገችው መረጃ አለመኖሩን ሲኤንኤን ዘግቧል፡፡

የሩሲያ ፕሬዚዳነት ቭላድሚር ፑቲን ዩክሬን ሚሳኤሉን ከማስወንጨፏ አስቀድሞ ከሰዓታት በፊት፤ ግልጽ የደህንነት ስጋት መከሰቱን በመግለጽ የኒውክሌር ሚሳኤል መመሪያ እንዲቀየር ትዕዛዝ አስተላልፈው እንደነበርም ተመላክቷል፡፡

ባሳለፍነው እሁድ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ዩክሬን ሩሲያን ለመምታት ረጅም ርቀት ተወንጫፊ የአሜሪካ ሚሳኤሎችን እንድትጠቀም ፍቃድ መስጠታቸው ይታወሳል፡፡

ሩሲያ ይህንን የባይደን ፍቃድ ተከትሎ ዩክሬን ሚሳኤሎቹን የምትጠቀም ከሆነ የአጸፋ እርምጃ እንደምትወስድ አስጠንቅቃ ነበር።

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

ኮሚሽኑ የዲያስፖራ ማሕበረሰብ በሀገራዊ ምክክሩ የተሳትፎ ልየታ የሚሳተፉበት ሂደት አስቸጋሪ እንደሆነበት ተናገረ

ሕዳር 10/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን የምክክር ሂደቱ ላይ የሚሳተፉ የዲያስፖራ ማሕበራት ልየታ በማድረግ ረገድ ከባድ ፈተና እንደገጠመው አስታውቋል።

ኮሚሽኑ "አስቸጋሪ ሆነውብኛል" ካላቸው ጉዳዮች መካከል፤ የውክልና ጉዳይ የተሞላ ነገር እየቀረበ አለመሆኑን እንደምክንያት እንደሚነሳ በምክክር ኮሚሽኑ የክልሎች፣ ከተማ መስተዳድሮችና የዲያስፖራው አስተባባሪ አቶ ረታ ጌራ ለአሐዱ ተናግረዋል።

የዲያስፖራው ማሕበረሰብ እንዲመለስለት የሚፈልገው የተለያዩ ጉዳዮች በመኖራቸው ሌላው ሂደቱን አስቸጋሪ ካደረጉ ጉዳዮች መካከል አንዱ መሆኑንም ገልጸዋል።

ይሁንና በየአካባቢው እየተነሱ ያሉ ጉዳዮችን ለማስታረቅ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ቢሆንም፤ በታለመለት ልክ ለማስኬድ ግን አዳጋች እንደሆነበት አስረድተዋል።

የኮሚሽኑ በመጨረሻ የሚደረገው የምክክር ጉባኤ በማሳተፉ ረገድ ምን እየተሰራ ነው? ለሚለው ከአሐዱ ለቀረበላቸው ጥያቄ፤ "ኮሚሽኑ የሚቻለውን ሁሉ በማድረግ ላይ ነው" ሲሉ አቶ ረታ ጌራ ምላሽ ሰጥተዋል።

የዲያስፖራው ማሕበረሰብ በምክክር ጉባኤው በምን መልኩ ተሳታፊ ይደረጋሉ የሚለውን መልስ ሳይሰጥበት መቆየቱ ይታወሳል።

አሁን ላይ በተቻለ አቅም በልየታ ሂደቱ ላይ እንደሚሳተፉና አጀንዳዎቻቸው በጉባኤው እንዲካተቱ ይደረጋል ተብሏል።

በአማኑዔል ክንደያ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ:www.facebook.com/ahaduradio
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በመዲናዋ 9 ሺሕ ለሚሆኑ አርሶ አደሮች ካርታ ለመስጠት መረጃቸው መጣራቱ ተገለጸ

ሕዳር 10/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በአዲስ አበባ ከተማ የአርሶ አደሮችን ጥያቄዎች ከመመለስ አንፃር በዚህ ዓመት፤ 9 ሺሕ ለሚሆኑት ካርታ ለመስጠት መረጃቸው መጣራቱን የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ከንቲባዋ በዛሬው ዕለት በተካሄደው የአዲስ አበባ ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 4ተኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ማብራሪያ፤ "ከአርሶ አደር ካርታ ጋር በተያያዘ የሚነሳው ተደጋጋሚ ጥያቄ ምላሽ ማግኘት አለበት።" ብለዋል።

አክለውም፤ "በሕዝብ እያስተቸን በመሆኑ ስናጣራ ጥቆማ የቀረበባቸውንና አጠራጣሪ የሆኑትን አዘግይተናል። ሌላውን አስተናግደናል።" ያሉ ሲሆን፤ በዚህ ዓመትም 9 ሺሕ ለሚሆኑት ካርታ ለመስጠት መረጃቸው መጣራቱን ተናግረዋል።

"መንግሥት መዋቅር ውስጥ ሆነው ጭምር በአርሶ አደር ሥም ለመጠቀም መረጃ የሚያዛቡ አሉ" ያሉት ከንቲባ አዳነች፤ ይህም በመጣራት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

የአርሶ አደር መሬት ካሳን በተመለከተ በተሻሻለው መመሪያ መሰረት ነው አገልግሎት እየተሰጠ እንደሚገኝም የገለጹ ሲሆን፤ በድሮው መመሪያ እያስተናገደ ያለ ካለ ጥቆማው እንዲመጣላቸውም ጠይቀዋል።

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

"የህወሓት አመራሮች መከፋፈል የምሰራው ሥራ ላይ እንቅፋት አይሆንብኝም" የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን

ሕዳር 12/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን በትግራይ ክልል ከ 274 ሺሕ 800 በላይ የቀድሞ ታጣቂዎችን ወደ ማህበረሰቡ የመቀላቀል ሥራ በዚህ ሳምንት ጀምሮ በአራት ወራት ውስጥ ለማጠናቀቅ እየሰራ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ "በትግራይ በአሁን ወቅት ያለው የፖለቲካ ውጥረት፤ በተለይም በህወሓት አመራር መከፋፈል የተፈጠረው መካረር ሥራው ላይ እንቅፋት አይሆንም ወይ?" የሚል ስጋት ፈጥሯል፡፡

ይህንን በሚመለከት የተሃድሶ ኮሚሽን የትግራይ ተወካይ የሆኑት አቶ ተስፋዓለም ይህድጎ፤ "በህወሓት እና በትግራይ ግዚያዊ አስተዳደሩ መካከል የተፈጠረው ውጥረት ታጣቂዎችን ወደ ማህበረሰብ የመቀላቀሉ ሥራ ላይ እንቅፋት አይሆንም" ሲሉ ለአሐዱ ገልጸዋል፡፡

"በህወሓት ውስጥ ያለው ጉዳይ በራሱ በህወሓት እንዲሁም በፌደራል መንግሥት ጣልቃ ገብነት የሚፈታ ሲሆን፤ የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ተግባራዊነት ሁለቱም አካላት ይሰራሉ ብለን እናምናለን" ብለዋል፡፡

የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሰረት ተፈፃሚ ለማድረግ የተቀረጸ ሲሆን፤ ይህንን ሥራ ተፈፃሚ ለማድረግም የሁሉንም ተሳትፎ እንደሚጠይቅ ተገልጿል፡፡

የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት አሁን ተፈፃሚነቱ ላይ እየተሰራ ቢሆንም፤ በተለይም "የኤርትራ ሠራዊት አሁንም ከኢትዮጵያ ግዛት አልወጣም" ተብሏል፡፡

"አሁን ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ አካላትም ጥያቄያቸውን በሰላማዊ መንገድ መፍታት አለባቸው" ሲሉም፤ የኮሚሽኑ የትግራይ ተወካይ አቶ ተስፋዓለም ጠቁመዋል፡፡

ኮሚሽኑ ከሰባት ክልሎች ከ371 ሺሕ በላይ የቀድሞ ተዋጊዎችን ወደ ማህበረሰቡ ለመቀላቀል ከ760 ሚሊዩን የአሜሪካን ዶላር በላይ የሆነ ወጪ እንደሚያስፈልገው በትናንትናው ዕለት ማስታወቁን አሐዱ መዘገቡ ይታወሳል፡፡

በሁለት ዓመታት ውስጥም ትጥቅ የማስፈታት እና መልሶ ማቋቋም ሥራውን ለመጨረስ የሚያስችል ዝግጅት ማጠናቁን ገልጿል፡፡

በዚህም መሰረት ከዛሬ ሕዳር 12 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮም በመጀመሪያው ምዕራፍ 75 ሺሕ የቀድሞ ተዋጊዎችን፤ ከትግራይ ክልል ትጥቅ የማስፈታት እና ወደ ማህበረሰቡ የመቀላቀል ሥራውን በይፋ መጀመሩን ገልጿል፡፡

በአቤል ደጀኔ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

ሕገወጥ ሥራን የሚሰሩ የጉዞ ወኪሎች መበራከት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል ተባለ

ሕዳር 12/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በየጊዜው የውጪ ሀገር የጉዞ ወኪልና አማካሪ ድርጅቶች እንዲሁም ደላሎች "ወደ ውጪ እንልካችኋለን" በሚል ምክንያት 'ተጭበርብረናል፣ ተዘርፈናል' እያሉ ቅሬታ የሚያቀርቡ ሰዎች መበራከታቸውን የአዲስ አበባ ፍትህ ቢሮ አስታውቋል፡፡

በቢሮው የሰው መነገድና ሰውን በሕገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀል መከላከል ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ታደሰ ፈይሳ፤ እነዚህ ቅሬታዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመሩ መምጣታቸውን ገልጸው፣ ቢሮው ወንጀሉን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የተለያዩ ሥራዎችን በማከናወን ላይ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚሁ ጉዳይም በ2017 ሩብ ዓመት ከ50 በላይ ምርመራ የተካሄደባቸው መዝገቦች ተይዘው 30 ያህሉ ላይ ክስ እንደተመሰረተባቸው ለአሐዱ ተናግረዋል።

"እነዚህ ቅሬታዎች ተሰምተዉ ዝም የሚባልበት አግባብ የለም" ያሉት ኃላፊው፤ በቀጥታ ለአዲስ አበባ እና ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን በመላክ ተጠያቂነት እንዲሰፍን እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

"በኢትዮጵያ ውስጥ በተለይም ወደ አውሮፓ የሚሄዱ ሰዎች ፍላጎት መበራከቱን ተከትሎ፤ ዜጎች ከሕግ ውጪ በሚሰሩ ድርጅቶችና ደላሎች አማካኝነት ረብጣ ገንዘባቸውን መጭበርበራቸው እየተባባሰ ይገኛል" ነዉ ያሉት።

በብዙዎች ጥቆማና ቅሬታ መሰረት፤ ከዚህ ቀደም ከ40 በላይ ሕገ-ወጥ ሥራን በመስራት የተሰማሩ የውጪ ሀገር የጉዞ ወኪሎች ላይ እርምጃ መወሰዱን አቶ ታደሰ አስታውሰዋል።

በመሆኑም ህብረተሰቡ በተለያየ መንገድ ወደ ውጪ ለመውጣት ሲፈልግ፤ ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሕጋዊ የሆኑ ወኪሎችን ለይቶ ስላሰራጨ፤ በተለያዩ ማህበራዊ ሚድያዎች ማግኘት እንዲችሉ አልያም በአካል ቀርበው መረጃ እንዲያገኙ ኃላፊው አሳስበዋል።

በስፍራሽ ደመላሽ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

መልካም ቀን!
አሐዱ ሬድዮ 94.3  የኢትዮጵያውያን ድምፅ!

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

ኢትዮጵያ በ2010 ዓ.ም የሀገር ውስጥ ብድሯ 900 ሚሊዮን ብር እንደነበር የፕላንና ልማት ሚኒስቴር አስታወቀ

ሕዳር 11/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) አሁን በስልጣን ላይ ያለው የብልፅግና መንግሥት ወደ ስልጣን ሲመጣ፤ የኢትዮጵያ የሀገር ውስጥ ብድር 900 ሚሊዮን ብር ገደማ እንደበር የፕላንና ልማት ሚኒስቴር አስታውቋል።

የፕላንና ልማት ሚኒስትሯ ዶክተር ፍፁም አስፋ እንደገለጹት፤ ከሀገር ውስጥ ብድር በተጨማሪ ባለፉት ስድስት ዓመታት መንግሥት 10 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ብድር ከፍሏል፡፡

በዚህም ከፍተኛ የሆነ የዕዳ ስርዛ የተደረገ ሲሆን፤ ሙሉ ለሙሉ ኢትዮጵያ ከዕዳ ነፃ እንድትሆን የተደረገበት ወቅት መኖሩንም ሚኒስትሯ ተናግረዋል፡፡

በዚህም ከተለያዩ የልማት አጋሮች ጋር የተሻለ ትብብር የተፈጠረበት መሆኑን የገለጹ ሲሆን፤ በቀድሞው የኢህአዴግ ዘመነ መንግሥት ከውጭ እንዲሁም ከሀገር ውስጥ በርካታ ብድሮችን የተወሰዱበት ወቅት እንደነበር አንስተዋል፡፡

አክለውም በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ10 ቢሊዮን ብድር በላይ አሁን በስልጣን ያለው መንግሥት፤ ለመክፈል የተገደደበት ሁኔታ መኖሩን ገልጸዋል፡፡

ሚኒስትሯ በኢህአዴግ ጊዜ የነበረው ብድር ከውጪም ብቻም ሳይሆን፤ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ከሀገር ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ብድር መወሰዱን በማንሳት፤ "ይህ ብድር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክንም ጭምር ከፍተኛ ችግር ውስጥ ከቶት ቆይቷል" ብለዋል፡፡

"በዛን ጊዜ ያልተከፈለ ከ900 ሚሊዮን ብር በላይ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች የሀገር ውስጥ ብድር ዕዳ ነበረባቸው" ብለዋል፡፡

"ቀደም ብሎ በነበረው ከፍተኛ የሆነ ዕዳ ምክንያት ኢትዮጵያ ያለፉትን ስድስት ዓመታት እዳ መመለስ ላይ ትኩረት አድርጋ ቆይታለች" ሲሉ ተናግረዋል፡፡

አክለውም "ብድሩ በአጭር ጊዜ የሚመለሱ ከፍተኛ ወለድ ያላቸው የነበሩ በመሆኑና የተበደሩበት ፕሮጀክቶች አምራች ሆነው ባለመመለሳቸው ዕዳ ውስጥ ቆይተናል" ብለዋል፡፡

የብልፅግና መንግሥት ወደ ስልጣን ከመጣ በኃላ በዓለም ላይ የኮቪድ 19፣ የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነትና የአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ የዓለም አቀፍ አጋሮች ትብብር ቀንሶ የነበረ ቢሆንም፤ አሁን ላይ ግን የተሻሉ ሂደቶች መኖራቸውን ሚኒስትሯ ጨምረው ገልጸዋል፡፡

በአቤል ደጀኔ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የኢትዮጵያ ጥራጥሬና የቅባት እህል ገበያ በአለም ዓቀፍ ደረጃ ያለው ተቀባይነት እየጨመረ መምጣቱን ተነገረ

ሕዳር 11/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ጥራጥሬና የቅባት ምርት ከፍተኛ ተቀባይነት ያለው ቢሆንም፤ ከዘርፉ ሲገኝ የነበረውን ጥቅም እዚህ ግባ የሚባል አልነበረም።

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን "ኮንትራት ፋርሚንግ" የተሰኘውን ስትራቴጂ እንዲተገበር መደረጉን ተከትሎ፤ የተወሰኑ ለውጦች መታየት መጀመራቸው ተነግሯል።

ከጥራጥሬና ቅባት እህሎች ኢትዮጵያ እያገኘች ያለችውን ጥቅም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደረገ መምጣቱን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።

በአዲስ አበባ ከተማ አድዋ አደባባይ የተካሄደውን የአለም ዓቀፍ የጥራጥሬና የቅባት እህሎች ጉባኤ በርካታ ጎረቤት አገራት ጭምር የተሳተፉበት እንደነበር ተገልጿል።

በመሆኑም የገበያ ትስስር መፍጠርና የተለያዩ የንግድ ትውውቅ የሚደረግበት መድረክ እንደነበር የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር የተናገረ ሲሆን፤ ከፍተኛ ጠቀሜታ የተገኘበት እንደነበርም ተነስቷል።

እንዲህ ያለውን ጉባኤ ከ30 በመቶ በላይ የገበያ ትስስር መፍጠርያ መሆኑን በሚኒስቴሩ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሥራ አስፈፃሚ ወንድሙ ፍናቴ ለአሐዱ ገልጸዋል።

የጥራጥሬና የቅባት እህሎች ወጪ ምርት የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በተያዘው በጀት ዓመት በከፍተኛ ትኩረት እየሰራበት እንደሚገኝ ተገልጿል።

በተያዘው ሩብ ዓመት የሥራ አፈፃፀምም በዘርፉ በርካታ ሥራዎች መሰራታቸውን ገልጸው፤ የጥራጥሬና ቅባት እህሎች ወጪ ምርቶች ላይ ትኩረት ተሰጥቶበት መሰራቱን የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሥራ አስፈፃሚው ወንድሙ ፍናቴ ተናግሯል።

ኢትዮጵያ ወደ አውሮፓ የምትልከውን የጥራ ጥሬ ምርት እየቀነሰ መምጣቱን ቢነገርም፤ ወደ ውጭ የሚላከውን ምርት በመጠን ደረጃ ግን ማሳደግ እየተቻለ አለመሆኑን ተገልጿል።

በአማኑዔል ክንደያ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በተያዘው ሩብ ዓመት ጎዳና ላይ የሚኖሩ 800 ሕጻናት ወደ ቤተሰቦቻቸው ተቀላቅለዋል ተባለ

ሕዳር 11/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በ2017 አንደኛ ሩብ ዓመት 800 ሕጻናትን ከጎዳና ላይ አንስቶ የማህበራዊ ተሃድሶ ስልጠናን በመስጠት፤ ወደ ቤተሰቦቻቸው መቀላቀሉን የአዲስ አበባ ሴቶች፣ ሕጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ አስታውቋል።

ከአሐዱ ጋር ቆይታ ያደረጉት የቢሮው ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሀድጉ ፀሀዬ ሕጻናቱ ከክልል ከተሞች ወደ አዲስአበባ የመጡ መሆናቸውን ገልፀው፤ "በፍላጎታቸው ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲመለሱ ተደርጓል" ብለዋል።

በ2013 በተካሄደ ጥናት ከ96 በመቶ በላይ የሚሆኑ ጎዳና ላይ የሚኖሩ ሕጻናት ከአዲስአበባ ውጪ የመጡ መሆናቸውን ያሳያል ያሉት ኃላፊው፤ በከተማዋ ይህ አይነት ችግር እንዳይፈጠር የሕዝብ አደረጃጀት በመፍጠር እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ችግሩ በሁሉም አካባቢዎች ቢኖርም እስካሁን ድረስ ግን በአፋርና ሶማሌ ክልል ብዙም አላጋጠመም ተብሏል።

በተቃራኒው በርከት ያለውን ቁጥር የሚይዙት ከደቡብ ክልል የሚመጡ ሕጻናት መሆናቸው የገለጹት አቶ ሀድጉ፤ ወደ አካባቢው በመሄድም የተለያዩ ሥራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል።

ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በክልሎች ላይ ሕጻናት ሲመጡ መመለስ ብቻም ሳይሆን እዛው እያሉ ለመደገፍ ማህበረሰቡን የግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራ፣ ከኢፌዴሪ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመቀናጀት እንዲሁም የሲቪል ማህበራትን በማሳተፍ የጋራ ትስስርን በመፍጠር እየተሰራ መሆኑን አክለዋል።

በስፍራሽ ደመላሽ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በሩብ ዓመቱ 171 ሃሰተኛ ሰነድ መገኘቱን የሰነዶች ማረጋገጫ አገልግሎት አስታወቀ

👉ተቋሙ ሃሰተኛ ሰነድን ለመቆጣጠር ዲጂታል መታወቂያ መፍትሄ ይሆናል ብሏል


ሕዳር 11/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት በአዲስ አበባ ከሕዳር 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለሰነዶች ማረጋገጥና ምዝገባ አገልግሎት ግዴታ ያደረገው ዲጂታል መታወቂያ ሀሰተኛ ሰነዶችን ለመከላከል ያስችለኛል ሲል ገልጿል።

ተቋሙ በ2017 በጀት ዓመት በመጀመሪያው ሩብ ዓመት ከአረጋገጣቸው ሰነዶች መካከል፤ 171 ሃሰተኛ ሰነዶች መገኘታቸውን፤ የተቋሙ የሕዝብ ግንኙነትና ኮምዩኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዓለምእሸት መሸሻ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

ከእነዚህም ውስጥ 148 ያክሉ ሃሰተኛ የማንነት ማረጋገጫ መታወቂያዎች ናቸው ብለዋል።

በተጨማሪም ዘጠኝ ሃሰተኛ ያላገባ ማስረጃ፣ ስድስት ሃሰተኛ የውክልና ማስረጃ፣ አንድ ሃሰተኛ ሊብሬ፣ ሁለት ሃሰተኛ የገቢዎች ክሊራንስ ጨምሮ ሌሎችም ሀሰተኛ ማስረጃዎች መገኘታቸውን ተናግረዋል፡፡

ይሁን እንጂ ተቋሙ በአዲስ አበባ በሚገኙት 16 ቅርንጫፎች ከሕዳር 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለሚሰጠው አገልግሎት ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ወይም የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ ግዴታ እንደሚሆን የገለጹት ኃላፊው፤ ይህም የተደረገው ሀሰተኛ ሰነድን ለመከላከል እንዲረዳ ነው ብለዋል።

ሀሰተኛ ሰነዶችን ለማስቀረት ከፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ በተጨማሪ ስውር የኤሌክትሮኒክስ ማህተም ተቋሙ ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።

በአበረ ስሜነህ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

ሩሲያ ዩክሬን ለፈጸመችው ጥቃት የአጸፋ ምላሽ እንደምትሰጥ ገለጸች

ሕዳር 11/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የዩክሬን ጦር ከአሜሪካ የተበረከተለትን የረጅም ርቀት መሳሪያ ወደ ሩሲያ ማስወንጨፏን ተከትሎ፤ ሞስኮ አጸፋዊ ምላሽ እንደምትሰጥ አስታውቃለች፡፡

ዩክሬን አሜሪካ ሰራሽ ሚሳኤሎችን እንድትተኩስ የባይደን አስተዳደር መፍቀዱን ተከትሎ፤ በትናንትናው ዕለት ወደ ሩሲያዋ ብርያንስክ ግዛት ስድስት ሚሳኤሎች መተኮሷ ይታወሳል።

አሜሪካ ፍቃዷን ከሰጠች ከሁለት ቀናት በኋላ ዩክሬን የተፈጸመችውን ይህን ጥቃት ሩሲያ ማክሸፏን የገለጸች ሲሆን፤ ነገር ግን የአንደኛው ሚሳኤል ፍንጣሪ በሩሲያ ጦር አቅራቢያ የተወሰነ የእሳት አደጋ ማስከተሉን አስታውቃለችል።

ይህንን ተከትሎ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ሞስኮ 'ተገቢውን ምላሽ እንደምትሰጥ' የገለጹ ሲሆን፤ "ምክንያቱም ኬቭ የግጭቱን መባባስ ትፈልጋለች" ሲሉ ገልጸዋል።

አክለውም "ዋሽንግተን ግጭቱን ለማባባስ እየሰራች ነዉ" ሲሉ ገልጸው፤ አሜሪካ መሳሪያዎቹን ለዩክሬን ከማቅረብ ባለፈ የጦር ባለሙያዎቿን ስለማሳተፏ ሩሲያ ማረጋገጧን ተናግረዋል።

"በምዕራቡ ዓለም እንደ አዲስ የተከፈተው አዲስ ጦርነት እንወስደዋለን" ያሉት ላቭሮቭ፤ "ለጥቃቱ ተገቢዉን ምላሽም እንሰጣለን" ሲሉም ተናግረዋል።

የሩሲያ የደህንነት ምክር ቤት ምክትል ሊቀመንበር ዲሚትሪ ሜድቬዴቭ በበኩላቸው በኤክስ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ፤ "ይህ ጥቃት አሜሪካ እና የኔቶ አባል ሀገራት በሩሲያ ላይ ጦርነት እንደከፈቱ ሊቆጠር ይችላል" ያሉ ሲሆን፤ "ትርጉሙ 'ሦስተኛው የዓለም ጦርነት' ማለት ነው" ብለዋል።

ዬክሬንን ጥቃት ተከትሎ ቭላድሚር ፑቲን የተሻሻለውንና የሩሲያን የኒዩክሌር መሳሪያ አጠቃቀም የሚወስነው ሕግ ማጽደቃቸውን ክሬምሊን አስታውቋል።

ይህ የኒዩክሌር ሕግ ሩሲያ በ2020 በይፋ ያወጣችው ሲሆን፤ ሕጉን ማሻሻሏን ስትገልጽ ቆይታለች፡፡ ባይደን ለኬቭ ይሁንታ መስጠታቸውን ተከትሎ በትናንትናው ዕለት ፑቲን ማሻሻያውን ማጽደቃቸው ተነግሯል፡፡

ማሻሻያው "ሩሲያ ለሚሰነዘርባት የጦር መሳሪያ ጥቃት ምላሽ ለመስጠት የኒውክሌር ጥቃት እንድትሰነዝር የሚያስችል ነው" የተባለ ሲሆን፤ "ኒዩክሌር ያልታጠቁ ሀገራት ከታጠቁት ጋር በመተባበር በሩሲያ ላይ ጥቃት ካደረሱ በሞስኮ ላይ “የጋራ ጥቃት” እንደከፈቱ ይቆጠራል" የሚል ሃሳብን ማካተቱን ሮይተርስ ዘግቧል።

በሌላ በኩል ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በምስራቃዊ ዩክሬን እየጨመረ የመጣውን የሩሲያ ወታደሮችን እንቅስቃሴ ለመገደብ የሚያስችል ጸረ-ሰው ፈንጂዎችን ለዩክሬን ለመስጠት መስማማታቸውን የቢቢሲ ዘገባ አመላክቷል።

ባይደን በዩክሬን ግዛት ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውል ጸረ-ሰው ፈንጅ ለመስጠት ቢስማሙም፤ በኬቭ በኩል ፈንጂውን የመጠቀም ፍላጎት እንደሌለ ተመላክቷል።

ከተጀመረ 1 ሺኛ ቀኑን ያስቆጠረው የሩሲያ ዩክሬን ግጭት በከፍተኛ ሁኔታ ተባብሶ የቀጠለ ሲሆን፤ ግጭቱ ወደ ሦስተኛው የዓለም ጦርነት ያመራል የሚል ስጋት ፈጥሯል፡፡

በእዮብ ውብነህ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ከታክሲ ማሕበራት ጋር መስማማቱን ገለጸ

ሕዳር 11/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የታክሲ ማሕበራት ከትራንስፖርት ቢሮ ጋር የፈጠሩት አለመግባባት መፍትሄ ማግኘቱን የከተማ አስተዳደሩ ትራንስፖርት ቢሮ ለአሐዱ ተናግሯል።

የታክሲ አሽከርካሪዎች የተማሪዎች መዉጫና መግቢያ ሰዓት አጠቃቀምን በተመለከተ የተፈጠረው አለመግባባት መፍትሔ እንደተሰጠው ነው ቢሮ የገለጸው።

ከማሕበራቱ የቀረቡለትን ቅሬታዎች ገምግሞ መፍትሔ ማስቀመጡንና ከስምምነት መደረሱን የአዲስ አበባ የትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳኛቸው ሽፈራው ለአሐዱ ተናግረዋል።

በዚህም የተማሪዎች መውጫና መግቢያ ሰዓትን ተገን በማድረግ፤ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚያስተጓጉሉና ታሪፍ የሚጨምሩ የታክሲ አሽከርካሪዎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ማሳሰቢያ የተሰጠ ሲሆን፤ የታክሲ ማሕበራቱ ከቢሮው ጋር በመተባበር ችግሩን ለመፍታት ጥረት እንደሚያደርጉ መግለጻቸውን ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

አክለውም በከተማዋ የሚሰተዋለውን የትራንስፖርት ችግር ለመፍታት በርካታ ሥራዎች መሰራታቸውን ገልጸው፤ በቀጣይ ችግሮችን ለማቃለል እተየሰራ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።

ከዚህ ቀደም የታክሲ ማሕበራቱ በርካታ ቅሬታዎች ሲያቀርቡ የነበረ ቢሆንም ችግሮቹ ከሞላ ጎደል እየተፈቱላቸው መሆኑን ተናግረዋል።

በአዲስ አበባ ያለው ሥር የሰደደ የትራንስፖርት ችግር የሚታወቅ ሲሆን፤ ከተማ መስተዳድሩ ችግሮቹን ለመፍታት የተለያዩ ጥረቶች በማድረግ ላይ መሆኑን ገጸዋል።

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ደግሞ በአዲስ አበባ እየተስተዋለ ያለውን የኮሪደር እንቅስቃሴ የትራንስፖርት ዘርፉ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ፈጥሮ መቆየቱን ይታወቃል።

የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር 'ችግሩን ፈትቼዋለሁ' ይበል እንጂ፤ የትራንስፖርት አገልግሎቱ አሁንም በርካታ ችግሮች የሚስተዋሉበት መሆኑ ይገለጻል።

በአማኑዔል ክንደያ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

"ኢትዮጵያ እንደሁኔታው የሚቀያየር ካፒታሊዝም ስርዓት ነው የምትከተለው" የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር)

ሕዳር 11/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ኢትዮጵያ የሕዝቡን ሁኔታ የሚረዳ፣ ዓለም አቀፍ ተቀባይነትንም ሊያመጣ የሚችል እንዲሁም እንደ ሁኔታው የሚቀያየር ካፒታሊዝምን እየተከተለች መሆኑ የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡

ሚኒስትሯ በ2010 ዓ.ም መጥቷል ባሉት ለውጥ አማካኝት የተለያዩ በጎ ሥራዎች መሠራታቸውን የገለጹ ሲሆን፤ ይሁን እንጂ አሁንም መንግሥት በተመረጡ ስትራቴጂ ዘርፎች ላይ እንደተሰማራ ተናግረዋል፡፡

ያደጉ ሀገራትም በዚህ መንገድ አልፈዋል የሚሉት ሚኒስትሯ፤ "ከፍተኛ ዕድገት ላይ ደርሰዋል የሚባሉት እንደ አሜሪካ ያሉ ሀገራትም መንግሥት ስትራቴጂክ በሚባሉ ዘርፎች ላይ እጁን ያስገባ ነበር" ሲሉ ገልጸዋል፡፡

አሁንም ድረስ በርካቶች 'መንግሥት በግሉ ዘርፈ ላይ ጣልቃ መግባት የለበትም' የሚሉ አስተያየቶችን እንደሚያነሱ የገለጹም ሲሆን፤ "ይህ ስህተት ነው" ብለዋል፡፡

"በተለይም መንግሥት የግል ዘርፉን በማገዝ ኢኮኖሚውን ወደ ፊት ማሳደግ ላይ ማተኮር ይኖርበታል" ሲሉም አስረድተዋል፡፡

ከመንግሥት ልማት ድርጅት ጋር በተያያዘ መንግሥት ጣልቃ ገብነትን መቃውም አዝማሚያ በተደጋጋሚ እንደሚታ ያነሱት ሚኒስትሯ፤ "የግሉ ዘርፍ ደርሶ መረከብ እስከሚጀምር ድረስ መንግሤት ውጤታማ በሆነ መንገድ መምራት አለበት" ብለዋል፡፡

መንግሥት በኃላፊነት መሰረት ልማቶች ላይ ማተኮር ስላለበት፤ የግል ዘርፉን ላይ በአስፈጊነቱ ጣልቃ እንደሚገባም ጭምር የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፍፁም አስፋ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

ፕላንና ልማት ሚኒስቴር የኢትዮጵያ የረጅም ግዜ ኢኮኖሚያዊ ለውጥን አስመክቶ የ60 ዓመት ፍኖተ ካርታ ላይ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡

በሂደቱም በ60 ዓመታት ኢትዮጵያ እየተከተለች የቆየችውን የኢኮኖሚ ፖሊሲ ምን እንደሚመሰልና በቀጣይ ምን ዓይነት ኢኮኖሚ መንገዶች እንደምከተል ሚኒስትሯ ገልጸዋል፡፡

በዚህ ኢትዮጵያ በአሁን ወቅት ተለዋዋጭ የሆነ እንደሁኔታው የሚቀያየር ካፒታሊዝም እየተከተለች እንደምትገኝም ጨምረው ተናግረዋል፡፡

በአቤል ደጀኔ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

መልካም ቀን!
አሐዱ ሬድዮ 94.3  የኢትዮጵያውያን ድምፅ!

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የመንግሥት ሠራተኞች በሳምንት 48 ሰዓት እንዲሰሩ የሚያስገድደው ረቂቅ አዋጅ ከሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባላት ቅሬታ ተነሳበት

👉አዋጁ በምክር ቤቱ
በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል

ሕዳር 10/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የመንግሥት ሠራተኞች በሳምንት ቢያንስ ከ48 ሰዓት በታች መሥራት የለባቸውም በሚል የሰፈረው አንቀፅ፤ ከአለም ዓቀፉ የሠራተኞች መብት አንፃር የሠራተኛውን መብት የሚጥስ መሆኑን ተገልጿል።

ይህ የተነሳው የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት ምክርቤቱ የ4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው ዕለት ሲያካሂድ ነው ።

በነባሩ አዋጅ የመንግሥት ሠራተኞች የሥራ ሰዓት በቀን 8 ሰዓት በሳምንት ደግሞ 39 ሰዓት እንዲሰሩ የሚደነግግ የነበረ ሲሆን፤ በአዲሱ ረቂቅ አዋጅ ወደ 48 ሰዓት ከፍ እንዲል መደረጉ አግባብነት የለውም ሲሉ የምክር ቤት አባላት ተናግረዋል።

ሠራተኞች ተጨማሪ ሰዓት የሥራ ክፍያ የሚጠይቁበትን አግባብ የሚጥስና ተጨማሪ ገቢ የሚያገኙበትን መብት የሚያሳጣ መሆኑን በመግለጽ፤ የምክር ቤቱ አባላት በረቂቁ ላይ ያላቸውን ቅሬታ ሲያነሱ ተደምጠዋል።

ይህ እንዲህ እንዳለ ረቂቅ አዋጁ የሠራተኞች ማህበራት ብቻ አወያይቶና ሠራተኞች በየመስርያ ቤቶቻቸው ሳይወያዩበት መቅረቡ ተገቢነት እንደሌለው የሕዝብ እንደራሴዎቹ ተናግረዋል።

በሠራተኞች መብት ጥበቃ ላይ ችግር እንዳይፈጥር ያላቸውን ስጋት የሰው ሀብት ልማት፣ ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገልጿል።

ረቂቅ አዋጁ ኢትዮጵያ የፈረመቻቸውን የአለም ዓቀፍ የሠራተኞች መብት አያያዝ ዙርያ ግጭት እንዳይፈጥር ያላቸውን ቅሬታ ገልጸዋል፡፡

ይህንንም ተከትሎ ረቂቅ አዋጁ በምክር ቤቱ ውይይት የተደረገበት ሲሆን፤ የፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 10/64/2010 ተሻሽሎ አዲሱ ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 1353/2017 በምክር ቤቱ በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል፡፡

👉የፀደቀው የፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ከላይ ተያይዟል፡፡

በአማኑዔል ክንደያ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የዛሬ ፕሮግራም ጥቆማ!

የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ም/ቤት በአውሮፓ ሕብረት የገንዘብ ድጋፍ የሚያዘጋጀውና የሰላም ግንባታ ላይ የሚያተኩረው ልዩ ፕሮግራም ዘወትር ማክሰኞ ከምሽቱ 11፤ 30 ጀምሮ በአሐዱ 94.3 ላይ ወደ እናንተ ውድ ቤተሰቦቻችን ያደርሳል፡፡

ፕሮግራሙን እንድትከታተሉና ሃሳብ እንድታደርሱን በአክብሮት እንጋብዛለን፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ፣ ይደውሉልን፡፡

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ!

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

#አሐዱ_ትንታኔ

ዶናልድ ትራምፕ በዋናነት የወጪ ቅነሳ ላይ የሚሰራ አዲስ ተቋም መመስረታቸው ተሰምቷል::

ተቋሙ 'ዶግ' የሚል ቅፅል ስም የተሰጠው ሲሆን፤ እንዲመሩት በትራምፕ ከተሾሙት ቢሊየነሮቹ ኤሎን መስክ እና ቪቬክ ራምሳዋሚ ጀምሮ ጥያቄ ተነስቶበታል፡፡ የዛሬው አለም ዓቀፍ ትንታኔያችን ትኩረት ነው፡፡

ትንታኔውን ለመከታተል ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👇
https://youtu.be/ZZQxpR_0I6g?si=YJDVccamMx-k9dzF

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

"በመርካቶ ሕጋዊ ግብይት እንዲደረግና ነጋዴው ደረሰኝ እንዲቆርጥ ቁጥጥር እያደረግን ነው" ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ሕዳር 10/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በመርካቶ ሕጋዊ ግብይት እንዲደረግና ለእያንዳንዱ ግብይት ነጋዴው ደረሰኝ እንዲቆርጥ ቁጥጥር እና ክትትል በመደረግ ላይ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ከንቲባ አዳነች ግብር እና ደረሰኝ ከመቁረጥ ጋር በተያያዘ ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል።

በምላሻቸውም "እንደ ሀገር ያለውን የግብይት ስርዓት በዘላቂነት ለማስተካከል የምናደርገውን ጥረት በጥናት ላይ ተመርኩዘን ክትትል ስናደርግ የቆየን ሲሆን፤ ያገኘነው ግኝት በርካታ ሕገ ወጥ የሆኑ አሰራሮች እንዳሉ ተመልክተናል" ብለዋል

በዚህም "ግማሹ ግብር እየከፈለ ሌላው የማይከፍልበት አሰራር መኖሩን ከነጋዴዎች ጋር ባደረግነው ውይይት እና ክትትል ተገንዝበናል" ሲሉም አክለዋል።

ግብር ለማስከፈል እና ደረሰኝ እንዲቆርጡ ለማድረግ በተደረገው ሂደት፤ በሀሰት ውዥንብር በመንዛትና መጋዘኖችን በመዝጋት በምሽት እቃዎች ሲጫኑ እንደነበርም ተናግረዋል።

"ይህ ፍፁም ስህተት ነው" ያሉት ከንቲባዋ፤ "በቀጣይ ሕጋዊ ስርዓት በመዘርጋት እና ለእያንዳንዱ ግብይት ደረሰኝ እንዲቆርጡ በማድረግ ግብርን በአግባቡ መሰብሰባችንን አጠናክረን እንቀጥላለን" ማለታቸውን ከከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official

Читать полностью…
Subscribe to a channel