"የማሳልፋቸውን ውሳኔዎች እና እቅዴን ለመገናኛ ብዙሃንም ሆነ ለንግዱ ማህበረሰብ የማሳወቅ ግዴታ የለብኝም" ብሔራዊ ባንክ
ሕዳር 14/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በተለያዩ ጊዜያት የማሳልፋቸውን ውሳኔዎች እና እቅዴን ለመገናኛ ብዙሃንም ሆነ ለንግዱ ማህበረሰብ የማሳወቅ ግዴታ የለብኝም ሲል ገልጿል።
ባንኩ ይህንን ያለው ከንግዱ ማሕበረሰብና የምጣኔ ሐብት ባለሙያዎች ተደጋግሞ ለሚነሳበት ጥያቄ መልስ ሲሰጥ ነው።
ብሔራዊ ባንክ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ማሻሻያን በተመለከተ ያሳለፋቸው ገንዘብ ነክ ፖሊሲዎች ከማዕከላዊው መንግሥት አስተዳደር የታቀዱ መሆናቸውን ለአሐዱ የተናገሩት፤ በባንኩ የውጭ ምንዛሪ ቁጥጥር ምክትል ዳይሬክተር አቶ አበባየሁ ዱራፌ ናቸው።
ምክትል ዳይሬክተሩ ባንኩ ያደረጋቸው ማሻሻያዎች ኢኮኖሚው እንዲሻሻልና የአገር ገቢ እንዲያድግ ጉልህ አስተዋፅኦ ማድረጋቸውን ተናግረዋል።
ማዕከላዊ ባንኩ እስካሁን የገንዘብ ስርዓቱን ለዘብተኛ በሆነ መንገድ እየመራው እንዳለም ጠቅሰው፤ አጠቃላይ ፖሊሲ ነክ ጉዳዮችን ይፋ ማድረግ እንደማይጠበቅበት ገልጸዋል።
አክለውም የውጭ ምንዛሪን ስርዓቱን ገበያ መር እንዲሆን ማስቻልን ጨምሮ፤ ለባንኮች እንዲተገብሩት የተላለፈው ከ14 በመቶ በላይ የብድር ጣርያ ተያያዥ ጉዳዮችን አንስተዋል።
ንግድ ባንኮች እርስ በእርስ የሚበዳደሩበት ስርዓት መዘርጋቱ በኢኮኖሚ ማሻሻያ ከተደረገባውና አንዳንዶቹ አዲስ ያስተዋወቃቸው የገንዘብ ገበያ ስርዓቶች መሆናቸውንም ጠቅሰዋል።
በዚህ መሰረት ሁሉንም የመንግሥት ውሳኔዎች እወቁልን እያሉ በየጊዜው ማስተዋወቁን ብሔራዊ ባንክ አስፈላጊ ብሎ እንደሚያምንበት፤ የባንኩ የውጭ ምንዛሪ ቁጥጥር ስርዓት ምክትል ዳይሬክተሩ አበባየሁ ዱራፌ ሲናገሩ ሰምተናል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በተደጋጋሚ የሚደረገውን የፖሊሲ ለውጥ ተከትሎ፤ "ገበያውን ከመጠበቅ አንፃር ጥንቃቄ የጎደላቸው ሕጎች እያወጣ ነው" በሚል ከፍተኛ ትችት ሲቀርብበት መቆየቱ የሚታወቅ ነው።
ይሁንና ባንኩ "የተሳኩ ውሳኔዎች አሳልፌያለሁ" የሚል እምነት እንዳለው ከዳይሬክተሩ መረዳት ተችሏል።
በሌላ በኩል አጠቃላይ የገንዘብ አስተዳደር ስርዓቱ ያለበትን አሁናዊ ሁኔታና የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን በተመለከተ የተሳካ ውጤት መመዝገቡን ተናግረዋል።
በተለይም ሕገ ወጥ የውጭ ምንዛሪ እንቅስቃሴዎች ለመግታት ያከናወናቸው ሥራዎች የተሳለጡና የተሳኩ እንደነበሩም ገልጸዋል።
አሁን ላይ ባንኩ በፍራንኮ ቫሉታ የወሰደውን እርምጃ ሕገወጥ የውጭ ምንዛሪ እንቅስቃሴ በፍጥነት የሚገታ ስልታዊ እርምጃ መሆኑን ተነግሯል።
የገንዘብ ሚኒስቴርና የጉምሩክ ኮሚሽን መስርያ ቤቶች ውሳኔውን ተፈፃሚ የሚያደርጉበትን ሁኔታ ለመተግበር የሚያስችሉ ስርዓቶች በመዘርጋት ረገድ እየተሰራበት መሆኑን ብሔራዊ ባንክ ገልጿል።
የባንኩ ውሳኔዎችም መለካት ያለባቸው በምጣኔ ሐብቱ በመጡት ተጨባጭ ውጤቶች መሆን እንደሚኖርበትም አቶ አበባየሁ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
በአማኑዔል ክንደያ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከ60 በላይ መምህራኖች መታሰራቸውን ተገለጸ
ሕዳር 14/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን 66 የሚደርሱ መመህራኖች "ደመወዝ ይከፈለን" የሚል በመጠየቃቸው ታስረዋል ሲል የኢትዮጵያ የመምህራን ማህበር አስታውቋል፡፡
የማህበሩ ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑቱ አቶ ሽመልስ አበበ፤ "መምህራኖቹ ደመወዝ ይከፈለን ብለው ስለጠየቁ ብቻ ለእስር ታዳርገዋል" ሲሉ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
"በየትኛውም መልክ ደመወዝ መጠየቅ ለእስር ሊዳርግ አይችልም" ያሉት ምክትል ፕሬዝዳንቱ፤ "ይህ አይነት ስርዓት አልበኝነት አካሄድ የትምህርት ስርዓቱን ለማደከም የታለም ነው" ሲሉ አውግዘዋል፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት መመህራን ማሰር የጀመረው ከባለፈው ረቡዕ ጀምሮ መሆኑን ያስታወሱም ሲሆን፤ "ይህ አይነት መምህራንን የማሸማቀቅ አካሄድ ሊቆም ይገባል" በማለት አሳስበዋል፡፡
መመህራኖቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት በክልሉ ፖሊሶች እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን፤ ከፍተኛ የሆነ ድብደባ ደርሶባቸው ለአካል ጉዳት የተዳጉም ሳይኖሩ እንዳልቀር የደረሰን መረጃ ያመለክተዋል፡፡
በውል የማይታወቁ መምህራን አሁንም የሕክምና እርዳታ የሚፈልጉ ቢሆንም፤ እርዳታ እንዲያገኙ በጸጥታ ሃይሎች ክልከላ እንደተደረገባቸው ተገልጿል፡፡
የኢትዮጵያ የመምህራን ማህበር ምክትል ፕሬዝዳንት አክለውም፤ "ስልጣንም ያልፋል፣ ሁሉም ነገር ባለበት አይቀጥልም፣ ነገር ግን በተለይ ተደጋጋሚ የመምህራን ጥያቄ ማፈን ተቀባይነት የሌለው ጉዳይ ነው፡፡ በታሪክም የሚያስወቅስ ነው" ሲሉ ቅሬታቸውን ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
መምህራኖቹ ተቃውሞ ያነሱት፤ በክልሉ መንግሥት ይሁንታ የ25 በመቶ የደመወዝ ቅነሳው ከትምህርት ቤት ርዕሰ መምህራን እና ሱፐርቫይዘሮች ላይ መደረጉን ተከትሎ እንደሆነ ተነግሯል፡፡
በኮሬ ዞን 683 መምህራኖች እንዳሉ የተገመተ ቢሆንም፤ 66 የሚደርሱት መታሰራቸው ተገልጿል፡፡
በደረጄ መንግስቱ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
"ተሃድሶ የሚወስዱት የቀድሞ ታጣቂዎች ከፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት በኃላ ያሉት ብቻ ናቸው" ብርጋዴር ጄነራል ደርቤ መኩሪያ
ሕዳር 14/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የቀድሞ ታዋጊዎች ሲባል ግርታ ውስጥ የመግባት ነገር መፈጠሩን የብሔራዊ ተሃድሶ ምክትል ኮሚሽነርና የመከላከያ ሠራዊት ተወካይ ብርጋዴር ጄነራል ደርቤ መኩሪያ ተናግረዋል፡፡
"ታጣቂዎችን የመለየቱ ሥራ በምን አግባብ ነው እየተሰራ ያለው?" የሚለው ሌላ ጥያቄ የሚያስነሳ መሆኑን የገለጹት ጄነራሉ፤ የተለያዩ ማረጋገጫዎችን መጠቀማቸውን ገልጸዋል፡፡
በዚህም "የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር እንደ ክልል ያለውን የተዋጊ ብዛት አሳውቋል" ያሉ ሲሆን፤ የሀገር መከላከያ ሚኒስቴርም ባለቤት በመሆኑ እንደ ሀገር ያለውን የታጠቀ አካላትን በመለየት ተከታትሎ ማስረጃ ማቅረቡን አስረድተዋል፡፡
ይህ ቁጥጥር የሚረጋገጠው ግን ተመዝግቦ ይፋ ሲደረግና መስፈርቶችን ሲያሟላ ብቻ መሆኑን የተገለጹ ሲሆን፤ "በስምምነቱ መሰረት ትጥቁን ያሰረከበ መሆን አለበት" ሲሉም ተናግረዋል፡፡
አንዳንድ ቦታ አሁንም የትጥቅ ትግል ውስጥ ያሉ ወገኖች መኖራቸውን ያነሱት ጀኔራል ደርቤ፤ ይህንን በሚመለከት ሌላ ኮሚሽን ሳያስፈልግ ባለው ኮሚሽን ተጠቅመው ወደ ትጥቅ መፍታት እንዲመጡ ጠይቀዋል፡፡
በዚህም በአማራ፣ ኦሮሚያ፣ ቤንሻንጉል፣ ትግራይ እና አፋር አካባቢ ላሉ ታጣቂዎች ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን፤ በአፋር ክልል ከሰሞኑ ትጥቅ የማሰፈታት ሂደቶች መኖራቸውንም ተናግረዋል፡፡
የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን የጀመረው ትጥቅ የመፍታትና ወደ ማህበረሰብ የመቀላቀል ሥራ በትግራይ ክልል መቀሌ የተጀመረ ሲሆን፤ በመጀመሪያ ዙር 320 ታጣቂዎች ወደ ተሃድሶ ማዕከል መግባታቸው ተገልጿል፡፡
በአቤል ደጀኔ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
#ADVERTISMENT
#ጊፍትሪልስቴት
ታላቅ የምስራች!
**
ጊፍት ሪል ስቴት ከ10% ቅድመ ክፍያ ጀምሮ በ22 ሳይቶቹ ቅንጡ አፓርትመንቶችን እና የንግድ ሱቆችን ለሽያጭ አቅርቧል፡፡
ይህ ሳይት ለአፓርትመንትና ንግድ ሱቆች የሚውሉ G+25 ሶስት መንታ ህንጻዎች ያሉት ሲሆን የዚህ 6ኛ መንደር መለያዎች፡-
•ከባለአንድ እስከ ባለአራት መኝታ ክፍሎች ያሉት፣
•ለመኖሪያም ሆነ ለንግድ ተመራጭ አካባቢ የሆነ፣
•በአንድ ወለል ሶስት ቤቶች ብቻ ያሉት፣
•በእያንዳንዱ ወለል ስድስት አሳንስር ያለው፣
•አራት ቤዝመንት ያሉት በቂ የመኪና ማቆሚያ የተዘጋጀለት፣
•24 ሰዓት የኤሌክትሪክ፣ ኢንተርኔትና ውሃ አቅርቦት አሉት፣
ጊፍት ሪል ስቴት
ማህበረሰብን እንገነባለን!
ለበለጠ መረጃ፡-
Website: https://www.giftbusinessgroup.com
Twitter: https://twitter.com/GIFTBusinessG
YouTube: www.youtube.com/channel/UCcqr7cpVv9ski-F7haxXx4w
Facebook: www.facebook.com/profile.php?id=100090918391017...
Telegram: /channel/giftbusinessgroup
Short Code: 8055
#አሐዱ_ትንታኔ
ትንታኔውን ለመከታተል ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👇
https://youtu.be/D-Ym20sgESM?si=AEOonzBrxMMdLro_
"አለም ዓቀፉ ፍርድ ቤት ያወጣው የእስር ማዘኛ 'ፀረ-ሴማዊ' ውሳኔ ነው" ቤንያሚን ኔታንያሁ
ሕዳር 13/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የዓለም ዓቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በእርሳቸው እና በቀድሞው የመከላከያ ሚኒስትር ዮአቭ ጋላንት ላይ ያስተላለፈው የእስር ውሳኔ ማውገዛቸው ተነግሯል፡፡
"ይህ ፀረ-ሴማዊ ውሳኔ ነው" ያሉት ኔታኒያሁ፤ በአለም ዓቀፉ ፍርደድ ቤት የቀረበባቸውን ክስ እንደማይቀበሉት ገልጸዋል፡፡ "በጦርነቱ ወቅት በሲቪሎች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለማስወገድ የምንችለውን ሁሉ ስናደርግ ቆይተናል" ሲሉም መናገራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
አክለውም አለም ዓቀፉ ፍርድ ቤት (አይሲሲ) “በውሸት ሰላማዊ ሰዎች ላይ አነጣጥረዋል” በሚል እየከሰሳቸው መሆኑን ተናግረዋል።
አለም ዓቀፉ ፍርድ ቤት በበኩሉ "ኔታኒያሁና የመከላከያ ሚኒስትሩ ዩአቭ ጋላንት ሆን ብለው በሰላማዊ ሰዎች ላይ ሲያነጣጥሩ ነበር" ሲል ከሱዋቸዋል፡፡
በዚህም "ኔታንያሁ እና ጋላንት የአለም ዓቀፍ የሰብአዊ ህግን በመጣስ በጋዛ ለሚኖሩ ነዋሪዎች ሰብአዊ እርዳታዎችን እንዳይደርሳቸው አድርገዋል" ያለ ሲሆን፤ በጋዛ የውሃ አቅርቦት እና ሆስፒታሎች የህክምና አገልግሎት የመስጠት አቅም ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳድረዋል ሲል በክሱ አመላክቷል።
አለም ዓቀፉ ፍርድ ቤት (አይሲሲ) ኔታኒያሁና የመከላከያ ሚኒስትሩ ዩአቭ ጋላንት በተጨማሪ፤ ለሐማሱ አዛዥ መሐመድ ዴይፍም የእስር ማዘዣ ያወጣ ሲሆን፤ እስራኤል ግን አዛዡ በጋዛ ውስጥ በሐምሌ ወር መገደሉን ተናግራለች።
የአይሲሲ ዳኞች ሦስቱ ሰዎች በእስራኤል እና በሐማስ መካከል እየተደረገ በሚገኘው ጦርነት ለፈጸሙት ጥፋት “የወንጀል ተጠያቂነት” መኖሩን ለማመን “በቂ ምክንያቶች” እንዳሉ ተናግረዋል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በኔታኒያሁና በመከላከያ ሚኒስትሩ ዩአቭ ጋላንት ላይ የቀረበውን ክስ "አሳፋሪ እርምጃ" ብለውታል፡፡
“አይሲሲ ምንም ይሁን ምን በእስራኤል እና በሐማስ መካከል ምንም ዓይነት እኩልነት በጭራሽ የለም። በደኅንነቷ ላይ የሚደርሱ ስጋቶችን ለመከላከል ሁሌም ከእስራኤል ከጎኑ እንቆማለን” ሲሉ ባይደን ባወጡት መግለጫ ተናግረዋል።
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
በኢትዮጵያ የፖለቲካ አሰራር የጋራ አመራር ስርዓት የለም ሲሉ ምሁራን ገለጹ
ሕዳር 13/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ኢትዮጵያ ላለፉት በርካታ ዓመታት የመንግሥታት የተናጠል አመራር እንጂ የጋር አመራር ስርዓት አለመኖሩን አሐዱ ያነጋገራቸው ምሁራን ተናግረዋል።
የጋራ አመራር፣ የጋራ ሃላፊነትና የጋራ ተጠያቂነት እንዲኖር ለማስቻል የሚያግዝ የአመራር መንገድ ነው የሚሉት፤ የታሪክ ባለሙያው አቶ ደረጄ ተክሌ ናቸው።
"የጋራ አመራር ልምድ አለመኖር፣ መሪዎች በሚኒስተሮቻቸው ባለመተማመን በሁሉም የመንግሥት ተቋማት ላይ ጣልቃ በመግባት ውሳኔ የመስጠት ሁነት እና መሪዎች ገጽታ የመገንባት ፍላጎታቸው የጋራ አመራር እንዳይኖር የሚያደርግ ነው" ሲሉ ገልጸዋል።
"ፓለቲካዊ ታሪካችን የአንድ ሰው ሚና በስፋት የሚስተዋልበት ነው" ያሉት ደግሞ የአለም አቀፍ ግንኙነት መምህሩ አለሙ አራጌ ሲሆኑ፤ "ይህም መሪዎች የጋራ አመራርን ተግባራዊ ሊያደርጉ የሚሹ የመከራከር የመጠየቅ ዝንባሌ ያላቸውን አካላት አጠገባቸው እንዲርቁ የሚያደርጉበት ነው" ሲሉ ገልጸዋል።
የጋራ አመራር (Collective leadership) እንደ ሀገር ቢኖር የተሻለ ቢሆንም በኢትዮጵያ በተግባር ያለው የአንድ ሰው አመረራር ነው በማለትም አክለዋል።
"የጋራ አመራር በሀገራት ላይ ስልጣን በአንድ አመራር ላይ ከመሆን ይልቅ በተለያዩ አካላት እጅ እንዲሆን ያደርጋል" የሚሉት ምሁራኑ፤ ስልጣን በአንድ አመራር ላይ የሚጫንበት ሂደት አሁንም መኖሩን ያነሳሉ።
ስለሆነም በኢትዮጵያ የጋራ አመራርን ተግባራዊ ማድረግ ከተቻለ ተለዋዋጭ በሆኑ በሀገር፣ አህጉር እና አለም ዓቀፋዊ ሁነቶች ውሰጥ ያለመናወጥ የሚያልፍ ትውልድን መፍጠር ያስችላል ብለዋል።
በፍርቱና ወልደአብ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ሕብረተሰቡ ሪሊፍ የተባለ ሕገ ወጥ መድሃኒት ከመጠቀም እንዲቆጠብ ማሳሰቢያ ተሰጠ
ሕዳር 13/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ሪሊፍ (RELIEF) የተባለና በውስጡ ዲክሎፌናክ፣ ፓራሲታሞል፣ ክሎረፊኒራሚን እና ማግኒዥየም ትራይሲሊኬት እንዳለው የሚገመት ሕገወጥ መድኃኒት፤ በኢትዮጵያ ገበያ በስፋት እየተዘዋወረ መሆኑ እንደተደረሰበት የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን ገልጿል።
ይህ መድኃኒት በሕጋዊ መንገድ በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ያልተመዘገበ በመሆኑ፤ ጥራቱ፣ ደህንነቱና ውጤታማነቱ እንደማይታወቅ አስታውቋል።
በተጨማሪም፣ የዚህ መድኃኒት የጎንዮሽ ጉዳቶች የምግብ ፍላጎት ማጣት፣ ተቅማጥ፣ የሆድ ህመም፣ ማቅለሽለሽ ፣ ማስታወክ፣ እንቅልፍ ማጣት፣ ድካም፣ የእይታ መዛባት፣ መፍዘዝ፣ ራስ ምታት፣ የቆዳ ሽፍታ፣ የጉበት ኢንዛይሞች መጨመርና ለረጅም ጊዜ ጥቅም ላይ ሲውል የኩላሊት ጉዳትን እንደሚያመጣ አመላክቷል።
ይህንን መድኃኒት ለረጅም ጊዜ መጠቀም ከባድ የጉበት፣ የኩላሊት ጉዳት፣ የልብ ድካም እና ስትሮክ የመያዝ እድልን ከፍ ሊያደርግ እንደሚችልም ጥናቶች ማመላከታቸውን ባለስልጣኑ አስታውቋል።
በመሆኑም ሕብረተሰቡ ይህንን መድኃኒት ከመጠቀም እንዲቆጠብ እና መድኃኒቱን ጥቅም ላይ ሲውል ከተገኘ፤ በነጻ ስልክ ቁጥር 8482 በመደወል ለባለስልጣኑ ወይም ለክልል ጤና ተቆጣጣሪ አካላት እንዲጠቁሙ ጥሪ አቅርቧል።
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ኢትዮጵያ የግብርና ምርቶቿ በአለም ዓቀፍ ገበያ የምትሸጥበትን ዋጋ መወሰን እየቻለች አይደለም ተባለ
👉 የመሸጫ ዋጋ ተመኑን የሚወስኑት ሌሎች ባለጉዳዮች መሆናቸውን ተነግሯል
ሕዳር 13/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ኢትዮጵያ እንደ አኩሪ አተር፣ ቦለቄና ተልባ የመሳሰሉት የግብርና ምርቶችን የምትሸጥበት ዋጋ የመደራደር አቅም እያነሳት መምጣቱን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።
ኢትዮጵያ የግብርና ምርቶቿን የመሸጫ ዋጋ ተመን ማውጣት የተሳናት፤ "በአለም ገበያ የምታቀርበው ምርት አንዴ ከፍ አንዴ ዝቅ በማለት የሚዋዥቅ በመሆኑ ነው" ተብሏል።
ለዚህም ካለው አቅም አንፃር በበቂ እየተጠቀመች እንዳልሆነና በዘርፉ ከወጪ ንግድ የሚገኘውን ገቢ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እያሳደረ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ወደ ውጭ የሚላኩ የግብርና ምርቶች የመሸጫ ዋጋ ተመን ማውጣት እንዳትችል ካደረጓት ምክንያቶች አንዱ፤ የምርት ጥራት ዝቅተኛ የመሆን ጉዳይ መሆኑም ተጠቅሷል።
ኢትዮጵያ የግብርና ምርቶቿን በአለም ገበያ በሚወሰነው ገበያ እየተሸጠ በመሆኑ ይህን እክል ለማስተካከል የተለያዩ ሥራዎች እየተሰራ መሆኑን የሚኒስቴሩ የኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈፃሚው ወንድሙ ፍላቴ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
ሚኒስቴር መስርያ ቤቱ ይህንን ችግር ለመፍታት የተለያዩ ስትራቴጂዎች ወይም አሰራሮች ነድፎ እየተንቀሳቀሰ መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ የግብርና ምርቶች በአለም ዓቀፍ ደረጃ ተፈላጊነታቸው እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ፤ ዘርፉን በማዘመን ረገድ የግሉ ክፍለ ኢኮኖሚ የሚጠበቅት ተግባር መኖሩን ያነሱም ሲሆን፤ መንግሥት ያለበትን ቀሪ የቤት ሥራ እንዳለ ተናግረዋል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህም በተለይም የጥራጥሬና ቅባት እህሎች እንዲሁም ቅመማ ቅመም በአለም ዓቀፍ ደረጃ ተቀባይነቱ እያደገ መምጣቱን የኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈፃሚው ለአሐዱ ገልጸዋል።
የንግዱን ሚዛን ለማስተካከል የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከተለያዩ አገራት የንግድ ሚኒስትሮች ጋር እየተነጋገረ ይገኛል ተብሏል።
በቅርቡም ከቻይና መንግሥት የንግድ ሚኒስቴር ባልደረቦች ጋር በተደረሰው ስምምነት መሰረት፤ ኢትዮጵያና ቻይና በየገንዘቦቻቸው እንዲነግዱ ከስምምነት ላይ መደረሱን አሐዱ መዘገቡ ይታወሳል።
በአማኑዔል ክንደያ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ኢትዮጵያ በሕጻናት መቀንጨር የምታጣው 55 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በእጥፍ ሊጨምር እንደሚችል ተነገረ
ሕዳር 13/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ኢትዮጵያ በሕጻናት መቀንጨር ምክንያት በጤና፣ በትምህርት እንዲሁም በምጣኔ ሃብት ዘርፎች በዓመት 55 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር እንደምታጣ፤ የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከኢኮኖሚ ኮሚሽን ፎር አፍሪካ እና ከዓለም ምግብ ፕሮግራም ጋር በመሆን የተጠናው ጥናት ያመላክታል።
ይህም ወደ አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት GDP ሲለወጥ፤ በየዓመቱ 16 ነጥብ 5 በመቶ እንደሚታጣ ይጠቁማል።
ይሁን እንጂ ይህ ጥናት ከተጠና 15 ዓመታት የተቆጠሩ እንደመሆኑ መጠን፤ በአሁኑ ወቅት የምታጣው ሀብት በእጥፍ ሊጨምር እንደሚችል በኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በምግብ ሳይንስና ስነ-ምግብ ምርምር ዳይሬክቶሬት ውስጥ መሪ ተመራማሪ ዶ/ር አረጋሽ ሳሙኤል ለአሐዱ ተናግረዋል።
አክለውም የሕጻናት መቀንጨር በአሁኑ ወቅት እየጨመረ መሆኑን የገለጹ ሲሆን፤ በትክክል ምን ያክል እንደሆነ በቅርቡ ይፋ የሚደረግ ጥናት መኖሩን ጠቁመዋል።
ስለሆነም እዚህ ላይ በትኩረት መስራት የሚገባ መሆኑን ያመላከቱት መሪ ተመራማሪዋ፤ ሕጻናት በተወለዱ በአንድ ሺሕ ቀናት ውስጥ ወይም ከተወለዱ ሁለት ዓመት እስከሚሆናቸው ድረስ በቂ ንጥረ-ነገር እንዲያገኙ አስፈላጊውን ክትትል ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል።
ለሕጻናት መቀንጨር የተለያዩ መንስኤዎች ያሉ ቢሆንም በዋናነት ከእናት ጋር የተያያዘ ነው የተባለ ሲሆን፤ "እናት በእርግዝና ወቅት በቂ የሆነ ተመጣጣኝ ምግብ ሳትመገብ ስትቀር እንዲሁም በተለያዩ በሽታዎች ተጠቅታ ከነበረ የሕጻናት መቀንጨር ይከሰታል" ብለዋል።
በፈረንጆቹ 2023 ዩኒሴፍ ኢትዮጵያ ይፋ እንዳደረገው ከሆነ፤ በኢትዮጵያ 39 በመቶ እድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ ሕጻናት መቀንጨር ሲያጋጥማቸው በተመሳሳይ 21 በመቶ ያክሉ ደግሞ መቀጨጭ ወይም የሚገባቸውን ክብደት እንዳላገኙ አመላክቷል።
በአበረ ስሜነህ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ከተማ አስተዳደሩ በመርካቶ ሸማ ተራ አካባቢ በእሳት አደጋ ንብረት ለወደመባቸው ነጋዴዎች የ20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ
ሕዳር 13/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መርካቶ ሸማ ተራ አካባቢ ተከስቶ በነበረው የእሳት አደጋ ሱቅ የተቃጠለባቸው ነጋዴዎችን በጊዜያዊነት መልሶ ለማቋቋም የ20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል።
በድጋፍ መርሃ ግብሩ ወቅት ንግግር ያደረጉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ፤ "አካባቢው ደረጃውን በጠበቀ መልኩ መልሶ እስኪገነባ ሱቅ ለተቃጠለባቸው ነጋዴዎች የመስሪያ ቦታ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተገንብቶ እንዲጠናቀቅ ከተደረገው የ20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ በተጨማሪ የአይነት እና የቴክኒክ ድጋፎችን እናደርጋለን" ብለዋል።
በአካባቢው ያለውን ጥግግትና መጨናነቅ በዘላቂነት በመቅረፍ፣ የተሽከርካሪ መንገድን በማካተት እንዲሁም ለአደጋ ተጋላጭ በማያደርጋቸው መልኩ በዘላቂነት በአክሲዮን ተደራጅተው ደረጃውን የጠበቀ የገበያ ማዕከል መገንባት እንዲችሉ የከተማ አስተዳደሩ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርግ ከንቲባ አዳነች ጨምረው ገልጸዋል።
ድጋፉን የተቀበሉት የአካባቢው ነጋዴ ተወካዮች በበኩላቸው የከተማ አስተዳደሩ አደጋው ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ ላደረገው ድጋፍ እና ክትትል አመስግነው፤ ድጋፉ በፍጥነት ወደ ሥራ እንዲገቡ የሚያደርጋቸው መሆኑን መናገራቸውን ከከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
በኢትዮጵያ ከ13 ሺሕ በላይ ሕጻናት ከኤች.አይ.ቪ ቫይረስ ጋር እንደሚወለዱ ተገለጸ
ሕዳር 12/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ በያዝነው የ2017 ዓ.ም. ብቻ 13 ሺሕ 312 ሕጻናት በኤች.አይ.ቪ ቫይረስ ተይዘው መወለዳቸዉን የጤና ሚኒስቴር አስታዉቋል።
ለዚህ ደግሞ ዋናኛ ምክንያት የሆነዉ እናቶች በእርግዝና ወቅት በቂ የሆነ የሕክምና ክትትል ባለማድረጋቸዉ መሆኑን በሚኒስቴሩ የኤች አይ ቪ ፕሮግራም ባለሙያ አቶ ምላጎ ሻፊ ተናግረዋል።
ሕጻናቶች ሲወለዱ እስከ ሁለት ወር ባለዉ ጊዜዉ ዉስጥ የኤች አይ ቪ ምርመራ ማድረግ እንዳለባቸ ባለሙያው አሳስበዋል።
"ነገር ግን በአሁኑ ወቅት እናቶች ከወለዱ በኋላ ልጃቸዉን ለማስመርመር ወደ ጤና ተቋማት ባለመሄዳቸዉ ተግዳሮት ፍጥሯል" ነዉ ያሉት።
"ይህ ደግሞ እናቶች ለበሽታዉ የሚሰጡት ግንዛቤ አናሳ በመሆኑ ጨቅላ ሕጻናት ሕይወታቸዉ እያለፈ ነዉ" ሲሉ ስጋታቸዉን ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ እናቶች ከወለዱ በኋላ ልጆቻቸዉን ወደ ጤና ተሟት ይዘዉ በመምጣት ምርመራ የማያስደርጉ ከ53 በመቶ በላይ ነዉ ተብሏል።
በደረጄ መንግስቱ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
በጋምቤላ ክልል በአራት ወራት ውስጥ ከ 80 ሺሕ በላይ ዜጎች በወባ በሽታ መጠቃታቸው ተገለጸ
👉በክልሉ በሳምንት ከሦስት ሺሕ በላይ ሰዎች በወባ በሽታ ይያዛሉ ተብሏል
ሕዳር 12/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በጋምቤላ ክልል ባለፉት አራት ወራት ውስጥ ብቻ ከ80 ሺሕ በላይ ዜጎች በወባ በሽታ መጠቃታቸውን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታውቋል።
በአገር ዓቀፍ ደረጃ በተጀመረው ወባን የመከላከልና የመቆጣጠር ንቅናቄ መሰረት፤ በጋምቤላ ክልል ከ150 ሺሕ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የነፃ ሕክምና አገልግሎት መሰጠቱን የክልሉ ጤና ቢሮ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ወንድማገኝ በላይነህ ለአሐዱ ገልጸዋል፡፡
ከዚህም ውስጥም ከ80 ሺሕ በላይ የሚሆኑት በወባ በሽታ መጠቃታቸውን የገለጹት ኃላፊው፤ በሳምንት ከሦስት ሺሕ በላይ ሰዎች በሽታው እንደሚያዙ መረጋገጡን ተናግረዋል።
የሕዝብ ግኑኙነት ኃላፊው አክለውም በክልሉ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ በበሽታው ተጠቂ ቢሆንም፤ እስካሁን ግን ሕይወቱ ያለፈ ሰው የለም ብለዋል።
ለበሽታው መራባት ዋንኛው ምክንያት በክልሉ በተደጋጋሚ የሚከሰተው ጎርፍ መሆኑን የገለጹም ሲሆን፤ ይህን ችግር ለመፍታት የተለያዩ ሥራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
በክልሉ ያለውን የወባ ስርጭት ለመከላከልም ከ200 ሺሕ በላይ የአልጋ አጎበር ስርጭት፣ ከ100 ሺሕ በላይ ቤቶች የፀረ ወባ ኬሚካል ርጭት ክንውን እንዲሁም ኅብረተሰቡን በማሳተፍ ለወባ ትንኝ መራቢያ አመቺ የሆኑ ቦታዎችን የማዳፈን ተግባር መከናወኑን ገልጸዋል።
እንዲሁም በክልሉ የወባ በሽታ ስርጭትን ለመግታት በሚደረገው ጥረት የወባ ሳምንት ክልላዊ ንቅናቄ መድረክ ላይ፤ የጋምቤላ ሕዝብ ዓመቱን ሙሉ ለበሽታው ተጋላጭ መሆኑ ተጠቅሷል።
የኢትዮጵያ መልክዓ ምድርም 75 በመቶ ለስርጭቱ አመቺ ሲሆን፤ 69 በመቶ የሚሆነው ሕዝብ ደግሞ በዚሁ አካባቢ የሚኖር በመሆኑ ለበሽታው ተጋላጭ ነው ተብሏል።
በክልሉ ለወባ በሽታ መጨመር ለቀበሌዎች ከሚላኩ የወባ መከላከያ የአልጋ አጎበሮች በአንዳንድ ቀበሌዎች በአግባቡ ባለመያዛቸውና ለስርቆት መዳረጋቸው እንደ ዋና ምክንያት ተጠቅሷል።
በተጨማሪም የጤና ኤክስቴንሽን ሠራተኞች በሥራ ቦታቸው አለመገኘት፣ የፀረ ወባ መድሀኒትን በአግባቡ ያለመውሰድ እና የአልጋ አጎበርን ከታለመለት አላማ ውጪ መጠቀም የሚሉት ተጠቃሽ መሆናቸውም ተመላክቷል።
በስፍራሽ ደመላሽ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የዓመቱ ምርጥ አየር መንገድ ሽልማትን ለ8ኛ ጊዜ አሸነፈ
ሕዳር 12/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአፍሪካ አየር መንገዶች ማኅበር የዓመቱ ምርጥ አየር መንገድ ሽልማትን አሸንፏል፡፡
አየር መንገዱ በማኀበሩ በዓለም አቀፍ አገልግሎት የዓመቱ ምርጥ አየር መንገድ ተብሎ ሲሸለም የአሁኑ ለስምንተኛ ጊዜ ነው፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሽልማቱን ያሸነፈው በግብጽ ካይሮ በተካሄደው 56ተኛው የማኀበሩ አጠቃላይ ስብሰባ ላይ መሆኑን አየር መንገዱ አስታውቋል፡፡
የአፍሪካ አየር መንገዶች ማኅበር ዓመታዊ ሽልማት፤ በአፍሪካ የአቪዬሽን ኢንዱስትሪ ውስጥ የላቀ ዓለም አቀፍ አገልግሎት አሰጣጥ፣ ፈጠራ እና ተወዳዳሪነት ላሳዩ አየር መንገዶች፣ ግለሰቦች እና አገልግሎት ሰጪዎች በየዓመቱ እውቅና ይሰጣል።
በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በፈረንጆቹ ሰኔ 2023 በአስደናቂ ትርፋማነት፣ ከሌሎች አየር መንገዶች ጋር በምሳሌነት የሚጠቀስ ትብብር፣ በአህጉሪቱ ያለው የካርጎ አገልግሎት እድገት እና አፍሪካን ከተቀረው አለም ጋር የሚያገናኝ ሰፊ የሥራ አፈጻጸም በማስመዝገብ ላቅ ያለ አፈጻጸም በማሳየቱ እውቅና አግኝቷል።
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
#አሐዱ_አብይ_ጉዳይ
ጥንቅሩን ለመከታተል ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👇
https://youtu.be/I657y-_k_YI?si=5BJAQbP9cRmWDbzg
በሰሜን ሸዋ ዞን አለልቱ መንገድ ላይ ከባድ የትራፊክ አደጋ መከሰቱ ተሰማ
ሕዳር 14/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በዛሬው ዕለት በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አለልቱ መንገድ ላይ ከባድ የትራፊክ አደጋ መድረሱን አሐዱ የደረሰው መረጃ ያመለክታል፡፡
አደጋው አለልቱ አቅራቢያ ጮሌ ጸበል ጋር የተከሰተ ሲሆን፤ ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ የሚጓዝ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ከሲኖ ትራክ ተሸከርካሪ ጋር በመጋጨቱ መከሰቱን በስፍራው ያሉ ነዋሪዎች ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
በአደጋው በርካታ ሰዎች መጎዳታቸውን እንዲሁም ለጊዜው ቁጥራቸው ያልታወቀ ሰዎች ሕይወት ማለፉን የተናገሩት ነዋሪዎቹ፤ የሲኖ ትራክ ተሸከርካሪው ረዳት መኪና ውስጥ ተቀርቅሮ በመቅረቱ እርሱን ለማውጣት ከአንድ ሰዓት በላይ ጥረት ቢደረግም ሕይወቱን ማትረፍ አለመቻሉን ተናግረዋል፡፡
በዚህም ምክንያት መንገዱ ለእረጅም ሰዓት መዘጋቱ የተነገረ ሲሆን፤ በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች ወደሆስፒታል የማድረስ ሥራ እየተሰራ መሆኑም ተገልጿል፡፡
አደጋው ያደረሰውን ጉዳት መጠን አስመልክቶ፤ አሐዱ ዝርዝር መረጃ ባገኘበት ሰዓት ወደእናንተ ያደርሳል፡፡
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
በሩብ ዓመቱ ለ871 የምግብ አይነቶች የገበያ ፈቃድ መሰጠቱ ተገለጸ
ሕዳር 14/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በ2017 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት ለ32 ተጨማሪ ምግብ፣ ለ4 የሕጻናት ምግብ፣ ለ96 ሌሎች ልዩ ልዩ የምግብ አይነት እና ለ739 በቅድመ ማሳወቅ የምዝገባ ዘዴ በአጠቃላይ ለ871 ምግብ አይነቶች የገበያ ፈቃድ መስጠቱን የኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን አስታውቋል።
ባለስልጣኑ በተመረጡ 31 የምግብ አይነቶች ውስጥ 222 ናሙናዎች ላይ የኮንሳይመንት ጥራት ምርመራ ተደርጎ 155 ናሙናዎች የአገሪቱን የጥራት ደረጃ በማሟላታቸው ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ ተደርጓል ብሏል።
በተጨማሪም፤ ለ38 የምግብ አምራቾች እና ለ288 የምግብ ላኪ አስመጪና አከፋፋዮች የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት መሰጠቱን ገልጿል።
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በሩብ ዓመቱ ከ54 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ የተለያየ የምግብ ምርት እንዲሁም፤ ከ97 ሺሕ ብር በላይ የሚገመት ደረጃውን ያልጠበቀ የመዋቢያ ምርት እንዲወገድ አድርጊያለሁ ብሏል።
የኢትዮጵያ የምግብና የመድኃኒት ባለስልጣን በአዋጅ ቁጥር 1112/2011 የምግብ ጥራትና ደህንነትን ለማስጠበቅ ስልጣን በተሰጠው አግባብ መሰረት፤ ጥራትና ደህንነቱ ባልተረጋገጠ የምግብ ምርት የህብረተሰቡ ጤና አደጋ ላይ እንዳይወድቅ በምግብ ቁጥጥር ላይ የተለያዩ ሥራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡
በስፍራሽ ደመላሽ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
በኦሮሚያ ክልል በሩብ ዓመቱ 400 ሺሕ የሚሆኑ ሕገ ወጥ አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ መወሰዱ ተገለጸ
ሕዳር 13/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኦሮሚያ ክልል በተያዘው የ2017 ሩብ ዓመት ብቻ ከመመሪያው ወጭ በማሽከርከር 400 ሺሕ የሚሆኑ አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን የክልሉ ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል፡፡
ቢሮው በዚህም ግማሽ ሚሊዮን ብር መሰብሰብ መቻሉን ለአሐዱ ገልጿል፡፡
በተያዘው ዓመት ሕገ ወጥ አሽከርካሪዎችን ለመቆጣጠር 6 ነጥብ 1 ሚሊዮን ተሸርካሪዎች ላይ ቁጥጥር ለማድረግ እቅድ የተያዘ ሲሆን፤ በሩብ ዓመቱ 2 ነጥብ 4 ሚሊዮን በሚሆኑት ተሸከርካሪዎች ላይ ቁጥጥር ማድረጉን የኦሮሚያ ክልል ትራንስፖርት ኤጀንሲ የመንገድ ደህንነት ዳይሬክተር አቶ አለሙ ለማ ተናግረዋል፡፡
እንደ ክልል የትራፊክ ቁጥጥ በማድረግ ሕገ ወጥ አሽከርካሪዎች ላይ የተወሰደ እርምጃ መሆኑን አንስተው፤ ቅጣቱ መንጃ ፈቃድ ሳያወጡ እንዲሁም መንጃ ፈቃድ ኖሯቸው ሳይዙ በሚያሽከረክሩ ላይ የተወሰደ እርምጃ መሆኑን አንስተዋል፡፡
አክለውም የተለያዩ የትራፊክ መመሪያዎችን በመጣስ ግማሽ ሚሊዮን ብር መሰብሰቡን የገለጹ ሲሆን፤ የትራፊክ ደህንነትን ለማረጋገጥ ለማህበረሰቡ ግንዛቤ በመስጠት በስፋት እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የትራፊክ ደህንነትን ለማረጋገጥ እንዲሁም የማህበረሰቡን መብትና ግደታውን እንዲያውቅ ከማድረግ አንጻር በገበያዎች፣ በስብሰባዎች፣ እንዲሁም ሰዎች በሚሰበሰቡበት አካባቢ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን እየሰሩ መሆኑንም አቶ አለሙ ገልጸዋል፡፡
በአለምነው ሹሙ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ) እገዳ እንደተጣለበት ተሰማ
ሕዳር 13/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል በምህፃሩ (ካርድ) የተሰኘው የሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅት እገዳ እንደተጣለበት ተሰምቷል።
ድርጅቱ ከሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን በደረሰው ደብዳቤ መሰረት ከሥራው እግድ እንደተጣለበ በፅሁፍ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
ባለስልጣኑ እግዱን ለመጣል ያስረዳበት ምክንያትም "የካርድን እንቅስቃሴ የሚገልፅ አይደለም" ሲል ድርጅቱ በመግለጫው ገልጿል።
ከሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ከተቋቋመት ዓላማ ውጭ በመንቀሳቀስ የአገርን ጥቅም የሚጎዱ ተግባራት ላይ ተሠማርቷል የሚል በደብዳቤ ማሳወቁ ተነግሯል።
ካርድ በበኩሉ ውሳኔው አስፈላጊ የሆኑትን ሕጋዊ አካሄዶችን ያልተከተለ መሆኑን በመግለፅ፤ ከዓላማው ውጪ ምንም ዓይነት ተግባራት ተሳትፎ እንደሌለው አስታውቋል።
ድርጅቱ በፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ፍጹም ገለልተኛ ተቋም መሆኑን በፅሁፍ ያሰራጨው መግለጫ ላይ ጠቅሷል።
ካርድ በኢትዮጵያ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች የሚከሰቱ ተግዳሮቶች መፍትሔ እንዲገኝ በመንቀሳቀስ ላይ ያለ ተቋም መሆኑን ገልጾ፤ "በምክንያትነት የቀረቡ ሐሳቦች የድርጅቱን አይገልፁትም" ብሏል።
በአማኑዔል ክንደያ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
#አሐዱ_ትንታኔ
ዶናልድ ትራምፕ ኋይትሃውስ ከመረከባቸው በፊት አሜሪካ እና ሩሲያ ወደ ጦርነት ሊገቡ እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡
"አባቴ ቤተ መንግሥት ከመግባቱ በፊት ጆ ባይደን 3ኛውን የአለም ጦርነት ለማስጀመር እየሞከሩ ነው" ሲል፤ የትራምፕ ልጅ ትራምፕ ጁኒየር ቅሬታ አቅርቧል፡፡ በዚህ እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የዛሬው ዓለም አቀፍ ትንታኔያችን ትኩረቱን አድርጓል፡፡
ትንታኔውን ለመከታተል ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👇
https://youtu.be/UxfAj-Xyuxc?si=zQ5TIM5j8E3VZYel
ሩሲያ በፖላንድ፣ አሜሪካና ብሪታኒያ ላይ ጥቃት ልትፈጽም እንደምትችል አስጠነቀቀች
👉የሩሲያ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ፖላንድ የመጀመሪያ ኢላማ እንደምትሆን ገልጿል
ሕዳር 13/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ሩሲያ በአሜሪካ እና ብሪታኒያ ላይ ጥቃት ልትፈጽም እንደምትችል ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን አስጠንቅቀዋል፡፡
ፑቲን ዩክሬን የአሜሪካ እና የእንግሊዝ የጦር መሳሪዎችን ተጠቅማ ጥቃት መፈጸሟን ተከትሎ በሰጡት መግለጫ፤ “አሜሪካ፣ ብሪታኒያ እና ፈረንሳይ አርሚ ታክቲካል በተባለው ዘመናዊ ሚሳኤል ሩሲያ ላይ ጥቃት እንዲፈጸም አድርገዋል” ብለዋል፡፡
ለዚህም ጥቃት ሩሲያ አዲስ የስትራቴጂክ ሚሳኤሎችን በመጠቀም የአፀፋ ምላሽ መስጠቷን የገለጹም ሲሆን፤ በአፀፋ ጥቃቱ የሩሲያ ባላስቲክ ሚሳኤል የዩክሬን የጦር መሰረተ ልማቶችን ኢላማ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡
አክለውም “ለዩክሬን መሳሪያ በመላክ ጥቃት እንዲፈፀም ለሚያደርጉ ሀገራት ሞስኮ ምላሽ የመስጠት መብት አላት” ያሉ ሲሆን፤ የሩሲያ ጦር ለዩክሬን የጦር መሳሪያ ድጋፍ ባደረጉት አሜሪካ እና ብሪታኒያ ላይ እርምጃ ሊወስድ እንደሚችል ማስጠንቀቃቸውን ሲኤንቢሲ ዘግቧል፡፡
በሌላ በኩል የሩሲያዉ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ፖላንድ የመጀመሪያ ኢላማ እንደምትሆን ገልጿል፡፡
የመስሪያ ቤቱ ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ ይህንን መግለጫ ለማዉጣት የተገደዱት፣ አሜሪካ እና አጋሮቿ በዋርሶ ፀረ ሚሳኤል የጦር መሳሪያ መክፈታቸዉን ተከትሎ መሆኑን ገልጸዋል።
ዛካሮቫ አክለዉም፤ ፖላንድ አካሄድ “የኔቶ ወታደራዊ መሠረተ ልማትን ወደ ሩሲያ ድንበር ለማቅረብ ለአሥርተ ዓመታት የተሰራ የአጥፊ ፖሊሲ” አካል ነዉ ሲሉ መወንጀላቸውን የሲኤንኤን ዘገባ አመላክቷል።
ቃል አቀባዋ እንደገለፁት ከሆነ ሞስኮ እንዲህ ያሉ የሩሲያ ስጋቶችን፤ ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎች በመጠቀም ልታወድም እንደምትችል ዝተዋል።
ይሁን እንጂ ጉዳዩን አስመልክታ ፖላንድ ይህንን ዜና እስካጠናቀርንበት ጊዜ ድረስ ዝምታን መምረጧ እያነጋገረ ይገኛል።
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
የደህንነት መስፈርቶችን ባላሟሉ ተቋማት ላይ ከ10 ሺሕ ብር ጀምሮ ሊያስቀጣ የሚችል መመሪያ ጸደቀ
ሕዳር 13/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የተለያዩ የደህንነት መስፈርቶችን ባላሟሉ ተቋማት ከ10 ሺሕ ብር የገንዘብ መቀጮ ጀምሮ እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችለውና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የተዘጋጀው መመሪያ መጽደቁ ተሰምቷል፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የአደጋ መከላከል ቁጥጥር ፍተሻና ብቃት ማረጋገጥ ስርዓት መመርያ ቁጥር 163/2017ን ያጸደቀ ሲሆን፤ መመርያውን ተግባራዊ በማያደርጉ ተቋማት ላይም ከገንዘብ ቅጣት ጀምሮ ንግድ ፍቃድን እንዲታገድ ፈቃዱን ለሰጠው አካል እስከማሳወቅ የሚደርስ እርምጃን ማካተቱ ተገልጿል፡፡
በቂና ተገቢ የእሳት ማጥፊያ መሳሪያዎችን ያላሟላ፣ በቂ መተላለፊያዎችን ከነሆሱ ያላዘጋጀ፣ አውቶማቲክ የውሃ መርጫ ስርዓትና መለያዎችን (ዲቴክተሮችን) ያላሟላ፣ የኮሚሽኑን የአደጋ ደህንነት ብቃት ማረጋገጫ የሌለው እና ሌሎች ለደህንነት አስፈላጊ የሆኑ ቁሶችን ያላዘጋጀ ተቋም ቅጣቱ እንደሚተላለፍበት ተጠቁሟል፡፡
መመሪያው የከተማዋ ነዋሪዎች ሕይወትና ንብረት እንዲሁም መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማትን ደህንነት ከማንኛውም አደጋዎች እንዲጠበቁ ለማድረግ የወጣ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በተጨማሪም የተቋማትን የአፈጻጸም ለመከታተል የሚያስችል አመቺ ሁኔታዎችን በመፍጠር የሃላፊነትና የተጠያቂነት ስርዓት ለመዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ ኮሚሽኑ መመርያውን እንዳወጣ ተነግሯል፡፡
በዳግም ተገኝ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን የቆይታ ግዜው እንደሚራዘም የሚኒስቴሮች ምክር ቤት አስታወቀ
ሕዳር 13/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የብሔራዊ የተሃድሶ ኮሚሽን በሚኒስትሮች ምክር ቤት ሕዳር 3 ቀን 2015 ዓ.ም በተካሄደ 15ኛ መደበኛ ስብሰባ፤ በደንብ ቁጥር 525/2015 መቋቋሙ ይታወቃል።
በማቋቋሚያ ደንቡ መሠረት የኮሚሽኑ የሥራ ጊዜ ሁለት ዓመት ሆኖ እንደ አስፈላጊነቱ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ሊራዘም ይችላል።
በመሆኑም "የኮሚሽኑ ሥራ አሁን ላይ ግዜው የተጠናቀቀ በመሆኑ ቀጣይ በምን ዓይነት መልኩ ሊቀጥል ይችላል?" ሲል አሐዱ የኮሚሽኑን ኮሚሽነር ጠይቋል።
በዚህም ብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን ሲመልሱ፤ "የቆይታ ግዚያችንን ሚኒስቴሮች ምክር ቤት እንዲያራዝምለን ተስፋ እናደርጋለን" ብለው ነበር።
በትናንትናው ዕለት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባካሄደው 40ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ያሳለፈ ሲሆን፤ በዚህም ምክር ቤቱ የብሄራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን ማቋቋሚያ ደንብን ለማሻሻል በወጣ ደንብ ላይ ተወያይቷል።
ተቋሙ በሕግ የተሰጠውን ተግባርና ኃላፊነት መወጣት እንዲችል ማቋቋሚያ ደንቡን ማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ደንቡ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ማቅረቡን ገልጿል።
ምክር ቤቱም በደንቡ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ በፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ በሙሉ ድምጽ መውሰኑ ተገልጿል።
የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን በተሻሻለው ደንብ ቁጥር 541/2016 መሰረት በደድጋሚ መቋቋሙ ይታወሳል።
በአቤል ደጀኔ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
#ADVERTISMENT
#AmharaBank
የአማራ ባንክ አ/ማ የባለአክሲዮኖች 3ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ማክሰኞ ታህሳስ 01 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ በሚሊኒየም አዳራሽ ስለሚካሄድ ባለአክሲዮኖች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጉባዔው እንድትገኙ ጥሪ እናስተላልፋለን፡፡
የጉባዔው አጀንዳዎችን እና ተጨማሪ መረጃዎችን ጥቅምት 06 ቀን 2017 ዓ.ም በወጡት አዲስ ዘመን እና ሪፖርተር አማርኛ እትም ጋዜጦች ላይ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ለበለጠ መረጃ ነፃ የጥሪ ማዕከል 690 ወይም
የባንኩን ድረ ገጽ www.amharabank.com.et ይጎብኙ፡፡
አማራ ባንክ
ከባንክ ባሻገር!
የአማራ ባንክ ትክክለኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾች
Website: www.amharabank.com
Facebook: www.Facebook.com/amharabanksc1
Telegram: /channel/Amhara_Banksc
Instagram: https://instagram.com/amhara_bank
Twitter: https://twitter.com/Amharabanksc
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/amharabank/
YouTube: https://youtube.com/channel/UC73x9uuGYV0Uxw0EkpVZN8g
TikTok: amharabanks.c" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@amharabanks.c
#አማራባንክ #AmharaBank
#አሐዱ_መድረክ
"አሃዱ ባንክ የባንኮች የውህደት አጀንዳ አላቀረበም" ከአሃዱ ባንክ ዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አንተነህ ሰብስቤ ጋር የተደረገ ቆይታ (ክፍል 1)
ቆይታውን ለመከታተል ከሥር ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ!
👇
https://youtu.be/-5cRUFRHTi0?si=3K8ds9UTvrKCzGLG
ጥራጥሬና ቅባት እህል ላኪዎች ተጨማሪ የገበያ መዳረሻ እንዲያፈላልጉ ጥሪ ቀረበ
ሕዳር 12/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በአገር ውስጥ ጥራጥሬና ቅባት እህል በማምረት ወደ ውጭ አገራት የሚልኩና በወጪ ንግድ ዘርፍ የተሰማሩ ኩባንያዎች፤ አዳዲስ ገበያ በማሰስ ረገድ ክፍተት እየተስተዋለባቸው እንደሚገኝ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።
ሚኒስቴሩ ኩባንያዎቹ በወጪ ንግድ ላይ እንዲበረቱለት የተለያዩ ሐሳቦች እየቀመረ እንደሚገኝ ለአሐዱ ተናግሯል።
ነባር ገበያዎችን ለማፅናት እና ተያያዥ ሥራ የሚሰሩ የውጭ ኩባንያዎች ጋር የንግድ ትስስራቸውን እንዲያጠናክሩ ለማድረግ የተለያዩ ሥራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝ የገለጹት የሚኒስቴሩ የኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈፃሚ አቶ ወንድሙ ፍላቴ፤ ላኪዎች የሚያደርጉትን እገዛ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የኢትዮጵያ ጥራጥሬና ቅባት እህል ምርቶች በውጭ አገራት ተፈላጊነት እንዳላቸው በመጥቀስም፤ በተለይ ምርቶቹ ተፈጥሮአዊ ይዘታቸው ባለ ልዮ ጣዕም በመሆኑ ተወዳጅነት ካተረፉ መካከል መሆናቸውን ተናግረዋል።
በዚህም በአለም ላይ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን የጥራጥሬና የቅባት እህሎች ከሚያቀርቡ ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ ቀዳሚዋ መሆንዋን ገልጸዋል፡፡
ይህንን ዕድል ለመጠቀምም የምርቶች ጥራት ደረጃና መጠን ለማሻሻል የተለያዩ ስትራቴጂዎች ተነድፈው እየተሰራባቸው እንደሚገኝ አስረድተዋል።
ከዚህ በተጨማሪ ከአርሶ አደሮች የሚያስመርቱ ላኪዎችና ባለሐብቶች መቆጣጠር የሚያስችል መመርያ እንደተነደፈ መሆኑን ሥራ አስፈፃሚው ተናግረዋል።
በንግዱ ማሕበረሰብ ገበያን በማስፋፋትን ጨምሮ አዳዲስ መዳረሻ አገራት ማፈላለግ በብርቱ እየተሰራበት መሆኑንም አክለው ገልጸዋል፡፡
በተያዘው በጀት ዓመት ኢትዮጵያ ከጥራጥሬና የቅባት እህሎች የወጪ ንግድ የገቢ መጠን ለማሳደግ እየሰራች መሆኑንም አቶ ወንድሙ ለአሐዱ አስረድተዋል።
ከጥራጥሬና የቅባት እህሎች የወጪ ንግድ የገቢ በተያዘው ሩብ ዓመት ካለፉት ዓመታት ጋር ሲነፃፀር የተሻለ ገቢ የተገኘበት እንደነበር ከሚኒስቴር መስርያ ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
በአማኑዔል ክንደያ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እንደ አዲስ ማዋቀር የሚፈልግ ነው ሲሉ ባለሙያዎች ገለጹ
ሕዳር 12/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬ ዕለት ባደረገው ስብሰባ የማክሮ ኢኮኖሚና ፊሲካል ማዕቀፍ ላይ ተወያይቶ ሥራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
የማክሮ ኢኮኖሚ እና ፊስካል ማዕቀፉ በሁለተኛው ምዕራፍ ሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ የሚከናወኑ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎችንና የመንግሥት የፊስካል ፖሊሲ ማሻሻያዎችን ተግባራዊ ለማድረግ እና ለ2017 የፌዴራል መንግሥት ተጨማሪ በጀትና የወጪ አሸፋፈን ማስተካከያ መነሻ ሆኖ የሚያገለግል ሲሆን፤ በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ተቃኝቶና ተሻሽሎ የቀረበ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ማዕቀፉ ከመጽደቁ ቀናት በፊት ከአሐዱ ጋር ቆይታ ያደረጉት የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ዶ/ር አጥላው አለሙ፤ "የኢኮኖሚውን ችግር ዘለቄታዊ መፍትሄ እንጂ በአጭር ጊዜ በጊዜያዊ አማራጮች የሚፈታ አይደለም" ያሉ ሲሆን፤ "ኢኮኖሚው እንደ አዲስ መዋቀርን ይፈልጋል" ብለዋል።
አክለውም፤ "ጥቂት የደሞዝ ጭማሪ በማድረግ እና ተጨማሪ ሥራዎችን በመስራት ኅብረተሰቡ ላይ የመጣውን የኑሮ ጫና መቋቋም አያስችለውም" ሲሉ ገልጸዋል።
"ሰላምና መረጋጋት በሌለበት ሥራዎችን መስራት አልተቻለም" ያሉት ባለሙያው፤ በዚህም ምክናያት የሰው ጉልበት እና ንብረት መባከኑን ተናግረዋል፡፡
ሌላው ከአሐዱ ጋር ቆይታ ያደረጉት የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ካህሳይ ሃጎስ በበኩላቸዉ፤ "የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ሊያመጣቸው የሚችላቸውን ጫናዎች ለመቋቋም ይደረጋሉ የተባሉ አንዳቸውም ሳይተገበሩ መቅረታቸውን በማንሳት፤ "ኅብረተሰቡ ከነበረበት የዋጋ ንረት እንዲጨምርና እንዲጎዳ ሆኗል" ይላሉ።
"እንዲሁም ኅብረተሰቡ ስለቀን ውሎው ብቻ እንዲያስብና በሌሎች ጉዳዮች ውስጥ እንዳይሳተፍ የሚያደርጉ ሁኔታዎች ይስተዋላሉ" ብለዋል።
እንዲሁም ለኅብረተሰቡ በአማራጭነት በመንግሥት መስሪያ ቤትም ሆነ በግል ተቋማት ሠራተኞቻቸው እንዲደራጁና የተለያዩ የቢዝነስ ሥራዎችን እንዲሰሩ እድሎች ቢመቻቹለት አማራጭ መፍትሔ እንደሚሆን ገልጸዋል።
"ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ሰላምና መረጋጋት ብቸኛው መፍትሔ ነው" የሚሉት የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ሸዋፈራው ሽታሁን፤ "የሰላሙ ጉዳይ ግን ችላ ተብሏል" ሲሉም ተናግረዋል።
እንዲሁም በቀደመው ስርዓት ኢሕአዴግ መካከለኛ እና ጥቃቅን የሥራ ዕድል ፈጠራዎች የነበሩ ቢሆንም፤ አሁን ይኼ እንቅስቃሴ ቀርቶ የሥራ ዕድሎች ሁሉ በመንግሥት እጅ ውስጥ እንደገቡ እና ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ ጉዳዮች መዘንጋታቸውን አንስተዋል።
የፖለቲካ ግቡ ኢኮኖሚያዊ የበላይነት ለመያዝ መሆኑ እሙን የሚሉት የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ሸዋፈራሁ፤ ግጭቶች ከባድ ኢኮኖሚያዊ ቀውሶችን እንደሚያጣ መገንዘብ ይገባል ብለዋል።
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 40ኛ መደበኛ ስብሰባው የመካከለኛ ዘመን (2017-2021) የማክሮ ኢኮኖሚ እና ፊስካል ማዕቀፍ ላይ ተወያይቶ በሥራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምጽ መወሰኑን አስታውቋል፡፡
በፍርቱና ወልደአብ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳለፈ
ሕዳር 12/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 40ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
ያሳለፋቸው ውሳኔዎቹም እንደሚከተሉት ቀርበዋል፡-
1. በቅድሚያ ምክር ቤቱ የተወያየው የመካከለኛ ዘመን (2017-2021) የማክሮ ኢኮኖሚ እና ፊስካል ማዕቀፍ ላይ ነው፡፡ ማዕቀፉ በሁለተኛው ምዕራፍ ሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ የሚከናወኑ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎችንና የመንግስት የፊስካል ፖሊሲ ማሻሻያዎችን ተግባራዊ ለማድረግ እና ለ2017 የፌዴራል መንግስት ተጨማሪ በጀትና የወጪ አሸፋፈን ማስተካከያ መነሻ ሆኖ የሚያገለግል ሲሆን በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ተቃኝቶና ተሻሽሎ የቀረበ ነው፡፡ ምክር ቤቱም በማዕቀፉ ላይ በሰፊው ከተወያየበት በኋላ በስራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
2. በመቀጠል ምክር ቤቱ የተወያየው በፌዴራል መንግስት የተጨማሪ በጀት እና የወጪ አሸፋፈን ማስተካከያ አዋጅ ላይ ነው፡፡ የተጨማሪ በጀት እና የወጪ አሸፋፈን ማስተካከያው የተሻሻለውን የ2017-2021 የመካከለኛ ዘመን የማክሮ ኢኮኖሚ እና ፊስካል ማዕቀፍ ማስፈጸም በሚያስችል መልኩ የመንግስት የፋይናንስ አቅምና ተጠባቂ ገቢዎችን ታሳቢ በማድረግ፣ የተጨማሪ በጀት ታሳቢዎችንና የወጭ ታሳቢዎችን ግምት ውስጥ በማስገባት ተዘጋጅቷል፡፡
በዚሁ መሰረት ለመደበኛ ወጪዎች እና የወጪ አሸፋፈን ለማስተካከል የሚውል 581, 982, 390,117 /አምስት መቶ ሰማንያ አንድ ቢሊዮን ዘጠኝ መቶ ሰማንያ ሁለት ሚሊዮን ሶስት መቶ ዘጠና ሺህ አንድ መቶ አስራ ሰባት ብር/ ተጨማሪ በጀት ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በቀረበው የፌዴራል መንግስት የ2017 በጀት ዓመት የተጨማሪ በጀትና የወጪ ማስተካከያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ከተወያየ በኋላ ግብአቶችን በማከል ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
3. ከዚያም ምክር ቤቱ የተወያየው በኢትዮጵያ የተመሰከረላቸው የሂሣብ ባለሙያዎች ኢንስቲትዩት ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው። ኢንስቲትዩቱ ብቁ እና ብዛት ያላቸውን ባለሙያዎች በማፍራት በመንግስት እና በግል ተቋማት የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀት እና አቀራረብ ሥርዓት በመዘርጋት ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ የሚኖረው ነው፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ በሰፊው ከተወያየበት በኋላ ግብዓቶችን በማከል ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
4. የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ረቂቅ አዋጅ ሌላው ምክር ቤቱ የተወያየበት አጀንዳ ነው፡፡ ደረቅ ቆሻሻ በአካባቢ እና በሰዎች ደህንነትና ጤና ላይ እያስከተለ ያለውን ተፅእኖ እና ጉዳት ለመከላከልና ለመቆጣጠር እንደሀገር ባለፉት አመታት ከጀመርናቸው የግሪን ሌጋሲ ስራችንና የኮሪደር ልማት ውጤታማና ዘላቂ ለማድረግ፣ በዜጎች ጤንነት የከተማ ውበት መጠበቅ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ያለውን ለአንድ ጊዜ ግልጋሎት የሚውሉ የፕላስቲክ ምርቶችን ወደ ሀገር እንዳይገቡ ክልከላ በማድረግ፣ ህብረተሰቡንና ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ መልኩ የደረቅ ቆሻሻ አሰባሰብ፣ አጓጓዝ፣ አከመቻቸት፣ መልሶ መጠቀም፣ መልሶ ኡደት እና አወጋገድ ሥርዓት ለመዘርጋት የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ በማስፈለጉ አዋጁ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በአዋጁ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምፅ ወስኗል፡፡
5. ሌላው ምክር ቤቱ የተወያየው የብሄራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን ማቋቋሚያ ደንብን ለማሻሻል በወጣ ደንብ ላይ ነው፡፡ ተቋሙ በህግ የተሰጠውን ተግባርና ሀላፊነት መወጣት እንዲችል ማቋቋሚያ ደንቡን ማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ደንቡ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በደንቡ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ በፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
6. ከዚያም ምክር ቤቱ የተወያየው የውሃ አካል ዳርቻ አከላለል፣ ልማት፣ እንክብካቤ እና አጠቃቀም ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ በሀገራችን በውሃ አካላት ዳርቻዎች ላይ እየደረሰ ያለውን ጉዳት ለመከላከል እንዲቻል የውሃ አካላት ዳርቻ መከለልና በዘላቂነት ማልማት፣ መንከባከብና ጥበቃ ማድረግ የውሃ ስነ-ምህዳር አግልግሎትን ከማሻሻል ባሻገር ለአካባቢው ማህበረሰብ ተጨማሪ ማህራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞችን የሚያስገኝ በመሆኑ አዋጁ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል:: ምክር ቤቱም በአዋጁ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምፅ ወስኗል፡፡
7. በመጨረሻም ምክር ቤቱ የተወያየው የተቀናጀ ውሃ ሀብት አስተዳደር ማስፈጸሚያ የተፋሰሶች ከፍተኛ ምክር ቤት ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ያላትን የገፀ ምድርና የከርሰ ምድር የውሃ ሀብት በፍትሃዊነትና በዘላቂነት መጠቀም እንድትችል የሚመለከታቸው አካላት የውሃ ሀብትን በጋራ ለማልማት፣ ለመጠቀም፣ ለመንከባከብ፣ ለመጠበቅ እና ለመቆጣጠር የሚያስችል የተቀናጀ ውሃ ሀብት አስተዳደርን በተፋሰስ ደረጃ ተግባራዊ በማድረግ ስትራቴጂካዊ አመራር መስጠት አስፈላጊ በመሆኑ ረቂቅ አዋጁ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በአዋጁ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብአቶችን በማከል ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምፅ ወስኗል፡፡
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ