ahaduradio | Unsorted

Telegram-канал ahaduradio - AHADU RADIO FM 94.3

19349

አሐዱ ራድዮ 94.3 Your source for top local and international news and analysis. "Voice of Ethiopian" የአሐዱ የቴሌግራም ቻናል ቤተሰብ በመሆን ወቅታዊና እውነተኛ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ

Subscribe to a channel

AHADU RADIO FM 94.3

መልካም ቀን!
አሐዱ ሬድዮ 94.3  የኢትዮጵያውያን ድምፅ!

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የክልሉ መንግሥት ድጋፍ እያደረገልን አይደለም ሲል የጋምቤላ ክልል ሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳይ ቢሮ አስታወቀ

ሕዳር 17/2017 (አሐዱ ሬዲዮ)  በጋምቤላ ክልል በየጊዜው የሚፈፀመውን ጾታን መሠረት ያደረገ ጥቃት መቆጣጠር እና መከላከል በሚሰራው ሥራ፤ የክልሉ መንግሥት ድጋፍ እያደረገልን አይደለም ሲል የጋምቤላ ክልል ሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳይ ቢሮ አስታውቋል።

በቢሮው የሴቶች እና ሕጻናት ዘርፍ ምክትል ኃላፊ ኦላንግ ጋች በክልሉ ያለ ዕድሜ ጋብቻ፣ አስገድዶ መድፈር፣ ጾታን መሠረት ያደረገ ጥቃት በየጊዜው እንደሚፈጸም የገለጹ ሲሆን፤ በተለይም በየአካባቢው በቤተሰቦቻቸው የሚጣሉ ሕጻናት ቁጥር ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ለአሐዱ ተናግረዋል።

ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ የቅድመ መከላከል እና መቆጣጠር ሥራዎችን ቢሮ በሚያከናውንበት ወቅት የክልሉ መንግሥት በበጀት፣ በሰው ሀይል እና በተለያዩ ነገሮች ድጋፍ አለማድረጉ ፈተና እንደሆነባቸውም ገልጸዋል።

የክልሉ መንግሥት ችግሩን የመቅረፍ ሃላፊነት የቢሯቸው ሥራ ብቻ አድርጎ ማሰቡም፤ ችግሮች እንዲስፋፉ ምክንያት መሆኑን ጠቁመዋል።

በተለይም እንደ ክልል እየጨመረ የመጣውን ያለ ዕድሜ ጋብቻና አስገድዶ መድፈር ወንጀልን ለማስቀረት እና ለመቆጣጠር ሥራዎች ቢሰሩም በቂ ባለመሆኑ ለውጥ ማምጣት እንዳልተቻለ አንስተዋል።

የክልሉን መንግሥት ችግር እንዲፈቱ ፌደራል ላይ ላሉ የበላይ አካላት ቢያሳውቅም፤ መፍትሔ እንዳልተበጀለት አስረድተዋል።

ኃላፊው አያይዘውም የፌደራል ከፍተኛ አመራሮች ወደ ክልሉ የተሰሩ ሥራዎችን ለመጎብኘት በሚመጡበት ወቅት የክልሉ መንግሥት ድጋፍ እንደሚያደርግ ከማሳወቅ ውጭ ይህን የሚባል ሥራ አብሯቸው እየሰራ እንዳማይገኝ ነግረውናል። ካሉት ሌሎች ተግዳሮቶች ውስጥ ይህም የጎላ መሆኑንም አብራርተዋል።

የችግሩን ሥር እየሰደድ ምጣቱን በመረዳት የክልሉ መንግሥት ድጋፍ እንዲያደርግላቸው የቢሮው የሴቶች እና ሕጻናት ዘርፍ ምክትል ኃላፊ ኦላንግ ጋች ጥሪ አቅርበዋል።

አሐዱም ጉዳዩን አስመልክቶ፤ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ አለሚቱ ኡሞድ ጠይቋል።

ርዕሰ መስተዳድሯ በሰጡት ምላሽ፤ ችግሮች እንዳሉ አምነው፤ በክልሉ የሚስተዋሉ ጾታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶችን ለመቆጣጠር እና ለመቀነስ ድጋፍ እያደረጉ እንደሚገኝ ለአሐዱ ተናግረዋል።

በወልደሐዋርያት ዘነበ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

ባለስልጣኑ በሥሩ ያሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ላይ የሚደርስ ጫናዎችንና መዋከቦችን የመከለከል ሀላፊነቱን እንዲወጣ ተጠየቀ

ሕዳር 17/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የሲቪል ማህበረሰብ ባለስልጣን በሥሩ ያሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ላይ የሚደርስ ጫናዎችንና መዋከቦችን የመከለከል ሀላፊነቱን ይወጣ ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ተሞጋቾች ማዕከል ጠይቋል።

ድርጅቱ ለአሐዱ በላከው መግለጫ፤ "የሲቪክ ምህዳሩን ሊያጠቡና አደጋ ላይ ሊጥሉ የሚችሉ ምልክቶችን እያየን በመሆኑ መንሥስት አፋጣኝ እልባት እንዲሰጣቸው" ሲል አሳስቧል፡፡

ከተለያዩ የሲቪል ማህበራት አባላት እና የመብት ተሟጋቾች በርካታ አቤቱታዎችን እና ጥቆማዎች ሲቀበል መቆየቱን የገለጸው ድርጅቱ፤ ከእነዚህም መካከል የተወሰኑ የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች አመራር የሆኑ ግለሰቦች በጸጥታ አካላት በአካልና በስልክ ተደጋጋሚ ወከባና ማስፈራሪያ የደረሰባቸው መሆኑን አስታውቋል፡፡

ለምሳሌነትም የመብቶች እና ዴሞከራሲ እድገት ማዕከል (CARD) የተሰኘው አገር በቀል ድርጅት መስራችና የቀድሞ የፕሮግራም ዳይሬክተር የነበሩት አቶ አጥናፍ ብርሃኔ፣ የስብስብ ለሰብአዊ መብቶች በኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ወ/ት መሰረት አሊ እንዲሁም በቅርቡም አንጋፋውና ግንባር ቀደሙ የሰብአዊ መብቶች ድርጅት የሆነው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) ዳይሬክተር የነበሩትና የድርጅታችን መስራችና የቦርድ አባል የሆኑት አቶ ዳን ይርጋ በተመሳሳይ ሁኔታ በጸጥታ አካላት በደረሰባቸው ከፍተኛ ጫና ሀገር ለቀው መሰደዳቸውን አንስቷል፡፡

በእነዚህ ድርጅቶች ላይ "ከፖለቲካዊ ገለልተኝነቶች ነፃ ባልሆነ መንገድና ከተሰጣቸው ስልጣን በላይ ተንቀሳቅሰዋል፣ የሀገርንና የሕዝብን ጥቅም የሚጎዱ ተግባራትን አከናውነዋል" በሚል የሲቪል ማህበረሰብ ባለሥልጣን በጻፈው ግልጽ ደብዳቤ ከሰሞኑ እገዳ የተጣለባቸው መሆኑን ለመረዳት መቻሉንም ገልጿል።

እገዳ የተደረገባቸው ድርጅቶችም፤ የመብቶች እና ዴሞክራሲ እድገት ማዕከል፣ ስብስብ ለሰብአዊ መብቶች በኢትዮጵያ እና የሕግ ባለሙያዎች ለሰብአዊ መብቶች ናቸው።

ይህንን በሚመለከት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል ባወጣው መግለጫ፤ "ሕገ መንግሥታዊ መብቶችን፤ ማለትም በነጻነት የመደራጀት፣ የመሰብሰብ እና ሐሳብን የመግለጽ መብትን የሚጎዳ እና ለሲቪክ ምህዳሩ መጥበብ የጎላ ተጽእኖ የሚያሳድር ሆኖም አግኝተነዋል" ብሏል።

ከእገዳው በፊት የተሰጣቸው ምንም አይነት ማስጠንቀቂያም ሆነ እነሱ የሚያውቁት በግልጽ የተካሄደ ምርመራ አለመኖሩን በመግለጽም፤ "አካሄዱን ሕግን ያልተከተለ፣ ግልጽነት የጎደለው እና በድርጅቶቹ አመራሮችና ሠራተኞች ላይ ድንጋጤን የፈጠረ ድንገተኛ ክስተት አድርጎታል" ብሏል፡፡

በዚህም "ጥሩ ጅምርና እምርታ አሳይቶ የነበረው የሲቪክ ምህዳሩ ተጠናክሮ እንዲቀጥልና እንዲሰፋ ሃላፊነት የተጣለባቸው አካላት፣ የሲቪል ማህበረሰቡ አባላትና በዋነኝነት ተገቢውን ጥበቃ እንዲያደርጉ" ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል ጠይቋል፡፡

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በመዲናዋ ከደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ጋር በተያያዘ ከ2 ሺሕ 700 በላይ ሰዎች ላይ የገንዘብ ቅጣት እንደተላለፈባቸው ተገለጸ

ሕዳር 17/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በተያዘው የ2017 ሦስት ወራት ውስጥ ከደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ጋር በተያያዘ ከ2 ሺሕ 700 በላይ ሰዎችን እስከ 100 ሺሕ ብር ድረስ መቅጣቱን የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አስታውቋል።

ቅጣቱ በተሻሻለው የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የቅጣት ሰንጠረዥ መሰረት መከናወኑን የባለስልጣኑ የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ የምስራች ግርማ ለአሐዱ ተናግረዋል።

አክለውም ደንቡ ማንኛውም ሰው ወይም ድርጅት ከፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ እውቅና ውጪ ወደ ከተማዋ ቆሻሻ ያስገባ እንዲቀጣ መደንገጉን አስረድተዋል።

በዚህም "ከሰሞኑን ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ በመኪና የጫኑትን ቆሻሻ ከተማ ውስጥ አስገብተው ያራገፉ ሦስት ግለሰቦች እያንዳንዳቸው 100 ሺሕ ብር ተቀጠዋል" ብለዋል።

በአጠቃላ በሦስት ወራት ውስጥ ከደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ጋር በተያያዘ 2 ሺሕ 722 ሰዎች ከሁለት ሺሕ ብር ጀምሮ እስከ 100 ሺሕ ብር ድረስ መቀጣታቸውን ተናግረዋል።

በአበረ ስሜነህ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በትግራይ ክልል ለተፈጠረው ችግር ዋና ምክንያት የግዚያዊ አስተዳደሩ በአግባብ ሀላፊነቱን ባለመወጣቱ ነው ሲሉ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ገለጹ

ሕዳር 17/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የትግራይ ክልል ግዚያዊ አስተዳደርን በዋናነት ህወሓት ሰዎች ሙሉ ለሙሉ የተቆጣጠሩት ቢሆንም፤ ከዶክተር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ቡድን ውስጥ ህወሓት የነሱ ብቻ አድርገው የሚቆጥሩት እንዳሉ የባይቶና አባይ ትግራይ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር ዮሴፍ በርሄ ተናግረዋል፡፡

በዚህም "ግዚያዊ አስተዳደሩ ወደታች ወርዶ ወረዳ ድረስ መስራት ባለመቻሉ ሌላኛው ቡድን የቀድሞ ህወሓቶች ወረዳዎች ላይ ላይ ያላቸውን ተቀባይነት በመጠቀም በመቆጣጠራቸው ግዚያው አስተዳደሩ መስራት ሳይችል ቀርቷል" ብለዋል፡፡

"ግዚያዊ አስተዳደሩ ክልሉ ላይ ተንጠለጥሎ በመቅረቱ የተነሳ እንዲሁም ባለበት ጫና ምክንያት በሚገባ እያስተዳደር አይደለም" ሲሉም ገልጸውታል፡፡

በግዚያዊ አስተዳደሩና በህወሓት መካከል የተፈጠረው ችግር እየተካረረ መሄዱን ተከትሎ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር "መፈንቅለ መንግሥት ሊደረግብኝ ነው" የሚል ቅሬታዎችን እያሰማ ይገኛል፡፡

ይህንና ሌሎች በክልሉ እየተካረሩ የሄዱ ጉዳዮችን በመመልከት "በተለይም ክልሉ አሁን ገና ከጦርነት ያገገመ እንደመሆኑ የፌደራል መንግሥት መፍትሄ አያስፈልገውም ወይ? ሲል አሐዱ ጠይቋል፡፡

ይህንን በሚመለከት የሳልሳይ ወያነ ትግራይ ፓርቲ ሊቀመንበር አሉላ ሀይሉ፤ "ጣልቃ ገብነት በተለይም እርምጃ መውሰድ ችግሩን ማባባስ ነው" ይላሉ፡፡

ቀደም ተብሎ የተነሳውን አሳብ የሚጋሩት የባይቶና አባይ ትግራይ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር ዮሴፍ በርሄ በበኩላቸው "የፌደራል መንግሥት ጣልቃ ገብነት የሚያስፈልገው ችግር የለም" ያሉ ሲሆን፤ "ነገር ግን ጠንካራ ግዚያዊ አስተዳደር እንዲፈጠር  ማድረግ ይችላል" ብለዋል፡፡

ችግሮችን ከሚያባሱ ጉዳዮች አንዱና ዋነኛውን የፕሪቶሪያው ውል በአግባቡ ያለመተግበሩ በመሆኑ በትኩረት ስምምነቱ ላይ መስራት ያስፈልጋል ሲሉም ተናግረዋል፡፡

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ እሁድ ዕለት የክልሉን ወቅታዊ የፖለቲካ፣ የደህንነት እና የማህበራዊ ጉዳዮች አስመልክቶ ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ በሰጡበት ወቅት፤ በህወሓት አመራሮች መካከል የተፈጠረው መከፋፈል ተባብሶ መቀጠሉን ገልጸዋል።

አክለውም "የፌደራል መንግሥት ውስጣዊ ችግራችንን እንድንፈታ እየገለጸ ነው" ነው ያሉ ሲሆን፤ "ካልተቻለ ግን የማስተዳደር ስልጣኑን ብልፅግና በብቸኝነት እንደሚይዘው ግልፅ አድርጎልናል" ሲሉ መናገራቸው ይታወሳል።

በአቤል ደጀኔ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የኮፕ 29 ጉባዔ ለአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ መቋቋሚያ የሚውል የ300 ቢሊዮን ዶላር ማፅደቁ ተገለጸ

ሕዳር 17/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በአዘርባጃን ባኩ ለተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የቆየው 29ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ፤ ለአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ መቋቋሚያ የሚውል የ300 ቢሊዮን ዶላር በማፅደቅ መጠናቀቁን ፕላንና ልማት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ 

ጉባዔው በተለይ በፓርሲ ስምምነት አንቀፅ 6 ነጥብ 2 ማለትም፤ አፍሪካዊያን ሀገራት የሁለትዮሽ ስምምነቶችን በመከወን የካርበን ግብይት እንዲፈፅሙ የሚፈቅድ የፓሪስ አየር ንብረት ለውጥ መከላከል ቃል ኪዳን አዋጅ ላይ ውይይት ማድረጉ ተገልጿል።

በዚህ ስምምነት ጥላ ሥር ኢትዮጵያ ቀድማ የዘላቂ አረንጓዴ ልማት ትብብር መመስረትና አማራጭ ገቢ ማስገኛ ዕድሎቿን ማሳየቷ ተመላክቷል።

እንዲሁም በጉባዔው 6 ነጥብ 4 ማለትም የካርበን ግብይት ቁጥጥር አፍሪካዊያን ሀገራት በዓለም አቀፍ ምዘና ብቁ ከሆኑ ፕሮጀክቶቻቸው የካርበት ክሬዲት ማልማትና መሸጥ የሚፈቅድ ስምምነት መሰረት፤ የካርበን ሽያጭን ተግባራዊ ማድረግ በሚቻልበት ሂደት ዙሪያ ውይይት ተደርጎ መጠናቀቁን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡ 

ይህም በተለይ በአረንጓዴ ዘላቂ ልማት ትልም የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ እና የታዳሽ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክትን በማከናወን ላይ ለምትገኘው ለኢትዮጵያ ተጨማሪ ጥቅም ይዞ መምጣቱ ተነግሯል።

በጉባዔው እጅጉን ያነሰ የብክለት ድርሻ ይልቁንም የበዛ የአየር ንብረት ለውጥ ዳፋ የሚያርፍባቸው አፍሪካዊያን ሀገራት የካርበን ሽያጭና ግብይትን በፍትሀዊነት የማዳረስ፣ በተፅዕኖ የሚፈተኑ ዜጎችን የመለየት፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ብቁና ተወዳዳሪ የሚያደርግ የፖሊሲ ድጋፍና የትብብር ዕድሎች በቀጣይ ስምምነቶቹ በትግበራቸው ሊያጋጥሙ የሚችሉ ስጋቶች ተብለው ተቀምጠዋል።

በዚህም መሠረት እነዚህን ስጋቶች ለመቀነስ በተደረገው ጉባኤ ኮፕ ለአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ መቋቋሚያ የሚውል የ300 ቢሊዮን ዶላር የፋይናንስ አቅርቦት ስምምነትን አፅድቋል።

በ28ኛው የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ወቅት የበለጸጉ ሀገራት ለታዳጊ ሀገራት ለአየር ንብረት ለውጥ ምላሽ የሚውል የ792 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን ጥፋትና ውድመት ፈንድን ጨምሮ የ85 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ለመስጠት ቃል ገብተው ነበር።

ከዚህ በተጨማሪም ያደጉ ሀገራት የአዳፕቴሽን ፈንድ ድጋፍን እጥፍ ለማድረግም የተስማሙ ሲሆን፤ በተያያዘም የባለብዙ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ለአየር ንብረት ለውጥ ምላሽ ድጋፎች በድምሩ ከ22 ነጥብ 6 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ተጨማሪ በጀት ለመመደብ ቃል መግባታቸው ይታወሳል፡፡

በፍርቱና ወልደአብ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

መልካም ቀን!
አሐዱ ሬድዮ 94.3  የኢትዮጵያውያን ድምፅ!

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የ3 ዓመት ሕጻን በመድፈር የተከሰሱ 2 ግለሰቦች በ15 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጡ

ሕዳር 16/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 2 ቀበሌ 04 ልዩ ስሙ “በግ ተራ” ተብሎ በሚጠራው አካባቢ፤ የ3 ዓመት ሕጻንን አስገድደው በመድፈር ወንጀል የተከሰሱ 2 ግለሰቦች በ15 ዓመት ጽኑ እስራት መቀጣታቸው ተገልጿል።

የወንጀል ድርጊቱ የተፈጸመው ሰኔ 8 ቀን 2016 ዓ.ም. በአሶሳ ከተማ ነው።

የምርመራ መዝገቡ እንደሚያሳየው፤ በተጠቀሰው አካባቢ በግምት ከቀኑ 6 ሰዓት ለጨዋታ ቤታቸው የሄደችን የ3 ዓመት ከ6 ወራት እድሜ ያላት ሕጻን፤ 1ኛ ተከሳሽ አስገድዶ ደፍሯታል። 2ኛ ተከሳሽ አንገቷን በመያዝ የድርጊቱ ተባባሪ በመሆን ለጥቃት አጋልጧታል።

በአሶሳ ከተማ አስተዳደር የወረዳ 2 ፖሊስ የምርመራ መዝገቡን በሰውና በሰነድ ማስረጃ በማስደገፍ ለዐቃቤ-ሕግ መላኩን የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር አወደላ አልሃሪብ ለአሐዱ ተናግረዋል።

ዓቃቤ ሕግ በበኩሉ ተከሳሾቹ በፈጸሙት በህጻናት ልጆች ላይ የሚፈፅም የግብረ-ሥጋ ድፍረት በደል ወንጀል ክስ መስርቷል።

የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 2 ፍ/ቤት በዓቃቤ ሕግ ተጣርቶ የቀረበለትን መዝገብ ከተመለከተ በኋላ ተከሳሾቹ ላይ የጥፋተኝነትን ብይን አስተላልፏል።

ፍርድ ቤቱ ሕዳር 13 ቀን 2017 ዓ.ም. በዋለው ችሎት 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች እያንዳንዳቸው በ15 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ወስኗል።

በአበረ አልማው
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

መስከረም አበራ ጥፋተኛ በተባለችበት "የኮምፒውተር ወንጀል ክስ" የአንድ ዓመት ከአራት ወር እስራት ተፈረደባት

ሕዳር 16/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) 'ኢትዮ ንቃት' የተሰኘው የማኅበራዊ ሚዲያ መሥራች እና ባለቤት መስከረም አበራ ከሦስት ሳምንት በፊት ጥፋተኛ በተባለችበት የኮምፒውተር ወንጀል ክስ የአንድ ዓመት ከአራት ወር እስራት ተፈረደባት።

የቅጣት ውሳኔውን ያስተላለፈው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ልዩ ልዩ ከባድ ወንጀሎች ችሎት ሲሆን፤ መስከረም አበራ ውሳኔው ሲገለጽ ችሎት አለመገኘቷን ጠበቃዋ አቶ ሄኖክ አክሊሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

መስከረም ጥፋተኛ የተባለችው በባለቤትነት በምታስተዳደረው 'ኢትዮ ንቃት' የዩቱዩብ ገጽ ላይ በተላለፉ ሁለት ፕሮግራሞች ምክንያት መሆኑም ተገልጿል።

እነርሱም ቀዳሚው ፕሮግራም ሚያዝያ 4 ቀን 2014 ዓ.ም. "መልዕክት ለጄኔራል አበባው ታደሰ" በሚል ርዕስ የቀረበ ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ከሦስት ቀናት በኋላ በተመሳሳይ የዩቲዩብ ገጽ ሚያዝያ 7 ቀን 2014 "አማራ ክልል ምን እየተደረገ ነው?" በሚል ርዕስ የተላለፈ ነው።

ባለፈው ጥቅምት ወር የዋለው ችሎት መስከረም አበራ ጥፋተኛ መሆኗን በመግለጽ የቅጣት ውሳኔ ለማስተላለፍ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር።

ሰኞ ሕዳር 16 ቀን 2017 ዓ.ም. የዋለው ችሎት የቅጣት ውሳኔውን ማስተላለፉን የገለጹት ጠበቃ ሄኖክ፤ "ይህ ውሳኔ የተላለፈው መስከረም አበራ ቅሬታ አለኝ ብላ ችሎት ባልቀረበችበት ሁኔታ ነው" ብለዋል።

አቶ ሄኖክ "ከዚህ ቀደም ያቀረብኳቸው መከላከያ ምስክሮቹ በአግባቡ ያልታዩልኝ ስለሆነ ከዚህ ችሎት ፍትህ አልጠብቅም፤ እናንተ ተገቢ ነው የምትሉትን ቅጣት ወስኑ፤ ከዚህ በኋላ በችሎት አልገኝም ብላ ገልጻለች ይሄንንም ለፍርድ ቤት በጽሁፍ አሳውቃለች" ሲሉ የደንበኛቸውን ቅሬታ አስረድተዋል።

የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ተከትሎ የይግባኝ አቤቱታ ያቀረቡ እንደሆነ ጥያቄ የቀረበላቸው ጠበቃው ምላሽ ሰጥተዋል።

በዚህም "ከእሷ ጋር በተነጋገርነው መሠረት ቅጣቱ ላይ ሳይሆን መስከረም ጥፋተኛ የተባለችባቸው ሥራዎች ምንም ዓይነት የማነሳሳት፣ ሕዝብን ከሕዝብ የማጋጨት ባህሪ የሌላቸው እና በወንጀል የሚያስቀጡ ስላልሆኑ ፍርዱን ብቻ በተመለከተ ለፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኛችንን አዘጋጅተን እናቀርባለን" ማለታቸውን ዘገባው አመላክቷል።

መስከረም አበራ ከዚህ ክስ በተጨማሪ በእነ ዶክተር ወንድወሰን አሰፋ መዝገብ፣ ከዳዊት በጋሻው፣ ከጎበዜ ሲሳይ እና ከገነት አስማማው ጋር "የሽብር ድርጊት በመፈጸም" ሌላ የወንጀል ክስ እንደቀረበባት ይታወቃል።

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

"ግጭቶች ባሉባቸው አካባቢዎች ጾታዊ ጥቃት ለደረሰበቸው አንድ ሺሕ ሴቶች ድጋፍ ተደርጓል" ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)

ሕዳር 16/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ባሳለፍነው የ2016 ዓ.ም ግጭቶች ባሉባቸው አካባቢዎች ለሚኖሩና ጾታዊ ጥቃት ለደረሰበቸው አንድ ሺሕ ሴቶች ድጋፍ መደረጉን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ በሁሉም አካባቢዎች በሚባል ደረጃ በሚፈጠሩ ግጭቶች ምክንያት፤ በአካባቢዎች በሚኖሩ ሴቶች ላይ ጾታን መሠረት ያደረገ ጥቃት በብዛት እየተፈጸመ መሆኑ ይስተዋላል፡፡

በዚህም አስገድዶ መድፈር፣ ግድያና ሌሎች ጾታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች ሰለባ ከሆኑት ውስጥ፤ ለአንድ ሺሕ ሴቶች ብቻ ስነልቦናዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ድጋፍ እንደተደረገላቸው ሚኒስትሯ ገልጸዋል፡፡

አክለውም "ጾታዊ ጥቃትም ሆነ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት ሴቶች በከባድ፣ ሞራላዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ለከፋ ጤናዊ ጉዳት ሰለባ አድርጓቸዋል" ብለዋል። ችግሩ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝም አክለዋል።

ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ በሀገራችን የችግሩ መስፋፋት በመገንዘብ በርካታ ሥራዎች እየተሰሩ ቢሆንም በቂ አለመሆኑን አንስተዋል።

ችግሩ ከመቅረፍ አኳያ የሕግ ክፍተት ከሚነሱ ተግዳሮቶች ውስጥ አንዱ መሆኑን ጠቁመው፤ "የወንጀል፣ የቤተሰብ፣ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ፣ የመንግስት ሠራተኛ አስተዳደር አዋጅ ህጎች ላይ ማሻሻያ ሊደረግ ይገባል" ብለዋል።

የጥቃቱ አድርሾች አስተማሪ ቅጣት እንዲቀጡ አቅጣጫዎች ተይዘው ከፍትሕ አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት ወደ ሥራ እንደተገባም አመላክተዋል።

ሚኒስትሯ ይህንን የተናገሩት ዓለም አቀፍ የጸረ-ጾታ ጥቃት ቀን "የሴቷም ጥቃት የኔም ነው ፣ዝም አልልም ከሕዳር 16 እስከ ታህሳስ 1 በሚቆየው በድሬዳዋ ከተማ ንቅናቄ ማስጀመሪያ መድረክ ላይ ነው።

ዓለም አቀፍ የጸረ- ጾታዊ ጥቃት ቀን ዘንድሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ33ኛ ጊዜ "Towards+30: UNITE to End Violence against women and Girls" በሚል መሪ ቃል፤ በሀገራችን ደግሞ ለ19ኛ ጊዜ "የሴቷ ጥቃት የእኔም ነው ዝም አልልም" በሚል መሪ ቃል ለ16 ተከታታይ ቀናት ይከበራል።

በወልደሐዋርያት ዘነበ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

"በትግራይ ክልል ወባን ጨምሮ ሌሎች ተላላፊ በሽታዎች መስፋፋት ፈተና ሆኗል" የክልሉ ጤና ቢሮ

ሕዳር 16/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በትግራይ ክልል በቅርቡ በፍጥነት የተዛመተው የወባ በሽታን ጨምሮ፤ ሌሎች ተላላፊ በሽታዎችን ለመቆጣጠር እየተቻለ እንዳልሆነ የክልሉ ጤና ቢሮ ለአሐዱ አስታውቋል።

በክልሉ በወባ በሽታ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 17 ሺሕ በላይ መሻገሩንና በርካቶችን ሕክምና ማዳረስ እየተቻለ አለመሆኑን ነው ቢሮው የገለጸው፡፡

በክልሉ ጤና ቢሮ የበሽታዎች ቁጥጥር ኃላፊ አቶ አረጋይ ገብረ መድኅን የበሽታውን ስርጭት ከክልሉ ከቁጥጥር በላይ መሆኑን ገልጸው፤ ከጤና ሚኒስቴር የተላከው የወባ መድኃኒት ማለቁንም ተናግረዋል፡፡

አክለውም፤ ቢሮው በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች የጤና ባለሙያዎችን መድቦ በሽታውን መቆጣጠር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ እየተሰራ መሆኑን የተናገሩ ሲሆን፤ "አሁንም ክልሉ ከየትኛውም ጊዜ በላይ የመድኃኒት እና የባለሙያ እርዳታ ይፈልጋል" ብለዋል።

በተለይም ቆላማ የክልሉ አካባቢዎችና የአፋር ክልል አዋሳኝ ስፍራዎች በበሽታው መጠቃታቸውን የጠቀሱት ኃላፊው፤ "የመከላከያ ዘዴው መላው ጠፍቶብናል" በማለት የችግሩን አሳሳቢነት አስረድተዋል።

ከዚህ በተጨማሪም የኮሌራ በሽታን ጨምሮ ሌሎች ውሃ ወለድ በሽታዎች በክልሉ ስጋት መደቀኑን የገለጹ ሲሆን፤ በፀጥታ ችግር ምክንያትም መድኃኒት ማዳረስ እየተቻለ እንዳልሆነ ተናግረዋል።

በክልሉ ባለፉት ሁለት ሦስት ዓመታት በቂ የመድኃኒት አቅርቦት እየቀረበ እንዳልነበረና፤ በዚህም የተነሳ አሁን ላይ የተከሰቱት በሽታዎች በሰዓቱ መቆጣጠር እንዳይቻል ማድረጉንም ገልጸዋል።

ከዚህ በተጨማሪ በአገራቀፍ ያሉ ረጂ ተቋማት ሰዎችን ለማትረፍ እጃቸውን እንዲዘረጉ የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ እየጠየቀ መሆኑን የክልሉ የበሽታዎች ቁጥጥር ኃላፊው አቶ አረጋይ ለአሐዱ ተናግረዋል።

አሐዱም እንደ ሀገር የወባ በሽታ ስርጭትን ጨምሮ ተላላፊ በሽታዎች መከላከል ረገድ ምን እየተሰራ እንደሆነ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጥያቄ ቢያቀርብም ኃላፊነቱ የጤና ሚኒስቴር ነው የሚል ምላሽ ሰጥተውናል።

በጉዳዩ ላይ የጤና ሚኒስቴርን ለመጠየቅ በተደጋጋሚ ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

የወባ በሽታ ስርጭት እንደ አገር አስቸጋሪ ደረጃ ላይ መሆኑን ቢታወቅም፤ በአጭር ጊዜ ባሳየው ስርጭት በትግራይ ክልል የታየው ከፍተኛው ነው ተብሏል።

በአማኑዔል ክንደያ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የትራምፕ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ በቀጣይ የዩክሬን ጦርነትን ለማስቆም እየሰተራ መሆኑን አስታወቁ

ሕዳር 16/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የሩሲያ እና የዩክሬንን ጦርነት በፖለቲካዊ መንገድ ለመፍታት እቅድ ተይዟል ሲሉ የትራምፕ የብሄራዊ የደህንነት አማካሪ ማይክ ዋልትዝ ተናግረዋል።

ዋልትዝ እሁድ ዕለት ለፎክስ ኒውስ በሰጡት ቃል፤ ተመራጩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የጦርነቱ መባባስ እና ቀጣይ ሂደት በጣም እንደሚያሳስባቸው ገልጸዋል።

አክለዉም "ዋናውና ቅድሚያ የሚሰጠው በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል የሚደረጉ ንግግሮችን ማደራጀት ነው" ያሉ ሲሆን፤ "አላማውም ሁለቱም ወገኖች የተኩስ አቁም ወይም የሰላም ስምምነትን እንዲያደርጉ ማደራደር ነዉ" ብለዋል።

ትራምፕ የ2024ቱን የአሜሪካ ምርጫ ከማሸነፋቸዉም በፊትም ሆነ ካሸነፉ በኋላ ጦርነቱን እንደሚያስቆሙት ቃል የገቡ ቢሆንም፤ ስልጣኑን ሊያስክብ የወራት እድሜ የቀረዉ የባይደን አስተዳደር በአለም አቀፍ ሕግጋት መሰረት በጦርነት ግንባር የማይፈቀዱ የጦር መሳሪያዎችን ለዩክሬን መፍቀዱ ጦርነቱን እንደ አዲስ እንዲባባስ አድርጓታል ሲሉም ወቅሰዋል።

በተጨማሪም የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች በግጭቱ ውስጥ ተሳትፈዋል ስለመባሉ ያነሱት የብሄራዊ ደህንነት አማካሪው፤ ደቡብ ኮሪያም "ግጭቱን ለመቀላቀል" እያሰበች መሆኑን ጠቅሰው፣ ግጭቱ የሚመለከታቸው አካላት ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ ሁኔታው ይበልጥ አሳሳቢ እንዳደረገው ተናግረዋል፡፡

አዲሱ የትራምፕ አስተዳደር ይህንን ግጭት በዘላቂነት ለማስቆም ቁርጠኛ መሆኑንም አስታውቀዋል።

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

#ADVERTISMENT
#AmharaBank
የአማራ ባንክ አ/ማ የባለአክሲዮኖች 3ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ማክሰኞ ታህሳስ 01 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ በሚሊኒየም አዳራሽ ስለሚካሄድ ባለአክሲዮኖች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጉባዔው እንድትገኙ ጥሪ እናስተላልፋለን፡፡

የጉባዔው አጀንዳዎችን እና ተጨማሪ መረጃዎችን ጥቅምት 06 ቀን 2017 ዓ.ም በወጡት አዲስ ዘመን እና ሪፖርተር አማርኛ እትም ጋዜጦች ላይ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ለበለጠ መረጃ ነፃ የጥሪ ማዕከል 690 ወይም
የባንኩን ድረ ገጽ www.amharabank.com.et ይጎብኙ፡፡

አማራ ባንክ
ከባንክ ባሻገር!

የአማራ ባንክ ትክክለኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾች
Website: www.amharabank.com
Facebook: www.Facebook.com/amharabanksc1
Telegram: /channel/Amhara_Banksc
Instagram: https://instagram.com/amhara_bank
Twitter: https://twitter.com/Amharabanksc
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/amharabank/
YouTube: https://youtube.com/channel/UC73x9uuGYV0Uxw0EkpVZN8g
TikTok: amharabanks.c" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@amharabanks.c

#አማራባንክ #AmharaBank

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

#አሐዱ_ወንዞች

ጥንቅሩን ለመከታተል ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👇
https://youtu.be/xhpwUL9w2zI?si=7kgJ-Todxf4DjOWB

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

#UPDATE
በአለልቱ ወረዳ በደረሰው የትራፊክ አደጋ የ11 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገለጸ

👉 በ40 ሰዎች ላይ ከባድና 11 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል ጉዳት ደርሷል


ሕዳር 14/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አለልቱ ወረዳ በደረሰው የትራፊክ አደጋ የ11 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የዞኑ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት አስታውቋል።

ዛሬ ጠዋት 2:30 ላይ ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ የሚጓዝ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ በተቃራኒ አቅጣጫ ከሚጓዝ ሲኖ ትራክ ተሸከርካሪ ጋር በመጋጨቱ አደጋው መከሰቱን በስፍራው ካሉ ነዋሪዎች ሰምቶ አሐዱ መዘገቡ ይታወሳል።

በአደጋው በርካታ ሰዎች መጎዳታቸውንና የሲኖ ትራክ ተሸከርካሪው ረዳት መኪና ውስጥ ተቀርቅሮ በመቅረቱ እርሱን ለማውጣት ከአንድ ሰዓት በላይ ጥረት ቢደረግም ሕይወቱን ማትረፍ አለመቻሉን ነዋሪዎቹ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

በአደጋው እስካሁን የ11 ሰዎች ሕይወት ማለፋን እንዲሁም፤ በ40 ሰዎች ላይ ከባድ እና 11 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል ጉዳት መድረሱን የዞኑ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ሥራ ሒደት ሃላፊ አቶ ሰለሞን ዘውዴ ለኤፍቢሲ ተናግረዋል።

በአደጋ የተጎዱ ሰዎች በሰንዳፋ ሆስፒታል ሕክምና እየተከታተሉ እንደሚገኙም ተመላክቷል።

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በሀገሪቱ እስካሁን ድረስ የቀጠለው ግጭት እንዲቆም እና ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን የኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጥሪ አቀረበ

👉 ጉባዔው በደራ ወረዳ ስላሌ አካባቢ የተጸመውን አሰቃቂ እና ጭካኔ የተሞላበት የግድያ ድርጊት አውግዟል


ሕዳር 17/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ በአንድ አንድ አከባቢዎች በተለያዩ ጊዜያት በንጽሀን ላይ ያነጣጠሩ የግድያ፣ የጥቃት፣ የእገታ፣ የመፈናቀል እና የዘረፋ ተግባራት መፈጸሙን በማንሳት፤ የተፈጸመውት ተግባራት በየትኛውም የሀይማኖቶት አስተምህሮት ፈጽሞ የተወገዙ መሆናቸውን የኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ አስታውቋል።

ጉባዔው በዛሬው ዕለት በሰጠዉ መግለጫ የሰሜኑ ጦርነት ሲጀምር ጀምሮ በተደጋጋሚ የሰላም ጥሪ ሲያደርግ መቆየቱን ገልጾ፤ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ያሉ የታጠቁ አካላት ወደ ሰላማዊ ትግል እንዲገቡ አሁንም ጥሪ እንደሚያቀርብ አስታዉቋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም "በተለይም ከቅርብ ቀናት በፊት በሰሜን ሸዋ ዞን በደራ ወረዳ ስላሌ አካባቢ የተጸሙ አሰቃቂ እና ጭካኔ የተሞላበት የግድያ ድርጊትም ችግሩ የደረሰበትን አስከፊ ደረጃ ለመድረሱ ማሳያ ነው" ሲሉ የጉባኤው ጠቅላይ ጸሀፊ ቀሲስ ታጋይ ታደለ ገልጸዋል።

አክለውም እነዚህን እና መሰል ድርጊቶችን ጉባኤዉ በጽኑ እንደሚያወግዝ እና በተለያዩ አካባቢዎች አሁንም እየተፈጸሙ ያሉ አጸያፊ ድርጊቶች እንዲቆሙ የሰላም ጥሪዉ ቀጣይነት እንደሚኖረው ገልጸዋል።

"በተለይም በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ያለው የታጣቂዎች እንቅስቃሴ ጋር ተያይዞ በክልሎቹ አዋሳኝ አካባቢዎች ለሚኖሩ ሕዝቦች ከባድ ፈተና ሁኗል" ያለው ጉባዔው፤ በሁሉም ወገን ከምንም በፊት ቅድሚያ ለሰላም እንዲሰጡ አሳስቧል።

በዚህም መሠረት ሁሉም አካላት ጉዳዮቻቸውን በጠረጴዛ ዙሪያ በማድረግ መነጋገሩና መደራደሩ በእጅጉ አስፈላጊ መሆኑን በመረዳት ለሁሉም ወገን የሰላም ጥሪውን አቅርቧል፡፡

ጉባዔው አክሎም በቅርቡ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የሁሉም አባትና ሽማግሌ በመሆን ፍፁም ገለልተኛ በሆነ አግባብ ግጭት ውስጥ የሚገኙ አካላትን ሁሉ ለማቀራረብ፣ ለማደራደርና ለማስታረቅ ቁርጠኛ እና ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።

በፅዮን ይልማ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

ቢሮው በመዲናዋ የተሽከርካሪዎች ማቆሚያ አጠቃቀም ችግርን መፍታት አለመቻሉን ገለጸ

ሕዳር 17/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ የተሽከርካሪዎች ማቆሚያ (ፓርኪንግ) አጠቃቀም ችግርን መፍታት አለመቻሉን አስታውቋል።

በአዲስ አበባ ከተማ ምንም እንኳን በርካታ መኪና ማቆሚያ ስፍራዎች ቢገነቡም፤ በታለመለት ልክ ተጠቃሚዎችን እያገኙ እንዳልሆነ ነው ቢሮው የገለጸው።

የቢሮው ኃላፊ ዳኛቸው ሽፈራው፤ በአዲስ አበባ ከተማ የትራፊክ መብራትን ጨምሮ የፓርኪንግ አጠቃቀም ላይ ከፍተኛ ችግር መኖሩን የገለጹ ሲሆን፤ የመኪና ማቆያ ስፍራዎች ላይ የሚስተዋለው የአጠቃቀም ችግር መሻሻል የሚገባው መሆኑን ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

አክለውም ከተማ አስተዳደሩ ከኮሪደር ልማት ዉስጥ ለመንገድ የተለየ ትኩረት መሰጠቱን በማንሳት፤ "ሆኖም ግን የመዲናይቱ መንገዶች ከታለመላቸዉ አላማ ውጪ እየዋሉ ነው" ብለዋል።

መንገዶች ለባስ፣ ለእግረኛ፣ እንዲሁም ለሌሎች የትራንስፖርት አማራጭ ተከፍለዉ ቢሰሩም፤ ለጉሊት ንግድ እንዲሁም ለሌሎች ጉዳዮች መዋላቸዉ ፈታኝ መሆኑን ተናግረዋል።

ባልተፈቀደ ስፍራ ተሳፋሪን መጫን እና ማውረድ እንዲሁም በእግረኛ መንገድ ላይ የሸቀጣ ሸቀጥ ንግድ ማካሄድ ዋና ዋና ችግሮች ስለመሆናቸውም አንስተዋል፡፡

በተጨማሪም "በአድዋ ሙዚየም 2 ሺሕ በላይ ፓርኪንግ ቢኖርም ባለተሽከርካሪዎች በተዘጋጀው ቦታ ላይ ማቆም አለመቻላቸዉ ከባድ ተግዳሮት ሆኖብናል" ብለዋል።

የከተማ መስተዳድሩ እየተስተዋለ ለሚገኘው የደምብ መተላለፍ አስፈላጊውን የማስተካከያ እርምጃ እንደሚወስድ የቢሮው ኃላፊ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

#አሐዱ_ትንታኔ

ትንታኔውን ለመከታተል ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👇
https://youtu.be/-z1pVS9hxCo?si=oRWfg_HlLkKiy28F

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የ2017 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግሥት ተጨማሪ 582 ቢሊየን ብር በጀት ጸደቀ

ሕዳር 17/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 6ኛ መደበኛ ስብሰባ የቀረበለትን የ2017 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግሥት ተጨማሪ 582 ቢሊየን ብር በጀት አጽድቋል።

የተጨማሪ በጀት ረቂቁን በምክር ቤቱ የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ ቤልጂጌ (ዶ/ር) አቅርበዋል።

ምክር ቤቱ በተጨማሪ በጀቱ ላይ ከተወያየ በኋላ በሦስት ተቃውሞ እና በአምስት ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ አጽድቆታል።

በዚህ በፊት በ6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 36ኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ፤ የፌዴራል መንግሥት የ2017 በጀት ዓመት አጠቃላይ በጀት 971 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ሆኖ መጽደቁ ይታወሳል።

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

ኢራን በእስራኤል መሪዎች ላይ የሞት ቅጣት እንዲወሰን ጠየቀች

ሕዳር 17/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ እና በግብረአበሮቸው ላይ የእስር ትዕዛዝ ማውጣት ብቻ ሳይሆን፤ የሞት ቅጣት እንዲወሰን ሲሉ የኢራን ጠቅላይ የሃይማኖት መሪ አያቶላህ አሊ ካሚኒ ጠይቀዋል።

አለም ዓቀፉ ፍርድ ቤት (አይሲሲ) ባለፈነው ሳምንት ሐሙስ ዕለት በእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚኒን ኔታንያሁ እንዲሁም፤ በቀድሞው መከላከያ ሚኒስትር ዮአብ ጋላንት የእስር ማዘዣ ማውጣቱ ይታወሳል።

ይህንንም ተከትሎ ካሚኒ የእስር ማዘዣውን አስመልክቶ በሰጡት አስተያየት፤ የእስራኤል ባለስልጣናት በጋዛ እና በሊባኖስ ላይ ለፈፀሙት አሰቃቂ ወንጀል የሞት ፍርድ ውሳኔ እንዲተላለፍባቸው ጠይቀዋል።

"አለም ዓቀፉ ፍርድ ቤት (አይሲሲ) በጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ እና በቀድሞው መከላከያ ሚኒስትር ላይ ያስተላለፈው ውሳኔ በቂ አይደለም" ሲሉም መናገራቸውን አልጄዚራ ዘግቧል።

የአይሲሲ ዳኞች ኔታንያሁ እና ጋላንት “በጋዛ ንፁሃን ላይ” ረሃብን እንደ ጦር መሳሪያ ተጠቅመዋል በሚል የእስር ትዕዛዝ እንዲተላለፍባቸው ባለፈዉ ሳምንት መወሰናቸዉ ይታወሳል።

ውሳኔውን የእስራኤል ባለስልጣናት "ተቀባይነት የሌለዉ ነው" ሲሉ ውድቅ ያደረጉት ሲሆን፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ውሳኔው "ፀረ-ሴማዊ ውሳኔ ነው" ብለውታል።

አክለውም "በጦርነቱ ወቅት በሲቪሎች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለማስወገድ የምንችለውን ሁሉ ስናደርግ ቆይተናል" ሲሉ ተናግረው ነበር።

አይሲሲ ከኔታኒያሁ እና ከዩአቭ ጋላንት በተጨማሪ፤ ለሐማሱ አዛዥ መሐመድ ዴይፍም፤ ለጦርነቱ መቀስቀስ ምክንያት በሆነውና ባለፈው ዓመት ጥቅምት ወር እስራኤል ውስጥ በተፈጸመው የጅምላ ግድያ ወንጀል የእስር ማዘዣ ማውጣቱ ይታወሳል።

ነገር ግን እስራኤል አዛዡ በጋዛ ውስጥ በሐምሌ ወር መገደላቸውን የተናገረች ሲሆን፤ ሀማስ ስለአዛዡ መገደል በይፋ አላረጋገጠም።

በደረጄ መንግስቱ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

#ADVERTISMENT
#ጊፍትሪልስቴት
ታላቅ የምስራች
!
**
ጊፍት ሪል ስቴት ከ10% ቅድመ ክፍያ ጀምሮ በ22 ሳይቶቹ ቅንጡ አፓርትመንቶችን እና የንግድ ሱቆችን ለሽያጭ አቅርቧል፡፡

ይህ ሳይት ለአፓርትመንትና ንግድ ሱቆች የሚውሉ G+25 ሶስት መንታ ህንጻዎች ያሉት ሲሆን የዚህ 6ኛ መንደር መለያዎች፡-
•ከባለአንድ እስከ ባለአራት መኝታ ክፍሎች ያሉት፣
•ለመኖሪያም ሆነ ለንግድ ተመራጭ አካባቢ የሆነ፣
•በአንድ ወለል ሶስት ቤቶች ብቻ ያሉት፣
•በእያንዳንዱ ወለል ስድስት አሳንስር ያለው፣
•አራት ቤዝመንት ያሉት በቂ የመኪና ማቆሚያ የተዘጋጀለት፣
•24 ሰዓት የኤሌክትሪክ፣ ኢንተርኔትና ውሃ አቅርቦት አሉት፣

ጊፍት ሪል ስቴት
ማህበረሰብን እንገነባለን!
ለበለጠ መረጃ፡-
Website: https://www.giftbusinessgroup.com                                                                                             
Twitter: https://twitter.com/GIFTBusinessG                                                     
YouTube: www.youtube.com/channel/UCcqr7cpVv9ski-F7haxXx4w                                                     
Facebook: www.facebook.com/profile.php?id=100090918391017...                                                       
Telegram: /channel/giftbusinessgroup

Short Code: 8055

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

#አሐዱ_አንቀፅ

"ችግራችን ቢያጥቡት ቢያጥቡት አልጠራ ያለ የጣት መቀሳሰር የፖለቲካ አስተሳሰባችን ነው። ከዘመነው አስተሳሰብ ጋር እኩል መራመድ አለመቻላችን በብዙ እጥፍ ዋጋ እያስከፈለን ነው"

ሙሉ ጥንቅሩን ለመከታተል ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👇
https://youtu.be/07a3GL2IObI?si=-XsPvrz5VTsFvjIg

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

ለትግራይ ክልል 200 አምቡላንሶች ድጋፍ መደረጉን የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር አስታወቀ

ሕዳር 16/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ለትግራይ ክልል 200 አምቡላንሶች ግዢ ተፈፅሞ ወደ ሀገር ውስጥ በመግባት ላይ እንደሚገኙና የተወሰኑትም አገልግሎት ለመስጠት እንቅስቃሴ ላይ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ገልጿል።

ከአሐዱ ጋር ቆይታ ያደረጉት የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የሰብዓዊ፣ ዲፕሎማሲና የኮሚኒኬሽን አገልግሎት ኃላፊ መስፍን ደረጄ፤ "የተገዙት አምቡላንሶች ከዚህ በፊት በጦርነቱ ምክንያት የወደሙትን 200 የሚደርሱ አምቡላንሶች የሚተኩ ናቸው" ብለዋል።

በግጭቱ ምክንያት እንደ ቀይ መስቀል ማኅበር ብቻም ሳይሆን አጠቃላይ የአምቡላንስ አገልግሎት ያቆመበት ጊዜ እንደነበር ጠቅሰው፤ "በርካታ የሕብረተሰብ ክፍል በችግር ውስጥ ነበር፤ አሁን ላይ ያንን ችግር ለመቅረፍ አምቡላንሶች ገብተዋል" ብለዋል።

የአምቡላንሶች ግዢ የተፈፀመውም በአንድ የአሜሪካ ባለሀብት በኩል መሆኑን አክለዋል። "ባሳለፍነው ዓመት ከ500 በላይ አምቡላንሶች በመላው ሀገሪቱ ድጋፍ ሲያደርጉ ነበር" ብለዋል።

በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማሕበርና እህት ማኅበራት አማካኝነትም በሁሉም ክልሎች አምቡላንሶች እንደተከፋፈሉ ያስታወሱት ኃላፊው፤ በቅርብ ጊዜም ሀያ አምቡላንሶች ግዢ ተፈፅሞ ለክልሎች ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

የኮሚኒኬሽን ኃፊው "የያዝነውን ዓመት ጨምሮ ባሳለፍነው ዓመት በግጭትና በድርቅ የተጎዱና የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም ከ3 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርግና ከአደጋ ስጋት ለማላቀቅ ሰፊ ሥራና ርብርብ ተደርጎ አመርቂ ውጤት አስገኝቷል" ብለዋል።

ማሕበሩ በእንግሊዝና በአሜሪካ መንግሥት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ለግጭት፣ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋ የተጋለጡ አካባቢዎች ተለይተው በአማራ፣ ትግራይ፣ ኦሮሚያና ቤንሻንጉል ክልሎች የጤና ምርመራ ድጋፍ እያከፋፈለ እንደሚገኝ አክለዋል።

በስፍራሽ ደመላሽ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በፒያሳ ደዳች ውቤ ሰፈር ከፍተኛ መጠን ያለው የእሳት አደጋ ተከሰተ

ሕዳር 16/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በአዲስ አበባ ከተማ፤ አራዳ ክፍለ ከተማ ራስ መኮንን አካባቢ፤ በተለምዶ ፒያሳ ደጃች ውቤ ተብሎ በሚጠራው ሰፈር ከፍተኛ መጠን ያለው የእሳት አደጋ ተከስቷል።

አደጋው በአካባቢው በሚገኘው በቻይና ጃንጉዜ የኮንስትራክሽን ሥራ ድርጅት ላይ ሲሆን፤ እሳቱን ለማጥፋት ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ይገኛል።

በአሁን ሰዓትም በሁሉም አቅጣጫዎች ተሽከርካሪዎች ወደቦታዉ እንዳይንቀሳቀሱ እየተደረገ መሆኑን አሐዱ ከቦታው ተገኝቶ ተመልክቷል።

በስፍራው ሲሚንቶና ኮንክሪት ለማዘጋጀት የሚጠቅሙ ኬሜካሎች እንዲሁም፤ ከፍተኛ መጠን ያለው ነዳጅ በመኖሩ የእሳት አደጋው እንዳይባባስ ስጋት መፍጠሩን ለመገንዘብም ተችሏል።

የአዲስ አበባ የእሳትና አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን በበኩሉ፤ የእሳት አደጋው በቁጥጥር ሥር ለማዋል የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ርብርብ እያደረጉ መሆኑን ገልጿል።

የአደጋው መንስኤ እስካሁን ምንም የተገለጸ ነገር የለም። አሐዱ ቀሪዉን መረጃ እየተከታተለ ወደእናንተ የሚያደርስ ይሆናል።

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

"እስራኤል ማክሸፍ ያቃታት የሒዝቦላ 250 ሚሳኤል"

በኢራን የሚደገፈውና መቀመጫውን ሊባኖስ ላይ ያደረገው ደግሞም "እስራኤል ከሃማስ ጋር የምታደርገውን ጦርነት ካላቆመች፤ እኔም በእስራኤል ላይ ጥቃት መሰንዘሬን እቀጥላለሁ" ያለው ሂዝቦላህ፤ ባለፉት ሁለት ወራት ውስጥ እጅግ ከፍተኛ የሚባል ቁጥር ያለውን ሚሳኤል በትናንትናው ዕለት ተኩሷል፡፡

እስራኤል በሊባኖስ እያደረገች ያለውን 'ጸረ-ሂዝቦላህ' ዘመቻ አጠናክራ መቀጠሏም ተሰምቷል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የአውሮፓ ሕብረት ለሊባኖስ ጦር ማጠናከሪያ የገንዘብ ድጋፍ አደርጋለሁ ብሏል፡፡ እነዚህን እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን በዛሬው አለም ዓቀፍ ትንታኔያችን እንመለከታለን፡፡

ሙሉ ትንታኔውን ለመከታተል ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👇
https://youtu.be/d7yI6ofEIfM?si=2IjDRn5cP5HpTob7

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

ሄዝቦላህ ወደ እስራኤል ከ340 በላይ ሮኬቶችን በማስወንጨፍ 11 ንፁሃን ሰዎችን ማቁሰሉ ተገለጸ

ሕዳር 16/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የሊባኖሱ ታጣቂ ቡድን ሄዝቦላህ ከ340 በላይ ሮኬቶችን እና ሰዉ አልባ ድሮኖችን ወደ እስራኤል በመተኮስ፤ 11 ሰዎችን ማቁሰሉ ተገልጿል።

በጥቃቱ በሰሜንና ማዕከላዊ እስራኤል በርካታ ሰዎች መጎዳታቸው የተገለጸ ሲሆን፤ ሕጻዎችና መኖሪያ ቤቶች መውደማቸውም ተነግሯል፡፡ በቴልአቪቭ ላይም መጠኑ ያልታወቀ ጉዳት አድርሷል ተብሏል፡፡

ቡድኑ ይህን ጥቃት ለመፈፀም የተገደደዉ "የእስራኤል ጦር የደቡባዊ ሊባኖስን ግዛት ለመቆጣጠር እያደረገ ያለዉን ግስጋሴ ለማክሸፍ ነዉ" ሲል አስታዉቋል።

ይህ ጥቃት፤ እስራኤል ቅዳሜ ዕለት በሊባኖስ መዲና ቤሩት ላይ በተለያዩ አቅጣጫዎች በተመረጡ የሂዝቦላህ ይዞታዎች ላይ ለፈጸመችው ጥቃት ምላሽ ነውም ተብሏል።

በቅዳሜው ጥቃት 29 ንጹሃን ለህልፈት መዳረጋቸውን የሊባኖስ ጤና ሚኒስቴር መግለጹ ይታወሳል።

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት፤ በአሁኑ የሄዝቦላህ ጥቃት እስካሁን ድረስ በ11 ሰዎች ላይ ከቀላል እስከ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ በተጨማሪም በሚሊየን የሚቆጠሩ እስራኤላውያን ከጥቃቱ በመሸሽ ወደ ምሽግ መግባታቸው ተነግሯል፡፡

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በወታደራዊ ማሰልጠኛ ካምፕ እና ተፈናቃዮች በሚኖሩባቸው አካባቢዎች የኤች አይቪ ስርጭት ከፍተኛ ስጋት መሆኑ ተገለጸ

ሕዳር 16/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የጤና ሚኒስቴር በወታደራዊ ማሰልጠኛ ካምፕ፣ ተፈናቃዮች በሚኖሩበት አካባቢ እንዲሁም ለሱስ ተጋላጭ የሆኑ ግለሰቦች በሚኖሩባቸው አካባቢዎች ላይ የኤች አይቪ ቫይረስ ስርጭት ከፍተኛ ስጋት ሆኗል ሲል ገልጿል፡፡

እነዚህ አካባቢዎች እና ግለሰቦች ለበሽታው ስርጭት ክፎኛ ተጋላጭ ስለሚሆኑ፤ ቅድሚያ ሰጥቶ እየሰራበት መሆኑንም አስታውቋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በኢትዮጵያ አንዳንድ ክልሎች የሚታዩ ግጭቶች፤ ለዜጎች የኤች አይቪ ምርመራ እና ክትትል ለማድረግ ተግዳሮት እየሆነበት መምጣቱን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

አሐዱም "በኢትዮጵያ ከ2012 ጀምሮ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ፣ በሰሜኑ ጦርነት እና አሁን በሚታዩ የእርስ በርስ ግጭቶች ምክንያት በበሽታው ስንት ሰዎች ሕይወታቸው አለፈ? ስንት ሰዎች በበሽታው ተያዙ? ስንትስ ሰዎች ለበሽታው ተጋልጠው ክትትል እየተደረገላቸው ነው" ሲል ጠይቋል፡፡

በጤና ሚኒስቴር የኤችአይቪ መከላከል ዴስክ ኃላፊ ወ/ሮ አብነት አሰፋ በሰጡት ምላሽ፤ ሰላም አለመኖሩ ሥራዎችን ለመስራት ፈታኝ እየሆነ መምጣቱን ገልጸው፤ ነገር ግን የሞቱ ሰዎችም ሆነ በበሽታው የተያዙ ሰዎችን ይፋዊ ቁጥር ከመናገር ተቆጥበዋል፡፡

"ይህ ሲባል ግን አቅም በሚችለው ልክ፤ ዜጎች ይበልጥ ለበሽታው ተጋላጭ እንዳይሆኑ ክትትል እየተደረገ ነው" ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ኃላፊዋ አክለውም፤ "ስርጭቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ እንደ አዲስ አስጊ ሆኗል" ያሉ ሲሆን፤ ይህንን ታሳቢ በማድረግ እንደ ጤና ተቋማት፣ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ካምፖች እንዲሁም በብዛት ተፈናቃይ በሚኖርባቸው አካባቢዎች እና ለሱስ ተጋላጭ ግለሰቦች በሚኖሩበት አካባቢዎች ቅድሚያ ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ እስካሁን ድረስ 605 ሺሕ የሚደርሱ ሰዎች ቫይረሱ በደማቸዉ መኖሩ ተረጋግጧል የተባለ ሲሆን፤ "ከእነዚህ መካከል ከ500 ሺሕ በላይ የሚሆኑት ወጣቶች ናቸው" ሲል ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በደረጄ መንግስቱ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

መልካም ቀን!
አሐዱ ሬድዮ 94.3  የኢትዮጵያውያን ድምፅ!

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

መንግሥት የሠራተኞችን የመጠቀም ዕድል እስካላመቻቸ ድረስ የሚሰሩበትን የሥራ ሰዓት ቢጨምር ውጤታማ አይሆንም ተባለ

ሕዳር 14/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የፌደራሉ መንግሥት የሠራተኞችን የመጠቀም ዕድል ቅድሚያ ሰጥቶ እስካላሻሻለ ድረስ፤ የሰዓት ጭማሪ ብቻውን በሕግ ቢያጸድቅ፤ ውጤታማ ሊያደርደገው አይችልም ሲሉ አሐዱ ያነጋገራቸው የሕግ ባለሙያዎች ገልጸዋል፡፡

አሐዱ ከሰሞኑ የመንግሥት ሠራተኞች ከዚህ ቀደም በሳምንት ሲሰሩ የነበረውን የ39 ሰዓት ወደ 48 ሰዓት ከፍ አድርገዉ እንዲሰሩ የሚያስገድደዉን ረቂቅ አዋጅ መሰረት በማድረግ፤ “በሠራተኞቹ ላይም ሆነ በመንግሥት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ አያሳድርም ወይ? እንዲሁም ከአለም ዓቀፍ ሕግጋት አንጻር እንዴት ይታያል” ሲል ጠይቋል፡፡

የሕግ ባለሙያው አቶ ጥጋቡ ደሳለኝ በሰጡት ምላሽ፤ "አንድ ሰው በአለም ዓቀፍ ሕግ በቀን መስራት ያለበት 8 ሰዓት ነው" ብለዋል፡፡

ከዚህ በላይ ከሆነ ግን እንደ ድርጅቱ እና ሠራተኛው ፍቃደኝነት የሚወሰን መሆን እንዳለበት አስረድተዋል።

የውሳኔውን ረቂቅ አዋጅ በሁለት መልኩ እንደሚመለከቱት የገለጹት የሕግ ባለሙያው፤ በአንድ በኩል መንግሥት በሠራተኞች ላይ የሰዓት ጭማሪ ሲያደርግ የደሞዝ ጭማሪም ማድረግ እንዳለበት ጠቁመው፤ "በሌላ መልኩ ደግሞ በመንግሥት ላይ የሚያሳድረው አሉታዊ ተጽዕኖ ቀላል የሚባል አይደልም" ሲሉ ተናግረዋል።

ሌላኛው የሕግ ባለሙያ አቶ ወንድሙ ኢብሳ በበኩላቸው፤ "በምንም አይነት መልኩ በሠራተኛ ላይ አንድ ተቋም ሥራ ሲጨምር ሆነ የሥራ ሰዓት ሲያራዝም በዛው ልክ የሠራተኛውን ደሞዝ ማሻሻል አለበት" ባይ ናቸው፡፡

"ነገር ግን ይህን ማድረግ ካልተቻለ አመርቂ ውጤት ማምጣት አይቻልም" ብለዋል፡፡

"ሠራተኞችን ሳያስፈቅዱ አስገድዶ ለማስራት መሞከር ሀገርን ለይበልጥ ኪሳራ ማጋለጥ እንጂ ግብ የሚያመጣ ለውጥ ማምጣት አይቻልም" ሲሉም የሕግ ባለሙያዎቹ ተናግረዋል፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሳምንቱ መጀመሪያ ሕዳር 10 ቀን 2017 ዓ.ም ባከናወነው 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ስብሰባ፤ የፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች አዋጅን ለማሻሻል የቀረበለትን ረቂቅ አዋጅ መርምሮ ማጽደቁ ይታወሳል።

በደረጄ መንግስቱ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

ጾታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶችን ከመከላከል አኳያ የሕግ ክፍተት መኖሩ ተገለጸ

ሕዳር 14/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ጾታን መሠረት ባደረጉ ጥቃቶች ላይ እየተደረገ ያለ ቅደመ መከላከል ሥራ ቢኖርም እንደ ሀገር የሕግ ክፍተት መኖሩን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒሰቴር ለአሐዱ አስታውቋል።

ከችግሩ ጋር ተያይዞ የጥቃቱ ፈፃሚ አካላት በሕግ ቁጥጥር ሥር ከዋሉ በኋላ የሚበይነው ውሳኔ አስተማሪ አለመሆኑ ተነስቷል፡፡

በተለይም የተቀመጠው ሕግ በሥራ ቦታ ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ብቻ እርምጃ የሚወሰድባቸው በመሆኑ፤ በሥራ ባልደረባ አማካኝነት ከሥራ ገበታ ውጭ  የሚሰነዘሩ ጥቃቶችን ለመከላከል የሕግ ክፍተቶች መኖራቸውን የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሚኒስቴር ዴኤታ ሂክማ ከይረዲን ተናግረዋል፡፡

የሕግ ክፍተቶች በመኖራቸው ሳቢያ በስፋት እየተስተዋለ የመጣዉን የአስገድዶ መድፈር፣ ግድያ እና ፆታን መሠረት ያደረገ ጥቃትን ለመቆጣጠር እና ለመከላከል አስቻይ አለማድረጉን ሚኒስቴር ዴኤታዋ ገልጸዋል፡፡

አክለውም ቀድመዉ የወጡ ነገር ግን በጊዜያቸው ትክክል የነበሩ ውሳኔዎች፤ አሁን ላይ 'አስተማሪ አይደሉም' ተብሎ የተለዩ ሕጎች ተለይተው እንዲሻሻሉ ጥናት ተደርጎ መጠናቀቁን ጠቁመዋል።

በቀጣይ በየደረጃቸው ካሉ በሚመለከታቸው ተወካዮች ምክር ቤት አና ከፍትሕ አካላት ጋር በቅንጅት በመወያየት የተለዩ ሕጎች ማሻሻያ እንዲደረግ እና ድርጊቱን ፈፃሚዎችን አስተማሪ እንዲሆን ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በወልደሐዋሪያት ዘነበ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official

Читать полностью…
Subscribe to a channel