ahaduradio | Unsorted

Telegram-канал ahaduradio - AHADU RADIO FM 94.3

19349

አሐዱ ራድዮ 94.3 Your source for top local and international news and analysis. "Voice of Ethiopian" የአሐዱ የቴሌግራም ቻናል ቤተሰብ በመሆን ወቅታዊና እውነተኛ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ

Subscribe to a channel

AHADU RADIO FM 94.3

መሐመድ እድሪስ የሰላም ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ

ሕዳር 20/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሕዳር 18 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ መሐመድ እድሪስን የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር አድርገው መሾማቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።

አዲሱ የሚኒስቴሩ ተሿሚ አቶ መሀመድ እድሪስ በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ሲያገለግሉ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ላይ የሚደረገው እገዳ ሊቆም ይገባል ሲል ቅድሚያ ለሰብዓዊ መብቶች አሳሰበ

ሕዳር 20/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በሰብዓዊ መብት ተሟጓች ድርጅቶች ላይ እየተጣለ የሚገኘው ከአዋጅ ውጪ እገዳ አሳሳቢ በመሆኑ፤ ሊቆም ይገባል ሲል ቅድሚያ ለሰብዓዊ መብቶች አሳስቧ።

ባሳላፍነው ሳምንት በሰብዓዊ መብት ተሟጓች ድርጅቶች ላይ የእገዳ እርምጃ በኢፌዴሪ የሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን መወሰዱን ያስታወሰዉ ድርጅቱ፤ "ይህ እርምጃ በሕገ መንግሥቱ እና ኢትዮጵያ በተቀበለቻቸው ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ አቀፍ የሰብዓዊ መብት ስምምነቶች የተረጋገጠውን የመደራጀት መብት የሚጋፋ ነው" ብሏል።

"የሰብዓዊ መብት ተሟጓች ድርጅቶች በመንግሥት ላይ የሚያቀርቡት ወቀሳ፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ምርመራ፣ ሰብዓዊ መብት እንዲከበሩ የሚያቀርቡት ክሶች እና ክርክሮች እንዲሁም የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ እና ወደ ትኩረት እንዲመጡ የሚያግዙ ለመንግስትም አጋዥ የሆኑ እንቅስቃሴዎች መሆናቸው መረዳት ያስፈልጋል" ሲልም በሲቪል ማህበረሰቦች ላይ እየደረሰ ያለዉን ጫና ተችቷል፡፡

በሰብዓዊ መብት ተሟጓች ድርጅቶቹ ላይ የተጣሉ እገዳዎች የድርጅቶቹን መብትና ዓላማዎች የሚያጠቡ፣ የሲቪል ማሕበረሰብ እንቅስቃሴ የሚያቀጭጩ ናቸው የሚል ስጋት እንዳለውም ገልጿል፡፡

በሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ መሰረት አዋጁን እና ሌሎች ሕጎችን በሚጥሱ ድርጅቶች ባለስልጣኑ በፅሁፍ ማስጠንቀቂያ ሊሰጥ እንደሚችል መደንገጉን የገለጸው ቅድሚያ ለሰብዓዊ መብቶች፤ በአዋጁ ባለስልጣኑ በሲቪል ድርጅቶች ላይ በምርመራ ከባድ የሕግ ጥሰት መፈጸሙን ሲያረጋግጥ ደግሞ ጊዚያዊ እግድ ሊጥል እንደሚችል መቀመጡን አስታውሷል።

ሆኖም ግን አሁን ከታገዱ ድርጅቶች መካከል አንዱ ባለስልጣኑ በአዋጁ መሰረት ቢሮ ድረስ በመምጣት የባለስልጣኑ ክትትል ያልተደረገባቸው፣ ማስጠንቀቂያ ያልተሰጣቸው ምንም አይነት ምርመራ ያልተጀመረባቸው እና አስተካክሉ የተባለበት መነሻ ሳይኖር ቀጥታ እግድ እንደተጣለባቸው መረዳቱን ገልጿል።

"ይህ ደግሞ ከአዋጁ ውጭ የሆነ እገዳ በመሆኑ አሳሳቢ ያደርጓል" ሲል ቅድሚያ ለሰብዓዊ መብቶች ገልጿል፡፡

ስለሆነም መንግሥት አዋጁን ሳይከተሉ የሚወሰዱ እርምጃዎች የሲቪል ማህበረሰብን እንቅስቃሴ እጅግ የሚጎዳና እና የሚያቀጭጭ መሆኑን ተረድቶ፤ ጉዳዩን ሕጉ በሚያዘው መሰረት ብቻ መርምሮ ተገቢ መፍትሔ እንዲሰጣቸው ጠይቋል።

በፅዮን ይልማ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

መልካም ቀን!
አሐዱ ሬድዮ 94.3  የኢትዮጵያውያን ድምፅ!

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

ፑቲን ሩሲያ የኃይል ማመንጫ መሰረተ ልማት ላይ የፈጸመችው ጥቃት፤ ዩክሬን ለተጠቀመችው የረዥም ርቀት ሚሳኤል ምላሽ መሆኑን ገለጹ

ሕዳር 19/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ሩሲያ ዛሬ ማለዳ በዩክሬን የኃይል ማመንጫ መሰረተ ልማት ላይ ያነጣጠሩ ተከታታይ የሚሳኤል እና ሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቃቶችን መፈጸሟን የዩክሬን ባለስልጣናት አስታውቀዋል።

ሩሲያ ክሩዝ በተሰኘው ሚሳይል ጥቃት ከፈጸመችባቸው ከተሞች መካከል ኦዴሳ፣ ክሮፒቭኒትስኪ፣ ካርኪቭ፣ ሪቪን እንዲሁም ሉትስክ እንደሚገኙበት የተገለጸ ሲሆን፤ በርካታፐፍንዳታዎች በመላው ዩክሬን መሰማታቸው ተዘግቧል።

ይህን ተከትሎ የዩክሬን የኢነርጂ ሚኒስተር ሄርን ሁለስቼንኮ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባጋሩት መረጃ፤ "በጠላት መጠነ ሰፊ ጥቃት የኃይል መሰረተ ልማች በድጋሚ ኢላማ ተደርገዋል" ሲሉ ገልጸዋል።

በሩሲያ ከሦስት ቀናት በፊት በምዕራብ ዩክሬን የምትገኘውነሰ ቴርኖፒል የጥቃት ኢላማ አድርጋ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን፤ ዛሬ በምዕራብ ዩክሬን ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት ስታደርስ ይህ ሁለተኛው ነው።

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ዩክሬን ከእንግሊዝና አሜሪካ የተሰጣትን የረጅም ርቀት ሚሳኤሎች ሩሲያ ላይ እየተጠቀመች እንዳለች ከገለጹ በኋላ፤ ምሽቱን በኤሌክትሪክ ጣቢያዎች ላይ ከሀገራቸው የተሰነዘረውን ጥቃት "ለረጅም ሚሳኤሎቹ ምላሽ ነው" ብለዋል፡፡

ቀጣዩ የፑቲን እርምጃ  የዩክሬን ማእከላዊ ማዘዣ ጣቢያን በአዲስ የባለስቲክ ሚሳኤል መምታት ሊሆን እንደሚችል መግለጻቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

የዩክሬን ባለስልጣናት እንደገለጹት 12 በሚሆኑ ኢላማዎች የኤሌክትሪክ ጣቢዎች የወደሙ ሲሆን፤ የሩሲያ የኤሌክትሪክ ጥቃቶች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዩክሬናውያን የኤሌክትሪክ ሃይል እንደተቋረጠባቸው ተነግሯል፡፡

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት በጥቃቱ መቶ ድሮኖች እና 90 ሚሳኤሎች ከሩሲያ እንደተተኮሰባቸው ገልጸዋል፡፡

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የሽግግር ፍትህ ፖሊሲው በተሟላ ሁኔታ መተግበር ለተጎጂዎች አስፈላጊ መሆኑ ተገለጸ

ሕዳር 19/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ ለተፈፀሙ በደሎች እና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እውነትን በማፈላለግ እና ይፋ በማውጣት እንዲሁም፤ የተቋምና የሕግ ማሻሻያ ሥራዎችን ተግባራዊ በማድረግ በተጎጂዎች ላይ ያተኮረ የተሟላ የሽግግር ፍትህ ስርዓት መተግበር አስፈላጊ መሆኑ ተገልጿል።

ወጥነት ያለው ግልጽ፣ ተጠያቂነትና ፍትህን የሚያሰፍን የሽግግር ፍትህ ትግበራ ሂደትን ለመምራት እንዲቻል ብሔራዊ የሽግግር ፍትህ ፖሊስ መውጣቱ ይታወቃል።

የኢትዮጵያን ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አውድ መሰረት ያደረገ፣ የተቀናጀ እና የተናበበ የሽግግር ፍትህ ሂደት የሚመራበት እና የሚተገበርበትን ስርዓት በመዘርጋት ዘላቂ ሰላም፣ ዕርቅ፣ የሕግ የበላይነት፣ ፍትህ እና ዲሞክራሲ የሚረጋገጥበትን መደላድል መፍጠር የፖሊሲው ዓላማ እንደሆነም ተመላክቷል።

በትግበራው የገዳ ስርዓትን ጨምሮ በኢትዮጵያ የሚገኙ ባህላዊ የፍትህ ስርዓቶች እና እሴቶች እንደ አስፈላጊነቱ ተገቢ ማሻሻያዎችን እንዲካሄዱ በማድረግ፤ በሂደቱ ሚና እንዲኖራቸው የሚደረግ መሆኑንም የሽግግር ፍትህ አማካሪ ወይዘሮ ሳምራዊት ጣሰው መናገራቸውን አሐዱ ሰምቷል።

ይህንኑ ፖሊሲ የሚደግፈው የአፍሪካ ሕብረት የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ማዕቀፍ የሽግግር ፍትህ ሀገራት የተለያዩ የፖሊሲ እርምጃዎች እና ተቋማት አሠራሮችን በመጠቀም ያለፉ ጥሰቶችን፣ ክፍፍሎችን እና ሌሎችንም ጉዳዮች ለለውጥ ስርዓት ግንባት ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር  አስፈላጊ እንደሆነ ተገልጿል።

ፖሊሲው እስከ ዛሬ የተፈጸሙ ጉልህ በደሎችን እውቅና መስጠት፣ ለበደሎች ተጠያቂነት ማስፈንና ተጎጂዎችን መካስ እና ሌሎች ተመሳሳይ ሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዳይፈፀም ከማድረግ አኳያ ሚናው ከፍ ያለ መሆኑም ተመላክቷል።

በአበረ ስሜነህ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

መድኃኒት መደብሮች ከጤና ተቋማት በ100 ሜትር ርቀት ላይ እንዲከፈቱ የሚደረግበት አሰራር ስለመኖሩ ተገለጸ

ሕዳር 19/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በመዲናዋ የሚከፈቱ የመድሃኒት መደብሮች በአካባቢው አገልግሎት ከሚሰጡ ከጤና ተቋማት በአንድ መቶ ሜትር ርቀት ላይ እንዲሆኑ የሚደረግበት አሰራር መኖሩን የአዲስ አበባ አስተዳደር ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን አስታውቋል፡፡

በባለስልጣኑ የጤና ተቋማትና ባለሙዎች ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ ገልገሎ ኦልጅራ የመድሃኒት መደብሮች አገልግሎት ለመስጠት፤ ከአራት መሰረታዊ መስፈርቶችን ቢያንስ ሦስቱን ማሟላት እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል፡፡

ከእነዚህም ውስጥ የመድሃኒት መሸጫ መደብሩ የሕንጻ ግንባታ ሁኔታ፣ የጤና ባለሙያዎች እና የመድሃኒት መደብሩ ምን ያህል መድሃኒቶችን መያዝ አለበት የሚሉ ጉዳዮች ተጠንተው እንደሚከፈቱ ለአሐዱ አስረድተዋል፡፡

በመሆኑም የመድሃኒት መደብሮች ከጤና ተቋማት በ100 ሜትር ርቀት ላይ እንዲከፈቱ የሚደረግበት አሰራር፤ በአንድ አካባቢ ላይ በብዛት አገልግሎት በመስጠት በሌሎች አካባቢዎች ላይ እጥረት እንዳያጋጥም ለማድረግ ታስቦ የተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

አክለውም በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ከአንድ ሺሕ ስድስት መቶ በላይ የመድኃኒት መደብሮች መኖራቸውን ተናግረዋል።

በዚህም ሆስፒታሎች እና ጤና ጣቢያዎች ከሚሰጡት አገልግሎት አንጻር የራሳቸው የመድሃኒት መደብሮች እንዲኖራቸው ስለመደረጉም አብራርተዋል፡፡

በሌላ በኩል በ2017 ሩብ ዓመት በሦስት ወራት ውስጥ ብቻ፤ ከ3 ሺሕ 600 ኪሎ ግራም በላይ የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸው መድኃኒቶች መወገዳቸውን ዳይሬክተሩ ለአሐዱ ተናግረዋል።

የአገልግሎት ጊዜ ያለፈባው መድኃኒቶች በመድኃኒት መደብሮች ውስጥ ከ6 ወራት በላይ መቆየት ባይኖርባቸውም፤ ባለው የመድሃኒት ማስወገጃ ቦታ እጥረት ምክንያት ለማስወገድ ስለመቸገራቸው ጨምረው ገልጸዋል።

በቀጣይ ተጨማሪ የአገልግሎት ጊዜ ያለፈባቸውን መድኃኒቶች የማስወገጃ ቦታ ለማዘጋጀት እቅድ ስለመያዙም ተናግረዋል።

በእሌኒ ግዛቸው
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

"እስካሁን ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት በቅርሶች ላይ የደረሰ ጉዳት የለም" የአማራ ክልል የባህልና ቱሪዝም ቢሮ

ሕዳር 19/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በአማራ ክልል ከአንድ ዓመት በላይ በዘለቀው ጦርነት እና ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት፤ እስካሁን በቅርሶች ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩን የክልሉ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ለአሐዱ አስታውቋል።

"በክልሉ የጸጥታ ችግር መኖሩን ተከትሎ ምን ያህል ቅርሶች ጉዳት ደረሰባቸው?" ሲል አሐዱ የቢሮው የቅርስ ጥበቃና እንክብካቤ ዳይሬክተር አቶ ጋሽዬ መለሰን ጠይቋል፡፡

ዳይሬክተሩም በምላሻቸው "የጸጥታ ችግር ለሕገወጥ የቅርሶች ዝውውር  ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል" ያሉ ሲሆን፤ በክልሉ ከአንድ ዓመት በላይ በተራዘመው ግጭት ምክንያት እስካሁን በቅርሶች ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩን ገልጸዋል።

አክለውም በበጀት ዓመቱ ወደ 40 የሚደርሱ የቅርስ ቦታዎች ላይ በቢሮው የቅርስ ጥገናና እንክብካቤ ለመስራት በእቅድ መያዙን ተናግረዋል።

በተጨማሪም "በሩብ ዓመቱ በቢሮው ብቻ ወደ 40 የሚደርሱ ቋሚ ቅርሶች የጥገናና እንክብካቤ ሥራዎች ሰርተናል" ያሉ ሲሆን፤ በ2017 በጀት ዓመት ወደ 29 የሚደርሱ ገንዘብ የሚመደብላቸው ግን ከዛም በፊት የተጀመሩ የቅርስ ማዕከላት ስለመኖራቸው ገልጸዋል።

እንዲሁም ወደ 11 የሚደርሱት የቅርስ ማዕከላት በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ተቋም (ዩኒስኮ) የተመዘገቡ ሲሆን፤ በመንግሥት አነሳሽነት እየተሰሩ ስለመሆናቸው አብራርተዋል።

በሁሉም የክልሉ  አካባቢዎች የቅርስ ጥበቃና እንክብካቤ ይደረጋል ያሉት ዳይሬክተሩ፤ ከከተማ አስተዳድሮች ውጭ በሰሜን ጎንደር፣ በማዕከላዊ ጎንደር፣ በደቡብ ጎንደር፣ በሰሜን ወሎ፣ በደቡብ ወሎ፣ በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ፣ ምስራቅ ጎጃም፣ ምዕራብ ጎጃም እንዲሁም ሰሜን ጎጃምን አጠቃሎ በሁሉም ዞኖች ቅርስ ጥገና እንደሚደረግም አስረድተዋል።

በአንማው በሪሁን
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

"የጊዚያዊ አስተዳደሩ አመራሮች ህወሓትን በአመፅ ለመበተን ወጣቶች እያሰለጠኑ ናቸው" አቶ አማኑኤል አሰፋ

👉አማኑኤል አሰፋ አቶ ጌታቸው ረዳን "የቀድሞው ፕሬዝዳንት" ሲሉ ጠርተዋቸዋል


ሕዳር 19/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ለሚመራው ህወሓት ምክትል ሊቀመንበር አቶ አማኑኤል አሰፋ፤ የጊዚያዊ አስተዳደሩ አመራሮች ህወሓትን በአመፅ ለመበተን ወጣቶች እያሰለጠኑ ናቸው ሲሉ ወንጅለዋል፡፡

አቶ አማኑኤል ትናንት መቐሌ ላይ ለብዙኀን መገናኛ በሰጡት መግለጫ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳን "የቀድሞው ፕሬዝዳንት" ሲሉ የጠሯቸው ሲሆን፤ በእነ ዶ/ር ደብረጽዮን የሚመራው ቡድን ባካሄደው ጉባኤ ከሥልጣን የተነሱ በመሆናቸው ፕሬዝደንትነታቸውን እንደማይቀበል ተናግረዋል፡፡

"የፕሬዝዳንት ውክልና ሲነሳ ፕሬዝዳንቱ በሌለበት ማን እንደሚሰራ ይታወቃል" ያሉት አቶ አማኑኤል፤ "ኃላፊ በሌለበት ጊዜ እሱን ተክቶ የሚሰራ እንዳለ ይታወቃል ምንም የስልጣን ክፍተት አይፈጠርም፣ ህወሓት የወከላቸውን የተወሰኑ ሰዎች ውክልና አንስቷል ውክልናውን ስላነሳን ነው የቀድሞ ፕሬዜዳንት የሚለውን ቃል የተጠቀምኩት" ሲሉም አክለዋል፡፡

እንዲሁም "ፕሬዝዳንቱን የሚተካ ሰውን በሚመለከት ህወሓት ከፌዴራል መንግሥት ጋር እየተነጋገር ነው" ያሉ ሲሆን፤ ውጤቱ ይፋ እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡

ከቀናት በፊት የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በሰጡት መግለጫ የህወሓት አመራሮች በውስጣቸው ያለውን ክፍፍልና ልዩነት ካልፈቱ የክልሉን አስተዳደር ፌዴራሉ መንግሥት ሊይዘው እንደሚችል ማሰስቡን መግለጻቸው የሚታወስ ሲሆን፤ አቶ አማኑኤል ግን "ይህ ከሀቅ የራቀ ነው" ሲሉ መግለጫውን አጣጥውታል።

በዚህም 'የጊዜያዊ አስታዳደሩን ስልጣን ብልፅግና ይረከበዋል ተብሏል' ተብሎ የተነገረው "ፍጹም የተሳሳተ ነው" ያሉት አቶ አማኑኤል፤ "ወደዚህ ደረጃም አልደረስንም እንዲህ አይነት መልስም አልተሰጠም። ከፌዴራል መንግሥት ጋር የተጀመረው ውይይት ይቀጥላል" ሲሉ ተናግረዋል።

በተጨማሪም ከባለፈው ጉባኤ በኃላ ፓርቲያቸው በወረዳና ከተሞች የአመራር ማስተካከያ ማድረጉን፣ የወረዳና ከተማች ምክር ቤት በህወሓት አብላጫ ወንበር የተያዘ በመሆኑ የተሻለ አመራር መመደቡን እንዲሁም፤ በጊዜያዊ አስተዳደሩ የሚገኙ ፕሬዝዳንቱን ጨምሮ 13 አመራሮች ውክልና ቀድሞ መነሳቱን አቶ አማኑኤል በሰጡት መግለጫ ገልጸዋል።

በሌላ በኩል "የቀድሞ ተዋጊዎችን ትጥቅ በማስፈታት እና ወደ ኅበረተሰቡ የማቀላቀል ሥራ፣ የቀድሞ ተዋጊዎችን ተጠቃሚ በሚያደርግ መልኩ እየተሠራ አይደለም" ያሉት አቶ አማኑኤል ሂደቱን መቃወማቸውን ቪኦኤ ዘግቧል።

የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው በቅርቡ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ በህወሓት አመራሮች መካከል የተፈጠረው ችግር በክልሉ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ህይወት ላይ ከፍተኛ ጫና እና ስጋት መፍጠሩን ገልጸዋል፡፡

በዚህም “ጉባኤ ያካሄደው ቡድን ከዞን እስከ ቀበሌ ባለው ኔትዎርክ አማካኝነት የመንግሥት ሥራ እንዲሽመደመድ በማድረግ መፈንቅለ መንግሥት እየፈጸመ ይገኛል” ማለታቸው ይታወሳል፡፡

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በአማራ ክልል በሚገኙ የጤና ተቋማት ላይ የደረሰውን ጉዳት ለዓለም አማቀፉ ማኅበረሰብ የሚያስረዳ ሰነድ መዘጋጀቱ ተሰማ

ሕዳር 19/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በአማራ ክልል ባለው ግጭት ምክንያት የጤና አገልግሎቱ የሚገኝበትን አሳሳቢ ደረጃ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የማስተዋወቅ እና የደረሰውን ጉዳት የመታደግ ዓላማ ያለው ሰነድ መዘጋጀቱን የክልሉ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ፎረም አስታውቋል።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፎረም ዋና ጸሐፊ ዶክተር ተፈራ መላኩ ለአሐዱ እንደተናገሩት፤ ዓለም አቀፍ የረድኤት ተቋማት በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ባሉ ግጭቶች ምክንያት አብዛኛዎቹ የጤና አገልግሎት መስጫ ተቋማት መጎዳታቸውን ከተረዱ በኋላ፤ በክልሉ የሚገኙ የጤና አገልግሎት ተቋማትን በዓይነት እና በገንዘብ እንደሚያግዙ ይጠበቃል።

ዶ/ር ተፈራ በተጨማሪም በክልሉ የጤና ተቋማት ብቻ ሳይሆኑ በርካታ ትምህርት ቤቶች ከአገልግሎት ውጭ መሆናቸውን ጠቅሰው፤ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴአቸው እንዲመለሱ የዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ እርዳታ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፎረም ማክሰኞ ሕዳር 17 ቀን 2017 ያዘጋጀውን የስትራቴጂ ሰነድ በአገር ውስጥ ያሉትን ጨምሮ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ አስተዋውቋል።

ፎረሙ ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ያዘጋጀው ጉባኤ ምላሹ ተስፋ አስቆራጭ እንደነበር ያስታወሱት ዋና ጸሐፊው፤ አሁን የዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ ለመጠየቅ እንደተገደዱ ተናግረዋል።

በክልሉ ከ2012 ጀምሮ በግጭት ምክንያት 40 ሆስፒታሎችን ጨምሮ ከ450 በላይ ጤና ጣቢያዎች፣ ከ1800 በላይ ጤና ኬላዎች እንዲሁም ከ120 በላይ አምቡላንሶች ላይ ውድመት እንደደረሰባቸው ተመላክቷል።

እንዲሁም አሁን ላይ ከ4 ነጥብ 7 ሚልዮን በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ መሆናቸውን፣ 4 ሺሕ 870 ት/ቤቶች መዘጋታቸውን እና 1552 የሚሆኑት ደግሞ መውደማቸውን ተነግሯል።

በአማኑዔል ክንደያ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

መልካም ቀን!
አሐዱ ሬድዮ 94.3  የኢትዮጵያውያን ድምፅ!

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 አካባቢ ነዋሪዎች "ቦታው ሕገ ወጥ ነው" በሚል ከቤት ካስወጡን በኋላ ሌላ ሰው እንዲገባ እየተደረገ ነው ሲሉ ቅሬታ አቀረቡ 

ሕዳር 18/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በአዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 አካባቢ ከ15 እስከ 40 ዓመት የኖሩበትን ቤት "ሕገ -ወጥ ነው" በሚል ከቤት እንዲወጡ ከተደረገ በኋላ፤ ሌላ ሰው ገብቶበታል ሲሉ ቅሬታ አቅራቢዎች ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

በቀድሞ ሥሙ ቀበሌ 19 በአሁኑ ወረዳ 6 አካባቢ የሚገኙት ነዋሪዎቹ፤ በአንድ ቦታ ውስጥ 13 አባወራዎች የሚኖሩ ሲሆን አጠቃላይ ብዛታቸው 40 እንደሚሆኑ አንስተዋል፡፡

እንዲኖሩ የፈቀዱላቸዉ ግለሰብ ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩ "የሰራችሁት ቤት ሕገ ወጥ ነው ትወጣላችሁ" በሚል በሁለት ቀን ማስጠንቀቂያ ከቤት እንዲወጡ መደረጋቸውን ነግረዉናል፡፡

አክለውም "የተሰራው ቤት ሕገ ወጥ ከሆነ ለምን አይፈርስም? ለምን ለሌላ ነዋሪ አሳልፋችሁ ሰጣችሁ?" በማለት በተደጋገሚ ወረዳና ክፍለ ከተማ በአካል ቅሬታችውን ቢያቀርቡም ምላሽ እንዳላገኙ ገልጸዋል፡፡

በአሁኑ ሰዓት ሸራ ወጥረው በረንዳ ላይ እንደሚገኙና ከወጡ ከ16 ቀን በላይ እንደሆናቸው የገለጹት ቅሬታ አቅራቢዎቹ፤ ልጆቻቸው ትምህርት ለመማር እንደተቸገሩና ተጽዕኖ እንደደረሰባቸው ተናግረዋል፡፡ 

አሐዱም ይህንን ችግር በተመለከተ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ምስጋናው ሒጂሉን ያናገረ ሲሆን፤ ኃላፊው በምላሻቸው ቦታው የቀበሌ ቤት መሆኑን አንስተው "ሰዎቹ ሁሉም ተከራይ ናቸው" ሲሉ ተናግረዋል፡፡ 

አክለውም "በሕጉ መሰረት የቀበሌ ቤትን መከራየት አይቻልም፡፡ ይሁን እንጂ ባለቤት የነበሩት ሲያርፉ የተከራዩትን እንዲወጡ ተደርጓል" ያሉ ሲሆን፤ በመመሪያው መሰረት ቤቶች አስተዳደር ቤቱን ለሌላ ሰው አሳልፎ መስጠቱን ተናግረዋል፡፡

ማንኛውም ሰው ከመመሪያውና ከሕጉ ውጭ የሚሰራ እንደሌለ አንስተው፤ የቤቶች አስተዳደር ባወጣው መመሪያ መሰረት እየተሰራ መሆኑንም ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

በአለምነው ሹሙ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

#አሐዱ_ትንታኔ

ትንታኔውን ለመከታተል ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👇
https://youtu.be/J8xKhYe3L_Y?si=82NChc4j1Sr1OEcX

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በኮየ ፈጬ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ያለው የኤሌክትሪክ አቅርቦት መቆራረጥ ችግር ሆኖብናል ሲሉ ነዋሪዎች ቅሬታቸውን ገለጹ

ሕዳር 18/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በሸገር ከተማ ኮየ ፈጬ ክፍለ ከተማ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የሚኖሩ ነዋሪዎች ያለው የኤሌክትሪክ አገልግሎት መቆራረጥ እና ጠፍቶ መቆየት ችግር ፈጥሮብናል ሲሉ ቅሬታቸውን ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

ነዋሪዎቹ አክለውም፤ ለአንድ ብሎክ ያለው አንድ ቆጣሪ በመሆኑ እና ነዋሪዎች ቁጥራቸው እየጨመረ በመሆኑ ችግር ውስጥ ነን ብለዋል፡፡

አሐዱም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ይህን ችግር መፍታት ለምን አልተቻለም የጋራ መኖሪያ ቤቶች አንድ ቆጣሪ ብቻ መደረጉስ ለምንድን ነው ሲል የአገልግሎት መስሪያ ቤቱን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ መላኩ ታየን ጠይቋል፡፡

ባገኘው ምላሽም የኮየ ፈጬ አካባቢ ብቻ ሳይሆን በቦሌ ቡልቡላ የጋራ መኖሪያ ቤቶችም ችግሩ ማጋጠሙን የገለጹ ሲሆን፤ "ይህም የተፈጠረው ቤቶቹ ሲገነቡ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማትን ታሳቢ ባለማድረጋቸው መዘርጋት ባለመቻሉ ነው" ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በግለሰብም ይሁን በመንግሥት የሚገነቡ ሕንጻዎች የኤሌክትሪክ ዝርጋታን ታሳቢ ማድረግ አለባቸው ያሉት ዳይሬክተሩ፤ "ሥራዉ ከተጠናቀቀ በኋላ መታሰቡ የሃይል አቅርቦታን ለመዘርጋት ፈታኝ ነው" ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በእመቤት ሲሳይ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የእስራኤል እና ሄዝቦላህ የተኩስ አቁም ስምምነት ተግባራዊ መደረግ ጀመረ

ሕዳር 18/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) እስራኤል እና የሊባኖሱ ሄዝቦላህ ትናንት ሕዳር 18 ቀን 2017 ዓ.ም. ባደረጉት የተኩስ አቁም ስምምነት መሰረት፤ ዛሬ ስምምነቱ ተግባራዊ መደረግ መጀመሩ ተገልጿል፡፡

ለ13 ወራት የዘለቀውን ውጊያ ለመቋጨት የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ እንዲደረስ የእስራኤል የጸጥታ ካቢኔ ትናንት ባደረገው ምክክር ወስኗል፡፡

ይህንን ግጭት ለማቆም ስምምነት ላይ መደረሱን የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ያረጋገጡ ሲሆን፤ የተኩስ አቁሙ ግጭትን በዘላቂነት ወደማቆም ስምምነት ለመምራት ያለመ መሆኑን መናገራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

ነገር ግን በኢራን የሚደገፈው ሄዝቦላህ በስምምነቱ ላይ የሰጠው መግለጫ የለም።

በአሜሪካ አደራዳሪነት አሁን የተደረሰው ስምምነት በሄዝቦላህ እና እስራኤል መካከል በአውሮፓውያኑ 2006 የተከሰተውን ጦርነት የቋጨው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 1701 በተሰኘው ውሳኔን የተሰመረው ድንበር የተመሰረተ እንደሆነም ተገልጿል።

ይህም እስራኤል እና ሊባኖስ ከሚዋሰኑበት ሊታኒ ከተሰኘው ደቡባዊ ሊባኖስ ስፍራ የሄዝቦላህ ተዋጊዎች እንዲርቁ ማድረግን ያካተተ ነው ተብሏል።

እስራኤል፣ ሄዝቦላህ የተኩስ አቁም ስምምነቱን ከጣሰ ወታደራዊ እርምጃ የመውሰድ መብት እንዳላት የገለጸች ሲሆን፤ ፕሬዚዳንት ባይደንም፤ “ከዓለም አቀፍ ህግ ጋር በተጣጠመ መልኩ ራሷን የመከላከል መብት አላት” ማለታቸው ተነግሯል።

በዚህ የተኩስ አቁም ስምምነት መሰረት እስራኤል በሚቀጥሉት 60 ቀናት ከወረረቻቸው የሊባኖስ ደቡባዊ ክፍል ቀስ በቀስ ወታደሮቿን ታስወጣለች የተባለ ሲሆን፤ በምትኩም የሊባኖስ መንግሥት ወታደሮች ስፍራውን እንደሚቆጣጠሩት ተመላክቷል።

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

አስቸኳይ ሕክምና 15 ሺሕ ብር እንዲሁም ለሕይወት ማለፍ ካሳ ከ30 እስከ 250 ሺሕ ብር የሚያስከፍል ሕግ ተሻሽሎ መጽደቁ ተገለጸ

ሕዳር 18/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በትራፊክ አደጋ ለሚከሰቱ ጉዳቶች ለአስቸኳይ ሕክምና 15 ሺሕ ብር እንዲሁም በአደጋው ለደረሰው የሕይወት ማለፍ ከ30 እስከ 250 ሺሕ ብር የሚደርስ ካሳ ተሻሽሎ መጽደቁ ተገልጿል፡፡

ከአስር ዓመት በፊት በነበረው ሕግ ለትራፊክ አደጋ የአስቸኳይ ጊዜ ሕክምና 2 ሺሕ ብር እንደነበር የተገለጸ ሲሆን፤ በአደጋው ለሚከሰት የሕይወት ማለፍ ካሳ ከ5 ሺሕ እስከ 40 ሺሕ ብር እንደነበር ተነግሯል፡፡

በመሆኑም ደንብ ቁጥር 554 ካሳ እና አስቸኳይ ሕክምናን የተመለከተ ሕግ ተሻሽሎ መጽደቁን ለአሐዱ የተናሩት፤ በመንገድ ደህንነት መድን ፈንድ አገልግሎት የድህረ ትራፊክ አደጋ ኢኒስፔክሽን ባለሙያ አቶ ቡኮና ዱጋሳ ናቸው፡፡

በተሸሻለው ሕግ መሰረት፤ በትራፊክ አደጋዎች ለሚከሰቱ የሕይወት ማለፍ ከ30 ሺሕ ብር እስከ 2 መቶ 50 ሺሕ ብር የሚደርስ የካሳ ክፍያ የሚከናወን እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡

ተቋሙ የትራፊክ አደጋ ከመከሰቱ በፊት ለህብረተሰቡ ግንዛቤ የመፍጠር ሥራ እንደሚያከናውን እና አደጋዎች ከደረሱ በኋላ ተጎጂዎች አስቸኳይ የሕክምና እርዳታ እንዲሁም ካሳ እንዲያገኙ እንደሚያመቻች ተገልጿል፡፡

ባለሙያው አክለውም፤ እየጨመረ ያለው የትራፊክ አደጋ መበራከት፣ የአስቸኳይ ሕክምና ለማመቻቸት የነበረውን ሕግ ለማሻሻል ምክንያት መሆኑን አመላክተዋል፡፡

ከዚህ ቀደም በነበረው መመሪያ መሰረት በሚደርሱ የትራፊክ አደጋዎች ከአስቸኳይ ሕክምና እና ከሕይወት ማለፍ በተጨማሪም ለንብረት መውደም ደግሞ አንድ መቶ ሺሕ ብር ይከፈል እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

ከሀምሌ 23 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ሕጉ መሻሻሉ የተገለጸ ሲሆን፤ በተተሸሻለው ሕግ መሰረት የሚከናወነው የካሳ ክፍያ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ስነልቦናዊ ጫናን ለማቃለል ያለመ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡

በእሌኒ ግዛቸው
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የመንግሥት ሠራተኛው በማህበር መደራጀት አለመቻሉ የሚደርስበትን ጫና ለማስቆም ጥረት እንዳላደርግ እንቅፋት ሆኖብኛል ሲል ኢሰማኮ ገለጸ

ሕዳር 20/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የደመወዝ ጉዳይንም ሆነ ሌሎች ጥያቄዎች ምላሽ እንዲሰጥባቸው ጥረት ለማድረግ የመንግሥት ሠራተኛው በማህበር መደራጀት አለመቻሉ መሰናክል ሆኖብኛል ሲል የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) አስታውቋል፡፡

በመንግሥት ሠራተኞች በኩል በተደጋጋሚ የሚቀርበው የደመወዝ ጭማሪ ጥያቄን በሚመለከት "በጥቅምት ወር ላይ ጭማሪው ተግባራዊ ይደረጋል" ተብሎ ቢጠበቅም፤ ባልታወቀ ምክንያት መራዘሙ ቅሬታ አስነስቷል፡፡

ከአሐዱ ጋር ቆይታ ያደረጉት በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር የመንግሥት ሠራተኞች፤ "የደመወዝ ጭማሪው በጥቅምት ወር ይጀመራል ተብሎ ቢጠበቅም፤ ተግባራዊ ሊሆን አለመቻሉ ቅሬታ ፈጥሮብናል" ብለዋል፡፡

በተለይም ለጭማሪው መዘገይት "የመረጃ አለመጥራት ነው" የሚል ምክንያት መሰጠቱ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ያነሱት ቅሬታ አቅራቢዎች፤ "ይህ ችግር እስከመቼ እንደሚቀጥል እርግጠኛ አይደለንም" ብለዋል፡፡

የማክሮ ኢኮኖሚው ማሻሻያ መደረጉን እንዲሁም ከአንዴም ሁለቴ "ይከፈልበታል" የተባለው የደሞዝ ጭማሪ መዘግየቱ ተከትሎ፤ የኑሮ ውድነቱ በከፍተኛ ሁኔታ ጫና እያሳደረባቸው ስለመሆኑም ሠራተኞቹ ገልጸዋል፡፡

ይህንን የደሞዝ መዝግየት በሚመለከት አሐዱ የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽንን ለመጠየቅ ተደጋጋሚ የስልክ ሙከራ ቢያደርግም አልተሳካም፡፡

የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማህበራት ኮንፌደሬሽን የዘገየውን የሠራተኞች ደመወዝንና የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ሠራተኛው ላይ እያሳደረ ያለውን ጫና አስመልክቶ አሐዱ ለኮንፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ካሳሁን ፎሎ ጥያቄ አቅርቧል፡፡

ፕሬዝዳንቱ በምላሻቸው በኢትዮጵያ የመንግሥት ሠራተኛው መደራጀት እንደማይችል ገልጸው፤ "ከእኛ ጋር የተደራጁት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ናቸው" ብለዋል፡፡

በአፍሪካ ኢትዮጵያን ጨምሮ ኤርትራ እና ጅቡቲ የመንግሥት ሠራተኛ ማህበር ማደራጀት እንደማይችሉም ፕሬዝዳንቱ ጨምረው ተናግረዋል፡፡

በዚህም ምክንያት የሠራተኛውን ጥያቄ ማንሳት የማይችሉበት ሁኔታ መኖሩን አስታውቋል፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሕዳር 17 ቀን 2017 ባካሄደው 6ኛ መደበኛ ስብሰባዉ የቀረበለትን የ2017 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግሥት ተጨማሪ 582 ቢሊየን ብር በጀት በማፅደቅ፤ አጠቃላይ በጀቱን 1 ነጥብ 5 ትሪሊየን ብር ማድረሱ ይታወሳል፡፡

ይህንን በጀት ባፀደቀበት ወቅትም ከምክር ቤት አባላት፤ የመንግሥት ሠራተኞች የደሞዝ ጭማሪ ተግባራዊ ባለመሆኑ እና የተደረገው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ የደምወዝተኛውን ማህበረሰብ አኗኗር እንዳከበደው ሀሳብ ተነስቷል፡፡

በአቤል ደጀኔ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

#ADVERTISMENT
#AmharaBank
የአማራ ባንክ አ/ማ የባለአክሲዮኖች 3ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ማክሰኞ ታህሳስ 01 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ በሚሊኒየም አዳራሽ ስለሚካሄድ ባለአክሲዮኖች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጉባዔው እንድትገኙ ጥሪ እናስተላልፋለን፡፡

የጉባዔው አጀንዳዎችን እና ተጨማሪ መረጃዎችን ጥቅምት 06 ቀን 2017 ዓ.ም በወጡት አዲስ ዘመን እና ሪፖርተር አማርኛ እትም ጋዜጦች ላይ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ለበለጠ መረጃ ነፃ የጥሪ ማዕከል 690 ወይም
የባንኩን ድረ ገጽ www.amharabank.com.et ይጎብኙ፡፡

አማራ ባንክ
ከባንክ ባሻገር!

የአማራ ባንክ ትክክለኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾች
Website: www.amharabank.com
Facebook: www.Facebook.com/amharabanksc1
Telegram: /channel/Amhara_Banksc
Instagram: https://instagram.com/amhara_bank
Twitter: https://twitter.com/Amharabanksc
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/amharabank/
YouTube: https://youtube.com/channel/UC73x9uuGYV0Uxw0EkpVZN8g
TikTok: amharabanks.c" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@amharabanks.c

#አማራባንክ #AmharaBank

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

#አሐዱ_ሳድስ

"3ኛው የአለም ጦርነት በሩን እያንኳኳ ነው" በአብይ ይልማ

ሙሉውን ለመከታተል ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👇
https://youtu.be/MpIPBKMvrD8?si=rTtaJeaX9EMwmYaa

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የታገቱ የቀይ መስቀል ሠራተኞች የት እንዳሉ እንደማይታወቅ ተገለጸ

👉 ከ15 በላይ የሚሆኑ አባላት ከአምቡላንስ ተሽከርካሪዎች ጋር አብረው በመቃጠላቸው ሕይታቸው አልፏል


ሕዳር 19/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ከዚህ በፊት ግጭት ባለባቸው የተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ላይ በመንቀሳቀስ ሰብዓዊ እርዳታን በሚሰጡበት ወቅት፤ በታጣቂዎች ታፍነው የተወሰዱ ሠራተኞቹ እስካሁን የት እንዳሉ እንደማይታወቅ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር አስታውቋል።

ማህበሩ ግጭት ባለባቸው የተለያዩ አካባቢዎች ላይ በመንቀሳቀስ ሰብዓዊ እርዳታን የሚያድርግ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ይሁን እንጂ በሥራ እንቅስቃሴ ወቅት በጎ ፈቃደኛ የማህበሩ ሠራተኞች ጥቃት እየደረሰባቸው ስለመሆኑና አለፍ ሲልም ታግተው የተወሰዱት እስካሁን የት እንዳሉ አለመታወቁን፤ የማህበሩ የሰብዓዊ ዲፕሎማሲያዊና የኮሚኒኬሽን አገልግሎት ኃላፊ አቶ መስፍን ደረጄ ለአሐዱ ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም በግጭት ቀጠናዎች ላይ ድጋፍ በሚያደርጉበት ወቅት እስካሁን ከ15 በላይ የሚሆኑ አባላት ከአምቡላንስ ተሽከርካሪዎች ጋር አብረው በመቃጠላቸው ሕይታቸው ማለፉን የገለጹት ኃላፊው፤ አሁንም ማህበሩ ተንቀሳቅሶ ለመስራት ስጋት የሆኑ ቦታዎች መኖራቸውን አንስተዋል፡፡

በቅርቡም ግጭት ያለባቸው አካባቢዎች ላይ መድሀኒት ማድረስ አለመቻሉን፣ ተሽከርካሪዎች ተይዘው እስከ ወር ድረስ የሚቆዩበት አጋጣሚዎች መኖራቸውን ያነሱ ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት በአንዳንድ ቦታዎች ላይ መጠነኛ መሻሻል ስለመኖሩ ተናግረዋል።

"የትኞቹም ሰብዓዊ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት፣ በጎ ፈቃደኞች፣ ሕጻናትና ሴቶች፣ ጤና ተቋማትና ትምህርት ቤቶች የጥቃት ሰለባ መሆን የለባቸውም፤ ይህ አይነት ድርጊት የሰውን ሕይወት ከመቅጠፍ በቀር ምንም ለውጥ አያመጣም" ሲሉም ኃላፊው አሳስበዋል።

አክለውም የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ከየትኛውም ባህል፣ ሀይማኖት፣ ብሔርና አስተሳሰብ ገለልተኛ የሆነ ፤  የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ህጎችን ጠብቆ በጄኔቫ ስምምነቶች የሚንቀሳቀስ በመሆኑ እንዲህ አይነት ድርጊት መፈጸም ተገቢ አለመሆኑን አንስተው፤ ድርጊቱ በአለም ዓቀፍ ሕግም በሞራልም የሚያስጠይቅ በመሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ስለሆነም "የቀይ መስቀልን አርማ አድርገው የሚንቀሳቀሱ ሠራተኞች እንዲሁም በጎ ፈቃደኞች በሙሉ ተገቢ ክብር ሊሰጣቸው ይገባል" ብለዋል።

በስፍራሽ ደመላሽ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በ6 ነጥብ 5 ሚሊየን ፓውንድ የክትባት ተደራሽነት ለማስፋት የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ

ሕዳር 19/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ሴቭ ዘ ችልድረን ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመሆን በሦስት ክልሎች በአስራ ስድስት ወረዳዎች የሚተገበርና 6 ነጥብ 5 ሚሊየን ፓውንድ (ከአንድ ቢሊየን ብር በላይ) በጀት የመደበለት ፕሮጀክት በዛሬው ዕለት ይፋ ተደርጓል።

ፕሮጀክቱ ለአራት ዓመት የሚቆይ ሲሆን፤ የሚተገበርባቸው ክልሎችም የክትባት ተደራሽነት የቀነሰባቸው አማራ፣ ኦሮሚያ እና ሶማሊያ ክልሎች መሆናቸው ተገልጿል።

ከክልሎቹ ባሻገር ምንም አይነት ክትባት ያልወሰዱ እንዲሁም ክትባት ጀምርው ያቆሙ ሕጻናት ቁጥር በጥናት የተለዩ ወረዳዎች ላይ መሆኑ ነው የተገለጸው።

ፕሮጀክቱን ለማስጀመር በተደረጉ ጥናቶች ክትባት ያልወሰዱ ሕጻናት ቁጥር መጨመር እንደምክንያት ከተጠቀሱት የክትባቶች እጥረት፣ የባለሙያዎች አለመኖር፣ የጤና ተቋማት ርቀት፣ ተንቀሳቃሽ ማህበረሰቦችን የግንዛቤ እጥረት ጨምሮ ሌሎች ምክንያቶች መኖራቸው ተነስቷል።

እነዚህን ክፍተቶች ለመሙላት የተቀረጸው ፕሮጀክት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ይሠራል ተብሏል።

የፕሮጀክቱ ይፋዊ ማስጀመሪ ላይም የክትባቶችን ተደራሽነት ለማገዝ 52 የክትባት ማስቀመጫ ፍሪጆች ያሏቸው ሞተር ሳይክሎች ለጤና ሚኒስቴር አስረክቧል።

እንዲሁም ያሉትን የመረጃ ክፍተቶች ለመሙላት የሚውል 50 የሞባይል ታብሌቶችን ሴቭ ዘ ችልድረን ሰጥቷል።

የጤና ሚኒስቴር በ2016 በጀት ዓመት ብቻ፤ ከ1 ሚሊየን በላይ ሕጻናት ምንም አይነት ክትባት (zero dose) አለመውሰዳቸውን መግለጹ ይታወሳል።

በፍርቱና ወልደአብ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

#አሐዱ_ትንታኔ

ትንታኔውን ለመከታተል ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👇
https://youtu.be/citQHnVaQ7Q?si=133Wnw6e8lrJtSQD

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በመዲናዋ በ2017 የመጀመሪያው ሩብ ዓመት 5 ሺሕ 530 ሞት መመዝገቡ ተገለጸ

ሕዳር 19/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በ2017 ዓ.ም የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ውስጥ 5 ሺህ 530 ሞት መመዝገቡን፤ የአዲስ አበባ ከተማ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጄንሲ አስታውቋል፡፡

በ2016 ተመሳሳይ ወቅት ጋር የነበረው የሞት መዝገብ 3 ሺሕ 466 የነበረ ሲሆን፤ በ2017 የተመዘገበው 5 ሺሕ 530 መዝገብ 59 ነጥብ 55 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።

በዚሁ ሩብ ዓመት 8 ሺሕ 124 ጋብቻ ተመዝግቦ 1 ሺሕ 790 ያህል ፍቺ መመዝገቡ የተገለጸ ሲሆን፤ ይህም ከ2016 ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የፍቺ መጠኑ በ52 ነጥብ 73 በመቶ ከፍ እንዲል አድርጓል ተብሏል።

አሐዱ ያነጋገራቸው የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጄንሲ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር ወ/ሮ ጀሚላ ረዲ፤ ኅብረተሰቡ ወዲያው የተፈጠሩ ኩነቶችን የማስመዝገብ ልምዱ በየጊዜው መሻሻል ቢኖርም አሁንም አናሳ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

"ኩነቶችን የማስመዝገብ ዋናው አላማ ለሕግ፣ ለመረጃ እና ለአስተዳደራዊ እርምጃዎች ጠቃሚ በመሆኑ በወቅቱ ምዝገባ ማድረግ አስፈላጊ ነው" ብለዋል።

በዚህም መሰረት ወቅታዊ ኩነት ተመዝግቧል የሚባለው ልደት ከተደረገ በ90 ቀን ሲመዘገብ፣ ጋብቻ፣ ፍቺ፣ ሞት እና ጉዲፈቻ በ30 ቀን ውስጥ ምዝገባው ሲጠናቀቅ መሆኑን የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተሯ ጠቁመዋል፡፡

በስፍራሽ ደመላሽ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

ምክር ቤቱ የፖሊሲ፣ የሕግ እና የአሰራር ጥሰት ፈጸመዋል በተባሉ ኃላፊዎች ላይ እርምጃዎች መወሰዱ ተገለጸ

ሕዳር 19/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የንግዱን ማኅበረሰብ ሀብት ያባከኑ፣ ቦርዱ የማያውቃቸውን የውጪ ጉዞዎችና የተጋነነ የውጪ ምንዛሬ ያከናወኑ እንዲሁም የፖሊሲ፣ የሕግ እና የአሰራር ጥሰትን ፈጽመዋል በተባሉ ኃላፊዎች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን የአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማኅበረሰብ ምክር ቤት አስታውቋል።

ምክር ቤቱ ለአሐዱ በላከው መግለጫ እንዳለው፤ ውሳኔው የተላለፈው በዳይሬክተሮች ቦርድ የተሰየመው የምክር ቤቱ የውስጥ ኦዲተር በኦዲት ልዩ ክትትል እና በጠቅላላ ዳይሬክተሮች ቦርድ አቅጣጫ ሰጪነት ምርመራውን አጠናቆ፣ የመጨረሻ ግኝቱን ሚስጥራዊነቱን ጠብቆ በማስረጃ እና በመረጃ አስደግፎ ለዳይሬክተሮች ቦርድ ባቀረበው የውሳኔ ሐሳብ መሰረት ነው፡፡

ምክር ቤቱ የቀረቡትን 23 ጥቆማዎች መነሻነት የኦዲት ኮሚቴ ከቦርዱ አባላት በማዋቀር በጽ/ቤቱ ላይ ልዩ የኦዲት ምርመራ እንዲካሄድ መወሰኑን ገልጿል።

ለአፈጻጸሙም ተቋማዊ ሪፎርምን የሚመሩ ከቦርድ የተወጣጡና በምክትል ፕሬዝዳንት የተመሩ 3 የስትሪንግ ኮሚቴ አባላት እና ከጽ/ቤት ከተወጣጡ 9 የለውጥ አመራሮች ሪፎርሙን እውን እንዲያደርጉ መመረጣቸው ተመላክቷል።

ኮሜቴው በተሰጠው ተግባር መሰረት የአሰራር ጥሰቶችን ጥልቀትና መጠን በመለየት፤ የመመሪያ፣ የደንብ እና የፖሊሲ ክፍተቶችን በጥልቀት በመመርመር የፖሊሲ፣ የሕግ እና የአሰራር ጥሰት ፈጸመዋል በተባሉ ኃላፊዎች ላይ እርምጃዎች መወሰዱን አስታውቋል፡፡

ተቋሙ ለአሐዱ በላከው መግለጫ በምን ያህል አመራሮች ላይ እርምጃ እንደወሰደ አልገለጸም፡፡

በወልደሀዋርያት ዘነበ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

#ADVERTISMENT
#ጊፍትሪልስቴት
ታላቅ የምስራች!

**
ጊፍት ሪል ስቴት ከ10% ቅድመ ክፍያ ጀምሮ በ22 ሳይቶቹ ቅንጡ አፓርትመንቶችን እና የንግድ ሱቆችን ለሽያጭ አቅርቧል፡፡

ይህ ሳይት ለአፓርትመንትና ንግድ ሱቆች የሚውሉ G+25 ሶስት መንታ ህንጻዎች ያሉት ሲሆን የዚህ 6ኛ መንደር መለያዎች፡-
•ከባለአንድ እስከ ባለአራት መኝታ ክፍሎች ያሉት፣
•ለመኖሪያም ሆነ ለንግድ ተመራጭ አካባቢ የሆነ፣
•በአንድ ወለል ሶስት ቤቶች ብቻ ያሉት፣
•በእያንዳንዱ ወለል ስድስት አሳንስር ያለው፣
•አራት ቤዝመንት ያሉት በቂ የመኪና ማቆሚያ የተዘጋጀለት፣
•24 ሰዓት የኤሌክትሪክ፣ ኢንተርኔትና ውሃ አቅርቦት አሉት፣

ጊፍት ሪል ስቴት
ማህበረሰብን እንገነባለን!
ለበለጠ መረጃ፡-
Website: https://www.giftbusinessgroup.com                                                                                             
Twitter: https://twitter.com/GIFTBusinessG                                                     
YouTube: www.youtube.com/channel/UCcqr7cpVv9ski-F7haxXx4w                                                     
Facebook: www.facebook.com/profile.php?id=100090918391017...                                                       
Telegram: /channel/giftbusinessgroup

Short Code: 8055

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የትግራይ ክልልን ፍቃድ ካገኘ በሦስት ሳምንት ውስጥ ውስጥ ሥራዎችን መጀመር እንደሚችል የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታወቀ

ሕዳር 18/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዋጅ የተቋቋመ ኮሚሽን ቢሆንም የክልሎችን ትብብር በመፈለጉ፤ የትግራይ ክልል ግዚያዊ አስተዳደር ፍቃድ እስካሁን አለማግኘቱን አስታውቋል፡፡

ነገር ግን የጊዜያዊ አስተዳደሩን ፈቃድ የሚያገኝ ከሆነ ሥራውን በጥቂት ቀናት ውስጥ ማጠናቀቅ እንደሚችል ገልጿል፡፡

በተጨማሪም "የክልሉ መንግሥት ሥራዎችን በነፃነት ኮሚሽኑ እንዲሰራ የማመቻቸት ኃላፊነት አለበት" ሲሉ የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

በተደጋጋሚም ለክልሉ ጥሪ እያደረገ መሆኑን የገለጹት ኮሚሽነር መስፍን፤ "በማንኛውም ጊዜ ክልሉ ጥሪ በሚያቀርብልን ወቅት ወደ ሥራ ለመግባት ዝግጁ ነን" ብለዋል፡፡

የትግራይ ክልልን ያገለለ ምክክር ማድረግ ፍላጎት እንደሌለው በተደጋጋሚ የሚገልጸው የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ፤ የፍላጎቱን ያህል ግን በክልሉ ምንም ዓይነት ሥራ መስራት አለመቻሉ ይገለጻል፡፡

ኮሚሽኑ ለዚህም ተጠያቂ የሚያደርገው የክልሉን ግዚያዊ አስተዳደር ሲሆን፤ "ጊዜያዊ አስተዳደሩ በዚህ ላይ ዝምታን መምረጡ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑን ሥራ አዘግይቷል" የሚሉም አልጠፉም፡፡

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከሰሞኑ ከአራቱ የትግራይ ዩኒቨርሲቲዎች ማለትም ከመቀሌ፣ አክሱም፣ አዲግራት እና ራያ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ውይይት ማድረጉ ይታወሳል፡፡

ይህንንም በሚመለከት ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ከዩኒቨርሲቲዎቹ ጋር ጥሩ ውይይት እንዳደረጉ በማስታወስ፤ የክልሉን ፍቃድ የሚያገኙ ከሆነ በሦስት ሳምንታት ውስጥ ምክክሩን መጀመር እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ፤ "የሀገራዊ ምክክር ተካሄደ የሚባለው ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሲሳተፉበት ብቻ ነው" ሲሉም ተናግረዋል፡፡

በቅርቡ የአፈፃፀም ሪፖርቱን ለሕዝብ ተወካዮች ያቀረበው የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፤ በትግራይ ክልል አጀንዳ እና ተሳታፊዎችን ለመለየት የምክር ቤቱ እገዛ እንደሚያስፈልገው መግለጹ የሚታወስ ነው፡፡

በአቤል ደጀኔ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት በምክር ቤት በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ አለመገኘታቸው ትችት ቀረበበት

ሕዳር 18/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ቋሚ ኮሚቴ የ2015/16 በጀት ዓመት የኢሚግሬሽን ዜግነት አገልግሎት የፓስፖርት አሰጣጥ ውጤታማነትን የክዋኔ ኦዲት እና የ2015 በጀት ዓመት የፋይናንስ ሕጋዊነት ኦዲት ሪፖርት መነሻ በማድረግ ይፋዊ የውይይት መድረክ ተዘጋጅቷል።

የኢሚግሬሽን ዜግነት አገልግሎት ላይ የቀረበውን ሪፖርት ተከትሎም፤ የቋሚ ኮሚቴው ዋና ሰብሳቢ የሺእመቤት ደምሴ (ዶ/ር) በመድረኩ ላይ የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ካሳ መገኘት እንደነበረባቸው ገልጸዋል።

በውይይት መድረኩ ላይ የተገኙ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት የሚያነሱት ሃሳብ እና ጥያቄ ላይ ዋና ዳይሬክተሯ ተገኘተው ምላሽ መስጠት ግዴታ መሆኑ አንስተዋል።

"ሆኖም ግን ዋና ዳይሬክተሯ መደርኩ መዘጋጀቱ ከ10 ቀናት በፊት ደብዳቤው ከደረሳቸው በኃላ፤ ከሀገር መውጣታቸው ተገቢ አይደለም" ሲሉም የቋሚ ኮሚቴው ዋና ሰብሳቢ ተናግረዋል፡፡

አክለውም፤ ምክር ቤቱ በቦታው ላይ ሲያስቀምጣቸው የፌደራል ዋና ኦዲተር ሪፖርት እና ሌሎች ሪፖርቶች ላይ የሚቀርቡ ጥያቄዎችን በቦታው ተገኝቶ የመመለስ ኃላፊነት እንዳለባቸው ጠቁመዋል።

"አገልግሎቱ ለፌደራል ኦዲት ሪፖርት ያለውን ምልከታ ማሳያ ነው" በማለት፤ "እንዳይድገም" ሲሉም አሳስበዋል።

በውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት የኢሚግሬሽን ዜግነት አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ቢቂላ መዝገቡ ዋና ሰብሳቢዋ ላነሱት ሃሳብ "ይቅርታ" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

በፍርቱና ወልደአብ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በመዲናዋ ብቻ የሚሰጠው የዓይን ብሌን ንቅለ ተከላ በክልል ከተሞችም እንዲሰጥ ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ

ሕዳር 16/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ የሚሰጠው የዓይን ብሌን ንቅለ ተከላ በክልል ከተሞችም ለመስጠት ጥረት እየተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ የደም እና ህብረ-ህዋስ ባንክ አገልግሎት አስታውቋል፡፡

የተቋሙ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሀብታሙ ታዬ አገልግሎቱን በሌሎች የኢትዮጵያ ከተሞችም መሰጠቱ የአዲስ አበባውን ጫና ከማቃለሉም በተጨማሪ ለአገልግሎት ፈላጊዎች አማራጭ እንደሚሆን ነግረውናል፡፡

በአይን ጠባሳ ሕመም ምክንያት የአይን ብሌን ንቅለ ተከላ ማከናወን የሚያስፈልጋቸው ዜጎች ቁጥር እየጨመረ የሚገኝበት ሁኔታ ስለመኖሩ ለአሐዱ ገልጸዋል።

በመሆኑም በክልል ከተማዎች ላይ የሕክምና አገልግሎቱን ተደራሽ ለማድረግ፤ በቀጣይ በክልል አንድ የአይን ባንክ ለመክፈት መታቀዱ አስረድተዋል።

ምክትል ዳይሬክተሩ አክለውም፤ በሕብረተሰቡ ዘንድ ስለ ህክምናው ያለው ግንዛቤ ዝቅተኛ መሆን መሻሻል እንደሚገባው አንስተዋል።

እንዲሁም ለሕክምና የሚውል ግብዓት ላይ እጥረት እንዳለ የገለፁ ሲሆን፤ የዘርፉን ባለሞያዎችን ቁጥር መጨመር እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ዜጎች በአይን ብሌን ጠባሳ ምክንያት የአይን ብርሀናቸውን አጥተው፤ የአይን ብሌን ንቅለ ተከላ እየተጠባበቁ እንደሚገኝ በጤና ሚኒስቴር በተደረገ ጥናት አመላክቷል፡፡

የኢትዮጵያ አይን ባንክ በቅርቡ ባወጣው መረጃም፤ ተቋሙ ከተመሰረት 1995 ዓ.ም. ጀምሮ እስካሁን ድረስ ከ3 ሺሕ 500 በላይ ዜጎች በተለያዩ የህክምና ማእከላት የብሌን ንቅለ ተከላ እንደተደረገላቸው የገለጸ ሲሆን፤ ከ15 ሺሕ በላይ ወገኖች ከህልፈት በኋላ ብሌን ለመለገስ ቃል መግባታቸውን አስታውቋል፡፡

በእሌኒ ግዛቸው
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

#UPDATE
በኮሬ ዞን ታስረዉ የነበሩት 66 መምህራን ሁሉም ከእስር መለቀቃቸዉ ተገለጸ


ሕዳር 18/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ሳርማሌ ወረዳ፤ "ደመወዝ ይከፈለን" የሚል ጥያቄ በማንሳታቸው ለእስር ተዳርገው የነበሩ 66 የሚደርሱ መምህራን ሁሉም ከእስር መለቀቃቸውን የኢትዮጵያ የመምህራን ማህበር ለአሐዱ ገልጿል፡፡

መምህራኑ ምንም አይነት የሥራ ማስተጓጎልም ይሁን ሌሎች ሕገ ወጥ ተግባራትን ሳይፈፅሙ፤ መብታቸዉን ብቻ በመጠየቃቸዉ ለእስር ተዳርገው እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል፡፡

የመምህራን ማህበሩ ምክትል ፕሬዝደንት አቶ ሽመልስ አበበ መምህራኑ ከቀናት በፊት ከፊሎቹ ተለቀዉ እንደነበር ገልጸው፤ ትላንት አመሻሽ አካባቢ በደረሳቸዉ መረጃ ደግሞ ሁሉም ከእስር መለቀቃቸዉን ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

"በየትኛውም መልክ ደመወዝ መጠየቅ ለእስር ሊዳርግ አይገባም" ያሉት አቶ ሽመልስ፤ "መምህራንን ማዋከብና በዘርፉ ችግሮች እየተደራረቡ እንዲሄዱ ማድረግ አይገባም" ብለዋል፡፡

"በፀጥታ ሀይሎች ቁጥጥር ሥር የዋሉ መምህራን በሕግ ፊት መቅረብና ውሳኔ ማግኘት ሲገባቸዉ በእስር ቆይተዉ እንዲለቀቁ ሆኗል ነው" ያሉት፡፡

በቁጥጥር ሥር የዋሉት መምህራን በወረዳው ፖሊሶች እንደሆነና ድብደባ የተፈፀመባቸው እንዳሉም ተገልጿል የሕክምና እርዳታ እንዳያገኙ በጸጥታ ሃይሎች ክልከላ እንደተደረገባቸው መገለጹ ይታወቃል፡፡

መምኅራኖቹ መብታቸዉን የጠየቁትና ለእስር ያበቃቸዉም በክልሉ መንግሥት ይሁንታ የ25 በመቶ የደመወዝ ቅነሳው ከትምህርት ቤት ርእሰ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች መደረጉን ተከትሎ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

የመምህራን ማህበሩ ምክትል ፕሬዝደንት አቶ ሽመልስ "ፖሊስ 24 ሰዓት ብቻ በፖሊስ ጣቢያ ማቆየት የሚችል ቢሆንም ከሕግ አግባብ ዉጭ ለ7 ቀናት በፖሊስ ጣቢያ እንዲቆዩ አድርጓቸዋል" ያሉ ሲሆን፤ ትላንት ማክሰኞ ሕዳር 17 ቀን 2017 አመሻሽ አካባቢ ሁሉም ከእስር መለቀቃቸዉን ተናግረዋል፡፡

አክለውም እንደ አፋር ክልል ባሉ አካባቢዎች ለፓርቲ በሚል በተመሳሳይ የመምህራን የደሞዝ ቅነሳ እንደሚደረግና መምህራን ቅሬታ እንደሚያነሱ የገለጹ ሲሆን፤ የመምህራን ማህበሩ የበኩሉን ጥረት በማድረግ የተወሰኑ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ እያደረገ እንደሚገኝ አስታውቀዋል፡፡

የሃይማኖት የተሻ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የትግራይ ይዞታ በሌሎች ሃይሎች ቁጥጥር ሥር ባለበት ሁኔታ ተዋጊዎችን ትጥቅ ማስፈታት በነዋሪዉ ላይ ችግር ያመጣል ሲሉ ፓርቲዎች ገለጹ

ሕዳር 18/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን የቀድሞ ታጣቂዎችን ወደ ማህበረሰቡ የመቀላቀል ሥራ መጀመሩን ተከትሎ የሚቀድሙና ከግንዛቤ መግባት የነበረባቸው ነገሮች ወደ ጎን ተብለዋል ሲሉ አሐዱ ያነጋገራቸው በክልሉ የሚቀሳቀሱ ፖርቲዎች ገልጸዋል።

የሳልሳይ ወያነ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ አሉላ ሃይሉ "የፌደራል መንግሥት እንደ ሁሉም ክልሎች የትግራይ የጸጥታ ሁኔታ የሚመለከተው ነው" ያሉ ሲሆን፤ ለዚህ በክልሉ የሚገኙ ታጣቂዎች ቅጥቅ መፍታት እንዳለባቸው ገልጸዋል።

ነገር ግን "የተፈናቃዮች ወደ ቦታቸው አለመመለስ እንዲሁም ከትግራይ የጸጥታ ሃይሎች ውጪ የሆነ ይዞታዎች መኖራቸው፤ የቀድሞ ተዋጊዎችን ወደ ማህብረሰቡ ለመቀላቀልና ትጥቅ ማስፈታት የተጀመረው ሥራ ላይ እንቅፋት ይሆናል" ሲሉ ስጋታቸውን ተናግረዋል፡፡

"ሙሉ ለሙሉ ትጥቅ መፍታት ብቻ ሰላምን አያመጣም" ያሉት የሳልሳይ ወያነ ሊቀመንበር፤ ፖለቲካዊ ችግሮችን ጎን ለጎን እየፈቱ መሄዱ ዘላቂ መፍትሔ እንደሚኖረው አመላክተዋል።

ሌላው ከአሐዱ ጋር ቆይታ ያደረጉት የባይቶና ዕባይ ትግራይ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ዮሴፍ በርኼ በበኩላቸው የቀድሞ ተዋጊዎችን ወደ ማህበረሰቡ የመቀላለቁ ሥራ ጥሩ ሆኖ ሊቀጥል የሚገባ መሆኑ ገልጸው፤ "ከፕሪቶሪያው ስምምነት ሌሎች ነጥቦች ቸል ተብለዉ የቀደሞ ተዋጊዎችን ወደ ማህበረሰቡ መቀላቀል ላይ ብቻ ትኩረት ተደርጓል" ሲሉ ገልጸዋል።

ከመከላከያ ሃይሎች ውጪ ያሉ ታጣቂዎች ባልወጡበት፣ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው ባልተመለሱበት ሁኔታ መደረጉ ችግር እንደሚፈጥር አብራርተዋል።

አክለውም "የፕሪቶሪያው ስምምነት እነዚህ ሥራዎች ቀድመው እንደሚሰሩ የሚገልጽ ነዉ" ያሉ ሲሆን፤ የጸጥታ እና ደህንነት ስጋት ባለበት ሁኔታ ታጣቂዎችን ትጥቅ አስፈትቶ ማስቀመጥ አግባብ አለመሆኑን አንስተዋል።

"ይህ ተግባር ሕዝቡን ለአደጋ ማጋለጥ ነው የሚሆነው" ያሉት ምክትል ሊቀመንበሩ ዮሴፍ በርኼ፤ አሁን ላይ ትግራይ እየጠበቀ ያለው የትግራይ ሰራዊት መሆኑ ጠቁመዋል።

የቀድሞ ተዋጊዎችን ወደ ማህበረሰቡ የመመለስ ሥራ አስፈላጊ ቢሆንም፤ በቅድሚያ የክልሉን ነዋሪዎች ደህነንት የሚጠበቁበት ሁኔታ ሊመቻች ይገባል ሲሉ ፓርቲዎቹ አጽንዖት ሰጥተዋል።

በፍርቱና ወልደአብ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

#ADVERTISMENT
#AmharaBank
የአማራ ባንክ አ/ማ የባለአክሲዮኖች 3ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ማክሰኞ ታህሳስ 01 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ በሚሊኒየም አዳራሽ ስለሚካሄድ ባለአክሲዮኖች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጉባዔው እንድትገኙ ጥሪ እናስተላልፋለን፡፡

የጉባዔው አጀንዳዎችን እና ተጨማሪ መረጃዎችን ጥቅምት 06 ቀን 2017 ዓ.ም በወጡት አዲስ ዘመን እና ሪፖርተር አማርኛ እትም ጋዜጦች ላይ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ለበለጠ መረጃ ነፃ የጥሪ ማዕከል 690 ወይም
የባንኩን ድረ ገጽ www.amharabank.com.et ይጎብኙ፡፡

አማራ ባንክ
ከባንክ ባሻገር!

የአማራ ባንክ ትክክለኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾች
Website: www.amharabank.com
Facebook: www.Facebook.com/amharabanksc1
Telegram: /channel/Amhara_Banksc
Instagram: https://instagram.com/amhara_bank
Twitter: https://twitter.com/Amharabanksc
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/amharabank/
YouTube: https://youtube.com/channel/UC73x9uuGYV0Uxw0EkpVZN8g
TikTok: amharabanks.c" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@amharabanks.c

#አማራባንክ #AmharaBank

Читать полностью…
Subscribe to a channel