ahaduradio | Unsorted

Telegram-канал ahaduradio - AHADU RADIO FM 94.3

19349

አሐዱ ራድዮ 94.3 Your source for top local and international news and analysis. "Voice of Ethiopian" የአሐዱ የቴሌግራም ቻናል ቤተሰብ በመሆን ወቅታዊና እውነተኛ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ

Subscribe to a channel

AHADU RADIO FM 94.3

ሲቪል ማህበራት የሚያከናውኑትን ሥራ ያህል ተገቢው እውቅና አልተሰጣቸውም ተባለ

ሕዳር 27/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ዓመታዊው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሳምንት ለ4ኛ ጊዜ ዛሬ አርብ ሕዳር 27 ቀን 2017 በአዲስ አበባ ግዮን ሆቴል በይፋ ተከፍቷል።

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሳምንቱ "ለዘላቂ ሰላም እና ፍትሐሃዊ ልማት ቃልኪዳናችንን እናድስ" በሚል መሪ ቃል ነው በመከበር ላይ የሚ።

በፕሮግራሙ መክፈቻ ላይ በኢትዮጵያ የሲቪል ማህበራት ሰፊ ሥራዎችን ቢሰሩም የተሰጣቸው እውቅና ውስን መሆኑ ተነስቷል።

የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ዋና ዳይሬክተር ተረፈ ደግፌ በሲቪል ማህበራቱ ሰላም እንዲሰፍን የዲሞክራሲ ግንባታ ጨምሮ በርካታ ሥራዎች መሠራታቸውን ገልጸዋል።

አክለውም ባለፉት ጊዜያት ከተለያዩ መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት ጋር በጥምረት መሠራቱን አንስተዋል።

ነገር ግን የሲቪል ማህበራት ስለሚሰጡት አገልግሎት በቂ ግንዛቤ ባለመኖሩ "የሚሰጡ አስተያየቶች ዘርፉን የሚያሳንሱ ሆነው አግተናቸዋል" ብለዋል።

ስለሆነም ምክር ቤቱ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ጋር በመሆን በዘርፉ የሚሠሩ ሥራዎችን ለማህበረሰቡ የማስተዋወቅ ሥራዎች ተሰርተዋል ሲሉ ተናግረዋል።

በመድረኩ የክብር እንግዳ ሆነው የተገኙት የትራንስፓስትና ሎጂስቲክ ሚኒስቴር ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የሕዝብን ተጠቃሚነት ማዕከል አድርገው መስራት ይኖርባቸዋል ሲሉ አሳስበዋል።

በዘርፉ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን እንዲሁም በቀጣይ የሚሠሩ ሥራዎች ላይ ውይይት ሊደረግ እንደሚገባም አመላክተዋል።

በዚህ የሲቪል ማህበረሰብ ሳምንት ከ85 በላይ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የተሳተፉበት አውደ ርዕይ እና የፓናል ውይይት መኖሩ ተመላክቷል።

በርካታ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ይሳተፉበታል የተባለው ዓመታዊ ዝግጅት ከዛሬ ሕዳር 27 እስከ እሁድ ሕዳር 29 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ ነው።

በፍርቱና ወልደአብ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

"በየኬላው የሚጠየቀው የኮቴ ክፍያ ከፌደራል መንግሥት እውቅና ውጪ ነው" የትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ሚኒስቴር

ሕዳር 27/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በሀገሪቱ የተለያዩ መስመሮች ከጅቡቲ ወደብ ምርቶችን ጭነው ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች እና ባለንብረቶች የሚጠየቁት የኮቴ ክፍያ እንዳማረራቸው ሲገልጹ ይደመጣል።

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር)፤ ይህ በየኬላው የሚጠየቀው ገንዘብ ከሚመሩት መስሪያ ቤትና ከመንግሥት እውቅና ውጪ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

"ይህ ተግባር የትራንስፖርት ዘርፉን ዋጋ የሚያንር ተገቢ ያልሆነ አሰራር ነው" ሲሉም ተችተዋል።

አሐዱ በተለያየ ጊዜ ያነጋገራቸው የአሽከርካሪ ባለንብረቶች እና ሹፌሮች፤ ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኙ ኬላዎች ጭምር የሚጠየቁትን የኮቴ ክፍያ እና የሚደርስባቸውን ጥቃት ሲገልጹ ቆይተዋል።

ሚንስትሩ የክልል መንግሥታትም ጭምር የኮቴ ክፍያን በተመለከተ የሚያውቁት ነገር አለመኖሩን ገልጸው፤ "የከተማ መስተዳደሮች ገቢያቸውን ለማሳደግ በሚል የሚያደርጉት ነው" ሲሉ ለአሐዱ ተናግረዋል።

ይህንን ችግር ለመፍታት የክልል መንግሥታት አቅጣጫ ማስቀመጣቸውን በመግለጽም፤ "እርምጃ የሚወሰድበት አሠራር ተዘርግቷል" ብለዋል።

አክለውም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የክትትልና ቁጥጥር ሥራዎችን እንደሚሠራ የገለጽ ሲሆን፤ የተቀመጠው መመሪያ ተግባራዊ የማይሆን ከሆነ ሌሎች ተጨማሪ ሥራዎች እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

ሚኒስትሩ ይህንን ቢሉም የትራንስፖርት ማህበራቱና አሽከርካሪዎች ግን፤ ክፍያውን የሚጠይቁት ከመንግሥት አካል የተደራጁ ስለመሆናቸውና ሕጋዊ ክፍያ ክፈሉ እየተባሉ ስለመሆኑ ገልጸዋል፡፡

በፍርቱና ወልደአብ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

150 ሺሕ የሚጠጉ ስደተኞች ወደ ሀገር ውስጥ መግባታቸው ተገለጸ

ሕዳር 27/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ከ2016 ዓ.ም ጥቅምት ወር ጀምሮ እስከ 2017 ዓ.ም ደረስ 148 ሺሕ የሚደርሱ ስደተኞች ከተለያዩ የአለም ሀገራት ወደ ሀገር ውስጥ መግባታቸውን የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

"ሰዎች በሕግ ወጥ መንገድ ከሀገር ይወጣሉ፤ ከወጡም በኃላ በቂ የሆነ የሥራ ዘርፍ ሳያገኙ ሲቀሩ ደግሞ ወደ ሀገር ውስጥ ስለሚገቡ ተግዳሮት ፈጥሯል" ሲሉ፤ በሚኒስቴሩ የሕገ ወጥ ሰዎች ዝውውር መከላከል እና ቁጥጥር መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ደረጄ ተጊብሩ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

አሐዱ "ኢትዮጵያ አሁን ካለችብት ሁኔታ አንጻር ስደተኞችን ለማቋቋም አስቻይ ሁኔታ አለ ወይ?" ሲል ኃላፊውን ጠይቆል፡፡

የተቋሙ መሪ ሥራ አስፈጻሚ በሰጡት ምላሽ፤ እንደ ሀገር በቂ የሆነ በጀት አለ ብሎ መናገር እንደማይቻል ገልጸው፤ "ነገር ግን ከተለያዩ አለም ዓቀፍ እና ሀገር በቀል ድርጅቶች በሚደረጉ ድጋፎች መልሶ የማቋቋም ሥራው እየተሰራ ነው" ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም ወደ ሀገር የሚገቡ ስደተኞችን መልሶ ማቋቋሙን ውጤታማ ለማድረግ ለስደተኞች በቂ የሆነ ስልጠና በመስጠት የተሻለ አቅም ያሳዩት ተለይተው ድጋፍ መደረጉን አቶ ደረጄ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

ከ2014 ዓ.ም እስከ 2015 ዓ.ም ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ ስደተኞች ከ130 ሺሕ የሚደርሱ እንደነበር ያስታወሱት አቶ ደረጄ፤ በአሁኑ ወቅት ግን ወደ ሀገር የሚገቡ ስደተኞች ቁጥር መጨመሩን ተናግረዋል፡፡

ይህን ችግር ለመቅረፍ ደግሞ መንግሥት ከተለያዩ የአለም ሀገራት ጋር በሚደርጋቸው የሥራ ስምምነቶች መሰረት ሕጋዊ በሆነ መንገድ መሄድ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

በደረጄ መንግስቱ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የመኖሪያ አካባቢያችን ለባንክ ስለተሸጠ የጋራ መኖሪያ ቤት እንደምናገኝ ቢገለጽልንም ስቱዲዮ እንድንገባ እየተገደድን ነው ሲሉ ነዋሪዎች ቅሬታ አቀረቡ

ሕዳር 27/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በአዲስ አበባ ከተማ ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 አረቄ ፋብሪካ አካባቢ ነዋሪዎች፤ የመኖሪያ አካባቢያችን ለባንክ ስለተሸጠ የጋራ መኖሪያ ቤት እንደምናገኝ ካስፈረሙን በኋላ ያለፍላጎታችን ስቱዲዮ እንድንገባ እየተገደድን ነው ሲሉ ቅሬታቸውን ለአሐዱ አቅርበዋል።

በአካባቢው በሚገኝ የመኖሪያ መንደር የሚኖሩት 50 አባወራዎች፤ "አካባቢው ለባንክ ስለተሸጠ የቤተሰባችንን ቁጥር ያገናዘበ የጋራ መኖሪያ ቤት እንደሚሰጠን ተነግሮን ፎርም ሞልተን ነበር" ይላሉ።

ለአሐዱ ቅሬታቸውን ያሰሙት ነዋሪዎቹ የቤተሰባቸውን ቁጥር ባገናዘበ መልኩ ባለ 2 እና ባለ 3 መኝታ የጋራ መኖሪያ ቤት እደሚሰጣቸው ተስፋ በማድረግ ስምምነት ቢፈርሙም፤ ሕዳር 21 ቀን 2017 ዓ.ም. ያለው ቤት ባለ አንድ ክፍል ወይም ስቱዲዮ ብቻ መሆኑ እንደተነገራቸው እና በግዴታም ቢሆን ትገባላችሁ መባላቸውን ተናግረዋል።

የመኖሪያ አካባቢያቸው ለባንክ በመሸጡ ምክንያት ከአካባቢው እንደሚነሱ የተነገራቸው 50 አባወራዎች በእያንዳንዳቸው ሥር እስከ 10 የሚደርሱ የቤተሰብ አባላት እንዳላቸው ገልጸዋል።

አሁን ውሰዱ የተባሉት የመኖሪያ ቤት ካላቸው የቤተሰብ ብዛት አንጻር አነስተኛ መሆኑን በማንሳት ለወረዳ 09 ጽ/ቤት በተደጋጋሚ ቅሬታ ቢያቀርቡም፤ "ያለው ቤት ስቱዲዮ ብቻ ነው በግድም በውድም ትገባላችሁ" ተብለናል ብለዋል፡፡

በሦስት ቀናት ውስጥ መወሰን ካልቻሉም ቤታቸው በግብረ-ኃይል እንደሚፈርስ ተነግሯቸዋል፡፡

ይህንን ችግራቸውንም ሕዳር 23 ቀን 2017 ዓ.ም. ከንቲባ ጽ/ቤት በአካል በመወቅረብ እንዳስረዱ ተናግረዋል።

አሐዱም የነዋሪዎችን ቅሬታ በመያዝ የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 ሥራ አስፈጻሚ ታደሰ ዓለማየሁን አነጋግሯል፡፡

አቶ ታደሰ በምላሻቸው፤ "ከዚህ በፊት ባደረግነው ውል መሰረት በሚፈልጉት የጋራ መኖሪያ ቤት ልክ ተደራሽ ለማድረግ አልቻልንም፡፡ ለዚህም ምክንያቱ የቤት እጥረት በመኖሩ ነው" ሲሉ ነግረውናል፡፡

"የቤት እጥረት ስላለ ለሁሉም ፈላጊ ቤት ማድረስ አይቻልም፡፡" ያሉት ሥራ አስፈጻሚው፤ "እንደ አማራጭ ብዙ የቤተሰብ አባል ያላቸውን በመምረጥ የቀበሌ ቤት እንዲገቡ ካልሆነ እንደ ፍላጎታቸው ስቱዲዮ ቤት እንዲገቡ ውይይት የተደረገ ነው" ብለዋል።

ይሁን እንጂ አስገዳጅ ሁኔታ እንደሌለ አንስተዋል። ቦታው ለልማት ስለሚፈለግ የእቃ ማጓጓዣ የሚሆን ወጪን በመሸፈን ከቦታው ተነሽ ለሆኑ ሰዎች እንደየፍላጎታቸው ለማድረግ እንደተዘጋጀና ቤቶች ኤጀንሲ በመሄድ ዕጣቸውን ማውጣት እንደሚችሉም ሥራ አስፈጻሚው አስረድተዋል።

በአለምነው ሹሙ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

መልካም ቀን!
አሐዱ ሬድዮ 94.3  የኢትዮጵያውያን ድምፅ!

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የጸደቀው የሕንፃ አዋጅ የስነ ሕንጻ -ንድፍ ሙያተኞች ላይ ስጋት እንደሚፈጥር ተገለጸ

ሕዳር 26/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) አዲሱ የሕንፃ አዋጅ የስነ ሕንጻ -ንድፍ ባለሙያ (አርክቴክቶች)ን ሙያ የሚያሳጡ ነጥቦች የተካተቱበት ነው ሲል የኢትዮጵያ አርክቴክቶች ማህበር ቅሬታውን ለአሐዱ ገልጿል።

በዛሬው ዕለት በተከናወነው 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በ4ኛ ዓመት የሥራ ዘመኑ 9ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ የሪል ስቴት ልማትና የማይንቀሳቀስ ንብረት ግብይትና ግመታ አዋጅን ጨምሮ ሦስት አዋጆችን መርምሮ አጽድቋል።

"ይሁንና በፀደቀው አዋጅ ላይ ቅሬታችንን ብናቀርብም ተቀባይነት ተነፍጎንናል" ያለው የስነ ሕንፃ ንድፍ ባለሙያዎች ማሕበሩ፤ ቀድሞውኑ በረቂቅ አዋጁ ላይ ቅሬታው እንደነበረው አስታውቋል።

የስነ ሕንጻ - ንድፍ ባለሙያዎች ማህበር፤ "በቀድሞው የሕንፃ አዋጅ ላይ ተጠብቀው የኖሩና የሕንፃ ንድፈ ሐሳብ አፍላቂዎችን የሕንፃ ሥራ ባለሙያዎችን የማያካትቱ አሰራሮችን በአዲሱ አዋጅ ላይ ተካተዋል" ሲል ገልጿል ፡፡

በሕንጻ ሥራ ላይ ተጠያቂነት የሚሰፍንበትን አካሄድ ያላከበረ ከመሆኑ በተጨማሪም፤ በአለም ዓቀፍ ካለው ልምድ አንፃር የሚጣረስ መሆኑም ገልጿል፡፡

በሂደት ላይ በነበረው የሕንጻ ሥራ አዋጅ ላይ የተሰተዋሉትን ቅሬታዎች ለምክር ቤቱ ቢያቀርቡም ተቀባይነት አለማግኘታቸውን ለአሐዱ የገለጹት የማህበሩ ፕሬዝዳንት ሐብታሙ ጌታቸው ናቸው።

ልክ እንደ ሕክምና ባለሙያዎች ሙያ የሚዳኝበት ገለልተኛ ተቋም ሊቋቋም ይገባል እንጂ፤ በዘፈቀደ የሚታይበት አካሄድ የግንባታ ዘርፍን የሚጎዳው መሆኑን ገልጸዋል።

ሌላኛው በአዋጁ ላይ ከተነሱት ቅሬታዎች መካከል ሕንጻ በሚገነባበት ወቅት በሌሎች ባለሙያዎች በሚፈጥሩት ስህተት የስነ ሕንጻ ንድፋ ወይንም የአርክቴክቸር ባለሙያዎችን ተጠያቂ የሚያደርግበትን አካሄድ አንዱ እንደሆነም ማሕበሩ ስሞታውን ለአሐዱ አሰምቷል።

የማሕበሩ ፕሬዝዳንት አክለውም፤ የሙያ ደህንነትን ጉዳይ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መውደቁን የገለጹ ሲሆን፤ "በተጨማሪም አዋጁ በግንባታ ዘርፍ ላይ ለሚደርሱ ጥፋቶች ተጠያቂነትን የማያሰፍን ነው" ሲሉ ተችተዋል።

አዋጁ ባለፈው ወር ለሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ለውይይት ቀርቦ የነበረ ቢሆንም፤ በርካታ አለመግባባቶች የተስተዋሉበት እንደነበር አሐዱ መዘገቡ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ግንባታ ተቋራጮች ማሕበርን ጨምሮ የኢትዮጵያ አርክቴክቶች ማህበር በአዋጁ ላይ ከፍተኛ ትችት ከሰነዘሩ መካከል ይገኙበታል

ነገር ግን እነዚህ ቅሬታዎች እና ትችቶች ምላሽ ሳያገኙ ምክር ቤቱ አዋጁ ተፈፃሚ እንዲሆን አፅድቆ ወደ የሚመለከተው አካል መምራቱ ነው የተገለጸው።

በአማኑኤል ክንደያ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

#አሐዱ_ትንታኔ

በደቡብ ኮሪያ ሕዝባዊ አመጽ መቀስቀሱ ተሰምቷል፡፡

የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ዮን ሱክ የወታደራዊ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ (ማርሻል ሕግ) ማውጣታቸውን ተከትሎ፤ በመላው ሀገሪቱ አመጹ ተባብሶ ቀጥሏል፡፡

ጉዳዩን ጉረቤት ሀገር ሰሜን ኮሪያን ጨምሮ አንዳንድ ሀገራት በቅርበት እየተከታተሉት መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ይህንን እና ተያያዥ ጉዳዮችን በዛሬው አለም ዓቀፍ ትንታኔያችን መርጠን ተመልክተነዋል፡፡

ትንታኔውን ለመከታተል ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👇
https://youtu.be/2cyXZ659YA0?si=16A-JQ3wtwme9Q1V

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የሪል ስቴት ልማትና የማይንቀሳቀስ ንብረት ግብይትና ግመታ አዋጅን ጨምሮ ሦስት አዋጆች ጸደቁ

ሕዳር 26/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በ4ኛ ዓመት የሥራ ዘመኑ ባካሄደው 9ኛ መደበኛ ስብሰባ፤ የሪል ስቴት ልማትና የማይንቀሳቀስ ንብረት ግብይትና ግመታ አዋጅን ጨምሮ ሦስት አዋጆችን መርምሮ አጽድቋል።

የኢትዮጵያ ሕንፃዎች አዋጅ በነባሩ ሕግ በአፈፃፀም የተለዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን የሚፈታ፣ የአካል ጉዳተኞችን ተደራሽነት የሚያረጋግጥ፣ የግንባታ ጥራትና የሀብት ብክነት ችግሮች የሚቀርፍ፣ ግልፅና ለአተገባበር ምቹ የሆነ የአሰራር ስርዓት መዘርጋት የሚያስችል መሆኑ በቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ተገልጿል፡፡

ምክር ቤቱም በቀረበው ረቂቅ ላይ በስፋት ከተወያየ በኋላ የኢትዮጵያ ሕንፃዎች አዋጅን በሙሉ ድምጽ አፅድቆታል፡፡

በተመሳሳይም የሪል ስቴት ልማት እና የማይንቀሳቀስ ንብረት ግብይትና ግመታ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ ሪፖርትና የውሳኔ በዝርዝር ቀርቧል፡፡

የሪል ስቴት ልማቱ አቅርቦት እጅግ ወደኋላ የቀረና የሕዝቡን ፍላጎት የማያሟላ በመሆኑ የማይንቀሳቀስ ንብረት ግመታ ስርዓቱ ዘመናዊና በመረጃ የተደገፈ ተገማች ዋጋ እንዲኖረው ማድረግ በማስፈለጉ እና በማይንቀሳቀስ ንብረት ገበያው ግልጽነት መጓደሉ የኢኮኖሚ መዛባት እያስከተለና የመንግስትን ጥቅም የሚያሳጣ እንዳይሆን ለማድረግ የሚያስችል አዋጅ መሆኑን ተገልጿል፡፡

ምክር ቤቱም በቀረበው ረቂቅ ላይ በስፋት ከተወያየ በኋላ አዋጁን በሁለት ተቃውሞና በአንድ ድምፀ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምጽ አጽድቆታል።

በመቀጠልም ምክር ቤቱ የኤሌክትሮኒክስ ፊርማ አዋጅን ለማፅደቅ የቀረበው ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ ማዳመጡን አዳምጧል፡፡

ምክር ቤቱ ረቂቁን ከመረመረ በኋላ አስፈላጊነቱን በሙሉ ድምፅ የተቀበለው በመሆኑ በቀረበው ረቂቅ ላይ በስፋት ከተወያየ በኋላ የኤሌክትሮኒክስ ፊርማ አዋጅን በሙሉ ድምጽ ማጽደቁን አሐዱ ከምክር ቤቱ ያገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

👉የሪል ስቴት ልማት እና የማይንቀሳቀስ ንብረት ግብይትና ግመታ ረቂቅ አዋጅ ማብራሪያው ከላይ ተያይዟል፡፡

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ 97 ነጥብ 6 በመቶ መጠናቀቁ ተገለጸ

👉 በ12 ዓመታት ውስጥ ለግንባታው ከ20 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ ተሰብስቧል


ሕዳር 26/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ 97 ነጥብ 6 በመቶ መጠናቀቁን የፕሮጀክቱ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።

የኮርቻ ግድቡ በ2010 ዓ.ም ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ በአራት ተከታታይ ዙር ዓመታዊ ውኃ መያዝ መጀመሩን የገለጸው ጽ/ቤቱ፤ ሁለቱን ግድቦች የሚያገናኘው የድልድይ ሥራ ሙሉ በሙሉ እየተጠናቀቀ እንደሚገኝም ተናግሯል፡፡

በተጨማሪም የግድቡ የማስተንፈሻ በሮች ሙሉ በሙሉ መጠናቀቃቸው የተገለጸ ሲሆን፤ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራዎች 87 በመቶ መድረሱን አመላክቷል፡፡

1 ሺሕ 800 ሜትር የሚረዝመው እና ከባህር ጠለል በላይ 645 ሜትር ከፍታ ያለው የዋናው ግድብ የሲቪል ሥራዎች አፈፃፀም 99 ነጥብ 6 በመቶ በላይ የተጠናቀቀ መሆኑንም ጽ/ቤቱ ለአሐዱ በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በበጀት ዓመቱ አራት ወራት ለግድቡ ግንባታ ከ311 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን ገልጿል፡፡

እንዲሁም ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ባሉ ዓመታት፤ ለግድቡ ግንባታ ከ20 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን ጽ/ቤቱ ገልጿል።

እስካሁን ኃይል እያመነጩ ካሉት የግድቡ አራት ተርባይኖች ሁለቱ ተርባይኖች እያንዳንዳቸው በሙሉ አቅማቸው 375 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም እንዳላቸው የተገለጸም ሲሆን፤ ቀሪዎቹ ሁለቱ ደግሞ 400 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም አላቸው፡፡

የቀሪዎቹ 9 ዩኒቶች ተከላና የቅድመ ኃይል ማመንጨት ሙከራ ተጠናቆ በሙሉ አቅማቸው ኃይል ማምረት ሲጀምሩ ደግሞ፤ አሁን ያለውን የአገራችንን የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም በ83 በመቶ እንደሚያሳድገው ተነግሯል፡፡

ታላቁ የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ ደግሞ 5 ሺሕ 150 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያመነጭ ሲሆን፤ ዓመታዊ የኃይል ምርቱ ደግሞ 15 ሺሕ 760 ጊጋ ዋት በሰዓት እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

"ለቋሚ ኮሚቴ የተመራው የትምህርት ረቂቅ አዋጅ መሰረታዊ ችግሮች ያሉበት ነው" የኢትዮጵያ የግል ትምህርት ቤቶች ማህበር

👉ቋሚ ኮሚቴው አጠቃላይ የትምህርት አዋጅ ላይ የሕዝብ ውይይት አድርጓል

ሕዳር 26/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለዝርዝር እይታ ወደ ቋሚ ኮሚቴ የመራው የትምህርት ረቂቅ አዋጅ፤ መሰረታዊ ችግሮች ያሉበት በመሆኑ በረቂቁ በቀረበው ሃሳብ ላይ አንስማማም ሲል የኢትዮጵያ የግል ትምህርት ቤቶች ማህበር አስታውቋል፡፡

ማህበሩ የትምህርት ረቂቅ አዋጁን አስመልክቶ በትናንትናው ዕለት ውይይት ማድረጉን በመግለጽ፤ በዚህም ረቂቁ መሰረታዊ ችግሮች ያሉበት መሆኑ መገምገሙን የማህበሩ ፕሬዝደንት አቶ አበራ ጣሰው ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

የረቂቅ አዋጁ አጠቃላይ የትምህርት ረቂቅ አዋጅ በሚል የቀረበ ሲሆን፤ ረቂቁ ከያዛቸው ጉዳዮች አንዱ "የግል ትምህርት ቤቶች ሥራ ሲጀምሩም ሆነ ሥራ የጀመሩት ለ6 ወር ለመምህራን የሚከፍሉት ደሞዝ በዝግ አካውንት ሊኖራቸው ይገባል" የሚል ሃሳብ እንዳለው ፕሬዝደንቱ በአብነት ጠቅሰዋል፡፡

"ረቂቅ አዋጁ ይህንና መሰል ጉዳዮችን የያዘ በመሆኑ ከመፅደቁ በፊት ማሻሻያዎች ሊደረጉበት ይገባል ነበር" ሲሉም አክለዋል፡፡

"በረቂቁ የተካተቱ አንዳንድ ነጥቦች የግል ትምህርት ቤቶችን ዘርፍ የሚጎዱ እና የንግድ ሕጉንም የሚጥሱ ሆነው አግኝተናቸዋል" ሲሉም ገልጸዋል፡፡

የማህበሩ ፕሬዝደንት "የግል ትምህርት ቤቶች የመንግሥትን ጫና የሚቀንሱ መሆናቸውም መዘንጋት የለበትም" ሲሉም አሳስበዋል፡፡

በተያያዘ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብት ልማት፣ ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አጠቃላይ የትምህርት አዋጅ ላይ ይፋዊ የሕዝብ ውይይት አካሂዷል።

በውይይቱ የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ነገሬ ሌንጮ (ዶ/ር) ትምህርት የነገ ተስፋ የሆኑ ሕጻናትና ወጣቶችን የሚያዘጋጅ በመሆኑ፤ ትኩረት የሚፈልግ ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል።

አዋጁ የትምህርትን ጥራት የሚያስጠብቅ፣ የመምህራንን ብቃትና ጥቅም የሚያስከብር እንዲሁም ማስተማር የሚመረጥ ሙያ ሊያደርግ የሚችል እንደሚሆን አስረድተዋል።

በመድረኩ ላይ ማብራሪያ የሰጡት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በኩላቸው፤ የትምህርት ስርዓቱን ለማሻሻል የተለያዩ እርምጃዎች እየተወሰዱ መሆኑን ገልጸዋል።

ከዚህ በፊት የትምህርት ፖሊሲና ፍኖተ ካርታ መዘጋጀቱን ያስታወሱት ሚኒስትሩ፤ አሁን ላይ ደግሞ የማስፈፀሚያ ረቂቅ አዋጅ አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል።

በመሆኑም የተዘጋጀው አዋጅ አሁን ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ የሚያሳይና በቀጣይ ሊደረስበት የሚገባውን ራዕይ የሚያመላክት መሆኑን ተናግረዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎችም አዋጁ የመምህራንን ጥቅም የሚያስከብር መሆን እንዳለበት፣ የትምህርት ተደራሽነት ብቻ ሳይሆን ጥራት የሚያስጠብቅ እንዲሆን፣ አካል ጉዳተኞችን በሚመለከት አካታችና ፍትሃዊ መሆን እንዳለበትና ለምልክት ቋንቋ ትኩረት መስጠት እንደሚገባ አስተያየት ሰጥተዋል።

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አየለች እሸቴ፤ በተሳታፊዎች የተነሱ ጠቃሚ ሃሳቦችን በመውሰድ በረቂቅ አዋጁ የሚካተቱ መሆኑን ገልጸዋል።

ጥቅምት 19 ቀን 2017 በተካሄደው የሕዝብ ተወካዮች ምክር-ቤት ጉባኤ የአጠቃላይ ትምህርት ረቂቅ አዋጅን ምክር ቤቱ በአንድ ተቃውሞ በአብላጫ ድምጽ በማጽደቅ፤ ለዝርዝር ዕይታ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መምራቱን አሐዱ መዘገቡ ይታወሳል፡፡

በእመቤት ሲሳይ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በትግራይ ክልል ባለፋት ሦስት ወራት ውስጥ ከ40 ሺሕ በላይ በሚሆኑ የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ መውሰዱ ተገለጸ

ሕዳር 26/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በትግራይ ክልል ሕገ ወጥ ነጋዴዎች ላይ በ3 ወራት ውስጥ ቤት ለቤት በተደረገ ድንገተኛ ክትትልና ፍተሻ፤ 40 ሺሕ 341 በሚሆኑ የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ መውሰዱን የክልሉ ንግድ ቢሮ አስታውቋል።

በቢሮው የንግድና የውጭ ኤጀንሲ ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ ጉኡሽ ወልዴ ለአሐዱ እንደተናገሩት፤ እርምጃ ከተወሰደባቸው ውሰጥ 13 ሺሕ የሚሆኑ ነጋዴዎች ያለ ንግድ ፈቃድ በመስራትና ያልታደሰ የንግድ ፈቃድ በመያዝ የተገኙ ናቸው።

ዳይሬክተሩ አክለውም፤ እንደየጥፋቱ አይነት ታይቶ 3 ሺሕ 300 የሚሆኑ ተቋማት መታሸጋቸውን ገልጸዋል፡፡

የአገልግሎት ዘመን ያለፈባቸው ሸቀጦችን ወደ ገበያ በማቅረብ ሲሸጡ የተገኙ 1 ሺሕ 900 በሚሆኑ ንግድ ተቋማት ደግሞ፤ እንዲታሸጉ የማድረግ እርምጃ መወሰዱን ጠቁመዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም፤ መመሪያ የጣሱ ሌሎች 28 ተቋማት ከንግድ ፈቃድ እንዲታገዱ መደረጉንና ጉዳያቸው ወደ ሕግ የተወሰደ ነጋዴዎችም እንዳሉም አቶ ጉኡሽ ተናግረዋል፡፡

እርምጃ ከተወሰደባቸው ተቋማት ውሰጥ 9 ሺሕ 600 የሚሆኑት የጹሑፍ ማስጠንቀቂያ ሲሰጣቸው፤ 27 ሺሕ የሚሆኑት ደግሞ ስህተታቸውን በማመንና ከዚህ በኋላ ተመሳሳይ ስህተት እንደማይፈጽሙ ቃል በመግባታቸው ተለቀው ወደ ሥራ እንዲገቡ መደረጉን አስታውቀዋል፡፡

በትግራይ ክልል ሕገ ወጥ ንግድን ለመከላከል እየተወሰደ ያለው እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የጠቆሙት ዳይሬክተሩ፤ ሸቀጣ ሸቀጦችን ለማህበረሰቡ ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝም አጽንኦት ሰጥተዋል።

በአለምነው ሹም
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

መልካም ቀን!
አሐዱ ሬድዮ 94.3  የኢትዮጵያውያን ድምፅ!

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

ጆ ባይደን አሜሪካ ለተፈናቀሉ አፍሪካውያን ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደምትለግስ አስታወቁ

ሕዳር 25/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ተሰናባቹ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አሜሪካ ለተፈናቀሉ አፍሪካውያን ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ድጋፍ እንደምታደርግ አስታውቀዋል።

ስልጣናቸዉን ከመልቀቃቸው በፊት አፍሪካን ለመጎብኘት በገቡት ቃል መሰረት ጉብኝታቸውን በአንጎላ የጀመሩት ጆ ባይደን፤ በሀገሪቱ ዋና ከተማ ሉዋንዳ ባደረጉት ንግግር ወቅት ለአፍሪካ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብተዋል።

"የአፍሪካ መሪዎች እና ዜጎች ከእርዳታ ባሻገር የሚያሰፈልጋቹ ነገር እንዳለ እናውቃለን። ኢንቨስትመንት ያስፈልጋቹሃል ስለዚህም አሜሪካ በመላው አፍሪካ የምትሰራቸውን ሥራዎች እያሰፋች ነው" ሲሉም ገልጸዋል፡፡

በዚህም መሠረት በድርቅ ለተፈናቀሉ አፍሪካውያን ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ የሰብአዊ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል፡፡

ድጋፉ በ31 የአፍሪካ ሀገራት በድርቅ እና በግጭት ለተፈናቀሉ ዜጎች የሰብአዊ እርዳታ እንደሚውል ተናግረዋል።

ባይደን አክለውም፤ በስልጣን ዘመናቸው የአሜሪካና አፍሪካን ሁለንተናዊ ግንኙነት ለማጠናከር ሥራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን ተናግረዋል፡፡

የጋራ ትብብር እንደሚያስፈልግ በመጥቀስም፤ "ጥያቄው አሜሪካ ለአፍሪካ ምን ማድረግ እንደምትችል ሳይሆን፣ ከአፍሪካ ሕዝቦች ጋር ምን እናድርግ የሚል መሆን አለበት" ማለታቸውን የፎክስ ኒውስ ዘገባ አመላክቷል።

የአሜሪካ መንግሥት የልማት ተራድኦ ድርጅት (ዩ.ኤስ.ኤ.አይ.ዲ) ባወጣው መግለጫ፤ “በጦርነት፣ በአስከፊ የአየር ሁኔታ ክስተቶች፣ በተፈጥሮ አደጋዎች እንዲሁም በሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች ምክንያት በአህጉሪቱ ያለው ሰብዓዊ ፍላጎት እየጨመረ መምጣቱን ገልጿል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በበኩሉ፤ በ2023 ከአምስት አፍሪካውያን አንዱ ወይንም 300 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ለረሃብ የተጋለጡ መሆናቸውን የገለጸ ሲሆን፥ በአህጉሪቱ ለከፋ የምግብ ዋስትና እጦት እንዲሁም ለተመጣጠነ ምግብ እጦት የተጋለጡ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን አስታውቋል።

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

#አሐዱ_ስንክሳር

"የሕዝብ ቁጥሯን መጠቀም ያቃታት ኢትዮጵያ" (በጥበቡ በለጠ)

ሙሉ ጥንቅሩን ለመከታተል ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👇
https://youtu.be/dVVDCUkNJus?si=ZL1e9ui2zgE0ylVk

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

እስከ 700 ሺሕ ብር የሚደርስ መቀጮና 7 ዓመት እስራት የተካተተበት ሕግ ሲፀድቅ፤ ሕገ-ወጥ የነዳጅ ግብይትን ለመግታት ያስችላል ተባለ

ሕዳር 25/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ሕገወጥ የነዳጅ ግብይትን ይገታል የተባለለት ከ 300 ሺሕ እስከ 700 ሺሕ ብር የገንዘብ መቀጮ ያለው ሕግ ወጥቶ፤ ባለፈው ሳምንት ጀምሮ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቅረቡን የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን አስታውቋል።

አሐዱ ያነጋገራቸው የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰሀረላ አብዱላሂ፤ ሁሉም ባለድርሻ አካል ተወያይቶበት ከከፍተኛ የገንዘብ መቀጮ እስከ ፈቃድን መሰረዝ የሚችል ሕግ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

በቅርቡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያፀድቀዋል ተብሎ ከሚጠበቀው ሕግ መካከል፤ ዲጂታል ግብይቱን ሲያጭበረብር የተገኘ እስከ 300 ሺሕ ብር፣ የነዳጅ በርሜልን በሕገ ወጥ መንገድ በተለይም ማደያ በሌለባቸው አካባቢዎች ሲቸረችር የተገኘ እስከ 350 ሺሕ፣ ማደያ ላይ ወይም ቦቴ ላይ ካሊብሬሽን ሲያጭበረብር የተገኘ እስከ 500 ሺሕ የሚሉት የሚገኙበት ሲሆን፤ በአጠቃላይ እስከ 700 ሺሕ ብር የሚያስቀጣ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሯ ገልጸዋል።

ቅጣቱ የገንዘብ ብቻም ሳይሆን እስከ 7 ዓመት የሚደርስ ፅኑ እስራት የተካተተበት መሆኑንም አክለዋል።
ሕገወጥ የነዳጅ ግብይቱን በተመለከተ ነዳጅ ይዞ ያለአቅጣጫ ሲጓዝ ሲገኝ፣ ከማደያ በበርሜል ጭኖ ሲወጣ እንዲሁም ከዲጂታል ውጪ የገንዘብ ግብይት ሲፈፅም ቢገኝ እርምጃ እንደሚወሰድበት አስረድተዋል፡፡

እስካሁን የነበረው አካሄድ አስተዳደራዊ ብቻ በመሆኑ ባለስልጣኑ ሙሉ በሙሉ እርምጃ ለመውሰድ የተወሰኑ የሕግ ማዕቀፍ ክፍተቶች እንደነበሩበትም ጨምረው አንስተዋል።

አሁን ላይ የነዳጅ እጥረቱ እንዲባባስ ያደረገው ዋነኛው ምክንያት ሕገወጥ ንግዱ በመሆኑ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በተለይም ከክልል ንግድ ቢሮዎች ጋር በጋራ እየሰራ እንደሚገኝ ጠቅሰው፤ የተለያዩ አስተዳደራዊ እርምጃዎች እየተወሰዱ መሆኑንና በቅርቡም ለ 229 ማደያዎች የመጨረሻ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ መስጠቱን ዋና ዳይሬክተሯ ለአሐዱ ተናግረዋል።

በስፍራሽ ደመላሽ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

#አሐዱ_ትንታኔ

ከባይደን የአንጎላ ጉዞ ጀርባ ምን አለ?

ትንታኔውን ለመከታተል ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👇
https://youtu.be/OYFXoAcfHvk?si=ed4wLtZH0w6regL-

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በኦሮሚያ ክልል ሕፃናትና የአእምሮ ሕሙማንን ጨምሮ በርካታ ሰዎች በግዳጅ የመከላከያ ሠራዊት አባል እንዲሆኑ እየተመለመሉ መሆኑን ኢሰመኮ ገለጸ

ሕዳር 27/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የክልሉ የአስተዳደር እና የጸጥታ አካላት "የመከላከያ ሰራዊት አባል ለመሆን የሚፈልጉ ዜጎችን ምልመላ እናከናውናለን" በሚል፤ የሰራዊቱን አሠራር እና መስፈርቶች በጣሰ ሁኔታ ሕፃናትና የአእምሮ ሕሙማንን ጨምሮ በርካታ ሰዎችን በግዳጅ መያዛቸውን አረጋግጫለሁ ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በዛሬው ዕለት ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል፡፡

ኮሚሽኑ የተያዙትን ለመልቀቅ ቤተሰቦቻቸው ገንዘብ እንዲከፍሉ ስለማስገደዳቸው የደረሱትን መረጃዎች ተከትሎ፤ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ከሕዳር 4 እስከ 20 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ ክትትል እና ምርመራ ማከናወኑን ገልጿል።

ኢሰመኮ በዚህ ክትትል እና ምርመራ በኦሮሚያ ክልል፣ በአዳማ፣ በቢሾፍቱ፣ በጅማ እና በሻሸመኔ ከተሞች የሚገኙ እጩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ማቆያ ስፍራዎችን በመጎብኘት፤ በማቆያ ስፍራዎቹ ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን እና ቤተሰቦቻቸውን ማነጋገሩን ገልጿል፡፡

እንዲሁም የሚሊሻ እና የፖሊስ ተቋማትን ጨምሮ ከክልል እስከ ቀበሌ መዋቅር ያሉ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችን በማወያየት ስለጉዳዩ መረጃዎችንና ማስረጃዎችን ማሰባሰቡን ተናግሯል።

የመከላከያ ሰራዊት አዋጅ ቁጥር 1286/2015 በአንቀጽ 6 (1) የመከላከያ ሚኒስቴር በሚያወጣው መመዘኛ መሠረት ለወታደርነት ብቁና ፈቃደኛ የሆኑ ሰዎችን ሊመለምል እንደሚችል መደንገጉን ያስታወሰው ኮሚሽኑ፤ "የኦሮሚያ ክልል አስተዳደርም የምልመላ ሂደቱን በመከላከያ ሚኒስቴር መስፈርቶች መሠረት እንዲያከናውን የተጠየቀ መሆኑን ተረድቻለሁ" ብሏል።

ኢሰመኮ ክትትል እና ምርመራ ባደረገባቸው አንዳንድ አካባቢዎች ተይዘው የነበሩ ሕፃናትን እና የአእምሮ ሕሙማንን ጨምሮ በግዳጅ የተያዙ በርካታ ሰዎችን ለማስለቀቅ መቻሉንም አስታውቋል።

በወቅቱ ኢሰመኮ ያነጋገራቸው የክልሉ የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ እንዲሁም በጅማ እና በሻሸመኔ ከተሞች የሚገኙ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ችግሩ መኖሩን አምነው፤ የማቆያ ስፍራዎችን በመፈተሽ የእርምት እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም ድርጊቱን በፈጸሙ የመንግሥት ኃላፊዎች እና የሚሊሻ አባላት ላይ እርምጃ እንደሚወስዱ መግለጻቸውን ኮሚሽኑ አስታውቋል።

የኮሚሽኑ የምርመራ ሪፖርት በመጠናቀር ላይ በነበረበት ወቅት በተለይም ሕዳር 14 እና 15 ቀን 2017 ዓ.ም. በኦሮሚያ ክልል ሲከናወን የቆየው የመከላከያ ሰራዊት አባላት ምልመላ ሥራ መጠናቀቁን እና ሰራዊቱ በፈቃደኛነት የተመዘገቡ እና የምልመላ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ምልምሎችን ለይቶ ወደ ማሰልጠኛ ተቋማት እንዲገቡ ማድረጉን አስታውቋል።

ኢሰመኮ በሻሸመኔ ከተማ ባደረገው ክትትል እና ምርመራ በሁሩፋ ክፍለ ከተማ፣ ሀሌሉ ወረዳ ውስጥ በማቆያ አዳራሽ ከነበሩ እና ኢሰመኮ ካነጋገራቸው 32 ሰዎች መካከል 14ቱ ዕድሜያቸው ከ15 እስከ 16 ዓመት መሆኑን የገለጹ ሲሆን፤ አንድ ሕፃን ደግሞ ዕድሜው 11 ዓመት መሆኑን ገልጿል።

ከትምህርት ቤት ሲወጡ ከነዩኒፎርማቸው ሀሌሉ ወረዳ ወደ ሚገኘው ማቆያ አዳራሽ እንዲገቡ የተደረጉ የ5ኛ ክፍል ተማሪ የሆኑ ሁለት የ15 ዓመት ሕፃናት ወደ አዳራሽ ከገቡ ሁለት ሳምንት እንደሆናቸው መግለጻቸውንም አስረድቷል፡፡

ሕጻናቱ ወደ ማቆያው የገቡበትን ሁኔታ ሲያስረዱም “ከትምህርት ቤት ስንመለስ መከላከያ ለሚገቡ 25,000 ብር ይሰጣል ብሎ አንድ ግለሰብ በባጃጅ አሳፈረን፤ ከዚያ 010 ቀበሌ (ሀሌሉ ወረዳ) ወደ ሚገኘው አዳራሽ ገባን፤ ነገር ግን ከገባን በኋላ መውጣት አልቻልንም” ሲሉ ለኢሰመኮ ገልጸዋል፡፡

በጅማ ከተማ ኢሰመኮ ያነጋገረው የ14 ዓመት ሕፃን ስለተያዘበት ሁኔታ ማስረዳቱን የገለጸው ኮሚሽኑ፤ ሕጻኑ የ7ተኛ ክፍል ተማሪ መሆኑን እና የቀበሌ መታወቂያ እንደሌለው ቢገልጽም በጸጥታ አካላቱ መወሰዱን ገልጿል፡፡

ኢሰመኮ በጎበኛቸው የማቆያ አዳራሾች ውስጥ የሚገኙ ሰዎች በተመሳሳይ መንገድ በተለይ በምሽት በርካታ ሰዎች ከፈቃዳቸው ውጪ በሚሊሻ እና በፖሊስ ተይዘው ወደ ማቆያ አዳራሾቹ እንደገቡ ገልጸዋል።

በተጨማሪም እነዚህ በግዳጅ የተያዙት ሰዎች ለመልቀቅ ከ20 ሺሕ እስከ 100 ሺሕ ብር ድረስ መጠየቃቸውን ኮሚሽኑ አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡

በየኢሰመኮ የክትትል እና ምርመራ ግኝቶችን ተከትሎ በጅማ እና በሻሸመኔ ከተሞች ከሚገኙ የመንግሥት አመራሮች ጋር በተደረጉ ውይይቶች፤ ከሕግ እና ከሰራዊቱ መስፈርቶች ውጪ የተያዙ 8 ሕፃናት እና 1 የአእምሮ ሕመምተኛን ጨምሮ ከ36 በላይ ሰዎች እንዲለቀቁ ለማድረግ መቻሉንም ገልጿል።

ኢሰመኮ ለመከላከያ ሚኒስቴር እና ለኦሮሚያ ክልል አስተዳደር እና ጸጥታ ቢሮ ሕዳር 17 ቀን 2017 ዓ.ም. በጻፋቸው ደብዳቤዎች ችግሩን በዝርዝር በመግለጽ፤ ተገቢው ማጣራት ተደርጎ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ፣ የተከናወኑ ወይም በመከናወን ላይ የሚገኙ ተግባራት ላይ ምላሽ እንዲሰጡ ቢጠይቅም ይህ ሪፖርት ይፋ እስከተደረገበት ድረስ ተቋማቱ ምላሽ አለመስጠታቸውን ገልጿል።

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተጀመረውን የዲያሌሲስ አገልግሎት ለማስቀጠል ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ተነገረ

ሕዳር 27/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የኩላሊት እጥበት ዲያሌሲስ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የገለጸው ሆስፒታሉ፤ የአገልግሎቱን ቀጣይነት ለማረጋገጥ የሁሉም አካላት ድጋፍ ያስፈልገኛል ሲል አስታውቋል።

የኩላሊት እጥበት ታካሚዎች አገልግሎቱን ለማግኘት ወደ ተለያዩ አካባቢዎች በሪፈራል ተልከው አገልግሎት ለማግኘት እንደሚገደዱ የሆስፒታሉ ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ካሊድ ሸረፋ ለአሐዱ ተናግረዋል።

በዚህም በሆስፒታሉ የአገልግሎቱ መጀመር ለበርካቶች እፎይታን የሚሰጥ መሆኑንም አክለዋል። ነገር ግን አገልግሎቱን በዘላቂነት ለማቅረብ በርካታ የሕክምና ቁሳቁስ ስለሚያስፈልግ የባለድርሻ አካላት ድጋፍ የሚጠበቅ መሆኑን ተናግረዋል።

ይህን አገልግሎት ለማስጀመር ከማሽን ግዢ፣ ማሽን ተከላና የዘርፉን ሰብ-እስፔሻሊስት ሀኪም ማፈላለግ እንዲሁም ሌሎች ባለሙያዎችን ማሰልጠንን ጨምሮ ቅድመ ዝግጅቱ ግዜ መውሰዱን ያስታወሱም ሲሆን፤ "አሁን ላይ የአገልግሎቱን ቀጣይነት ለማረጋገጥም የሁሉም አካላት ድጋፍ ያስፈልጋል" ሲሉ ገልጸዋል።

"በተለይም ሆስፒታሉ የበጀት እጥረት ያለበት ከመሆኑ አንፃር አገልግሎቱን በስፋት ለመስጠት እንዲቻል ድጋፍ አስፈላጊ ነው" ብለዋል።

በአሁኑ ጊዜ ሆስፒታሉ የኩላሊት እጥበት አገልግሎት መስጠት የጀመረው በውስን ማሽኖች በመሆኑ እንዲሁም ከአገልግሎቱ ፈላጊዎች ብዛት አንፃር በቅድሚያ ሥር የሰደደ ችግር ለገጠማቸው እና እጥበት እያደረጉ ለሚገኙ ታካሚዎች እንደሆነ ተጠቁሟል።

የኩላሊት እጥበት ገንዘብ ከፍሎ ለመታከም በቀላሉ እንደማይገኝ የሚገልጹት ሥራ አስኪያጁ፤ የአገልግሎቱ መጀመር የበርካቶችን እንግልት የሚቀንስ መሆኑንም አስገንዝበዋል።

በአበረ ስሜነህ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

#ADVERTISMENT
#AmharaBank
የአማራ ባንክ አ/ማ የባለአክሲዮኖች 3ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ማክሰኞ ታህሳስ 01 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ በሚሊኒየም አዳራሽ ስለሚካሄድ ባለአክሲዮኖች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጉባዔው እንድትገኙ ጥሪ እናስተላልፋለን፡፡

የጉባዔው አጀንዳዎችን እና ተጨማሪ መረጃዎችን ጥቅምት 06 ቀን 2017 ዓ.ም በወጡት አዲስ ዘመን እና ሪፖርተር አማርኛ እትም ጋዜጦች ላይ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ለበለጠ መረጃ ነፃ የጥሪ ማዕከል 690 ወይም
የባንኩን ድረ ገጽ www.amharabank.com.et ይጎብኙ፡፡

አማራ ባንክ
ከባንክ ባሻገር!

የአማራ ባንክ ትክክለኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾች
Website: www.amharabank.com
Facebook: www.Facebook.com/amharabanksc1
Telegram: /channel/Amhara_Banksc
Instagram: https://instagram.com/amhara_bank
Twitter: https://twitter.com/Amharabanksc
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/amharabank/
YouTube: https://youtube.com/channel/UC73x9uuGYV0Uxw0EkpVZN8g
TikTok: amharabanks.c" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@amharabanks.c

#አማራባንክ #AmharaBank

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነርን ለመሾም ለህብረተሰቡ ማስታወቂያ ወጣ

ሕዳር 26/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የኮሚሽን መስርያ ቤቱ ዋና ኮሚሽነር የሚሆኑ እጩዎችን ህብረተሰቡ እንዲጠቁም የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት ማስታወቂያ አውጥቷል።

ከዚህ ቀደም መስርያ ቤቱን ኮሚሽነር ሆነው ሲመሩ የነበሩት ዶክተር ዳንኤል በቀለ በግል ጉዳይ ስልጣናቸውን መልቀቃቸው ተከትሎ፤ በምክትል ኮሚሽነሯ ራኬብ መሰለ በተጠባባቂነት እየተመራ መሆኑ ይታወቃል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ኮሚሽኑን የሚመራ ግለሰብ እንዲቀርብለት በጠየቀው መሰረት፤ የጥቅማ ማስታወቂያ ለሕዝብ አውጥቷል።

የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በዋና ኮሚሽነር እንዲመራ በአዋጅ በተደነገገው መሰረት፤ በዋና ኮሚሽነር የሚሆኑ ጥቆማ እንዲደረግበት ኮሚቴ ማቋቋሙ ተገልጿል።

ጠቋሚዎች የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ በተቀመጠው መሰረት ከሕዳር 26 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታህሳስ 10 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናት ውስጥ ለቦታው የሚመጥን እጩ መጠቆም እንደሚቻል አሐዱ ከምክር ቤቱ ያገኘውን መረጃ አመላክቷል።

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

ህወሓት ሕዳር 29 በመቀሌ ከተማ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ጥያቄ አቀረበ

ሕዳር 26/2017 (አሐዱ ሬዲዮ)ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) በመጪው ሕዳር 29 ቀን 2017 ዓ.ም. በመቀሌ ከተማ ላይ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ይፈቀድልኝ ሲል ለከተማዋ አስተዳደር ደብዳቤ ጽፏል።

ህወሓት ለመቀሌ ከተማ አስተዳደር በተጻፈው ደብዳቤ እንደተገለጸው፤ ሕዳር 23 ቀን 2017 ዓ.ም "በትጥቅ የተደገፈ የአስተዳደር ፈረሳ በመከናወኑ ይህን ለመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ እናደርጋለን" ብሏል።

"ለዘመናት መስዋዕት ከፍለን የመሰረትናቸው ምክር ቤቶች በግለሰቦች ሲፈርሱ አንታገስም በሚል ምክንያት፤ ከሕዝባችንና አባላቶቻችን በተደጋጋሚ ጥሪ እየቀረበልን በመሆኑ ሕዳር 29 በመቀሌ ከተማ ሰልፍ ለማድረግ አቅደናል" ሲልም በደብዳቤው ገልጿል።

በዚህም መሰረት በተጠቀሰው ቀን ከጠዋቱ 2 ሰዓት እስከ 6:30 ሰልፉን ለማድረግ መዘጋጀቱን የገለጸው ፓርቲው፤ "የጸጥታ ኃይል ጥምር ኮሚቴ እንዲፈቅድልንና ከለላ እንዲያደርግልን እንጠይቃለን" ሲል ጠይቋል።

የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ከሰሞኑን 6 አዳዲስ ሹመቶች የሰጡ ሲሆን፤ ከስድስቱ ሹመቶች ሁለቱ በደብረፅዮን ገ/ ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት የተሾሙትን በማንሳት በሌሎች አመራሮች ተክተዋል።

ይህንንም ተከትሎ በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ትናንት ባወጣው መግለጫ፤ ለአቶ ጌታቸው ረዳ ሰጥቷቸው የነበረው የፕሬዝዳንት ውክልና ማንሳቱን የገለጸ ሲሆን፤ በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት እንዴት እና በማን እንዲሚተኩ ከፌደራል መንግሥት እየተወያየበት እንደሚገኝ አስታውቋል።

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

ለምክክር ኮሚሽኑ እስካሁን ድረስ አጀንዳ አለማስረከባቸውን የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት እና የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ማህበር ገለጹ

ሕዳር 26/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ዘርፍ እንቅስቃሴ እስር እና እግልትን ጨምሮ በርካታ ጫናዎች እየደረሱባቸዉ መሆኑን በዘርፉ ላይ የሚንቀሳቀሱ ተቋማት ሲያነሱ ይደመጣል።

በዘርፉ ላይ የሚደርሰዉ ጫና መፍትሄ እንዲያገኝ ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ አጀንዳ ስለማስረከባቸው አሐዱ የሚመለከታቸዉን አካላት ጠይቋል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ማህበር አጀንዳ የመለየት ሥራ አለመስራቱንና ምንም ዓይነት ጥሪ በዚህ መልክ ለአባላቱ አለመቅረቡን አሐዱ ገልጿል።

በተመሳሳይ አሐዱ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ታምራት ሃይሉን የጠየቀ ሲሆን፤ ለኮሚሽኑ ምንም አይነት አጀንዳ አለማስረከባቸውን ተናግረዋል።

በቅርቡ አንድ ጉባኤ በመጥራት መገናኛ ብዙሃን ሀሳባቸውን እንዲሰጡ ለማድረግ መታሰቡን ያነሱም ሲሆን፤ ነገር ግን እስካሁን ባለው ሂደት ውስጥ ምንም ዓይነት አጀንዳ ከሚዲያ ተቋማት አለመሰብሰቡን ገልጸዋል፡፡

"በዚህም መሰረት በቅርቡ ምክር ቤቱ በሚያዘጋጀው ጉባኤ ላይ የመገናኛ ብዙሃኖችን ሀሳብ በማካተት ለኮሚሽኑ እናሰረክባለን፡፡ አሁን ባለው ግን ሂደቱ ገና ነው" ሲሉም አቶ ታምራት ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ በበኩላቸው "ከመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ምንም አይነት አጀንዳ አልተረከብንም" ያሉ ሲሆን፤ ኮሚሽኑ ከመገናኛ ብዙሃን ተቋማት አጀንዳ እንዲቀርብለት ፍላጎት እንዳለው ተናግረዋል፡፡

አክለውም፤ "በሀገራዊ ምክክር ሥራዉን ለማሳካት የመገናኛ ብዙሃን ሚናው ቀላል የማይባል ነው" ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በትናንትናው ዕለት ሕዳር 25 ቀን 2017 የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ተወያይቶ ያፀደቀውን የውይይት አጀንዳ ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማስረከቡን አሐዱ መዘገቡ ይታወሳል።

በአቤል ደጀኔ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

አቶ ታዬ ደንዳኣ ከአንድ ዓመት እስር በኋላ ተፈተው ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተቀላቀሉ

ሕዳር 26/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የቀድሞ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታዬ ደንዳኣ ከአንድ ዓመት እስር በኋላ ዛሬ ሕዳር 26 ቀን 2017 ከእስር ተለቀው ከቤተሰቦቻቸው ጋር መቀላቀላቸው ተገልጿል።

አቶ ታዬ ትናንት አመሻሹን ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በመውጣት ላይ እያሉ በመንግሥት ጸጥታ ኃይሎት ተይዘው ወደ ፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ የተወሰዱ ሲሆን፤ ዛሬ ረፋዱ ላይ ሜክሲኮ ከሚገኘው የወንጀል ምርመራ ማዕከል ተለቀው ወደ ቤታቸው መግባታቸውን ባለቤታቸው ወ/ሮ ስንታየሁ ዓለማየሁ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።

ዛሬ ጠዋት ሜክሲኮ በሚገኘው የወንጀል ምርመራ ማዕከል ቤተሰብ ምግብ አድርሶላቸው ከተመለሰና ደህንነታው ከጠየቀ በኋላ፤ ዛሬ እኩለ ቀን ምሳ ሰዓት ላይ ከማቆያው እንዲወጡ ተወስኖ ሰባት ሰዓት አካባቢ መኖራቸው ቤት መድረሳቸውን ባለቤታቸው አስረድተዋል።

አቶ ታዬ ባለፈው ሰኞ ሕዳር 23 ቀን 2017 በ20 ሺሕ ብር ዋስትና ክሳቸውን ከውጪ መከታተል እንዲችሉ ታዞ፤ ከእስር እንዲለቀቁ በፌዴራሉ ሰበር ሰሚ ችሎት ተወስኖላቸው ነበር።

በዚህም መሠረት የተለያዩ ከማረሚያ ቤት የማስለቀቂያ ሂደቶች ተጠናቀው አቶ ታዬ ትናንት አመሻሽ 11 ሰዓት ላይ ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የተለቀቁ ሲሆን፤ ነገር ግን የፀጥታ ኃይሎች የማረሚያ ቤቱ በራፍ ላይ ጠብቀው ወዳልታወቀ ስፍራ እንደወሰዱዋቸው ባለቤታቸው ወ/ሮ ስንታየሁ ዓለማየሁ ተናግረው ነበር፡፡

የቀድሞ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታና የገዢው ብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ ባለስልጣን የነበሩት አቶ ታዬ ደንደዓ ከተከሰሱባቸው ሦስት ክሶች ሁለቱ ውድቅ ተደርጎላቸው “ከሕግ አግባብ ውጪ የጦር መሳሪያ ይዘው ተገኝተዋል” በሚል የተመሰረተባቸውን አንዱን ክስ በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት በመከላከል ሂደት ላይ እንደሆነም ዘገባው አመላክቷል።

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

በዲሞክራቲክ ኮንጎ ለጊዜው ባልታወቀ በሽታ ምክንያት የ79 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገለጸ

ሕዳር 26/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በዲሞክራቲክ ኮንጎ ከሕዳር 10 እስከ 25 ባለው ጊዜ ውስጥ ብቻ ከ60 በላይ ሰዎች ለጊዜው ባልታወቀ ጉንፋን መሰል በሽታ ምክንያት ሕይወታቸው ማለፉ ተነግሯል፡፡

በደቡብ-ምዕራብ ዲሞክራቲክ ኮንጎ ኩዋንጎዋ ግዛት የተከሰተው ይህ በሽታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ የተገለጸ ሲሆን፤ በበሽታው ሕይወታቸው ያለፈው በአብዛኛው ከ15 እስከ 18 ዓመት እድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ታዳጊዎች ናቸው ተብሏል፡፡

በአጠቃላይ በግዛቱና አካባቢው ባለፈው ወር የሞቱት ሰዎች ቁጥር 79 መድረሱንም የሀገሪቱ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታውቋል።

በተጨማሪም ከ300 በላይ እንደ ትኩሳት፣ ራስ ምታት፣ ሳል፣ የመተንፈስ ችግር እና የደም ማነስ ያሉ ምልክቶች በሀገሪቱ በስተ ምዕራብ በሚገኙ በፓንዚ፣ ካሙቸኬ እና ሙካንዛ ግዛቶች መመዝገባቸውን ገልጿል።

ስለሆነም ኅብረተሰቡ ተረጋግቶ በንቃት እንዲጠብቅ፣ እጁን በሳሙና እንዲታጠብ፣ ከስብሰባዎች እንዲርቅ እንዲሁም የሟቾችን አስከሬን ያለ ብቁ የሕክምና እርዳታ እንዳይነካ አሳስቧል።

የበሽታውን ትክክለኛውን ምንነት ለማወቅ የባለሙያዎች ቡድን ወደ አካባቢው መላኩንም የጤና ሚኒስቴሩ ጨምሮ ገልጿል፡፡

ሚኒስቴሩ ቀደም ሲል የዝንጀሮ ፈንጣጣ (MPOX) እና ኢቦላ በሀገሪቱ መከሰታቸውን አስታውሶ፤ ምናልባትም የክስተቱ ምንጮች እነዚህ በሽታዎች ሊሆኑ ይችላሉ ብሏል፡፡

በተላላፊ በሽታዎች ችግር ውስጥ የምትገኘው ኮንጎ ክስተቱ ተጨማሪ ድንጋጤን መፍጠሩ ተገልጿል፡፡

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

ቴሌግራም የተጠቃሚዎችን ደኅንነት በተመለከተ የአቋም ለውጥ ማድረጉ ተሰማ

ሕዳር 26/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ተጠቃሚያቸው እያደገ ከሚገኙት የማኅበራዊ ሚዲያ የትስስር መተግበሪያዎች መካከል አንዱ የሆነው ቴሌግራም ሲወቀስበት የነበረውን የተጠቃሚዎች ደኅንነት ጥበቃን በተመለከተ የአቋም ለውጥ ማድረጉ ተገልጿል።

በዚህም ቴሌግራም ከዓለም አቀፍ ተቋም ጋር በመተባበር የሕጻናት የወሲብ ብዝበዛ ይዘቶች በገጹ ላይ እንዳይዘዋወሩ ለመገደብ መስማማቱ ቢቢሲ ዘግቧል።

ቴሌግራም ለሕጻናት ጥበቃ የሚያደርግ አሠራርን እንዲከተል ለዓመታት ጫና ሲደረግበት ቢቆይም፣ ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቶ ነበር።

ቴሌግራም አብሮት ለመሥራት የተስማማው ‘ዘ ኢንተርኔት ዋች ፋውንዴሽን’ ወይም አይደብሊውኤፍ ተቋም የበይነ መረብ አገልግሎት ሰጪዎች ለሕጻናት ጥበቃ የሚገለገሉበት ነው።

ባለፈው ነሐሴ ወር ላይ የቴሌግራም መሥራች ፓቫል ዱሮቭ በፓሪስ አውሮፕላን ማረፊያ በቁጥጥር ሥር ከዋለ በኋላ፤ ቴሌግራም ይዘቶች ላይ ቁጥጥር ለማድረግ ተስማምቷል።

ቴሌግራምን ከ950 ሚሊዮን በላይ ሰዎች የሚጠቀሙት ሲሆን፤ ሌሎች ዓለም አቀፍ ማኅበራዊ ሚዲያዎች ከሚከተሉት ፖሊሲ በተለየ የተጠቃሚዎችን የግል መረጃን የሚጠብቅ መተግበሪያ እንደሆነም በመግለጽ ራሱን ያስተዋውቃል።

ነገር ግን በቴሌግራም ላይ አደንዛዥ ዕፅ ዝውውርን ጨምሮ የሕጻናት ወሲባዊ ይዘት ያላችው ይዘቶች ይዘዋወራሉ፤ የበይነ መረብ ምዝበራም እንደሚፈጸም መገናኛ ብዙኃን የሠሩት ምርመራ ያሳያል።

ቴሌግራም መሥራቹ በፓሪስ ከታሰሩ በኋላ፤ ፖሊስ ሕጋዊ ጥያቄ እስካቀረበ ድረስ ደንብ የጣሱ ሰዎችን የኮምፒውተር አድራሻ እና የስልክ ቁጥር ለሕግ አስከባሪዎች መስጠት፣ በቅርብ ያሉ ሰዎችን የሚጠቁመው እና ለበይነ መረብ አጭበርባሪዎች የሚዳርገውን ‘ፒፕል ኒር ባይ’ አሠራር ማጥፋት እንዲሁም ደንብ ጥሰዋል የተባሉ ምን ያህል ይዘቶች ከገጹ እንደወረዱ ሪፖርት ማድረግን የመሳሰሉ ለውጦችን አድርጓል።

ቴሌግራም እንደ ዋትስአፕ እና እንደ ሲግናል በተጠቃሚዎች መካከል ያለን የመረጃ ልውውጥ በምሥጢር የሚይዝ መተግበሪያ መሆኑም ተገልጿል።

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

#ADVERTISMENT
#ጊፍትሪልስቴት
ታላቅ የምስራች
!
**
ጊፍት ሪል ስቴት ከ10% ቅድመ ክፍያ ጀምሮ በ22 ሳይቶቹ ቅንጡ አፓርትመንቶችን እና የንግድ ሱቆችን ለሽያጭ አቅርቧል፡፡

ይህ ሳይት ለአፓርትመንትና ንግድ ሱቆች የሚውሉ G+25 ሶስት መንታ ህንጻዎች ያሉት ሲሆን የዚህ 6ኛ መንደር መለያዎች፡-
•ከባለአንድ እስከ ባለአራት መኝታ ክፍሎች ያሉት፣
•ለመኖሪያም ሆነ ለንግድ ተመራጭ አካባቢ የሆነ፣
•በአንድ ወለል ሶስት ቤቶች ብቻ ያሉት፣
•በእያንዳንዱ ወለል ስድስት አሳንስር ያለው፣
•አራት ቤዝመንት ያሉት በቂ የመኪና ማቆሚያ የተዘጋጀለት፣
•24 ሰዓት የኤሌክትሪክ፣ ኢንተርኔትና ውሃ አቅርቦት አሉት፣

ጊፍት ሪል ስቴት
ማህበረሰብን እንገነባለን!
ለበለጠ መረጃ፡-
Website: https://www.giftbusinessgroup.com                                                                                             
Twitter: https://twitter.com/GIFTBusinessG                                                     
YouTube: www.youtube.com/channel/UCcqr7cpVv9ski-F7haxXx4w                                                     
Facebook: www.facebook.com/profile.php?id=100090918391017...                                                       
Telegram: /channel/giftbusinessgroup

Short Code: 8055

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

#አሐዱ_ከመሪዎች_ዓለም

ጥንቅሩን ለመከታተል ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👇
https://youtu.be/5B0RmoS31sQ?si=rhbcjFBq6Fhyg5jL

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

"ለቀድሞ ታጣቂዎች የሚሰጠው ገንዘብ አስተኛ ነው መባሉ ተገቢ ጥያቄ ነው" ብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን

ሕዳር 25/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የቀድሞ ተዋጊዎችን ወደ ማህበረሰቡ ለመቀላቀል እየተሰራ ያለው ሥራ መቀጠሉን የገለጸው የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን፤ በትግራይ ክልል ወደ ማህበረሰቡ ለመቀላቀል ካሰባቸው 70 ሺሕ በላይ የቀድሞ ተዋጊዎች መካካል 2 ሺሕ ገደማ የሚሆኑት በማዕከሉ ስልጠና መውሰዳቸውን ገልጿል፡፡

የመጀመሪያ ዙር የገቡትን የቀድሞ ተዋጊዎችን በጥሩ አቀባበል ወደ ካምፕ ገብተዉ የሚገባውን ስልጠና እንዲያገኙ መደረጉን ለአሐዱ የተናገሩት የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ተስፋዓለም ይህደጎ ናቸው፡፡

ምክትል ኮሚሽነሩ አክለውም ወደ መቐለና ዕዳጋ ሀሙስ ማዕከላት ከገቡት 2 ሺሕ ገደማ ሰልጣኞች ውስጥ፤ 1 ሺሕ 640 የሚሆኑ የቀድሞ ተዋጊዎች ስልጠናውን አጠናቀው ወደ ማህበረሰቡ መቀላቀላቸውን ተናግረዋል፡፡

ቀሪዎቹም በተመሳሳይ ስልጠና ወስደዉ የወጡ ሲሆን፤ "በአጠቃላይ ከ2 ሺሕ በላይ የሚሆኑ የቀድሞ ተዋጊዎች ወደ ማህበረሰቡ የመቀላቀል ሥራ ተሰርቷል" ብለዋል፡፡

ይህ እንዳለ ሆኖ የቀድሞ ተዋጊዎችን ለማቋቋም የሚሰጠው ገንዘብ አነስተኛ መሆኑ ይነሳል፡፡ ይህንን በሚመለከት አሐዱ የጠየቃቸው የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ተስፋዓለም ይህደጎ፤ "ገንዘቡ አንሷል መባሉ ተገቢ ነው" ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ነገር ግን የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታና አቅም በላይ መሆኑን በመግለጽ፤ የቀድሞ ተዋጊዎች ችግሮቻቸውን ሊፈታ የሚችል በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ሥር ያለ አብይ ኮሚቴ መቋቋሙን ጨምረው ገልጸዋል፡፡

ኮሚቴው የሙያ ክህሎት ግብዓቶች ከተገኙ የማስተባበር ሥራ የሚሰራ መሆኑ የተነሳ ሲሆን፤ የተለያዩ ፕሮጀክቶች በመቅረፅ መንግሥታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር ሥራዎችን እየሰሩ እንደሆነም አስረድተዋል፡፡

ኮሚሽኑ በአሁን ወቅት በሥሩ ከ300 ሺሕ በላይ የቀድሞ ተዋጊዎችን መዝግቦ እየተንቀሳቀሰ ሲሆን፤ ከዚህ ውስጥ 70 በመቶ የሚሆነው በትግራይ ክልል የሚገኝ ነው፡፡

በአቤል ደጀኔ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

"በአገር ውስጥ ተፈናቃዮች ዙሪያ ከተለያዩ ረጂ ተቋማት የሚወጡ መረጃዎች መሬት ላይ ካለው ሀቅ ጋር  አይገናኙም" የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን

ሕዳር 25/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ብሔራዊ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን፤ በአገር ውስጥ ተፈናቃዮች ዙሪያ ከተለያዩ ረጂ ተቋማት የሚወጡ መረጃዎች መሬት ላይ ካለው ሀቅ ጋር አይገናኙም ሲል ለአሐዱ ገልጿል።

ኮሚሽኑ በኢትዮጵያ ያሉ የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች ቁጥር በተመለከተ መረጃ የሚናገሩ ተቋማት መበራከታቸውን ገልጾ፤ የሚያወጡት ጥናት ዙርያ ተአማኒነት እንደሚጎድላቸው አስታውቋል።

"በአብዛኛው የሚወጡ መረጃዎች ወደ አንድን ወገን ያጋደሉ ናቸው" ያለም ሲሆን፤ በዚህ ላይ ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት አሳስቧል።

እየቀረቡ ያሉ አሃዛዊ መረጃዎች 'ጥናት' በሚል ሰበብ የሚቀርቡ መሆናቸውን ጠቅሶ፤ "በተለይም ከፋይናንስ ደህንነት አንፃር የሚመለከተው መንግሥታዊ አካል ክትትል ሊያደርግበት ይገባል" ብሏል።

"በየመጠለያ ጣቢያው የሚገኙትን ተፈናቃዮችን 'እንደግፋለን' 'እርዳታ እናደርሳለን' በሚል፤ ለራሳቸው ጥቅም የሚያውሉ በረጂ ድርጅትት ሥም የተቋቋሙ አካላት መኖራቸውን ደርሼበታለሁ" ሲልም ለአሐዱ አስታውቋል።

የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች በተመለከተ በኮሚሽኑ በርካታ ሥራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ለአሐዱ የገለጹት የኮሚሽኑ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አለማየሁ ወጫቶ (ዶ/ር)፤ ባለፈው ሩብ ዓመትም የተመዘገቡ ውጤቶች አመርቂ መሆናቸውን ተናግረዋል።

"በጎ ፍቃደኛ ረጂዎችና አጥኚዎችም የአገር ውስጥ ተፈናቃዮችን በተመለከተ የሚፈልጉት መረጃ ካለም ከኮሚሽኑ የመረጃ ቋት እንዲጠቀሙ እናበረታታለን" ሲሉም ዶክተር አለማየሁ አክለዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ከረጂ ተቋማት ገንዘብ ለማግኘት ሲባል፤ የተጋነነ ቁጥር እንዳለ የማስመሰልና የማቅረብ አዝማሚያ እየተስተዋለ መሆኑን ገልጸዋል።

ይህ ተግባር እውነተኛ ረጂዎችን የሚያወዛግብ ከመሆኑ በተጨማሪም፤ የኮሚሽኑ መልካም ሥም የሚያጠለሽና በተቋሙ አመለካከት እንዲፈጠር እያደረገ መሆኑን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ ከየአካባቢያቸው የተፈናቀሉ በሚልየኖች የሚቆጠሩ የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች መኖራውን ሲገለጽ ቢቆይም፤ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ መምጣቱን መረጃዎችን ዋቢ አድርጎ ኮሚሽኑ ገልጿል።

የብሔራዊ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ይህንን ይበል እንጂ፤ ተፈናቃዮች አሁን ላይ አስፈላጊው ጥበቃ እየተደረገላቸው እንዳልሆነ፤ አሐዱ በተለያዩ ጊዜያቶች  ያሰባሰባቸው መረጃዎች ይጠቁማል። 

በአማኑኤል ክንደያ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…

AHADU RADIO FM 94.3

"በመርካቶም ይሁን በተለያዩ አካባቢዎች ከደረሰኝ ጋር በተያያዘ የታሸገ ሱቅ የለም" ገቢዎች ቢሮ

👉 "ከደረሰኝ ጋር ቁጥጥር እያደረገ የሚገኘው ገቢዎች ቢሮ ነው" ንግድ ቢሮ


ሕዳር 25/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የአዲስ አበባ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ "ከደረሰኝ ጋር በተያያዘ ምንም አይነት ሱቆችን አሽገን አናውቅም" ያለ ሲሆን፤ በሌላ በኩል ደግሞ የከተማ አስተዳደሩ ንግድ ቢሮ፤ "ከደረሰኝ ጋር ቁጥጥር እያደረገ የሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ነው" ሲል ገልጿል፡፡

አሐዱ "ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በመርካቶ እና በሌሎች የገበያ ማዕከሎች ከደረሰኝ ጋር በተያየዘ እየታሸጉ ያሉ የንግድ ማዕከል ሱቆችን እስከመጨረሻው፤ መፍትሄ ለመስጠት ምን እየተሰራ ነው?" ሲል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮን እና የንግድ ቢሮን አነጋግሯል፡፡

የገቢዎች ቢሮ የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሰዉነት አየለ በሰጡት ምላሽ፤ "ከደረሰኝ ጋር በተያያዘ ምንም አይነት ሱቆችን አሽገን አናውቅም" ሲሉ ተናግረዋል፡፡

አክለውም "ከዚህ ጋር በተያየዘ እኛ ደረሰኝ ከመቁረጥ ውጭ ሱቆችን አሽገን አናቅም" ያሉ ሲሆን፤ "እንደ ተቋም ግን ግብረ ሃይል ተቋቁሞ እየተሰራ ነው" ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

በሌላ በኩል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የንግድ ቢሮ የገበያ ጥናት መረጃ እና ፕሮሞሽን ዳይሬክተር ሙስማ ጀማል በሰጡት ምላሽ፤ እንደ ተቋም ግብረ ኃይል ተቋቁመዉ በጋራ እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

አክለውም፤ "ንግድ ቢሮ እየሰራ ያለው ከንግድ ፍቃድ ጋር በተያየዘ እና በምርት አቀርቦቶች ላይ ክትትል እና ቁጥጥር ማድረግ ነው እንጂ፤ ከደረሰኝ ጋር በተያየዘ ጉዳይ የሚመለከተው እና ስልጣን ያለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ነው" ሲሉ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

ይሁን እንጂ ሁለቱም ተቋማት ቀጥተኛ ኃላፊነት ከመውሰድ ቢቆጠቡም፤ ከቅርብ ቀናት ወዲህ እንደ መርካቶ ያሉ ትላልቅ የንግድ ማዕከሎችና ሱቆች "ከደረሰኝ ጋር በተያያዘ እየታሸጉ ነው" የሚል ቅሬታ ሲቀርብ ይሰማል፡፡

በተጨማሪም "ይህንን ችግር በተሟላና ሕጋዊ በሆነ መልኩ እልባት እየተሰጠው አይደለም" በሚል፤ ከተለያዩ በንግድ ዘርፉ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች ተደጋጋሚ ቅሬታ እያቀረቡ ይገኛል፡፡

በደረጄ መንግስቱ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Читать полностью…
Subscribe to a channel