alateriqilhaq | Unsorted

Telegram-канал alateriqilhaq - የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ

14591

Subscribe to a channel

የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ

ስልጣን፣ ዝናና ሀብት አይናቸውን የሸፈናቸው “አሊም” ተብዬዎች፤ የአሏህ አንድ ቁጥር ሀቅ የሆነውን ተውሂድ ማስተማራቸውን በጀርባቸው እንደወረወሩት ሁሉ ዝም ብለው ቢቀመጡ ኖሮ፤ ተውሂድን የታጠቁ ደረሳዎች፣ ዳኢዎች፣ ሼሆችና አሊሞች ተውሂድን ለማስፋፋት እያደረጉት ያለው ትግል ይህን ያህል ውጣ-ውረድና እንቅፋት፣ ክስና ውንጀላ ባልበዛበት ነበር… ስልጣን፣ ዝናና ሀብት ቀልባቸውን የደፈነው “አሊም” ተብዬዎች፤ የአሏህ አንድ ቁጥር ሀቅ የሆነውን ተውሂድ ማስተማራቸውን በጀርባቸው እንደወረወሩት ሁሉ፣ ዝም ብለው ቢቀመጡ ኖሮ፤ የተውሂድ ትምህርት በከፍተኛ ፍጥነት አገሪቱን ባዳረሰ፣ የሽርክ ተራራ በተፈረካከሰ፣ የቢድአ ጎራ በተደረማመሰ ነበር…

አሏህ ሁላችንንም ወደ ቅኑ ጎዳና ይምራን!

በዶክተር ጀማል ሙሀመድ

/channel/alateriqilhaq
كن على بصيرة

 

Читать полностью…

የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ

🔹ከሽርክ አዘቅጥ ለተዘፈቀው ወሎ ማን ይድረስለት?

“ሾናት” ሌላው 'ጨሌ' (4)

ወሎ፣ ተንታ ወረዳ አካበቢ የምትገኝ አንዲት ሙስሊም፣ የሆነ ህመም ከተሰማት፣ በአካባቢው “ወልይ” ተብሎ ወደሚታመንበት (ሆኖም በጥንቆላ ተግባር ላይ ወደ ተሰማራ) ሰው ዘንድ ትሄዳለች፡፡ “በያመቱ ሾናት ብይ” በማለት ያዛታል (ሾናት በሌላው የወሎ አካባቢ “ጨሌ” ተብሎ ይጠራል)፡፡ በተጨማሪም ከጥቅምት፣ ከጥር ወይም ከግንቦት ወር የትኛው ጊዜ  ለእሷ ተስማሚ መሆኑንና  የእሷን የሾናት የሚያበላትን፣ ማለትም ስርአተ አምልኮውን (ritual) መምራት ያለበትን ወንድ ይመርጥላታል፡፡

“ቀይ ሰው” ወይም “ጥቁር ሰው ያብላሽ”
ጠንቋዩ፣ “ቀይ ሰው” ወይም “ጥቁር ሰው ያብላሽ!” ሊላት ይችላል፡፡ ለምሳሌ፡- “ቀይ ሰው ያብላሽ!” ተብላ፣ ባሏ ቀይ ከሆነ፣ እሱ ያበላታል፡፡ ባሏ ጥቁር ከሆነ ደግሞ፣ ከመንደሯ ወንዶች ቀይ ሰው ትፈልጋለች፡፡ ወይም ደግሞ የባሏ መልክ ጠንቋዩ ይሁን ካላት መልክ ጋር ተስማሚ ቢሆንም፣ “ባልሽ እንዳያበላሽ፣ የባልሽና ያንቺ ኮከብ አይገጥምም” ሊላት ይችላል፡፡ ጠንቋዩ ከነገራት መንገድ ውጭ፣ ሾናቱ  ቢከናወን ተቀባይነት የለውም፡፡ የአምልኮው ተከታዮች እንደሚያምኑት ከሆነ፣ ሴትዬዋ ከመታመም አትድንም፤ ታማም ከሆነ ፈውስ አታገኝም…

የሾናት ዝግጅት
የሾናትን ሰርአተ አምልኮ ለመፈፀም የተለያዩ ዝግጅቶች ይከናወናሉ፡፡ ዝግጅቱ ሙሉ ለሙሉ ማለት በሚቻል ደረጃ፣ ከምግብና መጠጥ ጋር የተያያዘ ነው፡-
ከሽንብራ ቂጣ የተዘጋጀ የማር ፍትፍት፣ ጭብጦ፣ ዳቦ፣ የኑግ ልጥልጥ (እንደ ቂጣ የተጠፈጠፈ)፣ ሽምብራ ቆሎ፣ ፋፎ ቆሎ (ፈንዲሻ)፣ የገብስ ቆሎ፣ ዳቦ፣ ጠላ፣ ቡቅር… የቆሎ ዝርያዎች በሙሉ እንቅብ (በሰሀን መንገድ ከሳር የተሰራ ትልቅ እቃ) ላይ ተደርገው ይቀላቀሉና ከላያቸው ላይ የኑግ ልጥልጡ እየተቆረሰ ይደረጋል…

የአምልኮ ስርአቱ ከመጀመሩ በፊት፣ ከሴትዬዋ ቤት ውስጥ መጋረጃ ይጋረዳል፡፡ ሴትዬዋን የሚያበላት ሰውና እሷ ከመጋረጃው ውስጥ ይሆናሉ፡፡ ሾናት የምትበላው ሴት ቤተሰብም ሆነ ጎረቤት፣ የአምልኮ ስርአቱ መፈፀም ከመጀመሩ በፊት፣ ክትት ብሎ መግባት አለበት፡፡ ከመጀመሩ በፊት ያልገባ ሰው፣ በሶስተኛው ቀን የሾናት የመጨረሻው የአምልኮ ስርአት እስከሚከናወን ድረስ ወደ እዚያ ቤት መግባት አይችልም፡፡

ከገባስ? ባለሾናቷ ትታመማለች፤ ወይም ትታመማለች ተብሎ ይታሰባል፡፡ ስለሆነም ያላወቀ ሰው ወይም እንግዳ ከሩቅም ሆነ ከቅርብ ቦታ ቢመጣ “ሾናት አለ” ይባላል፡፡ በውጭ ተስተናግዶ ይመለሳል እንጂ በፍፁም አይገባም፡፡ የመረጃ ምንጬ እንዲህ ይላል - “ያቺ የመጣች ሴት ለምን እናቷ አትሆንም፤ መግባት አትችልም” ይላል፡፡ 
ከዙህር በኋላ ጎረቤቱ በሙሉ ክትት ብሎ ከገባ እንደ ገባ፣ የሚያበላት ሰውዬ ጪስ ማጨስ ሲጀምር፣ የሾናት የአምልኮ ስርአት “ሀ” ብሎ ይጀምራል፡፡ ከቤቱ መካከል ካለው ምድጃ ጋ' ጋቻ (ማጨሻ) ይቀመጣል፤ አድሩስ (እጣን) ይጨሳል፡፡ ባለሾናቷ ከምትቀመጥበት መደብ አካባቢ ሌላ ጋቻ ይቀመጣል፤ እሱም ላይ ይጨሳል፡፡ ከቤቱ በር ላይ እንዲሁ ጋቻ ይቀመጣል፤ እሱም ላይ ይጨሳል፡፡

ከጎድን በር (ከቤቱ በስተጀርባ በኩል ካለው በር)  ላይ ጋቻ ይቀመጣል፤ እሱም ላይ ይጨሳል፡፡ የሚጨሰው ግን እንደ ሌሎቹ ጋቻዎች አድሩስ ሳይሆን፣ ቶርበን (ትንባሆ) ነው፡፡ በዚህ በኩል ስለሚጨስበት ምክንያት፣ የመረጃ ምንጬ፣ “ጅኑ እንዳይወጣ ነው” በሚል እምነት መሆኑን ይናገራል፡፡ ጅኑ ሴትዮዋን እንዲታረቃት ነው ይህ ሁሉ ዝግጅት፣ ይህ ሁሉ ድግስ፣ ይህ ሁሉ ማጫጫስ፡፡ እሱ ከወጣ ማን ይታረቃታል? (የሰውንስ ድግስ ጥሎ የት ነው የሚሄደው? የማንነው ቀልደኛ!)

ዋናው የሾናት የአምልኮ ስርአት ሊጀምር ሲል፣ ከመጋረጃ ውጭ የታደመው የአካባቢው ሰው በሙሉ ዝም እንዲል ይነገራል፡፡ አንድ ትንፍሽ የሚል ሰው የለም - ሴትዬዋም እንደዚያው፡፡ ዝም ብላ ማዳመጥ ብቻ ነው…

ጅንን መማፀን
የተዘጋጀው ምግብ በሙሉ - በእየእቃው ላይ እንዳለ - ከመደቡ ላይ ከተቀመጠችው ከባለሾናቷ ፊት ይደረደራል፡፡ በመቀጠልም፣ ሰውዬው ጅኑን መማፀን ይጀምራል፡-

“እባካችሁ! እባካችሁ! በእገሊት ላይ ያላችሁ፤ አለሞቼ! ወርቆቼ! እናቶቼ! ያጠፋን ባሪያ ማሩት፡፡ ጨንረጋችሁ አጥፍታለች፤ አንበሷችሁ አጥፍታለች፤ ነጭ ዶሮ አጥፍታለች… ይሄን ሁሉ አጥፍታለች፡፡ ጌታ ያጠፋን ባሪያ ይምራል፡፡

“አለሞቼ! ወርቆቼ! እናቶቼ! ከናንተ በላይ እሷን እሚደግፋት፣ እሚጠግናት የለም፡፡ ቤተሰቦቿን ደህና አክርሙላት፤ ከብቶቿን፣ ቤቱን፣ ጎረቤቱን አማን አድርጉ… እጠራው ውሀ፣ እለመለመው ሳር አድርሷት…”

በዚህ መንገድ ዘለግ ላለ ጊዜ፣ የሴትዬዋን ጅን ይለምናል፤ ይማፀናል… ከዚያም ሰውዬው የማር ፍትፍት ያለበትን ሳህን በመያዝና ወደ እሷ እንደ ዞረ ጎንበስ በማለት፣ አሁንም ጅኑን መማፀን ይጀምራል፡-“ያመት ግብርህን በአይነት አቅርበናል” ይላል፡፡
የቀረበውን የግብር (የሚበላና የሚጠጣ) አይነት በሙሉ ይዘረዘራል፡-

“ግብርህን ጀባ! የማር ፍትፍት ጀባ! ቆሎ ጀባ! ዳቦ ጀባ! ጠላ ጀባ!…” በማለት፡፡ “የኑግ ልጥልጡን አሳምረን ወቅጠን፤ ማሩን ጥሩ አድርገን ፈትፍተን አቅርበናል… አሽከርህን/ባሪያህን ማር…” በማለት ይለማመናል፣ ማለትም ጅኑን ይማፀናል፡፡

በዚህ መካከል ሴትዬዋ ጉሪያ ትጀምራለች… የመረጃ ምንጬ እንደ ነገረኝ፣ አብዛኛዎቹ ሴቶች የሚያጎሩት አውቀው ነው፡፡ ካጎሩ “አውሀል” ወይም ዛር አለባቸው ስለሚባልና በህብረተሰቡ ውስጥ ክብር የሚያሰጥ ስለሆነ ነው፡፡ ያው አውሀል ያላት ሴት መሆኗ ከታመነ፣ የመፈራትም እድል ይኖራታል፡፡

ጉሪያዋን እንደ ጨረሰች፣ ሰውዬው የማር ፍትፍት ያለበትን እቃ በመያዝ፣ ጎንበስ ብሎ ያጎርሳታል፡፡ በዚህ መንገድ ከሁሉም የምግብ አይነት እያጎረሰ ያቀምሳታል፡፡ ከጠላውም ቀድቶ ይሰጣታል፤ ትቀምሳለች፡፡ ከዚያ በኋላ ከመጋረጃ ውጭ ላሉት ታዳሚዎች ምግቡ ይሰጣል፤ “ቀምሰውታል ብሉ” ይባላል፡፡

ታዳሚው በልቶ እንዳበቃ - መውጫው ሲደርስ - የሚያበላው ሰውዬ ከመጋረጃው ይወጣና በጣሳ ውሀ በመያዝ፣ ወደ ቤትም፣ ወደ ውጭም ሶስት ጊዜ ወጣ-ገባ በማለት ከውሀው እየዘገነ ይረጫል፡፡ ከዚያ “ወጣ-ገባ ተብሏል ውጡ” ይባላል፡፡ በመቀጠልም ሰው ወደየቤቱና ወደየስራው ይበተናል፡፡

ሴትዬዋ ግን እስከ ሶስተኛው ቀን ድረስ፣ ወደ መፀዳጃ ቤት ካልሆነ በስተቀር ወደ ውጭ መውጣት አትችልም፤ ዛሯ አይፈቅድም፡፡ ወደ መፀዳጃ ቤት ስትሄድም፣ አንካሴ ይዛና አንድ ሰው ከኋላዋ ተክትሏት መሆን አለበት፡፡

የሾናት አጨራረስ
በሶስተኛው ቀን ያ ያበላት ሰውዬ መጥቶ ገላዋን ያጥባታል፡፡ ለሾናት የምግብ አገልግሎት የዋሉ እቃዎች እጥብጣቢ በአንድ እቃ ላይ ይጠራቀማል፡፡ ልብሷን ታወልቅና ራቁቷን እንዳለች፣ የእቃው እጥብጣቢ እገላዋ ላይ ይፈሰሳል፡፡ በመቀጠል ንፁህ ውሀ እያደረገ ያጥባታል፡፡

በዚሁ በስተኛው ቀን፣ የጎረቤቱ ሰው - የመጀመሪያው የሾናት ቀን የተገኘው ሁሉ - ይጠራል፡፡ ክትት ብለው ከገቡ በኋላ፣ በመጀመሪያው ቀን እንደ ተደረገው፣ ጭስ የማጨስ ስርአት ይከናወናል፡፡ በመቀጠልም ብዙ የተልባ ጭብጦዎች (የጤፍ ቂጣ ተጋግሮ፣ ከተቆራረሰ በኋላ በተልባ የተጨበጠ) የያዘውን እቃ በማቅረብ ያ የሚያበላት ሰውዬ “ጀባ” ይላል - ለባለሾናቷ፣ ከመጋረጃው ውስጥ እንዳለች፡፡

Читать полностью…

የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ

''ሸርሁ ዓቂደቲል 'ዋሲጥያ''

 
✍️ፀሀፊ: ሸይኹል ኢስላም አህመድ ኢብኑ ተይሚያህ

ሸርህ ( ትንታኔ):- በሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ኸሊል ሀራሥ ረሒመሁሏህ

🎤የሚያቀራው:-ሸይኽ ዩሱፍ አህመድ ሀፊዞሁሏህ

ክፍል=የመጨረሻ

መጠን=7.7MB

🗓 ዘወትር ከሰኞ እስከ እሁድ ከዙህር ሰላት በፊት

🕌 በቡኻሪ መስጂድ

🌍  ባህር ዳር ኢትዮጲያ

የኪታቡ pdf
/channel/alateriqilhaq/6096

የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ
/channel/alateriqilhaq

كن على بصيرة

Читать полностью…

የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ

  
السلام علیكم ورحمۃ الله وبركاته

  🚨በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው ታላቅ የንያና ገቢ  ማሰባሰቢያ ፕሮግራም🚨
               
ከባህርዳር ሰለፊያ ቢላል መስጅድ የቴሌግራም ግሩፕ ልዩ የዳዕዋ ና የንያ ጥሪ አዘጋጅቷል

  📣🔈ቅዳሜ ምሽት 3:00 📣🔈

አድራሻ 👉 /channel/bilalmesji  ✈️✈️

📣በአይነቱ ለየት ያለ ታላቅ የዳዕዋ የንያ ፕሮግራም የፊታችን ቅዳሜ= 10/1/2018 ዓል ምሽት 3:00 ጀምሮ

ይህ ታላቅ ፕሮግራም በታላቅ ሸይኾችና ኡስታዞች ምሽቱ ደምቆ ያመሻል ኢንሻአላህ

◉◉  ቅዳሜ ምሽት
   ⏱ 3:00 ጀምሮ


🪑በአሏህ ፍቃድ የእለቱ ተጋባዠ እንግዶቻችን✈️ ፦

🎙 1⃣  ሸይኽ ሀሰን ገላዉ ( ሀፊዘሁሏህ) ከባህርዳር

🎙 2⃣  ሸየኽ ዩሱፍ አህመድ      ( ሀፊዘሁሏህ )ከባህርዳር

3⃣ ዶ/ር ሸይኽ ሁሴን መሀመድ አስልጢ ከአዲስ አበባ

4⃣ ሸይክ መሀመድ ጀማል ከ ኮንበልቻ

5⃣ ሸይኽ አቡዘር ሀሠን ከ ኮንበልቻ

7⃣ ሸይኽ መሀመድ ሀያት ከሀራ

8⃣ ኡስታዝ ሻኪር ሡልጣን ከአዲስ አበባ

9⃣ ኡስታዝ አብዱልቃድር ሀሠን ከአዳማ

     ኢንሻአሏህ ሌሎችም ተጋባዥ እንግዶችም ይኖራሉ

ይህንን ፕሮግራም የባህርዳር አባይ ማዶ ሰለፊያ ቢላል መስጅድ ግዥና ግንባታ ማሰባበሰቢያ  የቴሌግራም ግሩፕ ላይ በተባለው ቀንና ሰአት ጎራ በማለት ይሳተፉ ሌሎችንም ያሳትፉ

 🌎  ➡️ሼር
      
🗓
10-1-2018 የፊታችን ቅዳሜ ደማቅ      ምሽት

🌎  👉ሼር
       👉 ሼር   👉ሼር  👍አድ👍 አድ 👍 አድ በማድረግ ሀላፊነታችን እንወጣ  ለአኼራችን አሻራ እናሳርፍ !!
/channel/bilalmesji

Читать полностью…

የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ

''ሸርሁ ዓቂደቲል 'ዋሲጥያ''

 
✍️ፀሀፊ: ሸይኹል ኢስላም አህመድ ኢብኑ ተይሚያህ

ሸርህ ( ትንታኔ):- በሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ኸሊል ሀራሥ ረሒመሁሏህ

🎤የሚያቀራው:-ሸይኽ ዩሱፍ አህመድ ሀፊዞሁሏህ

ክፍል=45

🗓 ዘወትር ከሰኞ እስከ እሁድ ከዙህር ሰላት በፊት

🕌 በቡኻሪ መስጂድ

🌍  ባህር ዳር ኢትዮጲያ

የኪታቡ pdf
/channel/alateriqilhaq/6096

የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ
/channel/alateriqilhaq

كن على بصيرة

Читать полностью…

የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ

"ሸርሁ ሱና በርበሓሪ"


ማብራሪያ: ሸይኽ ሳሊህ ቢን ፈውዛን ቢን አብዲላህ አል ፈውዛን(ሃፊዞሁሏህ)

🎤ያቀራው: ሸይኽ ዩሱፍ አህመድ (ሃፊዞሁሏህ)


የተቀራው: ባህር ዳር  ሰለፊያ መስጅድ

ክፍል = 48

የኪታቡ pdf 

/channel/alateriqilhaq/5423

የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ

/channel/alateriqilhaq

كن على بصيرة

Читать полностью…

የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ

የጁምዓ ኹጥባ (ምክር)

የጤና ፀጋ


በሸይኽ ዩሱፍ አህመድ - ሀፊዞሁሏህ

በሰለፍያ መስጂድ

መጠን =7.38MB

03/01/2018

የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ

/channel/alateriqilhaq

كن على بصيرة

Читать полностью…

የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ

"ሪያዱ አስ-ሷሊሂን"

የደጋጎች ጨፌ (መዝናኛ)
ከሩሡሎች አይነታ ከነቢዩ (ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም) ንግግሮች የተሰበሰበ


✍️አዘጋጅ: ሙሒዲን አቢ ዘከሪያ የህያ ኢብኒ ሸረፍ አን' ነወዊ

🎙ያቀራው : ኡስታዝ ዩሱፍ አህመድ ሀፊዞሁሏህ

የተቀራው :

🌍  በባህር ዳር 

🕌 ፈትህ መስጅድ


ክፍል  58

መጠን = 12.55MB

የኪታቡ pdf 

/channel/alateriqilhaq/5575

የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ

/channel/alateriqilhaq

كن على بصيرة

Читать полностью…

የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ

''ሸርሁ ዓቂደቲል 'ዋሲጥያ''

 
✍️ፀሀፊ: ሸይኹል ኢስላም አህመድ ኢብኑ ተይሚያህ

ሸርህ ( ትንታኔ):- በሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ኸሊል ሀራሥ ረሒመሁሏህ

🎤የሚያቀራው:-ሸይኽ ዩሱፍ አህመድ ሀፊዞሁሏህ

ክፍል=43

መጠን= 15MB

🗓 ዘወትር ከሰኞ እስከ እሁድ ከዙህር ሰላት በፊት

🕌 በቡኻሪ መስጂድ

🌍 ባህር ዳር ኢትዮጲያ

የኪታቡ pdf
/channel/alateriqilhaq/6096

የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ
/channel/alateriqilhaq

كن على بصيرة

Читать полностью…

የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ

ዳውዶን አንቀጥቅጦ እንደማይገዛት ምንም ዋስትና የለም።

በሌላ አነጋገር ዳውዶዎች የግንቦት የቀየ ደምን ስለመተዋቸው እንጂ፣ ቶብተው ከዚህ አምልኮና መሰል ሸርኮች ራሳቸውን ነፃ ስለማውጣታቸው ማረጋገጫ መስጠት አይቻልም፡፡ በግንቦት የቀየ ደም ተሳታፊ የነበሩትና በስልክ ያነጋገርኳቸው የሰፈሬ ሰዎች፣ “ዛሬማ ቀርቶ”፣ “ከተውነው ስንት ጊዜው” እያሉ ማረጋገጫ ሲሰጡኝ፣ የተውበተን ምክንያት የነገሩኝ ከላይ የተጠቀሱትን ሁለት “መሰናክሎች” (የማህበረ ኢኮኖሚያዊ ጫና demographic change) በመጥቀስ ነው - ቶብታ የተወች መሆኑን የነገረችኝ አንዲት ሴት ብቻ ናት፡፡

የግንቦት ደም ጥቂት በሆኑ ሰዎች በቤት ውስጥ እየተከወነ ያለም ይሁን፣ ለመሞት በማጣጣር ላይ የሚገኝ፤ በሶስት ምክንያቶች ምንነቱን አሳምሮ ማጋለጥና በደንብ ማውገዝ የግድ አስፈላጊ ነው ፡-

አንደኛ፡- በእውቀት ላይ ሳይመሰረቱ (ሳይቶብቱ) የተተወ፣ ከአመድ ውስጥ የተዳፈነ እሳት ማለት ነው፡፡ አመዱ ሲገለጥ እሳቱ መፋጀቱ እንደማይቀር ሁሉ፣ የሽርክ ተግባርም አመች ሁኔታ ሲፈጠርለት፣ የሰውን ልብ እንደገና መቆጣጠሩ አይቀሬ ነው፡፡ (አንድ በእድሜ ጠና ያለ የሰፈሩ ነዋሪ፣ “የግንቦት የቀየ ደም ከቀረ በኋላ ነው አገራችንም፣ መንደራችንም ሰላም የራቀው” በማለት ጠንከር አድርጎ ቢገስፅ፣ ህብረተሰቡ ወደ ነበረበት የሽርክ አምልኮ የመመለስ እድሉ ሰፊ ነው)፡፡

ሁለተኛ፡- የግንቦት ደም በተውሂድ የትምህርት ሰይፍ ተመትቶ፣ ሰፈሩን የተሰናበተ ቢሆን ኖሮ፣ ሌሎች የሽርክና ወደ ሸርክ ሊያዳርሱ የሚችሉ የቢድአ ተግባራት በዚህ ሰፈርም ሆነ በሌላው የደሴና አካባቢው ሙስሊም ነዋሪዎች ሲከወኑ ባልታዩ ነበር - ባለፈው ያየነውና አሁንም እየተከወነ ያለው የዱበርቲ ወዳጃ አንዱ ማሳያ ነው፤ የቢለኑ “የሸሆቹ ውሀ”፣ የሙሽራው ድንጋይ፣ ወዘተ ሁሉ ያሉት እዚያው ደሴ ነው፡፡ ለምን? የተውሂድ ትምህርት በተገቢው መንገድ፣ ደረጃና መጠን ስላልተሰጠ፡፡
በዚህ ሰፈር (ዳውዶ) አሁንም ድረስ ከሚፈፀሙ የሸርክ ተግባራት መካከል ለምሳሌ “የዳውዶ አምዋቶች ይረዳሉ” ብሎ ማመን አንዱ ነው፡፡ “ዳውዶ ረግረጉ፣ አፈሩ መጀን” እያሉ ዱአ ማድረግም ሌላው ማስረጃ ነው፡፡

ሶስተኛ፡- የቀየ ደም ዳውዶ ላይ ክዋኔው ተመናመነ ማለት፣ በሌላው የደሴ ክፍል ወይም በአጠቃላይ በወሎ ውስጥ ትግበራው “ተመናምኗል” ወይም “ጠፍቷል” ማለት አይደለም፡፡ በከፋና በከረፋ ደረጃ መተግበሩ ጥርጥር የለውም - ወሎ ከሸርክ አዘቅጥ እንደ ተዘፈቀች ናትና፡፡

ማጠቃለያ፡-

አዋጅ! አዋጅ! አዋጅ!
የወሎ አሊሞች፣ የወሎ ሼሆች፣ የወሎ ዳኢዎች… ኧረ የት አላችሁ? ኧረ የት ገባሁች? ኧረ የት ተደበቃችሁ?

ህዝበ ሙስሊሞ “ገጠር፣ ከተማ” ሳይል መውጫ የሌለው የጀሀነም እሳት ማገዶ ከሚያርግ የሸርክ ተግባር ተዘፍቆ እያለ፣ የእናንተ ፀጥታ ምን ይባላል? ዛሬ በዱንያ ላይ “አየሁ፣ አላየሁም” ብላችሁ ብታልፉ፤ አሏህ በፍርዱ ቀን “እውቀት ሰጥቸህ ነበር፣ ለምን አላስተማርካቸውም? ለምን ከዛሬዋ ቀን ቅጣት አላስጠነቀቅካቸውም?” ብሎ ሲጠይቃችሁ፣ መልሳችሁ ምን ይሆን?

የአሏህን ሀቅ ለመወጣት ጥረት በማድረግ ላይ ያላችሁ ወንድሞችና እህቶች - ጥቂቶች ብትሆኑም - በትግላችሁ ቀጥሉ፡፡

ዝምታን የመረጣችሁ፣ ቢረፍድም አልመሸም፣ ቶብታችሁ ሀቁን በመጋፈጥ በሀገረ ወሎ የገነገነውን የሸርክ ዋርካ ገንድሳችሁ ጣሉ፡፡ መትረፊያው መንገድ እሱና እሱ ብቻ ነው፡፡

በዶክተር ጀማል ሙሀመድ

/channel/alateriqilhaq
كن على بصيرة

 

Читать полностью…

የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ

''ሸርሁ ዓቂደቲል 'ዋሲጥያ''

 
✍️ፀሀፊ: ሸይኹል ኢስላም አህመድ ኢብኑ ተይሚያህ

ሸርህ ( ትንታኔ):- በሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ኸሊል ሀራሥ ረሒመሁሏህ

🎤የሚያቀራው:-ሸይኽ ዩሱፍ አህመድ ሀፊዞሁሏህ

ክፍል=42

መጠን= 11.38MB

🎤ዘወትር ከሰኞ እስከ እሁድ ከዙህር ሰላት በፊት

🕌በቡኻሪ መስጂድ

🌍 ባህር ዳር ኢትዮጲያ

የኪታቡ pdf
/channel/alateriqilhaq/6096

የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ
/channel/alateriqilhaq

كن على بصيرة

Читать полностью…

የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ

👉  የፀሐይ ወይም የጨረቃ ግርዶሽ ግርዶሽ

ሸኽ ኢብኑ ባዝ አላህ ይዘንላቸውና ስለፀሐይ ግርዶሽ በሸሪዓ የመጣውና አሁን ደግሞ ከመከሰቱ በፊት ስለፀሀይና ጨረቃ የሚያጠኑ ሰዎች ስለ ክስተቱ ቀደም ብለው መናገራቸው እንዴት ይታያል ተብለው ተጠየቁ ።

➡ ️መልሳቸው ይህን ይመስላል :–

" የአላህ መልእክተኛ - ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም - የፀሐይና የጨረቃ ግርዶሽ አላህ ባሮቹን ሊያስፈራራበት እንዲከሰት እንደሚያደርገው ተናግረዋል ። እነዚህን ክስተቶች እንዲጠባበቁ ገፋፍተዋል ። እሱን እንዲፈሩና እንዲታዘዙ መክረዋል ። የፀሀይም ይሁን የጨረቃ ግርዶሽ ለማንም ሞት ወይም ህይወት እንደማይከሰቱ አስረድተዋል ። ነገር ግን ከአላህ ተአምራቶች ናቸው ። አላህ ባሮቹን ሊያስፈራራበት እንዲከሰቱ ያደርጋቸዋል ብለዋል ። ክስተቱን ባያችሁ ጊዜ ወደ ዱዓእና ዚክር ሽሹ እስኪከፈቱ ድረስ በሶላት ላይ ሆናችሁ አላህን ለምኑ ብለዋል ። ( የግርዶሽ ሶላት አሰጋገድን ለማስታወስ መጀመሪያ ኢማሙ ሶላት ውስጥ ከገባ በኋላ ፋቲሐን ይቀራና ረዥም ምእራፍ ይቀራል ። ከዛ ሩኩዕ ያደርጋል ። ከሩኩዕ ቀና ካለ በኋላ አሁንም ፋቲሐ ይቀራና ከመጀመሪያው አነስ ያለ ምእራፍ ቀርቶ ሩኩዕ ይወርድና ቀና ብሎ ወደ ስጁድ ይወርዳል ። ሩኩዕና ስጁዱን ማስረዘም ይወደዳል ። ከዛ ቆሞ ፋቲሐ ይቀራና እንደመጀመሪያው አድርጎ ተሸሁድ ተቀምጦ ሶላቱን ይጨርሳል )።
አላህን በማላቅ ፣ ባሪያ ነፃ በማውጣት ፣ ሶደቃ በመስጠት አዘዋል። ከቅጣቱ መፍራት እሱን በመታዘዝ መጠንቀቅ መፍትሔ መሆኑን አመላክተዋል "
ካሉ በኃላ ስለፀሐይና ጨረቃ የሚያጠኑ ሰዎች ይህን ክስተት በሒሳብ ማወቃቸው የአላህ ተአምር መሆናቸውና አላህ ባሮቹን ሊያስፈራራበት እንዲከሰት ማድረጉን አይፃረርም ብለዋል ።
ምክንያቱም አላህ ነው ሰበብ ያደረገላቸው
ሁለቱም በተወሰነላቸው ጊዜ እንዲወጡና እንዲገቡ ያደረጋቸው እሱ ነው ( በሱ ትእዛዝ ነው የሚንቀሳቀሱት ) በዘፈቀደ አይደለም ።
እነዚህ አጥኚዎች የሚያውቁበት ሰበብ መኖሩ ተአምር መሆናቸውን አይከለክልም ። ሌሎችም የሚታዩና የሚታወቁ ተአምራቶች እንዳሉ ሁሉ እነዚህ ሁሉ አላህን እንድንፈራው እንድንታዘዘው የሚያደርጉ ናቸው ። አነዚህ አጥኚዎች አብዛኛው ጊዜ ቀደም ብለው ሊያውቁት ይችላሉ ይህ ዒልመል ገይብ አይደለም ምክንያቱም እነዚህ ሰዎች በጥናት የሚያውቁት ዙርና ማረፊያ  ስላላቸው ። ይህ በዚህ ጥናት የተካኑት ያውቁታል አንዳንዴ ሊሳሳቱ ቢችሉም ግን የሩቅ ሚስጥር አይደለም ። ይህ አላህ በመልእክተኛው ምላስ ያዘዘውን አይፃረርም አይከለክልም ።
አላህ ለባሮቹ የሚጠቅማቸውንና ከጉዳት የሚጠብቃቸውን ነው የሚያዛቸው
ይላሉ ።
ውድ የአላህ ባሮች ይህ ክስተት ሂስይ ወይም ዛሂር በሆነው ሰበቡ የሚታወቅ ሲሆን ሸሪዓዊ በሆነው ሰበብ ደግሞ የአላህ ተአምር ነው ። ይህም ማለት የምንዝናናበት ፎቶ የምናነሳበት አንድ ቦታ ተሰብስበን እየተሳሳቅን እንደ መልካም አጋጣሚ የምናየው ሳይሆን አላህን የምንፈራበት መጥፊያችን እንዳይሆን የምንማፀንበት በምንችለው ሁሉ ወደ አላህ የሚያቃርበን መልካም ስራ የምንሰራበት ነው ። የቀደምት ነብያት ህዝቦች መጥፊያቸውን ሲያዩ መጠቀሚያቸው መስሏቸው በተሰባሰቡበት ይጠፉ ነበር ። ይህ የሚጠፉ ህዝቦች ተግባር ነው ። የኛ ነብይ - ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም - ግን መዳኛችንን ነግረውናልና ምክራቸውን እንቀበል ።
አላህ መልካሙን ሰምተው ከሚከተሉት ያድርገን

http://t.me/bahruteka

Читать полностью…

የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ

“ያንተማ ሀጃ - ያንተማ
ያንቺማ ሀጃ  - ያንቺማ
ከአርሽ አደባባይ - ተሰማ፡፡
አሁኑ ይሁን አሁን
ውሎ ማደሩ ለምን?
ማን ይሁን ዋቢ
አሏህና ነቢ፡፡” 

አራተኛው መሰረታዊ ችግር ጀባታ ከመስጠት ጋር የተያያዘ ነው፡፡ የዱበርቲ ወዳጃ፣ አሏህ የሚታመፅበትና የሽርክ ዱአ የሚደረግበት ክዋኔ ነውና በዚህ ተግባር ለሚሳተፉ ሰዎች ገንዘብ መስጠት፣ የሸርክ ተግባርን መደገፍና ማበረታታት ነው፡፡ ገንዘቡ ምግብ ለማዘጋጀትና ጫት ለመግዛት በመዋል፣ ዱበርቲዎቹ የሸርክ ዱአ (ወዳጃ) እንዲያደርጉ ስለሚያስችል ጀባታ ሰጪውን የወንጀል ተባባሪ ያደርገዋል፡፡

3ኛ. ልቅ የሆነ የሴትና ወንድ ቅልቅል አለበት

የዱበርቲ ወዳጃ በሴቶች የሚከናወን ቢሆንም፣ ከወንዶች ጋር የመቀላቀል ሁኔታ ባብዛኛው ይታያል፡፡ ለዚህ ችግር መፈጠር ሶስት አስቻይ ሁኔታዎች አሉ፡፡
አንድ - ወዳጃው በአደባባይ ጭምር ስለሚከናወን፣ በቂ የሆነ መጠለያ ሳይኖራቸውና እንደ ነገሩ በሆነ መንገድ ሂጃብ ስለሚለብሱ ለአጂነብይ እይታ የተጋለጡ ናቸው፡፡

ሁለት - ወንዶች ጀባታ ለመስጠትና የተለያዩ አገልግሎቶችን ለማቅረብ (ምግብ ለማዘጋጀትና ውሀ ለማቅረብ፣ ወዘተ.) ከሴቶቹ ጋር ይደባለቃሉ፡፡
ሶስት - አንዳንድ ወንዶችም፣ አብረው ሲቅሙ የሚታይበት አጋጣሚም አለ፡፡

4ኛ. ሀራም የሆነው ጫት ዋናው ግብአት ነው  

ጫት ባይኖር፣ አበጋሯ ያን ሁሉ የግጥምና የምርቃት ዶፍ በከፍተኛ ስሜትና ግለት ማውረድ አይሆንላትም፡፡ ጫት ባይኖር፣ አጃቢዎቹም መረባውን ያን ያህል ማሞቅና ማድመቅ አይሳካቸውም፡፡ ጫት ባይኖር፣ የዱበርቲ ወዳጃ ታዳሚዎች ፊታቸው ሊያብረቀርቅ፣ በየተቀመጡበት ሊወዛወዙና የመረባውን እምቢልታ ሊያስጮሁት አይችሉም፡፡ ስለዚህም ዋናው የዱአው አንቀሳቃሽ ሞተር ጫት ነው፡፡

ይህ ብቻ አይደለም፤ ጫት ባይኖርና እሱ እያቀጣጠለ የሚረጨው የመነቃቃትና የምርቃና ድባብ በወዳጃ ታዳሚዎች ላይ ባይፈጠር፤ “የዱበርቲ ዱአ ስለሚደርስ፣ ከመረቁኝ ሀጃዬ ይሳካል” ብለው በማሰብ ሰዎች ጀባታ ባልሰጡ ነበር፡፡ ጀባታ ከሌለ ደግሞ - በተለይ በአደባባይ የሚደረገው - የዱበርቲ ወዳጃ ህልውናው ያከትም ነበር፡፡ የምግቡን፣ የቡናውን፣ የጫቱን፣ የእጣኑን… ወጭ ማን ይሸፍናል - ከጀባታ የሚገኝ ገንዘብ እንጂ!? ጀባታው የሚገኘው ደግሞ፣ የጫቱ ምረቃና ከሚያቀጣጥለው የምረቃ ዶፍ ነው፡፡  እናም ጫት የዱበርቲ ወዳጃ ሞተር ብቻ ሳይሆን፣ የደም ስሩም ነው፡፡

አቅልን የሚቀይረው፣ እንቅልፍን የሚነሳው፣ ሱስ ሆኖ የሚያጀዝበው፣ ጤናን የሚያቃውሰው፣ ኢኮኖሚን የሚያናጋው፣ ቤተሰብን የሚያበጣብጥና ግፋ ሲልም የሚበትነው ሀራሙ ጫት ከሌለ ወዳጃ የለም፡፡ እናም የዱበርቲ ወዳጃ በሀራም ተጀምሮ፣ በሀራም ነው የሚያልቀው - በጫት ተጀምሮ፣ በጫት ነው የሚጠናቀቀውና፡፡ 

6ኛ. አቂዳን የሚነካ የተወኩል ችግር አለ 

ወሎ አካባቢ ያሉ ሙስሊሞች ከዱበርቲ ወዳጃ በተጨማሪ “የጢነኛ ወዳጃ” (በወጣት ወንዶች የሚደረግ) እና በትልልቅ ሰዎች (ወንዶች) የሚደረግ ወደጃ አላቸው፡፡ አንድ ሙስሊም ችግር ሲያጋጥመው፣ “አሏህ ችግሬን ያስወግድልኛል” ብሎ በማሰብ ዱአ ማድረጉ፣ አንዱ የተወኩሉ መገለጫ ነው፡፡ ወሎ የሚገኙ የሱፍያ እምነት ተከታይ ሙስሊሞች ዱንያዊ ፈተና በግለሰብ ደረጃ እንኳን ሲደርስባቸው፣ በተናጠል ከሚደረግ ዱአ ይልቅ (አንድ ሰው ለራሱ ችግር ራሱ ዱአ ከማድረግ ይልቅ)፣ በህብረት ወደሚደረግ ዱአ ያደላሉ ብቻ ሳይሆን፣ በህብረት የሚደረግን ዱአ አብልጠው ይመርጡታል፡፡

ይህ ብቻ አይደለም፤ አንድ ሰው የዱበርቲ ወዳጅ አድርጎ፣ ሀጃው (ጉዳዩ) ካልተሳካለት፣ ወደ ጢነኛ ወዳጃ፣ በዚህም ካልተሳካ ወደ ትልልቆቹ (ወንዶች) ወዳጃ ፊቱን ያዞራል፡፡ አንዱን የቡድን ወዳጃ (የሴቶች፣ የወጣቶች ወይም የትልልቅ ሰዎች) በመደጋገም የሚያደርግበትም አጋጣሚ ሞልቷል፡፡ እናም አሏህ የባሪያውን ዱአ ሰሚ በመሆኑ ላይ ካላቸው መተማመን ይልቅ፣ በቡድን ወዳጃ ውስጥ በአበጋር የሚደረግ ምርቃት “ይደርሳል” ወይም “ይሳካል” የሚለው መተማመናቸው ሚዛን ይደፋል፡፡ ይህ ሁሉ የሚያሳየን፣ ሰዎቹ በቡድን ወዳጃ ላይ ያላቸውን ድንበር ያለፈ መተማመን (ተወኩል) ጭምር ነው፡፡   
 
በሌላ በኩል ዱበርቲዎቹ፣ ጢነኞቹም ሆኑ ትላልቆቹ (ወንድ) የወዳጃ ተሳታፊዎች እራሳቸው፣ ለቡድን ዱአቸው የሚሰጡት ቦታ ከፍተኛ ነው፡፡ አንድ ችግር የገጠመው ሰው፣ አንዱን ሰው “ዱአ አድርግልኝ” ቢለው፣ ባብዛኛው “ወዳጃ ጥራ” ማለቱ አይቀሬ ነው፡፡ አንድ ሰው የሁኔታዎችን ወይም ክስተቶችን አዝማሚያ በማየት፣ በአካባቢው ወይም በአገር ደረጃ የሆነ ችግር (ጦርነት፣ ርሀብ፣ ተላላፊ በሽታ) ሊከሰት እንደሚችል ስጋት ቢያድርበት፣ የአካባቢው ሰዎች ወዳጃ እንዲወጡ መጎትጎት ወይም ማስተባበር ነው የሚቀናው፡፡ እናም ለጋራ ችግር መፍትሄ ለማግኘትም፣ በህብረቱ ወዳጃ ላይ ያለው የተወኩል ደረጃ ከልክ በላይ ከፍተኛ ነው፡፡

በሌላ በኩል ከፍ ሲል እንደ ጠቀስነው፣ ያለ ጫት የቡድን ወዳጃ (ዱአ) የለም፡፡ ዱበርቲዎቹ፣ ጢነኞች፣ ትላልቆቹ ወንዶች ጫት መቃም ቢከለከሉ፣ የአደባባዩን ቀርቶ፣ ሰው ሲታመም ወይም የሆነ ችግር ሲደርስበት በቤቱ የሚያርጉትን ዱአ ፍቃደኛ ሆነው ያደርጉታል ብሎ ማሰብ ሞኝነት ነው፡፡ ስለሆነም የዱአው ክንውን የጫት ጥገኛ ነው፡፡

“ጫት የዱአ መሳሪያ ነው” የሚልም የቆየ የሱፍያዎች አባባል አለ፡፡ የመቁረጫው መሳሪያ (መጥረቢያ ወይም መጋዝ) ከሌለ፣ ዛፍን መቁረጥ እንደማይቻል ሁሉ፣ የዱአው መሳሪያ (ጫት) ከሌለ - እንደነሱ እምነት - ዱአ ማድረግ አይቻልም፤ ቢደረግም አይሳከም፡፡ “ሀቁን እንናገር” ከተባለ ግን፣ ጫት የዱአ ሳይሆን የሸይጧን መሳሪያ ነው፡፡ (በነገራችን ላይ ይህ የሸይጧን መሳሪያ መቼ ይሆን፣ የአረብ ገንዳ መስጊድ ሰጋጆችን ከግራና ከቀኝ አጅቦ ማስገባቱና አጅቦ ማስወጣቱ የሚቀረው? እነዚያ ፎቷቸው ፒያሳን “ያደመቀው” የመጅሊስ ሰዎችስ፣ ጫት ሀራም መሆኑን መቼ ይሆን የሚናገሩት?)
ለማንኛውም ቃሚ ለሆኑ ሱፍያዎች ያለ ጫት ወዳጃም፣ ወዳጅም የለም፡፡ የወዳጃ ሰዎች ይህ በሽርክም፣ በቢድአም የተርመጠመው ዱአቸው ይከወን ዘንድ፣ ጫት አንዱ ዋና ቅድመ ሁኔታ ነው፡፡ እናም ጫት ካላቸው ተወኩል ላይ “ቀላል የማይባል ድርሻ አለው” ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ በአጠቃላይ የወዳጃ ሂደቱና ሰዎቹ በወዳጃው ላይ ያላቸው እርግጠኝነት (የቂን) ተደምሮ ሲታይ፣ ወዳጃ ተወኩልን በመሸርሸር አቂዳን የሚንድ የአምልኮ ስርአት መሆኑ አያጠራጥርም፡፡   
  
5ኛ. ሶላት ላይ መዘናጋት አለ

ዱበርቲ ወዳጃ ላይ የሚሳተፉ አብዘኛዎቹ ሴቶች፣ ሶላታቸውን ሰአቱን ጠብቀው አይሰግዱም፡፡ ለዚህ ደግሞ ዋናው ምክንያት፣ የወዳጃው ጫት ቂምሀ ምርቃና (ሀድራ) የሚሟሟቅበት ጊዜ ከሶላት ሰአት ጋር የመገጣጠሙ ነገር አይቀሬ የመሆኑ ጉዳይ ነው - በተለይ የአስርና የመግሪብ ሶላቶች ባብዛኛው ለዚህ አደጋ የተጋለጡ ናቸው፡፡ ሀድራው ተጋግሎ ወደ ሌሊት ከተሸጋገረም፣ የሱብሂ ሶላት ሳይሰገድ የመንጋቱ ነገር አያጠራጥርም፡፡ በነገራችን ላይ “ዱበርቲ” ተብለው፣ በወዳጃ ክዋኔ ውስጥ ተሳታፊ ከሆኑት መካከል ሶላት ጭርሱን የማይሰግዱም ይኖራሉ፡፡

ማጠቃለያ፡-

Читать полностью…

የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ

የጁምዓ ኹጥባ (ምክር)

ከሀቅ ማፈግፈግ የሚያስከትለው ጉዳት


በሸይኽ ዩሱፍ አህመድ حفظه الله تعالى

በቡኻሪ መስጂድ

መጠን = 8.05MB

30-12-2017

የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ

/channel/alateriqilhaq

كن على بصيرة

Читать полностью…

የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ

"ሪያዱ አስ-ሷሊሂን"
የደጋጎች ጨፌ (መዝናኛ)
ከሩሡሎች አይነታ ከነቢዩ (ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም) ንግግሮች የተሰበሰበ

✍️አዘጋጅ: ሙሒዲን አቢ ዘከሪያ የህያ ኢብኒ ሸረፍ አን' ነወዊ

🎤ያቀራው : ኡስታዝ ዩሱፍ አህመድ ሀፊዞሁሏህ

የተቀራው :

🌍  በባህር ዳር 

🕌 ፈትህ መስጅድ


ክፍል  57

መጠን = 8.81MB

የኪታቡ pdf 

/channel/alateriqilhaq/5575

የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ

/channel/alateriqilhaq

كن على بصيرة

Читать полностью…

የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ

ከዚያም ሰውዬው ሶስት ጊዜ ካሞኛት በኋላ ጭብጦውን ያጎርሳታል፤ ማለትም ጭብጦውን ወደ አፏ ያስጠጋና ለመጉረስ አፏን ከፈት ስታደርግ ጭብጦ የያዘ እጁን ይመልሳል፡፡ ይህን ተግባር ሶስት ጊዜ ይፈፅማል፡፡ ሶስቱን ያሞኘባቸውን ጭብጦዎች፣ ጭብጦዎችን ከያዘው እቃ ላይ ለብቻ ለይቶ ካስቀመጠ በኋላ፣ ለአራተኛ ጊዜ ሌላ ጭብጦ ያነሳና ያጎርሳታል፡፡

ከዚያ እነዚያን ለይቶ ያስቀመጣቸውን (ሴትዬዋን በማጉስ ያታለለባቸውን) ጭብጦዎች ይዞ ከመጋረጃው ይወጣል፤ ከቤቱ መሀል አካባቢ ወዳለው ምድጃ ይሄዳል፡፡ አንድ በአንድ ምድጃውን ወይም የምድጃውን ጉልቻ እያስነካ ወደ ውጭ ይወረውራቸዋል - ሶስቱንም ጭብጦዎች ተራ በተራ፡፡

ከዚያ በኋላ፣ “ቀምሰውታል፤ ብሉ” ይባላል፡፡ በእቃ ላይ የተቀመጠው የተልባ ጭብጦው ለታዳሚዎቹ ይታደላል፡፡ ጭብጦው ከተበላ በኋላ፣ ዳቦው፣ ቂጣው፣ ጠላው… ይከተላል፡፡ ከዚያ አወል ቡናው ከተጠጣ በኋላ፣ ባለሾናቷን ያበላት ሰውዬ ወጣ-ገባ ይላል፡፡ የሾናቱ የአምልኮ ስርአት ፍፃሜ ይሆናል፡፡ ሰውዬውም፣ ታዳሚዎቹም ወደየመጡበት ይመለሳሉ…

አሏህ በተከበረው ቁርአኑ እንዲህ ይላል:-
በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ «አላህን ተገዙ፤ ጣዖትንም ራቁ» በማለት መልእክተኛን በእርግጥ ልከናል:: (ሱረቱ ነህል÷ 36)
ከአንተ በፊትም እነሆ ከእኔ ሌላ (በእውነት የሚመለክ) አምላክ የለምና ተገዙኝ በማለት ወደርሱ የምናወርድለት ቢኾን እንጅ ከመልእክተኛ አንድንም አልላክንም፡፡ (ሱረቱ አንቢያ÷ 25)

አባዱሎ አገር - ሾናት ተዋረደ
በ2004 ዓ.ል. የሾናት አምልኮ ብርክ በሚያስይዛት የተንታ ወረዳ፣ በበሽሎ አካባቢ፣ ልዩ ስሙ አባዱሎ አገር በሚባለው አካባቢ እንዲህ ሆነ፡፡ አንድ የተውሂድ እውቀት ከልቡ የገባ ደረሳ (የመረጃ ምንጬ የሆነው) አክስቱ ሾናት ልትበላ (የሾናትን አምልኮ ልትፈፅም) በመዘጋጀት ላይ እያለች፣ በስርአቱ ላይ እንዲገኝ ጠራችው - ስለምትወደው፡፡ ጥሪዋን አክብሮ ሄደ… የሾናቱ ክዋኔ ሳይጀመርና ባለሾናቴዋ (አክስቱ) ሳትቀምሰው ከተዘጋጀው ምግብ በላ፡፡ በመሆኑም ቤተሰቡ በጣም ተቆጣ፡፡ በዚህ አላቆመም፣ የሚያበላት ሰውዬ ወጣ-ገባ ሳይል (ለታዳሚዎች ከቤት መውጣት ሳይፈቀድ) ወጥቶ ሄደ…

ይህ ወጣት በፈፀመው የሾናት አምልኮተ ስርአት ጥሰት የተነሳ አክስቱ መታመም ነበረባት፡፡ ቤተሰቡ፣ ጎረቤቱ፣ ጥሰቱን የሰማ ሁሉ ሴትዬዋ ትታመማለች ብሎ ጠበቀ፤ ጠበቀ፡፡ ቢያዩ፣ ቢያዩ እሷ ግን ወይ ፍንክች! “ወገቤን ከተከተኝ፤ የሰራ አካሌን በላኝ” ልትል ቀርቶ፣ ሰው “ራሴን አመመኝ” እንኳን አይልም፡፡ ኧረ ምንም እቴ!... ከዚህ በኋላ አክስቱ ሾናት ማብላቷን ተወችው፤ ቶበተች - ማሻአሏህ!

በዚያው ሰሞን አካባቢ የኢደል አዱሀ በአል ደረሰ፡፡ የበሽሎ ህዝብ ግልብጥ ብሎ፣ ከሰፊው የአባዱሎ አገር ሜዳ ላይ ተሰበሰበ - ለኢዱ ሶላት፡፡ የኢዱን ሶላት ከተሰገደ በኋላ ይህ ደረሳ በጣም ሰፊ ዳእዋ አደረገ - ሾናትን የሚያወግዝ፣ ሽርክነቱን የሚያጋልጥ፣ ሰይጣንን መገዛትና የክህደት አምልኮ መሆኑን በሚገባ የሚያብራራ… ደረሳው በዚህ አላቆመም፡፡
ከጓደኛው ጋር ሆኖ፣ ወደ ጠንቋዩ ቤት በመሄድም “ህዝቡን ከክህደት ተግባር ላይ በመጣል አታክስር” በማለት መከሩት፤ ገሰፁት… ፀረ ሾናት፣ ባጠቃላይም ፀረ ሽርክ ዳእዋቸውን ቀጠሉ፡፡ እናም በበሽሎ አካባቢ የሚከናወነው ሾናት በከፍተኛ ሁኔታ ተዳከመ…   
   
ማጠቃለያ፡-
ከዚህ በላይ ያየነው የሸርክና የጥንቆላ ኮተት፣ የጅን አምልኮና የለየለት የክህደት ተግባር በተንታ ወረዳ ብቻ ሳይሆን፣ በድፍን ወሎ ያለ ሀቅ ነው፡፡ ሊኖር የሚችለው የቅርፅ ልዩነት ብቻ ነው - ጨሌ፣ በሾናት እንደ ተተካው አይነት፣ በሸርክ ክዋኔ ደረጃና አይነት ላይ መጨመር ወይ መቀነስ፣ ለጅን አምልኮ ከሚቀርበው የምግብ አይነት ላይ መጨመር ወይ መቀነስ ወይም ቆሎን በንፍሮ፣ ድፎን በገንፎ የመተካት አይነት ለውጥ፡፡ በይዘት ግን ከወሎ መሀል እስከ ዳሩ፣ ከአንዱ ጫፍ እስከ ሌላው ጫፉ የሚከወነው የሽርክ አምልኮ በሙሉ፣ ለሰይጣን በማጎብደድ የሚፈፀም የክህደት ተግባር ነው፡፡

በሀገራችን በመጅሊሱ የስልጣን ኮርቻ ላይ ያሉትና “ታላላቅ አሊም” የሚባሉት ሼሆች ስለኢትዮጵያዊ ሙስሊሞች ምንድነው ያሉት? ከእዚያው ከወሎ አካባቢ የተገኙት ሼህ ሙሀመድ ሀሚዲን ስለወሎ ብቻ ሳይሆን ስለኢትዮጵያ ሙስሊሞች ምን ነበር ያሉት? “ዛሬ እዚህ አገራችን ላይ - አንዳንዶቹ ደስ ባይላቸውም፣ በግልፅ የምናገረው - ሀገራችን የአህለ ሱና አገር ነው፡፡ ሁሉም አህለ ሱና ነው፡፡”

ስለዚህ ይህ ሼህ በሀገራችን ከኩፍር የሚያደርስ የሽርክ ተግባር ይቅርና ቢድአም እንደሌለ እየነገሩን ነው፡፡ “አንዳንዶች ደስ ባይላቸውም”ም ተብሎልኛል፡፡  አቡቦክር አሲዲቅ፣ ኡመር ኢብኑል ኸጧብ፣ ኡስማን ኢብን አፋን… ይሄን ጉድ በዘመናቸው ቢሰሙ ደስ አይላቸውም ብቻ ሳይሆን፣ ይህን የመሰለ ቅጥፈት በተናገረ ላይ ሰራዊት ማዝመታቸው አይቀሬ ነበር፡፡   

ከዚያው ከወሎ የተገኙት ሌላው ሼህ - ኡመር ገነቴ - በበኩላቸው “የሚዳረሱበት አካል በህይወት ያለም ይሁን የሞተ፤ አቅለኛም ይሁን አቅል የሌለው ተወሱል (መዳረስ) ይበቃል፡፡  ተወሱል ከአላህ ውጭ በሆነ አካል ይበቃል፡፡”
ይህ ሰው በመጅሊሱ ስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት በአረብኛ በሰጡት “ፈትዋ”፣ እንኳንስ ህይወት ያለው ሰውና ጅን እንዲሁም እንስሳ ይቅርና ድንጋዩ፣ እንጨቱ፣ ውሀው፣ እበቱ… ቢማፀኑት ወደ አሏህ ለመቃረብ እንደሚያችል አረጋግጠዋል…

እና በህዝቡ ላይ እንደምን መፍረድ፣ እንደምንስ መደፍደፍ ይቻላል? ከአብራኩ የወጡትና ለሸህነት የበቁት ልጆቹ እንዲህ የሚያስቡና የሚያምኑ ከሆነ፣ ይህ ህዝብ ለጠንቋይ ታዛዥ ቢሆን፣ ለጅን ቢሰግድ፣ ለጣኦት ቢያርድ፣ ከዚህም አልፎ እንደ ህንዶች ያገኘው ነገር ሁሉ አምላክ አድርጎ ቢያዝ ይፈረድበታልን?
በተለይ የገጠሩን ህዝብ ስለተዘፈቀበት የክህደት አምልኮ ማን ነገረው? ማን አስተማረው?  የሚነግረው ካለ ሀቁን ለመቀበል ህዝቡ ምን ያህል ዝግጁ እንደ ሆነ፣ ከፍ ሲል የተጠቀሰው የበሽሎ ተሞክሮ ጥሩ አብነት ነው - በአንድ ቀን ብቻ ብዙ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል፡፡ 
ስልጣን፣ ዝናና ሀብት አይናቸውን የሸፈናቸው አሊም ተብዬዎች የአሏህ አንድ ቁጥር ሀቅ የሆነውን ተውሂድን ማስተማራቸው ቢቀር፣ ዝም ብለው ቢቀመጡ ጥሩ ነበር፡፡ መጅሊሱን እንደ መሳሪያ በመጠቀም፣ መውሊድ መከበር ያለበት ትክክለኛ በአል መሆኑን በመፈራረም ከማፅደቅና በየመስጊዶች ውስጥ የተውሂድ ኪታቦች እንዳይቀሩ ከማገድም አልፈው፣ በየጊዜው በሚነዙት ውዥንብር፣ የተምታታና ፀረ ተውሂድ የሆነ ግብስብስ ንግግራቸው፣ የሀቅ ብርሀን ብቅ ያለለትን ህዝብ እንዲወናበድ እያደረጉት ነው፡፡ ጃሂሉ ህብረተሰብ “እነሱ የሚያውቁት ነገር ቢኖር ነው” በማለት በቢድአና በሽርክ ተግባሩ ላይ ፀንቶ እንዲኖርና እንዲሞት እያደረጉት ነው፡፡ ከቶ በህዝቡ ላይ እንዴት መፍረድ ይቻላል? እሱ የሚያየው ስልጣናቸውን፣ ቁልል ጥምጣማቸውን፣ ተጎታች ካባቸውን፣ ሼህ-አሊም-ሙፍቲ (አሁን፣ አሁን ደግሞ ዶክተር) የሚል የስም ግትልትላቸውን ነው፡፡
“እነዚያ የቅርቢቱን ህይወት ከመጨረሻይቱ ሕይወት ይበልጥ የሚወዱ፣ ከአሏህም መንገድ የሚያግዱና መጣመሟን የሚፈልጉ ናቸው፡፡ እነዚያ በሩቅ ስሕተት ውስጥ ናቸው፡፡” (የኢብራሂም ምእራፍ፣ 3)

Читать полностью…

የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ

ታላቁ ሙፍቲ ወደ ማይቀረው አኺራህ

إنا لله وإنا إليه راجعون..  توفي قبل قليل سماحة المفتي العام للمملكة الشيخ عبدالعزيز بن عبدالله آل الشيخ غفر الله له ورحمه وأخلف الأمة كل خير
‏اللهم اجزه عنا خير الجزاء وارفع درجته في عليين برحمتك يا أرحم الراحمين . اللهم اخلف علينا فقده بخير خلف يا رب العالمين .

የተከበሩ ሸይኽ ዐብዱ-ል-ዐዚዝ ቢን ዐብዱላህ አሊ-ሸይኽ፣ የሳዑዲ ዓረቢያ መንግሥት ታላቅ ሙፍቲ ወደማይቀረው አኺራህ ሄደዋል።
አላህ ምህረቱን ይለግሳቸው፤ በህይወት ዘመናቸው ያስተላለፉትን እውቀት፣ የሰጡትን ፈትዋ እና ለህዝበ ሙስሊሙ የለገሱትን ምክር በመልካምም ሥራቸው ሚዛን ላይ ያድርግላቸው። ጀነተ-ል-ፊርደውስንም ከነብያት፣ ከሲዲቆች፣ ከሸሂዶችና ከመልካም ሰዎች ጋር አብረው እንዲኖሩ ይወፍቃቸው።

/channel/AbuImranAselefy/11281

Читать полностью…

የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ

የጁምዓ ኹጥባ(ምክር)

እስልምና እና የጃኂሊያ መስፋፋት


በሸይኽ ዩሱፍ አህመድ -ሀፊዞሁሏህ

በቡኻሪ መስጂድ

09/01/2018

የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ

/channel/alateriqilhaq

كن على بصيرة

Читать полностью…

የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ

''ሸርሁ ዓቂደቲል 'ዋሲጥያ''

 
✍️ፀሀፊ: ሸይኹል ኢስላም አህመድ ኢብኑ ተይሚያህ

ሸርህ ( ትንታኔ):- በሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ኸሊል ሀራሥ ረሒመሁሏህ

🎤የሚያቀራው:-ሸይኽ ዩሱፍ አህመድ ሀፊዞሁሏህ

ክፍል=46

🗓 ዘወትር ከሰኞ እስከ እሁድ ከዙህር ሰላት በፊት

🕌 በቡኻሪ መስጂድ

🌍  ባህር ዳር ኢትዮጲያ

የኪታቡ pdf
/channel/alateriqilhaq/6096

የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ
/channel/alateriqilhaq

كن على بصيرة

Читать полностью…

የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ

ሸይኽ ሑሰይን ምን አሉ?⤵️👇
/channel/IbnShifa/5672

✍🏻ሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን ቢን ሙሀመድ አስ-ሲልጢ (ሀፊዘሁላህ) በባህርዳር አባይ ማዶ ለመስጂድ ቦታ ግዢ በተከፈተው ጉሩፕ ላይ ሙሃዶራ ሲያደርጉ ካስተላለፉት መልእክት የሚከተለውን አንብባችሁ ተጠቀሙበት…

= የአላህ ቤት የሆነን መስጂድ የሱንና ሰዎች የሚሰግዱበትን መስጂድ ከሀገር ውጭም ሀገር ውስጥም ያሉ ሰለፊዮች ተባብረን ቦታውን መግዛትና መገንባት አለብን!!

=> በመቀጠል:- የባህርዳር መሻይኾችንና የተባረከ የሆነውን ጀመዓቸውን በጠቅላላ እናመሰግናለን፣ በተለይ ሸይኽ ሐሰን ገላውንና ሸይኽ ዩሱፍ አሕመድን እንዲሁም ከእነሱ ጋር ያሉ የኮሚቴና (የሹራ አባላትን) ማመስገን እወዳለሁ። በአላህ ላይ ማንንም አናጠራም፣ ነገር ግን እነዚህን ሰዎች ማመስገን ይገባል፣ ሐበሻ ላይ ያሉ ሰለፊዮች በመልካም አርኣያነት ከሚመለከቷቸውና እንደነሱ በሆንን ብለው ከሚመኟቸው ሰዎች ናቸው። በቅድሚያ ለአላህ ብለን እንወዳቸዋለን! በመቀጠል በመካከላቸው ባለው ወንድማማችነት፣ መከባበር፣ለርስበርሳቸው መተናነስና መተባበር፣ መደማመጥ እንደ ጥሩ አርኣያ አድርገን ነው ምንመለከታቸው፣ (ሰለፊዮችም እንደነሱ መሆን ከሚፈልጓቸው) ሰዎች ሲሆኑ ለሌሎች መልካም አርኣያ ይሆናሉ ብለንም ነው ምንመኛቸው። የባህርዳር ጀመዐህ በጀመዐህ አንድነታቸው፣ ልዩነትን አሽቀንጥሮ በመጣል ረገድ፣ ሌሎችም እንደነሱ በሆንን ብለው ከሚመኟቸው ጀመዓዎች ናቸው። በተለይ ፊትና በሚከሰትበት ወቅት በመካከላቸው በአንድነት በመተሳሰር የሚያሳዩት አንድነት ሌሎችንም ሰለፊዮች አቅጣጫ በማስያዝ ረገድ የሚደንቅ አካሄድ ነው ያላቸው። ከባህርዳር ውጭ ባሉ ቦታዎችም የሰለፊዮችን አንድነት በማስጠበቅ ላይ ያለቸው አሻራ የላቀ ነው። አላህ በረካ እንዲያደርግባቸውና ለሌሎች መልካም አርኣያነታቸው ቀጣይ እንዲሆን አላህን እጠይቀዋለሁ!። ሸይኽ ረቢዕ (ረሂመሁላህ) ለሚዘይሯቸው ሰዎች ስንት አመት ከመግሪብ እስከ ዒሻእ ሲመክሩ አደራ ወንድማማችነታችሁን፣ በመካከላችሁ አንድነታችሁን ጠብቁ እያሉ ሁሌ ይመክሩ ነበር… በኢትዮጵያ ደረጃ ሌሎች አካባቢ ያሉ ሰለፊዮችም ከነሱ ሊማሩና እንደነሱ ሊሆኑ በአካሄዳቸውና የጀመዐህ አንድነታቸውን ጠብቀው ቁርኣንና ሀዲስን በማሰራጨታቸው አርኣያ አድርገው ሊይዟቸው ይገባል።
ከድምፅ ፋይሉ የተወሰደ

ወደ ቻናላቸው ለመቀላቀል⤵️⤵️
/channel/HussinAssilty
/channel/HussinAssilty

#Join ⤵️⤵️ ቴሌግራም ቻናል
/channel/IbnShifa
/channel/IbnShifa

Follow Ibn Shifa's WhatsApp Channel: ⤵️⤵️ https://whatsapp.com/channel/0029VbAU7moHgZWXXXnNiL3f

Читать полностью…

የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ

''ሸርሁ ዓቂደቲል 'ዋሲጥያ''

 
✍️ፀሀፊ: ሸይኹል ኢስላም አህመድ ኢብኑ ተይሚያህ

ሸርህ ( ትንታኔ):- በሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ኸሊል ሀራሥ ረሒመሁሏህ

🎤የሚያቀራው:-ሸይኽ ዩሱፍ አህመድ ሀፊዞሁሏህ

ክፍል=44

መጠን= 14.03MB

🗓 ዘወትር ከሰኞ እስከ እሁድ ከዙህር ሰላት በፊት

🕌 በቡኻሪ መስጂድ

🌍  ባህር ዳር ኢትዮጲያ

የኪታቡ pdf
/channel/alateriqilhaq/6096

የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ
/channel/alateriqilhaq

كن على بصيرة

Читать полностью…

የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ

የጁምዓ ኹጥባ (ምክር)

ስለ ሞት እና ሞትን የማስታዎስ ጥቅሞች


በኡስታዝ ሰዕድ አብዱለጢፍ

በቡኻሪ መስጂድ

03/01/2018

የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ

/channel/alateriqilhaq

كن على بصيرة

Читать полностью…

የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
ኢንሻአሏህ

ዛሬ በዚሁ ግሩፕ ያማረና ያሸበረቀ የዳዕዋ🎙 ፕሮግራም ይኖረናል ሸር 🌟 በማድረግ ወርቃማ ምሽቱን ሌሎችንም ተጠቃሚ እናርግ

ሸር
      

      ሸረ

              ሸር
/channel/bilalmesji
/channel/bilalmesji

Читать полностью…

የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ

  
السلام علیكم ورحمۃ الله وبركاته

                       🕌🕌🕌

             አስደሳች ዜና


  🕌🕌🕌

ከባህርዳር ሰለፊያ ቢላል መስጅድ የቴሌግራም ግሩፕ ልዩ የዳዕዋ ጥሪ

  📢 ቅዳሜ ምሽት 3:00

↪️አድራሻ 👇🏽
              
/channel/bilalmesji
              
/channel/bilalmesji
              
/channel/bilalmesji

📢 ይህን በአይነቱ ለየት ያለና ሚሊዮኖች የሚጠብቁትን ታላቅ የዳዕዋ ፕሮግራም የፊታችን ቅዳሜ= መስከረም= 03/2018ዓል ምሽት 3:00 ጀምሮ እንካችሁ


🕌🕌🕌🕌🕌🕌🕌🕌

       👉እነሆ
                👇

◉◉  ቅዳሜ ምሽት  🕌 🕌

      ⌚️ 3:00 ጀምሮ

🪑በአሏህ ፍቃድ የእለቱ ተጋባዠ እንግዶቻችን ፦

🎙 ① ዶ/ር ሸይኽ ሁሴን ሙሀመድ አስልጢ(ሀፊዘሁሏ) ከስልጤ

🎙 ②  ኡስታዝ አብዱልቃዲር ሀሰን (ሀፊዘሁሏህ) ከኦሮሚያ ክልል ዋና ከተማ አዳማ

🕌 ይህንን የዳዕዋ ፕሮግራም የባህርዳር አባይ ማዶ ሰለፊያ ቢላል መስጅድ ግዥና ግንባታ ማሰባበሰቢያ  የቴሌግራም ግሩፕ
(
/channel/bilalmesji) ላይ በተባለው ቀንና ሰአት ጎራ በማለት እርሶና ቤተሰቦ ተጠቃሚ ይሁኑ ሌሎችንም ያሳትፉ 🕌

    ➢   👉
/channel/bilalmesji
                
/channel/bilalmesji
                
/channel/bilalmesji
የጅ ስልኮን ብቻ በመጠቀም የነኝህን ብርቅዬ የሱና ሸይኾች ዳዕዋ ባሉበት ቦታና ሆነው  ያድምጡ ፣ ይጠቀሙ ሌሎችንም ይጋብዙ
📢📢📢📢📢📢

🌐  👉ሼር
       👉 ሼር   👉ሼር  👍አድ👍 አድ 👍 አድ በማድረግ  ለአኼራችን አሻራ እናሳርፍ !!

🗓 መስከረም 3 -2018 የፊታችን ቅዳሜ ደማቅ ምሽት ኢንሻ አሏህ

  🕌🕌  🕌🕌  🕌🕌
  🕌🕌  🕌🕌  🕌🕌 

በዳዕዋው ፕሮግረሙ ላይ ለሚኖራችሁ ተሳትፎና አስተያየት ይህን ሊንክ በመጫን ይግቡ !!!

◼️⬇️⬇️⬇️

/channel/bilalmesji
/channel/bilalmesji
/channel/bilalmesji

Читать полностью…

የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ

🔶ከሽርክ አዘቅጥ ለተዘፈቀው ወሎ ማን ይድረስለት?

‘የግንቦት የቀየ ደም' - መተው ወይስ መቶበት (4)

ሰፈራችን “ዳውዶ” ይባላል። በሰሜን ምእራባዊ አቅጣጫ፣ ከጦሳ ተራራ ስር የሚገኝ የደሴ ከተማ አካል ሲሆን፣ ደሴ ከተማ ከመቆርቆሯ በፊት ጀምሮ ከነበሩት ጥቂት መንደሮች አንዱ ነው፡፡ እኛ ወጣት እያለን ዳውዶ ላይም ሆነ፣ በአብዛኛው ወሎ ውስጥ ከሚፈፀሙ የሸርክ አምልኮዎች አንዱ ነው - “የግንቦት የቀየ ደም”…

በወጣትነት እድሜዬ ከነበሩት የግንቦት ቀናት በአንዱ እለት የተፈፀመውን እስካሁን አልረሳውም፡፡ ለእኔ የቅርብ ዘመዴ የሆነችውና የግንቦት የቀየ ደምን በዋናነት የምተስተባብረው ሴትዮ፣ እኔንና ከእኔ ጋር ተቀራራቢ እድሜ ያላትንና የሺወርቅ። የምትባለውን የሰፈራችንን ልጅ፣ የግንቦት የቀየ ደም አምልኮ ስርአት ወደሚፈፀምበት ቦታ ወሰደችን፡፡ ቦታው ከነየሺወርቅ ቤት አጠገብ የሚገኝና መጠነኛ ስፋት ያለው ነው፡፡

ፊታችንን ወደ ደቡብ አቅጣጫ በማዞር፣ እኔን ከፊት ለፊት፣ የሺወረቅን ከኋላዬ እንድትቆም አደረገች፡፡ ነጩን ወንድ ዶሮ ለእኔ፣ ሴቷን ነጭ ዶሮ ለየሺወርቅ በእቅፋችን ካስያዘችን በኋላ፣ “ጀማሉ አንተ እየመራህ፤ የእነ እንትናን ቤት ወደ ግራ፣ የእነእንትናን ደግሞ ወደ ቀኝ፣ የእንእንትናን ቤት ወደ ግራ፣ የእንትናንም ወደ ግራ… ታደርጉና ጉርቢያው (ሸለቆው) ጋ' ስትደርሱ፣ ሳትሻገሩ የጉርቢያውን ዳር ዳሩ ይዛችሁ ቶሎ ኑ፡፡ ወደ ኋላ ማየትም፣ መነጋገርም የለም፤ ነግሪያችኋለሁ ትንፍሽ እንዳትሉ፡፡” …

ወንዱን ነጭ ዶሮ እንደታቀፍኩ ከፊት እየመራሁ፣ የሺወርቅም ሴቷን ነጭ ዶሮ እንደታቀፈች ከኋላዬ ተከትላኝ ጉዟችንን ቀጠልን… ዞሮ ማየት የለ! መናገር፣ መነጋገር የለ!  መነሻችን አመታዊው የግንቦት የቀየ ደም የሚቋደስበት ቦታ እንደ ሆነ ሁሉ፣ መንደሩን ክብ ሰርተን ስንመለስም መድረሻችን እሱ ነው…

ዶሮ ታቅፍን በምንሰራው ወልገድገድ ያለ ክብ ውስጥ ወደ ግራችን በማድረግ እንዲካተቱ የሚደረጉት ቤቶች ለግንቦቱ የቀየ ደም ገንዘብ ያዋጡ አባዋራዎች/እማዋራዎች ቤቶች ሲሆኑ፣ ወደ ቀኝ የተተውትና ከክቡ ውጭ የተደረጉት ቤቶች ገንዘብ ያላዋጡና በድግሱ የማይሳተፉ ናቸው… በተሰጠን ትእዛዝ መሰረት ክቡን ሰርተን እንደ ተመለስን፣ የሰፈራችን ሼህ መጡና ዶሮዎቹን አረዱ፤ የግንቦቱ የቀየ ደም ተሷረፈ ማለት ነው… ከዙህር ሶላት በኋላ ሸህዬው ይመጡና ድግሱ ይበላል… ከዚያ ልጅ-ልጆቹ ስንበተን፣ ትልልቆቹ ሰዎች ወደ ጫት መቃሙና ዱአ ወደሚሉት ክዋኔ ይገባሉ…

ይህ ሸርካዊ የአምልኮ ስርአት ለምን አስፈለገ?

የአምልኮ ስርአቱን የምታስተባብረው ይህች የቅርብ ዘመዴ፣ የግንቦት ወር ገብቶ አራት ወይ አምስት ቀናትን እንዳስቆጠረ፣ በየቤቱ በመዞር የመንደራችን ሰዎች ገንዘብ እንዲያዋጡ ቅስቀሳ ማድረግ ትጀምራለች፡-

“አምና የቀየ ደማችንን ወቅቱን ጠብቀን በማውጣታችን፣ ሳይነጥለን-ሳይገነጥለን ይሄው ለአመቱ በደህና አደረሰን፡፡ ክረምቱን በደህና አሳልፎ፣ ለዛሬ አመት በሰላም እንዲያደርሰን የግንቦት ደማችንን ቶሎ እናውጣ…”

ደሙ የሚሷረፍበትን ቦታ ብቻ ሳይሆን፣ የደሙን ክዋኔ አስፈላጊነት ለማጉላት ጭምር፣  ከአባቶች የተነገራት መሆኑን በማረጋገጥ ሁሌም የምትናገረውን አፈ ታሪክም አልረሳውም፡-

“ግንቦትን ጠብቆ በየአመቱ ከሌላ አገር የሚመጣ ትልቅ፣ ወተት የመሰለ ነጭ አሞራ ነበር፡፡ የግንቦቱን ደም ከምናፈስበት ቦታ ላይ ከነበረና መሀሉ ላይ ጉድጓዳ ካለው ትልቅ ድንጋይ ላይ ወተት ይቀመጥለታል፡፡ ወተቱን ጠጥቶ ይሄዳል፡፡”

ጥበቃን ከአሏህ ውጭ ካለ አካል መፈለግ

ይህ ከላይ የቀረበው የአምልኮ ተግባር - የግንቦት የቀየ ደም - “አደጋ፣ መከራና ችግር እንዳይደርስብኝ” በማለት፤ ከአሏህ ብቻ የሚፈለገውንና የሚጠየቀውን ጥበቃና ከለላ ከሌላ አካል መፈለግ በመሆኑ የለየለት በአሏህ ላይ የማጋራት ተግባር ነው፡፡ አሏህ ሙስሞች ሊገጥማቸው ከሚችል መከራ፣ ችግር፣ የኑሮ ውጣ ውረድ… ራሳቸውን ለመጠበቅ መጠየቅ ያለባቸው እሱንና እሱን ብቻ እንደ ሆነ በቁርአኑ እንዲህ በማለት አዟል፡-

በል፡- “በተፈልቃቂው ጎህ ጌታ እጠበቃለሁ - (1) ከፈጠረው ፍጡር ሁሉ ክፋት፤ (2) ከሌሊትም ክፋት በጨለመ ጊዜ፤ (3) በተቋጠሩ (ክሮች) ላይ ተፊዎች ከሆኑት (ደጋሚ) ሴቶችም ክፋት፣ (4) ከምቀኛም ክፋት በተመቀኘ ጊዜ (እጠበቃለሁ በል)፡፡”

በነገራችን ላይ የግንቦት የቀይ ደም አምልኮን የሚፈፅሙት ሰዎች፣ “ሙስሊም ነን” የሚሉ ቢሆንም፣ በወቅቱ (እኛ ወጣት በነበርንበት ወቅት) አብዛኛዎቻቸው ረመዷንን ከመፆም ውጭ ሶላት እንኳን የማይሰግዱ ነበሩ፡፡

የግንቦት ደም አሁን ያለበት ሁኔታ

ከ1990ዎቹ አ.ል. አጋማሽ በኋላ ይህ አደገኛ የሸርክ ተግባር ከአደባባይ ወደ ቤት በመግባት፣ ከወል ክዋኔነት ወደ ግለሰብ ክዋኔነት መቀየሩን፤ ከዚያም ቀስ በቀስ በጥቂቶች የሚከናወን የአምልኮ ስርአት ወደ መሆን መሸጋገሩን አሁንም እዚያው የሚኖር ዘመዴ አረጋግጦልኛል፡፡ ከዚህ አንፃር አንዳንዶች፣ “ይሄኮ እየቀረ ያለ ነገር ነው” በማለት ልንፅናና፣ ሌሎች ደግሞ ምናልባትም “በተውት አምልኮ፣ ሰዎችን መውቀስ ተገቢ አይደለም” ልንል እንችላለን፡፡ የሚፃፍበት የሸርክ ርእሰ ጉዳይ ደርቆብን የምናድርገው ሊመስል የሚችልበት እድልም ሊኖር ይችል ይሆናል፡፡ ይህ ሁሉ ግን ስህተት ነው፡፡

የግንቦት የቀየ ደም ከዳውዶ የአደባባይ ትእይንትነት ወደ ቤት በመግባት፣ የጥቂቶች የጓዳ ጉዳይ የሆነው፤ ህብረተሰቡ የግንቦት ደም ከኢስላም የሚያስወጣና ለዘላለም የእሳት ቅጣት የሚዳርግ የሸርክ አምልኮ መሆኑን ስላወቀ አይደለም፡፡ “የሀገራችን አሊሞች ዋና መፍለቂያ”፣ “ኢትዮጵያዊው አልአዝሀር ዩኒቨርሲቲ” እየተባለ ከሚሞካሸው ሀገረ ወሎ፣  ለዳውዶ ሰዎች ተውሂድን የሚያስተምር ሼህ በመገኘቱም አይደለም፡፡ አሏህን በብቸኛነት ማምለክ፣ አሏህ (ሱብሀነሁ ወተአላ) ፍጥረተ አለሙን ያስገኘበት፣ የእሱ አንድ ቁጥር ሀቅ መሆኑን የሚያስተምር ዳኢ ወይም ደረሳ በመፈጠሩም አይደለም፡፡

የግንቦት ደም እንዴት ወደ ጓዳ ገባ?

የቀድሞ ጎረቤቶቻችን እንደ ነገሩኝ፣ የግንቦት ደም ከድሮው የእኛ ሰፈር የአደባባይ ትእይንትነት የተሰናበተው በሁለት ምክንያቶች ነው፡-

አንደኛ - አስተባባሪ የነበሩት ሰዎች አገር በመልቀቅና በሞት ምክንያት ከአካባቢው ስለተለዩ፣ በትጋት የሚያስተባብር ሰው በመጥፋቱና ገንዘብ ማዋጣት ላይ አንዳንድ ሰዎች ዳተኝነት እያሳዩ በመምጣታቸው ነው፡፡ ባጭሩ የማህበረ ኢኮኖሚያዊ ጫና (socio-economic pressure) አንዱ ምክንያት ነው፡፡

ሁለተኛ - የከተማው መስፋፋት በፈጠረው ግፊት፣ በሰፈሩ ውስጥ በርካታ አዳዲስ ቤቶች በመሰራታቸው የተነሳ “መጤው” በመብዛቱ ጭምር ነው፡፡ እናም በዳውዶ ሰፈር ላይ demographic change መከሰቱ፣ በሽርክ አምልኮው የአደባባይ ክዋኔነት ላይ አሉታዊ ጫና መፍጠሩ ሁለተኛ ምክንያት ነው፡፡

መተው፣ መቶበት አይደለም

ከላይ ከቀረበው ገለፃ እንደምንረዳው፣ በቀየ ደም ስም ዳውዶ ሰፈራችንን ለዘመናት አንቀጥቅጦ ሲገዛት የኖረው ሽርክ፣ ወደ የጥቂቶች የጓዳ ውስጥ ተግባርነት የተቀየረው፣ ዳውዶ ላይ የተውሂድ ትምህርት በመስፋፋቱ አይደለም፡፡ ዳውዶዎች የተውሂድን ሰይፍ በመታጠቃቸው፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ በሚተላለፍ መንገድ በጭንቅላታቸው ውስጥ ሰርፆ የገባውን ሽርክ እጅና እግር፣ አንገትና ወገብ ቆራርጠው በመጣላቸው አይደለም፡፡ ስለዚህ የግንቦት የቀየ ደም፣ ነገ አፈሩን አራግፎ ወይም መልኩን ቀይሮ

Читать полностью…

የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ

"ሸርሁ ሱና በርበሓሪ"


ማብራሪያ: ሸይኽ ሳሊህ ቢን ፈውዛን ቢን አብዲላህ አል ፈውዛን(ሃፊዞሁሏህ)

🎤ያቀራው: ሸይኽ ዩሱፍ አህመድ (ሃፊዞሁሏህ)


የተቀራው: ባህር ዳር  ሰለፊያ መስጅድ

ክፍል = 48

መጠን = 11.81MB

የኪታቡ pdf 

/channel/alateriqilhaq/5423

የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ

/channel/alateriqilhaq

كن على بصيرة

Читать полностью…

የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ

አዋጅ! አዋጅ! አዋጅ!
የወሎ አሊሞች፣ የወሎ ሼሆች፣ የወሎ ዳኢዎች… ኧረ የት አላችሁ? ኧረ የት ገባሁች? ኧረ የት ተደበቃችሁ? ህዝበ ሙስሊሙ “ገጠር፣ ከተማ” ሳይል መውጫ የሌለው የጀሀነም እሳት ማገዶ ከሚያርግ የሸርክ ተግባር ተዘፍቆ እያለ፣ የእናንተ ፀጥታ ምን ይባላል? ዛሬ በዱንያ ላይ “አየሁ፣ አላየሁም” ብላችሁ ብታልፉ፤ አሏህ በፍርዱ ቀን “እውቀት ሰጥቸህ ነበር፣ ለምን አላስተማርካቸውም? ለምን ከዛሬዋ ቀን ቅጣት አላስጠነቀቅካቸውም?” ብሎ ሲጠይቃችሁ፣ መልሳችሁ ምን ይሆን?

ፎቷችሁን በየሄዳችሁበት ከተማ የምታስለጥፉትና የምትለጥፉት የመጅሊስ መሪዎችስ? የስልጣን ወንበራችሁን ከማደላደልና ጥቅማችሁን ከማደን አልፋችሁ መቼ ይሁን ከጫንቃችሁ ላይ የተቆለለውን የአሏህ ሀቅ የምታደርሱት? መቼ ይሆን ለዚህ ከሸርክ አረንቋ ለተዘፈቀ ህዝብ ሀቁን የምትነግሩት?  
የአሏን ሀቅ ለመወጣት ጥረት በማድረግ ላይ ያላችሁ ወንድሞችና እህቶች - ጥቂቶች ብትሆኑም - በትግላችሁ ቀጥሉ፡፡ ዝምታን የመረጣችሁ፣ ቢረፍድም አልመሸም፣ ቶብታችሁ ሀቁን በመጋፈጥ በሀገረ ወሎ የገነገነውን የሸርክ ዋርካ ገንድሳችሁ ጣሉ፡፡ መትረፊያው መንገድ እሱና እሱ ብቻ ነው፡፡

በዶክተር ጀማል ሙሀመድ

/channel/alateriqilhaq
كن على بصيرة

 

Читать полностью…

የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ

🔹ከሽርክ አዘቅጥ ለተዘፈቀው ወሎ ማን ይድረስለት?
 
'የዱበርቲ ወዳጃ' (3)

በመጋቢት ወር 2015፣ የመጀመሪያው ሳምንት አካባቢ ወደ ደሴ ሄጄ ነበር - ከልጄ ጋር… ፒያሳ ላይ ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ የሄዱ የመጅሊስ አመራሮችን ፎቶ የያዘና “እንኳን ደህና መጣችሁ” የሚል ትልቅ ባነር ተሰቅሏል…

ፒያሳን እንዳለፉ የአረብ ገንዳ መስጊድ ይገኛል፡፡ መስጊዱ ጥንታዊ ከመሆኑም በላይ፤ ፎቅ ሆኖ በአዲስ ስለተሰራ ስፋቱ፣ ቁመቱና ግዙፍነቱ ከውበቱ ጋር ተዳምሮ እጅግ አስደማሚ አድርጎታል፡፡
በመስጊዱ ምስራቃዊ አቅጣጫ በኩል ስገባ ያየሁት ትርኢት ግን፣ በጣም ከማስገረምም አልፎ አሳዝኖኛል፡፡ በቤቶች መካከል ወደ መስጊዱ ከሚያስገባው ጠባብ የእግረኛ መንገድ ግራና ቀኝ ላይ የጫት ሻጮች፣ ከታዳጊ ወጣት ቁመት የማይተናነስ ርዝመት ያለውን የጫት ክምራቸውን ከፊታቸው ደቅነው ተደርድረዋል፡፡ አንዳንዶቹ የጫቱን ዛላዎች እየሰባበሩ፣ የተወሰኑት ደግሞ እራሳቸውም እየቃሙ ስለሆነ፣ የጫቱ ሽታ ክፉኛ አጠነኝ፡፡ በእርግጠኝነት ቃሚ ላልሆኑ ሰዎች የሚረብሽ ሽታ ነው ያለው - የማይፈልጉትን ሽታ እየታጠኑ ወደ መስጊድ መግባትና ከመስጊድ መውጣት! ምን አይነት እርግማን ይሆን፣ ሙስሊሞችን ከጫት ጋር ያጣበቀን?

ይህ የጫት መሸጫ የሆነው የእግረኛ መንገድ፤ የዛሬ ሰላሳ፣ አርባ አመትም የጫት መሸጫ ነበር፡፡ ይሄው ዛሬም የጫት መሸጫ ነው… አረብ ገንዳ መስጊድ ለነበሩትና ላሉት ሼሆች፣ ዳኢዎች፣ ኢማሞች… የጫት ሀራምነት የሚገለጥላቸው መቼ ይሆን? ቢያንስ-ቢያንስ የመስጊዱ ኮሚቴ በከተማው ደንብ አስከባሪዎች አማካይነት፣ ጫት ሻጮች ከዚያ እንዲነሱ ለማድረግ፣ አቅመ ቢስ የሆነው ለምን ይሆን? ለነገሩ ጫት ሀራም ካልሆነ፣ ሰርቶ በሎችን እንዲባረሩ ማድረግ በደል ነው የሚሆነው…
ከአስር ሶላት በኋላ ወደ ሆጤ፣ ከዚያም “አራሪያ” ወደሚባለው ሰፈር አመራን - ከልጄ ጋር፡፡ የአጎቴ ልጅ ከሞተች ሳምንቷ ስለሆነ፣ ልጆቿን “አሏህ ይሶብራችሁ” ለማለት… ከቤቱ ደረስን፡፡ ወደ ቤት እንደ ገባን፣ ከሌላ ክፍል የሚመጣ “መረባ!”፣ “መረባ!” (“ይሁን!”፣ “ይሁን!”) የሚል የሴቶች የህብረት ጩኸት ይሰማን ጀመር፡፡ ይህ ማለት “የዱበርቲ ወዳጃ” አለ ማለት ነው፡፡

ወሎ ውስጥ በህብረት የሚፈፀም የዱአ ስርአተ አምልኮ “ወዳጃ” በመባል ሲጠራ፣ በአምልኮ ተግባሩ የሚሳተፉ ሴቶች ደግሞ “ዱበርቲ” የሚል የጋራ መጠሪያ አላቸው፡፡ ስለሆነም ሴቶች በህብረት የሚፈፅሙት ዱአ “የዱበርቲ ወዳጃ” በመባል ይታወቃል፡፡ ዱበርቲ በኦሮምኛ “ሴት” ማለት ሲሆን፣ “ወዳጃ” ማለት ወሎ አካባቢ ያለው ትርጉም “ዱአ” ማለት ነው (በወጣት ወንዶች ብቻ የሚደረግ ዱአ ደግሞ፣ “የጢነኛ ወዳጃ” ይባላል)...

“የዱበርቲ ወዳጃ” ለታመመም ሆነ ማንኛውም ችግር ለገጠመው ሰው ጭምር ይደረጋል፡፡ ከዚህም በላይ ድርቅ፣ ርሀብ፣ አደገኛ የሆነ ተላላፊ በሽታ፣ ጦርነት፣ ወዘተ ከተከሰተ፤ በአብዛኛው በእድሜ በሰል ያሉና ባልቴት ሴቶች “ወዳጃ እናድርግ” በማለት፣ በአካባቢያቸው ወደሚገኝ ሰፋ ያለ ክፍት ቦታ (ሜዳ፣ መንገድ ዳር…)  በመውጣት፣ ለተወሰኑ ተከታታይ ቀናት ወይም በየሳምንቱ ለተወሰ ጊዜ ይቀመጣሉ፡፡
ከወዳጃ ቡድኑ መካከል አንዷ በእድሜ ገፋ ያሉ ሴት፣ የዱአውን ስርአት ይመራሉ፡፡ “አበጋር” በማለት ይጠራሉ፡፡ ከወዳጃው ተሳታፊዎችም ሆነ ተሳታፊ ካልሆኑት ሰዎች (መንገደኛ፣ የሰፈር ሰው…) ጀባታ (ገንዘብ፣ ለእርድ የሚውል የቤት እንስሳ፣ ጫት፣ ቡና…) ሲሰጥ፣ ስጦታውን በመቀበል የሚመርቁት አበጋሯ ናቸው፡፡ የምረቃው ስርአት (ritual) በሚከተለው መንገድ ይከናወናል፡-

ጀባታ ሰጪው (ወንድም ሆነ ሴት) ፊቱን ወደ አበጋሯ በመዞር አጎንብሶና እጆቹን ዘርግቶ፤ አበጋሯ ድምፅዋም ከፍ አድርጋ የምረቃውን ዶፍ እያወረደችው እያለ፣ ያለማቋረጥ “አሚን! አሚን!” ማለት አለበት፡፡ የወዳጃው ታዳሚ ሴቶች በበኩላቸው፣ አበጋሯ በምረቃዋ መሀል የምትሰጠውን ፋታ በመከተል፣ በጋራ ድምፅ ጮክ ብለው “መረባ! መረባ!” በማለት የሚያጅቡ ሲሆን፤ ምርቃቱ እንዳለቀም - እንደ ሁኔታው አጎንብሶ ባለበት ወይም ከማጎነበስም አልፎ በመንበርከክ፣ አናቱን ከመራቂዋ እጅ ላይ ደፍቶ የመራቂዋን እጅ ይስማል…(እንደ ዶ/ር ሀውለት አህመድ የጠናበት ደግሞ፣ የአበጋሯን እግር ሊስም ይችላል)
ደሴ ካሉ ወዳጆቼ እንደሰማሁት - ከአራት አመት በፊት - የህወሀት ሰራዊት በራያ በኩል አድርጎ ወደ አማራ ክልል መስፋፋት ሲጀምርና የወረራው ስጋትና ሽብር ደሴዎችንም እያሳሰበ ሲመጣ፣ በደሴ ከተማ አንድ በኩል ያሉ ዱበርቲዎች ለወዳጃ በየሳምንቱ አደባባይ በመውጣት እንዲህ እያሉ ይመራረቁ ጀመር፡-

“እዚያው አሏህ ያብርድልን!”
“መረባ!”
“እዚያው ዘንቦ፣ እዚያው ያባራ!”
“መረባ!”
ወዲያ የሚያንሾካሹክ፣ እዚያው አብዶ ይሂድ!” 
“መረባ!”...

ካሉበት ሰፈር አካባቢ ቤት ተከራይቶ፣ ለወያኔ መረጃ የሚያቀብል አንድ ሰውዬው እንደሚከታተላቸው ግን አያውቁም ነበር - እነ እትዬ ዱበርቲዎች… ህወሀት ደሴን ይዛ በተቆጣጠረች ሰሞን፣ ይህ ሰውዬ ወደ አበጋሯ በመሄድ ጀባታ (ስጦታ) ካበረከተላቸው በኋላ፣ “'እዚያው አብዶ ይሂድ' ስትሉኝ የነበረው እኔ ነኝ” ብሏቸው እርፍ!...

ወደ ዋናው አጀንዳችን እንመለስ፤ የዱበርቲ ወዳጃ ተሳታፊዎች ሙስሊሞች ናቸውና ከኢስላም አንፃር ይህ የአምልኮ ስርአት ያሉበትን ዋና ዋና ችግሮች እንፈትሽ - በስድስት ዘርፎች ከፍለን፡-

1ኛ. የዱአ አምልኮው ቢድአ ነው

ቀጠሮ በመያዝ ከሆነ ቦታ ተሰብስቦ በመቀመጥ፣ አንዱን መሪ በማድረግ፣ እየተመራረቁ ዱአ ማድረግ ይህ በኢስላም የተደነገገ አይደለም፡፡ ስለዚህ የዱበርቲም ሆነ ሌሎቹ ወዳጃዎች በኢስላም ላይ የተደረጉ አዲስ ፈጠራዎች/ቢድአዎች ናቸው፡፡ የአሏህ መልእክተኛ (አለይሂ ሶላቱ ወሰላም) ያስተማሩን ማንኛውም ቢድአ ጥመት መሆኑን ነው፡፡ እናም የዱበርቲ ወዳጃ ፈፃሚዎችና አስፈፃሚዎች ጥመት ላይ የወደቁ የቢድአ ተዋናዮች ናቸው፡፡

2ኛ. ምረቃው በቢድአና ሸርክ የተሞላ ነው
 
የዱበርቲ ምረቃ፣ በኢስላም መነጽር ሲታይ፣ አራት መሰረታዊ ችግሮችን የያዘ ነው፡፡ 
የመጀመሪያው ችግር ከምረቃው ስርአት (ritual) ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ሶስቱም የምረቃው ስርአት ታሳታፊዎች - መራቂ፣ ተመራቂና አጃቢዎች (የወዳጃው ታዳሚ ሴቶች) - ኢስላም ያልፈቀደላቸውን የምረቃ ስርአተ አምልኮ ይፈፅማሉ፡-

ተመራቂው፡- ከመራቂዋ ፊት አጎንብሶ በመቆም፣ እጆችን ዘርግቶ “አሚን! አሚን!” በማለት፤
መራቂዋ (አበጋሯ)፡- እየጮኸችና ንግግሯን በዜማ እያደመቀች ሰውን አስጎንብሳ በመመረቅ፤
የወዳጃው ታዳሚ ሴቶች፡- ተሰብስበው በመቀመጥ “መረባ! መረባ!” በማለት፣ እየጮሁ ጭምር በማጀብ፤
ይህ ሁሉ በኢስላም የማይታወቅ የምረቃ ስርአት ነው፡፡ ባጭሩ በወዳጃ ስርአት መሰረት ምረቃ ማካሄድ እንዳለብን ወይም ተገቢ ስለመሆኑ የመጣ የቁርአንም ሆነ የሀደስ ማስረጃ የለምና የወዳጃ ምርቃት ቢድአ ነው፡፡

ሁለተኛው ችግር ከተመራቂው ሰው ወይም ሴት ጋር የተያያዘ ነው፡፡ አንድ ሰው ማጎንበስም ሆነ በግንባሩ መደፋት ያለበት ለአሏህ ብቻ ነው፡፡ ዱበርቲ ወዳጃ ላይ ይህ ለአሏህ ብቻ የተገባ መብት ለሰው ተላልፎ ይሰጣል፡፡

ሶስተኛው ከምረቃው ጋር የተገናኘው ችግር፣ በምረቃውና በዱአው ውስጥ የሚባሉት ግጥሞችም ሆኑ ዝርው ንግግሮች ሸርክ የተቀለቀለባቸው የመሆናቸው ጉዳይ ነው፡፡ ለአብነት የሚከተሉትን እንመልከት፡-

Читать полностью…

የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ

''ሸርሁ ዓቂደቲል 'ዋሲጥያ''

 
✍️ፀሀፊ: ሸይኹል ኢስላም አህመድ ኢብኑ ተይሚያህ

ሸርህ ( ትንታኔ):- በሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ኸሊል ሀራሥ ረሒመሁሏህ

🎤የሚያቀራው:-ሸይኽ ዩሱፍ አህመድ ሀፊዞሁሏህ

ክፍል=41

መጠን= 14.1MB

🎤ዘወትር ከሰኞ እስከ እሁድ ከዙህር ሰላት በፊት

🕌በቡኻሪ መስጂድ

🌍 ባህር ዳር ኢትዮጲያ

የኪታቡ pdf
/channel/alateriqilhaq/6096

የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ
/channel/alateriqilhaq

كن على بصيرة

Читать полностью…

የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ

  
السلام علیكم ورحمۃ الله وبركاته

     አስደሳች ዜና
               
ከባህርዳር ሰለፊያ ቢላል መስጅድ የቴሌግራም ግሩፕ ልዩ የዳዕዋ ጥሪ

  📢🔊ቅዳሜ ምሽት 3:00 📢🔊

አድራሻ 👉 /channel/bilalmesji

📢በአይነቱ ለየት ያለ ታላቅ የዳዕዋ ፕሮግራም የፊታችን ቅዳሜ= 01/13/2017 ዓል ምሽት 3:00 ጀምሮ

ይህ ታላቅ ፕሮግራም በታላቅ ሸይኾችና ኡስታዞች ምሽቱ ደምቆ ያመሻል ኢንሻአላህ

◉◉  ቅዳሜ ምሽት
   ⏱ 3:00 ጀምሮ 


🪑በአሏህ ፍቃድ የእለቱ ተጋባዠ እንግዶቻችን ፦

🎙 1⃣  ሸይኽ ዶ/ር ሁሰይን ሙሀመድ አስልጥይ( ሀፊዘሁሏህ) ከአዲስአበባ

🎙 2⃣  ኡስታዝ አብዱልቃድር ሀሠን      ( ሀፊዘሁሏህ )=አዳማ ከተማ

     ኢንሻአሏህ ሌሎችም ተጋባዥ እንግዶችም ይኖራሉ

ይህንን ፕሮግራም የባህርዳር አባይ ማዶ ሰለፊያ ቢላል መስጅድ ግዥና ግንባታ ማሰባበሰቢያ  የቴሌግራም ግሩፕ ላይ በተባለው ቀንና ሰአት ጎራ በማለት ይሳተፉ ሌሎችንም ያሳትፉ

🌐  👉ሼር
      
🗓
01-13-2017 የፊታችን ቅዳሜ ደማቅ      ምሽት

🌐  👉ሼር
       👉 ሼር   👉ሼር  👍አድ👍 አድ 👍 አድ በማድረግ ሀላፊነታችን እንወጣ  ለአኼራችን አሻራ እናሳርፍ !!
/channel/bilalmesji

Читать полностью…
Subscribe to a channel