ለኢትዮጵያ መንግሥት፥ በኢትዮጵያም ውስጥ ላላችሁ ማናቸውም የመንግሥት ጠላትነትን ለመመከት የተሰለፋችሁ ሁሉ፥ ኢትዮጵያን ለማፍረስ እየደከማችሁ ያላችሁ ሁሉ፥
በጥቅሉ የኢትዮጵያ ጠላት የሆናችሁ ሁሉ፥ በመሰላችሁ መንገድ መፍትሔ ለማምጣት የምትሮጡ ሁሉ፥
#በግድም_በውድም
#ለኢትዮጵያ_የዓለም_ብርሃናዊ_መንግሥት_ትንበረከካላችሁ። ለመትረፍም ትለምናላችሁ!
ይህ ከላይ ያያችሁትን ሁሉ የእግዚአብሔር ትእዛዝ ለማስፈጸም፥ በተለይ የከበረው መልአክ ሊቀ መላእክት #ቅዱስ_ገብርኤል ከነሠራዊቱ ከዚህ ደብዳቤና ከሌሎቹም 6 ዓይነት ደብዳቤዎች ጋር ለአፈጻጸሙ ተነቃንቋል።
በተጨማሪም ሁሉም ሊቃነ መላእክት ከነሠራዊታቸው የተሰጣቸውን አምላካዊ ትእዛዝ ለመፈጸም ተነቃንቀዋል። የሰው ዘር በሙሉ ከዚህ በሗላ ታየዋለህ። ውጤቱንም በግብር በዓይንህ ታየዋለህ።
ይህን ደብዳቤ፥ ያየኸውም ያላየኸውም፣ በስሚም የሰማኸውም፣ ፍጹምም ያላደመጥከውም
በነዚህ ምግባርህ ሳቢያ ከፍርድ የሚያስጥልህ አይደለም! ይልቅስ ፍርዱ ባንተው ላይ የሚበረታ ሆኖ ይደመድምሃል።
በስተመጨረሻ ልታውቁት የሚገባው እንደቀደመው ድርጊታችሁ አሁንም በትዕቢታችሁ፣ በንቀታችሁ
የምትገፉ ከሆነ፥ መልካም ነው #ለውጤቱ_ተዘጋጁበት። ደብዳቤውን ጊዜ ወስዳችሁ ስለተመለከታችሁት እናመሰግናለን።
በስተመጨረሻም እዚህ ሰዓት ላደረሰን ቸሩ አምላካችን #የአብርሃሙ_ሥላሴ፣ እንዲሁም ድንግል እናታችን ቅድስተ ቅዱሳን፥ በሰማይም ንግሥት በምድርም ንግሥት ለሆነችው እመቤታችን ማርያም ምስጋና እንደማያቋርጥ ጅረት ይፍሰስላቸው! አሜን።
— የሥላሴና የድንግል አገልጋይና ባርያ፥
#ከሥላሴ መክበሪያና መመስገኛ፥ ከርስተ ድንግል ቅድስት አገር #ኢትዮጵያ።
📍ብርሃናተ ዓለም የኢትዮጵያ ብርሃናዊ መንግሥት፥ የመንግሥት ምክር ቤት ዋና ሰብሳቢ፨
ጥር 7 2016 ዓ.ም ከወጣ ደብዳቤ የተወሰደ፨