🥀አሰላሙአለይኩም
ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ
የተወደዳችሁ የአዳማ ከተማ ነዋሪዎች በሙሉ ከላይ በድምፅ መልእክት ለመግለጽ እንደተሞከረው ወንድማችንን ለማገዝ ኢንሻአላህ ነገ ጠዋት 3:00 ላይ ሹራ ይኖረናል። ቦታው አብራር መስጂድ ውስጥ (ሙገር አካባቢ )ነው። ‼️ሰዓት ማክበር የሙዕሚን ባህሪ ነው‼️
‼️በመጨረሻም ይሄ መልእክት የደረሳቹ ወንድም እህቶች ለምታውቋቸው በሙሉ እንድታደርሱልን በአላህ ስም እንጠይቃለን!!
SHARE SHARE SHARE
ለማንኛውም ጥያቄ 👇👇👇
@hpsmuslimjemabot
join&share 👇👇
@hpsmuslimjema
ሙስሊሞችን ያስቆጣው የግሪኩ ኦርቶዶክስ ሊቀጳጳስ 'ሌሬንየሞስ'
ንግግር፦
«እስልምና ህዝብ ነው እንጂ ሀይማኖት አይደለም፣ የፖለቲካ ፖርቲና
የፖለቲካ አሳዳጅም ነው።»
@AmirelMueminin
አይኖች ተከፍተዉ ፤ ልቦች ትኩረት ሰጥተዉ ሊከታተሉት የሚገባ ፕሮግራም!!
እንንቃ!! እንደዚህ አይነት ፕሮግራሞችን ትኩረት ሰጥተን ማስተዋወቅ አለብን!!
ዛሬ ምሽት 3:00 ሰአት
@AmirelMueminin 👈join & share
🧕ሂክማ🧕
ክፍል ሃያ ሦስት
✍ኢብኑ ኢብራሂም
ቅዳሜ ከጠዋት ጀምሬ አሞኛል በሚል ከአልጋዬ ሳልወርድ አረፈድኩ። የቅዳሜ ቀን ግዳጃችንን አባቢ የኔንም የሱንም ድርሻ ሲወጣ ነው ያረፈደው። በኔ መታመም ተጨንቀው ስለነበር እንደበፊቱ በወኔ እና በፉክክር አልነበረም ሲሰሩ ያረፈዱት። የምሳ ሰዓት ተቃርቦ እየለባበሱ እንኳን ከጠዋት ጀምረው ሲነዘንዙኝ የነበረውን ጥያቄያቸውን ከማቅረብ አልተቆጠቡም ነበር።
"ሳሊሜ ለምን የዛሬው ምሳ ለሳምንት ተዛውሮ ሀኪም ቤት አንወስድህም?" አለኝ አባቢ ለባብሰው የጨረሱትን ማሚን እና ሪን ከኋላው አሰልፎ የመኝታ ቤቴ በር ላይ እንደቆመ።
"ያን ያህል እኮ አይደለም ትንሽ እራሴን ስላመመኝ ነው። ግብዣው ደግሞ የሚቀርልህ አይምሰልህ! በሌላ ቀን ብቻዬን ትጋብዘኛለህ!" አልኩት። ሪ በህመሜ ስለተደናገጠች ምላሷን ቆጠበች እንጂ ይሄኔ የሆነ ነገር ብላ ታበሽቀኝ ነበር።
ለመቅረትም ሆነ ይዘውኝ ለመሄድ ያልቻሉት ቤተሰቦቼ ለኔ ብለው ያዘጋጁልኝን ምሳ መኝታ ቤቴ ድረስ አስገብተውልኝ ተያይዘው ወጡ። የማሚ ፊት ላይ እስከዛሬ ስታመም አይባት የነበረውን ጭንቀት አላስተዋልኩም ነበር። እንዲያውም ግንባሯ ላይ ሊወጣ የሚተናነቅ ሳቅ ነበር ማስተዋል የቻልኩት። "ምናልባት ህመምን ከእናት መደበቅ አይቻል ይሆን? የእውነት የታመመን እና የውሸት የታመመን መለየት የሚያስችል ልዩ ሀይል በእናት ልቦና ውስጥ ይኖር ይሆን?" ስል አሰብኩ ወጥተው ከሄዱ በኋላ።
ገና የውጩን በር ከመዝጋታቸው ነበር ከአልጋዬ ላይ ተስፈንጥሬ የተነሳሁት። ለሂክማ ቀጠሮ 40 ደቂቃ ብቻ ነበር የቀረኝ። በነዚህ ደቂቃዎች ውስጥ ተጣጥቤና ለባብሼ በቴክስት ወደላከችልኝ ሆቴል መድረስ ይኖርብኛል። በነገራችን ላይ በማላውቀው የስልክ ቁጥር ከሂክማ መልዕክት ደርሶኛል። መልዕክቱ ላይ የምንገናኝበትን ሆቴል ስም ልካልኛለች። ትንሽ ግራ ያጋባኝ በፌስቡክ የላኩላትን የመጨረሻ መልዕክቴን ሳታይ እንዴት ስልኬን ልታውቅ እንደቻለች ነው።
ለባብሼ ጨርሼ የግቢውን በር እየቆለፍኩ እያለ ሌላ መልዕክት በስልኬ ደረሰኝ። ያሁኑ መልዕክት ደግሞ የተቀመጠችበትን የጠረዼዛ ቁጥር ነበር የያዘው። ከመልዕክቱ ቀድማኝ ሆቴል መድረሷን ተረዳሁ። ደግነቱ ሆቴሉ ከቤታችን ብዙም አይርቅም። በ10 ደቂቃዎች ውስጥ በአንድ ታክሲ መድረስ እችላለሁ። የታክሲ ሰልፍ ስላልነበር ቶሎ ነው ታክሲ ማግኘት የቻልኩት። የታክሲው መጨረሻ ተሳፋሪ እኔ ነበርኩ። የኔን መግባት ተከትሎ ታክሲዋ ወዲያውን ተንቀሳቀሰች።
አሁን የሆቴሉ መግቢያ ላይ ደርሻለሁ። ለሁለት ደቂቃ ያህል እግሬ አልታዘዝ ብሎኝ ደርቄ ቆምኩ። እግሬ አልንቀሳቀስ ብሎ ሲደርቅ በተቃራኒው ደግሞ ልቤ ከኔ ተለይታ ለመሮጥ ትጥር ነበር። መላ ሰውነቴ ይንቀጠቀጣል። በጀርባዬ ነጭ ላብ ሲወርድ ይሰማኛል። ቅድም እንዳመመኝ የነገርኳቸው ቤተሰቦች ቢያዩኝ የእውነት አሞኝ ለመሞት የደረስኩ ሳይመስላቸው አይቀርም።
"ምን ልታዘዝ አለቃዬ!" አለኝ ለብዙ ደቂቃ ደርቄ መቆሜን ያስተዋለው የሆቴሉ ጥበቃ ሰራተኛ። ዝንጥ ብዬ ባልለብስ ኖሮ አለቃዬ በሚለው ምትክ ሌባ መስዬው በያዘው ዱላ ባሯሯጠኝ ነበር።
"አመሰግናለሁ!" ብዬው ሳልወድ በግዴ ወደ ውስጥ ገባሁ። ልቤ ከቅድሙ በባሰ እየደለቀች ነው። ሙሽራ ሲገባ ሴቶች እየመቱ የሚዘፍኑበትን ከበሮ ትመስል ነበር ልቤ። በነዚህ ቅፅበታት ውስጥ ብዙ የሴት ምስሎች በምናቤ ተከስተው አልፈዋል። ቀይ፣ ጥቁር፣ ጠይም መልክ፤ ቀጭን፣ ወፍራም፣ መካከለኛ ሰውነት፤ ረጅም፣ አጭር፣ መለስተኛ ቁመት፤ ሰሜያዊ፣ ጥቁር፣ ቡኒ ጅልባብ። ብቻ ብዙ የሂክማ ምስሎችን አገለባብጩ አንዱም ላይ ሳልወስን አልፌያለሁ።
የሆቴሉን ሰፊ የመስታውት በር አልፌ እንደገባሁ ትልቅ የመመገቢያ አዳራሽ ገጠመኝ። ዙሪያውን ስቃኝ የአዳራሹ ምሶሶዎች ላይ እና ግድግዳዎች ላይ የመቀመጫዎች መለያ ቁጥር ተፅፎ አስተዋልኩ። ከቁጥሮቹ በፊት የተፃፈውን ፊደል ሳይ ሌላ አዳራሽ መኖሩን ተገነዘብኩ። ይሄኛው አዳራሽ ’A’ የሚል ኮድ የተሰጠው ሲሆን ሂክማ የላከችልኝ የጠረዼዛ ቁጥር መለያ ደግሞ ’B’ የሚል ኮድ ነው ከፊት ለፊቱ የተቀመጠው። ’B-22’ ሂክማ የላከችልኝ ቁጥር ነበር። ወደ ቀጣዩ አዳራሽ ስገባ ያየሁትን ነገር ማመን ተስኖኝ ፈዝዤ ቀረሁ። ገና የሁለተኛውን አዳራሽ ከመርገጤ ነበር ከአባቢ ጋር አይን ለአይን የተጋጨነው። አንዳንድ ጨረፍታዎች የወራትና ያመታቶች ያህል ይረዝማሉ። ከአባቢ ጋር አይን ለአይን በተጋጨንባት ቅፅበት ውስጥ ረዢም ወደመሰሉ የሃሳብ አፅናፎች ደርሼ ተመልሻለሁ። በነዚህ አፅናፎች ውስጥ ድንጋጤ፣ ግራ መጋባት፣ ሀፍረት የተሰኙ ወረዳዎችን ጎብኚቻለሁ። በደመ ነብስ ወደነሱ ሄጄ ክፍት ያገኘሁት ወንበር ላይ ዘፍ ብዬ ተቀመጥኩ።
"አሞኛል አላልክም ነበር?" ሲል አባቢ የፈራሁትን ጥያቄ ሰነዘረብኝ።
"ቤቱን ለማን ጥለህ መጣህ?" ማሚ ሁለተኛ ጥያቄ ደገመችኝ።
"ደግሞ አምሮብሃል። ከደቂቃዎች በፊት ታሞ የነበረ ሰው አትመስልም!" ሪ በነገር ወጋችኝ። የሚጠይቁኝን ጥያቄ ችላ ብዬ ፊታቸውን ማንበብ ጀመርኩ። አባቢ የፌዝ ሳቅ ፊቱን ሞልቶታል። ማሚ ደግሞ ቅድም ሳስተውልባት የነበረው የተዳፈነ ሳቅ አሁንም ተዳፍኖ ፊቷ ላይ ይነበባል። ሪ ጉንጮቿ ቀልተው የሚፈነዳ እንቡጥ ፅጌረዳ መስለዋል። ጉንጮቿ የመወለጃ ጊዜው የደረሰ ሳቅ እንዳረገዙ ያስታውቃሉ። ሃምዱ... እንዴ! ሀምዱም መሃላቸው አለ ለካ። በድንጋጤና ሀፍረት ውስጥ ስለነበርኩ አላስተዋልኩትም ነበር። አንዳንዴ ስንደነግጥ ካፈጠጠው አይነ ስጋችን ይልቅ በምናባችን የሳልነው ክስተት ጎልቶ ይታየናል። የሚያየውን ለማስተዋል እድል ያልሰጠሁት አይኔ ቤተሰቦቼ ከቤት ሲወጡ ባስተዋለው ምስል ብቻ ለመወሰን ተገዶ ነበር። እንዲህ ባለው የውርደቴ ቀን ከወላጆቼ ውጭ ማንም ባይኖር ምኞቴ ነበር። ነገር ግን ሀምዱ ታዳሚ ሆኖ ጠበቀኝ። ራሴን ከቅዤት ለማላቀቅ እየጣርኩ፤
"ትንሽ የተሻለኝ ሲመስለኝ ተነስቼ መጣሁ።" አልኳቸው ምንተፍረቴን።
"ወደዚህ እንደምንመጣ እኮ አልነገርንህም!" አለች ሪ በቅድሙ ሁኔታ እንዳለች። ጥያቄዋን ችላ ብዬ በድንጋጤ የረሳኋትን ሂክማን ባይኔ መፈለግ ጀመርኩ። በምናቤ የሳልኳት አይነት ሂክማን በዙሪያዬ ሳጣ ወደተቀመጥኩበት ጠረዼዛ አይኔን መለስኩ። ጠረዼዛው ማሃል ላይ በሦስት መዓዘን ቅርጽ የታጠፈ ፓስት ካርድ ተቀምጦ አየሁ። ካርዱ ላይ የጠረዼዛው ቁጥር ሰፍሮ ያየሁ ስለመሰለኝ አንስቼ አስተዋልኩት። ’B-22’ ይላል። ወንበሩ ራሱ ነው። እሷ የት ገባች? መልስ ያጣሁለት ጥያቄ ነበር።
"ሰው የጠፋብህ ትመስላለህ!" አለኝ አባቢ በአይኑ ሲከታተለኝ ቆይቶ።
"እ! አዎ!...አይ አልጠፋብኝም!" ስል ተንተባተብኩ።
"ልጄ ምን ሁነህብኛል? ልክ አይደለህም።" አለችን ማሚ የእውነት ደንግጣ።
"ሂክማን እየፈለክ ነዋ?" ስትል ጠየቀችኝ ሪ። ለአፍታ ያህል ቤተሰቦቼ መሃል መሆኔን ዘንግቼ፤
"አዎ የታለች?" ስል ጠየቅኩና በሁኔታዬ መልሼ ሀፍረት ተሰማኝ።
.
.
ይቀጥላል!
@AmirelMueminin
🥀🥀
የአደም ልጅ ሆይ!
ዋጋህን ብታውቅ ኖሮ እራስህን
በወንጀሎች አታዋርድም ነበር‥
ከሁሉም ፍጥረታት የተመረጥክ ነህ
ጀነትም ላንተው ነው የተዘጋጀችው ።
@AmirelMueminin 👈join
#አብዱ_ሰመድ
ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ሙሀመድ ሀሚዲን ከ'አልኮል ነፃ መጠጦችን አስመልክቶ የሰጡትን ፈትዋ ተመለከትኩት ሸይኹ ከዚ ቀደም የማያሰክር ከሆነ ይፈቀዳል ወይም 'ሀላል' ነው ብለው ከሰጡት ብይን እንደተመለሱና አሁን ላይ ግን ዝርዝር ነገሮችን ካጤኑ በኋላ ከአልኮል ነፃ መጠጥ ተብለው የሚሸጡት መጠጦች እንደማይፈቀዱ ገልፀዋል። ለዚህም መጀመሪያ ላይ የጠቀሱት ምክኒያት ከመነሻው መጠጦቹ ሙሉ ለሙሉ ከአልኮል ነፃ አይደሉም የሚለው ሲሆን እንደ ኢትዮጲያ ስታንዳርድም ከአልኮል ነፃ የሚባለው 5 ፐርሰንትና ከዚያ በታች የአልኮል መጠን ያላቸውን እንደማያካትት ገልፀዋል።
ነብዩ ቡኻሪ በዘገቡት ሀዲሳቸው ላይ "ብዙው የሚያሰክር ቲኒሹም ሀራም" ነው ያሉትን ሀዲስ ጠቅሰው፣ የአልኮል መጠኑ ቲኒሽ ቢሆንም በርከት ተደርጎ ቢጠጣ ሊያሰክር ስለሚችል ቲኒሽም ቢሆን መጠቀም ሀራም ይሆናል ብለዋል። ሌላው ያነሱት ነጥብ መጠጡ ልክ እንደ ኸምር ሱስ መሆኑና አስካሪ መጠጦች በሚታቸጉባቸው ጠርሙሶች መታሸጉ እንዲሁም በብዛት የሚሸጠው ግሮሰሪ ውስጥ በመሆኑ ኸምርን ለመደፋፈር በር ይከፍታል ሲሉ ገልፀዋል።
በተጨማሪም ከአልኮል 'ነፃ' መጠጦች ሲመረቱ በፋብሪካ ውስጥ የሚያልፉበትን ሂደት በተመለከተም ሸይኹ ከባለሙያዎች እንደጠየቁና በምርት ሂደት ላይ አስካሪውም ከአልኮል ነፃ የሚባለውም በአንድ አይነት ሂደት አልፎ ሲፈላም አብሮ ፈልቶ ኸምር ከሆነ በኋላ በማሽን አማካኝነት 'ነፃ' የሚባለው የአልኮል መጠኑ እንዲያንስ እንደሚደረግ ተናግረዋል፣ ይህ ደሞ 'ኸምር በራሱ ጊዜ 'ተኸሉል' እስካላረገ ወይ እስካልጠራ ድረስ ነጃሳ ወይም ሀራም መሆኑ ከተነገረው ሀዲስ ጋ እንደሚጋጭ ገልፀው፣ አልኮል ኖሮበት አይደለም ባይኖርበት እንኳ በዚ ምክኒያት ብቻ እንደሚከለከልና መራቅ እንዳለብን አሳስበዋል።
ሀፊዘሁላህ🙏
@hpsmuslimjema
*የሰዎችን ጥፋት እንደ ጌታ ሆናቹ:የራሳችሁን ጥፋት እንደ ባርያ ሆናቹ አትመልከቱ:በወንጀል የተፈተኑ ሰዎችን ስታዩ እዘኑላቸው:አሏህ ከዛ ስለጠበቃችሁም አመስግኑት"
ኢማሙ ማሊክ
@AmirelMueminin
❤️በዑመር ኢብኑ አል ኸጣብ ዘመን
ከባባድ ድርቅ ተከስቶ ነበር በዛ ወቅት
አስገራሚ ታሪክ ነው ሼር አድርጉት
@AmirelMueminin
ዑመር ቂጣ ብቻ ነበር የሚበሉትና በረሃብ ሆዳቸው ሲጮህ ለሆዳቸው《ብትጮህ ባትጮህ የተራቡት ህዝቦቼን ሳላጠግብ አትቀምስም》 ይሉት ነበር ጉድ ዑመር አሁን ያሉ መሪዎችን ቢያዩ ምን ይሉ ይሆን! ዑመር ኢብኑል ኸጣብ የሚተኙበት ጊዜ አልነበራቸውም በተቀመጡበት ማንቀላፋታቸውን የተመለከቱት ባልደረቦቻቸው <አንቱ የምእመናን መሪ ሆይ ለምን አይተኙም> ሲሏቸው እሳቸውም እንዴት እተኛለው ቀን ብተኛ የሰዎችን ሃቅ አጠፋለው ሌሊት ብተኛ ከጌታዬ ዘንድ ያለኝን አጣለው ይሉ ነበር። አንድ ቀን ዑመር ታመው ማርን እንደ መድሃኒት እንዲወስዱ ታዘዛላቸው በቤተል-ማል' ውስጥም ማር ነበረና ዑመር ከማሩ ለመጠቀም ህዝቦችን ሰበስበው 'ሜምበር' ላይ በመውጣት አስፈቀዱ ካልፈቀዳችሁልኝ አልጠቀምም በኔ ላይ ሓራም ነውና አሏቸው ሰዎችም ፈቀዱላቸው ለሳቸውም አዝነው አለቀሱ አንተ ዑመር ሆይ! ካንተ በኃላ ለሚመጡ መሪዎችን አደከምክ ይሏቸው ነበር እንደሳቸው መሆን እንደሚከብድ ስለተረዱ። ዑመር መሪ ሆነው እንደተሾሙ ሚስታቸው ወደ ቤት ሲገቡ ዑመር እያለቀሱ አገኟቸው የተፈጠረ ነገር አለን? ጠየቀቻቸው ዑመርም የነብዩ ሙሐመድ ﷺ ህዝብ ጉዳይ በጫንቃዬ ላይ ሆነ አሏቸው አሰብኩም ደሃው ፣የተራበው የታመመው የጠፋው የታረዘው የተበደለው የታሰረው ስለ ሁሉም ጌታየ እንደሚጠይቀኝ አስቤ ነው ያለቀስኩ አሉ ስልጣን ሲሰጠው ሃላፊነቴን በትክክል አልወጣ ይሆናል ብሎ የሚሰጋ ሰው እሱ ለስልጣኑ ተገቢ ሰው ነው አላህ ስራህን ይውደድልህ ያ ፋሩቅ❤️
-----------------------------------
❤️ከዑመር በኃላ የትኛውን መሪ ላሞግስ ?❤️
ይንገሩኝ
______\\\\_______________
Join በማለት ይቀላቀሉ
👇👇👇👇👇
@AmirelMueminin
🧕ሂክማ🧕
ክፍል ሀያ ሁለት
✍ኢብኑ ኢብራሂም
፡
"አንተ! የዘንድሮን ኢንትራንስ ያወጣው ኡስታዝ በድሩ ሁሴን ነው አሉህ እንዴ?" አለችኝ ሪ ያለወትሮዬ ከትምህርት መልስ "ለውጥ" የተሰኘውን መፅሐፍ ሳሎን ቁጭ ብዬ ሳነብ አይታኝ።
"ሰው እኮ ሁሌ ባለበት አይቆምም ይለወጣል። አለሽ እንጅ አንቺ ሁሌም ምላሳም ሆነሽ የምትኖሪ።" ስል ወረፍኳት።
"እስኪ ያድርግልህ! በኋላ ይሄን ምላስህን እንዳትረግም!"
"ያንች ምላስም አልተረገመ!" ስል መለስኩላት።
"የኔማ በዶክትሬት ተመርቆ ነው የተሰጠኝ! ባይሆን እስከዛሬ እንደምታነባቸው ልብወለዶች መስሎህ እንዳታሯሩጠው! በደንብ ካነበብከው እንደ ስሙ ለዋጭ መፅሐፍ ነው።"
’’ምነው ታዲያ አንች ሳትለወጭ ቀረሽ?’’
’’ምናልባት እንዳንተ ሂክማ ስላላዘዘችኝ ይሆን? ሃሃሃ’’ ብላኝ ሩጣ ወደ ውስጥ ገባች። እቺ ሙጢ እውነቷን ነበር፡፡ ትላንት ማታ በሂክማ ከተመረጡልኝ አምስት መፅሐፍቶች ውስጥ አንዱ የሆነውን መፅሐፍ ነው እያነበብኩ ያለሁት። መፅሐፉ ቤት ውስጥ ለአመታት ያህል ተገዝቶ የተቀመጠ ቢሆንም ለአፍታ እንኳን ከፍቼ አይቼው አላውቅም ነበር። አሁን ሳነበው ግን ከዚህ በፊት ባለማንበቤ ተቆጨሁ።
የቀኑ ውሎዬ ደስ የሚል ስለነበር ነው መሰለኝ መፀሐፉን በጥሩ ሙድ ነው እያነበብኩ ያለሁት። የዮኒ እናት ዮኒ በመስለሙ በመስማማቷ እና ነገ ቅዳሜ ሂክማን የማገኝበት ቀን በመሆኑ ስፈነጥዝ ነው የዋልኩት።
"ልጄ! አንተ ብቻ ልብ ግዛልኝ እንጂ የፈለከውን እምነት ብትከተል አይከፋኝም። ብቻ በየመጠጥ ቤቱ ከመንዘላዘልና ያለ እድሜህ ከሴት ጋር ከመማገጥ የሚቆጥብህ እምነት ይሁን። ደግሞ እስላሞችን ድሮውንም ቀልቤ ይወዳቸዋል። "እስላም ከዋሸ ቀኑ መሼ፤ እስላም ካበለ ቀኑ ዘነበለ!" እያልን በተረት ታማኝነታቸውን ስንመሰክር ነው ያደግነው። ለወላጆቻቸውም ጥሩ ከበሬታ አላቸው። እንደነሱ ከሆንክልኝማ በምን እድሌ!" ነበር ያሉት የየኑ እናት። የኑ የዮኒ የእስልምና ስሙ ነው። አዲሱ ስሙ የኑስ ነው። ሲቆላመጥ ደግሞ የኑ።
ሀሳቤ በዚህና በነገው የሂክማ ቀጠሮ እየተሰረቀም ቢሆን ማንበቤን ቀጥያለሁ። ነገ ሳገኛት ምን እንደማወራት ጨንቆኛል። እንደማን ሆኜ እንደምቀርባትም እንደዛው። ’’እንደ ዱሮው ሳሊም ለፍላፊ ሆኜ ልቅረባት ወይንስ እንዳሁኑ ሳሊም ጨዋ ሆኜ? እንደወንድም ልሁን ወይንስ ለፍቅር አልያም ለትዳር እንደምመኛት ሆኜ ልቅረባት? ልክ እንደ ፌስቡኩ ሁሉ በአካልም ተጫዋች ትሆን ይሆን? ወይንስ ለጨዋታ የምትከብድ አይነት ሰው ትሆን?’’ እነዚህ አሁንም ድረስ መልስ ያላገኘሁላቸው ጥያቄዎች ናቸው። ከዚህ በተጨማሪም "ቆይ ግን ካፌ ውስጥ አልያም የሆነ ቦታ አጅነቢ ከሆነች ሴት ጋር መገናኘቱ እንዴት ነው?" የሚል ሃሳብ ውልብ ብሎ ልቤን ይረብሸኛል። ነገር ግን "ምንስ ቢሆን ከኔ በላይ እሷን ሳያሳስባት አይቀርም። ይህ ሃሳብ ከኔ በላይ ሊያስጨንቃት የሚችለው እሷኑ ነው። የሆነ ደሊል ቢኖራት እንጅ በባዶ ሜዳ እንዳገኛት አትፈቅም ነበር!" ስል ልቤን ለማረጋጋት እሞክራለሁ። አንዳንዴ በእውቀትም ይሁን በኢማን ይበልጡናል ብለን ባመንባቸው ሰዎች ላይ እምነታችን የጠና ነው። ግልፅ የሆነ ስህተት ቢፈፅሙ እንኳን "የሆነ ነገር ቢኖራቸው እንጅ ከመሬት ተነስተው ይሄን አያደርጉም!" ስንል ምክኒያት እንሰጣለን። አንዳንዴም ያንን ምክኒያት ሳናጣራ በጭፍን ከጥፋታቸው የምንቋደስበት አጋጣሚዎችም ብዙ ናቸው። ነገር ግን እንዲህ ያለ ደረጃ ላይ ያሉ ሰዎች ይሄንን ጉዳይ ልብ ያሉ አይመስለኝም። ለዛም ነው ታዋቂ ሰዎች በቸልተኝነት በሚፈፅሟቸው ስህተቶች ምክኒያት ተራው ማህበረሰብ የሃጥያት አረንቋ ውስጥ ሲዘፈቅ የሚስተዋለው።
ንባብ ላይ ፈጣን የምባል አይነት ነኝ። በተለይ የመፀሐፉ ይዘትና ሃሳብ ከጣመኝ በሰዓታት ውስጥ ብዙ ገፆችን ማንበብ እችላለሁ። ከሃሳቤ ጋር እየታገልኩ የማነበው መፀሐፍ እንኳ ይሄው አንድ ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ወደ 40 ገፅ ደርሶልኛል። ቢያንስ የወሬ አጀንዳ ቢጠፋ እንኳን በመፀሐፉ ዙሪያ ከሷ ጋር ለመወያየት ስላሰብኩ ዛሬ ማታ ቴሌብዥን ከመመልከት ይልቅ መፀሐፉን እያነበብኩ ለማምሸት ወስኛለሁ።
መግሪብ ሊደርስ አካባቢ አባቢ ጥርስ በጥርስ ሆኖ መጣ። እንዲህ ያስፈነጠዘው ከስራው ጎን ለጎን በረፍት ጊዜው የሚሰራው የግል ጦማር ድረ ገፁ ተከፋይ የሚያደርገውን Adsense ስላገኘ ነው። ድረ ገፁ ከወቅታዊ መረጃዎች በተጨማሪ ሀይማኖታዊ መልዕክቶችንና ስነ ፅሁፎችን ስለሚሰጥ ብዙ ተከታታዮች አሉት። ምናልባት በቀጣይ ወራቶች ከድረ ገፁ የሚያገኘው ክፍያ የወር ደሞዙን ሳያስንቅ አይቀርም። እንግዲህ ዛሬ ደስታ የበዛበት ቀን መሆኑ ነው። በተለይ ደግሞ ለኔ።
"ነገ የደስ ደስ ምሳ ውጭ እጋብዛችኋለሁ ከወዲሁ ተዘጋጁ!" አለን አባቢ ላፕቶፑን ከተከሻው ላይ አውርዶ ለማሚ እየሰጠ። ሪ ደስ ብሏት አባቢ ላይ ተጠመጠመችበት። እኔ ደስ ቢለኝም ከሂክማ ቀጠሮ ጋር እንዳይጋጭብኝ ስለሰጋሁ ግራ ተጋብቼ ዝም አልኩ።
"ምነው ሳሊሜ ቅር ያለህ ትመስላለህ?" አለኝ አባቢ ሁኔታዬ ግራ አጋብቶት። ከዚህ በፊት እኔ ነበርኩ ውጭ ካልጋበዝከን እያልኩ የማስቸግረው። ዛሬ አባቢ ልጋብዛችሁ ሲል ስቀዛቀዝበት ገርሞታል።
"ኧረ ምንም በጣም ደስ ስላለኝ ነው።" ብዬ ወደ ንባቤ ገባሁ። እሱም ሳያስጨንቀኝ ውዱዕ ሊያደርግና ልብሱን ሊቀይር ወደ ጓዳ ገባ።
"በእውነት በጣም ደስ የሚል ነገር ነው የነገርከኝ!" አለችኝ ሂክማ ስለ የኑ ስነግራት።
"ብታይ የኔን ጀለብያ ለብሶ ጁሙዓ ሲሰግድ ብታይው የቆየ ደረሳ እንጅ አዲስ ሰለምቴ አይመስልም።"
"ሲጀመር እኛ በራሳችን ጊዜ ከመስመሩ ርቀን እንጅ ድሮውንም እኮ የሰው ልጅ መሰረቱ ኢስላም ነው። ለማንኛውም ራሳችሁን ለፈተና አዘጋጁ!"
"ለየትኛው ፈተና? ለኢንትራንስ ከሆነ ከሚገባው በላይ ነው እየተዘጋጀን ያለነው።"
"አይ አላህ ለሚፈትናችሁ ፈተና።" ብላ የአላህ ባሮች አምነናል ካሉ በኋላ አላህ የእምነት ደረጃቸውን ሊፈትን ብዙ ፈተናዎችን እንደሚያቀርብ የሚጠቅሰውን የቁርዓን አንቀፅ ጠቅሳ፤ ብዙ ፈተናዎችን መወጣት በቻሉ ነብያቶችና ደጋጎች ታሪክ አሳረገችልኝ።
"አንተም በቅርቡ አንድ ትልቅ ፈተና ሳያጋጥምህ አይቀርም!" አለችኝ።
"የምን ፈተና ነው? አንችስ በምን ልታውቂ ቻልሽ?" ስል ግራ ተጋብቼ ጠየቅኳት።
"ሁሉንም ነገር ሰዓቱ ሲደርስ ታውቀዋለህ! ባይሆን ልብህን ጠንከር አድርግ።"
"አታስቢ! ላመንኩበት ነገር አንገቴን የምሰጥ ሰው ነኝ። አይደለም ለፈጣሪዬ ለስንቱ ውዳቂ ተግባር በፅናት ስጋፈጥ ነው ያደግኩት።" ስል መለስኩላት።
"እንዳልከው እንዲሆን ምኞቴ ነው።"
"አትጠራጠሪ! ነገ ስንት ሰዓት ነው የምንገናኘው? ቦታውስ?" ስል ጠየቅኳት። ከምሳ ሰዓት ቀደም ብሎ አልያም ከዛ በኋላ እንዲሆን እየተመኘሁ።
"ላሳየኸው ለውጥ ምሳ ልጋብዝህ ነው ያሰብኩት።"
"ከምሳ ሰዓት ውጭ ማድረግ አይቻልም?" አልኳት በውስጤ እሽ እንድትለኝ እየተማፀንኩ።
"አይዞህ ጋባዧ እኔ ስለሆንኩ አትጨነቅ! ኪኪኪ"
"እንደዛ ማሰቤ እንኳን አይደለም። ነገ ከሌላ ሰው ጋር ምሳ ግብዣ ስላለኝ ነው!" አልኳት በደፈናው። ከቤተሰቦቼጋ ብላት ከዛ ሰዓት ውጭ የማይመቻት ከሆነ የቤተሰብህን ግብዣ አስቀድም ብላ ሃሳቧን እንዳትቀይርብኝ ስለሰጋሁ ነው ጋባዦቼን ያልነገርኳት።
"ታዲያ ምን ችግራለው ወደ ቀጣይ ሳምንት እናዘዋውረዋ!" ስትል የፈራሁትን ነገር ተናገረች። ይሄ ሳምንት እንዴት እንደራቀብኝ እኔ ነኝ የማውቀው። እንኳንስ ሌላ ሳምንት ልጠብቅ የዛሬዋን ሌሊት እንኳን ማሳለፍ አልያም ማሳጠር ብችል ደስታውን
🌹 ዐሊይ በሌለበት ምድር ላይ መኖር ምንኛ ከፋ كرم الله وجهك
🍂 በአንድ ወቅት ሰይዲና ሁዞይፋ ሰይድ ኡመር ወዳሉበት ይገባሉ። ኡመርም ••ሰላም አለይኩም እንዴት አደርክ ሁዞይፋ •• ይላቸዋል። ግራ የሚያጋባውን ተከታዩን መልስ ይመልሱለታል
🍂أصبحت أحب الفتنة
ፊትናን የምወድ ሆኜ አንግቻለው ያ ኡመር
🍂وأصبحت أبغض الحق
እውነትን የምጠላ
🍂وأصلي من غير وضوء
ያለ ዉዱእ የምሰግድ
🍂ولي في الأرض ما ليس لله في السماء
አሏህ በሰማይ የሌለውን እኔ በምድር ኖሮኝ አንግቻለሁ።
ሰይድ ኡመር ይህንን መልስ ሲሰሙ ፊታቸው በንዴት ተቀያየረ።ንዴታቸው ጦፎ እንዳለ ሰይዲ ዐሊይ አል አክረም ወደነኡመር ክፍል ዘለቁ።
•• ምነው ያ ኡመር ፊትህ ልክ አይደለምሳ?••ቢላቸው ከሁዞይፋ የሰሙትን አስደንጋጭ መልስ ነገሩት። 💗የሙስጦፋው መሳይ 💗የፋጢማ ሙሽራ ቀጣዩን መለሱለት
••ያ ኡመር አትቆጣ
🍂ፊትናን የምወድ ሆኜ አንግቻለው ማለቱ ገንዘብና ልጆችን እወዳለሁ ማለቱ ነው። ጌታችን አሏህ ያለውን በመንተራስ
وَٱعْلَمُوٓا۟ أَنَّمَآ أَمْوَٰلُكُمْ وَأَوْلَٰدُكُمْ فِتْنَةٌۭ وَأَنَّ ٱللَّهَ عِندَهُۥٓ أَجْرٌ عَظِيمٌۭ
ገንዘቦቻችሁና ልጆቻችሁም ፈተና ብቻ መኾናቸውንና አላህም እሱ ዘንድ ታላቅ ምንዳ ያለው መኾኑን እወቁ፡፡(አንፋል 28)
🍂 ሓቅን(እውነትን) የምጠላ ሆኜ አነጋሁ ማለቱ ••የማይቀረውን ሞትን የምጠላ ሆኜ ማለቱ ነው•• ያ ኡመር ማንስ ሞትን ይወድና?
🍂•ያለ ዉዱእ እሰግዳለሁ• ያለው ረሱላችን ላይ ሶለዋትን አወርዳለሁ ማለት ነው።ሶለዋት ደግሞ ያለ ዉዱእ ያለ ቂብላ የሚሰገድ ሶላት ነው(ሶሉ አለይሂ ብሏልና)
🍂•ለአሏህ በሰማይ የሌለውን እኔ በምድር አለኝ ማለቱ• ደግሞ ሚስት እና ልጆች አሉኝ ለማለት ነው። ጌታችን አሏህ ከነዚህ ነገሮች የጠራ ነውና።
🌺ስይድ ኡመር ይህን የጥበብ ቃል ሲሰሙ ነበር ❕ዐሊይ የሌለባት ምድር ላይ መኖር ምንኛ ከፋ❕ ብለው
ንዴታቸውን ወደ አጀባ የቀየሩት።
📚ክስተቱን ታላቁ ሙፈሲር ኢማም አሻእራዊይ ከትበውታል።
❤️ ውዱ ወንድሜ ውዷ እህቴ እኛም በእውቀት በሚበልጡን ሰዎች ላይ የቋንቋ ግድፈት እና ጥፋቶች ከመፈለግ ይልቅ ከልሳናቸው ላይ ጥበብን እንቅዳ ።ጥበብን የተሰጠ የመልካም ነገርን ድልብ ተሰጥቷልና።ሰላም አለይኩም 🌹
❤️🌹 اللهم صل على محمد وعلى آله وصحبه أجمعين
@AmirelMueminin
ት ትክክለኛ ቦታ መስጂድ እንደሆነ ነው የሚሰማኝ።" ሲል ከልቡ መሆኑን አረጋገጠልን።
"እናትህስ? ዝም የምትልህ ይመስልሃል?" ሃሚ ጠየቀው።
"በየቢራ ቤቱ ሳውደለድል ምንም ያላለች ወደ ተፈጥሮዬና ወደ አምላኬ ስመለስ የሚከፋት አይመስለኝም። ቢከፋትም እስካመንኩበት ድረስ ከማድረግ የሚያግደኝ ምድራዊ ሀይል አይኖርም!" አለን። የማይበት አቋም የሱ እስከማይመስለኝ ድረስ ተገረምኩበት።
.
.
ይቀጥላል!
@AmirelMueminin
እንኳን እንደማይፈቅደው ነው። ስለዚህ አንተም ሀይማኖትህ እንድትሆን የሚያዝህን አይነት ጨዋ ሰው ለመሆን ሞክር። እስኪ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ በየሰው ቤቱ ልብስና እንጀራ በመጋገር እየተንከራተተች ላሳደገችህ እናትህ ሸክም ነው ወይስ ሸክሟን የምታቀልላት፣ ህልሟን አሳክተህ አለሟን የምታሳያት ልጅ ነው መሆን ያለብህ? በርግጠኝነት እናትህ አሁንም ድረስ እጇን ወደ አምላኳ በዘረጋች ቁጥር አንተ ልብ እንድትገዛላት እንደምትማፀን አልጠራጠርም። ስለሆነም እኔ እየጠራሁህ ያለሁት ወላጆቻችን እንድንሆንላቸው የሚፈልጉት አይነት ሰው እንድንሆንላቸው ነው።" ስል መለስኩለት።
"በቃ እንዳስብበት ጊዜ ስጡኝ።" አለን።
"ይቻላል። ባይሆን ግን እስካሁን ያጠፋነው ጊዜ ቀላል የማይባል እንደመሆኑ ለማሰብ ብዙ ጊዜ እንደማይፈጅብህ ተስፋ አደርጋለሁ።" አልኩት። ይሄን የምናወራው የጠዋቱን ክፍለ ጊዜ ከመግባታችን በፊት ባለችው ክፍት ጊዜ ስለነበር ወደ ክላስ እንድንገባ የምታዘው ደዎል ስለሰማን ወደዬክላሳችን ተበታተን።
.
.
.
ይቀጥላል!
@AmirelMueminin
ቤተል መስጂድ ውስጥ ቤተክርስቲያን ካልሰራን በሚመስል መልኩ በፌደራል ታጅበው በመረበሽ ላይ ይገኛሉ።
ሁል ጊዜ ለሀገርና ለሰላም ፀር መሆን ግን አይከብድም?????
ከየበታችነት ስሜት የሚወጡት መች ነው!!!
〰〰〰〰〰〰〰〰〰
@USTAZ_ABUHAYDER
@USTAZ_ABUHAYDER
"አዲስአበባን እንደ አክሱም"
እውን መስጂዶች የአዲስ አበባ መሬትን ወረዋል?
በመስገጃ ቦታ ጥያቄዎች ረገድ የአማኞች እና የየሐይማኖቶች እኩልነት አለን?
ለመስጂዶች የደም ግብር እስከመቼ?
ልዩ ዘጋቢ ፊልም ዛሬ ጥር 10/2013 በአምስት ኢስላማዊ ቻናሎች (ዛውየ ቲቪ ፣ ሀሚልተን ቲቪ፣ ኑረልሁዳ ፣ቢ ኤስ ቲ እና ሚንበር ቲቪ) በተመሳሳይ ሰዓት ምሽት 3፡00 ይከታተሉ፡፡
ዛውያ ቲቪ
ተግባራ ዳዕዋ!
🧕ሂክማ🧕
ክፍል ሀያ አራት
✍ኢብኑ ኢብራሂም
"ሂክማን እየፈለክ ነዋ?" ስትል ጠየቀችኝ ሪ። ለአፍታ ያህል ቤተሰቦቼ መሃል መሆኔን ዘንግቼ፤
"አዎ የታለች?" ስል ጠየቅኩና በሁኔታዬ መልሼ ሀፍረት ተሰማኝ።
"እዚሁ እኛ መሃል ናት።" ሲል ተናገረ እስካሁን ዝም ብሎ የቆየው ሀምዱ። እየሆነ ያለው ነገር እንቆቅልሽ ነው የሆነብኝ። የሆነ የማይፈታ ደረቅ እንቆቅልሽ። በቁጣ ሀምዱ ላይ አይኔን ጎልጉዬ
"እኮ የታለች?" ስል ጠየቅኩት። ማሚ ያ ስታመም የማይባት እውነተኛ ገፅታዋ ፊቷን ተቆጣጥሮት ነበር። ስጋት ገብቷት በስስት ታዬኛለች። እንዲያ ከተናደድኩ በኋላ በሁኔታዬ መልሼ ተሸማቀቅኩ።
"ሳሊሜ! ሂክማ ማለት አንተ እንደምታስባት አንዲት ሴት ሳትሆን የቤተሰቦችህ ድምር ውጤት ናት።" ማሚ ነበረች የመለሰችልኝ።
"አዎ! ሂክማ የብዕር ስም እንጅ የአንዲት ግለሰብ መጠሪያ አይደለም።" አባቢ ሊያስረዳኝ ሞከረ።
"ሂክማ ማለት እኛ ነን። ሂክማ አንተን ለማስተካከል የፈጠርናት ገፀ ባህሪ ስያሜ ስትሆን..." ሀምዱን አላስጨረስኩትም ልክ ስርጭት እንደሌለው የቴሌቪዥን ጣቢያ ፂውውውው እያለ የሚጮህብኝን ጭንቅላቴን ይዤ ተነስቼ ወጣሁ። እኔ በተነሳሁበት ሰዓት እነ አባቢ ያዘዙት ማዕድ ደርሶ እየቀረበ ነበር።
"የት ነው የምትሄደው? ምሳው እኮ ደርሷል ና ብላ እንጂ!" የሚለው ያባቢ ድምፅ ይሰማኛል። እኔ ግን ጆሮዬን ለመስጠት ፍቃደኛ ሳልሆን ሆቴሉን ለቅቄ ወጣሁ። ቅድም ስገባ ግራ ተጋብቶ ሲመለከተኝ የነበረው ጥበቃ ስወጣም ግራ ተጋብቶ እያዬኝ ነበር።
የሆቴሉን ሰፊ በር እንደወጣሁ የምሄድበት ግራ ገብቶኝ ቆምኩ። ከሆቴሉ አቅራቢያ ያለው መስጂድ አዛን እያሰማ እንደሆነ የተገነዘብኩት አዛኑ ሊገባደድ ገደማ ነበር። ወደ መስጂዱ ለመሄድ እግሬን ካነሳሁ በኋላ እነ አባቢ ተመግበው ሲጨርሱ ወደዚሁ መስጂድ እንደሚመጡ ስለገመትኩ እነሱን ላለማግኘት ታክሲ ውስጥ ገብቼ ወደ ሌላ መስጂድ አመራሁ።
ዙሁርን ከራሴ ጋር ሳልሆን ሰግጄ ወጣሁ። ስወጣ ወደ የት እንደምሄድ አላውቅም ነበር። ዙሪያዬን ስቃኝ ከመስጂዱ ፊት ለፊት ካፌ አስተዋልኩና ወደዛው አመራሁ። የካፌው አንድ ጥግ ተቀምጬ እየሆነ ያለውን በዝግታ ማሰብ ጀመርኩ። የሃሳቤን መልህቅ ከሂክማ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ወደተገናኘንበት ቀን ላይ ነበር የጣልኩት። የለጠፍኩት ፎቶዬ ላይ ሆነ ተብሎ እኔን ለማጥመድ ኮመንት እደፃፉ ገባኝ። ስለ ራሷ ስጠይቃት
"ሂክማ ማለት የራሷ የሆነ ፎቶ የሌላት ናት።" የሚለው ምላሿ የገባኝ አሁን ነው። እንዴት የውስጥና የውጭ ሚስጥሬን ለማወቅ እንደቻለች ግራ ስጋባበት የነበረው እንቆቅልሽ ቢዘገይም አሁን ተፈታልኝ። ከሂክማ ጋር ማውራት በጀመርኩባቸው የመጀመሪያ ቀናቶች ሪ ለምን እነአባቢጋ ማደር እንደፈለገችም ገና አሁን ፍንትው ብሎ ታዬኝ። ለምን ግጥሞቿ ከማሚ ጋር እንደሚመሳሰልብኝም እንደዛው። "ወይኔ ሳሊም!" ስል የካፌውን ጠረጴዛ በቡጢ ነረትኩት። አስተናጋጇ ገላመጠችኝና ጠረዼዛውን በቡጢ ስመታ ፊት ለፊቴ ከተቀመጠው ማኪያቶ ላይ ወደ ጠረዼዛው የተደፋውን በፎጣ ወልውላልኝ ሄደች። በራሴ ቀሽምነት በጣም ተናድጃለሁ። ቅድም በራሴ ላይ ያሟረትኩት ራስ ምታት "ከጠራሃኝ አይቀር" ብሎ ነው መሰል ጭንቅላቴን በሀይል ሰቅዞ ይዞኛል። በዚሁ ሁኔታ ላይ እያለሁ የኑ ደወለልኝ።
"አንተ በቃ የሂክማ ግብዣ አጠገበህና እረሳህና? ቆይ ከእሷ እንደተለየህ ወዲያውን ልትደውልልን አይደል የተነጋገርነው?" አለኝ። ስለ ሂክማ ለመስማት በቋመጠ ስሜት ውስጥ ሆኖ።
"ተወኝ ባክህ ጉድ ሆኛለሁ።" ስል ቀዝቀዝ ያለ ምላሽ ሰጠሁት።
"ምነው ፊቷ አስቀያሚ ሆኖ ጠበቀህ? ነው ወይስ ፊልም ላይ እንደምናየው ባልቴት ሆና አገኘሃት? ሃሃሃሃ"
"አሁን ስልኩን ትዘጋልኝ?" ስል ጮህኩበት።
"ቆይ የት ነው ያለኸው? እኔና ሃሚ እኮ አንድ ላይ ሆነን እስክትደውል እየጠበቅን ነበር።" አለኝ ደንገጥ ብሎ። ያለሁበትን ነግሬያቸው ተመልሼ ወደ ሃሳቤ ማዕበል ሰመጥኩ።
ከፊቴ ያለውን ማኪያቶ ዘንግቼዋለሁ። በዚህ ሰዓት ማጬስና መጠጣት ነው ያማረኝ። ነገር ግን አሁን የተላበስኩት ስብዕና ይሄን ለማድረግ አልፈቀደልኝም። የቀዘቀዘውን ማኪያቶ አንስቼ በአንድ ትንፋሽ ጨለጥኩት።
"ሳሊሜ ብዙ ጊዜ አባቴ 'አላህ የሚወደውን ነው የሚፈትነው!' ሲል እሰማዋለሁ። ምናልባት በትክክል የሱን ፊት ፈልገህ የቶበትክ መሆኑን ሊፈትንህ ፈልጎ ይሆናል!" አለኝ ሃሚ። እነ የኑ ብዙም ሳይቆዩ ነበር ያለሁበት ካፌ መድረስ የቻልሉት። ሃሚ ስለ ፈተና ሲያወራ ማታ ሂክማ "አንተም በቅርቡ አንድ ትልቅ ፈተና ሳያጋጥምህ አይቀርም!" ያለችኝ ትዝ አለኝ። "እውነትም ትልቅ ፈተና!" አልኩኝ ጮክ ብዬ። ግራ ተጋብተው ሲያዩኝ ሂክማ ያለችኝን ነገርኳቸው። (የሚገርመው አሁንም ድረስ ሴት እንደሆነች አድርጌ ነው የማወራው! ሃሃሃ)
"ደግሞም ልታዝን ሳይሆን ደስ ሊልህ ነበር የሚገባው።" አለ የኑ።
"እንዴት ነው ደስ ሊለኝ የሚገባው?" ስል ጠየቅኩት። የሃሚም ጥያቄ ነበር መሰል እሱም የየኑን ምላሽ ለመስማት ጆሮውን አቁሟል።
"እስኪ አስበው። ሂክማ የጠበቅካት አይነት ሴት ሳትሆን ያረጠች ሽማግሌ ብትሆን ኑሮስ? አልያም ደግሞ ቀልብ የሚሰርቅ ውበት ኖሯት ባለ ትዳር ብትሆንስ? ወይም መልከ ጥፉ አልያም አካለ ጎደሎ ሆና ብታገኛት ኖሮስ? አሁን ከገጠመህ የበለጠ የምታዝን አይመስልህም? አሁን ግን ሂክማ ያንተው ናት። አዎ! ሂካማ ማለት እናትህ፣ አባትህ፣ እህትህና ስላንተ የሚጨነቅልህ ዘመድህ ናት። አየህ በዚህ መንገድ ካልሆነ በቀር 100% ሂክማ ያንተ ልትሆን የምትችልበት አጋጣሚ ጠባብ ነው።" ሲል የልቤን እብጠት ያስተነፈሰልኝን ንግግር ተናገረኝ። ሃሚ ተደንቆ አንገቱን እየወዘወዘ በሃሳቡ መስማማቱን እየገለፀ ነበር ሲያዳምጥ የነበረው።
የኑ ልክ ነበር። አሁን ከዘረዘራቸው አንዷ ብትሆን ኑሮ እጅጉን እንደማዝን ጥርጥር የለውም። ለመጀመሪያ ጊዜ የቤተሰቦቼን ተግባር በአወንታዊ መልኩ ማሰብ ጀመርኩ። ከስራ ደክሞ ውሎ ሌሊቱን ማረፍ ሲገባ ከኔ ጋር ሲዳረቅ የሚያመሸው አባቢ አንጀቴን በላኝ፣ ከህፃንነቴ ጀምራ ወገቧ እስኪጎብጥ ድረስ አንከባክባ ያሳደገችኝ ማሚ ቀን ደፋ ቀና ስትል የዋለችው እንሷት ለኔ ስትል የማትወደው የስልክ እስክሪን ላይ አፍጥጣ ማምሸቷን ሳስበው አንጀቴ ተላወሰብኝ፣ ከንባብ በኋላ አንዲት ደቂቃ ማምሸት የማትወደው ሪ ለኔ ስትል እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ ከአልጋዋ ተለይታ ማምሸቷን ስገነዘብ ሆዴ ተተራመሰብኝ። የፊቴን መለዋወጥ የተገነዘቡት እነ የኑ ደንግጠው፤
"ምነው አመመህ እንዴ?" ሲሉ ተጨንቀው ጠየቁኝ። እንዳላመመኝ ነገርኳቸው።
"የኑ እንዳለው በቤተሰቦችህ ልታዝን ሳይሆን ልትኮራባቸው ነው የሚገባው። ድርጊታቸው አንተ ወደ አላህ እንድትመለስላቸው ያላቸውን ፅኑ ጉጉትን ነው የሚያሳየው። ደግሞም ተሳክቶላቸዋል። ካንተም አልፈው እኛም ጭምር እንድንስተካከል ሰበብ ሆነውናል።" አለ ሃሚ።
"አሁንስ ወደ ቤት መመለስ ያለብህ አይመስልህም? ይሄኔ ተጨንቀው እየጠበቁህ ይሆናል። መልካም አስበው የፈፀሙትን ቀና ተግባር፤ ያልሆነ ነገር ፈፅመህ እንዲፀፀቱበት እንዳታረጋቸው።" ሲል የኑ አከለልኝ።
"እንሂድ!" አልኳቸው ከመቀመጫዬ ድንገት ተነስቼ። ሂሳብ ከፈልንና ተያይዘን ወደ ቤት ሄድን።...
የመጨረሻው ክፍል ነገ ይቀጥላል!😔
.
.
@AmirelMueminin
ኦዚል በቻይና ውስጥ ለሚገኙ ሙስሊሞች ድምፁን ስላሰማ ቻይና በሀገሯ ውስጥ የኦዚል ማልያን ማድረግ ከልክላለች።ኮሜንታተሮችም ኳስ ሲያሰተላልፉ የኦዚልን ስም መጥራት አይፈቀድላቸውም።
አሏህ በሄድክበት ሁሉ ይከተልህ አቦ!❤
ሲዋሹ እኮ ዓይናቸውን በጨው አጥበው ነው‼
=============================
«አል-አክሱም፣ አል-ላሊበላ፣ አል-ቁልቢ…" – የሙስሊሞች ደሴት¡
||
✍አንዱ (ስሙን መጥራት ይባስ ማስተዋወቅ እንዳይሆንብኝ በመስጋት ነው!) ትናንት ቤተል የተከሰተውን ነገር ለማጣራት ዛሬ ጠዋት ወደ ቤተል በማቅናት በአካባቢው ያሉ ሰዎችን እንዳነጋገረና ያገኘው እውነታ ፌስቡክ ላይ ከሚራገበው በተቃራኒ እንደሆነ በመናገር ከአፍታ በኋላ ዝርዝሩን ጠብቁኝ ይላል ለተከታዮቹ!
ከዚያ በጉጉት በተጠበቀው ፖስቱ ላይ እንዲህ አለ፦
«ሙስሊሞች ቤተልን እንደ መካና መዲና ማድረግ ነው የሚፈልጉት።
"ቤተል" የሚለው ስያሜ ከቤተል ሆስፒታል የተወሰደ ነው።
ሙስሊሞች የዚህን ሆስፒታል ባለቤት ቤተልን መካና መዲና ለማድረግ በማሰብ "2 ሚሊዮን ብር እንስጥህና የሆስፒታልህን ስም "አል-ቤተል" በለው ብለው ለምነውት ነበር!» አሉኝ ብሎ ጻፈ።
ቤተልን ለማስለም "አል" የሚል ቅጥያ በማስጨመር "አል-ቤተል" ብሎ ስያሜ መስጠት¡
ለዚህም ሲባል 2 ሚሊዮን ጉቦ ተሰጥቶና ተለምኖ¡
ደግሞ አለመሳካቱ¡
Inferiority complex at the tip‼
እንግዲህማ እያንዳንዱን ቦታ "አል" እየጨመርን ማስለም ነው።
አክሱምንም "አል-አክሱም" ብለን እናስልም!
ያ ሰላላላም‼
"ጅል አይሙት፤ እንዲያጫውት!" አሉ።
አንዳንድ ጊዜ እንዲህ አይነት ሰውማ አይጥፋ¡
በማን እንስቃለን?! ማለቴ እንሳቀቃለን?¡
ከዋሹ አይቀር እንዲህ በሰፊው መቀደድ ነው።
ለመሆኑ «አምላክ ተወለደ‼» ከሚለው አስተሳሰብ በላይ ትልቅ ውሸትና ቅጥፈት የለም!
ሰዎቹ ግን ገራሚ ናቸው።
(በነገራችን ላይ ይህን ብሎ የጻፈው ግለሰብ ተራ የፌስቡክ ተጠቃሚ እንዳይመስላችሁ!
አሁን ግን ሙስሊሞች "አል" እያሉ ሙድ የያዙበት ጊዜ ፖስቱን አጥፍቶታል።)
#አል_Challenge ጀምረናል
😂😂😂
@AmirelMueminin
◌መልካም ጓደኛ💛
💙ሁለት ወጣት ጓደኛሞች ከእላታት አንድ ቀን አብረው ጉዞ ላይ ሳሉ በጫወታቸው መካከል ትንሽ አለመግባባት ተፈጠረና ሳያስቡት አመረሩ፣ይህም ወደ እጅ መነሳሳት ደረጃ ደረሰ፣ከዝያም አንዱ ቀድሞ በፍጥነት ሌላኛውን ይመተዋል ከዝያም ተመቺው መዳጁ ወደቀ፣ ከወደቀበትም ተነሳና አፀፋውን ሳይመልስ ቀረ መቺውም ተፀፀተ ነገር ግን ይቅርታ አልጠየቀም፣ አቧራውን እያራገፈ ተነሳና ወደ መሬት አጎንብሶ አፈር ላይ ጓደኛዬ መታኝ ብሎ ፃፈ፣ ሳይነጋገሩ በመኮራረፍ ጉዟቸውን ቀጠሉ የድካም ስሜት ሲሰማቸው ውሃ እየተጎነጩ፣እያረፉ በመሄድ ላይ ሳሉ ቅድም የተመታው ልጅ የውሃ እቃው ባዶ ስለነበረች ውሃ ተጠማ ፣ጓደኛውም ስሜቱን በመረዳት የራሱን ውሃ ሰጠው ደስ ብሎት ተቀብሎ ጠጣ ከዝያም ዘወር አለና ትልቅ የማይንቀሳቀስ ድንጋይ ላይ ጓደኛዬ አዳነኝ ብሎ ፃፈ። ጓደኛው በጣም ተገረመና "ቅድም ስመታህ አሸዋ(አቧራ) ላይ ፃፍክ፣አሁን ውሃ ሳጠጣህ ድነጋይ ላይ ፃፍክ ለምንድን ነው ይሄን የምታደርገው? " በማለት ጠየቀው ፣እሱም "ቅድም ክፋት ፈፀምክብኝ አሸዋ ላይ ፃፍኩት ንፋስ ከደቂቃዎች በኋላ ያጠፈዋል፣ ሁለተኛው ላይ መልካም ዋልክልኝ ድንጋይ ላይ ሁሌ እንዲቆይ ፃፍኩት" ብሎ መለሰለት።
@AmirelMueminin
. ከሰለፎች አንዱ
=> ከዲንህ ጋር እንዴት ነህ?!"
ተብሎ ሲጠየቅ…
=> በኃጢአቴ እየቀደድኩት በኢስቲግፋር
እየሰፋሁት አለሁ!» አላቸው።
Join us 👇
@AmirelMueminin
ባልቻልኩት።
አይ በቃ የኔውን ቀጠሮ ወደ ነገ መለወጥ ስለምችል ያንቺ ግብዣ ይቅደም።"
"መርሃባ! እንደዛ ከሆነ ነገ የምንገናኝበትን ሆቴል በቴክስት አሳውቅሃለው።" ብላኝ ተሰናበተችኝ። ስልኬን እንዳልተቀበለችኝ ያወቅኩት ከወጣች በኋላ ነበር። ምናልባት አስታውሳ ድጋሚ ኦንላይን ከገባች ብዬ ብጠብቃትም ተመልሳ አልገባችም። በመጨረሻም ቁጥሬን አስቀምጬላት ወጣሁ።
.
.
ይቀጥላል!
@AmirelMueminin
🧕ሂክማ🧕
ክፍል ሃያ አንድ
✍ኢብኑ ኢብራሂም
"እንግዲያውስ ሰባት ሰዓት ላይ ወደ መስጂድ ስንሄድ አብረኸን ትሄዳለህ!" አልኩት። ወላሂ! እኔ ለማጥፋትና ለማበላሸት እንጅ እንዳሁኑ በዙሪያዬ ያሉትን ለመለወጥ ሰበብ መሆን መቻሌን አላውቅም ነበር። ምናለ ቀን ላይ ሂክማን ኦንላይን የማገኛት በሆነና የዮኒን ነገር በነገርኳት። ምናለ ስልኳን ሰጥታኝ በነበረና ደውዬ የጥረቷ ፍሬ እንዳፈራ ባወቀች።
በደስታ እንደሰከርኩ ወደ ክፍላችን ገባን። ረፍት ላይ ዮኒን እና ሃሚን አንድ ላይ ትቻቸው የቤት ስራዬን ለመወጣት ህይወቷን ወዳመሰቃቀልኩባት ፌሩዛ ሄድኩ። ፌሩዛ ከሁለት ጓደኞቿ መሃል ተቀምጣ እየተጫወተች ነበር። ላናግራት እንደምፈልግ ነግሬ ነጥዬ ወሰድኳትና የክላሶች መወጣጫ ደረጃ ላይ ተቀመጥን። የፈለግኳት ድጋሚ እሷ ጋ መሆን ፈልጌ ሳይመስላት አልቀረም መሰል ፊቷ ደስታ በደስታ ሆኗል።
"ፌሩ! ድንገት ወደ ህይወትሽ ጣልቃ ገብቼ ዛቢያሽን እንዳመሰቃቀልኩት የገባኝ አሁን ነው። አብረሽኝ በነበርሽባቸው ጊዜያቶች ውስጥ ለኔ ያለሽን እውነተኛ ፍቅር መረዳት ችያለሁ። በራቅኩሽም ጊዜ ጉዳትሽ ጥልቅ መሆኑን ለመረዳት ማስረጃ መጥቀስ አያስፈልግም። አሁንም የፈለግኩሽ በኔ ምክኒያት ለተፈጠረብሽ ቀውስ ሁሉ ይቅርታሽን እንድትቸሪኝ በመሻት ነው። ምናልባትም ቁስልሽኝ የሚያጠግግ ቅጣት ካለም ለመቀጣት ዝግጁ ነኝ።" አልኳት።
"ሳሊሜ ለኔ ድጋሚ ወደ ህይወቴ መመለስህ ካሳዬም ደስታዬም ነው። ባይሆን ድጋሚ እንደማትርቀኝ ቃል ግባልኝ።" አለችኝ ቀይ ፊቷ ላይ ውስጣዊ ሀሴት እየተንፀባረቀበት። ጥርጣሬዬ ልክ ነበር። አሁን እያዋራኋት ያለሁት ይቅርታ አድርጋልኝ የጀመርነውን ፍቅር ካቆምንበት እንድንቀጥል እንደፈለኩ አድርጋ ነው እያሰበች ያለችው። ከሁሉም የገረመኝ ከዚህ በፊት ቃሌን አጥፌ ያደማሁት ልቧ በድጋሚ ቃሌን ሊያምን አፈር ልሶ መነሳቱ ነበር።
"ፌሩ ባሁኑ ይቅርታ እየጠየኩ ያለሁት አንችን ብቻ ሳይሆን ከፈጣሪዬ ጀምሬ ሁሉንም የበደልኳቸውን ሰዎች ጭምር ነው። እኔ ወደ ፈጣሪዬ ፊቴን አዙሪያለሁ። በአላህ ፍቃድ ከዚህ በኋላ ልቧን የምሰብርባት አንድም ሴት አትኖርም! ወደ በፊቱ ማንነቴም ፈፅሞ ለመመለስ አልሻም። የፈጣሪዬን ይቅርታ በመጠባበቅ ላይ ነኝ። አንችም ላደረስኩብሽ በደል ይቅር ብለሽኝ ከህሊና ፀፀት ብታተርፊኝ ምኞቴ ነው።" አልኳት። የጠበቀችውን ነገር ባለማግኘቷ ቅር ብትሰኝም የጠበቅኩትን ያህል አልተከፋችም ነበር። ምናልባት የመጀመሪያው ክህደቴ ልቧን ሳያጠነክረው አልቀረም።
"እሱም ቢሆን አንድ ነገር ነው። እኔ እንኳንስ የተፀፀተ ልብ ኖሮህ፤ በድለህኝ ፊትህን ባዞርክብኝ ቀናቶች ውስጥም አንተ ላይ ቂም የሚቋጥር ልብ ኖሮኝ አያውቅም። ኢንሻ አላህ ማን ያውቃል በድጋሚ በሌላ መስመር በትክክለኛ ቦታ ላይ ድጋሚ እንገናኝ ይሆናል።" አለችኝ። እሷም ሃላሏ ብሆን ምርጫዋ እንደሆነ በእጅ አዙር እየነገረችኝ ነው። የጨረስን ስለመሰለኝ አመስግኛት በተረፈችኝ ጊዜ ሌሎችን ቁስለኛዎቼን ይቅርታ ለመጠየቅ ተነሳሁ።
አልሐምዱ ሊላህ! በጊዜ መቶበቴ የመርዜን አድማስ ሲገድብልኝ፤ የዕድሜዬ ለጋነት ደግሞ የጥፋቴን ማዕበል ተቆጣጥሮልኛል። ለዛም መሰለኝ በአንዲት የዕረፍት ሰዓት ብቻ ሁሉንም የበደልኳቸውን ሰዎች አግኝቼ ይቅርታ ለመጠየቅ የቻልኩት። ምንም እንኳን ቀልባቸውን መስበሬ ቀላል የማይባል በደል ቢሆንም በይቅርታ የማይሽር ቁስል ግን አልነበረም። ቁስሉም ትቶት የሚያልፈው ጠባሳ ባለመኖሩ ልባቸውን ለይቅርታ ከመከፈት አላገደውም። በጊዜ ከጥፋቴ ባልቆጠብ ኖሮ ዛሬ ላይ ብዙ በኔ ጥፋት የሚመሰቃቀሉ ህይዎቶች በኖሩ ነበር። ግን አልሐምዱ ሊላህ ያ እንዲሆን አምላኬ አልፈቀደም።
በሂክማ የተሰጠኝን ተልዕኮ ፈፅሜ ወደነ ዮኒ ስመለስ ሃሚ ስለ እስልምና እያብራራለት ደረስኩ። ንግግራቸውን ሳላቋርጥ ተቀላቅያቸው ማዳመጥ ያዝኩ። እናንተ! ለካ ሃሚ ስለ እስልምና ብዙ ያውቅ ኖሯል። የእኛ የወንጀል ቋጥኝ አንገቱን ቀና አድርጎ ቅርንጫፎቹን እንዳያንሰራፋ ተጭኖት እንጅ ለጥላነት የማያንስ የዕውቀት ዋርካ ነበር። ሲጨርስ ይሄን ሁሉ እውቀት ከየት እንደሸመተው ጠየቅኩት። አባቱ ከልጅነቱ እንዳስተማሩት ነገረን። በሳምንት ሦስት ቀን አያቴጋ ሦስት ቀን ደግሞ የእሱ አባት ጋ ኪታብ ለመቅራት ወሰንን። ዮኒን ደግሞ ዙሁር ላይ ሸሃዳ ካስያዝን በኋላ ቁርዓን ልናስቀራው እቅድ አውጥተን የዕረፍት ጊዜው ተገባዶ ወደ ክፍላችን ገባን።
*
"መድዬን! አዲስ የተወለድኩ ያህል ነው የተሰማኝ።" አለን ዝሁር ላይ መስጂድ ወስደን ሸሃዳ አስይዘነው ወደ ትምህርት ቤታችን እየተመለስን እያለ። እኔና ሃሚ ተያይተን ተሳሳቅን።
"ቆይ የሚያስቅ ነገር ተናገርኩ እንዴ?" ሲል ጠየቀን።
"ኧረ አልተናገርክም።" አልነው።
"እስኪ መድዬን በሉ!" ሲለን ሳቃችንን ማፈን ተስኖን ለቀቅነው። ቆይቶ ለምን እንደሳቅን ሲገባው በሳቅ ከኛ ብሶ ተገኘ። ሳቃችን ሲያባራ፤
"አሁን በተናገርኩት እስላሜ ይበላሽብኛል እንዴ?" ብሎ ቆዘመ።
"አይ ለምዶብህ እንጂ አምነህበት ስላላልከው ችግር የለውም። ባይሆን ለመተው ሞክር!" ሲል መለሰለት ሃሚ!
"ይሄው መዲዬን! ከዚህ በኋላ አይለመደኝም!" ብሎ የሃሚን መዳፍ በመሃላነት መታ አደረገው። ሌላ ሳቅ!
እንደተለመደው ማታ ላይ ጥናቴን ጨርሼ ከሂክማ ጋር እያወራን ነው። ሰላምታ እንኳን ሳልሰጣት ነበር ቀኑን ሙሉ እስክነግራት ድረስ የቸኮልኩበትን የዮኒን መስለም የነገርኳት። የነገርኳት ነገር የፈጠረባት ደስታ አነሳስቷት ነው መሰለኝ
"የኔ ጀግና! የኔ ዑመር ኢብኑል ኸጧብ!" ብላ ታዕምር የሆኑብኝን "የኔ" የሚሉ ቃላቶችን አዘነበችብኝ። በምድር ላይ አለ የተባለ ጠቢብ ተጠቦ ከሚናገራቸው የፍቅር ቃላት ይልቅ የሂክማ የኔታን የሚያህ ማራኪ ቃል መኖሩን እስከምጠራጠር ድረስ በሀሴት ሰከርኩ። የእውነት የሷ ብቻ የሆንኩ እስኪመስለኝ ድረስ የማላውቀው አለም ውስጥ ተጓዝኩ።
"ታውቃለህ! ዑመርም ልክ እንዳንተ ከመስለሙ በፊትም ሆነ ከሰለመ በኋላም ሰዎች የሚከተሉት ጀግና ነበር። ባንተ ውስጥም ዑመርን ነው ያስተዋልኩት። አላህ ፅናቱን ያጎናፅፍህ!" ስትል የአድናቆት ናዳ ላዬ ላይ ከመረችብኝ። ደስታዋ ተራ ደስታ መስሎ አልታይ አለኝ። የሆነ የእናትነት አልያም የታላቅ እህትነት ለዛ ያለው መስሎ ተሰማኝ። የማልደብቃችሁ ነገር ቢኖር ይህችን ሴት ለዘላለሙ ከጎኔ ሆና ባትለየኝ፤ በዱንያም ሆነ በአኼራ የሃላል ሚስቴ ብትሆን መመኘቴን ነው።
"የሰጠውህንስ የቤት ስራ ተወጣህ?" ስትል ጠየቀችኝ።
"በሚገባ ነዋ! አላህም ሳይረዳኝ አልቀረም መሰል የሁሎችም ልብ ለይቅርታ ተገርቶ ነው የጠበቀኝ። እንዴት ቅልል እንዳለኝ አትጠይቂኝ። አሁን ውስጤን እየረበሸኝ ያለው አላህ ይማረኝ አይማረኝ አለማወቄ ነው።"
"ቆይ ተራው የሰው ልጅ ይቅር ለማለት ያልሳሳው የእዝነት ጥግ የሆነው አምላክ ይቅር ከማለት የሚሳሳ ይመስልሃል? በአንዲት እዝነት ብቻ የሚያዝኑት ፍጡራኖቹ ይቅር ብለውህ ከመቶ በላይ እዝነቶች ባለቤት የሆነው አላህ ይቅር የማይልህ ይመስልሃል?" ስትል በአንዴ በተስፋ የሞሉኝን ቃላቶችን ሰነዘረችልኝ።
"በፍፁም!" ከማለት በቀር ልላት የቻልኩት ነገር አልነበረም።
"ሳሊሜ! አላህ ባሮቹ ባሰቡት ቦታ ነው የሚገኘው። ይምረኛል ብሎ ላሰበ መሃሪ፤ አይምረኝም ብሎ ላሰበ ደግሞ ምህረቱን አዘግይ ነው። በአላህ ላይ ያለህን ተስፋ ከፍ አድርግ! ያለ ጥርጥር ይምርሃል።" ስትል አሁንም በተስፋ ሞላችኝ። ከተነጋገርን በኋላ ተሰነባብተን ተለያየን።
.
ይቀጥላል!
@AmirelMueminin
ቤተል መስጂድ ውስጥ ቤተክርስቲያን ካልሰራን በሚመስል መልኩ በፌደራል ታጅበው በመረበሽ ላይ ይገኛሉ።
ሁል ጊዜ ለሀገርና ለሰላም ፀር መሆን ግን አይከብድም?????
ከየበታችነት ስሜት የሚወጡት መች ነው!!!
〰〰〰〰〰〰〰〰〰
@USTAZ_ABUHAYDER
@USTAZ_ABUHAYDER
🧕ሂክማ🧕
ክፍል ሀያ
✍ኢብኑ ኢብራሂም
እረፍት ሰዓት ላይ ለይላን አግኝቼ ከባንዴራዋ ስር ተቀምጠን እያወራን ነው። በፊት እዝችው ቦታ ላይ ተማሪዎችንም ሆነ አስተማሪዎችን ሳላፍር ብዙ ሴቶችን የሳምኩ ቢሆንም ዛሬ ላይ ግን የዘነጋሁትን አምላኬን አፍሬ ከለይላ ጋር የምለያይበትን ሰዓት በጉጉት እንድጠባበቅ ሆኛለሁ። ለይላን የማኮርፍበት ወኔ ስላጣሁ በስርዓት እያዋራኋት ነው።
"ሊ! አሁን ላለሽበት የስነ-ምግባር ዝቅጠት መነሻሽ እኔ እንደሆንኩ አውቃለሁ። ከእኔጋ ከመግጠምሽ በፊት የነበረሽን አይናፋርነት በኔ ብልግና እንደተገፈፈም አልጠፋኝም። ቢሆንም ግን እኔ ያደፈረስኩትን እኔው እንዳጠራው ብትፈቅጅልኝ ተመኘሁ። እባክሽን የለውጤ አንዱ አካል ሁኚልኝ!" ስል ከልመና በማይተናነስ አነጋገር ተማፀንኳት።
"ሳሊሜ እኔ እስካሁን የሆንኩትን የሆንኩት ላንተ ብዬ እንደሆነ ታውቃለህ። የፈጣሪዬን ትዕዛዝ ስጥስ አንተ የገባህበት ጉድጓድ አብሬ ለመግባት ወስኜ ነው። አሁንም ቢሆን አንተ የሌለህበት አለም ለኔ ምንም ነው። ጉድጓድ ስትገባ አብሬህ ለመግባት ያላመነታሁ፤ አንተ ስትስተካከል የማልስተካከልበት ምክኒያት አይኖርም። ነገር ግን አንተን እንደማላጣህ ማረጋገጥ እፈልጋለሁ።" አለችኝ ስጋት ግብት እያላት።
"ለይላ! እኔ የነበርኩበትን አለም ተፀይፌ ወደ ጌታዬ ለመቃረብ ስወስን የማንንም ፍላጎት ለሟሟላት ብዬ አይደለም። ለሰው ብዬ አቋሜን የምለውጥ ብሆን ኑሮ የቤተሰቦቼን ደስታ ለማግኘት ስል ገና ድሮ አቋሜን በለወጥኩ ነበር። ነገር ግን ለመለወጥ ስወስን ዋነኛው አላማዬ የአምላኬን ፍቃድ ለመሙላት ብዬ ብቻና ብቻ ነው። ለሱ ብለሽ ስትለወጪ ደግሞ ሁለመናሽን መስጠት ይጠበቅብሻል። ስለሆነም ከለውጤ ጋር አብሬ መለወጥ ካለብኝ ነገር ውስጥ በኔና ባንች መካከል የነበረውን ፆታዊ ግንኙትንም ጭምር ነው። ስለሆነም አንችም ለመለወጥ ስታስቢ ልክ እንደኔ ፊትሽን ያዞርሽበትን አምላክ ፊት ፈልገሽ መሆን አለበት።" አልኳት ምን ያህል ልትጎዳ እንደምትችል እያሳሰበኝ። ምናልባት ከኔጋ በመለየቷ እንዳትጎዳ የተጨነቅኩላት የመጀመሪያዋ ሴት እሷ ሳትሆን አትቀርም።
"የምትለው ይገባኛል። አይደለም ወደ ፈጣሪህ በተቃረብክበት ሰዓት፤ ከሱ በራቅክበት ሰዓት እንኳን ከመሳም የዘለለ ሴቶችን ተዳፍረህ እንደማታውቅ አውቃለሁ። እኔ እየጠየቅኩህ ያለሁት የሃላል ምስትህ እንድሆን ቃል እንድትገባልኝ ነው።" ስትል ያልጠበቅኩትን ጥያቄ ጣለችብኝ። የምመልስላት ጠፋኝ። ምናልባት የለውጤ መንስዔ የሆነችውን ሂክማን አገባታለሁ የሚል ተስፋ ስላለኝ ይሁን ወይስ ለትዳር ዝግጁ ስላልሆንኩ፤ ብቻ ለለይላ ቃል መግባቱ አስፈራኝ። ለይላ ከፍቅሯ አንፃር ለኔ ስትበዛብኝ ነው። ምናልባትም ልሰማው ፍቃደኛ ያልሆንኩት ፍቅር በውጤ ሳይኖር አይቀርም። ለዛም ይመስለኛል እንደሌሎቹ በቶሎ ልርቃት ያልደፈርኩት።
"ሊ! ዛሬ ላይ ቁመን ስለነገ እርግጠኛ መሆን አንችልም። ባልተጨበጠ ነገር ቃል መገባባት ነገ ቃሉን ጥሰን የቃልን ክብር ማራከስ ነው የሚሆነው። ስለነገ ነገ ስንደርስ ብንወስን ይሻላል።" ስል መለስኩላት። የተናገርኩት ምን ያህል እንደሚያሳምናት አላውቅም። ብቻ ግን ማለት የቻልኩት ይሄንኑ ብቻ ነበር።
"እሽ እንዳልክ። አንድ ነገር ግን እንድታውቅልኝ እፈልጋለሁ። አንተ የሌላ ሴት ባለቤት መሆንህን እስከማረጋግጥ ድረስ ተስፋ ሳልቆርጥ እጠብቅሃለው። ይሄንን እንዳትረሳ።" አለችኝ። የፍቅሯን ሀይል ሳይ የማስበው ሁሉ ተምታታብኝ። ሂክማን የማገባበት ሁኔታ ቢመቻችልኝ ከሁለቱ ማንን መምረጥ እንዳለብኝ መወሰን ተሳነኝ። ለይላን ከዚህ በኋላ እንደማንገናኝ አስገንዝቤያት ተለያየን። ስንለያይ በሂጃቧ የአይኗን እንባ እየጠረገች እንደነበር አስተውያለሁ። እኔም ሃዘኗ ተጋብቶብኝ ወንድነቴን እስክረሳ ድረስ የእንባ ከረጢቴ ተፈታብኝና እኔም እንባዬን በመዳፌ እየጠረኩ ወደፊት አቀናሁ።
እንደተለመደው ማታ ሂክማን አግኝቼ የቀን ውሎዬን ዘገብኩላት። ቁርጠኛነቴን እያነሳች ትንሽ አወደሰችኝ። የለይላን ታሪክ ነግሬያት ስለነበር። በተመሳሳይ መልኩ ከዚህ በፊት ቀርቤ የጎዳኋቸውን ሁሉ ይቅርታ መጠየቅ እንዳለብኝ ነግራ የነገ የቤት ስራዬ መሆን እንዳለበት ጠበቅ አድርጋ አስገነዘበችኝ።
ማክሰኞ ጠዋት ላይ እንደተለመደው ክላስ ከመግባታችን በፊት ሦስታችንም ተሰባስበን እያወራን ነው። በመሃል ዮኒ እንዲህ አለን፦
"ሳሊሜ! ትላንት ከናንተ ከተለየሁ በኋላ የነገርከኝን በሙሉ አስቤበት ነበር። ያልከኝን ንግግር አምኜበትም የዛኑ ማታ ከተፈጠርኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሄጄ ነበር።" አለኝ።
"ማሻ አላህ ደስ ሲል። ወትሮም ከኛ ሃሳብ እንደማትወጣ እርግጠኛ ነበርኩ።" አለው ሃሚ ከልቡ ተደስቶ።
"በርግጥ ለመለወጥ ማሰቤ የሚያስደስት ነገር ነው። ነገር ግን የለውጥ ቦታ ነው ብዬ የሄድኩበት ቦታ ግን ልክ እንዳልሆነ እየተሰማኝ ነው።" ሲል ያልጠበቅነውን ነገር ተናገረ።
"ማለት አልገባኝም?" ስል ካፉ ነጥቄ ጠየቅኩት።
"የለውጥ ቦታዬ ነው ብዬ የሄድኩበት ቦታ ትክክለኛ የለውጥ ቦታ የሆነ ያህል ሊሰማኝ አልቻለም። ሰላም አገኝበታለሁ ብዬ የሄድኩበት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተለውጠዋል የሚባሉት ሰዎች ሲተገብሩት ያየሁት ነገር ልክ መስሎ አልታየኝ አለ።"
"ምን አይተህ ነው?" ሲል ሃሚ ልቡ ተሰቅሎ ጠየቀው።
"ገና ወደ ግቢው ስቃረብ አጥሩ ላይ ግንባራቸውን ተክለው ሲስሙት አስተዋልኩ። የሚያደርጉትን ላድርግ ብዬ ባደርግም የግራ ጫማዬን ቀኜ ላይ የተጫማሁ ያህል ነው የተሰማኝ። ወደ ውስጥ ጠልቄ ወደመቃብሩ ስፍራ ሄጄ ፀጥ ያለው ቦታ ላይ ሃጢያቴን እያሰብኩ እያለ የሁለት ሰዎች ንግግር ፀጥታውን ሰብሮ ተሰማኝ። አንድ ወጣት አንድ ቄስ ፊት ተቀምጦ የሰራውን ሀጢያት እየዘከዘከ ይናዘዛል። ቄሱ አፋቸውን በመዳፋቸው ደግፈው ያዳምጡታል። የነብስ አባቱ መሆናቸው ነው። ወጣቱ ሰራሁት የሚለውን ሀጢያቱን ሲያጠናቅ። የሰራው ተግባር አግባብ አለመሆኑን እና እግዚያብሔርን የሚያስቆጣ መሆኑን ከነገሩት በኋላ የሀጢያቱ ማስተሰረያ ይሆነው ዘንድ መቶ ስግደት እንዲፈፅም አዘውት ተያይዘው ወጡ። ወደ ራሴ መለስ ብዬ ሳስበው ፈጣሪዬ ላይ ለፈፀምኩት ሀጢያት እንደኔ ሰው ለሆነው አካል መናዘዜ አልዋጥልኝ አለኝ። ጭራሹኑ ለፈጣሪ በደል የሰው ልጅ በማያገባው ገብቶ የካሳውን መጠን መወሰኑ ፈፅሞ ልቀበለው የማልችለው ሆኖ ተሰማኝ።" አለን ነገሩ ምን ያህል እንዳንገበገበው በፊቱ ገፅታ እየገለፀልን።
"ዮኒ ምናልባት ከእምነት ብዙ ዘመን መራቅህ የፈጠረብህ ግሬታ እንዳይሆን ተረጋግተህ አስብበት።" አልኩት። ላፌ ያህል።
"በፍፁም በማሰብ የሚለወጥ ነገር አይኖርም። ቆይ ግን እናንተ ንሰሃ ስትገቡ በምን መልኩ ነው?"
"እኛማ የፈፀምነውን ወንጀል ፈጣሪያችን ፊት በቀጥታ በመቆም ከልብ ተፀፅተን ይቅር እንዲለን እንማፀነዋለን። ፀፀታችን እውነተኛ መሆኑን ለማረጋገጥም በፊት ወደነበርንበት ላለመመለስ ቁርጥ ውሳኔ እንወስናለን። ሰዎች ዘንድ ያደረስነው በደል ካለም የተበደሉትን መካስ ወይም ይቅርታቸውን ለማግኘት እንጥራለን።" ስል ከአያቴ የሰማሁትን የተውበት መስፈርት ጠቅሼ መለስኩለት።
"በቃ ይሄን ብቻ ነው ምታደርጉት? እንደኛ ለሸኪዎቻችሁ አትናዘዙም?" ሲል ተገርሞ ጠየቀን።
"በፍፁም! እንዲያውም ፈጣሪ ፀፀቱን በቶሎ የሚቀበለው የሰሩትን ወንጀል ግልፅ ለማያወጡት ባሮቹ ነው።" ስል መለስኩለት።
"በናትህ ወደ መስጂድ ውሰደኝ!" አለኝ። እኔና ሃሚ ግራ ገብቶን ተያየን።
"እርግጠኛ ነህ ግን?" ስንል ጠየቅነው።
"በሚገባ! አሁን ላይ የምለወጥበ
🧕ሂክማ🧕
ክፍል አስራ ዘጠኝ
✍ኢብኑ ኢብራሂም
"መልካም! በአንድ ወቅት ጫካ ውስጥ መሽጎ የዘመኑን ሰው እየዘረፈ የሚያስቸግር ዝነኛ ሽፍታ ነበር። ይህ ሽፍታ ከግለሰቦችም አልፎ በወቅቱ ለነበረው ንጉስም ያስቸገረ ነበር። ታዲያ አንድ ቀን እንደለመደው በሌሊት የአንድን ግለሰብ ቤት ለመዝረፍ አጥሩን ዘሎ ይገባል። እንዳጋጣሚ ሆኖ የቤቱ ባለቤት የሌሊት ሶላት እየሰገደ ስለነበር አልተኛም። ይህ ሽፍታ የመጣበትን አላማ ረስቶ የቤቱን ግድግዳ ተደግፎ በሰውዬው ድምፅ ተመስጦ ማዳመጥ ያዘ። የቤቱ ባለቤት፥
"ألم يأن للذين آمنوا أن تخشع قلوبهم لذكر الله وما نزل من الحق ولا يكونوا كالذين أوتوا الكتاب من قبل فطال عليهم الأمد فقست قلوبهم وكثير منهم فاسقون"
"ለነዚያ ለአመኑት ለአላህ ተግሳጽና ከቁርኣንም ለወረደው ልቦቻቸው ሊፈሩ እንደ እነዚያም በፊት መጽሐፍን እንደ ተሰጡትና በእነርሱ ላይ ጊዜ እንደረዘመባቸው ልቦቻቸውም እንደ ደረቁት ላይኾኑ (ጊዜው) አልቀረበምን? ከእነርሱም ብዙዎቹ አመጸኞች ናቸው፡፡"
[ ሱረቱ አል-ሐዲድ - 16 ]
የሚለው አንቀፅ ላይ ሲደርስ ይህ ሽፍታ ከሰባት ሰማያት በላይ ያለው አምላኩ በቀጥታ እሱን እያናገረው እንደሆነ አሰበ። አይኖቹም እንባ እያጎረፉ፤
"እንዴታ አምላኬ!" ሲል ለቁርዓኑ ጥያቄ ምላሽ ሰጠ። ከዚህ በኋላ እግሮቹ ችለው ሊሸከሙት ስለተሳናቸው እንባውን እያበሰ ወደ ቤቱ አቀና። ከዚች ቅፅበት በኋላ የዚህ ሰው ህይዎት ፈፅሞ ተለወጠ። የድሮ ማንነቱ ተቃራኒ እስኪሆን ድረስ የህይወት ባቡሩ ሃዲዱን ቀየረ። ከዚህ በኋላ ሰዎች ለታላላቅ ሸሪዓዊ ብይን ሊጠይቁት የሚመጡለት፣ ንግግሩ በወርቅ ቀለም የሚፃፍለትና ዛሬም ድረስ ስሙ ሲሰማ ግርማ ሞገስ የማይለየው ታላቅ ሰው ለመሆን በቃ። እርግጠኛ ነኝ ስሙን ብነግራችሁ ሁላችሁም ታውቁታላችሁ።" ብሎ ቃኘት አደረገን። ታሪኩን ከጀመረልን ጊዜ አንስቶ እስካሁኗ ቅፅበት ድረስ ታሪኩ የተፈፀመበት ጊዜ ውስጥ ያለሁ እስኪመስለኝ ድረስ ተመስጬ እያዳመጥኩ ነበር። ወላሂ እስካሁን ተዘናግቼ ልብ ሳልላቸው ያለፉኝን ታሪኮች ድጋሚ ባገኘኋቸው እስክል ድረስ ተቆጨሁ። አያቴ ስሙን ታውቁታላችሁ ሲል እኔን እንደማያካትት እርግጠኛ እንደሆንኩ፤
"ቆይ ግን እኒህ አሊም ማን ናቸው?" ስል ጠየቅኩት።
"ፉደይል ኢብኑ ኢያድ!" ሲል የአሊሙን ስም ነገረን። አያቴ ልክ ነበር። ስማቸውን ከዚህ በፊት እንደሰማሁት እርግጠኛ ነኝ። ነገር ግን የት እንደሰማሁት ላስታውስ አልቻልኩም። ከብዙ ማብሰልሰል በኋላ ግን ከሂክማ ጋር የተለዋወጥናቸው ምክሮች ውስጥ የሳቸውን ምክር ከነ ስማቸው ነግራኝ እንደነበር አስታወስኩ። በግሏ timeline ላይም በተደጋጋሚ የሳቸውን ንግግሮች እንደምትጠቀም ማስታወስ ቻልኩ። እውነት ለመናገር አሁን እየተሰማኝ ያለው ስሜት ልክ እንደሳቸው የህይወቴን ምዕራፍ ሙሉ ለሙሉ መቀየር እንዳለብኝ ነው።
"አያያ! ባለፈው ያሁኑን አመት ግማሽ ሴሚስተር እኔጋ ነው ምታሳልፈው ብለህኝ የለ? በቃ በ15 ቀኖች ውስጥ አምስት ኪታቦችን ታስቀራኛለህ።" አልኩት በታላቅ ወኔ። በምናቤ ባንዴ አሊም ስሆን እየታየኝ ነበር።
"ሃሃሃሃ ማሻ አላህ! ንያህ በጣም የሚበረታታ ነው። ነገር ግን በ15 ቀናት ውስጥ አይደለም አምስት ኪታብ አምስት ባብ (ምዕራፍ) እንኳን መቅራት ይከብዳል። የአሊሙን ታሪክ ስናገር የኢልም መንገዱን አሳጥሬ የነገርኳችሁ ታሪኩ እንዳይረዝምባችሁ ብዬ እንጅ ሸይኹ የነገርኳችሁ ደረጃ ላይ ለመድረስ የብዙ አመታትን መስዋዕትነት ከፍለዋል። ባይሆን የዛኔ ኡሱልን ትጀምርና ከዚያ በኋላ በሳምት ሁለት ቀን እየመጣህ ትቀራለህ። ብቻ አንተ ፅናት ይኑርህ።" አለኝ አያቴ። ሪሃና በደስታና በኩራት እያስተዋለችኝ እንደሆነ ያስተዋልኩት ድንገት ወደሷ አንገቴን ሳዞር ነበር። በኔ እውነተኛ ለውጥ እንደተደሰተችብኝ ያስታውቅባታል። ሀምዱ እንዳለው በጥላቻና በፉክክር የታሸገ ፍቅር ነው ያለን። ወላሂ አንድ ቀን ብንራራቅ ፀባችን እንደሚናፍቀን አልጠራጠርም።
አያቴ ብዙ ነገር መክሮን ማታ ላይ ወደቤታችን ተመለስን። ከጥናት ያተረፍኳትን ጥቂት ጊዜ ከሂክማ ጋር ለማሳለፍ ፌስቡኬን ከፈትኩ። ለምን እንደሆነ ባላውቅም ልክ የቤት ስራውን የሰራ ተማሪ ለመምህሩ እስከሚያሳይ ድረስ እንደሚጓጓው፤ እኔም የየዕለት ለውጤንና ውሳኔዬን ከሳምንታት በፊት ላወቅኳት ሂክማ ለመናገር ቸኮልኩ። ምናልባት እሷን የማይበትን ጊዜ ለማፋጠን ይሆን? አንዳንዴ ከቤተሰቦቼ በላይ እንዳቀረብኳት ይሰማኛል። አንዳንድ ግንኙነቶች ከግንኙቱ እድሜ በላይ የጠበቁ ሊሆኑ ይችላሉ። ልክ በወጣትነቱ ሙሁር መሆን እንደቻለ ሰው እና በስተርጅናው እንደ ህፃን እንደሚያስብ አዛውንት ልዩነት። አዎ ከአንዳንዱ ሰው ጋር ካሳለፍካቸው በርካታ አመታት ይልቅ፤ እንደ ሂክማ አይነት ሰው ጋር የምታሳልፋቸው ደቂቃዎች እልፍ ጊዜ ይበልጣሉ።
ለሂክማ የቀኑን ውሎዬን ከነ ፉደይል ታሪክ ስነግራት በጣም ተደሰተች። ይሄንን ለውጤን በማስመልከት በቀጣዩ ቅዳሜ ልታገኘኝ ቃል ገባችልኝ። እውነት ለመናገር የተሰማኝን ደስታ ልገልፅላችሁ ስለማልችል ብዘልለው ነው የሚሻለኝ። ቃላት ላይገልፁልኝ ነገር ከምዳክር በዝምታ አልፌው ዝምታዬን እናንተ ትርጉም ሰጥታችሁ ብትረዱልኝ ይሻለኛል።
ለይላ በፌስቡክ የልደቱ ቀን ማታ ምን እንደሆንኩ ጠይቃኝ ነበር። ከጥያቄዋጋ አያይዛም የልደቱን ድባብ እንዳደፈረስንባቸው ነገረችኝ። ለይላን ልትፈፅመው በነበረው ተግባር ተናድጄ ልዘጋት አስቤ ነበር። ነገር ግን በኔ ምክኒያት ለተበላሸው ስብዕናዋ ዋነኛው ተጠያቂ እኔ ነኝና እንዲሁ ከመራቅ ይልቅ ልክ እንደ ሃማድ ላስተካክላት ከቻልኩ ለመሞከር አስቤ ነገ ትምህርት ቤት ላገኛት ቀጠርኳት። ዮኒም ምክኒያቴን እንድነግረው እየወተወተኝ ነው። ነገ አግኝቼ ያለውን ነገር እንድነግረው ባግባባውም ሊታገሰኝ አልቻለም። በዚህ ልነግረው እንደማልችል በግድ አግባብቼ ነገ ሁሉንም ነገር ልነግረው ተስማማን። ሰሞኑን እንደማደርገውም ሁሉንም በጊዜ ተሰናብቼ እስከዛሬ ከምተኛበት ሰዓት ቀደም ብዬ ተኛሁ።
"በጣም አዝናለሁ! እኔ እንደዛ አልመሰለኝም ነበር።" አለ ዮኒ ጠዋት ላይ ተገናኝተን ምክኒያቱን ስንነግረው።
"በርግጥ በነሱም መፍረድ ይከብዳል። ምናልባት ይህ የሆነው ሂክማን ከማወቅህ በፊት በነበሩት ቀናቶች ውስጥ ቢሆን ኖሮ የጉዳዪ መሪ ተዋናይ አንተ ትሆን እንደነበር አልጠራጠርም። so ያንተን መለወጥ አይደለም እነሱ እኛ እንኳን የእውነት ስለመሆኑ እርግጠኞች አልነበርንም። ስለዚህ በነሱ ባንፈርድ ጥሩ ይመስለኛል።" ሲል የተሰማውን ተናገረ ዮኒ።
"እሱ ልክ ነህ። እኔም እኮ በነሱ ላይ ከመፍረድ ይልቅ ሊከሰት የነበረውን አደጋ መሼሽን የመረጥኩት ያን ብዬ ነው። ለማንኛውም እኔና ሃሚ ያለፈውን ማንነታችንን ለመለወጥ አስበናል። እስካሁን የተጓዝነው ጉዞ ፍፃሜው አደጋ መሆኑን ተገንዝበናልና የህይወት መስመራችንን ለመለወጥ ወስነናል። አንተም የለውጣች አንዱ አካል እንድትሆን ምኞታችን ነው። ምናልባት ያለፍነውን ጊዜያት አይንህን ገልጠህ ማየት ብትችል ለኛ የተገለጠልን እውነታ እንደሚገለጥልህ አልጠራጠርም።" አልኩት።
"ሃሚ ብቻ እንደዘመኑ ሰው ከመሬት ተነስተህ ነብይ ካልሆንኩ እያልከኝ እንዳይሆን?" ሲል ጠየቀኝ ነገሩ ሁሉ ተደበላልቆበት።
"በዛ መልኩ አትረዳኝ። እኔ እንድትለውጥ የምነግርህ እምነትህን ሳይሆን ስነ ምግባርህን ነው። እስከማውቀው እያደረግን የነበረውን ወራዳ ተግባር የክርስትና እምነትም ሆነ የሀገራችን ባህል