በኢስላማዊ ተፈጥሯችን በመልካም ንግግር (ከሊመተል ኢኸላስ)፣ በነብያችን በሙሐመድ ሃይማኖት ፣ ቀጥያለ ሙስሊም በነበረውና ከሙሽሪኮች ባልነበረው በአባታችን በኢብራሂም ጎዳና ላይ እንደ ፀናን አነጋን፡፡
☀️🌤⛅️🌥
አል-ሓሪሥ አል-ሙሓሲቢ እንዲህ ይላል -
‹ ከአላህ ዘንድ በርሱ ላይ የተወረደውን ነገር የማያውቅ ሰው፤ ከርሱ ዘንድም ወደ አላህ ሊሄድ የሚችልን ነገር የማያውቅ እንዳይሆን ያሰጋል፡፡ ›
አዎን ... በየቀኑ ጠዋትና ማታ ወዳንተ የሚወርዱትን የአላህ (ሱ.ወ.) ፀጋዎች፣ በይፋም ሆነ በስውር ወዳንተ የሚንቧቡትን ችሮታዎች የማታውቅ ከሆነ ይህ የሚያሳየው የቀልብህ እይታ የተጋረደ መሆኑን ነው፡፡ ስለሆነም በመጋረዱ የተነሳ መጥፎን ነገር ከጥሩ ለይቶ ሊያውቅ አይችልም፡፡ ወደ ጀነት የሚያቃርበውንና ለእሣት የሚዳርገውን ነገር አይለይም፡፡
ከዕውርነት ሁሉ ክፉው የልብ ዕውርነት ነው፡፡ ቀልብ የታወረ እንደሆነ በየጊዜው ወደ ጌታው የሚወጣውን ሥራውን መለየት ይሳነዋል፡፡ አላህ ይጠብቀን፡፡
ይህ መጽሐፍ አንዳንድ ከኛ የተጋረዱና የተደበቁ የአላህ ችሮታዎችን ይገልፅልናል፣ ከፍቶ ያሳየናል፡፡ በዚሁ መነሻነትም ያስተዋልናቸውን ፀጋዎች እናጣጥማለን፡፡ የደረስንባቸውን ችሮታዎች እናመሰግናለን፡፡ ቀልባችንም አላህ ላደረገልህ በጎ ነገር ጥሩ ምላሽ ይኖረዋል፡፡ የአላህን በጎነትም በበጎ ይመልሳል፡፡ እሱ የመረጠለትንም ነገር ከሌላው ነገር ሁሉ ያስበልጣል፡፡
ምንጭ ፦ የሁለት ዓለም ጀነት
ኻሊድ አቡ ሻዲ
ትርጉም ፡ ሙሐመድ ሰዒድ
/channel/AmirelMueminin
#ከድንቃድንቅ_የኡለሞች_ንግግር...
#አድማጭ_ሁን!
ታላቁ ዓሊም ዓጧእ ኢብኑ ረባህ ረሂመሁሏህ እንዲህ ይላሉ :
"አንድ ሰው የሆነ ሀዲስ (ወሬ) ሲያወራኝ ልክ በጭራሽ ወሬውን #ሰምቼው እንደማላቅ ሁኜ በደንብ #አዳምጠዋለሁ፣ ነገር ግን ያህንን ወሬ ምናልባች እሱ #ከመወለዱ በፊት ሰምቼው ሊሆን ይችላል።"
@AmirelMueminin
" እኔ እንደማስበው ሴቶች ከወንዶች እኩል ነን ብለው ማሰባቸውና ራሳቸውን ማሳመናቸው ሞኝነት ነው፡፡ ሁልጊዜም ቢሆን ሴቶች ከወንዶች በጣም የላቁና የበለጡ ናቸው፡፡ ለሴት ልጅ ምንም ነገር ብትሠጣት እጥፍ ድርብ አድርጋና አባዝታ ትመልስልሃለች፡፡ ለምሣሌ ዘርህን ብትሠጣት ልጅ ትሠጥሃለች፤ ቤት ብትሠጣት የሞቀ ጎጆ አድርጋ ታስረክብሃለች፤ ፈገግታህን ብትሠጣት ልቧን ትቸርሃለች፡፡ ማንኛውንም ነገር ለሴት ልጅ ብትሠጣት አባዝታ እና አተልቃ ታስረክብሃለች፡፡" እንግሊዛዊዉ ደራሲ ዊሊያም ጎልዲንግ
...
ክብር ለሴቶቻችን
@AmirelMueminin
ንፁህ ልቦች በደል ሲደርስባቸው ለመበቀል ያስቡና እድሉን ስያገኙ ግን ህሊናቸው ይቅርታን ታስቀድማለች ይቅር ባዮች ያድርገን❤️
ውብ ቀን❤️
@AmirelMueminin
📮 አዳማ ___ሰበር ዜና
ዛሬ በአዳማ ከተማ ከ 3:00ጀምሮ እስከ 1:00 ባለው ሰዓት ብቻ በተወሰኑ ቦታ ላይ በመዟዟር ከ 60,000 ብር በላይ ማግኘት ተችሏል።
ዘመቻው ነገም ይቀጥላል
📮 አስተባባሪ
የሀዋስ መ / ት/ቤት ሙስሊም ተማሪዋች ጀመዓ ከ አዳማ ከተማ ወጣቶች ጋር በመተባበር።
👇
ኑ..... በጋራ መሀመድን እናድነው
@HpSmuslimjema
ዱንያ ላይ ከመሥራትና ከመበርታት ውጭ አማራጭ የለህም። የሚያበረታታህ ብታጣ እንኳን ራስህን አበርታ። ለራስህ ነዳጅ ሁን፤ ራስህን ግፋ፤ ራስህን ሸልም። ሌላውን እንደምትመክረው ሁሉ ራስህንም ምከር -ጎበዝ! በርታ! በል ራስህን።
የሆነ ነገር ጀምረህ ሰዎች አይሳካልህም ቢሉህ እንኳ ያ የራሳቸው፣ የግላቸው አስተያየታቸው መሆኑን አስብ። እነርሱ የራሳቸው አስተያየት እንዳላቸው ሁሉ አንተም የራስህ አቋም ይኑርህ። ያ አቋምህ የነርሱ አመለካከት ተቃራኒ መሆን አለበት። ንግግራቸውን መስማት የለብህም። መስሚያህን ጥጥ አርገው። ንግግራቸውን ሰማህ ማለት ምኞታቸውን አሳካህ፣ ፍላጎታቸውን አሟላህ፣ ለስንፍና እጅ ሠጠህ… ማለት ነው።
አስተያየታቸውን ወደ ሕይወትህ አታምጣ፤ ራስህን አታወናብድ፣ ራስህን አታወዛግብ።
ትክክል ከሆነና ራስህ ካላመንክበት በስተቀር በሰዎች አስተያየት መንገድህን አታቋርጥ። ከአሉታዊ ሃሳባቸው ከፍ በል፤ ከፍ ብለህም ብረር። መብረሪያ ክንፍህን እንዲቆርጡ፣ ወደታች እንዲጎትቱህ ዕድል አትስጣቸው። ሃሳባቸውን ካላነሳህ፣ ንግግራቸውን ካልሰማህ፣ አስተያየታቸውን ካላዳመጥክ ይሳካልሃል። ማንም ቢናገርህ፣ ቢያሸማቅቅህና ቢስቅብህ እጅ አትስጥ። ይሳካልኛል በላቸውና ያለድካም ተጓዝ። ትክክለኛው መስመር ላይ እያለህ ተው አይሳካልህም ቢሉህ “አልተውም፤ ያ የናንተ አስተያየት እንጂ የኔ አቋም አይደለም” በላቸው።
ምንጭ -
ከአላህ ጋር መጽሐፍ
@AmirelMueminin
ውድ ወንድም እህቶች ወንድማችንን ከፈጣሪ በታች ከሞት እንታደገው፤በጣም እየተሰቃየ ነው እንዲሁም 4 ልጆቹ የሱን መዳን በጉጉት አየተጠበቁ ነውና በምንችለው አቅም እንርዳው!!
አዳማ ከተማ የምትገኙ ወገኖች በአካል ተገኝታችሁ ማገዝ ለምትሹ👉@hpsmuslimjemabot 👈አናግሩን
#ሼር #ሼር #ሼር
@hpsmuslimjema
🧕ሂክማ🧕
የመጨረሻው ክፍል 25
✍ኢብኑ ኢብራሂም
፡
"አሁንስ ወደ ቤት መመለስ ያለብህ አይመስልህም? ይሄኔ ተጨንቀው እየጠበቁህ ይሆናል። መልካም አስበው የፈፀሙትን ቀና ተግባር፤ ያልሆነ ነገር ፈፅመህ እንዲፀፀቱበት እንዳታረጋቸው።" ሲል የኑ አከለልኝ።
"እንሂድ!" አልኳቸው ከመቀመጫዬ ድንገት ተነስቼ። ሂሳብ ከፈልንና ተያይዘን ወደ ቤት ሄድን።
የቤታችንን አጥር አልፈን ወደ ውስጥ ስንገባ ቤቱ ሞቅ ብሎ ነበር የጠበቀን። ቅድም ሆቴል ውስጥ ከነበሩት ቤተሰቦቼ የጎደለ ሰው አልነበረም። በመምጣቴ እርግጠኛ እንደነበሩ ያስታውቃል። ሌላው የደነቀኝ ነገር ደግሞ እነ ሃሚ መምጣታቸውን እርግጠኛ የሆኑ ይመስል በቁጥራችን ልክ ማዕድ ተሰናድቶ ማዬቴ ነበር።
እንደገባሁ አባቢ ላይ እያነባሁ ሂጄ ተጠመጠምኩበት። "አብሽር ልጄ!" እያለ ግንባሬን ደጋግሞ ሳመኝ። ማሚ ከእኔ እኩል እያነባች በስስት ታዬኝ ነበር። ከአባቢ እቅፍ ወጥቼ ማሚ ላይ ተለጠፍኩ። ፀጉሬን በጣቶቿ እየፈለፈለች አንገቴ ስር ሳመችኝ። በመቀጠል ውዷን እህቴን ጭምቅ አድርጌ ሳምኳት። ምናልባት ከተወለደች እንደዛሬ ስስማት ለመጀመሪያ ጊዜ ሳይሆን አይቀርም። ሪ ስሜቷን ማፈን ተስኗት ድምፅ አውጥታ እያለቀሰች ነበር። ሃምዱንም ወደ ደረቴ አስጠግቼ አቀፍኩት።
"ቆይ ግን ይሄን ሰይጣን እንኳን ሊያስበው የማይችለውን ሃሳብ ያፈለቀው ማን ነው?" ስል ጠየቅኳቸው የተሰናዳውን ምግብ እየተመገብን እያለ።
"መቼም ሰይጣን የማያስበው ከሆነ መልዓክ መሆን አለበት ያሰበው።" ሲል የኑ አሳቀን።
"ሙጢ! እያልክ የምትሰድባት ታናሽ እህትህ ናት ሀሳቡን ያመነጨችው። ብልሃተኛው አባትህ ደግሞ ደህና አድርጎ አቀናበረው።" ስትል መለሰች ማሚ ወደ ሪ በኩራት እየተመለከተች።
"እቺ ሙጢ!" ብዬ ስሳደብ ቤት ያለው ሁሉ ሳቀ።
"ሳሊሜ ቀና አስበን በፈፀምነው ነገር ተከፍተህብን ከሆነ አውፍ እንድትለን እንጠይቃለን!" አለ አባቢ።
"በዛው እኛንም አውፍ በለን።" አለ የኑ።
"እናንተ ደግሞ ምን አደረጋችሁ?"
"እውነታውን ያወቅነው ትላንት ማታ ነው። ቅድም ያለህበትን ቦታ አጣርተን እንድናገኝህና አግባብተን ወደ ቤት እንድናመጣህ ተልዕኮ የሰጡን የሂክማ ደራሲዎች ናቸው።" አለ ሃሚ።
"በተዋጣላቸው ተዋናዮች መሃል ተከብቤ ነዋ ያለሁት። ለምን ለትወና አትወዳደሩም? እንደሚዋጣላችሁ አልጠራጠርም!" ብዬ ስስቅ ሁሉም አብረውኝ ሳቁ።
"ለማንኛውም ምንም ይቅር የሚባል ጥፋት የለባችሁም። ባይሆን ይሄን ያህል ስላስለፋኋችሁ እናንተ አውፍ በሉኝ።" አልኩና ቀጠል አድርጌ፤
"እና ሂክማ የተሰኘው ሚሽን በእኔ ሊያበቃ ነው ማለት ነው? ለምን አጠናክረናት እንደኔ ያሉትን ወጣቶችን ህይወት ከጨለማ ለማውጣት አንጥርም?" ስል ሃሳቤን ሰነዘርኩ። በሃሳቤ ሁሉም ተስማሙ። ለጊዜው በፌስቡክና በቴሌግራም ሂክማ የተሰኘ ቻናል ከፍተን ጥበብ አዘልና ውጤታማ ዳዕዋ ለመስጠት አሰብን። ወደፊት ትምህርታችንን ስንጨርስ የተጠናከረ የዳዕዋ ተቋም ለማቋቋም አቀድን።
በእቅዱ መሰረት እኔ የስነ ልቦና ትምህርት በመውሰድ የማማከሩን ሃላፊነት እንድመራ፣ የኑ ማኔጅመንትን አጥንቶ ቡድኑን በማናጀርነት ሊያስተዳድር፣ ሪ ሶፍትዌር ኢንጅነሪንግ አጥንታ ተቋሙን በዲጂታይዜሽን የማጠናከሩን ሃላፊነት እንድታጠናክር፣ ሃሚ አካውንቲንግ በማጥናት የሂሳብ ስራውን በበላይነት ሊመራ፣ ሀምዱ ደግሞ ኢኮኖሚክስ አጥንቶ በፋይናስ በኩል ያለውን ሃላፊነት ሊወጣ፣ ማሚና አባቢ በዳዕዋውና በስነ ፅሁፉ ዘርፍ የበኩላቸውን ሊወጡ ተስማማን። ከሙያው ባሻገር ሁላችንም ዲናዊ እውቀት መገብየት እንዳለብን ተስማምተን ነገውኑ እንድንጀምር አቅደናል። የተቋሙ ስም ደግሞ #ሂክማ የሚሰኝ ይሆናል። ኢንሻ አላህ!
ሂክማ
፡
ወጣቶች ከተዘፈቁበት የስሜት አረንቋ ይወጡ ዘንድ በሂክማ የሚጠራቸው ሰው ይሻሉ፣ ወንጀልን እየተቀለቡ የጎለመሱ ጎልማሶችና አዛውንቶች ለዘመናት የደረቀው ልባቸው ረጥቦ ይለዝብ ዘንድ ሂክማ ያስፈልጋቸዋል። የወደፊት ትውልዶች ትውልዳቸው የደገሰላቸውን ማዘናጊያ አሻንጉሊቶች ሳያታልሏቸው መልካም ስብዕናን ይላበሱ ዘንድ በሂክማ እየመከረ የሚኮተኩታቸው ማህበረሰብ ያሻቸዋል። ዳዕዋዎች፣ ፈተዋዎችና በየ ትምህርት ማዕከሉ የሚሰጡት ትምህርቶች ከሂክማ ያገለሉ ከሆኑ ሳራ በርሃ ላይ እንደሚስተጋባ የይድረሱልኝ ጩኸት እንጅ ፋይዳ ሊኖረው አይችልም። ልፋታችንና ድካማችን እንዲያፈራና ልክ እንደነብዩላህ ኢብራሂም የሃጅ ጥሪ የኛም ጥሪ ለዘመናት እንዲስተጋባ ከሻን በሂክማ የተቀመመ ሊሆን ግድ ይላል! ሁላችሁም ከዚህ በታች የተቀመጠውን ቃል ልቦናችሁ ውስጥ ያብብ ዘንድ ቅበሩት። "ሂክማ"
"ادع إلى سبيل ربك بالحكمة والموعظة الحسنة وجادلهم بالتي هي أحسن إن ربك هو أعلم بمن ضل عن سبيله وهو أعلم بالمهتدين"
"ወደ ጌታህ መንገድ በብልሃትና በመልካም ግሳጼ (በለዘብታ ቃል) ጥራ፡፡ በዚያችም እርሷ መልካም በኾነችው (ዘዴ) ተከራከራቸው፡፡ ጌታህ እርሱ ከመንገዱ የተሳሳተውን ሰው ዐዋቂ ነው፡፡ እርሱም ቅን የኾኑትን ሰዎች ዐዋቂ ነው፡፡" [ሱረቱ አል-ነሕል፥ -125]
።።።።።።።።----( ተ - ፈ - ፀ - መ)----።።።።።።።።
@AmirelMueminin 👈join
ቤት ዉስጥ ሱረቱ አል-በቀራህን መቅራት
ረሱል ﷺ እንዲህ አሉ፦
"ቤቶቻቹህን መቃብር አታድርጉ! ሸይጧን ሱረቱ አል-በቀራህ ከሚቀራበት ቤት ይሸሻል"
📚 رواه مسلم
@AmirelMueminin 👈join
ማስታወቂያ‼😂😂
ETV 😂ጅልባብ😂 ቤት
★★★★★★★
ምርጥ ምርጥ ጅልባብ እና ኒቃብ ይፈልጋሉ እንግዲያውስ ወደ ETV ጅልባብ ብቅ ይበሉ 😂
የኛን ጅልባቦች ለየት የሚያደርጋቸው ዋሻ ውስጥ እንኳን ለወራት ተለብሶ አይቆሽሽም አያረጁም 😂
የተለያዩ የከለር አማራጮች ቀርበውላችዋል ኑና ይጎብኙን ከእርሶ እስታየል ጋ የሚሄደውን መርጠው ይውሰዱ😂
‼አድራሻችን‼
በሁሉም የማንቂያ ደውል የተሰኘው ፊልም በሚታይባቸው ሲኒማ ቤቶች ያገኙናል😂
የጀነት ተበሳሪዎች /ከአሥርቱ ሌላ/
ምንጭ - አንዲት ዕለት በጀነት
ትርጉም - ዒማዱዲን ዙልፊቃር
1- ሰዕድ ኢብን ሙዓዝ (ረ.ዐ)
በአል-በራእ (ረ.ዐ) እንደተተረከው፥ ለአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) የሐር ልብስ (ጨርቅ) በስጦታ ተበረከተላቸው። ሶሐቦችም ይደባብሷትና በልስላሴዋ ይደነቁ ጀመር። (መልዕክተኛው (ሰ.ዐ.ወ) “በዚህ ልስላሴ ትደመማላችሁን?” አሉ። “በጀነት ያለችው የሰዕድ ኢብን ሙዓዝ መሀረም (የእጅ ፎጣ) ከዚህ ትልቃለች ወይም ትለሰልሳለች!”
2. ቢላል ኢብን ረባሕ (ረ.ዐ)
የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) “ጀነት ሦስቶችን ናፍቃለች ዐሊ፣ ዓማር እና ቢላልን!”
ቡረይዳህ (ረ.ዐ) እንዳወሱት፣ “ የሆነ ቀን የአላህን መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ቢላልን ጠርተው እንዲህ አሉት፡-
‘አንተ ቢላል ሆይ፣ ወደ ጀነት የቀደምኸኝ በምን ይሆን? እኔ ትላንት ጀነት ገባሁ፣ ዱካህንም ከፊቴ ሰማሁ…’ቢላልም ‘የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ሆይ፣ እኔ አዛን አላደርግም፣ ሁለት ረከዐ (ነፍል) የሰገድኩ ቢሆን እንጂ፣ ውዱእም አልፈታም ወዲያውኑ ውዱእ ያደረግኩ ቢሆን እንጂ’ አላቸው፡፡ የአላህ መልዕክተኛም (ሰ.ዐ.ወ) ‘በዚህ ነዋ!’ አሉ።”
3. ዘይድ ኢብን ኑፈይል (ረ.ዐ)
እናታችን ዓኢሻህ (ረ.ዐንሃ) ከመልዕክተኛው (ሰ.ዐ.ወ) አንደበት እንደሰማችውን እንዲህ አሉ፡- “ጀነት ገባሁ፤ የዘይድ ኢብን ዐምር ኢብን ኑፈይል ሁለት ደረጃዎችንም ተመለከትሁ።”
4. ሓሪሣ ኢብን አን-ኑዕማን (ረ.ዐ)
እናታችን ዓኢሻ (ረ.ዐ) ከአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) አንደበት የሰማችውን እንዲህ አውስታለች፡-
“ጀነት ገባሁ፤ በውስጧም (የቁርአን) ንባብን ሰማሁ፣ ʻማነው እሱ?ʼ ስል ጠየቅሁ፤ ʻሐሪሣ ኢብን አን-ኑዕማን ነው!ʼ አሉ(ኝ)፤ (ሰ.ዐ.ወ) ለእኛ “እንዲህላችሁ ነው መፅደቅ፣ እንዲህላችሁ ነው መፅደቅ! አሉ(ን)።”
5. ጀዕፈር ኢብን አቢ ጧሊብ (ረ.ዐ)
አቢ ሁረይራህ (ረ.ዐ) ከመልዕክተኛው አንደበት (ሰ.ዐ.ወ) ቀስመው ያወሱልን ሐዲስ እንዲህ የሚል ነው፡-
“ጀዕፈር ኢብን አቢጧሊብን በሁለት ክንፎች ጦርነት የሚሳፈፍ መልዕክ ሆኖ አየሁት።”
6. ሐምዛ ብን ዐብዱል ሙጠሊብ (ረ.ዐ)
ኢብን ዐባስ (ረ.ዐ) ከመልእክተኛው የሰሙትን ብስራት እንዲህ ያወጋሉ፡-
“ትናንት ጀነት ገባሁ፤ በውስጧም ባማተርሁ ጊዜ፥ ጀዕፈርን ከመላእክቱ ጋር ይከንፋል፤ ሐምዛ ደግሞ ከአልጋ ላይ ተንጋሎ (የመዝናናት ዓይነት) ነበር።”
ቀሪዎቹን ከመጽሐፉ
ነጃሺ ማተሚያ ቤት
ነጃሺ መፃሕፍት መደብር
/channel/AmirelMueminin
#በአሁኑ_ሰዓት_ዋርካ_ገበያ_ውስጥ_እንገኛለን
#ሰውን_ለመርዳት_ሰው_መሆን_በቂ_ነው።
#መስጠት_የሚሻ_የሚሰጠው_አያጣም!!
#ውድ_ወገኖቻችን_እናመሰግናለን
#አላህ_ይስጥልን
@hpsmuslimjema
#ፍራንኮ_አካባቢ_እንገኛለን
#እናመሠግናለን_ውድ_ወገኖቻችን #ኑ_በጋራ_ወንድማችንን_እንታደገው
#ለወገን_ደራሽ_ወገን_ነው
@hpsmuslimjema
#ጁመዐ_እና_ትጥበት🚿
ኢብን ዑመር ረ.ዐ እንዳስተላለፉት ረሱል ﷺ እንዲህ ብለዋል : አንዳችሁ ወደ ጁምዓ በሚመጣ ጊዜ ገላውን ይታጠብ።
ሙተፈቁን ዓለይህ(ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)
@AmirelMueminin
በዚ የበጎ ፍቃድ ስራ ላይ መሳተፋ የሚሻ ወይም የሚፈልግ ማንኛውም ሰው በተሰማራንበት አካባቢ በመገኘት
እንዲሁም 👇👇👇
በመደወል :#0963920243
#0933869735
#መቀላቀል_ትችላላችሁ
#ሰውን_ለመርዳት_ሰው_መሆን_በቂ_ነው
#ወንድማችንን_በአቅማችን_እናግዘው!!
የሚሰጥ ልብ ካለ የሚሰጥ ነገር አለ ሁላችንም የቻልነውን በመስጠት ህወቱን እናትርፍ።
በዚህ ሰዓት ሚጊራ መነሀርያ
በ 02 ቀበሌ
🍁አስተባባሪ
የ ሀዋስ ት /ቤት ሙስሊም ጀመዓ እና ከ አዳማ ወጣቶች ጋር በመተባበር
@HpSmuslimjema
ህይወት ገፅታ ብቻ ሆናለችና
የሰው ንግግሩ ስለተመቸህ ብቻ አትመነው
የከፊል ሰው ጥላ ከእውነተኛው ሰውነት ይዘት ይገዝፋል።
@AmirelMueminin
ውድ ወገኖቼ ከፈጣሪ በታች ሒወቴ በእጃቹ ላይ ይገኛል። እባካችሁ አድኑኝ፤ለሞት አሳልፋቹ አትስጡኝ!!
#Share #share #share #share
ይሄንን መልዕክት ለምታውቋቸው በሙሉ እንድታደርሱልን በፈጣሪ ስም እንጠይቃለን
@hpsmuslimjema
✋የጀሊሉ ሰላምና እዝነት በናንተ ላይ ይስፈን!
❤️ውድ ቤተሰቦቻችን እንደምን አላችሁልን
🌺 ታሪኩን ሳታነብቡ ከርማችኋልና አሁን ደግሞ የናንተን አስተያየት የማነብበት ሰአት ነው። እንደው ታሪኩ እንዴት ነበር ('❤' ይቺን በመንካት መውደዳችሁን ግለፁልን)
ከታሪኩ ምን ተማራችሁ በአጠቃላይ በታሪኩ ዙሪያ ያላችሁን አስተያየት ላይ ጀባ በሉን!
👇👇👇👇👇
@AmirelMueminin_bot
share👇👇👇
@AmirelMueminin
╭─────────╮
ፍቅር ማለት..❣
╰─────────╯
አቡበከር አሲዲቅ [ረ.ዐ] ከነብዩ [ሰ.ዐ.ወ] ጋር በሂጅራ ጉዟቸው ወደ ዋሻ ከመግባታቸው በፊት..
«ወሏሂ ካንቱ በፊት ካልገባው በስተቀር አትገቡም፣ የሆነ ነገር ቢኖር እንኳ ካንቱ በፊት እኔን ይጉዳኝ» ማለታቸው ነው።
@AmirelMueminin
("እውቀት ምስል ቢኖረው ኖሮ ምስሉ
ከፀሀይና ከጨረቃ በላይ ያማረ ምስል ይሆን ነበር")
📚ኢብነል ቀይም ረሂመሁሏህ
@AmirelMueminin 👈join
🥀Assalaamu aleeykum warahmatullaahi wabarakaatuh
Jaalatamtoota jiraattota magaalaa Adaamaa hundaaf, akkuma armaan olitti sagaleen ibsuuf yaalametti obboleessa keessa gargaaruuf inshaallaah, boru ganama sa'aa 3:00 irratti shuuraa ni qabaanna.
iddoon masjiida Abraar keessa (naannawa muugar) dha.❗️❗️
Yeraa kabajuun amala mu'uminaati❗️
Dhuma irrattis namni ergaan kun gahe hiriyyaa keessaniif share akka gootan maqaa rabbiitiin isin gaafanna!!
SHARE SHARE SHARE
gaaffii kamiifuu
👇👇👇👇👇👇
@hpsmuslimjemabot
Join &share
👇👇👇👇
@hpsmuslimjema