amlkoo | Unsorted

Telegram-канал amlkoo - እናመልክሃለን

327

“Speaking to yourselves in psalms and hymns and spiritual songs, singing and making melody in your heart to the Lord;” — Ephesians 5:19

Subscribe to a channel

እናመልክሃለን

👉🏾Drum
🥁 @drum4Christ 🥁

Читать полностью…

እናመልክሃለን

. ሀሌ ሉያ
ዘማሪያን ዘፀአት ኳዬር

New Amazing Live Worship
ሼር በማድረግ ለወዳጆ ያካፍሉ
sʜᴀʀᴇ💯 sʜᴀʀᴇ 💯 sʜᴀʀᴇ💯
@amlkoo
@amlkoo

Читать полностью…

እናመልክሃለን

Music Theory

Type of Music

ክፍል 9

Hip- Hop

ይህ ሙዚቃ የራፕ ሙዚቃ በመባል የሚታወቀው በ 1970ዎቹ ውስጥ በኒዎርክ አካባቢ ውስጥ በአሜሪካ ውስጥ በውስጠኛው የከተማ አፍሪካ አሜሪካውያን እና ላቲኖ አሜሪካኖች የተገነቡ ተወዳጅ የሙዚቃ አይነቶች ናቸው።

የሂፕ ሆፕ ሙዚቃ ለመጀመሪያ ጊዜ በ 1970 ዎቹ መገባደጃ ላይ ሲጀመር ብዙ ሰዎች ስለዚህ ጉዳይ አያውቁም ነበር ፡፡ በኒው ዮርክ ሲቲ በጣም ድሃ በሆኑ አውራጃዎች የተፈጠረው በአፍሪካ አሜሪካዊ እና በላቲኖ ወጣቶች እንደ ሂፕ ሆፕ ትዕይንት አካል ሆኖ የደስታ እና የግራፊቲ ጥበብን ያመረተ ነው ፡፡ ከእነዚህ ወጣቶች መካከል ብዙዎቹ ሥራ አጥዎች ነበሩ ፣ ግን አንዳንዶች እንደ ዲጄዎች በዲጂዎች ሆነው ሥራ ያገኙ ሲሆን ሁለት መዞሪያዎችን እና የዲጄ ድብልቅን ያለማቋረጥ ለማጫወት የሚጠቀሙባቸውን የዲጄይንግ ቴክኒኮችን ተምረዋል፡፡

በ 80 ዎቹ መገባደጃ ላይ በርካታ የሂፕ ሆፕ beats በስቱዲ ውስጥ ከበሮ ፣ ከሰውነት ማቀነባበሪያዎች እና ከድሮ funk እና disco ሪኮርዶች ጋር ይሠሩ ነበር።

በ90ዎቹ መጀመሪያ አቀናባሪዎች audio editing software እና digital effectዎችን በመጠቀም አዲስ የ hip hop style መፍጠር ጀመሩ።

የamharic እና የ engilsh hip hop መዝሙሮችን ከዚህ በታች ያገኙታል👇👇👇

Читать полностью…

እናመልክሃለን

. ለምድነው የምንኖረው
መስከረም ጌቱ | Worship
ሼር በማድረግ ወዳጆ ያካፍሉ
sʜᴀʀᴇ ◈ JOIN ◈ sʜᴀʀᴇ
🔰ኢየሱስ እንደቃሉ ይመጣል
@amlkoo
@amlkoo

Читать полностью…

እናመልክሃለን

. እረዳኝ
ዘማሪት ምህረት ማቲዎስ

New Amazing Cover Song
ሼር በማድረግ ለወዳጆ ያካፍሉ
sʜᴀʀᴇ💯 sʜᴀʀᴇ 💯 sʜᴀʀᴇ💯
@amlkoo
@amlkoo

Читать полностью…

እናመልክሃለን

በቃላችን መሰረት #እኔ_እዘምርልሃለሁ #ሁለተኛው ምዕራፍ ሀሙስ ምሽት 3:00 ላይ ይጀምራል #በzema_Pictures አዘጋጅነት

በአዲስ ዳኞች 🎹🎤🎤🎤
#በዝማሬ_በቤቶproject ብቻ

ለመሳተፍ @abenulu
@Eliziyo
ማሳሰቢያ !!!

Ⓟ መጠቀም የሚቻለው 1-2 ደቂቃ ብቻ ነው ያለምንም የሙዚቃ መሳሪያዎች።


#ዙሩን_በሙሉ_1ኛ_ሆኖ_ለሚያሸንፍ_ነፃ_video_clip 🎬🥇🥇🥇🥇🥇🥇🥇

ዝማሬ_በቤቶ project
@zemavocal
@zemavocal

Читать полностью…

እናመልክሃለን

. "ከምንም ከማንም"
ማልዳ ቢቂላ | Cover Song
🕒-10:2Min | 💾-42.0MB
Share 📲 Share 📲 Share
@amlkoo
@amlkoo

Читать полностью…

እናመልክሃለን

የምዕራፍ አራት ማጠቃለያ ሀሳብ

1. ቤተክርስቲያን ምዕመኖቿን ከተጋረጠባቸው የ"ዘፈናምነት" አደጋ የመከላከል ግዴታ
አለባት።

2. ከ"ዘፈናምነት" አደጋ መከላከል የምትችለው አማኞችን ደቀመዝሙር በማድረግ፣ እቅበተ
እምነት አገልግሎት በማጠናከርና ለሙዚቀኞች ተገቢውን ትኩረት በመስጠት ነው።

3. በየትኛውም የአገልግሎት ዘርፍ ከመሰማራት በፊት የሚቀድመው ደቀ መዝሙር መሆን ነው።

4. እቅበተ እምነት አገልግሎት ማለት የተለያዩ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሙግቶችን በማዘጋጀት መሰረታዊ የክርስትና አስተምህሮን ከስሕተት ትምህርታትና ልምምዶች መመከት ነው።

5. “ፖለሚክስ” የመጣውን ማጥቃት ብቻ ሳይሆን ያለውን ሄዶ ማጥቃት ነው።

6. የወንጌላዊያ ዓቅበተ እምነት/Apologetics ብዙ ጊዜ መከላከል ላይ ያተኩራል።
ፖለሚክስ/Polemics ላይም ትኩረት መደረግ አለበት።

7. የሙዚቃ ትምህርት እየተማሩ በጎን የሥነ መለኮት ትምህርት የሚማሩበትን አማራጮችን
ቤተክርስቲያን ማዘጋጀት አለባት።

@amlkoo
@amlkoo
@amlkoo

Читать полностью…

እናመልክሃለን

ከማመስገን ጋር በጸሎት እየነቃችሁ ለእርሱ ትጉ።
ወደ ቆላስይስ ሰዎች 4:2

Читать полностью…

እናመልክሃለን

. ጋሻዬ
ሱራፌል & ጆን | New Song
⏰ 8:03Min 📥 27.7MB
ለኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
sʜᴀʀᴇ ◈ JOIN ◈ sʜᴀʀᴇ
@amlkoo
@amlkoo
@amlkoo

Читать полностью…

እናመልክሃለን

የምዕራፍ ሁለት ማጠቃለያ ሀሳብ

1. ዘፈን ማለት ምግባረ ብልሹነት የተጠናወተው ግጥም ወይም ዜማ እንዲሁም መልካምም ሆኖ የማናዜመው ቅኔ ነው።

2. ይዘትን በተመለከተ ዓለማዊ መዝሙር እንደሌለ መንፈሳዊ ዘፈንም የለም።

3. የሚዘፍን የዘፋኙን መንፈስ ይካፈላል።

4. ዘፍ-ሙር(ዘፈንና መዝሙር) ዘፈን ነው።

5. በአንድ ጊዜ ዘማሪም አዝማሪም መሆን አይቻልም።

@amlkoo
@amlkoo
@amlkoo

Читать полностью…

እናመልክሃለን

ክፍል 8
@amlkoo
@amlkoo
@amlkoo
Music theory

R&B Music (Rhythm and Blues)

ይህ Music አለም ያወቀው በ 1940ዎቹ አካባቢ እንደሆነ ይነገራል በአፍሪካ እና በአሜሪካ ውስጥ R&B ሂፖፕን ፣ ዳንስን ፣ ፖፕን ያማከለ music እንደሚሰሩ ያሳያል።

እ.ኤ.አ. በ 1950 ዎቹ እስከ 1970ዎቹ ባሉት ዓመታት በ1950ዎቹ በተለመደው ምት እና በብሉዝ ሙዚቃ ውስጥ ባንዶቹ ብዙውን ጊዜ ፒያኖ ፣ አንድ ወይም ሁለት ጊታሮች ፣ ከበሮ እና ሳክስፎን በመጫወት ይሰሩት ነበር።

"R&B” የሚለው ቃል በትርጉም በርካታ ስሞችን አግኝቷል፡፡
በ1950ዎቹ መጀመሪያ ላይ ለብሉዝ መዛግብት በተደጋጋሚ ይተገበራል፡፡
ከ1950ዎቹ አጋማሽ ጀምሮ ይህ የሙዚቃ ዘይቤ ለሮክ እና ሮል እድገት አስተዋፅዖ ካበረከተ በኋላ “አር ኤንድ ቢ” የሚለው ቃል ከኤሌክትሪክ ብሉዝ የተገነቡ እና የተቀላቀሉ የሙዚቃ ቅጦች እንዲሁም የgosple እና የsoul ሙዚቃን ለማመልከት ጥቅም ላይ ውሏል ፡፡
እ.ኤ.አ. በ 1960ዎቹ እንደ ሮሊንግ ስቶንስ ያሉ በርካታ የብሪታንያ ዓለት ባንዶች የ ‹R&B› ባንዶች ተብለው ተጠቅሰዋል ፡፡
እ.ኤ.አ. በ 1964 በማራኪው ክበብ ውስጥ ለማን መኖርያ መታወቂያ ወረቀቶች ‹ከፍተኛው አር ኤንድ ቢ› የሚል መፈክር ይዘዋል።

“R&B” የሚለው ቃል በቢልቦርዱ በሰንጠረዥ ዝርዝሩ ውስጥ ከሰኔ 1949 እስከ ነሐሴ 1969 ድረስ የነጠላዎች ገበታ ምርጥ ሽያጭ የነጠላዎች ነጠላ ተብሎ ተሰየመ።

የብሪታንያ R&B music በ1960ዎቹ መጀመሪያ ላይ መሰራት ተጀምሯል።

በዘፈኑ አለም ብዙ የብሪታንያ ጥቁር ሙዚቀኞች የብሪታንያ አር ኤንድ ቢ ትዕይንትን ፈጥረዋል፡፡

እነዚህ እንግሊዝ ውስጥ የተቀመጠውን አሜሪካዊ ዘፋኝ Geno Washingtonን ያጠቃልላል፡፡
እ.ኤ.አ. በ 1965 ጊታሪስት Pete Gage Geno Washingtonን Ram Jam የተሰኘውን ባንድ እንዲቀላቀል ጥሪ አድርጎለት ነበር።
በ 1969 ቡድኑ ከመከፋፈሉ በፊት 40 ምርጥ ነጠላ ዜማዎችን እና ሁለት ምርጥ 10 አልበሞችን ባንዱ አግኝቷል፡፡
@amlkoo
@amlkoo
የEnglish እና የamharic R&B music የሚባሉትን ከዚህ በታች ያገኙታል👇👇

Читать полностью…

እናመልክሃለን

😇የሚባርክ መዝሙር😇

🎷እስቲ ልለምነው ጌታዬን ስለሀገሬ🎷

🎤ቤዛዊት ተስፋሁን🎤

Читать полностью…

እናመልክሃለን

ምዕራፍ አራት

ክፍል ሁለት

3.ለሙዚቀኞች ተገቢውን ትኩረት መስጠት

በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ለሙዚቀኞች ያለው ትኩረት በጣም ዝቅተኛ ነው። ከዚህም የተነሳ
ብዙ ሙዚቀኞች ዘፋኞች እና የዘፈን ስራ ላይ ተሰማርተዋል። እንደዚህ ዓይነት ክፍተቶች እንዳይፈጠሩ ቤተክርስቲያን ተገቢውን ትኩረት ማድረግ አለባት።
ቤተክርስቲያን በመዝሙር አገልግሎት እግዚአብሔርን የምያገለግሉ ሙዚቀኞች ሁለንተናዊ ሥልጠና የሚሰለጥኑበት ተቋም መገንባት አለባት ብየ አስባለሁ(ያሉትንም ማጠናከር ያጠቃልላል)። የሙዚቃ ትምህርት እየተማሩ በጎን የሥነ መለኮት ትምህርት የሚማሩበትን
አማራጮችን ማዘጋጀት ያስፈልጋል። ሙዚቃ ብቻ ተምረው ሕይወታቸውን የሚመሩበት
መንፈሳዊ እውቀት ካላገኘ ሰይጣን ጥቃቅን ምድራዊ ጉዳዮች በማቅረብና በማማለል ወደ ዘፈን
እና ዓለም እንዳያስገባ ጥንቃቄ እና ተገቢ ክትትል ማድረግ ያስፈልጋል።
ክትትል ብቻ ሳይሆን ሰልጥነው የመጡ ሙዚቀኞች በአጥቢያ ቤተክርስቲያን አቅም በቂ ቀለብ
ሊሰፈርላቸው ይገባል ብዬ አስባለሁ።

4.እቅበተ እምነት አገልግሎት ማጠናከር

እቅበተ እምነት አገልግሎት ማለት የተለያዩ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሙግቶችን በማዘጋጀት
መሰረታዊ የክርስትና አስተምህሮን ከስሕተት ትምህርቶችና ልምምዶች መመከት ነው።
መከላከል ላይ ትኩረት ያደረገ አገልግሎት ነው።
ሐዋሪያው ጴጥሮስም በመልዕክቱ “ለሚጠይቁአችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ...” (1ኛ ጴጥ 3፡15) ብሎ ሁሉም ክርስቲያን እምነቱ ላይ የሚቃጣ ኑፋቄን መመከት(መከላከል) እንደሚጠበቅበት ይናገራል።ክርስቲያን መከላከል ብቻ ሳይሆን ሄዶ ማጥቃት አለበት።

“ፖሌሚክስ”/Polemics የመጣውን የኑፋቄ ትምህርት መከላከል ሳይሆን ሄዶ ማጥቃት ነው። ሐዋሪያው ጳውሎስ የማይታወቅ አምላክ የሚያመልኩ የአቴና ሰዎችን ሄዶ የማይታወቀው አምላክ በማን እንደታወቀ እና ራሱን እንደገለጠ ተናገራቸው። 37 በቆሮንቶስ መልዕክቱም“የሰውንም አሳብ በእግዚአብሔርም
እውቀት ላይ የሚነሣውን ከፍ ያለውን ነገር ሁሉ እናፈርሳለን ለክርስቶስም ለመታዘዝ አእምሮን
ሁሉ እንማርካለን” (2ኛ ቆሮ 10፡5) ብሎ የሚከላከል ብቻ ሳይሆን ሄዶ የሚያፈርስ፣ የሚያጠቃና የሚማርክ “ፖሌሚክስ” አገልግሎት እንደሚያስፈግ እንመለከታለን።
የቤተክርስቲያን እቅበተ እምነት(በዘፈን ጉዳይ) መመንጨት ያለበት ከእምነቷ መሆን አለበት።
እምነቷን ለመመከት ቁርጠኝነቱ ከሌላት፣ እምነቷ ከንቱ ነው። በትክክል እምነት ሲኖራት አይ፣
እምቢኝ የምትለው ነገር ይኖራታል። እዚህም፣ እዛም አትጣድም። ወይ እዚህ ነህ ካልሆነም እዛ ነህ ትላለች። ወይ ዘምር አልያም ዝፈን ትላለች። “ዘፈን ኃጢአት አይደለም፣ መርጠን እንዝፈን” የሚሉ ትምህርቶችን መከላከል ላይ ብቻ ሳይሆን ማጥቃት ላይም መስራት
ይጠበቅባታል። የወንጌላዊያን ዓቅበተ እምነት/Apologetics ብዙ ጊዜ መከላከል ላይ
ያተኩራል። ፖሌሚክስ ላይም ትኩረት መደረግ አለበት። እቅበተ እምነት ያለ ፖሌሚክስ
አገልግሎት ስኬታማ ላይሆን ይችላል።
ስለዚህ ቤተክርስቲያን እንደ አንድ ኃላፊነት እንደሚሰማው መንፈሳዊና ምድራዊ ተቋም ቁጭ
ብላ ልትመክርበትና ምትክ የሌለውን እምነቷንና አቋሟን በይፋ ልታቀርብና እርምጃ ልትወሰድ
እንዲሁም የእቅበተ እምነትና ፖሌሚልስ አገልግሎት በአጥቢያ ደረጃ እንደ አንድ አገልግሎት
ክፍል ወይም ዩኒት ማደራጀት አለባት ብየ አስባለሁ።
@amlkoo
@amlkoo
@amlkoo

Читать полностью…

እናመልክሃለን

ዘማሪ ምናሴ እና ዘማሪ ሃብታሙ በታዲያስ አዲስ የራዲዮ ፕሮግራም ላይ !

ሰሞኑን በብዙዎቹ ዘንድ ተወዳጅነት ያተረፈው "አንተ ማለት ለኔ" የተሰኘው ዝማሬ ዘማሪዎች ምናሴ እና ሃብታሙ በታዲያስ አዲስ የራዲዮ ፕሮግራም ከሰይፉ ፋንታሁን ጋር ያደረጉትን አጭር ቆይታ እነሆ ጋበዝናችሁ።😍🎄🔥🎄
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@amlkoo
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@amlkoo
#ሼር

Читать полностью…

እናመልክሃለን

ዲና{DINA}
{ተከታታይ ልበወለድ}

✍written by Aksan Adane

PERESENT BY #እናመልክሀለን

ክፍል 1⃣

ዲና እባላለሁ የተወለድኩት ሀዋሳ ከተማ ውስጥ ነው አሁን የምኖረው ግን ቡታጅራ ከአያቴ እበርአምሹ ጋር ነው እኔ ግን ታትዬ ነው የምላት ታትዬ የእናቴ እናት ናት ከእናቴ ተለይቼ ወደ ቡታጅራ የመጣሁት በ2 አመቴ አባቴ ጥሎን እንደጠፋ ይሙት ይኑር እንደማይታወቅ ተነግሮናል በሰአቱ ምንም ስራ ያልነበራት እናቴ እኔን ለማሳደግ ሰው ቤት መስራት ጀምራ ግን የምትገባበት ቤት ሁሉ ልጅ ይዛ መስራት እንደማትችል እየነገሩ ያባሩአታል የዚህኔ አያቴ ታቲዬ ወስዳኝ ከሷ ጋር ነው ምኖረው እናቴ አሁን ላይ ሰፈር ውስጥ አነስተኛ ሱቅ ከፍታ ትተዳደራለች እረፍት እረፍት እየሄድኩ እጠይቃታለሁ የእናቴ ታላቅ ወንድም አሜሪካ ነው የሚኖረው ደልቶት ይሁን ቸግሮት እንደሚኖር አላውቅም በስንት አመት አንዴ ለታትዬ ብር ይልክላታል ከእናቴ ጋር በአባት ስለሚለያዩ አብረው አላደጉም እሱ ከአባቱ ጋር እናቴ ከታትዬ ጋር ነው ያደጉት ለዚህ ይሁን መፈጠሯን እንኳን ረስቶታል ታትዬ ኦርቶዶክስ ናት እኔ ደግሞ ቸርች ውስጥ ባላገለግልም ከትምህርቴ ጎን ለጎን መዝሙሮች እፅፋለሁ እፀልያለሁ መፅሀፍ ቅዱስ አነባለሁ በቃ የእግዛብሔርን ህልውና እወደዋለሁ ምህረት እና ሰገነት የትምህርት ጓደኞቼ ናቸው ሁለቱም ከእኔ በተሻለ ቸርች ውስጥ ያገለግላሉ በሙሉ ወንጌል ቤተክርሰቲያን እኔ ግን ወደ አገልግሎት ባልገባም አምልኮ በሚኖርበት በማንኛውም ቀን እሄዳለሁ ግን ሁሌ የሚያናድደኝ ሶስታችንም ክርስቲያኖች ሆነን ከአህዛብ ጓደኞቻችን ጋር ስንሆን ክርስትና ሚባል ነገር ይረሳል
ወሬ እንቀይር ደስ አይልም ስላቸው የኛ ፓስተር እያሉ ያሾፉብኛል ቆይ ማነው ፓስተር ብቻ በቅድስና ይመላለስ ያለው ሆሆሆ ደግሞ በመድረክ ዙሪያ እያገለገሉ እንዲ መሆናቸው ያናደኛል ቸርች ሌላ ሰው ትምህርት ቤት ከአህዛብ ጋር ተመሳስለው ይውላሉ ብቻ እግዚያብሔር አይኖቻችንን ያብራ ።

ዛሬ ቀኑ እሁድ ነው ታትዬም በጠዋት ቤተክርስቲያን በጠዋት ስለምትሄድ እኔም በጠዋት ተነስቼ ሰአቴ እስኪደርስ ቤቱን አፅድቼ ቡና አፈላልቼ ጠብቃታለሁ ታትዬ ከምታከራየው 5 ክፍል ቤት ውጪ ሌላ መተዳደሪያ የላትም እኔንም በዚሁ ነው ምታስተምረኝ ደሞ ምትገርመኝ ቤት ውስጥ መዝሙር ስከፍት ኡኡ ትላለች ለዛ ታዝናናኛለች በዛ ላይ ፍቅር የሆነች ናት ከኔ ጋር መጫወት መላፋት ያስደስታታል ስለወንጌል ሳነሳ ግን ኦኦ ትቀያየራለች ቢሆንም ተስፋ አልቆርጥም ቀስ እያልኩ ነዘንዛታለሁ እና እሷ በጠዋት ሄዳለች እኔም ቸርች ሰአቴ ደርሷል ግን ታትዬ ቆየች ሌላ ቀን እስከ 2:30 ትመለስ ነበር አሁን 3:00 ሆኗል እኔም ሰአት እያለፈብኝ ነው ምን ሆናብኝ ይሁን ........

................ይቀጥላል................

✍written by Aksan Adane

━━━━✦✗✦━━━━━━
⇲⇲⇲⇲ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲
አዘጋጅ፦
⇨ @amlkoo
⇨ @amlkoo
⇨ @amlkoo
─── ❖ ── ✦ ── ❖ ───
👆👆👆join&shear👆👆👆

Читать полностью…

እናመልክሃለን

. ኢየሱስ
ዘማሪት ፂዮን ተስፋዬ

New Amazing Cover Song
ሼር በማድረግ ለወዳጆ ያካፍሉ
sʜᴀʀᴇ💯 sʜᴀʀᴇ 💯 sʜᴀʀᴇ💯
@amlkoo
@amlkoo

Читать полностью…

እናመልክሃለን

ስትከታተሉን ስለነበር ከልብ እናመሰግናለን ከዚህ በኃላም አብሮነታችሁ አይለየን።
ከ እንዘምር ወይስ እንዝፈን የሚለው መፀሀፍ በዚህ ተጠናቋል በሚቀጥለው ሰኞ ጀምሮ ዲና የተሰኘ አሪፍ ልበ ወለድ እንጀምራለን እስከዛው አብሮነታችሁ አይለየን

የደራሲውን አድራሻ ለምትፈልጉ👇

ቴሌግራም👇👇
http፡//t.me/LeulLemaPulpit

ኢሜል
leullema2009@gmail.com

ፌስቡክ
Leulseged Lema

Читать полностью…

እናመልክሃለን

🎬 METI ABERA BESELAM "በሰላም" Cover of Tamirat Haile song Ethiopian protestant Mezmur 2021/2013 !!!

🕙 07:51 💾 30.7 MB

Join us 👇👇👇
@amlkoo
@amlkoo

Читать полностью…

እናመልክሃለን

🔳Jesus
🔳The way of life and truth
🔳 @drum4Christ

Читать полностью…

እናመልክሃለን

. "ቃልኪዳን"
ኬልቅያስ ግርማ | New Clip
🕒-6:42Min | 💾-25.0MB
Share 📲 Share 📲 Share
@amlkoo
@amlkoo

Читать полностью…

እናመልክሃለን

. "ባንተ ደስ ይለኛል"
ዳንኤል አምደሚካኤል | Worship
🕑-9:06Min | 💾-36.3MB
Share 📲 Share 📲 Share
@amlkoo
@amlkoo

Читать полностью…

እናመልክሃለን

የምዕራፍ ሶስት ማጠቃለያ ሀሳብ

1. ሦስት ምርጫ የለም። ዘፈን
ወይም መዝሙር ምረጥ?!

2. በጎ ነገር ብንናገር መጥፎ አይደለም። በጎ ነገር ለመናገር መዝፈን አለብን ወይ?

3. መጽሐፍ ቅዱስ ዘፈንን ሙሉ ለሙሉ ስለከለከለ፣ ሙሉ ለሙሉ ልንከፍተው አንችልም።

4. የማንዘፍንበት ስምንት ምክንያቶች፦

 ኃጢአት ስለሆነ

 የእምነት አባቶች ስላልዘፈኑ

 ከማንነታችን ጋር ስለማይሄድ

 ስለማያንጽ

 ከጥሪያችን ጋር ስለማይሄድ

 ከአምልኮ ጋር ስለማይሄድ

 ከወንጌል ምስክርነት ጋር ስለማይሄድ

 ለመንፈሳዊ ውጊያ ስለማይጠቅመን

@amlkoo
@amlkoo
@amlkoo

Читать полностью…

እናመልክሃለን

Music 4 Gospel
Music4Gospel
ሙዚቃ ለመላክ👇
@Robitomtom
/channel/music4gospel

Читать полностью…

እናመልክሃለን

Drum for worship
"If any man among you seem to be religious, and bridleth not his tongue, but deceiveth his own heart, this man's religion [is] vain."
(James 1:26)
/channel/drum4christ

Читать полностью…

እናመልክሃለን

የምዕራፍ አንድ ማጠቃለያ ሀሳብ

1. መዝሙር መንፈሳዊ ነው።

2. መዝሙር ከሰው ለሰው ያልሆነ፤ ከሰው ለእግዚአብሔር የሆነ መስዋዕት፣ ውዳሴ፣ ምስጋና፣
አምልኮና ክብር ነው።

3. መዝሙር ከተቀደሰ ማንነት የሚመነጭ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ግጥምና ዜማ ነው።

4. የመዝሙሮች መመዘኛዎች፦

 የዘማሪው ማንነት፤

 መጽሐፍ ቅዱሳዊ ግጥምና ዜማ፤

 የምትታነጽበት፣ ሌሎችም የሚታነጹበት፤

 መጸለይን ወይም ማምለክን ወይም ማመስገንን የሚያስከትል መሆን አለበት፤

 እርስ በርስ የምንዘምረው መሆን አለበት።

@amlkoo
@amlkoo
@amlkoo

Читать полностью…

እናመልክሃለን

Today's quotes

Psalms 23

¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ The LORD is my shepherd; I shall not want.
² He maketh me to lie down in green pastures: he leadeth me beside the still waters.
³ He restoreth my soul: he leadeth me in the paths of righteousness for his name's sake.
⁴ Yea, though I walk through the valley of the shadow of death, I will fear no evil: for thou art with me; thy rod and thy staff they comfort me.
⁵ Thou preparest a table before me in the presence of mine enemies: thou anointest my head with oil; my cup runneth over.
⁶ Surely goodness and mercy shall follow me all the days of my life: and I will dwell in the house of the LORD for ever.

Читать полностью…

እናመልክሃለን

ውዶች በቅርብ ቀን እጅግ ልብ አንጠልጣይ <<ዲና>> የተሰኘ መንፈሳዊ ልብወለድ ይዘንላችሁ እንቀርባለን ፡፡ የትም እንዳትሄዱ እሺ ውዶች 😳😳😳፡፡
😘😘👈 ነው ምናደርጋችሁ፡፡

ለአስተያየት @Isabelle1992 ተጠቀሙ፡፡

Читать полностью…

እናመልክሃለን

ምዕራፍ አራት

ክፍል አንድ

ቤተክርስቲያን ምን ታድርግ?

ቤተክርስቲያን ምዕመኖቿን ከተጋረጠባቸው የ"ዘፈናምነት"
አደጋ የመከላከል ውዴታዋ ብቻ
ሳይሆን ግዴታዋም ጭምር መሆኑን መረዳት ይኖርባታል። ይህንን አደጋ መከላከል የምትችለው አማኞችን ደቀመዝሙር በማድረግ፣ ዘማሪዎች ከቃሉ እንዲዘምሩ በማድረግ፣ ለሙዚቀኞች
ተገቢውን ትኩረት በመስጠት እና እቅበተ እምነት አገልግሎት በማጠናከር ይመስለኛል።

1.አማኞችን ደቀመዝሙር በማድረግ

ደቀመዝሙር ማለት የተማረ ማለት ሳይሆን የሚማር ተማሪ ወይም በመማር ሂደት ላይ ያለ
ማለት ነው። ደቀ መዝሙር ቀን በቀን መምህሩን ለመምሰል በመምህሩ ትምህርትና አስተሳሰብ የሚቀረጽና የሚቃኝ ማለት ነው። እንደ መምህሩ የሚኖር፣ የሚያስተምር፣ የሚያስብ፣
የሚያገለግል የሚራመድ፣ የሚያወራ፣ የሚበላ፣ የሚሰራ… ወዘተ መላው እንቅስቃሴው እንደ
መምህሩ የሆነ እርሱ እውነተኛ የመምህሩ ደቀ መዝሙር ነው። መምህሩ በውስጡ የሚታይ
እርሱ እውነተኛ ደቀመዝሙር ነው።
ቤተክርስቲያን ምዕመናንን ደቀመዝሙር እንዲሆኑ ትኩረት አደርጋ መስራት አለባት።
በየትኛውም የአገልግሎት ዘርፍ ከመሰማራት በፊት የሚቀድመው ደቀ መዝሙር መሆን ነው።
ደቀ መዝሙር የሆኑ አማኞች ስለሌሉን ነው የአስተምህሮ ጥራት፣ የህይወት ጥራት እና
የልምምድ ጥራት የጎደለው። የአማኞች ደቀ መዝሙር ያለሆነ ህይወት በቤተክርስቲያንም
አቅም ላይ አሉታዊ ተፅኖ እየፈጠረ ነው ያለው። ስለዚህ ቤተክርስቲያን ከፊቷ ያለውን ዘፈናምነት አደጋ ለመትረፍ አማኞችን ደቀመዝሙርት ማድረግ አለባት።

2.ዘማሪዎች ከቃሉ እንዲዘምሩ በማድረግ

ክርስቲያን ዘማሪያን ቀጠሮ ስለማክበር፣ ስለወንድማማችነት ፍቅር አስፈላጊነት፣ ስለቤተሰብ
ፍቅር፣ ጠንክሮ ስለመሥራት ወዘተ (እንዲዘምሩ ማድረግ የእነዚህ ነገሮች ሁሉ መሠረት አምላካችን እግዚአብሔር እንደ ሆነ በሚያስገነዝብ መልኩ)
ችግሩ የአማራጭ መዝሙሮችን
ማጣት፣ ወደ “መርጠን እንዝፈን” ወስዶን ከሆነ፣ መዝሙሮቹን እኛው ብናዘጋጃቸው ለተጋረጠብን “ዘፈናምነት” አደጋ መፍትሔ ሊሆን ይችላል ለማለት ነው።
@amlkoo
@amlkoo
@amlkoo

Читать полностью…

እናመልክሃለን

ምዕራፍ ሶስት

ክፍል አስር

8. ለመንፈሳዊ ውጊያ ስለማይጠቅም

“ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ ከእናንተም ይሸሻል።” (ያዕ 4፡7)
ዲያብሎስን ለመዋጋት ሁለት ነገር ማድረግ ያስፈልጋል። ለእግዚአብሔር መገዛት እና
ዲያብሎስን መቃወም ለውጊያ በጣም ወሳኝ ነው። ለእግዚአብሔር መገዛት ማለት ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ነው። ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ የዲያብሎስን ነገር ማስወገድ
ያስፈልጋል። ሥጋን ይዞ ውሻን ማባረር እንደማይቻል ሁሉ እየዘፈኑ ከሰይጣን ጋር መዋጋት
አይቻልም። የሰይጣንን ንብረት የሆነውን ዘፈን መጣል ግዴታ ነው። ስምንተኛው የማንዘፍንበት ምክንያት ለመንፈሳዊ ውጊያ ስለማይጠቅም አንዘፍንም! በቃ!

ሦስት ምርጫ የለም
በየ መንገዱ ወራጅ ሞልቷል ተሳፋሪ፤
ከጠጣ በኋላ ወጭቱን ሰባሪ፤
ትናንትናን አትርሳ አትሁን ውለታ ቢስ፤
ገባ ወጣ አትበል ጸንተህ ቁም በየሱስ፤
ያዝ ለቀቅ ሔድ መጣ ገባ ወጣ፤
ሕይወት ትርጉም ሲያጣ፤
ወይ ከየሱስ ወይ ከዓለም
ምረጥ እንጂ፤ ሦስት መንገድ የለም።

“በፊታችሁ ሕይወትንና ሞትን በረከትንና መርገምን እንዳስቀመጥሁ እኔ ዛሬ ሰማይንና ምድርን በአንተ ላይ አስመሰክራለሁ፤ እንግዲህ አንተና ዘርህ በሕይወት ትኖሩ ዘንድ ሕይወትን ምረጥ።
” (ዘዳ 30፡19)
ዘዳግም ምዕራፍ ሥላሳ ከቁጥር አንድ ጀምሮ እስከ አስር ወደ እግዚአብሔር በመመለስ
ስለሚገኝ በረከት ይናገራል። ከቁጥር አስራ አንድ ጀምሮ በእስራኤላያዊያን ፊት ሁለት ምርጫ እንደቀረበላቸውን መጽሐፍ ይናገራል። በረከት እና መርገም። በሕይወት ትኖሩ ዘንድ ስለናንተ ሕይወትን መርጭያለሁ አይልም። ሕይወትን ምረጡ ብሎ ምርጫቸውን እንዲጠቀሙ
ይመክራቸዋል።
ዘማሪ(መጋቢ) ታምራት ኃይሌ“ሦስት መንገድ
የለም” ብለው እንደዘመሩ ሶስት ምርጫ የለም። ከሁለቱ ሌላ ምርጫ የለም። ሶስት መንገድ
እና ሶስት ምርጫ የለም። ምርጫው ግልጽ ነው። መዝሙር ወይም ዘፈን ነው።ዛሬም ለክርስቲያኖች መዝሙርና ዘፈን የምርጫ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የሕልውና ጉዳይ ነው።
ለእስራኤላዊያን በረከትና መርገም ምርጫ እንደሆነላቸው መዝሙርና ዘፈንም ለአማኞች ምርጫ ነው። እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ፈቃድ ሰጥቷል። ፈቃዱ ፈቃዳችን እንዲሆን የእግዚአብሔር ፈቃድ የሆነውን መዝሙር መምረጥ አለብን። ምንም እንኳን ተጽዕኖዎች ቢኖሩም ክርስቲያን ፈቃዱን ተጠቅሞ የፈለገውን የመምረጥ መብት አለው።
@amlkoo
@amlkoo
@amlkoo

Читать полностью…
Subscribe to a channel