amu6380 | Unsorted

Telegram-канал amu6380 - Amir Abdo official 📸📸📸

-

አሰላሙኣለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ ሙሂቦች በዚ ቻናል ላይ ሙሂቦች ይዳሰሳሉ የተለያዩ ቁምነገር የሚያስጨብጡ ምስሎች ፣ ፁፎች እንዲሁም አዳዲስ መንዙማዎች ይለቀቃሉ የናንተው አሚር @Ame6380 @amirabdo1

Subscribe to a channel

Amir Abdo official 📸📸📸

👆👆👆Share share share.....
2ቱ ወንድማማቾች አዲስ ነሺዳ ❤"መልኩ ሸጋ"❤ ሀሙስ ማታ ይጠብቁን።

Читать полностью…

Amir Abdo official 📸📸📸

ኢላሂ! እኛ አንተ በአዘል የወሰንከውን ሁሉ አምነን ተቀብለናል።አንተ ይሁን ባልከው ጊዜ ሁሉም ነገር ይሆናል።የአንተ ውሳኔ ምንጊዜም ተፈፃሚ ነውና
ኢላሂ! ወዳጃችንን፣ሸይኻችንን፣ልበ ቀናውን፣ በፈገግታ የተሞላ አንደበተ ርቱዕ ወንድማችንን ሸይኽ አሕመድ ሙሐመድን አንተ በወሰንከው ጊዜና ሰአት ደቂቃና ሰከንድ እነሆ በሞት አጥተናቸዋል።
ﺇﻧﺎ ﻟﻠﻪ ﻭﺇﻧﺎ ﺇﻟﻴﻪ ﺭﺍﺟﻌﻮﻥ
አሏህ ለዲን የሚለፋ ባሪያውን አጅር አያጠፋምና እነሆ መኖሪያቸውን ጀነት ያደርገው ዘንድ እንማፀነዋለን
ﺇﻧﺎ ﻟﻠﻪ ﻭﺇﻧﺎ ﺇﻟﻴﻪ ﺭﺍﺟﻌﻮﻥ
በያላችሁበት በመልካም ዱዓችሁ አትርሷቸው።ፋቲሐ ቅሩላቸውና ሰዋቡን
አድርሱላቸው።አሏህ ምንዳውን ይክፈላችሁ !
ﺇﻧﺎ ﻟﻠﻪ ﻭﺇﻧﺎ ﺇﻟﻴﻪ ﺭﺍﺟﻌﻮﻥ😭😭😭

Читать полностью…

Amir Abdo official 📸📸📸

ኢናሊላህ ወኢና ኢለይሂ ራጅዑን
የገታ ሐሪማ ኸሊፋ የሆኑት
ሸህ ሙሒዲን ገታ አልፈዋል አሏህ ይዘንልን !
አልፋቲሃ!

Читать полностью…

Amir Abdo official 📸📸📸

በ 48hr ሰአት 15k view እናመሰግናለን!!! 💚🙏😍⬇️
https://youtu.be/ySPBZOOHcNA

Читать полностью…

Amir Abdo official 📸📸📸

ሙራዲና 2 Muradina 2 አሚር ሁሴን & ሰለሀዲን ሁሴን ( 2ቱ ወንድማማቾች ) አዲስ የመንዙማ ቪዱዮ ክሊፕ
https://youtu.be/ySPBZOOHcNA

Читать полностью…

Amir Abdo official 📸📸📸

ሙራዲና 2 Muradina 2 አሚር ሁሴን & ሰለሀዲን ሁሴን ( 2ቱ ወንድማማቾች ) አዲስ የመንዙማ ቪዱዮ ክሊፕ ⬇️
https://youtu.be/ySPBZOOHcNA

Читать полностью…

Amir Abdo official 📸📸📸

#መራዲና ቁ - 2
ክፍል አምሰት
#ማክሰኞ_ምሽት

#አበል_ሐሠን ጀኔ ሙራድ ጌኜ
ኑረ ዛቲ ኬሠኒ ኡፈኔ
አሸነፍኔ በላ ሜቃተማ
ይህ ግጥም ከአዲሱ ሙራዲና መንዙማ ላይ ያለ ነዉ መጀመሪያ እንደሠማሁት ነበር ከሌሎች ግጥሞች በተለየ የወደድከት ከዚህ በፊትም ዝም ብዬ በተደጋጋሚ ግጥሙን ማለት ያስደስተኝ ነበር ዛሬ ላይ ግን ይህን ግጥም እንደ ወትሮዉ በቀላሉ ለማለት አልቻልኩም #ለካ በምክንያት ሲባል ስሜቱ ጥልቅ ነዉ ፣ ልብን ያርዳል ፣ አይንን ያስለመልማል ፣ ከሀሳብ ትዝታ ጥግ አድርሶ ይመልሳል ዳግም..... ..
........ .. ጅማ ለቀረፃ ከገባን አንስቶ ከቀረፃዉ እሰከ ዛሬ በሙራዲና ክሊፕ ስራ እና ጎን ለጎን በኢሽቅና በመደድ ለይሉን በቅጡ ካረፍን አንድ ወር ሊሞላን ነዉ
የፊት ለፊታችን ያለዉን ግድግዳ ሰዐት ቀና ብዬ ስመለከት ገና ከምሽቱ ሁለት ሠዐት ነዉ ነገር ግን ከወትሮ በተለየ የዛሬዉ ምሽት ግን ከሌላዉ ቀን በተለየ እጅግ ደምቋል እኛ ባለንበት ክፍል ዉስጥ ሳቅ ጨዋታ ደስታ ሁሉም ሠዉ ፊት ላይ ይነበባል ከዚህም በዘለለ ከሌላዉ ቀን በተለየ ሁኔታ አብዛኞቻችን እግራችን ዘርግተን ነዉ የተቀመጥነዉ እኔ እንደ ግል የገባኝ ነገር ቢኖር የሙራዲና ክሊፕ ስራዉ ምን ያህል ጭንቅ እንደነበር እና እግርም ጭምር እንደማያዘረጋ #ልብ ብያለዉ የመጨረሻዉ ሙራዲና ቁ.2 ክሊፕ ቪዲዮ ምልከታና ሳንሱር ሁላችንም በተገኘንበት ተመልክተን ስናበቃ እንከን አልባ ስራ ነዉ ለመንዙማዉ ማህበረሰብ ይመጥናል ብለን በሙሉ ድምፅ ያለምንም ድምፀ ተሀቅቦ ወሰንን
ነገር ግን አሁንም የመጨረሻ አንድ ሰዉ እይታ እና የይሁንታ ፈቃድ መጠባበቅ ይዘናል የተባለዉ ሰዐት ደርሶ እኛ ወዳለንበት ክፍል ዘለቁ
ሁላችንም ከመቀመጫችን ተነሳን ..........
...........................አልቆ ሲወጡ አሁንም በድጋሚ ከተቀመጥንበት ተነስተን በክብር ሸኘናቸዉ፡፡
ለግማሽ ሰዐታት ሰዉ የሌለበት ባዶ ክፍል ይመስል የነበረዉ ፀጥታ ወደ ቀድሞዉ ቦታዉ ተመልሷል ሁሉም ላይ ደስታ ይነበብ ነበር።
በዚህ በሙራዲና ስራ አንድ ግቢ ዉስጥ ከትመን በአንድ ጎጆ ዉስጥ እንደ ቤተሰብ ሆነን መኖር ከጀመርን አንድ ወር ሊቆጠር ነዉ ሁላችንም ግን ግኝታችን ከተለያየ አቅጣጫ ከተለያየ ቤተሠብ ነዉ ስብስባችን ፡፡
ከኛ መሀል ደግሞ አንድ ሰዉ አለ በስነምግባሩም ልዩ በስራዉም ታታሪ ነዉ
ይህ ሰዉ ወንድማችን #ሱራፌል_ተክሌ ይባላል በኢትዮ ነሺዳ ዩ ትዩብ ቻናል የሚሰሩ መንዙማና ነሺዳዎችን ቪዲዮ ክሊፕ ኤዲቲንግ ሚሰራዉ ይህ ወጣት ብላቴና ነዉ።
ከሙራዲና አንድ አንስቶ ለመዉሊድ የተሰሩትን በአሚር እና ሳላ ዩትዩብ የተለቀቁት ክሊፖች የሱ እጅ ያረፈባቸዉ ናቸዉ።
ከእኔ ጋር የመጀመሪያ ትዉዉቃችን ጅማ ከተማ ሲሆን ሙራዲና ቁ.1 ሲሰራ ነዉ ሡራፌል ኤዲተሩ እሡ ነዉ ብለዉ ሲያስተዋዉቁኝ #በዉስጤ_እየቀለዱ መሆን አለበት እነዚህ ሰዎች ብዬ አሰቤ ነበር ያን ወቅት ምክንያቱም ሱራፌልን ሣየዉ በእድሜዉ ትንሽ ልጅ ነዉ ሀያዎቹ መጀመሪያ ያለ እንደሆነ ፊቱ ይመሰክራል
እኔ ከዚህ በፊት አብሬያቸዉ የሰራኀቸዉ ቪዲዮ ኤዲተሮች ከዚህ በተቃራኒዉ በእድሜያቸዉ ጠና ያሉ: ቦሮጫም :ፀጉራቸዉ የሸሸ
................ሆኖም ሱራፌል ከሶስቱም ከጠቀስቋቸዉ ገፅታዎች አንዱን እንኳ አያሟላም ነገሩ አልዋጥ ቢለኝም የሚሆነዉን ልይ ብዬ ወሠንኩ ............
........... ልጁ አምብዛም ማያወራ ሙሉ ትኩረቱን ስራዉ ላይ የሚያደርግ እና በችሎታዉ ከዚህ በፊት ከማዉቃቸዉ አብሬያቸዉ ከሰራኀቸዉ ባለመያዎቸች የተሻለ ሳይሆን የበለጠ ሆኖ አገኘዉት .........
በግሌ ሡራፌል እስካሁን ከሰራቸዉ የመንዘማ ክሊፕ ስራዎች ደሞ #ሙራዲና #ቁ.2 እጅግ የተዋበ እና አቻ ማይገኝለት ልዩ ስራ ነዉ
ይህን ፅሁፍ ሙራዲና ክሊፕ ሐሙስ ምሽት 1:00 ሰዐት ከተለቀቀ በዋላ ያለዉን የሠዉን አስተያየት ምን ይመስላል ከሚለዉ ጋር አያይዤ እቀጥለዋለዉ

✍ጎራዉ ነኝ ከጅማ

Читать полностью…

Amir Abdo official 📸📸📸

#ሙራዲና ቁ.2 በጉጉት እየጠበቃቹ ላላቹ ውድ የኢትዮ ነሺዳ እና መንዙማ ቤተሰቦች ሀሙስ ምሽት 1:00 ሰአት ላይ በYouTube ይጠብቁን!

Subscribe 🔔 ⬇️⬇️⬇️
https://www.youtube.com/ethioneshidamenzuma

https://youtu.be/q3POWTH_P1Q

Читать полностью…

Amir Abdo official 📸📸📸

ሙራዲና 2 የዛሬ ሳምንት (ሀሙስ) ይጠብቁን!

Читать полностью…

Amir Abdo official 📸📸📸

ሙራዲና 2 በቅርብ ቀን Muradina 2 coming soon ⬇️
https://youtu.be/q3POWTH_P1Q

Читать полностью…

Amir Abdo official 📸📸📸

#ክፍል_አንድ
#ሙራዲና ቁ-2 ....Loading

ፍቅር ደስ ደስ መዉደድ ደስ ደስ
ከሙራዲና ሁለት ስንደርስ

የዛሬ አመት አሀዱ ብለን ሙራዲና አንድ ብለን ጀምረን ብዙሀኑን የመንዙማ ቤተሠብ እንዳስደሰትነዉ ሁላ የኛም ሙራዳችን ጨምሮ ሙራዲና #2 ብለን ቀጥለናል!
ሙራዲና እና ጅማ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸዉና ሳላና አሚር የድምፅ ቅጂ ጨርሠዉ ልዩ የሆነ የመንዙማ ክሊፕ ለመስራት ነገ ጅማ ይገባሉ : :
#በነገራችን ላይ
ሙራዲና #1 ሙራዲና #2 ...3.... 4 ........
እያለ ሚቀጥል ስራ ነዉ በዐመት ዐመት እየቀጠለ ሚሄድ ነዉ ማለት ነዉ። ይህ አይነት ስራ በሌሎቹም ማዲሆች ቢሠራ ኸይር ነዉ እላለዉ።
ሁሌም የኸይር ነገራቶች ፈር ቀዳጅ መሆንን በግሌ እመርጣለዉ መንዙማ ወዳድ ለሆነዉ ማህበረሰብ ሁሌም በተሻለ ስራ እና ብቃት አዲስ ነገር ማሰማት የሁልግዜም ሙራዳችን ነዉ
እንደ ባለፈዉ ሁላ ይህን የቪዲዮ ክሊፕ ለመስራት ከጅማ ወንድሞቻችን ከ @Ethio_Neshida & #Menzumawoch ጋር በመሆን ለመስራት ቀጣዮቹን ሳምንታት በጅማ ከተማ በሠይድ ጠለሀ (ሞቲ) ቤት እንከትማለን።
እንደተለመደዉ ስለ ጉዞ ማስታወሻ በመያዝ ስለ ስራዎቻችን እና ገጠመኞቻችንን በተከታታይ ለእናንተ ወዳጆቻችን በፅሁፍ ምናካፍላቹ ይሆናል።
ዉድ የመንዙማ ወዳጆች የሡፊያ ቤተሠቦች ይኸዉ ሳላ እና አሚር ለወራት ዝምታን መርጠዉ ከመድረክ ስራዎችም ጠፍተዉ አሁን ለረመዳን ለእናንተ ሚሆኑ ስራዎችን ለማቅረብ ደፋ ቀና ሲሉ ከርመዉ አሁን ወደ ማገባደጃዉ ላይ ደርሰዉ የምስል ቀረፃ ብቻ ቀርቶዋቸዋል.......

✍ጎራዉ ነኝ

Читать полностью…

Amir Abdo official 📸📸📸

አዲስ የመንዙማ ክሊፕ ሀሙስ ምሽት ይጠብቁን! ⬇️⬇️⬇️
https://www.youtube.com/ethioneshidamenzuma

Читать полностью…

Amir Abdo official 📸📸📸

© ከ Atiqa Ahmed Ali Facebook የተወሰድ
#ኸሚስ_አመሻሹ_ላይ!

አንድ የክፍለ ሃገር ሰው መሃል አገር ገብቶ ንብረቱ ተዘርፎ በሌላም በሌላም ነገር ተማሮ ወደ አገሩ ሊመለስ እንደተሳፈረ ዞር ሲል ሰማዩ ጠቋቁሮና ደመና አርግዞ ቢያይ "የታባቱ በልልኝ ይሄን ከተማ ጌታዬ!" አለ። ይሄ ወግ ትዝ ያለኝ ከሰሞኑ ግርግር በኋላ አንድ ወዳጄ "እኔማ እንደ በደዊኑ (የዓረብ ገጠሬ) ‘ጌታዬ ሆይ እኔንና ሙሐመድን ብቻ ምረህ ሌላውን ቅጣልኝ’ ትያለሽ ብዬ ነበር የጠበቅኩት።" ብሎ አስቆኝ ነው።😀
እነሆ የዓረቡ ገጠሬ ታሪክ…!
የኔ ውድ ነብይ ሰለዋቱ ረቢ ወሰላሙ ዓለይህ ‘አምር ቢልመዕሩፍ ወንነህይ አኒል ሙንከር’ ስለተባለ ብቻ ሰውን ከመጥፎ ለመከልከልና በመልካም ለማዘዝ በሚል አያስደነግጡም አያስደነብሩም!…የኔ ወለላ ሁሉን ሲያደርጉ ከማር በጣፈጠ መንገድ ነበር። ተግሳፃቸው ሆነ አስተምህሮታቸው የግብር ይውጣ እና ራስን ቅዱስ ሌላውን እርኩስ ያደረገ አይነት አይደለም! አዛኝና እጅግ ለስላሳ ነበሩ። ለዛም ነው

فَبِمَا رَحْمَةٍ مِّنَ اللَّهِ لِنتَ لَهُمْ ۖ وَلَوْ كُنتَ فَظًّا غَلِيظَ الْقَلْبِ لَانفَضُّوا مِنْ حَوْلِكَ ۖ فَاعْفُ عَنْهُمْ وَاسْتَغْفِرْ لَهُمْ وَشَاوِرْهُمْ فِي الْأَمْرِ ۖ
ያላቸው። "ከአላህም በሆነች ችሮታ ለዘብክላቸው። ዐመለ መጥፎ፣ ልበ ደረቅም በሆንክ ኖሮ ከዙሪያህ በተበተኑ ነበር። ከእነርሱም ይቅር በል። ለእነርሱም ምህረትን ለምንላቸው።"
ታድያ አንድ ጊዜ ምን ሆነ መሰላችሁ?…ያ የገጠር ሰው መስጅድ ውስጥ ገብቶ በአንዱ ጥግ ላይ ሽንቱን መሽናት ጀመረ። በዚህ ጊዜ ሰዎች ሁሉ ተንጫጩበት፣ ጮሁበት።
ያኔ ጥበብን እንደ ሸማ የደረቡት አዛኙ ነብይ "ተውት አታቋርጡት ይጨርስ!" አሉና ቦታው ላይ በባልዲ ውሃ አምጥተው እንዲደፉበት ሰዎችን አዘዙ። ከዚያም ተነስተው ወደ ሰውዬው በመሄድ "መስጅድ የሚገነባው አላህን ለማስታወስና ሶላት ለመስገድ ነው፤ ስለሆነም አይሸናበትም።" አሉት። ሰውዬውም ምክራቸውን እንደሰማ "አላህ ሆይ!እኔና ሙሐመድን ብቻ ማር ከእኛ ጋር ሌላ ማንንም አትማር!" አለ።😀
ውጤቱን ግን አያችሁ?!… ጥበብ፣ ሥነ ምግባርና እዝነት ሲጠፋ ሰዎች ሳያውቁት ለሙስሊሞች በአጠቃላይ ቀስ በቀስም ለኢስላም ጥላቻ ያድርባቸዋል፣ እንደ ውዴዋ በጥበብ መላሽ ካላገኘ ስንቱ ከመንገድ እንደወጣ፣ ስንቱ ከመግባት እንደታቀበ አላህ ይወቀው! ረሱልም ሰ.ዓ.ወ በሰውዬው ንግግር ፈገግ ብለው "ለሁሉም የሚዳረሰውን የአላህን ምህረት አጠበብከው!" አሉት።
ሰውዬው ከዚያ በኋላ እንዲህ ሲል ይሰማ ነበር…"ለነብዩ አባቴም እናቴም መስዋእት ይሁኑላቸውና ከመቀመጫቸው ተነስተው ወደ‘ኔ መጡ፤ አልሰደቡኝም፤ አልወቀሱኝም፤ አልመቱኝም!"
መርዝ የተባለ ሁሉ ወተትም ሀውድም በሆነው ዚክራቸው ይረክሳልና ወዳጆቻቸው ትካዜ አያገኛቸውም!
ፊዳከ አቢ ወኡሚ ያረሱለሏህ!
#ሶሉ_ዓለል_ሃቢብ!
አላሁመሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዓለይህ!💚💚💚
@Ethio_Neshida

Читать полностью…

Amir Abdo official 📸📸📸

#Muradina_2 loading...

Читать полностью…

Amir Abdo official 📸📸📸

ጉዞ ወደ ሰይድ አልፈኪፈ አህመድ ዑመር መንደር#Travel_Ethiopia #Sayid_Al_Fakih_Ahmed
⬇️
https://youtu.be/iiowclgHffI

Читать полностью…

Amir Abdo official 📸📸📸

Watch "{ መልኩ ሸጋ } 2ቱ ወንድማማቾች አዲስ ነሺዳ ሀሙስ ማታ ይጠብቁን! { Melku Shega } New Neshida ⬇️⬇️⬇️
https://youtu.be/EjlZZ9uh0V4

Читать полностью…

Amir Abdo official 📸📸📸

ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን

የሱፍዬች ፈርጥ የሆኑት ኡስታዛችን ሸይክ አህመድ ቻግኒ በድንገተኛ የመኪና አደጋ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ ።
ይህ አደጋ የተከሰተው የገትይ ኸሊፍ የሆኑትን የሀጅ ሙሂዲን የቀብር ስነ ስርአት ለመፈፀም ወደ ወሎ ኮምቦልቻ በሄዱበት አጋጣሚ ነው ።
አሏህ የጀነት ያድርጋቸው
ፋቲሃ እንቅራላቸው ።

Читать полностью…

Amir Abdo official 📸📸📸

sahiibal miraj 💚
Manzuma Sheh Bedradin
🥁👏🥁👏😍

Читать полностью…

Amir Abdo official 📸📸📸

https://youtu.be/ySPBZOOHcNA

Читать полностью…

Amir Abdo official 📸📸📸

ሙራዲና 2 Muradina 2 አሚር ሁሴን & ሰለሀዲን ሁሴን ( 2ቱ ወንድማማቾች ) አዲስ የመንዙማ ቪዱዮ ክሊፕ ⬇️
https://youtu.be/ySPBZOOHcNA

Читать полностью…

Amir Abdo official 📸📸📸

ሙራዲና 2 Muradina 2 አሚር ሁሴን & ሰለሀዲን ሁሴን ( 2ቱ ወንድማማቾች ) አዲስ የመንዙማ ቪዱዮ ክሊፕ
https://youtu.be/ySPBZOOHcNA

Читать полностью…

Amir Abdo official 📸📸📸

#ሙራዲና ቁ.2 በጉጉት እየጠበቃቹ ላላቹ ውድ የኢትዮ ነሺዳ እና መንዙማ ቤተሰቦች ሀሙስ ምሽት 1:00 ሰአት ላይ በYouTube ይጠብቁን!

Subscribe 🔔 ⬇️⬇️⬇️
https://www.youtube.com/ethioneshidamenzuma

https://youtu.be/q3POWTH_P1Q

Читать полностью…

Amir Abdo official 📸📸📸

ክፍል አራት
ሙራዲና ቁ -2
ከአንድ ወር በላይ የወሰደዉ #የሙራዲና ቁ-2 ክሊፕ አሁን ሁሉም ነገር ኤዲቲንግ ስራዉ አልቆ የዛሬ ሳምንት ሀሙስ ምሽት ለህዝብ ይደርሳል።
ይህ ሙራዲና ቁ-2 ከዚህ ቀደም ከነበረዉ ከሙራዲና አንድ የቀጠለ ሲሆን ስለ ታላቁ ሸህ አባ ቆሪቻ፣ዛሂዱ፣ወልዩ፣ተቅዩ፣አሊሙ #በጎፍታ_ደምቢ #ሰይድ_አልፈኪ_አህመድ_ዑመር ታሪክ ላይ ያተኮረ ነዉ
#ሙራዲና ቁ-2 መንዙማ ክሊፕ #አመታዊ ስራ እደመሆኑ መጠን የግዜያት እርዝማኔዉ 17 ደቂቃዎች ያህል የሚቆይ ነዉ በነዚህ ሙሉ ደቂቃዎች በዉስጡ ሶስት ልዩ ጣዕም ያላቸዉ ዜማዎች በተርታ ይቀያየራሉ
የመጀመሪያዉ እንጉርጉሮ ዘዉግ ያለዉ ሲሆን አዝማቹም
#ሠላሙን ሚን ረቢል ወራ አልፊ አልፊ መራ
ዐለይኩም ያሳዳቱና አህመድ ዑመራ

ይህ አሳዛኝ እንጉርጉሮ ስለ ሰይድ አልፈኪ ናፍቆት ትዝታ የሚያወሣ ይዘት ያለዉ ነዉ ለሁለት ደቂቃ ተኩል የግዜ እርዝማኔም አለዉ፡፡
ከዚህ ቀጥሎ ሞቅ ወዳለዉ የሐድራ ክፍል ያሸጋርና በሰልሀዲን ጅማሮዉን ያደርጋል
አዝማቹም
#አስከ_ሪዳ ወሠሊም ተስሊማ
አለይኩሙ ያጊያሰል ዑማ
ዘይና አልፈኪ ያሚዛበ ራህማ

ቅብብሉን ከአሚር ጋር ዉብ አድርገዉታል በዚህ ክፍል ዉስጥ ስለ አልፈኪ ሸሆች በተቻለን ባወቅነዉ ልክ ሲፋቸዉን ፣ ስነ ምግባር ፣ ለዲኑ የዋሉት አስተዋፅኦ ፣ ስለ #ተገናኟቸዉ_የሀበሻ_መሻኢኮች በከፊል ይጠቅሳል ይዳስሳል
ከዚህ በመቀጠል የመጨረሻዉ እና በአይነቱም #በቋንቋም ለየት ያለዉ #ሦስተኛዉ ክፍል ዜማ በአሚር ጅማሮ ያደርጋል
#ሰላሙላሂል ዋሊ አለይኩሙ ፊኩሊ ሀሊ
ዘይኒ ሠይድ ማህሙድ በድረ ጀማሊ
ይህ መንዙማ አብዛኛዉ ግጥሞች #በኦሮመኛ ሲሆኑ ከስድስት የማይበልጡ አማረኛ ግጥሞች ጣል ተደርገዉበታል የመንዙማዉ ታሪክ የሚያዉጠነጥነዉ ስለ #ሞቲ_ሰይድ_ማህመድ ናፍቆ፣በናፍቆት ላይ አሁንም መፅናት፣እሣቸዉን ለማየት መጓጓትን የሚያወሣ መንዙማ ነዉ
ለዚህ ድንቅ መንዙማ እንደ መነዙማዉ ክሊፑን የተሻለ ለማድረግ በተቻለን መጠን ሁላችንም ተረባርበናል በሶስት ክፍል አርገን የተለያዩ ለአይን ማራኪ የሆኑ ስፍራዎችን ተጠቅመናል በአልባሣትም ደረጃ ከዚህ በፊት ከነበረዉ በተሻለ መልኩ ከመንዙማዉ ይዘት ጋር የሚሄዱ አልባሳት ክሊፑ ላይ ተጠቅመናል ይህም ክሊፑን ከምንም በላይ ልዩ እና ደማቅ አድርጎታል ከዚህ ቀደም ከሠራናቸዉም #ቀጣይም ከምንሠራቸዉ አቻ ማይገኝለት ወርቃማ ግዜያችን እንደሆነ አልጠራጠርም
እኔ አንደግል ዛሬ ላይ ሆኜ ሙራዲና ቁ-2 ቪዲዮ ክሊፕ እያየዉ #ቀጣዮቹ ሙራዲና #ቁ -3-...4..እንዴት ይሆን ብዬ ይናፍቀኝ ጀምሯል.....

✍ ጎራዉ ነኝ

https://youtu.be/q3POWTH_P1Q

Читать полностью…

Amir Abdo official 📸📸📸

(ክፍል ሦስት)
#ሙራዲና ቁ -2
የጅማዉ መንዙማዉ ሊቅ

የጅማ ህይወቴ ቀጥሏል #በቆይታዬ ሶስት ሣምንታት እያስቆጠርኩ ቢሆንም የሶስት ቀን ያህል የቆየዉ አይነት ስሜት ነዉ ሚሰማኝ : ሙራዲና ክሊፕ ቀረፃ አልቆ ኤዲቲንግ ስራዉ በመጠናቀቅ ላይ ነዉ
ከዚህ ጎን ለጎን የሀድራዉ መግነጢስ ስቦኝ #ከሞቲ ሰይድ ጠለሀ ቤት ግቢ ዉስጥ ከአንዲት ጎጆ ዉስጥ ለብቻዬ እንደ ባህር ዳር ዛፍ ያወዛዉዘኝ ይዟል የትናንቱ መዉሊድ የለይሉ ድባብ ሰለዋቱ ፡ #የቲጃኒዉ #የመዉሊድ ኪታብ #ኢንሳኑል_ከማል በጆሮዬ እያቃጨለ ቀጣዩ መዉሊድ እንዴት ይሆን ? ብዬ ይናፍቀኛል
ጅማ ከአንድ የቲጃኒ መዉሊድ ቤት ለመታደም ችያለዉ ድባቡ ለኔ እጅግ ልዩ እና አዲስ ነበር
መዉሊዱ ላይ ከተገኙ ከሙላ ሠዉ ታዳሚ እንደ ተራራ የገዘፈ: እንደ ባህር የሠፋ :እንደ ዋርካ የሚያስጠልል አንድ ገምቱ የግጥምና የዜማ ቀማሪ ሠዉ ለዐይን ሞልቶ ይታያል : ይህ ሰዉ #የጅማዉ_የመንዙማ_ሊቅ
#ሸህ_አብዱረህማን_ጅማ ናቸዉ
ከዚህ ቀደም አንድ ሁለቴ በመዉሊድ ላይ ባያቸዉም እንደ አሁኑ ግን ቀርቤ ተገናኝቼ የመተዋወቁን እድል አላገኘዉም ነበር
እኚህ ሊቅ በሚገርም ሀይባ እና ግርማ የተሞሉ ናቸዉ ከሩቅ ሲታዩ ልባም ለምንም ነገር እንደማይደነግጡ ከፊታቸዉ ያስታዉቃል
ከፍ ያለ የሡና ኮፍያ ያደረጉ: ሲሆን በየመሀሉ ወለቅ ሲያደርጉት ፀጉራቸዉ ወደ ገብሳማነት ያደላ እና ፀጉራቸዉ ከግምባራቸዉ ወደ ኀላ ያልሸሸ ግጥም ያለ
ከቅንድቦቻቸዉ መለሀል የተቋጠሩ : አይኖቻቸዉ ለመከደን የቀረቡ ሚመስሉ "ዝምታ ያወጋል ከቃላት በጠና " እንደሚባለዉ ከንፈሮቻቸዉ የተጋጠሙ እምብዛም ማያወሩ : ነገር ግን ዝምታቸዉ የሚሠማ እንዲሁም #ከሙላ_ፊታቸዉ ከአፍንጫቸዉ በታች ጥቂት ፂሞች የበቀሉ : ከአቀማመጣቸዉ ሸንቀጥ ማለት ከፊታቸዉ ጋር ባለዉ ሁኔታ ተደምሮ ቆፍጣና ባለ ሙሉ ማዕረግ #ጀነራል አስመስሏቸዋል
በዙሪያቸዉ ከዚህ በፊት የትም ሀድራ ላይ አይቼዉ በማላዉቀዉ አቀማመጥ ስልት ዙሪያቸዉ በጀመዐቸዉ ተከበዋል
የጀመዐዉ አቀማመጥ ስልት ድርድር ከኀላ ሆኖ ሲታይ እንደ ዘምባባ አይነት ቅርፅ እንዲይዙ አድርጓቸዋ እኔም አደቡን ጠብቄ አቀማመጤን እንደ ጀመዐዉ አድርጌ መዉሊዱን ታድሜያለዉ ፡፡
በለይሉ አጋማሽ ግን አንድ ልዩ ነገር ተከሰተ
ለሸህ አብዱረህማን አጠገባቸዉ ያለዉ ሰዉ
"ያ ልጅ ነዉ አብድልመሊክ (#ጎራዉ)" ነዉ ብሎ ወደኔ በጣቱ አመላከታቸዉ አይናቸዉን በደንብ ከፈት አርገዉ አገላበጠዉ አዩኝ መዉሊዱ ላይ መገኘቴ ሣያስ ገርማቸዉ የቀረ አይመስልም .......
ከዚህ በዋላ ሁሉም ነገር ቀለል አለኝ ምናልባትም #የሣቸዉን መንዙማ #ያለ_ፈቃድ ኢጃዛ #የሠራን ቢሆን ኖሮ ዛሬ እሣቸዉን ቀና ብዬ የማይበት አይን ፊት ለፊታቸዉ የመቀመጥ ሞራሉ አይኖረኝም ነበር ምክንያቱም ሌብነት ሁሌም አንገት ያስደፋል እና
ከትዉዉቁ በዋላ መዉሊዱም መዉሊድ መደዱም መደድ ሆኀ ሸህ አብዱረህማን በቅጂ ከምናዉቀዉ ድምፅ በአካል ደም ይበልጡን ጨምሮ ሰማሁት በትንሹ ሚንቀሳቀሱ ሚመስሉት ከንፈሮቻቸዉ መንዙማ ሲሉ ከጀመዐዉ በላይ ጎልተዉ ይሰማሉ ፊታቸዉ ላይ የረጅም ግዜ የሐድራ የመዉሊድ ታሪክ ይነበባል በዚህ የመዉሊድ ህይወት ብዙ ወጥተዉ እንደወረዱ መንዙማ ሲቀሩ የሚያሳዩት አኳሀን እዉን ምስክር ነዉ
አንግዲህ ይህን ምታነቡ የሸህ አብዱረህማን ወዳጆች እኔ በአንድ ቀን እይታዬ ባወኳቸዉ በገባኝ መጠን እደፃፍኩት ሊታወቅልኝ ይገባል ፡ ፡

✍ጎራዉ፡ነኝ

Читать полностью…

Amir Abdo official 📸📸📸

የኸሚስ ልዩ ግብዣ አለን ይጠብቁን!

Читать полностью…

Amir Abdo official 📸📸📸

ማዲህ ኢስማኢል ተክሌ አዲስ የመንዙማ ክሊፕ ሀሙስ ምሽት ይጠብቁን! ⬇️⬇️⬇️
https://www.youtube.com/ethioneshidamenzuma

Читать полностью…

Amir Abdo official 📸📸📸

⬇️⬇️⬇️ 200k Views
https://youtu.be/V-3W7TgfDRo

Читать полностью…

Amir Abdo official 📸📸📸

❤❤❤❤❤❤Werkoche fuwa yal kemis yihunilachu ❤️❤️❤️❤️❤️❤️

Читать полностью…

Amir Abdo official 📸📸📸

❤❤❤❤Fuwa yal kemis yihunilachu werkoche❤❤❤❤

Читать полностью…

Amir Abdo official 📸📸📸

ሼኽ በድሩ "አሰላት ወሰላም" | የጅማ መውሊድ የመድረክ ላይ መንዙማ | ASELAT WESELAM BY SHIEKH BEDRU ⬇️
https://youtu.be/ZB7FNPOHF5A

Читать полностью…
Subscribe to a channel